Sunday, February 22, 2009

ክፍል-2- በሰማእት እና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር (ካነበብናቸዉ) ጌታቸዉ ረዳ
ከላይ የሚታዩት ፎቶግራፍ የወያኔ ሰለባ የሆኑት በእሳትና በፈላ ዉሃ እየተቃጠሉ በድብደባ አካላቸዉ የተጎዳ፤ ከሞት ጉድጓድ ወጥተዉ እሳቸዉ በሚያመልኩት በቅዱስ ሚካኤል እና በእግዚአብሔር ተአምር ሰሪነት ከሞት አምልጠዉ ታሪካቸዉን ለቀሪዉ ትዉልድ እያስተላለፉልን ያሉት የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ክቡር ፊታዉራሪ ገዛኢ ረዳ ናቸዉ
ለዛሬ ከመጻሕፍት ዓለም የመረጥኩላችሁ
ታሪክ አጉዳፊ የአልባኒያ ደብተራ -
የህወሓት መሪዎችና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት”
ደራሲዉ ታጋይ ገሰሰ እንግዳ፡
ከላይ የተመለከተዉ የመጽሃፍ ርዕስ ሰሞኑን እና በዛሬዉ የካቲት 11 /2000 ዓ.ም ወያኔ እና ካድሬዎቹ በሰማእት እና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር ለሚጫወቱት ሃፍረተቢስ የወያኔ ፋሽስቶች-ተስማሚ ትችት ሆኖ ስላገኘሁት፤ አብራችሁኝ እንድታነቡት እነሆ፦ እነ መለስ ዜናዊ አዲስ አበባ ገብተዉ በምኒሊክ ቤተመንግስት ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በሗላ በራሱ ታጋዮች ላይ ሳይቀር የተጫወተዉ የፖለቲካ ቁማር እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ሁሉ ከዉስጡ ከሕሊናዉ የሚረዳዉ ጉዳይ ነዉ (እነሱም ከዉስጣቸዉ የሚክዱት አይደለም የሚል ግምት አለኝ)። ዛሬ በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር እየተጫወቱ ስለ የካቲት ምንነት ሊያበስሩን “የካቲት፤የካቲት” በማለት ሲዋሹን “ በአንጻሩ ግን ትግሉ ያደከማችሁ፤ ወይንም የቤተሰብ ናፍቆት የበረታባችሁ ታጋዮች ካላችሁ እጃችሁን በማዉጣት ወደ ቤተሰቦቻችን/ወደ ከተማ ለመሄድ እንመለሳለን ካላችሁ በሰላም ትሸኛላችሁ ተብለዉ በቅን ልቦና የተነገራቸዉ መስሏቸዉ እጃቸዉን በማዉጣት ፤ በስምምነት ከትግሉ ለመዉጣት የተፈቀደላቸዉ ወጣት ታጋዮች” በተሓሕት ባለስልጣኖች ዉሳኔ እንደተረሸኑ አብዛኞቻችሁ ታሪኩን የሰማችሁት/ በወቅቱ ታጋይ የነበራችሁ ታሪኩን ያወቃችሁት እና ሌሎቻችሁም ምስጢሩን ካጋለጡ ታጋዮች ወይንም ከተረሸኑት ቤተሰብና ጋደኞቻቸዉ የተነገራችሁ ይህ አሳዛኝ ፋሽስቶች ተግባር እስካሁን ድረስ የንጹሃን ደም እዮኸ እንዳለ ነዉ። “ቁንጮ ዘፋኞቻቸዉ” እና “ገጣሚዎቻቸዉ” የሚዘፍኑት እና የሚጫጭሩት የየካቲት ግጥሞቻቸዉ፤ ያለ ፍትህ ለተረሸኑት ንጹሃን ታጋይ ጓዶቻቸዉ ቢጮሁላቸዉ ምንኛ ባስመሰገናቸዉ ነበር። ሆኖም፤ እነሱም በግድያዉ በስለላዉ፤ነገር ባማሳበር፤ በመዋሸት እና በማስወንጀል ስራ ተሰማርተዉ የግፍ ፈጻሚዎች አካል አጎብዳጆች ኖሮዉ ካልሆኑ በስተቀር በያመቱ በሚዘፍኑት አና በምያከብሩት በ አላቸዉ ያለፍትህ በወያኔ አለቆቻቸዉ የተገደሉ የትግራይ የህወሓት ታጋዮች መዘከር እና ስለ እነሱ ቆመዉ መጮህ በተገባ ነበር። አለመታደል ሆኖ እነሱም ከባለ ጊዜዎቹ እየዋሹ፤ሓቅ እንድትድበሰበስ የበኩላቸዉን ግፉን ሲያራዝሙ ታዝበናል። በዚህ አጋጣሚ በየሙዚቃ ድግሶቻቸዉ የተገኛችሁ ወይንም ምትገኙ ሰዎች በከንቱ ሕይወታቸዉ ያለፈዉ፤ የጠፉ፤የተሰወሩ ታጋዮች የድርጅቱ ተጠያቂነት የት አል? ብላችሁ ለፍትሕ እንደምትቆሙ እየተማመንኩ ሓቅነታቸዉን በእግዚአብሔር እና በሞቱት ተጋይ ጓዶቻችሁ እና ዘመዶቻችሁ መንፈስ ፊት ሓላፊነቱን እንዲሸከሙ ጠይቁ።ጓዶቻችሁ ሙታን ቢሆኑም መንፈሳቸዉ በዚህ ዓለም እየዞረ ፍትሕን በመፈለግ ህዋ ላይ ነዉና ሙታኖቹ መንፈሳቸዉ በሰላም እንዲያርፍ አብረን ፍትሕ አናፈላልግልቸዉ። እንደምታዉቁት ለሙታኖች እና በሕይወት ያሉት ምንም አላተረፉ የአፍ ሙገሳ ሲደረግላቸዉ የካቲት የካቲት በማለት አስክንደኖቁር በያመቱ የሚዋሹት የወያኔ መሪዎች ራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉ ወደ ዉጭ አገር በመላክ የዘመኑ ዕዉቀት እንዲገበዩ ሲያደርጉ፤ ከገበሬዉ ጉያ ነጥቀዉ ለሥልጣናቸዉ ማቀጣጠያ ማገዶ እንዳደረጉዋቸዉ የትግራይ ገበሬ የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ። -ለዚህም ነበር “የህወሓት መሪዎች ሲወዱህ በግ አርደዉ ያበሉሃል ሲጠሉህ ደግሞ እንደ በግ አርደዉ ያበሉሃል!” በማለት የወያኔ ነብሰበላነት የገለጸዉ። ለማንኛዉም ወደ መጽሃፉ አንግባ። ሰዉ እንደ ሎሚ ጨምቀዉ መጣል (ሰዉን በሆዱ በሬን በጭዱ መቅጣት)
ከላይ የተጠቀሰዉ የወያኔ ዓይነተኛ መለያ ባህሪ ነዉ። የአንድን መሪ ወይንም መንግሥት መመዘኛ በወገኑ ላይ ያለዉ አክብሮትና በሃገሩ ላይ ያለዉ ፍቅር ነዉ።የህወሓት መሪዎች ግን ርህራሄ የሌላቸዉ የጫካ አራዊቶች ናቸዉ። የሰዉ ልጅ ህይወትና ደም እንደመሳሪያ መጠቀምና ወደ ስልጣን መሸጋገሪያ ማድረግ የለመዱ ናቸዉ። ሰዉ ሲሰቃይ ሲንከራተት፤ ሲቸገር የሞትና ሲታሰር ሲያዩ እንደ “ሳዲስቶች” የአእምሮ እርካታ የሚያገኙ እሰየዉ የሚሉ በንጹሃን ደም የሰከሩ የቀን ጅቦች ናቸዉ። በአደባባይ በገሃድ ሲዋሹ ሲያምታቱ ሲሰርቁና ሲያታግሉ ሕዝቡ ይታዘበናል አይሉም። ሲዋሹ ትላንት ምን እያልን ነበር? ዛሬስ ምን እያልን ነዉ? ነገስ ሰዉ ምን ይለናል አይሉም። በሕዝብ ፊት ሲያጭበረብሩ እንደማንኛዉም ሰዉ ነገ የምታልፍ ሕይወት ያላቸዉም አይመስላቸዉም። መሪዎቹ ስነምግባር የሌላቸዉ በሕግ በባህል በታሪክና በሃይማኖት የማይገዙ ጉግ ምንጉጎች ናቸዉ። በትግራይ ህዝብ በተለይም በገበሬዉ አካባቢ ከሚጠሉበት ምክንያት አንዱ መጥፎ ባህሪያቸዉ በሃገር ሉአላዊነት ላይ የፈጸሙትን ክሕደት ብቻ አይደለም። የትግራይን ሕዝብ በተለይም የዋሁ ገበሬዉ ለስልጣናቸዉ መቆናጠጫ መሳለልና መረማመጃ አድርገዉ ደሙንና ጉልበቱን ከተጠቀሙበት በሗላ እንደ ሎሚ ጨምቀዉ መጣላቸዉን ነዉ። ለምሳሌ የህወሓት ታጋዮች 90 ከመቶ ከአርሶ አደሩ የመጡ ገበሬዎች ናቸዉ። እነዚህ ታጋዮች በግድም በዉድም ለህወሓት መሪዎች ብቻ ሳይሆን ሻዕቢያንም ለስልጣን ያበቁ ናቸዉ። እነ መለስ ዜናዊ አዲስ አባባ ገብተዉ በምኒሊክ ቤተመንግሥት ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በሗላ ግን ጥቂቶች እዚህ ግባ የማይባል ማቋቋሚያና መካካሻ ተሰጥቶአቸዉ ሲሰናበቱ፤ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች ያላንዳች መካካሻ ሳይወዱ በግድ ተባረዋል። ተቃዉሞ ያሳዩትም በተለያየ ቦታ በእስር ቤት ታጉረዉ ይገኛሉ። ብዙዎቹ ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተሰደዋል። የቀሩትም ባዶ እጃቸዉ ወደ ነበሩበት ወደ ግብርና ስራቸዉ ተመልሰዋል። እንደሚታወቀዉ በትግሉ ወላፈን የተለበለበዉ “ፈንጅ ርገጥ” አየተባለ የጠላት ምሽግ የሰበረዉ በየጉራንጉሩ የአሞራ ሲሳይ ሆኖ የቀረዉ በቦምብ ናዳ ቤት ንብረቱ የተቃጠለበት የመከራና የጨለማ ኑሮ ያሳለፈዉ ገበሬዉንና የገበሬዉ ልጅ ነዉ። ከድሉ በሗላ ግን በትረስልጣን ጨብጦ መኪና እንደ ሸሚዝ እየቀ ያየረ የሚዉለዉ ልጆቹ ወደ ፈረንጅ ሀገር እየላከ የሚያስተምረዉ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ ሃገርና መሬት እየቸረቸረ የሚዉለዉ በሰማእታትና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ እንደ እስስት ቀለሙ እየቀያየረ ሕዝብን የሚያጭበረብረዉ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ የሚናገረዉ ሃገርና ወገን ሸያጩ የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ሆዳም ካድሬና አጨብጫቢዉ ፓርላማ ናቸዉ። ይህን የተረዳ የትግራይ አርሶ አደር ነበር ሁኔታዉን በጥቅሉ እንዲህ ሲል “የህወሃት መሪዎች ሲፈልጉህ በግ አርደዉ ይበሉሃል! ሲጠሉህ ደግሞ እንደ በግ አርደዉ ይበሉሃል!” በማለት ቁጭቱን የገለጸዉ። ይህ ማለት የህወሓት መሪዎች በትረ-ስልጣናቸዉ እስከ ሚያደላድሉ ድረስ በስልት በመያዝ እንደመሳልል ወይም እንደኮረቻ መቆናጠጫ አድርገዉ ይጠቀሙቡሃል ከዚያም በሗላ ሲጠሉህ “ሰብብ -አስባብ” እየፈለጉ እንደ ቆሻሻ ዕቃ ይጥሉሃል ማለት ነዉ። ይህ ዓይነት ድርጊትም በገበሬዎቹና በታጋዮቹ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። በተለያዩ የመንግሥት መስርያቤቶች ተቀጥረዉ በሚሰሩ ሲቭል ሰራተኞችም የሚደርሰዉ በደል ተመሳሳይ ነዉ። የህወሓት ኢሕአዴግ አመለካከት እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ተብለዉ በሚጠረጠሩ ሎሌዎች ዜጎች ላይ የደረሰ በደልም ጥቂት አይደለም።ዛሬ በ ኢትዮጵያ በተለይም በመንግሥት መሥርያቤቶች አካባቢ ለነገ ብሎ የሚያስብ የለም። ምክንያቱም ለነገ ብሎ የሚያስብ መንግሥትና መሪ ስለሌለ ነዉ። ይህን ሁሉ ጉድ የታዘበ አንድ የጎጃም ገበሬ ስለ ስርዓቱ ያለዉን አስተያያት ሲገልጽ ”የጅብ ገበሬ! ያህያ በሬ! የዝንጀሮ ጎልጓይ! የጦጣ ዘር አቀባይ! አንድም የላቸዉ ሁሉም አንብላ ፤እንብላ ባይ! በማለት ቁጭቱን እና ጥላቻዉን ይገልጻል። ዛሬ በኢትዮጵያ ዉስጥ አብዛኛዉ የመንግሥት ሠራተኞ የህወሓት መሪዎች ሃሳብ ፈልገዉ ዛሬ ነገ ሊያባሩረኝ ይችላሉ ብሎ የሚሰጋ ነዉ። ከዚሁ በመነሳትም ለራሱ በፈርሃትና በስጋት ላይ ያለ ሠራተኛ ስለመጪዉ የሃገር ዕድገትና ስለተተኪዉ ትዉልድ ማሰብና መተንበይ አይችልም። የሃገራችን የወደፊት ዕድል አስጊና በአደጋ ላይ ያለ ሁኔታ ነዉ የምንልበት ምክንያትም አንዱ ባህሪ ከግንባታዉ ይልቅ የማፍረስ ሁኔታዉ ሚዛኑ ስለሚያይል ነዉ።” (ታጋይ ገሠሠ እንግዳ ገጽ 170-173) በየአመቱ በየካቲት ወር በሕዝብ ልጆች ደም” የፖለቲካ ቁማር” እየተጫወቱበት ያሉት የወያኔ መሪዎች እና አዳማቂ ካድሬ ሎሌዎቻቸዉ የፌዝ ጊዜያቸዉ ሲያበቃ ፋሽስቶቹ የወያኔ ነብሰገዳዮች ወደዉ ሳይወዱ “አንድ ቀን” በሕግ ፊት ቀርበዉ በቤተሰቦቻችን እና በሕዝብ ላይ የቀለዱበትን የንጸሃን ደም መልስ ይሰጡበታል። “ዘይወግሕ መሲሉዋስ ኣብ ቡኹራ ታሓርእ”! ክወግሕ እዩ! http://www.ethiopiansemay.blogspot.com

ክፍል-2- በሰማእት እና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር (ካነበብናቸዉ) ጌታቸዉ ረዳ
ለዛሬ ከመጻሕፍት ዓለም የመረጥኩላችሁ “ታሪክ አጉዳፊ የአልባኒያ ደብተራ - የህወሓት መሪዎችና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት” ደራሲዉ ታጋይ ገሰሰ እንግዳ፡ ሰሞኑን እና በዛሬዉ የካቲት 11 /2000 ዓ.ም ወያኔ እና ካድሬዎቹ በሰማእት እና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር ለሚጫወቱት ሃፍረተቢስ የወያኔ ፋሽስቶች ተስማሚ ትችት ሆኖ ስላገኘሁት፤ አብራችሁኝ እንድታነቡት እነሆ፦ እነ መለስ ዜናዊ አዲስ አበባ ገብተዉ በምኒሊክ ቤተመንግስት ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በሗላ በራሱ ታጋዮች ላይ ሳይቀር የተጫወተዉ የፖለቲካ ቁማር እጅግ አሳዛኝ ነበር። ዛሬ በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር እየተጫወቱ ስለ የካቲት ምንነት ሊያበስሩን “የካቲት፤የካቲት” በማለት ሲዋሹን “ወደ ወላጆቻችን እንመለሳለን በማለት በስምምነት ከትግሉ ለመዉጣት የተፈቀደላቸዉ ወጣት ታጋዮች” በግድያ ኮሚቲ ተሰማርተዉ ከፍተኛ ወንጀል የፈጸሙ አስከ ዛሬ ድረስ በሕግ ያልተጠየቁ በንግድ ዓለም ተሰማርተዉ የናጠጡ ሲራራ ነጋዴዎች የሆኑት “ቁንጮ ዘፋኞቻቸዉ” እና “ገጣሚዎቻቸዉ” የሚዘፍኑት እና የሚጫጭሩት የየካቲት ግጥም ለማያዉቃቸዉ ሰዉ እዉነትም “ታጋዮች ሊመስሉ ይችሉ ይሆናል- ”ሃቁ ግን በነብስ ግድያ ከፍተኛ ሚና የነበራቸዉ “ደም የጠማቸዉ” ታጋዮች እንደነበሩ በቦታዉ የነበሩ የዓይን ምስክሮች እና ማስረጃዎች ሁሉ ማንነታቸዉ ይገልጻሉ። የካቲት የካቲት በማለት አስክንደኖቁር በያመቱ የሚዋሹት የወያኔ መሪዎች ራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉ ወደ ዉጭ አገር በመላክ የዘመኑ ዕዉቀት እንዲገበዩ ሲያደርጉ፤ ከገበሬዉ ጉያ ነጥቀዉ ለሥልጣናቸዉ ማቀጣጠያ ማገዶ እንዳደረጉዋቸዉ የትግራይ ገበሬ የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ። -ለዚህም ነበር “የህወሓት መሪዎች ሲወዱህ በግ አርደዉ ያበሉሃል ሲጠሉህ ደግሞ እንደ በግ አርደዉ ያበሉሃል!” በማለት የወያኔ ነብሰበላነት የገለጸዉ። ለማንኛዉም ወደ መጽሃፉ አንግባ። ሰዉ እንደ ሎሚ ጨምቀዉ መጣል (ሰዉን በሆዱ በሬን በጭዱ መቅጣት) ከላይ የተጠቀሰዉ የወያኔ ዓይነተኛ መለያ ባህሪ ነዉ። የአንድን መሪ ወይንም መንግሥት መመዘኛ በወገኑ ላይ ያለዉ አክብሮትና በሃገሩ ላይ ያለዉ ፍቅር ነዉ።የህወሓት መሪዎች ግን ርህራሄ የሌላቸዉ የጫካ አራዊቶች ናቸዉ። የሰዉ ልጅ ህይወትና ደም እንደመሳሪያ መጠቀምና ወደ ስልጣን መሸጋገሪያ ማድረግ የለመዱ ናቸዉ። ሰዉ ሲሰቃይ ሲንከራተት፤ ሲቸገር የሞትና ሲታሰር ሲያዩ እንደ “ሳዲስቶች” የአእምሮ እርካታ የሚያገኙ እሰየዉ የሚሉ በንጹሃን ደም የሰከሩ የቀን ጅቦች ናቸዉ። በአደባባይ በገሃድ ሲዋሹ ሲያምታቱ ሲሰርቁና ሲያታግሉ ሕዝቡ ይታዘበናል አይሉም። ሲዋሹ ትላንት ምን እያልን ነበር? ዛሬስ ምን እያልን ነዉ? ነገስ ሰዉ ምን ይለናል አይሉም። በሕዝብ ፊት ሲያጭበረብሩ እንደማንኛዉም ሰዉ ነገ የምታልፍ ሕይወት ያላቸዉም አይመስላቸዉም። መሪዎቹ ስነምግባር የሌላቸዉ በሕግ በባህል በታሪክና በሃይማኖት የማይገዙ ጉግ ምንጉጎች ናቸዉ። በትግራይ ህዝብ በተለይም በገበሬዉ አካባቢ ከሚጠሉበት ምክንያት አንዱ መጥፎ ባህሪያቸዉ በሃገር ሉአላዊነት ላይ የፈጸሙትን ክሕደት ብቻ አይደለም። የትግራይን ሕዝብ በተለይም የዋሁ ገበሬዉ ለስልጣናቸዉ መቆናጠጫ መሳለልና መረማመጃ አድርገዉ ደሙንና ጉልበቱን ከተጠቀሙበት በሗላ እንደ ሎሚ ጨምቀዉ መጣላቸዉን ነዉ። ለምሳሌ የህወሓት ታጋዮች 90 ከመቶ ከአርሶ አደሩ የመጡ ገበሬዎች ናቸዉ። እነዚህ ታጋዮች በግድም በዉድም ለህወሓት መሪዎች ብቻ ሳይሆን ሻዕቢያንም ለስልጣን ያበቁ ናቸዉ። እነ መለስ ዜናዊ አዲስ አባባ ገብተዉ በምኒሊክ ቤተመንግሥት ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በሗላ ግን ጥቂቶች እዚህ ግባ የማይባል ማቋቋሚያና መካካሻ ተሰጥቶአቸዉ ሲሰናበቱ፤ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች ያላንዳች መካካሻ ሳይወዱ በግድ ተባረዋል። ተቃዉሞ ያሳዩትም በተለያየ ቦታ በእስር ቤት ታጉረዉ ይገኛሉ። ብዙዎቹ ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተሰደዋል። የቀሩትም ባዶ እጃቸዉ ወደ ነበሩበት ወደ ግብርና ስራቸዉ ተመልሰዋል። እንደሚታወቀዉ በትግሉ ወላፈን የተለበለበዉ “ፈንጅ ርገጥ” አየተባለ የጠላት ምሽግ የሰበረዉ በየጉራንጉሩ የአሞራ ሲሳይ ሆኖ የቀረዉ በቦምብ ናዳ ቤት ንብረቱ የተቃጠለበት የመከራና የጨለማ ኑሮ ያሳለፈዉ ገበሬዉንና የገበሬዉ ልጅ ነዉ። ከድሉ በሗላ ግን በትረስልጣን ጨብጦ መኪና እንደ ሸሚዝ እየቀ ያየረ የሚዉለዉ ልጆቹ ወደ ፈረንጅ ሀገር እየላከ የሚያስተምረዉ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ ሃገርና መሬት እየቸረቸረ የሚዉለዉ በሰማእታትና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ እንደ እስስት ቀለሙ እየቀያየረ ሕዝብን የሚያጭበረብረዉ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ የሚናገረዉ ሃገርና ወገን ሸያጩ የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ሆዳም ካድሬና አጨብጫቢዉ ፓርላማ ናቸዉ። ይህን የተረዳ የትግራይ አርሶ አደር ነበር ሁኔታዉን በጥቅሉ እንዲህ ሲል “የህወሃት መሪዎች ሲፈልጉህ በግ አርደዉ ይበሉሃል! ሲጠሉህ ደግሞ እንደ በግ አርደዉ ይበሉሃል!” በማለት ቁጭቱን የገለጸዉ። ይህ ማለት የህወሓት መሪዎች በትረ-ስልጣናቸዉ እስከ ሚያደላድሉ ድረስ በስልት በመያዝ እንደመሳልል ወይም እንደኮረቻ መቆናጠጫ አድርገዉ ይጠቀሙቡሃል ከዚያም በሗላ ሲጠሉህ “ሰብብ -አስባብ” እየፈለጉ እንደ ቆሻሻ ዕቃ ይጥሉሃል ማለት ነዉ። ይህ ዓይነት ድርጊትም በገበሬዎቹና በታጋዮቹ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። በተለያዩ የመንግሥት መስርያቤቶች ተቀጥረዉ በሚሰሩ ሲቭል ሰራተኞችም የሚደርሰዉ በደል ተመሳሳይ ነዉ። የህወሓት ኢሕአዴግ አመለካከት እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ተብለዉ በሚጠረጠሩ ሎሌዎች ዜጎች ላይ የደረሰ በደልም ጥቂት አይደለም።ዛሬ በ ኢትዮጵያ በተለይም በመንግሥት መሥርያቤቶች አካባቢ ለነገ ብሎ የሚያስብ የለም። ምክንያቱም ለነገ ብሎ የሚያስብ መንግሥትና መሪ ስለሌለ ነዉ። ይህን ሁሉ ጉድ የታዘበ አንድ የጎጃም ገበሬ ስለ ስርዓቱ ያለዉን አስተያያት ሲገልጽ ”የጅብ ገበሬ! ያህያ በሬ! የዝንጀሮ ጎልጓይ! የጦጣ ዘር አቀባይ! አንድም የላቸዉ ሁሉም አንብላ ፤እንብላ ባይ! በማለት ቁጭቱን እና ጥላቻዉን ይገልጻል። ዛሬ በኢትዮጵያ ዉስጥ አብዛኛዉ የመንግሥት ሠራተኞ የህወሓት መሪዎች ሃሳብ ፈልገዉ ዛሬ ነገ ሊያባሩረኝ ይችላሉ ብሎ የሚሰጋ ነዉ። ከዚሁ በመነሳትም ለራሱ በፈርሃትና በስጋት ላይ ያለ ሠራተኛ ስለመጪዉ የሃገር ዕድገትና ስለተተኪዉ ትዉልድ ማሰብና መተንበይ አይችልም። የሃገራችን የወደፊት ዕድል አስጊና በአደጋ ላይ ያለ ሁኔታ ነዉ የምንልበት ምክንያትም አንዱ ባህሪ ከግንባታዉ ይልቅ የማፍረስ ሁኔታዉ ሚዛኑ ስለሚያይል ነዉ።” (ታጋይ ገሠሠ እንግዳ ገጽ 170-173) በየአመቱ በየካቲት ወር በሕዝብ ልጆች ደም” የፖለቲካ ቁማር” እየተጫወቱበት ያሉት የወያኔ መሪዎች እና አዳማቂ ካድሬ ሎሌዎቻቸዉ የፌዝ ጊዜያቸዉ ሲያበቃ ፋሽስቶቹ የወያኔ ነብሰገዳዮች ወደዉ ሳይወዱ “አንድ ቀን” በሕግ ፊት ቀርበዉ በቤተሰቦቻችን እና በሕዝብ ላይ የቀለዱበትን የንጸሃን ደም መልስ ይሰጡበታል። “ዘይወግሕ መሲሉዋስ ኣብ ቡኹራ ታሓርእ”! ክወግሕ እዩ! http://www.ethiopiansemay.blogspot.com

Friday, February 20, 2009

በሰማእታትና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር (ካነበብኳቸዉ ) ክፍል 1 ከጌታቸዉ ረዳ
በቅርቡ ያስነበብኳችሁ የወያኔ ሰለባ የሆኑት ፊታዉራሪ ገዛኢ ረዳ እና የቤተሰባችን አባል የሆኑት በወያኔ ድብደባ እና በእሳት ተቃጥለዉ ጉልበታቸዉ በመድከሙ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸዉ በእነ ሌ/ል ጀኔራል አበበ ተክለሃይማኖት (“ዑስማን” በመባል በሜዳ ስሙ ሚጠራ ፤ ወያኔ ስልጣን ከያዘ በሗላም ያለ ምንም ልምድ “የአየር ሃይል አዛዥ” አድርጎ ከሾመዉ በሗላ “ጆቤ” በመባል የሚጠራዉ የወያኔ ታጋይ ባሁኑ ጊዜ ያዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ሆኖ በደም የጨቀየዉ እጁ “ጠመኔ” ይዞ ሕግን በማስተማር ላይ ያለዉ ፤ለወደፊቱ በሕግ የሚፈለግ ወንጀለኛ እና አብሮት በግድያዉ እና እስረኞችን በማሰቃየት የሚታወቀዉ በሜዳ ስሙ “አዉዓሎም ወልዱ” ትከክልኛ ስሙ “ትኩእ ወልዱ” (የመለስ ታማኝ “የዓባይ ወልዱ/የሜዳ ስሙ “ዓባይ ዴራ” ታላቅ ወንድም የሆነዉ ወያኔ ኤርትራን ሲያስገነጥል “የኤርትራ አምባሳደር” በመሆን ተሹሞ በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያዉያኖች በሻዕብያ ግፍ ደረሰብን ብለዉ ሲጮሁ የአባቱ አገር የሆነችዉን “ኤርትራ” እንዳትወቀስበት በማዳላት ተስፋ ኣስቆራጭ መልስ ይሰጣቸዉ የነበረዉ ‘ዘረኛ እና ደሞቶራዉ” ግለሰብ ፤ ከወያኔ ተገንጥሎ… በቅርቡ ደግሞ “ዓረና” በመባል ሚታወቀዉ ያዉ የወንጀለኞች ሰብስብ “አረጋሽ አዳነን ጨምሮ” (ስለ አረጋሽ ካሁን በፊት በ7 ጥይት ተኩሰዉ ጫካ ዉስጥ ጣሉኝ ብሎ ወያኔን ያጋለጡ “ድያቆን ብርሃነ ገ/ሕይወትን በተያያዘ ጉዳይ ያቀረብኩትበን ሳትዘነጉ) የስበሓት ነጋን ምኞት እና የወያኔ ማኒፌስቶን በተግባር ለማዋል አንቀጽ39ን ቀዳሚ ፖሊሲዉ በማድረግ ከመሰረቱት ከእነ ገብሩ አስራት ጋር በመሆን ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን በአንዳንድ ግራ በተጋቡ እና ተስፋ በቆረጡ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አይዟችሁ ባይነት ሽር ጉድ በማለት ስለዲሞክራሲ እና ስለ የትግራይ ሕዝብ መብት እና መጨቆን የበላይነት ሲሰብክ የሚደመጠዉ ግለሰብ ምክንያት ቤተሰቦቻችን በእነዚህ ግለሰቦች በእሳት እየተጠበሱ ለሞት አና ለአካለ ጎዶሎነት መድረሳቸዉ ያቀረብኩት ማሕደር ይታወሳል። ሆኖም ካለ “ዘሓበሻ” የተባለዉ የድረገጽ ጋዜጣ (ድሮ የመዲና አዘጋጅ የነበሩት ግሩም ኢትዮጵያዊ የሚዘጋጅ ) እና እንደዚሁም ኢትዮሜድያ እና አዲስ ድምጽ ራዲዮ እና ስሙን አሁን ለዘነጋሁት አትላንታ የሚገኝ ራዲዮ ጣቢያ በስተቀር “በተቃዋሚ ነት” የቆሙ 47 የዌብሳይት ባለቤቶች ዜናዉን ሰምተዉ እንዳልስሙ ገሸሽ በማለታቸዉ “ያልጠበቅነዉ” –“ወገናዊነት” የሚያንጸባርቁበት ጊዜ በማየታችን እጅግ ቅሬታችን ለማስተላለፍ እንፈልጋለን። ሌሎቹም የፓርቲ መሪዎቻቸዉ አና እዉቅ ዘፋኝ በወያኔ ስለታሰረባቸዉ መድረኩን 24 ሰዓት በማጨናነቅ ነጋ ጠባ ስለ እነሱ ብቻ ሲነግሩን ሌሎቹ በዝና ወይንም በመድረክ ያልታወቁ “ተራ” የትግራይ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች እና አረጋዉአን ግን ለአንዳፍታ እንኳ በወያኔ የደረሰባቸዉ ግፍ በጨረፍታ እንደዜና በመድረካቸዉ ለማቅረብ አልተጨነቁም። ለምን? ለሚለዉ ጥያቄ የሚመልሱት ወግንተኞቹ ሲሆኑ መልስ ለመስጠት ይጨነቃሉ ባንልም በታሪክ ጉዞ ነን እና ዳመናዉ እየጠራ ሲሄድ አብረን መልሱ የምናዉ ይሆናል። ሌላ ቀርቶ “የሕግ ባለሞያተኞች ነን” “ሕግን እናስተምራለን” “ለተበደለዉ ለተጠቃዉ ወገናችን እንቆማለን፤እንከራከራለን፤ሃሳብ እንሰጣለን እናማክራለን” “ስለ ፍትሕ እንጮሃለን…..” በማለት ነጋ ጠባ ስለ ብርቱካን እና ስለ ተዲ አፍሮ ሕግ ማጣት ከገጽ ወደ ገጽ ከድረገጽ ወደ ድረገጽ መድረኮቹን በማጣበብ የሚጥፉ “የሕግ ምሁራን ኢትዮጵያዉያን” በዚህ አሰቃቂ በደል ደረሰባቸዉ የትግራይ ዜጎች ግን “ትነፍሽም” አላሉ! ለምን? የሚለዉ ጥያቄ መልሱን ለማግኘት ለወደፊቱ አብረን የምናየዉ ይሆናል። እነኚህ ወገኖቻችን ስለ ሕግ ሲጽፉ ለማን ነዉ የቆሙት? ለተራዉ ዜጋ፤ ወይስ ለታዋቂ እና ዝናን ላተረፉ ዜጎች? ወይስ ለማንም የተበደለ ዜጋ? የፓርቲ ፈቅር እና ሰብአዊ መብት በሕግ ፊት የተለያዩ መሆናቸዉ ሕግን ለተማሩ እና ሕግን ለሚያስተምሩ የሕግ ሰዎች ፤ -እኛ ሕግ ያልተማርነዉ ዜጎች ድክመታቸዉን ስናስረዳ “ሕግ” የተባለዉ ሰዉ ምንኛ ይታዘባቸዉ ይሆን? “ለዝናብ ደመና፤-ለሰዉ ልጅ ጤና” የተባለዉ የአበዉ ብሂል አለና ጤና ሰጥቶን ሁላችንም የመጨረሻዉ አቀበት ስንወጣ እንዘክረዋለን። በዚህ የፓርቲ እና ወገናዊነት ሩጫዉ ከቀጠለ “አቶ ወያኔ” ከመንበራቸዉ ይነሳሉ ማለት “የሚታሰብ” አይደልም። ጅቡ ከምሽጉ ሳይንቀሳቀስ ተቀምጦ እራቱን የሚበላበት ወቅት ያፋጥነዋል የሚል እምነት አለኝ። ለዛሬ በዚህ ልሰናበት እና ፣ከላይ የጠቀስኩትን “በሰማእታት እና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር” የተሰኘዉ የወያኔ ባዓል “የካከቲትን” አስመልክቶ ሰሞኑን እንቃኛለን። ደህና እንሰንብት። getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com

Friday, February 13, 2009

የሞራል ጸጋ የተላበሱ እናት ወ/ሮ ማንአህሎሽ ጎላ ጌታቸዉ ረዳ

ምንጭ ከኮሎኔል አስናቀ እንግዳ (ማነዉ በደለኛ? ከሚለዉ መጽሃፋቸዉ) ክብርት ወይዘሮ መንአሀሎሽ ጎላ ፋሽስታዊ አገዛዝ ተቃዉመዉ ልጆቻቸዉን ትተዉ በመዉጣት ታጋይ ሃይሎችን ሲረዱ ቆይተዉ ትግሉ እየረገበ ሲሄድ በሁኔታቸዉ ግፊት ወደ ሱዳን በመሄድ በስደት ላይ የነበረዉን ተቃዋሚ ሃይል ሲረዱ ቆይተዋል። ወደ አሜሪካ ከመጡ ጀምሮ ለአንድነት ለዲሞክራሲ ለፍትህ የሚታገሉትን ተቃዋሚ ሃይሎችን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ።
ወ/ሮ ማንአህሎሽ ጎላ የመለስ ዜናዊን ሚስት አዜብ መስፍንን ያሳደጉ ናቸዉ። መለስ ዜናዊም የጋብቻ ትስስርን በመጠቀም ስልክ እየደወለ ለማግባባትና ደጋፊያቸዉ ለማድረግና በእሳቸዉም አማካይነት የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ ለመያዝ ብዙ ሞክሮ ነበር።ባለቤቱ አዜብም ለማግባባት ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች።ስምን መልአክ ያወጣዋልና አጅሪት ክብርት ወይዘሮ ማናህሎሽ ለነሱ ከንቱ ጥረት አልተበገሩላቸዉም። እሳቸዉ በሃጢአት የሚገኝ ምቾትና ጥቅም ይበልጥብኛል ብለዉ ያልተታለሉ የከሃዲዎችን የሙታን መንፈስ የተጸየፉ፤የነቁ አገር ወዳድ ለመሆናቸዉ የሞራል ጸጋን የተላበሱ ናቸዉ። ድንቁርና መደብ በሰራበት በወያኔ የአመራር ቡድን በሐረርጌና በአርሲ በድንቁርና ያልተደረገ የግፍ ዓይነት የለም። በበደኖ በገደል የተወረወሩት በገለምሦ በመቻራ እየተቆራረጡ በዘር ማጥፋት ዘመቻ ነዉ። በጎንደር ክፍል ክፍለሃገር በወልቃይትና ጠገዴ ከጎንደር ክፍለ ሃገር ተነጥለን ወደ ትግራይ አስተዳደር አንዛወርም በማለታቸዉና ብዙ አዛዉንት እየተለቀሙ ግህን በሚባለዉ የመሬት ዉስጥ አሰቃቂ እስር ቤት እና በመቀሌ እስር-ቤት እወንዲማቅቅ ተደርጓል ከፋኝን አብልታችሗል አጠጥታችሗል በመባል መሬታቸዉን ተቀምተዋል። የሴቶች ክብረ ንጽህና ተደፍሯል።መቸም ደንቆሮዉ ወያኔ በሚያስተዳድረዉ በወልቃይትና ጠገዴ ሕዝብ ላይ ያልፈጸመዉ ግፍ የለም። በደብረ ታቦር ሕዝብ ላይ ደንቆሮዉ ወያኔ የተደራረበ ግፍ ፈጽሞበታል። ከደርግ ጋር በማበር ወግታችሁኛል በሚል በቂም በቀል የሚገባዉን መብቱን ሁሉ ከልክሎታል። በተለይም የደብረ ታቦርን ከተማ እንዳይለማ አድርጎ ጨርሶ ለማጥፋት እየጣረ ነዉ። አንድን ግለሰብ ጀኔራል ሃይሌን ደግፋችሗል በማለት ምንም የማያዉቁትን አርሶ አደሮች እየሰበሰበ እረሽኗል።ልዩ ልዩ ስቃይም ፈጽሞባቸዋል። ደብረታቦር አዉራጃም ሆነ ከተማዋ መሰረታዊ የልማት አዉታር ሊዘረጋባቸዉ ቀርቶ ያሏትንም አጥታለች። በአዲሰ አባባ ከተማ የተረሸኑት ምሁራን ተማሪዎችና የፋብሪካ ሰራተኞች የወያኔ የድንቁርና ሰላባ የሆኑት እጅግ ብዙ ናቸዉ።ከዚህም ሌላ የኤርትራንም ሆነ የትግራይ የመገንጠል ቅስቀሳና ማኒፌስቶ የተቃወሙ የትግራይ አዛዉንቶች ከያሉበት እየለቀሙ የረሸኗቸዉን ታሪክ ነገ ፈልፍሎ ያወጣዋል። ወያኔ በትግራይ ዉስጥ ታሪክ የሚያዉቁትን አዛዉንቶች ሲያመቸዉ በግልጽ ሳያመቸዉ በስዉር ስለ አጠፋቸዉ በአንድ ወቅት ሽበት ያለዉ ትልቅ ሰዉ በትግራይ አልነበረም። በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉትን ብሔረሰቦችን ተቃዋሚየን ትደግፋላችሁ እየተባሉ ያለ ፍርድ ተገድለዉ የመሬት ማዳበሪያ የሆኑ አያሌ ናቸዉ። በሽፍታዉ ወያኔ የጋምቤላ ሕዝብ ነገዶችን ኑየርና አኝዋክን እርስ በርሳቸዉ እያጋጩ የብዙ ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት እነዲጠፋ አድርጓል።ወ ያኔ የጥወፋት ሠራዊቱን ወደ ጋምቤላ ልኮ በግፍ በመጨፍጨፍ ሕይወታቸዉን ለማዳን ጋምቤላዎችን በመጨፍጨፍ ሕይወታቸዉን ለማዳን ጋምቤላዎች ወደ ሱዳን ተሰድደዉ በረሃብ እና በበሽታ በመሰቃየት ላይ ናቸዉ። በጠቅላለዉ በኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና ነገዶች ላይ የፈጸሙት ልዩ ልዩ ግፍ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። የአእምሮ ቀዉስ ያለባቸዉ በሽተኞች ብሎ ማለፍ ይሻላል። በኦነግ ምክንያት የተረሸኑትም ቤቱ ይቁጠረዉ። በመለስ ዜናዊና ቡድኑ ጤናቸዉ ተመርምሮ ጤናማ መሆናቸዉ በባለ ሞያ ሓኪሞች (ሳይክያትሪስቶች) ከተረጋገጠ በአገር ክሕደትና ሕዝብን እርስ በርሱ በማጨፋጨፋቸዉና በሌሎች ወንጀሎች ተከሰዉ ሊፈረድባቸዉ ይገባል።//-// ኢትዮጵያ ለዘላም በነጻነቷና በምሉእ ሉአላዊነቷ ለዘላም ትኑር! ሕዝብን እና አገርን የደፈሩ እና የበደሉ ለፍርድ ኢቅረቡ! ጌታቸዉ ረዳ የካቲት 2000 ዓ/ም የትዮጵያ ሰማይ ዌብሎግ አዘጋጅ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ getachre@aol.com

Tuesday, February 10, 2009

ከዚህም ከዛም ክፍል 1- እናዉቅላችሗለን ለሚሉን “ጸሃፍት እና ድረገጸቻቸዉ” ከጌታቸዉ ረዳ ሰሞኑን ደግሞ “መድረክ” የተባለ የወያኔ “ነበር” ፕረዚዳንቶች፤”ነበር” ወያኔ ጀኔራሎች እና “ነበር” የወያኔ ሊህቃን መሪዎች በተጠቀሰዉ “መድረክ” በተባለዉ የመገናኛ አዉድ - ወይዘሪት ብርቱካን የምትመራዉ አዲሱ “የተቃዋሚ ድርጅት” እና ተቃዋሚ የተባሉት የወያኔ/ኢሕአዴግ ፓርላሜንታሪያን/አባሎች (እነ መራራ እነ በየነ …) “ተቀላቀለ” የሚል ዜና ሰምተናል። ምን ለምደርግ እንደሆነ “ትንንሽ ነጥቦችን” ለቅምሻ ቢወረዉርልንም መሰረታዊ የመጨረሻ ግቡ **“ወያኔን” በሌላ አነጋገር-“ቡድን-39” ብየ የምጠራዉን ዓረና እና ከመለስ ወያኔ ቡድን ጭምር (ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸዉ እና )” /ወያኔን ለመጣል/ለመለወጥ/ ለማሻሻል ወይንስ ደግሞ --- “የኢትዮ-ሚዲያዉ አዘጋጅ ወንድሜ አቶ አብረሃ በላይ በዌብ ሳይቱ ርዕስ እንደሚነበበዉ “ወያኔ የኢትዮጵያ እና የትግራይ ጠላት ስለሆነ “መጥፋት” አለበት የሚለዉ መሪ አቁዋም ተግባራዊ ለማድረግ? ?
የወንድሜ የአቶ ግርማ ካሳ አንደኛዉንም ወያኔን አትንኩ/አትዝለለፉ ስላሉን አቋማቸዉ እናዉቀዋለንና አዲስ ነገር ሲመጣ ተሎ ከበሮ የመምታት ልምድ ስላላቸዉ ብዙም አልገረመኝም። ከላይ ያለዉ ጥያቄ ግን ፦ለጥያቄዉ መልስ “ከመድረክ- አባሎች” መልስ እንጠብቃለን። መድረክ የተባለዉ አዲስ “እርግብ” አላማዉ ምን ድነዉ? ለመጣል/ለማስወገድ/ለማሻሻል/ለመመሳሰል/ለመጎዳኘት/ለመሞዳሞድ/ለማገዝ/ -ወይስ “ከምርጫዉ በሗላ መረራ ጉዲና ሸዉዶን ፓርላማ ሲገባ እንዳለን “ፓርላማ ዉስጥ ገብቶ “ደሞዝ” ለማግኘት ? መልሱ እንጠብቃለን። አቶ ግርማግርማን ማንሳቴ ላልቀረ እሳቸዉንም ልጠይቅ። እነገብሩ ካልመጡ ወያኔን መጣል አይቻልም ሲሉን ለመሆኑ እነ ገብሩስ እነ ስየስ ቢሆን በማን እጅ ሆኑ እና ነዉ መለስን ለመጣል የሚችል ታምር ሊኖራቸዉ የሚችል? ራሳቸዉን መከላከል ያልቻሉ ወህኒ የበሰበሱ ምስኪኖች ‘መለስን ይጥላሉ እኛን ነጻ ያወጡናል ስትሉ ይገርመኛል።
ለመሆኑ የሕዝብ ታላቅ ታሪክ ሰሪነቱ እንዴት ረሳችሁት? ካለ ዓረና ሱታፌ፤ካለ ጊዳዳ ካለ ስየ ሱታፌ በምርጫዉ ወቅት ወያኔን መድረሻ አሳጥቶት አልነበረም? መለስ መሬት ጠብባዉ ደብረዘይት ድረስ ተሸሽጎ አልነበረም? ዓረና እና መሰሎቻቸዉ እማ ቅንጅትን ለመምታት “ልዩ ኮሚቴ አዘጋጅተዉ እንደ ነበር ጀኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት (ዑስማን) በደሃይ መጽሄት ነግሮን ነበር። አቶ ግርማ ካሳ ትግረኛ ያነብባሉ የሚል ግምት አለኝ (ካልተሳሳትኩ) አቶ ግርማ ይህነን ምስጢር ለምን ድነዉ የሚሸሽጉን? ወይስ አሁን ምን ክስተት ተፈጠረ እና ነዉ “እነ “ነበር” ፕረዚዳንቶች፤ጀነራሎች፤ ነበር ወያኔ መሪዎች” እንደ ደርግ ወታደሮች እንጠቀምባቸዉ የምትሉን? ለመሆኑ ሁለቱ ክስተቶች “ልዩነታቸዉ ያዉቁታል? የወያኔ ታጋዮች/መሪዎች እና እና የደርግ ጀኔራሎች/ወታደሮች” አመለካከት አንድ ነዉ? እንሸዉዳቸዉ ቢባልስ “ይቻላል?” ዉድ አንባቢዎች ሆይ፡ “ዋች ዶግ” (ታዛቢ) የሚባሉ ክፍሎች በፖለቲካዉ ዓለም እንዳሉ የምታዉቁት ነዉ። ታዲያ በኛዉ ማሕበረሰብ አልተለመደም እና “የዋች ዶግ- የታዛቢ” ጭሆት እና ስራ ስንሰራ “አፍራሾች” የኤርትራ
ዜጎች ስለሆናችሁ ወደ ኤርትራችሁ ሂዱ ከኢትዮጵያ ዉጡልን ይሉናል። የማንባለዉ የለም።
አብሶ እማ ለእኔ እና ለወንድሜ አቶ እያሱ አለማዮህ “የትዝብት ስራችነን በጦቆምን እና በጻፍን በጮህን ቁጥር” ጭራሽኑ “ኤርትራዉያኖች አድርገዉን ከኢትዮጵያ ዉጡልን፤ዜግነታችሁ ኢትዮጵያዊ አይደለም እያሉን ነዉ። ይሄ ደግሞ አሲምባ ከተባለዉ የህዋ ሰሌዳ (ለኔ በተለይ) እና ሰሞኑን ደግሞ አቡጊዳ ከተባለዉ የህዋ ሰሌዳ የዉይይት መድረከ ሃሳባችንን በለገስን ቁጥር “ዜግነታችን” ጭራሽኑ ተገፍፈን መድረኩ ሆን ተብሎ ለሚዘልፉን ለዘረኞች እየተፈቀደ “ባዙሪት” ደም ፍላታቸዉን ለመወጣት እየተወጡ ታዝበናል። በሁለቱም መድረኮች ተመሳሳይ “መፈክር” በድረ ገጾቻቸዉ ተለጥፎ ተለይቶ ይነበባል። “አሲምባ ዳት ኦርግ” ልጀምር፦ አሲምባ የተባለዉ መድረክ ስታነቡ “የሚከተለዉን ታነባላችሁ- “እምቢኝ ለአንጃዎች!ለሆዳሞች! ለበታኞች!እምቢኝ እመቢኝ ለወያኔዎች! ለዘረኞች! ለጎጠንነት! ወዘተ…”ይላል። ታዲያ ወደ የዉይይት መድረካቸዉ ገብታችሁ ስትፈትሹ “ዘረኞችን፤ጎጠኞችን፤ጸረ ኢትዮያ አስተያየቶችን ፤የብልግና ቃላቶች የሚጽፉ ሰዎችን አረጋዉያን ቤተሰቦቻችንን የሚዘልፉ ቃላቶችን የሚጽፉ ግለሰዎች ሲያስተናግዱ ደግሞ ታነባላችሁ። አስቀድሜ ለህዝብ ይፋ ስላደረግኩት አሁን መድገሙ ያሰለቻል እና ወደ አቡጊዳ ድረ-ገጽ እንለፍ። ወደ አቡጊዳ ወደ ተባለዉ ድረ ገጽ ስትግቡ ደግሞ ልክ እንደ አሲምባዉ “መፈክሩ” ከላይ አሸበርቆ ይነበባል “የአደራ ዕዳ” ይላል - ከ ወደ ዉይይቱ መድረክ ስትገቡ ደግሞ አንድ ዘበኛ እንዲህ ሲል ከበሩ አፋፍ ላይ የተለጠፈ መፈክር ያስነብባችሗል - “ህወሓት እና ሻዕቢያ መድረካችን ላይ አስጸያፊ ቃላቶችን በመጻፍ ስላስቸገሩ ሁሉንም አስተያየት ሳንሱር ለማድረግ ተገደናል። አስተያየትዎ ከተገመገመ በሗላ እንለጥፈዋለን። ከይቅርታ ጋር።(አቡጊዳ) ይላል፡፤ ታዲያ ሻዕቢያ እና ህወሓት ብቻ እንጂ ኦነጎችን ወይንም “ኢትዮጵያዉያን” አስጸያፊ ቃላቶችን አይጽፉም የሚል አቋም በመያዝ የሚከተለዉ አስጸያፊ ብቻ ሳይሆን “ዘረኛ” ጽሁፍ እራሳቸዉ ገምግመዉ “የይለፍ” ፈቃድ አትመዉ እንዲለጠፍ ፈቅደዋል። የሚከተለዉ እንዲህ ሲል ስለ እኔ እና ስለ አቶ እያሱ አለማዮሁ “ወደ ኤርትራችሁ ሂዱ” የሚል በአቡጊዳ ሳንሱር ፈቃድ የተለጠፈዉ -ልጥቀስ GUYs, leave alone the lost Getachew Reda. Is Getachew Reda Berhane Meskel Reda’s brother? Getachew Reda is another Eyasu Alemayohu from Eritrea. Both are hidden snakes to poison Ethiopia’s unity and Ethiopians in support to their Eritreans in Menlik’s Palace. Getachew Reda will continue with his destructive and divisible against all oppositions parties except on his Eritreawi Eyassu’s EPRP. UDJ stands for Ethiopia’s unity, democracy and freedom of Ethiopians and belongs to Ethiopians not to Eritreans. The Eyassu Trojan Horse Getachew Reda must take off his hand from our country Ethiopia peacefully. Getachew was very busy hand from our country with his divisible articles when Ethiopians were created AFD. And we know now how this man has involved in destroying of CUPD and KIL along with Meto Aleka’s son in law (Eyaassu). Who knows may be millions dollars is behind the door. So Getachew must be leave our Ethiopian’s issues for Ethipians, other wise you will face Ethiopians. Your country (Eritrea) is separated from Ethiopia. You have done all what you could for it’s separation.” End of quote. ዉድ አንባቢዎች ይህ እና ይህንን የመሳሰሉት የዜጎችን መብት የሚነጥቁ ዋልጌዎች በተጠቀሰዉ “ዌብ ሳይት” አዘጋጆች ተነብቦ ፤ተገምግሞ “የስደብዋቸዉ፤ዝለፏቸዉ፤ኢትዮያጵያዊያን አይደሉም ብላችሁ ለዓለም ንገሩ፡ በማለት “ ድረገጻቸዉ ከሚለጥፈዉ መፈክር “በተቃራኒ” ጽሁፉን ገምግመዉ በእዉቅናቸዉ ሲለጠፍ ታዝበናል። ትግላችን ከወያኔ ብቻ ሳይሆን እኛን መስለዉ የዘረኝነትን ጽሁፍ አንብበዉ ገምግመዉ ይለጠፍ በማለት የሚለጥፉ የድረ-ገጽ ባለቤቶችን ለኢትዮጵያዉያን በመንገር ለታሪክ እንድትመዘግቧቸዉ ይሄዉ አቤቱታችነን ከማስተላለፍ አንቆጠብም። ይህንን ስንል ደግሞ “ትግሉ እናቆማለን ማለት እንዳልሆነ እነዚህ ተባባሪዎቻቸዉ እንዲያዉቁልን ደጋግምን ለማሳሰብ እንወዳለን።
2ኛዉ ክፍል ለአቶ ግርማ ካሰ የሰጠሁትን መልስ አንብቡ። አቶ ግርማ ካሳ በወያኔ ተገደሉብን የምትሉ ሰዎች አደብ አድርጉ ፤ሕግ እስክናቋቁምላችሁ እነ ገብሩ እነ ስየ እነ አዉዓሎም እነ እነ የወያኔ ፕረዚዳነቶች እና ሊህቃኖች እና ጀኔራሎች እና ባቶ ግርማ ካሳ ድርጅት በመተባበር እያሰብንላችሁ ነዉ እና እስከዛዩ አፋችሁን ክደኑ “አደብ! አደብ!” እያሉን በዛዉ ድረገጽ ዉይይት መድረክ አንብበናቸዋል።
ወንድሜ አቶ ግርማ ካሳ “በዓረና/በወያኔ” የተሰቃየበዎት/የተነጠቀበዎት ወንድም ዘመድ ወዳጅ፤ጎረቤት ጓደኛና የትግል ጓደኛ ላይኖረዎት ይችላል እና የቤተሰብ ሃዘን አልተሰማዎትም። "እንዴታ አለኝ እንጂ" ነገር ግን በሗላ እንተሳሰብ "በገደሉብን፤ በነጠቁብን፤አገር በሸጡት፤አገር ባዋረዱት" ሰዎች እጅ በእነ ገብሩ በእነ በእነ..በእነ "ነጻ"-እንወጣለን የሚሉትን ፖለቲካዎ "ለመሞኘት እና ለማሞኘት" መብትዎ ነዉ እና አከብረዋለሁ። ነገር ግን ካሁን በፊት "ወያኔን መዝለፍ፤ አፋኝ፤ገዳይ፤ባንዳ፤ ጨቋኝ ...ማለቱን "መቆም አለበት!"የሚል ትዕዛዝዎ ሲያስተላልፉልን "ሞኝነትዎን አከበርን። ሞኝነትዎን ግን መልሰን "እባክዎ ወደ እኛ ጅላጅል ፖለቲካዎን አያስተላልፉት? ወደያ ይጣሉት" ስንለዎት "ተቆጥተዉን ነበር" ግን ትንሽ ሳይቆዩ ከሕልምዎ "ባነኑ እና" ወደ ልብዎት ሲመለሱ "እኔስ መስሎኝ ነበር" ብለዉ ደግሞ ሞኝነትዎን" አስተካከሉ እና ወደ ልብዎ ገቡ። ያ ያስታዉሱታል የሚል እምነት አለኝ። አሁንም ወያኔ በተጠጋዎት ቁጥር “ተስፋ፤ተስፋ ተስፋ” የሚል መፈክር እያሰሙን ነዉ “መልካም ተስፋ ለሁላችን”
እኔ የሚገርመኝ አሁንም አርስዎ እነ ስየ እነ ገብሩ የትግራይን ህዝብ ወደ እኛ እያስገቡልን ነዉ እያሉን ነዉ ። ስልትዎን አደንቅለዎታለሁ "ዉጤቱ ሳይ" በበለጠ አድናቆቴን እለግስለዎታለሁ። ያስ ባልከፋ ነገር ግን ቤተሰቦቻችን ያዉም በሺዎቹ የትግራይ ዜጎች አሁን እርስዎ ነጠላዎን "አወንዝፈዉ" "ሽር ጉድ በሚሉላቸዉ ነብሰ ገዳዮች እና አገር አስገንጣዮች" እጅ ቤተሰብ እና ጓደኛ ያለቀባቸዉ የትግራይ ሰዎች እና የተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ጩኸት "ሲያጣጥሉ" ሕግ “ሲቋቋም ገድለዉ በድለዉ ከሆኑ እንተሳሰባልን” በማለት ፍረደ ገምድልነትዎን አስሰምተዉናል። እኛ የእርስዎ ተባበሪነት ማጣት እንጂ እዚሁ ሲመጡ ከስሰን ፍረድ ማግኘት ይቻል ነበር ነገር ግን ለዚህ አልታደልንም። የሕግ ሰዎች ምናልባት እያነበቡኝ ከሆነ ምን እያልኩ እንደ ሆነ ከገባቸዉ ሃለፊነታቸዉ በተግባር ያሳዩን፡እዚሁ አገር- “አሁኑኑ!! ግርማ ካሳ "ጅልነትዎ አሁን ሳይሆን፤ ለወያኔ ማዘንዎ መከላከልዎ አሁን ሳይሆን" የቆየበዎት በሽታ ስለሆነ አስከዚያዉ ግን ፡ነብሰገዳዮችን የማጋለጥ፤ባንዳዎችን የመኮነን፤ስረዎቻችን አና ማሕደሮቻቸዉን የመጻፍ መብታችንን እባክዎን በሚከላከልሉዋቸዉ በወያኔ አምላክ ስም አይንፈጉን" ገዝቸዎታለሁ!

Monday, February 9, 2009

ስልጣንና ህገ-መንግስት በኢትዩጵያ….

ስልጣንና ህገ-መንግስት በኢትዩጵያ….
ከጀሚላ አብዱልቃድር ጥር 26/2001 አ.ም
መንግስታት በየጊዜው በተለወጡ ቁጥር ህገ-መንግስትን በህግ አርቃቂ አካላት በማርቀቅና በማሻሻል ለሚመሩትና ለሚያስተዳድሩት ማህበረሰብ ጠቃሚ ከለላና ጠባቂ ሆኖ ህገ-መንግስት የአንድ ሀገር የበላይ ህግ ሆኖ ይረቀቃል። የህግ አውጪውም ክፍል በህገ-መንግስቱ መሰረት ህግ ያወጣል።ስራ አስፈጻሚው ክፍልም በህግ መሰረት ይሰራል የሚለው የህገ-መንግስቱ ጽንሰ ሃሳብ የህገ-መንግስትን የበላይነት ያረጋግጣል። ህገ-መንግስት በመሰረቱ በዜጎች መብት፣ዲሞክራሲ፣የነፃ እንቅስቃሴና ስልጣን የህዝብ አካል በሚሉ ሃሳቦች የተመረኮዘ ቢሆንም እንኳን ከንጉሰ ነገስታቱ የህገ-መንግስት ረቂቅ ጀምሮ ያሉት ህገ- መንግስታዊ ረቂቆች ባገሪቱ ያለውን የሃይል ሚዛን ባልተዛባ ሁኔታ የዜጎችን መብት የሚያረጋግጡ ረቂቆች ሆነው አያውቁም። የኢህአዴግ ህገ-መንግስት ስልጣን ለተለያዩ አካላት የማከፋፈልና ስልጣንን ለህገ-መንግስቱ ተገዢ ላልሆኑ በፓርቲው ጀሌዎች ታጥሮ ያለና የዳኝነቱን ክፍል ነፃነት የሚያረጋግጥ አይደለም፡፡በህግ ሰፍረው የሚገኙ የህግ የበላይነትን የሚያረጋግጡ አንቀጾች በፓርቲው ፈላጭ ቆራጭ አመራሮች ያለ ምንም ገደብ በቀላሉ ሊጣሱና ሊረገጡ የሚችሉ ናቸው፡፡የገዢው ፓርቲ አባሎች በህዝብ ላይ ለሚያደርሱት አፈና ግድያና የሰብሃዊ መብት ረገጣዎች የስልጣንን የበላይነት የሚቃወምም ሆነ የሚከላከል ብሎም የህገ-መንግስቱን መከበር የሚያረጋግጥ ነጻ የሆነ የህግ አካል የለም። ነፃ የሆነ የዳኝነት አካል መኖር የዲሞክራሲ አንዱ ገጽታ ነው።የኢህአዲግ ህገ-መንግስታዊ አንቀጽ 79/3 “ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነት ያከናውናሉ።ከህግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም።”ይላል ግን በየጊዜው በየፍርድ ቤቶች ከገዢው ፓርቲ ያፈነገጡና የኢህአዴግ ኢሰብሃዊ የዜጎች አፈናና ጭፍጨፋ አሜን ብለው ሳይቀበሉ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ንፁህ ዜጎች ገዥው ፓርቲ ባሴረላቸው የሃሰት ውንጀላና በሃሴትነት ባስቀመጣቸው ዳኞች ሐሴተኛ ውሳኔ ለእስራት፣ለግርፋት፣ ብሎም ለግድያ የተዳረጉትን ንፁህና ሰላማዊ ዜጎቻችን እሮሮ የየእለቱ ዜና ነው።የኢህአዴግ ህገ-መንግስታዊ ረቂቅ በህዝብ ሃሳብና ፍላጎት የተመረኮዘ ሳይሆን ጥቂት ለዚህ ህዝብ እኛ እናውቅልሃለን በሚሉ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በር ተዘግቶ ለጭቆናዊ አመራራቸው አመቺ በሆነ መልኩ የስልጣን ጥም እድሜ ማራዘሚያነት ያረቀቁት ነው። በጥር 12 ቀን 2001 አ.ም በእነ አቶ መለስ ዜናዊ እና በጀሌዎቻቸው አቅራቢነት ለይስሙላ ለህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ቀርቦ የፀደቀውና አወዛጋቢው የ27 ፌዴራል ዳኞች ሹመት ከተለያዩ ታላላቅ አገር በቀል ምሁራን ተቃውሞ የገጠመውና ከህገ-መንግስቱ አዋጅ ቁጥር 24/88 አንቀፅ 8’’2 ጋር የሚጋጭ ነው።በዚህ አንቀፅ “ማንኛውም ሠው በመንግስት ህግ አውጪ ወይም አስፈፃሚ ውስጥ በአባልነት በሚያገለግልበት ጊዜ አጣምሮ የዳኝነት ሥራ ሊሰራ እንደማይችል ይደነግጋል።” ነገር ግን በዚህ የዳኞች ፌዴራል ምርጫ በርካቶቹ በራሱ በ ኢህአዴግ ፓርቲ ውስጥ በአባልነት የሚያገለግሉ ናቸው።ምነው ኢህአዴግ ራሱ ያረቀቀውን ህገ-መንግስታዊ ረቂቅ ዘንግቶት ነው ? ወይስ ሻሪም ሿሚም እኛው ነን ነው ? የዳኝነት አካላት ነፃና ከማንኛውም የፖለቲካ ወገን ገለልተኛ ካልሆኑ በዜጎች ላይ የህግ የበላይነትን ማስፈን ያዳግታል። ይህን የነ አቶ መለስ ዜናዊን ሴራ የህግ የበላይነትን ሳይሆን የስልጣንና የጭቆናዊ ወታደራዊ አገዛዝን የበላይነት ፍንትው አድርጎ የሚያንፀባርቅ ነው። ከጀሚላ አብዱልቃድር ጥር 26/2001 አ.ም

ስልጣንና ህገ-መንግስት በኢትዩጵያ….

ስልጣንና ህገ-መንግስት በኢትዩጵያ…. መንግስታት በየጊዜው በተለወጡ ቁጥር ህገ-መንግስትን በህግ አርቃቂ አካላት በማርቀቅና በማሻሻል ለሚመሩትና ለሚያስተዳድሩት ማህበረሰብ ጠቃሚ ከለላና ጠባቂ ሆኖ ህገ-መንግስት የአንድ ሀገር የበላይ ህግ ሆኖ ይረቀቃል። የህግ አውጪውም ክፍል በህገ-መንግስቱ መሰረት ህግ ያወጣል።ስራ አስፈጻሚው ክፍልም በህግ መሰረት ይሰራል የሚለው የህገ-መንግስቱ ጽንሰ ሃሳብ የህገ-መንግስትን የበላይነት ያረጋግጣል። ህገ-መንግስት በመሰረቱ በዜጎች መብት፣ዲሞክራሲ፣የነፃ እንቅስቃሴና ስልጣን የህዝብ አካል በሚሉ ሃሳቦች የተመረኮዘ ቢሆንም እንኳን ከንጉሰ ነገስታቱ የህገ-መንግስት ረቂቅ ጀምሮ ያሉት ህገ- መንግስታዊ ረቂቆች ባገሪቱ ያለውን የሃይል ሚዛን ባልተዛባ ሁኔታ የዜጎችን መብት የሚያረጋግጡ ረቂቆች ሆነው አያውቁም። የኢህአዴግ ህገ-መንግስት ስልጣን ለተለያዩ አካላት የማከፋፈልና ስልጣንን ለህገ-መንግስቱ ተገዢ ላልሆኑ በፓርቲው ጀሌዎች ታጥሮ ያለና የዳኝነቱን ክፍል ነፃነት የሚያረጋግጥ አይደለም፡፡በህግ ሰፍረው የሚገኙ የህግ የበላይነትን የሚያረጋግጡ አንቀጾች በፓርቲው ፈላጭ ቆራጭ አመራሮች ያለ ምንም ገደብ በቀላሉ ሊጣሱና ሊረገጡ የሚችሉ ናቸው፡፡የገዢው ፓርቲ አባሎች በህዝብ ላይ ለሚያደርሱት አፈና ግድያና የሰብሃዊ መብት ረገጣዎች የስልጣንን የበላይነት የሚቃወምም ሆነ የሚከላከል ብሎም የህገ-መንግስቱን መከበር የሚያረጋግጥ ነጻ የሆነ የህግ አካል የለም። ነፃ የሆነ የዳኝነት አካል መኖር የዲሞክራሲ አንዱ ገጽታ ነው።የኢህአዲግ ህገ-መንግስታዊ አንቀጽ 79/3 “ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነት ያከናውናሉ።ከህግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም።”ይላል ግን በየጊዜው በየፍርድ ቤቶች ከገዢው ፓርቲ ያፈነገጡና የኢህአዴግ ኢሰብሃዊ የዜጎች አፈናና ጭፍጨፋ አሜን ብለው ሳይቀበሉ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ንፁህ ዜጎች ገዥው ፓርቲ ባሴረላቸው የሃሰት ውንጀላና በሃሴትነት ባስቀመጣቸው ዳኞች ሐሴተኛ ውሳኔ ለእስራት፣ለግርፋት፣ ብሎም ለግድያ የተዳረጉትን ንፁህና ሰላማዊ ዜጎቻችን እሮሮ የየእለቱ ዜና ነው።የኢህአዴግ ህገ-መንግስታዊ ረቂቅ በህዝብ ሃሳብና ፍላጎት የተመረኮዘ ሳይሆን ጥቂት ለዚህ ህዝብ እኛ እናውቅልሃለን በሚሉ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በር ተዘግቶ ለጭቆናዊ አመራራቸው አመቺ በሆነ መልኩ የስልጣን ጥም እድሜ ማራዘሚያነት ያረቀቁት ነው። በጥር 12 ቀን 2001 አ.ም በእነ አቶ መለስ ዜናዊ እና በጀሌዎቻቸው አቅራቢነት ለይስሙላ ለህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ቀርቦ የፀደቀውና አወዛጋቢው የ27 ፌዴራል ዳኞች ሹመት ከተለያዩ ታላላቅ አገር በቀል ምሁራን ተቃውሞ የገጠመውና ከህገ-መንግስቱ አዋጅ ቁጥር 24/88 አንቀፅ 8’’2 ጋር የሚጋጭ ነው።በዚህ አንቀፅ “ማንኛውም ሠው በመንግስት ህግ አውጪ ወይም አስፈፃሚ ውስጥ በአባልነት በሚያገለግልበት ጊዜ አጣምሮ የዳኝነት ሥራ ሊሰራ እንደማይችል ይደነግጋል።” ነገር ግን በዚህ የዳኞች ፌዴራል ምርጫ በርካቶቹ በራሱ በ ኢህአዴግ ፓርቲ ውስጥ በአባልነት የሚያገለግሉ ናቸው።ምነው ኢህአዴግ ራሱ ያረቀቀውን ህገ-መንግስታዊ ረቂቅ ዘንግቶት ነው ? ወይስ ሻሪም ሿሚም እኛው ነን ነው ? የዳኝነት አካላት ነፃና ከማንኛውም የፖለቲካ ወገን ገለልተኛ ካልሆኑ በዜጎች ላይ የህግ የበላይነትን ማስፈን ያዳግታል። ይህን የነ አቶ መለስ ዜናዊን ሴራ የህግ የበላይነትን ሳይሆን የስልጣንና የጭቆናዊ ወታደራዊ አገዛዝን የበላይነት ፍንትው አድርጎ የሚያንፀባርቅ ነው። ከጀሚላ አብዱልቃድር ጥር 26/2001 አ.ም

Saturday, February 7, 2009

ዉሉ የጠፋ ጭንቅ ያለ ነገር!

ዉሉ የጠፋ ጭንቅ ያለ ነገር! ከጌታቸዉ ረዳ በሕዳር-ታሕሳስ 2000 ዓ/ም ደሃይ የተባለዉ መቀሌ ከተማ የሚታተመዉ የትግርኛ መጽሄት አቶ ገብሩ አስራትን ለቃለ መጠይቅ አቅርቦ ነበር።ቃለ መጠይቁ አመት ቢሆነዉም፤ ዛሬ ላቀርብላችሁ የፈለግኩበት ምክንያት “በቅንጅት ነበር” (ኤክስ ቅንጅቶች ልብል?) ዛሬ ተለያዩ የድርጅት ስሞች በመያዝ የምናደምታቸዉ ድርጅቶች እና ድረገጾቻቸዉ/ጋዜጦቻቸዉ እና ደጋፊዎቻቸዉ ስለ አቶ ገብሩ አስራት፤ አና “የትግራይ ህዝብና የትምክህተኞች ሴራ ከትናንት እስከ ዛሬ” የሚለዉ ዘረኛ “ጸረ አማራ” እና “ጸረ ሸዋ” “ጸረ-ምኒልክ” መጽሃፍ “አማካሪ” (ገምቢ ሃሳብ ይለዋል ደራሲዉ መምህር ገ/ኪዳን ደስታ) የነበረዉ ጠበቃ ነን ባዩ “ብርሃኑ አባዲ” እና “ድያብሎስ/መላከሞት” በመባል በተሃሕት እስረኞች የሞታወቀዉ ነብሰ ገዳዩ “አዉዓሎም ወልዱ/ትኩዕ ወልዱ” የሚመራዉ የዓረና ፓርቲ በቅርቡ ያዘጋጀዉ ስብሰባ ሰፊ ዘገባ የዘገቡላቸዉ “ድሮ ቅንጅት” አባሎች እና ደጋፊ ድረገጾቻቸዉ ስላስነበቡን፦ እኔም በመገርም “እነኚህ ቅንጅቶች” ነበርን የሚሉት የዓረና አወዳሾች ፤እዉን አቶ ገብሩ አስራት ስለነሱ /ስለ “ነበር ቅንጅቶች” አቃሉ? የሚል ጥያቄ ስለቻረብኝ ፤አቶ ገብሩ አምና የሰጠዉ ትግርና ቃለ መጠይቅ ተርጉሜ ለ አማርኛ አንባቢ ላቅርብ እና ሃሳቦች ቢንሸራሸሩ በማለት አቅርቤአለሁ። አነሆ፦ ደሃይ-መጽት-
ቅንጅት ተከተለዉ የምርጫ ሰትራቴጂ ብዙ ቅሬታ ፈጥሯል። በ ተለይም በትግሬዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስንቷል።(ቅንጅት) ዘር መሰረት ያደረገ (ቅስቀሳ) ስለነበር እነሱ (ቅንጅት) በጠሩት ሰለማዊ ሰልፍ ተገኝዉ በመስቀል አደባባይ ወጥተዉ ንገግር በማድረግዎ በትግሬዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል። ለምንድ ነዉ ራስዎን በዛ ሁኔታ ሊከቱ የፈቀዱት? በዚህ ያለዎት አስተያየት ካለ? ገብሩ አስራት (መልስ)፦ ይህ ጉዳይ ስናነሳ መሰረተ ሃሳቡን ከመሰረቱ ካላየነዉ ችግር ነዉ። ይህነን በሚመለከት አንድ ነገር ማለት የምችለዉ፤ መስቀል አደባባይ የተደረገ ሕዝባዊ ጥሪ (በገብሩ ቃል (“የፖለቲካ ስብሰባ”) ነበር። ጥሪዉም በቅንጅት ብቻ የተጠራ ስብሰባ አልነበረም። ሕብርት የተባሉት አሁን ፓርላማ ዉስጥ ያሉት ፓርቲዎችም ነበሩበት። ቅንጅትም እነዚህ ሁሉ በጠሩት ስብሰባ እንዱ አካል ነበር። እነዚህ ሁሉ በተሳተፉበት እኔ አንዴት በእነሱ ጥሪ ለመገኘት እንደቻልኩ ማንሳቱ አስፈላጊ ነዉ። በወቅቱ የነበሩት ሁኔታዎች ማንሳቱንም አስፈላጊ ነዉ። በወቅቱ ገዢዉ ፓረቲ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አሳልፎ የሰጠ ባለ አምስት ነጥብ የተባለ የዉሳኔ ሃሳብ አስተላልፎ ነበር። ዉሳኔዉ በወቅቱም ሆነ ዛሬ የኢትዮጵያ ጥቅም አያስጠብቅም የሚል አቋም አለኝ። ይህ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ዉሳኔዉ የአገርን ጥቅም አሳልፎ ለጠላት የሚሰጥ “ያገር ክህደት” ነዉ (ገብሩ ተጠቀመበት ቃል “ስህተት ነዉ” የሚል ቃል ነዉ) ብለዉ ተቃወሙ። እዚህ ላይ እኔ የምነሳበት ማአዝን ሌላ ሊሆን ይችላል፤ እነሱ ሚነሱበት ማአዝን ደግሞ ሌላ ሊሆን ይችላል። የተላያዩ መነሻዎችዎች አሉን። መነሻዎቻችን የተለያዩ ቢሆኑም ከፖለቲካ ፓርቲ የላቀ የጋራ መሰረታዊ ጥያቄ ነክ ነዉ። በገዢዉ ፓርቲ የአገር ጠቀሜታም ሆነ የሉዓላዊነት ክብር አሳልፎ ለኤርትራም ይሁን ለሌላ ክፍል የሚሰጥ ዉሳኔ ሲወሰን ተቃዉሞ ማሰማቴ እንደ ዜጋ ግዴታ አለብኝ። የዜግነት ግዴታየ ለማሰማት ጥሬየን/ተቃዉሞየን በ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ፤በኢትዮጵያ ቴሌቭዢን ፤በድምጺ ወያነ ቢተላለፍልኝ እና እነኚህ የገዢዉን መድብ መገናኛዎች ስሞታየን ለማሰማት ክፍት ቢኖሩ ኖሮ ወደ ቅንጅት ስብሰባ አልሄድም ነበር። ተቃዉሞየን ለማሰማት ዕድሉ ስላገኘሁ መግለጽ ነበረብኝ። ስለዚህም ጥሪ ሲአስተላልፉልን ዶ/ር ነጋሶም ተገኝተዉ ነበር። ለሕዝቡ አስተያየታችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ ተባልን፡ የተሰበሰብነዉ ከቅንጅት ጋር ለመነጋገር አይደልም ስበሰባዉና ጥሪዉ ለተሰበሰበዉ ህዝብ እና ብሎም ለመላ ኢትዮጵያ ነዉ። ስለዚህ ስበሰባዉ ከሕዝብ አንጂ ከቅንጅት ጋር አልነበረም። እናም ባገኘነዉ መድረክ በኩል ታፍኖ የቆየዉን አስተያየቴን ለመግለጽ ያገኘሁትን የመድረክ ዕድል ያ ብቻ ስለነበር ስብሰባዉ ላይ ተገንቼ መግለጽ ነበረብኝ። እንዲያ በማድረጌ ስህተት ነበር ብየ አሁንም አላምንም። ግን ቅንጅትም እኮ በወቅቱ በሕግ ተመዝግቦ ሕጋዊነቱ አግኝቶ ከኢሕአዴግ ጋር ሲሰራ የነበረ ፓርቲ ነዉ። የሗላ ሗላ የምርጫዉ ሙቀት እየበረታ ሲሄድ ኢሕአዴግ “ቅንጅትን” እንደ “ጋኔን” አድርጎ አየዉ። ቅንጅትም በበኩሉ ኢሕአዴግን እንደ ሰይጣን ቆጠረዉ ከኢሕአዴግም አልፎ “የትግራይን ሕዝብ” እንደ “ጋኔን” አየዉ። ይህ ከተፈጠረ ቧሓላ ( ቅንጅት የትግራይን ሕዝብ እንደ “ጋኔል/ዲያብሎስ” ከቆጠረዉ በሗላ የቅንጅቶችን ሃሳብ መደግፍ አልችልም። በመሰረቱ እንኳን እኔ አንድ ታጋይ ቀርቶ ማንም ዜጋም ሊደግፈዉ አይገባም።የትግራይ ሕዝብ እና ህወሓት የተለያዩ ናቸዉ። ፓርቲዉን እንዳሻቸዉ ሊሰድቡት ይችላሉ ፤የትግራይ ህዝብ ግን “ሕዝብ ነዉ” ቅንጅቶች ሕዝብን መንካት የለባቸዉም። የቅንጅት ትልቁ ስሕተት ፓርቲዉን/ወያኔን እና ሕዘቡ የተለያዩ እንደመሆናቸዉ መጠን ፓርቲ እና ሕዝቡ ለይቶ ማየት ባለመቻሉ ነዉ። ቅንጅት በትግራይ ሕዝብ ላይ የወሰደዉ አመለካከት ያኔም አሁንም/ዛሬም የምቃወመዉ ጉዳይ ነዉ። መድረኩ ላኢ ሃሳቤን ለሕዝብ ለማስተላለፍ በእንግዳነት ሲተሩኝ፤ ያ መድረክ እነደዚአ አልነበረም።የሗላ ሗላ ቅንጅት ያሳየዉ አቋም እና ያ መድረክ ለየብቻ ነበሩ። ያገር ጉዳይ በመሆኑ መድረኩ ፓርላማ ያሳለፈዉ ዉሳኔ ስህተተኛ ዉሳኔ መሆኑን ተቃወመ። ያችን መድረክ ለመኮነን ሲባል (ገብሩ) ቅንጅት ነዉ ተባለ። ይህ የድክምት ምልክት ነዉ።አኔ አስተላለፍኩት ጥሪ ያነበብኩት ጽሁፍ ዛሬም በእጄ ይገኛል። የኤርትራ ነጻነት አልተቃወምኩም። የኤርትራ ነጻነት በመሰረቱ አምነንበት የሄደ/ያለቀ ጉዳይ ነዉ።ኤርትራ በተለይም ሻዕብያ በግዛታችን ጦርነት እንዳወጀብን ጦርነቱን መመከት ነበረብን። ዛሬም ከነሱ ጋር መለሳለስ መለማመጥ የለብንም። የሚል መስመር ነበር ያስተጋባሁት። እንግዲህ ይህችን ስላልኩ ከትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች ጋር ተሰልፏል፡ የትግራይን ሕዝብ ከሚያንቋሽሹ ቡድኖች ጋር ተሳትፏል ተባልኩ። ይህ ፕሮፖጋንዳ እና ስም የማጥፋት ዘመቻ ነዉ የምለዉ። ለወደፊቱም ቅንጅት እና እኔ በሚመለከት ምንም ድርጅታዊም ፖለቲካዊም ትስስር የለኝም። በዚህ ጉዳይ የምለዉ ካለ እንግዲህ ለመጨረሻ ጊዜ የምሰጠዉ መልስ ይሄ ይሆናል።ለትግራይ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሃሳቤን ለመግለጽ መድረኩ ሲዘጋብኝ መድረኩ ወደ ሕዝብ ማስተላለፍ የሚቸል መድረክ አስከ ሆነ ድረስ የተገኘን መድረክ ተጠቅሞ ሃሳብን ማስተላለፍ ተገቢ ነዉ እላለሁ። ደሃይ፦ይቅርታም እኮ ጠይቀዋል? አቶ ገብሩ፦ አዎ። ይሄ የይቅርታ ጥያቄ ምን መሰለህ፦ያም ሁሉ በሚገባ መታየት ያለበት ይመስለኛል። በኤርትራ እና በኢትዮጵያ የነበረዉ ጉዳይ አያያዛችን የተሳሳተ አያያዝ ነበረን።ለዛም ነበር ይቅርታ የጠየቅነዉ።በዛ ስበሰባ ብቻ ሳይሆን ከዛ በፊትም በጽሁፍ ያተምናቸዉ ጽሁፎች ሁሉ ሳይቀሩ የገለጽነዉ ጉዳይ ነዉ። አንድ ከፓርቲዉ ጋር ያጣላን አንደኛዉ ምክንያት’ኮ ኤርትራ የ ኢትዮጵያ ሃብት እየመዘበረች ተገቢዉ እና ህጋዊ ቁጥጥር አላደረግንበትም፡ በ ኢትዮጵያ ዉስጥ የራሷ (የኤርትራ) የጸጥታ ቡድን ባገሪቱ ላይ ቅርንቻፎቹን በማደራጀት አሰማርቶ ያሻቸዉን ሰዉ ሲገድሉ አላቆምናቸዉም።ተገቢ ቁጥጥር አላደረግንባቸዉም። ኢትዮጵያዉያን በኤርትራ ምድር መብታቸዉ ሳያከበርላቸዉ እኛ እዚህ የነሱን መብት እናከብር ነበር። ያዉም የኤርትራዉያንን መብት እንዲከበር እናደርግ ነበር።ኢትዮጵአዉያን መብት የሚባል ማንኛዉም ነገር አልተጠበቀላቸዉም ነበር።ጦር ሰብቆ ሲወረንም የኛ ቸልተኝነት እና እንዝህላልነት ነበር።70 ሚልዮን ሕዝብ ሲወረር የሚሳፍር ጉዳይ ነዉ።አልተዘጋጀንበትም ነበር። ስለዚህ ኢህ ሁሉ ሆኖ ድርጅታችን/ፓርቲያችን በፈጸመዉ ጥፋት ብዙ ጉዳት ደርሷል።እዛዉ በፓርቲዉ ዉስጥ እያለን የፈጸምናቸዉ/የተከሰቱ ችግሮች ለኢትዮጵያ ሕዝብ “የራስ ነቀፌታ” (ሰልፍ ክርትሲዝም) አድርገን ይቅርታ እንጠይቀዉ ፤ ..ድክመታችሁ አርማችሁ ቀጥሉ ካለን ድክመቶቻችነን አርምን ተጠናክረን እንቀጥላልን ..የለም..ዉረዱ ፣ካለን ደግሞ ከስልጣን እንወርዳለን (እንለቃለን) የሚል ነበር፤ ከመጀመሪያዉም ከመነሻዉ ወደ ፓርቲዉ ያቀረብነዉ (አጀንዳ)። ይህ (ጉዳይ) ነበር “ጸረ-ዲሞክራሲ” ነዉ ተብሎ፤ “በራሱ-መሪት” ከማየት ይልቅ ወደ ሌላ አካል/ክፍል ጉዳዩን ተወስዶ ተድበስብሶ እንዲቀር ሆነ። ስለዚህ ይህ ይቅርታ ሊጠየቅበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ። ለትግራይ ሕዝብ በዚህ ጉዳይ እዚህ ስተት ፈጽመናል ነዉ ያልኩት እንጂ “የኤርትራን ነጻነት በሚመለከት ስሕተት ነዉ ብየ አላቀረብኩም።ወይንም ደግሞ የይቅርታ ጥያቄዉ የቀረበዉ ለቅንጅት ወይንም ለአንድ ለተወሰነ ፓርቲ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀረበ ይቅርታ ነዉ። አሁንም ደጋግሜ ምለዉ ነገር ትላልቅ መሰረታዊ ስህተቶች ተፈጽመዋል። እነዚህን አፍነህ መጓዝ በታሪክ የሚያስወቅስ እና የሚያስከስስ ነዉ። ህወሓት አስካሁን ድረስ ይህን (ይቅርታ) አልጠየቀም።//-// ለዚህ ቅንጅቶች ምን ይላሉ? እዉን አቶ ገብሩ ለትግራይ ሕዝብ እየነገረን እንዳለዉ ከሆነ “ቅንጅት የትግራይን ሕዝብ እንደ ዲያብሎስ/ጋኔል/” ተምልክቶታል? እንጅቶች የአቶ ገብሩ አስራት አባባል ‘የዉሸት ዉንጀላ” ነዉ የሚሉ ከሆነ “ለምን የድሮ የቅንጅት አባሎች (ዉጭ አሉት የእነ አንዳርጋቸዉ እና የነ ብርሃኑ ነጋ) ተከታዮች አቶ ገብሩን በጤናማ የድርጅት መሪ እና የቅንጅት ወዳጅ አድረጎ ወሰዳቸዉ”? ይህስ ከሆነ ለምን የህዋ ሰሌዳዎቻቸዉ/ድረገጾች እና ጋዜጦች ስለ አቶ ገብሩ እና “ዓረና ድርጅታቸዉ” ሰፊ የሆነ ጤናማ ድጋፍ እና ዘገባ እየሰጡ ይገኛሉ? እኔ “ጥያቄዉን እንደ ጥያቄ” ያቀረብኩት “ቅንጅቶች” ይህ የአቶ ገብሩ አባባል “ያዉቁት ኖሮዋል”? የሚል ጥያቄ ስለጫረብኝ ነዉ። ካላወቁ አሁን ይወቁት እና “ቅንጅቶች- የነ ብርሃኑ ነጋ፤እዮኤል ወዘተ… እና ደጋፊዎቻቸዉ) በዚህ ያላቸዉን አቋም እንዲያሳዉቁን እየጠቆምን -በዚህ መልስ ካላገኘን ወይንም አቶ ገብሩ እና ድርጅታቸዉ “ከቅንጅቶች- እነ ብርሃኑ ..አንዳርጋቸዉ. ብረቱካን.ወዘተ የመሳሰሉ ያሉበት የተላያዩ ድርጅቶች ድጋፍ ከተሰጣቸዉ “በአበባሉ ግራ የተጋባነዉ” ከትግራይ ክፍለሃገር የመጣነዉ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች” እዉነተኛዉ ማን ነዉ? “ቅንጅት የትግራይን ሕዝብ እንደ ዲያብሎስ/ጋኔል/” ተምልክቶታል?

Wednesday, February 4, 2009

የኢሕአደግ እና የህወሓት መሪዎች ጥምር አፈና

የኢሕአደግ እና የህወሓት መሪዎች ጥምር አፈና በሰብአዊ ተሟጋች ድርጅቶች እይታ ከጀሚላ ብደልቃድር (ጥር 6/2001)
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከረጂም ጊዜ ጀምሮ አመታት ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን ባደረጉት መራራ ትግል በቁርጥ ቀን ዜጎች ደም ሃገራዊ ህልዉናዋ ለዘመናት ተጠብቆና ተከብሮ የኖረች አገር ብትሆንም እንኳን ከራሷ በፈለቁ ለሃገርና ለወገን ስቃይና እንግልት ደንታ ቢስ በሌላቸዉ ጨቋኞችና አስተዳደራዊ ስርአትን ባልተላበሱ መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ዛሬም እየደማች እና እየቆሰለች ትገኛለች። ዜጎች በሃገራቸዉ ማህበራዊ ኑሮአቸዉን በሰላማ መንገድ የመምራት፤ የዜግነት መብታቸዉን የመጠበቅ፣የማክበር፣የመምርጥ፣በነጻ የመንቀሳቀስ መብቶቻቸዉ በግፈኛ ገዢዎች መዳፍ ስር ታፍኖ ኑሮአቸዉን በስቃይ እና በፍርሃት ተሸብበዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜታቸዉ ተገፎ በመኖርና በሞት ጣር ዉስጥ ተዘፍቀዋል። የኢህአዴግ መንግስት በዉጭ ያለዉን ዲፕሎማሲያዊና ግንኙነቱንና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎችና በምዕራባዉያኑ ያለዉን ጥቅማ ጥቅሞች ለማስከበር ደፋ ቀና አያለ የዲሞክራሲንና የሰብአዊ መብቶችን እንደሚአከብርና የዜጎችን መብትና ነጻ እንቅስቃሴ እንደሚአከብር ራሱ ባዘጋጃቸዉ ሚዲያዎች ሁለተኛ ፕሮፖጋንዳዉንና የአስመሳይነት ባሕሪዉን ቢያንጸባርቅም እንኳን በድብቅ እና በገሃድ የሚያራምደዉን የአፈና ፣የእስራትና የግድያ ወንጀሎቹ ለአደባባይ በገሃድ ፍንትዉ ብለዉ ወጥተዋል። በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን የሰብአዊ መብት አካሄድ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እና የሕአዴግ መንግስት በህዝብ በፕሬስ -አፈና፣ እስራት ግድያ፣በጅምላ ጭፍጨፋ፣ በተለያዩ ጊዜዎች ባካሄዳቸዉ ጦርነቶች ዉስጥ የፈጸማቸዉ ልዩ ልዩ የጦርነት ወንጀለኞች እና የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ላይ ያለ አምባገነን መንግስት መሆኑን፡ ዋና ጽ/ቤቱ አሜሪካን አገር የሆነዉ “ፍሪዶም ሃዉስ” በመባል የሚታወቀዉ ዓለም ዓቀፍ የእንባ ጠባቂ ተቋም ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ገልጿል:፡ ስለዲሞክራሲና ስለ ዜጎች መብት የሚለፈልፍልን የኢሕአዴግ/የህወሓትና በእነርሱ ስር የታቀፉ እና የጭቆና ኣላማቸዉን በየክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ የፈለፈሏቸዉ ፖለቲካዊ ስፋን በሰጣቸዉ ፓርቲዎቹ ኢስብአዊ አመራር ተግባራዊ ያደርጋል። በሌላ በኩል “ሂዩማን ራይትስ ዎች” የተባለ የሰብአዊ መብት ጠበቃ ድርጅት ባወጣዉ የ2008 ኣመታዊ አጠቃላይ ሪፖርቱ ላይ እንደሚያመለክተዉ በተቃዋሚዎችና ትችት ሰንዛሪዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እየተወሰደ ነዉ።የኢትዮጵያ የጦር ሃይሎች የተለያዩ የጦርነት ወንጀሎችን መፈጸሙን የቀጠለ ሲሆን በተለይም በሱማሌ ክልል በኦጋዴን እና እንዲሁም በሶማሊያ በሰፊዉ ታይቷል” ይላል። የኢሕአዴግ መንግስት ለመጪዉ የምርጫ ሂደት ዝግጅት ይመስላል። አገር ዉስጥ ሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎችን ባገኘዉ አጋጣሚና አቅጣጫ እንቅስቃሴአቸዉን በማዳከም እና በሃሰት በመወንጀል ለእስራት በመዳረግ በአገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የፖለቲካ እና የህዝብ እንቅስቃሴ ከሕግ ዉጭ በሆነ አፈና እና ወታደራዊ አፈና በተላበሰ እንቅስቃሴ ይገኛል። የሕአዴግ መሪዎች ካለፈዉ ምርጫ የሕዝቡን ስሜትና የዲሞክራሲ ጥማቱን እና ብሎም ለኢሕአዴግና ተከታዮቹ ያለዉን ጥላቻ የተገነዘቡ ይመስለኛል። ክፍል 2 በሚቀጥለዉ ጊዜ ይቀርባል። ለዉድ እህቴ ጀሚላ አብደልቃድር ይህንን ወቅታዊና አንገብጋቢ የሰብአዊ ነክ ጉዳዮችን በመላክዋ በ እኔ እና በአንባቢዎች ስም አመሰግናለሁ