Saturday, November 15, 2008

(በቅርቡ በአንድ ኤርትራዊ ይፋ የሆነዉ አዲስ የምስጢር ሰነድ)

(በቅርቡ በአንድ ኤርትራዊ ይፋ የሆነዉ አዲስ የምስጢር ሰነድ) ጌታቸዉ ረዳ ግባችን ከወዲሁ መጪዉን አስፈሪዉ ዳመና መበተን ነዉ!!! ከዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ
መግቢያ-በጌታቸዉ ረዳ-
ከላይ በኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ የተለጠፉት ፎቶ ግራፎቹ መንግሥቱ ሃይለማርያም እና ኒሜሪን በመገልበጥ ስልጣናቸዉን በገዛ ራሳቸዉ ለመራጩ ሕዝብ በማስረክብ የተመሰገኑት የሱዳን ፕረዚዳንት ጀኔራል ሱዋር ዳሃብ፤ ከሳቸዉ ቀጥሎ የመጣዉ ሳድቅ አልማህዲ፤ ቀጥሎ የሱዳኑ ያሁኑ ፕረዚዳንት የሆኑት አል በሽር ፤፤ዶ/ር አልቱራቢ፤ኢሳያስ አፈወርቅ፤ ሰሎሞን ጴጥሮስ እና ቡጥሮስ ቡጥሮስ ጋሊ መለስ ዜናዊ፤ ጂሚ ካርተር እና ሄርሞን ኮሄን ናቸዉ።
ከላይ የተመለከተዉ ርዕስ “ዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ” በተባሉ ኤርትራዊ በትግርኛ ተጽፎ Assena.com በመባል የሚታወቀዉ የኤርትራዉያኖቹ የህዋ ሰሌዳ በOctober, 2008 (ከዚህ ጀምሮ ዘመኖቹ የሚቀርቡት በአዉሮጳዉያን አቆጣጠር ነዉ) “ግባችን የመጪዉን አስፈሪ ዳመና መበተን ነዉ!!!” በሚል ርዕስ የቀረበዉን የአሜሪካኖቹ የስለላ ማዕከል (CIA) በኢትዮጵያ ሠራዊት እና አገራቸዉን ከድተዉ ለCIA እሽክርና ያደሩት የትግራዩ “የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” እና የኤርትራዉ “ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ” መሪዎች ከCIA ወቅታዊ የሆኑ ወታደራዊ የስለላ መረጃዎችን በማግኘት እንዴት ለድል እንደበቁ ሲገልጽ፤በሌላ በኩል ደግሞ ከCIA በተሰጠዉ መመሪያ መሠረት የኤርትራዉ ህዝባዊ ግምባር መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ የኢትዮጵያ እና የሱዳን መንግሥቶች ለመገልበጥ ያቀነባበራቸዉ የመንግሥት ግልበጣዎችን ይፋ ያደረጉልንን ሚስጥራዊ ሰነድ ወደ አማርኛ ተርጉሜ አቀርብላችሗለሁ። በትረጉሙ ላይ ስህተቶች ቢኖሩ ሃለፊነቱ የነዉ የተርጓሚዉ እንጂ የአቶ ዉሕሉል እንዳልሆነ ስገልጽ፡ ሰነዱ ይፋ እንዲሆን አስበዉ ላቀረቡልን ለጸሐፊዉ ለአቶ ዉሕሉል ፈዳይ ንጉሥ በእኔ እና “በኢትዮጵያን ሰማይ ” አንባቢዎች ስም ሳመሰግን፡ አያይዞም በሕዝባዊ ግምባር (ሻዕቢያ) ተማርከዉ የነበሩት የኢትዮጵያ ሠራዊቶች አንዳንዶቹ የት እንደደረሱ ለኛ ፍጹም አዲስ የሆነብን ሌላ ሚስጢር ጸሐፊዉ ያቀረቡትንም በሌላ ጊዜ ለማቅረብ በዚሁ እመለስበታለሁ።www.ethiopiansemay.blogspot.com
ግባችን ከወዲሁ መጪዉን አስፈሪዉ ዳመናን መበተን ነዉ!!!
(የሰሜን አትላንቲክ ኔቶ አዛዥ ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ፋን ቤንጃንኩዝ)
ሰሞኑን ለዓለም በተለይም ደግሞ ለአገራችን እና ለአፍሪቃ ቀንድና የቀይ ባሕር ተጓዳኝ አገሮች በተለይ ለ ኤርትራዉያን እያሳሰባቸዉ ባለዉ ሁኔታ አስመልከቶ ስጽፍ የሰሜን አትላንቲክ (ኔቶ) ዋና አዛዥ ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ፋን ቤንጃንኩዝ ወደ ቀይ ባሕር ባደረገዉ ጉዞ ላይ በ12/10/08 ያደረገዉ ንግግር ተመርኩዤ ያለኝን መረጃ ለማካፈል የአካባቢዉን ፖለቲካና ወታደራዊ ሁኔታዎችን አስመልክቼ ስተነትን፡ለጽሁፌ መነሻ ያደረግኩት የቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ቤንጃንኩዝ “ግባችን ከወዲሁ መጪዉን አስፈሪዉ ዳመናን መበተን ነዉ!!! በማለት ያደረገዉን ንግግር ተመርኩዤ ነዉ።” መልካም ንባብ_
ክፍል 1
በሁለቱም ሃያላን መንግስታት ማለትም በአሜርካን እና ሶቭየት ህብረት በመባል ሰትታወቅ የነበረችዉ/ሩሲያ/ መሃል የነበረዉ የፖለቲካ፤የምጣኔ ሃብት እና የስነ ሃሳብ የበላይነት ፍትጊያ የፈጠረዉ ዉጥረት ፕሮስትራይካ በመባል የሚታወቀዉ በሚኻኤል ጎርቫቸፍ አማካይነት የተከሰተዉ የቀዝቃዛዉ ጦርነት ለዉጥ አስቀድሞ ከመምጣቱ በፊት የቀይ ባሕር አዋሳኝና እና አካባቢዉ 5ኛ መርከብ ተብሎ በሚጠራዉ ማዕከሉ በዲያጎ ጋርሲያ ያደረገዉ በሪድ አድሚራል ጆን ላት አሌክስ እዝ ሲመራ የነበረዉ የአሜሪካዉ የባሕር ሃይል ነበር ሲቆጣጠረዉ የነበረዉ።
በሌላ በኩል ደግሞ “ቀይ-ነብር” በመባል የሚጠራዉ የሶቭየት ሕብረት ሠራዊትም በቺፍ አድሚራል ኪዮሎቪስኪ ሻሮቨክ አመራር ማዕከሉ ዳህላክ ደሴት በማድረግ ሠፍሮ ሁለቱም ወገኖች ታጥቀዉት በነበሩት የተለያዩ አደገኛ የጦር መሣሪያዎች ተፋጥጠዉ ይተያዩ የነበረበት ወቅት ነዉ።
ወቅቱ በሶቭየት ሕብረት ሕለዉና አሜሪካኖች አና አጋሮቿ ግምባር ሲደረግ የነበረዉ ጣልቃ ገብነት ሩሲያን ከሥር መንግሎ ለማዳከም ጥሮ ብዙ ባይሳካለትም በሚካኤል ጎርቫቸፍ በኩል በ1986ቱ መገባደጃ የተጀመረዉ አዝጋሚ ለዉጥ በ1989 ላይ ፕሮስትራይካ በመባል የታወቀዉ የፖለቲካ ለዉጥ የሩስያን ህልዉና ብቻ ሳይሆን የለወጠዉ ከተቀሩት ተፎካካሪዎች አስቀምጧት የነበረዉን የሃይል ሚዛንዋን ጭምር ክፉኛ ስላዛባዉ የግሎባላይዘሽን ተቆጣጣሪነቱ የበላይነቱ ወደ አሜሪካ በማዘንበሉ፡ የዓለም ጸጥታ ፖሊሲ ጉዳይና ቁጥጥር በአሜሪካን እጅ እንዲነደፍ ክፍተት ፈጠረ።
በዚህ ወቅት ዳህላክ ደሴት ሰፍሮ ነበረዉ ሶቭየት ሕብረት ጦር ቀደም ብሎ ባጋጠመዉ ዉስጣዊ የሩስያ እዝጋሚ የፖለቲካ ማዕበል ሠራዊቶቹን ከአካባቢዉ ማስወጣት የጀመረ ቢሆንም፤በወቅቱ የ ኢትዮጵያ ክፍለሃገሮች ተብለዉ ሲታወቁ የነበሩት በኤርትራ እና በትግራይ የተመሰረቱት ሁለት የሽምቅ ተዋጊ ሃይሎችን ለመረዳት CIA በአካባቢዉ የሰፈረዉ የሶቭየት ሃይልን ለመቀናቀን ሲል ኤርትራ ዉስጥ ለኤርትራ ሐርነት ህዝባዊ ግምባርን የስለላ መረጃ በማቅረብ አፍዓበት ላይ ሰፍሮ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንዲጠቃ ሲያደርግ፦በትግራይም ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የስለላ መረጃ በማቀበል፤ እንዳባጉና (ሽሬ አዉራጃ-ትግራይ ዉስጥ) ላይ ሰፍሮ ዘመናዊ የስለላ መሣሪያዎች ታጥቆ በነበረዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይም አመርቂ ጥቃት እንዲፈጽሙ አስችሏቸዋል።
ቀደም ብሎ በ1984 በህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ እና በህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ መካከል የነበረዉ ግንኙነት ሻክሮ ቅራኔ ዉስጥ በመግባቱ የአሜሪካ የስላላ ማዕከል ድርጅት (CIA) ሁለቱንም አገናኝቶ የጋራ መረጃዎቹን ላማቀበል አስቸጋሪ ስለሆነበት ለጊዜዉም ቢሆን ሁለቱንም ለየብቻ እያነጋገረ አስፈላጊ የሆኑ ወቅታዊ መረጃዎቹን ለማስተላለፍ አማራጭ ብሎ የወሰደዉ ለየብቻ በማነጋገር ነበር። ስለሆነም-በ08/87 እጅግ ወቅታዊና ጠቃሚ የሆኑ ወታደራዊ መረጃዎች ማቅረብ ጀመረ።
የአሜሪካ ቅኝት በኤርትራ የዉሃ አዋሳኞች የሶቭየት ሕብረት መኖር ከወታደራዊ የበላይነቷ ጋር ስላያያዘችዉ፤ሁለቱም በተናጠል እየተረዱ በደርግ ሠራዊት ላይ የማጥቃቱን እርምጃ ሲያፋጥኑ፡በደረሱት ጥቃቶችና በአካባቢዉ የሰፈሩ ሶቭየቶችም ከዉስጥ የሶቭየት የፖለቲካ ቀዉስ ጋር ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ ለቀዉ በመዉጣታቸዉ ደርግም ብቻዉን ቀርቶ እርቃኑ በመዉጣቱ ጋር ተያይዞ በታየዉ ክፍተት አሜሪካን አጋጣሚዉን በመጠቀም በልዩ አጀንዳ ይዛ ክስቱን ወደ ራሷ ጠቀሜታ እንዲዉል በንቃት መንቀሳቀስ ጀመረች። ስለሆነም አሜሪካ በJanuary 19/1989 ሪቻርድ ፈን ዳላስ የተባለ የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ የስላላ ሥራ ተጠሪዋን በመላክ ሱዳን ካርቱም ከተማ ዉስጥ ሜሪዲያን ሆቴል በተባለ ሆቴል የህዝባዊ ግምባር መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ እና የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሪ መለስ ዜናዊ በምስጢር ጠርቶ ሁለቱም የጋራ ወታደራዊ ንድፍ እንዲያወጡና አሜሪካም የለት ተለት ወታደራዊዉና ፖለቲካዊዉ የስላላ መረጃዎች እንደምታቀርብላቸዉና ብሎም ሁለቱም ቡድኖች ህጋዊ ተቀባይነት እንዲኖራቸዉ አሜሪካ እንደምታደርግ ቃል ተገብቶላቸዉ በዚህ ተስማምተዉ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲገናኙ ሆነ።
በተካሄደዉ በዚሁ የስብሰባ ስምምነት ዉጤትም የህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ የፖለቲካ ጽ/ቤት በFebruray 05/1989 አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ በማካሄድ የተባለዉ ንድፍ ተስማምተዉ ሲያሳልፉ- መሳ ለማሳ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይም በFebruary17/1989 አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ተመሳሳይ ዉሳኔ አሳለፈ። ስበሰባዉ በተናጠል ቢካሄድም፤ግቡ ለአንድ ዓለማ ነበር።ይሄዉም የደረግን መገርሰስ እና የኤርትራ ነጻነት ታዉቆ ለዓለም ሕዝቦች ማስተዋወቅ፤አስታክኮም የህዝባዊ ግምባር የአካባቢዉ ወታደራዊ የበላይነት እንዲታይ በር ከፍቶ ደርግን ለመጨረሻዉ ሞት ፈርዶ በሶቭቶች ላይ የመጨረሻዋ በር የሚቆልፍ ስትራተጂ ነበር።
ከዚያ በሗላ በApril 16/1989 የአሜሪካን ፕረዚዳንት የነበሩት ጂሚ ካርተር ሰብሳቢነት መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወረቅ ለሁለተኛ ጊዜ በመሪድያን ሆቴል ተገናኝተዉ፡የጋራ ወታደራዊ ዕቅድ ነደፉ። ቀጥሎም በሕዝባዊ ግምባርን የወከለ እጅግ ምስጢራዊ በሆነ ምደባ አንድ (ግለሰብ) ብቻ ሚስጥራዊ የስለላ መረጃዎችን የሚያከናዉን ሲመረጥ። በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በኩል በሥራ ክፍፍል ያተኮረ ማዕከልነትን ያላተኮረ ነበር።
ወታደራዊ ስትራተጂ፤ ስለላ እና መረጃ አስመልክቶ በመጀመሪያ ስብሰባዉን የመራዉ ከህዝባዊ ግመባር ጴጥሮስ ሰለሞን ሲሆን ቀጥሎ ከትግራይ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ድግሞ ሓየሎም፤ጻድቃን፤ ክንፈ ገብረመድህን እና አሰፋ ገብሩ ናቸዉ።
ሁለቱም ድርጅቶች አስፈላጊዉ መመርያ ከተቀበሉ በሗላ፦በተለይም በጊዘዉ የነበረዉ የሱዳን መንግሥት ለታቀደዉ ወታደራዊ ዕቅድ እንቅፋት እንዳይሆንና እንደሚሆንም ስለታመነበት፡ስጋቱን ለማስወገድ በጊዜዉ በስልጣን የነበረዉ የሱዳን መንገሥት በመፈንቅለ መንግሥት መወገድ አለበት ተብሎ በCIA ስለታመነበት፡ ይህነን ከባድ ሃላፊነትም እንዲሸከም የህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ ኢሳያስ አፈወረቅ ሆኖ፡ ከ1979 ጀምሮ የኢሳያስ አፈወረቅ የቅርብ ወዳጅ የነበረዉ ሱዳናዊዉ ዶክተር ሐሰን አልቱራቢ ግንኙነት ተደርጎ ሱዳን ዉስጥ መፈንቅለ መንግሥት እንዲካሄድ ለኢሳያስ አፈወርቅ መመሪያ ከተሰጠዉ በሗላ፤ ለግንኙነታቸዉ ማጠናከሪያ እንዲሆን ታስቦ የዶክተር ሓሰን አልቱራቢ ልጅ በ1982 ኤርትራ በረሃ ድረስ በመዉስድ በወቅቱ ሒምቦል ተብሎ በሚጠራዊ የህዝባዊ ግምባር የመኪና ጥገና ማዕከል እየሰራ አገልግሎቱ እንዲያበረክት ተብሎ በጥገናዉ ማዕከል ሃለፊ ለነበረዉ አሕመድ መሓመድ በዓልኼር አደራነቱ ተሰጥቶት እንዲሰራ ተደረገ።
ከዚህ የመነጨ ጥብቅ የወዳጅነት መተማመንና ትስስር በመመረኮዝ በኢሳያስ አፈወርቅ እጅ በኩል ተሰጥቶ ሱዳን ዉስጥ የህዝባዊ ግምባር የስለላ እና የመረጃ ቅርንጫፍ የሆነ ምድብ 72 ተብሎ የሚታወቀዉ የስለላ ክፍል ሃላፊ በነበረዉ መልአከ ወዲ አፍተራሪ ለተባለዉ ታጋይ 14 ሚሊዮን ዶላር መፈንቅለ መንግሥቱን ለሚያካሂደዉ ቡድን ሥራዉን ለማከናወን እንዲረዳ ለዶክተር ሐሰን አልቱራቢ እና ለጀኔራል መሐመድ ሑሴን አልበሽር በእጅ እንዲሰጥ ተደርጓል።
መልአከ ወዲ አፍተራሪ እና ካርቱም ዉስጥ በሜሪዲያን ሆቴል አካባቢ ጸጉር አስተካካይ ሆኖ ሲሰራ የነበረ አቶ መብራህቱ ከተባለ ሰዉ ጋር በመተባበር በህዝባዊ ግምባር ተቃዋሚዎች ላይ የግድያ እና የጠለፋ ስራ ሲያካሂድ የነበረ ሰዉ ነዉ። እንደታቀደዉም በህዝባዊ ግምባር አቀነባባሪነት የታቀደዉ የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት ተጠናቅቆ በቦታዉ በጀኔራል ሐሰን አል በሽርና ዶክተር ሐሰን አልቱራቢ የሚመሩት አዲስ መንግሥት ተመሰረተ።
በዛዉ ዓመት ዉስጥ በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ የደርግ መንግሥት ላይ በሕዝባዊ ግምባር ሐርነት ኤርትራ የስለላ እና የመረጃ አቀነባባሪነት ኤርትራ ዉስጥ ከነበረዉ በጀኔራል ደምሴ ቡልቱ በኩል የሚመራዉ የሁለተኛ አብዮታዊ ሠራዊት በመንግሥቱ ሃይለማርያም መንግሥት ላይ ያነጣጠረ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግሥት ሲካሄድ 72 ሰዓት የቆየ የቶክስ ማቆም አዋጅ እርምጃ ወስዶ ነበር።
የኤርትራዉ ህዝባዊ ግምባር በተጠቀሱት ክንዋኔዎች እጁን ሲያስገባ ከአሜሪካ መንግሥት የስለላ ማዕከል ድርጅት (ሲ አይ ኤ) በኩል በተደረሱት የስምመነት ዉሎች መሰረት ነዉ።ከዘያ በመነሳት ነበር የአሜሪካ የስለላዉ ማዕከል (ሲ አይ ኤ) በጦርነቱ ወቅት ከህዝባዊ ግምባር በስተጀርባ በመሆን የሗላ ደጀን ሊሆነዉ የበቃዉ።
በህዝባዊ ግምባር የተካሄደዉ ጠምፅዋዉ የፈንቅል ዘመቻ እና በወያኔ ትግራይ የተካሄደዉ ዘመቻ ዋለልኝ በሗላ በወታደራዊ አነጋገር ደርግ እጁን የሚሰጥበት ዜሮ ሰዓት በመድረሱ፤ሶቭየት ህብረቶቹም በራሳቸዉ ዉስጣዊ ዉጥረት በመጠመዳቸዉ በማይቀረዉ የደርግ ዉድቀት በመመልከት አሜሪካም በአካባቢዉ የህልዉናዋ ሽግግር ድልድይ ሆኖ እዉን ለማደረግ ከነበራት ጉገትና ዕቅድ ጋር ስለተሳካላት ሕዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ በMarch 1981(መጋቢት) ያወጣዉ ባለ 9 ነጥብ አዋጅ የሰላም ጥሪ ተመርኩዞ በApril 16/1989 (ሚያዚያ) ጀምሮ ከኤርትራ ህዝባዊ ግምባር እና ከትግራዩ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጋር እጅግ የጋለ ወዳጅነት መስርቶ የነበረዉ የአሜሪካ ፕረዚደንት በነበረዉ በጂሚ ካርተር በኩል ከደርግ ጋር የዕርቅ በር እንዲከፈት በተደረገዉ የሽንግልና ዉይይት የኤርትራዉ ህዝባዊ ግምባር መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ብቻ ከደርግ ጋር የመነጋገሩ ሁኔታ ሲቀበለዉ የትግራዩ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሪ መለስ ዜናዊ ግን የኢሳያስን አቋም በመቃወም አልደግፍም አለ። የኢሳያስን ሃሳብ ተቃዉመዉ ከመለስ ዜናዊ ሃሳብ ጋር የወገኑት የህዝባዊ ግምባር ከፍተኛ አማራር አባላት ስም ዝርዝርም፦ ማሕሙድ ሸሪፎ ሮሞዳን መሓመድ ኑር ሃይለ ወልደትንሳኤ ጵጥሮስ ሰለሞን ዑቑበ አብራ
ስብሓት ኤፍሬም - -
ከላይ የተጠቀሱት የኤርትራ ጉዳይ ከወያነ ሃርነት ትግራይ ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ስለሌለዉ ለየብቻቸዉ አጀንዳ ከተያዘላቸዉ ከደርግ ጋር እንወያያለን ካለዉ የወያኔዉ መሪ የመለስ ዜናዊን ሀሳብ ደግፈዋል።
ከዛዉ አቋም ከመነጨ ሃሳብ ነበር ታሳቢ አድርጎ የኤርትራን የነጻነት ጉዳይ በአትላንታ በኬኒያ በኢንግላንድ በጣሊያን አጀንዳ ተይዞለት እንዲቀጥል የተደረገዉ።ይህንን በሚመለከት ራሱን የቻለ አሰራር ተከትሎ በአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ጉዳይ ከፍተኛ ባለስልጣንና የCIA አባል በነበረዉ በሄርማን ኮሃን በመለስ ዜናዊ እና በኢሳያስ አፈወርቂ ጋራ የግል ስምምነታቸዉን በመፈጸም መጀመሪያ በግንቦት-May12 እስከ 17/1991፡ በሁለተኛዉ ዙር ደግሞ በሰኔ (June) 11 አስከ 16 ተካሄዶ ባለ 11 ነጥብ የያዘ ሰምምነት ተፈራረሙ። የሰነዱ ዝርዝር ፍሬ ነገሮች እንደሚከተለዉ ነዉ።- ይቀጥላል፡……

No comments: