Sunday, February 22, 2009

ክፍል-2- በሰማእት እና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር (ካነበብናቸዉ) ጌታቸዉ ረዳ
ለዛሬ ከመጻሕፍት ዓለም የመረጥኩላችሁ “ታሪክ አጉዳፊ የአልባኒያ ደብተራ - የህወሓት መሪዎችና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት” ደራሲዉ ታጋይ ገሰሰ እንግዳ፡ ሰሞኑን እና በዛሬዉ የካቲት 11 /2000 ዓ.ም ወያኔ እና ካድሬዎቹ በሰማእት እና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር ለሚጫወቱት ሃፍረተቢስ የወያኔ ፋሽስቶች ተስማሚ ትችት ሆኖ ስላገኘሁት፤ አብራችሁኝ እንድታነቡት እነሆ፦ እነ መለስ ዜናዊ አዲስ አበባ ገብተዉ በምኒሊክ ቤተመንግስት ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በሗላ በራሱ ታጋዮች ላይ ሳይቀር የተጫወተዉ የፖለቲካ ቁማር እጅግ አሳዛኝ ነበር። ዛሬ በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር እየተጫወቱ ስለ የካቲት ምንነት ሊያበስሩን “የካቲት፤የካቲት” በማለት ሲዋሹን “ወደ ወላጆቻችን እንመለሳለን በማለት በስምምነት ከትግሉ ለመዉጣት የተፈቀደላቸዉ ወጣት ታጋዮች” በግድያ ኮሚቲ ተሰማርተዉ ከፍተኛ ወንጀል የፈጸሙ አስከ ዛሬ ድረስ በሕግ ያልተጠየቁ በንግድ ዓለም ተሰማርተዉ የናጠጡ ሲራራ ነጋዴዎች የሆኑት “ቁንጮ ዘፋኞቻቸዉ” እና “ገጣሚዎቻቸዉ” የሚዘፍኑት እና የሚጫጭሩት የየካቲት ግጥም ለማያዉቃቸዉ ሰዉ እዉነትም “ታጋዮች ሊመስሉ ይችሉ ይሆናል- ”ሃቁ ግን በነብስ ግድያ ከፍተኛ ሚና የነበራቸዉ “ደም የጠማቸዉ” ታጋዮች እንደነበሩ በቦታዉ የነበሩ የዓይን ምስክሮች እና ማስረጃዎች ሁሉ ማንነታቸዉ ይገልጻሉ። የካቲት የካቲት በማለት አስክንደኖቁር በያመቱ የሚዋሹት የወያኔ መሪዎች ራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉ ወደ ዉጭ አገር በመላክ የዘመኑ ዕዉቀት እንዲገበዩ ሲያደርጉ፤ ከገበሬዉ ጉያ ነጥቀዉ ለሥልጣናቸዉ ማቀጣጠያ ማገዶ እንዳደረጉዋቸዉ የትግራይ ገበሬ የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ። -ለዚህም ነበር “የህወሓት መሪዎች ሲወዱህ በግ አርደዉ ያበሉሃል ሲጠሉህ ደግሞ እንደ በግ አርደዉ ያበሉሃል!” በማለት የወያኔ ነብሰበላነት የገለጸዉ። ለማንኛዉም ወደ መጽሃፉ አንግባ። ሰዉ እንደ ሎሚ ጨምቀዉ መጣል (ሰዉን በሆዱ በሬን በጭዱ መቅጣት) ከላይ የተጠቀሰዉ የወያኔ ዓይነተኛ መለያ ባህሪ ነዉ። የአንድን መሪ ወይንም መንግሥት መመዘኛ በወገኑ ላይ ያለዉ አክብሮትና በሃገሩ ላይ ያለዉ ፍቅር ነዉ።የህወሓት መሪዎች ግን ርህራሄ የሌላቸዉ የጫካ አራዊቶች ናቸዉ። የሰዉ ልጅ ህይወትና ደም እንደመሳሪያ መጠቀምና ወደ ስልጣን መሸጋገሪያ ማድረግ የለመዱ ናቸዉ። ሰዉ ሲሰቃይ ሲንከራተት፤ ሲቸገር የሞትና ሲታሰር ሲያዩ እንደ “ሳዲስቶች” የአእምሮ እርካታ የሚያገኙ እሰየዉ የሚሉ በንጹሃን ደም የሰከሩ የቀን ጅቦች ናቸዉ። በአደባባይ በገሃድ ሲዋሹ ሲያምታቱ ሲሰርቁና ሲያታግሉ ሕዝቡ ይታዘበናል አይሉም። ሲዋሹ ትላንት ምን እያልን ነበር? ዛሬስ ምን እያልን ነዉ? ነገስ ሰዉ ምን ይለናል አይሉም። በሕዝብ ፊት ሲያጭበረብሩ እንደማንኛዉም ሰዉ ነገ የምታልፍ ሕይወት ያላቸዉም አይመስላቸዉም። መሪዎቹ ስነምግባር የሌላቸዉ በሕግ በባህል በታሪክና በሃይማኖት የማይገዙ ጉግ ምንጉጎች ናቸዉ። በትግራይ ህዝብ በተለይም በገበሬዉ አካባቢ ከሚጠሉበት ምክንያት አንዱ መጥፎ ባህሪያቸዉ በሃገር ሉአላዊነት ላይ የፈጸሙትን ክሕደት ብቻ አይደለም። የትግራይን ሕዝብ በተለይም የዋሁ ገበሬዉ ለስልጣናቸዉ መቆናጠጫ መሳለልና መረማመጃ አድርገዉ ደሙንና ጉልበቱን ከተጠቀሙበት በሗላ እንደ ሎሚ ጨምቀዉ መጣላቸዉን ነዉ። ለምሳሌ የህወሓት ታጋዮች 90 ከመቶ ከአርሶ አደሩ የመጡ ገበሬዎች ናቸዉ። እነዚህ ታጋዮች በግድም በዉድም ለህወሓት መሪዎች ብቻ ሳይሆን ሻዕቢያንም ለስልጣን ያበቁ ናቸዉ። እነ መለስ ዜናዊ አዲስ አባባ ገብተዉ በምኒሊክ ቤተመንግሥት ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በሗላ ግን ጥቂቶች እዚህ ግባ የማይባል ማቋቋሚያና መካካሻ ተሰጥቶአቸዉ ሲሰናበቱ፤ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች ያላንዳች መካካሻ ሳይወዱ በግድ ተባረዋል። ተቃዉሞ ያሳዩትም በተለያየ ቦታ በእስር ቤት ታጉረዉ ይገኛሉ። ብዙዎቹ ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተሰደዋል። የቀሩትም ባዶ እጃቸዉ ወደ ነበሩበት ወደ ግብርና ስራቸዉ ተመልሰዋል። እንደሚታወቀዉ በትግሉ ወላፈን የተለበለበዉ “ፈንጅ ርገጥ” አየተባለ የጠላት ምሽግ የሰበረዉ በየጉራንጉሩ የአሞራ ሲሳይ ሆኖ የቀረዉ በቦምብ ናዳ ቤት ንብረቱ የተቃጠለበት የመከራና የጨለማ ኑሮ ያሳለፈዉ ገበሬዉንና የገበሬዉ ልጅ ነዉ። ከድሉ በሗላ ግን በትረስልጣን ጨብጦ መኪና እንደ ሸሚዝ እየቀ ያየረ የሚዉለዉ ልጆቹ ወደ ፈረንጅ ሀገር እየላከ የሚያስተምረዉ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ ሃገርና መሬት እየቸረቸረ የሚዉለዉ በሰማእታትና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ እንደ እስስት ቀለሙ እየቀያየረ ሕዝብን የሚያጭበረብረዉ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ የሚናገረዉ ሃገርና ወገን ሸያጩ የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ሆዳም ካድሬና አጨብጫቢዉ ፓርላማ ናቸዉ። ይህን የተረዳ የትግራይ አርሶ አደር ነበር ሁኔታዉን በጥቅሉ እንዲህ ሲል “የህወሃት መሪዎች ሲፈልጉህ በግ አርደዉ ይበሉሃል! ሲጠሉህ ደግሞ እንደ በግ አርደዉ ይበሉሃል!” በማለት ቁጭቱን የገለጸዉ። ይህ ማለት የህወሓት መሪዎች በትረ-ስልጣናቸዉ እስከ ሚያደላድሉ ድረስ በስልት በመያዝ እንደመሳልል ወይም እንደኮረቻ መቆናጠጫ አድርገዉ ይጠቀሙቡሃል ከዚያም በሗላ ሲጠሉህ “ሰብብ -አስባብ” እየፈለጉ እንደ ቆሻሻ ዕቃ ይጥሉሃል ማለት ነዉ። ይህ ዓይነት ድርጊትም በገበሬዎቹና በታጋዮቹ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። በተለያዩ የመንግሥት መስርያቤቶች ተቀጥረዉ በሚሰሩ ሲቭል ሰራተኞችም የሚደርሰዉ በደል ተመሳሳይ ነዉ። የህወሓት ኢሕአዴግ አመለካከት እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ተብለዉ በሚጠረጠሩ ሎሌዎች ዜጎች ላይ የደረሰ በደልም ጥቂት አይደለም።ዛሬ በ ኢትዮጵያ በተለይም በመንግሥት መሥርያቤቶች አካባቢ ለነገ ብሎ የሚያስብ የለም። ምክንያቱም ለነገ ብሎ የሚያስብ መንግሥትና መሪ ስለሌለ ነዉ። ይህን ሁሉ ጉድ የታዘበ አንድ የጎጃም ገበሬ ስለ ስርዓቱ ያለዉን አስተያያት ሲገልጽ ”የጅብ ገበሬ! ያህያ በሬ! የዝንጀሮ ጎልጓይ! የጦጣ ዘር አቀባይ! አንድም የላቸዉ ሁሉም አንብላ ፤እንብላ ባይ! በማለት ቁጭቱን እና ጥላቻዉን ይገልጻል። ዛሬ በኢትዮጵያ ዉስጥ አብዛኛዉ የመንግሥት ሠራተኞ የህወሓት መሪዎች ሃሳብ ፈልገዉ ዛሬ ነገ ሊያባሩረኝ ይችላሉ ብሎ የሚሰጋ ነዉ። ከዚሁ በመነሳትም ለራሱ በፈርሃትና በስጋት ላይ ያለ ሠራተኛ ስለመጪዉ የሃገር ዕድገትና ስለተተኪዉ ትዉልድ ማሰብና መተንበይ አይችልም። የሃገራችን የወደፊት ዕድል አስጊና በአደጋ ላይ ያለ ሁኔታ ነዉ የምንልበት ምክንያትም አንዱ ባህሪ ከግንባታዉ ይልቅ የማፍረስ ሁኔታዉ ሚዛኑ ስለሚያይል ነዉ።” (ታጋይ ገሠሠ እንግዳ ገጽ 170-173) በየአመቱ በየካቲት ወር በሕዝብ ልጆች ደም” የፖለቲካ ቁማር” እየተጫወቱበት ያሉት የወያኔ መሪዎች እና አዳማቂ ካድሬ ሎሌዎቻቸዉ የፌዝ ጊዜያቸዉ ሲያበቃ ፋሽስቶቹ የወያኔ ነብሰገዳዮች ወደዉ ሳይወዱ “አንድ ቀን” በሕግ ፊት ቀርበዉ በቤተሰቦቻችን እና በሕዝብ ላይ የቀለዱበትን የንጸሃን ደም መልስ ይሰጡበታል። “ዘይወግሕ መሲሉዋስ ኣብ ቡኹራ ታሓርእ”! ክወግሕ እዩ! http://www.ethiopiansemay.blogspot.com

No comments: