Saturday, November 29, 2008

የኢሳያስ አፈወረቅ የባሕር ላይ ዉንብድና ተግባር

               የኢሳያስ አፈወረቅ የባሕር ላይ ዉንብድና ተግባር ያጋለጠዉ ሰነድ

ጌታቸዉ ረዳ

ከላይ የሚታየዉ ፎቶግራፍ እና የዚህ ጽሑፍ ርዕስ የቀረበዉ ከእኔው ከተርጓሚዉ www.Ethiopiansemay.blogspot.com ነዉ።ይህ ጽሑፍ ካነበቡ በሗላ ከወደቀኝ በኩል የተለጠፈዉ የባሕር ጠለፋ ዉምብድና የሚያሳይ ቪዲዮ መመልከቱን አይርሱ። በዚህ ወር በተከታታይ እየተረጎምኩ ለናንተ እያዘጋጀሁት ያለሁን በቅርቡ ይፋ ሆኖ በተከታታይ ለትግርኛ አንባቢዎች በትግርኛ የተጻፈ ልዩ ልዩ ሚስጢራዊ ሰነዶችን በኤርትራዊዉ በአቶ ዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ ጸሓፊነት ይፋ እየሆኑ ያለዉትን ሚስጢራዊ ሰኖዶችን አንዳንዶቹ ባለፉት ዕትሞች በብሔራዊ ቋንቋችን ለአማርኛ እንባቢዎች እንዲነበብ አድርጌአለሁ። ጸሓፊዉ Saturday, 22 November 2008 http://asena-online.com/ በተባለዉ የኤርትራ የህዋ ሰሌዳ በዛሬዉ ክፍል 5 ይፋ ያደረጉት ሚስጢራዊ ሰነድ “ዕቅዳችን መጪዉን አስፈሪዉ ዳማና መበተን ነዉ!!!” በሚለዉ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን አገሮች “ኔቶ” ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ፋን ቤንጃንጉዝ ከተናገሩት ርዕስ በመነሳት የቀይ ባሕር አካባቢ ኤርትራ እና ሶማሊያ እንዲሁም አጎራባች አገሮችን አስመልክቶ የሚታዩት ዉጥረቶችና መጪ ሁኔታዎችን አስመልክቶ አሜሪካ ዓይኖቿን በአካባቢዉ የባሕር ቀጠና እያሳረፈችበት ያለችዉን አትኩሮት ይተነትናል። የሰነዱ ትንተና ብዙ ነገሮችን ያካተተ በመሆኑ እኔዉ ራሴ ለአንባቢዎቼ እንደሚመች በሦስት ክፍል በመመደብ (1-) የኢሳያስ አፈወርቅ የባሕር ላይ የዉምብድና ተግባሮች (2-) ሕገ ወጥ መሳሪያዎችን የመሸጥ እና የማስተላለፍ (3-) የኑክሌር አተላ በኤርትራ ዉሃዎች እንዲጣል የመፍቀዱ ሁኔታ የሚመለከቱትን ከፍየ የየራሳቸዉ ርዕስ ጠብቀዉ እንዲነበቡ በተለያዩ ገጾች የተበታተኑት ጉዳዮች እየለቀምኩ በ አንድነት እንዲነበቡ አጠናቅሬዋለሁ። በርዕስ ብከፍለዉም የትርጉሙ ይዘት አልተቀየረም። ከሦስቱ ርዕሶች ቅደም ተከተል ከቀረቡ በሗላ ዝምበባዌ ድረስ በመጓዝ በኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም የነብስ ግድያ የተሳተፈዉ “መቐለ” በመባል የሚታወቀዉ ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ ጎይተኦም ማን መሆኑን እና በነዚህ በሚጠቀሱት የዉምብድና ስራዎች ምን ሚና እንደነበረዉ በሰፊዉ ይብራራል።
መልካም ንባብ፦
-1-የባሕር ዉንብድናዉ የመርከቦች ጠለፋ
“… ዛካሮቭ የተባለዉ ሩስያዊ ባለንብረት የሆነችዉ 140 ቶን ክብደት ያላት መሳርያዎች የጫነች የጭነት አይሮፕላን በJuly 26/2007 በኤርትራዊዉ ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ ጎይተኦም (መቐለ) አጃቢነት ሶማሌ ዉስጥ የማራገፉን ሁኔታ እና በማስከተልም የአካባቢዉ ዉጥረት የመጨመሩ አሳሳቢነት በሚመለከት የአሜሪካ ፕረዚዳንት ጆርጅ ቡሽ እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ የሽብር ቡድኖችን ክትትል በሚመለከት የጋራ ስምምነት ለመፈራረም ያበቃቸዉ ሁኔታ የታወሳል። በተከታታይ በዳሂር አወይስ ሲመራ የነበረዉ የሶማሌዉ የእስላሞች ሕብርት የሽግግር መንግሥት በተቀናቃኞቹ ከተፈነቀለ በሗላ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከኤርትራ መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመመስረት መጠለያ ተሰጠዉ። የሶማሊያዉ ዳሂር አወይስ ከኤርትራ ጋር የጠበቀ ግንኙነት የጀመረዉ ግንኙነቱ የቆየ ሲሆን፡ መጠለያ ተስጥቶት የኤርትራ እንግዳ በመሆን ወዳጅነት የመሰረተዉ በቅረብ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሶማሌ ገና በ1994 በጎሳ ነገሥታት ስትታመስ ጀምሮ ወደ አሥመራ በመመላለስ ብርጋዴር ጀኔራል አብርሃ ካሳ በወቅቱ ሐማሴን ሆቴል እና አምባሴራ ሆቴልን ስያስተዳድር ለነበረዉ ለኮሎኔል ሰሎሞን አብርሃ በአደራነት ተሰጥቶት የክብር እንግዳ እንክብካቤ እንዲደረግለት መመሪያ ተላልፎ በክብር ይስተናገድ እነደነበረ እና ዛሬም አስፈላጊዉ የክብር እንክብካቤ እየተደረገለት በኤርትራ እንደተጠለለ ይታወቃል። ግንኙነቱ እየጠነከረ የአካባቢዉ ሁኔታ እየተለወጠ ሲሄድ በSeptember 2008 የአዉሮጳ ሕብርት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ስብሰባም በአፍሪቃ ቀንድ እየታየ ያለዉ አሳሳቢ ክስተት ካገናዘበ በሗላ ወታደራዊ ክንዋኔዎችን ለማካሄድ የሚያስችለዉን ዕቅድ አጸደቀ። ቀጥሎም በተመሳሳይ መንገድ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አድሚራል ፊሊፕ ግሪን ከየመን ጋር የባሕር ላይ ዉንብድና ለመግታት አሕጉራዊ የመተላለፊያ የቀ ይ ባሕር ቀጠናዎች ጸጥታን ለመቆጣጠር እንዲያመች ወታደራዊ የጋራ ትብብርን በሚመለከት ዉይይት ተደረገ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ አሜሪካ አንዲት መርከብ የተጠለፈች መሆኗን ካሳወቀች በሗላ፤ ወደ ኤርትራ የዉሃ መስመር በመቅዘፍ ተሰወረችዉ ነብረትነትዋ የኢራን የሆነች መርከብ ለመከታተል ወደ ኤርትራ የዉሃ መስመር የመግቢያ ፈቃድ ለማግኘት መርከቧን ለጠለፏት ሽፍቶች $7 ሚኒሊዮን ዶላር እንደከፈለ የተለያዩ ጋዜጦች አስተጋቡ ። አሜሪካ $7ሚሊዮን ዶላር ትክፈል እንጂ በተዘዋዋሪ መንገድ ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ጀምሮ የአካባቢዉ ጸጥታ በብቸኝነትና በበላይነት ለመቆጣጠር የነበራትን ጥም በደረግ ጊዜ አጥታዉ የነበረዉን ዕድል ከሰሜን አትላንቲክ ኔቶ ጋር ሃይሏን በማዋሃድ ወደ ቀይ ባሕር ቀጠና በማዝገም፡”የጥቁር ዳማና ጠረጋ ዘመቻ” ለማድረግ የተጠናከረ እንቅስቃሴ ለማድረግ ዕድሉን አገኘች። ሩሲያም በበኩሏ ከሴፕተምበር 2008 መጨረሻ ገደማ ጀምሮ በሶማሊያ የባሕር ደንደሶች ተዋጊ መርከቦቿን ለማንቀሳቀስ ዝግጁ እንደሆነች’ና ሲያስፈልግም ተዋጊ መረከቦቿም ስራ ላይ እንደሚዉሉ በተጓዳኝ አስታወቀች። ይበልጥ መስህቡ እየጎላ ሲሄድ M.V.Faina የተባለች መረከብ ከጠለፈች በሗላ የት እንደምታርፍ በቅጡ ያልታወቀ ታንክ እና ወታደራዊ ዕቃዎችን ጭና ስትጓዝ የነበረችዉ ንብረትነትዋ ይኩረይን የሆነች በሗላ ላይ በSeptember 28/2007 በኤርትራ ማርሳዎች(ወደቦች) በብርጋዴር ጄኔራል ፍጹም ገብርሕይወት ተረካቢነት የጫነቺዉ መሳሪያ ማራገፏን ከተደረሰበት በሗላ የአትላንቲክ ኔቶ ጦር ወደ ቀይ ባሕር ቀጠና የዉግያ መርከቦችን በመላክ አሰመርቶ ነበር። በወቅቱ የባሕር ሃይሉ አዛዥ የነበረዉ ብርጋዴር ጀኔራል ፍጹም ገ/ሕይወት ነዉ። ከጊዜ በሗላ የኤርትራ የባሕር ሐይል አዛዣነት ስልጣኑን ለመጄር ጄኔራል ሑመድ ካሪካሪ በሕዳር November 18/2007 እንዲለቅ ተደርጓል ። ለስልጣኑ ቅሚያ ምክንያትም ኢሳያስ አፈወረቂ የኒኩሌር አተላ ወደ የኤርትራ የቀይ ባሕር ዉሃዎች እንዲጣል የመፍቀዱን ጉዳይ በመቃወሙ ነዉ። ዛሬ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የባሕር ጠለፋ ዉምበድና እየበረታ መሄዱና ቢያንስ አስከ 61ጊዜ የመርከብ ጠለፋ ሲካሄድ መርከቦቹን ለማስለቀቅ የተከፈለዉ ገንዘብ ወደ 300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚጠጋ ይነገራል። የፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ አስተዳደርም በመርከቦች ጠላፋ እና ከኑክሊየር አተላ መጣያ በሚገኝ ገንዘብ ተግባር ላይ ተጠምዷል። Sirius Star ሳይረስ ስታር ተባለችዉ መርከብ 2ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ጭና ካሳዉዲ ዓረብያ ስትጓዝ ከመጠለፏ በፊት November 14/2008 ወደ 15 አጥቢያ ክዉ ብሎ ጸጥ ባለዉ ሌሊት በ5ፈጣን ጀልባዎች ተሳፍረዉ በጀኔራል ፍጹም ገ/ሕይወት ሸኚነት-ኮሎኔል መሓሪ ደስታ፤ ካፒቴን ያሲን ፈረጅ ካፒቴን ሓሰን ፍካክ የሚመሩት 46 ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቁ የኤርትራ የባሕር ሃይል አባላች አቅጣጫቸዉን ወደ ሕንድ ዉቅያኖስ አዙሮዉ በመቀዝፈ ተጓዙ ። ዕሁድ November 16/2008 በዛዉ ዕለት ንብረትነቷ የአሜሪካ የሆነች US bounder tanker ወደ ደቡባዊ ምስራቅ ሞምባሳ አካባቢ በምትጓዝበት ወቅትም ብርጋዴር ጄነራል ጠዓመ (መቐለ) ከሶማሊያዉ የእስላሞች ሕብረት ግምባር የሽምቅ አባል ኮማንደር አይዘን ሑሴን ከማል ከተባለ ቀደም ብሎ በኢራን የባሕር ሃይል አባል የነበረ በዜግነቱ ኩርድ የሆነ አብሮዉ ከአስመራ ወደ ኬኒያ የጥድፉያ በረራ አድርገዉ ነብር። Syrus Star የተባለች ካሁን በፊት ከተጠለፉት መርከቦች እጀግ ግዙፍ የሆነች መርከብ በሶማሌ ጫፍ በፑትላንድ አካባቢ የመጠለፉ ዜና ሲሰማ፤ነገሩ በፍጥነት እየተባባሰ መሆኑና የነገሩም ዉስብስብነት ይበልጥ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ጠላፊዎቹን እና የዉስብሰቡን ሁኔታ አድኖ የማግኙትን ጉጉት ይበልጥኑ ከፍ ሲያደርገዉ፤”ከበስተጀርባዉ ያለዉ ጥቁር መጋረጃ” እንዲገለጥ በር የሚከፍት መሆኑን የአሜሪካ የማዕከላዊ የስለያ ድርጅት ያምንበታል። በዚህ ትኩረት ላይ የፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ አስተዳደርም በመረከብ ጠለፋ እና ዝርፊያ እንዲሁም ቀይ ባሕርም የመርዘኛ ቆሻሻዎች መጣያ እንዲሆን በማድረግ በዛ የሥራ ትኩረት ተጠምዶ ይታያል። የመርከብ ጠለፋዉ ዉምብድና በጣም በመጧጧፉ በቅርቡ የኮሮሽያ ፤የፊሊፕኖ እና የፓልንድ መርከቦች የባሕር ጠለፋ ሰለለባ ሆነዋል። የጃፓን የቻይና ዘመናዊ አሳ አጥማጅ መርከብ እንደዚሁም ኬሚካል የጫነች የቱርክ መርከብ ስትጠለፍ የኤርትራ ባሕር ሃይል ወዲያ ወዲህ ሲወራጭ ነበር። በወቅቱ ተከታታይ የጠለፋ ክስተት ከታየ በሗላ የአሜሪካ መንግሥት በህዳር (November 2008) ዜጎቿ ብቻ ሳይሆን የአዉሮፓ ዜጎችም ጭምር ወደ ኤርትራ እና ወደ ሶማሌ እንዳይጓዙ ጥብቅ ማሳጠንቀቂያ የሰጠዉ። ተያይዞም በዛዉ ወር በህዳርNovember 19/2008 ደግሞ የአዉሮጳ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች የአሜሪካን መግለጫ በመከተል የሶማሊ እና የኤርትራን ሁኔታ በመገምገም አምባሲዎቻቸዉ በተጠንቀቅ እንዲቆዩ እና ዜጎቻቸዉም ወደ እነዚህ አገሮች እንዳይጓዙ አገደች። ይህንን በመቃወም የኤርትራ መንግሥት የፈረመበትን የተባበሩት መንግሥታት ተስማምተዉ ያጸደቁትን አንቀጽ 36ትን ዉል በማፍረስ በዲፕሎማቶች ላይ ጥበቅ ፍተሻ በማካሄድ ይገኛል። ይህ ክስተት የኔቶ ወታደራዊ ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ቤንጃንኩዝ በOctober 2008 የተናገረዉ “ዕቅዳችን ከወዲሁ እየተጠራቀመ ያለዉን አስፈሪዉ ጥቁር ዳመና መበተን ነዉ!!!” በማለት ያስተጋባዉን ማስገንዘቢያ የ አሜሪካ የባሕር ሃይል ወደ ቀይ ባሕር ዉሃዎች ማዝገሙ አና የአሜሪካ መንግሥት (ኖቨምበር) 11/2008 ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየተናኮሰችዉ ያለዉን አሳት እና በሌላ በኩል በጁቡቲ ላይም የምትጭረዉ የጠላትነት እሳት በመገንዘብ የፈረንሳይ የባሕር ሃይል ጦሮች ወደ ራስ ዳሜራ መገስገሳቸዉ እና ጁቡቲ አካባቢ ያሉት የጀርመን ጦርም በተጠንቀቅ መሆናቸዉን ስንመለከት “ሁኔታዉ ወዴት እያመራ ነዉ?” የሚለዉን የዉጥረቱ ሁኔታ አሳሳቢነት አሁንም እንዳለ ነዉ። የአሜሪካና የአወሮጳ ሕብረት በጣምራ እያካሄዱት ያለዉን ጸረ ሽብር እና የባሕር ላይ ዉንብድና የመከታተል ዘመቻ በመቃወም የኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኖቨምበር 20/2008 የሰጠዉ የቁዋሜ መግለጫዉ ላይ የቀይ ባሕር ዉሃ የኒኩልየር አተላ መጣያ እየሆነ ነዉ በማለት ያወጣዉ መግለጫዉንም ጭምር ድርጊቱ የሚፈጽሙት ወገኖች እነማን እንደሆኑ በስም ሳይገልጽ በደፈናዉ ተሽቀዳድሞ መክሰሱ -አንድ ዓይኗ ሌላዉን ሸዉራራ ዓይን ብላ አስቀድማ የመሳደቧን ጉዳይ “ሳትቀድመኝ ልቅደማት” ዓይነቱ መግለጫ አዉጥቷል። ያካባቢዉ ተነካኪ ሁኔታ ቢነኩት በቀላሉ ሊቀጣጠል የሚችል ዉጥረት በበዛበት ቀጠና ላይ ሆኖ፤ በዉጥረቱ ላይ ገብቶ ባለበት ሁኔታ የድሮዉ የአሜሪካ ፕረዚዳነት ቢል ክሊንተን መንግሥትነቴን ሊገለብጥ ሲያሾር ነበር በማለት የኤርትራ ፕረዚዳንተ ኢሳያስ አፈወረቅ ደጋግሞ የከሰሰዉን ፓርቲ እና የቢል ክሊንተን ባለቤት የሆኑት ዛሬ በኦባማ አዲሱ አተዳደር የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሆኑን ዜና ጋር ተያይዞ የ አካባቢዉ ዉጥረት ወደየት ሊያመራ ይችላል የሚለዉን ጥያቄ ያስነሳል? ከአካባቢዉ ዉጥረት በተጨማሪ የኢራን የባሕር ሃይል ወታደራዊ ባለሞያዎች ወደ ዳህላክ የመግባታቸዉን ጨምሮ የኤርትራ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እንደዚሁም በሕባዊዉ ሠራዊቱና በአዛዦቹ፤የሕግደፍ ዉስጣዊ ዉጥረትና የካቢኔ ሚኒስትሮቹ በሌላ ገጽ ያለዉን ሁኔታ ምን ይመስላል? ይቀጥላል…. ።

የኢሳያስ አፈወረቅ የባሕር ላይ ዉንብድና ተግባር

ግንኙነቱ እየጠነከረ የአካባቢዉ ሁኔታ እየተለወጠ ሲሄድ በSeptember 2008 የአዉሮጳ ሕብርት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ስብሰባም በአፍሪቃ ቀንድ እየታየ ያለዉ አሳሳቢ ክስተት ካገናዘበ በሗላ ወታደራዊ ክንዋኔዎችን ለማካሄድ የሚያስችለዉን ዕቅድ አጸደቀ። ቀጥሎም በተመሳሳይ መንገድ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አድሚራል ፊሊፕ ግሪን ከየመን ጋር የባሕር ላይ ዉንብድና ለመግታት አሕጉራዊ የመተላለፊያ የቀ ይ ባሕር ቀጠናዎች ጸጥታን ለመቆጣጠር እንዲያመች ወታደራዊ የጋራ ትብብርን በሚመለከት ዉይይት ተደረገ።
ይህ በሚሆንበት ጊዜ አሜሪካ አንዲት መርከብ የተጠለፈች መሆኗን ካሳወቀች በሗላ፤ ወደ ኤርትራ የዉሃ መስመር በመቅዘፍ ተሰወረችዉ ነብረትነትዋ የኢራን የሆነች መርከብ ለመከታተል ወደ ኤርትራ የዉሃ መስመር የመግቢያ ፈቃድ ለማግኘት መርከቧን ለጠለፏት ሽፍቶች $7 ሚኒሊዮን ዶላር እንደከፈለ የተለያዩ ጋዜጦች አስተጋቡ ። አሜሪካ $7ሚሊዮን ዶላር ትክፈል እንጂ በተዘዋዋሪ መንገድ ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ጀምሮ የአካባቢዉ ጸጥታ በብቸኝነትና በበላይነት ለመቆጣጠር የነበራትን ጥም በደረግ ጊዜ አጥታዉ የነበረዉን ዕድል ከሰሜን አትላንቲክ ኔቶ ጋር ሃይሏን በማዋሃድ ወደ ቀይ ባሕር ቀጠና በማዝገም፡”የጥቁር ዳማና ጠረጋ ዘመቻ” ለማድረግ የተጠናከረ እንቅስቃሴ ለማድረግ ዕድሉን አገኘች። ሩሲያም በበኩሏ ከሴፕተምበር 2008 መጨረሻ ገደማ ጀምሮ በሶማሊያ የባሕር ደንደሶች ተዋጊ መርከቦቿን ለማንቀሳቀስ ዝግጁ እንደሆነች’ና ሲያስፈልግም ተዋጊ መረከቦቿም ስራ ላይ እንደሚዉሉ በተጓዳኝ አስታወቀች። ይበልጥ መስህቡ እየጎላ ሲሄድ M.V.Faina የተባለች መረከብ ከጠለፈች በሗላ የት እንደምታርፍ በቅጡ ያልታወቀ ታንክ እና ወታደራዊ ዕቃዎችን ጭና ስትጓዝ የነበረችዉ ንብረትነትዋ ይኩረይን የሆነች በሗላ ላይ በSeptember 28/2007 በኤርትራ ማርሳዎች(ወደቦች) በብርጋዴር ጄኔራል ፍጹም ገብርሕይወት ተረካቢነት የጫነቺዉ መሳሪያ ማራገፏን ከተደረሰበት በሗላ የአትላንቲክ ኔቶ ጦር ወደ ቀይ ባሕር ቀጠና የዉግያ መርከቦችን በመላክ አሰመርቶ ነበር። በወቅቱ የባሕር ሃይሉ አዛዥ የነበረዉ ብርጋዴር ጀኔራል ፍጹም ገ/ሕይወት ነዉ። ከጊዜ በሗላ የኤርትራ የባሕር ሐይል አዛዣነት ስልጣኑን ለመጄር ጄኔራል ሑመድ ካሪካሪ በሕዳር November 18/2007 እንዲለቅ ተደርጓል ። ለስልጣኑ ቅሚያ ምክንያትም ኢሳያስ አፈወረቂ የኒኩሌር አተላ ወደ የኤርትራ የቀይ ባሕር ዉሃዎች እንዲጣል የመፍቀዱን ጉዳይ በመቃወሙ ነዉ። ዛሬ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የባሕር ጠለፋ ዉምበድና እየበረታ መሄዱና ቢያንስ አስከ 61ጊዜ የመርከብ ጠለፋ ሲካሄድ መርከቦቹን ለማስለቀቅ የተከፈለዉ ገንዘብ ወደ 300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚጠጋ ይነገራል። የፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ አስተዳደርም በመርከቦች ጠላፋ እና ከኑክሊየር አተላ መጣያ በሚገኝ ገንዘብ ተግባር ላይ ተጠምዷል። Sirius Star ሳይረስ ስታር ተባለችዉ መርከብ 2ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ጭና ካሳዉዲ ዓረብያ ስትጓዝ ከመጠለፏ በፊት November 14/2008 ወደ 15 አጥቢያ ክዉ ብሎ ጸጥ ባለዉ ሌሊት በ5ፈጣን ጀልባዎች ተሳፍረዉ በጀኔራል ፍጹም ገ/ሕይወት ሸኚነት-ኮሎኔል መሓሪ ደስታ፤ ካፒቴን ያሲን ፈረጅ ካፒቴን ሓሰን ፍካክ የሚመሩት 46 ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቁ የኤርትራ የባሕር ሃይል አባላች አቅጣጫቸዉን ወደ ሕንድ ዉቅያኖስ አዙሮዉ በመቀዝፈ ተጓዙ ። ዕሁድ November 16/2008 በዛዉ ዕለት ንብረትነቷ የአሜሪካ የሆነች US bounder tanker ወደ ደቡባዊ ምስራቅ ሞምባሳ አካባቢ በምትጓዝበት ወቅትም ብርጋዴር ጄነራል ጠዓመ (መቐለ) ከሶማሊያዉ የእስላሞች ሕብረት ግምባር የሽምቅ አባል ኮማንደር አይዘን ሑሴን ከማል ከተባለ ቀደም ብሎ በኢራን የባሕር ሃይል አባል የነበረ በዜግነቱ ኩርድ የሆነ አብሮዉ ከአስመራ ወደ ኬኒያ የጥድፉያ በረራ አድርገዉ ነብር። Syrus Star የተባለች ካሁን በፊት ከተጠለፉት መርከቦች እጀግ ግዙፍ የሆነች መርከብ በሶማሌ ጫፍ በፑትላንድ አካባቢ የመጠለፉ ዜና ሲሰማ፤ነገሩ በፍጥነት እየተባባሰ መሆኑና የነገሩም ዉስብስብነት ይበልጥ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ጠላፊዎቹን እና የዉስብሰቡን ሁኔታ አድኖ የማግኙትን ጉጉት ይበልጥኑ ከፍ ሲያደርገዉ፤”ከበስተጀርባዉ ያለዉ ጥቁር መጋረጃ” እንዲገለጥ በር የሚከፍት መሆኑን የአሜሪካ የማዕከላዊ የስለያ ድርጅት ያምንበታል። በዚህ ትኩረት ላይ የፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ አስተዳደርም በመረከብ ጠለፋ እና ዝርፊያ እንዲሁም ቀይ ባሕርም የመርዘኛ ቆሻሻዎች መጣያ እንዲሆን በማድረግ በዛ የሥራ ትኩረት ተጠምዶ ይታያል። የመርከብ ጠለፋዉ ዉምብድና በጣም በመጧጧፉ በቅርቡ የኮሮሽያ ፤የፊሊፕኖ እና የፓልንድ መርከቦች የባሕር ጠለፋ ሰለለባ ሆነዋል። የጃፓን የቻይና ዘመናዊ አሳ አጥማጅ መርከብ እንደዚሁም ኬሚካል የጫነች የቱርክ መርከብ ስትጠለፍ የኤርትራ ባሕር ሃይል ወዲያ ወዲህ ሲወራጭ ነበር። በወቅቱ ተከታታይ የጠለፋ ክስተት ከታየ በሗላ የአሜሪካ መንግሥት በህዳር (November 2008) ዜጎቿ ብቻ ሳይሆን የአዉሮፓ ዜጎችም ጭምር ወደ ኤርትራ እና ወደ ሶማሌ እንዳይጓዙ ጥብቅ ማሳጠንቀቂያ የሰጠዉ። ተያይዞም በዛዉ ወር በህዳርNovember 19/2008 ደግሞ የአዉሮጳ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች የአሜሪካን መግለጫ በመከተል የሶማሊ እና የኤርትራን ሁኔታ በመገምገም አምባሲዎቻቸዉ በተጠንቀቅ እንዲቆዩ እና ዜጎቻቸዉም ወደ እነዚህ አገሮች እንዳይጓዙ አገደች። ይህንን በመቃወም የኤርትራ መንግሥት የፈረመበትን የተባበሩት መንግሥታት ተስማምተዉ ያጸደቁትን አንቀጽ 36ትን ዉል በማፍረስ በዲፕሎማቶች ላይ ጥበቅ ፍተሻ በማካሄድ ይገኛል። ይህ ክስተት የኔቶ ወታደራዊ ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ቤንጃንኩዝ በOctober 2008 የተናገረዉ “ዕቅዳችን ከወዲሁ እየተጠራቀመ ያለዉን አስፈሪዉ ጥቁር ዳመና መበተን ነዉ!!!” በማለት ያስተጋባዉን ማስገንዘቢያ የ አሜሪካ የባሕር ሃይል ወደ ቀይ ባሕር ዉሃዎች ማዝገሙ አና የአሜሪካ መንግሥት (ኖቨምበር) 11/2008 ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየተናኮሰችዉ ያለዉን አሳት እና በሌላ በኩል በጁቡቲ ላይም የምትጭረዉ የጠላትነት እሳት በመገንዘብ የፈረንሳይ የባሕር ሃይል ጦሮች ወደ ራስ ዳሜራ መገስገሳቸዉ እና ጁቡቲ አካባቢ ያሉት የጀርመን ጦርም በተጠንቀቅ መሆናቸዉን ስንመለከት “ሁኔታዉ ወዴት እያመራ ነዉ?” የሚለዉን የዉጥረቱ ሁኔታ አሳሳቢነት አሁንም እንዳለ ነዉ። የአሜሪካና የአወሮጳ ሕብረት በጣምራ እያካሄዱት ያለዉን ጸረ ሽብር እና የባሕር ላይ ዉንብድና የመከታተል ዘመቻ በመቃወም የኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኖቨምበር 20/2008 የሰጠዉ የቁዋሜ መግለጫዉ ላይ የቀይ ባሕር ዉሃ የኒኩልየር አተላ መጣያ እየሆነ ነዉ በማለት ያወጣዉ መግለጫዉንም ጭምር ድርጊቱ የሚፈጽሙት ወገኖች እነማን እንደሆኑ በስም ሳይገልጽ በደፈናዉ ተሽቀዳድሞ መክሰሱ -አንድ ዓይኗ ሌላዉን ሸዉራራ ዓይን ብላ አስቀድማ የመሳደቧን ጉዳይ “ሳትቀድመኝ ልቅደማት” ዓይነቱ መግለጫ አዉጥቷል። ያካባቢዉ ተነካኪ ሁኔታ ቢነኩት በቀላሉ ሊቀጣጠል የሚችል ዉጥረት በበዛበት ቀጠና ላይ ሆኖ፤ በዉጥረቱ ላይ ገብቶ ባለበት ሁኔታ የድሮዉ የአሜሪካ ፕረዚዳነት ቢል ክሊንተን መንግሥትነቴን ሊገለብጥ ሲያሾር ነበር በማለት የኤርትራ ፕረዚዳንተ ኢሳያስ አፈወረቅ ደጋግሞ የከሰሰዉን ፓርቲ እና የቢል ክሊንተን ባለቤት የሆኑት ዛሬ በኦባማ አዲሱ አተዳደር የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሆኑን ዜና ጋር ተያይዞ የ አካባቢዉ ዉጥረት ወደየት ሊያመራ ይችላል የሚለዉን ጥያቄ ያስነሳል? ከአካባቢዉ ዉጥረት በተጨማሪ የኢራን የባሕር ሃይል ወታደራዊ ባለሞያዎች ወደ ዳህላክ የመግባታቸዉን ጨምሮ የኤርትራ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እንደዚሁም በሕባዊዉ ሠራዊቱና በአዛዦቹ፤የሕግደፍ ዉስጣዊ ዉጥረትና የካቢኔ ሚኒስትሮቹ በሌላ ገጽ ያለዉን ሁኔታ ምን ይመስላል? ይቀጥላል…. ።

Friday, November 21, 2008

በሻዕቢያ መሪዎች ትዕዛዝ ለአልማዝ ማዕድን ቁፈራ ከኤርትራ በሰንሰለት የፍጢኝ ታስረዉ ወደ ዛየር ተወስደዉ መረሸናቸዉን ያጋለጠዉ ሰነድ

 በሻዕቢያ መሪዎች ትዕዛዝ ለአልማዝ ማዕድን ቁፈራ
ከኤርትራ በሰንሰለት የፍጢኝ ታስረዉ ወደ ዛየር
ተወስደዉ መረሸናቸዉን ያጋለጠዉ ሰነድ
(ጌታቸዉ ረዳ)
ሰሞኑ የማቀረባቸዉ ጽሑፎች እየተከታተላችሁ እንደሆነ ከጎብኚዎች የቁጥር ብዛት መቁጠሪያ መገንዘብ ችያለሁ። በአንድ ኤርትራዊ ጸሐፊ ይፋ እየሆኑ ያሉት የምስጢር ሰነዶች ባለፈዉ ሰሞን ዋና ዋና ቁም ነገሮቹን እየጠቀስኩ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ አቅርቤአለሁ። ዛሬ ደግሞ በክፍል 2 የቀረበዉ ሰነድ በወያኔዉ መለስ ዜናዊ መንግሥት የሚተዳደረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት መጓጓዣ ተባባሪነት፣ በኤርትራዉ የሻዕቢያዉ መንግሥት መሪ በኢሳያስ አፈወርቅ ትዕዛዝ ለአልማዝ ማዕድን ቁፈራ ከኤርትራ በሰንሰለት የፍጢኝ ታስረዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ማመላለሻ ወደ ኮንጎ ተወስደዉ የቁፈራዉ ሥራ ካጠናቀቁ በሗላ፣ እነኚህ የኢሰፓ አባሎች ነበራችሁ ተብለዉ ተይዘዉ ዕድሜ ይፍታህ በኤርትራ በእስር ሲሰቃዩ የነበሩ የተለያዩ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ አባላት (132 ዜጎች) እና የሻዕቢያ ኢዲሞክራሲያዊ አሰራር በመቃወም የታሰሩ የራሱ ታጋዮች 18 ኤርትራዉያን የመረሸኑ ጉዳይ እና ሌሎች ምስጢሮችን ኤርትራዊ ጸሐፊ “አቶ ዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ” የተባሉ ይፋ ያደረጉትን የምስጢር ሰነድ ባጭሩ ቀንጭቤ ያዘጋጀሁላችሁ ንባብ ቀርቧል። ከላይ የተዘገቡት ፎቶግራፎች በኢትዮጵያን ሰማይ ዌብ ሎግ የተዘጋጁ ናቸዉ።
ኤርትራዉያን ምሁራን የሻዕቢያን የተለያዩ ወንጀሎች በሚገባ እያጋለጡት ሲገኙ፦ አስከ ዛሬ ድረስ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በዓረብ እና በእስላም አገሮች ሴት እህቶቻችነን በጉቦ መልክ ለባዕዳን አገር ፖሊሶች በማቅረብ ተቃዋሚዉን ሲገድሉ/ሲያስገድሉ እና ሲያሳፍሱ እንደነበር ካሁን በፊት በመጠኑም ቢሆን ዘግቤዉ እንደነበረ ቢታወቅም፤ ድርጅቱ ነብሰገዳዮቹን በማሰማራት የሻዕቢያን ተመሳሳይ ድርጊት ይፈጽም እንደነበር የትግራይ ምሁራን ሳያዉቅት ቀርቶ ሳይሆን፡ በጣም አስገራሚ፤አሳፋሪና አስገማች በሆነ ቸልተኝነት ድርጅቱ ሲሰራቸዉ የነበረዉን በትግራይ ሕዝብ ያሳረፈዉ ግፍና በትር፤ እንዲሁም በየዉጭ ሀገሮች የአፈና፤የግድያ እና የሕገ-ወጥ ገበያ ድርጊቶቹን ከማጋለጥ ታቅበዋል።ለምን?
መልካም ንባብ፦
(“ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ ከ1973 (በፈረንጆች አቆጣጠር) ጀምሮ የመሳሪያ ሽያጭ እና የአልማዝ የጥቁር ገበያ/ኮንትሮባንድ ተሰማርቶበት የነበረዉን ህቡእ ሥራዉ ከረፈረንደሙ በሗላም ቢሆን ትላልቅ ሓይቅ አገሮች ተብለዉ ወደ ሚጠሩ አካባቢዎች ለምሳሌ ዛየር ዉስጥ ሎረንት ካቢላ ሲመራዉ ለነበረዉ የሽምቅ ተዋጊ ቡድንና የዛሬዋን ሩዋንዳ በመምራት ላይ ላለዉ ፓወል ካጋመ ሲመራዉ ለነበረዉ የሽምቅ ተዋጊ ሃይል ከደረግ ማርኳቸዉ የነበረዉን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት መጓጓዣ እየተጠቀመ መሸጥ እና ማስተላለፍን ቀጠለበት።
ከጥቁር ገበያዉ እንቅስቃሴ ዉጭ በኤርትራ ጊዜዊ መንግሥት ስም ራሱን ሹሞ ለዓለም ያስተዋቀዉ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ “ወዲ ስኞራ” እና “ሰለሞን ሃይለ” (ራሻይዳ) በሚበላዉ ታጋይ የሚመራ አንድ መካናይዝድ ጦር እና የክፍለ ጦር አዛዥ የነበረዉ “ገብረ እግዚአብሔር ዓንደማርያም”/ዉጩ/ የሚመራ የኤርትራ ጦር ወደ ዛሬዋ ዛየር የድሮዋ ኮንጎ ሪፑብሊክ በመላክ ፕረዚዳንት መቡቱ ሰሲሴኮን በመቃወም ሲዋጋ ለነበረዉ ሎሬንት ካቢላን በማገዝ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዉግያ በማድረግ ካቢላን ወደ ሥልጣን ለማምጣት 29 ኤርትራዉያን መስዋዕት ከፍለዋል።
ለቅጥር ዉለታዉም ሎሬንት ካቢላ ወደ ሥልጣን ከመጣ በሗላ ከወረሳቸዉ ሰፋፊ የማዕድን ቦታዎች አንዱን ለኤርትራ ጊዜዊ መንግሥት በባለቤትነት ለግሶታል።ለማዕድኑ ፍለጋና ቁፋሮም የሰዉ ሃይል ስላስፈለገ፤ደርግን በማገልገል የኢሰፓ አባሎች ነበራችሁ ተብለዉ “ናይዘጊ ክፍሉ” በተባለዉ የሻዕቢያ ታጋይ ተፈርዶባቸዉ ለዓመታት ሲሰቃዩ ከቆዩት ኢትዮጵያዉያንና ተቃዋሚ ተብለዉ ለእስር የተዳረጉ 18 ኤርትራዉያን ታጋዮች በድምሩ 150 ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን በሰንሰለት የፍጢኝ ታስረዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ማጓጓዣ አይሮፕላን ወደ ኮንጎ እንዲተላለፉ አድርጓል።
የአልማዝ ፍለጋ ቁፋሮዉ እየተካሄደ እያለም የተባበሩት መንግሥታት እና የፈረንሳይ መንግሥት ወደ ኮነጎ ሪፑብሊክ በመግባታቸዉ ጋር ተያይዞ ቁፋሮዉ ከቆመ በሗላ ምስጢሩ እንዳይታወቅበት በመስጋት በማዕድን ቁፋሮ አሰማርቷቸዉ የነበሩትን 150 ዎቹ ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን አስረኞች እንዲረሸኑ ተደርጎ በአንድ ጋጥ ጉድጓድ ተቆፍሮ ሬሳቸዉ በአንድነት እንዲቀበር ተደርጓል ። ይህነን አስመልክቶ ጀርመን ሀገር ሚታተም አንድ ጋዜጣ ድርጊቱን ይፋ በማድረግ ለሕትመት አድረሶት እንደነበር ይታወሳል።
ይህ ሁሉ ሲሆን፣ አንዳንድ የዋሃን ወገኖች የትናንቱ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ-የዛሬዉ ህዝባዊ ግምባር ፍትህና ዲሞክራሲ- ንቅዘት የሌለዉ በብልሹ ስነ ምግባር እጁን ያልነከረ ጥንቱም ሲፈጠር ሆነ ዛሬ ገና ከመወለዱ በፊት ጻድቅ የሆነ እንከን የለሽ ቡድን አድርገዉ የሚገልጹልን የዋሃን አሉ።ሆኖም ሃቁ ከዛ እጅግ የራቀ ነዉ። እንደሚሉትም አይደለም።ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ በትግሉ ጊዜ ጀምሮ የአልኮሆል መጠጦች፤የዕጸ-ፋርስ (ሓሽሽ) እና በመርፌ የሚወጉ ሕገ ወጥ መድሃኒቶች፤አልማዝና ወታደራዊ ንበረቶችን ወደ መሃከለኛዉ ምስራቅና የመሳሰሉ አገሮች በመሸጥና በማዘዋወር ሥራ ተሰማርቶ የነበረ ሃይል ነዉ።
ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ አህጉሮች ሕገ ወጥ ገንዘብ በማሸሽ እና በማካበት ድርጊት ተሰማርቷል። በዘህ ድርጊት ተሰማርተዉ ሲያገለግሉት የነበሩት አባሎቹ አንዱ የዛሬዋ የኤርትራ መንግሥት የአገር መከላከያ ሚኒስተር የሆነዉ የጀኔራል ስብሐት ኤፍሬም ታላቅ ወንድም ዳዊት ኤፍሬም ነበር። ዳዊት ኤፍሬም በሕገ ወጥ ተግባር ሓሽሽ እና አልኮሆል ጭና ስትጓዝ በነበረችዋ መርከብ በመያዙ የካቲት (February 1983) በኢጣሊያን መንግሥት ተይዞ የ5 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ሲያበቃ ሁኔታዉ ባልታወቀ ምክንያት እስራቱ ሳይፈጽም እንዲለቀቅ ተደረገ።
በመሳሰሉት ሕገ ወጥ ድርጊቶች የአልኮሆል የሕገ ወጥ መድሃኒቶችና የመሳሰሉት ገንዘብ ማስገኚያ ሕገ-ወጥ ገበያ ድርጊቶች ላማከናወን ካሰማራቸዉ ግለሰቦች -(ምንም እንኳን ከሚጠቀሱት ሰዎች ዛሬ በተላያዩ ምክንያቶች እስር ቤት ቢገኙም)፡ በድርጊቱ ተሰማርተዉበት የነበሩበት ቦታና ስም ዝርዝራቸዉ አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ያህል፦
(1) እስቲፋኖስ ሃይለ መኮንን (በዛየር-ኮንጎ) (2) ኤርሚያስ ደበሳይ/ፓፓዮ/ (በአዉሮፓ አገሮች) (3) ሰለሞን ሐድሽ (በሱዳን) (4) ደስበለ ተስፋጽዮን/ደሱ ወዲ ማዓሎ/ (በኤርትራ እና በመካከለኛዉ አፍሪካ) (5) ሙሴ በኺት (ሱዳንና በመካከለኛዉ ምስራቅ አገሮች) (6) ዳዊት መንግሥት አብ (አፍሪካ፤አዉሮጳ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ)መሓመድ አሕመድ ቓስም (መካከለኛዉ ምብራቕ) እና ሌሎች የመሳሰሉት ግለሰዎች በሚገኝበት ቡድን በኩል ነበር ሕገ-ወጥ ገበያዉ ሲያከናዉን የነበረዉ።
ድርጅቱ ከሕዝብ እና ከጠላት ማርኮ ያግበሰበሰዉ ዶላር ወደ ጎን ትተን ሕጋዊ ባልሆኑ ገበያዎች ያካበተዉ ሕጋዊ አስመስሎ በተለያዩ አህጉሮች በሚገኙ ባንኮች ሕጋዊ ሰነድ ከፍቶ ያስመዘገበዉ ገንዘብ 3.7 ቢልዮን ዶላር ነበረዉ። በጣም የሚገርመዉ በየባንኩ የተቀመጠዉ የገንዘቡ መጠን/አሀዝ ከኢሳያስ አፈወርቅ በቀር ማንም የሕዝባዊ ግመባር ባለስልጣን አያዉቀዉም።የገንዘቡ ባለቤትነትና መጠን የተመዘገበዉ በተለያዩ ግለሰቦች ሰም ስለተመዘገበ በባለቤትነት የተመዘገቡት ግለሰዎች በሕይወታቸዉ ላይ ቅራኔን በሚያስከትል የባለቤትነት አሰራር ዘዴ ነበር ሲጠቀሙበት የነበረዉ። ከኤርትራ ነፃነት በሗላ የንግድ ኮሚሽኑ ወደ ሚኒስቴርነት ሲሸጋገር የተቋሙ ሀላፊነት 09 እንዲረከበዉ ትዕዛዝ ተላለፈ።
ሐምሌ 1991 ደንጎሎ በተካሄደ ስብሰባ አስገራሚ ዜና ተላለፈ። ግምባር ማለትም ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ አዲስ በመቋቋም ላይ ለነበረዉ የኤርትራ ጊዜዊ መንግሥት ለመቋቋሚያ በጀት የሚዉል 250 ሚልዮን ዶላር ማበደሩ ነበር። ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ መስከረም 1991 አጋማሽ ከጣልያን መንግሥት ጋር ባደረገዉ ግንኙነት በአለፉት 50 ዓመታት ፋሺስት ኢጣሊያ በኤርትራ ሕዝብና መሬት ላይ ላደረሰዉ ጉዳት በካሳ መልክ በራሱ አነሳሽነት ወደ 360 ሚሊዮን ዶላር ሊለግስ ዝግጁነቱ ካስታወቀ በሗላ፡ሊለግሰዉ የታቀደዉ ገንዘብ ለአየር ማረፊያ፤ለባቡር ሃዲድ መጠገኛ ለዘመናዊ መጓጓዣ እና መገናኛ መንገዶች ለመሳሰሉት እንዲዉል የመደበዉ ቢሆንም፡ ኢሳያስ አፈወርቅ ግን “ጥሬ ገንዘቡን በእጆችን ስጡን” በማለቱ ከተጠቀሰዉ ገንዘብ ከፊሉ እንዲሰጠዉ ቢደረግም፤ ጥያቄዉ ስላላስደሰታት፤ ለጋሿ ጣሊያን ላለመቻቸዉ የዕድገት ዘርፎች የማይዉል ከሆነ ብላ የተባሉት ዕቅዶች ሳይተገበሩ ልገሳዉ ሙሉ በሙሉ ተሰረዘ።
የአሜሪካ መንግሥትም የህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ አካሄድ በቅርብ ሲከታተለዉ ከቆየ በሗላ ህዝባዊ ግምባ ሓርነት ኤርትራ በዓለማችን እጅግ አደገኛ ቡድኖች መካከል ከሆኑት አንዱ ብሎ ማህደሩ ዉስጥ ለመመዝገብ ጊዜ አልፈጀበትም። ይቀጥላል…………..”)
ማሳሰቢያ_
ወደ ጎነጎ የፍጢኝ ታስረዉ ወደ ኮነጎ ዛየር ማዕድን ቁፈራ ሲሄዱ ሃለፊነቱን የወሰደዉ ግለሰብ የህዝባዊ ግምባር የእስረኞች ጉዳይ ዋና መርማሪ የነበረዉ ወልደዝጊ ባህታ የተባለ ሲሆን በዉሳኔዉ ግምባር ቀደም ተዋናያን የነበሩ ባለስልጣኖችም ከሟቹ ዓሊ ሰይድ ዓብደላ ጀምሮ 9 ትላልቅ የሻዕቢያ ባለስልጣናት በዉሳኔዉ መሳተፋቸዉ ስምዝርዝር የገለጸ ሲሆን፤ ዛየር ኮነጎ ሄደዉ ማዕድን ቁፈራ ተሰማርተዉ ሲሰሩ እላይ በተብራራዉ ምክንያት የህዝባዊ ግምባር መሪዉ ኢሳያስ አፈወርቅ ምስጢሩ እንዳይታወቅ በማለት 150 ዎቹ እንዲረሸኑ ሲያደርግ ከነዚሁ 18 ኤርትራዉያኖች ሲሆኑ፤ የ18ቱ ስም ዝረዝር እና ምድብ ክፍላቸዉ፤ ዕድሜ፤ትዉልድ ቦታ እና የተማሩበት ትምርት ቤት እንደዚሁም በቁጥጥር የዋሉበት ዕለት እና ዓመተ ምሕረት በሰነዱ ላይ በዝርዝር ቀርቧል።-/-www.ethiopiansemay.blogspot.comSaturday, November 15, 2008

(በቅርቡ በአንድ ኤርትራዊ ይፋ የሆነዉ አዲስ የምስጢር ሰነድ)

(በቅርቡ በአንድ ኤርትራዊ ይፋ የሆነዉ አዲስ የምስጢር ሰነድ) ጌታቸዉ ረዳ ግባችን ከወዲሁ መጪዉን አስፈሪዉ ዳመና መበተን ነዉ!!! ከዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ
መግቢያ-በጌታቸዉ ረዳ-
ከላይ በኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ የተለጠፉት ፎቶ ግራፎቹ መንግሥቱ ሃይለማርያም እና ኒሜሪን በመገልበጥ ስልጣናቸዉን በገዛ ራሳቸዉ ለመራጩ ሕዝብ በማስረክብ የተመሰገኑት የሱዳን ፕረዚዳንት ጀኔራል ሱዋር ዳሃብ፤ ከሳቸዉ ቀጥሎ የመጣዉ ሳድቅ አልማህዲ፤ ቀጥሎ የሱዳኑ ያሁኑ ፕረዚዳንት የሆኑት አል በሽር ፤፤ዶ/ር አልቱራቢ፤ኢሳያስ አፈወርቅ፤ ሰሎሞን ጴጥሮስ እና ቡጥሮስ ቡጥሮስ ጋሊ መለስ ዜናዊ፤ ጂሚ ካርተር እና ሄርሞን ኮሄን ናቸዉ።
ከላይ የተመለከተዉ ርዕስ “ዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ” በተባሉ ኤርትራዊ በትግርኛ ተጽፎ Assena.com በመባል የሚታወቀዉ የኤርትራዉያኖቹ የህዋ ሰሌዳ በOctober, 2008 (ከዚህ ጀምሮ ዘመኖቹ የሚቀርቡት በአዉሮጳዉያን አቆጣጠር ነዉ) “ግባችን የመጪዉን አስፈሪ ዳመና መበተን ነዉ!!!” በሚል ርዕስ የቀረበዉን የአሜሪካኖቹ የስለላ ማዕከል (CIA) በኢትዮጵያ ሠራዊት እና አገራቸዉን ከድተዉ ለCIA እሽክርና ያደሩት የትግራዩ “የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” እና የኤርትራዉ “ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ” መሪዎች ከCIA ወቅታዊ የሆኑ ወታደራዊ የስለላ መረጃዎችን በማግኘት እንዴት ለድል እንደበቁ ሲገልጽ፤በሌላ በኩል ደግሞ ከCIA በተሰጠዉ መመሪያ መሠረት የኤርትራዉ ህዝባዊ ግምባር መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ የኢትዮጵያ እና የሱዳን መንግሥቶች ለመገልበጥ ያቀነባበራቸዉ የመንግሥት ግልበጣዎችን ይፋ ያደረጉልንን ሚስጥራዊ ሰነድ ወደ አማርኛ ተርጉሜ አቀርብላችሗለሁ። በትረጉሙ ላይ ስህተቶች ቢኖሩ ሃለፊነቱ የነዉ የተርጓሚዉ እንጂ የአቶ ዉሕሉል እንዳልሆነ ስገልጽ፡ ሰነዱ ይፋ እንዲሆን አስበዉ ላቀረቡልን ለጸሐፊዉ ለአቶ ዉሕሉል ፈዳይ ንጉሥ በእኔ እና “በኢትዮጵያን ሰማይ ” አንባቢዎች ስም ሳመሰግን፡ አያይዞም በሕዝባዊ ግምባር (ሻዕቢያ) ተማርከዉ የነበሩት የኢትዮጵያ ሠራዊቶች አንዳንዶቹ የት እንደደረሱ ለኛ ፍጹም አዲስ የሆነብን ሌላ ሚስጢር ጸሐፊዉ ያቀረቡትንም በሌላ ጊዜ ለማቅረብ በዚሁ እመለስበታለሁ።www.ethiopiansemay.blogspot.com
ግባችን ከወዲሁ መጪዉን አስፈሪዉ ዳመናን መበተን ነዉ!!!
(የሰሜን አትላንቲክ ኔቶ አዛዥ ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ፋን ቤንጃንኩዝ)
ሰሞኑን ለዓለም በተለይም ደግሞ ለአገራችን እና ለአፍሪቃ ቀንድና የቀይ ባሕር ተጓዳኝ አገሮች በተለይ ለ ኤርትራዉያን እያሳሰባቸዉ ባለዉ ሁኔታ አስመልከቶ ስጽፍ የሰሜን አትላንቲክ (ኔቶ) ዋና አዛዥ ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ፋን ቤንጃንኩዝ ወደ ቀይ ባሕር ባደረገዉ ጉዞ ላይ በ12/10/08 ያደረገዉ ንግግር ተመርኩዤ ያለኝን መረጃ ለማካፈል የአካባቢዉን ፖለቲካና ወታደራዊ ሁኔታዎችን አስመልክቼ ስተነትን፡ለጽሁፌ መነሻ ያደረግኩት የቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ቤንጃንኩዝ “ግባችን ከወዲሁ መጪዉን አስፈሪዉ ዳመናን መበተን ነዉ!!! በማለት ያደረገዉን ንግግር ተመርኩዤ ነዉ።” መልካም ንባብ_
ክፍል 1
በሁለቱም ሃያላን መንግስታት ማለትም በአሜርካን እና ሶቭየት ህብረት በመባል ሰትታወቅ የነበረችዉ/ሩሲያ/ መሃል የነበረዉ የፖለቲካ፤የምጣኔ ሃብት እና የስነ ሃሳብ የበላይነት ፍትጊያ የፈጠረዉ ዉጥረት ፕሮስትራይካ በመባል የሚታወቀዉ በሚኻኤል ጎርቫቸፍ አማካይነት የተከሰተዉ የቀዝቃዛዉ ጦርነት ለዉጥ አስቀድሞ ከመምጣቱ በፊት የቀይ ባሕር አዋሳኝና እና አካባቢዉ 5ኛ መርከብ ተብሎ በሚጠራዉ ማዕከሉ በዲያጎ ጋርሲያ ያደረገዉ በሪድ አድሚራል ጆን ላት አሌክስ እዝ ሲመራ የነበረዉ የአሜሪካዉ የባሕር ሃይል ነበር ሲቆጣጠረዉ የነበረዉ።
በሌላ በኩል ደግሞ “ቀይ-ነብር” በመባል የሚጠራዉ የሶቭየት ሕብረት ሠራዊትም በቺፍ አድሚራል ኪዮሎቪስኪ ሻሮቨክ አመራር ማዕከሉ ዳህላክ ደሴት በማድረግ ሠፍሮ ሁለቱም ወገኖች ታጥቀዉት በነበሩት የተለያዩ አደገኛ የጦር መሣሪያዎች ተፋጥጠዉ ይተያዩ የነበረበት ወቅት ነዉ።
ወቅቱ በሶቭየት ሕብረት ሕለዉና አሜሪካኖች አና አጋሮቿ ግምባር ሲደረግ የነበረዉ ጣልቃ ገብነት ሩሲያን ከሥር መንግሎ ለማዳከም ጥሮ ብዙ ባይሳካለትም በሚካኤል ጎርቫቸፍ በኩል በ1986ቱ መገባደጃ የተጀመረዉ አዝጋሚ ለዉጥ በ1989 ላይ ፕሮስትራይካ በመባል የታወቀዉ የፖለቲካ ለዉጥ የሩስያን ህልዉና ብቻ ሳይሆን የለወጠዉ ከተቀሩት ተፎካካሪዎች አስቀምጧት የነበረዉን የሃይል ሚዛንዋን ጭምር ክፉኛ ስላዛባዉ የግሎባላይዘሽን ተቆጣጣሪነቱ የበላይነቱ ወደ አሜሪካ በማዘንበሉ፡ የዓለም ጸጥታ ፖሊሲ ጉዳይና ቁጥጥር በአሜሪካን እጅ እንዲነደፍ ክፍተት ፈጠረ።
በዚህ ወቅት ዳህላክ ደሴት ሰፍሮ ነበረዉ ሶቭየት ሕብረት ጦር ቀደም ብሎ ባጋጠመዉ ዉስጣዊ የሩስያ እዝጋሚ የፖለቲካ ማዕበል ሠራዊቶቹን ከአካባቢዉ ማስወጣት የጀመረ ቢሆንም፤በወቅቱ የ ኢትዮጵያ ክፍለሃገሮች ተብለዉ ሲታወቁ የነበሩት በኤርትራ እና በትግራይ የተመሰረቱት ሁለት የሽምቅ ተዋጊ ሃይሎችን ለመረዳት CIA በአካባቢዉ የሰፈረዉ የሶቭየት ሃይልን ለመቀናቀን ሲል ኤርትራ ዉስጥ ለኤርትራ ሐርነት ህዝባዊ ግምባርን የስለላ መረጃ በማቅረብ አፍዓበት ላይ ሰፍሮ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንዲጠቃ ሲያደርግ፦በትግራይም ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የስለላ መረጃ በማቀበል፤ እንዳባጉና (ሽሬ አዉራጃ-ትግራይ ዉስጥ) ላይ ሰፍሮ ዘመናዊ የስለላ መሣሪያዎች ታጥቆ በነበረዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይም አመርቂ ጥቃት እንዲፈጽሙ አስችሏቸዋል።
ቀደም ብሎ በ1984 በህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ እና በህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ መካከል የነበረዉ ግንኙነት ሻክሮ ቅራኔ ዉስጥ በመግባቱ የአሜሪካ የስላላ ማዕከል ድርጅት (CIA) ሁለቱንም አገናኝቶ የጋራ መረጃዎቹን ላማቀበል አስቸጋሪ ስለሆነበት ለጊዜዉም ቢሆን ሁለቱንም ለየብቻ እያነጋገረ አስፈላጊ የሆኑ ወቅታዊ መረጃዎቹን ለማስተላለፍ አማራጭ ብሎ የወሰደዉ ለየብቻ በማነጋገር ነበር። ስለሆነም-በ08/87 እጅግ ወቅታዊና ጠቃሚ የሆኑ ወታደራዊ መረጃዎች ማቅረብ ጀመረ።
የአሜሪካ ቅኝት በኤርትራ የዉሃ አዋሳኞች የሶቭየት ሕብረት መኖር ከወታደራዊ የበላይነቷ ጋር ስላያያዘችዉ፤ሁለቱም በተናጠል እየተረዱ በደርግ ሠራዊት ላይ የማጥቃቱን እርምጃ ሲያፋጥኑ፡በደረሱት ጥቃቶችና በአካባቢዉ የሰፈሩ ሶቭየቶችም ከዉስጥ የሶቭየት የፖለቲካ ቀዉስ ጋር ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ ለቀዉ በመዉጣታቸዉ ደርግም ብቻዉን ቀርቶ እርቃኑ በመዉጣቱ ጋር ተያይዞ በታየዉ ክፍተት አሜሪካን አጋጣሚዉን በመጠቀም በልዩ አጀንዳ ይዛ ክስቱን ወደ ራሷ ጠቀሜታ እንዲዉል በንቃት መንቀሳቀስ ጀመረች። ስለሆነም አሜሪካ በJanuary 19/1989 ሪቻርድ ፈን ዳላስ የተባለ የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ የስላላ ሥራ ተጠሪዋን በመላክ ሱዳን ካርቱም ከተማ ዉስጥ ሜሪዲያን ሆቴል በተባለ ሆቴል የህዝባዊ ግምባር መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ እና የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሪ መለስ ዜናዊ በምስጢር ጠርቶ ሁለቱም የጋራ ወታደራዊ ንድፍ እንዲያወጡና አሜሪካም የለት ተለት ወታደራዊዉና ፖለቲካዊዉ የስላላ መረጃዎች እንደምታቀርብላቸዉና ብሎም ሁለቱም ቡድኖች ህጋዊ ተቀባይነት እንዲኖራቸዉ አሜሪካ እንደምታደርግ ቃል ተገብቶላቸዉ በዚህ ተስማምተዉ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲገናኙ ሆነ።
በተካሄደዉ በዚሁ የስብሰባ ስምምነት ዉጤትም የህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ የፖለቲካ ጽ/ቤት በFebruray 05/1989 አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ በማካሄድ የተባለዉ ንድፍ ተስማምተዉ ሲያሳልፉ- መሳ ለማሳ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይም በFebruary17/1989 አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ተመሳሳይ ዉሳኔ አሳለፈ። ስበሰባዉ በተናጠል ቢካሄድም፤ግቡ ለአንድ ዓለማ ነበር።ይሄዉም የደረግን መገርሰስ እና የኤርትራ ነጻነት ታዉቆ ለዓለም ሕዝቦች ማስተዋወቅ፤አስታክኮም የህዝባዊ ግምባር የአካባቢዉ ወታደራዊ የበላይነት እንዲታይ በር ከፍቶ ደርግን ለመጨረሻዉ ሞት ፈርዶ በሶቭቶች ላይ የመጨረሻዋ በር የሚቆልፍ ስትራተጂ ነበር።
ከዚያ በሗላ በApril 16/1989 የአሜሪካን ፕረዚዳንት የነበሩት ጂሚ ካርተር ሰብሳቢነት መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወረቅ ለሁለተኛ ጊዜ በመሪድያን ሆቴል ተገናኝተዉ፡የጋራ ወታደራዊ ዕቅድ ነደፉ። ቀጥሎም በሕዝባዊ ግምባርን የወከለ እጅግ ምስጢራዊ በሆነ ምደባ አንድ (ግለሰብ) ብቻ ሚስጥራዊ የስለላ መረጃዎችን የሚያከናዉን ሲመረጥ። በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በኩል በሥራ ክፍፍል ያተኮረ ማዕከልነትን ያላተኮረ ነበር።
ወታደራዊ ስትራተጂ፤ ስለላ እና መረጃ አስመልክቶ በመጀመሪያ ስብሰባዉን የመራዉ ከህዝባዊ ግመባር ጴጥሮስ ሰለሞን ሲሆን ቀጥሎ ከትግራይ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ድግሞ ሓየሎም፤ጻድቃን፤ ክንፈ ገብረመድህን እና አሰፋ ገብሩ ናቸዉ።
ሁለቱም ድርጅቶች አስፈላጊዉ መመርያ ከተቀበሉ በሗላ፦በተለይም በጊዘዉ የነበረዉ የሱዳን መንግሥት ለታቀደዉ ወታደራዊ ዕቅድ እንቅፋት እንዳይሆንና እንደሚሆንም ስለታመነበት፡ስጋቱን ለማስወገድ በጊዜዉ በስልጣን የነበረዉ የሱዳን መንገሥት በመፈንቅለ መንግሥት መወገድ አለበት ተብሎ በCIA ስለታመነበት፡ ይህነን ከባድ ሃላፊነትም እንዲሸከም የህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ ኢሳያስ አፈወረቅ ሆኖ፡ ከ1979 ጀምሮ የኢሳያስ አፈወረቅ የቅርብ ወዳጅ የነበረዉ ሱዳናዊዉ ዶክተር ሐሰን አልቱራቢ ግንኙነት ተደርጎ ሱዳን ዉስጥ መፈንቅለ መንግሥት እንዲካሄድ ለኢሳያስ አፈወርቅ መመሪያ ከተሰጠዉ በሗላ፤ ለግንኙነታቸዉ ማጠናከሪያ እንዲሆን ታስቦ የዶክተር ሓሰን አልቱራቢ ልጅ በ1982 ኤርትራ በረሃ ድረስ በመዉስድ በወቅቱ ሒምቦል ተብሎ በሚጠራዊ የህዝባዊ ግምባር የመኪና ጥገና ማዕከል እየሰራ አገልግሎቱ እንዲያበረክት ተብሎ በጥገናዉ ማዕከል ሃለፊ ለነበረዉ አሕመድ መሓመድ በዓልኼር አደራነቱ ተሰጥቶት እንዲሰራ ተደረገ።
ከዚህ የመነጨ ጥብቅ የወዳጅነት መተማመንና ትስስር በመመረኮዝ በኢሳያስ አፈወርቅ እጅ በኩል ተሰጥቶ ሱዳን ዉስጥ የህዝባዊ ግምባር የስለላ እና የመረጃ ቅርንጫፍ የሆነ ምድብ 72 ተብሎ የሚታወቀዉ የስለላ ክፍል ሃላፊ በነበረዉ መልአከ ወዲ አፍተራሪ ለተባለዉ ታጋይ 14 ሚሊዮን ዶላር መፈንቅለ መንግሥቱን ለሚያካሂደዉ ቡድን ሥራዉን ለማከናወን እንዲረዳ ለዶክተር ሐሰን አልቱራቢ እና ለጀኔራል መሐመድ ሑሴን አልበሽር በእጅ እንዲሰጥ ተደርጓል።
መልአከ ወዲ አፍተራሪ እና ካርቱም ዉስጥ በሜሪዲያን ሆቴል አካባቢ ጸጉር አስተካካይ ሆኖ ሲሰራ የነበረ አቶ መብራህቱ ከተባለ ሰዉ ጋር በመተባበር በህዝባዊ ግምባር ተቃዋሚዎች ላይ የግድያ እና የጠለፋ ስራ ሲያካሂድ የነበረ ሰዉ ነዉ። እንደታቀደዉም በህዝባዊ ግምባር አቀነባባሪነት የታቀደዉ የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት ተጠናቅቆ በቦታዉ በጀኔራል ሐሰን አል በሽርና ዶክተር ሐሰን አልቱራቢ የሚመሩት አዲስ መንግሥት ተመሰረተ።
በዛዉ ዓመት ዉስጥ በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ የደርግ መንግሥት ላይ በሕዝባዊ ግምባር ሐርነት ኤርትራ የስለላ እና የመረጃ አቀነባባሪነት ኤርትራ ዉስጥ ከነበረዉ በጀኔራል ደምሴ ቡልቱ በኩል የሚመራዉ የሁለተኛ አብዮታዊ ሠራዊት በመንግሥቱ ሃይለማርያም መንግሥት ላይ ያነጣጠረ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግሥት ሲካሄድ 72 ሰዓት የቆየ የቶክስ ማቆም አዋጅ እርምጃ ወስዶ ነበር።
የኤርትራዉ ህዝባዊ ግምባር በተጠቀሱት ክንዋኔዎች እጁን ሲያስገባ ከአሜሪካ መንግሥት የስለላ ማዕከል ድርጅት (ሲ አይ ኤ) በኩል በተደረሱት የስምመነት ዉሎች መሰረት ነዉ።ከዘያ በመነሳት ነበር የአሜሪካ የስለላዉ ማዕከል (ሲ አይ ኤ) በጦርነቱ ወቅት ከህዝባዊ ግምባር በስተጀርባ በመሆን የሗላ ደጀን ሊሆነዉ የበቃዉ።
በህዝባዊ ግምባር የተካሄደዉ ጠምፅዋዉ የፈንቅል ዘመቻ እና በወያኔ ትግራይ የተካሄደዉ ዘመቻ ዋለልኝ በሗላ በወታደራዊ አነጋገር ደርግ እጁን የሚሰጥበት ዜሮ ሰዓት በመድረሱ፤ሶቭየት ህብረቶቹም በራሳቸዉ ዉስጣዊ ዉጥረት በመጠመዳቸዉ በማይቀረዉ የደርግ ዉድቀት በመመልከት አሜሪካም በአካባቢዉ የህልዉናዋ ሽግግር ድልድይ ሆኖ እዉን ለማደረግ ከነበራት ጉገትና ዕቅድ ጋር ስለተሳካላት ሕዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ በMarch 1981(መጋቢት) ያወጣዉ ባለ 9 ነጥብ አዋጅ የሰላም ጥሪ ተመርኩዞ በApril 16/1989 (ሚያዚያ) ጀምሮ ከኤርትራ ህዝባዊ ግምባር እና ከትግራዩ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጋር እጅግ የጋለ ወዳጅነት መስርቶ የነበረዉ የአሜሪካ ፕረዚደንት በነበረዉ በጂሚ ካርተር በኩል ከደርግ ጋር የዕርቅ በር እንዲከፈት በተደረገዉ የሽንግልና ዉይይት የኤርትራዉ ህዝባዊ ግምባር መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ብቻ ከደርግ ጋር የመነጋገሩ ሁኔታ ሲቀበለዉ የትግራዩ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሪ መለስ ዜናዊ ግን የኢሳያስን አቋም በመቃወም አልደግፍም አለ። የኢሳያስን ሃሳብ ተቃዉመዉ ከመለስ ዜናዊ ሃሳብ ጋር የወገኑት የህዝባዊ ግምባር ከፍተኛ አማራር አባላት ስም ዝርዝርም፦ ማሕሙድ ሸሪፎ ሮሞዳን መሓመድ ኑር ሃይለ ወልደትንሳኤ ጵጥሮስ ሰለሞን ዑቑበ አብራ
ስብሓት ኤፍሬም - -
ከላይ የተጠቀሱት የኤርትራ ጉዳይ ከወያነ ሃርነት ትግራይ ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ስለሌለዉ ለየብቻቸዉ አጀንዳ ከተያዘላቸዉ ከደርግ ጋር እንወያያለን ካለዉ የወያኔዉ መሪ የመለስ ዜናዊን ሀሳብ ደግፈዋል።
ከዛዉ አቋም ከመነጨ ሃሳብ ነበር ታሳቢ አድርጎ የኤርትራን የነጻነት ጉዳይ በአትላንታ በኬኒያ በኢንግላንድ በጣሊያን አጀንዳ ተይዞለት እንዲቀጥል የተደረገዉ።ይህንን በሚመለከት ራሱን የቻለ አሰራር ተከትሎ በአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ጉዳይ ከፍተኛ ባለስልጣንና የCIA አባል በነበረዉ በሄርማን ኮሃን በመለስ ዜናዊ እና በኢሳያስ አፈወርቂ ጋራ የግል ስምምነታቸዉን በመፈጸም መጀመሪያ በግንቦት-May12 እስከ 17/1991፡ በሁለተኛዉ ዙር ደግሞ በሰኔ (June) 11 አስከ 16 ተካሄዶ ባለ 11 ነጥብ የያዘ ሰምምነት ተፈራረሙ። የሰነዱ ዝርዝር ፍሬ ነገሮች እንደሚከተለዉ ነዉ።- ይቀጥላል፡……

Tuesday, November 11, 2008

አይ ምፅዋ!

በቅደም ተከተል ከላይ ወደታች የቀረቡት ፎቶግራፎች አፄ ቴዎድሮስ፤ብርጋዴር ጀኔራል ተሾመ ተሰማ፤ ሻምበል ሸዋንታዮ ዓለሙ እና ከሥር የሚታየዉ የመጨረሻዉ ፎቶግራፍ በምፅዋ ጦርነት ወቅት ከመጀመሪያ አስከ መጨረሻ ድረስ በጀግንነት ተዋግተዉና አስተባብረዉ የጀግኖችን አደራ እና ቃል ዘግበዉ ለኛ ያስተላለፉልንን የ“አይ ምፅዋ!” ደራሲ ባለዉለታችን ናቸዉ። ከተረሱት ጀግኖቻችን ማህደር አይ ምፅዋ! ሞት የተፈረደባቸዉ 17ሺህ የኢትዮጵያ ሠራዊት ደራሲ ታደሰ ቴሌ ሰልቫኖ (የብዕር ሥም) ጌታቸዉ ረዳ (http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/) “ሰዓቱ ለካቲት 9 አጥቢያ ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት ነበር።… በሁሉም አቅጣጫዎች የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት በከባድ ጀግንነት ከሻዕቢያ ጋር በጥይት፤በእጅ ቦምብና ላዉንቸር ተጨፋጨፈ። መሬቱ እየነጋ ሲሄድ የምፅዋ ከተማ በአስከሬን ክምር፤በሰዉ ሥጋ ብጥስጣሽና በደም ጎርፍ ጨቅይታለች፡ ድመትና ዉሻ የመረጡትን አስከሬን ይጎትታሉ።አንዳንድ ቦታ ደግሞ የሰዉ እስከሬንና የዉሻ ሬሳ ጎን ለጎን ተኝቷል። በጣም የሚዘገንን ዕልቂት ነበር። የከባድ መሣሪያ ጥይት የቆራረጠዉ ሰዉ አካል በየቦታዉ ዕጣ ያልወጣለት የቅርጫት ሥጋ መደብ መስሏል…” ለዛሬ “ከረሳናቸዉ ጀግኖቻችን ማህደር” ይህነን የመሰለ የሉአላዊነት የሞት የሽረት ኢትዮጵያዊ የጀግንነት ገድል በምቾት እየተንደላቀቀ አእምሮዉ ለላሸቀበት ባልታገለበት ባዶ ሜዳ ላይ እቅፍ አበባ የሚታቀፈዉ አስሰዳቢዉ የዘመናችን “ሀፍረተ-ቢስ ምሁር”- “አይ ምፅዋ” ከሚል በየካቲት 1982 ዓ.ም ታትሞ ለሕዝብ ይፋ የሆነ እጅግ ታሪካዊ መጽሓፍ ጀግንነትና ኢትዮጵአዊነት ምን ማለት እንደሆነ ቢገባዉ ከሚል እሳቢ የቀረበ ዝግጅት እነሆ። ግብዞቹ “የደርግ ወታደር” እያሉ የሚጠሩት “ኢትዮጵያዊ ሠራዊት” በግብዞቹና በእርሱ መሃል ያላቸዉና የነበራቸዉ የኢትዮጵያዊነት ትርጉም ልዩነታቸዉ በግበር እንመለከታለን።የታሪክ ከሃዲዎች ናቸዉና ይህ ገድል ዛሬም ቢያንኳስሱት አይገርመንም።ዛሬ የምሁራን ዓይን ታዉሮ የተደረጉት ዕልክ አስጨራሽ የሉአላዊነት የደም ገድል ማየት ቢያቅተዉም ፤መጪዉ ትዉልድ የምጸፅዋ ዳግማዊ ቴዎድሮሶቻችነን መስዋእትና ታሪክ በቁርጥ ቀን ልጆቻቸዉ መታደሱ ምንም አልጠራጠርም። በታሪኩ ዉስጥ የምናየዉ የእነ ራስ አሉላ እና የንጉሥ ዮሐንስ ገድለ ታሪክ በማንኳሰስ ለዓረቦችና ለሻዕብያ በባንዳነት አድሮ ምፅዋ ላይ ታሪካዊ ወደባችንን ላለማስነጠቅ ዘብ ቆሞ በነበረዉ በ17 ሺህ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት ያደረሰዉ “ባንዳዉ -ህዝባዊ ሐርነት ትግራይ” እና የዓረቦቹ “ቀንደኛዉ ዉሻቸዉ ሻዕብያ” ከተባለዉ ቡድን ፤ማንነታቸዉን አምታትተዉ “ዉዥምብር ፍለጋ” ገብተዉ ሁለቱም አሳፋሪ የጫካ መንጋዎች በጋራ ያደረጉት ብሔራዊ ወንጀል የፈጸሙት ክህደትና ጭካኔ፤ እንዲሁም ለምፅዋ ሽንፈት ምክንያት ቀዳሚ ምክንያት የነበረዉ በመንግሥቱ ሃይለማርያም ደካማ እና አረሜናዊ አመራር የተከናወኑትን ሁሉ ጦርነቱ ተጀምሮ አስክያልቅ በጦርነቱ ተካፍሎ ቆስሎ ተማርኮ በወታደራዊ ሞያዉ የተሻገረባቸዉ ደራሲዉ ከዘገባቸዉ የጦርነቱ ድርጊቶች በከሃዲዎቹ እና በጀግኖቻችን መሃል የተደረጉት የሞት ሽረት “የመጨረሻ ትግል” መጽሀፉን ለማንበብ ዕድሉን ላላገኛችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ከመጽሐፉ ምስክርነት ፤ አንጀት የሚበላዉን በምፅዋ ወደብ እና ከተማ “የመጨረሻዋ የግብግብ ሰዓት” እንዴት እንደተደመደመ ከዛ የሞት በር በርግዶ ሞትን ካሸነፉት ከጀግኖቻችን አንዱ ከሆነዉ በደራሲዉ አማካኝነት የምፅዋ ጀግኖቻችን ከመሰዋታቸዉ በፊት እንድንሰማቸዉ ያስተላለፉልነን የተናገሯቸዉ ንግግሮች በደራሲዉ እንደበት አደራቸዉን እና የጦርነቱ ሁኔታ አነሆ።
“በየካቲት ወር 1982 ዓ.ም በአብዮታዊ ሠራዊት እና በሻዕቢያ መካከል በቀይ ባሕር አዉራጃ በምፅዋ ግንባር ከባድ እና አሰቃቂ ዉጊያ ተካሂደዋል። ለአስር ቀናት ቀንና ሌሊት ለ240 ሰዓታት በእያንዳንዷ ሰኮንድና ደቂቃ እንደ ቅጠል የረገፉት የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ጎን ተሰልፌ ተፋልሜአለሁ። የሠራዊቱን ተጋድሎ እና የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ መስክሬአለሁ። በምፅዋ ግንባር የተደረገዉ ፍልሚያ ለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለሠራዊቱና ቤተሰቡ ይህን የታሪክ መጽሐፍ ለማዘጋጀት ችያለሁ።….
“…እኔ የዚህ መጽሓፍ ደራሲ በምፅዋ ግንባር ከመጀመሪያ አስከ መጨረሻ የዉጊያ ሰዓት ድረስ ተሳትፌ የኢትዮጵያን ሠራዊት ሽንፈት ተጋርቼአለሁ። በዉጊያዉም ቆስየ በሻዕቢያ ተማርኬ ከምፅዋ ወደ ናቅፋ ሳሕል አዉራጃ አንደርበብ በተባለ ቦታ የሻዕቢያ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ተወስጄ ከፍተኛ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ምርመራ ተደርጎብኛል። ጭልጥ ባለ የበጋ በረሃ የሳሕል ሀሩር በጉድጓድ እስር ቤት ታስሬ ፍዳየን አይቻለሁ። እንደዚህ ዓይነቱ መከራ ዉስጥ አልፌ ይህን ጽሁፍ ለማዘጋጀት መብቃቴ ራሱ ከሙታን ዓለም ተመልሼ የመታየት ያህል መስሎ ታይቶኛል።”
-ለታሪክ ፀሐፊዎች- (ገጽ 187 አስከ 198)
የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ምፅዋ ከተማ ለተከማቸዉ አብዮታዊ ሠራዊትና አመራሩ ክፉ ቀን ነበረች። ሻዕቢያ ደግሞ እንደ ልደት ቀን ይቆጥረዋል። ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ ምፅዋ ከተማን የረገጠዉ በዚች ዕለት ነዉና።
ሻዕቢያ በ1970 ዓ.ም ከጀብሃ ተዋጊዎች ጋር በመሆን አብዛኛዉን የኤርትራ ግዛት ተቆጣጥሮ ነበር። አሥመራ፤ባሬንቱ፤ምፅዋና ዓዲቀይህ ከተማ የነበሩትን የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት ደምስሶ እነዚህን ከተሞች መቆጣጠር ግን አልቻለም። በመሆኑም የሃያ ስምነት ዓመታት ምኞቱን ሻዕቢያ በምፅዋ እዉን ያደረገበት ቀን የካቲት 9 ቀን 1982 ናት።
የ6ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ጀኔራል ተሾመ ተሰማ ካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በምፅዋ ከተማ ርዕሲ ምድሪ በተባለ አካባቢ በከባድ መሣሪያ በፈራረሱ ቤቶች ጥግ ሆነዉ የተወሰኑ የጦር መኮንኖችን እና ባለሌላ ማዕረግተኞችን ሰብስበዉ ንግግር አደረጉ።
“ሻዕቢያ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ በእጅ ቦምብና በክላሽን በአሁኑ ሰዓት የከተማ ዉስጥ ዉጊያ በማድረግ ላይ ነዉ። ሻዕቢያ ከባድ መሣሪያ ድብደባ አቁሞ በእግረኛ ብቻ ለመዋጋት አዲስ ተዋጊ ሃይሉን በመኪና እያመላለሰ ዕዳጋ ከተማ ላይ እያከማቸ ነዉ። በአዲስ ጉልበት ተዋግቶ ምጸፅዋን ለመያዝ ቆርጦ ስለመነሣቱ ጥርጥር የለዉም።… “እኔ የሚፈለግብኝን አደራ ተወጥቻለሁ። ከጥር 30ቀን 1982 እስከ ዛር የካቲት 9 ቀን 1982 ሞት ሽረት ትግል አድረጌአለሁ።የሻዕቢያን የጥፋት ዓለማ ለመግታት ያላደረግኩት ጥረት የለም። ከዚህ በሗላ ግን የራሴን ሕይወት በክብር ከማጥፋትና ለኢትዮጵያ ጀግኖችና ታሪክ ፀሐፊዎች ታላቅ ተምሳሌት ከመሆን ሌላ አማራጭ የለኝም። ጀግንነት ማለት በሁሉም መልክ ለጠላት አመች ሆኖ አለመገኘት ማለት ነዉ።…
“በዚች የኢትዮጵያ ህዝብ የባሕር በርና ዓለም አቀፍ ወደብ በሆነችዉ በምፅዋ ከተማና በቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ ቆሜ ሽጉጤን ለመጠጣት ዝግጁ ሆኜአለሁ። በ እዉነት እኔ ዛሬ በሞት ብሸነፍም በታሪክና በመጭዉ የኢትዖጵያ ትዉልድ ፊት አልሸነፍም። የ አፄ ትዎድሮስን ዕድል በማግኘቴም በጣም እኮራለሁ። እኔ አሁን የተዘጋጀሁለት ሞት ዘለዓለማዊ ክብርና ሕይወት ይሰጠናል። በሻዕቢያ እንደ እነ ጀኔራል ጥላሁን እና ጀኔራል ዓሊ ሓጂ ተማርኬ የሻዕቢያን መሪዎች ዓይን ማየት ግን የሞት ሞት ነዉ። አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ወድቀዉ ከመዋረድ ሞትን መርጠዉ የራሳቸዉን ሕይወት መቀቅደላ ላይ አጠፉ። እኔ ደግሞ በተራየ ከኢትየጵያ ሕዝብ መንግሥት የተሰጠኝን የጄኔራልነት ማዕረግ ሳላስደፍር ለመንግሥትና ለሕዝብ በገባሁት ቃል ኪዳን መሰረት አስቀድሜ የፈቀደዉን ያህል ተዋግቼና አዋግቼ ሻዕቢያን አራግፌአለሁ። እንደ ጦር መሪም እንደ ተራ ተዋጊም ሁኜ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ይዤ ተፋልሜአለሁ። አሁን ግን ለመጨረሻዋ መስዋዕትነት ህይወቴን ለማጥፋት የቀሩኝ ጥቂት ደቂቃዎች ናቸዉ።… “ጎበዝ ስሙኝ! ይህ አደራ መልዕክቴ ነገ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይደርስ ይሆናል። ምናልባት አምለክ ካለ ከእናነተ አንዱ መልዕክቴን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት አደርስ ይሆናል። ዛሬ ሻዕቢያ ምፅዋን ተቆጣጥሬአለሁ በማለት የዓለምን መገናኛ ብዙሃን እንደሚያጨናንቅ ጥርጥር የለዉም። ይህ ደግሞ ለ ኢትዮጵያ ሀግርና ሕዝቧ ትልቅ አደጋ ነዉ። በቀይ ባሕር በራችን በኩል ብዙዉን ጊዜ ወረራ ፈጽመዉብን በተደጋጋሚ የሳፈርናቸዉና ፊት ለፊት ያልቻሉን ምዕራባዉያን ሀገሮችና ዓረቦች ዛሬ የሻዕቢያን ጊዜያዊ ድል ሰምተዉ ይፈነጥዛሉ። ምናልባትም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድንበር የሆነዉንና ለዘመናት በአባቶቻችን የደም ዋጋ ፀንቶ የቆየን የባሕር በራችንን በመዝጋት እንዲሁም ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ባሕር አይደለም በማለት በምድር ተወስነን እንድንቀር ይደረግ ይሆናል። ይህ ደግሞ የሞት ሞት ነዉ። “ ይሁን! ምንም ማድረግ አልችልንም። ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ዉጭ ሆኗል። ከሙታን ዓለም መጥቼ ማረጋገጥ ባልችልም የፈለገ ጊዜ ይጠይቅ እንጂ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር በር አልባ ሆኖ ፤በኢምፔርያሊስቶችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ተሸንፎና እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም። ይህ ከሆነማ የአፄ ዮሐንስ የቀይ በሕር ተጋድሎ እና የጀግናዉ ራስ አሉላ አባነጋ አጥንት እንዲሁም የእኔን ጨምሮ የአበዮታዊ ሠራዊት አባላት አጥንትና ደም የኢትዮ ያን ትዉልድ ሁሉ እሰከዘላለሙ የፋረዳል። ኢትዮጵያ ሀገሬ የጀግኖች መፍለቅያና ገናና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በመሆኑም ጀግናዉ ሕዝቧ ሕዝባዊ የባሕር በሩ በሻዕቢያ ተይዞና የጠላቶቹ መፈንጫ ሆኖ አይኖርም። የፈለገ ጊዜ ይቆይ እንጂ ሻዕቢያ ምፅዋን እንደያዛት ለዘላለሙ አይኖርም”። ጊዜዉ ጠብቆ የኢትዮጵያ ጀግና ጠላትን ደምስሶ ምፅዋን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያስረክብ እምነቴ የፀና ነዉ።”
አሉና ትንፋሽ ዋጡ: የትንሽ ፋታ ወሰዱ። የጀኔራል ተሾመ ዓይን የቆሰለ የነብር ዓይን መስሏል፡ ከንፈራቸዉ በዉሃ ጥም ደርቆ ቅርፊት ይዟል። ፊታቸዉ በደረቅ ላብ ዥንጉርጉር ሆኗል። ሆዳቸዉ ከወገባቸዉ ተጣብቋል። በተሰበሰበዉ አባል ዉስጥ በሰፈነዉ ጸጥታና ዝምታ መሃል “እናንተ አብየታዊ መኮንኖች ባለሌላ ማዕረጎች! ስሙኝ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ።” አሉ ጀኔራል ተሾመ ቆጣ ብለዉ።“አንድ ሰዉ ቤት ሲሰራ የሚሠራዉ ቤት በርና መስኮቶች አሉት። አንድ ሰዉ ደግሞ ሞተ እንበል። መቃብር በርና መስኮት የለዉም። በርና መስኮት የሕይወት ምልክቶች ናቸዉ። በመሆኑም ያለሀገር ነፃነትና ያለባሕር በር ብልጽግና ስለሌለ የኢትኦጵያ ሕዝብ የባሕር በር ተነጥቆ የሚኖር ሕዝብ አይደለም። ከሻዕቢያ ጀርባ ሆነዉ ቀይ በሕር የኢትዮጵያ አይደለም የሚሉ ሀገሮችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ሁሉ በቀጥታም ሆኑ በተዘዋዋሪ ፍላጎታቸዉ የ ኢትዮጵያ ሞት ነዉ።
“ይህ ምሳሌ ከገባችሁ የባሕር በር የሌላት ሀገር ሞቶ ከተቀበረ ግለሰብ የምትለየዉ በትንሹ ነዉ። ምክንያቱም የባሕር ሀብት ከማጣቷ በላይ ምርቷን ወደ ዉጭ ለመላክ የግዴታ ወደብ ስለምትከራይ ለወደብ ክፍያ የምትከፍለዉ የገንዘብ ዉጭ ዜጎቿን ያደኸያል። በአኳያዉ ጠላቶቿን ባለወደቦቹን ያበለጽጋል። ይህ ዕድል ለኢትዮጵያ እንዳይደርሳት ቀይ ባሕር የኢትየጵያ ትዉልድ ይፋረድ።፡ቀይ ባሕር ለእኔ ዘላለማዊ ቤቴ እንዲሆን ወስኛለሁ። ደስተኛ እና ዕድለኛ ጀኔራል ነኝ። እኔ ብሞት ታሪኬ አይሞትም። የእኔ ታሪክ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕሊና ዉስጥ እንደሚኖር አምናለሁ። ቻዉ! ቻዉ!ቻዉ!” አሉና ጀኔራል ተሾመ ፤መኮንኖቹን ከሰበሰቡበት ቦታ ተፈናጥረዉ ወደ ቀይ ባሕር ጠረፍ አመሩ። የባሕሩ፡ጠረፍ ከስብሰባዉ ቦታ በግምት ከስልሳ ሜትር አይበልጥም። በፍጥነት ወደዚህ በሕር ጠረፍ ገሰገሱ። ክላሺንኮቭ ጠመንጃዉን አቀባብለዉና አዉቶማቲክ ላይ አድርገዉ በቀኝ እጃቸዉ ጨብጠዋል፡ከምፅዋ ወደብ በስተቀኝ ከሚገኘዉ ወታደራዊ ወደብና መደብር ላይ ሲደርሱም ለቀይ ባሕር ዉሃ መገደቢያ በተሰራ ግንብ ጠርዝ ላይ ጀርባቸዉን ወደ ቀይ ባሕር ፊታቸዉን ወደ ምፅዋ ከተማ አድርገዉ ቆሙ። ቀጥሎ በእጃቸዉ የነበረዉን ክላሺንኮቭ ጠመንጃ ወደ ቀይ ባሕር ወረወሩት። ከዚያም በወገባቸዉ ታጥቀዉት የነበረዉን ኮልት ሽጉጥ አወጡና የሽጉጡን አፈሙዝ በአፋቸዉ ጎርሰዉ የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጥወቱ 2፡10 ሰዓት ሲሆን ቃታዉን ሳቡት። የሽጉጥ ቶክስ ድምፅ እንደተሰማ ወደ ጀርባቸዉ በቀይባሕር ዉሃ ላይ ወድቀዉ ሰጠሙ። ከጭንቅላታቸዉ የሚፈስ ደም በቀይ ባሕር ዉሃ ላይ ቀልቶ ይታይ ነበር።
ወዲያዉም ይህን የጀኔራል ተሾመ ሞት በምስክርነት ቆመዉ ከአዩት መካከል ከ150 የማያንሱ የጦር መኮንኖች ባለሌላ ማዕርጎች በሽጉጥ፤ በእጅ ቦምብና በክላሽ ጠመንጃ ሕይወታቸዉን አጠፉ። ከእነዚህም መካከል ሻለቃ ሮሪሣ ዳዲ በእጅ ቦምብ፤ሻምበል ሸዋንታዮ ዓለሙ በማካሮቭ ሽጉጥ፤ሻምበል አዲሱ በማካሮቭ ሽጉጥ፤ሻምበል ባሻ አማረ ናጂ በክላሽ፤ሻምበል ወንድወሰን በሽጉጥ የሃምሳ አለቃ ፈቃዱ ቦጋለ በክላሽ፤ወታደር ሽንገረፋ በክላሽ ሕይወታቸዉን አጠፉና በስም የሚታወሱ ናቸዉ። ሌሎችም በብዛት ራሳቸዉን ገድለዋል። በአጭር ደቂቃ ዉስጥ አካባቢዉ ሬሳ በሬሳ ሆነ።
ሌሎች ደግሞ ሻዕቢያን ገድየ መሞት አለብኝ እያሉ ወደ ጠላት ወረዳ በመገስገስ ገድለዉ የሞቱትም ነበሩ። ወደ ጠላት እየሮጡ በእጅም በቦምብም ታንክ ተሽከርካሪዎችን እያቃጠሉ ራሳቸዉን የገደሉ በሻዕቢያም የተገደሉ ጥቂት አልነበሩም።ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ የ3ኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ከጀኔራል ተሾመ፤ከሌሎች መኮንኖችና ባለሌላ ማዕረጎች ሞት በሗላ የተረፉትን አሰባስበዉ የሻዕቢያን ከበባ ሰብሮ ለመዉጣት ሞከሩ። የአምሳ አለቃ ታደሰን (ደራሲዉ) እና ከ300 ያላነሱ የአብዮታዊ ሠራዊት በቀጥታ በመምራት ከምፅዋ ከተማ ዋናዉን የመኪና መንገድ ይዘዉ አዋጉ። ዉጊያዉ ከባድ ዕልቂት አስከትሎ ነበር። ሸዕቢያን እያባረሩ እየገደሉ ፤ሻዕቢያም የአብኦታዊ ወራዊት አባላትን እያባረረ እየገደለ የእጅ በእጅ ዉጊያ ጭምር ተደረገ። የኮሎኔል በላይ ሠራዊት በዚህ መራራ ፍልሚያዉ ከምፅዋ ዓለም አቀፍ ወደብ በግመት በሁለት ኪሎ ሜትር ርቃ ወደ ምትገኘዉ በረዶ ፋብሪካ ወይም ጠዋለት ወደተባለችዉ የምፅዋ ክፍለ ከተማ የ70 ደቂቃ ዉጊያ በማድረግ ሻዕቢያን ሰብሮ ለማለፍ ቀይ በሕር ሆቴል ደረሰ። ግማሹ ሃይልም ቀይ ባሕር ሆቴል ያዘ።ይሁን እንጂ በዚህ አካባቢ የተከማቸዉ የሻዕቢያ ሃይል በጣም ብዙ ስለነበር የሠራዊቱ ሙከራ ተገታ። ሻዕቢያን ሰብሮ ወደ ዕዳጋ ከተማ ለመሻገር አልቻለም። በዚህም ሁለተኛ ትራጀዲ ተከሰተ።
ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ለብሰዉ ከቀይ ባሕር ሆቴል በረንዳ ላይ በአንዲት ጥልፍልፍ የቃጫ ወንብረ ላይ ተቀምጠዉ አጠገባቸዉ ለነበሩት ጥቂት አባላት መልዕክት ያስተላልፋሉ። “ጀግና ቢሞት በእልፍ እአላፍ ጀግና ይተካል።የእኔ ታሪክ ለትዉልድ ይቀራል። ታሪክ ይናገራል እንጂ እኔ አልናገርም።” የምትል መልዕክት ነች። መልዕክታቸዉም አንደጨረሱ ፊታቸዉን ወደ ምፅዋ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስትያን አዙረዉ አማተቡና የክላሽንኮቭ ጠመንጃቸዉን አፈሙዝ ጎርሰዉ ቃታዉን ሳቡት። ለጥቂት ሰኮንዶች አዉቶማቲክ ክላሽንኮቭ ድመፅ አስተጋባና ፀጥታ ሆነ።
ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ክላሽንኮቭ ጠመንጃቸዉ እንደያዙ ወንበር ተደግፈዉ ተዝለፍልፈዋል። የለበሱት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ባንዴራ በላያቸዉ ላይ ደምቆ ይታያል።ይህነን ትዕይንት ሻዕቢያ በፎቶግራፍ አንስቶታል። በቪዲዮ ካሜራም ቀርጾታል፡ የወታደዊ ሸሚዝና ሱሪያቸዉን ኪስ ሻዕቢያ ሲበረብርም ከንጽህና ወረቀት በስተቀር ምንም አላገኘም። አንድ የሻዕብያ ተዋጊ ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ለብሰዉ የተሰዉትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ባንዴራ ካላያቸዉ ላይ ገፈፈና ክብሪት ጭሮ አቃጠለዉ። የኮሎኔሉ አስከሬን ከወንበሩ ላይ ገፍትሮ በመጣልም በደም የተጨማለቀዉን ወንበር በአንድ እጁ ወደ ላይ አነሳዉ። ይህ ድርጊት ጋብ ያለዉን ተኩስ በመጠኑ ቀሰቀሰዉ። ከአንድ አቅጣጫ የተተኮሰች ጥይት ያን የሻዕቢያ አባል ከወንበሩ ጣለችዉ።ከዚያ በሗላም የሻዕቢያ ተዋጊዎች ተደናግጠዉ አካባቢዉን ማሰስ ጀመሩ።ፎቅ ላይ እየወጡና ምድር ቤቱን አሰሱ ቁስለኛም ይሁን ጤነኛ በየቤቶቹ ፍርስራሽ ሥር ተደብቆ ያገኙትን የአብዮታዊ ሠራዊት አባል ጭምር በየቦታዉ መረሸን ጀመሩ። የአብዮታዊ ሠራዊት አባላትም ሻዕቢያን ገድሎና የራሳቸዉን ጥይት እየጠጡ ሞቱ። “ኢትዮጵያ ወይም ሞት! ቀይ ባሕር የ ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ባሕር ነዉ!”። እያሉ መፈክር በማሰማት የክላሽ ጥይት እየጠጡ የተሰዉም ብዙ ናቸዉ።
ከጥዋለት ወደ ባፅዕ ከተማ ወይም ወደ ምፅዋ ወደብ የሸሹም የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት ብዙ ናቸዉ። የሃምሳ አለቃ ታደሰም ከሸሹትና ካመለጡት አንዱ ነበር።በዚህ ግርግር ዉስጥ ብዙ አስደናቂ የግለሰብ ጀግንነቶች ታይተዋል። ለአብነት የሚከተሉትን እንመልከት።
አንድ የ6ኛ ክፍለጦር መረጃ መምሪያ ባልደረባ የሆነ ዕድሜዉ በግምት 42 የሚሆን፤ መልኩ ጠየም ያለ እና ቀጭን ሰዉነት ያለዉ የሃምሳ አለቃነት ማዕረግ ያለዉ ኤም 14 ጠመንጃ ታጥቆ በምፅዋ ወደብ አካባቢ ቦታ ይዟል። ሻዕቢያዎች ሊማርኩት እንደተጠጉ ባረጋገጠ ጊዜ “ዘራፍ! አልሆንም ምርኮኛ! ጀኔራል ተሾመ ዛሬ ጠዋት “የጀግናዉ የአፄ ቴዎድሮስን ዕድል በማግኘቴ ዕድለኛ ነኝ” በማለት ሽጉጥ ጠጥተዉ በጀግንነት በቀይ ባሕር ዉሃ ላይ ወድቀዉ መቃብራቸዉን ቀይ ባሕር ሲያደርጉ መስክሬአለሁ። ዛሬም ነገም ለዘላለም ይህ የጀኔራል ተሾመ ጀግንነት በትዉልድ ፊት በወርቅ ቀለም ተጽፎ የሚቆይ በመሆኑ እኔም በሻዕቢያ ተማርኬ የመኪና መንገድ ለሻዕቢያ ጠራጊ ሆኜ ከምሠራ ሞቴን በጀግነንነት እንደ ተሾመ መርጫለሁ። “ዘራፍ! ዘራፍ! የጎንደር ልጅ! የጎንደር ልጅ ሞት አይፈራም! ዘራፍ!ዘራፍ! የአማራ፤የኦሮሞ፤የትግሬ የአገዉ፤የጉራጌ፤ወላይታ፤የሶማሌ፤ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ለሀገሩ አንድነት ክብርና ነፃነት በግምባር ቀደምትነት ይሞታል! ኢትዮጵያዊ ማለት ጀግንነት ማለት ነዉ። ኢትዮጵያ ወይም ሞት!! ሞት ለሻዕቢያ!! ዘራፍ!ዘራፍ!የቴዎድሮስ፤የአሉላ የዬሓንስ የአብዲሳ የተሾመ ወኔ በእኔ ልብ ዉስጥ በቅሏል!” አለና ቦታዉን በመልቀቅና ወደ ሻዕቢያ ተዋጊዎች በመሮጥ እያከታተለ የ እጅ ቦምብ ወርዉሮ አራት የሻዕቢያ አባላትን ገደለ። በመቀጠልም ብቻዉን በሻዕቢያ መካከል ገብቶ ካላሽን ጥይት እሩምታ አወረደባቸዉ። ሃምሳ አለቃዉ አጥፍቶ ለመጥፋት በልበ ሙሉነት ከጠላት ጋር ተቀላቅሎ የልቡን አደረሰ። በሻዕቢያ ጥይት ቆስሎ ከወደቀበት ቦታ ሆኖም ቦምብ በራሱ ላይ አፈነዳና ሰዉነቱን በታተነዉ። ሕይወቱ አለፈች።
የሃምሳ አለቃዉን ጀግንነት ያየ ብዙ የጦር መኮንኖችና ወታደሮች ሽጉጥና ጠመንጃ ሕይወታቸዉን አጠፉ። ቢያንስ ቢያንስ ከዘጠና ያላነሱ ራሳቸዉን በዚህ መንገድ አጥፍተዋል። በዚሁ ዕለት በዚህ ጊዜ ከነሙሉ ትጥቃቸዉ እየዘለሉ ቀይ ባሕር ዉሃ ገብተዉ በመስጠም ያለቁት ደግሞ ከ150 በላይ ናቸዉ።
የቀይ ባሕር ዉሃ የአብዮታዊ ሠራዊት አባላትን አስከሬን እያንሳፈፈ እያንገላታና ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ እየገፈተረ የዋለባት እንዲት ቀን በታሪክ ብትኖር ይህቺ ናት። የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት እዉነተኛ የሀጋር ፍቅር ምን ያህል እንደሆነም የቀይ ባሕር ዉሃ የተገነዘበ ይመስላል። ምክንያቱም አስከሬናቸዉ እየገፋ ከየባሕሩ ጠረፍ ወደ መሃል መበዉሰድ በአጠቃላይ ሻዕቢያ ሊማርከኝ ቀርቶ ሬሳየን በዓይኑ ማየት የለበትም የሚል የዉስጥ ኑዛዜያቸዉ ተግባራዊ ያደረገ ይመስላል። የቀይ ባሕር ዉሃ የጨዉ ዉሃ ስለሆነ ዉስጡ ወለል ብሎ ይታያል። የአብየታዊ ሠራዊት አባላት ዘለዉ ሲገቡ አስከተወሰነ ርቀት ይታያሉ። እንደገቡም እጃቸዉ የያዘዉን ጠመንጃ ይለቃል። ከዚያም ከአንድ ከ አስር ደቂቃ በሗላ ሆዳቸዉ ተነፍቶ ከባሕሩ ዉስጥ ወደ ላይ ይወጡና በባሕር ላይ ይንሳፈፋሉ። ባሕሩ በማዕበሉ እየገፋ ወደ መሃል ይወስዳቸዋል። የካቲት 9 ቀን 1982 በምፅዋ ከተማ አዉራ ጎደናዎችም ልዩ ትርኢትታይቷል። የቆየ እና ትኩስ የአብዮታዊ ሠራዊት እና የሻዕቢያ ሬሳ በየጎደናዎቹና በየቤቱ ሥር ተከምሮ ነበር። ይሁንና የሻዕቢያ ታንክና መኪና እየተነዳበት ተጨፈላለቀ። መጥፎ በሽታና ጠረን አካባቢዉን ተበክሎ ሰዉ መሆንን ያስጠላል።
በየቤተክርስትያኑም እንዲሁ ልዩ ትርኢት ታይቷል። ለምሳሌ ጠዋለት በተባለ ቦታ የቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን አለች።የቤተክርስትያኗ መስኮቶች፤በሮች ግድግዳዎችና ጣርያ በሻዕቢያ ከባድ መሣሪያ ድብደባ ወድሟል። የቤተክርስትያኗ ዉስጣዊ አካል በእሳት ተለብልቦ ከአገልግሎት ዉጭ ሆኗል። አብዛኛዉ አካሉ ማለት ከመቶዉ እጅ ሰማኒያዉ ፈርሷል። በቤተክርስትአኗ ዙሪያ በየፍራሹ ጥግ የኢትዮጵያን ባንዴራ በአንገታቸዉ በእጃቸዉ፤በራሳቸዉ፤በወገባቸዉና በጠመንጃቸዉ ላይ አስረዉ ራሳቸዉን የረሸኑ ብዙ የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት የዘለዓለም እንቅልፍ አሸልበዋል። መሣሪአዎቻቸዉ ለአስከሬኖቻቸዉ የክብር አጀብ ሆነዋል።
በምፅዋ ከተማ በሕይወት በየምሽጉ የሚገኙት የአብዮታዊ ሠራዊት አባላትም ቢሆኑ ጀኔራል ተሾመ ተሰማ እና ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ራሳቸዉን በመግደላቸዉ መሪና አስተባባሪ መዳከሙን እነደተገነዘቡ ሻዕቢያ ከአንድ ሺህ የማያንሱ ተዋጊዎች በተጨማሪ ከዕዳጋ ከተማ ወደ ምፅዋ ከተማ አሰማርቶ ስለ አስከበባቸዉ መፈናፈኛ አጥተዋል። ዉጊያዉ ሙሉ ለሙሉ ቆመ። ከዚህ በሗላ ምፅዋ ከዉጊያ ቀጠናነት ወደ ሙርኮ ጣቢያነት ተቀየረች። በወጣት ሃይል የተገነቡት የሻዕቢያዉ ተዋጊዎች በኮማንዶ የሰለጠኑ ናቸዉ። በምፅዋ ከተማ ተበታትነዉ የነበሩት የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት እያሰሱ ከአለምንም ቶክስ መማረክ ጀመሩ። የመጀመሪያ ሥራቸዉ ትጥቅ ማስፈታት ነበር። ቀጥሎ ፍተሻ ይከናወናል። በፍተሻዉ የእጅ ሰዓት የጣት ቀለበት፤የአንገት ሐብል ወርቅ፤የጋብቻ ቀለበት የመሳሰሉት ሻዕቢያዎች እየተስገበገቡ የሚቀራመቷቸዉ ናቸዉ። ጥሬ ገንዘብ ቀበቶ የእግር ጫማ፤ ካልሲ የዓይን መነጽር፤የግል ማስታወሻ፤መንጃ ፈቃድ፤መታወቂያ ፊልድ ጃኬት፤የጦር መለዮ፤ስክሪፕቶ እና ወረቀት ሳይቀር ከምርኮኞቹ ኪስ ወስደዋል። ከተሰዋ የሠራዊቱ አባል ላይ እንኳን ፊለድ ጃኬት ጫማ ሳይቀር አስከሬንን እየጎተቱ ያወልቁ ነበር።
ማንኛዉም ምርኮኛ የሚሄደዉ ባዶ እግር ነዉ። ለብዙ ጊዜ ጫማ የለመደ እግር ያለጫማ መሄድ ባለመቻሉ አብዛኛዎቹ የ አብዮታዊ ሠራዊት አባላት ያነክሳሉ። አንዳንዶቹ በአሸዋ በጠጠር፤በእሾህ፤በጠርሙስ ስባሪ ብረታ ብረት በእንጨት ስንጥር እየተወጉ የእግራቸዉ መዳፍ በደም ተጨማልቆ ይታይ ነበር።
በመጨረሻም ሻዕቢያ በዚህ መልክ ከምፅዋ ከተማ በየቦታዉ የተቆጣጠራቸዉንና የማረካቸዉን የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት አጠቃልሎ ወደ ምፅዋ ወደብ ወታደራዊ መደብር አሰባሰባቸዉ። የተማረኩት የ አብዮታዊ ሠራዊት የፖሊስ የባሕር ሃይል የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ናቸዉ። ከእንግዲህ ወዲያ ምፅዋ የምርኮኞችን ሥቃይና የሻዕቢያን ፈንጠዝያ የምታስተናግድ ከተማ ሆነች።”}
በማለት ደራሲዉ በዛ እሳት ፤ሰማይና ምድር በተደበላለቀበት ዉጊያና ፈታኝ ሕይወት በማስታወሻቸዉ ዘግበዉት የነበረዉን ሰነድ ዘርዝረዉ እንዴት እንደነበረ በአደራነት የተረከቡት የጀግኖቻችን ቃል ለኢትዮጵአ ሕዝብ ማስተላለፋቸዉ በእኔና በአንባቢያን ስም ከፍ ያለ አድናቆትና ምስጋና አቀርባለሁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስተላለፍ የምፈልገዉ በዛ ጦር ግምባር በአዛዥነትና በዉሳኔዉ ዉስጥ የተሳተፉት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት አመራር አባላት ለፍረድ እንዲቀርቡ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ጠንክሮ መግፋት አለበት። ይህ አደራ የገዛ ዓይኑ ጠብሶ ለበላዉ አሰፋሪዉ ምሁር ሳይሆን አደራዉና ምከሬ ለኔ ብጤዉ ኢትዮጵያዊ ነዉና ወያኔን በጠላትነት ፈርጃችሁ አስከ መጨረሻዉ ፍልሚያ በቻላችሁት መንገድ ሁሉ ብሔራዊ ወንጀሉን አጋልጡት! ታገሉት! የባሕር በራችን የጊዜ ጉዳይ እንጂ ይመለሳል! ቴዎድሮሶች ትናንት ኖሯል ለወደፊቱም ይኖራሉ!
ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያዊያን አንጂ የባንዳዎች መፈንጫ እንድትሆን መፍቀድ ተባባሪነት ነዉ። ወየነ የኢትዮጵያ ክፉ ጠላት ነዉ። መጽሐፉን ብታነብቡ ጀነራሎቹን ምጽዋ ላይ ሲማርክ የነበረ ወታደሮችን በጨካን አንጀቱ በዉሃ በተከበበ መሬት በከባድ መሳሪያና በእጅ በቦምብ ሲፈጅ የነበረዉ አብዛኛዉ የወያኔ እጅ እንደነበር የተለያዩ የተዘገቡት ሰነዶች መስክረዋል። በመሆኑም ኩፉ ጠላትነቱን አስመስክሯልና ለጠላት የሚገባዉ ትግል አትንፈጉት። እናዉቅልሃለን የሚሏችሁ ሙሁራን ነን ባዮቹ “ከባሕሩ ዉሃ የተቀላቀለዉ የጀግኖች ደም “እርሱት” ቢሏችሁ እንኳ “አንረሳም!” በሏቸዉ። ድሮም ሰንፈዉ ያስሰነፉን እነሱ ዛሬም ሰንፈዉ እያስሰነፉን የሚገኙት ያዉ እነሱ ናቸዉና ወደር የሌለዉ የጀግኖችን ገድል የመንፈሳችሁ መመሪያ አድርጉ። የጀግኖች ደም በኢትዮጵያ ሰማይ ሕያዉ ሆኖ በክብር ለዘላም ይኖራል! http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ /-////-/

Friday, November 7, 2008

The Nature of American Imperialism & the Election of Obama

The Nature of American Imperialism & the Election of Obama
By Professor Aleme Eshete The election of Obama is a great victory that fills our heart with joy. But as I said in my last mail on the subject I have no illusion as what Obama could do to change the nature of American imperialism in the world and in particular in Ethiopia to advance our liberation and restore our liberty, independence, sovereignty, our territorial integrity and our pride. What I recommend is that the Ethiopian Diaspora in the States should write to Obama reminding him of our condition, and the true condition of Kenya, and entertain him to find a way and means to bring a change to our condition. He has marginally touched upon the subject in his speech yesterday. Our admiration for America's democracy that has proved the liberation of the black race by his election to the most powerful chair in the world will every day be undermined as long as their are 70 million Ethiopians tortured, killed, arrested and kicked around by scoundrels that American imperialism has put in power since seventeen years and for an indefinite era. Every member of the Ethiopian Diaspora should write every day of the year , 365 days a year for as long as he remains in power to press upon him the sad inhuman condition that Ethiopian at home and the millions disfranchised all over the world are suffering.//-/-/

The Nature of American Imperialism & the Election of Obama

The Nature of American Imperialism & the Election of Obama By Professor Aleme Eshete The election of Obama is a great victory that fills our heart with joy. But as I said in my last mail on the subject I have no illusion as what Obama could do to change the nature of American imperialism in the world and in particular in Ethiopia to advance our liberation and restore our liberty, independence, sovereignty, our territorial integrity and our pride.
What I recommend is that the Ethiopian Diaspora in the States should write to Obama reminding him of our condition, and the true condition of Kenya, and entertain him to find a way and means to bring a change to our condition.
He has marginally touched upon the subject in his speech yesterday. Our admiration for America's democracy that has proved the liberation of the black race by his election to the most powerful chair in the world will every day be undermined as long as their are 70 million Ethiopians tortured, killed, arrested and kicked around by scoundrels that American imperialism has put in power since seventeen years and for an indefinite era.
Every member of the Ethiopian Diaspora should write every day of the year , 365 days a year for as long as he remains in power to press upon him the sad inhuman condition that Ethiopian at home and the millions disfranchised all over the world are suffering.//-/-/

Saturday, November 1, 2008

“አሰከ መገንጠል” ሞግዚት ላጣች አገር የተመረጠ የመግደያ መርዝ

“አሰከ መገንጠል” ሞግዚት ላጣች አገር የተመረጠ የመግደያ መርዝ
ጌታቸዉ ረዳ ባለፈዉ ርዕሴ ማርክሲዝም እና ሌኒኒዝም አገርንና ሕዝበን አስመልከቶ እነ ዋለልኝ እና ስለተራማጆቹ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በመጠኑ አንስቼ ነበር። የኔ ትንተና እስከ ዕንጥላቸዉ የሞላባቸዉ አንዳንድ ምሁራኖቻችን ላይጥማቸዉ ቢሆንም በዛዉ አንጻር የወደዱት እንደነበሩም ከተላኩልኝ በርከት ያሉ የግል ደብዳቤዎች መረዳት ችያለሁ። ማርክሲዝም መጥፎም ደግም አለበትና እንደ “ሽቱ” አንዱ ሲወደዉ ሌላ ሊጠላዉ ስለሚችል ሁሉም ይረብርበዉ ማለት አይቻልምና በልዩነታችን እንቀጥል።
ክፍል 1 ትንታኔየ በአንድ ድረ-ገጽ “በማሕደር.ዳት ካም” ብቻ ሲለጠፍ “በአሲምባ እና በደብተራዉ” ድረ-ገጽ ግን የላኩሁላቸዉ መሆነኔን ቢታወቅም “አልወደዱትምና” አንባቢ “ግንዛቤዉ” እንዲያሳርፍበት “አገዱት”። ለምን ለሕዝብ እናዳለቀረቡት ደፍሬ ባልጠይቃቸዉም፤የቁርጥ ቀን ወንድሞቼ ናቸዉና ቅር አላለኝም። ደግነቱ የራሴዉ የሕዋ ሰሌዳ መኖሩ በበቂ አንባቢ መነበቡ ከተዘገቡት የእንግዶች ቁጥር መቀበያ ማወቅ ችያለሁና ክፍል ሁለት የመጨረሻዉ ትንታኔየ ዛሬ ይቀርብና ወደ ሌላ ርዕስ እንሸጋገራለን።
ማርክሲስቶች እና ስታሊኒሰቶች አስካሉ ድረስ ዛሬም ኢትዮጵያን በጣረሞት አፋፍ ላይ ሰቅዞ የያዛት ብሔር/ብሐረስብ እስከመገንጠል የሚባለዉ መርዛቸዉ ዛሬም ለወደፊቱም ከመፈታተን ስለማይቦዝን ከሁሉም በፊት በቅድሚያ የሚቀርብ የፖለቲካ አጀንዳ ነዉና ይህነኑ አስመልከቶ እንወያያለን። በዚህ ክርክር ዛሬም ለወደፊትም ሁሌም የሚጠብቀን ደንቃራ ፈተና ነዉና እያንዳንዳችን ራሳችንን ማዘጋጀት ይጠበቅብናል።
በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ በአፍሪቃ የማይታወቀዉ እንግዳ የማርክሲሲቶች የብሔሮች፤ብሔረሰቦች፤ሕዘቦች… መብት “አስከ መገንጠል” ፍልስፍና በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እና ግስጋሴ ማርክሲስቶቹ ቀዳሚ መመሪያ አድርገዉ ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ትግል እና ትምህርት ሰጥተዋል። በዚህ በኩል በግምባር የሚጠቀሱ ቀን ቀንቷቸዉ ወደ ስልጣን የመጡት እነ ወያኔ እና ለአንድ ዓመት በላይ ቢሆን አብሮት ስልጣን ላይ ወጥቶ ከፍተኛ ብሔራዊ ጉዳት ያደረሰዉ የሌንጮ ለታ “ሃይማኖት” የነበረዉ “ኦነግ” የተባለዉ ወንጀለኛ የፓለቲካ ድርጅት አማርኛን በላቲንና በዓረብኛ ቋንቋ ተክተዉ የብሔሮች መብት አስከ መገንጠል በሕገመንግሥት አጽድቀዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከህዝቡ መንፈስ እንዲገፈፍ ከፈተኛ ጉዳትና ሚና ተጫዉተዋል። (በነገራችን ላይ ሌንጮ የኮሎኒዉ ጥያቄ ያፍላ ወጣትነት የማርክሲስቶች ንቃተ ሕሊና ቅስቀሳችን ስለነበር ዛሬ አርጅቼ ልብ ገዝቻለሁና የኮሎኒዉ ጥያቄ ጥየዋለሁ በማለት በብርሃኑ እና በአንዳርጋቸዉ ራዲዮን በሰጠዉ ቃለ መጠይቅ ማረጋገጡ አንድ እርምጃ ነዉ። አዘጋጁ አፍላ የራዲዮን አዘጋጅ በመሆኑ ወይም ሌንጮንና የኦነግ ታሪክ ካለማወቅ ይመስለኛል “እንደርስዎ ያለ የፖለቲካ ስብዕና የተላበሰ…” በማለት ቢያመካሸዉም፤ ሌንጮ ሸርተቴ ነዉና ለማንኛዉም እቀድመን ከመካብ ተቆጥበን በጊዜ የሚታይ ነዉና ሂደቱን በንቃት እንከታተል።)
ብሔር/ብሔረስብ አስከ-መገንጠል የሚለዉ የስታሊኒስቶች መመሪያ “ኦሪት” ለሆነችዉ አገራችን የዉጭ ጠላቶች -እና የቆየ የሙሶሊኒ ከፋፋይ መምሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የተወሰነዉ ካሁን በፊት በጦር ሞክረዋት አልሳካ ያላቸዉን መርዛማዉ የመገነጣጠል ሴራቸዉ ዛሬ ያላንዳች የዉጭ አስፈራሪነት በልጆቿ እጅ መርዙን ተግታ/ጠጥታ እንድትሞት ተደርጎ፤ ሞቷ ጊዜ ፈጅቶ ቀስ በቀስ እየኮሰመነች ብሔራዊ ሃይሏ እየተዳከመ ሕዝቦቿ እርስ በርስ በስድብ እየተቦጫጨቁ ጥላቻዉ ተስፋፍቶ መጨረሻ ግብአተ መሬቷ ከጊዜዉ እና ከመንፈስ መዳከም ጋር እንደሚከናወን እየተፈጸሙ ያሉ ሂደቶች እና ሁኔታዎች እያመላከቱን ነዉ።
በሴራዉ ምክንያት እርስ በርስ ከመጠላላት አልፎ ያንድ ሀገር ልጆች በሕዝብ ስም በፓለቲካ እና በሐይሞኖት ስም እየተነሱ ሽበር እና ግድያ በመፈጸም ሰዉን ከነ ሕይወቱ ወደ ገደል ገፍትሮ መግደል እና ህጻናት በትምርት ገበታ ላይ እንዳሉ እሳት ለኩሶ መፍጀት፤ ዕዉራን አረጋዊያን ብልታቸዉ በሰላ ተቆርጦ በሙት/ሬሳ አፍ ላይ ማጉረስ፤ እናቶች በቢላዋ ጡታቸዉን መቁረጥ፤እመጫት ህጻንዋን ታቅፋ ከሞት ለማምለጥ ስትሸሽ በጥይት እንደ ዥግራ እያባረሩ መግደል፤ወዘተ፡ በኢትዮጵያ ምድር የታየበት ዋናዉ የጭካኔዉ መነሾዉ ከሰዉ ልጆች ጭካኔ ጋር የተያያዘ ባሕሪያዊ ምንጭ ቢሆንም አንዳንድ ጭካኔዎች ካለመማር ተጨምሮበት ለጭካኔዉ ተጨማሪ ነዳጅ የሚሰጡ አፍራሽ የሆኑ ቅስቀሳዎች ያላስፈላጊ መተላለቅ ሊያስከትል እንደቻለ ከላይ የጠቀስኩዋቸዉ በምደሪቷ የተፈጸሙ ክስተቶች የተጠቀሰዉ የግራኛዉ ፍልስፍና ምንጮች ሰበብ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለተከሰቱት በጥላቻ የመተላለቅ እና የመጠላላት ምንጮች ሁሌም ገዢ መደቦች እና የሥልጣን ጥመኞች በሚከተሏቸዉ መርሆዎች የሚከሰቱ ናቸዉ።
በሙሶሎኒያዉያን ወያኔዎች እና በ“ግራ አወንዛፊዎቹ”/ክንፎች (ማርክሲሰስቶች) የፍልስፍና መመሪያ ተመርተዉ የአገሪቱን ሕዝቦች በጎሳ ካፋፍለዉ የአንድነት አርማ የሆነዉን የኢትዮጵያ ገበሬ ለማናቆር ወያኔዎች ወደ ሥልጣን እንደመጡ ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ የተጣደፉበት አጀንዳ አገሪቷን በብሔሮች (አገሮች) እና በብሔረሰቦች ቀጥሎም በነሱ አጠራር “ሕዝቦች” ሁሉ ተደራጅተዉ አስከ መገንጠል ድረስ የሚለዉን መብታቸዉ አንደሆነ ነበር የሰበኩት።
ለዚህ ሥራ አስፈጻሚ እንዲሆኑ ለሰበካዉ ከተመዘዙት የወያኔ የፍልስፍና ካድሬዎች ዉስጥ ወያኔን በአምበሳደርነት ያገለገለዉ በጸረ-አማራ ፕሮፖጋንዳዉ “እኝኝ” የሚል ግለሰብ ዛሬ በጥሮታ ተገልሎ በመደበኛ አምደኛነት በወያኔዉ ሰሌዳ በዓይጋ-ፎረም ላይ ዘወትር ስለ ብሔር እና ስለ አማራ ወንድሙ ከሆኑት ከተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ ከደቡቡ ህዝብ ጋር የነበረዉ ግኑኝነት የሻከረ እንደነበር አድርጎ የሕሊና ደንቆሮዎችና የጥላቻ ቅኔኛዎች የገጠሙትና ያሰላሰሉትን የመሸታ ቤት “ጸረ-አማራ” ምሳሌና ግጥም ለቃቅሞ በህዝቦች ላይ ጥላቻ እንደነበረ አስመስሎ ለወያኔ ፖለቲካ ዉሃ እያጠጣ የሚያስነብበን አቶ ተስፋየ ሃቢሶ፦በሽግግሩ ወቅት ወሎ ክፍለ ሃገር ድረስ ሄዶ ገበሬዎችን ለመመረዝ ቅስቀሳ ሲያደርግ፤ ገበሬዎቹ የተናገሩትን በገዛ ብዕሩ ያሰፈረዉ ልጥቀስ እና የወሎ ገበሬዎች በሚከተለዉ አንደበታቸዉ ምዕዳናቸዉ (ረዚስታንስ) ለወያኔ ቢያሰሙም እነ ወያኔ እና እነ ኦነጎች ለሕዝብ ከበሬታ የላቸዉምና በወቅቱም ሆነ ዛሬም ዋጋ/ከበሬታ አልሰጡትም።
ልጥቀስ፦ (እኛ በሽግግሩ ወቅት የብሔር ጥያቄዎችን በተመለከተ በየክልላችን ስንዘዋወር ነበርን። የምናስተምረዉን ትምህርት የሚያዳምጠዉ ሕዝብ ትምህርታችን አልጣመዉም ነበርና አንድ አባት ገበሬ ተቃዉሞአቸዉን በሎሆሳስ ሲገልጡ “ይሄ በብሔር በጎሳ መደራጀት የምትሉት ነገር በተለይም ገበሬዉን አላስደሰተዉም። ልጆቻችን/ ይልቁንስ እኛ ታሪክ እንንገራችሁ። የምታስተምሩትን ነገር ከታሪክ ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮ ጋር አገናዘባችሁ ብታዩት ጥሩ ነዉ። የዱባ ተክል አንድ ቦታ ነዉ የሚበቅለዉ። የሚያብበዉ እና የሚያፈራዉ ግን ተንሰራፍቶ ሄዶ ሌላ ቦታ ለይ ነዉ። ያንን ዱባ ወደ ሗላ ወደ በቀለበት ብትመልሱት ይበሰብሳል። ይሞታል። የኢትዮጵያም ሕዝብ ታሪክ ይኸዉ ነዉ። በመቶ ዓመት ታሪክ ዉስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራዉ ፤ትግሬዉ፤ከንባታዉ ፤ጉራጌዉና፤ወላይታዉ በአሁኑ ጊዜ የሚገኘዉ በመላ ሀገሪቱ ተንሰራፍቶ ነዉ። እስቲ የኛ ሕዝብ ያለበትን ተመልከቱ። ያንን በሀገሪቱ የሞላዉን ሕዝብ በቋንቋና በጎሳ ክልል ብቻ ታጥረህ ተቀመጥ የሚል ትምህርት ብታስተምሩ ሕይወታችን (በዚሁ ጉዳይ ላይ ሲናገሩ) የጥፋት ዘመን መሆኑን ብቻ ነዉ የምታስረዱን” አሉ።
ሌላዉ አባት “ብሔረተኝነትና ሐይማኖት በጥንቃቄ ካልተያዘ አደጋ አለዉ። ብሔረተኝነትና አረቄ አንድ ናቸዉ። እና ድሮ አጋሰስ ለመሸጥ ስንፈልግ አጋሰሱን አረቄ እንግተዋለን። ፈረሱ ወዲያዉኑ ጊዜያዊ ጉልበት ያገኝና ጮሌ ሰንጋ ፈረንስ መስሎ አርፍ ይላል። እናም ጥሩ የደረስ ዕቃ ጭነን ወደ ገበያ ወስደን እንሸጠዋለን፡ ያ ፈረስ አረቄዉ ከላዩ ላይ ተንኖ ሲያልቅ ግን ወደ ጌኞነቱ ይመለሳል። ስለዚህ እናነተ አሁን የምታስተምሩን ነገር ከሕዝቡ ጥቅም አንጻር የሚያዋጣ ስላይደለ ይህን መሰሉን ትምህርት ከእኛ ብታርቁልን እንመርጣለን” ብለዋል።
ሲል ሕዘቡ በቋንቋ፤በጎሳ… መደራጀቱ አደገኛነቱ ገና ከጥንቱ ከጥዋቱ ያስጠነቀቃቸዉ ቢሆነም አገሪቷ ሞግዚት ያጣች አገር ነበረችና እንዲገድሉዋት ከጠላቶቿ ከነ ሞሶሎኒ የተሰጣቸዉን መርዝ ያግቷት ጀመር።ያ ሁሉ ሆኖም ወያኔ እና የጎሳ አቀንቃኞች ምኑ ያክል ቢጥሩም ዉጭ ሲጓዙ ማን ብሎ እንደሚጠራቸዉ ካደሬዎቻቸዉ ሳይቀሩ እንዲህ ሲሉ ይመሰክራሉ፦ “በአሁን ጊዜ ወዴትም አገር ብንሄድ “አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ?” ይላሉ እንጂ እንተ “አማራ፤አሮሞ አንተ ወላይታ ወይም ትግሬ ብሎም የሚጠራን የለም።…….” (ተስፋየ ሓቢሶ) የአፍሪካ ሰላምና የግጭት ማነጅመንት ጥናት መዕከል ሰኔ 30 ቀን 1993 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሕዝቦች የመወራረስ ታሪክ ላይ ዉይይት ተካሂዶ በነበረበት ወቅት ከተገኘዉ ሰነድ።
ለመሆኑ ይሄ ብሔር ብሔረስብ የሚባል ቃል ማርክሲሲቶቹ እና ወያኔዎች እንደሚተረጉሙት ያገራችን የቋንቋ ጠበብት የሚተረጉሙት ልክ እንደነሱ ነዉ? አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁና አንድ ነገር ሲተረጎም የቃሉ ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ከአገሬዉ ቋንቋ ጋር ካልሄደ የተሳሳተ የዉጭ ትርጉም ተይዞ ለጥፋት ስለሚዉል የቃላቱ አተረጓጎም ትከክለኛነቱ እና ስሕተቱን ለማወቅ ይረዳን ዘንዳ በአገር ወዳድ እና በአንድነት ሃይሎች የተወገዘዉ ጎሰኝነትን ከትዉልድ ትዉልድ አስተላልፎ ለማለፍ ከከጀለዉ ከታወቀዉ ጎሰኛዉ የወያኔዉ ምክትል ያዲስ አበባ ከንቲባ፤እና “የወያኔዉ ያማርኛ ፕሮፖጋንዳ ክፍል” የሚባለዉ የኢሕአዴን/“ብአዴን” ታጋይ የነበረዉ “የአማራዉ ሕዝብ ከየት ወዴት” መጽሐፍ ደራሲ “እንዳርጋቸዉ ጽጌ” በጻፈዉ ጸረ አማራ እና ጸረ-ኢትዮጵያዊነት መጽሐፉ ለመተቸት በሞረሽ ቅጽ 2 ቁጥር 2 (1986) የቋንቋ እና የተለያዩ ዘመናዊ እና ጥንታዊ ትምርቶች ጠቢብ የሆኑት ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ቋንቋ እና ብሔርን በሚመለከት አንዳረጋቸዉም ሆነ ወያኔዎች በተሳሳተ መንገድ እንዴት እንደሚተረጉሙት እና ራሳቸዉን አሳስተዉ አዲሱን ትዉልድ እንዴት እንዳሳሳቱት የአመራዉ ሕዝብ ከየት ወዴት” ደራሲ የለበሰዉን አደናጋሪ የዉሸት ልብስ ፕሮፌሰሩ ሲያጋልጡት እንመልከት። (ብሔር የመታወቂያ ባንዴራ) በሚል ንኡስ ርዕስ እንዲህ ይላሉ። ደራሲዉ የተቃዋሚዉን አፍ ለማስያዝ የሞከረዉ ገጽ 7-8 ላይ ባሰፈራቸዉ ከዚህ በታች ባሉት ቃላት ነዉ፦ “በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሰባ የሚበልጡ ብሄር ብሄረሰቦች መኖራቸዉ ተቀብለዉ ነገር ግን ብሄረተኝነት ጥያቄ ሲመልሱ በኢትዮጵያ ሚገኘዉ ብሄረተኝነት አንድ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት ብቻ ነዉ የሚሉ አልታጡም። እንዲህ የሚሉ ሃይሎች ሊመልሱት የማይችሉት ጥያቄ አለ። ብሄረተኝነቱ ኢትዮጵያዊ ከሆነ ምን ዓይነት ቋንቋ ባህል ታሪክ ወግ፤ወዘተ፡ በአጭሩ ይዘቱ ምን ይሆናል የሚለዉን ነዉ።”
ክቡር ዶክተር ጌታቸዉ ሃይሌ ለዚሁ ሲመልሱ እንዲህ ሲሉ እርቃኑን አስቀሩተዉታል።
{ “በደራሲዉ አስተሳሰብ የብሔር ማወቂያ (ባንዴራዉ) ቋንቋዉ ነዉ።በኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ ቋንቋዎች ስላሉ ብሔረሰቦችም ቁጥራቸዉ በዚያዉ ልክ ሊሆን ነዉ-- ከዚያም ላይበልጥ ከዚያም ላያንስ። በ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ቋንቋ ብቻ ቢኖር ኖሮ ቢሔርተኝነታችን ኢትዮጵያዊ ብቻ ይሆን ነበረ ሊል ነዉ። በብሔረተኝነት የሚጫረሱ ሶማሌዎች የሚናገሩት አንድ ቋንቋ እንደሆነ ደራሲዉ ያዉቅ ይመስለኛል። ሰዉ ጎሳቸዉን (ብሔራቸዉ) አንድ ያደርግባቸዋል እንጂ እነሱ ቢጠይቋቸዉ ሱማሌነታቸዉ ቢያምኑም ጎሳችን አንድ ነዉ አይሉም። ተጠራቅማችሁ አንድ ብሔር፤ አንድ ሕዝብ፤አንድ አገር፤አንድ መንግሥት ሁኑ ብላ ያስቸገረቻቸዉ እንደ አቶ አንዳርጋቸዉ የምታስብ እንግሊዝ ናት። ዩጎዝላቢያ ዉስጥ በብሔረተኝነት የሚተላለቁት ሰርቦች፤ክሮዋቶች ቦዝኒያዉያን በቋንቋ አንድ ናቸዉ። ግን አንድ ጎሳ (አንድ ብሔር) ነን አላሉም። የብሔረተኝነት ምንጩ ቋንቋ ብቻ ቢሆን አይሪሾች ግማሾቹ ከእንግላንድ ጋር መሆኑንን ሲመርጡ ሌሎቹ መለይትን አይመርጡም ነበረ። አሜሪካና ካናዳ ሁለት አገር ሁለት መንግሥት ባልሆኑም ነበር።ጌርማኒያንና ነምሳ ሁለት አገር፤ሁለት መንግሥት ባለሆኑም ነበር። የአሜሪካን ዩሁዲዎች ቋንቋቸዉ እነደሌላዉ የአሜሪካ ሕዝብ እንግሊዝኛ ነዉ። የኦሮሞ ጎሳዎችን ጨፍልቆ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር) የሚያደርጋቸዉ ሃይል አስካልመጣ ድረስ ቋንቋቸዉ አንድ ስለሆነ ብቻ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር)ናቸዉ ማለት የሌለዉን አለ ብሎ መናገር ነዉ። ጎንደሬዉንና ጎጃሜን የሚናገረዉ ቋንቋ አንድ ስለሆነ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር) ማድረግ ከነሱ የተለየ ቋንቋ የሚናገረዉን ትግሬዉን በቋንቋዉ ከጎንደሬዉ ይለያል ማለትን ያስከትላል። የእንግዲሁን አናዉቅም አንጂ አስከ ዛሬ እንዲህ አልነበረም።”
አንዳረጋቸዉ ጽጌ (በመጽሓፉ በገጽ 12 ላይ) እና የዛዉ ፍልስፍና ደቀመዛሙረቱም ጭምር እንደሚሉት “በኢትዮጵያ ብሄረተኝነትም ይኖራል። የብሄረተኝነት መፈጠር የራሱ መሠረት ስላለዉ ብቻ እንጂ በጉትጎታና በቅስቀሳ የመጣ አይደለም።” በማለት ጭልጥ ያለ ዉሸቱን/ታቸዉን አዲሱን ትዉልድ መርዙን ሊግቱት ሞክረዋል። ሃቁ ግን እሱ አይደለም።
ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ የሚከተለዉ ያስተምሩናል፦
{እዉነታቸዉ ግን በጉትጎታና በቅስቀሳ የመጣብን እዳ ነዉ። የደራሲዉን አስተያየት የሚቀበል በኢትዮጵያ የብሔረተኝነት ታሪክ የማያዉቅ ሰዉ ነዉ።ታሪኩን የሚያዉቅ (እንዲያዉም ራሷን ይቺን ቁንጽል መጽሐፍ በጥሞና የሚያነባት) በኢትዮጵያ ብሔረተኝነት የተፈጠረዉ በሻዕቢያ አምላክነት እነደሆነ አይሰወረዉም።አፈጣጠሩም ብዙዎች ደጋግመዉ እንደጻፉትና እንደተናገሩት “ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የሚቻለዉ የኢትዮጵያን ሕዝብ በብሔረተኝነት በማተራመስ ነዉ” በሚል ፍልስፍና ነዉ። ሻዕቢያ ሐሳቡን ያገኘዉ ከቅን ገዢዉዎች ነዉ። ቅን ገዢዎች ኢትዮጵያን ለመግዘት አለዚያም ለማዳከም ሚቻለዉ በሃገሩ ላይ ብሔረተኝነትን እሳት በማቀጣጠል ብቻ ነዉ። ብለዉ በጊዜዉም ተጠቅመዉበታል። ዛሬ ኤርትራ ራሷን የምትችል ሀገር ብትሆንልን በሃገራችን የጎሰኝነት ጉዳይ ገብ ይልልን ነበር።ኤርትራ ረሷን አስካልቻለች (ግን የምትችል አይመስልም፡ ሐረግ ሬሳይቱ ያለዋርካዉ ድጋፍ ራሷን ችላ አልቆመችም፡) ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ በዲሞክራሲ አስካልተዳደረ ድረስ ሻዕቢያና ወያኔ ቅድሚያ ሚሰጡት ሀገሪቱን ለማዳበር ሳይሆን ጎሰኝነትን ለማፋፋም ነዉ። ከሁሉ አስቀድመን መገንዘብ ያለብን ብሔረተኝነት ከዉጭ የመጣ ሓሳብ እንጂ እኛ ኢትዮጵያዉያን ከጥንት ጀምሮ የምንወግነዉ ለሀገራችንና ለሃይማኖታችን ነዉ። ብሔረተኝነት አለ ቢባል ሃይማኖታዊ ግፋ ቢል ጎጣዊ ነዉ። ካዲሰቱ ኢትዮጵያ ይጠበቅ የነበረዉ ሃይማኖትን የግል ብቻ አድርገን ዉገናችንን በሀገር ላይ ብቻ ነበር። ….አሁን ግን “ጎሳ የጋራ፤ሃይማኖት የሚያጣላ፤ሀገር የግል” የሚል ፈሊጥ ሊያመጡብን ነዉ። }
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነዉ ባጭሩ በማያሻማ ተብራርቷል። በመጨረሻ ምሁሩ ሲያብራሩ ለመሆኑ ይህ ዛሬ ብሔር እየተባለ የሚጠቀስ የዘመኑ ቃል ባገሪቷ ቋንቋ አጠቃቀም ብሔር ስንል ትርጉሙ ምን ማለት ነዉ?
አሁንም ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ፦
“ብሔር/ብሔረስብ የሚባለዉ ቃል በዛሬ ትረጉሙ በቋንቋችን አልነበረም። የተፈጠረዉ አሁን በኛ ዘመን ነዉ። የፈጠሩትም የ ኢትዮጵያ አንድነት ጠላቶች ናቸዉ። እዚሁ ሀገራችን ዉስጥ የበቀለ ቢሆን ኖሮ ሀገራችን ዉስጥ እንደበቀለዉ እንደማንናቸዉም ነገር ሁሉ ስም ይዞ እናገኘዉ ነበር፦…” ይሉና አስቀድመን የጠቀስነዉ “የአማራዉ ሕዝብ ከየት ወዴት” መጽሐፍ ደራሲ “አንዳርጋቸዉ ጽጌ” እና የዛሬዎቹ ማርክሲስቶች ስለብሔር ያላቸዉ የተሳሳተ ትርጉም ፕሮፌሰሩ ሲገልጹ፦ ደራሲዉ
ብሄር ሲባል ከቀጥታ ትርጉሙም ከስሜቱም ተነስተን በምዕራፍ 1 ከቀረበዉ ሀተታ ጋር አገናዝበን ስናየዉ ኦሮሞ ትግሬ አፋር ቢል ትክክልም ተገቢም ይመስላል” ይላል። ተሳስቷል፤ትክክልም ተገቢም አይመስልም፤አይደለምም። “ብሔር” የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ሀገር” ማለት ነዉ። ቃሉ ምድርን እንጂ ሕዝብን አያመለክትም። እንዲህ ከሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ብሔሩን ሲጠይቁት፤ አትዮጵያ፤ ቡልጋ፤ጎንደር ኤሉባቡር፤ መንደፈራ ቢል ምኑ ነዉ “ግር የሚያሰኘዉ”? (ገጽ 14 )? ወደድንም ጠላንም ለዚህ ስንጠቀምባቸዉ የነበሩ ቃላት “ዘር”፤”ነገድ”፤”ጎሳ”፤”ቤት”፤”ወረ” (ለምሳሌ ወረ ቃሉ ወረ ኢሉ ወዘተ)።” ናቸዉ)።
የቋንቋ፤የሐይማኖት፤ እና የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ዘማናዊ ትምሕርት ሊቁ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ያብራሩልንን ባለፉት ወደ አርባ አመታት አንዱ ጎሳ በሌላ ጎሳ ተጠቅቷል እየተባለ በእነ ወያኔዎች እና በተቀሩት ግራኛ ሃይሎች ለዘመናት የተናፈሰዉ/የተሰበከዉ አናካሽ ጽሁፋቸዉ/ቅስቀሳቸዉ አፍራሽ እና ፈሩን የሳተ፤ካገሪቱ ሁኔታ ያልሄደ የተሳሳተ የፖለቲካ መርሆ መሆኑን እላይ በሙሁራን መዝገብ አስደግፌ ለማመብራራት እንደገለጽኩት ደንቃራነቱ የት እንደሆነ ግልጽ እንደሚሆንላችሁ እርግጠኛ ነኝ።ለማጠቃለል፦”ብሔር” ግራኛዎቹ አሁን በሚተረጉሙት መልክ ያገራችን ግዕዝ እንደማያዉቀዉ” ግልጽ ነዉ። “ርዕሰ ብሔር” ሲል የሀገሪቱ/የምደሪቱ መሪ ማለት እንጂ ሌላ ትርጉም እንደሌለዉ እናዉቃለንና የሀገራችን ቋንቋዎች ለፖለቲካቸዉ መጠቀሚያ በማድረግ እያምታቱ ሕዝብን የሚያጋጩ ሁሉ ነቅተን እንጠብቅ። /-/ -*/ ኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅ። www.Ethiopiansemay.blogspot.com

“አሰከ መገንጠል” ሞግዚት ላጣች አገር የተመረጠ የመግደያ መርዝ

አሰከ መገንጠል” ሞግዚት ላጣች አገር የተመረጠ የመግደያ መርዝ ጌታቸዉ ረዳ
ባለፈዉ ርዕሴ ማርክሲዝም እና ሌኒኒዝም አገርንና ሕዝበን አስመልከቶ እነ ዋለልኝ እና ስለተራማጆቹ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በመጠኑ አንስቼ ነበር። የኔ ትንተና እስከ ዕንጥላቸዉ የሞላባቸዉ አንዳንድ ምሁራኖቻችን ላይጥማቸዉ ቢሆንም በዛዉ አንጻር የወደዱት እንደነበሩም ከተላኩልኝ በርከት ያሉ የግል ደብዳቤዎች መረዳት ችያለሁ። ማርክሲዝም መጥፎም ደግም አለበትና እንደ “ሽቱ” አንዱ ሲወደዉ ሌላ ሊጠላዉ ስለሚችል ሁሉም ይረብርበዉ ማለት አይቻለምና በዛዉ እንቀጥል።
ክፍል 1 ትንታኔየ በአንድ ድረ-ገጽ “በማሕደር.ዳት ካም” ብቻ ሲለጠፍ “በአሲምባ እና በደብተራዉ” ድረ-ገጽ ግን የላኩሁላቸዉ መሆነኔን ቢታወቅም “አልወደዱትምና” አንባቢ “ግንዛቤዉ” እንዲያሳርፍበት “አገዱት”። ለምን ለሕዝብ እናዳለቀረቡት ደፍሬ ባልጠይቃቸዉም፤የቁርጥ ቀን ወንድሞቼ ናቸዉና ቅር አላለኝም። ደግነቱ የራሴዉ የሕዋ ሰሌዳ መኖሩ በበቂ አንባቢ መነበቡ ከተዘገቡት የእንግዶች ቁጥር ማወቅ ችያለሁና ክፍል ሁለት የመጨረሻዉ ትንታኔየ ዛሬ ይቀርብና ወደ ሌላ ርዕስ እንሸጋገራለን። ማርክሲስቶች እና ስታሊኒሰቶች አስካሉ ድረስ ዛሬም ኢትዮጵያን በጣረሞት አፋፍ ላይ ሰቅዞ የያዛት ብሔር/ብሐረስብ እስከመገንጠል የሚባለዉ መርዛቸዉ ዛሬም ለወደፊቱም ከመፈታተን ስለማይቦዝን ከሁሉም በፊት በቅድሚያ የሚቀርብ የፖለቲካ አጀንዳ ነዉና ይህነኑ አስመልከቶ እንወያያለን። በዚህ ክርክር ሁሌም እያንዳንዳችን ራሳችንን ማዘጋጀት ይጠበቅብናል።
በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ በአፍሪቃ የማይታወቀዉ እንግዳ የማርክሲሲቶች የብሔሮች፤ብሔረሰቦች፤ሕዘቦች… መብት “አስከ መገንጠል” ፍልስፍና በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እና ግስጋሴ ማርክሲስቶቹ ቀዳሚ መመሪያ አድርገዉ ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ትግል እና ትምርት ሰጥተዋል። በዚህ በኩል በግምባር የሚጠቀሱ በለስ ቀንቷቸዉ ወደ ስልጣን የመጡት እነ ወያኔ እና ለአንድ ዓመት ከምናምን ወራትም ቢሆን አብሮት ስልጣን ላይ ወጥቶ ከፍተኛ ብሔራዊ ጉዳት ያደረሰዉ የሌንጮ ለታ “ሃይማኖት” የነበረዉ “ኦነግ” የተባለዉ ወንጀለኛ የፓለቲካ ድርጅት አማርኛን በላቲንና በዓረብኛ ቋንቋ ተክተዉ የብሔሮች መብት አስከ መገንጠል በሕገመንግሥት አጽድቀዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከህዝቡ መንፈስ እንዲገፈፍ ከፈተኛ ጉዳትና ሚና ተጫዉተዋል። (በነገራችን ላይ ሌንጮ የኮሎኒዉ ጥያቄ ያፍላ ወጣትነት የማርክሲስቶች ንቃተ ሕሊና ቅስቀሳ ስለነበር ዛሬ አርጅቼ ልብ ገዝቻለሁና የኮሎኒዉ ጥያቄ ጥየዋለሁ በማለት በብርሃኑ እና በአንዳርጋቸዉ ራዲዮን በሰጠዉ ቃለ መጠይቅ ማረጋገጡ አንድ እርምጃ ነዉ። አዘጋጁ አፍላ የራዲዮን አዘጋጅ በመሆኑ ወይም ሌንጮንና የኦነግ ታሪክ ካለማወቅ ይመስለኛል “እንደርሶ ያሉት የፖለቲካ ስብዕና የተላበሱ” በማለት ቢያመካሸዉም፤ ሌንጮ ሸርተቴ ነዉና ለማንኛዉም እቀድመን ከመካብ በጊዜ የሚታይ ነዉ ሂደቱን በንቃት እንከታተል)::
ብሔር/ብሔረስብ አስከ-መገንጠል የሚለዉ የስታሊኒስቶች መመሪያ “ኦሪት” ለሆነችዉ አገር የዉጭ ጠላቶች -እና የቆየ የሙሶሊኒ ከፋፋይ መምሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የተወሰነዉ ካሁን በፊት በጦር ሞክረዋት አልሳካ ያለቸዉን መርዛማዉ የመገነጣጠል ሴራቸዉ ዛሬ ያላንዳች የዉጭ አስፈራሪነት በልጆቿ እጅ መርዙን ተግታ/ጠጥታ እንድትሞት ተደርጎ፤ ሞቷ ጊዜ ፈጅቶ ቀስ በቀስ እየኮሰመነች ብሔራዊ ሃይሏ እየተዳከመ ሕዝቦቿ እርስ በርስ በስድብ እየተቦጫጨቁ ጥላቻዉ ተስፋፍቶ መጨረሻ ግብአተ መሬቷ ከጊዜዉ እና ከመንፈስ መዳከም ጋር እንደሚከናወን እየተፈጸሙ ያሉ ሂደቶች እና ሁኔታዎች እያመላከቱን ነዉ። በሴራዉ ምክንያት እርስ በርስ ከመጠላላት አልፎ ያንድ ሀገር ልጆች በሕዝብ ስም በፓለቲካ እና በሐይሞኖት ስም እየተነሱ ሽበር እና ግድያ በመፈጸም ሰዉን ከነ ሕይወቱ ወደ ገደል ገፍትሮ መግደል እና ህጻናት በትምርት ገበታ ላይ እንዳሉ እሳት ለኩሶ መፍጀት፤ ዕዉራን አረጋዊያን ብልታቸዉ በሰላ ተቆርጦ በሙት/ሬሳ አፍ ላይ ማጉረስ፤ እናቶች በቢላዋ ጡታቸዉን መቁረጥ፤እመጫት ህጻንዋን ታቅፋ ከሞት ለማምለጥ ስትሸሽ በጥይት እንደ ዥግራ እያባረሩ መግደል፤ወዘተ፡ በኢትዮጵያ ምድር የታየበት ዋናዉ የጭካኔዉ መነሾዉ ከሰዉ ልጆች ጭካኔ ጋር የተያያዘ ባሕሪያዊ ምንጭ ቢሆንም አንዳንድ ጭካኔዎች ካለመማር ተጨምሮበት ለጭካኔዉ ተጨማሪ ነዳጅ የሚሰጡ አፍራሽ የሆኑ ቅስቀሳዎች ያላስፈላጊ መተላለቅ ሊያስከትል እንደቻለ ከላይ የጠቀስኩዋቸዉ በምደሪቷ የተፈጸሙ ክስተቶች የተጠቀሰዉ የግራኛዉ ፍልስፍና ምንጮች ሰበብ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለተከሰቱት በጥላቻ የመተላለቅ እና የመጠላላት ምንጮች ሁሌም ገዢ መደቦች እና የሥልጣን ጥመኞች በሚከተሏቸዉ መርሆዎች የሚከሰቱ ናቸዉ።
በሙሶሎኒያዉያን ወያኔዎች እና “በግራ አወንዛፊዎቹ”/ክንፎች (ምዉንዛፍ፤ ከሚል የግራ እና የቀኝ የነጠላ አለባበስ መልክ የተጠቀምኩበት የትግርኛ ቃል ነዉ-) (ማርክሲሰስቶች) የፍልስፍና መመሪያ ተመርተዉ የአገሪቱን ሕዝቦች በጎሳ ካፋፍለዉ የአንድነት አርማ የሆነዉን የኢትዮጵያ ገበሬ ለማናቆር ወያኔዎች ወደ ሥልጣን እንደመጡ ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ የተጣደፉበት አጀንዳ አገሪቷን በብሔሮች (አገሮች) እና በብሔረሰቦች ቀጥሎም በነሱ አጠራር “ሕዝቦች” ሁሉ ተደራጅተዉ አስከ መገንጠል ድረስ የሚለዉን መብታቸዉ አንደሆነ ነበር የሰበኩት። ለዚህ ሥራ አስፈጻሚ እንዲሆኑ ለሰበካዉ ከተመዘዙት የወያኔ የፍልስፍና ካድሬዎች ዉስጥ ወያኔን በአምበሳደርነት ያገለገለዉ በጸረ-አማራ ፕሮፖጋንዳዉ “እኝኝ” የሚል ግለሰብ ዛሬ በጥሮታ ተገልሎ በመደበኛ አምደኛነት በወያኔዉ ሰሌዳ በዓይጋ-ፎረም ላይ ዘወትር ስለ ብሔር እና ስለ አማራ ወንድሙ ከሆኑት ከተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ ከደቡቡ ህዝብ ጋር የነበረዉ ግኑኝነት የሻከረ እነደነበረ አድርጎ የሕሊና ደንቆሮዎችና የጥላቻ ቅኔኛዎች የገጠሙትና ያሰላሰሉትን የመሸታ ቤት “ጸረ-አማራ” ምሳሌና ግጥም ለቃቅሞ በህዝቦች ላይ ጥላቻ እንደነበረ አስመስሎ ለወያኔ ፖለቲካ ዉሃ ሲያጠጣ የሚነበበዉ አቶ ተስፋየ ሃቢሶ፦በሽግግሩ ወቅት ወሎ ክፍለ ሃገር ድረስ ሄዶ ገበሬዎችን ለመመረዝ ቅስቀሳ ሲያደርግ፤ ገበሬዎቹ የተናገሩትን በገዛ ብዕሩ ያሰፈረዉ ልጥቀስ እና የወሎ ገበሬዎች በሚከተለዉ አንደበታቸዉ ምዕዳናቸዉ (ረዚዚስታንስ) ለወያኔ ቢያሰሙም እነ ወያኔ እና እነ ኦነጎች ለሕዝብ ከበሬታ የላቸዉምና ዋጋ አልሰጡትም።
ልጥቀስ፦ (እኛ በሽግግሩ ወቅት የብሔር ጥያቄዎችን በተመለከተ በየክልላችን ስንዘዋወር ነበርን። የምናስተምረዉን ትምህርት የሚያዳምጠዉ ሕዝብ ትምህርታችን አልጣመዉም ነበርና አንድ አባት ገበሬ ተቃዉሞአቸዉን በሎሆሳስ ሲገልጡ "ይሄ በብሔር በጎሳ መደራጀት የምትሉት ነገር በተለይም ገበሬዉን አላስደሰተዉም። ልጆቻችን/ ይልቁንስ እኛ ታሪክ እንንገራችሁ። የምታስተምሩትን ነገር ከታሪክ ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮ ጋር አገናዘባችሁ ብታዩት ጥሩ ነዉ። የዱባ ተክል አንድ ቦታ ነዉ የሚበቅለዉ። የሚያብበዉ እና የሚያፈራዉ ግን ተንሰራፍቶ ሄዶ ሌላ ቦታ ለይ ነዉ። ያንን ዱባ ወደ ሗላ ወደ በቀለበት ብትመልሱት ይበሰብሳል። ይሞታል። የኢትዮጵያም ሕዝብ ታሪክ ይኸዉ ነዉ። በመቶ ዓመት ታሪክ ዉስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራዉ ፤ትግሬዉ፤ከንባታዉ ፤ጉራጌዉና፤ወላይታዉ በአሁኑ ጊዜ የሚገኘዉ በመላ ሀገሪቱ ተንሰራፍቶ ነዉ። እስቲ የኛ ሕዝብ ያለበትን ተመልከቱ። ያንን በሀገሪቱ የሞላዉን ሕዝብ በቋንቋና በጎሳ ክልል ብቻ ታጥረህ ተቀመጥ የሚል ትምህርት ብታስተምሩ ሕይወታችን (በዚሁ ጉዳይ ላይ ሲናገሩ) የጥፋት ዘመን መሆኑን ብቻ ነዉ የምታስረዱን" አሉ።
ልላዉ አባት "ብሔረተኝነትና ሐይማኖት በጥንቃቄ ካልተያዘ አደጋ አለዉ። ብሔረተኝነትና አረቄ አንድ ናቸዉ። እና ድሮ አጋሰስ ለመሸጥ ስንፈልግ አጋሰሱን አረቄ እንግተዋለን። ፈረሱ ወዲያዉኑ ጊዜያዊ ጉልበት ያገኝና ጮሌ ሰንጋ ፈረንስ መስሎ አርፍ ይላል። እናም ጥሩ የደረስ ዕቃ ጭነን ወደ ገበያ ወስደን እንሸጠዋለን፡ ያ ፈረስ አረቄዉ ከላዩ ላይ ተንኖ ሲያልቅ ግን ወደ ጌኞነቱ ይመለሳል። ስለዚህ እናነተ አሁን የምታስተምሩን ነገር ከሕዝቡ ጥቅም አንጻር የሚያዋጣ ስላይደለ ይህን መሰሉን ትምህርት ከእኛ ብታርቁልን እንመርጣለን" ብለዋል። ሲል ሕዘቡ በቋንቋ፤በጎሳ… መደራጀቱ አደገኛነቱ ገና ከጥንቱ ከጥዋቱ ያስጠነቀቃቸዉ ቢሆነም አገሪቷ ሞግዚት ያጣች አገር ነበረችና እንዲገድሉዋት ከጠላቶቿ ከነ ሞሶሎኒ የተሰጣቸዉን መርዝ ያግቷት ጀመር።
ያ ሁሉ ሆኖም ወያኔ እና የጎሳ አቀንቃኞች ምኑ ያክል ቢጥሩም ዉጭ ሲጓዙ ማን ብሎ እንደሚጠራቸዉ ካደሬዎቻቸዉ ሳይቀሩ እንዲህ ሲሉ ይመሰክራሉ፦ “በአሁን ጊዜ ወዴትም አገር ብንሄድ <አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ?” ይላሉ እንጂ እንተ “አማራ፤አሮሞ አንተ ወላይታ ወይም ትግሬ ብሎም የሚጠራን የለም።…….” (ተስፋየ ሓቢሶ) የአፍሪካ ሰላምና የግጭት ማነጅመንት ጥናት መዕከል ሰኔ 30 ቀን 1993 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሕዝቦች የመወራረስ ታሪክ ላይ ዉይይት ተካሂዶ በነበረበት ወቅት ከተገኘዉ ሰነድ።
ለመሆኑ ይሄ ብሔር ብሔረስብ የሚባል ቃል ማርክሲሲቶቹ እና ወያኔዎች እንደሚተረጉሙት ያገራችን የቋንቋ ጠበብት የሚተረጉሙት እንደነሱ ነዉ? አስፈላጊ ሆኖ አግንቸዋለሁና አንድ ነገር ሲተረጎም የቃሉ ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ከአገሬዉ ቋንቋ ጋር ካልሄደ የተሳሳተ የዉጭ ትርጉም ተይዞ ለጥፋት ስለሚዉል የቃላቱ አተረጓጎም ትከክለኛነቱ እና ስሕተቱን ለማወቅ ይረዳን ዘንዳ በአገር ወዳድ እና በአንድነት ሃይሎች የተወገዘዉ ጎሰኝነትን ከትዉልድ ትዉልድ አስተላልፎ ለማለፍ ከከጀለዉ ከእዉቁ ከጎሰኛዉ የወያኔዉ ምክትል ያዲስ አበባ ከንቲባ፤እና “የወያኔዉ ያማርኛ ፕሮፖጋንዳ ክፍል” የሚባለዉ የኢሕአዴን/“ብአዴን” ታጋይ የነበረዉ “የአማራዉ ሕዝብ ከየት ወዴት” መጽሐፍ ደራሲ “እንዳርጋቸዉ ጽጌ” በጻፈዉ ጸረ አማራ እና ጸረ-ኢትዮጵያዊነት መጽሐፉ ለመተቸት በሞረሽ ቅጽ 2 ቁጥር 2 (1986) የቋንቋ እና የተለያዩ ዘመናዊ እና ጥንታዊ ትምርቶች ጠቢብ የሆኑት ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ቋንቋ እና ብሔርን በሚመለከት አንዳረጋቸዉም ሆነ ወያኔዎች በተሳሳተ መንገድ እንዴት እንደሚተረጉሙት እና ራሳቸዉን አሳስተዉ አዲሱን ትዉልድ እንዴት እንዳሳሳቱት የአመራዉ ሕዝብ ከየት ወዴት” ደራሲ የለበሰዉን አደናጋሪ የዉሸት ልብስ ፕሮፌሰሩ ሲያጋልጡት እንመልከት። (ብሔር የመታወቂያ ባንዴራ) በሚል ንኡስ ርዕስ እንዲህ ይላሉ። ደራሲዉ የተቃዋሚዉን አፍ ለማስያዝ የሞከረዉ ገጽ 7-8 ላይ ባሰፈራቸዉ ከዚህ በታች ባሉት ቃላት ነዉ፦ “በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሰባ የሚበልጡ ብሄር ብሄረሰቦች መኖራቸዉ ተቀብለዉ ነገር ግን ብሄረተኝነት ጥያቄ ሲመልሱ በኢትዮጵያ ሚገኘዉ ብሄረተኝነት አንድ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት ብቻ ነዉ የሚሉ አልታጡም። እንዲህ የሚሉ ሃይሎች ሊመልሱት የማይችሉት ጥያቄ አለ። ብሄረተኝነቱ ኢትዮጵያዊ ከሆነ ምን ዓይነት ቋንቋ ባህል ታሪክ ወግ፤ወዘተ፡ በአጭሩ ይዘቱ ምን ይሆናል የሚለዉን ነዉ።”
ክቡር ዶክተር ጌታቸዉ ሃይሌ ለዚሁ ሲመልሱ እንዲህ ሲሉ አርቃኑን አስቀሩተዉታል። { በደራሲዉ አስተሳሰብ የብሔር ማወቂያ (ባንዴራዉ) ቋንቋዉ ነዉ።በኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ ቋንቋዎች ስላሉ ብሔረሰቦችም ቁጥራቸዉ በዚያዉ ልክ ሊሆን ነዉ-- ከዚያም ላይበልጥ ከዚያም ላያንስ። በ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ቋንቋ ብቻ ቢኖር ኖሮ ቢሔርተኝነታችን ኢትዮጵያዊ ብቻ ይሆን ነበረ ሊል ነዉ። በብሔረተኝነት የሚጫረሱ ሶማሌዎች የሚናገሩት አንድ ቋንቋ እንደሆነ ደራሲዉ ያዉቅ ይመስለኛል። ሰዉ ጎሳቸዉን (ብሔራቸዉ) አንድ ያደርግባቸዋል እንጂ እነሱ ቢጠይቋቸዉ ሱማሌነታቸዉ ቢያምኑም ጎሳችን አንድ ነዉ አይሉም። ተጠራቅማችሁ አንድ ብሔር፤ አንድ ሕዝብ፤አንድ አገር፤አንድ መንግሥት ሁኑ ብላ ያስቸገረቻቸዉ እንደ አቶ አንዳርጋቸዉ የምታስብ እንግሊዝ ናት። ዩጎዝላቢያ ዉስጥ በብሔረተኝነት የሚተላለቁት ሰርቦች፤ክሮዋቶች ቦዝኒያዉያን በቋንቋ አንድ ናቸዉ። ግን አንድ ጎሳ (አንድ ብሔር) ነን አላሉም። የብሔረተኝነት ምንጩ ቋንቋ ብቻ ቢሆን አይሪሾች ግማሾቹ ከ እንግላንድ ጋር መሆኑንን ሲመርጡ ሌሎቹ መለይትን አይመርጡም ነበረ። አሜሪካና ካናዳ ሁለት አገር ሁለት መንግሥት ባልሆኑም ነበር።ጌርማኒያንና ነምሳ ሁለት አገር፤ሁለት መንግሥት ባለሆኑም ነበር። የአሜሪካን ዩሁዲዎች ቋንቋቸዉ እነደሌላዉ የአሜሪካ ሕዝብ እንግሊዝኛ ነዉ። የኦሮሞ ጎሳዎችን ጨፍልቆ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር) የሚያደርጋቸዉ ሃይል አስካልመጣ ድረስ ቋንቋቸዉ አንድ ስለሆነ ብቻ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር)ናቸዉ ማለት የሌለዉን አለ ብሎ መናገር ነዉ። ጎንደሬዉንና ጎጃሜን የሚናገረዉ ቋንቋ አንድ ስለሆነ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር) ማድረግ ከነሱ የተለየ ቋንቋ የሚናገረዉን ትግሬዉን በቋንቋዉ ከጎንደሬዉ ይለያል ማለትን ያስከትላል። የእንግዲሁን አናዉቅም አንጂ አስከ ዛሬ እንዲህ አልነበረም።”
አንዳረጋቸዉ ጽጌ (በመጽሓፉ በገጽ 12 ላይ) እና የዛዉ ፍልስፍና ደቀመዛሙረቱም ጭምር እንደሚሉት “በኢትዮጵያ ብሄረተኝነትም ይኖራል። የብሄረተኝነት መፈጠር የራሱ መሠረት ስላለዉ ብቻ እንጂ በጉትጎታና በቅስቀሳ የመጣ አይደለም።” በማለት ጭልጥ ያለ ዉሸቱን/ታቸዉን አዲሱን ትዉልድ መርዙን ሊግቱት ሞክረዋል።
ሃቁ ግን እሱ አይደለም።ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ እንዲህ ይላሉ፦
{እዉነታቸዉ ግን በጉትጎታና በቅስቀሳ የመጣብን እዳ ነዉ። የደራሲዉን አስተያየት የሚቀበል በኢትዮጵያ የብሔረተኝነት ታሪክ የማያዉቅ ሰዉ ነዉ።ታሪኩን የሚያዉቅ (እንዲያዉም ራሷን ይቺን ቁንጽል መጽሐፍ በጥሞና የሚያነባት) በኢትዮጵያ ብሔረተኝነት የተፈጠረዉ በሻዕቢያ አምላክነት እነደሆነ አይሰወረዉም።አፈጣጠሩም ብዙዎች ደጋግመዉ እንደጻፉትና እንደተናገሩት “ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የሚቻለዉ የኢትዮጵያን ህዝብ በብሔረተኝነት በማተራመስ ነዉ” በሚል ፍልስፍና ነዉ። ሻዕቢያ ሐሳቡን ያገኘዉ ከቅን ገዢዉዎች ነዉ። ቅን ገዢዎች ኢትዮጵያን ለመግዘት አለዚያም ለማዳከም ሚቻለዉ በሃገሩ ላይ ብሔረተኝነትን እሳት በማቀጣጠል ብቻ ነዉ። ብለዉ በጊዜዉም ተጠቅመዉበታል። ዛሬ ኤርትራ ራሷን የምትችል ሀገር ብትሆንልን በ ሃገራችን የጎሰኝነት ጉዳይ ገብ ይልልን ነበር።ኤርትራ ረሷን አስካልቻለች (ግን የምትችል አይመስልም፡ ሐረግ ሬሳይቱ ያለዋርካዉ ድጋፍ ራሷን ችላ አልቆመችም፡) ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ በዲሞክራሲ አስካልተዳደረ ድረስ ሻዕቢያና ወያኔ ቅድሚያ ሚሰጡት ሀገሪቱን ለማዳበር ሳይሆን ጎሰኝነትን ለማፋፋም ነዉ። ከሁሉ አስቀድመን መገንዘብ ያለብን ብሔረተኝነት ከዉጭ የመጣ ሓሳብ እንጂ እኛ ኢትዮጵያዉያን ከጥንት ጀምሮ የምንወግነዉ ለሀገራችንና ለሃይማኖታችን ነዉ። ብሔረተኝነት አለ ቢባል ሃይማኖታዊ ግፋ ቢል ጎጣዊ ነዉ። ካዲሰቱ ኢትዮጵያ ይጠበቅ የነበረዉ ሃይማኖትን የግል ብቻ አድርገን ዉገናችንን በሀገር ላይ ብቻ ነበር። ….አሁን ግን “ጎሳ የጋራ፤ሃይማኖት የሚያጣላ፤ሀገር የግል” የሚል ፈሊጥ ሊያመጡብን ነዉ። }
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነዉ ባጭሩ እና በማያሻማ ተብራርቷል። በመጨረሻ ምሁሩ ሲያብራሩ ለመሆኑ ይህ ዛሬ ብሔር እየተባለ የሚጠቀስ የዘመኑ ቃል ባገሪቷ ቋንቋ አጠቃቀም ብሔር ስንል ትርጉሙ ምን ማለት ነዉ? አሁንም ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ፦ “ብሔር/ብሔረስብ የሚባለዉ ቃል በዛሬ ትረጉሙ በቋንቋችን አልነበረም። የተፈጠረዉ አሁን በኛ ዘመን ነዉ። የፈጠሩትም የ ኢትዮጵያ አንድነት ጠላቶች ናቸዉ። እዚሁ ሀገራችን ዉስጥ የበቀለ ቢሆን ኖሮ ሀገራችን ዉስጥ እንደበቀለዉ እንደማንናቸዉም ነገር ሁሉ ስም ይዞ እናገኘዉ ነበር፦…” ይሉ እና አስቀድመን የጠቀስነዉ “የአማራዉ ሕዝብ ከየት ወዴት” መጽሐፍ ደራሲ “አንዳርጋቸዉ ጽጌ” እና የዛሬዎቹ ማርክሲስቶች ስለብሔር ያላቸዉ የተሳሳተ ትርጉም ፕሮፌሰሩ እንዲህ ሲሉ ያብራሩልናል።
ደራሲዉ “ብሄር ሲባል ከቀጥታ ትርጉሙም ከስሜቱም ተነስተን በምዕራፍ 1 ከቀረበዉ ሀተታ ጋር አገናዝበን ስናየዉ ኦሮሞ ትግሬ አፋር ቢል ትክክልም ተገቢም ይመስላል” ይላል። ተሳስቷል፤ትክክልም ተገቢም አይመስልም፤አይደለምም። “ብሔር” የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ሀገር” ማለት ነዉ። ቃሉ ምድርን እንጂ ሕዝብን አያመለክትም። እንዲህ ከሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ብሔሩን ሲጠይቁት፤ አትዮጵያ፤ ቡልጋ፤ጎንደር ኤሉባቡር፤ መንደፈራ ቢል ምኑ ነዉ “ግር የሚያሰኘዉ”? (ገጽ 14 )? ወደድንም ጠላንም ለዚህ ስንጠቀምባቸዉ የነበሩ ቃላት “ዘር”፤”ነገድ”፤”ጎሳ”፤”ቤት”፤”ወረ” (ለምሳሌ ወረ ቃሉ ወረ ኢሉ ወዘተ)።” ናቸዉ)።
እንግዲህ የቋንቋ፤የሐይማኖት፤የፖለቲካ እና የማሕበራዊ ዘርፍ ሊቁ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ያብራሩልንን እንደተመለከታችሁት አንዱ ጎሳ በሌላ ጎሳ ተጠቅቷል እየተባለ በእነ ወያኔዎች እና በተቀሩት ግራኛ ሃይሎች ለዘመናት የተናፈሰዉ/የተሰበከዉ አናካሽ ጽሁፋቸዉ/ቅስቀሳቸዉ አፍራሽ እና ፈሩን የሳተ፤ካገሪቱ ሁኔታ ያልሄደ የተሳሳተ የፖለቲካ መርሆ መሆኑን እላይ በሙሁራን መዝገብ አስደግፌ ለማመብራራት እንደገለጽኩት ደንቃራነቱ የት እንደሆነ ግልጽ እንደሚሆንላችሁ እርግጠኛ ነኝ።ለማጠቃለል፦”ብሔር” ግራኛዎቹ አሁን በሚተረጉሙት መልክ ያገራችን ግዕዝእንደማያዉቀዉ” ግልጽ ነዉ። “ርዕሰ ብሔር” ሲል የሀገሪቱ/የምደሪቱ መሪ ማለት እንጂ ሌላ ትርጉም እንደሌለዉ እናዉቃለንና የሀገራችን ቋንቋዎች ለፖለቲካቸዉ መጠቀሚያ በማድረግ እያምታቱ ሕዝብን የሚያጋጩ ሁሉ ነቅተን እንጠብቅ። /-/ -*/ ኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅ:: Ethiopiansemay.blogspot.com