Wednesday, October 27, 2021

አዝማሪ መስፍን በቀለን ገልጠን ስናየው ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) 10/28/2021

 

 

አዝማሪ መስፍን በቀለን ገልጠን ስናየው

ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)

10/28/2021

­­­­


በፎቶግራፉ የተመለከተው ምስል የአብይ አሕመድ እና የሻዕቢያ ፕሮፖጋንዲሰት የሆነው አዝማሪ መስፍን በቀለ ይባላል። ዛሬ ቀን ሚከተለው ዜና አነበብኩ፡ "አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16 2014 (ኤፍ ) አገርን አፈርሳለሁ  ብሎ ከሚመጣ ማንኛውም ኃይል ለመታደግ አይደለም መዝፈን ግንባር ድረስ በመዝመት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ድምጻዊ መስፍን በቀለ ገለጸ።ድምጻዊ መስፍን እንደሚለው፤ በሥራ አጋጣሚ ነዋሪነቱን አሜሪካን አገር ቢያደርግም ከእናት አገር የሚበልጥ የለም ብሎ የቻለውን ሁሉ ሊሰጥ ሁርሶ የወታደሮች ማሠልጠኛ በመገኘት ሠልጣኝ ወታደሮችን በሙዚቃ እንዲበረታቱ ማድረጌ ትንሹ ተግባር ነው ሲልም ገልጿል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ወታደር ልጅ ነኝ ያለው መስፍን፥ አባቱ ለእናት አገሩ 20 አመት በላይ በውትድርና ሙያው ሲያገለግል በካራማራ ቆስሏል፣ ደምቷልም ብሏል።

በወታደር ሕይወት ውስጥ አለማለፌ ያስቆጨኛል የሚለው ድምጻዊ መስፍን ፥አሁን የአባቴን መስዋዕትነት፣ ገድል እኔም መድገም አለብኝ ሲል ገልጿል።" ይላል ዜናው።

መዝመቱ ጥሩ ነው፤ የሚመሰገን ነው፤ የሚበረታታም ነው። ግን ይህ አዝማሪ በተፈጥሮ የተቸረው ልሳኑን በመጠቀም የአምባገነኖች አወዳሽ ሆኖ በመቀጠል ላይ መገኘቱንም ላለመርሳት እንደ እኔ ያሉ የዜጎች አስታዋሾችን ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያን ሉኣላዊ ግዛትን በአስነዋሪ ፕረሮፓጋንዳ  አዳማቂ ሆኖ ሲያሰራጨው ከነበረው ወደ አለፈው ማሕደሩ ከማለፌ በፊት አሁን እንኳ በራሱ ፌስቡኩ ላይ በቅርቡ ስለ አብይ አሕመድ የጻፈውን የሚከተሉት ሦስት የፍቅር (ልብ) ምልክቶች በአረንጓዴ፤ቢጫ እና ቀይ ቀለም የተቀቡ ምልክቶች ያጀበበትን ጽሑፍ ሰንምለከት የሚገርም ነው። ሃቀኛ ኢትዮጵያዊያንን እነ እስክንድር ነጋ አስቴር እና በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ያንገላታ፤ያስገረፈደም የጠማውአምባገነን ግለሰብ አብይን እንዲህ እያለ አወድሶታል፡

💚💛❤️

congratulations

💚💛❤️ “ኢትዮጵያዊነት አሸናፊነት ነው: ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ መልካም የስራ ዘመን እመኝሎታለሁ!!! የተግባር ሰው !!!

💚💛❤️እንኳን ደስ አለሽ ሀገሬ ኢትዮጵያ💚💛❤️ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የተግባር ሰው !!!

ቀጥል አድርጎም እንደገና

ኢትዮጵያዊ አንድነታችንና እሴታችን: ይበልጥ የሚያብበት ቀጣይ መሪዎቾ እውነተኛ አገልጋይ የሚሆኑባት እና ብሎም ያአፍሪካ ጠበቃ ጭምርነታቸውን የሚያስመሰክሩበትታላቅ ቀንይሆናል ብዬ አምናለሁ።ሲል ብዙዎቻችንን አስቀይሞናል።

 ዛሬ ወደ ጦር ግምባር እዘምታለሁ አለ ተብሎ በአብይ አሕመድ የዜና ማዕከሎች እየተነገረ ያለው ዜና እኔም እንዳይቀርብኝ እዛ ሄጀልሞዝቅብሎበእኔም አይቅርብኝ ስሜትካልሆነ በቀር ሰንደቃላማችንን እየረከሰ ያለን መሪ እያወደሰ ስለ ሰንደቃላማ እና አገራዊ ክብር ምንነት ከእንዲህ ያሉ አዝማሪዎች አንደበት ሲወራ ያማል።

መሪየ” “የተግባር ሰውእያለ የሚያሞካሸው በአስነዋሪው መሪው ትዕዛዝጦርነት ተክፍቶባቸውቃሊቲ ተወርውረው እየተደበደቡ ያሉ እነ እስክንድርቢሰሙአጥንታቸው እና ቆዳቸው ምን ያህል እንደሚያማቸው በእነሱ ጫማ ሰውነትና መንፈስ እራሳችሁን አስገቡ እና ላንዴ ገምቱት።

አዝማሪዎች፤ ገጣሚዎች፤ተዋናያን፤ሰዓሊዎች ወዘተአገር ሲፈርስ እንዲጠገን፤ መጥፎ መሪ ሲነግሥ ተቀባይነት እንዳይኖሮው የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው። ሆኖም የዘንድሮ ዘፋኞች ግን 30 አመት ሙሉ ጠመንጃ አነግበው ሥልጣን በተቆጣጠሩ ዕብድ ሰዎች የሚተላለፉ አገር አፍራሽ ውሳኔዎች ተቀብለውያንን አስፋፍተው እና አቆነጃጅተውየዋሁን አዲስ ትውልድ እንዲቀበለው አደገኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የአገር አፍራሾች ማንነት ታግለው በጽናት የቆሙ እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው። ዛሬ በጥሩ ምሳሌ ተወስዶ በወርቅ ቀለም ሊመዘገብ የሚገባው የማደንቀው የኪነት ሰው አለ።ቀልድን ተንተርሶ እያሳሳቀ  አምባገነኖችን ዕርቃናቸውን በማጋለጥ እና የማሕበረሰቡንም የደከመ ሕሊና ለማሳየትፍራሽ አዳሽበሚል ትዕይንታዊ የመድርክ በቀልድ አፍላቂነቱ የታወቀውተስፋሁን ከበደመቸም ጊዜ ኢትዮጵያ ታሪክ በወርቅ ቀለም መዝግቦ ሲያደምጠው የሚኖር ጥሩ ኢትዮጵያዊ የኪነት ሰው ነው።

በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ የሆነው የተስፈሁን ከበደ  የመንግስት ምስረታውና የፌስቡክ መዘጋት-ፍራሽ አዳሽ-21-“  የሚለውን አስገራሚ ቀልዱን ያየ ሰው የተስፋሁን ከበደ ኪነታዊ ብቃትከደናቁርቱ እነ መስፍን በቀለ አለቅላቂ አዝማሪዎችምን ያህል አገራዊ ብቃት በረዢም የርቀት ልዩነት እንደተጓዘ ማየት ትችላላችሁ።

ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉአስደማሚወጣት የኪነት ሰዎችን ሰትፈጥር በአንጻሩ ደግሞ መላ ቅጥ የሌላቸው እንደ አህያ የሚያናፉ ጮክ ብለው ምድሪቱን የሚያደነቁሩ የአምባገኖች መለከቶችም ስንመለከት እጅግ እንበሳጫለን።

እነዚህ እጅግ ጥቂቶች ሲሆኑ ብዙዎቹ አዝማሪዎች ግን በማያውቁት የፖለቲካ ዋና እየዋኙ አገር በመበጥብጥ ላይ ናቸው። ከነዚህ ከአብይ አሕመድ ምንጣፍ ጎታቾች መካካል አንዱ መስፍን በቀለ መቸውንም ቢሆንይቅርታ ካልጠየቀ ይቀር አንለውም።

ይቅርታ የሚጠይቅም አይመስልም። ምክንያቱም እራሱ እንዲህ ሲል ግልጽ አድርጓል፡

"አንተን መደገፌ ሰሕተት ከሆነ እኔ ልክ ልሆን አልፈልግም! አብቹ ፤ካንተ ጎን ለመቆም እልፍ ምክንያቶች አሉኝ!”

ይላል አዝማሪው መስፍን በቀለ። ልጁ ምን ያህል በአብቹ ፍቅር መውደቁን ማየት ቀላል ነው።

 ማሕደሩን መዝዘን ስንተቸው በሾርት ሜሞሪ”- የምትጓዙየማስታወስ ችሎታችሁ ዝግምተኛ የሆናችሁዝግምተኞችወደ ዘመቻ አቀናለሁስላለ ትንጫጩ ይሆናል። በበራዦች/በከላሾች ዝምታ የለም::

ይህ አዝማሪ  ሳብቨርዥን” (subversion) በሚባለው የብረዛ ፕሮፓጋንዳ መሪ ተዋናይ ሆኖ ቆይቷል። ለምሳሌ ከላይ በፎቶግራፍ ያቀረብኩላችሁ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /በጣሊየን  መለስ ዜናዊ  እና ፋሺሰት ሙሶሊኒየተቀነባበረው ከሕግ ውጭ በሃይል የተሰራውን የኢትዮጵያ ካርታ ተብየው በታዳጊ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ሕሊና ውስጥ እንዲቀረጽ ሆን ተብሎ ትውልድ በዚህ ሴራ ተቀርጾ እንዲያድግ የሚያስተምሩበትን መርዛማ የሙዚቀኞቹ  ባንዳዊ ፕሮፓጋንዳበቪዲዮ ያሰራጩት ፎቶግራፍ ስትመለከቱ እኛ ይህንን ሴራ ለምንቃወም እና ለማንቀበል ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ጥቃት ነው።

ይህ የመልክኣምድር የተቀነባበረው ምስል ትኩር ብላችሁ ስትመለከቱህጻናት ታዳጊዎችበተቆረጠውካርታፊት ለፊት ተያይዘው በመቆም በልባቸው እንዲቀረጽ የተደረገ ሴራ ነው። ይህ ያቀነባበረው ደግሞ የመስፍን በቀለ ሙዚቃ አሳታሚምነው ሸዋየተባለ ጸረ ኢትዮጵያ አሳታሚ ድርጅት ነው። ለኛ ካርታውን ለማንቀበለው እና እየታጋልነው ላለው  ሴራ መስፍን በቀለ እናምነው ሸዋአሳታሚ ድርጅት ከሴረኞች የተረከቡትን ስለት ተቀብለውበልባችን ላይስለት ሰክተውብናል

በዚህ ጉዳይነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ቁጥር 2)” ላይ በሰፊው ስለጻፍኩት አንብቡ። ሆኖም ባጭሩ ለማስታወስ ያክል ሰው እንሁንበሚለው ሙዚቃው ላይየሻዕቢያና የመለስ ዜናዊ  የትግል ውጤት የሆነውየኤርትራ ካርታከኢትዮጵያቆራጣ መልክኣምድርጋር አገናኝቶ ሙሉውን ሕጋዊው የቆየው መልክኣምድራችንን የሚያሳይ ምስል በሙዚቃውክሊፕውስጥ በመታተሙ የሻዕቢያው ታዛዥ የሆነው አብይ አሕመድና ሻዕቢያዎች ስለተቆጡዋቸውምነው ሻዋየሚባለው አሳታሚ (ስዕሉ ላይ ይቅርታ የጠየቀበትን በፌስቡኩ የለጠፈው) በስሕተት ስለሆነ ታላቅ ይቅርታ ይደረግልኝ ሲልምነው ሸዋ እና አዝማሪው በጋራአሳፋሪ  መግለጫ በማውጣት የኤርትራ ባንዳዎችን ይቅርታ ጠይቋል።

እነዚህ ነጋዴዎች እና የኪነት ሰዎች፤ የማሕበረሰቡን የአዲሱ ትውልድ ሕሊናን በመመረዝ ሕዝቡ አገራዊ “”ቁጭት፤ እልሀ እና ጀግንነቱእንዲጥልናቁጭትእንዳይሰማው በመመረዝተሸናፊነትንበመስበክ በተለያዩ መልኮችተንበርካኪነትን  እንዲቀጥሉባህልን፤ ሰንደቃላማን፤ አገራዊ ክልልን፤ ታሪክን፤ ጽናትንየፖለቲካው ክርክር በሚያበላሽ መልኩ ከሴረኞች ተረክበው በመስራት ላይ ናቸው።

የሰላም መሪ  የሚለውን አሳፋሪ ዘፈኑን እንዳለ ሆኖ የቀድሞ ሠራዊት አባል ልጅ ነኝ የሚለን ይህ አዝማሪለሻዕቢያ ባንዴራአለቅላቂነቱን ከመጠን በላይተደጋግሞይቅርታ ሳይጠይቅ ያሳያው ፕሮፓጋንዳ ስንምለከት ያውምየደርግ ካርታእያሉአብደውከሚያብዱት ዕብዶች ጋር አብዶ ስመለከተው፤ ልጁከወታደር ልጅ የተወለደ አይመስልም ወላጁ የተሰውለት ብሔራዊ ክብር ለሻዕቢያ አጎብድዶ ስናይአሳዛኝ ትውልድመድረሳችን የሚገርም ነው። ችግሩ እንዲህ ያሉትን አዝማሪዎች ሙዚቃቸውን እየገዙ የሚያጅብዋቸው መኖራቸውንም የሕዝባችን ንቃተ ሕሊና ደረጃ ምን ላይ እንዳለ ይነግረናል።

ጽሑፌን በሚከተለው የማይረሳ እውነታ ልቋጭ።

 ዛሬ በኢትዮ 360 ዩቱብ / ወይይት 10/26/21 (በፈረንጅአቆጣጠር) ሃብታሙ፤ ኤፍሬም እና ብሩክ ሲወያዩ፡ የሰማሁት አስገራሚ እውነታ ;

በሃብታሙ አያሌው የአዲስ አባባ ሕዝብበፖለቲካው ሱታፌ መደንዘዝ  በወያኔ ዘመን አጫወቱኝ ያላውን የአንድ አዛውንት አባት ማስተዋል እንዲህ አሉኝ ይላል

መጀመሪያ ሃብታሙ ከታች ለተጠቀሰው መደምደሚያ መነሾ የሆነውን እንዲህ ይላል።

አዲስ አበባ ላይ አስታውሳለሁ አንድ  ትልቅ ሰው ናቸው እና ነገሩ ያኔ ትግል በነበረበት ጊዜ ነው። ሕዝቡ ምን ነካው? ሰልፍ ለመውጣት፤ምብቱ እንዲጠይቅ ለማድረግ ፤እኛ የህይወት መስዋእትነት የሚያስጠይቅ ጉዳይ ከፍለንሁለት ቀን ሦስት ቀን ቀድመን አዲስ አበባ ከተሞች ሁሉ ዞረን ቀስቅሰን እጁን ይዘን ነግረን እኮ ነው የምናስወጣው፦ ሕዝብ እምቢ ብሎ እራሱ መውጣት ነበረበት፤መሪ መውለድ ነበረበት፡ ሕዝቡ ምን ሆኖ ነው እንዲህ የሆነው? ብለን ተወያየን፤ ሰልፍ የሚወጣም ከሆነ በሩቅ ሆኖ ኮፍያ አድርጎ መነጽር አድርጎ በሩቅይተኮሳል? አይተኮስም?” እያለ በማዶ የሚያማትር ነው የነበረው (አሁንማ እርሳው)....

....አንድ የፓርቲ አባል የነበረ ሰው ነበር: መንግሥት ለሰልፉ ፈቃድ ከሰጠድብደባ እስራትአይኖርምናክራባት አድርጎሮጦ ከፊት ይሰለፋል፤ መንግሥት ይህንን ሰልፍ አልፈቀድኩም ካለ፤ እኛ ደግሞ ማነው ፈቃድ ያደረግህ ብለን እንወጣለን ብለን በወጣንበት ቀን አርሱ ወይአሞኛል ብሎ ይተኛል፤ወይንም ናዝሬት ነኝ አዋሳ ነኝ ያለሁት ይልሃል። እና ይህ ሁሉ መከታና ግፍ በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ሕዝቡ እንዴት አይነሳም? ምን ነካው ብለን ካንድ ትልቅ ሰው ናቸው ስንነጋገር፡ ምን አሉኝ መሰለህ፤ ...

 “… ስማ አሁን ሕዝቡወንድ ወንዱንነገ ቀበሌ መጥተህ ተሰልፈህሽንት መሽኒያህ ይቆረጣልብሎ መንግሥት ቢወስን እንዴት ነው የምትቆርጠው? ምን መብት ቢኖርህ ነው? ብሎ የሚጠየቅ ሰው ሳይሆን የሚኖር የሚመስለኝእባካችሁ ሥራ አለብኝና እንዳይረድፍብኝ ተሎ ቁረጡኝና ልሂድ ብሎ የሚል ሕዝብ ነው ያለው ይመስለኛልብለው አጫወቱኝ። ያለውን አስገራሚና እውነታ ባለው አባባል ጽሑፌን ልደምድም።

ሼር አድርጉ ሌላውን አንቁበት!

በሰላም እንሰንብት!

ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)

 

No comments: