
የኛ ሰራዊት ከእነደዚያ ዓይነቱ ምርጥ አዋጊና ተዋጊ ጦር መግጠማችን ያኮራናል። የጠላት አዋጊዎችም በኛ ሰራዊት አድናቆትን አትርፎላቸዋል። በእንደዚህ ዓይነት ሃየለኛ ሰራዊት እና አዋጊዎች ባየነበት ዓይናችን የወያኔን ጦር ስንመለከት አንደነዚያ ዓይነት አዋጊዎችና ባለሞያተኞች የሉትም። ለሽታ ፈልገህ አታገኝባቸዉም……….። << ….ወያኔን ከአዲሱ የዓለማችን ስርዓት ጋር አያይዘህ ነዉ ማየት ያለብህ። አዲሱ የ ዓለማችን ስርዓት ዓለምን በ ኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ አንቆ ሊይዝህ የሚፈልግ ነዉ።ከዚም ከዚህም እየዘረፈ ወደ ሌላ መጓዝ። ያለንበት ዓለም በዚህ እየተመራ ስላለ በዓለም ዉስጥ ያሉት የብዙሃን የመገናኛ ጋዜጦች ሁሉ ተቆጣጥሮ ሁሉም ጋዜጦች በአንድ ርዕስ አንዲዘጋጁ ያደረግጋል።ከሚተነተነዉ ርዕስም አብሮ ትንሽ ወታደራዊ ነክ ጉራ ይጨመርበታል።
ከሚተነተነዉ የስነ ዓእምሮ ትነተና ዉስጥ የወያኔ ሃይል ትነሽ ነጥብ ነች።የወያኔ ጦርነት የስነ-ዓእምሮ ጦርነት ነዉ። ሌላዉ ነገር ዉስጡ ባዶ ነዉ። ያ የስነ ዓእመሮ ጦርነት ነጥለህ ብትለየዉ የወያኔ አቅም ኢሚንት ነዉ። ምን ዉግያ አለዉ?የለዉም! ወታደራዊ ስልቱ ስፍር ቁጥር የሌለዉ የሰዉ ሃይል ሰብሰቦ መዋጋት ብቻ ነዉ። ትንሽ ቦታ ለማግኘት በብዙ ሺህ የሚቆጠር የሰው ሕይወት ያስፈጃል። ኤርትራ 19,000 ሺህ ሰዉ ሲሰዋባት ዉያኔ 170,000 ሺህ ሰዉ ነዉ ያስፈጀዉ። የከፈለዉ ሕይወት በጣም ብዙ ነዉ። ታሞ በህመም የሞተ ሳይጨምር ማለት ነዉ። የደርግ ሰራዊት እኮ ልክ አንደፊተኛዉ ሰራዊት በስለቱም በጥንካሬዉም እያደገ የመጣ ሰራዊት ነበር። የወያኔ ሰራዊት ጥርቃሞ ነዉ። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሞ ያቆመዉ ነዉ።
ከወያኔ በፊት የነበረዉ ጦር በፍጹም ታወዳዳሪ አይገኝላቸዉም። ወያኔ አቅሙን መጥኖ ስለመያዉቅ፡ አቅምም ስለሌለዉ፤ የኢኮኖሚ ረዳት የሌላትን ኤርትራን በኢኮኖኖሚ እናንቃታልን እያለ ነዉ የስነ እምሮ ዉግያዉን እየነዛ ያለዉ።
<<……..የዓእምሮዉ ጦርነቱን አብረዉ የሚያጫፈሩት አንዳንድ ኤርትራዊያን አቅጥረኞቹን ድሮ የተረሱ ፤የበሰበሱ ፤የሞቱ በድን ድርጅቶችን አፈላልጎ እያስባሰባቸዉ ነዉ። አነዘሂም በነገርኩህ በዛዉ በስነ ዓእምሮዊ ዉግያዉ ዉስጥ እንደ ፓኬጅ ጨምራቸዉና ገምግመዉ። ግልጽ ነዉ! ዉግያዉ ከዚያ አያልፍም። ወያኔ ሊያደረጋት የሚችላት አቅሙ ያች ብቻ ነች። በዚህ መለኪያ ስትመዝነዉ የወያኔ አቅም ለመገመት የሚያሳስት ነገር አይደለም።>>
የወያኔ ሰራዊት ገፍቶ ወደ ዉስጥ ኤርትራ በመዝለቁ እንደ ዋታደራዊ የበላይነት ተደርጎ ይታያል።የሄንን እንዴት ትመለከተዋለህ?
<< ወያኔ በወታደራዊ ሃይል የበላይነት ለማግኘት ሦስት ጊዜ=ሞከረ።መጀመሪያ፤ሁለተኛ፤…..ሦስተኛ ጊዜ የባሰ መጣበት። ከዚያ ወዲያ መቀጠል ስላልቻለ አቅም ስላልነበረዉ ወደ አልጀሪስ ለመሄድ ተገደደ። እዛም በሽንፈት ተከናንቦ የውርደት ዉርደቱን አገኘ።በሽንፈት ላይ ሽንፈት ኪሳራ ደረሰበት። ያካሄደዉ ዉግያ የስነ ዓእምሮ ዉግያ ነበር፡ በሺዎቹ የሰዉ ሕይወት ታስፈጅና በምትኩ፤ ትንሽ ቦታ ይዘህ ከየአቅጣጫዉ ጋዜጠኞችን ሰብስበህ “ኑ እዩልኝ፤ዘግቡልኝ” ይላል። የኛ ጦር በ ኤርትራ ምድር በየአቅጣጫዉ በስፋት ስለዘረጋነዉ፤ ወያኔ በሺዎቹ የሰዉ ሃይል ሰባስቦ በአንድ አቅጣጫ መጣ። ያ ዕድል ነበር ለወያነ የሰጠነዉ። እኛ በአቅማችን እንተማመናለን።ይሄ የሚያስጨንቀን አይደለም።የዉግያ ሙያ የሚያዉቅ ያዉቀዋል። ቀስ እያልን እንደምንጠርገዉ ያዉቅ ነበር። ለዚያም ነበር ያቆመዉ። አስኪ እንደዉ በእወነቱ ወያነ ከጸሮና ዉግያ ወዲያ ዉግያ መቀጠልና ማሰብ ነበረበት? ያ የታየዉ የሬሳ ክምር፤የዉትድርና ብቃት ምለክት አይደለም። በዓለም ጋዜጦች የተዘረጋዉ በቲቪ የታየዉ የሬሳ ክምር እኮ ሙሉዉን አልታየም። በዓይን ስታየዉ እኮ የክምሩ ብዛት በእዉነቱ “በፍሊት” መርዝ የተፈጁ ነበር የሚመስሉት። በፍሊት የተገደሉም እንደዚያ ዓይነት የሰዉ ሬሳ “ክምር፤ በክምር ላይ ተደራርቦ” ማየት ያስቸግራል። 170.000 ሰራዊት አስፈጅቶ አንዴት ድል በድል ሆንን ይላል? አቅም ኖሮት ወያኔ ቢችል ኖሮ ነበር 10 ጊዜ ወደ ፍርድ ቤት እየሄደ ዉሸትና መለማመጥ የመረጠዉ? ያ ሊያደርገዉ የሚችለዉ አቅሙ ያኔ አብቅቷል። ጊዜዉ አልቋል። አሁን የቀረዉ ፕሮፖጋንዳ የስነ ዓእምሮ ፤ጉራና መዋሸት ብቻ ነዉ።
ወያነ ደካማ መሆኑን የምታዉቀዉ ባደረጋቸዉ ሥስት ሙከራዎች ላይ ነዉ። የወያኔ የድሮ ተዋጊዎች አብዛኛዎቹ በዉግያዉ ተፈጅተዋል። ትግራይ ዉስጥ የመወያያ ርዕስ ሆኖ የሚነገረዉም ይህነኑ ነዉ። ድል አመጣሁ እያለ ወያነ የሚለፍፈዉ፤-ድሉ ከየት መጣ ቢባል- የስነ ዓእምሮ የፖለቲካ ወግያና የዲፕሎማሲ ዉግያዉ ነዉ። ያነን የስነ እምሮዉ ዉግያዉ ብትለየዉ ወታደራዊ አቅሙ 20% አይበልጥም። …ወያነ ኤርትራን ቢቆጣጠር ነብሰጡሮች ቁጥቋጦ ስር ነበር የሚወለዱት። ተመልከት ለአማራ ህዝብ እያደረጉት ያሉትን ግፍ። መልከመልካም ሚስቶቻቸዉን እየነጠቁ ያማግጧቸዋል። ልጆቻቸዉም አንደዚሁ። ባኦጋዴን፤ በሶማሊ እየፈጸመ ያለዉን ድርጊት በአልጀዚራ በቲቪ ያየነዉ ነው።>>
ወያነ የያዛቸዉን ሉአላዊ መሬታችን አልሰጥም ብሏል በዚህ የምትለዉ ነገር ካለ አስተያየትህ?
