ዉሉ የጠፋ ጭንቅ ያለ ነገር!
ከጌታቸዉ ረዳ
በሕዳር-ታሕሳስ 2000 ዓ/ም ደሃይ የተባለዉ መቀሌ ከተማ የሚታተመዉ የትግርኛ መጽሄት አቶ ገብሩ አስራትን ለቃለ መጠይቅ አቅርቦ ነበር።ቃለ መጠይቁ አመት ቢሆነዉም፤ ዛሬ ላቀርብላችሁ የፈለግኩበት ምክንያት “በቅንጅት ነበር” (ኤክስ ቅንጅቶች ልብል?) ዛሬ ተለያዩ የድርጅት ስሞች በመያዝ የምናደምታቸዉ ድርጅቶች እና ድረገጾቻቸዉ/ጋዜጦቻቸዉ እና ደጋፊዎቻቸዉ ስለ አቶ ገብሩ አስራት፤ አና “የትግራይ ህዝብና የትምክህተኞች ሴራ ከትናንት እስከ ዛሬ” የሚለዉ ዘረኛ “ጸረ አማራ” እና “ጸረ ሸዋ” “ጸረ-ምኒልክ” መጽሃፍ “አማካሪ” (ገምቢ ሃሳብ ይለዋል ደራሲዉ መምህር ገ/ኪዳን ደስታ) የነበረዉ ጠበቃ ነን ባዩ “ብርሃኑ አባዲ” እና “ድያብሎስ/መላከሞት” በመባል በተሃሕት እስረኞች የሞታወቀዉ ነብሰ ገዳዩ “አዉዓሎም ወልዱ/ትኩዕ ወልዱ” የሚመራዉ የዓረና ፓርቲ በቅርቡ ያዘጋጀዉ ስብሰባ ሰፊ ዘገባ የዘገቡላቸዉ “ድሮ ቅንጅት” አባሎች እና ደጋፊ ድረገጾቻቸዉ ስላስነበቡን፦ እኔም በመገርም “እነኚህ ቅንጅቶች” ነበርን የሚሉት የዓረና አወዳሾች ፤እዉን አቶ ገብሩ አስራት ስለነሱ /ስለ “ነበር ቅንጅቶች” አቃሉ? የሚል ጥያቄ ስለቻረብኝ ፤አቶ ገብሩ አምና የሰጠዉ ትግርና ቃለ መጠይቅ ተርጉሜ ለ አማርኛ አንባቢ ላቅርብ እና ሃሳቦች ቢንሸራሸሩ በማለት አቅርቤአለሁ። አነሆ፦
ደሃይ-መጽት-
ቅንጅት ተከተለዉ የምርጫ ሰትራቴጂ ብዙ ቅሬታ ፈጥሯል። በ ተለይም በትግሬዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስንቷል።(ቅንጅት) ዘር መሰረት ያደረገ (ቅስቀሳ) ስለነበር እነሱ (ቅንጅት) በጠሩት ሰለማዊ ሰልፍ ተገኝዉ በመስቀል አደባባይ ወጥተዉ ንገግር በማድረግዎ በትግሬዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል። ለምንድ ነዉ ራስዎን በዛ ሁኔታ ሊከቱ የፈቀዱት? በዚህ ያለዎት አስተያየት ካለ?
