Saturday, June 2, 2018

አይበገሬው ሃይሉ ያንተን አቀባበል ያላየ በሻዕቢያ አፈቀላጤዎች አቀባበል ይደነቃል! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


አይበገሬው ሃይሉ ያንተን አቀባበል ያላየ በሻዕቢያ አፈቀላጤዎች አቀባበል ይደነቃል!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ሃይሉ! እንጂኔር ሃይሉ~! ሃይሉ! ኢንጀኔር ሃይሉ!!! እንወድሃለን ኢንጂኔር ሃይሉ!! ነበር በሃይሉ ሻውል አቀባበል የሰማናቸው ትዝታዎች። ይህንን ቪዲዮ ተመለክቱልኝ።

Engineer Hailu Shawel arrival Part I


ሁለት ጉዳዮችን አነሳለሁ። አሁን ስላለው ወጣት እና ሌላው ስለ ኢንጂነር ሃይሉ ቅንጅት ትዝታ። እዚህ ላይ የለጠፍኩት ቪዲዮ ውስጥ እንድታዩት የምፈልገው ትዝታችሁን ወደ ላ ወስጄ አገር ወዳዶች ምን ያህል ኢንጂኔርን ይወድዋቸው እንደነበር ለማስታወስ ነው። በዚህ ቪዲዮ አብራችሁ ለማየት የምፈልገው የግንቦት 7 አባሎች የብልግና ባህሪ ከወያኔ ተከታዮች የማይሻል በጣም ቫየለንት/ስልጣኔ ያልቃኛቸው ሞገደኞች የሆኑት የያኔው የብርሃኑ እና የበርቱካን ተከታዮች (የዛሬ ግንቦት 7 ተከታዮች) (የራሳቸው ሰው አበበ በለውንም እንኳ አልማሩትም። ታሪኩን ታስታውሳላችሁ። ለምን ግንቦት7 ወደ ኤርትራ ሄደ ስላለ ብቻ አስፈራርተውት መኖራቸውን ታስታውሳላችሁ፤) የኢንጂኔር ደጋፊዎችን ለመልከፍ የብርሃኑ /ብርቱካን ደጋፊዎች አብራችሁ ባህሪያቸውን በዚህ ቪዲዮ ቃኝዋቸው።

በኦሮሚያዎቹ የአብርሃ ሊነከን ቡዱኖች ነጻ የወጡት ሁለት ሰዎች እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። 1ኘው) ራሱን  ማስፈታትም ሆነ ሌላውን ማስፈታት አቅም ያልነበረው ከእስር እንፍታህ ሲሉት እምቢ አገሪቱ ነፃ ካልወጣች እምቢ  አልፈታም ያላለ "ኢትዮጵያዊ ማንዴላ" ብለው አንዳንዶቹ የዲያስፖራ ምስኪኖች የሰየሙት አንዲ አንዳርጋቸው እና ፤

2) ሌሎቹ ደግሞ የአውሮጳ ብርድ በርዶናል ብለው ወደ 3/4ኘኛው ኦሮሚያ ብለው ‘እራሰቸው ከልለው ያጸደቋት የፈጠራ ክልል” መጥተው እንዲሞቁ የተፈቀደላቸው አዛውንቶቹ የኦነግ ሽማግሌዎች” እንኳን ደስ አላችሁ።


የኢትዮጵያ ወጣት ሲነጻጸር የብዙ አገሮች ወጣት በስሜት ማስጋለብ እንደ ከባዱ አስቸጋሪው የሜዳ ፈረስ ሲሆን ፤ በአፍሪካ ምድር እንደ ለማዳ የቤት ፈረስ በቀላሉ በሰሜት መጋለብ የሚቻል ወጣት ፈልጉ ቢባል ‘የጎሰኞች የፖለቲካ ጡት እየጠባ  ያደገ ኢትዮጵያ ወጣት ጥሩ ምሳሌ ነው።

ስሜት በጣም አደገኛ እሳት ነው። በስለሞቀህ አሁንም አሁንም ደጋግሞ እሳት ላይ መጫወት ራስን ይበላል።ስሜት የትራይባሊስቶች የጎሰኞች የፋሺስቶች መሳቢያ ጥሩ መሳሪያ ነው። ብዙ ምሁራኖች ‘የዛሬ ወጣት ብልህ ነው” ይላሉ።  ሲያልፍ አልነካው። 27 አመት በጎሰኞች ሲገዛ እራሱ ዝምታን ንም መሳሪያ ሆነ ቆይቷል። ከዚህ ወዲያ ምን የተበላሸ ብልህነት ማግኘት ይቻላል? ብዙ ወጠቶቻችን በስሜት ፖለቲካውን ሳይመረምሩ በተለያዩ ድርጅቶች ተጥደው እየተናጡ ናቸው። 

ዘፋኞች ቴዎድሮስን እና ምንልክን “ዲሞክራቶች እና ሰው ያልገደሉ በጽድቅ ላይ ጽድቅ የተጎናጸፉ” በማስመሰል ዮሃንስን ፤አሉላን ሃይለስላሴን “ጨፍጫፊዎች ኢ-ዲሞክራቶች” ናቸው ተብ ከምርጥ የጎሳቸው ነገሥታቶቻቸው ሚያገልል ዘፈን በማስሰማት ፡አሞናል በለው” የሚለውን (ትግሬን አግልለው) እያሉ እየጨመሩበት በየፌስ ቡኩ ሰምተናል። ጎሰኞች የትግራይን ህዝብ እና ከትግራይ የተወለዱት ነገሥታት እና ራሶችን “ትግሬዎች” በመሆናቸው ብቻ አናካሽ ዘፈን በመቅረጽ ሴራ ላይ ይገኛሉ። በጣም አደገኛ! እነኚህ በዘረኞች እና የዛሬ ፖለቲካቸው እንኳ በቅጡ ማሸነፍ ያቃታቸው ጮርቃዎች፤ በቪዲዮኣቸው የኛ የሚሉዋቸው ነገሥታት ብቻ ለይተው በክብር በመዘከር ሌሎቹ የኛ አይደሉም (ትግሬዎች ናቸው በሚል) በቪዲዮዎቻቸው ሰነዶች እንዳይታዩ ማእቀብ በመጣል፡ትኩስ የጎሳ ቅስቀሳ ሴራ እሸረቡ ናቸው። ያለ ትግሬ ምን  ይነት ኢትዮጵያ ሊቀርጹ እንደፈለጉ ቢነግሩን እጅግ ደስተኞች ነን (ለመስማት)!

እነዚህ ትግሬዎች ብቻ ስለሆኑ ማዕቀብ የተፈረደባቸው ነገሥታት ዛሬ ዘፋኞች ሆነው ማን ባቀናላቸው መሬት ላይ ሆነው እየፈነጩ እንዳሉ ቢነግሩን ለውይይት እጋብዛቸዋለሁ። ጮርቃዎቹ በስሜት እየተነዱ ‘ባልነበሩበት ጊዜ፤ታሪክ እና ምድር” ዛሬ በዛሬው ጮርቃ ፍርዳቸው ለምን ያኔ እንዲህ አልተደረገም  ብለው እየተመጻደቁ አገሪቱን በመቅረጽ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ነገሥታት በማግለል፤ በመስደብ፤ ሃውልት እንዳይቆምላቸው የሚከራከሩ ካፍንጫቸው ማሰብ ያልቻሉ ብልጣብልጥ ወጣን ወጠን የሚሉ የዘመናችን አዳዲስ ጠባብ ጎሰኞች በሚኦረኩራቸው ስሜት ብቻ እየጋለቡ አገሪቷን ያስረከቡዋቸው አባቶችም ሲያጥላሉ ሲጥሉ ሲያነሱ ለማየት በቅተናል። ወያኔ ሲያባርራቸው እንደ ወጣቶቹ ጠምነጃ ተሸክመው በረሃ መውጣት እምቢ ብለው እዚህ አውጭ በሞቀ ኑሮ ሆነው በሙዚቃ ጭፈራ መገሥታትን ማብለጥለጥ አስገራሚ ነው። ኣይጋ ፎርም እና ትግራይ ኦን ላይን የተባሉ የወያኔ ምጣዶችም እንደዚሁ “ምኒልክን” አግልለው ቴዎድሮስና እና ዮሃንስን ከዚጣ የወያኔ ታጋዮችን ሓየሎም፤ ቀሺ ገረዝጊሔር፤ አሞራ ….. የጨመረን ቪዲዮ ቀርጸው ህዝብን ሲሰብኩት እና የሚያበጣብጥ ጎሰኛ ስራ ሲሰሩ አይተናል። እነዚህም ከነሱ ተቀብለው ወደ ጭቃ ገብተው የወላጆቻችን እና የባህላችንን ማሳጣት፤ማበላሸት ጀምረዋል።

 በዚህ የደነዘው ትውልድ ብቻ ሳይሆን በ60ዎቹ የነበሩት ኮሚኒስት ተማሪዎች የጀመረ የባህል ብከላ ውጤት እንደነበረ ለዛሬ ውርደታችን ያበቃን መከራ እያየን ነው። ያ ትውልድ እንደዚያ ተጨማልቆ ነገሥታትን የሰው ስጋ ይበላሉ እያለ ታሪክን እና የሰውን ክብር ሲዳፈር’ የውጭ አገር ኮሎኒያሊሰት ሰላዮች ኢትዮጵያ ምድር ተቀምጠው በወያኔ ጊዜ ከ3 አመት በፊት በውስጥ ተባባሪዎች “ኢትዮጵያ በ16ኛው ክፍለዘመን የነበሩት ሴት መነኮሳት የመጀመሪያ አፍሪካውያን “ለዝቢያን ነበሩ” እያሉ መፅሐፍ ሲጽፉ አገሬኞቹ አብረው ግዕዙን እያጣመሙ ሲተረጉሙላቸው ለማንበብ በቅናል”። አልፎ ዛሬም፤ ይህ ትውልድም ከ60ዎቹ ኮሚኒሰት ተማሪዎች ስህተት  የተማረው አንድም ነገር የለውም። ምናልባትም በሌላ መልኩ እየለወጠ ያው ያገሪቱን ነገሥታት ለያይቶ ማወደስ፤ ታሪክ ማበላሸት ህዝብን ማቃቃር በሙዚቃ ስልት ሕዝብን ወደ ማናከስ ስራ ገብተውበታል። “አሞናል በለው’ የሚለው ሙዚቃ አገር ውስጥ ባይገባ እመርጣለሁ። ለብጥብጥ ከፍተኛ በር ከፋች ነው። አገሪቱ በገዛ ልጆቿ  ከውርደት ወደ ውርደት እያሸጋገርዋት ይኼው እዚህ ደርሰናል። በዚህ ከቀጠለ፤ ዘረኛ ሙዚቃዎችን ካለወገዝን፤ያች አገር አገር እንደማትሆን ግን በእርግጠኛነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ።

ይህ ግልጽ ወገንተኛነትና ጠባብ ጎሰኛነት ለማንጸባረቅ በሙዘቃ አሳትሞ ለፖለቲካ መሪዎች መቀበያ ዘፈን ሆኖ ተቀርጾ ከማስጨፈር የሚዘገንን ነገር አይኖርም። ህዝብን ማለያየትና ማስቆጣት ጉዳቱ እውጭ አገር በደላ ህይወት የሚኖሩት አይደለም።  እሳት ቀማሹ እዛው አገር ያለው ነው።

አሁን ወደ ቅንጅት ልውሰዳችሁ።

ቅንጅትን አንድነትን ያፈረሰው ማን ነው? ብዙ ተከራክረናል። የዛሬዎቹ እነ አንዳርጋቸው እነ ብርሃኑ “ቆሻሾቹን ጠራርገን ከመንገዳችን እናስወግዳለን በተባለው መሰረት፡ በሴራ ከሻዕቢያ ጋር ተጣብቀው አገሪኛውን ጠራርገው የተነበዩት ሴራ እውን ሆኖ፤ “አማራው ለጥቃት” “አንድነት ሃይሉ ለጥቃት” ተጋልጦ፤ ይኼው የስሜት ፖለቲካ እየነዳው ይገኛል። በዚህ ሴራ ላይ ኤልያስ ክፍሌን በሚመለከት እራሱ የቻለ ዘገባ አቀርባለሁ። ከዚያም እነ አል ማርያም፤ ታማኝ፤ አበበ በለው፤ንአምን፤ሜሮን፤ ሉሊት ወዘተ…የተጫወተቱት ሚና እንመለከታለን ለጊዜው ይህ ኤልያስ እና ሴረኞቹ በአገር አርበኞችና አገር ወዳዶች ላይ ሲያሰሩባቸው የነበረውን ካርቱን ኤልያስ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ሴራ ተጠምዶ ይለጥፋቸው የነበረውን ካርቱኖች ላስታውሳችሁ (ከታች ታዩታላችሁ)። አስገራሚው ደግሞ እንደዚያ ሁሉ “አገር ወዳድ ነኝ እያሉ ‘ሃይሉን በባንዳነት ታየን በባንዳነት በገንዘብ …ሲከስሱዋቸው” መጨረሻ አገር ጥለው ብርሃኑም አንዳርጋቸውም ኤልያስም ከዛ ሁሉ በሰው ክብር ላይ መጸዳዳት አልፈው “ሁሉም እየሮጡ ኢሳያስ ጉያ ውስጥ ገቡ”። ለሁሉም ጊዜ አለው! ወጣቱ ዛሬም እመቦጭ የውሃ ፖለቲካ ወቀጣ ውስጥ ገብቶ ይወቅጣል። የት ይሄዳል ኣያውቀውም። ሃብል እና መኪና እስከ ሸለመ ድረስ ተፈናቃይ ረሃብተኛ በየቦታው ፈስሶ የረዳት ያለህ፤ የዳቦ ያለህ እስካለ ድረስ ያ ጉዳዩ ኣይደለም።የድሮ ተማሪዎች የባህል ብልሽታቸውን ወደ ጎን ትተን ስለ ርሃብተኛው እና ተፈናቃዩ ያሳየው የማይረሳው ታሪክ ማን ይድገመው! በህይወት የሉም ወይንም ሁሉም ሸምግለዋል።
Hailu Sahul and Taye Weldesmayat and Bedru Adem all respected politicians disrespected by the dispeakble Elias Kifle of Ethiopian Review (Mereja)- Read what he named the each on his own shocking writing to defame these patriots. This is how Kenijit and our unity destroyed to ashes. History will never forget this brutal behavior in politics. Elias or Berhanu Negga or Bertukan Mediksa or Andaragachew Tsge and the likes never never ask forgiveness. Sad indeed!

 እንዲህ  ዓይነት ብልግና እየተሰራ ነበር አንድነት እና ቅንጅት ሊፈርስ የቻለው። ሴረኞቹ ዛሬም እንደ ጀግኖች ይጠራሉ። ለሁሉም ጊዜ አለው!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


No comments: