Tuesday, October 29, 2013

ድምፃችን ዛሬም ነገም የጎሹ ወልዴ ነው!

 
The Ethiopian Gallants in Eritrea before they fall by conspirators and mercenaries!
 Goshu The Lion Shaming the Ethiopian Enemies
Getachew Reda still stand against all odds!
 ድምፃችን ዛሬም ነገም የጎሹ ወልዴ ነው!
(ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) October 29/2013


 
የርዕሰ ጉዳዬ መነሻ የምመራበት ‘የፖቲካ መርሃ ግብር’ የለኝም፤ ለመንበረ ሥልጣን አደለሁም የምታገለው እያለ ውስጠ ስራው እንዳይታወቅበት የሚሸሸገው ግንቦት 7 ብሎ ራሱን የሚጠራ ‘ፌክ ቡድን’ (የክቡር ዶክተር ማንከልክሎት ሃይለስላሴ ቃል ልዋስ እና)  ከኤርትራው ሻዕቢያ ቡድን ጋር ያለው የቅጥረኛ ግንኙነትን የሚያትት ነው።
 ለነገሩ ኤርትራ ሄደም አልሄደም ‘ዲሞክራሲ’ የሚባል የማስገንጠያ ሽፋን ተጠቅሞ ‘ኦኖጎች እና መሳይ ተገንጣዮችን” በ40 የጐሰኞች ባንዴራ የተሰነጣጠቀቺው  አገራችንን ግብአተ መሬቷን ለማጠናቀቅ ቃል ገብቶ እየሰራበት ስለሆነ  አስመራ ሄደ አልሄደ ለኛ ትርጉም ባይሰጠንም፤ ባንዳዎችና አርበኞች ልዩነታቸውን ‘በአወድዮ በቪዲዮ’ ታሪክ ቀርጾ የተወልንን ምስክርነቱን እንድታደምጡ ግን አግባዛችሗለሁ። በዚህ እንነጋገራለን።
ከዚያ በፊት ግን በአማራዎች እና በክርስትያኑ ማሕበረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ የፈጸሙ እና ለወደፊቱም እንዲካሄድ የሚያበረታቱ እና የሚቀሰቅሱ ‘የፖለቲካ ወንጀለኞችን’ የጥላቻ ዘመቻ እያካሄዳችሁባቸው ነው እያለ “የሚወነጅለን” ከወደ ትግሬ ከመቀሌ እየጮኸብን ስላለው ወጣት አንድ ብየ ወደ ርዕሴ ልሻገር ነው።
ዛሬ፤ዛሬ “ባንዳነት” ነውር እንደሌለው እየተቆጠረ በወጣቱ ሕሊና ሰፊ ቦታ እያገኘ ነው። ብዙ የተበሻቀጠ የባንዳ ትምህርት አስተማሪ እና ተቀባይ ተማሪ እንደ ጉንዳን ተራብቷል። ከትግራይ እስከ ምስራቅ ከደቡብ እስከ ምዕራብ በግንጣላ ስራ እና በዘር ማጥፋት ተግባር የተሳተፉ የድርጀት መሪዎች እና ግለሰቦች በሕብረተሰቡ ዘንድ ምንም ዓይነት ቅዋሜ እንዳይደርሳቸው በ1983 ያየነው ዓይነት ጥብቅና ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ ከእኛው ጉያ ተከላካዮቻቸው ሆነው የሚያገለግሉ እያገኙ ነው።
በወያኔ ዘመን የተወለዱ ወይንም ህጻናት የነበሩ  ወጣቶች ዛሬ አድገው ባደጉበት የተመረዘ የፖለቲካ ትምህርት በመዋኘት ግንጠላም ሆነ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚያስተምሩ እንደ እነ ጃዋር መሐመድ የመሳሰሉት አደገኛ ‘የሰው አንስሳት’፤ ከትግራይ ከመቀሌ ‘አብርሃ ደስታ’ እያለ ራሱን የሚጠራ ወጣት እና የዓረና ድርጅት አባል ‘በፌስ ቡክ’ እና ዘሐበሻ በተባለው ድረገጽ የሚያሰራጨው የነቀዘ ቅስቀሳው ‘ለጃዋር መሐመድ’ (ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ሶማሊያ! ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ! ፈካሪ) በተደጋጋሚ ለሦስተኛ ጊዜ  ድጋፍ በመቆም “በጃዋር ላይ የጥላቻ ዘመቻ አራማጆች” በማለት ወንጅሎናል።

አንደ አሜባ እየተራቡ የባንዳ ደጋፊዎች እየሆኑ የመጡ  አገራዊነት በቅጡ ያልተረዳቸው በወያኔ ዘመን የተወለዱ ወይንም ህፃናት ሆነው ያደጉ እንደ አብርሃ ደስታ የመሳሰሉ “በግማሽ የተለወሱ ሊጦች” ታሪኩን በሚገባ ሳያጠኑ እራሳቸውን ተጃጅለው ሌላውን  በማጃጃል ‘በአገር የግዝገዛ’ ዘመቻው ላይ ተዋናይ እየሆኑ የመጡበት ወቅት ስለሆነ የአንድነት ሃይሉ፤ በተለይ ምሁራን እንዚህን ‘ጐደሎ ወጣቶች’ የግዝገዛው ሱታፌአቸውን  ከማስፋፋታቸው በፊት፡ እነኚህን የተጃጃሉ ወጣቶች መቋቋም የሚችል ኢትዮ ጵያዊ አዲስ ትውልድ አዘጋጅቶ  ማስተማር ለነገ የማይባል አጣዳፊ የቤት ስራችን ነው።


ወጠቱ አብርሃ ደስታ በጃዋር መሐመድ የሚመራው “ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ፤ እና “የክርስትያን አንገት የቆረጣ አብዮት” ቀስቀሳ እና የኦነግ ፕርንሲፕል ዘመቻ  ደጋፊ በመሆን በጃዋር ላይ የጥላቻ ዘመቻ እያካሄዳችሁበት ነው ብሎ የቀሰረብንን የውንጀላ ብዕሩ እና “ተበዳይ በድየሃለሁ ብሎ ለበዳይ ይቅርታ” ይጠይቅ ያለበትን ፍረደገምድል ጽሑፉን  ላመንበብ እዚህ ጫን ይበሉ።

ወደ ርዕሳችን እንግባ። ውይይታችን ስለ ኤርትራ ነው። በሰሜን አይጦች የተቦሮቦሮ የተደፈረው የአንበሶች  ቤት አንዲህ ‘በእርሱት እርሱት’ በግንቦት 7 ደላላዎች ተጃጅለን የምናልፈው አይሆንም።  ያልተቋጨው የኤርትራና ኢትዮጵያ ጉዳይ ሲነሳ ፤ ሻዕቢያ ወያኔን ወልዶ፤ወያኔ ደግሞ ግንቦት 7ን በአምሳያው ወልዶ ወያኔና ሻዕቢያ  ያላጠናቀቋቸው የመጨረሻ የቤት ስራዎቻቸው በግንቦት 7 በኩል አንዲፈጸም ጥረት እየተደረገ ነው። የማስፈፀሚያው ድብቅ መሳሪያው ደግሞ ‘ዲሞክራሲ’ነው። እነ ሂትለር እነ ሴዛር የማሰሰሉት አምባገነኖቸን ወደ ስልጣን ያመጣ “ዲሞክራሲ” ግንቦቴዎችም በዛው መሰለላል ለመረማመድ ዲሞክራሲን ተጠቅመው “በማጆሪቲ ካርድ” መፈክር አገር ለማፍረስ ተዘጋጅቷል። በዚህ ላይ በሰፊው እመለስበታለሁ (ሌላ ቀን)።
እስከእዚያው ድረስ በነሓሴ ወር 2005/2013 ‘ንሂሊስቶቹ’ “ዲሞክራሲ” አገር በማፍረስ የሚጫወተው ሚና እና የግንቦት 7 እና የኦኖግ ተዋናዮቹ በአገር ዕጣ የሚሸርቡበት የዲሞክራሲ ካርዳቸው ተጠቅመው እንዴት አንደሚያጠናቅቁት የሰጠሁት ቃለመጠይቅ  “You Tube”  ላይ ሰፍሯል፡ ያንን ያድምጡ።
ወዳጄ ደራሲ፤ገጣሚ እና አርበኛው ኢያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) “በቀዳዳ ጨረቃ” መጽሐፉ ላይ በገጽ 29 እንዲህ ይላል፡
“…ከጥቂት ደቂቃዎች በሗላ ስነሳ ውሻይቷም ቢራቢሮቹም ጠፍተው አገኘሁ። ላም የሚያክል ጥንቸል ፈገግ ብሎ-አራት ጥርሱን እያሳየኝ- ሲመለከተኝ አገኘሁት።
          “አንተ ማነህ? በብስጭት ድምፅ።”
          “መሪህ ነኝ አለኝ።
          “የማን መሪ?”
          “የቀጣይ ጉዞህ።”
          “ወዴት?”
          “ሳትደርስ፤ሳታየው ስሙ ምን ያደርግልሃል? “ተሳፈር” አለኝ። ላም የሚያክል ጥንቸል መሳፈር የለመድኩ ይመስል ፍንጥር ብየ በጀርባው ወጣሁ።ላም-ጥንቸሉ በመጋለብ ፍጥነት ጨመረና በረረ። ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ ሆኖ የማየው አጣሁ። ወደላይ ባንጋጥጥ ቀዳዳ ጨረቃ ይበልጥ ተበጣጥቃ አየሁ። ብዙም ሳንበር ላም-ጥንቸል ከወገቡ አሽቀንጥሮ ወደ ጨለማው ቁልቁል ወረወረኝ።” (ቀዳዳ ጨረቃ ደራሲ ሃማ ቱማ)
የመጪው ጊዜ መሪዎቻችን (ዕድሜ ከሰጠን) እነማን ናችሁ? ሲባሉ፤ የምትመሰርቱት የአገር አንድነትስ የስርዓቱ ስልት ምን ይመስላል፤ሲባሉ- እዛው ሳትደርሱ ምን ያደርጉላችሗል። ይሉናል። የሰሜን ሽፍቶች እጆቿን  በካቴና አስረው አፏን በጨርቅ አፍነው አዘናግተው የጠለፏት ‘ጨረቃዋ ኢትዮጵያ’ እየታመጸች ከምትገኝበት ዝግ ቤት ነፃ ለማውጣት ‘በሕግም ሆነ በጉልበት” በሩን መበርገድ የሚያስችል ባሕሪ የላቸውም። ብዙ የሚጠየቁ ጥያቄዎች አሉን።
ቢሸፋፍኑትም ለጥያቄዎቻችን ሳያስቡት ድንገት ቀጥተኛ መልስ አግኝተናል። የግንቦት 7 መሪዎች በብርሃኑ እና በዋና ጻሐፊያቸው ‘በአንዳርጋቸው ጽጌ’ እንዲሁም በሕዝብ ግንኙነት ክፍል ተጠሪያቸው ‘ኤፍሬም ማዴቦ’ አማካይነት ግልጽ የሆነ መልስ አግኝተናል። ሲያወላውሉ “እዛ ሳትደርሱ? ምን ያደርግላችሗል!” ሲሉን፤  ደፈር ሲሉ ደግሞ “አይቻልም!” ብለውናል። ሲነሽጣቸውም በማደንቀው ወዳጄ ጋዜጠኛ እና ደራሲ በመስፍን ማሞ  ተሰማ  መጽሐፍ የጆርጅ ኦርዌል “አኒማል ፋርም” ትርጉም “የእንስሳት አብዮት” ላይ የተተረከው ‘የሸንኮር አገዳ ተራራ’ ታሪክ ለሚጥማቸው ለአማኞቻቸው ጀሮ ያስደምጣሉ።
በመግቢያ ላይ እንደጠቀስኩት ለማንኛውም የችግራችን መሰረት ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በአክሱማዊያን እና በእነ ዘርዓ ያዕቆብ በእነ ዓምደ ጽዮን እና በተፈሪ የተጠበቀው የምድራችን ምድሪ ባሕሪ እና ተያያዥ ሁኔታ እኛኑን በእኩል በሚጠቅም መልኩ ካልተጠናቀቀ ኤርትራኖች የሶማሌ ዕጣ ፈንታ ይደርስባቸዋል። (እመኑኝ)። ጠላቶቻችን ሰብረው የሚገቡበት ቀዳዳ በር በኤርትራ ነው። ለዘመናት የተፈታተኑን ጠላቶቻችን ተሳክቶላቸው ‘በሩን’ ተቆጣጥረውታል። ኢትዮጵያም ያለ ባሕር በር ቀርታ በጠላቶች ተከብባ ትገኛለች።ዝም በሉ የሚሉን እና ጦርነት ናፋቂዎች እያሉ የሚያጃጅሉን ባንዳዎችን አንታግሳቸውም።
ይህ ያለ ህግ በሸር እና በአመጽ የተጠናቀቀ የኤርትራ ግንጣላ እና የኢትዮጵያ የባሕር እገዳ፤ አርበኞቿ ዛሬም ኢፍትሓዊው አመጽ ለመቀልበስ የተቻለንን  የፖለቲካ ክርክር በማድረግ ላይ አንገኛለን። በአንጻሩ ለጠላት የሚያጎበድዱ ደካማ ፍጡሮችም የጠላት ፕሮፓጋንዳ ሕጋዊ አድርገው በመቁጠር ከኤርትራኖቹ ወግነው ‘ኢትዮጵያን’ አመጸኛ በማድረግ ‘ጠላፊዎቿን’ ከወንጀላቸው ነፃ ለማድረግ ከኤርትራኖች በላይ ኤርትራኖች እየሆኑ ያሉትን በግንቦት 7 ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ባንዳ መሪዎቻቸው እና ተከታዮቻቸውን በጥብቅ እንኰንናለን።
ግንቦት 7 ምንም ተዋጊ ሠራዊት ሳይኖረው በባዶ ጉሮሮው ቢጐረናም፤ የተማመነው ተዋጊ ሃይል “ድምሒት” የተባለው ኢሳያስ አፈወርቂ ያሰለጠነው ቅጥረኛ የትግሬ ሚሊሻ ተዋጊውን ለመጥለፍ በማቀድ ነው። እዚህ ላይ የኤርትራን ውስጣዊ ጉዳይ በቋንቋ እጥረት ምክንያት አብዛኛዎቻችሁ ለማትከታተሉ ሁሉ፤ ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር አለ። ድምሒት የተባለው ሰራዊት ‘አርማው’ የአገራችን ሰንደቃላማ ሆኖ ከመሃሉ ‘የአክሱም ሃውልት’ ጨምሮበታል (ይህ ሕገ ወጥ ቡድን  ስልጣን ቢወጣ ወያኔ እንዳደረገው ሁሉ ያለ እዚሁ አርማ ሌላ አንዳይውለበለብ ሕግ ያወጣል ማለት ነው)። ድምሕት የተባለው ቡድን ግን ተዋጊዎቹ በበረሃ እና በውጊያ የተጎሳቆሉ ሳይሆኑ ቁንድላ ተሰርተው ጎፈሬ አበጥረው ወዛቸው ለምልሞ በሙዚቃ ባንድ ታጅበው የምታዩዋቸው የትግሬ እና ኤርትራ ድብልቅ ወጣቶች ዋነኛ ስራቸው ድምበር
የኤርትራን ድምበር መጠበቅ እና አስመራ ውስጥ ከዘመቻ የሚሸሹትን ወጣቶች እና በሻዕቢያ የሚፈለጉ ሰዎችን በየቤቱ እና ጎዳናው አድፍጠው በመሰማራት “ድብዳባ” እና “አፈና” የሚፈጽሙ /መርሲናሪ/ ታጣቂዎች አንደሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ከአንድ ውስጥ አዋቂ ሰው ያገኘሁትን መረጃ አስነብቤአችሁ እንደ ነበር ይታወሳል።
 
ዛሬም በድጋሚ ያንኑ ዘገባ ተንተርሶ ከወደ አስመራ ሽው የሚለው ወሬ እየተናፈሰ ነው። የኢሳያስ ቡድን ችግር ውስጥ ሲገባ ድምበርም ሆነ ከተማውን በመቆጣጠር ‘የሹት ትኪል’ (ነጻ እርምጃ) ሃላፊነት የሚሰጣቸው እነሱ እንደሆኑ እና፣ ድምበር ላይ ሰውን በማሻገር ገንዘብ የሚቀበሉም እነኚሁ መሆናቸው በሰፊው ይወራል።
ሰሞኑ አስመራ እና በመሳሰሉት ከተሞች “አሰሳ” እየተደረገ ነው።በዚህ ስራ የተሰማራውም ይህ ቅጥረኛ ቡድን ነው እያሉ ኤርትራኖቹ ይህንን ቡድን ይወነጅላሉ። በነዋሪዎቹ አጠራር  “ከምድላዬ” የሚል ቅጥያ ተሰጥቷቸዋል። “እንዳሻኝ” ይሏቸዋል። ‘አጋሜ’ እያልን አንዳላሳነስናቸው ሁሉ የግረም ብሎ የድምበሮቻችን እና ከተሞቻችን ጸጥታ አስከባሪዎች ሆነው የቤቶቻችን በሮች እያንኳኩ አፋችን ከድነን በፍርሃት ተውጠናል። እስከማለት ኤርትራኖች ምሬታቸው እየገለጹ እንደሆነ ለዚህ ጸሐፊ የተሰጠው መረጃ ያስረዳል።
ከወዲሁ የግንቦት7 ጸሓፊው የኢሳያስ ተክለሰውነት እያሞካሸ ለሕዝብ መስበክ የጀመረበት ዋናው ምስጢርም ፤ ድምሕት የተባለው ኤርትራ እና ትግሬ የደበላለቀ ተዋጊ ሃይል በኢሳያስ ትእዛዝ ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ እንዲሆነው በግንቦት 7 ቁጥጥር ስር አንዲውል በድምሕት ላይ እየተሸረበ ነው የሚሉ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። ኤርትራ በረሃ ውስጥ አለ የሚባለው “አርበኞች ግምባር” የግንቦት 7 ሴራ አስቀድሞ ስለገባው ከበትናቸው ጽጌ (አንዳርጋቸው ጽጌ) በግምቦት 7 እንዳይጠለፍ አስቀድሞ ስለተጠነቀቀ ነበር ‘ብርሃኑ ነጋ’ በግልጽ ኢሳትን ‘እንግዲህ ወዲህ ስለ አርበኞች ግምባር ህልውና በኤርትራ ውስጥ አለ ብሎ ኢሳት አያወራም” ብሎ ትዕዛዙን ለኢሳት ያስተላለፈለት።    

ኤርትራ እነዚህን ሁሉ እየሰባሰበ የሚረዳበት ምክንያት ኤርትራኖች የሚያሰጋቸው መጪው ሕጋዊ የጦርነት ዳመና “በኢትዮጵያ የአንድነት ሃይል ተዋጊዎች እና መሪዎች” እንዳይከፈትባቸው ስለሚሰጉ ነው። ዋናው ጉዳይ ግን ‘ድንገት አገራችን ሁከት ውስጥ ብትገባ’ የኢሳያስ የግል ወዳጅ የሆነው ጀኔራል ስብሓት ኤፍሬም የተባለው መልከ ጥፉ ዘረኛ “ፈንቅል” በተባለው የሻዕቢያ ወታደራዊ መጽሔት በሰጠው ቃለ መጠይቅ አንደገለጸው “በጐመራው ላይ እየነደዱ ያሉት እንጨቶች ስንት አንደሆነ በቁጥር እናውቃቸዋለን፡ እሳቱ ተቃጥሎ አመድ ለመሆን ጭልምል እያሉ ያሉት ጭራሮዎች፣ኢ ስንት እንደሆኑ እናውቃለን። ነድደው ለማለቅ የቀራቸው እነኚህ ጭራሮዎች የቀራቸው ጊዜ ጥቂት ነው፡ በእሳቱ ዙርያ ቆሞ እሳቱ ነድዶ እስኪያልቅ ድሰር እየቆሰቆሰ በቅረብ እየተቆጠራጠረው ያለው ሃይል ደግሞ እኛ ስለሆንን የተነጠቅነውን መሬትም መልሶ ለመንጠቅም ሆነ (ባድመ) በፖለቲካ ማዕበል እየተንገላታች ያለቺው ምሲኪኗ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እኛ ትዘረጋለች” ብሏል።
 
ትዕቢቱና ሴራው ስናገናዝብ አሁን ለሚረዳቸው ግነቦት 7 እና ኦነጐች ሶማሌዎች ኦጋዴኖች ሲዳማዎች፤ቤንሻንጉሎች….ለምን እንደሚራዳ የምትስቱት አይመስለኝም። ነድደው ያለቁ ትላልቆቹ ግንዶች ወደ ጭራሮነት ተለውጠው አመድ ሲሆኑ በነሱ ምትክ ለመተካት አንደሆነ አትስቱትም።

እራሱ እድሜ አይኖረውም እንጂ እቅዱ እነዚህን ቡድኖች አስከትሎ ከሗላ በመሆን የመቶ አመቱ የቤት ስራው የመጨረሻ ፍጻሜ ለማጣናቀቅ ነው። ሆኖም መጀመሪያ ማን አመድ አንደሚሆን የሚታይ  የማይቀር ትርኢት ቢሆንም ለጊዜው የኤርትራ ጉዳይ የተዳፈነ እሳት ቢሆንም የታመጽነው አመጽ ፍትሕ እሰኪያገኝ ድረስ ዘመናትም ይፍጅ “ጦርነቱ ይቀጥላል!!!!”። ይህ የኔ እምነት እና መመሪያየ ነው። “ጦርነት አትቀስቅሱ” ፤ “አንዴ የሆነ ሆኗል” ፤ “ስታተስ-ኮ”-ውን ተቀብልን  ሰላም አንፍጠር”  እያለ ያለው ክፍል፤ እራሱን ያጃጀለ ምሁሩ ክፍል ስለሆነ ከነ’ዚህ “ቆሻሻዎች” ጋር ላለመነካካት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋ።
   
ጠላቶቻችን እኛን አላሸነፉንም፤ እኛን ያሸነፉን የኛ የምንላቸው የቆሸሹ ወገኖቻችን ናቸው። የወቅቱ ቀዳሚ የውጊያችን ደግሞ በ1983 የተከሰተው “የክፍሌ ወዳጆ ሲንድሮም” (የጋሸ ቀለሙ ርዕስ ልዋስ እና) በሽታ አንደገና በድጋሚ አንዳይከሰት ሕዝባችንን ማስተማር ነው። ወጣቱ እኛን ማድመጥ አለበት። አሻፈረኝ ካለ፤ የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ወጣቱ እንጂ እኛ አልፈንባታል። ለራሳችሁ ስትሉ ኢትዮጵያን ጠብቁ። ካልሆነ በየጐጣችሁ ታፍጋችሁ ማንነታችሁ ይፋቃል። ሲገነጣጠል ተገንጣዩም፤አስገንጣዩም ችግር ውስጥ አብሮ ይዳክራል። ማንኛችሁም ነጻ አትሆኑም።ለኔ ሳይሆን ለራሳችሁ ስትሉ ታገሉ! እኔ የምኖረው እዚህ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ኢፈሲያነስ 6 ላይ ‘የምንታገለው ሰይጣንን እንኳ ቢሆንም ትግላችን እሱ ካሰማራቸው ጃንደረባዎቹ ጋር ነው።’ ይላል።  
እያናገረን ያለው ጥቃት ነው። እኛ ተጠቅተናል! እስካሁን ድረስ ለጉዳታችን ተጠያቂ ሆኖ በፍትሕ ፊት ቀርቦ የተጠየቀ የለም።ስለዚህም ጥቃት ፈጻሚዎቹ ዛሬም የወቅቱ ፖሊተካ መድረክ በአስመሳይ ምላሳቸው በመቆጣጠር ዳግም ወደ ቀረቺዋ ኢትዮጵያ ጠላቶቻችንን ለማስገባት የረቀቀ ሴራ እየሸረቡብን ነው።  
በኤርትራ ምድር ለዘመናት የከፈልንበት የደም ግብር አለ። አያቶቻችን እና ወላጆቻችን እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን አጥንታቸው በኤርትራ ባሕር እና በኤርትራ በረሃዎች ተረጭቷል/ተዘርቷል። በዚህ የማንንት ጥያቄ አርበኞቻችን የዘሩት አጥንት መልቀም ይኖርብናል። ያለ ምንም ሰቀቀን ኤርትራ በረሃ ውስጥ ሄደው በእነዛ አርበኞች አንጥንት ላይ እየተረማመዱባቸው ያሉት የግንቦት 7 መሪዎች የአርበኞቻችን አጥንት በማርከሳቸው በወንጀል ይጠየቃሉ።
ያልተሰማችሁ ብዙዎች ናችሁ። በሰሜን አካባቢ የተወለድን እና የነበርን የዓይን እና የጀሮ ምስክሮች እኮ ያለፈው ትንንቅ አሁንም ከሕሊናችን አልለቅ ስላለን ነው። አንዲያ ያለ ብርታት እና ትንንቅ ተደርጎ ከሗለችን ‘በሴራ’ ስንመታ አንዴት ነው በእኛ ላይ የምትፈርዱብን?
እስኪ ላንዳፍታ ወደ 1983 ግንቦት ወር ሕሊናችሁ መልሱት እና ለ22 ዓመት ተጉዛችሁ አሁን ወዳለንበት ፌርማታ/ማቆሚያ/ አተኩሩ። የደረሰብን ጥቃት ሊስቱ/ዝርዝሩ ስንት ገጽ ነው? ይህ ሁሉ ጥቃት ሲጫንብን የቆዳችን ውፍረቱ እና ቻይነቱ ለታዛቢ የሚገረም አይመስላችሁም። ጥቃታችን አንድንረሳ ተጃጅለን አንድንኖር እና ኢትዮጵያ በጠላቶች የተሸረበባት የባሕር ወደብ እገዳ ሕጋዊነት አንዳለው በማስመሰል ለኤርትራ ወንበዴዎች ዛሬም ጥብቅና የቆሙ ተቃዋሚዎች ስንመለከት አዲስ ውርደት ላይ ገብተናል። ለምን ዝም በሉ እንባላለን?!
ወታደሮች ፤ አርበኛ ሚሊሺያዎች እንዲሁም ሲቪል እና የመንግሥት ሰራተኞች በዛው ምድርና እና በሕር የገበሩት የሕይወት ግብር ያፈሰሱት ደም አንዴት ነው አታንሱት የምትሉን? የስድባቸው ክምር እኮ ድፍረቱ አንዴት አንዳገኙት ለኔ ይገርመኛል።እንዲያ ተበድለን አጥቂዎችችንን ነጻ እንዲያወጡን እኮ ነው እየሰበኩን ያሉት? ኢሳያስ ነጻ እንዲያወጣን የሚያምኑና የሚማጸኑ የግንቦት ሰዎች ‘በስቶክ ሆልም ሲንድሮም’ ልክፍት የተጠቁ ይመስሉኛል ። በሽታ ካልሆነ እንዲያ ላለ እጅግ ክፉ ጠላት እና አጥቂ አንዴት ጥብቅና ቀሞ መልካም ዝና ይሰጡታል?
ያለማፈር እና በተቃዋሚው ጐራ እየተለመደ እየመጣ ያለው የባንዳነት ባሕሪ አስገራሚ ክስተት ‘ጋሻ ቀለሙ’ የተባሉ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ጸሐፊ ከጥቂት አመታት በፊት ( ከ5 አመት በፊት) ያቀረቡት ቆየት ያለ ትችታቸውን ቀንጨብ አድርጌ ላቅርብላችሁ እና ባንዳነት ምን ያህል ተቀባይነት እያገኘ አንደሄደ እነሆ እንዲህ ይላሉ:-
 
“Politics should have been a game with rules and boundaries enforced by integrity, morality and truth. It is only the rational political argument that hits the target and accomplishes its goal not the irrational argument that can be pushed to get a result of false positive which crumbles down when it encountered the real truth.
We can’t reason with people who position themselves purposely to deceive us……..The method used to attract followers and attack opponents is beyond my imagination; you don’t hear or read in history books this kind of characters a few decades ago. The old way of showing and keeping your dignity by respecting your opponent is a thing of the past. So does not selling yourself to the highest bidder. Unlike our contemporary politicians in the old days treason was unthinkable, even if one or two in history has done it, they were outcastes and ashamed alienated themselves from the glaring eyes of society. But these days our politicians are advertising their treasonous acts through internet radios and their foot soldiers, no shame is involved anymore.
 They are not only treasonous and backstabbers themselves, they are teaching the next generation to do the same thing like they do, act like they act. Being sellout is not a shame it has to be glamorized adapted and followed.”  Gashe Kelemu ( Kifle Wodajo Syndrome)
ጸሐፊው ባንዳነት አዲስ ትግል ፈር ሆኖ ቀርቧል፤ ነው የሚሉን። ከአምስት አመት በፊት የነገሩን እኚህ ኢትዮጵያዊ ሃቅ  መሆኑን ዛሬ በግንቦት 7 እና አጫፋሪዎቻቸው ገሃድ ሆኖ ስለ ሻዕቢያው መሪ ሰብአዊነትና ስለ ኢትዮጵያ ተቆርቋሪነቱ ሳያፍሩ በሻዕቢያ ገንዘብ እርዳታ የሚደጐመው በኢሳት ቲቪ በኩል ቀርበው ሰፊ የባንዳነት ስራ ለሕዝባችን የሕሊና አጠባ አጋዥ እንዲሆን ቅስቀሳው ወደ ኢትዮጵያ ተላልፏል። ባንዳነት  ተቀባይነት እያገኘ፤ አገርን የመገዝገዙ “የክፍሌ ወዳጆ ሲንደሮም” ዘመቻ ሁለተኛው ዙር በግንቦት 7 መሪዎች ተጀምሯል።

ለዘመናት እስካሁንም ድረስ ጠላቶቻቸን የመረጡት  ይነተኛ የመጫወቻ ሜዳ “የኤርትራ ጉዳይነው”።ኤርትራ የማን ናት? የግንጣለው ሕጋዊነትስ ምን ያህል ሕጋዊነት አለው? ሁለት ወገኖች ያላቸው አቋም በስእለ ድምጽ አስደግፌ ላቅርብላችሁ እና ልደምድም።
 
Our heroes Professor Mesfin W/Mariam and Colo Dr. Goshu Wolde
Banda of the Year 2013 Efrem Madebo of Ginbot 7 propagating in defense of Eritrea and dehumanizing our Ethiopian heroes on behalf of Eritrean bandits calling them extremists

ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ እና ጠላት የሸረበብንን የመጥለፊያ መረብ አንቀበልም የሚለው አንድ አርበኛ ኢትዮጵያዊ እና በሌላ በኩል ደግሞ የጠላት ሴራ ሕጋዊነት ተቀብሎ በጠላት ቅስቀሳ የተሰማራው የመጥለፊያው መረብ ተቀበሉ የሚለን  አንድ ‘ኢትዮጵያዊ ባንዳ’ የሚታይ የሕሊና መራራቅ አድምጣችሁ መንፈሳቸውን መዝኑት እና እናት ኢትዮጵያ በዥጉርጉር አንጀቷ አንዴት ሁለት ዓይነት ልጆች ወልዳ አንዱ አጥቂዋ ሌላው ተከላካይዋ አንደሆነ ከዚህ በታች ያለው ‘ስእለ ድምፅ’  ከፍታችሁ አድምጡ። የተከበረው ኩሩ የኦሮሞው ተወላጅ ኢትዮጵያዊው “ዶክተር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ” ጠላት ባዘጋጀው መድረክ በመገኘት የወያኔ እና የሻዕቢያ ባንዳ ወኪሎችን እሳት በለበሰው አንደበተ ርቱእ ተጠቅሞ አንገታቸውን ያስደፋ፤ ፈረንጅን የገዛ ቋንቋው ተጠቅሞ አፉን አስከፍቶ አንዲያደንቀው ያደረገው ዓለም ያስደነቀ ተከራካሪ በዚህም ይሁን ባለፈው ትውልድ እንደ ጎሹ አይነት እናት ወልዳ አታውቅም። የጎሹ ቃል ዛሬም ሆነ ነገ ቃላችን ነው። አርበኛው ቀብራራው ኦሮሞ ኢትዮጵያዊው ጎሹ ወልዴ ማድነቅ አለባችሁ። የፈለገው ስህተት ቢኖረውም ጎሹን የሚያክል የባንዳን አንገት ያስደፋ ኢትዮጵያዊ በክብር ማህደር መመዝገብ አለበት።

ቀጥሎ የማቀርብላችሁ  የስዕለ ድምፅ ማሕደር በሁለት የተከፈለ ነው። አንደኛው ማሕደር የግንቦት 7 አመራር አባል የሆነ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለኤርትራ/ሻዕቢያ የቆመ ባንዳ ሲሆን፡ ሌላው ያው፤ ቀብራራው ኢትዮጵያዊው ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ነው።  ከሁለቱም ተከራካሪዎች ካንደበታቸው የሚወጣው የኢትዮጵያዊነት ትርጉም እና ስለ ኢትዮጵያ ዘብ መቆም ምንነት፤ ስለ ኤርትራ ጉዳይ እና የደረሰብን ሴራ እና ኢፍትሓዊነት የቀረበው ተቃራኒ ክርክር መዝናችሁ አርበኛችሁን ምረጡ። ስእለ ድምጽ 1 ስእለ ድምፅ 2 ከዚህ በታች ቀርባል።

Colonel Goshu Wolde - Historical Speech http://youtu.be/orod3OU3jfM

Ephrem Madebo of Ginbot 7 Ethiopian opposition movement at Eritrean  http://youtu.be/pW1mopFgf2k

አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getcahre@aol.com ድረገጽ እና ፌስ-ቡክ ለመጐብኘት ለምትፈልጉ (Ethiopian Semay)ጉጉል ብታደርጉ በቀላሉ ታገኙታላችሁ። በዚህ አጋጣሚ አዳዲስ መጽሐፍቶቼ ዳግም በጥቂት ቅጅ ታትሞ ለገበያ ቀርቧል። ጠይቁ። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ። (Ethiopian Semay)

 

 

 

No comments: