የመርዶ ዜና
Dr.Mesfin Araya |
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሚዲያዎችም ሆኑ ኤርትራ ተቃዋሚ ሚዲያዎች ያልዘገቡት
የእውቁ ምሁር ደ/ር መስፍን አርአያ ‘ሕልፈተ ሞት’ ከዚህ ዓለም መለየት እጅግ አዝኛለሁ። እናንተ አንባቢዎቼም ይህንኑ አሳዛኝ
ዜና ስትሰሙ በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ አስገንጣይ ባንዳዎችንና ከሃዲ ተገንጣዮችን በመድረክ በግልጽ ሲቃወም ስለነበረው ይህ ተወዳጅ
ኤርትራዊ ኢትዮጵያዊው ምሁር ለምታውቁት ከዚህ ዓለም በሞት ስለመለየቱ እንደምታዝኑ እርግጠኛ ነኝ።
እዛው ኮለጅ
አብረውት የሚያስተምሩና የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ አውቃለሁ። አንደኛው በየኢንተርኔቱ የሚጽፍ ሰው ነው። ለምን ስለ እሱ ዜና
ዕረፍት ለሚዲያዎች አላስተላለፈም፤ እጅግ ገርሞኛል።
ደ/ር መስፍን
ሲያስተምርብት በነበረበት የትምህርት ተቋም የዮርክ ኮሌጅ ድረገጽ ስለመስፍን የዘገበው የሃዘን መግለጫው
ላይ እንዲህ ይነበባል;-
“It is with great sadness that I share with you that Dr. Mesfin
Araya passed away in February 2015. Dr. Araya served as Associate Professor of
Black Studies in the Department of Social Sciences at York College from 1994
until his retirement in March 2013. He earned his Ph.D. in Political Science in
1988 from the CUNY Graduate Center and his BA in Political Science and
Economics from Haile Selassie University , Addis Ababa, Ethiopia.” መስፍን
አርአያ እዚህ እኔ ካለሁበት ሳንሆዘ ካሊፎርኒያ ውስጥ ካልተሳሳትኩ በ March 2010 ኢትዮ/ኤርትራ ወዳጅነት ውይይት (?)
በሚል ኮንፈረንስ ተደርጎ በነበረበት ወቅት ጋዜጠኛ አበበ ገላው የመስፍን አርአያ የአማርኛ ንግግር ወደ እንግሊዝኛ በተረጎመው ዘገባው
ላይ ፤መስፍን አርአያ እንዲህ ብሎ ነበር ““It was merely the EPLF’s agenda that was carried out with TPLF.
The intellectual class never demanded a public debate over the cost and
benefits of independence,” …..”It was merely the EPLF’s agenda that was carried
out with TPLF. The intellectual class never demanded a public debate over the
cost and benefits of independence,” The Eritrean middle class that blindly
rallied around Isaias Afeworki and the Eritrean People’s Liberation Front
committed a “collective suicide in post-independence Eritrea.”” ሙሉን ለማንበብ
ይህንን ይጫኑ።https://www.york.cuny.edu/news/the-passing-of-dr-mesfin-araya
ለመላ ቤተሰቦቹና
ወዳጆቹ ጽናቱን እመኝላቸዋለሁ። ስለ ኢትዮጵያ ሲከራከር እድሜው በሙሉ ያሳለፈው አገር ወዳዱ ከዚህ ዓለም ቦት ሲለይ፤ የተቃዋሚ
የዜና ድረገፆች ስለ ሕይወት ታሪኩና ሞቱ አንዲት ቅጠል ሳይለግሱለት በማለፋቸው እጅግ ያሳዝናል። ይህ ክስተት በደ/ር መስፍን አርአያ
ብቻ የተከሰተ ሳይሆን፤ ካሁን በፊትም በዶ/ር አለሜ እሸቴም ሚዲያዎቹ የሐዘን መግለጫ ለማውጣት ሆን ብለው ነፍገዋቸዋል (የኢትዮጵያን
ሪቪው አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌ እግዚሃር ይስጠው እሱ በስተቀር አብዛኛዎቹ ታዋቂ ሚዲያዎች ዜናውን ከሰሙም በሗላ አልዘገቡትም ነበር)፤አሁንም ተልኮላቸው አላወጡትም።ለተለየን ወንድማችን ብቻ ሳይሆን፤ በትዕቢት አንተባበርም ብለው ዜና ዕረፍቱን ያፈኑት፤ እየኖሩ እየመሰላቸው በቁም የሞቱት፤የቁም
ሙታንም ይታዘንላቸዋል።
ጌታቸው ረዳ
(ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)።getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment