Tuesday, December 27, 2011

እኛና ንጉሥ የሌላቸው አንበጦች


To see the page/font with a wider range, please press the key Ctrl and + sign. To view the page/font with a narrow range, please press the key CTRL and _ sign

የሚታየው የወያኔ ገበና ማህደር አዲሱ መጽሐፍ ለመግዛት $30.00 ዶላር ሲሆን ይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፍ ደግሞ $25.00 ወይንም ሓይካማ የሚለው የትግርኛ መጽሐፌ ደግሞ $15.00 ዶላር ብትልኩ መጽሐፎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።Getachew Reda P. O.Box 2219 San Jose, CA 95109 getachre@aol.com Phone (408) 561 4836

እኛና ንጉሥ የሌላቸው አንበጦች

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ዘጋጅ) www.ethiopiansemay.blogspot.com
የሚመለከተው ግጥም የተገጠመው ከዳዊት ግርማ አዲስ አበባ በሐመር መጽሔት ላይ ታትሞ ነበር። ርዕሱ ጥቃቅን ፍጡሮች የሚል ነው።

ጥቃቅን ፍጡሮች

አንበጦች ንጉሥ የሌላቸው

በመልካም ሥርዐት ሲሔዱ አየናቸው

ጠቢቡ በመጣፍ አደናነቃቸው

የነገሥታት ንጉሥ

ሳለ ንጉሣችን ሕግና ሥርዐት ሰጥቶ አወጥቶልን

ካንበጦቹ መንጋ  እንዲህ ያሳነሰን

መራመድ በስርዐት እንዴት አልሆንልን አለን?

አዎን ይህ ግጥም ለፖለቲከኞችም ሆነ ሃይማኖትን እናከብራለን ብለው በየቤተጸሎቱ (መስጊድ፤ቤተክርስትያን) እሁድ እሁድ በየሳምንቱም ሆነ በየቀኑ ጸሎታቸውን ለፈጣሪያቸው የሚያደርሱትን ሰዎች/ማሕበረሰቦችን ሁሉ ይመለከታል።

ወላጆቻችን ኢትዮጵያ የምትባል አገር መሥርተው አብሮነትን በማስተማር ሲያቆዩልን፤ ይህ ትውልድ ከገጠመው ፈተና በላይ ገጥሟቸዋል። አሁን የምናያቸው የርስ በርስ መጠላለፍ፤ጥላቻ፤ትምክሕት፤አዋቂ ነኝ ባይነት፤ምቀኝነት፤ጦርነት፤መካሰስ፤መወቃቀስ፤የነገድ ጥላቻ፤ሀሰት፤መረን ያለፈ ቁጣ፤መገዳደል፤በውሸት ራስን መካብ ክሕደት ወዘተ…የመሳሰሉ የማሕበረሰባዊ ጠንቆች አሁን የተከሰቱ ሳይሆኑ የሰው ልጅ ሲፈጠር ጀምሮ የተከሰቱ የሕሊና በሽታዎች ናቸው።
እነኚህ የሕሊና በሽታዎች እኛን እንደጠመዱን ሁሉ ፤ወላጆቻችን እና ቅድመ ወላጆቻችን የነበሩ ወላጆቻቸውም ጭምር የገጠሟቸው ማሕበራዊ ጠንቆች ናቸው። ነገር ግን በእንኚህ ጠንቆች ሲጠለፉ በፈሪሃ እግዚአብሐር/አላህ ነገሮችን በውይይት እና በትዕግሥት ሲፈቷቸው ብዙ ጊዜ ታሪክ አንብበናል። ነገሥታቱም፤ነገዶችም የተከተሉት የመፍቻ ዘዴ ሽማግሌዎች እና ወጣቶች በዕርቅ ሂደት እና በጋብቻ ነበር።  ለዚህ መሳርያ የሆነው “ትዕግስት” የተባለ አቅል የሚፈትን ፈተና በመሸከም እና በመቻል ነው።

ትዕግስት የመረጡበት የመፍቻው ዘዴአቸው ተጠቅመው ለማምጣት የፈለጉት ግብ “የአብሮነትን መኖር” ለማጎልበት እና ለማቆየት የዛው ዘመን ሰዎች መለኪያቸው “ፈሪሃ እግዚአብሔር እና ወዳጆቻቸዉን ላለማስቀየም” በጣም የሚጠነቀቁ ሕብረተሰቦች ነበሩ።

የጥንት አይሁድ፤ክርስትና እና እስላም የመሰረተች አገር ኢትዮጵያ እና አሁን ያለው ትውልድ ስናወደድረው መስጊድ ወይንም ቤተክርስትያን እሁድ እሁድ/አርብ አርብ ስለሄደ ወይንም በየሬዲዮኑ እና በዘመኑ ኢንተርነት ፓል ቶክ ስለ ሃይማኖት ስለ ፖለቲካ ሰበካ ስለተወያዩ “እውነት የጨበጡ” እየመሰላቸው አብሮዋቸው በየመስጊዱ/ቤተክርስትያን ያልሄዱትን ወይንም የማይሳተፉትን ክፍሎች በየምክንያቱ ከነሱ ጋር ሳይስማሙ በቀሩ ቁጥር “ሃይማኖተ ቢሶች/ኤቲስት” “ሃጥአን” እያሉ ሲመጻደቁ ይደመጣሉ። ስለዚህም “ካለ እኔ በስተቀር አትፍረድ” ያለውን መመሪያ በመጣስ በሃሰት እና መጠን ባለፈ ትምክሕት ራሳቸውን “ክፍ፤ከፍ” በማድረግ “አንድን ነገር በራሳቸው ትርጉም እየተረጎሙ” ከፈጣሪያቸው ጋር ይጣላሉ።

ፖለቲካውና ሃይማኖቱ አሁን ባለው ሁኔታ እየደፈረሰ ያለበት ዋናው ምክንያት “ፈሪሃ እግዚአብሔር አለን” በሚሉ እና “ሃይመኖተ ቢሶች” በሚሏቸው የሃይማኖት አማንያን እና “አድሃሪ እና ተራማጅ” “ብሔረተኛ እና አገር ወዳድ” “ባንዳ እና አገር አስከባሪ” በሚባባሉት የፖለቲካ ተከታዮች እየታየ ያለው የደፈረሰው አየር ስንመለከት አብሮ ለመኖር የሚያስፈልገውን የመቀባበልን ሕግ ስላልተከተለ ነው።

ቡድንተኛነት፤ወገንተኛነት፤በጎሳ መሰባሰብ አልፍ ብሎም ሰዎች በጎሳቸው ወይንም በተወለዱበት አካባቢ በማያስፈልግ ጊዜ እና ቦታ ሰውየውን ለማስቀየም በመጥራት የሚፈልጉትን ትምክሕት ለመጫን በመሞከራቸው ነው። ብዙ ጊዜ ስለተናገርንበት መድገሙ ኣላስፈለገኝም።
ባለፉት ጽሑፎቼ እንደገለጽኩት “አገር ውስጥም ሆኑ ውጭ አገር ያሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች እና ግለሰዎች የወያኔን ጎሰኛ እና ፀረ ኢትዮጵያ ስርዓት ለማስወገድ ከፈለጉ “በመልካም ስርዓት ተሰልፈው እንደሚጓዙ ንጉሥ እንደሌላቸው አንበጦቹ” ባንድነት እና በሥርዓት ካልተጓዙ አሁን ባለው የተዘበራረቀ፤ ጥላቻ፤ጎሰኛነት፤ውሸት፤ ትምክሕት እና ቡድንተኛነት የሚመራው ባሕሪ ከተከተለ ደግሜ ደጋግሜ እንደተናገርኩት “ወያኔን” በስሜት ካልሆነ በቀር በተግባር ወያኔን ማስወገድ አይቻልም።አራት ነጥብ።

ይህ ዕውነታ አልዋጥ ያላቸው ሰዎች እኔኑን በመሰላቸው መንገድ እየተረጐሙ ረዥሙን የጥላቻ፤የትምከሕት እና የድንቁርና እንዲሁም የጎሰኛነት ጅራፋቸው ሲያስጮሁብኝ አደምጣቸዋለሁ።
ትግሉ ከመቸውም በበለጠ “መሪ” ያጣበት ወቅት ሆኖ እያለ በስሜት እየተነዱ “ማለቂያ የሌለው “ጋዜጣዊ”መግለጫ እና አዳዲስ የመሪዎች ፊት እና ቃለ መሓላ ማሰማት” የወያኔን ብርክ እያንቀጠቀጠው እንደሆነ፤ እና ወያኔ “አንድ ዓርብ” እንደቀረው አስመስለው የሚደሰኩሩ በስሜት የተጠመዱ የትግል አቀበት እና የጠላት ጥንካሬ የማያውቁ፤ዓቀበቱ ፈታኝ ሲሆን ሸብረክ በሚሉ ሰዎች/ክፍሎች የሚነዛው ትግልን የሚያሳስት አጭበርባሪ ፕሮፓጋንዳ ማስተጋባቱ የትግሉ ፈታኝነት አቅሙ ምን ያህል እንደሆነ እንዳይታይ የሚያደርጉ የዜና አውታሮች እና ተቺ ሃፊዎች ከዚህ ስንፍና መራቅ አለባቸው።
 
ያለውን የተቃዋሚው ደካማ ጉልበት እና ቆራጥ መሪ ማጣት መጠቆም ያለበት ድክምት እንዳለፈው ሌላ አሳፋሪ ውጤት እንዳይከሰት ከመደገሙ በፊት በጊዜው ስንጠቁም የውሸት እና የስሜት ፕሮፓጋንዳ እና የፓል ቶክ ጎሰኞች ወሬ ሱስ የየዛቸው  ዙረተኞች ተግሳፅ ስናዳምጥ ‘ተቃዋሚን መውቀስ’ ታቦትን እንደ መንካት አስመስለው የሚተረጉሙ ሰዎች አሉ። በአንጻሩ አንድ የተቃዋሚ መሪ ከአገር ውስጥ እንዳስተላለፉልኝ መልዕክት ግን “ያንተ ወቀሳ ለክፋት ሳይሆን ለኛ ብርታት ፍለጋ በመሆኑ በርታ፤እንፈልገዋለን እንጂ አንጠላውም” ሲሉኝ ከልብ አመሰገንኳቸው። ለዚህም አንዲት የበረሐ ወፍ የተናገረችው ተግሳፅ ምሳሌን ያስታውሰናል።

“አንድ ገበሬ የአንዲት ወፍ አንድ ዐይን በወንጭፍ ድንጋይ ያጠፋል። ወፊቱ ደሟን እያንጠፋጠፈች ስታለቅስ አንድ ሥራ ጠል ዘዋሪ ባሕታዊ አይቶ ርኅሩሕ በመመሰል “የዚችን ወፍ አንድ ዐይን እንዳጠፋህ የአንተ ሁለት ዐይኖች ድርግም ይበሉ፡ እስኪ ምን በድላህ ነው አንድ ዐይኗን ያጠፋህ?” እያለ ረገመው፡
የእግዚአብሐር መንፈስ ሰብአዊ አንደበትን የሰጣት ያች ወፍ ሰምታ “እረ የአንተ ዐይኖች ድርግም ይበሉ! ገበሬው ዐይኔን ቢያጠፋ እየመገበ  ያድነኛል። እንዳንተ ካለው ሥራ ፈት ግን ምን ይገኛል? ስለዚህ በእኔ እና በገበሬው መካከል ምንም አያገባህም ዝም ብለህ ዙረትህን ቀጥል” አለችው ይባላል። (መጋቤ አእላፍ መክብብ አጥናፉ)።
የፖለቲካ መሪዎቹ ደካሞች እንኳ ቢሆኑም ትግሉ እና ትግሉን የሚመሩ መሪዎች እንዳይጠነክሩና ጠላትን በበቂ እንዳይመክቱ የሚያደርጉት “አትውቀሷቸው፤አትንኳቸው፤አታርሟቸው፤…” የሚሉን ደጋፊዎቻቸው እና የፓል ቶክ መሸተኞች እንጂ መሪዎቹ ለድክመታቸው ብዙም ተጠያቂዎች አይመስለኝም።
እንዲህ ከሆነ፤ እኛ በስርዐት ከሚሄዱ ንጉሥ ከሌላቸው አምበጦች እና ጥቃቅን ፍጡሮች የበለጠ ሕሊና ይዘን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ማቅናት ካልቻልን፤ዳዊት ግርማ ተዋናይ በሚለው ግጥሙ እንዳለው፤
“ሞትን ሰባት ሳይሆን ሺሕ ዓመት በቆምከው
ፊት ዘመን ያለፉ ደጋግ አባቶቼን አሁን እንዳያቸው” ያሰኛል።
 ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ዘጋጅ) www.ethiopiansemay.blogspot.com


Monday, December 19, 2011

አክራሪ እስልምና እና የሚዲያዎች አዘጋገብ ባሕሪ በኢትዮጵያ

 

አክራሪ እስልምና እና የሚዲያዎች አዘጋገብ ባሕሪ በኢትዮጵያ
ታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

ትጉ እንጂ ስለ ስማችሁ መጥፋት አታስቡ! (የሳምንቱ የዚህ ዝግጅት ጥቅስ)

የአገራችን ሚዲያዎችም ነገሩ በውል ሳያጤኑና በበቂ ሳይረዱ በአክራሪ እስልምናው ወጥመድ ውስጥ ተዘፈቁ።በዚህም ለእነርሱ መብት የሚታገሉ ወይም ክብር የሚሰጡ መሆናቸውን ለመግለጽ ሲጣደፉ በሌሎቹ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ወድቀው የግፍ ተባባሪዎች ሆኑ’   ከዚህ ዓምድ የቀረበው ትችት የተቀነጨበ።

በዚህ ዓምድ የሚቀርበው ትችት ሰሞኑን አክራሪ እስላሞች በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረሱት በኦርቶዶክስ እና በጠቅላላ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰ እና ለበርካታ ዓመታት የደረሰው ጥቃት አብዛኛዎቹ ሚዲያዎች ለብዙ ዓመታት አውቀውም ሳያውቁም ለአክራሪው እስላም ትንኰሳ የዜና እና የፖለቲካ ሽፋን በመስጠት ያበረከቱት ድርሻ እንመለከታለን።
ጽሑፉ  ተገኘው ምሬታቸው ከገለጹ አንድ ድያቆን ሲሆኑ - ድረ ገጼ ፒዲኤፍ መቀበል ስለማይችል በዎርድ ፎርማት እራሴው እንደገና በመጻፍ አቅርቤዋለሁ። ትችቱን  ለላኩልኝ ከልብ አመሰግናለሁ።
በትችቱ ላይ አንዳንድ ነገሮች እርምት አድረጌአለሁ/ወይንም ላለማስረዘም ብዙ ሐተታ የያዙ ገጾችን ዘልያለሁ።  የትችቱ ዘገባ “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ” /ማቴ.፳፮፶፪/ የሚል ነው።
(“ወነገረኒ ዓዲ በእንተ ምጽአተ እስላም ወይበለነ ናሁ ይበጽሕ ጊዜሁ ከመ ኵሉ ዘይትቀትለክሙ ኢመስሎ ከመ ዘመሥዋዕረ ያበውእ ለእግዚአብሔር፣” (“ዳግመኛም ስለ እስልምና መምጣት ነግሮናል፣ እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዳቀረበ የሚመሰልበት ጊዜ ይደርሳል፣ ብሎናልና።”) አንቀጸ አሚን
የህን የወንጌል ቃል ጠቅሰው ስለ እስላም እንደተነገረ ያስረዱት አባ እንባቆም መጀመሪያ በእስላም ሃይማኖት የነበሩ ሰው ናቸው። አባ ዕንባቆም በትውልድ የመናዊ ሲሆኑ ቁርዓንን ሲመረምሩ የተነገረውን ይዘው አብዝተው በመጸለይና እውነቱን ግለጽልኝ በማለት ሱባ ሲገቡ ጌታችን እውነቱን ገልጾላቸው ወደ ክርስትና የተመለሱ ሰው ናቸው። አባ ዕንባቆም ወደ ክርስትና ሲመለሱ እንደተለመደው ሁሉ አክራሪ እስላሞች ሊገድሏቸው ተነሡ።
በእሳቸው ክርስትያን መሆን ምክንያትም ብዙ አብያተ ክርስትያናትን ያቃጠሉ ፤ክርስትያኖችንም ያሳድዱ ጀመር። አባ ዕንባቆምም ከአክራሪዎቹ እየሸሹ ነገር ግን ከዚያው ከቁርዓን እየጠቀሱ ክርከራቸውን በጽሑፍ ይልኩላቸው ጀመር። በዚህ ወቅት እርሳቸውን አሳድዶ ለመያዝ የተላከ አንድ የአክራሪ እስላም የጦር እዝማች እስኪ የምትለውን በደንብ አስረዳኝ፤ ከዚህ በላ እኔ ቤተ ክርስቲያንም አላቃጥልም፤ ክርስትያኖችንም አልገድልም፤ ሲላቸው ለእርሱ አንድ መጽሐፍ አዘጋጅተው ላኩለት፤ “አንቀጸ አሚን”ን።
ከዚህ መጽሐፍ በመጥቀስ የምንነሣው ክርስትና እንኳንስ የኖሩበትን የተለወጡትንም ሰይፍ ከማንሣትና በሰይፍ ከማጥቃት ኅሊና መልሶ እንዴት ሰላማዊ እንደሚደረግ ለማሳየት ነው። ራሳቸው አባ ዕንባቆምም ወደ ክርስትና ከተመለሱ በላ ሲጽፉለት “ኦ እማም እምይእዜሰ እወስአከ በቃለ ትሕትና በከመ አዘዘኒ መጽሐፈ እምነትየ፦(ኢማም ሆይ ከእንግዲህስ በላ የምመልስልህ የሃይማኖቴ መጽሐፍ እንዳዘዘኝ በቃለ ትሕትና ነው’) ይላሉ።
በዚሁ መሠረት ክርስትና ቀማኛውን መጽዋች፤ዓማፂውን አገልጋይ፤ዘማውን ድንግል ያደርገ፤…የትሕትና እና የፍቅር ሃይማኖት ነው። አባ ዕንባቆም ከሀገራቸው ከየመን ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በተለያዩ ገዳማት ተዟዙረው የቤተ ክርስትያኒቱን ትምህርት ልቅም አድርገው የተማሩ እና በምንኩስና የኖሩ በመጨረሻም ለደብረ ሊባኖስ ገዳም አበምኔትነት/እጨጌነት/ የተመረጡ የበቁ ሰው ነበሩ። እስካሁንም የሚታወቁት እጨጌ ዕንባቆም በመባል ነው።
 ኢጨጌው ታሪክ ለመግቢያነት ቀንጨብ አድርገን ያየነው ክርስትና መርሑና አስተምህሮው ምን እንደሆነ በተግባር ከለወጣቸው ሰዎች ለማሳየት ብቻ አይደለም። ይልቁንም በየዘመኑ የነበሩ አባቶቻችን በየዘመናቸው ከአክራሪ እስላሞች የደረሰባቸውን የግፍና መከራ በመጠቆም ወደ ዘመናችን የአክራሪዎች ትንኰሳ ለመግባት ነው።
የአክራሪ እስላሞች ትንኰሳ በዘመናችን
በዚህ ጽሑፍ ትንኮሳውን በሦስት ደረጃ ከፍለን እንመከተዋለን።
ደረጃ አንድ
በኢትዮጵያ የአክራሪ እስልምናው የ፲፱፻፹ዎቹ እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ ጥላውን የዘረጋ፤ ስውር ነበር ማለት ይቻላል። “ቀደም ባሉት ዘመናት የነበሩት የኢትዮጵያ ነገሥታት የእስልምና ሃይማኖትን ጨቁናዋል”፤ “እስላሞች የሚገባቸውን ቦታ አላገኙም”፤…የመሳሰሉትን ደጋግመው በማሰማት ለእስላሞች መብት የቆመ ይመስል ነበር። ይሁን እንጂ ዓላማውና እንቅስቃሴው እንደሚያሰማው ድምፅ ቦታዬን ላግኝ ብቻ  አልነበረም። ይህን ለማየት ባሳለፍናቸው ዘመናት የፈጸማቸውን ድርጊቶች መቃኘት ያስፈልጋል።
ብዙዎቻችን ባልተረዳንበት ጊዜ አክራሪዎች በኦሮሚያ እና በደቡብ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች ክርስቲያኖቹን ለይተው “ነፍጠኞች” በማለት ነገራቸውን መደባዊ ፖለቲካ በማስመሰል ብዙ በደል አድርሰዋል።በተለይ በጅማ እና  በኢሊባቡር አካባቢ ክረስትያን ሆኖ መገኘት “ነፍጠኛ” ለመባል ቀዳሚ ምስክር የሆነ እስኪመስል ድረስ ፍጹም ድሆች እንኳ ሳይቀሩ በክርስትናቸው ብቻ ተገፍተው ነበር። አክራሪዎች ይህ የማስመሰል ሒደታቸው እንዳልተነቃበት ሲያስተውሉ ነበር አካባቢውን ሙሉ በሙሉ የእስላማዊ ነፃ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ የ እስላማዊ ነፃ መሬት ብቻ ለማድረግ በነበራቸው ጽኑ ፍላጐት ሰይፋቸውን ይዘው የወጡት።
በሓረር ገለምሶ፤ በአርሲ የተለያዩ ቦታዎች ያየነው የ፲፱፻፹ዎቹ (የ1980ዎቹ) አሰቃቂ ግፍ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለምን ተገን ያደረገ የአክራሪዎቹ ዘመቻ መሆኑን አሁን መገንዘብ ይቻላል። የአክራሪ እስልምናው አራማጆች ይህም ተገልጦ ሳይነገርባቸው ሲቀር እንደገና ቀስ እያሉ ወደ ባሱ የድፍረት ሥራዎች ተሸጋገሩ። በተለያዩ ቦታዎች አብያተ ክርሲያናትን ማቃጠል፤ካህናትን ማሠርና መደብደብ፤አልፎ አልፎም በስውር መግደል፤ክረስቲያን ሴቶችን አስገድዶ መድፈር፤ካህናትን ሻሽ እንዳይጠመጥሙ የክርስትና ምልክት እናዳይዙ መከልከል ዋና ዋናዎቹ መገለጫዎቻቸው እየሆኑ መጡ። እነዚህ ዘገምተኛ ጥቃቶች ሲያደርጉ የተለየ ትኩረት አልተደረገም። መንግሥትም ምንም ትኩረት ወይንም እርምጃ አላደረገበትም።
ደረጃ ሁለት
አክራሪ እስልምናው ቀደም ብለን የገለጽነውን ሁሉ እያደረገ ዝም  በተባለ ጊዜ ወደ ሁለተኛ ትንኰሳ ተሸጋገረ።ሁለተኛው ደረጃ “እዚያ ማዶ ጠብ አድርሰኝ” ዓይነት መርሕን ይዞ የተነሣ ነበር። የሕዝቡ በውል ያለመረዳት ያስተዋለው የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ምክንያት እየፈጠረ ግጭት ማስነሳቱን ጀመረ። እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲ የተባረረው የሐዋሳውን የተማሪው ለዚህ አብነት መጥቀስ ይቻላል።
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ከነበሩት አንዱን ባለ ዕድል ከላው በመከተል ቁርዓን ቀድዶ ለመጸዳጃነት ተጠቅሟል የሚል ዓመጽ አቀጣጠሉ። ይህን የአክራሪዎች ወጥመድ በጊዜው ማንም አልተገነዘበም ነበር።በቤቱ ወይንም በዶርሙ ምንም ዓይነት ዓረባዊ ጽሑፍ የማግኘት ዕድል የሌለውን አንድ ክርስቲያን መጸዳጃ ቤት ገብተው ሲጠቀምበት ያላዩትን፤በርግጥ የተባለው የተቀደደ የቁርዓን ብጣሽ ሲጠቀምበት ያላዩትን በእርግጥ የተባለው የተቀደደ የቁርዓን ብጣሽ ለዚያ አገልግሎት ውሎ ከሆነ እንኳ ከእርሱ በፊት የተጠቀሙ ሰዎች ይሁን የእርሱ ሳይጣራ ግፊቱን አጧጧፉት።
ከውስጥና ከውጭ በሚዲያ ለማስተጋባት ተዘጋጅቶ የነበረው የአክራሪ እስልምና ሠራዊት ሁሉ “አሁንም እስላም ይገፋል/ተበድሏል” እያለ ይጮኽ ጀመረ። የአገራችን ሚዲያዎችም ነገሩ በውል ሳያጤኑና በበቂ ሳይረዱ በአክራሪ እስልምናው ወጥመድ ውስጥ ተዘፈቁ።በዚህም ለእነርሱ መብት የሚታገሉ ወይም ክብር የሚሰጡ መሆናቸውን ለመግለጽ ሲጣደፉ በሌሎቹ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ወድቀው የግፍ ተባባሪዎች ሆኑ።
ከላይ የጠቀስኩት ምሳሌ እውነቱን ለመናገር ሰውየው መጠቀሙን ቀርቶ ከሳሾቹ አክራሪዎቹ ወረቀቱን ከመጸዳጃ ቤት ማምጣታቸውን ለማረጋገጥ እንኳ የጣረ አልነበረም። ጤናማ ኣእምሮ ላለው ሰው መጸዳጃ ቤት ውስጥ ብዙ ሺሕ ተማሪዎች ባሉበት ዩቢቨርሲቲ ውስጥ ቀርቶ በሌላም ቦታ ቢሆን ላይንሳዊ በሆነ  መንገድ የአሻራና ሌሎች ምርመራዎች እስካልተካሔዱ ድረስ ማን ምን እንደተጠቀመ ማወቅ አይቻልም። የተከሰሰው ሰው እንደወጣ ስለገባን ነው ቢሉ እንኳ ከእርሱ በፊት ያ ወረቀት ጥቅም ላይ ላለመዋሉ ማረጋገጫ የስፈልጋል። ነገር ግን ሁኔታው ሆነ ተብሎ የተቀነባበረ ስለነበረ በየቦታው አንድ ጊዜ አክራሪው ሁሉ ጮኸ። በዚህ ሚዲያዎችም ሰለባቸው ውስጥ ጣሉት። በእርግጥ ሚዲያው በእነሱ ሰለባ የወደቀው በዚህ ብቻ አልነበረም።
ሁለት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ሕዘብ ይኖርባታል በተባለችው አዲስ አበባ ፲፭ በመቶው ፬፻፭  ሺሕ ብቻ የሚሆኑትን ግማሽ ሚሊዮን እንኳን የማይሆኑትን የእስልምና አማኞች ወገኖቻችን አንድ ጊዜ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ በማለት በአራት እያባዛ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሁለት ሚሊዮን በላይ በማለት በአምስት እያባዛ ሲናገር እናዳምጣለን። ሚዲያውም ያንኑ በማስተጋባት ዘው ብሎ በመግባት በዚህ ጉዳይ እዚህ ለመዘርዘር የማያስፈልግ ብዙ ትዝብት ላይ የ የሚጥሉ ነገሮችን አሳይቶናል።
የሐዋሳውን ተማሪ ጉዳይ እና የቁጥራቸውን ጉዳይ እንደ ምሳሌ አነሳነው እንጂ አክራሪዎቹ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያስነሧቸው ነውጦችና በአስተዳደርም ላይ የፈጠሯቸው ጫናዎች እጅግ ብዙዎች ናቸው። ሚዲያው ለዚህ ብዙ መጥፎ አስተዋጽኦ አድርጓል። በዚህ ጩሆታቸው እየተገፋፉ ያለ አግባብ ቦታ የሰጡ፤የክርስቲያኖቹን ያሠሩ ያፈናቀሉ ብዙ የመንግሥት እስፈጻሚዎችም ነበሩ። ደመራ ሲደመር ወይንም የጥምቀት በዓል ሲከናወን ድንጋይ በመወርወር፤ሆ በማለት ጩኸት ሲያስነሳ፤ሚዲያው ተቀብሎ ወጣቱ አመጽ አስነሳ እያሉ የአክራሪ ሴራ መሆናቸወን ሳያጣሩ ወደ ፖለቲካ ይዘት በመለወጥ ይዘግባሉ። እረ ስንቱ።
ሦስተኛው ደረጃ፤-
አክራሪዎቹ ትንኮሳቸው ግቡን እየመታ ዕቅዳቸው እያሳካ ሲመጣ ደረጃ በደረጃ ቀጠሉበት እንጂ አላቆሙም። በዚህ ጽሑፍ በሦስተኛ ደረጃ ያስቀመጥነው ትንኰሳቸው ገን እጅግ አብዝቶ መረን የለቀቀና የክርስቲያኑንም ትዕግስት በከፍተኛ ደረጃ እየተፈታተነ ያለ ነው።ለዚህ ማሳያ የሚሆን የቅርብ ጊዜ ትንኮሳዎች ጥቂቶቹን እናቅርብ። ይኸኛውን በደንብ ለመረዳት እንዲቻል በአምስት ከፍለን እንመለከተዋለን።
. የመስጊድ መሥሪያ ቦታዎች፦
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እጅግ ባልተለመደና በሚገርም ሁኔታ የአክራሪዎች ጤናማ ያልሆነ የመስጊድ ግንባታ እንቅስቃሴ ይታያል።”ጤናማ ያልሆነ” የምንለውም ቦታው አምልኮን ለመፈጸም ከመጠቀም ባለፈ ሁኔታ ነገር መፈለግ ስለሚታይበት ነው።ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አክራሪዎች ለመስጊድ መሥሪያነት የሚጠይቋቸው ቦታዎች ሆነ ብለው ክርስቲያኑን የሚያነሳሣሱ እየሆኑ ነው። አንደኛ የመስቀል ደመራ ቦታዎችን የጥምቀት ባሕር ቦታዎችን፤ከዚያም አልፎ ቤተክርስቲያን ተጠግተው ወይም በዋናው መግቢያ ፊት ለመሥራት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። በደሴ ሀገረ ስብከት ፊት ለፊት ለመሥራት የጠየቁት፤ በጎን ዳር በኣታ ለማርያም  ቤተ ክርስትያን ጥምቀተ ባሕር ፊት ለፊት እየሰሩት ያለው በአፋር ዱብቲ በተ ክርስትያኒቱ ፊት ለፊት ለመሥራት የሚደረውን ጥረት እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ይቻላል።
በአዲስ አበባ የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ጥምቀተ ባሕርን ክፍሎ ወስዶ የተሠራ ወይንም መስጊድ እና ያደረሰውን ግጭት እዚህ ላይ ይታወሳል።
ለትንኮሳ ሳሆን ብሎ የሚደረግ መሆኑን የምናውቀው ደግሞ አንዳንዶቹን ለመኖሪያ ወይም ለንግድ ቤትነት ከተቀበሉና ቤቱንም ከሠሩ በላ ቀስ ብለው የመስጊድ ምልክት የሆነውን  ሾጣጣ ነገር ምልክት ያወጣሉ የጨረቃውንም ምልክት ይሰቅላሉ። ይህን ካደረጉ በላ ቦታውን ለጠየቃችሀት አገልግሎት አውሉ ተብለው ሲጠየቁ በተለመደ የነቅተህ ጠብቅ እና የተባብሮ መጮኽ ዘዴ “እስልምና ተደፈረ…” በማለት ባንድ ጊዜ ይጮኻሉ። ሚዲያወም አብሮ ይጨፍራል፤ ጩኸታቸወን በገነነ መልኩ ያስተጋባዋል።
በመንግሥት በኩል ያሉ ለዘብተኞችና ይህን ይህን ዘዴ ያላወቁ አስፈጻሚዎችም ጩኾታቸውን በመፍራት ይረዷቸዋል። የህንን በምሳሌ ጠቀስናቸው እንጂ ባለፉት ሃያ ዓመታት የተፈጸሙ ትምኮሳዎች  እና የአስፈጻሚዎቻቸው ትብብር በርካታዎች ናቸው።
ሰላማዊ የእስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንማ እስካሁን ድረስ መስጊድ ሲሠሩ ኖሮዋል። አገራቸው ነውና ለወደፊትም ይሠራሉ። ይሁን እንጂ “እስላም ተበደለ” የማስደንገጫ እና የማስፈራሪያ ደወል እየደወሉ ጩኾታቸውንም እንደ ገደል ማሚቶ የሚያስተጋቡላቸው ሚዲያዎች እና በዓለም ዓቀፍ ትስስራቸው (ፍንዳሜንታል ኔት ዎርክ)ስልት ሰለባ እየሆኑ ያልተገባ ሥራ መሥራት ግን ሊገታ ይገባል። የአንዱ ውድመት ላንዱ መሆኑን አና ሀገሪቱም የጋራችን መሆኗን መዘንጋት አይገባም።”)
 ከኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ፡ መደምደሚያ
ያገራችን ሚዲያዎች ብዙ ችግሮች እንዳላቸው አሌ ቢሉም ታሪክ የሚዘግበው ስለሆነ ብዙ ጉድለት እንዳላቸው አያጠያይቅም። የወቅቱ ስስነት በመመልከት ጊዜያዊ የፖለቲካ ጠቀሜታ ለማግኘት ከመጣር ይልቅ ለብዙ ዓመታት አክራሪ እስላም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሥሩ የተንሰራፋ መሆኑን እና የተዘረጋው ሥርም ወደ አጋራችን በፍጥነት እየገባ መሆኑን በመዘንጋት አሸውርረው ወደ ሚያመለከቱት የጣት ቅሰራ ወደ አንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትን የፖለቲካ መጠቀሚያቸው በሚያደርጉት ግራ እና ቀኙ ሁለቱንም (መንግሥትም አክራሪው ሃይልም) በሃላፊነት መጠየቅ ይጠበቅባቸዋል።  
ሰፍቶ እና ተንሰራፍቶ የምናየው አገር በቀል ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ችግር መሆኑን ሚዲያዎች መርሳት የለባቸውም። እንደዚህ አድጎ እና አፍርቶ፤ ሰፍቶ ተንሠራፍቶ የምናየውን ነገር ሰላማዊ መፍትሔ ለማምጣት ምን ብናደርግ ይሻላል በሚለው በንነጋገር ነው የሚሻለው እንጂ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እና የማይገባ ድጋፍ ለማግኘት በኢትዮጵያ ውስጥ ከበባውን እያጠናከረ እና እያነጣጠረ የመጣው አክራሪ እስልምና እንዳለ እና እንቁላሉ አገር ውስጥ እየጣለ እና እየፈለፈለ እንዳለ እየታወቀ “እስላም ተበደለ”በሚል ሃይማኖትን ተገን አድርገው የጠነሰሱት ፖለቲካ በማፋጠን ሰላማዊ ሰዎች እየታረዱ፤ቤተርስትያናት፤ገዳማት እየተቃጠሉ ፤ አረጋውያን እና ህጻናት እያለቀሱ፤ሚዲያዎች አንዱን ወገን ብቻ በማሳጠት ግቡን የሳተ ሽፍንፍን ጨዋታ እራሰቸው ከመዘፈቅ መራቅ ይጠበቅባቸዋል። እንዲህ ያለው ጥቃት እና እንቅስቃሴ አንድ ሥርዓት ከተወገደ በላም ቢሆን የሚቀጥል እንጂ አሁን ተሸፋፍኖ በሁለተኛ ደረጃ የሚታየው ጠላት የተዳፈነው እሳት ነውና የሁለቱንም ተጠያቂ ሽብርተኞች ማለትም የወያኔው ሥርዓትና ሃይማኖትን ተገን በማድረግ ወንጀል፤ብጥብጥ እና ሁከት ለመፍጠር ገዳማትና ቀሳወስት የሚያቃጥሉ  አክራሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ተጠያቂዎች እና አደገኞችም ስለሆኑ በግልጽ ሕዝቡ እንዲያውቅ እና ነቅቶ አንዲመራመር እና እንዲጠብቅ ራሱንም ከጥቃት እንዲከላከል ፤እስላሙና ክርስትያኑ ሕብረተሰብ ባንድነት የጋራ ጠላተቹን ነጥሎ ኣንዲያወቅ እንዲያመቸው ይረዳው ዘንድ ሚዲያው  በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ድርጅት የተሰገሰጉ፤በውጭ አክራሪዎችም ጭምር የሚነዱ አክራሪ ድርጅቶችንም ማጋለጥ ይጠበቅባቸዋል። በየፓልቶኩ የሚነዙት የጥላቻ፤ የጎሳ እና አክራሪ የሃይማኖት ሰበካዎች ሚዲያዎች እየተከታተሉ ለሕዝብ በማስታወቅ ማጋለጥ አለባቸው እላለሁ። እኛ ሰዎች እውነትን ማጠፍ ይቻለን ይሆናል  መስበር ግን አይቻለንም! አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com.

Monday, December 12, 2011

ወደ ዘረኞቹ ወደ “እናት ክፉሉ” የተመለሰው ወታደር ታማኝ በየነ
To see the page/font with a wider range, please press the key Ctrl and + sign. To view the page/font with a narrow range, please press the key CTRL and _ sign.
የሚታየው የወያኔ ገበና ማህደር አዲሱ መጽሐፍ ለመግዛት $30.00 ዶላር ሲሆን ይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፍ ደግሞ $25.00 ወይንም ሓይካማ የሚለው የትግርኛ መጽሐፌ ደግሞ $15.00 ዶላር ብትልኩ መጽሐፎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።Getachew Reda P. O.Box 2219 San Jose, CA 95109 getachre@aol.com Phone (408) 561 4836


ወደ ዘረኞቹ ወደ “እናት ክፉሉ” የተመለሰው ወታደር ታማኝ በየነ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com

አርበኛ እና ደፋር ስለው የነበረው፤ ዘፋኞችም እንዲሁ “ታማኝ የታለ” እያሉ የዘፈኑለት አዝማሪው/ቀልደኛው/የኪነት ሰው/ፖለቲከኛ/ታጋይ/የስባዊ መብት ጠበቃ…..ታማኝ በየነ ዛሬ በማያሻማ አነጋገር ማንነቱን ነገረኝ። ለዚህም አናደደኝ፤ ስለሱም አፈርኩለት።
ታማኝን በመገሰጼ ብዙ ሰዎች እዚህ በመምጣትም ሆነ በየፎረሙ/ መድረኩ ሊንጫጩብኝ ይሆናል፡ ተንጫጪዎቹ ያላወቁልኝን ነገር ካለ እንዲያውቁት የምሻው ነገር አንድ ነገር ልበል። እኔ ትግል ስጀምር ገና በጣም እጅግ በጣም ወጣት ሁኜ ነው የጀመርኩት። ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስከዚቺው ደቂቃ ድረስ ብዙ ጠላቶች አፍርቻለሁ፤ ብዙ ወዳጆችም አፍርቻለሁ። ትግል ውስጥ ስገባ እኔ ሁለቱንም እንዳፈራ ብየ አልገባሁም። ያከበሩኝ ሲጠሉኝ የጠሉኝ ሲያከብሩኝ እንደዚሁ ሲቀያየሩ አይቻቸዋለሁ። አትኩሮቴ ሁኔታው የምመለከተው ለእኔ ኢትዮጵያ በጣላት እንደ ተከበበች ሁሉ እኔም በተለያዩ ጠላቶች እንደተከበብኩ አውቃለሁና ልምዱም ስላለብኝ ብዙም ባትንጫጩ እና እራሰችሁን ሳታበሳጩ የምለውን ብቻ በአትኩሮት አገናዝቡት። መንጫጫቱ፤ስድቡ፤ ጋጋታው ያስደነግጠዋል የምትሉ ግሪን ካርድ አመልካቾች/ አዲስ መጤ የግንቦት 7 የሽምቅ ተዋጊ ሃይሎች ካላችሁ ጌታቸው ረዳን አላወቃችሁትም ማለት ነውና ብዙ ሳትለፉ ለምሰጠው ተግሳጽ ተገቢውን መልስ መስጠት ይጠበቅባችል።
እኔ ወያኔዎችን ስቃወም ከትግራይ ሰዎች ውስጥ እጅግ ጥቂቶች ነበርን። ያኔ ሲደርስብኝ የነበረው የጎሳ ስድብ፤ የፖቲካ ስድብ፤ የማስፈራራት ስድብ በጣም በጣም ብዙ ነበር። በስሕተት ጎዳና እና በስሜት ተወጥረው ይጓዙ እንደ ነበር ስለማውቅ ጉዳይም አልቆጠርኩት። ከጊዜ ብዛት ሲሰድቡኝ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ዛሬ አብረውኝ በመቆም የተቃዋሚ ድረ ገጽ በመክፈት ወያኔን ከኔ በባሰ ሲቃወሙ እና ሲዘልፉት ለማየት በቃሁ። ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔርን አመሰገንኩት። አንዳንዶቹ ምን ይሉኝ፤ምን ይጽፉብኝ  እንደ ነበረም አልነገርኳቸውም። አንዳንድ ጽሑፋቸው ሳነበው ተክ ብየ እስቃለሁ። አንዳንዱ ዶክተርነቴን ይሰጠኛል አንዳንዱ ዶክተርነቴን ይነጥቀኛል። ምንነቴን ሳያውቁ ምን እያሉ ያሙኝ እንደ ነበር ሰዎች ስልክ ይደውሉልኝ እና የተናገሩትን ይነግሩኛል። ዛሬ ወያኔ ስለተቃወሙ ይቅር ብያቸው አውቄ እናዳላወቅኩባቸው በሆዴ ይዤው ከነሱ ጋር እስቃለሁ/በስልክም አወራለሁ።
ተሻሽለው ስላልተሸሻሉ ግን ”ገዛ ተጋሩ በሚባለው የሌሎኞቹ ዘረኞች ፓል ቶክ ክፍል ተጋብዞ “ኢመርጀንሲ” ከገጠማት ትግራይ አንቀጽ 39 በመጠቀም መገንጠል አለባት ያለውን የእነ ገብሩ አስራት” እና መሰል ጓዶቹ ደጋፊዎች ሆነው ብቅ ሲሉ ‘ያለኝን ሃሳብ ድረ ገጻቸው ላይ እንዲለጥፉት ስልከው “አልጣማቸው ነበርና ውጠውት ዝም ይሉ ነበር”። ሲያፍኑኝ፦ መጨረሻ የምተነፍስበት የግሌ ድረ ገጽ ከፍቼ በነፃነት አሁን አስተነፍሳለሁ። ሲያግዱኝ የነበሩትም፤የተበሳጩም፤ ያልተበሳጩም ተቃዋሚዎቼም  የማይቀወሙኝም በብዛት ከመላው ዓለም  እየጎበኙት ነው።  
ተወደደም ተጠላም “ታዋቂ ተቃዋሚ ሰዎች” ታቦቶች ናቸው እና አትንኩብን የሚሉ ካሉ  ጌታቸው ረዳ “የዘረኞች የአፍ ልፍለፋ ተዋጊ ቡድኖች ታማኝ ወይንም ኢሳት ወይንም ግንቦት 7 ተነካብን ብለው  ያሻቸው ቢቀባጥሩብኝ” መለስ ዜናዊ እንዳለው “የስኒ ላይ ማዕበል” ከመሆን አያልፉም እና ወደ ርዕሳችን እንቀጥል።  አዎ የሻይ ስኒ ማዕበል!
ቅዳሜ ዕለት አንድ የትግራይ ሰው ባለፈው ሳምንታዊ ዘገባህ ታማኝን አርበኛ ስትለው አንብቤ “ሰውየው እንዳለወቅከው” አውቄ ነበር። “አርበኛህ ይኼውልህ “የትም ዞሬ ዞሬ ትዝ አለኝ ሩሜ/ክፍሌ በማለት “እናት ክፍሌ” ብለው ከሚጠራው ለብዙ ዓመታት ከትግሬ ጋር እንዳትጋቡ’ እነሱ 5 ሚሊዮን እኛ 80 ሚሊዮን መግጠም አንችላለን” “ካንሰሮች” … ወዘተ እያሉ “ኢንተርሃሙዬ ቅስቀሳ በሚካሄድበት የጸረ ትግሬዎች ‘ካረንት አፌይርስ”ፓልቶክ  ክፍል ዘንድ በመሄድ “ሲያሞግሳቸው  አመሸልህ/ዋለልህ”  ብሎ የቀዳውን ቃለ መጠይቁ ልኮልኝ፤ ሳዳምጠው እውነትም ፡እኔም ሰው ነኝ (ወያኔዎቹ) በተለወጡ ቁጥር የኔም ስሜት በዛው ልክ ይለወጣል” ሲል ኢሳት ውስጥ የተናገረውን ትዝ አለኝ እና ፤እንዴ ለካ ይሄ ሰው የሚናገረው የሚያምነውን ነው ብየ አሁን ከሰነዘረው “ከናት ክፍሉ” ያስተላለፈውን ቃል በቃሉ ላስደምጣችሁ።
ቃለ ምልልሱ የምትመራው ሴትዮ በዕደሜ ባለጸጋ ነች ነው  የሚሏት።ዘረኛ በመሆኗ “እንደ ዕድሜዋ ስለማታስብ፤ አንቱታውን ሳልለግሳት” “ባንቺታ”ልጥራት።  በጣም ሲበዛ ድንቁርና እና ስሜት ጉራ እና ተራ ውሸት የሚያሸንፋት ጸረ ትገሬ አቋሟ በግልጽ ሳትደብቅ “ጸረ ትግሬ መሆኔን እና ከዛሬ ጀምሮ ዘረኛ መሆኔን እንድታውቁት” በማለት ሳይሰለቻት ሁሌም ደጋግማ እቅጩን በማስታወቂያ መልክ የምትናገረን “ዘረኛዋ ሙያየ ምስክር” የተባለችዋ ሴትዮ  ነበር መድረኩን/ቃለ መጠይቁን ለታማኝ በየነ እንዲህ ስትል ጥያቄዋን የምታስቀድምለት።
ሙያየ ምስክር “ወደ ኢትዮጵያውያን  ካረነት አፈይርስ የመወያያ መድረክ አንኳን ደህና መጣህ ይላሉ። አንተ ምን ትላለህ?”
ታማኝ በየነ “በጣም አመሰግናለሁ። ከረዥም ጉዞ እና አገልግሎት በላ ወደ እናት ክፍሉ ወታደር እንደተመለሰ ወታደር ይሰማኛል።በክፉ ጊዜ የማንለያይ ወገኖቼ እንደምናችሁ ብየ እጅ እነሳለሁ። እንደ ዱሮ እንደ መድረክ ሞያ ከሆነ ደግሞ እንግዲህ “ታማኝ በየነ እባላለሁ።ታማኝ በየነ ማለት ባመነበት የወሰነ፤ወስኜ የምሰራ፤ለምሰራው የማልፈራ፤ሳወራ ከሰውነት ጋራ….እላለሁ፤ እንደምናችሁ እያልኩ እጅ እነሳለሁ….።” (ታማኝ በየነ ካረንት አፈይርስ ከተናገረው የተወሰደ በከፊል 12/12/2011 በፈረንጅ አቆጣጠር)
ትዝ ይላችል “ከቅንጅት አመራር ሁለት ሰዎች እንጂኔር ግዛቸው እና ዳኛ ብርቱካን መዲቅሳ ለትግራይ ሕዝብ ይቅርታ ሲጠይቁ”? ያኔ እኔ ሁለቱም ሰዎች ይቅርታቸው መሰረት እንደሌለው ተቃዉሜ ነበር።  ቢያንስ ማፈር ነበረባቸው። አድርባይንት ወይንም ደካማ የፖለቲካ ዕውቀት……የፈለጋችሁት ስም ስጡት” ብቻ ተገቢ አንዳልነበረ አሁን አሁን የቅንጅቱ አባሎች እና አመራሮች ከኔው ጋር ተስማምተዋል። አሁን ከወር በፊት በቅርቡ እንኳ “አቡጊዳ” በተባለው ድረገጽ ላይ ስዊዘር ላንድ በሚኖር አንድ የቅንጅት አባል እና ጋዜጠኛ የተጻፈው ጥያቄ “ለጥያቄው የሰጠሁትን መልስ ይመልከቱ”።

ከአራት ዓመት በፊት እንዲሁም ለማስተዋስ እንዲመቻችሁ ስለ ብርቱካን የጻፍኩትን እንዲህ ይላል;- Why her group decided to come out with this bad publicity and communication is beyond believe. Her thoughts to apologize for Tigrayans on behalf of Kinijt is absolutely irresponsible and showed that there seems to be no potential buyer to her group if she and her supporters used such appology for cheap and temporary political gains and popularities. It is only a matter of time if I or she or her group are correct to appologize or not to appologize Tigrayans with such baseless ground of appology.”
በዚህ መልክ ሃቁ ዛሬ ምን እንደሆነ የምትረዱት ይመስለኛል። በወቅቱ ግን ብዙ ዘለፋ ተሰንዝሮብኝ ነበር (በቅንጀት ይቅርታ ጠያቂ ደጋፊ ወገኖች እና በወያኔ ትግሬዎች በኩል)።
ታማኝ በየነም በእዛው አዲስ (ዊርድ) ንግግሩ የታዘብኩት ነገር ቢኖር “”ፓወር ኮራፕትስ ፓወር” እንደሚባለው፤ ለዓመታት የገነባው ገናናነት ታማኝን “ኮራፕት” (ያበሰበሰው/ያበላሸው/ያጃጃለው” መሰለኝ። ሁሉም በኔ እጅ ነው ፤ብዙ ሰው አፍርቻለሁ፡ ሙዚቃው ለኔ ሕዝቡ ለኔ፤ዛፉ ድንጋዩ ወደ እኔ ይሰግዳል፤ያንጨበጭበልናል ወደ ሚለው “ፍጹም ዘላቂ እምነት”ራሱን እየመራ ይመስላል። ገናናነቱ እያደገ በመጣ ቁጥር “ኤምፓየርነት/ጉልተኛነት/ሃያልነት/ያበጠው ይፈንዳ/ የምን ይሆናሉ-ነት..” ስሜት በውስጥ እየተገነባ ይመጣል” ፍጹማዊ እውነታው ከሕዝቡ ሲለገስለት እና አውን ሲሆን መስመር ይዟል እና የሰው ፍጡር በመሆኑ ወደ “ዕብጠት”በመለወጥ ወደ ውሸት የመንፈስ አዘቅት ይዘፈቃል። “ስልጣን እና ታዋቂነት” ሞኛ ሞኝ ይሰሩሃል። እኛ እና እግዚአብሔር የሚለየን በዚህ ባሕርይ ነው። ለዚህም ይመስላል፤ የትግራይ ሕዝብ በሚሰደብበት እና ከትግራይ ሕዝብ ጋር ወይንም የትግራይ ደም ካለው ሰው ጋር እንዳትጋቡ; እንዳትበሉ; እንዳትጠጡ……እየተባለ በሚነገርበት “ራዲዮ ቴሌቪዚዮን ሊብሬ ዴስ ሚሌ ኮሊኒስ” የተባለው ለ1994 ቱ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ዕልቂት ተጠያቂ ዘረኛ ራዲዮ  ዓይነቱ ወደ ሆነው “ኢትዮጵያን ካረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም” ወደ ተባለው ዘረኛ የፓል ቶክ ቡድን በመሄድ  “ትግሬዎች ምን ልትሆኑ ነው”በሚል ዕቡይ ስሜት ተወጥሮ መረን በመልቀቅ  “ወደ ኢትዮጵያውያን  ካረንት አፈይርስ የመወያያ መድረክ አንኳን ደህና መጣህ ይላሉ። አንተ ምን ትላለህ?” ብላ ዘረኛዋ የመድረኩ ዋና መሪዋ ስትጠይቀው
 “በጣም አመሰግናለሁ። ከረዥም ጉዞ እና አገልግሎት በላ ወደ እናት ክፍሉ ወታደር እንደተመለሰ ወታደር ይሰማኛል።”  ይህ እንዲህ ዓይነት ለእኛ ለትግሬዎች ጀሮ በጣም አስቀያሚ መልስ መስጠት የተገደደበት ምክንያት በግልጽ እንዲያብራራልኝ እጠይቀዋለሁ።
ታማኝ ገናናነቱን በገዛ እጁ እራሱ ኮራፕት/እያበላሸው/ እንዲሆን የመምጣቱ ጉዳይ ይህ ነጋሪ ምልክት ነው እላለሁ። ለተወሰነ ጊዜ ከዛው ከዘረኞቹ ምድጃ ተነጥሎ ቆይቶ አሁን ግን ተመልሶ ወደ ምድቡ በመመለሱ “ልክ ወደ እናት ክፍሉ ወታደር እንደተመለሰ ወታደር ይሰማኛል።” ሲል የታማኝ ምድብ ቦታ “በጸረ ትገሬነቱ ትግሬዎች ብቻ ሳንሆን ሌሎች ወንድሞቻችንም ጭምር ብዙ ጽፈው ያወገዙት የካረነት አፈይርስ ፓልቶክ ሩም እንደነበረ እና፤ ዛሬ ግን፤ ከብዙ ጊዜ በላ ወደ ምድብ ቦታው ወደ “ዘረኞቹ” መመለሱ በደስታ እና በኩራት ሲገልጽ “የገናናነት ብልሹነት ባሕሪ” (ገናናነትን በትዕግስት እና ባግባቡ ባለመንከባከብ) የመጀመሪያው ደረጃ ሳይሆን “ከፍተኛው የገናነነት ንቅዘት” ባሕሪ ነው።ለብዙ ሰዎች “ሥልጣን እና ገናናነት” የሚያጓጓ ቢሆንም ሁለቱም ነገሮች መጠበቅ ካልቻልክ እና ባሕሪያቸውን እና አጠቃቀማቸው ካላወቅክባቸው ንቅዘቱ እያደረ ቀስ እያለ ከጊዜ ብዛት ልክ ሰማይ የወጣህበትን ርቀት ያህል ወደ ቁልቁል ሰትወርድ አደገኛ አወዳደቅ ይገጥምሃል።
እነ ጋዳፊ እንደዚያ ሲንጨበጨብላቸው፤ ገናናነቱ ስላባለጋቸው እና አጠቃቀሙ ስላላወቁበት “ወደ ትዕቢት” በማምራት መጨረሻቸው ያየነው ነው። ታዋቂ ግለሰዎች ከዘረኞች እና ከማይገቡ ክፍሎች መደበላለቅ ካበዙ “እንዳልተከደነ ጠላ እያደሩ ይነፍሳሉ”።
የትግራይ ሕዝብ የፈለገው ቢቃወመኝ ጉዳዬ አይደለም፤ወይንም ጥቂት የትግራይ ሰዎች “ካረንት አፈይርስ ስለተቃወሙ” ወይንም “የካረንት አፈይርስ ስብስብ ዘረኛ ግለሰዎች የጠየቁኳቸውን ፍራንክ እና ሰላማዊ ሰልፍ ስለሚያዋጡልኝ እና ስለሚወጡልኝ” “ስለ ትግራይ ሕዝብ አቋማቸው ጉዳያችን አይደለም”  ስለ ዛቻው እና ቅስቀሳው ትግሬዎቹ ይቸገሩበት”……ትግሬዎች ካወገዙት ፓል ቶክ መግባት እና መልክታችንን ማስተላለፍ ሃጢያት የለበትም……..ወዘተ፣ የሚሉ ሰዎች በማወቅም ባለማወቅም ለዘረኞቹ “የዘምባባ ዝንጣፊ” እያቀበሏቸው እና “ዘረኛነታችሁ፤ ጸረ ትግሬነታችሁ ቀጥሉበት” እያሉ እያበረታቱ እንደሆኑ መታወቅ ይኖርበታል።
የሰው ልጅ የሚለካው በስብስብ፤ በሆሆታ፤ በገናናነት፤በደምጸ መረዋነት ሳይሆን “በሚከተለው መንገድ እና በሚያስተላልፈው የመልእክት ጥራት ነው” ከትግራይ ሕዝብ ጋር እንዳትጋቡ፤ አርቋቸው፤ ነቀርሳዎች ናቸው፤ ታማኞች አይደሉም፤ስልጣን ስይዙ አገር ይሸጣሉ.. “ካንሰሮች” ናቸው እና ከመለከአ ምድራችን ቀፍፈን አናሰወግዳቸው” ከሚሉ የተለያዩ ዘረኞችና ክፍሎች ጋር መተሻሸት ወይንም እጅ መንሳት ወይንም ማመስገን ፤ጣምራ ትግል ማካሄድ፤ በበኩሌ መወገዝ ያለበት ያልተቀደሰ አካሄድ ነው።
ዘረኞቹ  እነ ሙያየ ታማኝ በየነ እንዳለው “በክፉ ጊዜ የማይለያዩ ወገኖቹ” ከሆኑ እነኚህ ደንቆሮዎች ሊያመጡብን የሚመኙትን ክፉ ቀን አብሯቸው እንደማይደባለቅ ተስፋ አድረጋለሁ። እሱ እንደሚለው “ታማኝ በየነ ማለት ባመነበት የወሰነ፤ወስኖ የሚሰራ፤ ለሚሰራው የማይፈራ ከሆነ ወደ እዛው ምድብ ቦታው መመለሱ ደስ ያለው ይህ “የካረንት አፈይርስ ምድብ ወታደር” አስቦበት እና ወስኖ የተቀለቀላቸው ስለሆነ ለዛውም ምንም  ፍራቻ እንደሌለው እና ቅሬታ እንደማይሰማው ስለነገረን በገዛ እራሱ ገናናቱ ለማበላሸት “ቁልቁለት አፋፍ” ላይ እንዳለ ገናና ወታደር እንደሆነ ስነግረው በወንድማዊ ምክር ልብ እንዲለው ይህ መልእክት አስተላልፍለታለሁ። ታማኝ የትግራይን ሕዝብ ዘላፊዎች እና መጥፎ ተመኚዎች “ምድብ ቦታየ” ነው ብሎ በካረንት አፈይርስ ወታደርነት ለማገልገል “ወስኖ ከተነሳም” ትግሬዎች እንደሚሉት “ከይኮነ ለብም፤ ከይተሰብረ ጸግን” (ከመሆኑ በፊት ልባም ሁን ከመሰበሩ በፊት ጠግን”) ይላሉ። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮያን ሰማይ) www.ethiopiansemay.blogspot,com getachre@aol.com


Wednesday, December 7, 2011

የኢትዮጵያን ሰማይ ዘገባ በዚህ ሳምንት


To see the page/font with a wider range, please press the key Ctrl and + sign. To view the page/font with a narrow range, please press the key CTRL and _ sign.

የሚታየው የወያኔ ገበና ማህደር አዲሱ መጽሐፍ ለመግዛት $30.00 ዶላር ሲሆን ይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፍ ደግሞ $25.00 ወይንም ሓይካማ የሚለው የትግርኛ መጽሐፌ ደግሞ $15.00 ዶላር ብትልኩ መጽሐፎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።Getachew Reda P. O.Box 2219 San Jose, CA 95109 getachre@aol.com Phone (408) 561 4836

የኢትዮጵያን ሰማይ ዘገባ በዚህ ሳምንት
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) www.Ethiopiansemay.nlogspot.com (getachre@aol.com)

በዚህ አምድ ትንንሽ ንኡስ ክፍሎች እና አንድ ትልቅ አርዕስት ይቀርባል።

1-     ለመፈርጠጥ አስቀድመው የተናዘዙት ጋዜጠኞች
2-     በአፍቃሬ ሻዕቢያው ኤሊያስ ክፍሌ እና በጸረ ትግሬ ቅስቀሳ የታወቀው የከረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም ተፈጠረ የተባለው ስምምነት/ትብብር (ግምባር)
 3     ታማኝ በየነ  ሰሞኑ በሰጠው የወያኔ አኬልዳማ መልስ በሚመለከት
 4     ግብረሰዶም ምርምራ በወያኔ ተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች ላይ ስለመፈጸሙ ጉዳይ በሚመለከት
5-   የሟቹ ሳይንቲስት እጅጉ ቅጣው ንግግር (በሚቀጥለው ሳምንት የሚቀርብ ነው። አገራዊ ፍቅርን እና የኢትዮጵያዊ ኩሩ ማንንት የተሞላበት ንግግር ስለሆነ ተከታተሉት)
 ከኤርትራ በኩል እየተላኩ በግምቦት 7 በኩል ሽብር እየፈጠሩ ነው ብሎ ወያኔ ግንቦት 7ን ሲከስ “ግንቦት 7 እና ደጋፊዎቹ” ደግሞ “ውሸት ነው፤ የወያኔ ቲያትር ነው፤ እኛ የለንበትም” ሲሉ (በመግለጫው ደግሞ ወያኔ “መውጫ መግቢያ” እያሳጣነው ነው በርቱ ይበል እንጂ) ከወደ ኤርትራ ለ20 አመት የሰለጠኑ ሽምቅ ተዋጊዎች ሸዋ አከባቢ ይሁኑ ወሎ አካባቢ እያቆራረጡ ወደ መዲናዋ እየገሰገሱ ይሁን ባናውቅም። የት አንዳሉ ባናውቅም ለኢንተርኔት ምስጋና ይግባው እና  Raya Liberation Front (RLF) ወይንም  “Raya Rayuma” የተባለ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ አዲስ የራያ ነፃ አውጪ የተባለ “ጥይት ሳይተኩስ” “ጫካ ሳይወጣ” ከወያኔ ጋር አብሮ እየበላ እየጠጣ ወያኔን መውጫ መግቢያ አሳጥተነዋል። የሚል ደግሞ መጥቷል።
የወያኔ የኪነት ክፍሎች አብቶቡስ የገለበጠው እሱ መሆኑን እንዲሁም ወያኔው ኢያሱ በርሐን የገደለው ይሄው ድርጅት መሆኑን የሚቀባጥር “ቁጭ በሉ ላሞኛችሁ” የመንደር ወሬ ለአትላንታው የኢ ኤም ኤፍ ጋዜጠኛው ለመቶ አለቃ ዳዊት ከበደ ወየሳ ዜናውን እንድትዘግብልን ዜናውን ተቀበለን፡ ተብሎ በዛው ድረገጽ የተጻፈው ከሰማይ የወረደ ወያኔን መውጫ መግቢያ የሚያሳጣ ነፃ አውጪ ድርጅት አንደኔው በጉጉት እየተበቃችሁ ይሆን? ወይ ትጉዱ! አለ ትግሬ።
አይዞህ ተነስ፤ አንደ ሊቢያ እንደ ሶርያ እንደ ግብፅ ትግልህን አቀጣጥል ፤መስዋዕት ክፍል፡ እያሉ ሕዝቡን ላመስነሳት ሲጽፉ የነበሩ ብዕርተኞች/ጋዜጠኞች እና አሽሙረኞች ሁሉ አይዞህ ከጎንህ አለን፤ ተነስ፤ መስዋእት ክፍል በወያኔ አለንጋ አትበርግግ፤ እንደ ቦአዚዝ እራስህን አቃጥል” ሲሉ የነበሩ ጋዘጠጠኞች፡ ቦአዚዝን ተክቶ የመስዋዕትንትን አርአያነት በራሱ ሕይወት ፈርዶ በተግባር ባርበኝነት ያለፈው “የኔሰው” የተባለው ኢትዮጵያዊው “ቦአዚዝ” ብቅ ሲል አርአያነቱን ከመከተል እና ትግሉን ከማቀጣጠል ይልቅ “የወይን ጎማ እግሩ” ፋሽስታዊ አለንጋ ሲወዛወዝ አይተው እንደ ምጢጢ “ወፍ” ብር ብለው ከእኛው ከፈሪዎቹ መንደር የመደባለቃቸው ጉድ ምን ትሉታላችሁ?
የአውራምባው ዳዊት ከበደ ሲቢጀይ የተባለው ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (?) ሽልማት ማግኘቱን ይታወቃል። ማሕበእነ ኤልያስ ወንድሙ (የጻሐይ አሳታሚ ድርጅት ባለቤት ሎስ አንጀለስ እና ምናልባትም “የሻዕቢያው ወዳጅ “ኤልያስ ክፍሌም ሳይኖርበት አይቀርም - በጠቋሚነት እና በማሕበሩ አባልነት አሉበት ይባላል።) እንግዲህ ዳዊት በ ‘ሲቢጄ’ አለም ዓቀፍ እውቅና አግኝቶ “በሲኤን ኤን” ጋዜጠኛዋ ቃለ ምልልስ ስያደርግ “ሲቢጄ” የተባለው ድርጅት ስለ እሚሰማው ሦስት ነገሮችን እንዲያብራራ ጠይቆት ነበር። ከመለሳቸው ሦስቱ ልጥቀስ

 1- “I can’t leave without the profession I have now”  2- “unless it becomes a matter of life and death, I will never leave Ethiopia” 3- “I am not an opposition. If I believe for the betterment of this nation, I will never hesitate criticizing whatever power…..This my ultimate…..”
ኢትዮጵያዊው ቦአዚዝ ተብሎ የተሰየመው የኔ ሰው ገብሬ ግን የጋዜጠኞቹን አይዟችሁ በርቱ፤ተነሱ መስዋእት ክፈሉ ቅስቀሳ እና የወያኔ አፈና እና የወንጀል ገበና እየተመለከቱ ራሳቸው በሞትና በሽረት ትግል አሳትፈው መስዋእት ሲሆኑ፡ ጋዜጠኞች ግን ሞት መጣ “በቃ!” እያሉ ሕዝቡን ለወያኔ ጥለንለት መፈርጠጥ ነው ያሉትን በተግባር አሳይተውናል። ይሄ “ሲ ቢ ጄ” የተባለው ቅራ ቅንቦ ምን የሚሉት መመዘኛ እያስቀመጠ ነው “ሽልማት” የሚለጥፍላቸው እኔ አልገባኝም። ዳዊት ቃሉን ስላከበረ እንዴት መውቀስ እንችላልን? “የሞት የሽረት ነገር ከመጣ አገሬን ለቅቄ እፈረጥጣለሁ አለ። አደረገው፡ ለምን እንውቀሰው። ቢያንስ አስቀሰድሞ ነግሮናል። ገጠር ውስጥ ያለቺው ታላቋ እህቴ “ዝሞተ ሞተ እዩ ምቕዳም አይግበርካ” ትላለች። የሞተ ሞተ ነው፤ ለሞተው ይብላልኝ እንጂ….የሞተው ሰው  አያድርግህ እንጂ ፤/ለመሞት ግምባር ቀደም አይድርግህ እንጂ ….”። አውነት ነው። የሞተው ይብላልኝ እንጂ አስቀድመው የተናዘዙትማ እንዴት አንውቀሳቸው?
2-    በአፍቃሬ ሻዕቢያው ኤሊያስ ክፍሌ እና በጸረ ትግሬ ቅስቀሳ የታወቀው የከረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም ተፈጠረ የተባለው ስምምነት/ትብብር (ግምባር)
 የሰሞኑ ጉድ በተለይም ባንዳንድ ኢትዮጵያውያን  አፍቃሬ ኢሳያስ አፈወርቂ/የሻዕቢያ አፈቀላጤዎች እና  በጸረ ትግራይ ፓልቶክ መሃንዲሶች (ኢካድ ፎረም/ኢትዮፕያን ካረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም) መሃል ተደረገ የተባለው የትግል ጥምረት ለተቃዋሚ ራዲዮ ጣቢያዎች ማጠናከሪያ እንዲሆን “በየወሩ ቋሚ የገንዘብ ዕርዳታ” እንዲደረግ፤ እንዲሁም  በወያኔ ሱቅ ቤቶች ምግብ ቤቶች ሕዝቡ እንዳይገበያይና እንዳይመገብ፤አፍቃሬ ኢሳያስ አፈወረቅ በሆነው የኢትዮጵያን ሬቪው ባለቤት በ“ኤሊያስ ክፍሌ” የሚመራው (አል ማርያም፤አክሎግ እና የመሳሰሉት ሰዎች አሉበት የሚባለው የቦይ ኮት መርሃ ግብር ዘመቻ አቅድ አቀነባባሪ ቦርድ) ተደረገ የተባለው የዘመቻው ስምምነት አንብበናል።
በእዛው ምሽት በካረንት አፈይርስ የተደመጡ ካንዳንድ ታዳሚዎች (በጸረ ትግራይ ሕዝብ ቅስቀሳ የታወቀቺው “ሙያየ ምስክር” የተባለቺው ሴት ነበር ዝግጅቱን የመራቺው) የቀረቡ አጸያፊ እና አስፈሪ ንግግሮች አንዲሁም

ባንድ አስተያየት ሰጪ ግለሰብ "በስመ ትግሬ ሁሉም ወያኔዎች ናቸው እየተባሉ በማይገባ እርምጃ በትግሬ ወገኖቻችን ላይ የተሳሳተ እርምጃ እንዳንወስድ በቂ ጥንቃቄ መደረግ አለበት የሚለውን፤ በተለይ “ኤልያስ ክፍሌ መረጃ ሲያቀርብ “በስማ በለው” መረጃ እየተቀበለ መለጠፉን የተለመደ የድረገጹ ባሕሪ መሆኑን አንድ ከስዊዘር ላንድ ኗሪ የሆነ የብርቱካን መዲቅሳ ደጋፊ “በዛው ከተማ ስትጋበዝ የወያኔ ደጋፊ የሆነ እገሌ ነው የጋበዛት በማለት ስሜን አጥፍተኸዋል” ስለዚህ አሁንም እንደዚያ ያለ ስህተት እንዳትደግም “ጥንቃቄ አድርግ” ብሎ የሰነዘረው ጠቃሚ ሃሳብ አልቀረበም። ሌላው ይህ እንዲህ ያለው ግለሰብ ጥንቃቄ አድርግ ሲል ቆይቶ “እንደ እኔ ፍላጐት ቢሆን ኖሮ የወያኔ ንበረቶች/መኖርያቤቶች በእሳት ማቃጥል እምርጥ ነበር” ያለውን- የወያኔ ንብረት/ቤት ለማቃጥል ሲባል “ህጻናትን ወላጆቻቸውን፤ፖለቲካቸው ውስጥ ያልተሳተፉበት ዘመዶቻቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ የቅስቀሳ ንግግር ለምን ተቆርጦ ለኤልያስ የተጠየቁ እና እሱ የመለሳቸውን ብቻ ቀርበው ጤነኛ ውይይት እንደነበር ተመስሎ ቀረበ?

 በወቅቱ ይህ አደገኛ ቅስቀሳ ሲሰነዘር “ለምን እንዲህ አልክ” ብላ የመድረኩ መሪዋ ማረም አልቻለችም? ምክንያቱም በእራሷ አንደበት (በዛው ወቅት ለደ/ር አክሎግ ቢራራ ስትናገር “የናንተን አቋም አላውቅም እንጂ ለእኔ ትግሬ በሙሉ ወያኔ ነው፡ ያለችበትን ብቻ ሳይሆን ከሦስት ሳምንት በፊትም በሌላ ፓል ቶክ ክፍል ገብታ “ከዛሬ ጀምሮ እኔ ዘረኛ ነኝ” “ጸረ ትግሬ ነኝ” ያለቺበትን ንግግር ካንደበቷ የወጣውን ንግግር በድምፅ መቅጃ ተቀርጿል እና ከአንዲት ናላዋ የዞረባት ዘረኛ ሴት ስነ ስርዓት ለማስከበር ብቃቱም ባሕሪዋም አይፈቅድም እና አድምጠነዋል።
በወያኔ ደጋፊዎች ንግድ ላይ ማዕቀብ መጣል አስፈላጊ ነው ተገቢም ነው። ነገር ግን “ቤታቸውን /ንብረታቸውን ማቃጠል የሚሰጠው ውጤት ምን እንደሆነ እና የሚያስከትለው የፍጅት መዘዝ ሳያጤኑ በስሜት የሚሰነዘር የፓል ቶክ ስካር “ቁጥር እና ተገቢው ሕጋዊ ገደብ ቢደርግበት ይሻላላል”። የኔ ወንድም ገና በሎጋ እድሜው ጀምሮ ጫካ በመግባት የወያኔ ታጋይ ሆኖ ታግሏል። በቅርቡ ቦታው ልነግራችሁ የማልፈለገው ኢትዮጵያ ከተማ ውስጥ እሱ እና ሌሎች ትግሬዎች በሚኖሩበት መንደር ላይ በጀርባ ተደብቀው እሳት በመልቀቅ የወንድሜ መኖርያ እና ሌሎች የትግሬ ቤቶች በቃጠሎ ወድመው መኖርያ አጥተው የትም ወድቀው ነበር። ይታያችሁ ወንድሜ  የተማረ አይደለም ይህ ወጣት ወንድሜ ትምህርቱን ትቶ ወያኔዎችጋር ተደባለቀ። የሚያውቀው ትምህርት “ወያኔ” እንጂ ሌላ “ትምህርት” አያውቅም። ትንንሽ ልጆቹ እና ምንም የማያውቁ እሱን ለመጠየቅ የመጡ ዘመዶቻችንም አብረው ለእሳት ሲዳረጉ አብሮ የሚጐዳ ነገር በህሊናችሁ ፍረዱት።  ስለዚህ በቢራ ሞቅታ ወይንም በዘረኝነት ባሕሪ እንዲህ ያለ አስነዋሪ ንግግር በየፓል ቶኩ ከሚሰነዝሩ ጸረ ትግሬ ፓል ቶክ ክፍሎች እና አፍቃሬ ኢሳያስ አፈወርቂ መካካል ተደረገ የሚባለው ትብብር የሚገኝ ዕርዳታ በኔ ትርጉም “እርዳታ ይደረግልን ብለው የሚጠይቁ የራዲዮን ባለቤቶች ቢቀራቸው ጥሩ ነው። የትግርኛው አባባል
“ኣቕሓ ስኢንና ሓቢርና
በላዕና እምበር መዓዝ ዓዕሩኽ ኮይንና”
“ዕቃ በማጣታችን አብረን በላን እንጂ  መቸ ጓዶች ሆንን”  ቢሉንም
መልሴ  (ንብር ነቢራ ዕውር ተመርዒያ)  “ ያ ሁሉ ረዢም ጊዜ ባል ስታማርጥ ዓይኑ ደቃቃ ነው፤ ዓይኑ ሸውራራ ነው፤ ወገቡ ወልጋዳ ነው… ስትል ኑራ ኑራ ዕውር ተዳረች” (ዓይነ ስውራን ጓደኞች አሉኝና አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ይህ የጥንት ምሳሌ በመጠቀሜ)።
ኑራችሁ ኑራችሁ “ዘረኞች ጋር እና አፍቃሬ ኢሳያስ ሻዕቢያ” ጋር መሞዳመድ እና ገንዘብ መቀበል ክብር ይቀንሳል ነው የኔ የዘወትር ምክሬ። ከአፓርታይዷ ደቡብ አፍሪካ ጋር የንግድ፤የትግል፤የዲፕሎማሲ እና ማሕበራዊ ግንኙነት ሲያደርጉ በነበሩት ላይ ውግዘት ሲደርስባቸው የነበረበት ምክንያት “ደቡብ አፍሪካ እንደ ተቋም “ዘረኛነትን” የሚያራምድ ተግባር እና ቅስቀሰቀ በማካሄዱ ነው። ወያኔን የምናወግዝበት ምክንያትም የሄው ነው። አሁንም በየፓል ቶኩ የ“ወያኔ/መለስ” አባሎችን ከማውገዝ ይልቅ በእኛ በትግሬዎች ላይ የሚደረግ ግልጽ የጥላቻ ዘመቻ ከሚያካሂዱ ክፍሎች ዘንድ በመሄድ “ቃለ መጠይቅ ማድረግ፤ግምባር መፍጠር፤የገንዘብ ዕርዳታ መቀበል….” የመሳሰሉት ተግባሮች እናወግዛቸዋለን።
3ኛ- ታማኝ በየነ ሰሞኑ በሰጠው የወያኔ አኬልዳማ መልስ በሚመለከት
 ታማኝ ጀግኖቻችን ከምንላቸው ደፋር ጀግና፤ ጥሩ ተሟጋ ች አንዱ ነው። ግን ትግሬዎች ሲመስሉ “ሕማቕካ ዎሆይ ይበልካ” (ወንድምህ (ድክመትህ) እንደ አውድማ ከብት “ዎሆ!” ብሎ ቢቆጣጠርልህ አትጥላው’። ይባላል። እኔ በታማኝ ያለኝን እርምት ወይንም ስለሱ አንድ ባልኩ ቁጥር እሱ ወይንም ሌሎች የሚከፉ ካሉ፤ በክፋት እንዳልሆነ አውቁልኝ። እሱ ስለ እኔ እንዳለው ትዕቢት ሳይሆን እኔ ስለሱ ያለኝ አክብሮት እንጂ ትዕቢት/ንቀት የለብኝም እና ነው።
አሁን ወደ እርምቱ ልግባ። ሰሞኑን ወያኔ ከሽብርተኞች ጋር ግንኙት አድርገዋል፤ የተለያዩ ቅስቀሳዎች ለማድረግ ይዣቸዋለሁ ወዘተ… በማለት የያዛቸው ሰዎች (ፖለቲከኞች….) በሚመለከት “አኬልዳማ” በሚል ርዕስ  አገኘሁባቸው ያለውን የምርምራ ውጤት በተንቀሳቃሽ ምስል ለመረጃ ብሎ ያስተላለፈውን ማሕደር ተመልክተናል።
እያንዳንዳችን የየራሳችን ግንዛቤዎች አሉን። ሁሉም የየራሱ ግምገማ መያዙ እንደተጠበቀ ሆኖ ታማኝ ያቀረባቸው ግምገማዎች ሁላችንም አድምጠነዋል። የወያኔ ሽብር ምን ያህል የተለጠጠ እንደ ሆነ ከጫካ ባሕሪው ጀምሮ በዘመዶቻችን ላይ ያደረሰው ሽብር የምታውቁት ይመስለኛል። በምጽሓፍም በቃለ መጠይቅም ያቀረብኳቸው መረጃዎች ተመለክቱ።
የኔ ችግር ወያኔ ሽብርተኛ ነው አይደልም በሚለው አይደለም። ወያኔ ሽብርተኛ ነው፤ፋሺስት ነው….የፈለጋችሁት የጋኔል ስም ብትሰጡት የሚገባው ነው። ችግሬ ግን ወያኔ ስለምንቃወም  በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ከ36 በላይ ተሰነዘሩ የተባሉ የሽብር ተግባሮች ወያኔ እንጂ ሌላ ድርጅት አልፈጸመውም እየተባለ ለዛውም “ዊኪ ሊኪ” “አሜሪካ ኤምባሲ የተላለፈው የመረጃ ራፖር” “ሲናኒሞስ” እንዳስተላለፈው መረጃ እያተባለ “ስማቸው የማይጠቀስ የፖለቲካ ተንታኞች እንዳሉት” እየተባለ እንደ መረጃ እየተወሰደ “ወያኔ” የቀነባበረው ያፈነዳው ቦምብ፤ ክርስትያኖች ወያኔ ያረዳቸው ያቀነባበረው ሴራ እንጂ ሌላ ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅት/ሃይል የለም ወይንም እጅ የለበትም፡ እየተባለ ሌሎችን ሽብር ፈጻሚዎች ነፃ ለማድረግ የሚደረገው “በማውቅ አለማወቅ” (ለነሱ ልተው) በጣም አሳስቦኛል።ሽብር ፤ግድያ፤ቦምብ፤የጸሎት ተቋማት ማቃጠል፤ሰዎችን ማረድ የሚያከናውነው “ወያኔ” ብቻ ከሆነ እንደምንሰጋው ኢትዮጵያ ብዙ ጠላት የላትም  እና አገሪቱ ጠኔኛ ነች ማለት ነው።
ለምሳሌ ታማኝ ለ“አኬልዳማ” መልስ ሲሰጥ የመሰለውን አስተያየት ሰቷል። ችግር የለኝም። ችግር ያለብኝ አንድ ነገር ልጥቀስ። “እኔ ኦነግን ፈጸመው ከሚባልለት ድርጊት ነፃ ለማቀውጣት አይደለም” ይል እና የበደኖን የአማራ ሕዝብ እልቂት የሚያሳይ የፊል/የስዕል መረጃ ሲያቀርብ “ወያኔ ይህንን ዕልቂት ሲፈጸም አስተካክለው በካሜራ ይቀርጹት ነበር” ብሏል።አኔ ይህን አባባሉ ስህተት አለበት። ምክንያቱም እስካሁን ድረስ የተመለከተኳቸው መረጃዎች ወያኔዎች ያቀረቡት መረጃ በበደኖ አካባቢ “የ ኦሮምኛ ስም ያለው ገደሉ
አሁን ዘንግቼዋለሁ “ቁንድፍቱ” (?)” የሚገኝ ገደል ውስጥ ከገደሉ የተወረወሩ ሬሳ/ሰዎች ነብሳቸው በገመድ ተጐትቶ ሲወጣ እንጂ ከነ ነብሳቸው ሲገፈተሩ የሚያሳይ መረጃ አላሳየንም። እኔም ካሁን በፊት አላየሁም። ወያኔ የድርጊቱ ተጠያቂ መሆኑን አያከራክረንም። ኦንግም ከድርጊቱ ተጠያቂነት አያመልጥም (ኢሳቶች የዲማ ነገዎን “እኛ በዚያ አካባቢ አልነበርንም፤ ቁጥጥር አልነበረንም “ “አንዳንድ አበላቾቻን በግለሰብ ተነሳስተው አድርገውትም ላያደርጉትም ይችላሉ፤ እኔ እሱን አላውቅም….” የሚለውን የተምታታ ምስክርነትና ቃለ መጠይቅ እንደ መረጃ ለመናገር ቢቃጣቸውም፡ “ኦነግ እና የነጋሶ ጊዳዳ ‘ኦ ፒ ዲ ኦ’ ድርጅት ታጋዮች መካከል  ከእርስ በርስ የሴቶች ጡት መቆራረጥ እና የሰው የጭን ስጋ በቢላዋ እየቆረጡ በሃይል ወደ አፋቸው መጎራረስ (የነጋሶ ጊዳዳ መጽሐፍ (“ዳንዲ - የነጋሶ መንገድ” ያላቸው ሰዎች አንዳነበቡልኝ እና ከሰዎችም እንደተነገረኝ የኦነግ ታጋዮች በበደኖ ካባቢው እንደ ነበሩ ነው) እንደደረሱ እና ሁለቱም ድርጅቶች ባልታጠቀው የአማራው ሕብረተስብ ሰላማዊ ኗሪ የደረሰው ዕልቂት ተጠያቂዎች መሆናቸው መረጃዎቹ ናቸው።
ሆኖም ታማኝ እያለን ያለው፡- ኦነግን ‘ከወንጀሉ ነፃ ለማውጣት አይደለም’ ይበል እንጂ ከአንደበቱ ይፋ እየተናገረን ያለው ግን የሃውዜኑ ዓይነት የገብረመድህን ትረካ ነው። ወያኔዎች ድርጊቱ ሲፈጸም ካሜራቸው አነጣጥረው ነበር የዘገቡት ካለን “ወንጀሉ ሲፈጸም በካሜሬ እየቀረጹ እንደነበር ከሳያን ወያኔ በተባባሪነት በወንጀሉ ተከሳሽ ነው (ሌሎች ክፍሎች የፈጽሙት መሆኑን ፊልሙ የሚያሳይ ከሆነ)። ካልሆነ ድግሞ ድርጊቱ የፈጸመው ክፍል በመረጃው እስካሁን ድረስ ያየነውን “ሬሳ ከገደል ሲወጣ” እንጂ ፈጻሚው ማን እንደሆነ በፊልሙ አላየንም። ስለዚህ በወቅቱ ዲማ ነገዎ የማስታወቂያ ሚኒሰትር ስለነበር ፈጻሚዎቹ ሲፈጽሙት ፊልም አለ የሚል ከሆነ በጉግት እንጠብቃለን። ወይንም “ወያኔዎች” ከደሙ ንጹሕ ነን የሚሉ ከሆነም “ድርጊቱ ሲፈጽም” የተነሳ ክፍል ካለ ፊልሙ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ወያኔዎች ከዚህ ክስ ራሳቸውን ነፃ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ይህ ሐተታ ሆነ ብየ የማቀርበው እጅግ አወዛጋቢ ነው የሚሉ ክፍሎች የጠራ ነገር ለማግኘት (“ትሪገር”) የተደባባቀውን መወነጃጀል ተንኩሶ ይፋ እንዲወጣ ይረዳ ዘንድ እንዲረዳን በማለት ነው።
ለነገሩ አልን እንጂ በኦነግ ወታደሮች እና ያካባቢ የኦነግ ቀበሌ ተጠሪዎች (ኦነግ በመንግሥት ጥምረት ውስጥ እያለ) አርሲ የተፈጸመው ጭፍጨፋ የወንጀሉ ተካፋዮች ስም ዝርዝር (አንዳንዶቹ አሜሪካ እና ካናዳ ተደብቀው በ ኦነግ ጥገንነት/ደጋፊነትበሰላም እየኖሩ ያሉትንም) ዝርዝር ሐተታ የተዘገበ ነውና “የግድ ኦነግ በበደኖ ተካፈለ አልተካፈለ” ከወንጀሉ ነፃ አይሆንም።
4ኛ - ግብረሰዶም ምርምራ በወያኔ ተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች ላይ ስለመፈጸሙ ጉዳይ በሚመለከት፦
 አስኪ በዚህ ጉድ የተመለከተው Woyanne threatened to sodomize Debebe Eshetu’s family December 1st, 2011  By Elias Kifle በሚለው ርዕስ አንጀምር።እውነት እንደዚህ ዓይነት ድርጊት ተፈጽሟል? ቢፈጸምስ እንዲህ ያለ ጉድ እንደ ዜና ለሕዘብ ይፋ መውጣት ነበረበት? ትግሬዎች “ሸራፍ ስኒ መንፈሲ ጽዋ፤ ሸራፍ ዕትሮ መነፈሲ ስዋ” ይላሉ (ሸራፋ ጥርስ ነገር ያወጣል፤ሸራፋ ጋን ጠላ ያነፍሳል” ማለት ነው። በሌላ አባባል “ካብ ተዛራቢኡስ ደጋሚኡ (ከተናጋሪው ደጋሚው ይብሳል) ማለት ነው።
ኤልያስ እንዲህ ያለ ጸያፍ ነገር እንደ ዜና ማቅረቡ ብዙ ጉዳቶች አለበት። እንዲያ ብሎም አልተወሰነም አንዲህም ይላል; “Sodomizing opponents, which is foreign to Ethiopian culture, is a method that Meles brought from his country Yemen.” እኔ የማውቀው መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያዊ  (ነግር ግን ባንዳ) እንጂ የመናዊ መሆኑን አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እየሰማሁ ያለሁት። መለስ ዜናዊ እናቱ እና አባቱ የመናዊ መሆናቸው መረጃ ከላቀረበልን የዘገባው ተልእኮ ከሻዕቢያ ዘጋቢዎች የሚለይ ዘገባ አይደለም።
 
ይሄ ጉድ ደግሞ ተመልከቱልኝ “Victims of sodomy are extremely traumatized and that they are too ashamed to tell even those closest to them. In recent past, at least two prominent opposition politicians I know of who had been subjected to sodomy. I will not mention their names to keep their privacy. But in time, they themselves may be willing to talk about it in public so that the perpetrators face justice.”

ይህ ጉደኛ ዜናስ ምን ትሉታላችሁ? ሁለት የፖለቲካ ትላልቅ/ እውቅ መሪዎች በወያኔ እስር ቤት እያሉ ግበረሰዶም ተፈጽሞባቸዋል። ለክብራቸው ስል ማንነታቸው አልገልጽም፡፤ ነገር ግን ከጊዜ ብዛት እራሳቸው ሚስጢሩን ለማጋለጥ ፈቃደኞች ይሆኑ ይሆናል። ነው የሚለን ኤልያስ። ተፈጽሞ ይሆናል እንበል፡ እና ግን ኤሊያስ በምን ማሳመኛ ባሕሪው ነው ማመን የሚቻለው? ምናልባት ወያኔዎች ራሳቸው በተዘዋዋሪ ዜናው እንዲለጥፈው እና ተቃዋሚ መሪዎች ለወደፊቱ እንዲህ እንዳይፈጸምብን ፖለቲካውስጥ አንሰተፍም በማለት ሞራላቸው እንዲነካ እንዳይቃወሙት  ማስፈራሪያ እንዲሆን  የተሰራጨ የወያኔ ተንኰል ቢሆንስ? ኤሊያስ ብዙ የተሳሳቱ የዜና መረጃዎች ካሁን በፊት ይዘግብ እንደ ነበር የምታስታውሱት ነውና ሰውየው የሻዕቢያ በሽታ ልክፍት ስለተናወጠው ኢትዮጵያዊ ባሕሪ እና ባሕል ርቆታል። መነገር እና የማይነገር ባሕል ከመጤፍ አልቆጠረውም።
“ዚስ ኢዝ አሜሪካ፤ ዚስ ኢዝ ካናዳ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ቢሰቀል ቢቃጠል ቢደበቅ ጉዳየ አይደልም” ሲለን የነበረው ከወደ ኦታዋ ካናዳ የሚኖረው ልጅ ተክሌ ተባለው የኢካዴፍ ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ እና የብርሃኑ ነጋ አቀንቃኝ ይህን አስመልክቶ የሚከተለውን በጣም አስነዋሪ ጥያቄ አቅርቧል

 “Even a year after Birtukan was released, we do not know anything about what happened to her inside the jail that made her admit the crime she did not commit, other than the solitary confinement. I am not underestimating the solitary confinement. I also do not believe that Birtukan made a confession of the crime she did not commit in front of a camera only because of a solitary confinement. Because based on the story we knew, Birtukan allegedly made the confession long time after she came out of solitary confinement. Since we have not heard anything from her, other than some of the fragments of minor evils she told us about on a couple of occasions, we can only guess or speculate what happened to her. If we succeed in convincing Birtukan to tell her story to the world, then that will be one more piece of evidence of the cruelties this TPLF/EPRDF commits, and it will put the TPLF on the defensive position. That will also help our heroes who are currently in jail to sustain them longer. In the absence of action from people who were subjected to horrific brutality inside TPLF jails, the remaining prisoners will slowly give up.
እንዲህ ያለ ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር የጐደለው ጋጠ ወጥ ወጣት ፖለቲከኛ አይቼም ሰምቼም አላውቅም። እኔ ጌታቸው ረዳ ብርቱካን መዲቅሳን  ባሳየቺው የፖለቲካ ድክመት ልቃወማት ብችልም ድክመቷን ነው እንጂ አሁን ይህ ስድ ግለሰብ የተፈጸመባትን የጨለማ እስር አሳንሶ እስር ውስጥ እያለች “…..” ሌላ ነገር ተፈጽሞባት ይሆናል እንጂ ላላደረገቺው ወንጀል ፈጽሜአለሁ ለማለት ባልበቃች ነበር ብሎ ክብሯን ለማንኳሰስ መሞከሩ እጅግ በጣም ኢትዮጵያዊነት የራቀው የጥያቄ ባሕሪ ስለሆነ እቃወመዋሉ።ሁላችሁም ይህ ያልበሰለ ወጣት አውግዙት። የህ ወጣት የተረገመ የኢትዮጵያ “ኩስ” ነው።

እንዲያ በሚለውም አልተወሰነም። እንዲህም ሲል ሌሎቹን ሁለት ታላለቅ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች ተፈጸመባቸው የተባለው ግብረሰዶማዊ ጥቃት እነማን እንደሆኑ እንዲነግሩን ይወተውታል። ጉድ ነው! Elias also said in his remark that he would do the same if he is in Debebe’s position. I would also do the same if I were Birtukan or Debebe. However, I do not agree with Elias’s remark in our private email exchanged that “some people are criticizing me for even writing about Debebe Eshetu’s situation. Right now I want to focus on Woyanne, so I am trying to minimize controversial issues such as this.” I have two answers for that. First, these days, I do not understand why politician and activists fear to confront controversial issues head-on.” “It is in the best interest of our country and our politics for Birtukan and in a few moments Debebe Eshetu to tell us what made them say what they said. I can only assume that TPLF has brutalized them. However, unless the people who experienced the brutality tell us what exactly happened, Reyot, Eskindir, Andualem and Beqele, Olbana are next in line for the brutalization and subsequent confession of the crime theydid not commit.”…..” “Therefore, I appeal to Ms. Birtukan Mideksa, to speak out to the world what they did to her so that her testimony would be Olbana, Reyot, Eskindir’s and et al insurance …. “ 

ውድ ወገኖቼ፡ ይህ ጋጠ ወጥ ወጣት ብርቱካን እንድትነግረው የሚማጸነው እና ሌሎች  እስር ቤት ውስጥ አያሉ ሁለት የፖለቲካ ተቃዋሚ አውቅ ሰዎች ተፈጽሞባቸዋል እያለን ያለው  የግብረሰዶም ጥቃት (በሻዕቢያው ወዳጅ በኤልያስ ክፍሌ ውዥምብራም ዜና የተዘገበው) ጥቃቱ ቢፈጸምጸምባቸው እንጂ  “እንዲህ ጨለማ ቤት ውስጥ አመት ሙሉ ቢቀመጡም ያላደረጉት ወንጀል አድርገናል ብለው አያምኑም ነበር” ሲል ምን ያህል ስድ እና ኢትዮጵያዊ ባሕል እና ስነ ምግባር እየራቀው እንደሄደ መገንዘብ ትችላችሁ። ይህ ወጣት ብርቱካን ምን ጥቃት ደረሰብኝ ብላ ልትነግረው ነው የሚጠይቅ? ምን ጉድ ነው እያሰማን ያለው? እባካችሁ ባሕላችሁን አትናቁ። የሚነገር እና የማይነገር ጽያፍ እና ነውር ነገር ለይታችሁ እወቁ። ባሕላችን እና ነውራችን ከፖለቲካ ጋር አትደባልቁ። ይሄ ወያኔ የሚባል ስንት ግሳንግስ ሰብስቦ ነው ወደ ውጭ እየላከልን ያለው?  ወይ ዘመን!
  በሚቀጥለው ሳምንት
4ኛ--የሟቹ አገር ወዳድ አርበኛ የሳይንቲስት እጅጉ ቅጣው ንግግር አቀርብላሁ።