ኢትዮጵያዊያንን ከሊቢያ እስር ቤት አስወጥታ ወደ ግብፅ እንዲሸሹ ያደረገች ኢትዮጵያዊት!
እዝራ
“ድንቅ በሆነ ጥበብ በተሞላበት በራሷ መንገድ በተለመደው ወገኗን በምድረ ሊቢያ እስር ወጥተው ወደ ግብፅ በነፃነት እንዲሸኙ ያደረገች ውድ እና ብርቅ የሆነች ኢትዮጲያዊት ላስተዋውቃችሁ።”
Yeharerwerk Gashaw with President Mandela |
የኢትዮጲያ ወርቅ-የሀረር ወርቅ ጋሻው የኢትዮጵያ ስደተኞች እናት እና አባት ነች። የሀረር ወርቅ አስተዋጽኦ ንግስት አስቴርን እንድናስታውስ ያደርገናል። ። ንግስት አስቴር ወገኖችዋን እስራኤሎችን ከመታረድ ያዳነች ቅድስት ነች። ታሪኳም በብሉይ ኪዳን መጽሃፈ አስቴር በሚል ይገኛል።
ወገኖቼ በዚህ ሰአት በሀገራችን መንግስት በሌለበት በውጭ ያለው ወንዱም ወሬኛ በሆነበት ዘመን ለወገን ዘሎ የሚጋፈጥ ጠብቃ ማግኘት ከላይ መግቢያ ላይ እንዳልኩት የነበረው የጉዳዩ ባለቤት ያውቀዋል ። ኢትዮጲያ ሀገራችን የእግዚአብሄር ሀገር ነች ህዝቧም ተባርኯአል እግዚአብሄር ወርዶ ሳይሆን በሰው አድሮ ነው ስራውን የሚሰራው በሀረርወርቅ በኢትዮጵያወርቅ አድሮ ስራውን ስላየን አቅማችን ምስጋና ነው።
የሚገርመው ከማንም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ምንም እርዳታ ሳትጠይቅ በግሏ በራሷ የፈፀመችው በመሆኑ ከምንም በላይ የሚያኮራ የሚያስደንቃት ብርቅዬ የኢትዮጲያ ልጅ በመሆኗ እንኳን ደስ ያለሸ እንበላት እኔ በቅርብ እከታተል ስለነበር ያሳየቺው ብርታትና ኢትዮጵያዊ እልኽ ለመግለጽ ቋንቋ ያጥርብኛል ።
ስደተኛው አንድም ኢትዮጵያዊ ግለሰብም ይሁን የፓለቲካ ድርጅት የደረሰልን ባለመኖሩ "ወኪላችን አድርገን የሀረር ወርቅ ጋሻውን መርጠናል" ብሎ በይፋ መግለጫ ቃልኪዳን አስሮላታል።
እኛ ወንዶቹ ቁጭ ብለን ከምድረ አሜሪካን ተነስታ በጦር ሜዳ ውላለች። በጄኔቫ ኮንቨንሽን ሕግ መሰረት ምርኮኞቹ የጥበቃ መብት እንዲኖራቸው አድርጋለች። ሙርከኞቹ መኖራቸውንም ለሚመለከተው ሁሉና ለኢትዮጵያም ሕዝብ በቪዲዮ በተደገፈ ማስረጃ አረጋግጣለች። ማንም ሳይነግራት፤ ማንም ሳይገፋፋት፤ በራስዋ ገንዘብ ጭምር ወጪዋን ችላ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ለብሳ፤ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች በተባለችዋ የኤርትራ ምድር ላይ ኤርትራ ኢትዮጵያ መሆንዋን ለሙርከኛው፤ ለዓለም እና ለኢሳይያስ አፈወርቂ አስመስክራለች። ሙርከኞቹን ለማስለቀ ከኢሳያስ ስትደራደር የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፊት ለፊቷ በክብር እየተውለበለበ ነበር ድርደር ያደረገቺው
የቀድሞውን የኢትዮጵያን ባሕር ሃይል ባልደረቦች ከእነ ሲቪል ሰራተኞቹ በየመን ሲሰቃዩ የነበሩትን ከረጂም የስደት ስቃይ በኋላ ከእነቤተሰባቸው የአሜሪካንን ምድር እንዲረግጡ አድርጋለች። ባህር ሃይሉን ወደ አሜሪካን ያስገባችው በአሜሪካን መንግስት ባላት ተቀባይነትና በጊዜው በነበሩት የአምሬካን መሪና ቤተሰቦቻቸው ጋር ባላት የቅርብ ግንኙነትና ጉዳዮችን አቅርባ የማሳመን ልዩ ችሎታዋ ነው። ንግስት አስቴ ወገኖችዋን ከመታረድ ያዳነችው የተጻፈላት ካልሆነ በስተቀር (መጸሃፈ አስቴር) የሚገርመኝ ሴት ልጅ ወገኖችዋን ለማዳን ብቻዋን እንዲህ ግራ ቀኝ ስትራወጥ፤ ዶክተር፤ ፕሮፌስር፤ የፖለቲካ መሪ፤ የሬዲዮ ጡሩንበኞች ድህረ ገጽ ቴሌቪዢን ወዘተ የታሉ የት ገቡ? ያሳዝናል። ግን ባረረው አንጀቴ ለወገኔ የማስተላልፈው ጎበዝ ገንዘባችሁን ያዙ በናንተ ገንዘብ ከብረዋል ተጠንቀቁ ብቻ ነው ማለት የምችለው።
በመጨረሻ ለሀረር ወርቅ ጋሻዉ ፤ እውነትም የኢትዮጲያ-ወርቅ!! እግዚአብሄር ለወገንሽ ጠበቃ ተቆርቋሪ እንደሆንሻቸው ላንቺምም ለቤተሰቦችሽም እድሜና ጤና ጠባቂ ይዘዝልሽ።
ቀጣዩን የሀረር ወርቅ የኢትዮጲያን ወርቅ ስራዎችን ይዤ እመለሳለሁ
ቸር ይግጠመን ። እዝራ። Posted at Ethiopian Semay getachre@aol.com
1 comment:
Thank you, Wro.Yeharer Werk Gashaw. You are a true Ethiopian. If we had many more nationalist individual like you, Ethiopians wouldn't continue to suffer under the hands of the TPLF/EPRDF. As we all know, the main cause to the killing of our brothers under the hands ISIS terrorists is the ethnic based authoritarian regime in Ethiopia. As I point out, and those TPLF ethnicists would hate to hear, is that the racist regime in Ethiopia has made life miserable for the majority of Ethiopians, who are viewed as second class citizens by the racist regime in power. The "world's fastest growing economy," as BBC and Walta like to tell us, is not an economy at all, where the people are deemed to live like zombies, while below standard towers and roads are constructed all around them, by money that is stolen in masses from Ethiopian banks and are never paid back by the TPLFiets that stole it.
Post a Comment