Tuesday, October 29, 2013

ድምፃችን ዛሬም ነገም የጎሹ ወልዴ ነው!

 
The Ethiopian Gallants in Eritrea before they fall by conspirators and mercenaries!
 Goshu The Lion Shaming the Ethiopian Enemies
Getachew Reda still stand against all odds!
 ድምፃችን ዛሬም ነገም የጎሹ ወልዴ ነው!
(ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) October 29/2013


 
የርዕሰ ጉዳዬ መነሻ የምመራበት ‘የፖቲካ መርሃ ግብር’ የለኝም፤ ለመንበረ ሥልጣን አደለሁም የምታገለው እያለ ውስጠ ስራው እንዳይታወቅበት የሚሸሸገው ግንቦት 7 ብሎ ራሱን የሚጠራ ‘ፌክ ቡድን’ (የክቡር ዶክተር ማንከልክሎት ሃይለስላሴ ቃል ልዋስ እና)  ከኤርትራው ሻዕቢያ ቡድን ጋር ያለው የቅጥረኛ ግንኙነትን የሚያትት ነው።
 ለነገሩ ኤርትራ ሄደም አልሄደም ‘ዲሞክራሲ’ የሚባል የማስገንጠያ ሽፋን ተጠቅሞ ‘ኦኖጎች እና መሳይ ተገንጣዮችን” በ40 የጐሰኞች ባንዴራ የተሰነጣጠቀቺው  አገራችንን ግብአተ መሬቷን ለማጠናቀቅ ቃል ገብቶ እየሰራበት ስለሆነ  አስመራ ሄደ አልሄደ ለኛ ትርጉም ባይሰጠንም፤ ባንዳዎችና አርበኞች ልዩነታቸውን ‘በአወድዮ በቪዲዮ’ ታሪክ ቀርጾ የተወልንን ምስክርነቱን እንድታደምጡ ግን አግባዛችሗለሁ። በዚህ እንነጋገራለን።
ከዚያ በፊት ግን በአማራዎች እና በክርስትያኑ ማሕበረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ የፈጸሙ እና ለወደፊቱም እንዲካሄድ የሚያበረታቱ እና የሚቀሰቅሱ ‘የፖለቲካ ወንጀለኞችን’ የጥላቻ ዘመቻ እያካሄዳችሁባቸው ነው እያለ “የሚወነጅለን” ከወደ ትግሬ ከመቀሌ እየጮኸብን ስላለው ወጣት አንድ ብየ ወደ ርዕሴ ልሻገር ነው።
ዛሬ፤ዛሬ “ባንዳነት” ነውር እንደሌለው እየተቆጠረ በወጣቱ ሕሊና ሰፊ ቦታ እያገኘ ነው። ብዙ የተበሻቀጠ የባንዳ ትምህርት አስተማሪ እና ተቀባይ ተማሪ እንደ ጉንዳን ተራብቷል። ከትግራይ እስከ ምስራቅ ከደቡብ እስከ ምዕራብ በግንጣላ ስራ እና በዘር ማጥፋት ተግባር የተሳተፉ የድርጀት መሪዎች እና ግለሰቦች በሕብረተሰቡ ዘንድ ምንም ዓይነት ቅዋሜ እንዳይደርሳቸው በ1983 ያየነው ዓይነት ጥብቅና ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ ከእኛው ጉያ ተከላካዮቻቸው ሆነው የሚያገለግሉ እያገኙ ነው።
በወያኔ ዘመን የተወለዱ ወይንም ህጻናት የነበሩ  ወጣቶች ዛሬ አድገው ባደጉበት የተመረዘ የፖለቲካ ትምህርት በመዋኘት ግንጠላም ሆነ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚያስተምሩ እንደ እነ ጃዋር መሐመድ የመሳሰሉት አደገኛ ‘የሰው አንስሳት’፤ ከትግራይ ከመቀሌ ‘አብርሃ ደስታ’ እያለ ራሱን የሚጠራ ወጣት እና የዓረና ድርጅት አባል ‘በፌስ ቡክ’ እና ዘሐበሻ በተባለው ድረገጽ የሚያሰራጨው የነቀዘ ቅስቀሳው ‘ለጃዋር መሐመድ’ (ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ሶማሊያ! ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ! ፈካሪ) በተደጋጋሚ ለሦስተኛ ጊዜ  ድጋፍ በመቆም “በጃዋር ላይ የጥላቻ ዘመቻ አራማጆች” በማለት ወንጅሎናል።

አንደ አሜባ እየተራቡ የባንዳ ደጋፊዎች እየሆኑ የመጡ  አገራዊነት በቅጡ ያልተረዳቸው በወያኔ ዘመን የተወለዱ ወይንም ህፃናት ሆነው ያደጉ እንደ አብርሃ ደስታ የመሳሰሉ “በግማሽ የተለወሱ ሊጦች” ታሪኩን በሚገባ ሳያጠኑ እራሳቸውን ተጃጅለው ሌላውን  በማጃጃል ‘በአገር የግዝገዛ’ ዘመቻው ላይ ተዋናይ እየሆኑ የመጡበት ወቅት ስለሆነ የአንድነት ሃይሉ፤ በተለይ ምሁራን እንዚህን ‘ጐደሎ ወጣቶች’ የግዝገዛው ሱታፌአቸውን  ከማስፋፋታቸው በፊት፡ እነኚህን የተጃጃሉ ወጣቶች መቋቋም የሚችል ኢትዮ ጵያዊ አዲስ ትውልድ አዘጋጅቶ  ማስተማር ለነገ የማይባል አጣዳፊ የቤት ስራችን ነው።


ወጠቱ አብርሃ ደስታ በጃዋር መሐመድ የሚመራው “ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ፤ እና “የክርስትያን አንገት የቆረጣ አብዮት” ቀስቀሳ እና የኦነግ ፕርንሲፕል ዘመቻ  ደጋፊ በመሆን በጃዋር ላይ የጥላቻ ዘመቻ እያካሄዳችሁበት ነው ብሎ የቀሰረብንን የውንጀላ ብዕሩ እና “ተበዳይ በድየሃለሁ ብሎ ለበዳይ ይቅርታ” ይጠይቅ ያለበትን ፍረደገምድል ጽሑፉን  ላመንበብ እዚህ ጫን ይበሉ።

ወደ ርዕሳችን እንግባ። ውይይታችን ስለ ኤርትራ ነው። በሰሜን አይጦች የተቦሮቦሮ የተደፈረው የአንበሶች  ቤት አንዲህ ‘በእርሱት እርሱት’ በግንቦት 7 ደላላዎች ተጃጅለን የምናልፈው አይሆንም።  ያልተቋጨው የኤርትራና ኢትዮጵያ ጉዳይ ሲነሳ ፤ ሻዕቢያ ወያኔን ወልዶ፤ወያኔ ደግሞ ግንቦት 7ን በአምሳያው ወልዶ ወያኔና ሻዕቢያ  ያላጠናቀቋቸው የመጨረሻ የቤት ስራዎቻቸው በግንቦት 7 በኩል አንዲፈጸም ጥረት እየተደረገ ነው። የማስፈፀሚያው ድብቅ መሳሪያው ደግሞ ‘ዲሞክራሲ’ነው። እነ ሂትለር እነ ሴዛር የማሰሰሉት አምባገነኖቸን ወደ ስልጣን ያመጣ “ዲሞክራሲ” ግንቦቴዎችም በዛው መሰለላል ለመረማመድ ዲሞክራሲን ተጠቅመው “በማጆሪቲ ካርድ” መፈክር አገር ለማፍረስ ተዘጋጅቷል። በዚህ ላይ በሰፊው እመለስበታለሁ (ሌላ ቀን)።
እስከእዚያው ድረስ በነሓሴ ወር 2005/2013 ‘ንሂሊስቶቹ’ “ዲሞክራሲ” አገር በማፍረስ የሚጫወተው ሚና እና የግንቦት 7 እና የኦኖግ ተዋናዮቹ በአገር ዕጣ የሚሸርቡበት የዲሞክራሲ ካርዳቸው ተጠቅመው እንዴት አንደሚያጠናቅቁት የሰጠሁት ቃለመጠይቅ  “You Tube”  ላይ ሰፍሯል፡ ያንን ያድምጡ።
ወዳጄ ደራሲ፤ገጣሚ እና አርበኛው ኢያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) “በቀዳዳ ጨረቃ” መጽሐፉ ላይ በገጽ 29 እንዲህ ይላል፡
“…ከጥቂት ደቂቃዎች በሗላ ስነሳ ውሻይቷም ቢራቢሮቹም ጠፍተው አገኘሁ። ላም የሚያክል ጥንቸል ፈገግ ብሎ-አራት ጥርሱን እያሳየኝ- ሲመለከተኝ አገኘሁት።
          “አንተ ማነህ? በብስጭት ድምፅ።”
          “መሪህ ነኝ አለኝ።
          “የማን መሪ?”
          “የቀጣይ ጉዞህ።”
          “ወዴት?”
          “ሳትደርስ፤ሳታየው ስሙ ምን ያደርግልሃል? “ተሳፈር” አለኝ። ላም የሚያክል ጥንቸል መሳፈር የለመድኩ ይመስል ፍንጥር ብየ በጀርባው ወጣሁ።ላም-ጥንቸሉ በመጋለብ ፍጥነት ጨመረና በረረ። ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ ሆኖ የማየው አጣሁ። ወደላይ ባንጋጥጥ ቀዳዳ ጨረቃ ይበልጥ ተበጣጥቃ አየሁ። ብዙም ሳንበር ላም-ጥንቸል ከወገቡ አሽቀንጥሮ ወደ ጨለማው ቁልቁል ወረወረኝ።” (ቀዳዳ ጨረቃ ደራሲ ሃማ ቱማ)
የመጪው ጊዜ መሪዎቻችን (ዕድሜ ከሰጠን) እነማን ናችሁ? ሲባሉ፤ የምትመሰርቱት የአገር አንድነትስ የስርዓቱ ስልት ምን ይመስላል፤ሲባሉ- እዛው ሳትደርሱ ምን ያደርጉላችሗል። ይሉናል። የሰሜን ሽፍቶች እጆቿን  በካቴና አስረው አፏን በጨርቅ አፍነው አዘናግተው የጠለፏት ‘ጨረቃዋ ኢትዮጵያ’ እየታመጸች ከምትገኝበት ዝግ ቤት ነፃ ለማውጣት ‘በሕግም ሆነ በጉልበት” በሩን መበርገድ የሚያስችል ባሕሪ የላቸውም። ብዙ የሚጠየቁ ጥያቄዎች አሉን።
ቢሸፋፍኑትም ለጥያቄዎቻችን ሳያስቡት ድንገት ቀጥተኛ መልስ አግኝተናል። የግንቦት 7 መሪዎች በብርሃኑ እና በዋና ጻሐፊያቸው ‘በአንዳርጋቸው ጽጌ’ እንዲሁም በሕዝብ ግንኙነት ክፍል ተጠሪያቸው ‘ኤፍሬም ማዴቦ’ አማካይነት ግልጽ የሆነ መልስ አግኝተናል። ሲያወላውሉ “እዛ ሳትደርሱ? ምን ያደርግላችሗል!” ሲሉን፤  ደፈር ሲሉ ደግሞ “አይቻልም!” ብለውናል። ሲነሽጣቸውም በማደንቀው ወዳጄ ጋዜጠኛ እና ደራሲ በመስፍን ማሞ  ተሰማ  መጽሐፍ የጆርጅ ኦርዌል “አኒማል ፋርም” ትርጉም “የእንስሳት አብዮት” ላይ የተተረከው ‘የሸንኮር አገዳ ተራራ’ ታሪክ ለሚጥማቸው ለአማኞቻቸው ጀሮ ያስደምጣሉ።
በመግቢያ ላይ እንደጠቀስኩት ለማንኛውም የችግራችን መሰረት ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በአክሱማዊያን እና በእነ ዘርዓ ያዕቆብ በእነ ዓምደ ጽዮን እና በተፈሪ የተጠበቀው የምድራችን ምድሪ ባሕሪ እና ተያያዥ ሁኔታ እኛኑን በእኩል በሚጠቅም መልኩ ካልተጠናቀቀ ኤርትራኖች የሶማሌ ዕጣ ፈንታ ይደርስባቸዋል። (እመኑኝ)። ጠላቶቻችን ሰብረው የሚገቡበት ቀዳዳ በር በኤርትራ ነው። ለዘመናት የተፈታተኑን ጠላቶቻችን ተሳክቶላቸው ‘በሩን’ ተቆጣጥረውታል። ኢትዮጵያም ያለ ባሕር በር ቀርታ በጠላቶች ተከብባ ትገኛለች።ዝም በሉ የሚሉን እና ጦርነት ናፋቂዎች እያሉ የሚያጃጅሉን ባንዳዎችን አንታግሳቸውም።
ይህ ያለ ህግ በሸር እና በአመጽ የተጠናቀቀ የኤርትራ ግንጣላ እና የኢትዮጵያ የባሕር እገዳ፤ አርበኞቿ ዛሬም ኢፍትሓዊው አመጽ ለመቀልበስ የተቻለንን  የፖለቲካ ክርክር በማድረግ ላይ አንገኛለን። በአንጻሩ ለጠላት የሚያጎበድዱ ደካማ ፍጡሮችም የጠላት ፕሮፓጋንዳ ሕጋዊ አድርገው በመቁጠር ከኤርትራኖቹ ወግነው ‘ኢትዮጵያን’ አመጸኛ በማድረግ ‘ጠላፊዎቿን’ ከወንጀላቸው ነፃ ለማድረግ ከኤርትራኖች በላይ ኤርትራኖች እየሆኑ ያሉትን በግንቦት 7 ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ባንዳ መሪዎቻቸው እና ተከታዮቻቸውን በጥብቅ እንኰንናለን።
ግንቦት 7 ምንም ተዋጊ ሠራዊት ሳይኖረው በባዶ ጉሮሮው ቢጐረናም፤ የተማመነው ተዋጊ ሃይል “ድምሒት” የተባለው ኢሳያስ አፈወርቂ ያሰለጠነው ቅጥረኛ የትግሬ ሚሊሻ ተዋጊውን ለመጥለፍ በማቀድ ነው። እዚህ ላይ የኤርትራን ውስጣዊ ጉዳይ በቋንቋ እጥረት ምክንያት አብዛኛዎቻችሁ ለማትከታተሉ ሁሉ፤ ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር አለ። ድምሒት የተባለው ሰራዊት ‘አርማው’ የአገራችን ሰንደቃላማ ሆኖ ከመሃሉ ‘የአክሱም ሃውልት’ ጨምሮበታል (ይህ ሕገ ወጥ ቡድን  ስልጣን ቢወጣ ወያኔ እንዳደረገው ሁሉ ያለ እዚሁ አርማ ሌላ አንዳይውለበለብ ሕግ ያወጣል ማለት ነው)። ድምሕት የተባለው ቡድን ግን ተዋጊዎቹ በበረሃ እና በውጊያ የተጎሳቆሉ ሳይሆኑ ቁንድላ ተሰርተው ጎፈሬ አበጥረው ወዛቸው ለምልሞ በሙዚቃ ባንድ ታጅበው የምታዩዋቸው የትግሬ እና ኤርትራ ድብልቅ ወጣቶች ዋነኛ ስራቸው ድምበር
የኤርትራን ድምበር መጠበቅ እና አስመራ ውስጥ ከዘመቻ የሚሸሹትን ወጣቶች እና በሻዕቢያ የሚፈለጉ ሰዎችን በየቤቱ እና ጎዳናው አድፍጠው በመሰማራት “ድብዳባ” እና “አፈና” የሚፈጽሙ /መርሲናሪ/ ታጣቂዎች አንደሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ከአንድ ውስጥ አዋቂ ሰው ያገኘሁትን መረጃ አስነብቤአችሁ እንደ ነበር ይታወሳል።
 
ዛሬም በድጋሚ ያንኑ ዘገባ ተንተርሶ ከወደ አስመራ ሽው የሚለው ወሬ እየተናፈሰ ነው። የኢሳያስ ቡድን ችግር ውስጥ ሲገባ ድምበርም ሆነ ከተማውን በመቆጣጠር ‘የሹት ትኪል’ (ነጻ እርምጃ) ሃላፊነት የሚሰጣቸው እነሱ እንደሆኑ እና፣ ድምበር ላይ ሰውን በማሻገር ገንዘብ የሚቀበሉም እነኚሁ መሆናቸው በሰፊው ይወራል።
ሰሞኑ አስመራ እና በመሳሰሉት ከተሞች “አሰሳ” እየተደረገ ነው።በዚህ ስራ የተሰማራውም ይህ ቅጥረኛ ቡድን ነው እያሉ ኤርትራኖቹ ይህንን ቡድን ይወነጅላሉ። በነዋሪዎቹ አጠራር  “ከምድላዬ” የሚል ቅጥያ ተሰጥቷቸዋል። “እንዳሻኝ” ይሏቸዋል። ‘አጋሜ’ እያልን አንዳላሳነስናቸው ሁሉ የግረም ብሎ የድምበሮቻችን እና ከተሞቻችን ጸጥታ አስከባሪዎች ሆነው የቤቶቻችን በሮች እያንኳኩ አፋችን ከድነን በፍርሃት ተውጠናል። እስከማለት ኤርትራኖች ምሬታቸው እየገለጹ እንደሆነ ለዚህ ጸሐፊ የተሰጠው መረጃ ያስረዳል።
ከወዲሁ የግንቦት7 ጸሓፊው የኢሳያስ ተክለሰውነት እያሞካሸ ለሕዝብ መስበክ የጀመረበት ዋናው ምስጢርም ፤ ድምሕት የተባለው ኤርትራ እና ትግሬ የደበላለቀ ተዋጊ ሃይል በኢሳያስ ትእዛዝ ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ እንዲሆነው በግንቦት 7 ቁጥጥር ስር አንዲውል በድምሕት ላይ እየተሸረበ ነው የሚሉ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። ኤርትራ በረሃ ውስጥ አለ የሚባለው “አርበኞች ግምባር” የግንቦት 7 ሴራ አስቀድሞ ስለገባው ከበትናቸው ጽጌ (አንዳርጋቸው ጽጌ) በግምቦት 7 እንዳይጠለፍ አስቀድሞ ስለተጠነቀቀ ነበር ‘ብርሃኑ ነጋ’ በግልጽ ኢሳትን ‘እንግዲህ ወዲህ ስለ አርበኞች ግምባር ህልውና በኤርትራ ውስጥ አለ ብሎ ኢሳት አያወራም” ብሎ ትዕዛዙን ለኢሳት ያስተላለፈለት።    

ኤርትራ እነዚህን ሁሉ እየሰባሰበ የሚረዳበት ምክንያት ኤርትራኖች የሚያሰጋቸው መጪው ሕጋዊ የጦርነት ዳመና “በኢትዮጵያ የአንድነት ሃይል ተዋጊዎች እና መሪዎች” እንዳይከፈትባቸው ስለሚሰጉ ነው። ዋናው ጉዳይ ግን ‘ድንገት አገራችን ሁከት ውስጥ ብትገባ’ የኢሳያስ የግል ወዳጅ የሆነው ጀኔራል ስብሓት ኤፍሬም የተባለው መልከ ጥፉ ዘረኛ “ፈንቅል” በተባለው የሻዕቢያ ወታደራዊ መጽሔት በሰጠው ቃለ መጠይቅ አንደገለጸው “በጐመራው ላይ እየነደዱ ያሉት እንጨቶች ስንት አንደሆነ በቁጥር እናውቃቸዋለን፡ እሳቱ ተቃጥሎ አመድ ለመሆን ጭልምል እያሉ ያሉት ጭራሮዎች፣ኢ ስንት እንደሆኑ እናውቃለን። ነድደው ለማለቅ የቀራቸው እነኚህ ጭራሮዎች የቀራቸው ጊዜ ጥቂት ነው፡ በእሳቱ ዙርያ ቆሞ እሳቱ ነድዶ እስኪያልቅ ድሰር እየቆሰቆሰ በቅረብ እየተቆጠራጠረው ያለው ሃይል ደግሞ እኛ ስለሆንን የተነጠቅነውን መሬትም መልሶ ለመንጠቅም ሆነ (ባድመ) በፖለቲካ ማዕበል እየተንገላታች ያለቺው ምሲኪኗ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እኛ ትዘረጋለች” ብሏል።
 
ትዕቢቱና ሴራው ስናገናዝብ አሁን ለሚረዳቸው ግነቦት 7 እና ኦነጐች ሶማሌዎች ኦጋዴኖች ሲዳማዎች፤ቤንሻንጉሎች….ለምን እንደሚራዳ የምትስቱት አይመስለኝም። ነድደው ያለቁ ትላልቆቹ ግንዶች ወደ ጭራሮነት ተለውጠው አመድ ሲሆኑ በነሱ ምትክ ለመተካት አንደሆነ አትስቱትም።

እራሱ እድሜ አይኖረውም እንጂ እቅዱ እነዚህን ቡድኖች አስከትሎ ከሗላ በመሆን የመቶ አመቱ የቤት ስራው የመጨረሻ ፍጻሜ ለማጣናቀቅ ነው። ሆኖም መጀመሪያ ማን አመድ አንደሚሆን የሚታይ  የማይቀር ትርኢት ቢሆንም ለጊዜው የኤርትራ ጉዳይ የተዳፈነ እሳት ቢሆንም የታመጽነው አመጽ ፍትሕ እሰኪያገኝ ድረስ ዘመናትም ይፍጅ “ጦርነቱ ይቀጥላል!!!!”። ይህ የኔ እምነት እና መመሪያየ ነው። “ጦርነት አትቀስቅሱ” ፤ “አንዴ የሆነ ሆኗል” ፤ “ስታተስ-ኮ”-ውን ተቀብልን  ሰላም አንፍጠር”  እያለ ያለው ክፍል፤ እራሱን ያጃጀለ ምሁሩ ክፍል ስለሆነ ከነ’ዚህ “ቆሻሻዎች” ጋር ላለመነካካት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋ።
   
ጠላቶቻችን እኛን አላሸነፉንም፤ እኛን ያሸነፉን የኛ የምንላቸው የቆሸሹ ወገኖቻችን ናቸው። የወቅቱ ቀዳሚ የውጊያችን ደግሞ በ1983 የተከሰተው “የክፍሌ ወዳጆ ሲንድሮም” (የጋሸ ቀለሙ ርዕስ ልዋስ እና) በሽታ አንደገና በድጋሚ አንዳይከሰት ሕዝባችንን ማስተማር ነው። ወጣቱ እኛን ማድመጥ አለበት። አሻፈረኝ ካለ፤ የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ወጣቱ እንጂ እኛ አልፈንባታል። ለራሳችሁ ስትሉ ኢትዮጵያን ጠብቁ። ካልሆነ በየጐጣችሁ ታፍጋችሁ ማንነታችሁ ይፋቃል። ሲገነጣጠል ተገንጣዩም፤አስገንጣዩም ችግር ውስጥ አብሮ ይዳክራል። ማንኛችሁም ነጻ አትሆኑም።ለኔ ሳይሆን ለራሳችሁ ስትሉ ታገሉ! እኔ የምኖረው እዚህ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ኢፈሲያነስ 6 ላይ ‘የምንታገለው ሰይጣንን እንኳ ቢሆንም ትግላችን እሱ ካሰማራቸው ጃንደረባዎቹ ጋር ነው።’ ይላል።  
እያናገረን ያለው ጥቃት ነው። እኛ ተጠቅተናል! እስካሁን ድረስ ለጉዳታችን ተጠያቂ ሆኖ በፍትሕ ፊት ቀርቦ የተጠየቀ የለም።ስለዚህም ጥቃት ፈጻሚዎቹ ዛሬም የወቅቱ ፖሊተካ መድረክ በአስመሳይ ምላሳቸው በመቆጣጠር ዳግም ወደ ቀረቺዋ ኢትዮጵያ ጠላቶቻችንን ለማስገባት የረቀቀ ሴራ እየሸረቡብን ነው።  
በኤርትራ ምድር ለዘመናት የከፈልንበት የደም ግብር አለ። አያቶቻችን እና ወላጆቻችን እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን አጥንታቸው በኤርትራ ባሕር እና በኤርትራ በረሃዎች ተረጭቷል/ተዘርቷል። በዚህ የማንንት ጥያቄ አርበኞቻችን የዘሩት አጥንት መልቀም ይኖርብናል። ያለ ምንም ሰቀቀን ኤርትራ በረሃ ውስጥ ሄደው በእነዛ አርበኞች አንጥንት ላይ እየተረማመዱባቸው ያሉት የግንቦት 7 መሪዎች የአርበኞቻችን አጥንት በማርከሳቸው በወንጀል ይጠየቃሉ።
ያልተሰማችሁ ብዙዎች ናችሁ። በሰሜን አካባቢ የተወለድን እና የነበርን የዓይን እና የጀሮ ምስክሮች እኮ ያለፈው ትንንቅ አሁንም ከሕሊናችን አልለቅ ስላለን ነው። አንዲያ ያለ ብርታት እና ትንንቅ ተደርጎ ከሗለችን ‘በሴራ’ ስንመታ አንዴት ነው በእኛ ላይ የምትፈርዱብን?
እስኪ ላንዳፍታ ወደ 1983 ግንቦት ወር ሕሊናችሁ መልሱት እና ለ22 ዓመት ተጉዛችሁ አሁን ወዳለንበት ፌርማታ/ማቆሚያ/ አተኩሩ። የደረሰብን ጥቃት ሊስቱ/ዝርዝሩ ስንት ገጽ ነው? ይህ ሁሉ ጥቃት ሲጫንብን የቆዳችን ውፍረቱ እና ቻይነቱ ለታዛቢ የሚገረም አይመስላችሁም። ጥቃታችን አንድንረሳ ተጃጅለን አንድንኖር እና ኢትዮጵያ በጠላቶች የተሸረበባት የባሕር ወደብ እገዳ ሕጋዊነት አንዳለው በማስመሰል ለኤርትራ ወንበዴዎች ዛሬም ጥብቅና የቆሙ ተቃዋሚዎች ስንመለከት አዲስ ውርደት ላይ ገብተናል። ለምን ዝም በሉ እንባላለን?!
ወታደሮች ፤ አርበኛ ሚሊሺያዎች እንዲሁም ሲቪል እና የመንግሥት ሰራተኞች በዛው ምድርና እና በሕር የገበሩት የሕይወት ግብር ያፈሰሱት ደም አንዴት ነው አታንሱት የምትሉን? የስድባቸው ክምር እኮ ድፍረቱ አንዴት አንዳገኙት ለኔ ይገርመኛል።እንዲያ ተበድለን አጥቂዎችችንን ነጻ እንዲያወጡን እኮ ነው እየሰበኩን ያሉት? ኢሳያስ ነጻ እንዲያወጣን የሚያምኑና የሚማጸኑ የግንቦት ሰዎች ‘በስቶክ ሆልም ሲንድሮም’ ልክፍት የተጠቁ ይመስሉኛል ። በሽታ ካልሆነ እንዲያ ላለ እጅግ ክፉ ጠላት እና አጥቂ አንዴት ጥብቅና ቀሞ መልካም ዝና ይሰጡታል?
ያለማፈር እና በተቃዋሚው ጐራ እየተለመደ እየመጣ ያለው የባንዳነት ባሕሪ አስገራሚ ክስተት ‘ጋሻ ቀለሙ’ የተባሉ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ጸሐፊ ከጥቂት አመታት በፊት ( ከ5 አመት በፊት) ያቀረቡት ቆየት ያለ ትችታቸውን ቀንጨብ አድርጌ ላቅርብላችሁ እና ባንዳነት ምን ያህል ተቀባይነት እያገኘ አንደሄደ እነሆ እንዲህ ይላሉ:-
 
“Politics should have been a game with rules and boundaries enforced by integrity, morality and truth. It is only the rational political argument that hits the target and accomplishes its goal not the irrational argument that can be pushed to get a result of false positive which crumbles down when it encountered the real truth.
We can’t reason with people who position themselves purposely to deceive us……..The method used to attract followers and attack opponents is beyond my imagination; you don’t hear or read in history books this kind of characters a few decades ago. The old way of showing and keeping your dignity by respecting your opponent is a thing of the past. So does not selling yourself to the highest bidder. Unlike our contemporary politicians in the old days treason was unthinkable, even if one or two in history has done it, they were outcastes and ashamed alienated themselves from the glaring eyes of society. But these days our politicians are advertising their treasonous acts through internet radios and their foot soldiers, no shame is involved anymore.
 They are not only treasonous and backstabbers themselves, they are teaching the next generation to do the same thing like they do, act like they act. Being sellout is not a shame it has to be glamorized adapted and followed.”  Gashe Kelemu ( Kifle Wodajo Syndrome)
ጸሐፊው ባንዳነት አዲስ ትግል ፈር ሆኖ ቀርቧል፤ ነው የሚሉን። ከአምስት አመት በፊት የነገሩን እኚህ ኢትዮጵያዊ ሃቅ  መሆኑን ዛሬ በግንቦት 7 እና አጫፋሪዎቻቸው ገሃድ ሆኖ ስለ ሻዕቢያው መሪ ሰብአዊነትና ስለ ኢትዮጵያ ተቆርቋሪነቱ ሳያፍሩ በሻዕቢያ ገንዘብ እርዳታ የሚደጐመው በኢሳት ቲቪ በኩል ቀርበው ሰፊ የባንዳነት ስራ ለሕዝባችን የሕሊና አጠባ አጋዥ እንዲሆን ቅስቀሳው ወደ ኢትዮጵያ ተላልፏል። ባንዳነት  ተቀባይነት እያገኘ፤ አገርን የመገዝገዙ “የክፍሌ ወዳጆ ሲንደሮም” ዘመቻ ሁለተኛው ዙር በግንቦት 7 መሪዎች ተጀምሯል።

ለዘመናት እስካሁንም ድረስ ጠላቶቻቸን የመረጡት  ይነተኛ የመጫወቻ ሜዳ “የኤርትራ ጉዳይነው”።ኤርትራ የማን ናት? የግንጣለው ሕጋዊነትስ ምን ያህል ሕጋዊነት አለው? ሁለት ወገኖች ያላቸው አቋም በስእለ ድምጽ አስደግፌ ላቅርብላችሁ እና ልደምድም።
 
Our heroes Professor Mesfin W/Mariam and Colo Dr. Goshu Wolde
Banda of the Year 2013 Efrem Madebo of Ginbot 7 propagating in defense of Eritrea and dehumanizing our Ethiopian heroes on behalf of Eritrean bandits calling them extremists

ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ እና ጠላት የሸረበብንን የመጥለፊያ መረብ አንቀበልም የሚለው አንድ አርበኛ ኢትዮጵያዊ እና በሌላ በኩል ደግሞ የጠላት ሴራ ሕጋዊነት ተቀብሎ በጠላት ቅስቀሳ የተሰማራው የመጥለፊያው መረብ ተቀበሉ የሚለን  አንድ ‘ኢትዮጵያዊ ባንዳ’ የሚታይ የሕሊና መራራቅ አድምጣችሁ መንፈሳቸውን መዝኑት እና እናት ኢትዮጵያ በዥጉርጉር አንጀቷ አንዴት ሁለት ዓይነት ልጆች ወልዳ አንዱ አጥቂዋ ሌላው ተከላካይዋ አንደሆነ ከዚህ በታች ያለው ‘ስእለ ድምፅ’  ከፍታችሁ አድምጡ። የተከበረው ኩሩ የኦሮሞው ተወላጅ ኢትዮጵያዊው “ዶክተር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ” ጠላት ባዘጋጀው መድረክ በመገኘት የወያኔ እና የሻዕቢያ ባንዳ ወኪሎችን እሳት በለበሰው አንደበተ ርቱእ ተጠቅሞ አንገታቸውን ያስደፋ፤ ፈረንጅን የገዛ ቋንቋው ተጠቅሞ አፉን አስከፍቶ አንዲያደንቀው ያደረገው ዓለም ያስደነቀ ተከራካሪ በዚህም ይሁን ባለፈው ትውልድ እንደ ጎሹ አይነት እናት ወልዳ አታውቅም። የጎሹ ቃል ዛሬም ሆነ ነገ ቃላችን ነው። አርበኛው ቀብራራው ኦሮሞ ኢትዮጵያዊው ጎሹ ወልዴ ማድነቅ አለባችሁ። የፈለገው ስህተት ቢኖረውም ጎሹን የሚያክል የባንዳን አንገት ያስደፋ ኢትዮጵያዊ በክብር ማህደር መመዝገብ አለበት።

ቀጥሎ የማቀርብላችሁ  የስዕለ ድምፅ ማሕደር በሁለት የተከፈለ ነው። አንደኛው ማሕደር የግንቦት 7 አመራር አባል የሆነ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለኤርትራ/ሻዕቢያ የቆመ ባንዳ ሲሆን፡ ሌላው ያው፤ ቀብራራው ኢትዮጵያዊው ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ነው።  ከሁለቱም ተከራካሪዎች ካንደበታቸው የሚወጣው የኢትዮጵያዊነት ትርጉም እና ስለ ኢትዮጵያ ዘብ መቆም ምንነት፤ ስለ ኤርትራ ጉዳይ እና የደረሰብን ሴራ እና ኢፍትሓዊነት የቀረበው ተቃራኒ ክርክር መዝናችሁ አርበኛችሁን ምረጡ። ስእለ ድምጽ 1 ስእለ ድምፅ 2 ከዚህ በታች ቀርባል።

Colonel Goshu Wolde - Historical Speech http://youtu.be/orod3OU3jfM

Ephrem Madebo of Ginbot 7 Ethiopian opposition movement at Eritrean  http://youtu.be/pW1mopFgf2k

አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getcahre@aol.com ድረገጽ እና ፌስ-ቡክ ለመጐብኘት ለምትፈልጉ (Ethiopian Semay)ጉጉል ብታደርጉ በቀላሉ ታገኙታላችሁ። በዚህ አጋጣሚ አዳዲስ መጽሐፍቶቼ ዳግም በጥቂት ቅጅ ታትሞ ለገበያ ቀርቧል። ጠይቁ። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ። (Ethiopian Semay)

 

 

 

Thursday, October 17, 2013

Eritrea Opposition Sites Funded and Backed by CIA: Wikileaksኤርትራ ድረገጾች በሲ አይ ኤና በወያኔዎች ወጪ እየተደገፉ እንደሆነ የሚያጋልጥ ዜና ከማንበባችን በፊት በዚህ አስደሳች ብስራት አንጀምር።

Ethiopian Semay is glad to announce, that you can now order (1) ይድረስ ለጐጠኛው መምህር ($25.00 ፖስታ አገልግሎት ይሸፍናል) (2) ደቂቀ ተወልደ መድኅን $20 ፓስታ አገልግሎት አይጨምርም)፤*** (3) የወያኔ ገበና ማሕደር የሚለው መጽሐፌ አልቋል። ምናልባት በቁጥር ሦስት ቅጂ ካሉኝ ቀድመው የላኩ ሊያገኟቸው ይሆናል። በተረፈ አልቋል። በተራ ቁጥር አንድ እና ሁለት የተመለከቱት መጽሐፍቶች አልቀው ነበር፡ ሆኖም ብዙዎቻችሁ አንደገና እንዳሳትም ስለጠየቃችሁ፤ ይኸው በናንተው ጥያቄ ጥቂት ቅጂዎች ታትመዋል።

ወያኔ ያበላሻቸው ታሪኮችና ውሸቶቹ የሚጋፈጡ በማያወላውል በሃቅ የተደገፉ ሰነዶችና ክርክሮች የጻፍኳቸው መጽሐፎች ስለሆኑ መጪው ትውልድ በውሸት አንዳይታፈን፤በትምህርት ተቋማትም ሆነ በፖለቲካ ክርክር የሚጠቀሙት ሰነዶች ስለሆኑ፤ እየገዛችሁ ለተረካቢው መጪው ትውልድ አስተላልፉለት።


ወያኔዎች የውሸት መጽሐፍቶች በደጋፊዎቻቸው እየተደገፉ በመላ ዓለም ያሰራጭዋቸው መጽሐፍቶች መጪውን ትውልድ የሚያሳስቱ እና የሚያጋጩ መሰሪ መጽሐፍቶች ስለሆኑ ፤እነኛ መርዛም መጽሐፍቶችን የሚቋቋሙ ኢትዮጵያዊ ሰነዶች በእጥፍ እንዲሰራጩ ካልተደረገ፤ ተረካቢው ትውልድ ውዥምብር ውስጥ  ገብቶ ሰነድ አልባ መከራከሪያ የሌለው ትውልድ ሆኖ አንዳይቀር ሁላችንም ሃላፊነታችን እንወጣ። የኔ ድርሻ ይኸው ተወጥቻለሁ፤ የተቀረውና የማስተላለፉ ሃላፊነት ለናንተ ትቸዋለሁ። እኔ ከታሪክ ተወቃሽነት ለመዳን በምችለው ሁሉ ተወጥቻለሁ።
ባለት ወራቶች ንድልክልቻሁ፣ ኢመይል ያደረጋችሁልኝ ወገኖች፤ እባካችሁ ንደገና ኢመይል አደርጉልኝ። የአንዳንዶቻችሁ ኢመይሎች ድንገት ሳልመዘግባቸው ቀርቼ አንዳልሆን መጽሐፍቶቹ ንድትገዙ የምትፈልጉ ወገኖች በድጋሚ አሁንም “ስማችሁ አድራሻችሁ እና ስለክ ቁጥር አና ኢመይላችሁ” በማሳወቅ አሜሪካ ላላችሁ “በቼክ/ወይንም በፖስታ ማኒ ኦርደር” ብቻ ላኩ። ለታሪካዊ ትብራችሁ አመሰግናለሁ። ከመላካችሁ በፊት አስቀድማችሁ ኢመይል  አድርጉልኝ። ለስለ ዝባዊ ወገንተኝነታችን በሃቅ ስንቆም ፈራጁ ጊዜ ብቻ ይሆናል። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com
CIA and Ethiopian Backed Eritrean Opposition Websites


 

CIA and Ethiopian Backed Eritrean Opposition Websites


Whistle blower website Wikileaks citing email communications from U.S. intelligence contractor STRATFOR suggests that most of the Eritrean opposition websites are funded and backed by CIA and the Ethiopian government.

The dramatic revelation comes after it published the five million e-mails dated between July 2004 and late December 2011 from the Texas based “Global Intelligence” company Stratfor.

The emails show Stratfor’s web of informers, pay-off structure, payment laundering techniques and psychological methods. 

Besides exposing the devastating portrait of the Eritrean “Opposition”, the release also reveals the inner workings of Stratfor, a company that fronts as an intelligence publisher, but provides confidential intelligence services to large corporations, such as Bhopal’s Dow Chemical Co., Lockheed Martin, Northrop Grumman, Raytheon and government agencies, including the US Department of Homeland Security, the US Marines and the US Defence Intelligence Agency.

The latest revelation only confirms what the Eritrean government has been trying to warn ever since.

The Eritrean “Oppositions” is usually characterized by divisions along regional, ethnic, religious, and ideological parameters.

Due to their alarming ties with arch-rival Ethiopia (and the alleged but now certain backing from the CIA) they failed big time to garner any tangible support from the Eritrean people.

That creates a situation for them to thrive only in the imaginary world of the Internet trying to stay visible and relevant."
 Posted at www.ethiopiansemay.blogspot.com
 

 

Friday, October 11, 2013

“ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ”ከአዘጋጂው-ማሳሰቢያ፡(getachre@aol.com) www.ethiopiansemay.blogspot.com
When you want to minimize or magnify this page: - use Ctrl and the + sign on your key together or to minimize use the Ctrl and - sign  on your keyboard. የኢትዮጵያን ሰማይ አንባቢዎች ሆይ። ይህ “ሆድ ሲያውቀው ማታ ዶሮ” የሚል እዚህ የቀረበው ትችት የሻዕቢያው ሰላይ የተስፋዬ ገብረአብ  የተሸሸገ የመንንት ምስጢር ሰሞኑን በሰነድ አስደግፈው ለህዝብ ይፋ አድረገው ያጋለጡት በብርሃኑ ነጋ በግንቦት 7 የሚደገፈው (አንዳንዶቹም የግንቦት 7  ንብረት ይሉታል) የኢሳት ቴ/ቪዥን እና ራዲዮ አገልግሎት ድጋፍ ሰጪ አባል የሆኑት “ዳኛ ወልደሚካል መሸሻ” የተባሉ ኢትዮጵያዊ ላይ ያነጣጠረ ነው። እኔም በዳኛው ላይ ያለኝን ቅሬታ (አቶ የሶማው ያቀረቡትን ጽሑፍ) ለማቅረብ ስዘጋጅ ነበር ፤ወንድሜ አቶ ሶማው በግሩም አቀራረብ የቀደሙኝ። ስለዚህም የሳቸውን ትችት ሁላችሁም አንደታጠኑት ነው የምማጸነው። ዳኛው ጥሩ ስራ ቢሰሩም፤ “አድርባይ/ወላዋይ” አቋም በመያዝ ተስፋን ያክል መርዘኛ ሰው ቦታ ሰጥተው ሲያሰድቡን እና “ሲያስጎረጉሩን/ሲያጃጅሉን” የነበሩት እንደ እነ ክንፉ አሰፋ የማሳሰሉ መርዘኛ እና ቡድንተኞችና በታኝ ጋዜጠኞች አንዲሁም መላው የኢሳት ጋዜጠኞች ይህ ጉድ እያወቁ ለሁለት ዐመት “ሸሽገውት” ለምን አንደቆዩ ጸሐፊው ያስገረማቸውን ያህል እኔም አስገርሞኛል። እነዚህን ነው ዳኛው “ሲያቀብጣቸው በጥሩ ስራቸው ላይ ከማተኮር ይልቅ  “ የሻዕቢያ” መጽሐፍ አራሚዎችና አሻሻጭ ደላሎች እና መተላለፊያ ድልድይ ሆነው ሲየገለግሉ የነበሩትን “ሚዲያዎች” እን ግለሰዎች “መካባቸው” ያስገረመኝ።

ሚዲያዎች ይቀርታ መጠየቅ አለባቸው። የአማራ ሕዝብ በኦሮሞዎች፤ በሐረሬዎች ወዘተ ወዘተ… እንዲጠላ እና አንዲገደል የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸምበት የተቻለውን ያህል በመጣር ፤መጽሐፈት ሳይቀር በአማራ ሕዘብ ላይ ግድያ እና ጥላቻ እንዲፈጸምበት የጻፈ፤ የዋሁ አማራው ሕዝብ  በመጽሐፉ ላይ ”በበግ”  እንሰሳ የሚመሰል “እራሱን” *የበግ ነጋዴ* በማለት አማራውን “ለጭዳ/ለ ዕርድ” የሚያዘጋጅ አደገኛ የዘመናችን “ወንጀለኛው ጋዜጠኛ” ፤ በጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት ሳይቀር ‘አማራን ሕዝብ በመጨፍቸፍ የዘር ማጥፋት የፈጸመው “ኦነግ” የተባለው ሽብረተኛ እና ወንጀለኛ ድርጅት “ተስፋ ገብረአብን “ኦቦ” የሚል የታጋይ ክብር መጠሪያ “ማዕረግ” የተሰጠው “የሻዕቢያ እና የኦነግ” ጠበቃ፤ መሆኑ እያወቁ ሚዲያዎች በዚህ ጨዋታ ተነክረው እንደነበሩ ‘ዳኛው’ እያወቁ “ግለሰቦች በማይገባ ‘ማካብ’ ባሕሪ ውስጥ መግባታቸው የሚያስተቻቸው ስለሆነ፤ ይኸው የጥሩ ኢትዮጵያዊው የአቶ ሶማው ትችት ባዳኛው ላይ የቀረበው አንድታነቡት እጋብዛለሁ። አመሰግናለሁ። ትችቱ ይኸው ከዚህ በታች ፡ መልካም ንባብ!  (ጌታቸው ረዳ  ኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ)

 

“ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ”

(የሶማው)

በቅድሚያ አቶ ዓለማየሁ ስለሰሩት ጀግንነት ከልብ የምነጨ አድናቆቴን እገልጽሎታለሁ ነገርግን ይህን የመሰለ መረጃ ሳይወጣ መቆየቱ የሚያሳዝን ነው። አቶ ወልደሚካኤል መሸሻ እንዲወጣ ላደረጉትን ትብብር ምስጋናዬ ይድረሶት። ነገርግን እስከ ዛሬ ድረሰ ለሚዲያ ያላወጣሁብት ምክንያት ብለው የሰጡት ማስተባበያ ውኃ የማያነሳ ነው። ምክንያቱ ይህ መረጃ ለኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ከደረሰው ሁለት ዓምት ሊሞላው ምንም ጊዜ አልቀረውም ነገረግን በግንቦት7 መሪዎች ጫና እንዳይወጣ መደረጉ እኛ የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴዎች ማለትም አቶ ወልደሚካኤል መሸሻ፣ አቶ ካሳውን

አሊ፣ አቶ ብስራት ኢብሳ፣አቶ ፋሲል የኔዓልም፣ አቶ ዘውዱ ከበደ እና ወንድወሰን ገብረሂይወት እንዲሁም ከአንድ ዓመትበፊት የለቀቀው ብራስልስ የሚገኛው ተስፋዬ የምናውቀው እና የማንክደው ሚስጢር ነው። በዚህም ጉዳይ ብዙ ተነጋግረናል። እውቁ እና ታላቁ ኢትዮጵያዊ አቀንቃኝ ጥሌ ስያቀነቅን “ ሐሰት ለመናገር አትሻ ምላሴ ለእውነት እሞታለህ አልሳሳም ለነፍሴ” ሲል የሙያ አጋሩ እና ታላቁ አቀንቃኝ ሙሃሙድ “ ቆሞ የምናየው በመልካም ሰውነት ነገ የጉድጓድ ነው የዛሬ ሰውነት” በማለት ጨርሶታል። ነገ ሟች ነን እውነት እውነቷን እንጫወት። ታዲያ የተስፋዬ ሰላይነት እንዲደበቅ ያደረጉና በመጽሀፉ ክለሳ፣ህትመትና ፕሮፓጋንዳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉት የግንቦት7 መሪዎች እና

ኢሳቶች ለምን በዚህ ጉዳይ አልተተቹም?

ፋሽስቱ ተስፋዬ (ፌሊሲዮን ካቡጋ)

ስለተስፋዬ ማንነት በተለያዩ ጊዜያት ሰላይነቱን እና ፀረ-የኢትዮጵያዊነቱ፣ መደዴ ዘረኝነቱ ግልጽ ካደረጉት መካከል እኔ

ከማውቃቸው መካከል በግሪን የሎርድ ቅጽል ስም የሚጠራው ሰው በፓልቶክ፣ ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ ሰማይ በሚለው ብሎጉ “ ትቁር አሞራው ሙሴ” በማለት እንዲሁም መምህር አንተነህ ጌትነት ኤርትራ ለትግል ደርሶ የተመለሰ በግንቦት7d ዌብ ሳይት ላይ ማነነቱን አስረግጠው ነግረውናል። በእኔ እምነት ተስፋዬ ሰላይ ብቻ የሚለው ስም በቂው አይደለም የዘር ፍጂት እንዲነሳ የቀሰቀስው ሁለተኛ አፍሪካዊው ካቡጋ ጭምር ነው እንጂ። ይህን ስል ለአማራ መጨፍጨፍ( ጀኖሳይድ) በአስተባባሪነት ሻቢያ፣ ወያኔ እና ኦነግተጠቃሾች ናቸው። ይህንንም እያወቀ ከነዚህ ፋሽስቶች ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ከፈጥሩት ውስጥ ከሻቢያ፣ ከኦነግ እና ከተስፋዬ ገብርአብ ጋር ከፍተኛ ግኑኙነት( ቁርኝት) ያላቸው ግንቦት7 እና ኢሳት በመጀመሪያው ረድፍ ይምደባሉ። ይህን እያወቁ ጀሮ ዳባ ልበስ ማለታቸው “ አውቆ የተኛን...” እንደሚባለው ነው።

አቶ ወልደሚካኤል እስኪ ልጠይቆት?

ሀ/ የተስፋዬ የደራሲው ማስታወሻ ለቀማውን፣እርማቱን እና ህትመቱ በአንዳርጋቸው መከናወኑን አያውቁም ነበር? ለምንስ በዚህ ጉዳይ አንዳርጋቸውን ተጠያቂ አልደረጉም? አንዳርጋቸው አፉን ሞልቶ የተስፋዬን መጽሃፍ እስኪታተም ድረስ የረዳሁት ከተስፋዬ 60.000 ብር ስለምናገኝ ነው በማላት አፉን ሞልቶ ለትግል የሄዱትን ታጋዬት ቅስም መስበር ምን ይሉታል? “ ቃሉን ከሚበላ ሰው የበለጠ አውሬ የለም።”

 

ለ/ አንተነህ ሙሉጌታ “ የሁለት ዓለም ሰዎች” መጽሃፍ ለማሳተም ያስገባ ሲሆን የተስፋዬ መጽሃፍ ቀድሞ እንዲወጣ መደረጉን አያውቁም? በዚህ ጉዳይ አንተነህ እና ብርሃኑ የተካረረ ፀብ እንደገቡ መቅረታቸውን አያውቁም ነበር? ያ ሁሉ ችኮላ ኢትዮጵያን ለመገነባት ወይስ ለማጥፋት? መልሱን ለእርሶ እተወዋለሁ።

 

ሐ/ የግንቦት7 ( የአንዳርጋቸው እና የብርሃኑ ጦር ኤርትራ መክተሙን አያውቁም? ጦር ስልዎት ግር እንዳይሰኙ በ4 ዓምት ውስጥ 30 ሰዎች የድረሱት እስክግንቦት 2013 ባለኝ መረጃ ማለቴ ነው።

 

መ/ ተስፋዬ ወደኤርትራ የሄደው ከአለቆቹ መመሪያ ለመቀብል ነው ይሉናል ተስፋዬስ መመሪያ ለመቀበል ከሄደ የግንቦት7 ታጋዩ አንዳርጋቸ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ ከሚፈልግ ሻቢያ ብብት ስር የተሸጎጠው?ለምን ይሆን? እባክዎን ይመልሱልኝ? በኢትዮጵያስ ህዝብ እየቀለደ ያለው ማን ነው?“ ዳር ቆሞ የሳቀ ማሃል ገብቶ ያለቅሳል” ይባላል ።

 

በኢትዮጵያ ህዝብ የቀለደ የኢትዮጵያ አምላክ እንደሚቅጣው ከመለስ(ለገሰ) እና ከታጋይ ጳውሎስ

ቅጣት መማር በቂ ነው። አይመስሎትም?

 

ሠ/ ይህ መንግስት ያለነፍጥ አስገዳጅነት ስልጣን ሊለቅ አይችልም የሚል ህልም አለኝ ይሉናል ታዲያ ግንቦት7 ህልሞን ሊፈታሎት ነው ሻቢያ ስር የተሸጎጠው?ኧረ ኧረ ግፍ ይፍሩ ሻቢያ ጠላታችን ነው እያሉ በሌላ በኩል ነፍጥ የያዘውን እንርዳ ይሉናል። ነፍጥ እዣለሁ የሚሉ ያሉት ኤርትራ ውስጥ እንደሆነ አጥተውት ነው?

 

ረ/ ሰለኢሳት እና ስለተወስኑ የነፃ ሚዲያ ጋዜጠኞች ያሉን ደግሞ “ ከሀገር ኮብልለው ከወጡ በኋላ የጉሮሮ አጥንት እየሆኑ ናቸው ያሉዋቸው ክንፉ አስፋ፣ ኤልያስ ክፍሌ ( እህቱም ሂሩት ክፍሌ ማንነቷ ለምናውቅ ውስጡን ለቄስ ማለቱ ይሻላል? ይህ ከእኔ የተጨመረ)፣ ደረጀ ሐብተወልድ ( ዶሮው ፍርድ ቤት ቀረበ)፣ፋሲል የኔዓለም የግንቦት7 አባል እንደሆነ እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ ታዲያ ይህ ሰው ነፃ ጋዜጤኛ የሚሆነው በየትኛው መለኪያ ነው? እና አበበ በለው የመሳሰሉት ሙያቸውን ሽክን አድርገው ወያኔ መደበቂያ እያሳጡ ያሉ እና እሳት የላሱ፤ እንደሻማ ደግመው ደጋግመው እየቀለጡ፣እየወደቁ፣እየተነሱ (የትኛው ጦር ሜዳ? የእኔ ጥያቄ ነው) ከእውነት ላይሸሹ ቃልኪዳናቸውን ሁሉ እንዳደሱ

ቀጥለዋል? ባንጻሩ ደግሞ ተስፋዬን የመሳሰሉ የእናት ጡት ነካሾች በሀገር የጀመሩትን ወኔ መስለባቸውን እውጭም ከውጡ በኋላ አባዚያቸው አለቀቃቸውም ብለውናል። እኔ ደግሞ “ ከዝንጀሮ ቆንጆ...” ብለዎት ምን ይሰማዎታል? ደምስ በለጠ የሚባሉ “ የጋዘጤኝነት ሙያ እና በውጭ ያሉ ሚዲያዎች አገልገሎት ሲገመገም” ከሚለው መጣጥፉ በመውሰድ እርሶ ያደነቋቸውን ጋዜጠኞች በነዚህ ሶስት መስፈርቶ ብከፍላቸው ቅር ይሠኙ ይሆን? ፍርዱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ልተወው።

 

1/ ወገንተኛ ጋዜጠኛ ( Advocacy Journalist)፡ እነዚህ ጋዜጤኞች አገልግሎታቸው ለተወሰነ ቡድን ወይም ስብስብ ብቻ ነው ይለናል። እውን እርሶ የገለጿቸው ጋዘኞች በዚህ ክፍል የሚመደቡ አይደሉም? ይህን ለሂሊናዎ እተወዋለሁ።

2/ ተለማማጭ ና ደብተራ ጋዜጤኛ ፡ እነዚህ ደግሞ እንደውሻ ጭራቸውን የሚቆሉ ያለቆቸውን ፍላጎት ብቻ የሚያራምዱ እንደ ደረጀ ሐብተወልድ እና እንደ ፋሲል የኔዓልም የመሳሰሉትን የኢሳት ጋዜጤኞችን ያካትትታል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ህዝብ ኤርትራን ውስጥ ትግል እንደማይሰራ እና እነ ኮሌኔል ታደሰ ፣ተስፋዬን እና የመሳሰሉትን ዕንቁ ኢትዮጵያዊ ያጠፋ ሻቢያ እንዴት ለኢትዮጵያ ቅን ያስባል በማለት ቢቃወምም ኢሳቶቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ዓይንና

ጆሮ በማለት ማፌዙን ምን ይሉታል? የነፃ ጋዜጤኞቾ፣እንደሻም ደገመው ደጋግመው ወድቀው እየተነሱከእውነት ላይሸሹ ቃል-ኪዳናቸውን ሁሉ እንዳደሱ ቀጥለዋል? ምን ማለቶ ነው ይህ ከአንድ ትልቅ ሰው እንዲህ ያለ ውሸት የሚጠበቅ ነው። “አይ ኢትዮጵያ የሞተለሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” መቼ ይሆን ከአንቺ የሚርቀው? እባክሽን እምዬ “ኢትዮጵያ እጅሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ!!!”

 

3/ ውጥንቅት ጋዜጤኛ ( Jazz Journalist): የሚባለው ደግሞ እውነትን ከሃሜት ጋር እየቀላቀለ በሌሎች ላይ የሚነዛ የአሉባለታ ጋዜጤኝነት ስለት ነው። አቶ ወልደሚካኤል የኢሳት ጋዜጤኛች በዚህስ አይካተቱም?

 

4/ በቀልተኛ ጋዜጤኛ ( Vendetta Journalist): የዚህ ዓይነት ጋዜጤኛ የራሱን ስሜት እና ፍላጎት ስለሚያስቀድም የህብረተሰብ ጥቅም ወይም የጋዜጤኝነትን ሙያ ግዴታን አይከተልም። ታዲያ የኢሳት ጋዜጤኞች በእርሶ ይመራሉ የሚባሉት እውን የህዝብን ጥቅም ያስከብራሉ? ሌሎችም አብዛኞች በነፃ ሚዲያ ስም የተቋቋሙ ባሌቤቶች በዚህ ይካተታሉ። ከማውቃቸው ሚዲያዎች የፕሮፌሴር መስፍንን እና የአቶ ጌታቸው ረዳ ብሎግን እና የጎልጉል ዌብ ሳይትን ሳላመሰግን

አላልፍም።

 

ተስፋዬ (ካቡጋ)፡ በቅድሚያ ቅንጣት ታክል ሰባዓዊነት ያልፈጠረበት ሰው እንዴት በጋዜጠኝነት ይመደባል። የዘረኝነት

በሽታ የተጸናወተው በሽተኛ በየትኛው መመዘኛ ጋዜጤኛ ሊባል ይችላል? ግንቦት7 እና ኢሳቶች ቆልላችሁት ነው ለዚህ እንዲበቃ ያደረጋችሁት። የአሜሪካ ድምጽም የግንቦት7 አጃቢ መሆናችሁ በላፈው በግንቦት7 ስብሰባ ከመገኘታችሁም በላይ አንዳርጋቸውን እንደጀግና አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ድረስ ሄዳችሁ ቃለ-መጠይቅ ማድረጋችሁ ምን ያህል እንደቀለላችሁ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ደንታ ቢስ መሆናችሁን ያሳየ ድርጊት ነው። ከዚህም በፊት አውሮፕላን ማሬፊያ ድረስ ሄዳችሁ ልከ እንደጀግና ስታደርጉት እሱም ለሥራ እንድሚቸኩል እና ጊዜ እንደሌለው የተናገረውን አሁን ከሶስት ዓመት በኋል ድራማውን ደግማችሁ ስትተውኑት የሰማው ህዝብ እንዴት እንዳቀለላችሁ ብታዩት!!! እውነቱን የምናውቅ ሰዎች ምን ያህል እንደአዘንባችሁ ብታውቁ ምን ያህል ማፈሪያዎች እንደሆናችሁ ትረዱ ነበር!!!

አቶ ወልደሚካኤል ሰሞኑን ከኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ በፍቃዱ የለቀቀው ወንድ ወሰን ገብረሂይወት በመልቀቂያው ላይ ምን ብሎ እንደጻፈ ላስታውስዎት።

ከዛሬ 2 አመት በፊት በጊዜያዊነት ተመርጠን እስካሁን በቆሁበት ግዜያት አንዳንድ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ምላቸውን በግልጽ በመናገርም ሆነ ኢሜል ወይም በድህረ ገጽ እንዲወጡ ያደረኳቸው ሃሳቦች ለድርጅቱም ለሐገራቸን ነፃ ሚዲያ መጠናከር ይጠቅማለ- በማለት ነበር። በጣም የሚገርመው አንድም የድርጅቱ ወይም የአምስተርዳም ሃላፊ ወይም የኮሚቴ አባል በዚህ ጉዳይ ላይ ሊያነጋግረኝ የቻለ ያለመኖሩ አስግርሞኛል። ባአለፈው በተደጋጋሚ በአምስተርዳም ለተደረገው ዝግጅት ህዝብን ጠርተን እናመስግን ከወጭ ቀሪ የተገኘውን ሂሳብ እናስረዳ አዲስ ምርጫም እናካሂድ ብዬ ብጎተጉትም ነገ ዛሬ እየተባለ ማካሄድ አልተቻለም፤ በጣም የሚግርመው በኢሳት የአውሮፓ ስብሰባም ሆነ በቅርቡ እንኳን ለኢሳት 3 አመት መታሰቢያ በተደረገው ወይይት ከሌላ ሀገር መስማቴ ምን ያህል ኢሳት በድርጅት የታጠረና በጥቂት ግለሰቦች ፈላጭ ቖራጭነት

መያዙን የተረዳሁበት ነወ።

 

ከኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ አባልነት ስለመልቀቅ ብሎ በጠየቀበት ወቅት በኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሆኘ በቆየሁበት 2ዓመታት ቆይታዬ ከውጭ ከምሰማው ይልቅ በጥቂት ቀርቤ የተረዳሁት ጭብጥ እና ለራሴም የህሊና ፍርድ ሊያሰጣኝ የሚችል መጠነኛ ግንዛቤ አግኝቻለሁ። በመሆኑም ወደፊት ሊስተካከሉ ይገባቸዋል የምላቸው ነጥቦች፡

ሀ/ ለአንድ ድርጅት ተጠሪነት እና የባለቤትነት ኃላፊነት ግንባር ቀደምተግባር ነው።ኢስት ከተመሰረተ ጀምሮ እስከአሁን ምላሽ ሊሰጥበት ያልቻለ የአደባባይ ሚስጥር ነው።እንዴኔ ግንዛቤ በሥራው ላይም እያሳደረ ያለውን ተጽዕእኖ የዚህ

ውጤት ይመስለኛል።

 

ለ/ በሙያ የተጠናከረ ኃላፊነት ሊወስድ የሚችል በግልጽ የሚታወቅ ኤዲቶሪያል ቦርድና የአስተዳደር ክፍል ያለመኖር። በየጊዜው ከውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች እና ከውጭ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያለመቻል።

 

ሐ/ ከዲያስፖራው ኢሳት ለሚቀርጻቸውን ያለአድሎ ሊተላለፍ የሚገባው ፕሮግራሞች አንዳንድ ጊዜ የመቆራረጥ ወይም የማይሆን ምክንያት ሰጥቶ ያለማቅረብ።

 

መ/ በእርምት መልክ የሚቀርብ ሃሳቦች ተቀብሎ ወዲያው ለማስተካከል ያለመቻልና ይቅርታ የመጠየቅን ባህል ለማዳበር ያለመቻል።

 

ሠ/ ኢሳት በአምስተርዳም፣በሆላንድ እና አጎራባች ሀገሮች ካሉ ኢትዮጵያን ማህበሮች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያለመፍጠር።

 

ረ/ በቋሚነት ድጋፍ ሊሰጡ የሚችሉ አባሎችን ሰፊ ጥረት አድርጎ ከማሰባሰብ ይልቅ በጊዜአዊ የገንዘብ ማሰባሰብያ ዝግጅቶች ላይ ሰፊ ጊዜ መስጠት።

 

ሰ/ ብዙው ኃላፊነት አንድ ሰው ደርቦ እንዲሰራ መደረጉ። ከኮሚቴ

አባልኔቴ ወቅት ከሰራናቸው ሥራዎች ውስጥ በተለይ በፋሲል የኔዓልምና ቤተሰቦቹ ላይ የሚደረገውን ውስጣዊ ደባ እና ሰባዊነት የጎደለው የማንገላታት ሴራ ለማስቆም ግልጽ ድጋፍ መስጠት ( እውን አቶ ወንደሰን የፋሲል ወንድሞች በወያኔ ስቃይ በልተዋል?ኧረ ተዉ እባካችሁ የፋሲል ወንድሞች ፌደራል ፖሊስ የነበረ፣ ወንድሙ እና እህቱ የቤአዴን አባል እንደነበሩ ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ነው እንደዚሁ የፋሲል ታናሽ ወንድም የቤአዴን የንግድ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ለብዙ ዓመታት የሰራ እና 2011 መጨረሻ በግል አለመስማማት የለቀቀ መሆኑ እየታወቀ እንዴት ስቃይ ደረሰባቸው ትለናለህ? ያሳዝናል ጊዜ ሁሉንም ያሳየናል) አቶ ወልደሚካኤል የእርሶ ኢሳት በታጋይነት ሰበብ የግል ጥቅም ማሳደድ ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን አያውቁትም?

 

ስለ ታማኝ ያሉንት ከልቦ ነው?

በልጃችን በታማኝ ላይ አትኩሮቱን ቢጥልም ታማኝ እንዲህ የዋዛ መስሎት ዘው ብሎ ለመግባት ቢጥርም ታማኝ መሰሪ

ቀበሮ ቀርቶ ለቀድሞ ጌቶችም ያልተበገረ፣ ግንባሩ የማይታጠፍ ቆፍጣና ኢትዮጵያዊ ነው። ታዲያ ለምን በአንዳርጋቸው ምትክ ኤርትራ ውስጥ አዋጊ እንዲሆን ለግንቦት7 ሃሳብ ያቅርቡ።በኢትዮጵያ ላይ ወለም ዘለም እርሱ ዘንድ የት አለና ይሉናል።ተስፋዬ በኢሳት ሲፈነጭ አንድ ቀን እንኳን ቅሬታ ያላቀርበ ሰው እውነት ይህን ያህል መካብ ነበረበት።ክንፉ አሰፋ እና መስፈን አማን ከታማኝ ጋር ያላቸውን ቀሬቤታ አያውቁትም ልበል? ተስፋዬ ካቡጋ ሁለቱን ብቻ እንዳታለለ ይነግሩናል? እውን ታማኝ ከተስፋዬ ጋር ግኑኙነት እንዳለው ሳያውቁ ቀርተው ነው? ታምኝን ከፍጡር በላይ ማድረጋችሁ ወዴት እንድወሰደው አልተረዱም?እስኪ በቅርቡ መልቀቂያ የጠየቀው ወንደሰን ገብረሂይወት በደብዳቤው የገለጸው እንዲህ ነበር ባአለፈው በተደጋጋሚ በአምስተርዳም ለተደረገው ዝግጅትህዝብን ጠርተን እናመስግን ከወጭ ቀሪ የተገኘውን ሂሳብ እናስረዳ አዲስ ምርጫም እናካሂድ ብዬ ብጎተጉትም ነገ ዛሪ እየተባለ ማካሄድ አልተቻለም። አዩት የእርሶ ጀግና? ካካካካካካካካካካካካ...

ከበደ ሚካኤል “ ትዕቢት እና ውርደት አካልና ጥላ ናቸው” ማለታቸው ይሄው በታማኝ እያየነው ነው።

 

ስለ ስዬ ያሉን ከምሮ ነው?

እጅግ እጅግ የገረመኝ ደግሞ የስዬ የኢትዮጵያ ፍቅር ነው “ዲንቄም ፍቅር”። በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቋል? ሌላው ተስፋዬ ካቡጋ መሆኑን ሳያዉቁ ቀርተው ነው ወይስ እያሾፉ ነው? እስኪ በጽሁፎ ላይ ያሰፈሩትን እንደገና ላስፍርሎት “ከህወሓት ክፍፍል በኋላ እንዳገኘሁት ኢንፎርሚሽን( ኢንፎርሜሽን ባሏት አንድ በጎጃም የሆነውን ልንገሮት ሰውዬው ካድሬ ቢጤ ነው ስብሰባ እተጠሩ በየጊዜው ገበሬው እንዴት እያለ ነው? ይባላሉ። እንደዚያ ሲባሉ አንዱ እጁን ያነሳል ምንድን ነው ሲባል “በእነሱ አነጋገር ፎርማሺን ይሏታል የዛን ቀን ፎርማሽን የምትለው የፈረንጆች ቃል ትጠፋው እና ሸውክ አለኝ ሲላቸው ሁሉም ተሰብሳቢ አንዴ ይስቅበታል ያም ገበሬ ነገሩ ስላናደደው ምን ያስቃችኋል ፎርማሽንም ብለው ሸውክም ብለው ያው ሽውክ ነው ምን ለውጥ አለው አለ ይባላል።”)

 

የእርሶም ኢንፎርሜስን ሸውክ ሸውክ ሸተተችኝ በነገራችን ላይ ይህ አህዛቡ ወይኔ አማርኛችንን ለማጥፋት የመለስን ለጋሲ ጂኒጃንካ ሆኗል አይደለም ቋንቋው? አልፈርድቦትም። ስዬ እና ሞቹ ሃየሎም ከመለስ ጋር ግጭት የጀመሩት ገና ከጠዋቱ እንድሆነ።ስዬ የደርግ( የኢትዮጵያ ተብሎ ቢጻፍ ይመረጣል የእኔ ነው) ወታደሮች እና ፖሊሶች በሙሉ እንዲባረሩ አይፈልግም። የኢትዮጵያ መከላከያ ከግራ ከቀኝ መሳ ለመሳ ሆኖ ተውጣጥቶ እንዲመሰረት ሃሳብ አቅርቦ እንደነበር ነግረውናል።” “ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ” እንደሚባለው አቶ ገብረመድህን አርአያ በቅርብ ባውጡት ” የህወሓት ፀር ኢትዮጵያዊ አካሄድ እና ዓላም በመቃወም የሂይወት መስዋዕትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?” በሚለው መጣጥፋቸው ስለ ስዬ የጻፉትን አላነበቡም? ጊዜ ካለዎት ያንብቡት ስለስዬ እውቀት ያገኛሉ።ይህቺን” በማር የተለወሰች መርዝ” ተውት አድርገው የአቶ ገብረመድህንን መጣጥፎችን ያንብቡ። ጥሩ ትምህርት ያገኛሉ!!!

ሌላው አማራው በበደኖ ሲጨፈጨፍ ስዬ በስልጣን ላይ እንደነበረ ረሱት እንዴ? ተስፋዬ ስዬን አምርሮ ይጠላዋል ይሉናል። ስዬ በአማራ ጭፍጨፋ በግንባር ቀድምትነት ተጠያቂ መሆኑን ዘነጉት? “ አህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም” ይባላል ስዬ እና ተስፋዬ ሁለቱም ፌሊሲዮን ካቡጋ መሆናቸውን ዘነጉ ልበል? ስዬ ማሞካሸት አህዛቡን ወያኔ ማሞካሸት መሆኑን አልተገነዘቡም።

 

በዘር ማጥፋቱ ወንጀል ሻቢያ፣ የኢትዮጵያ የሻቢያ መንግስት( ወያኔ)፣ኦነግ እና ተስፋዬ

ገብርአብ( ካቡጋ) በአንድነት መሆናቸውን ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለኝም።

 

መደምደሚያ

አቶ ወልደሚካኤ የተነሱበት ዋና ዓላማ ተስፋዬን እና ደጋፊዎችን ለህዝብ ማጋለጥ መስሎኝ ነበር። ነገርግን የተስፋዬን ሰላይነት እና አስጨፍጫፊነት ነግረውን ደጋፊዎችን መካብ ምን ማለት ነው? ለካ “ አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል” ስለሆኖቦት ዋናዎችን ግንቦት7ን፣ኢሳትን እና ሰዬን መካብ ብቻ ሆነ ቁምነገርዎን የእምቧይ ካብ አደረጉት። እንግዲህ በዚህ አባባሎች ልሰናበቶት፡

“ ቀበሮ ስህተቱ የእኔ ነው ብላ አታውቅም ሁልጊዜም የሚሳሳተው ወጥመዱ ነው። / ዊልያም ብሌክ “ጋዜጠኛ ሳይኖርህ መንግስት ከሚኖርህ፤ ጋዜጤኛ ኖሮህ መንግስት ባይኖርህ የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ ለአንዲት ቅጽበት እንኳን ሳላመነታ ሁለተኛውን እመርጣልሁ!!!” ነበር ያሉት ቶማስ ጃፈርሰን እኛስ ታዲያ መንግስትም ጋዜጤኛም እንዲሁም የተቃዋሚ መሪ እንኳን የሌለን ምን እንበል? ነገርግን በሀገር ቤት ትንታግ ወጣት ታጋዬች ተስፋችንን እያለመለሙ ናቸው እነሱን እግዚአብሔር እውቀቱን እና ጀግንነቱን ያድላቸው!!! ለባንዲራችን ክብር ደግሞ እንደ “ኮሪያ ጀግኖቻችንን” መስዋአትነት የሚከፍሉ መሪዎችን ይስጠን። ጊዮርጊስ በፈረሱ ይምራቸው። በሀገር ቤት ወያኔን እያርበደበደ ያለውን የሰላማዊ ትግሉን እንደገፍ።

እግዚአብሄር ለኢትዮጵያ በጎውን ቀን ያምጣላት

የሶማው ነኝ__