ድንቁርና የተባለ የአብይ አሕመድ
ሸቀጥ ዲሲ ውስጥ ለገበያ ቀርቦ ሲታይ ዋለ
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
የድንቁርና ሱሰኛነት
Saturday, October
10, 2020
ድንቁርናን ለመሸጥ የድንቁርና ጣዕም ያጣጣሙ ደንቆሮ ቸርቻሪዎች መፈለግ የግድ ነው። እነዚህ
የድንቁርና ሸመተኞችና ቸርቻሪዎች አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ዛሬ ቅዳሜ October 10, 2020 የአብይ አሕመድን የድንቁርናን ጣዕም በጭፈራ ሲገልጹ
በቪዲዮ አይተናቸዋል።
ትዕይንቱ ያስታወሰኝ ወደ ግንቦት
7 ወደ ሗላ ከጥቂት አመታት በፊት ወደ እነ ብርሃኑ ነጋ እና ንአምን ዘለቀ የሻዕቢያ ባንዴራ እያውለበለቡ ሲያስቁንና ሲያበሽቁን
የነበረውን አሳፋሪው የሻዕብያና የግንቦት 7 ጥምረት ሲያደርጉት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በትዝታ እንዳስታውስ አደረገኝ። እዚህ ሰልፍም
የተደገመው ያው ሻዕቢያ በማያገባው አገር ገብቶ ደምጽ ሲያስተጋባ ከውስጥ በጥምረት የተቀናጀ ሰልፍ እንደሆነ የሚያሳየው ባንዴራቸው
አብሮ ከኢትዮጵያ ባንዴራ ጎን እኩል ሲውለበለብ ማየት በአገሩ ውስጥ ያልፈቀደውን መብትና ትዕይነተ ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ጣልቃ
ገብቶ ሊፈተፍት የፈቀደው ማን ነው የሚል ትልቅ ጥያቄና ስጋት የሚጭር ነው።
ይህም በሕግ ዓይን deliberate disregard of the facts” እያዩ
እና እየሰሙ ሰምተው እንዳልሰሙና አይተው እንዳላዩ በሞራልም በሕግና በታሪክ ያስቀጣል (ሕግ ቢኖር)።
ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የችለማ ዘመን የኢትዮጵያውያኖች ጭፍጨፋ ርሃብና ስደት ከመጤፍ ባይቆጥሩትም፡ እዚህ አሜሪካ በቫይረስ በሸታ ደስታዋን በተነጠቀቺውና ስራ በታጣባት ምድር ዋሺንግተን እና አካባቢዋ እየኖሩ እንዲህ ያለ የጥጋብ ጭፈራ ማንጸባረቅ ካሁን በፊት እንዳየናቸው ሁሉ የነዚህም እንዲሁ የፍትሕ ትርጉም ፤ የአገር ትርጉም ከጠላት ባንዴራ ጋር አብሮ መጨፈር እጅግ ዘግናኝ መሆኑን ለደነቆሩ ሰዎች ለማስረዳት ከባድ ነው።
ዋና ተልዕኮአቸው ልክ እንደመሪያቸው
አብይ አሕመድና ልክ እንደ ተባባሪያቸው ሻዕቢያ “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ ፤ ራሳቸውን በጥልቅ የድንቁርና ባሕር ውስጥ እየዋኙ
፤ድሉዥን ውስጥ ገብተው’ የማይዳሰሰውን በመዳሰስ ላይ ናቸው። በሃዘን ድባብ በተወረረች አገር ኢትዮጵያ ላይ ጭፈራ የሚጨፍሩ እንዲህ
ያሉ ጨፋሪዎች ሲያዩ ወላጆቻችን ትግሬዎች “ጨርቁ ዝደርበየ ዕቡድ”
(ጨርቁን የጣለ ዕብድ) ይሉታል።
አብይን ለመክሰስ በር የተዘጋባትን “ፍትሕ” ፤ ድምጽዋን ለማፈን የተነሳው ዋሺንገተን የተበሰበው “የብዝሃነት ድንቁርና”
የሚነገረን ነገር ‘አገራችን ውስጥ ለ29 አመት የዘለቀ የወንጀለኞች
ሥርዓት ዛሬ ሥልጣኑን ላለመልቀቅና በወንጀል እንዳይጠየቅ የሚያደርጉት ጥረት ፤ በጉራጌው ፤ በጋሞውና በክርስትያኖች ህይወት ጥቃት
እንዲፈጽሙ ለማድረግ መሪያችን ነው የሚሉትን አበይ አሕመድ ድሮ በሕቡእ የጥፋት ሃይሎች አባል ሆኖ (በሁለት አለም ሰላይነቱ) ሲያደራጅና
ምስጢር ሲያቀብላቸው የነበሩትን ነብሰገዳዮች ጓዶቹ ከውጭ አገሮች ወደ አገር ውስጥ ያለ ምንም ውል እንዲገቡ በመፍቀድ፤ የሰለጠኑ የመንግሥት ወታደሮች ጠባቂ መድቦላቸው ዳግም ወንጀል እንዲፈጽሙ በማድረግ
በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች እንደ እንሰሳ ታርደው የዘርና የሃይማኖት ፍጅት እንዲከናወን ያደረገው ተጠያቂው መሪያቸውን ለመከላከል ነው።
የአባ ጂፋር አድናቂው “የበሻሻው
ንጉሥ አብይ አሕመድን” በመደገፍ በሻዕቢያ ባንዴራና ሁለት ዓይነት ይዘት ያላቸው የኢትዮጵያ ባንዴራ በያዙ ኢትዮጵያውያን እና በሻዕቢያ
ኤርትራኖች ጭፈራ እየጨፈሩ ከንቱ ዝላይ ቢደረግም ውሎ አድሮ አብይ አሕመድ ከወንጀል ተጠያቂነት ሊደብቁት ከቶ አይቻላቸውም። “በደንቁርና ሱሰኞች” እውነታዎች ችላ ቢባሉም መኖራቸው አያቆሙም!
አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian
Semay)
No comments:
Post a Comment