Saturday, May 24, 2014

አናካሹ ኢትዩጵያዊው እስላም ሸኽ ሳዲቅ መሐመድ (አቡ ሐይደር)

አናካሹ ኢትዩጵያዊው እስላም ሸኽ ሳዲቅ መሐመድ (አቡ ሐይደር) ወነገረነ አዲ በእንተ ምፅአተ እስላም ወይቤለነ ናሁ ይበጽሕ ጊዜሁ ከመ ኩሉ ዘይቀትለክሙ ይመስሎ ከመ ዘመስዋዕተ ያበውእ ለእግዚአብሔር።>> “ዳግመኛም ስለ እስልምና መምጣት ነግሮናል፡ እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዳቀረበ የሚመስልበት ጊዜ ይደርሳል፤ብሎናል።” ይህን የወንጌል ቃል ጠቅሰው ስለ እስላም እንደተናገረ ያስረዱት አባ እንባቆም መጀመሪያ በአስላም ሃይማኖት የነበሩ ሰው ናቸው። አባ እምባቆምም በትውልድ የመናዊ ሲሆኑ ቁርዓንን ሲመረምሩ ከቆዩ በኋላ በቁርዓን ስለክርስቶስ የተነገረውን ይዘው አብዝተው በመጸለይና እውነቱን ግለጽልኝ በማለት ሱባኤ ሲገቡ ጌታችን እውነቱን ገልፆላቸው ወደ ክርስትና የተመለሱ ሰው ናቸው። አባ ዕንባቆም ወደ ክርስትና ሲመለሱ እንደተለመደው ሁሉ አክራሪ እስላሞች ሊገድሏቸው ተነሡ። በእርሳቸው ክርስትያን መሆን ምክንያትም ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ያቃጥሉ፤ክርስትያኖችንም ያሳድዱ ጀመር። አባ እንባቆምም ከአክራሪዎቹ እየሸሹ ነገር ግን ከዚያው ከቁርዓን እየጠቀሱ ክርክራቸውን በጽሑፍ ይልኩላቸው ጀመር። በዚህ ወቅት እርሳቸውን አሳድዶ ለመየዝ የተላከ አንድ የአክራሪ እስላም ጦር አዝማች እሰኪ የምትለውን በደንምብ አስረዳኝ፤ከዚህ በኋላ እኔ ቤተክርስትያንም አላቃጥልም ክርስትያኖችንም አልገድልም ሲላቸው ለእርሱ አንድ መጽሐፍ አዘጋጅተው ላኩለት “አንቀጸ አሚን” (ሐመር ጥር 2001 ዓ.ም ወቅታዊ ጉዳዩች (ደ-/ን ብርሃኑ አድማስ - ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ ማቴ.26፤52) (ገጽ 19)። በአንቀጸ ብርሃን የተጠቀሰው የአባ እንባቆ ታሪክ ለአንባቢዎቼ ልጠቅስላችሁ የፈለግኩበት ምክንያት ከላይ በርዕስ የተጠቀሰ “ሸኽ ሳዲቅ መሐመድ ወይንም “አቡ ሐይደር” በመባል የሚታወቅ የእስልምና ሃይማኖት ሰባኪ በእለተ እሁድ በዶቸበሌ ራዲዩ የተላለፈው የሃይማኖት ችግሮችና መፍትሄው በኢትዩጵያ በሚል ርዕስ ከወያኔ መንግሥት የሃይማኖት ጉዳዩች፤ እንዲሁም ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው በቅርበት ያውቁ ይሆናል ብለው የገመቷቸው ከተለያዩ ሃይማኖቶች የተጠሩ እንግዶች አነጋግሮ ነበር። እስልምናን ወክሎ በማብራራት ከእንግዶቹ አንዱ የነበረው “አቡ ሓይደር” ነበር። አቡ ሓይደር ሃይማኖቱ የት እንደተማረ እና እንዳጠናቀቀ ባለውቅም የሃይማኖት መምህር ነው ብለው ደግ ሰው መስሏቸው ሰው አግኘን ብለው እንደዛ አይነቱ አናካሽና ውዥምብራም በእንግዳነት ማቅረባቸው ባልወቅሳቸውም በመንግሥት ደረጃ ተወክለው የተገኙት የወያኔ መንግሥት ተወካዮች ተብየዎች ግን እውን አንዳንድ ተቃዋሚዎች “ወያኔ ነው ከበስተጀርባ እያሳበበ የሚያቆራቁሰው/የሚያጋድለው” እያሉ የሚከሱት ዓይነት ክስ ልክ ሆኖ ካልሆነ በስተቀር እውን “የመንግሥት” ተወካዩች ከሆኑ ኣቡሃይደርን ጥላቻና ቅራኔ በሚያናፍስበት“Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice,” በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ማሕበራዊ የድረ ገጽ ራዲዩ መነጋገሪያ Pal Talk (ፓል ቶክ) መድረክ የሚዘለብደው የጥላቻና የጭካኔ ንግግሩን ተከታትለው አቡሐይደርን ወደ ሚመለከተው ዓለም አቀፍ የደህንነት ተቋማት በማስተላለፍ ወይንም እራሱ ወደ ሕግ (ወያኔ እውን ሕግ የሚያከብርና ግጭት የለም እያለ የሚያስተባብለው ውሸት የማያራግብ ስርዓት ባይሆን ኖሮ) አቅርቦ ተገቢውን ምርመራ እንዲካሄድበትን የፍትሕ ተቋማት (እውን ካሉ ፡ አንዳንድ የፍትሕ ሰዎች ላይታጡ ይችሉ ይሆናል የሚል እምነት አለኝና) በዚህ ሰው ላይ አንዲዳኙ ማድረግ ነበረባቸው።

ለምንድ ነው እንደዚህ ልል የቻልኩት? ከላይ የተጠቀሰው “Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice” የተባለው ፓል ቶክ አቡ ሃይደርና አንዳንድ እሱን መሳይ ጽንፈኞች በመሰባሰብ እስልምና በኢትዩጵያ ዋና አትኩሮታቸው በማድረግ በክርስትና አማኞች ጥቃት እንዲደርስ በግልጽ ሲሰብኩ የተቀዳ መረጃ አለ። ለምሳሌ አንድ የክርስትና እምነት ተከታይ በተጠቀሰው መድረክ “አቡሐይደርን (ሳዲቅ መሐመድን)“ እስልምና ሃይማኖት ጥለው ወደ ክርስትና ሃይማኖት የገቡ እስላሞች ላይ ምን ትላለህ ብሎ ሲጠይቀው መልሱ “አንገቱ ይቆረጣል! አንገቱ ያጣል፤ግድያ ነው!” በማለት በማያወላዳ መልሱ ሰጠቷል። ይህንን ቃል በቃሉ እንደወረደ ልጥቀስ፡ <<አንድ ሰው ከእስልምና ወደ ከክርስትና ወዶ በፈቃዱ አልተስማማኝም ብሎ መመለስ ይችላል ወይ? ቢመለስስ ለምንድ ነው ሞት እሚፈረድበት? መጽሐፋችሁ ለምን ሞት ይፈርድበታል? የኼን እንድታብራራልኝ እፈልጋለሁ። ፋክቱ/fact አሁን ላለው ዓለም የሚያንጸባርቅ ነው ወይ? እንግዲህ የመጀመሪያውን ጥያቄየ አትርሳ “አንድ ሰው ሃይማኖቱን ከተወ ይገደላል ሲል ከራሳችሁ ሰምቻለሁ፡ ይህንን ብታብራራል
"የ“ሸኽ ሳዲቅ መሐመድ(አቡሓይደር) መልስ እነሆ "ሃይማኖቱን የለወጠ ይገደል! ወይንም እምቢ ቢል ይገደል! እዚህ ጋር የሃይማኖት ጉዳይ ሳይሆን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እኮ ነው አሁን።… እምነቱ ለቆ የወጣ ሰውስ? እምነቱን ለቆ የወጣ ሰው፤- በመጀመሪያ “አላህን” መካድ “ወንጀል” ነው። ከወንጀሎች ሁሉ የመጨረሻው ጣራ የነካው አንዱንና እውነተኛውን አምላክ “አላህን” ክዶ መገኘት ነው። ሰው በፈጣሪ ላይ ለመወንጀል መብት አልተሰጠውም፡ ይሄ መብት አይደለም። ሃይማኖቱን ለቆ የወጣ ሰው በመጀመሪያ የሦስት ቀን ዕድል ይሰጠዋል፡ “ምንድ ነው ሰበቡ? ነው።” ይሄ ሰው ሰበቡ ምክንያቱ ምንድነው፡ አንደኛ የኢኮኖሚ ችግር ደርሶበት ባኮኖሚ ምክንያት ችግር ደርሶበት ከሆነ ያ ነገር ይመለስለታል፤(ይብራራለታል)።ያ ካልሆነ ደግሞ በሃይማኖቱ ላይ “ሹባሃት” ወይንም አስመሳዮች ገብተውበት ጥርጣሬ አድሮበት ከሆነ በሊቃውንቶች ይፈታለታል። እነዚህ ትቶ አልፈልግም ብሎ የሚወጣ ሰው ግን “ምን ይሆናል?” ጋሬጣ ይሆናል! ሌሎች ወደ እምነቱ እንዳይገቡ እኔም አውቀው ነበር እያለ ዕንቅፋት ይሆናል። ዕንቅፋትን ማስወገድ ደግሞ “በሸሪአችን” ግዳጅ ነው።ስለዚህ አላህን መካድ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከሆነ ቅጣቱ “ግድያ” ነው! ቅጣቱ ግድያ ነው! የሃይማኖት ነፃነት ሌላ ግድያ ሌላ'
 ምንጭ http://www.youtube.com/watch?v=A6rHwMBeNyU
ፋሺስቶች፤ኮሚዩኒስቶችና ደርግ እንዲሁም የነጻነት ግምባሮች ሲያደርጉት እንደነበረው ማለት ነው። {ምንላባትም የፖለቲካ ድርጀቶች ይሻሉ ይሆናል} አንድ የፖለቲካ አባል ድርጅቱን ከድቶ የወጣ ከሆነ ይገደል እንደነበረው ማለት ነው። እንግዲህ ይህ ሰዎች የሚደነግጉት ድንቁርና ነው። ካለይ ያነበባችሁት የአቡ አይደር ግን የአላህ/የእስልምና ትዕዛዝ ነው፡ሲል ነው ሰውን መግደል ወንጀል ሳይሆን “ሕጋዊ” መሆኑን ነው እየገለጸልን ያለው። እንግዲህ ከላይ እንዳነበባችሁት ለምሳሌ አንድ እስልምና ዕምነት አማኝ የነበረ ኢትዩጵያዊ ዜጋ በፈለገው ሁኔታ ወይንም በፈለገው ፍላጎታዊ ምክንያት ይኑረው እስልምናን ለቆ መውጣት እንደማይፈቀድለትና ሁሉንም ተሞክሮ አሁንም አማኙ ከእንግዲህ ወዲህ የፈለጋችሁ አሳማኝ ክርክርም ይሁን የኢኮኖሚ ድጎማ ብታደርጉልኝም ‘አልፈልግም’ ‘አልከተልም’ ማለት እንደማይችልና ሁሉንም ምክንያት ተሞክሮ አሁንም “አይሆንም” እስልምናን አልከተለም “በቃኝ” ካለ ሳድቅ መሐመድ (አቡ ሐይደር) እንዳለው ቅጣቱ “ግዲያ” እንደሆነ፤ አንገቱ እንደሚያጣ ‘በእስልምና ሃይማኖት ቀልድ’ እንደሌለና ቁርአናቸው ወይንም ሸሪኣቸው ሰውን የመግደል መብት እንደሰጣቸው፤ ይህ የመግደል መብትም ሕጋዊ እንደሆነ ነው ሳያመነታ በጠራ አገላለጽ ነበር መልሱን ያስቀመጠልን። ይህ ጭካኔ፤ይህ ጉድ፤ይህ ወንጀል በሃይማኖት የተደገፈ “ሕጋዊ” ሃይማኖታዊ ግድያ ከሆነ፤ በዚህ መሠረት በሺዎቹ የሚቆጠሩ የኢትዩጵያ እስላሞች የነበሩበት እምነት ለቀው ወደ ክርስትና እምነት በመቀላቀላቸው በየዓመቱና ባለፈው ወር የታየው በነዚያ አዲስ የክርስትና እምነት ተከታዩች ላይ በእስላም ሽብርተኞች ጥቃት ደርሶባቸው ስንመለከት “አቡሐይደር” የሃይማኖቱ መምሕራቸው ግድያ ይገባቸዋል እያለ በይፋ ሲሰብክ በነዚህ ንጹሃን ዜጎች ላይ ሰይፍ ሲመዘዝባቸውና ለወደፊቱም ማንም እሰላም ሃይማኖቱን ከለወጠ “እስልምናን መካድ ወንጀል” ነውና ቤቱን ንብረቱን እየተቃጠለ ፤አብረውት ወደ ሌላ ሃይማኖት የሄዱት ቤተሰቡና ዘር ማንዘሩ እንደሚጨፈጨፍ እያስተማረ ያለው ሰባኪ (ሸክ ሳዲቅ መሐመድ/አቡ ሓይደር) መንግሥት ተብየው ምን እየጠበቀ ነው? በጣም የሚገርመው ደግሞ ይህ ኋላ ቀር ሰው በግድያ ሰበካ ዜጎችን የሕሊና ጭንቀት እንዲያደርባቸው እያስፈራራና እስልምና የተወ ሰው ይገደል እያለ ሲሰብክ ለታየው ብጥብጥም እንዲህ ዓይነት ሰበካ በነፃ ሲለቀቅ ለሽብር ጥቃት በቀላሉ መስፋፋት ብር የሚከፍት ምክንያት ሆኖ እያለ “እስላሞች በአክሱም፤እስላሞች በኢትዩጵያ መብታቸው አልተከበረም እያለ በባዶ ጭንቅላቱ ሲጠይቅ “የመብት” ትርጉም የሚጻረረው “ሰው መግደልን” የመሰለ አረመኔነትና የፍጡራን “መብት” የሚጻረር ከሁሉም ወንጀሎች የበላይነት የያዘ ከባዱን ወንጀል “ሕጋዊ” ነው ሲል በጥላቻ ስብከት ሕሊናው የዞረበት ይህ አደገኛ ሰው እንዴት ልቅ እንደተተወ እንቆቅልሽ ትዕይንት ነው። እሱ በሚያስተምረው አረመኔነት የሚገደሉ ዜጎች መብት የላቸውም ሲል ይህ ሰው የሚኖረው በጫካ ሕግ The law of the jungle” ዘመን የሚኖር ወይስ በ21ኛው ክፍለ ዘመን? ለመሆኑ ሼኩ “መብት” ማለት ምን እንደሆነ ስለ የሰው ልጅ ክቡርነትና “መብት’ ትምህርት ቤት ውስጥ ተምሮ ያውቃል? ‘ዜጎች እስልምናን ከለቀቁ አንገታቸው ይቆረጥ ብሎ የሚያዘው የእርሱ ቁርአንም/ሸሪአም ይሁን የክርስትና ወይንም የማንም ሃይማኖት ይሁን የሰው ልጅ በሆስቴጅ/እገታ/ወደ ሌላ ቦታ /እምነት/ፍቅረኛ/ትዳር/ሥራ/ጓደኛ/ የመምረጥ መብቱን አግዶ “ባርያ” አድርጎ የሚይዝ ሃይማኖት፤ስለ ሰው ልጅ ቤተሰብነትና የሰው ልጆች ህይወት ክቡርነትና መብት ‘ምን እያለ ሊሰብክ ይሆን’? እግዚአብሔር/አላህ ማለት “ፍቅር” መሰሎኝ? አላህ ግድያ ውስጥ እንዴት ገባ? እኔ አይመስለኝም እራሳቸው ሰዎች ያጣመሙት ካልሆነ እንዲህ አይነት የራሱን ፍጡር የመመራመር ሃይል ሰጥቶ የሚያግድ ያውም እሱን ፍለጋ እውነታውን ለማግኘት ሩቅ መጓዙን እንዴት ይቃወመዋል? ሱኒው ውሃቢው ሺዓቱን እና ሌላውን ሲገዳደል የምናየው በዛው ሕግ ይሆን? መሰንበት ደጉ ማለት እኮ ጥሩ ነው። እንኳን እስላም አልሆንኩ። በዚህ የሰው ልጆች መብት ይከበር ምላሴ እስልምናውን ብተው ወይም ብወቅስ “አንገቴን ይቁኝ ነበር ማለት እኮ ነው” ጉድ! አቡ ሐይደርን ሳዳምጥ ተመስገን አምላኬ አንኳን ክርስትያን ሆንኩ አሰኘኝ አሁንስ።እንዴት ሰው በባርነት ተይዞ አትመራመር፤ ከተመራመርክ እንዴት ትገደላልህ ይባላል? እኔ የምገምተው ሼኮቹ የሚጠመዝዙት ሕግ እንዳይሆን? አቡ ሓይደርን ሳዳምጥ “ቶራ ቦራ” ሆኖ የሚያስብ የአፍጋን የሃይማኖት ጦረኛ ይመስለኛል፡ ንግግሩ ሁሉ ሳዳምጠው፡በጣም የጠበበ፤ አናካሽና ጉረኛ ትዕቢትም የወጠረው ባዶ ሰው እንደሆነ ይሰማኛል። ዘመኑ 21ኛ ክፈለዘመን ነን ያለነው፡ ሰውየው የሚዘባርቀው የሰው ግድያ ወንጀል “ህጋዊነት” እንዳለው የሚሰብከው የመቸ የዘመነ ጭካኔ ሕግ እንደሆነ ባይገባኝም፤ በዚህ ዘመን በዚህ በሰለጠነው ዓለም “ነውር፤ጥሩና በጎ” ተለይቶ በሚታወቅበት የሰው ልጅ ክቡርነት መብት ይብዛም ይነስ በሚከበርበት ዓለም እየኖረ፤“እስልምናን የተወ ሁሉ ይገደል” ብሎ በመላው ዓለም የተበተኑ ኢትዩጵያዉያን እስላሞችን በተጠቀሰው ፓል ቶክ በየጊዜው እየመጣ ሲሰብክ፤ አቡሓይደር በሚጠቅሰው የእስለሞች የመግደል መብትና ሕግ ተሞርኩዞ ብዙ ዜጎች ለጥቃት መጋለጣቸውና ለወደፊቱም የሚጋለጡ ከሆኑ የሰው ልጆች መብት ጠበቃዎችና መንግሥት ተብየው የወያኔው መንግሥት ይህንን ተከታትሎ እርምጃ ካልወሰደ የሱ መንግሥትንት ምን ሊረባ ነው? ይህ ትምክህት እየተዘረጋ እያዳመጠ እንኚህን ባዶ መንፈሶች በህግ ካልያዛቸው መንግሥት የማን ጐፈሬ ሊያበጥር ነው መንግሥት ሊሆን የሚችለው? ደግሞ እኔን የገረመኝ የዶቼቤላ ራዲዩ አዘጋጆች ይህ ቢከፍቱት ተልባ የሆነ በቶራ ቦራ ጭንቅላት የሚጓዝ ሰው አገኘን ብለው ለውይይት ማቅረባቸው በጣሙን ይገርማል። ሰውየው ባዶ መሆኑን እና ዋሾ መሆኑን የምትታዘቡት ደግሞ በአንድ የሰበካው አወድዩ ቪዲዩ ያስተላለፈው ንግግር በሌላኛው መርሐግብር/ፐሮግራሙ ያስተላለፈው ንግግር እርስ በርሱ ሲምታታበት ታዳምጣላችሁ።እየተደናገጠ ይሁን ወይንም ችሎታ አንሶት ወይንም ሆን ብሎ የመዋሸት ልምድ ኖሮት ብቻ አሁን ያለው ነገ ሲክደው ታዳምጣላችሁ። ያንን ቆየት ብየ አቀርብላችሗለሁ። የአቡ ሓይደር “የግደል ግደል” ሰበካ በሸሪዓ ከተደገፈ በየራሳቸው ምክንያት ብዙ ዜጎቻችን እስልምናን እየጣሉ ወደ ክርስትና ሲገቡ እየተከታተሉ ንበረታቸውን የሚያቃጥሉላቸውና አንገታቸውን በገጀራና በሰይፍ እየተቀሉ ያሉት ዜጎቻችን እያጠቋቸው ያሉ ቡድኖች ሃይማኖታቸው “አወስልምናን የተወ መግደል” ስለሚፈቅድላቸው “የእስልምና አክራሪ/ጽንፈኞች” ብለን ነው የምንጠራቸው ወይስ ምን ተብለው ነው የሚጠሩት? (ጉድ ዘመን እኮ ነው የገባነው!) እስኪ በሌላ መልኩ እንደገና ልጠይቅ፦<<ነብሰገዳዩችና ወንጀለኞች’ ሽብርተኞችና አክራሪ እስላሞች>> ብለን እንጥራቸው ወይስ <<ሕጋዊ ነብሰገዳዩች&፤ 'ሰላም አስፋኞች?>> ምን እንበላቸው? አሸባሪ እንዳንላቸው “አቡሓይደር” ሰውን መግደል “ሕጋዊ ነው” ሲል በይፋ እየሰበከ ነው። ለዚህም መጽሐፉ እንደሚደግፈው ይጠቅሳል። ይሄ ከሆነ በዚህ ሰበብ የሚገደሉ፤ንብረታቸው የሚወድምባቸው ሰዎች፤ በሽብር ኑሮአቸው በፈርሃት ኑሮአቸው የሚበጠበጥ ዜጎቻችን” ፤ “እንዲሞቱ፤ አንገታቸው በሰይፍ፤በገጀራ እንዲቀላ፤በድንጋይ ተወግረው እንዲሞቱ፤የትም ዞረው በነፃ የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት ተነፍገው ሕይወታቸው ለጥቃት የሚጋለጡ ዜጎቻችን “ቁርኣኑ/ሸሪአው መብታቸው ከገፈፈባቸው እና ገዳዩቹም ሰው ለመግደል ንብረት ለማቃጠል ተፈቀዶላቸዋልና ዜጎች እንዴት ከ“ጽንፈኞች አትበሉን” “ሕጋዊ ነብሰ ገዳዮች” መከላከል ይቻላል? ለመግደል/ነፃ እርምጃ ለመውሰድ በአላህ የተሰጠን መብት ነው ሊሉን ሽብርተኞች/አክራሪዎች ብለን ብንጠራቸው ፍረድ ቤት ቢወስዱን “ሕጋዊ” ነብሰገዳዩች (የአላህ የግደል፤ የአርዕድ፤አሸብር ትዕዛዝ አስፈጻሚዎች) ነን አንጂ ሽብርተኞች አይደሉም ልንባል ይሆን? እንዲህ ከሆነ ምን እንበላቸው? ወይስ ምን ቃል እንስጣቸው? መንግሥት ተብየውና የዓለም የደህንንትና የሰው ልጆች መብት ጠበቃዎች በዚህ ከፍተኛ ትኩረት አድርገውበት እውን ቁርኑ እንዲህ ዓይነት አሳፋሪና ኢሰብአዊ የግድያ ወንጀል ውስጥ ግቡ የሚል መጽሐፍ ከሆነና ዜጎች እንዳይገደሉ ንብረታቸውና ቤተሰቦቻቸው በሰይፍ እንዳያልቁ የአልሞት ባይ ተጋዳይ የመከላከል መብታቸው እንዴት ይከበር የሚለው ጥያቄ ሕብረተሰቡና መንግሥት መነጋገር ይኖርበታል። ሰው መግደል መብት የላቸውም የሚል ሕግ ካለም ፤ በይፋ የግድያ ስብከት የሚሰብኩት እንደ እነ አቡሐይኢደር አስከመቸ ቸል ተብለው ሊታለፉ ነው? ጽንፈኛው አቡሐይደር ቁርአኔ/ሸሪአው ይፈቅድልኛልና እስልምና ለቀው የሚሄዱ ሰዎች ተከታትየ እገድላቸዋለሁ ቁርአን/ሸሪዓ ፈቅዶልኛል እያለን ነው። ታዲያ ምን ይበጃል? በዚህ የተነሳ ሃይማኖታቸውን እየለቀቁ ወደ ሌላ ሃይማኖት የገቡ እና የመመራመር መብታቸው ተነፍጎ እየተገደሉ እንደሆነ ሁላችን የምናውቀው እውነታ ነው። የማያምን ካለ አብሮ ከዚህ ጋር በድምፅ የተቀዳ ቃለ መጠይቅ ለማስረጃ አቀርብላችኋለሁ። እንዲህ ከሆነ “አቡሐይደርም” ይሁን ሌሎች የኢትዩጵያ እስላሞች ኢትዩጵያ መብታችን አላስከበረችልንም፤ አክሱሞች የእስላሞች መብት አላስከበርም ብለዋል እያሉ የመብት ጥያቄ ሲያቀርቡ በሌላ በኩል የሰው ልጅ በሕይወት የመኖርና ደስ ያለው እምነት የመከተል መብት እንዳይኖረው “በግድያና ቤቱና ቤተሰቡ በእሳት ማጋየት፤ አንገቱን እንደ “በግ’ እነደ “በሬ” በቢላዋ እንዲታረድ በሰይፍ አንዲቀላ በድንጋይ ተወግሮ “እንዲሞት” ሕጋዊ ነው ብሎ መሰበክ “የአማኞች መብት መጣስ” ብቻ ሳይሆን “ወንጀል፤ጭካኔ አራዊትነት፤ነብሰ ገዳይነት፤ጥፋት፤እልቂት፤ብጥብጥ” እንዲነሳና እንዲስፋፋ ምክንያት ስለሚሆን ይህ እስካላቆሙና ካላወገዙ የእስላሞች መብት በአክሱምና በምድር የሚጠየቀው የመብት ጥያቄ የራስን ጭንቅላትን መጀመሪያ መወጠርና በሰብአዊ አስተሳሰብ በደግናትና በርህሩህነት አርቆ አሳቢነት ማነጽና ማጽዳትን ይጠይቃል። ሃሳዌ መሲሕ ማለት እንደዚህ ያለው ሰባኪ “ግድያን ህጋዊ” የሚያደርግ ስብከት ነው። ያፈለገው ይሁን ሃይማኖት ሃይማኖቱን ስለ ጣለ “ይገደል” የሚል በጣም አረመኔ፤ግራ ቀኝ ያለተመለከተ የሰው ልጅ ክቡርንት ሚጥል ስለሆነ ሁሉም ማውገዝ አለበት። ትልቁ የመብት ትርጉም ከዚህ ላይ ይጀምራል። ሰውን በካራ እያረዱ በሰይፍ በገጀራ እየቀሉ “መብቴን አክብሩልኝ” የሚል በጣም አስቂኝ ነው። ታራ ወንጀለኛና አሸባሪነትም ነው። እኔ እንደ ሚገባኝ ሃይማኖት ፍቅርን እንጂ ግድያን ላላንበት ዘመን የሚሄድ አይደለም። የቅድሙን ልጨምርላችሁለ- እስልምና ትተው ወደ ክርስትና የገቡት በተባለው የግድያ ሕጋዊነት እንደኔው የገረማቸው አባ ዕንባቆም እንዲህ ሲሉ ለቀድሞው ኢማማቸው ጽፈው እንደነበር መጽሐፋቸው ይመሰክራል፡


"ኦ እማም እምይእዜሰ አወስአከ በቃለ ትሕትና በከመ አዘዘኒ መጽሐፈ እምነትየ" ኢማም ሆይ ከእንግዲህ ወዲህ የምመልስልህ የሃይማኖቴ መጽሐፍ እንዳዘዘኝ በቃላት ትህትና ነው"

 ክርስትና እንኳንስ የኖሩበትን የተለወጡትም ሰይፍ ከማንሳትና በሰይፍ ከማጥቃት ሕሊና መልሶ እንዴት ሰላማዊ እንደሚያደርግ ለማሳየት ነው። “አባ ዕንባቆም ከሃገራቸው ከየመን ሸሽተው ወደ ኢትዩጵያ ገብተው በተለያዩ ገዳማት ተዟዙረው የቤተክርስትያኒቱን ትምህርት ልቅም አድርገው የተማሩና በምንኩስና የኖሩ በመጨረሻም በደብረ ሊባኖስ ገዳም አበምኔትነት /እጨጌነት/ የተመረጡ የበቁ ሰው ነበሩ። እስካሁን የሚታወቁት እጨጌ እንባቆም በመባል ነው። ( እንደላይኛው)።

ዛሬ አቡሐይደር ባለው ትኩስ ምላስ ቢያገኛቸው ምን ይላቸው ኖሯል? ያውም እኮ በጣም ከሚገርመው ነገር እሱ በሚያስተምርብት ፓል ቶክ ውስጥ የሚነገረው ጸረ ክርስትና እና ጸረ ኢትዩጵያዊነት፤ እንዲሁም አፍጋኒስታንና ዓለምን በሽብር የሚቆሏዋት የታሊባንና የአልቃይዳ ሽብርተኞችን እንደግፋለን በማለት በፓልቶኩ በይፋ ሲናገሩ እንዲሁም የኢትዩጵያ አብያተ ክርስትያናት በእሳት አቃጥሏቸው እያሉ የሽብር አዋጅ የሚነዙ በዛው አቡ ሓይደር በሚሰብክበት “Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice,” በተባለው ፓል ቶክ የሚናገሩትን በዩቱብ የተዘረጋውን ብታደምጡ ምን ትሉ ይሆን?

 ከዚህ በታች ሊንኮቹን/ መሰኮቱን/ቁልፎቹን እየከፈታችሁ አድምጡ። ሳዲቅ መሐመድ (አቡ ሓይደር) ለአላህ የሚውል ጥቅም ከሆነ ውሸት ዋሽቶ መስበክ በቁርአን ይፈቀዳል በማለት ውሸት እንደ እውነት ተደርጎ እስላሞች እንዲዋሹ የሰበከትንና እስልምናን ጥሎ የሄደ ሰው ግደሉት እያለ የሚሰብክበትን የሽብር መድረክ ምን እንደሚል እነሆ ከዚህ ቀጥሎ ያድምጡ። ይህነን ሲያደምጡ አምላክ ትዕግስቱን ይስጠዎት እላለሁ። የተዘገቡ 8ንት መዝገቦችን በቲ-ዩብ “ስዕለ ድምፅ” የተዘገቡትን ያድምጡ እነሆ፦

Please open the attached files to hear some of the audios. IF YOU CAN'T JUST COPY THE GIVEN URL ADRESS AND PASTE IT ON YOU TUBE. BUT, MAKE SURE CLICK ONLY WHAT I GAVE YOU TO HEAR SO YOU WILL NOT MISS ANY OF THEM. Audio evidences instigating Crime:-

1. The picture and teaching of Sheik Sadik Mohammed on killing X-Muslims : http://www.youtube.com/watch?v=A6rHwMBeNyU 2.Crime instigators lead by Sheik Sadik Mohammed : http://www.youtube.com/watch?v=k6PYrgrxtpE 3.Crime instigators lead by Sheik Sadik Mohammed video2: http://www.youtube.com/watch?v=cNwRPU-N2JQ 4.Instigators lead by Sheik Sadik Mohammed to burn Saint marry church in Ethiopia: http://www.youtube.com/watch?v=zskKK4X1smM&feature=related 5. Instigators lead by Sheik Sadik Mohammed declaring war : http://www.youtube.com/watch?v=v5wsqz7R4Vk&feature=player_embedded 6.A witness telling the damage of the violence in Jimma area and Muslims rejoicing: http://www.youtube.com/watch?v=sAdPBZD65zQ 7.A witness telling the reason for the violence was Muslims being converted to Christianity: http://www.youtube.com/watch?v=W4nIq7F8c3c 8.Crimes in jimma: http://www.youtube.com/watch?v=yTL3Yhlxb7Y Posted by Getachew Reda www.ethiopiansemay.blogspot.com Inquiry for any of my books please do call 408 561 4836

No comments: