Saturday, July 13, 2019

በኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ የተመረጠው የሳምንቱ ታላቅ ሰው! እነሆ፤- ጌታቸው ረዳ July 13, 2019


በኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ የተመረጠው የሳምንቱ ታላቅ ሰው! እነሆ፤-
ጌታቸው ረዳ
July 13, 2019
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድማገኝ
እስካሁን ድረስ የአማራ አስተዳዳሪዎች የሚባሉት ሁሉ በአማራ ላይ ሲደርስ የነበረው ጥቃትና አሁንም እያደረሰ ያለው ጥቃት ተጠያቂው ማን እንደሆነ በግልጽ ላለመናገር ‘እያድበሰበሱ’ መቆየታቸው የምናውቀው ሃቅ ነው። ሰሞኑን በኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ የተመረጠው የሳምንቱ ታላቅ ሰው በዕድሜው ወጣት፤ ደፋር እና አስተዋይ የሆነው “የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድማገኝ” ተመርጣል።

በአማራ ሕዝብ ላይ ቢያንስ 40 አመታት እስካሁን ድረስም ተታታይ ጥቃት እያደረሰ ያለው ጠላት “ሰው በላ” በሚል የቅጥያ ስም በመስጠት ያ ሰው በላ ጸረ አማራ የፋሺሰቶች ድርጅት “ኦነግ” (ኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር) እንደሆነ “የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድማገኝ” ለአስራት ቴ/ቪ የዜና አመሰራጫ ይፋ አድርጓል።፡

 ከዚህ ድርጅት የሚሰነዘረው ጥቃት የአማራ ሕዝብ እራሱን ለመከላከል መደራጀት እንዳለበት ግልጽ መመሪያ ከመስጠቱ ሌላ፤ በሕዝቡ ውስጥ ተሰግስገው በአማራ ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት ኦነጋዊ ወንጀለኞች መንግሥት  አድኖ ለፍርድ ካላቀረባቸው “የሕዝቡ ጸብ” ካኦነጎች ጋር ሳይሆን በመንግሥት ላይ እንደሚሆን ግልጽ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። ለዚህም የሳምነቱ ታላቅ ሰው ሆኖ በኢትዮ ሰማይ ድረገጽ ተመርጧል።

“ዛራቱስትራ ተናገረ” በተባለው የጀርመናዊው ፈላስፋ “ፍሬዴሪክ ኒች” የፍልስፍና ድርሰቱ ላይ (አዲስ አበባ ሲታተም የነበረው ከአሌፍ መጽሄት አለፍ አለፍ ብየ በአማርኛ ትርጉሙ ያገኘሁትን ጥቅስ) ለምርጫየ ማሳረጊያ እዚህ ልጥቀስ። ይህ ቀልቤን የሳበው የሰሜን ሸዋ ዞን ደፋር ወጣት አስተዳዳሪ ከሌሎቹ ተለይቶ ፍርሓቱን እንዴት ሊሰብር እንደቻለ ሌሎቹ ግን እንደበሰበሰ ዕዋት እዛው ቅርንጫፍ ላይ በመሆን ለረጂም ጊዜ ከፍርሓት የተነሳ “ግንዱን የሙጥኝ” ብለው እየተወዛወዙ ‘ቅርንጫፉንም ሆነ ግንዱን’ ጠራርጎ የሚወስዳቸው ማዕበላዊ ነፋስ እየጠበቁ እንደሆነ በፈላስፋው ‘ንች’ ላሳያችሁ።

ዛራቱስትራ ተናገረ ከተባለው ድርስቱ ኒች እንዲህ ይላል፦
<<< “…ምድራችን ኣዳዲስ ሕግጋት በሚፈጥሩ ሰዎች ትሽከረከራለች ሕዝብ እና ዝና ግን በተዋናያን ዙርያ ይሽከረከራሉ። የዐለማችን ነገር እንዲያ ነው። አንዳንድ ሰዎች በጣም አርጅተው ይሞታሉ። ሌሎች ደግሞ በለጋ ዕድሜአቸው ይቀጠፋሉ። መሞት ካልቀረ በትክክለኛ ሰዓት መሞቱ ይሻላል። የኛ መመሪ በወቅቱ መሞት ነው። እርግጥ በትከክለኛው ወቅት ኖሮ የማያውቅ ሰው በትከክለኛው ወቅት ሊሞት አይችልም። እንዲህ ያለ ሰው ቀድሞ ነገር ባይወለድ ይሻለው ነበር። 

የራሱን ህይወት በራሱ እጅ የሚያጠፋት ሰው በድል አድራጊነት ይሞታል። እንዲህ ያለው ሰው ለህያዋኑም ቢሆን ተስፋ ነው። በፈቃደኝነት መሞት ሁላችንም ልንማረው ይገባል። አንዳንድ ሰዎች ልባቸው ቀድሞ ያረጃል። ሌሎች ደግሞ መንፈሳቸው ያረጃል። በወጣትነታቸው  የሚሸመግሉ ሰዎች አሉ። ዘግይተው ወጣት የሚሆኑ ግን ለረዢም ጊዜ ወጣት እንደሆኑ ይቆያሉ።

አንዳንዱ ሰዎች ደግሞ መርዘኛ ትል ልባቸው ይበላዋል። እነዚህ ሰዎች መቼም ቢሆን የማያፈሩ፡ አዝመራ በሚያሸትበት (በእሸት) ወራት እንኳ የሚበሰብሱ ዕፅዋት ናቸው። ብዙዎቹ እዚያው ቅርንጫፋቸው ላይ በመሆን ለረጅም ጊዜ ይቆያሉ።ግንዱን የሙጥኝ የሚያሰኛቸው ፍርሀት ነው።  ሃያል ነፋስ መጥቶ ይህን ትልና በስባሽ ከዛፍ ላይ ባራገፈልኝ! ፈጣን ሞትን የሚሰብኩ መመህራን በመጡልኝ እንዴት በወደድሁ!..“>> ይላል ንች በድርሰቱ።

 አሁንም ይህ የሰሜን ወጣት አስተዳዳሪ ፍርሀት የሚባል በመምታት ትክክለኛ ጠላት ማን መሆኑን እና ይህ ጠላት መንግሥት እያደነ ለሕግ ካላቀረበው፤ ሕዝቡ በመንግሥት ላይ አትኩሮቱ እንደሚያደርግ ታላቅ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ እጅግ ቀልቤን የሳበ የሳምነቱ ታላቅ ሰው ብየዋለሁ። የወጣቱ አስተዳዳሪ ንግግር ለማድመጥ እነሆ https://www.facebook.com/kediamharawit.wollo/videos/160732701640176/
አመሰግናለሁ’
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)