Monday, February 19, 2018


የአክራሪነትና የጽንፈኝነት ቅኝት የተጠናወታቸው የፓለቲካ እንቅስቃሴዎች ባህርያት
በዶክተር አሰፋ ነጋሽ - 
(በሆላንድ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ)
Email address: Debesso@gmail.com

ክፍል አንድ፡

በዓለም ታሪክ ውስጥ ጽንፈኛነትንና አክራሪነትን የሚያራምዱ እንቅስቃሴዎች በፓለቲካ ድርጅት፤ በብሄረተኛ ድርጅትና በሃይማኖታዊ ድርጅት ሥም ሲካሄዱ ታይተዋል። እነዚህን ጽንፈኛነትንና አክራሪነትን መመሪያቸው አድርገው የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች፤

ሀ) በፓለቲካ ስም (አብዮታዊ ሌኒኒዝም/እስታሊንዚም/ማኦይዝም ወዘተ) ሥም፤
ለ) በአንድ ህዝብ ማንነት ላይ በቆመ ብሄረተኛ እንቅስቃሴ ሥም (የናዚ/ፋሽስት ሥርዓቶች ለዚህ ምሳሌ ናቸው)፤

ሐ) ወይም በአክራሪ ኃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ሥም (አክራሪ የእስልምናም ሆነ የክርስትና ድርጅቶች) ይመሩ እንጂ ሁሉም አንድ በጋራ የሚጋሩት ባህርይ አለ)። በዘመናችን ሳውድ አረቢያን በመሳሰሉት መንግስታት የሚረዳው የወሃቢ እንቅስቃሴ ለዚህ ኃይማኖታዊ አክራሪነት በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል።

በ ሀ እና ለ ሥር የጠቀስኳቸው እንቅስቃሴዎች ተመሳሳይ የሚያደርጋቸው የጋራ ባህርይ የሁለቱም እንቅስቃሴዎች ተከታዮች የግለሰብ ነጻነታቸውንና ማንነታቸውን ለመሪ ድርጅታቸው መሪዎች አሳልፈው የሰጡና በደመነፍስ መሪያቸው አድርጉ የሚላቸውን የሚፈጽሙ መሆናቸው ነው። በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች እንደ ሰው የሚገልጻቸውን በራሳቸው አይምሮ የመመራት ነጻነት ለመሪ ድርጅታቸው አሳልፈው በመስጠት የድርጅት መሪዎቻቸውን በጭፍንነት የመከተል ዝንባሌ ጠንክሮ ይታይባቸዋል። እነዚህ በቁጥር አንድና ሁለት ሥር የጠቀስኳቸው እንቅስቃሴዎች ኃይማኖታዊ ባህርያትን የተላበሱ ናቸው። ኃይማኖታዊ ናቸው ያልኩበት ምክንያት ሳትጠይቅና ሳትመረምር ድርጅትህንና መሪህን በጭፍን እንደ ፈጣሪ አምላክ እመን፤ መሪዎችህን በሙሉ እምነት ተከተል የሚል ጭፍን እምነትን የሚያራምዱ ስለሆኑ ነው። የሰው ልጆች በመንፈሳዊ ህይወታቸው የሚፈልጉትን ኃይማኖት ማምለካቸውን አልቃወምም፤ ይህንንም ለማድረግ ያላቸውን መብት አከብራለሁኝ። ነገር ግን ጭፍንነትን የተላበሰ የፓለቲካ እምነት የሰውን ልጆች ህሊና በማሳወር እንደ መንጋ አምባገነን ምድራዊ መሪዎችን እንዲከተሉ ሲያደርግ እያንዳንዱ የሰው ልጅ በተፈጥሮው የታደለውን በራሱ ሃሳብና ፈቃድ የመመራት ጸጋ የሚገፍ አክራሪ ምድራዊ የፓለቲካ ሃይማኖት (secular political religion) ይሆናል። ይህ አክራሪ የፓለቲካ ኃይማኖት የእያንዳንዱን ግለሰብ ነጻነት ስለሚገፍ የተገዢነት፤ የጭቆና መሰረት ይሆናል። በዚህም ምክንያት ነው ከላይ የገለጽኳቸው የፓለቲካ፤ የብሄርተኛ እንቅስቃሴዎች የተከታዮቻቸውን በራስ የማሰብና በግል ፈቃዳቸው የመመራት ነጻነት ይገፋሉ የምለው። እነዚህ በቁጥር አንድና ሁለት የጠቀስኳቸው እንቅስቃሴዎች ዓላማቸውን እጅግ ጣሪያ በነካ የጭፍንነትና የአክራሪነት ስሜት ይተገብራሉ።

በፓለቲካም ሆነ በብሄረተኛነት ስም የሚካሄዱ አክራሪና ጽንፈኛ እንቅስቃሴዎች እንደ አክራሪ ሃይማኖት ከሚያራምዱት የፓለቲካ ዓላማ ዝንፍ የማይሉ (ግትርነት የሚገንባቸው)፤ የሃሳብ ልዩነትን የማያስተናግዱ በሃሳብ የሚቃወማቸውን በጠላትነት በመፈረጅ ለማጥፋት የሚነሱ ናቸው። በእነዚህ በቁጥር አንድና ሁለት ሥር የጠቀስኳቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ ከግለሰብ ይልቅ አንድ-ወጥ (homogeneous) የሆነ የቡድን ወይም የመንጋ አስተሳሰብ (group thinking) በተከታዮቹ ላይ የሚሰለጥንበት ሁኔታ ይታያል። በዚህ ሰዎች እንደ እንስሳ መንጋ በቡድን ስሜት አንድን የፓለቲካዊም ሆነ ብሄረተኛ እንቅስቃሴ በሚከተሉበት ሁኔታ ውስጥ የግለሰብ ማንነት ይደበዝዛል፤ የግለሰብ ድምጽ ይዋጣል። የእያንዳንዱ የእነዚህ የአክራሪ ፓለቲካም ሆኑ አክራሪ ብሄረተኛ እንቅስቃሴዎች ተከታይ የሆነ ግለሰብ የማመዛዘን ችሎታው በእጅጉ ይዳከማል ወይም ጨርሶ ይከስማል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ በዚህ ዓይነት የመንጋ ወይም የቡድን አስተሳሰብ የሚመሩ፤ ኃይማኖታዊ መሰል ጭፍን እምነትን የሚያራምዱ አክራሪና ጽንፈኛ የሆኑ የፓለቲካ፤ የብሄር እንቅስቃሴዎች ተከታዮች በአይምሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ይሆናሉ። የመንጋ ቡድን ተከታዮች የሆኑ ሰዎች የግል ነጻነታቸውን አረጋግጠው እንደ ነጻ ሰው ማሰብና ማመዛዘን የማይችሉ ስለሆነ የሚከተሉት አክራሪ የፓለቲካም ሆነ የብሄረተኛ ድርጅት ዓላማ ቆይቶ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር አስቀድመውና አሻግረው ማየትና መገንዘብ አይችሉም። የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባለፉት አርባ አራት ዓመታት እነዚህን መሰል የመንጋ አስተሳሰብን የሚያራምዱ የፓለቲካ እንቅስቃሴዎችን በሁለት ዓይነት መልክ ሲያስተናግድ ቆይቷል። አንደኛው ቡድናዊ አስተሳስብን ያራምዱ በነበሩ የግራ ኃይሎች (ደርግና ተቃዋሚዎቹ በሆኑ የግራ ፓለቲካ ድርጅትች) አማካይነት ሲሆን ሌላው ደግሞ ማንነትን መሰረት አድርገው ቡድናዊ አስተሳሰብን ይዘው በተነሱ ብሄረተኛ እንቅስቃሴዎች (የኤርትራ፤ የትግራይ፤ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጅቶች ወዘተ) አማካይነት ነው። በተለይ የነገድ ማንነትን ይዘው የሚነሱ የመንጋ እንቅስቃሴዎች (crowd movements) እጅግ ጥልቅ የሆኑና የሰዎችን ስሜት ሊኮረኩሩ የሚችሉ ስለሆኑ ተከታዮቻቸውን በስሜት
የማሳበድና ህሊናቸውንም የማሳወር አቅምና ክህሎት አላቸው። (Ethno-nationalism has the propensity and quality of fanning effectively or emotionally-charged sentiments among its blind followers).

የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የከፋፍለህ ግዛው አስተዳደሩን ያጠናክርልኛል ብሎ ሰፊ የመፈንጫ ሜዳ የሰጠውና ከከበርቴ የነዳጅ ሀብት ባለቤቶች በሆኑ የአረብ ሀገሮች ይጎርፍለት በነበረ ገንዘብ በሺህ የሚቆጠሩ መስጊዶችን ሲገነባ የቆየ፤ ታሪካችንን የሚያፋልሱ፤ ህዝብን የሚከፋፍሉ የፕሮፓጋንዳ መጽሃፍቶችንና መጽሄቶችን በገፍ የሚያሰራጭ አክራሪ የሆነ ፓለቲካዊ ቃና ያለው የእስልምና እንቅስቃሴ (political islam) ወደ ኢትዮጵያ የፓለቲካ መድረክ ብቅ ብሏል። እስከ 2000 ዓ. ም ድረስ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ 180 መስጊዶች 130ዎቹ የተሰሩት ከ1986 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ ባሉት ወያኔ ሥልጣን ላይ በመጣባቸው 14 ዓመታት ውስጥ ነው። በዚሁ ጊዜ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ቁጥር ደግሞ130 ነበር። (ምንጭ፡ “በኢትዮጵያ የኃይማኖት መቻቻል አለን? የሚለውን በሚያዝያ 2000 ዓ.ም. በአባ ሳሙኤል የተዘጋጀ መጽሃፍ ገጽ 40 ላይ ሄደው ይመልከቱ)።

ዛሬ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን 16.2% የሚሆኑት የእስላምና ተከታዮች ሲሆኑ (Central Statistical Authority 2007) የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች የሆኑት ደግሞ 74.7% (source EPRDF's Revolutionary Democracy and Religious Plurality: Islam and Christianity in post-Derg Ethiopia Jörg Haustein and Terje Østebø) የሚሆነውን ድርሻ ይወስዳሉ። እነዚህ ሁሉ መስጊዶች ከሀገር ውስጥ በተዋጣ ገንዘብ ብቻ የተገነቡ እንዳይደሉ ማንም ህሊናው በአክራሪ የእስልምና እምነት ያልታወረ ሰው ይረዳል። ይህ አክራሪ እስላማዊ ፓለቲካን የሚያራምድ ኃይል አድብቶ ጊዜ የሚጠብቅና ለሀገራችን ህዝብ ሰላም ከፍተኛ አደጋን የሚጋብዝ ክህሎት ያለው ነው። ይህንን ገደምም ጠመምም ሳላደርግ ለመናገር እፈልጋለሁኝ። ኃይማኖትን የመሰለ ከሰዎች ስሜት ጋር በጥልቅ የተያያዘ ጉዳይ ሊያተኩርበት ከሚገባው መንፈሳዊ ህይወት ወጥቶ ምድራዊ የሆነ ሀገራዊ ፓለቲካ ውስጥ እጁን ሲያስገባ ለአንድ ሀገር ሰላምና ነጻነት ታላቅ አደጋን ይጋብዛል። እኔ ፋሽስት የምለው የወያኔ መንግስትም ሆነ የተግባር ወላጁ የሆነው የጣሊያን ፋሽዝም ኃይማኖትን ተገን በማድረግ ህዝባችን በመከፋፈል ያደረሰውን ጉዳት አንርሳ (ይህን ጽሁፍ የምታነቡ የጣሊያን ፋሽስቶች እንዴት አድርገው የእስልምናን ኃይማኖት መሳሪያ በማድረግ፤ አንዱን ኃይማኖት ወግነው ሌላውን በማዳከም የኢትዮጵያን ህዝብ እንደከፋፈሉ የኢጣሊያዊውን የታሪክ ጸሃፊ የAlberto Sbacchiን Ethiopia Under Mussolini: Fascism & the Colonial Experience እና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሰባት መጽሃፍቶችን የጻፈው እስራኤላዊው የታሪክ ጸሃፊ Haggai Erlichን Saudi Arabia & Ethiopia: Islam, Christianity & Politics Entwined የሚሉ መጽሃፍቶች እንድታነቡ አሳስባለሁኝ)።

ወያኔም ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ቅንጅት ምርጫ ድረስ ይህንን የጣሊያን ፋሽስቶችን ስልት በመጠቀም ራሱን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ወገን አድርጎ በተለይ የኦርቶዶክስ ክርስትና ኃይማኖት ተቋሞችን ለማዳከም ሞክሯል። ዛሬ ሳውዲዎች የመን ውስጥ እያደረጉ ያሉትን ቀጥተኛ ጣልቃ-ገብነት በማየት በሀገራችን ላይ የተደቀነውን አደጋ መረዳት ይችላል። ሳውዲ አረቢያ የግመል መፈንጫ ሆኖ ሥራ የፈታውን የአሰብ ወደብ ለሃምሳ ዓመታት ተኮናትራ አፍንጫችን ሥር ጦሯን ያሰፈረችበት ሁኔታ አለ። እድሜ ለወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ የወሃቢዎች አክራሪ እስላማዊ እምነት ስር ሰዷል። ኢትዮጵያ ውስጥ በልማት ሥም ሳውዲ አረቢያም ሆነ ሌሎች በአካባቢው ያሉና በረጅሙ ታሪካችን ለኢትዮጵያ በጎ አመለካከት የሌላቸው እስላማዊ መንግስታት እያበረታቱ ያለውን አክራሪ እስላማዊ ፓለቲካን (radical political islam) መመልከቱ ሊመጣ ያለውን አደጋ መጠን መገንዘብ ያስችላል። ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ በኢትዮያ ውስጥ በእነ ሳውዲ አረቢያ ገንዘብ በሚጎርፍለት የወሃቢዎች እንቅስቃሴ ምክንያት ከአለባበስ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የፈጠሩዋቸውን ተፅእኖዎች፤ በኢትዮጵያ ክርስቲያኖችና እስላሞች መካከል የፈጠሩዋቸውን በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ መራራቅና መጠራጠር ልብ ማለቱም ይበጃል። ይህንን እየሻከረ የመጣውን የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ግኑኝነት በተመለከተ መሀመድ ሰልማን የተባለ ጋዜጠኛ “ፒያሳ መሀሙድ ጋ ጠብቂኝ” በሚለው መጽሃፍ ውስጥ ሼ-መንደፈር በመርካቶ በሚል ርዕስ ሥር ያሰፈረውንና መጪውን ጊዜ በተመለከተ የሚያስፈራውን ሁኔታ በሚከተለው መልክ ገልጿል።

“የክሩሴድ (የመስቀል) ጦርነት ክተት የታወጀ እስከሚመስል ሁለቱም እምነቶች ዛቻን ያዘሉ ጽሁፎችን በአልባሳት እያተሙ ለአደባባይ አብቅተዋል። ይህች ደሴት እኔ ከምከተለው ኃይማኖት ሌላ ለማስተናገድ ቦታ የላትም ሲሉም ያወጁ ነበሩ። ይህን መሰሉን ነገር ስመለከት አብሮነታችን በቋፍ ያለ መስሎ ይሰማኛል። በድሮ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እስላምና ክርስቲያን በአንድ ላይ ተዋደው ይኖሩ ነበር ሊባል የሚችልበት ጊዜ ቅርብ ሆኖ ይሰማኛል። እንዲህም አስባለሁ። የሼ-መንደፈር ታሪካችን ዘፈን ብቻ ሆኖ ሊቀር ይችላል፤ አላህና እግዚአብሄር ካልታደጉት በቀር።” ምንጭ “ፒያሳ መሀሙድ ጋ ጠብቂኝ” ገጽ 151 በአቶ መሀመድ ሰልማን 2004 ዓ. ም. የተጻፈ መጽሃፍ። ምንም እንኳን መሀመድ ሰልማን ይህን ከላይ እሱ ከጻፈው መጽሃፍት የጠቀስኩትን ሁኔታ ከአክራሪው የወሃቢ ወይም ሳላፊዝም እምነት መስፋፋት ጋር ባያያይዘውም በእኔ እምነትና አረዳድ ይህ አዲስ ክህስተት በከፊል ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች የመጣ መሆኑ አያጠራጥርም። ይህን እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ያለ አሳዛኝ የኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ግኑኝነት ሁኔታ የሚያሳይ ትዝብቱን ለእኔ ከሀገሬ ከረጅም ዓመታት በፊት ወጥቼ ላልተመለስኩት ኢትዮጵያዊ ስለአስነበበኝ መሀመድ ሰልማን ምስጋና ይግባው።

የወያኔ ሥርዓት በፈጠራቸው እጅግ አሳዛኝ የሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የስነ ልቦና ችግሮች ሰለባ ሆነዋል። ይህን የስነ ልቦና ሰለባ የሆነና መድረሻ ያጣ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግርህ እርኩስ መንፈስ ነው እያሉት የሚያስጮኹትና የሚያደነዝዙት አክራሪ የፕሮቴስታንት እምነት አራማጆች ከምዕራቡ ዓለም ካሉ ኃይማኖታዊ ተቋማት ድጎማ የሚጎርፍላቸው ሲሆኑ ኢትዮጵያን በእጅጉ እየጎዱና ጠንካራ ዘመን ተሻጋሪ የነበሩ እሴቶቿንም እየሸረሸሩ ነው። እነዚህ በወያኔ መንግስት ይሁንታን ያገኙት የፕሮቴስታንት አክራሪዎች በበርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሥርጭቶቻቸው አማካይነት የኢትዮጵያን ህዝብ እያደነዘዙ ይገኛሉ። እነ መምህር ግርማን የመሳሰሉትም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነን ባዮች እንደ አክራሪዎቹ ፕሮቴስታንቶች የወያኔ ሥርዓት በፈጠረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀት የጭንቀት ህይወት ውስጥ የገባውንና መድረሻ ያጣ ህዝባችንን ሰይጣን ነው፤ እርኩስ መንፈስ ነው ወዘተ የሰፈረብህ እያሉ ያደነዝዙታል። የወያኔም ሥርዓት በኃይማኖት ሥም እነዚህን መሰል ማደንዘዣዎችን እየሰጡ ህዝቡን የሚያታልሉትን አክራሪ የኃይማኖት ተቋማት እንዲስፋፉ በማድረጉ ህዝቡ ለእነዚህ ሁሉ አይምሮ-አዋኪና ጭንቀት-ፈጣሪ የሆኑ ወያኔ-ወለድ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ዋነኛ መንስዔ በሆነው የወያኔ የአፓርታይድ ሥርዓት ላይ እንዳያተኩር አድርገውታል።

የኤርትራ ብሄረተኞችና ጭፍን እምነታቸው፤ ለታላቁ መሪያቸው የነበራቸው አክብሮት የመንጋ እንቅስቃሴ ላይ መሰረቱን የሚያደርገው ብሄረተኝነት እንዴት በህዝብ ውስጥ ጭፍንነትንና ድንቁርናን እንደሚያስፋፋ ለማሳየት አንድ ምሳሌ ልጥቀስ። ከዛሬ ሰላሳ አራት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ማህበር በሆላንድ ያዘጋጃቸው በነበሩ ስብሰባዎች ላይ በሻቢያና ባጠቃላይ በኤርትራውያን ብሄረተኞች ላይ ያለኝን የተቃውሞ አስተያየት በአደባባይ በነጻነት እገልጽ ነበር። በዚያን ጊዜ በኤርትራዎች እንደ አምላክ የሚታየው የሻቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ከደርግ መሪዎች የባሰ ሰው እንደሚሆንና ኤርትራውያንን ሲዖል ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል በግልጽና በእርግጠኛነት እናገር ነበር። ኤርትራውያን ብሄረተኞች ይህ አስተያየቴ እጅግ ያስቆጣቸውና ለድብድብና ለጠብ እንዲጋበዙ ያደርጋቸው እንደነበር ትዝ ይለኛል። አቶ አማኑኤል ነጋሲ የሚባል በሆላንድ የሻቢያ ወኪልና Eritrean Relief Association (ERA) የሚባል የእርዳታ አሰባሳቢ ድርጅት ተጠሪ የነበረ በዚያ ጊዜ እድሜው በአርባዎቹ ውስጥ የሚገመት ሰው ነበር። ታዲያ በአምስተርዳም ከተማ ውስጥ በተካሄደ አንድ ስብሰባ ላይ የሻቢያን ድርጅት አምባገነንነት፤ የመሪውን የኢሳያስ አፈወርቂን አረመኔነት ስናገር አቶ አማኑኤል ወደ እኔ እያመለከተ ይህ ሰውዬ የመሪያችንንና የድርጅታችንን ሥም በሀሰት ያጠፋል እያለ ተናገረኝ። እኔ በዚያን ጊዜ ስለ ሻቢያም ሆነ ስለ አምባገነኑ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ አረመኔነት እናገር የነበረው ዝም ብዬ በጥላቻ ስሜት ተነሳስቼ ሳይሆን መረጃ ይዤ ነበር። ያኔ ኢሳያስ አፈወርቂ አረመኔ ሰው ነው ብዬ በስብሰባ ላይ የተናገርኩት ይህ ሰው መንካዕ (የሌሊት ወፍ) የሚል ስም ተሰጥቷቸው የነበሩትና ሻቢያን ተቀላቅለው ለኤርትራ ነጻነት ይታገሉ የነበሩ የኤርትራ ምሁራን እንዴት በአሰቃቂ ዓይነት በእሱ ትዕዛዝ እንደተገደሉ ከታሪክ መዛግብት አንብቤ በመረዳቴ ነበር። 

መንካዕ በሚባል ስም ከሚታወቁትና የኢሳያስ አፈወርቂን አምባገነን አሰራር ከተቃወሙ የኤርትራ ብሄረተኞች መካከል ዮሃንስ ስብሃቱን፤ ሙሴ ተስፋሜካኤል፤ አፈወርቂ ተክሉን የመሳሰሉ ግለሰቦች ይጠቀሳሉ። በወቅቱ ስለነዚህ ሰዎች መገደል ማንም ጥያቄ ሊያነሳ አልቻለም። የአገዳደላቸው ሁኔታ እንኳን በውጭ ሀገር ያሉ ኤርትራውያን ያወቁት እነዚህ ሰዎች ከተገደሉ ከአርባ ዓመታት በኋላ ነበር (ለዝርዝሩ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ። http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=88221

እነዚህ በኢሳያስ የተፈጁ የኤርትራ ብሄረተኞች ቀደም ሲል በዐጼ ኃይለስላሴ ዩኑቨርሲቲ ውስጥ ተራማጅ የተሰኘና ዓለማቀፋዊነትን የሚሰብክ የግራ ፓለቲካ አቀንቃኞች ሆነው ይታዩ ነበር። ኋላ ላይ ግን እነዚህ ግለሰቦች ከሚያቀነቅኑት የግራ ፓለቲካ ጀርባ የኤርትራን የመገንጠልና ራሷን የቻለች ነጻ ሀገር የመሆን ድብቅ የፓለቲካ ዓላማ የሚያራምዱ ብሄረተኞች እንደ ነበሩ በተግባር አሳዩን። እነ ዮሃንስ ስብሃቱ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ አማራ ጠላታችን ነው ብሎ ድርጅታቸው ሻቢያ የሚያምንበትን እምነት የሚጋሩ ግለሰቦችም ነበሩ። እነዚህ በኋላ መንካዕ ተብለው በሻቢያ የተፈጁ የኤርትራ ተራማጆች ዐጼ ኃይለሥላሴ ዩኑቨርሲቲ ውስጥ ተማሪዎች በነበሩ ጊዜ የኤርትራን ችግር ዲሞክራሲያዊ በሆነ የኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ የመፍታት ዓላማ እንደነበራቸው የመሃል ሀገር ተወላጆች ለነበሩ የዋህ የኢትዮጵያ ተራማጆች ይገልጹላቸው ነበር። በተለይ ኢትዮጵያ በሚል ማር እስከ ተጠቀለለ ድረስ መርዝም ቢሆን ለመጠጣት ይሽቀዳደሙ የነበሩት የዋህ የመሃል ሀገር ተወላጆች በእነዚህ የኤርትራ ተራማጆች መታለላቸውን ያወቁት በጣም ዘግይተው ነበር። ይህ የዛሬው ትውልድ ከዚህ በትግርኛ ተናጋሪዎች (ይሄ የኤርትራን ብቻ ሳይሆን የትግራይን ተወላጆችንም ይመለከታል) በተደጋጋሚ ሲታለል ከነበረው የእኔ ትውልድ ልምድ ትምህርት ሊወስድ ይገባል። ይህ ትውልድ ዛሬ የግንቦት ሰባት መሪ ካድሬዎችና የኢሳት ቴሌቪዥን የኤርትራ መንግስት ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ስላለው “በጎ አመለካከት” የሚግቱትን ውሸት ለቅጽበትም ሊያምን አይገባም። የግንቦት ሰባትንና የኢሳትን አደንዛዥ ፕሮፓጋንዳ አምነው ኢትዮጵያን ከወያኔ ነጻ ሊያወጡ ወደ ኤርትራ የሚሄዱ የዋሆች ከእባብ እንቁላል እርግብ የሚጠብቁ መሆናቸውን ልብ ይበሉ።

በብርሃነ መስቀል ረዳ የሚመራውና ኋላ ኢህአፓ የሆነው ቡድን አባሎች ወደ ትግራይ ገብተው አሲምባ የሚባለው ቦታ ላይ የትጥቅ ትግል ለመጀመር ከማሰባቸው በፊት ወደ ኤርትራ ሄደው ሻቢያ የሚቆጣጠረው አካባቢ ለአንድ ዓመት ያህል እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። ታዲያ እነዚህ የኢህአፓ ቡድን ሰዎች ሻቢያ ጦር ሰፈር ሲደርሱ ቀደም ሲል በዐጼ ኃይለስላሴ ዩኑቨርሲቲ ሳሉ ተራማጆች ነን፤ ኢንተርናሽናሊስት ነን እያሉ የመሃል ሀገሩን ኢትዮጵያዊ ሲያታልሉ የነበሩትን የኤርትራ ተወላጆች የሻቢያ ተዋጊዎች ሆነው እዚያ እንዳገኟቸው በሚከተለው የግርምት መንፈስ ነበር የገለጹት፡

“ወደ ኤርትራ ሜዳ እንደገባን የገረመን ዮሃንስ ስብሃቱንና አፈወርቂ ተክሉን እዛው በማግኘታችን ነበር። እነዚህ ወጣት ምሁራን በአዲስ አበባ ዩኑቨርሲቲ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ብሩህ ተስታፊዎችና መሪዎችም ስለነበሩ ነው አልዋጥልን ያለው”። ምንጭ አስማማው ኃይሉ ከጻፈው “የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት (ኢሕአሰ) ከ1964-1970 ዓ. ም.” ቅጽ አንድ ገጽ 40 ላይ ይመልከቱ። የኤርትራ ብሄረተኞች ቅዠትና በድል ማግስት የተከሰተው መራር እውነታ
እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ የኤርትራ ብሄረተኛነት ስሜት በፈጠረው ሆያ ሆዬና እብደት ህሊናቸውን ስተው የነበሩ በርካታ ኤርትራውያን እንደ አምላክ ያመልኩት የነበረው ድርጅታቸው ሻቢያና አምባገነኑ መሪያቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ይሳሳታሉ ብለው አያምኑም ነበር። በዚህ በስደቱ ዓለም በደርግ ዘመን ኤርትራዊ ሆኖ ሻቢያንም ሆነ የእሱን ተቀናቃኝ ጀብሃን የማይደግፍ ፈልጎ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር። ኤርትራውያን ዛሬ እንዲህ አንገታቸውን ሊደፉ በደርግ ዘመን በዚህ በስደት ዓለም ስንኖር የኤርትራ ብሄረተኝነት በፈጠረባቸው ስሜት ምክንያት በጠላትነት የሚያዩዋቸውን ኢትዮጵያውያንን ማናገርና መቅረብ እንኳን ይጠየፉ ነበር። እነሆ የኤርትራ ብሄረተኝነት የደስታና የሰላም ምንጭ መሆኑ ቀርቶ እንደ አሜኬላና እሾክ ኤርትራውያንን እየወጋ ከሀገር አስወጥቶ ቀጣይ የኤርትራ ትውልዶችን ለሌላ ዙር ስደት፤ ለዐረብ ሀገሮች ባርነት ወዘተ ሥቃይና ሞት የሚዳርግበት ዘመን ላይ ደረስን።

የደርግ መንግስት ወድቆ ሻቢያና ወያኔ ሥልጣን ላይ እንደወጡ በሆላንድ የነበርን የእነዚህን ሁለት ቡድኖች እኩይ ዓላማ የምንቃወም ኢትዮጵያውያን በሰኔና በሃምሌ 1983 ዓ.ም. ተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎችን ዘሄግ (the Hague) በሚባለው የሆላንድ መንግስትና የውጭ ኤምባሲዎች መቀመጫ የሆነች ከተማ ውስጥ አደረግን። በዚያን ወቅት ኤርትራውያንና ወንድሞቻቸው የሆኑት የትግራይ ተወላጆች ደግሞ ደስታቸውን በአደባባይ በጭፈራ ሲገልጹ በቴሌቪዥን ይታዩ ነበር። በወቅቱ የእኛን ሰልፍና ተቃውሞ ማንም የሆላንድ ቴሊቪዥን ዜና አድርጎ ሊዘግብልን አልፈለገም። ታዲያ በዚህ ሀገር De Volkskrant የተባለ አንድ ትልቅ እለታዊ ጋዜጣ አንዱን የደች ጋዜጠኛ ልኮ የኤርትራውያንን፤ የትግራውያንንና እንደዚሁም የወያኔ ተቃዋሚ የሆነውን ኢትዮጵያውያን አስተያየት አካትቶ ለመዘገብ ተነሳ። በወቅቱ በሆላንድ የኢትዮጵያ ማህበር ሊቀመንበር ስለነበርኩ በኢትዮጵያውያኑ በኩል ያለውን አቋም እንዳስረዳ ተጠየቅሁኝ። ጋዜጠኛው “ኤርትራውያን ሀገራቸው ነጻ ወጥታ እጅግ ተደስተዋል፤ እንዲያውም አሁን ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በጦርነት የተጎዳ ሀገራቸውን ሊገነቡ እንደሚያስቡ ያነጋገርኳቸው ኤርትራውያን ሁሉ ነግረውኛል። የእናንተ ኢትዮጵያውያን ማህበር አባሎች ደግሞ ለውጡን በመቃወም ሰልፍ ትወጣላችሁ። ይህ ለምን ሆነ?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም “እኛ ኢትዮጵያውያን አሁን አዲሱን መንግስት የምንቃወመው በጠመንጃ ኃይል የመጣና አብዛኛውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያገለለ ጠባብ ማህበረሰባዊ መሰረት ያለው አናሳ ቡድን በመሆኑ፤ ጎሳንና ቋንቋን መሰረት ያደረገ የህዝብንና የሀገርን አንድነት የሚያፈርስ ፓሊሲ አራማጅ በመሆኑ፤ ጸረ-ዲሞክራሲያዊ የሆነ አቋም ያለው መንግስት በመሆኑ ነው” ብዬ አስረዳሁት። “ይህ የወያኔ መንግስት ፓለሲ ደግሞ በዘላቂነት ኢትዮጵያን የሚበታትን ነው” አልኩት። “ኤርትራውያን ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው ላልከኝ ምን አለ በለኝ እንኳን እዚህ ያሉት ኤርትራውያን ወደ ኤርትራ ሊመለሱ ቀርቶ ገና ብዙ ኤርትራውያን ከኤርትራ ወደ ምእራቡ ዓለም በገፍ እንደሚመጡ በእርግጠኛነት ልነግርህ እፈልጋለሁ” አልኩት። (Mark my words far from witnessing a return of Eritreans to independent Eritrea, you should expect even more Eritreans flocking out of Eritrea towards Western Europe)” ይህ ቃለመጠይቅ De Volkskrant ከሚባለው ጋዜጣ ጋር በJuly 1991 የተደረገ ነበር። 

ዛሬ ያቺ የአፍሪካ ቀንድ ሲንጋፓር ትሆናለች የተባለችው ኤርትራ የምድር ሲዖል መሆኗን የሚናገሩት ትላንት የኤርትራ ህዝብ በደርግ ደረሰበት ስለሚሉት ግፍ እጅግ የተጋነነና በቀዝቃዛው ጦርነት (የምዕራቡና የሶቪዬት ህብረት ፍጥጫ) ስሜት የተቃኘ ወገናዊ ዘገባ ያቀርቡ የነበሩት እነ አምነሲቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋችን የመሳሰሉ ተቋሞች ጭምር ናቸው። ይህንን አምነስቲ ኢነተርናሽናል From Hell to Hell: Eritreans at Home and Abroad በሚል ርዕስ ሥር ኤርትራን በሲዖልነት የፈረጀበትን ዘገባ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ። https://www.neweurope.eu/article/hell-hell-eritreans-home-and-abroad/ published on May 4, 2013.

እነሆ ከላይ እንዳመለከትኩት ይኸው ያልኩት ነገር አልቀረም፤ ኤርትራ ውጭ ያሉ ስደተኞቿ ወደ እሷ የሚጎርፉባት ሳትሆነ እንዲያውም ዋነኛ የስደተኞች ምንጭ ሆነች።ዛሬ ኤርትራውያን ጥይት እየተተኮሰባቸውም እንኳን ቢሆን ትላንት በብሄረተኛነት ስሜት ሰክረው እጅግ ያመልኩት ከነበረው ሻቢያ በመሸሽ ድንበር እያቋረጡ ወደ አውሮፓ እየጎረፉ ነው። እነሆ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም ከመላው ዓለም ወደ ሆላንድ ከገቡት ስደተኞች ውስጥ በብዛት ረገድ የአንደኛነቱን ደረጃ ሶርያዎች(36%) ሲይዙ እነሱን በመከተል የሁለተኛውን ደረጃ የያዙት ኤርትራውያን (21%) ስደተኞች ነበሩ። (የዚህ አሃዛዊ መረጃ ምንጭ ---› VLUCHTELINGEN IN GETALLEN 2015 የሚለው የሆላንድ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ያወጣው ዘገባ)። ለስድሳ ዓመታት ያህል አማራን ጠላት አድርጎ፤ በአማራ የመሰላትን ኢትዮጵያን የጥላቻው ዒላማ አድርጎ የተነሳው የጣሊያን ቅኝ ገዢዎች ስሪትና ውላጅ የሆነው የኤርትራ ብሄረተኛነትና የሚያጠነጥንበት ኤርትራዊ ማንነት፤ ከዚሁ ብሄርተኝነት የተጸነሰውና ኤርትራውያን በኩራት “ገድሊ” እያሉ የሚጠሩት ትግላቸው ጥፋትን እንጂ ልማትን አላመጣላቸውም። የኤርትራን ብሄርተኞች የስድሳ ዓመት ከንቱ ትግል በተመለከተ ራሱን ከኤርትራ ብሄርተኞች መንጋ ተርታ በማውጣት በነጻነት ለማሰብ በመቻሉ ሚዛናዊ አመለካከት ያዳበረውን የኤርትራዊውን ምሁር የአቶ ዮሴፍ ገብረህይወትን በሳል ትንተና በሚከተለው ማስፈንጠሪያ አማካይነት ያንብቡ።
(https://dissidentdiaries.files.wordpress.com/2013/06/romanticizing_ghedli.pdf

ይህ በአፍሪካ ረጅሙ ለነጻነት የተደረገ የትጥቅ ትግል እየተባለ ይነገርለት የነበረው “ገድሊ” የተባለ የነጻነት ትግል አርቀው ማሰብ በማይችሉና በኤርትራ ብሄረተኛነት ስሜት በሰከሩ የኤርትራ ምሁራን ሲቀነቀን ኖሮ ያተረፈው ነገር ሞትን፤ ስደትን፤ የትውልድን ምክነትን፤ ምሬትን፤ ነባር ባህሉንና እሴቶቹን ያጣ የኤርትራ ትውልድና ማህበረሰብን ነው። የብሄረተኛነት ፍሬ ሲያዩት ጣፋጭና አስጎምጂ ቢመስልም በመጨረሻ ላይ ግን እጅግ ጎምዛዛ ነው። አንድ ነገድም ሆነ ህዝብ ራሱን የመንጋ እንቅስቃሴ አካል ሲያደርግ የኋልዮሽ ጉዞ ያደርጋል (societal regression ይሉታል ሳይኮአናሊስቶች)። በስተመጨረሻ ይህ ራሱን የብሄረተኛ ድርጅት ተቀጥያ አድርጎ በመንጋነት የሚነዳ ህዝብ በህይወቱና በንብረቱ ከፍተኛ ዋጋን ይከፍላል። የጀርመን ናዚዎችን አጅበው ሆ ሲሉ የነበሩ በበርካታ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የጀርመን ተወላጆችና እንደዚሁም የጣሊያን ፋሽስቶችን አጅበው በሮም አደባባይ የወርቅና የአልማዝ የጋብቻ ቀለበታቸውን ጭምር ሙሶልኒ በኢትዮጵያን ላይ ለከፈተው ፋሽስታዊ ጦርነት ማካሄጃ እንዲሆን የሰጡት የጣሊያን ተወላጆች ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። እንደዚሁም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኤርትራ ብሄረተኛነት ስሜት አብደው ለሻቢያ ሲያረግዱ የነበሩ ኤርትራውያንና የድል አድራጊው የሻቢያ ጦር አስመራ ሲገባ አበባና ቆሎ ሲረጩ የነበሩ የኤርትራ ተወላጆች ከባድ የህይወትና የንብረት ዋጋ ከፍለዋል። የጊዜ ጉዳይ እንጂ የወያኔ ትግሬዎችም እጣ ከዚህ የሚለይ አይሆንም!!!!

እስካሁን ድረስ የሰዎችን መንጋ በማንቀሳቀስ የሚካሄዱ የፓለቲካ እንቅስቃሴዎችን ባህርይ ከገለጽኩኝ በኋላ ከዚህ ቀጥሎ በተከታታይ ትኩረቴን የማሳርፈው የነገድ ማንነትን መሰረት አድርጎ በተነሳው አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛ እንቅስቃሴና ይህ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ውስጥ በፈጠረው ፋሽስታዊ ሥርዓት ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ተከታታይ ጽሁፎቼን “ፋሽዝም በአንድ ህዝብ ማንነት ላይ የተመሠረተ ጽንፈኛና አክራሪ ብሄረተኛነት መገለጫ ነው” በሚል ርዕስ ሥር አቀርባለሁኝ። አንባቢ ይህንን ስለ አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት መገለጫ የሆነ የፋሽዝም ሥርዓት ምንነት ስገልጽ እያንዳንዱ የአንድን ነገድ ወይም ህዝብ ማንነት መሰረት ያደረገ አክራሪ ብሄረተኛ እንቅስቃሴ (የኦሮሞም ይሁን የሶማሌ፤ የአማራም ይሁን የጉራጌ፤ ወዘተ) በስተመጨረሻ አስከፊ ወደ ሆነ ፋሽዝምን የመሰለ ጭፍን የአምባገነነት ሥርዓት እንደሚያመራ ግንዛቤ እንዲወስድ እጠይቃለሁኝ። ማንኛውም ነጻ የሆኑ ግለሰቦች ሃሳብ የማይሰማበት፤ የመንጋ ቡድኖች ድምጽ የጎላበት የፓለቲካ እንቅስቃሴ ለአንድ ሀገር ወይም በውስጧ ለሚኖረው ህዝብ ታላቅ አደጋን ይጋብዛል። ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበት ሁኔታ በእጅጉ አውሮፓ በአስራ ዘጠኝ መቶ ሰላሳዎቹ ውስጥ የገባችበትን አክራሪ ብሄረተኛነትና የፋሽስት እንቅስቃሴዎች የተስፋፉባቸውን ወቅቶች ያስታውሰኛል። የእስላማዊ አክራሪነት አደጋም በዚች ሀገር ላይ እያንዣበበ ነው። ለሃያ ሰባት በፋሽስት አገዛዝ ምክንያት በደቀቀችና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ በተንሰራፋበት ሀገር ውስጥ ለአክራሪ ፓለቲካ፤ ለአክራሪ ብሄረተኛነትና ለአክራሪ ኃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች መስፋፋት አመቺ የሆኑ እድሎች ይፈጠራሉ። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1994 ዓ.ም 55.4 million የነበረው የኢትዮያ ህዝብ ቁጥር ዛሬ ወደ 106. 6 ሚሊዮን ከፍ ብሏል። እንግዲህ ይህ ቁጥር በሃያ አምስት ዓመት ውስጥ በእጥፍ አደገ ማለት ነው። ይህ ሁሉ አሳሳቢና ችግራችንን የሚያወሳስብ ነው። ላለፉት አርባ አራት ዓመታት ከኢትዮጵያ አብዮት ፍንዳታ ጀምሮ ያስተናገድናቸው የፓለቲካ እንቅስቃሴዎች ባመዛኙ ሀገራዊ ጥፋትና ውድመትን፤ የእርስ በርስ ጦርነቶችን፤ የጅምላ መፈናቀሎችን ወዘተ አስከትለዋል። በእነዚህ ረጅም የጥፋት ዓመታት ውስጥ በአስተሳሰባቸው የሰከኑ አዋቂ ሰዎች ነጻ ሃሳቦቻቸውን እንዳያሰሙ የታፈኑበት፤ የመንጋ ቡድኖች በስሜታዊነት የሚነዷቸው ጭፍን ወገኖች ድምጾች የገነኑበት ዓመታት ነበሩ። ከሃያ ሰባት ዓመት የወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝም በኋላ ኢትዮጵያን ወያኔ ባጸደቀው የጎሳ ፌዴራሊዝም ሥርዓት ሥር እንድትቀጥል የተማማሉት የአክራሪ ብሄረተኛ ኃይሎች ድምጾች ዛሬ እጅግ እየጎሉ በመምጣት ላይ ይገኛሉ። ከዛሬው ሆያ ሆዬ ባሻገር የዚህን የመንጋ ቡድኖች እንቅስቃሴዎች የገነኑበትን ፓለቲካ አሉታዊ ክትያዎች (consequences) ውጤቶች ማየት የቻሉ ድምጾች ጎልተው ዛሬም ድረስ አይሰሙም። እነዚህ የአክራሪ ብሄረተኛነት ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ድምጾች መጉላት መጪው ጊዜ ለኢትዮጵያ በጎ ነገርን ያመጣል የሚል ተስፋን እንድሰንቅ አያደርጉኝም።

-----------------------------------ክፍል ሁለት ይቀጥላል።  Posted at Ethiopian Semay

Friday, February 16, 2018

ለቪኦኤ እንግዶች፤ ብርሃኑ፤ ገብሩ፤ መረራና ልደቱ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)

ለቪኦኤ እንግዶች ብርሃኑ ገብሩ መረራና ልደቱ
ጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)
ትናንት ያደመጥነው የኃይለማርያም ደሳለኝ ከሥልጣን መውረድ አስመልክቶ የ4ት ታዋቂ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ባደረጉት ውይይት ላይ አንድ ልበል። በፌስ ቡክ  በተደረገው የስልክ ውይይት ከአድማጮችና ከአዘጋጆቹ  የቀረቡ በርካታ ጥያቄዎች ተቃዋሚዎቹ በቂ መልስ አልሰጡም። አወያይዎች ትርጉሙ ባልገባኝ ምክንያት ለብርሃኑ ነጋ ከሌሎቹ በበለጠ የተለጠጠ የመናገር ዕድል በመስጠት የሌሎቹን መልስ በበቂ እንዳናደምጥ ማድረጋቸው አድላዊ የሆነ የዘወትር ልማዳቸውን መከተላቸው ዛሬም እየደገሙት ነው። ያለ ብርሃኑ ነጋ ሌላ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ የማያውቁ ምስኪኖቹ  የቪ ኦ ኤ አማርኛው ክፍል አዘጋጆች ይህን የሚያደርጉት ሆን ብለው  በሻዕቢያ የሚረዳው ግንቦት 7 የተባለ ተቀጣሪ ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብ አድማጮች ጆሮ አንዲገባ በማስተዋወቁ ረገድ ምስኪኑ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለካ ተዋጊ ሃይል አለን ብሎ አጉል ተስፋ እንዲጥልበት ልዩ ማስታወቂያ (አድቨርታይዝ) እየሠሩለት መሆኑን እየታዘብን ነው። ትችቴ እንደሚከተለው ነው።

ውይይቱን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡
Ethiopia: Dr Berhanu Nega, Dr Merera Gudina, Lidet Ayalew, Gebru Asrat PM Hailemariam Resignation

ልደቱ ባለው የተበላሸ የፖለቲካ አቁዋሙ የሚያራምደው መስምር የማልወድለት ብሆንም፤ ያ እንዳለ ሆኖ በትክክል እንዳለው በእንግድነት የተጋበዙት “ተቃዋሚዎች” <<እራሱን ቸምሮ ለተጠየቁት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ  ያሳያል>> ያለውን በትክክል የኔን መስመር ማጠናከሩ ልደቱን ከፍተኛ ነጥብ (ማርክ) ሰጥቸዋለሁ። የኛን ተጠናክሮ መውጣት አልቻልንም ማለቱ ልክ ነው። አንባቢዎቼ ታስታውሱ ከሆነ እኔ “ኢትዮፓትርዮስትስ” በተባለው የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ ሲውድን አገር የሚገኘው ድረገጽ ባደረግኩት ቃለ መጠይቅ ላይ “ተቃዋሚው መፍትሔ ፍለጋውን እየጠበቀ ያለው ከወያኔ እና አጋር ድርጅቶቹ ከሚያደርጉት የጥገና ለውጥ ብቻ ታጥሮ መወሰኑ የሚያሳየን የተቃዋሚው “ክራይስስ” (ክስረት) እንደሆነ መግልጼን ያደመጣችሁኝ ታስታውሳላችሁ። ልክ እኔ ያልኩትም ልደቱ አያሌው አጠናክሮልኛል። ጥሩ መልስ ነበር የሰጠው።

ልደቱ ያለው ምንድ ነው? ከአንድ አድማጭ የቀረበው “ተቃዋሚዎች ከኢህዴጎች የድርድር ጥሪ ተድሮጋለችሁ ያውቃል ወይ?” ለሚለው ጥያቄ ልደቱ ሲመልስ “ለድርድር የጋበዘን አካል የለም፡ እየተካሄደ ነው ከሚባለውም ከድርድሩ እንድንወጣ ነው እየተደረግን ያለነው”…ካለ በላ << “ለመሠረታዊው ጥያቄ መልስ ለመስጠት አልቻልንም። ምክንያቱም  “ተቃዋሚው” መፍትሔ እየፈለገ ያለው ከገዢው ፓርቲ ነው። እውነት ነው ሥልጣን የያዘው ገዢ ፓርቲ አገሪቱ በስሩ ስለሆነች ዋናው መፍትሔ ከእርሱ ይጠበቃል።ግን ከሱ ብቻ አይደለም፤ ከኛም ይጠበቃል።>> ብሏል። ይኼ ልክ ነው።

ከልደቱ ጋር ተመሳሳይ መልስ ያስደመጠን ዶ/ር መረራ ጉዲና ነው።

 “መረራ” አጭር እና ጥሩ መልስ ሰጥቷል።“ተቃዋሚዎች ከኢህዴጎች የድርድር ጥሪ ተድሮጋለችሁ ያውቃል ወይ?” ለሚለው ጥያቄ፤ <<ተቃዋሚው ወያኔን በምንም መልኩ ለድርድር ማቅረብ መቻል አለብን>>  ብሏል። ሆኖም እንዴት ለድርደር ማቅረብ አለብን ለሚለው ግን “የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ” ማበረታታት እንዳለባቸው መረራ ቢገልጽም የሕዝቡን ቁጣ ተቃዋሚዎች እንዴት ይምሩት የሚለው (እኔ የቪ ኦ ኤ ጋዜጠኛ ብሆን ያነን ነበር የማቀርብላቸው) መረራም ሆነ ሌሎቹ የሰጡት ፍንጭ የለም፡ አልሰማሁም። ማንኛቸውንም መልስ የላቸውም።

የልደቱ ሌለው ነጥብ ተቃዋሚዎች ወጥ የሆነ ሥርዓቱን የምንገልጽበት መገለጫ እና መፍትሔዎቹ መስማማት ያለመቻላችን ለችግሩ አስተዋጽኦ አድርገናል፡የሚለው ትችቱ ፤ስንመለከት ደግሞ፤ ልደቱ እራሱ ሥርዓቱን የሚገልጽበት መገለጫ ከተቃዋሚዎቹ ጋር የሚያቀራርበው ስላልሆነ መጀመሪያ ልደቱ ሥርዓቱን የሚገልጽበት መገለጫ መነጽሩ ካላስተካከለ ወደ አንድ ወጥ ማግባቢያ የትግል አቅጣጫ ሊመራ የሚችል መስመር አይደልም እራሱ እያካሄደው ያለው ትግል። የልደቱ መጥፎ መስመር ካሁን በፊት ለአንባቢዎቼ ገልጫለሁ።ግልጽ ላደርገው፡ የልደቱ  አያሌው መስመር ምንድ ነው? ካሁን በፊት እንዲህ ሲል የገለጸውን ላስታውሳችሁ

የልደቱ አያሌው መስመር፤ በአንደበቱ እንዲህ ይላል፦

<<“ተቃዋሚዎች ለኢሕአዴግ ያላቸው የተሳሳተ አመለካከት ነው። ከሽግግሩ መንግሥት ጀምሮ የተከተሉትን አስተሳሰብ እስካሁን ድረስ ሊቀይሩት አልቻሉም። ኢሕአዴግ ይህን ሁሉ ልማት እየሰራ፤ ኢሕአዴግ እዚህ አገር የመጣው ‘አገር ለማፍረስ ነው! ለማጥፋት ነው!’ ብሎ እንደ አንድ ውጫዊ ሃይል መፈረጅ ይሄ አብሮ ለመስራት፤ለመመካከር፤አብሮ ለመስራት ትልቅ እንቅፋት የሆነው ይህ አቁዋማቸው ነው። ይህንን እምነታቸው መለወጥ አልቻሉም…..” >>፡ይላል፤ ልደቱ አያሌው ተቃዋሚ የሚባሉት እና ተማሩ የሚባሉ ክፍሎች ከገዢው ፓርቲ ጋር የአዳራሽ የውይይት ስብሰባ ላይ ከተናገረው የተወሰደ።

ልደቱ አያሌው እንዲህ ያለ ወያኔን የሚገልጽበት አቁዋሙ ከሌሎቹ የሚለይ ከሆነ ‘ልደቱ’ <<ይህ መንግሥት አገር ለማፍረስ የመጣ ወራሪ ሃይል ነው>> ብለው ከሚሉት ጋር የተቃራኒ መስመር አለኝ የሚለን ልደቱ አያሌው ዛሬ “ቪኦኤ“ ላይ ቀርቦ << ከመንግሥት በኩል ለድርደር የጋበዘን የለም፡ እንዳውም ድርጅታችን ለማፍረስ እየሞከረ ስለሆነ፤ ፍርድ ቤት ላይ ነን ያለነው፤ ከድረድሩ ተገፍተን ሳንወድ እንድንወጣ ተደርገናል”>> ይላል። ተቃዋሚዎቹ ከልደቱ የተለየ መስመር ስላላቸው “ገዢው መንግሥት ለድርድር ጋብዞ ኣብሮአቸው እንዲሰራ፤እንዲደራደር መንገድ የዘጋው “አገር ሊያፈርስ የመጣ  ወራሪ ሃይል ነው” ስላሉ ነው ካለ፤ “ታዲያ ለምንድነው ይህ ሥርዓት አገር አፍራሽ አይደለም፤ወራሪ አይደለም!” ሲል ተከራካሪ የሆነው ልደቱ አያሌው ከድርድሩ ተገፍትሮ መውጣት ብቻ ሳይሆን የልደቱ ፓርቲ የድርጅቱ (ኢዴአፓ) ህልውና አደጋ ለይ ወድቆ ገዢውን መንግሥት ፍርድ ቤት እንዲሞግት ህልውናውን እስከ መጥፋት እና አብሮ መስራት ያልቻለበት ምክንያት ምንድነው?

ሥርዓቱ ለድርደር ዝግጁ እንዳይሆን የልደቱን ዓይነት መስመር ተቃዋሚው ባለማራመዱ እንቅፋት ሆኗል የሚል ክስ በተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ ክስ ካስተጋባ የልደቱን ድርጅት ተደራዳሪዎች ለምን “ድረድር” ከሚባለው ተገፍተው እንዲወጡና በሌሎች አንዲተኩ ተደረገ? የሚለው ልደቱ መልስ ሊሰጠኝ ይገባዋል። እንደውም ለዚህ ሁሉ ችግር መድረስ ተቃዋሚው “በሙሉ” ሥርዓቱን በትከክል የሚገልጸውን “አገር ለማፍረስ የመጣ የወራረዎችን ተልዕኮ ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ሥልጣን የመጣ አፍራሽ ሃይል” ነው የሚለው መስመር ይዘው አገር ለሚያፈርስ የመጣን ቡድንም ሆነ መንግሥት ለመመከት የሚደረገው አገር አቀፍ የክተት ሥራ ያልመስራታቸው ለዚህ ሁሉ ችግር ተጋርጠናል። ልደቱ ለዚህ ብልሽት ይህ ነው የማይባል ከፍተኛ ብልሽት በትግሉ ውስጥ ውሃ ከከለሱበት አንዱ ልደቱ ነው።  ሆኖም ልደቱ <<“እኛ እንደ ተቃዋሚዎች ጥርት ያለ አቀውዋም ለሕዝቡ ማስያዝ አልቻልንም”>> በሚለው ላይ ከኔ ጋር ስለሚስማማ ትክክለኛ ተኩስ ተኩሷል።

ሌላው የቪኦኤ” እንግዳ ሆኖ ያደመጥነው፤ ሁላችሁም የምታውቁት “እየተነፋ እንደሚተነፍስ ጎማ ዓይነት ባሕሪ ያለው መያዣ መጨበጫ የሌለው አቁዋመ ቢስ “ሂፒክሪቱ” ብርሃኑ ነጋ መልስ አጥቶ ወዲያ ወዲህ ሲዋዥቅ አገር ለማዳን “ሠላማዊ የሽግግር መንግሥትስ እንዲመሠረት ምን ዓይነት እንቅስቃሴስ እያደረጋችሁ ነው? ተበሎ ለተጠየቀው ጥያቄ መልሱ እንዲህ ይላል-

<<ባንድ በኩል ብዙ ደም ሊያፋስስ ወደ እሚችል አቅጣጫ አገሪቱ አንደምትሄድ እና በሌላ በኩል ወደ ተረጋጋ ለውጥ ሊኬድ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል እናውቃለን….”>>

ካለ በላ ይቀጥልና

<<“ሶ/so/ ማናችንም አገሪቱ ወደ በየትኛው መንገድ ትሄዳለች የሚለውን ነገር አናውቀውም። ይህ እውቀት ያለው ‘ወታደሩን፤ደህንንቱን’ የሚቆጣጠረው ሃይል ጋር ነው።”>>

ይልና እንደገና

<<‘ያ ሃይል ወዴት እንደሚወስደን ባላወቅንበት ሁኔታ፤በዚህ መልክ ሊኬድ ይችላል፤በዚህ መንገድ መሄድ ይቻላል፤ እያልን በተረጋጋ መንፈስ እንኳ እሰኪ “እንዴት እንሂድበት” ወደ እምትልበት ውይይት መሄድ አትችልም”።>>  
በማለት አገሪቱ ወዴት እያመራች እንዳለች ባላወቅንበት ሁኔታ ለሽግግር መንግሥት የሚያመቻቹ ነገሮች የምንሰራበት እንቅስቃሴ ምንም ምክንያት የለምሲል የሽግግር መንግሥት የሚጠይቀው እንቅስቃሴዎች እንዳላደረገና ለማድረግም ፍላጎት እንደሌለው፤ለዚህም አገሪቱ ወዴት አንደምትሄድ ባላወቅንበት ሁኔታ እንዲህ ያለ እንቅስቃሴ አናደርግም ይላል። ይህ የሚያሳየን፤ ብርሃኑ እና ድርጅቱ ያገሪቱ ፖለቲካ ወደ መፍረስ እየሄደች ስለሆነ “ምን አለፋን” አይነት ደንቆሮ ፖለቲካ እየተከተለ ነው ወይንም ብዙዎቻችን እንደምንለው አምነት የማይጣልበት አታላይ ድርጅትና የሚጎነጉነው ሴራ እንዳለ ፍንጭ መሆኑን ያሳያል። እራሱን በለመደው መደበቅ ሲያምረው እንጂ ከነ ሌልጮ ጋር ምን እያደረገ እንደሆነ፤ በትግሬዎች ስም የሚነግደው የሻዕቢያው የፍተሻ ቡድን “ድምህት” ጋር ግምባር ፈጥሮ ምን እያደረገ እንዳለ፤ ቪዥን ኢትዮጵያ ከተባለው ጋር ምን እያደረገ እንዳለ እናውቃለን። አደልም እንዴ? ሆኖም ንግገሩን እንከተል እና እንተቸው።

ብርሃኑ የሽግግር መንግሥት ምሥረታ እንቅስቃሴ ሊያደርግ የሚችለው የሚከተለው ሁኔታ መደረጉ ማስያዣ (ኢንሹራንስ/መተማመኛ) ሲያገኝ ብቻ ነው። ያ መተማመኛ ደግሞ ከማን ነው የሚያገኘው? ወደ አንደበቱ ልውሰዳችሁ፤

እንዲህ ይላል፦

 <<..ስለዚህ በመጀመሪያ መሆን ያለበት ይሄ ሥርዓት በጉልበትም ሊሄድ እንደማይችል  አውቆ ካሁን በላ እዚህ ድርጅት ውስጥ በተለይ ህወሓት ውስጥ አሁንም በጉልበት እንሄዳለን ሥልጣናችንን ማስመለስ እንችላለን ቢሉ በፍፁም ለነሱም ላገሪቱም አደጋ እንደሆነና እዛ ሥልጣን ላይ ተመልሰው ልይዙ እንደማይችሉ ካወቁ ያንን እንደሚመለከት ደግሞ ግልጽ የሆነ አቅጣጫ ካስቀመጡ “then/ዜን” ያኔ እንዴት ያለ ብሔራዊ መግባባት እና ወደ እውነተኛ የሽግግረ ሂደት የምንገባበት ሁኔታ መኖሩ ከታወቀ፤ያኔ ሁሉም በተረጋጋ መንፈስ ያኔ እንዴት እንሂድበት ብለን መቀጠል ይቻላል። >>  ይላል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ። አስቂኝም፤ አስቆጪም ፤ፈገግ የሚያሰኝም የብርሃኑ እውነተኛ ስዕል የምናይበት ሌላው አጋጣሚ ነው።

በጣም ይገርማል! <<‘ያ ሃይል ወዴት እንደሚወስደን ባላወቅንበት ሁኔታ፤በዚህ መልክ ሊኬድ ይችላል፤በዚህ መንገድ መሄድ ይቻላል፤ እያልን በተረጋጋ መንፈስ እንኳ እሰኪ “እንዴት እንሂድበት” ወደ እምትልበት ውይይት መሄድ አትችልም”።>> 
በማለት አገሪቱ ወዴት እያመራች እንደለች ባላወቅንበት ሁኔታ ለሽግግር መንግሥት የሚያመቻቹ ነገሮች የምንሰራበት እንቅስቃሴ ምንም ምክንያት የለም ሲለን ወያኔዎች ለብርሃኑ ነጋ (ለግንቦት 7) ግልጽ የሆነ አቅጣጫ ካስቀመጡለት ያኔ “የቪ ኦ ኤው” ጠያቂ የጠየቀው <<“ሠላማዊ የሽግግር መንግሥት እንዲመሠረት ምን ዓይነት እንቅስቃሴስ እያደረጋችሁ ነው? >> ለሚለው ጥያቄ የምንሄድበት መንገድ በዚህ በዚህ ነው ብለን እንቅስቃሴ እንጀምራለን። ይላል። የብርሃኑ የሁሉም ጊዜ ‘ሂፖክሪቲክ” መልሱ “ልክ አንደ “ኢሳያስ አፈወርቂ” ከወዲያ ወዲህ እየጠማዘዘ አድማጮችን ግልጽ መልስ ላለመስጠት የሚጫወተው ጨዋታ “deceitful-lying and dishonesty” የማታለያና የውሸት መልሶች ሁሌም በነዚህ ሁለት ሰዎች ያየቸው ካራክተሮች ናቸው። ባንድ በኩል ‘አገሪቷ’ አስጊ ጎዳና ላይ እና ወደ ደም መፋሰስ ልትሄድ እንደምትችል ያምናል። ባንድ በኩል ወያኔዎች “ግልጽ የሆነ ብርት የማስቀመጥ ፍላጎት ካሳዩ” ሰላማዊ ሽግግር እንደሚደረግ ያትታል።” አንደገና ያንን የተለያዩ መላምቶች ያስቀምጥና ሁኔታው /አገሪቱ/ ወዴት እንደሚታመራ አይታወቅም ይላል። ከወያኔ ግልጽ አቅጣጫ ከመጠበቅ ይልቅ፡ እውነተኛ የፖለቲካ ሰው ሊናገረው የሚገባ ነገር <“ እንደ መስቀል ዳሜራ አገሪቷ የምትወድቅበት አቅጣጫ ማወቅ ካስቸገረው”> ለበጎም ለደግም “ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ” ብሎ ውዥምብር ውስ  ከመግባት የፖለቲካ ድርጅቶች ሃለፊነት ድንገት “ክፍተት” ሲፈጠርም ሆነ ድንገት “ጤነኛ ሽግግርና ድርድር” የሚጋብዝ ሁኔታ ነገ ቢፈጠር “በእጅ ላይ ያለውን ሠላማዊ የሽግግር መንግሥት አቀራረጽ እንቅስቃሴና የያንዳንዱ ድርጅቶች አምነት፤ መንግሥታዊ አወቃቀርና አስተዳዳር፤ ዕርቅ፤ የወንጀል ቅጣት፤ የግዛት አንድነት፤ ውጥንቅጡ ከወጣው የሰንደቃላማ ጉዳይ፤ አሁን የተያዙት የየክልሉ በየነገዶቹ የተሸነሸኑ መልክኣ ምድሮች አቀያየስ፤ የባሕር ወደብ፤ ሉዓላዊነት” ወዘተ የመሳሰሉትን አጀንዳዎች በግልጽ ይዞ መግባት ነው የሚቀለው ፤ ወይስ “ያኔ እናስብበታለን ነው? የሚባለው? ያውም የጠቀስኩዋቸው ነገሮች ያኔ ለወደፊቱ ሳይሆን “ሞረሽ ወገኔ” የተባለው አማራዊ ሲቪክ ማሕበር ከጥቂት ወራት በፊት አቁዋሙን ምን፤ምን መደረግ እንዳለት፤ ምን እንደሚፈልግ ለሕዝብ ይፋ እንዳደረገው ሁሉ ሌሎችም ዛሬውኑ አጀንዳችሁ ነግራችሁን ዜጎች የሚበጀውን የሚጎዳውን የሚጨምርም የሚቀነስም፤ የሚታረምም ካለ ይፋ ማድረግ ይጠበቅባችል። (The oppositions must be aware of their goals and positions and must identify the concerns to the public.. All opposiyions must determine their goals, anticipate what they want to achieve, and prepare for the negotiation process!)

ለነገሩ ሆኖ እንጂ ብርሃኑ ነጋ የሥልጣን ጥም የለኝም፤ግንቦት 7 ለሥልጣን አይታገልም፤ ይበል አይበል፤ እኩልነት ፤ ዲሞክራሲ፤ ሕዝብ ምናምን የሚለው የተለመደው የማታለያ ኮተቱ ለምናውቀው ሁሉ የማታለያ ዘዴ ከመሆን አያልፍም። ብርሃኑነን ለበርካታ አመታት የተከታተልን የፖለቲካ ተቺዎች ብርሃኑን በየመድረኩ ሲናገር በድምጹ የቀዳነውና እየታገለለት ያለው የምናውቀው መስመሩ እናውቀዋለን። ”ማንም ሕዝብ ልገንጠል ካለም ‘አትገነጠልም’ አንለውም፤ መገንጠል ከፈለገ “በሕዝብ ደምፅ” መገንጠል ይችላል”>> ሲል አድምጠነዋል። ብርሃኑ ወይንም ግንቦት 7 እያለን ያለው ማንም አካባቢ የወያኔን አንቀጽ 39 ተጠቅሞ እገነጠላለሁ ካለ ያንን የመገንጠል መብቱ በ51% ተጠቅሞ መገንጠል አንጂ “አገር አታፈርስም” ብለን በጠምንጃ አንይዘውም ሲል ሁሉም የመበታተን መብቱ በሕዝብ ድምጽ እንደሚያስከበር ብዙ ጊዜ ነግሮናል።ለዚህም ነው ከነ ሌንጮ ጋር እየተሻሸ ሰንደቃላማ ሲሰደብም አፉን ዘግቶ በየአዳራሹ ከነ ሌንጮ ጋር ሲሞዳሞድ የምናየው (የጋር መድርክም አላቸው! ይህንን ታውቃላችሁ አደለም?) ያንን “በሕዝብ” እና “በሕዝብ ብቻ” የሚለው ማጃጃያ መስመሩም ዛሬም በቪኦኤ አማርኛ ክፍል ፌስ ቡክ በተዘጋጀው በነ ሄኖክ ሰማ እግዚሔርና ከነ አሉላ ከበደ እንዲሁም ከአድማጮች ጋር በቀረበለት ጥያቄ ሁሉ ያንን “በሕዝብ የሚወሰን ሁሉ እንቀበላለን” መስመሩ ደጋግሞ አስደምጦናል።

የሕዝበ ውሳኔ የሚለው አገር ለማፍረስ የተላኩ ቅጥረኞች የሚጠቀሙባት ጣፋጭ ቃል። ብርሃኑ ነጋ አሜሪካን አገር እየኖረ፤ አሜሪካ አንድም ተገንጣይ ካሜሪካ ግዛት በሕዝብ ድምፅ አስረግጬ ልገንጠል የሚል ጠያቂ ሲኖር ምን መልስ እንደሚነገረው እያወቀ፤ ኢትዮጵያን የምታክል ጥንታዊት አገር “በሕዝብ ድምፅ” እናፈርሳለን እየተባለ ማንኛውንም አገር በድምጽ የተገነባ ይመስል የሥልጣኔና የዲሞክራሲ መገለጫ ነው በሚል “ኢትዮጵያን” በሕዝብ ድምጽ ለማፍረስ ዝግጁ ነኝ በማለት “የሕዝብ ውሳኔ” የሚለው ያረጀ ያፈጀ የሌኒኒስቶች “በሕዘብ ድምፅ ተንተርሶ እስከ መገንጠል” የንህሊስቶች አጀንዳ አሁንም ብዙ የዋህ “ገገማዎችን” የሚያሞኝ ሐረግ በመምዘዝ አገር ለማፍረስ ተዘጋጅቷዋል።

ኢንዲህ ያለ የተጭበረበረ ፖለቲካዊ ሰበካ የመያዙ አጀንዳ በብርሃኑ ነጋ ብቻ ሳይሆን በምክትሉ በንአምን ዘለቀም ኢሳት በተባለ ኔትወርክ የተዘጋጀው ቪዥን ኢትዮጵያ የተባለ በጌታቸው በጋሻው (ዶ/ር ዜሮ) የሚመራው “አፍቃሬ ኦነግ” ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መድረክ (ክፍል 3 ቪዲዮ በ2016 በፈረንጅ አቆጣጠር ( ESAT Special Program Vision Ethiopia & ESAT Conference Part 3 ) ሌንጮ ባቲ (የአውሮጳ ብርድ አልቻልኩትም አገሬ ልገባ ነው ያለንን ሽማግሌው ሌንጮ ለታ አይደለም እያልኩ ያለሁት። የአንድነት አስመሳይ ቀኝ አክራሪው ተገንጣዩ ወጣቱ ሌንጮ ባቲን ነው) አዲስ ቀለም ተቀብቶ የመጣብን “ዞር አሉ አልሸሹም” ሌላው የኦነግ ድርጅት ወክሎ ኦሮሞ በሚኒሊክ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የተቀላቀለች “በኮሊኒ” የተያዘች ነች (እራሱ ከተናገረው ቃል ልድገም እና የጋላ አገር እኮ መቸ እንደተያዘ ሲነገረን በወላጆቻችን ሲነገረን ያደግን ነን) ብሎ እዛው አዳራሽ ውስጥ ጅሎችን ሲያንጨጭብ ከነበረው ከባሌዎቹ  ”አክራሪው” ኦሮሞ ከ“ሌንጮ ባቲ” ጎን ቁጭ ብሎ ንአመን ዘለቀ የተናገረውን ቃል በቃል ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ።

 

ንአምን ዘለቀ እንዲህ ይላል፡

<< The most democtic system, powerful system ችግሮችን ልንፈታ የምንችልበት ሲስተም ዲሞክራቲክ ሲሰተም ነው። እነዚህ ሁለት የሆኑ ፒላሮች የኢትዮጵያ አንድነት እና ዲሞክራሲን ከተቀበልን እኛ ፖሊሲ አንመረምርም! ፖሊሲ የለንም እኛ።ንቅናቄ ነን። የኢትዮጵያ ፖሊሲ ምን ይሁን ፤ማሕበራዊ ፖሊሲ ምን ይሁን፤ ክልላዊ አወቃቀር ምን ዓይነት ይሁን..፤ ምን ዓይነት ፌደራላዊ አወቀቀር ይሁን የሚለው እኛ የለንም። በዚህ ከተስማማመን ወያኔ መወገድ ካለብት ከተስማማን ኩሉም ሃይሎች ጋር መተባበር እንደምንፈልግና አብርን መስራት እንደምንችል ግልጽ አድርገናል።>>  ይላል። (ንአምን ዘለቀ ቪዥን ኢትዮጵያ ከተባለው ‘የካባሎች’ ኔት ወርክ መድርክ ከተናገራቸው የተወሰደ)።   


እዚህ ላይ መሰመር ያለበት ነገር << መተባበር እና አብረን መስራት የምንችለው “የኢትዮጵያ አንድነት” እና  ‘ዲሞክራሲን’ መቀበል እንደ “ቅድመ ሁኔታ” አስቀምጧል። አንድነትን እንደ ቅድመ ሁኔታ እያስቀመጠ፤ አንደንትን የሚያፈርስ “የተለያዩ በዲሞክራሲ ውስጥ የተካተቱ የገሙ የገለሙ ፌደራሊዝም አወቃቀሮችን (ኤትኒክ…ግሩፕ..ፌደራሊዝም..) ያካተተ ዲሞክራሲ (እስከ መገንጠል ሁሉ ዲሞክራሲ ነውና) ነውና እንቀበላለን ይላል።

ቅድመ ሁኔታ ደግሞ፤ <ምን ዓይነት ዲሞክራሲ”? ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ “ድፍን ያለ” አሳሳች ዲሞክራሲ እንደሆነ ይነግረናል። ይሄውም ግልጽ ላድርገውና <<ፌዴራላዊ፤ክልላዊ አወቃቀር ምን ዓይነት ይሁን፤ ምንስ ዓይነት ፌደራላዊ አወቀቀር ይሁን የሚለው እኛ የለንም።>> በማለት ያ ለግንጠላ ሃይሎች መንገድ የሚፈቅድ /“ኤትኒክ ፌደራሊዝም”’\ ‘ያውም የወያኔው ዓይነት እና እነ ሌንጮ ባቲ ዓይነት የሚሰብኩትን ‘አሁን ያለው አወቃቀር’ እንዳውም ወደ ክልል ወርዶ “ቡድናዊ መብትን” በማጠናከር ኦቶኖሚውን ለጥጦ ‘እስከ መገንጠል ድረስ’ መፍቀድ የሚችለውን ፌደራሊዝምን የተቀበለ ቡድን ነው። ለዚህ ነው ፤ይህ ድርጅት “ካባል’ ነው ምስጢሩ አደገኛ እና ድብቅ ው የምላችሁ።

ብቻ ወያኔ እንጣል እንጂ ሲወድቅ ያኔ እንደርስበታለን የሚለው አነጋጋር ያኔም ችግር ከሚፈጥሩ አንዱ ግንቦት 7 እንደሆነ የታወቀ ነው። ምክንያቱም ተገንጣዮች አጀንዳቸው አሁን እና ከ40 አመት በፊትም ሠርተውበት አዘጋጅተው፤ተዘጋጅተውበት፤ ሙተውበት፤ ታስረውበት፤ ባንዴራ አቁመውበት፤ ቋንቋ ፈጥረውለት፤ ኦሮሚያ የሚባል አዲስ ክልል ፈጥረው 3/4ኛ መሬት ነጥቀው፤ ሕዝብ አደራጅተው፤ አወናብደውና አንቅተው ወዴት እንደሚሄዱ ስለሚያውቁ፤ እነ ብርሃኑና ንአምን ዘለቀ ግን ለሕዝባችን እየነገሩት ያሉት “ወዴት እንደምትሄድ ላ አንተ የምታውቀው ራስህ ነህ ፤ እዛ ላይ አናቅልህም! እያሉ ያሉትን ገበሬ ለተገንጣዮች እና አክራሪ ቡድኖች አመቻችተው ለጅብ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል ማለት ነው።

በመሰረቱ እነ ንአምን (ግንቦት7) የሚሰብኩት “ብቸኛ አማራጭ” The most democtic system, powerful system የሚሉት “ዲሞክራሲ <<“ብዙሃን ይመውኡ”> ማጆርቲ ዊን”“ማጆሪቲ ኦቨር ማይኖሪቲ”ብዙሃኑ በጥቂቶች ህይወት ላይ የመወሰን መብት ያለው”፤  የግለሰብ መብት የሚነጥቅ ስርዓት’ አይደለም ወይ እነ ንአምን “ብቸኛ እና የሰው ልጆች መብት አክባሪ” ብለው በትግሉ ለመተባባር “እንደ ቅድመ ሁኔታ” ያስቀመጡት ዲሞክራሲ የሚሉት?    

አንባቢዎቼ እዚህ ላይ እንድታውቁት የምፈልገው ኢትዮጵያ ሁለት አደገኛ ወጥመዶች ይጠብቋታል። አንደኛው ወጥመድ የወያኔ ወጥመድ ነው። ይኼውም አንደኛው እግርዋን አነጣጥሮ ለመቀርቀብ አፉን ከፍቶ ለመጨረሻ ግብአትዋ ተዘጋጅቶ እየጠበቃት ነው”>>፡ ሌላኛው ወጥመድ <<በዲሞክራሲ ሽፋን ስም በሕዝብ ድምፅ ‘ግንጣለን’ ለማከናወን የተዘጋጀው በነ ብርሃኑ ነጋና በተገንጣይ ሃይሎች የተጠመደው ወጥመድ ነው>>። እነዚህ ሁለት አፍራሾች ፊት ለፊት ቆመው የአገሪቷን እግሮች እንደ ‘ታራጅ ላም’ ጎትተው በመጣል የመጨረሻ ግብአትዋን ለማገባደድ የተዘጋጁ ሁለት ወጥመዶች እንዳሉ ልብ እንድትሉዋቸው እጠቁማለሁ።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)   ክፍል 2 ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን እና ትግሬዎች መልስ ለቬሮኒካ መላኩ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)

ክፍል 2 ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን እና ትግሬዎች
መልስ
ለቬሮኒካ መላኩ
ጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)
ባለፈው ሰሞን በክፍል 1 ጽሑፌ ኤርትራኖች እና ትግሬዎች በቋንቋ ብቻ ሳይሆን በደም አጥንትና በሃይማኖት የተዛመዱ መሆናቸውን በማስረጃ አቅርቤአለሁ። ቬሮኒካ መላኩ <<ትግራዮች እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ ሁለቱ የተለያዩ ነገዶች /ብሔሮች ናቸው !” በማለት ስለ ጻፈቺው>> የሰጠሁት መልስ የትግራይ ተወላጆች የቅርብ ጓደኞቼ የቬሮኒካን የታሪክ ደንቆሮነት አስገርሞአቸዋል። በርካታ ኢመይሎችም ደርሰውኛል። አንዳንዶቹ ኤርትራውያን ናቸው። በቀረበው ሰንድ ጭራሽ ያልገመቱት የሕዝብ ትስስር እና ስብጥር ሆኖ ስላገኙት በጣም በመገረማቸው፤ ከነሱ መካከል አንዱ እንዲህ ይላል፤-

<< “አገር ለመመስረት ትግሉን በመምራት እውን ያደረጉት የትግራይ ተወላጆች ወልደአብ ወልደማርያም እና ኢሳያስ አፈወርቅ ብቻ የመሰለን ብዙ ነን።የእነሱ ትግሬነትም በድፍን ድፈን ብዙ አይወራም ነበር። እንደብቅ ካላልንና እራሳችንን ለማሞኘት ካልፈለግን አንተ እንዳልከው እያንዳንዱ ኤርትራዊ ውስጣዊ ሐረጉ ምን እንደሆነ ስለሚጠራጠር ስለነሱ ትግሬነት ቀልብ አልሰጠውም ነበር ። በሚገርም ዘዴ በልዩ ሕዝብነት የሰበኩን ደግሞ እራሳቸው በአባትም እናትም ከትግራይ የተወለዱ እነ ወልደ አብ እና ኢሳያስ አፈወርቂ መሆናቸውን ስንመለከት ልዩ ጥናት ያስፈልገዋል። በጣም እናመሰግንሃለን፤ አስገራሚ ሰነድ!”>> ሲሉ በትግርኛ ጽፎልኛል።  እኔም አመሰግናለሁ።

ቬሮኒካ በጥርጣሬ ሻዕቢያው ተስፋየ ገብረአብ ሊሆን ይችላል በሚል አንድ መላምት ጠቅሼ ነበር። አሁን ግን እሱ አይደለም። ችግሩ ጸሐፊዎች በራስ መተማመን እና ያላወቅንላቸው ፍራቻ ስላላቸው በድብቅ ስም እየጻፉ ሕዝብን ሲያወናብዱ ማየት ከሚያሳዝነው ነገር አንዱ ይህ ችግር ነው። ባለፈው ክፍል መላው የትግራይ ክ/ሃገር አውራጃዎች ያካተተ በርካታ የትውልድ ሓረግ፤ እዛው መረብ ምላሽ ከነበረው ቀደምት ትውልድ ጋር በመደባለቅ የዛሬውን ትውልድ የፈጠረ መሆኑን እና በርካታ የኤርትራ ትውልዶች እና የቦታ ስሞች በነዚህ የትግራይ ሰዎች እንደተሰየሙ በማስረጃ አቅርቤአለሁ። ሳልጠቅስ የማላልፈው ግን፤ ያልተጠቀሱ የዛሬዎቹ የደምበዛን (ሓማሴን) ኗሪዎች ከደምብያ ጎንደር አካባቢ እንደመጡ በጣም በርካታ ማስረጃዎች በመጽሐፉ ውስጥ ይገኛሉ። እነሱም አስፈላጊ ስላልነበረ ዘልየዋለሁ።ከሞላ ጎደል ከያንዳንዱ  የትግራይ አውራጃ/ወረዳ ወደ መረብ ምላሽ ሄደው ከዘመነ አክሱም ጀምረው እስከ ቅርብ ጊዜ እንዴት እንደተዋለዱ አሳይቻለሁ። ያንን እውነታ የማፍረስ ሃይል ያለው “ፈጣሪ” እንጂ  በቅዠት ዓለም እየባነኑ ያሉት እነ “ቬሮኒካ መላኩ” ወይንም የቬሮኒካን ጽሑፍ ወደ ትግርኛ የተረጎመው ያልተከረከመው የሻዕቢያው “ድንጋይ” ኢብራሂም መሐመድ አይቻላቸውም።

ዛሬ የማቀርብላችሁ፤ በቬሮኒካ መላኩ ኤርትራ ውስጥ የሚገኙ “ብሔረ ትግርኛ” በሚል ሻዕቢያ የሰጣቸውን አዲስ የመጠሪያ ስም ተቀብለው ራሳቸውን የሚጠሩ የኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ‘ትግሬዎች” ከመረብ ምላሽ  ‘ወዲህ’ ላሉት ትግርኛ ተናጋሪ ትግሬዎች እንዴት እንደሚመለከትዋቸው በዓድዋው እና በተምቤኑ ተወላጁ በኢሳያስ አፈወርቂ የሚመሩ የሻዕቢያ “ካልቶች” በሚከተለው ሁኔታ ያይዋቸዋል ብላ ስላለቺው መልስ እሰጣለሁ። 

የቬሮኒካ ውሸት እጠቅሳለሁ፦
<< ብዙ ወገኖች ትግራዮች እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ አንድ አይነት ብሔር ይመስሉዋቸዋል። በመሰረቱ ግን ሁለቱ ፍፁም የተለያዩ ነገዶች ናቸው።ትግራዮች የኤርትራ ብሄረ ትግርኛን ትግራዮች ናቸው፤ አንድ ብሔር ነን ብለው ያስባሉ። ብዙ ትግራዮችም ኤርትራዊ የመሆን ፍላጎት አላቸው። የባድመ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት ብዙዎቹ ትግራዮች ራሳቸውን ኤርትራዊ እያሉ ይጠሩ ነበር። ከባድመ ጦርነት በሁዋላ እነዚህ ትግራዮች ከፍተኛ የሆነ የማንነት ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። በተቃራኒው ብሄረ ትግርኛዎች ስለ ትግራዮች ያላቸው ስሜት ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ትግራዮች ወይም አጋሜዎች እያሉ ይጠሩዋቸዋል። (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010) እነዚህ ኤርትራውያን ብሄረ ትግርኛዎች ትግራዮችን የማይታመኑ እና ልባቸው የማይገኝ አድርገው በአሉታዊ መንገድ ይስሉዋቸዋል።Eritreans sometimes contemptuously refer to them- cannot be trusted and never could.” (Smith,et al. 2003, Africa, volume 73, p.377) በኤርትራውያን ብሄረ ትግርኛዎች ላይ በተደረገው በዚህ አንትሮፖሎጅካል ማህበራዊ ጥናት ላይ አንድ eplf ታጋይ የነበረ ለፕሮፌሰር ሪድ አባቶቻችን እና ቅድመ አያቶቻችን እነዚህ ትግራዮች አደገኛ ናቸው በደንብ እናውቃቸዋለን ብለው አስጠንቅቀውናልብሎ ኤርትራውያን ነፃነታቸውን ባወጁበት ዓመተምህረት በአውሮፓ አቆጣጠር 1991 ወይም 1983 . ምስክርነት ሰጦ ነበር። “Be careful, these people are dangerous, we know them well!” (Smith,et al. 2003, Africa, volume 73, p.377 )>> (ቬሮኒካ መላኩ)

ስትል ሻዕቢያና የሻዕቢያ ፈረንጆች በማስረጃ አጣቅሳ የተናገሩትን የሻዕቢያ ስነልቦና አላዋቂነትዋን ነግራናለች። እንዲህ ያሉ ሕሊናዎች ትንንሽ ሰዎች ከመሆን አልፈው ያስተማራቸው ግብር ከፋይ ሕዝብ ቤተሰብንትና አንደነቱን ለመበተን ሲጥሩ ማየት ያሳዝናል። በሁለቱም በኩል ያሉት የተማሩት ክፍሎች በአሳፋሪ የሕሊና ውድቀት ሲታዩ ፈረንጆች ቦቶም ራክ ረገጠ የሚሉት የዝቅተት ወለል መርገጣቸውን ብዙ አመት ተናግሬአለሁ።፡ለዚህም ነው የተማሩ ክፍሎች አሁን ላለንበት ውድቀት ዳርገውናል ስል የነበረው።
ትግሬዎች የማይታመኑ ናቸው ስለተባለው መልስ እነሆ።

የኤርትራ አገርነት ምስረታና ህልውና ያለ ትግሬዎቹ ለምሳሌ ያለ ኢሳያስ አፈወርቂና ወልደአብ ወልደማርያም የማይታሰብ ነው። ኤርትራኖች በተለይ በትግሬው ኢትዮጵያዊው ኢሳያስ አፈወርቂ የተመራው የኤርትራን አገርነት የመመስረት ሰልት የሌላ አገር ሕዝብ መስሎ ለመታየት ምን ያህል ርቀት ተጉዞ በራስ ላይና በወላጆቻቸው ታሪክ ጭምር ክሕደት እንደተኬደ የማቀርብላችሁ ሚከተለው ማስረጃ ስትመለከቱ ሻዕቢያዎች ትግሬነታቸውን ብቻ ሳይሆን አፍሪቃዊ ማንነታቸውንም ጭምር በመፋቅ ለቅኝ ገዢዎች አጎብዳጆች ብቻ ሳይሆኑ የነጭ ቆዳ ልእልና በጥቀሮች ትግል ቅስም መሰበሩን አሳዝኖአቸው እንደነበር አሳያለሁ። ማስረጃየም እነሆ፡
የጥቁር ሕዝቦች አካል የሆነው በትግሬዎች የተመራው በቅኝ ገዢዎቹ በጣሊያኖች ላይ የተቀዳጀው የዶጋሊ ጦርነት ታስታውሳላችሁ። የጀግንነት ታሪክና አይበገሬነት  ከወራሪዎች ጋር ሲተናነቁ ለወደቁት በርካታየባሕረ ምድር እና የትግራይ ተወላጆችለከፈሉት ክቡር መስዋዕት የደርግ መንግሥት ያቆመው የመታሰቢያ ሃወልት ማን አፈረሰው? ለምንስ እንዲፈርስ ተደረገ? የሚለው በዚህ ጥያቄ እንድንጀምር እንድታሰምሩበት እፈልጋለሁ።

<<“ሻዕቢያ ኤርትራን ነፃ ካወጣ ላና በኤርትራመንግሥትካቋቋመ ተቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው ዶጋሊ ላይ የራስ አሉላን ሐውልት ማፍረስ ነበር። 1879 . ዶጋሊው ጦርነት ላይ 500 ጣሊያኖች በሞሞታቸው ኤርትራውያን ለምን እንዳዘኑ ብዙ ታዛቢዎች በውል ሊገባቸው አልቻለም።”>>

(መድሃኒየ ታደሰ -አዲስ አበባ በኮተቤ የትምህርት ተቋም አስተማሪና የምስራቅ አፍሪቃ ግጭቶችና የፖለቲካ ተንታኝ ልዩ ባለሞያ) Eritrean and Ethiopian war -Retrospect and Prospect (የኤርትራና የኢትዮጵያ ጦርነት የግጭቱ መነሸና መድረሻ ገጽ 34)
1879 . ዶጋሊው ጦርነት ላይ 500 ጣሊያኖች በሞሞታቸው ኤርትራውያን ለምን እንዳዘኑአንትሮፖሎጂስቶቹ ቬሮኒካ መላኩና ኢበራሂም መሐመድ መልስ እንጠብቃለን
 ትግሬዎች እነማን ናቸው ብላ ቬሮኒካ ለምትጠራጠረው ሕዝብ መልስ ልስጥ ። ለእርስዋ ብቻ ሳይሆን በቅርቡ ለምናያቸው መሰል ጸሐፍትም ጭምር። ትግራይ የሚለው ስም በአገር ስም፤ በክፍለሃገር ስም መጠሪያ ሆኖ ‘በአክሱም ዘመነ መንግሥትም ሆነ በዛጉዌ ዘመነ መንግሥት’ ትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማንነት ወይንም መጠሪያቸው ምን እንደነበር የሚታወቅ እንደሌለ ብዙ የታሪክ ጸሐፊዎች ይከራከራሉ። እኔ ደግሞ ለዚህ የሰጠሁት መልስ ነበር። እሱም በዘመነ አብርሃ አጽብሃ ትግሬዎች እንደነበሩና በስማቸው አንደተጠሩ ባለፈው ሰሞን በአቡነ ሰላማ የተጠቀሰ መሆኑን የግዕዙን ጥቅስ ገልጫለሁ። የኔን ክርክር ካልተቀበላችሁ፤ አንድ ነገር መስማማት እንችላለን። ይኼውም እንዲህ ነው።

“የታሪክ ምሁራን የሚስማሙበት አንድ ሃቅ አለ።ይሄውም ክልሉ የትግርኛ ተናጋሪዎች ማዕከል መሆኑ ነው” (ታደሰ ታምራት1964-53) (መድሃኔ ታደሰ) ዘኒ ከማሁ}። ይህንኑ አጠቃላይ ግንዛቤ የሚጻረር እስካልቀረበ ድረስ የዛሬዎቹ የትግርኛ ናጋሪዎች በአክሱምና በጥንቶቿ ቅርሶች አካባቢ መኖራቸው ከላይ በተጠቀሰው ድምዳሜ ይሆናል። 

የትግርኛ ተናጋሪዎች አካባቢ ማለትም የዛሬው የኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ እና የትግራይ ትግርኛ ተናጋሪ አካባቢ ማሕበረሰብ ሲመሰረት ቋንቋን መሰረት ያደረገ የግዛት አስተዳደር ነበር ብሎ ማለት ይቻላል። አሁን በቅርቡ በ17ኛ ምዕተ ዓመት ሁለተኛው አጋማሽ ላይ እንኳን የትግራይ ክልል ካርታ እንደሚያመለክተው የክልሉ ድንበር ሐማሴን ሰሜን ምስራቅ ጫፍ ወይም ቀይ ባሕር ዳርቻ ሲጠጋ ደቡብ ደግሞ እንደርታ ይደርሳል።>> (ባራዳስ) Tractatus Tres Historico-geographici 1634: A Seventeenth Century Historical and Geographical Account of Tigray, Ethiopia (Aethiopistische Forschungen) Dec 31, 1996 by Manoel Barradas and Elizabet Filleul) የውስጥ አስተዳደርን በተመለከተ ደግሞ የተለያዩ ገዢዎች በተለየ የማዕርግ መጠሪያ እስከ ዘመነ መሳፍንት መጀመሪያ ድረስ ገዝተዋል።ለምሳሌ የትግሬ መኮንን፤ባሕረ ነጋሽ፤,,,ወዘተ። ነገር ግን ሹም ሽሩን በተመለከተ ወሳኝ ሥልጣን የነበረው የጐንደር ቤተመንግሥት ወይም ንጉሥ ነበር። ይህንን አባባል በማስረጃ ለማስደግፍ ከተፈለገ ከ1512-1519 ዓ.ም ብቻ አራት ባሕረነጋሾች በንጉሡ ትዕዛዝ ሥልጣን እንዲለቁ ተደርገዋል ወይንም ቦታ ቀይረዋል (አልቫሬዝ፤ 1953፡93) ከላይ ከተጠቀሰው ዘመን በላም ቢሆን በትግራይ አካባቢ ያሉት የአካባቢ ገዢዎች (የባሕረ ነጋሹም ጭምር) ዕጣ ፈንታቸው የሚወሰነው በጐንደር ነገሥታት ነበር። ቢሆንም ግን የትግርኛ ተናጋሪዎች አከባቢ ትግራይን የፖለቲካ ማዕከል በማድረግ የተለያዩ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ማዕከል በማድረግ አንድ ዓይነት የሆነ (ከጥንት ጀምሮ የተገነባ) የቋንቋና የባህል መለያ ፈጥሯል። {መድሃኔ ታደሰ (ዘኒ ከማሁ)}። የሕዝቡን አንድነት እንኳን ከተመሳሳይ ባሕል፤ሃይማኖትና ቋንቋ ካለው አንድ ሕዝብ ቀርቶ አማርኛ ከሚናገረው የጎንደር አማራ ጭምር የተዛመደ መሆኑንም ጭምር ያሳያል።
                                                              
ትግሬዎችና ኤርትራኖች በተለያዩ ወቅቶች ጦርነት ውስጥ ገብተው ግጭት መፍጠራቸው የተለያዩ ሕዝቦች አድርገው ለመሰሪ ዓላማቸው መጠቀሚያ እንዲሆን እነ ቬሮኒካ መላኩ እና ሻዕቢያዎች የሚስሉት ጠማማና ከፋፋይ ስዕል በሚመለከትም መልሴ የሚከተለው ነው።በተለያዩ ከምድሪ ባሕሪ ወዲያ ና ወዲህ የሉት አውራጃ ወይንም አካባቢ ገዢዎች በየጊዜው ይታዩ የነበሩት አለመግባባቶች ምክንያቶች “አንድ ሕዝብ አይደለንም” ከሚል ሳይሆን የነዚህ አካባቢ ተወላጅ መኳንንቶች ራሳቸውን የትግርኛ አካባቢ የበላይ ገዢዎች ለማድረግ ከነበራቸው የሥልጣን መያዝ ፍላጎት እንጂ የተለዩ ሕዝቦች ሆነው ለማሳየት አልነበረም። የተለየን ሕዝቦች ነን ብለው ብቅ ያሉት አስገራሚ የሚያደርገው እራሳቸው ባባታቸውም በናታቸውም ከአክሱም፤ከዓድዋ፤ዓዲግራትና ከተምቤን የተወለዱ የኤርትራን ልዩ አገርነት እውን ለማድረግ የመሰረቱና የመሩት ሟቹ ወልደ አብ ወልደማርያም እና እስካሁንም በሠልጣን ላይ የሚገኙት እነ ኢሳያስ አፈወርቂ እና በሥሩ ያሉ የካቢኔው ባለሥልጣኖች ብዙዎቹ ትግሬዎች እንጂ ከዚያ በፊት በልዩ ሕዝብነት የተመሠረተ የጎላ እንቅስቃሴ አልነበረም። ከዚያ ባሻገር በጥንቱ ዘመን ሥልጣን ለማግኘት ራሳቸውን ያካባቢው ተወካዮች አድርገው በጎንደር ነገሥታት ፊት ለመታየት ሲያደርጉት የነበረው ግጭት እንዲሰመርበት እፈልጋለሁ። 

ለዚህም ማስረጃ ላቅርብ፡
አንድ ሕዝብና አካባቢ መሆናቸውን የሚያሳየው፤ የሕዝቡን መደበላለቅና መዋለድ ትልቁ ማስረጃ ያሳየሁት በቂ ሆኖ፤ አስተዳደራዊ ቁርኝቱም ቢሆን በፈረቃ አንድ ጌዜ የትግራይ ገዢዎች ከመረብ ምላሽ ሰሜንና ደቡብ ያለው ግዛት ሲገዙ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሃማሴኑ ተወላጅ አምደሃይማኖት መቀመጫቸው ዓድዋ አድርገው ይገዙ እንደነበር ይታወቃል። << የትግራይ ትግርኛ ተነጋሪ ገዢዎች ከመረብ ምላሽ ትግርኛ ተናጋሪ ገዢዎች በብዙ መልኩ ተሰሚነት ስለነበራቸው፤ከመረብ ምላሽ ሰሜን ያሉት ትግርኛ ተናጋሪዎች ከመረብ ደቡብ የሚገኙ የትግራይ ገዢዎችን እንደታላላቅ ወንድሞቻቸው ስለሚያዩዋቸው “ጥቃት” ሲደርስባቸው እንዲያግዣቸው ይጠይቋቸው ነበር።>> መድሃኔ ታደሰ (ዘኒ ከማሁ)። ይህ ሁኔታ የሚያሳየው ሁለቱም በመረብ ወንዝ የተጋረዱ ትግርኛ ተናጋሪዎችም ሆኑ ሌሎች ነገዶች ምንም ልዩነት እንደሌላቸው ነው። አፋር፤ ኩናማ፤ ትግርኛ፤ አገው፤ ሳሆ፤ እስልምና፤ ክርስትያን በሁለቱም ወገኖች ያሉት አንድ እንጂ የተለዩ አይደሉም።በሁለቱም ወገኖች የሚደመጡ የቃላት አወጣጥ አደማመጥ ዘይቤ ለልዩነት መነሻ አድርገው የሚወስዱ ወገኖች ካሉ እውቀት ያተራቸው ወገኖች ብቻ ናቸው። እነዚህ ጥቃቅን ድምጾች ለልዩነት የሚፈይዱት ፋይዳ አልነበርም፤ የለምም፤ አይኖርምም። ከመረብ ምላሽ ሰሜንም ሆኑ ደቡብ ያሉት የትግርኛ እና ሌሎች ነገዶች የሚደመጡት የቃላትም ሆነ የድምጽ አወጣጥ ካውራጃ አውራጃ የሚለያዩ መሆናቸውንም ልብ አላሉትም። ይህ በሌሎችም የሚታይ ሃቅ ነው።  

ቬሮኒካ መላኩ <<ብዙ ትግራዮችም ኤርትራዊ የመሆን ፍላጎት አላቸው።>> ስለምትለው ቅዠት ማስረጃ የላትም። ይህ ቅዠት ኤርትራኖች እራሳቸው የፈጠሩት ከጣሊያን የተማሩት ከንቱ ራንስ የማሳበጥ ዕብደት እንጂ  መሠረትም መረጃም የለውም።

 ቬሮኒካ አሁንም  <<የባድመ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት ብዙዎቹ ትግራዮች ራሳቸውን ኤርትራዊ እያሉ ይጠሩ ነበር።>>  ብላለች ይህም ከላይ እንዳሰመርኩበት መሰረተ ቢስ የኤርትራኖቹ ቅዠት ካልሆነ ምንም መረጃ የለም። ኤርትራኖቹ እንደ ትግሬው እና መላው ኢትዮጵያ 85% በግብርና ድህነት የሚኖር ገበሬ ነው። ስለሆነም በምን ስለተሻሉ ነው ትግሬዎች ኤርትራኖች ሊሆኑ ፍላጎት የሚያድርባቸው? ይህ ቅዠት ኤርትራዊው ዮሴፍ ገብረህይወት እንዳለው “አስማሪኖቹ” 85% የሆነውን ከኢትዮጵያ ገበሬዎች እኩል የሚኖሮው አርሶ አደር እና ዘላን ሕዝብ ጣሊያኖች በገነቡዋት በኮምቢሽታቶ ጎዳና የሚኩራሩ “የአስማሪኖ” ልጆች “ኤርትራን ሕዝብ” ባህልና አኗኗረት አያውቁትም።” ሲልኤርትራዊው ዮሴፍ ገብረህይወት ያረጋገጠልን  ቬሮኒካ የሰማች አትመስልም።

በመቀጠልም ቬሮኒካ መላኩ እንዲህ ትላለች፦
<<ከባድመ ጦርነት በሁዋላ እነዚህ ትግራዮች ከፍተኛ የሆነ የማንነት ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። >> ስላለችው አውነታው የተቃራኒ ነው።

ትግሬዎች ከጥንት ጀምረው ሃይለኛ ተዋጊዎች መሆናቸውን የሚጠራጠር ሰው ካለ ታሪክን አላነበበም ወይንም ሆን ብሎ በግል ጥላቸው ተነሳስቶ የሻዕቢያን ፈለግ የተከተለ ብቻ ነው። የትግራይ ታጋዮች የፖለቲካ መስመራቸውን ወደ ጎን ትተን፤ በተዋጊነት ብርታታቸው፤በርሃብ እና ውሃ ጥም ቻይነት ብርታታቸው እንደ ተንታኞች ለመነጋገር ከሆነ ሃቁ ኤርትራኖች ያለ ሃይለኛዎቹ የትግራይ ተዋጊ ሠራዊቶች (ወታደራዊም ፤ፖለቲካም) ድጋፍ “በምንም መልኩ” የኤርትራ ነፃነት ቅዠት ሆኖ ይቀር እንደነበር በእርግጠኛነት መናገር እችላለሁ (በዚህ የማይስማማ ተንታኝ ካለ በፈለገው መድርክ ክርክር ሊገጥመኝ እጋብዘዋለሁ)። ትግሬዎች በኤርትራኖች ላይ የበላይነት ያሳዩበት መድረክ የጀመረው ጀብሃ በተባለው ኤርትራ ተዋጊ ቡድን ላይ ነው። ይህ ቡድን ትግሬዎችን ብቻ ሳይሆን ሻዕቢያንም ጭምር ያስቸገረ የኤርትራን ትግል ጀማሪ የነበረው አንጋፋውና ሃይለኛው የጀብሃን ተዋጊ ሠራዊት ‘ኤርትራ ድረስ’ በመዝለቅ ‘እንክትክቱን’ አውጥቶ እስከወዲያኛው ድረስ ድምጥማጡ እንደማይሰማ አድርጎ ለበርካታ አመታት መሽጎበት ከነበረው ከኤርትራ መሬት ያስወጡት የትግራይ ተዋጊ ሠራዊቶች (ወያኔዎች) ናቸው።በዚህ የጀመረው የትግሬዎቹ ታጋዮች ቆፍጣና ተዋጊነትና የበላይነት ስሜት በኤርትራኖች መንፈስ ላይ የንቀትና የልዕልና ስሜት ያልጠበቁት ድንገተኛ ጫና በማሳረፍ ቀደም ብሎ  በሻዕቢያም ሆነ በበርካታ ኤርትራኖች በትግራይ ሕዝብም ሆነ በትግራይ ተዋጊ ሃይሎች ላይ የነበራቸው የተሳሳተ የንቀት ግምታቸው ባልጠበቁት ሁኔታ ስለተኮላሸባቸው ቆም ብለው እንዲአስቡ አድርጎአቸዋል።

በዚህም ምክንያት፤ ሳሕል ተራራ ላይ እንደ አይዮች እራሳቸውን ሸሽገው ለበርካታ አመታት ታራራ ላይ ተጣብቀው በጋለው የሳሕል ሓሩር እየተቃጠሉ ሲኖር የነበሩት ሻዕቢያዎች፤ “የወያኔ ትግሬ ተዋጊ ሃይሎች” ነፃ ባወጡላቸው የጀብሃ ሰፊ የኤርትራ መሬቶችን እንዲይዙ እና ከሳሕል ወጥተው ወደ ደጋማው ኤርትራ እንዲወርዱ ረዳቸው። ይህ ብርታት በጀብሃ ብቻ ሳየወሰን በተራ ሽፍቶችና ልምድ በነበራቸው ተዋጊ ሃይሎች በሱዳን እና በአሜሪካኖች ሲደገፍ በነበረው በኢድዩና በኢሕአፓ ላይ ሃያል ተዋጊነቱን አስመስክሮ ሁሉንም ከጥቅም ውጭ አድርጎአቸዋል። የዚህ ሽንፈት ቀማሾች ራስን ለመሸንገል ካልሆነ የሚክዱት አይሆንም። ታሪካዊ ትንተና ስለሆነ ከራስ ጋር ሲጋጭ ቢኮመጥጥም ‘ሃቁን’ መቀበል የግድ ይላል።

ጦርነቱ እየገፋ በሄደ መጠን የሻዕቢያ ተዋጊ ሃይሎች በኢትዮጵያ ተዋጊ ሠራዊቶች እየተነተረ፤ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ የኢትዮጵያን ተዋጊ ሃይሎች ብርቱ ክንድ መቋቋም ስላቃተው እንደገና ወደ መሸሺያው የሳሕል ታራራዎች ሸሽቶ ለሁተኛ ጊዜ ወገቡን አጎንብሶ “በሳሕል” ተራሮች ላይ እንዲወሰን ሆነ። አሁንም በከንቱ ጉራ ሲወጣጠር የነበረው ሻዕቢያ ለሁለተኛ ጊዜ በትግሬዎቹ ተዋጊ ሃይሎች የመዋጋት ብቃት የመዳኑን ውሳኔ ዕጣ ፍንታው በትግሬዎች እጅ ወደቀ። በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበር የተላከው ኢትዮጵያዊው ሠራዊት ሃያል ክንዱን በሻዕቢያ አከርካሪ ወገብ ላይ እያሳረፈ  የሳሕልን ተራራ ወገብ መክበብ ሲጀምር ፤ “ሻዕቢያ” ኤርትራ ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በተለይም ትግሬዎችን ከደርግ ጋር አብረዋል እያለ “በሰላይነት” እየከሰሰ ኤርትራኖች በመቀስቀስ ጥላቻ እንዲያድርባቸው ለሽንፈቱ መሸፈኛ የሚያገለግለው አዲስ ሴራ ጎነጎነ። 

ሻዕቢያ ለሽንፈቱ መሸፈኛ እንዲረዳውም በኪነት (ድራማ/ቲያትር) መልክ አዘጋጅቶ እንደ አይጥ በየመንደሩ ሾልኮ በመግባት ሕዝብ በመሰብሰብ ‘ኤርትራኖች’ በትግሬዎች ላይ ጥላቻ እንዲቋጥሩ ቀሰቀሰ። የድራማው ቅንብርም እውነት ለማስመሰል ከፌደሬሽኑ ጀምሮ እንደጀመረ ያላሰለሰ ጥርት በማድረግ ኤርትራዉያን የሆኑት የሐገር ፍቅር አባሎችም ሳይቀሩ በትግሬነትና በሰላይነት ኤርትራኖችም ጭምር በአባሪነት መክሰስ ጀመረ። በድራማው ውስጥም ትግሬዎች ሕዝብ በሚጠቀምባቸው ወንዞችና የጉድጓድ ውሃዎች ላይ “መርዝ እየጨመሩ ነው” በማለት በመዋሸት ሲያስፈልግም ውንጀላው አውነታ እንዲኖሮው እራሱ በኩሬዎች ላይ መርዝ እየጨመረ ሕዝብን ለማሳመን ሲል ያደረገውን ድራማ ወደ እውነታ እንደቀየረው ጦርነቱ ካበቃ በሗላ አንዳንድ ኤርትራኖች የተደበቀው የሻዕቢያ ወንጀል ሲዘረዝሩ ባደረጉት የፓልቶክ ቃለ መጥይቅና ውይየት በጆሮየ አድምጫለሁ። በዚህም ኤርትራ ውስጥ ለዘመናት የኖሩ ምስኪን የትግራይ ተወላጅ እረኞችማ ገበሬዎች እንዲሁም በንግድም ሆነ በሌላ ጉዳይ በየገጠሩ ሲዞሩ የተገኙትን ሁሉ እየለቀመ ሲሰልሉ ወይንም መርዝ በሚጠጣ የውሃ ምንጭ ላይ ሲጨምሩ የተያዙ “አጋሜዎች” እያለ ሕዝብ ፊት እያዞረ ከፍተኛ የጥላቻና የመለያየት ሴራ በመስራት ለሽንፈቱ መሸፈኛ ዘዴ እንዲሆነው ማጠንጠን ጀመረ።

ሕዝብን መዝለፍ ነውር ባልሆነባቸው በነዚህ የጫካ ትውልዶች ልሳን በድራማው ውስጥ የተካተቱ የጥላቻና የንቀት መቀስቀሻዎች “አጋሜ” የሚል ጣሊያኖች ያስተማርዋቸው የትግራይ አውራጃ አንዱ ክፍል በሆነው ጥንታዊው የአጋሜ  አውራጃ ስም በማንኳሰስ መልክ መጥራት  ነበር። ለዚህም ነው ምስኪንዋ “ቬሮኒካ መላኩ” << ብሄረ ትግርኛዎች ስለ ትግራዮች ያላቸው ስሜት ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ትግራዮች ወይም አጋሜዎች እያሉ ይጠሩዋቸዋል። (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010) >> ስትል እንደ ማስረጃ ታሳየናለች። በግልባጩ ትግሬዎች (ኢትዮጵያውያኖች) ኤርትራኖችን ምን ብለው እንደሚዘልፏቸው ቬሮኒካ ላንባቢዎቿ ልትነግር አልፈለገችም። አስቀድሜ እንደገለጽኩት በመሰዳደብ ምንም የምታስረዳው ነገር ስለሌለ ይህንን እንለፈውና እንቀጥል።

ከላይ እንደጠቀስኩት አጉል ጉራ ምክንያት አከርካሪው ላይ እስኪጎብጥ የተቀጠቀጠው ሻዕቢያ፤ ጦርነቱ እየገፋ በሄደ መጠን የሻዕቢያ ተዋጊ ሃይሎች በኢትዮጵያ ተዋጊ ሠራዊቶች እየተነተረ፤ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ እንደገና ወደ ለመደበት የመሸሺያው የሳሕል ታራራው ሸሽቶ ለሁተኛ ጊዜ “በሳሕል” ተራሮች እንደ አይጥ ሲወሸቅ፤ ሻዕቢያ ከደርግ ጋር ተደጋጋሚ ሚስጥራዊ ስምምነት በማድረግ “የዓሰብ ወደብን” ለኢትዮጵያ ለማስረከብ ምጽዋን ለኤርትራ ሰጥቶ በፌደሬሽን እንዲተሳሰሩ ጦርነቱ እንዲቆም መለመኑን እና መንግሥቱም እምቢ ብሎ ጦርነቱን እንደቀጠለ ይታወቃል። ሆኖም የትግሬ ተዋጊዎች ድረድሩ እንዲደናቀፍ ስለፈለጉ፤ የሻዕቢያ ዋነኛ ወታደራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ጠቅላይ እዝ (ቤዝ) የሆነውን የደቡብ ሳሕልን ክንፍ ከኢትዮጵያ ተዋጊ ሠራዊቶች ጥቃት ለመከላከል ተወዳዳሪ በሌለው ጽናት ተዋግቶ ሻዕቢያን ከመጨረሻ ግብአተ መሬቱ ጎትቶ አዳነው። ሻዕቢያ ማመን ቀርቶ መጠነኛ ምስጋና እንኳ ሊለግስ አልፈቀደም (መድሃኔ - ዘኒ ከማሁ)። ለሐፍረቱ መሸፈኛ ሲል ሊገልጸው ባይፈልግም በገለልተኛ ታዛቢዎች ሊካድ ከቶ አይቻልም።   

መድሃኔ ታደሰ እንዲህ ይላል፡ “በ974 ዓ.ም በቀይ ኮከብ ዘመቻ የተከፈተው በማክሸፍ ረገድ ህወሓት ወሳኝ ሚና መጫወቱን የሚያሳይ ፊልም ሆን ብለው እንዳጠፉት ይነገራል። እንዴት “ሃየለኞቹ” <<ኤርትራዉያን>> ትግራይ ሊያድናቸው ይቀበሉ?>> ካለ በላ <<ይኼውም የህወሓት ድጋፍ አንድ ቁም ነገር ያስታውሰናል።ይኼውም የጥንቶቹ ትግሬዎች ለመረብ ምላሽ ትግርኛ ተናጋሪ ወገኖቻቸው ያደርጉት የነበረው ድጋፍ መደገሙን ነው።>> መድሃኔ ታደሰ (ዘኒ ከማሁ)።

ለሁለተኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል የሆነው የትግሬ ሕዝብ መሬት በመድፈሩ የተነፈሰው ይህ የነ ቬሮኒካ መላኩ <<የኤርትራኖች የበላይነት ስሜት>> እንቆቅልሽ ለሦስተኛ ጊዜ እራሱ ሻዕቢያ በተነኮሰው ጦርነት በትግሬዎችና በኢትዮጵያውያን የተባባረ ክንድ ቁስሉን ላሰ። ለዚህም “ድፊትድ ኤርትራ/Defeated Eritrea” በሚል “ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ የተባለው  ዓለም አቀፍ የእንግሊዞች የቢቢሲው የዜና አውታር ይህንን ማቅረቡ ይታወሳል። ባድሜም እስካሁን ድረስ መንጠቅ አልቻለም። ለመንጠቅ ቢሞክር ያችን መራረ ብትር ጀርባው ላይ እንደምታርፍ ስለሚያውቅ ከጭኸትና አማልዱኝ በቀር በጉልበት ሊወስዳት አይቻለውም (አሁን ጦርነት ቢነሳም ሻዕቢያ ባድሜን መንጠየቅ እንደማይችል በእርግጠኛነት ስናገር በድፍረት ነው። ብዙ ተንታኞች በዚህ ከኔ ሊለዩ ይችላሉ። ካለው ሁኔታ፤ ሃቁ ግን ምንም ቢሆን ኢትዮጵያውያን በኢሳያስ ላይ ያላቸው ቂም ስላልበረደ ወያኔ ጥሪ ቢያደርግ የሚዋጋለት እንደማያጣ እሙን ነው፡ ከሚል ብቻ ሳይሆን፤ የኤርትራ ወጣቶች ባይል የተያዙ ስለሆኑ የመዋጋት አቅማቸውና ፍላጎታቸው የሟሸሸ ስለሆነ በጥቂት ሰአታት ውግያ እጃቸውን ይሰጣሉ። ሞላ አስገዶምን ያህል ተራ የሽምቅ ተዋጊ ቡድን ኤርትራን ድምበር ጥሶ ተዋግቶ ማለፍ ያቸለው የሚነግረን ነገር በወታደራዊ ዓይን እናንተው እንደትገምቱት እተወዋለሁ። ለዚህ ነው ኢሳያስ የባድመን ነገር በይደር ለማስቀመጥ እየመረጠ ያለው። የበሬው ቆለጥ ሲወዛወዝ ይወድቅልኝ ይሆን በሚል የቀበሮ ምኞት! ቢወድቅም ባይወድቅም ቢሞቱ ትግሬዎች ባድሜን ለሻዕቢያ አሳልፈው አይሰጡም። ለዚህ ነው፤በወያኔ ውስጥ የተሰገሰጉ “ለኤርትራ የሚያዳሉ ወያኔዎችም” መለስ ከሞተ በላ “ድፍረታቸውን” ውጠው ዝም እንዲሉ የተገደዱት)። ምክንያቱም ወያኔዎች ባድመን ለኤርትራኖች በተግባር አሳልፈው ከሰጡ በትግራይ ሕዝብ የቁጣ ማዕበል የወያኔ መሪዎች ህልውና በማግስቱ እንደሚያከትም ያውቃሉ
 (Defeated Eritrea Licks Its Wounds–BBC Focus On Africa -Ethiopian Semay 2000)

የኤርትራኖቹ የማንነት ቀውስ ዓለም ሙሉ ቢመጣ እናሸንፈዋለን ከሚለው ጀምሮ ማንነታቸውንም ጭምር ለአረቡ እና ለእስላም አገሮች ሸጠዋል። ቬሮኒካ ያላነበበቺው ማስረጃ ሊሆን ስለሚችል፤ ኣእምሮዋ ቢከፍትላት ይህ የሻዕቢያ ጋዜጣ እንዲህ ያለውን ልጥቀስ።

 <ኤርትራ የዓረቡና የእስላሙ ዓለምም እምብርት ናት>> (ሓዳስ ኤርትራ፤- 1988 ታሕሳስ 18)
የራስ ፍለጋ ቀውሱ በዛው ብቻ አልተቋጨም።የራስ ማንነት አግዝፎ በመሳልም  ዓንደብርሃን (ዶ/ር) የተባለ የድሮ ኢሳያስ አገልጋይ የነበረ ዛሬ በተቃዋሚነት ወዲያ ወዲህ የሚል ይህ ግለሰብም እንዲህ በሚል የግዝፍነት ቅዠት ሲቃዥ እንመለክት። እንዲህ ይላል፦  

<< የኤርትራ ፖሊሲ ከኤርትራ ድምበሮች ዘልቆ ወደ ኢትዮጵያ ድምበሮች ይመለከታል። ከኤርትራና ከኢትዮጵያ ድምበሮች ዘልቆም ወደ አፍሪቃ ቀንደም፤ ከአፍሪቃ ቀንድም ባሻገር አሁጉሪቱና ዓለማችንን ባጠቃላይ ይቃኛል።>> ሲል እራስን አግዝፎ በማሳየት ያስሰማው ትዕቢት ዛሬ ሕዝቦችዋ ነብር እንዳየች ፍየል ድምበሮችን እየጣሱ ከኤርትራ በመሸሽ የሲኦል ምድር ብለው አውግዘዋታል። እንዲህ ያለ ራስን ያለማወቅ ቁማር ገብተው የዓለም መሰቅያ ሆነዋል።

ኢትዮጵያን ቀርቶ ዓለምን እናሸንፋለን ሲሉ በአጉል ጉራ ሲበጠረቁ የነበሩት ኤርትራኖች “ቁስላቸውን ወደ መላስ ገብተው፤ ድሮ ጀምሮ የተካኑበትን ወደ ጥቁር ገበያ ገብተው ከሩስያ እስከ ኮንጎ ድረስ በተዘረጋ የመሳርያና የሉል/አልማዝ/ ሕገወጥ ግብይት በመሰማራት አውሮጳ ፤ዓረብ አገር እና አሜሪካ ድረስ አባሎቹን በማሰማራት በሕገ ወጥ ግብየት መሰማሩ አልፎ ሕገ ወጥ በሆነው የሰዎች ሽግግር ገበያ በመሰማራት የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ኤርትራን ሕዝብ በሚያሰቅቅ ስቃይ ውስጥ ከተቱት (ውጭ ጋር ልጆቻቸው ባይኖሩዋቸውና ገንዘብ ባይላክላቸው ሕዝቡ ባሰቃቂ ርሃብ ያልቅ ነበር)።

ቬሮኒካ መላኩ እንደምትቃዠው ሳይሆን ‘ትግሬዎች’ ከጦርነቱ በፊትም ሆነ በላ ትግሬዎች ኤርትራኖች የመሆን ፍላጎት ጭራሽ አድሮባቸውም አያወቅም፤ድሮም ዛሬም። አብሮነት አድሮባቸው ከሆነም አንድኖታቸውን ለማሳየት የሄዱበት ብቻ ነው። ለዚህም በትግሬዎች ምክንያት ኢትዮጵያ ለኤርትራኖች ምዝበራ ያጋለጥዋት መሆናቸው እራሳቸው የትግሬዎቹ መሪዎች ለሁለት አንዲሰነጠቁ ከሆነው ምክንያት አንደኛው እና ቀንደኛው ምክንያት ይህ ነበር። ሆኖም የኤርትራ ማንነት መስራቾች የሆኑት ሻዕቢያ መሪዎችና ተከታዮቻቸው የማይታመኑ ስለሆኑ፤ የመክዳት ባሕሪን እንደ አደገኛ አመል ስለተጠናወታቸው የፖለቲካ ዕውር ካልሆነ በቀር “ሻዕቢያን” አምኖ የሚራመድ ቡድን ካለ “ራሱን ችግር” ውስጥ ለመክተት ፈቃደኛ የሆነ ጅል ብቻ ነው።

ካስፈለገም በክፍል 3 እስክመለሰበት ድረስ “በመድሃኔ ታደሰ” ትንተና በዚህ ላጠቃልል።
< አንዳንድ ኤርትራውያን ምሁራንን ጨምሮ ስልጣኔን እንዴት እንደሚተረጉሙት ማየት ብቻ ይበቃል። ለነዚህ ክፍሎች የስልጣኔ ትርጉም ጣሊያኖች የተውትን ፊያት መኪና ከማሽከርከርና በጣሊያኖች ቪላ ከመኖር አያልፍም። “ከሌሎቹ የተሻለ ስልጡን ነን”  የሚለው አባባል አልፋና ኦሜጋው የጣሊያንን አገዛዝ ከማድነቅ አይዘልም። አፍሪካውያንና መላው የዓለም  ሕዝብ የሚኮንነውን በባርነት የመገዛት ተግባር ኤርትራውያን ታዋቂ ሰዎች እርካታን ያገኙበታል። በእርግጥም በርካታ ኤርትራውያን የአውሮፓ አገዛዝ ለሦስተኛው ዓለም ተስማሚ ነው ብለው በማስተዋወቅ ረገድ ዝነኞች ሁነዋል።

የዛሬይቱም ኤርትራ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ለቅኝ አገዛዝ ትልቅ ፍቅርን ሲያሳዩ ማየት ግራ የሚያጋባ ሁኗል። በአጠቃላይ ለመናገር ካስፈለገ የጣሊያን ቅኝ አገዛዝ አወዳሽ የሆኑት የኤርትራ ምሁራን ስለዛሬይቱ ኤርትራ ተጨባጭ ሁኔታ ከማውራት ይልቅ ስለቅኝ አገዛዝ ዘመን መጥቀሱ ይቀናቸዋል። ግራ የሚያጋባ ማሕበራዊ ስነልቦና ነው? ገጽ 55 (ዝኒ ከማሁ)

ለዚህ ነው ብዙ ታዛቢዎች ኤርትራውያን ጣሊያኖች ይፈፅሙባቸው የነበረውን የጥላቻና የትምክሕት ድርጊት  እንደማካካሻነት በትግሬዎች (ኢትዮጵያውያን) ላይ አማራውን ‘አድጊ’ ትግሬውን ‘አጋሜ’ እያሉ  ያንጸባርቁታል የሚሉት። “መድሀኔ ታደሰ” ለዚህ ማጠቃለያየ እንዲህ ሲል በጥሩ ደምድሞታል << ተገዢዎች  የገዢዎችን የኩራትና የጥላቻ ስሜት ተቀፅላ ናቸው፡ ብለው ብዙ ተንታኞች ያምናሉ>>።
 አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