<<ወያነ ከግዛታችን ካስነሳልን በጀ! ለሱም ይበጀዋል። ካላነሳም ማስነሳቱን የሚከብድ አይደለም።የድምበር ክርክር ጉዳይ ያበቃለት የሞተ ጉዳይ ነዉ። ኢትዮጵያን ስንመለከት አርግዛለች።ምን እንደምትወልድ ግን ሕዝቡ እየተጠባበቀ ነዉ። በእወነቱ ኢትዮጵያ ማርገዝ በተገባት ነበር? አያስፈልጋትም።ሕዝቡ ከወያኔ ማነቆ ተገላግሎ ወደ ሌላ ሽግግር እያመራ መሆኑን እያታዘብን ነዉ። ይህ ከድምበር ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን ሌላ ጉዳይ ነዉ። በኛ በኩል ፤የድምበር ጉዳይ አልቆለታል። የተባበሩት መንግሥታት ከዚህ ተባሯል። የቀረ ነገር ካለ፤ “ተመድ” ስሙን አንዴት ያስመልስ/ያ’ሳድስ ነዉ። ስሙን በእንዴት መልክ ማሳመር እንዳለበት የራሱ የግሉ ጉዳይ ነዉ። ለራሱ ችግር ሲል። የ ኤርትራ ጉዳይ አንደሆነ ያለቀለት ነዉ። የኛ የተሰጠዉ መሬት በፈለግንበት ሰዓት መልስን መዉሰዳችን የማይቀር ነዉ። ዓለምም ብትሆን ወዳ ሳትሆን በግዷ የኛዉን ትቀበላለች። ኤርትራንም እኮ ወዶ የሰጠን ሃይል የለም። ተመድ እኮ በ 50 ዎቹ ወደ ኤርትራ መጥቶ ነገር አበላሽቶ ሄደ። ነጻ ስናወጣት ተመልሶ መጣ። አሁንም መሬታችን ካስመለስን በሗላ፤ ያ ሲሆን- ተመልሶ እንደገና ይመጣል። ይሄ እኮ ነዉ ተመድ ማለት። ሌላ ተመድ የለም። የማናዉቀዉ ሌላ ተመድ የለም። ሄልኮፕተራችሁ ከዚህ አስነሱ፤ ልቀቁ ብለን ስናስነሳቸዉ አዉቀዉታል፡ ያኔ ያለቀ መሆኑን ያቃሉ።>>
…….ኤርትራ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ህጋዊም ሆነ ወታደራዊ መብት አላት።ተመድ ኖረ አልኖረ፤ተመድ ሄደ አልሄደ ጦርነት ሊያስቆም አይችልም።ለዚህ ነዉ ኤርትራ ዉስጥ ሲነጋ በነሱ ምሽት ሆኖ ጨለማዉ ገና መያያዝ የጀመሩት። ገና አልነጋላቸዉም። ኢትዮጵያ ሰላም አንድታገኝ ብልን ድሃ ስለሆነች በዉስጣዊ ዉጥረት ስለተወጠረች ሰላም እንድታገኝ ብለን፤ ለኛም ሸክሙ አንዲቀለን፤ ሸክማቸዉ የኛ እንዳይሆን፤ብለን እጃችን አስገብተናል።ኤርትራ አንደ መዓከላዊ ስበት ሆና መታየትዋ የማይቀር ነዉ።
……እሳቱ እየነደደ ነዉ።እኛ ከእሳቱ አጠገብ ነን፡ ያለነዉ።አሳቱ ነዶ ወደ አመድ ለመለወጥ ሊቀረዉ በቁጥር ስንት ያክል የማገዶ እንጨቶች እንደቀሩ የሚያዉቀዉ ከእሳቱ አጠገብ ላይ ያለዉ ሰዉ ነዉ የሚያዉቀዉ።ከእሳቱ አጠገቡ ላይ ያለነዉ ደግሞ እኛ ነን።……>>
በማለት “ተዓጠቕ”/ታጠቅ ከተባለዉ ወታደራዊ መጽሄት የሰጠዉ ቃለ መጠይቅ አንኳር አንኳር ነጥቦች እነዚህ ነበሩ።.
ኢትዮጵያ ለዘላም ትኑር!!!!-
1 comment:
I know it takes a lot of time and commitment to translate and present the information to our brothers and sisters, Ethiopians. Thank you and continue the great job that you are doing. It is obvious that Shaebia and Woyane are the enemies of Ethiopia. For not the hope of Ethiopia’s enemies to success, we Ethiopians should unite and fight for our survival before it is too late.
Long lives united Ethiopia.
Post a Comment