Tuesday, July 23, 2019

ለጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከል የምጠይቀው ጥያቄ አለኝ ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) (ጌታቸው ረዳ Facebook) July 22/2019/ሐምሌ16/ 2011


ለጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከል የምጠይቀው ጥያቄ አለኝ
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)
(
ጌታቸው ረዳ Facebook)
July 22/2019/
ሐምሌ16/ 2011
የአንድ ወዳጄ ጽሑፍ በድረገጽ ተለጥፎ አይቼው ወደፌስቡክስለላከኝ እሱን ፍለጋ ፌስ ቡክ ስገባ ምክንያቱ ባልታወቀ በድንገት ዋሺንግተን ውስጥ የሚገኘው የጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከል ፌስ ቡክ ውስጥ ከተተኝ።


መግባቴ ላልቀረ ብየ ፌስ ቡካቸውን ስዳስስበሥርዓተ አልባው ኦነጋዊው መሪ አብይ አሕመድ ትዕዛዝየከፍተኛ ዳኞች ሓላፊ ሆና የተሾመቺው የፍናፍንት (የሌዝቢያን እና ገብረሰዶማዊያን) መብት አከብራለሁ የምትል ከባሕላችን፤ከሃይማኖታችን እና ከመንግሥታዊ ሕግ ውጭ የፍንፍንት መብት ቢከበር አልቃወምም፤ ችግር የለብኝም የምትል ዳኛ / መዓዛ አሸናፊ በተጠቀሰውየጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከልበእንግድነት መጋበዝዋ በሜይ 2019 (ፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር) የተለቀቀው የዚህ ማዕከል ማስታወቂያ ስመለከት እንዴት አንድ የባሕል አስከባሪ እና አሳዳጊ ነኝ የሚል ማዕከል ባሕላችንን ሃይማኖታችንን የሚጻረር አቋም ያላትን አሳፋሪ ሴት እንዴት እውነት እንዴት፤እንዴት፤ምንዋ ስላማራቸው በክብር ሊያስተናግድ የማስታወቂያ ጥሪ አደረገ? የሚል ጥያቄ ጫረብኝ።

በነዚህ የአገራችን ፍናፍንት ላይ ምርምር ያደረጉ አጥኚዎች እንደሚሉትኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፍናፍንቶችእጅግ በቀልተኞች እንደሆኑ ብዙ ማስረጃዎች ይፋ አድርገዋል። ይህ ደግሞ ሌሎች አገሮች ካሉት ፍንፍንቶች በባህሪያቸው የተለዩ በቀልተኞች መሆናቸውን የሚቃወሙዋቸውን በክፋት ለማጥመድ የማይቆፍሩት ሰይጣናዊ ሴራ እንደሌለ የተደረጉው ጥናት ያሳያል።

ይህ እየታወቀ ይህችየፍንፍንትመብት ቢከበር አልቃወምም ባይዋ የሕብረተሰባችንን ያፈጠጠ ዓይን የማያስፈራትገታራ ቅንድብበእዛው አሳፋሪ አቋሟ ታሪክ ዘግቧታል። እንዲህ ያለ አቋም ከየት አገኘሺው ተብላ በጋዜጠኛ ቤቲ (የኤል ጋዜጠኛ) ስትጠየቅኢትዮጵያ ውስጥ እያለሁ የፍናፍንቶች መብት ጥያቄ እቃወም ነበር ነገር ግን አሜሪካ አገር ለትምህርት ሄጄ በነበርኩበት ጊዜ ነው አቋሜን የለወጥኩትብላ እርፍ! ወይ አሜረካ!

አያችሁ አሜሪካ እና አውሮጳ እንዲሁም ሩሲያ እየሄዱ የቀሰሙትን ማርክሳዊ ሌኒናዎ ትምህርት እንዲሁም 666 ቶቹ ቡድን የሚያጠናክረው እና የሚያስፋፋውየፍናፍንት መብትስለ መከበር ትምህርት እየቀሰሙ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ባሕሉን በርዘው አሁን ወዳለንበት የሲኦል አገር አደረግዋት። ይህች ዳኛምመሃላ ምላ፤ለባሕላችን ለሃይማኖታችን ክብርቃል ገብታየተረከበቺው ከፍተኛ የዳኝነት መንበርም ምንም ሰቀቀን ሳይሰጣት እንዲህ ያለ ድፍረት የተሞላበት የወጣቶች ሕሊና እና አስተሳሰብ የሚበርዝ በራዥ ንግግር በሚዲያ ማስተላለፍዋ የሚያሳየን የሕዝብ፤የሃይማኖት እና የባሕል አክብሮት እንደሌላት ማሳያ ነው። ኦነጋዊ አናርኪስ መንግሥት ባይሆን ኖሮ ይኼኔ ከሥልጣን ትወገድ ነበር።

ወላጅ እናትዋ ሁለት ሴቶች ግብረስጋ ቢፈጽሙ፤ቢሳሳሙ፤ ሁለት ተባዕት ሰዶማዊ ግብረስጋ ቢፈጽሙ በበኩሌ አልቃወምም ስትል ሰምተዋት ምን ተሰምቷቸው ይሆን? ይህ ጥያቄ ወላጅ እናትዋ ቢጠይቅዋት ለጋዜጠኛዋ የመለሰቺለላትን ዓይነት መልስ ትመልስላቸው ይሆን? የሚገርም ነውረኛ ዘመን!!

ስለ ይህች ዳኛ የመጀመሪያ እውቀቱ የነበረኝ አዲስ አበባ ሲታተም በነበረው ዜጋ መጽሔት ላይ ነው። እኔ በዛው መጽሔት መስከረም ጥቅምት 1994 ቁጥር አንድ ሦስተኛ ዓመትብርበራ በሚል አምድ የኔ ጽሑፍ ታትሞየእርስዋ ቃለ መጠይቅ ደግሞሰሞኑን ከማን ጋርበሚለው አምድ ላይ የሁለታችን ታትሞ በወጣበት ወቅት ነው ስለ ሴትዮዋ የሴቶች መብት ጠበቃ መሆንዋን ያወቅኩት። በዛው መስክ በጎ ስራ እንደሰራች እንዳለ ሆኖ በሗላ ወደ አሜሪካ ለትምህርት ሄዳ ጎትታ ያመጣቺው የአቁዋም ለውጥ ግን አነጋጋሪ ነው።

ሌላ ቀርቶ በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለው የመብት ረገጣ፤ የኦሮሞ አክራሪ ከንቲባዎች እና ፖሊሶች የዜጎችን መብት እየጣሱ፡ ቤቶቻቸው በቡልዶዘር እያስፈረሱ፤ ህጻናት እርጉዞች፤እመጫቶች እና አዛውንቶች ወደ ጎዳና እየተጣሉ የጐርፍ እና የዝናብ ዶፍ ሲወረድባቸው ምንም ተቃውሞ ያላሳየች ማስቆምም ያልቻለችለዳኝነት የማትመጥን የአፓርታይዱ ሥርዓት ሎሌ ነች። ለዚች ሴት ነው ይህ የጣይቱ ማዕከል ለዚች የአፓርታይድ ሥርዓት አገልጋይ ክብር የሠጠው።

በኋላ ከአንደበትዋ ሳደምጥ ደግሞክፍሌ ወዳጆየተባለ የመለስ ዜናዊ አፓርታይድ ሎሌን ስታመሰግን እና እርስዋም በአፓርታይዱ ስርዓት ሕገ መንግሥት እንዴት አንደሚዋቀር ያሳያት ክፍሌ ወዳጆ መሆኑን ስታመሰግነው ሰምቼበይ፤በበይ ዞር በይ!” ብያት ነበር። ቆየት ብላ የአሀገሪቱ ከፍተኛ ዳኛ ሆና ስትሾምበበኩሌ የፍንፍንትሴቶች መብት ቢከበር ችግር የለኝምስትል አድምጬኣት ሴትዮዋ ለዛ ቦታ የማትመጥን እንደሆነች አረጋገጠችልን። ዛሬ የጣይቱ ባሕል የሚባል ይህችን ባሕላችንን የማታከብር ዳኛ የአክብሮት እንግዳ ሆና ስትጋበዝጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከልጥያቄ ውስጥ አስገብቸዋለሁ። (?!) ወይ ዘመነ አብይ አሕመድ ስንቱን ጉድ አሳይን!

አንድ ጉደ ልጨምርላችሁ እና ላብቃ፦

ስዋ ብቻ እንዳይመስላችሁ። አንድዋ የቤተመንሥቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቃል አቀባይቢልለኔ ሥዩምየተባለች ሌላዋ ጉደኛ ደግሞ ዚምባቡዌ አፍሪካ ያደገቺው ወጣት ወንድን ማንብለህበሦስት አስጠሊታ ቃላት- እንደ መጥራት የመሰለ የመጨረሻ አስጠሊታ መጥፎ ቃላት የለም ብላ ወጣት ወንዶችን የወንድነት ባሕሪ እንዳይዙ የምትኮንንጽንፈኛ አንስት/ፌሚኒሰትጉዳይ በስዋም ላይ አንድ ልብል።

ይህች ወጣትኦነጋዊው አብይ አሕመድ ለሥልጣን የሾማት ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ሴትዮም ከስሜ በፊት/ ወይንም /ብላችሁ አትጥሩኝ ብላ ለዜና ማሰራጫ ደብዳቤ ጽፍ ስትቆጣ ሰምተናል። ይህችሴትዮብየ የምልበት ምክንያትምሴት ስለምትመስልሴትከማለት ውጭ ምን ብየ ልጥራት? አንዲት ሄዋን በዓለም አቀፍም ይሁን በኢትዮጵያ አጠራር በወ/ ወይንም በወ/ ካልተጠራች ምን ብለን እንጥራት? ለምን ያንን አስጠላት? መልሱን አናውቀውም።አቶበሉኝ ብትለን እኮአቶ ቢልለኔ ስዩምብለን እንጠራት ነበር። ግን እርሱም ግልጽ አላደረገችልንም። እንግዲህ የምስጢሩ እንቆቁልሽ ደብዳቤው ምን ማለት እንደሆነ የሚገባችሁ ይመስለኛል። ወይ አብይ አሕመድ! በአንድ አመት ዕድሜው ውስጥ ከምን እያፈናፈነ እንደሚያገኛቸው አላውቅምእየጎተተያላስተዋወቀን ጉድ የለም።

እምየ ኢትዮጵያ ሆይ! ጉድሽን ሰምተሻል? አንቺ በእናትነትሽአንቺ እመየ ኢትዮጵያእየተባልሽ የወለድሺያቸውሴት ልጆችሽግንአንቺወይንም / ወይንም / አትበሉን ሲሉ ሰምተሽ ምን ተሰምቶሽ ይሆን? ብርታቱን ይስጥሽ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ - ጌታቸው ረዳ ፌስ ቡክ)


No comments: