የኢሕአደግ እና የህወሓት መሪዎች ጥምር አፈና
በሰብአዊ ተሟጋች ድርጅቶች እይታ
ከጀሚላ ብደልቃድር
(ጥር 6/2001)
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከረጂም ጊዜ ጀምሮ አመታት ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን ባደረጉት መራራ ትግል በቁርጥ ቀን ዜጎች ደም ሃገራዊ ህልዉናዋ ለዘመናት ተጠብቆና ተከብሮ የኖረች አገር ብትሆንም እንኳን ከራሷ በፈለቁ ለሃገርና ለወገን ስቃይና እንግልት ደንታ ቢስ በሌላቸዉ ጨቋኞችና አስተዳደራዊ ስርአትን ባልተላበሱ መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ዛሬም እየደማች እና እየቆሰለች ትገኛለች።
ዜጎች በሃገራቸዉ ማህበራዊ ኑሮአቸዉን በሰላማ መንገድ የመምራት፤ የዜግነት መብታቸዉን የመጠበቅ፣የማክበር፣የመምርጥ፣በነጻ የመንቀሳቀስ መብቶቻቸዉ በግፈኛ ገዢዎች መዳፍ ስር ታፍኖ ኑሮአቸዉን በስቃይ እና በፍርሃት ተሸብበዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜታቸዉ ተገፎ በመኖርና በሞት ጣር ዉስጥ ተዘፍቀዋል። የኢህአዴግ መንግስት በዉጭ ያለዉን ዲፕሎማሲያዊና ግንኙነቱንና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎችና በምዕራባዉያኑ ያለዉን ጥቅማ ጥቅሞች ለማስከበር ደፋ ቀና አያለ የዲሞክራሲንና የሰብአዊ መብቶችን እንደሚአከብርና የዜጎችን መብትና ነጻ እንቅስቃሴ እንደሚአከብር ራሱ ባዘጋጃቸዉ ሚዲያዎች ሁለተኛ ፕሮፖጋንዳዉንና የአስመሳይነት ባሕሪዉን ቢያንጸባርቅም እንኳን በድብቅ እና በገሃድ የሚያራምደዉን የአፈና ፣የእስራትና የግድያ ወንጀሎቹ ለአደባባይ በገሃድ ፍንትዉ ብለዉ ወጥተዋል።
በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን የሰብአዊ መብት አካሄድ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እና የሕአዴግ መንግስት በህዝብ በፕሬስ -አፈና፣ እስራት ግድያ፣በጅምላ ጭፍጨፋ፣ በተለያዩ ጊዜዎች ባካሄዳቸዉ ጦርነቶች ዉስጥ የፈጸማቸዉ ልዩ ልዩ የጦርነት ወንጀለኞች እና የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ላይ ያለ አምባገነን መንግስት መሆኑን፡ ዋና ጽ/ቤቱ አሜሪካን አገር የሆነዉ “ፍሪዶም ሃዉስ” በመባል የሚታወቀዉ ዓለም ዓቀፍ የእንባ ጠባቂ ተቋም ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ገልጿል:፡ ስለዲሞክራሲና ስለ ዜጎች መብት የሚለፈልፍልን የኢሕአዴግ/የህወሓትና በእነርሱ ስር የታቀፉ እና የጭቆና ኣላማቸዉን በየክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ የፈለፈሏቸዉ ፖለቲካዊ ስፋን በሰጣቸዉ ፓርቲዎቹ ኢስብአዊ አመራር ተግባራዊ ያደርጋል።
በሌላ በኩል “ሂዩማን ራይትስ ዎች” የተባለ የሰብአዊ መብት ጠበቃ ድርጅት ባወጣዉ የ2008 ኣመታዊ አጠቃላይ ሪፖርቱ ላይ እንደሚያመለክተዉ በተቃዋሚዎችና ትችት ሰንዛሪዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እየተወሰደ ነዉ።የኢትዮጵያ የጦር ሃይሎች የተለያዩ የጦርነት ወንጀሎችን መፈጸሙን የቀጠለ ሲሆን በተለይም በሱማሌ ክልል በኦጋዴን እና እንዲሁም በሶማሊያ በሰፊዉ ታይቷል” ይላል። የኢሕአዴግ መንግስት ለመጪዉ የምርጫ ሂደት ዝግጅት ይመስላል። አገር ዉስጥ ሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎችን ባገኘዉ አጋጣሚና አቅጣጫ እንቅስቃሴአቸዉን በማዳከም እና በሃሰት በመወንጀል ለእስራት በመዳረግ በአገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የፖለቲካ እና የህዝብ እንቅስቃሴ ከሕግ ዉጭ በሆነ አፈና እና ወታደራዊ አፈና በተላበሰ እንቅስቃሴ ይገኛል። የሕአዴግ መሪዎች ካለፈዉ ምርጫ የሕዝቡን ስሜትና የዲሞክራሲ ጥማቱን እና ብሎም ለኢሕአዴግና ተከታዮቹ ያለዉን ጥላቻ የተገነዘቡ ይመስለኛል።
ክፍል 2 በሚቀጥለዉ ጊዜ ይቀርባል። ለዉድ እህቴ ጀሚላ አብደልቃድር ይህንን ወቅታዊና አንገብጋቢ የሰብአዊ ነክ ጉዳዮችን በመላክዋ በ እኔ እና በአንባቢዎች ስም አመሰግናለሁ።
No comments:
Post a Comment