ገብሩ አስራት (መልስ)፦
ይህ ጉዳይ ስናነሳ መሰረተ ሃሳቡን ከመሰረቱ ካላየነዉ ችግር ነዉ። ይህነን በሚመለከት አንድ ነገር ማለት የምችለዉ፤ መስቀል አደባባይ የተደረገ ሕዝባዊ ጥሪ (በገብሩ ቃል (“የፖለቲካ ስብሰባ”) ነበር። ጥሪዉም በቅንጅት ብቻ የተጠራ ስብሰባ አልነበረም። ሕብርት የተባሉት አሁን ፓርላማ ዉስጥ ያሉት ፓርቲዎችም ነበሩበት። ቅንጅትም እነዚህ ሁሉ በጠሩት ስብሰባ እንዱ አካል ነበር። እነዚህ ሁሉ በተሳተፉበት እኔ አንዴት በእነሱ ጥሪ ለመገኘት እንደቻልኩ ማንሳቱ አስፈላጊ ነዉ።
በወቅቱ የነበሩት ሁኔታዎች ማንሳቱንም አስፈላጊ ነዉ። በወቅቱ ገዢዉ ፓረቲ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አሳልፎ የሰጠ ባለ አምስት ነጥብ የተባለ የዉሳኔ ሃሳብ አስተላልፎ ነበር። ዉሳኔዉ በወቅቱም ሆነ ዛሬ የኢትዮጵያ ጥቅም አያስጠብቅም የሚል አቋም አለኝ።
ይህ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ዉሳኔዉ የአገርን ጥቅም አሳልፎ ለጠላት የሚሰጥ “ያገር ክህደት” ነዉ (ገብሩ ተጠቀመበት ቃል “ስህተት ነዉ” የሚል ቃል ነዉ) ብለዉ ተቃወሙ። እዚህ ላይ እኔ የምነሳበት ማአዝን ሌላ ሊሆን ይችላል፤ እነሱ ሚነሱበት ማአዝን ደግሞ ሌላ ሊሆን ይችላል። የተላያዩ መነሻዎችዎች አሉን። መነሻዎቻችን የተለያዩ ቢሆኑም ከፖለቲካ ፓርቲ የላቀ የጋራ መሰረታዊ ጥያቄ ነክ ነዉ። በገዢዉ ፓርቲ የአገር ጠቀሜታም ሆነ የሉዓላዊነት ክብር አሳልፎ ለኤርትራም ይሁን ለሌላ ክፍል የሚሰጥ ዉሳኔ ሲወሰን ተቃዉሞ ማሰማቴ እንደ ዜጋ ግዴታ አለብኝ። የዜግነት ግዴታየ ለማሰማት ጥሬየን/ተቃዉሞየን በ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ፤በኢትዮጵያ ቴሌቭዢን ፤በድምጺ ወያነ ቢተላለፍልኝ እና እነኚህ የገዢዉን መድብ መገናኛዎች ስሞታየን ለማሰማት ክፍት ቢኖሩ ኖሮ ወደ ቅንጅት ስብሰባ አልሄድም ነበር። ተቃዉሞየን ለማሰማት ዕድሉ ስላገኘሁ መግለጽ ነበረብኝ። ስለዚህም ጥሪ ሲአስተላልፉልን ዶ/ር ነጋሶም ተገኝተዉ ነበር።
ለሕዝቡ አስተያየታችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ ተባልን፡ የተሰበሰብነዉ ከቅንጅት ጋር ለመነጋገር አይደልም ስበሰባዉና ጥሪዉ ለተሰበሰበዉ ህዝብ እና ብሎም ለመላ ኢትዮጵያ ነዉ። ስለዚህ ስበሰባዉ ከሕዝብ አንጂ ከቅንጅት ጋር አልነበረም። እናም ባገኘነዉ መድረክ በኩል ታፍኖ የቆየዉን አስተያየቴን ለመግለጽ ያገኘሁትን የመድረክ ዕድል ያ ብቻ ስለነበር ስብሰባዉ ላይ ተገንቼ መግለጽ ነበረብኝ። እንዲያ በማድረጌ ስህተት ነበር ብየ አሁንም አላምንም።
ግን ቅንጅትም እኮ በወቅቱ በሕግ ተመዝግቦ ሕጋዊነቱ አግኝቶ ከኢሕአዴግ ጋር ሲሰራ የነበረ ፓርቲ ነዉ።
የሗላ ሗላ የምርጫዉ ሙቀት እየበረታ ሲሄድ ኢሕአዴግ “ቅንጅትን” እንደ “ጋኔን” አድርጎ አየዉ። ቅንጅትም በበኩሉ ኢሕአዴግን እንደ ሰይጣን ቆጠረዉ ከኢሕአዴግም አልፎ “የትግራይን ሕዝብ” እንደ “ጋኔን” አየዉ።
ይህ ከተፈጠረ ቧሓላ ( ቅንጅት የትግራይን ሕዝብ እንደ “ጋኔል/ዲያብሎስ” ከቆጠረዉ በሗላ የቅንጅቶችን ሃሳብ መደግፍ አልችልም። በመሰረቱ እንኳን እኔ አንድ ታጋይ ቀርቶ ማንም ዜጋም ሊደግፈዉ አይገባም።የትግራይ ሕዝብ እና ህወሓት የተለያዩ ናቸዉ።
ፓርቲዉን እንዳሻቸዉ ሊሰድቡት ይችላሉ ፤የትግራይ ህዝብ ግን “ሕዝብ ነዉ” ቅንጅቶች ሕዝብን መንካት የለባቸዉም። የቅንጅት ትልቁ ስሕተት ፓርቲዉን/ወያኔን እና ሕዘቡ የተለያዩ እንደመሆናቸዉ መጠን ፓርቲ እና ሕዝቡ ለይቶ ማየት ባለመቻሉ ነዉ። ቅንጅት በትግራይ ሕዝብ ላይ የወሰደዉ አመለካከት ያኔም አሁንም/ዛሬም የምቃወመዉ ጉዳይ ነዉ። መድረኩ ላኢ ሃሳቤን ለሕዝብ ለማስተላለፍ በእንግዳነት ሲተሩኝ፤ ያ መድረክ እነደዚአ አልነበረም።የሗላ ሗላ ቅንጅት ያሳየዉ አቋም እና ያ መድረክ ለየብቻ ነበሩ። ያገር ጉዳይ በመሆኑ መድረኩ ፓርላማ ያሳለፈዉ ዉሳኔ ስህተተኛ ዉሳኔ መሆኑን ተቃወመ። ያችን መድረክ ለመኮነን ሲባል (ገብሩ) ቅንጅት ነዉ ተባለ። ይህ የድክምት ምልክት ነዉ።አኔ አስተላለፍኩት ጥሪ ያነበብኩት ጽሁፍ ዛሬም
በእጄ ይገኛል። የኤርትራ ነጻነት አልተቃወምኩም። የኤርትራ ነጻነት በመሰረቱ አምነንበት የሄደ/ያለቀ ጉዳይ ነዉ።ኤርትራ በተለይም ሻዕብያ በግዛታችን ጦርነት እንዳወጀብን ጦርነቱን መመከት ነበረብን። ዛሬም ከነሱ ጋር መለሳለስ መለማመጥ የለብንም። የሚል መስመር ነበር ያስተጋባሁት።
እንግዲህ ይህችን ስላልኩ ከትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች ጋር ተሰልፏል፡ የትግራይን ሕዝብ ከሚያንቋሽሹ ቡድኖች ጋር ተሳትፏል ተባልኩ። ይህ ፕሮፖጋንዳ እና ስም የማጥፋት ዘመቻ ነዉ የምለዉ። ለወደፊቱም ቅንጅት እና እኔ በሚመለከት ምንም ድርጅታዊም ፖለቲካዊም ትስስር የለኝም። በዚህ ጉዳይ የምለዉ ካለ እንግዲህ ለመጨረሻ ጊዜ የምሰጠዉ መልስ ይሄ ይሆናል።ለትግራይ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሃሳቤን ለመግለጽ መድረኩ ሲዘጋብኝ መድረኩ ወደ ሕዝብ ማስተላለፍ የሚቸል መድረክ አስከ ሆነ ድረስ የተገኘን መድረክ ተጠቅሞ ሃሳብን ማስተላለፍ ተገቢ ነዉ እላለሁ።
ደሃይ፦ይቅርታም እኮ ጠይቀዋል?
አቶ ገብሩ፦
አዎ። ይሄ የይቅርታ ጥያቄ ምን መሰለህ፦ያም ሁሉ በሚገባ መታየት ያለበት ይመስለኛል። በኤርትራ እና በኢትዮጵያ የነበረዉ ጉዳይ አያያዛችን የተሳሳተ አያያዝ ነበረን።ለዛም ነበር ይቅርታ የጠየቅነዉ።በዛ ስበሰባ ብቻ ሳይሆን ከዛ በፊትም በጽሁፍ ያተምናቸዉ ጽሁፎች ሁሉ ሳይቀሩ የገለጽነዉ ጉዳይ ነዉ።
አንድ ከፓርቲዉ ጋር ያጣላን አንደኛዉ ምክንያት’ኮ ኤርትራ የ ኢትዮጵያ ሃብት እየመዘበረች ተገቢዉ እና ህጋዊ ቁጥጥር አላደረግንበትም፡ በ ኢትዮጵያ ዉስጥ የራሷ (የኤርትራ) የጸጥታ ቡድን ባገሪቱ ላይ ቅርንቻፎቹን በማደራጀት አሰማርቶ ያሻቸዉን ሰዉ ሲገድሉ አላቆምናቸዉም።ተገቢ ቁጥጥር አላደረግንባቸዉም። ኢትዮጵያዉያን በኤርትራ ምድር መብታቸዉ ሳያከበርላቸዉ እኛ እዚህ የነሱን መብት እናከብር ነበር። ያዉም የኤርትራዉያንን መብት እንዲከበር እናደርግ ነበር።ኢትዮጵአዉያን መብት የሚባል ማንኛዉም ነገር አልተጠበቀላቸዉም ነበር።