Friday, December 18, 2009

ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች እስካሉን ድረስ ወንጀለኞቹ ፍርድ ቤት የሚባል አያዩም!

ከለይ ፎቶግራፋቸዉ የሚታየዉ ብርሃኑ በርሀ (የዐረና ምክትል ሊቀመንበር)፤ ገብሩ አስራትስየ አብርሃ እና ቡልቻ ደምቅሳ፤ ሲሆኑ በመጨረሻ ልጁን ታቅፎ ሚታየዉ በወያኔ መሪዎች እና በጠባብ ብሄረተኞች የዘር አስተዳደር ፓሊሲ ምክንያት የተነሳ ባለቤቱ በጠባብ ብሔረተኞች የተገደለችበት እና እናቱ ያጣዉ ህጻን ልጅ የአማራ ብሔረስብ ገበሬ ነዉ።ዛሬ በእነ ገብሩ እና ብርሃኑ በርሄ ለዘለፋ ጥቃት እየተዳረጉ ያሉት በመኢአድ ዉስጥ ያሉት አመራሮች የአማራዉን ሕብረተሰብ ጥቃት በጽናት ቆመዉ የእነ ገብሩ እና ብርሃኑ አባዲ ፖሊሲ (አንቀጽ 39ኝን ጨምሮ) በመመከታቸዉ ነዉ። በመኢአድ መሪዎቹ ላይ እየዘነበ ያለዉ የተቀነባበረ የዘለፋ እና የስም የማጥፋት ዘመቻዉ ሴራ ዛሬም ህያዉ ሆኖ እየቀጠለ በመሆኑ ወደ ታሪኩ እንዉሰዳችሁ። መልካም ንባብ።
ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች እስካሉን ድረስ ወንጀለኞቹ ፍርድ ቤት የሚባል አያዩም! 
ጌታቸዉ ረዳ 

Friday, December 18, 2009

የኢትዬጵያን ህልዉና እና አንድነት ካናጉት የወያኔ መሪዎች መካከልትልቁ አድርባይእናብሄራዊ ወንጀለኛዉገበሩ አስራት የተባለዉ ትልቁ የወየኔ ዕቃ የትግራይ ህዝብ በርሃብ ሲያልቅ ለልቡ መታከሚያ ይሆነዉ ዘንድ ለርሃብተኛዉ ሕዝብ ከተመጸወተዉ እና ወያነ ከሕዝብ ባንክ በጠመንጃ አስፈራርቶ ከዘረፈዉ ካዝና $45 ሺህ ዶላር በላይ ከፍሎለት ለንደን እንግሊዝ አገር ድረስ አስታክሞት በሕይወት ቆይቶ ይሄዉና ተዘርዝሮ የማያልቀዉ የወንጀል የተባባሪነቱ እና ፈጻሚነትእድሜ ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆችየሰራቸዉ አሳፋሪ ድርጊቶቹ ተሸፍነዉለት እና ድሮ ተዘንግቶት፣ ባለፈዉ ሰሞን ትግራይ ክፍለሃገር ዉስጥ በማይጨዉ ከተማ የዋህ ተከታዬችን ለማሞኘት በጠራዉ ስብሰባ የመኢአድ መሪንወያኔ” (ኢሕአዴግ) ናቸዉ ብሎ ሲወነጅል አብሮት የወያኔን ዘረኛ ፖሊሲ እና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተግባር እዉን ለማድረግ ለብዙ ዓመታት ሲታገል የነበረዉ ብርሃኑ በርሀ የተባለዉ ወያነበጠበቃነት”/ ሙያ ያሰለጠነዉ ሌላዉ የዓረና ትግራይ ምክትል ሊቀመንበር ነኝ ባይ ድግሞ -እዚህ ዋሺንግተን ዲሲራዲዬ- ስኒትእተባለ በመኮነን ዘለለዉ የሚካሄድ የትግርኛ ራዲዬኦን ላይ በቃለ መጠይቁ በመሃንዲስ ሃይሉ ሻዉል ላይ ያንጸባረቀዉን ክፉ ጥላቻዉ እንዳይበቃዉ ማይጨዉ ከተማም በድጋሚ ኗሪዎችን ሰብስቦሃይሉ ሻዉልም የተክለሃይማኖት ሰፈር (ተክለሃይማኖት ሰፈር ኗሪ የሆኑት የትግራይ ማሕበረስብ) ሳይቀር መርጠዉናል እያለ የትግራይ ሕዝብ ከኢትዬጵያ ሕዝብ እንዲነጠል ሲያደርግ የነበረ ሰዉ ነዉ” (ኢትዬሚድያ- ላይ- “ዛሬ ይህንን ሰንሰለት ሰብራችሁታልበሚል ርዕስ ታደሰ ተስፋይ በተባለ ዘጋቢ ዓረናየተባለዉ ሌላዉ የወያኔ አንጃ ቡድን -ትግራይ /ሃገር ዉስጥ በማይጨዉ ከተማ የጠራዉ ሕዝባዊ ስብሰባ የተዘገበዉን ይመልከቱ) ሲል ዉንጀላዉን በቅጡ ለመረዳት ግራ በሚያጋባድፍን ዚቁንሲዘላብድ እና አያይዞምስለዚህም መኢአድ/ሃይሉ ሻዉል የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነዉ በመሆኑም አክራሪዉ ሃይሉ ሻዉል እና ትግራይ ጠላት ጋር (ከመኢአድ ጋር) አብሮ የተሳሰረዉ ያለዉ ኢሕአዴግ እንጂ ዓረና ትግራይ አይደለምሲል ወያኔ ባሰለጠነዉየአወሻሸት ትምህርቱመኢአድንበጸረ ትግራይ ሕዝብበመወንጀል፣ መኢአድን ዛሬም በድጋሚበመለስ የሚመራዉ የወያኔ ቡድንእናበገብሩ አስራት የሚመራዉ ሌላኛዉ የወያኔዉ ቡድን

መአከላዊ የጥቃት ኢላማቸዉ በማድረግ፣ እነ ገብሩ አስራት እና እነ መለስ ዜናዊ ኦኖጎች እና ከኤርትራዉ ሕዝባዊ ግምባር/ሻዕቢያ ጋር ግምባር በመፍጠር የጋራ ኢላማቸዉ ያደረጉትን የአማራዉን ሕብረተስብ በመጨፍጨፍ (ኢትኒክ ከሊንሲንግ) እና ከመደበኛ ሥራዉ፣ ከግብርና እንዲሁም ከንግድ የሥራ ዘርፍ እና የጥሮታ መብቱን በመንፈግ በሕይት እና በንብረት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱበትወያኔዎቹ እነ ብርሃኑ በርሀ እነ ገብሩ አስራትከወንጀላቸዉ ሳይጸጸቱየአማራዉን ሕብረተሰብከእነ ገብሩ ዘረኛ ጥቃት በመከላከል እና የነ ገብሩን ወንጀል ለዓለምና ለኢትዬጵያ የመገናኛ ዘርፎች በማጋለጥ 18 ዓመት በጽናት ቆሞ የአማራዉን ሕብረተሰብ እየሞተ፣ እየተገረፈ እና እየታሰረ ብቻዉን ቆሞ የተከላከለዉ የድሮዉ የመላዉ አማራ ድርጀት የዛሬዉመኢአድላይ ዛሬም ገብሩ አስራት እና መሰሎቹ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት የጥቃታቸዉ ኢላማ ማድረገቸዉ ይሄዉቀጥለዉበታል ፣፣

እነኚህ ግለሰቦች ለጥቃታቸዉ ኢላማ መነሻ ምክንያት ብንመረምር መልሱን ለማግኘት የሚያዳግት አይደለም፣፣ በእነ ገብሩ ድርጅት ሴራ ሕይወታቸዉን ያጡ የዚህ ድርጅት (የመኢአድ) አመራር አባሎች እና በሕይት ያሉ ድርጀቱን እየተከላከሉ የሕዝቡን ጥቃት በመዘገብ እያጋለጡ ያሉት መሪዎችን ለመተንኮስ የተነሳሱበት ምክንያት ይህ ድርጅት እነ ገብሩ አስራት በትግል ማኒፌስቶአቸዉ እና በፕሮፖጋንዳ ፖለቲካዊ ቅስቀሳቸዉ የመጀመርያ የጥቃት ኢላማቸዉ የደረጉት አማራዉን ሕብረተሰብ ማግለል በመኖሩ የመኢአድን አመራሮች ለመተንኮስ ያቀዱበት ዋነኛዉ ምክንያት የእነ ገብሩ ፋይል በመኢአድ አመራሮች እና በተከታየቹ፣ በደጋፊዎቹ እና የሰለባቸዉ ተጠቂ በሆነዉ ሕብረተሰብየሕሊና ማሕደር ዉስጥበጥንቃቄ ተመዝግቦና ታሽጎ እንዳለ ስለሚያዉቁመኢአድተደራጅቶ ዛሬም የነ ገብሩን ድርጅት 18 ዓመት የወንጀል ማሕደር ጉድ እያጋለጠ ፍትህ ፍለጋ እንዳለ ስለሚያዉቁ የሚል ስም ፖለቲካ መድረክ ዉስጥ መገኘቱ እንደ ቅዠት እያባነናቸዉ መሆኑን ግልጽ ነዉ፣፣

 ይህ ለምን ሆነ? የወያነ ትግራይ ብሔራዊ ወንጀለኞች አሁንም በሰለባቸዉ/በተጠቂ ላይ የሚያሾፉበት መድረክ እንዴት ሲኮን እና በምን ታምር እንዲህ ያለ ተደጋጋሚ ድፍረት ዐድሉ ሊያገኙት ቻሉ? የሚለዉን ጥያቄ መጠየቅ እንቆቁሉሹን መፍታት ያስችለናል፣፣ ወንድም ወንድሙን ገድሎ እርቃኑን አውጥተው፥ ሳንጃን በሞቀ እሳት እያጋሉ ገላን ማቃጠል እና እርቃኑን አስወጥቶ በእሳትና በፈላ ዉሃ እያቃጠሉ ገርፎ ፣ሰብአዊ ክብርን አዋርዶ፣ በሕግ ሳይጠየቅ እና ተገቢዉን ቅጣት ሳያገኝ በሰላም ተኝቶ በነጻ የሚንደላቀቁባት አገር በዓለም ዉስጥ ኢትዬጵያ ብቻ እንደሆነች እነገብሩ አስራትእነብርሀኑ በርሀ” “እነኣዉዓሎም ወልዱእነአረጋሽ ኣዳነእነአበበ ተክለሃይማኖትበሚገባ ያዉቁታል፣፣

 ወያኔዎች መጀመርያ ወደ ትግራይ ከተማ ሲገቡ የትግራይ ናሪ ተሰብስቦ ድምጹን በማሰመማት ሕዝቡን እና ገበሬዉን ያሰቃዩ የወያኔ ክፍሊ ሕዘቢ የተባሉ ገራፊዎች እና የወያኔ ከፍተኛ አመራሮች ፣የስለላ ክፍሎች እና ነብሰ-ገዳዬች እንፋረዳቸዋለን የሚሉ 500 የማያንስ ሕዝብ ሰለማዊ የፍትህ ጥያቄ ለገብሩ አስራት ሲያቀርቡለትበረሃ ላይ እያለን የሰራነዉ ወንጀል ካለ ለነጻነት ሲባል የተደረገ በመሆኑ አያስጠይቀንምበማለት አርፋችሁ ቁጭ በሉ  እያሉን ነው።በሕዝብ እና በፍትሕ ያሾፈዉን ገበሩ አስራት ከእነ ወንጀሉ 18 ዓመት በሰላም ተኝቶ እንዳደረ አዉቋል፣፣

 

ይህ የሆነበት ምክንያትም ሠራዊትን፣ ሕዝብን፣ ሕብተሰብን፣ሉዓላዊነትን በጅምላ ያጠቁ የፖለቲካ ወንጀለኞች እንደገና ጥቃቱን ዳር እንዲያደርሱት መንገዱን ቀጤማ እየነሰነሱላቸዉ የሚታዩ ለመጣዉ ሁሉአርጋጆችበብዛት የተፈለፈሉባት አገር ኢትዬጵያ ብቸኛዋ አገር በመሆኗም ጭምር ነዉ (ኢንጂነር ግዛቸዉ እና መረራ ጉዲና የተባሉዕቃዎች/ ዉዥምብራሞች/አርጋጆችለወንጀለኞቹ ጥብቅና ቆመዉ የሰጡትን ቃለ መጠይቅአዲስ ድምፅበተባለዉ የአበበ በለዉ ራዲዬን አርካኢቭ/ማሕደር ዉስጥ በመግባት ያድምጡ) ፣፣

ይዘገያል እንጂ አህያ የጅብ ናት እንደሚባለዉ ወንጀለኞቹም ይዘገይ እንደሆን እንጂ እንደዚሁ እየተንደላቀቁ እስከ ወዲያኛዉ ሊዘልቁ እንደማይችሉ እና በአንድ መጪ ወቅት አንድ ሃገራዊ ቆፍጣና መሪ ሲነሳ ሰብስቦ እስር በማስገባት ለፍርድ እንዲቀርቡ እንደሚያደርግ ምኞቴ የጸና ነዉ እላለሁ፣፣

የገበረመድህን አርአያ ለመጪዉ ትዉልድ ታሪክ እንዲሆን ያጠራቀመዉግዙፍ ፋይልእና የሺዎቹ ሕይወት ለሕልፈት መዳረግ፣ ግርፋት እና እንግልት ዘረፋና ፈርደገምድል፤ክህደትና ተንኮል የተዘገበበት ማህደር አፉን ከፍቶ ጊዜ እየተጠባበቀ ነዉና ፍትሕ ይዘገይ ይሆናል እነጂ አንድ ቀን ግን ፍትሕ አፉን ከፍቶ በነዚህ ጅቦች ላይ ያነጣጥራል! አንድፈስያ እንተትሓንከልካየሚባል የትግርኛ አባባል አለ፣- “ፈስታ ስታበቃ አለማፈርዋ” (ፈሳም- ፈስታ ስታበቃ የፈሳዉ ማን ነዉ? ብላ ሌላዉን ንጸሁን ሰዉ ለማሳጣትፈሳምብላ በድርቅና መወንጀሏን ያስገርማል ማለት ሲሆን) በሌላ አነጋገርሌባስያ ሌባ አይበልካየሚባልም አለ፣ሌባሌባአይበልህየሚሉት አባባል ስናስተዉል አረና ወያኔዎች ቀንደኞቹ ወያኔዎች ራሳቸዉ ሆነዉ መሃንዲሱ ሃይሉ ሻዉልንወያኔናቸዉ ብለዉ ሲከስሱየሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅሚባለዉ ተረት እነሆ በዓይናችን ለመመስከር በቅተናል።

ወይ ጊዜ! (እናንተየ የጥንት ወላጆቻችን እንደዚህ ያለዉ ድረቅና በምን ቃላት እንደሚገለጹት ግራ ሲገባቸዉ ለካ ነበርምን የሚሉት ነዉ፤ ጭንቅ ያለ ነገርበማለት አግርሞታቸዉ የገለጹት) ፣፣ ገብሩ እና ብርሀኑ፣ አረጋሽ እና ኣዉዓሎም የሚመሩትየዓረና ድርጅትመኢአድን የሚመሩት መሃንዲስ ሃይሉ ሻዉልንጸረ ትግራይ” (ወንጀለኛ፣ አክራሪ፤ወየኔ) ነዉ የማለት የሞራል ብቃቱ ከየት እንዳገኙት ድፍረታቸዉ ሳስበዉ እጅግ በእዉነት እጀግ አድርጎ ይደንቀኛል! ወንድሞቼ እና እህቶቼ አባቶች እና እናቶች ሆይ፦ አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ተክለሃይማኖት ሰፈር የሚኖሩ የትግራይ ማሕበረሰብ ተወላጆች ከወያኔ ይልቅቅንጀት ነበር የመረጡት ብለዉ ኢንጂነር ሃይሉ መናገራቸዉ በምን ስሌት ፣በምን ትረጉም፣ በምን ቋንቁኛ፣ጸረ- ትግራይእንዳሰኛቸዉ ለኔ በጣም በጣም እጅግ በጣም ግራ የገባ አባባል ነዉ፣፣

ብርሃኑ በርሀ የተባለዉ ነብሰ ገዳዬች፤ገራፊዎች እና አምባገነኖች የሚመሩት ዓረና የተባለዉ ድርጅት ምክት ሃላፊ እናየሕግ ጠበቃነኝ የሚለን ይህ ሰዉ አዲስ አበባ የሚኖርየትግራይ ማሕበረሰብ እንኳ ሳይቀር ለቅንጅት ድምጹን ሰጥጧልብሎ ማለት በየትኛዉ ትምህርት ቤት የተማረዉ ሕግ ነዉጸረ ትግትሬነትነዉ የሚል እምነት ሊያሳድርበት የቻለዉ? በመረጃ አስደግፈን ማቅረብ እንደሚቻለን እና ብዙ ጊዜ ካሁን በፊት መረጃዎቻችንን በተጨባች አስደግፈን እንዳቀረብነዉ ሁሉ አብዛኛዉ የከተማ የትግራይ ማሕበረስብ (በተለይ ቀለም የቀመሰዉ የከተማ ኗሪ) ከዚያ በፊት ሲነገር የነበረዉ ለወያነ ትግራይ ነበር ድምጹንም ድጋፉንም፣ጉልበቱንም ሕሊናዉም ስብሰባዉም ማህበሩም ገንዘቡንም ሌላ ቀርቶ ኤርትራ ነጻ ሙጣት አለባት ዓስብ እና ምጽዋ በኤርትራ አስተዳደር በሻዕብያ ቁጥጥር ይሁን ብለዉ የተስማሙት እነ ገብሩ አስራት የፓርላማ ድጋፍ የፈረሙት እነ ስየ አብርሃ ድምጽ እና ድጋፍ ሲሰጡ በየቀበሌዉ ተቀናጅተዉ የድምጽ ድጋፍ የሰጡት አዲስ አበባ ከተማ የሚኞሩ የትግራይ እና የኤርትራ ተወላጆች እንደነበሩ ብረሃኑ በርሀ ከመቸዉ ዘነጋዉ?

ባዲስ አበባ የሞኖሩ የትግራይ ተወላጆች እና የትግራይ ልማት ድርጅት (ቲዲኤ) ከወያኔ ድርጅት ጋር በመተሳሰር ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረዉ በማድረግ የትግራይ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ባስፈላጊዉ መንገድ ወያኔን እንዲያጠናክር የተደረገዉ ስራ ብረሃኑ በርሀ ያዉቀዋል? ወየኔዎች አዲስ አበባ ሲገቡ ከፍተኛ ትብብር እና ድጋፍ የለገሰዉ የትግራይ ተወላጅ እንደነበር ይዘነጋል? (ዉጭ አገር አለዉ የትግራይ ማህበረሰብ እማ ተዉት- ተነጋግረንበታል) በየሚድያዉ፣ እና በየኩባንያዉ ነጋዴዎች እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና በኪነት/በየትያትር ተቋማቶች ዉስጥ የነበሩ ትግራይ ተወላጆች ወያኔ ሲገባ አግልግሎታቸዉ ሙሉ በሙሉ ለማን ነበር የለገሱት?

ወያኔን በመረጃ ስምሪት እና ቅብብል 17 ዓመት ያገለገለዉ ማን ነበር? ሌላ ቀርቶ ወያኔ ትግራይ ዉስጥ 8 አዉራጃዎች ዉስጥ 7 የደርግ የሕዝብ ድርጅት /ቤቶች የወያኔ አባሎች ያስተዳድሩት እንደነብር ራሳቸዉ ያመኑት ነዉ፣፣ አነኚህ ክፍሎች ይዞ ነበር ወያኔ ለዚህ ደረጃ የደረሰዉ፣፣ ብርሃኑ በርሀ እና ገበሩ አስራት ወያኔ ጉያ ዉስጥ አስከነበሩ ድረስ እና ገብሩ አስራትም የትግራይን ሕዝብ 10 ዐመት ሙሉሲገዛ የሕዝብን ድምፅ እና ስሞታ ሲያፍንእስከነበረበት ጊዜ ድረስ የትግራይ ሕዝብ ከድርጅቱ ከወያኔ ጎን የቆመ ሕዝብ ነዉ እያለ ሲለፍፉ እንደነበር የሚዲያ ማስረጃዎች አሉን፣፣ ከዚያ ባሻገር ገበሩ አስራት እና ብርሃኑ በርሀ፣ አዉዓሎም ወልዱ አረጋሽ አዳነ …..ከወያኔዉከመለስ ዜናዊከተለዩ በሗላ የትግራይ መለስን አዉግዞ ወደአንጃዉ ዞሯል፣ ሌላ አማራጭ እፈልጋለሁ ብሏልሲሉም ይደመጡ እነደነበር አሰራጯቸዉ መግለጫዎቻቸዉ ይመሰክሩባቸዋል፣፣

 የትግራይ ሕዝብ የመለስን አስተዳደር በቃኝ ብሏል ካሉን 1995 ግንቦት 7የተደረገዉ ምርጫ ገብሩ አስራት 6 ዓመት አንቀጽ 39 እንዴት እዉን እንደሚሆን ዓረና ለመመስረት አድብቶ ከጓደኞቹ ጋር ማኒፌስቶ 39 ሲያዋቅር ጊዜ ስለፈጀበት እና 1995. ግንቦት ዉድድር ዉስጥ ገብቶ ለመወዳደር ስላልቻለ አዲስ አበባ ዉስጥ የሚኖሩ የትግራይ ማሕበረሰብ ተወላጆች የመለስ አስተዳደር ጠልተዉ ለቅንጅት ድጋፍ በመስጠታቸዉ እና ይህ አዲስ ክስተት (“ሺፍት”) በቅንጅት መሪዎች እንደምሳሌ ተደርጎ ቢቀርብ የቅንጅት መሪዎች እነ እነጂነር ሃይሉ ሻዉልሌላዉ ኗረስ ይቅር - አዲስ አበባ ዉስጥ ለብዙ ዓመታት ወያኔን ሲደግፉ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች አንኳ ሳይቀርለቅንጅት ድምፅ ሰጥቷልብለዉ መናገራቸዉጸረ የትግራይ ሕዝብየሚያስብለዉ ንግግር የቱ ላይ ነዉ?!

ትግሬ ወደ መቀሌ የተዘረፈ ንብረት ወደ ቀበሌብሎ በዉስጥ በተንኮል ሰራዉን ቀምሞ ያሰራጨዉ ማን ነበር?

በእርግጠንነት ለመናገርየቅንጀት አመራር እንደልለነበረ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁሌላ ቀርቶ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አድማም ሆነ 50 የተለያዩ የከተማዋ ቦታዎች ህዝባዊ አድማ ሲቀሰቀስቅንጅትየሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለዉ በርግጠኝነት መናገር እንችላለን።

 እነ ብርሀኑ በርሀ እና እነ ገብሩ አስራት አለቆቻቸዉ እነ መለስ ዜናዊ ቅንጅት እንተርሀሙዌ ቅስቀሳ አደረገ ብለዉ ስለነገርዋቸዉ የወያኔ አለቆቻቸዉ ናቸዉና ከመለስ ከቅንጅት ይልቅ መለስ እና በረከት ማመን ነበረባቸዉ፤፤ ምንም ቢሆን በጎሰኞች ራዕይትንሽ ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋነበርና። ስለነበርም ነዉ ገብሩ አስራትድሃይ ትግራይበተባለዉ ትግርኛ በሰጠዉ ቃለ መጠየቅቅቅንጅት ትግራይ ጠላት እንደሆነ እና ከነ ቅንጀት ምንም የሚያገናኝ የፖለቲካ ትስስር ያኔም ሆነ ለወደፊቱ እንደማያደርግ የለፈፈዉ (የትግርና ትርጉም በማርኛ የተረጎምኩት በኢትዬጵያን ሰማይ አርካኢቭይጎልጉሉ”/በማሰስ ይመልከቱ)

በዛዉ መጽሄትም አብሮ አዛዉንት ቤተሰቦቻችንን በእሳት እያቃጠለ ሲገርፋቸዉ ነበረዉ የድሮ የወያኔ የአየር ሃይል ኤታማዦር ሹም ነበረዉ የዛሬዉ ያዲስ አበባ ዩቨርሲቲየሕግ” (እባካችሁ አትገረሙ) መምህር የሆነዉ ጀኔራል አበበ ተክለሃይማኖትም (ጆቢ) ቅንጀት አዲስ አበባ ሲየሸንፍበኢንትርሃሙዌ ፕሮፖጋንዳምክንያት ሽፋን ተጠቅመዉከወያኔ የተባረሩት እና የለቀቁት የጦር ሹማምንት እና ወያኔ አንጃዎች ሁሉ ከመለስ ዜናዊ ቡድን ጋር በማበር ጊዜያዊ ኮሚቴ/ደርግ በማቋቋም በትጥቅ ማዕበሉን (መለስ ዜናዊ ከስልጣን/ወያኔ ከስልጣን እንዳይወርድ ማለት ነዉ) እንዲያቆሙት ምስጢራዊ ዝግጅት አድርገዉ እንደነበሩና መለስበቁጥጥር ሲያደርጋቸዉ እና ስልጠኑ መልሶ ካረጋገጡ በሗላ በምስጢር ተወቀረዉ ቡድን ለጊዜዉም ቢሆን እንደተበተነ (በይደር ዛሬም ሊኖር ይችላል) በሰጠዉ ቃለ መጠይቅ ተዘግቧል።

ስለዚህ የገብሩ እና የብርሀኑ በርሀ በማሃንዲሱ ሃይሉ ሻዉል መረባረብ አዲስ አይደለም እና ከስትራተጂ አንጻር የተጠና ከበባ ነዉ። ከዚህ በማያያዝም ልብ ልትሉት የሚገባዉ በወቅቱ 1993 አካባቢ ወያኔ እንደ ብርጭቆ ሲሰነጠቅ አዲስ አበባ ዉስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ዓባይ ፀሃየ ለስብሰባ ጠርቷቸዉ ካሰሙት ንግግር እና ዓባይ ጸሃየ እራሱ ለምን እምባ እንደተናነቀዉ በአንድ የትግራይ ተወላጅ ዘጋቢ የተላለፈዉን አስታዉሱት፣፣

 ተሰብሳቢዎቹ ካሁን በፊት የማን ደጋፊዎች እንደነበሩ በሚቀጥለዉ እትምዘገባዉ እንዳለለታሪክ ትዝብታችሁ እንዲዳብር በዝርዝር አቀርብላችሗለሁ፣፣ አሁን ብርሃኑ እየቀላመደ ያለዉን ዉንጀላዉ በምሳሌ እየተተቀሰዉ ያለዉ የከተማዉ የትግራይ ማሕበረሰብ ከቅንጅት በፊት በወያኔ ላይ የነበረዉን እምነቱ በትክክል ልትረዱት ትችላላችሁ፤፤ ስለዚህ ኢንጂነሩ ያዲስ አበባ የትግራይ ማሕበረሰብ ተወላጆች ሳይቀሩ ቅንጅትን መርጧል ማለታቸዉ አስመሰግናቸዋል እንጂ እንዴት ጸረ ትግራይ ሊያሰኛቸዉ ይችላል? የሰጡት ድምፅ ለኛዉ ለወያኔዎች ነዉ ብሎ መለስ ሲደሰኩር፤ በበኩላቸዉ ቅንጅትን የወከሉ መሃንዲስ ሃይሉ ሻዉል የለም ለኛ ለቅንጅት ነበር ድምፆቻቸዉ የሰጡት ብለዉ ቢሉ ምን ነዉር አለዉና ነዉ እነ ብርሃኑ እነ ገብሩ በመኢአድ መሪ ላይ ዓይናቸዉ ደም ለብሶ ለቁጣ እና ዉንጀላ ሊሰነዝሩ የበቁት?

እኚህ ወንጀለኞች በጣም ቀለዱብን አይደል! ሆሆሆሆሆ! ዳሩ እነሱ ምን ያርጉ! ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች በዉጭም በዉስጥ አገርም እንደ አሸን እስከፈሉ ድረስ እዉነታቸዉ ነዉ፤ እነሱ ምን ያድርጉ?

17 ዓመት ሙሉ የበረሃ ንገስታት ሆነዉ በሕዝብ ደም የነገዱ ወረበሎች፣ የስንቱን ሺህ ሕዝብ ደም አፍስሰዉ፣ ንብረት ሕይወት አፈናቅለዉ፣ አጣልተዉ፣ ኣባልተዉ አቀያይመዉ እና የሰዉ ልጅ በእሳትና በጋለ ሳንጃ ያቃጠሉደናቁርት/beasts” ፍርድ ቤት የሚባል መቸም ቢሆን አለቅላቂዎች አስካሉ ድረስ ፍትህ አያዩ! በእስር ይልቅ ተደላድለዉ በሞቀ ትዳር እና ሕይወት ነጻ የዉጭ አገር የሽርሽር ሕይወት በመኖ ተደላድለዉ እየኖሩ ነዉ እነሱ ምን በደሉ?

ይህ ለሰለባዎቻቸዉ የሚያበሳጭ እና የሚያቃጥል ሌላ ተጨማሪ ብትር እና ግፍ የሚየቀብሉዋቸዉ የኛዎቹ ናቸዉከመሃላችንያሉት! ወገኖቼ፤- ገራፊዎቻቸዉ እና ጨቋኞቻቸዉ በነፃነት እንዲህ እየተዝናኑ ተንደላቀዉ ሲኖሩ የታዘቡ ሰለባዎቻቸዉ ዉስጣዊ ሕሊናቸዉ ምን እንደሚሰማቸዉ አስቡት! ወንጀለኞቹ ፍርድ ቤት መቅረብ እና መጠየቁስ ይቅር እኔን ሁሌ የደንቀኝ ግንዛሬም እና እንደ ግመል ጎትቱንየሚሉአርጋጆችእናአለጥላጭ ወገቦችከማሃላችን ዉስጥ እንደ ሰንበሌጥ በቅለዉ እየተወዛወዙ የፍትህ መንገድ እንዳይታይ ሆን ብለዉ የነዚህ ወንጀለኞች ክብር እና ዝና እንዳይነካ የሚያራግቡትን ክፍሎችን ደጋግሜ ስታዘብ በቃላት ለመግለጸስ በሚከብድ ባገር እና በወገን ወንጀል የፈጸሙ እንኚህ ወንጀለኞች ዛሬ በኢትዬዖጵያዊያን እና በኢትዬያዊ የድርጅት መሪዎች ላይ የተካኑበትን የስም ማጥፋት ዘመቻ በድጋሚ ትግራይ ዉስጥ በትግራይ ሕብረተሰብ ተገኝተዉ ብርሃኑ እና ገብሩ አስራት ቀዳሚ አጀንዳቸዉ ያደረጉት የመወያያ አጀንዳመኢአድ/ሃይሉ ሻዉልመሆኑን ዛሬም ያላንዳች ሃፍረት/ይሉኝታ ሲጠመዱ ዘገባዉን ማንበብ እዉነትም እነሱ ምን ያድርጉ ያሰኛል? በኔ ይሁንባችሁለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች እስካሉን ድረስ ወንጀለኞቹ ፍርድ ቤት የሚባል አያዩም!” በከበባ እና በወከባ አጠፋነዉ ብሉዉ የበተኑት እንዲሁም ግፍ ፈጽመዉበት የትም የተበታተነዉ ኢትዬጵያዊነቱ እና ሉአላዊ ክበሩ የተነካዉ ክፍል ዛሬም ባንድነት በመቆም እነዚህን ብሄራዊ ወንጀሎኞች ወደ ዓለም አቀፍም ይሁን አገር አቀፍ ፍርድ ቤት ጎትቶ ለማስቀጥት ሁሌም አትኩሮቱ በዛዉ ማድረግ አልቻለም፣፣

እነዚህ ወንጀለኞች ፖለቲካዉን እንደ ሽፋን ተጠቅመዉ የመተንኮስ ሱሳቸዉን ካላቆሙ እኛ የነዚህ ወንጀለኞች ሰለባ የሆንን ክፍሎች ሁሌም እየቀለዱብን እየተዘለፍን የምናርፍበት ምክንያት በፍጹም አይታየኝም፣፣ የነዚህ ክፍሎች በፖለቲካዉ መድረክ መልሰዉ ማንሰራራት የዘለፋ ዘመቻዉ ሰይፋቸዉ በድጋሚ በማን ላይ አዝምሞ እንዳለ ማጤንደመናዉ የዝናሙ መምጣት ይጠቁማልእና ጠንቀቅ ማሉቱ አይጎዳም ሚል ምክር አለኝ። ሕዝቡን ለድጋሚ ማስጠንቀቅ አስፈላጊ ነዉ እላለሁ፣፣ መግቢያ በሮች ሁሉ ለነዚህ ወንጀለኞች ዝግ እንዲሆኑ በብርቱ መከላለከል ዛሬም ያስፈልጋል፣፣ በዓረና እና በስየ በኩል ጸረ ሃይሉ ሻዉልም ይሁን ጸረ ታየ ወልደሰማያት እና በሌሎች ኢትዬጵያዊያን ድርጅቶች እየተካሄደ የለዉ የጥላቻ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ የዋዛ ሳይሆን የተቀነባበረ የወያኔ ስልት መሆኑን ኢትዬጵያዊያን ካሁኑኑ ማወቅ ይገባል እላለሁ፣፣ ቅንጅት/( ) የመለስ ቡድ እና የገብሩ አስራት ቡድኖች እነዴት በማሃል አስገብተዉ የጥቃት እና የመከራከርያ ማአከላዊኢላማቸዉእያደረጉት እንደሚገኙ በመረጃ ላስግፍ እና ቅንጀት/ ኢአድን እንደአህያቆጥረዉ ሁለቱም የወያኔ የጅቦች ቡድን በማሃል አስገብተዉ እንዴት ከበዉ እንደሚቀጠቅጡት አስደግፌ በመረጃ ልሰናበት። ከዚህ በታች የቀረበዉ ዘገባ በአሜርካ ድምፅ የትግር ክፍለ ጊዜ የቀረበ አብርሃም ገብረመድህን የተባለ የመለስ ተጠሪ እና አሁን እንጂነር ሃይሉን በጸረ ትግራይ ሕዝብ በሃሰት እየከሰሰ ያለዉ የዓረናዉ ምክትል ሊቀመንበር ብርሃኑ በርሔ ያደረጉት ክርክር ነዉ።ቃለ መጠይቁ ቀረበዉ በትረ ስልጣን በተባለዉ ያሜረካ ድምፅ የትግርኛ ክፍለ ጊዜ ጋዜጠኛ ነዉ። ይሄዉና፦ 

By Betre Siltan Washington 04/03/2009 Ethiopians who represent the ideologies of the ruling Tigray People’s Liberation Front and the year-old Arena Tigray for Sovereignty and Democracy parties clashed in a heated radio debate on the Tigrigna service’s Crossfire show on Monday. Abraham Gebremedhin of the ruling TPLF and Berhanu Berhe, a leader of Arena Tigray for Sovereignty and Democracy, argued politics and purposes in a program moderated by Betre Siltan. Abraham says Arena is an agent of Kinijit, the 2005 coalition of political opposition to the EPRDF. Berhanu says the TPLF tries to dominate Ethiopia’s political discussion. “Arena Tigray is not an alternative party for the simple reason that all its programs are included in the EPRDF's policies," said Abraham. He called Arena-Tigray the mouth piece of Kinijit, the opposition coalition that was created during the 2005 Ethiopian election.” 

ሲል የመለስ ዜናዊ የወያኔዉ ቡድን ቅንጅትን/ ኢአድን ማአከላዊ ጠላት ቆጥሮ ዓረና ከቅንጅት ጋር መጠጋቱ ሲወነጅለዉ፤- የዓረናዉ ብርሃኑ በርሄ ደግሞ ቅንጀት 1995 በሊቀመንበርነት የመሩትን ማሃንዲስ ሃይሉ ሻዉልን (ቅንጅት/ ኢአአድ) የትግራይ ጠላት ሲል በቅርቡ ወንጇሏቸዋል። ከዚህ የምንረዳዉ ቢኖር ቅንጅትን በጠንካራ ክንድ የገነባዉ የመኢአድ አመራር አባላት ዛሬም በሁለቱ ወያኔዎች እንደ ማካላዊ ጠላታቸዉ እንድተገነዘቡት ያስፈልጋል። አመሰግናለሁ። /-/ ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com


1 comment:

KEANEBEBHUT said...

It is really nice to notice that there are also true Ethiopians from Tigrai like you and ato Gebre Medhin. Sooner or later truth triumphs and keep it up. Engineer Hailu is hope for millions who are starved of freedom and nourishment. YICHALAL! It is possible to build an Ethiopia free from Woyane tyrany and poverty and true Tigreans like their other Ethiopian brothers and sisters benefit from a free and democratic Ethiopia.