ኢትዮጵያዊ አማራ እና ንጹህ አማራ እኛና እነሱ
የዘመነ ካሴ የፋሺስት ፍረጃ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay 7/20/2024
ዘመነ ካሴ ከታላቁ የናዚ መሪ ሂትለር የቀሰማቸው ባሕሪዎች አሉ፡፡ ሂትለር ሕዝብ ያንቀሳቀሰበትን ስልት ልጀምር እንዲህ
የላል፡፡
"ብዙሃኑ ሕዝብ ከትንሽዋ እውነት ይልቅ ግነት ላገኘ ለትልቅ ውሸት በቀላሉ ሰለባ ይሆናሉ።" የላል፡-
ዘመነ ይህንን ስልት በመከተል ትልልቅ ውሸቶችን በመዋሸት ብዙ ስዎች የውሸቱ ሰለባዎች ሆነው እያየሁ ነው፡፡ እንደ ሙስሎኒ
እየተለጠጠ ደረቱን ነፍቶ ፤እንደ ሂትለር ቃላቶች እየደረደረ የዋሁን ሲያሰከተል ታዝቤ አለሁ፡፡
በእጅ ጽሑፍ የተጻፈው ለእስክንድር ነጋ የጻፈው የዘመነ ካሴ የልተቆነጠጠ ሞገደኛ መላሱ፤ ነውረኛና ዘረኛ መግለጫው ሰምታችሁ
ይሆናል፡፡ ለመነሻ እዚህ ለጥቀስ
መግለጫው እንዲህ ይላል፡
<<(ግጭታችን) የዓለሙና የከበደ የሁለት ሰዎች ግጭት አይደለም፡፡ይህ
የርዕዮተ ዓለም ግጭት
ነው፡፡ የሌባና ፖሊስ ትንቅንቅ ነው፡፡ የትውልዱን ትግልና ድል ሊሰርቁ ጭምብል ለብሰው ማጅራት መምቻ ቆመጥ ታጥቀው
በጠራራ ፀሐይ በመጡ ሌቦችና የትውልዱን ደምና አብዮት ሰለሚጠበቁ
ፖሊሶች መካከል ያለ ግብግብ ነው፡፡
ይህ ይሉኝታቸውን በሸጡ ያልዘሩትን አጫዶችና አበዮቱን
በ30 ዲናር አንሸጥም ባሉ የሕዝብ ልጆች መሃከል እየተደረገ ያለ ትንቅንቅ ነው፡፡ የዘመነ እና የእስክንድር የሁለት ሰዎች ጸብ
አይደለም፡፡ ዘመነ የወንደሞቹን ደም ለገበያ አወጥቶ በሊትር የሚሸጥ ከሃዲ አይደለም፡፡ በሕልሜ
የመጡብኝ አሁን ነው፡፡አሁንማ ተነቃቃን እኮ፡…
እሰከንድር ሲያምሰን ከርሞ ነገ ሽሉክ ይላል፡፡ያኔ
እንተዛዘባለን፡፡ የሚደበረው የምንታዘበው የራሳችን ወንድሞችን ነው፡፡ ወንድምን መታዘብ ትልቅ ሕመም አለው፡፡አንዳንዱ ወንድሞቻችን
በጨለማ ሄዱ አዝነናል፡፡>> (በእጅ ከተጻፈ ጽሑፍ)
ይህ የዘመነ ከትላንት በስትያ ያስተላለፈው “ዘረኛና ነውር የተሞላበት መግለጫው” በዝርዝር እንሄድበታለን፡፡
በመጨረሻ ጽሑፉ ልጀምር፡፟
<<ወንድምን መታዘብ ትልቅ ሕመም አለው፡፡አንዳንዱ
ወንድሞቻችን በጨለማ ሄዱ አዝነናል፡፡>>
የሚለው የሄሊኮፕተር አብራሪው ሲታሰር ሲፈታ አብሮ የታሰረና የተሰቃየ ፤ ሲደበቅ አበሮት የተደበቀ ፤ የቅርብ መሰጢር
አማካሪውና ጓዱ የነበረው የዘመነ ቃል አቀባይ የማርሸት ጸሃየ የእናት እህት ልጅ የሆነው ካፕቴን ማስረሻ ሰጤን ነው፡፡ የራሱን ፋኖ ያደራጀ ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ ዘመነን አልመርጥም ብሎ እስክንድርን ለመሪነት ድመጽ በመሰጠቱ ነው፡፡ (ወንድሞቻችን ከዱን የሚለው
ኡኡታው)
ከላይ እንዳነበባችሁት እኛና እነሱ፤ እኔ ንጹህ እስክንድር ግን አማራ መስሎ ጭምብል በመልበስ የአማራዎችን የኛን የንጹሃን
አማራዎች ትግል ለመጥለፍ የተቀላቀለን አማራ ያልሆነ ሰው ነው፡ ሲል
የፋሺስቶች ፍረጃ ውስጥ ገብታል፡፡ ይህ ደግሞ
መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ ሲሆን እስክንድር ግን አማራ ሰላልሆነ ጭምብል በመልበስ መነሻው አማራ ቢሆንም መዳረሻየ ግን
ኢትዮጵያ ናት ሲል “የርእዮተ አለም አመለካከት ልዩነት አለን እያለ የገለጸው ወያኔ የምንቃወም መዳረሻችንና መነሻችን ኢትዮጰያ ስንል “ሸዋውያን ተጋሩ” የሸዋ ትግርዎች እንደሚሉን ሁሉ ፤ የጽንፈኛ
ፋሺስት ብሔረተኛነት አቀንቃኙ ዘመነ ደግሞ እስክንድር አማራ ሳይሆን አማራ መስሎ የአማራነት ጭምብል የለበሰ “የኢትዮጵያ አማራ”
ማለቱ ነው (የኛ ያለሆነ ጭምብል የለበሰ “ጸጉረ ለወጥ”) ማለቱ ነው፡፡
የእበደቱ ብልግና ማሳያ አመባገነን ፋሺስታዊነቱ ደግሞ በሚገረም አፈራረጅ
እራሱን የአማራ ሕዝብ ፖሊስ አድርጎ
ሲሾም እስክንድር
ነጋ ደግሞ “ማጅራት መቺ እና ሌባ” በማለት በጸያፍ ቃል ዘልፎታል፡፡ እንግዲህ ይላል ዘመነ <<ይህ የሌባና
የፖሊስ ትንቅንቅ ነው፡፡ቆመጥ ታጥቆ በጠራራ ፀሐይ የመጣ ሌባ>> ሲል በስድ
መላሱ እስከንድርን እንዲሀ በወረደ ቃል ይዘልፈዋል፡፡ (ጨርቁን የጣለ ንክ ማለት ይህ ነው!! በቃ)
እራሱን ጉልበተኛ ድመት እስክንድርን ደግሞ ደካማ ዓይጥ አድርጎ በመሳል “ትግሉ የአይጥና የድመት ነው” አሁንማ ተነቃቃን
እኮ በማለት ደካምው እስክንድርን በ “ዲገላው ድመት” (በፖሊሱ ዘመነ) ተይዞ እንደሚበላ/እንደሚዋጥ ተዝቶበታል፡፡
ይህ የሚያመላክተው የዘመነ ፋሺታዊ ባሕሪ ነው፡፡ ፋሺስቶች አስተሳሰብን ሳይሆን “ወንድነትን” ( በጡንቻ/masculinity) እኔ የዓለም ፖሊስ
ነኝ በሚል ትምክሕት ተቃዋሚያቸውን በደካማ አይጥነት ስሎ ሊያጠፋው እንድሚችል፣ከመግለጫው መረዳት ትችላላችሁ፡፡ዛቻ እና
አመፅ በማመንጨት ሥልጣኑንና ሃይልነቱ በመግለጽ ታዛቢው ዓለም ፤ ተከታዮቹና ተቃውሚዎቹ እንዲያውቁለት የፈልጋል። ብዙ ጊዜ፣ ፋሺስቶች
ይህንን የድመትና አይጥ (የፖሊስና የሌባ) ስእል የሚጠቀሙበት ምክንያት ይፋ የወጡ ተቅዋሚዎቹም ሆኑ በተቃውሞ ለመምጣት የሚዳዱ
አዳዲሶች ካሉ ለማስደንገጥ ነው፡፡
የድመቶች ሁሉ አለቃ ሆኖ’ አድፈጦ ገርበብ ብሎ የሚያገኘውን መዝጊያ ሸልኮ ገብቶ ጫጩቶችን በመንጠቅ፤ የተሰቀለ ቋንጣ
ወይንም ለምሳ የተዘጋጀ ሥጋ ድስት እየከፈተ ነጥቆ የሚሮጥ ፤ ቆርቆሮ ጣራ ላይ ውጥቶ
ቆርቆሮውን እየቧጠጠ በከፈተኛ አስፈሪ ጩኸት በመጮህ ትንንሽ ድመቶች (ኪትን) እና አይጦችን ሁሉ መጣሁባችሁ እያለ የተኛውንም ሰው
አካቢውን የሚረብሽ የሚፈሩትና እንዲረበሹ የሚያደርግ የድመቶ ሁሉ አውራ ሞገደኛ ድመት << ሓኽሊ ድሙ>> እንለዋለን
በትግርኛ፤ አማርኛው “ዲገላ ድመት” ይመሰለኛል፡፡የዘመነ የዲገላ ድመት መጣሁብህ ባሕሪ አሁን ግልጽ ነው፡፡
ከዚሀ ባሻገር ዘመነ በመግለጫው
ዘመነ የአማራ ትግል እንዳይሸጥ ተከላካይ
፤እስክንድር ደግሞ የአማራ ትግል ለመጥለፍ ከአማራ ጠላቶች የተላከ
፤ ትግሉን በ30 ዲናር ለመሸጥ የመጣ
“ይሁዳ” ፤ የጠላት ተላላኪ በማለት ፈርጆታል፡፡ የህ ልጅ ነው እንግዲህ እንደ ሙሶሉኒ ደረቱንና አንገቱን አሳበጦ
የሰው ከብር ሲዘረጥጥ አማራ ነፃ ሊያወጣ “በቸኛ ፖሊሰ” ነኝ የሚለው፡፡
ለመሆኑ እኛ የማናውቃቸው የአማራ ጠላቶች እነማን ናቸው? በወዳጅ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ ዝርዝሮች ልጥቀስ
እንዲህ ይላል፤
የዐማራ ጠላቶች በስም ይታወቃሉ፡፡ የተወሰኑትን አሁን በዚህ አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በክፋት ደረጃቸው ቅደም ተከተል
ስለመጥቀሴ እጠራጠራለሁና ደረጃ ውስጥ አልገባም፡፡
1. ኢሕዲን - ብአዴን - አዴፓ፡፡
2- ሕወሓት -
3- . ሻዕቢያ -
4- ኦነግ - ኦህዲድ - ኦሮሙማ፡፡
5- ግብጽና ልጆቿ፡፡
6- ምዕራባውያን - በአሜሪካን መንግሥት የሚመራው…..
፤
7- የኑሮ ውድነት፡፡
በማለት ወዳጅ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ አምና የነገረንን የአማራ
ጠላቶች ሰፊውን ዝርዝር እንድታዩ ለጥፌው ከነበረው ነው እደታሰታወሱ የለጠፍኩት፡፡ ታዲያ ከነዚህ ባጨሩ የተገለጹት የአማራ
ጠላቶች እስክንድር የአማራን ጠላት ተላላኪ ከሆኑት ውስጥ በየትኞቹ ረድፎች ከተጠቀሱት የዘመነ አማራ ጠላቶች ነው እሰክንድር ተልእኮ
ተሰጥቶት ተበሎ ጭምብል ለብሶ ጫካ በመግባት “በንጹህ አማራው ዘመነ” መግለጫ “ኢትዮጵያዊ አማራው እሰከንድርን” “ወንድሙን ለመሸጥ
የመጣ ይሁዳ” ብሎ በይሁዳነት የገለጸው!?
ነፍጥ የታጠቁ እንዲህ ያሉ ፋሺቶች ሰውን በመወንጀል “የማያዳግም እርምጃ” የሚሉት የፋሺት መፈክሮች በመጠቀም ሰው ባልዋለበት
ድርጊት በማጠልሸት ታጋዮችን የሚፈጁበት መክንያት በዚህ መንገድ ነው፡፡
“እስክንድር አማራ አይደለም” ሰለሆነም ትግሉን አኮላሸቶ ሹልክ ብሎ እንደ አመሉ ወደ መዳረሻው ወደ “ኢትዮጵያው” ይህዳል፡፡
ባለፈው ወር ዘመነ ውንጀላውን እስክንደር ላይ እንዲህ ያለውን ላስታውሳችሁ፦
“(አብየ አሕመድ) በጦር ሜዳ ስናሸንፈው በካድሬ አዲስ ቀሰቀሳ አፈር ልሶ ሊነሳ መጣ”
ካድሬ እያለ ያለው እሰክንድርን ነው፡፡ እሰክንድርን የአብይ ተላላኪና ካድሬ ቀጥረኛ ነው
ሲል ሳያፍር ውንጅሎታል፡፡ ዘመነ ሰውን ሲወነጅል ማሰረጃ ሳይኖሮው ነው፡፡
የበረሃ ሽምቅ ተዋጊ ፋሺቶችና ኮሚኒስቶች ተቃውሚያቸውን መወንጀል የባሕሪ መለያ (trade mark)ነው፡፡
ይህ የተናገረበት ውቅት ባለፈው ጊዜ አዲሰ አበባ ያለው የአሜሪካን አምባሲ ተወካይ ሰለ ድርድር አንስቶ ስላቀረበው ሃሳብ
፤ እስክድር ለBBC ያደረገው ቃለ ምልልስ ተጥይቆ ሲመልስ “አሁን አንድ ሰላልሆንን ለድርድር አይመችም ፤ ፋኖዎች አንድ ስንሆን
ከማንም ጋር መደራደር ይቻላል፤ ድርድር የትግሉ አንዱ ሂደት ነው” ሲል መልስ በመስጠቱ ነው ‘ልቡ ያበጠበት የጎጃሙ ‘’ዲገላው
ዘመነ” ደግሞ ገድለን ከቀበርነው እብድ ጋር
ማን የደራደራል፤ ሥልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ለአማራ አስረከቦ ኢትዮጵያ ደግሞ ለዜጎቻ ያስረክብ” ሲል ዘመነ በዚህ መልክ እስክንድርን
“በካድሬነት የከሰሰው፡፡
አብይ አሕመድ ሥልጣኑን (*ምኒሊክ ቤተ መንግሥት አራት ኪሎና መናልባትም አዲሰ
አበባ*ሙሉ ለሙሉ ለአማራ (ብቻ) አስረክቦ “ኢትዮጵያ” የምትባል በዘመነ ችሮታ ከአማራ ጡንቻ የቀረቺዋ ኢትዮጵያ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ነን ለምንል ለነ እሰክንድር ነጋና ለመሳሰልነው
ለኛ ለዜጎቻ ማስረከብ” አለበት፡ ሥልጣን ተረካቢው ፈቃጅና አከፋፋይ በንጹህ አማራነቱ የሚመካው ቻንስለር ዘመነ ካሴ
በሚገርም ሁኔታ ግን የራሱ ቃል አቀባይ ማርሸት ጸሃየ የተባለ ልጅ ደግሞ “ድርድርን አንቃወምም” ሲል እሰክንድርን በመደገፍ
ተናግሯል፡፡ ባንድ ድርጅት ሁለት ምላስ፡፡
ዘመነ ካሴ ብቻ አይደለም አማራ ፋኖ እዝ በሸዋ የሚባለው አሰግድ የተባለ
“ዘረኛ” ድግሞ እስክንድርን “አማራ በመምሰል” የአማራን ታላላቅ ድርጅቶችን በማፈራረስ
የአማራን ትግል የማሰጠለፍ ሴራ አዘል ቀጥሎበታል የላል፡፡
የሚገርመው ደግሞ “የተጎዱ አማራዎችን በመጎብኘት” ጋዜጠኛ መአዛ መሐመድ
የተባለች ቅሌታም ‘ሰብአዊ በጎ ሥራ በመስራት አድናቆት አግኝታ የነበረቺው’ እዚህ አመሪካ ስደት ላይ ያለቺው ጋዜጠኛ
መአዛ መሐመድ ሲያቀብጣት ከዘረኞቹ ከእነ ዘመነ ካሴና አሰግድ ጋር በመወገን ክብርዋን ዝቅ ለማድረግ እዚህ ቅሌት ውስጥ በመግባት
በምታዘጋጀው የሮሃ ሚዲያ ላይ ለወገነችላቸው ለዘረኞቹ ቡደኖች የፕሮፓጋንዳ መስኮት በመሆን እስክንድር አማራ አይደለም የሚለው
“ኮማንደር አሰግድ” የተባለ የወያኔ አገልጋይ ወታደር የነበረ”
“የአማራ ፋኖ እዝ በሸዋ” በሚል ያስተላለፈውን ዘረኛና የሃሰት ውንጀላ በሮሃ ሚዲያዋ ሰታንብ የመሪዋ የአሰግድ ፈለግ በመከተል እስክንድርን አቶ እያለች
<<የአማራ ሕዝቦች አንድነት ድርጀትን አማራ መስሎ ሰርጎ በመገባት ያፈራረስ፡፡ እንዲሁም አማራ መሰል ድረጀቶችን በማቋቋም እውነተኛ የሕዝብ ድርጅት በማፈራረስ ተጠምዶ የነበረና ዛሬም የአማራ ፋኖ ይሕልውና ትግልን ቁማር ለማስያዝ ከጠላት ተልእኮ ይዞ የመጣ
አስቦበት እየተንቀሳቀሰ ነው>> ሲል <<የአማራ ፋኖ እዝ በሸዋ>> አቶ እስክንድር ነጋን ወቅሷል፡ በማለት መግለጫውን ያነበበቺው “ቅሌታማዋ” መአዛ መሕመድ የስራ ባልደረባዋ የነበረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አቶ
እያለች በማሳነስ (የሃሰት ውንጀላውን ደግሞ በማሳነስ ወቀሳ ትለዋለች)
በመቀጠል
<< አማራ መስሎ ሰረጎ በመግባት>>
<<“ፈጹም “አማራ” በመመሰል>> የሚሉትን የፋሺቶች
ቃላት በመጠቀም ልከ እንደ ዘመን ካሴን አባባል “አሰግድ” የተባለው ናዚ ያንን ቃል በመቅዳት
እየሰማን ያለነው “እስክንድር አማራዊ የደም ንጽህና የሌለው የኛ ያልሆነ ፤ እኛን መሰሎ ትግሉን ለመጥለፍ የተቀላቀል
“ባእድ” ነው>> ሲል ይወነጅለዋል፡፡
በዚህ መልክ ብሔርተኝነትን የሚያስረዳን ምንድን ነው?
ብሔርተኞ በተፈጥሯቸው የራሳቸው ካልሆኑ ብሔሮች ውጭ
"ሌሎች" ግለሰቦችን - ባእድ ነው በሚል እንዲመለከቱዋቸው የሚያደርግ አስተሳሰብ ነው፡፡የናዚዎች መነሻ አልፍ እና
ኦሜጋቸው “መነሻቸው የኛ የሚሉት ነገድና ዘር ሲሆን መዳረሻቸውም ያንኑ ነገድና ዘር ነው፡፡ መነሻችን ትግራይ መዳረሻችን ትግራይ፤ መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ፤ በማለት ልክ ሯጮች (አትልቶች) የሚሰመርላችው የመነሻ መስመርና የሚጨርሱት መድረሻ መሰመር ከተሰመረላቸው መነሻና መድረሻ ውጭ
መሻገር እንድማይችሉ ሁሉ ዘመነ ካሴና አጋሮቹ “መነሻቸው አማራ መደረሻቸው አማራ ነው” ከዚያ ወጭ ስለ አገራቸው ኢትይዮጵያ የሚጨነቁና
የሚመለከታቸው እኛን የመሰሉና እስክንድር የመሰሉት የኢትዮጵያ ዜጎችን ነው፡፡
ከላይ ዘመነ ራሱ እንደገለጸው “አብይ አሕመድ ሥልጣኑን ለአማራ አሰርክቦ የተቀረቺው ኢትዮጰያ ደግሞ ለዜጎቸዋ ኢትዮጵያዊያን
ያስረክብ” ሲል ተናግሯል፡፡ ለዚሀ ነው ብሔርተኞች ኢትዮጵያን መዳረሻቸው የማያደርጉዋት፡፡
የየትም አገር ብሔርትኞች መዳረሻቸውና
መነሻቸው ንፁህ የደም ጥራታቸውን የሚለኩት ከመጡበት ዘርና ነገድ ሚዛን ነው፡፡እኔ ፖሊሰ ፤ እሱ ቆመጥ የያዘ
ማጅራት መቺ ፤ ሌባ ፤ እኔ ድመት እሱ አይጥ ፤ኢትዮጵያዊ አማራ እና ንጹህ አማራ ፤ እኛና እነሱ የዘመነ ካሴ የፋሺስት ፍረጃ
ይህን ይመሰላል፡፡
ሰሞኑን ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ስናወራ
የነገረኝን ልጥቀስና ልሰናበት፡፡ አስተዋይ የቀድሞ አማራዎች መሳሌ እንዲህ የላል፡-
<<ወርቁ
ቢጠፋ ሚዛኑ አይጥፋ” ይላሉ አማራ አባቶቻችን ብሎኛል፤፡
ፍሬ ነገሩ የክፉ ቀን ወዳጅህ ስትጣላውም እንኳ
ግብረገብ በተሞላው ቃላት መሰናበት ባትችል እንኳ ፤ ኋላ የሚፀፅትህንና የሚያራረቅህን አበሮ ሲኖሩ የተካፈለካቸው መስጢሮችን ለሌላ
ሰው ክመዘክዘክና ከሚያሰቆጭ ከሚስተዛዝብ የስድብ ቃል መቆጠብ በሞራልም በሃይማኖትም በሕግም፤ በባሕል ሚዛን ላይ የሚለካ ጨዋነትን
ያለመርሳት መምረጥ አለብን ማለት ነው፡፡
ሰላም ሁኑ!
ጌታቸው ረዳ

No comments:
Post a Comment