ጦር ሰብቆ ሲወረንም የኛ ቸልተኝነት እና እንዝህላልነት ነበር።70 ሚልዮን ሕዝብ ሲወረር የሚሳፍር ጉዳይ ነዉ።አልተዘጋጀንበትም ነበር። ስለዚህ ኢህ ሁሉ ሆኖ ድርጅታችን/ፓርቲያችን በፈጸመዉ ጥፋት ብዙ ጉዳት ደርሷል።እዛዉ በፓርቲዉ ዉስጥ እያለን የፈጸምናቸዉ/የተከሰቱ ችግሮች ለኢትዮጵያ ሕዝብ “የራስ ነቀፌታ” (ሰልፍ ክርትሲዝም) አድርገን ይቅርታ እንጠይቀዉ ፤ ..ድክመታችሁ አርማችሁ ቀጥሉ ካለን ድክመቶቻችነን አርምን ተጠናክረን እንቀጥላልን ..የለም..ዉረዱ ፣ካለን ደግሞ ከስልጣን እንወርዳለን (እንለቃለን) የሚል ነበር፤ ከመጀመሪያዉም ከመነሻዉ ወደ ፓርቲዉ ያቀረብነዉ (አጀንዳ)። ይህ (ጉዳይ) ነበር “ጸረ-ዲሞክራሲ” ነዉ ተብሎ፤ “በራሱ-መሪት” ከማየት ይልቅ ወደ ሌላ አካል/ክፍል ጉዳዩን ተወስዶ ተድበስብሶ እንዲቀር ሆነ።
ስለዚህ ይህ ይቅርታ ሊጠየቅበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ። ለትግራይ ሕዝብ በዚህ ጉዳይ እዚህ ስተት ፈጽመናል ነዉ ያልኩት እንጂ “የኤርትራን ነጻነት በሚመለከት ስሕተት ነዉ ብየ አላቀረብኩም።ወይንም ደግሞ የይቅርታ ጥያቄዉ የቀረበዉ ለቅንጅት ወይንም ለአንድ ለተወሰነ ፓርቲ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀረበ ይቅርታ ነዉ። አሁንም ደጋግሜ ምለዉ ነገር ትላልቅ መሰረታዊ ስህተቶች ተፈጽመዋል። እነዚህን አፍነህ መጓዝ በታሪክ የሚያስወቅስ እና የሚያስከስስ ነዉ። ህወሓት አስካሁን ድረስ ይህን (ይቅርታ) አልጠየቀም።//-//
ለዚህ ቅንጅቶች ምን ይላሉ? እዉን አቶ ገብሩ ለትግራይ ሕዝብ እየነገረን እንዳለዉ ከሆነ “ቅንጅት የትግራይን ሕዝብ እንደ ዲያብሎስ/ጋኔል/” ተምልክቶታል? እንጅቶች የአቶ ገብሩ አስራት አባባል ‘የዉሸት ዉንጀላ” ነዉ የሚሉ ከሆነ “ለምን የድሮ የቅንጅት አባሎች (ዉጭ አሉት የእነ አንዳርጋቸዉ እና የነ ብርሃኑ ነጋ) ተከታዮች አቶ ገብሩን በጤናማ የድርጅት መሪ እና የቅንጅት ወዳጅ አድረጎ ወሰዳቸዉ”? ይህስ ከሆነ ለምን የህዋ
ሰሌዳዎቻቸዉ/ድረገጾች እና ጋዜጦች ስለ አቶ ገብሩ እና “ዓረና ድርጅታቸዉ” ሰፊ የሆነ ጤናማ ድጋፍ እና ዘገባ እየሰጡ ይገኛሉ? እኔ “ጥያቄዉን እንደ ጥያቄ” ያቀረብኩት “ቅንጅቶች” ይህ የአቶ ገብሩ አባባል “ያዉቁት ኖሮዋል”? የሚል ጥያቄ ስለጫረብኝ ነዉ።
ካላወቁ አሁን ይወቁት እና “ቅንጅቶች- የነ ብርሃኑ ነጋ፤እዮኤል ወዘተ… እና ደጋፊዎቻቸዉ) በዚህ ያላቸዉን አቋም እንዲያሳዉቁን እየጠቆምን -በዚህ መልስ ካላገኘን ወይንም አቶ ገብሩ እና ድርጅታቸዉ “ከቅንጅቶች- እነ ብርሃኑ ..አንዳርጋቸዉ. ብረቱካን.ወዘተ የመሳሰሉ ያሉበት የተላያዩ ድርጅቶች ድጋፍ ከተሰጣቸዉ “በአበባሉ ግራ የተጋባነዉ” ከትግራይ ክፍለሃገር የመጣነዉ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች” እዉነተኛዉ ማን ነዉ? “ቅንጅት የትግራይን ሕዝብ እንደ ዲያብሎስ/ጋኔል/” ተምልክቶታል?
Saturday, February 7, 2009
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment