Tuesday, January 25, 2011

The lie has become not just a moral category but a pillar of the state

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ ( ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com\ <አንዱ ሲቋጥር አንዲ ሲፈስበት የተቸገረው የጫካው መንግሥት ጌታቸው ረዳ የዘመናችን መንግሥት “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” ይባላል። ይህ ከጫካ የተሰጠን መንግሥት አስራ ስምንት ዓመት ሙሉ ብቻ ሳይሆን ከትግራይ የጫካ መንግሥትነቱ ጀምሮ ቢሰላ አንዱ ሲቋጥር አንዱ ሲፈስበት ከ34 ዓመት በላይ አስቆጥሯል። ይህ ቡድን ሲመሠረት ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ዘመኑ የተከተላቸው ፍልስፍናዎቹ ብንመረምር ከግልብ የለውጥ ስሜቱ አንስቶ በወረቀት ያሰፈራቸው ከምስራቁም ከምዕራቡም ቦጫጭቆ በመለገብ ለሕዝባችን ያስለበሰው ቡቱቶ ፍልስፍናው ለዛሬው ኑሮአችን ብቻ ሳይሆን የነገውንም ስጋት ጨምሮብናል። ከጫካ ዘመኑ ጀምሮ ይህ ቡድን የተከተላቸው መንግዶች ከተራ የሽፍቶች ባሕሪ አልፎ በዓለም አቀፍ የተራቀቁ ምስጢራዊ የሽብር አሰራሮች ከተከተሉት የግድያ እና የሽብር እንዲሁም ሕገወጥ የገንዘብ ድለባ ወደ ማካበት የተሸጋገረ በዓይነቱ እጅግ የተለየ አፍሪካዊ ሽብርተኛ የሽምቅ ተዋጊ መንግሥት ለመሆን በቅቷል። ሰሞኑን እየታዘብነው ያለነው የዋጋ ግሽበት በሌሎቹ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቀርቶ ብዙ ዋሾ ካድሬዎቹ እና ሚዲያዎቹ በሚኖሩባት ትግራይ ውስጥም ቢሆን ከቅርብ ወራት በፊት አገሪቱ አደገች፤ገበያው ነፃ ገበያ ነው…በማለት ሲዋሹን እና በሕሊናችን ሲዛበቱብን እንዳልነበረው ሁሉ ዛሬ የሪፖርተር ዘጋቢ በትግራይ በተለይም በመቀሌ ከተማ ምግብ ቤቶች እና ሱቆች በሥርዓቱ አገልጋዩች እየታሸጉ እንደሆነ ዘግቦታል። እነኚህ ባለሃብቶች ተቋሞቻቸው የታሸጉበት ምክንያት የዋጋ ንረት ተከትሎ ሸማቹ/ተጠቃሚው ሕብረተስብ ፍጆታዎችን የመግዛት አቅሙ መግዛት ከማይችልበት አቅም በመድረሱ፤ ለዋጋው ንረት ተጠያቂው ነጋዴውን በማድረግ የሚሸጡበትን የዋጋ መጠን በማውጣት፤ትዛዙን የተላለፉ ነጋዴዎች “ትዛዝ ባለማክበር” እየወነጀለ ተቋሞቻቸው እንዲታሸጉ አድርጓል። ይህ ድርጊት ቀደም ብሎ አዲስ አባባ ከተማ ውስጥ እንደታየ እና ውጭ አገር እዚሁ እኛ ጋር የሚኖሩ የሥርዓቱ ተከታዮች ልክ እንደጌቶቻቸው እኛኑን አንደዋሸን በመወንጀል በየዌብሳይቶቻቸውና በፓልቶክ ሸቃዮቻቸው አማካይነት የተመደቡበት ሃቅን የመሸፈን ተልዕኮ ሲያከናውኑ መደበቅ ከማይችሉበት ደረጃ በመድረሱ ይኸው ዛሬ ከአዲስ አበባ ተሻግሮ ችግሩ ወደ ትግራይም ጭምር በመሸጋገሩ የትግራይ ነጋዴም ሌሎቹ የቀመሱትን ጅራፍ መቅመስ ጀምሯል።በዚህ የውሸት ተልእኮ ለማካሄድ በትግራይና በውጭ አገር የተመደቡ የወያኔ የዜና ማሰራጫ ሸቃዮቹም አፍረው በመሸማቀቅ ይህ ካቅማቸው በላይ የተከሰተው ዱብ ዕዳ ዋሽተው እንዴት መከላለከል እንደሚችሉ አዲስ የውሸት ስልት ከጌቶቻቸው እየጠበቁ ይገኛሉ። ወያነ ትግራይ የኮሚኒስቶች ፍልስፍና አነግቦ መሬት በቁጥጥሩ ሥር አስገብቶ ሸቀጡን፤የመገናኛ አውታሮችን፤ ባንኮችና ንግድ ቤቶች በአስመጪና ላኪ በዋናነት ሃብታም ነጋዴ ሆኖ ለጥቂቶች ገነት ለብዙሃኑ የጭንቀት ኑሮ የሆነ ሥርዐት መሥርቷል።ሸማቹና አምራቹ በወያነ ትግራይ ዋና ታጁርነትና ቁጥጥር ስለሚገራ የዚህ ታጁር ተመፅዋች እና ትዕዛዝ አክባሪ ከመሆን አላለፈም። ታጁሮቹ ካቅም በላይ በሚጋብሱት ሃብት ሲተፉ ስለሚያድሩ ትፋታቸው የገባየው ዓየር በክሎታል።ምሕረት የለሽ ነጋዴ ቢፈጠርም የተማረው ከሥርዓቱ ነውና ተወቃሹ ነጋዴው ሳይሆን በዋናነት ሥርዓቱ ነው። በዚህም የተነሳ የገበያው ንረት ሲታወክ ስርዓቱን የሚመሩት ጥቂት ወረበሎችና አማካሮቻቸው “ደርግ” ሲያደርገው እንደነበረ የዋጋ ቁጥጥር ስልት ተከትለው ይኸው ዛሬም የዋጋ ንረት መነሻ ምክንያቱን በነጋዴው ላይ በማመካኘት አንዱን ሲቋጥሩ አንዱን ሲፈቱ ይታያሉ። ሥርዓት በዘመናዮቹ የወያኔ ትግራይ ያዲሱ ትውልድ የመሳፍንቶችና ጫካ በቀል ከብረቴዎች ስበስብ የሚመራ ስለሆነ እነኚህ መሳፍንቶች የሚከተሉት ሞራላዊ እሴት ቅጥፈት ሲሆን፤- ቅጥፈት ደግሞ“ በአገራችን ሞራላዊ እሴት ብቻ ሳይሆን የሥርዓተ መንግሥቱም ዋልታና ማገር ሆኗል። (In our country the lie has become not just a moral category but a pillar of the state) (ሰውነት መልካሙ) የዓለም የኖቤል ሽልማት ተሸላሚና የቀድሞ ሶቭየት ሕብረት ሥርዓተ -መንግሥት ነቃፊ ከነበሩት አለክሳንደር ሶልዘንስቲ ንግግር የተወሰደ።) <ስለሆነም ከትግራይ ጫካ የተሰጠን መንግሥት የሚከተለው ሞራላዊ እሴት “ቅጥፈት” ስለሆነ ቅጥፈትም የሥርዓቱ ዋልታና ማገር ስለሆነ በፖለቲካውም ሆነ በምጣኔ ሃብቱ በኩል በሕዝቡ ላይ የሚደረሰው የስቃይ ንዳድ ሲጨምር ሥርዓቱ የሚይዘውና የሚጨብጠው እያጣ አንዱ ሲቋጥር አንዱ ሲፈስበት ተጨንቆ ይታያል። አንዱ ሲቋጥር አንዱ እየፈሰሰበት ተቸግሮ ያለው ይህ ዝርክር ሥርዓት በተቃዋሚ ሃይሎች መወገድ አልቻለም። ይህ ከጫካ የተሰጥን መንግሥት የሚወገደው ዕጣ ፈንታችን ሆኖ “ባንድ አጉራ ዘለል ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት እንደሚሆን” ስጋቴ እየጨመረ ሄዷል። ሰላም እንሰንብት። ጌታቸው ረዳ Getachew Reda editor Ethiopian Semay www.ethiopiansemay.blogspot.com

3 comments:

Anonymous said...

Getachew, due to the racist structure of the military coup de'ta seems remote. What I am scared of is total chaos or civil war.

Anonymous said...

From the Editor:
Dear reader, thanks for commenting. Yes, I can’t dismiss what you commented entirely. Having said that there is one thing you seemed to miss. Coups are generally considered to be fundamentally undemocratic; the resulting government is not the outcome of a ballot of the people. Therefore be the TPLF Ethiopia’s army is majority staffed from one ethnic doesn’t necessarily meant there can be no conflict inside with interest changing the system, or doesn’t mean there will be individual or group who is frustrated and seek power. That is why I said Coups are generally conceding red to be undemocratic. So, Coups are not a government by the people to the people, or majority rule. So, if happened, it is still not of a government of majority.
If you recall those Ginbot7 (if that was true) ethnic Generals/military Coup that we saw last year in Ethiopia: - It was fundamentally undemocratic. Berhanu Nega (leader of Ginbot7) said –he supports anything including military coup. That showed the fellow is immature. Why I said this? Coups are generally undemocratic. One doesn’t wish nor shouldn’t look undemocratic change (coups) if a genuine leader who is looking a democratic change. If for example that coup was successful- there could have been leadership vacuum (don’t forget the Army is an ethnic staffed) might have been stained with blood (Meles supporter (TPLF) and the other group and who knows who other fifty ethnic affiliation armed military with each of their own desire and flag-could have been bloody and chaotic)
There are three basically 3 major Coups. Breaking Coups, (the TPLF type- when a successful guerrilla army overthrows a traditional or established government) Guardian Coups and Veto Coups ( These are

Anonymous said...

the kind of coups overthrow a popular government followed by blood shade (like the Derg or Argentina). Now, speaking the type of coups might happen in Ethiopia is the Guardian- that means the same familiar faces in the military and political hierarchies (same group of TPLF or other ethnic Gurus) take turn to run /repress the country (this could be with violence or no blood shade- depends with the character of the leader/s of the coup). So, I could have gone detail, but for now that is what I meant by Coups might take place if the opposition are not effective political agents. What might make Ethiopia lead to a chaotic situation if military Coup takes the stage is as you know TPLF and EPLF gave us the 100 years homework (that is ethnic politics), the terrorists and bloody OLF criminals, ONLF and other Islamic Ethiopian Talibans and Mujahedeen might create their own ethnic cleansing as they did in the past. So, those groups and the new coup leaders might create havoc in between of them and the people in the middle will have hard time to understand what is taking place. That is the scary situation. As you know those criminals lives outside the country, their supporters also lives in Europe and America in a warm sophisticated life- they give a dump to what will follow in Ethiopia-since they are rightwing ethno -centric or religious centric, all they will see at the conflict is as if it is their Monday FOOTBALL game (remember the Ethio/Eritrea war? A lot of people took that war as fan when bloody war was taking place- since they are not part of the pain- they will give their support to their fan living far from it). That is what might scare the hell out of me. Chaotic can bring aloe Military Coups. Chaotic situation can happen after or before Military Coup always. Thanks. Getachew Reda editor of Ethiopian Semay.