Monday, July 16, 2018

እውነቱን ለማወቅ ስቃይ እንድትናገር ፍቀዱላት ጌታቸው ረዳ (Ethiopian seamy)


እውነቱን ለማወቅ ስቃይ እንድትናገር ፍቀዱላት
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian seamy)
ከላይ ተጠቀምኩት ርዕስ የተናገረው ጥቁር አሜሪካዊ ፈላስፋው ከረነል ዌስት ነው። “you must let suffering speak if you want to hear the truth” (Professor Cornel West)። እየተናገርኩ ያለሁት ለናንተ ነው (ለኢትዮጵያውያን አፍቃሬ ሻዕቢያ)። አገራችን ከወያኔ ስርዓት ወደ አልታወቀ አቅጣጫ እየተጓዘች እንደሆነች እያየን ነው። አብይ አሕመድ እኔም እንደ እናንተው ሚሊዮኖች አድናቂው ነኝ። የምለይበትም የምደግፈውም ጎን አለኝ። ሰሞኑን ያለሉጓም በፍቅር ስሜት እያስጋለባችሁ እና እየስጨፈራችሁ ያለው ወደ ሻዕቢያነት የተለወጣችሁ ኢትዮጵያውያን አሽቃባጮች እናንተ እና ሻዕቢያ “ኢሱ” የምትሉት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ግን ‘መጽነታይ (ጨፍጫፊ) ብለው የሚጠሩት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ “ሁለት አገር አንድ ሕዝብ” መሆናችንን ሲገልጽላችሁ የስሜቱ ፈንጠዚያ ‘ሱሪያችሁን ባንገታችሁ ለማውጣት’ የቀራችሁ ነገር የለም።

መፈንጨት ጥሩ ነው። በስሜት ለጦዘ ማሕበረሰብ አይታወቀውም እንጂ አስገራሚ ያደረገው ግን የኤርትራ ባንዴራ ሳይሆን (የተባበሩት መንግስታት የሰጣቸው ጊዜያው ባንዴራቸው ሳይሆን) የሻዕቢያ ባንዴራ ማውለብለባቸሁ አልበቃ ብሎአችሁ  ሙታንታችሁን አላየነውም እንጂ ፤ ሎምቦጫችሁ እና ከንፈራችሁ በሻዕቢያ ባንዴራ  ቀለም አቅልማችሁ እንደ ገጣባ አህያ በደስታ እንጣጥ ስትሉ ማየት ከማዘኔ በላይ አስቃችሁኛል። እጅግ ያሳዘነኝ ግን በቴ/ቪዥን ሲተላለፍ ያየሁት ደረታቸው በኢትዮጵያ መዳሊያ እና በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ያሸበረቀ አንድ አዛውንት አርበኛ አባት ባጌጡበት አርበኛዊ ሽልማታቸው ላይ አንድ ወጣት የሻዕቢያን ባንዴራ ሊሰካላቸው ሲውረገረግ አይቼው ከሰቀጠጠኝ ትዕይንት አንዱ እና ቀዳሚዊ ይህ አሳዘኝ ክስተት ነበር።

 እንዲህ ያለ ቅብጠት ካሁን በፉት ትግሬዎች ከሻዕቢያ ጋር ሲቀብጡ አይተናቸዋል። ትግሬዎች “አማራ” ብለው የሚጠሩት ‘ደርግን’ (አብርሃ ደስታ አንዳረጋገጠው እና ብዙ ሰነዶች እንደሚያረጋግጡት) አሸንፈው ኢትዮጵያን አምበረከክናት ብለው  ከሻዕቢያ ጋር ሆነው የሚረግጧት ዓለም አልበቃ ብላቻቸው በየአሕጉራቱ እየዞሮ ፈረንጅ አገር ውስጥ ‘ከበሮ’ እየደለቁ ፤ ትግሬዎች የኤርትራን እናቶች ልዩ ማሕፀንነት እያወደሱ “ኤርትራን በቅኝ ግዛት የገዙ አማራዎች የወለደች የአማራ እናቶች ማሕጸን እያንኳስሱ” ሲፈነጥዙ ሰምተናቸው ‘ያልተገረዘው’ የጫካ ምላሳቸው የላ እራሳቸው በገዛ ጥርሳቸው እንደሚቆረጥሟት በተናገርን ልክ 7ኛው የጥጋብ አመታቸው ሲጨርሱ ዓለም አይቶት የማያውቀው አሰቃቂ ጦርነት ከፍተው እርስ በርስ ተላልቀው ሌላውን ኢትዮጵያዊ  የዕልቂታቸው ሰለባ አደረጉት።

 ያ እንዲያ አልፎ ዛሬ ደግሞ እናንተም የትግሬዎቹ ቦታ ተክታችሁ እንደ እግር ኳስ ‘ቲፎዞ” ሎምቦጫችሁ በሻዕቢያ የባንዴራ ቀለም ማቅለማችሁ ያስደምማል። ያስ ባልከፋ ነበር፡ ዋናው ጥያቄየ አብይ አሕመድ “ከኢሱ” ይዞላችሁ የሚመጣው “ፓኬጅ” ምን ይሆን? የሚል ነው ለኔ ያጓጓኝ ጥያቄ። መልስ ከናንተ እፈልጋለሁ።

ምክንያቴንም ልግለጽ። እኔ የምፈልገው ፍላጎቴ ባለፈው ሰሞን በግልጽ አብራርቻለሁ። የወደብ ጉዳይ በፍቅር በመደመር የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። እየተነጋገርን ያለነው ከሳሪ እና አትራፊ እየተደራደሩት ያለው ሉአላዊ ድርድር ምንድ ነው? የሚለው ጥያቄ በግልጽ እስካልነገሩን ድረስ እንዲሁ በፍቅር ስካር የምናልፈው አይደለም። እኔ እና መሰሎቼ የምንፈልገው አሳውቀናችኋል: እናንተ የምትፍልጉት ግን አታውቁትም (አልነገራችሀንም)። የተማራችሁት እና የምታውቁት እና የምትፈልጉት ነገር “ፍቅር እና መደመር” የሚሉ ቃላቶች ተምራችኋል። ያ አውቀነዋል። እነዚህ ነገሮች ለኢሳያስ አዲስ ክስተቶች አይደሉም።

አሁን አብይ እና ኢሳያስ እንደሚናገሩት፤ መለስ እና ኢሳያስ ይህንን ሲናገሩ ሰምተናቸዋል።በአማርኛ መመዝገቡ ትዝ አይለኝም እንጂ በትግርኛው “አሰር” ጋዜጣ የተመዘገበ ነው (ኢሳያስ የተናገረበት ቃለ መጠይቅ፤ ቅጁ ከኔው ጋር አለ)። የዱሮው እና የአሁን የግንኙነት ልዩነቱ፤ የዱሮዎቹ ትግሬ ለትግሬ ስለነበር ወደ መሃል አገር ወደ አዋሳ ወደ ….ወደ…. ከተሞች እየተዘዋወሩ ሕዝብን አላስጨፈሩም እንጂ ይህንኑ “የድምበር ትርጉም ወደ ሌለው ደራጃ ደርሰናል” የሚለው የኢሳያስ እና የአብይ ንግግር ድሮም መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ ደጋግመው ብለውታል።  አሁን ያለው ልዩነት ግንኙነቱ ትግሬ ያልሆነ ነገር ግን ትግርኛ መናገር የሚችል “ካሪዝማቲክ’ (ማራኪ) የሆነ የፍቅር ሰው አብይ አሕመድ የተባለ ኢትዮጵያዊ ‘አማርኛ መናገር አላውቅም’ እያለ እንደ ፈረንጅ ባስተረጓሚ ሲነጋር የነበረውን ኢሳያስን በአማርኛ እንዲናገር በታአምር እንድናደምጠው ካደረገ አስደናቂ መሪ ከሆነው ከአብይ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን በስፋት መጎብኘቱ ነው ልዩነቱ።

በሕይወቱ አድርጎት የማያውቀውን “አማርኛ” ለኢትጵያ ሕዝብ መናገሩ እጅግ ከሚያስገርሙት እና ለየት ካደረጉት ይህ ክስተት እንጂ ሌላው “የመደመር እና ሁለት አገር አንድ ሕዝብ” የሚሉት ንግግር ካሁን በፊት የተነገረ ነው። ከላይ እንደገለጽኩት እንዲያ ከተነገረ እና ከተጨፈረ በኋላ ግን የተከሰተው ጦርነት ለናንተ የሚነገር አይደለም። አሁን ከናንተው የምጠብቀው እየተጨፈረበት ያለው ፈንጠዚያ በምትኩ ምን እናገኝ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ስጠይቅ ብዙ ሰዎች በተለይ አሽቃባጨቹ አብይን እንደምጠላ አድርገው የሚያዩ ሊኖሩ ስለሚችሉ- ከዚህ ልጠፋችሁ ታቀቡ እና የምጠይቀውን ጥያቄ ብቻ መልስ እንደትሰጡኝ እጓጓለሁ።
  
ከላይ በመግቢያየ እንደገለጽኩት በዚህ ሰውየ ምክንያት ብዙ ሰዎች ስቃይ ተሸክመው ዛሬም አጭቀውት ይኖራሉ። ኢሳያስን መውቀስ በተቃዋሚ ጭምር የሚያስሰድብ፤ የሚያስደበድብ፤የሚያስሸማቅቅ ኖሮ ቆይቷል (ግንቦት 7 በተደባዳቢ ግብረሃይሎቹ እና በኢካዴፍ ፓልተኮቹ ኩል ዋናው ተጠቃሽ ነው)። እንደ እሚታወቀው የተቃዋሚ ሞዲያዎች እና የፓልቶክ መገናኛ ዘዴዎች በግንቦት 7 እና በኦነግ ደጋፊዎች ስለተመረዘ ሻዕቢያ አባሎች እኛን  ኢትዮጵያውያንን እንዲዘልፉ ሙሉ ነፃነት ተሰጥቶአቸው እንደነበር እና ዛሬም በባሰ መልኩ ኢሳያስን መንካት “ለወረበሎች ስድብ” ያጋልጣል።

ስለዚህ ኢሳያስን በዓለም ፍርድ ቤቶች ከስሰው ማስቀጣት ባይችሉም በሰራው ወንጀል የሚጮሁ ስላሉ ቢያንስ የኢሱአችሁ ባንዴራ በጉንጫችሁ መሸከም መብታችን ነው ብላችህ አንደነገራችሁን እኛም አክብረንላችል: ነገር ግን በኢሳያስ ጭካኔ የተጎዱ ወገኖቻችን ስቃያቸው እንዲጮሁበት መብታቸውን አትጋፉ። ስለዚህ በሁለቱ አገሮች እየተደረገ ያለው ግንኙነትም ሆነ ተበድለናል ብለው ስለ ኢሳያስ ግፍ የሚናገሩ ሰዎች ስቃያቸው እንዲጮህ መፍቀድ አለባችሁ። ምክንያቱም እውነቱን ለማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ ስቃይ እንድትጮኽ መፍቀድ አለባችሁ።

ኢሳያስ ጭራሽኑ ከሰይጣን ወደ መልኣክነት የለወጠው “የፍቅር መደመር” መዘዙ በናንተ ኢትዮጵያውያን ሳይሆን በሲኦል ላይ ያለው ብዙ ኤርትራዊ ጭራሽኑ ኢሳያስን መውቀስንም ሆነ መነከካት ፍጹም በባሰ መልኩ የሚያስኮንን ሆኖ መምጣቱ ሌላው የፍትሕ አስፈሪ ጥሰት እየሆነ በትግርኛ ተናጋሪ ሻዕቢያ አሽከሮች እያስደመጡን ያለው አስገራሚ አዲስ የተከሰተ ክስተት ነው። የሻዕቢያው መሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነ ባንዴራው ሕዝብን ሲያስጨፍር ማየት አዲስ ክስተት ቢሆንም ለኛ ይዞልን የሚመጣ ውል ምን እንደሚሆን ባናውቅም፤ ፍትሕ ለሚፈልጉ ኤርትራኖች ግን በከፋ መልኩ በሩ ሁሉ ዝግ እንደሚሆን ጥርጥ የለውም። ምክንያቱም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢሳያስ ከዲብሎሳዊነት ወጥቶ እንደ መልአካዊ መሪ ሆኖ በዓለም መስኮቶች እንዲታይ ማድረጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠያቂ ነው።ይህ ስራ ደግሞ አሜሪካኖች ጂቡቲ ባለው የአለም አቀፍ ሃያላን ሃይሎች የይዞታ መቀራመት ስላልተደሰቱ የቀይ ባሕር ኤርትራ ወደቦችን እና ቀጠናዎችን ብቸኛ ተቆጣጣሪ እንዲሆኑ ያቀናጁት አማራጭ ዕቀድ ስለሆነ በአብይ በኩል ኢሳያስ ጨዋታው ውስጥ እንዲገባ መደረጉ የታወቀ ነው። በዚህ ስካር ውስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈንድሻ እና ቀጤማ ነስናሽ ሆኖ እንዲቀርብ የተደረገ አስደናቂ ስልት ነው።

እዚህ ላይ ለመጥቀስ የምፈልገው፤ አብይ የሻዕቢያ ተከታዮችን ሲያስደስት የሻዕቢያ ተቃዋሚዎችን ግን አላነጋገረም፤ ምን እንዳሰበም የሚታወቅ ነገር የለም። የፍቅር መሪያችን አብይ የኤርትራ ተቃዋሚዎችን ከኢሳያስ ጋር  ሊያስታርቃቸው ይሆን  ወይስ የራሳቸው ጉዳይ ሊላቸው ነው? አብይ እዚህ ላይ ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲ ስራ መስራት አለበት። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ተገቢ የዲፐሎማሲ ውይይት ካላደረገላቸው ያላቸው ዕጣ ፈንታ ከህወሓት አክራሪ ክንፎች ጋር ተዳብለው/ተደምረው/ ትግራይ ውስጥ በመመሸግ በሁለቱ ሕዝብ እየተደረገ ያለው አዲስ የግንኙነት ክስተት እንዲሰናከል ያደርጋሉ።አክራሪው የወያኔዎች ክንፍ ይህንን አጥብቆ ለትግራይ ትግርኛ ቅዠቱ እና አብይን ለማሰናከል ሊጠቀምበት ይችላል።

ወያኔዎችም ይህንን ምከንያት ስሚፈልጉ ከፍተኛ ትኩረት መደረግ አለበት። ሆኖም ያ ከመሆኑ በፊት ከሁሉ በፊት የአብይ ግስጋሴ ‘የወያኔ ወንጀለኞች” ሊቆጣጠራቸው እና ወደ ፍትሕ ሊያደርስ የሚችልበት ዘዴ ወይንም ስልት አለው ወይ? የሚለው ጥያቄ መልስ ካላችሁ መልስ ስጡኝ። አብይ ደጋግሜ እንደገለጽኩት ህልውናው ለአደጋ ሳይጋለጥ በጠና እንዲኖር እፈልጋለሁ። ከጭለማ አውጥቶ ኢትዮጵያዊንትን ከፍ ያደረገ መሪ ስለሆነ ከነዚህ ከተሸነፉት የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች (ሰማያዊ የሚባል ሐፍረተ ቢስ ድርጅት እንኳ ድሮ ለድሮ ከአፍቃሬ ሻዕቢያ እና ኦነግ ጋር ከሆነው ኦከግንቦት 7 ጋር ጥምረት ፈጥሬአለሁ ብሎ “ኦነግ አሸባሪ አይደለም” ሲል አይገርማችሁም? ስንቱን የአማራ ሕብረተሰብ የፈጀው ድርጅት ኦነግን?!) እነዚህ ከሚመሩን አብይ ቢመራኝ በአስር ጣቴ እፈርማለሁ። ሆኖም አብይ ወዴት እየወሰደን ነው የሚለው ደግሞ ጣቴንም ቀስ በል እያልኩት ነው እና እናነትስ ምን ትላላችሁ?

 እዚህ ላይ አብይ እየተከተለ ያለው የፖፕሊስት (ሕዝብ መስማት የሚፈልገውን እየነካካ ማስጨፈር..) ፖሊሲ መውቀስ ብፈልግም አሁን አብይ ያለበት ሁኔታ ስመለከት ደግሞ የተሸከመው ጫና እጅግ ከባድ እና ከፖፕሊሰትነት ውጭ ባሁኑ ጊዜ እኛም ሆነ  እሱ ሊሰራቸውና ሊተገበሩ የሚፈልጋቸው እና የምንፈልጋቸው ‘መሰረታዊ’ የሆኑ ለውጦች ማድረግ እንደማይችል ስለማወቅ “ፖፕሊሰትነቱን’ አቁሞ መሰረታዊ “ቢፍ” የሚሉት እኛ “ሻኛ” (ብሩንዶ) የምንለው ለልብ እና ለዐይን የሚያጠግብ ነገር አሁን ስራ ብንለው ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ድቅን ይልብኛል።  በወንጀል የተጨማለቁ የሰው ደም በእጃቸው ላይ እየጮኸ ያለው ለ27 አመት አገር ሲያምሱ የነበሩት ባለስልጣናት አብይን ከብበው አማካሪዎች እና አጀንዳ ሰሪዎች ሆኖው እያየናቸው ነው። ይህ ከሆነ  ታዲያ ዶ/ር አብይ አሕመድ የሚያዋጣው የፖለቲካ እና ከብበውት ካሉት የቀን ጅቦች ቀለበት በጥሶ  ለመውጣት አማራጩ “ሽሩድነት” (ብልጥነት) ወይስ “መደመር መጦዝ እና መፋቀር”? የሚለው ጥያቄ ከባዱ እና ዋነኛው የአብይ ፈተና ነው።

ምክንያቱም አገሪቱ አሁንም አደጋ ላይ ነች። እባብ እና የሰው እግር ዘንዶ እና አርግብ ጅብ እና አህያ ነብር እና ፍየል አብረው ባንድ በረት ታሽገው እየተደነባበሩ እየተሻሹ እያየንበት ያለው የመንግሥት ስርኣት ነው። በጣም ሰትረንጅ/አዲስ ክሰተት/ እና ለመተቸት እጅ እግሩ የጠፋ ለመላምት የሚያስቸግር ክስተት ነው አሁን አያየን የለነው ታይቶ ተሰምቶ የሚታወቅ አይመስለኝም። በአይነቱ ልዩ የሆነ አስገራሚ ትርምስ።

ይህ ጥያቄ መፍትሔ ለማግኘት ለሱ ብቻ የተሰጠ ሳይሆን እያንዳንዳንዳችን መነጋገር እና መፍትሄ መለገስ ያለብን ጉዳይ ነው። እንደ እኔ እንደ እኔ ግን ምንም ያህል አስቸጋሪ ውጥረት ብንገኝም እውነት በዙፋንዋ ለማስቀመጥቅ የምትፈልጉ ሁሉ “ስቃይ እንደትጮህ ፈቀዱላት”። ያኔ “እውነታውን” ታውቁታላችሁ።

 ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


Tuesday, July 10, 2018

የባሕር በራችንን እስከ ዘላለሙ ሊያስነጥቀን የመጣው ሌላው መለስ ዜናዊ አብይ አሕመድ እንደሆነ አልጠራጠርም! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


የባሕር በራችንን እስከ ዘላለሙ ሊያስነጥቀን የመጣው ሌላው መለስ ዜናዊ አብይ አሕመድ እንደሆነ አልጠራጠርም!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
 
በርእሱ የተመለከተው ስሕተተኛ ሆኜ ብገኝ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ግን ቢሞት ኢሳያስ በስጦታ በመለስ ዜናዊ እና በትግሬዎች የተሰጠው ሕጋዊ የባሕር በራችንን እና ሕጋዊ ጥያቄያችንን በአብይ አሕመድ “ሸጋ ባሕሪ እና የመደመር ፍቅር’ ተማርኮ ኢሳያስ መልሶ ያለ ምንም ጦርነት ለአብይ ያስረክባል በሎ ማለት ቅዠት ነው። እኔን የሚያሳዝኑኝ በአብይ ፍቅር የስሜት ስካር ተጠምደው እጅ ተወርች የተያዙ ኢትዮጵያዊያን አሽቃባጮች ወዴት እንደሚሄዱ ሳያውቁ መጠን የሌለው ማሽቃበጣቸው እጅ እጅ የማለቱ ጉዳይ እንደ ምጥሚጣ ‘እየሰነጠፈኝ’ ነው’። አብይ ምን ሊያደርግ አስመራ ሄደ? የሚለው ጥያቄ እና በማንስ ድጋፍ? የሚለው ሌላው ጥያቄ ለመመለስ ግልጽ እና የሚከብድ አይደለም። 

አብይ አስመራ የሄደው ለምን ድነው? መልሱ ይሄው፡-

መለስ ዜናዊ እና ወያኔ ለኤርትራ በማዳላት የባሕር ወደባችን እና ድምበሮችን ለኤርትራ በሚጠቅም መልኩ የኤርትራ መገንጠል እና ባሕር ወደባችንን ያስነጠቀን ሕገ ወጡ ‘ሴራ’ ( ከአልጄሪሱ በፊት) እንዲሁም ‘10 አመት ቆይተው’ ሁለቱ ወረበሎች ሆን ብለው ሕዝብ ሳያውቀው ተጠያቂ የሌለው የድምበር ግጭት እና ጦርነት አስነስተው፤ ሲያበቁ ‘ትግሬዎች’ ተወረርን እርዱን ብለው መላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ሲለምኑት ፤ ሕዝቡም የሆዱን  በሆዱ አድርጎ ‘እሺ ብሎ’ ኢትዮጵያውያን ተዋጊ ሃይሎች ሻዕቢያን አባርረው ኢሳያስ እነጥቃቸዋለሁ ያላቸውን ድምበሮችን ወደ ባለቤቱ ወደ ትግራይ ሕዝብ ከስመለሱለት በ፤ ወራሪው ኢሳያስ ወደ አልጄሪስ መሄድ ሲገባው  እሱ ሳይሆን በተገላቢጦሽ በሚገርም እንቆቅልሽ ‘መለስ ዜናዊ’ የተባለው የትግሬዎች መሪ የነበረው እርኩስ ኤርትራዊው “እናት አገሩን ኤርትራን ለመጥቀም” ሲል (ባሕር የስዘጋብንን እንዳይበቃው) ወደ አልጄሪስ ሄዶ ሁሉም እሰጣለሁ ብሎ ኢሳያስ የጠየቃቸው አስፈላጊ ለም መሬቶችን እንዲያገኝ አስደረገለት።

ይህ ሴራ ደግሞ ባለፈው ወር በሰነድ ተገልጿል። የአሽቃባጮችን ሕሊና ለማስታወስ ያህል እዚህ እደግመዋለሁ። ይኼውም የአልጄሪስ ስምምነት ከመፈረሙ 4 ቀን በፊት (አሁን እደግመዋለሁ እንዲገባችሁ-“የአልጄሪስ ስምምነት ከመፈረሙ 4 ቀን በፊት”)  ትግሬዎች ነን የሚሉ አስመሳይ ትግሬዎች እነ መለስ እና አሽከሮቹ ሆን ብለው ከ 4 ቀን በፊት በፓርላማ እንዲጸድቅ ያደረጉትን ሴራ እውን ለማድረግ እና ሕጋዊ ለማድረግ ወደ አልጄሪስ ሄደው ሕግን በመተላለፍ ብሔራዊ ወንጀል ፈጽመው እዛውም በፌርማቸው ላመረጋገጥ ወደ አልጄሪስ ሄዱ። (የትግራይ ሕዝብም ምንም አላለም፤ አልተቃወመም ሰላማዊ ሰልፍ አላደረግም፤አንገዛም አላለም)።

ይህ ብሔራዊ የወንጀል ሰነድ ተደብቆ ቆይቶ ይፋ የሆነውም በጸሓፊው እና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር ስዩም ተሾመ አማካይነት ወንጀሉ የተፈጸመበት ቀን ከነ ፌርማው እና ቀን ማሕትም የፓርላማ ውሳኔ በማስረጃ ሰነዱን አስነብቦናል። በጥቂቱ እነሆ እንዲህ ይላል፤ በድረገጼም በመጠኑ ጠቅሼው ነበር፡-

"}
የአልጄርስ ስምምነት በቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የኤርትራው ፕረዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፊርማ የፀደቀው ታህሳስ 03/1993 ዓ.ም (እ.አ.አ. 12th December, 2000) መሆኑን ከላይ ካለው የስምምነቱ ሰነድ መገንዘብ ይቻላል (ጸሓፊው በማስረጃ የተደገፈ ሰነድ ለጥፎት ስለነበር ነው- ከላይ እያለ ያለው)። ይሁን እንጂ፣ የአልጄርስ ስምምነትን በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የታወጀው ህዳር 29/1993 ዓ.ም (እ.አ.አ. 8th December, 2000) ነው። በመሆኑም የሰላም ስምምነቱ አልጄርስ ላይ ከመፈረሙ አራት (4) ቀናት በፊት የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፅድቆት ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል። የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 55(4) ምክር ቤቱ “የህግ አስፈፃሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም-አቀፍ ስምምነቶች ያፀድቃል”

ይህ ሕገ ወጥ ብሔራዊ ወንጀል የአልጄርስ ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በምክር ቤቱ ፀድቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታውጇል። አይደለም እንዴ? ስለዚህ በሴራ የተከናወነ ድርጊት ስለሆነ ሕጋዊ አይደለም። ሆኖም አሁን አገሪቱ እየመራ ያለው አብይ ይህ ወንጀል መፈጸሙ አያውቅም ማለት አይቻልም። ካላወቀም፤ እንኳን እሱ እኛም አውቀነው ሰነዱን አንብበናዋል። ስለዚህ እዛ አስመራ ድረስ የሄደበት ምክንያት ፓርላማ አባለቶችን የተናገራቸውን ‘እናንተ ፈጽሙት ያለችሁን ነው እየፈጸምን ያለነው’ ብሎ ነው ወደ አስመራ የሄደው።  ሲሄድ ደግሞ ስምምነቱ ሕገ ወጥ መሆኑን እያወቀ ነው። ሌላ ቀርቶ “ዓሰብም ለሻዕቢያ” ሲበረከት ብ ያላማከረ ሕገ ወጥ መሆኑን እራሱ በፓርላ ውስጥ ነግሮናል። ስለሆነም እንኳን የድምበሩ ስምምነት ቀርቶ “ዓሰብን መጠየቅ ነበረበት”። ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን አስመራ ሄዶ “ኢሳያስን ተጎጂ ነህ ብሎ ሰምምነቱን እውን ለማድረግ እና በእግረ መንገዱም ኤርትራኖችንም ሓዘኑን ለመግለጽ አስመራ ሄዶ “ፍቅር ሊሰብክ ሄደ”።

ለመሆኑ ብምን ሂሳብ ነው የአልጄሪሱን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ነው የሄደው የምትለን ልትሉ ትችሉ ይሆናል። መልሴም ከአብይ አንደበት ላስነብባችሁ (ፓርላማ ውስጥ የተናገረው ነው) እንዲህ ሲል፤
“ሰላም ስንፈልግ የሚያስከፍለው ዋጋ አለ ወይ? አዎ አለ። ሰላም በነፃ ከየት ይመጣል! የደምበር ኮሚሽን ሲወስን ለኛ የሰጠው አለ ፤ለነሱ የሰጠው አለ። እኛ እንደምንጠይቀው በዛ በኩል ያለው ሕዝብም ይጠይቃል ብየ አስባለሁ። እኛ ግን ለድርድር እና ለንግግር ‘ውሳኔውን ለመቀበል እና ለመሄድ መዘጋጀታችንን ማረጋገጣችን  የናንተን ውሳኔ የዘገየው ማስፈጸማችን  ብቻ ነው። ወስናችሁ አስፈጽሙ  ብላችል አስፈጻሚው የናንተን ስራ ካልሰራ መጠየቅ አለበት።” (ጠ/ሚ አብይ  አሕመድ” ሲል ፓርላማ ውስጥ አቁዋሙን በግልጽ ነግሮናል።

ስለዚህ የሄደበት ዋናው ዓላማ ‘ውሳኔውን ለመቀበል” ነው። ማለት ነው። ስለሆነም ኢሳያስ የሚፈልገው በማግኘቱ ፋሺስቱ ኢሳያስ ሆን ብሎ የማሃል አገር ሕዝብ የዋህ ገራገር እና በትንሹ ልቡ የሚለሰልስ መሆኑን ስለሚያውቅ “በለስ” ጋበዛቸው። ቁልቋል በሊታ እየተባልን በየፓልቶኩ ስንሰደብ የነበርነው ሁሉ ‘ወዲ አፎም’ ሆን ብሎ ጣፋጩን ቁልቋል ሲጋብዛቸው የፓርላማ ተጠሪ ሁላ “ምን እሚሉት ጉደኛ የፍቅር ፍሬ ነው” ብለው ‘ፈረንጅ ይመስል’ እየተገረሙ አንድ አልበቃ በሎአቸው ‘እየደጋገሙ’ ገመጡት! መልካም ምሳ!

ወደ ቁም ነገራችን እንግባ። አብይ የሄደበትም ከላይ በራሱ አንደበት እንደነገረን ‘አስፈጽሙ አላችሁን ሥራ አስፈጻሚው የናንተን ትዕዛዝ ይፈጽማል” ያለውን ነው ተግባራዊ ለማድረግ የሄደው።

ይህ ሁሉ ክንዋኔ በማን ድጋፍ ነው ቅጽበታዊ ክስተቶች ለማየት የበቃነው የሚለው ሁለተኛው ከላይ የጠቀስኩት ጥያቄ ለመመለስ፦ በአሜሪካኖች እና በአረቦች። ይሄው እና ድሮ ድሮ የተባበሩት መንግሥታት ሰውየ (አንቶንዮ) አዲስ አባባ ለመሄድ ሽር ጉድ እያለ ነው። ለምን? ኢትዮጵያ ባሕርዋን ለመጨረሻ እና ለዘላለሙ በክራይ እና በምጣኔ ሃብት ልውውጥ እንጂ በባለቤትነት እንደማታገኝ አብይ እና አሜሪካኖቹ (ከላ) ስለወሰኑት ያንን ለመመረቅ ነው አዲስ አበባ እየደ ያለው። ድሮ ለድሮ  እየተጣደፈም አብይ ለኢሳያስ እና ከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ አዛዦቹ የተጣለው ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲነሳለት (ኤርትራ እራስዋ ሳታመለት) “አብይ ልክ አንደ መለስ ዜናዊ ማዕቀቡ ተሎ ይነሳለት ብሎ እራሱ ደብዳቤ ጽፎ ለተባበሩት መንግሥታት አመለክቶለታል”። ታሪክ ሲደገም ማለት ይሄ ነው።  ጦርነት ቀስቃሹ ኢሳያስ በአሸናፊነት ለመውጣቱ ሌላው ምልክት ይኼ ነው። አስቂኞቹ እነ ግንቦት 7ትም ሲጮኹለት የነበረው ዘመቻ እውን ሆነ እያለ ዳግማዊ ድል እያሉ ስለ ኢሳያስ መቦረቅ ጀምረዋል። አፈር ይብላ እና ሰማያዊ የተባለው እርስ በርስ ሲፈነካከት እና ሲሰዳደብ የነበረው ድርጅት ደግሞ ከዚህ አስቂኝ ድርጅት ጋር (ግም ለግም) የጋር ግምባር ፈጥሯል ተብሏል። ወይ አገር!

ስለሆንም ኢሳያስ በአሸናፊነት ስለወጣ የኤርትራ እናቶች አበባ እና ዘምባባ ይዘው በትግርኛ እንዲህ ሲሉ ዘፍነውለታል።

“ወዲ ኣፎም መዓረየ

ተዓዊትካላ አምበኣረየ”   

( ወዲ አፎም ወለላ ማራችን አሸነፍካት አሉ) ይላል። ቀጥተኛ ትርጉም “ተዓዊትካላ” የሚለው የትግርኛ ትርጉም “ተሸናፈዋ” ሴት ስትሆን አሸናፊው “ወንድ ነው” በሴት እየተጠራች ያለቺው (ላ ፊደል) ‘ኢትዮጵያ” ነች በወንድ እየተጠራ ያለው ተዓዊትካ (ካ) ወንዱ ኢሳያስ (ወዲ አፎም) ማለት ነው። “ላ” ሲጨመር ተሸናፊ አለ። “ላ” ለሴት ገላጭ ሆኖ “ሉ” ለወንድ ተሸናፊ በገላጭነት የሚጻፉ ቃላቶች ናቸው። ይህ የዘፈን ስንኝ ለማወቅ ትንሽ የትግርኛ ቋንቋ ጥልቀት ችሎታ ያስፈልጋል። ስለዚህ “ወዲ አፎም ወለላ ማራችን አሸነፍካት አሉ” ሲሉ ዘፍነውለታል። ተሸናፊዋ እምየ ኢትዮጵያ ዛሬም በልጆቿ ደጋግማ እየተሸነፈች እየተደቆሰች ነች። ኢትዮጵያ ህይቴ በሙሉ የቻልኩትን ታገልኳቸው- ምን አባቴ ላርግሽ?! 

በጣም እኮ ግልጽ ነው፡

ውሳኔውን ለመቀበል እና ለመሄድ መዘጋጀታችንን ማረጋገጣችን  የናንተን ውሳኔ የዘገየው ማስፈጸማችን  ብቻ ነው። ወስናችሁ አስፈጽሙ  ብላችል አስፈጻሚው የናንተን ስራ ካልሰራ መጠየቅ አለበት።” በሚል ነው ኢሳያስ ያሸነፈበትን ሴራ ለማስፈጸም  “ወሳኔውን ለመቀበል” አስመራ ድረስ የሄደው።


አሁን አየር መንገድ ወደብ ንግድ ወዘተ…. እየተባለ ያለው ወደቡን በቋሚነት ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ እንዳይሰጥ “ሽፋን” እና “ማስረሻ” ፤ “ማጃጃያ” የተደረገ የኢምፔሪያሊስቶች ስልት እና ምክር ነው። ዛሬም ሴራው ቀጥሏል። መደመር ለምስራቅ አፍሪቃ የተሰጠ የኢምፔሪያሊስቶች አዲስ “ቺፕስ” ነው።  አለም የብር/የገዘብ/የክሬዲት የመገበያያ ስልት ኖቶችን አስቀርቶ በቺፕስ አንዲሆን ስራው እንደተጀመረ ታውቃላችሁ አይደለም? ቆዳህ ውስጥ በመርፌ የሚተከል “የኮምፒተር ቺፕስ” ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ የ14 አመት ወጣት አማራ ተተክሎላት ስቃይ ውስጥ እንደነበረች አንብበናል? አላነበባችሁም? በወዳጄ በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ የዘጋጀው ሰነድ “ወልቀይት.ካም” በተባለው ድረገጽ እና ሌሎች ድረገጾች ወጥቶ ነበር። ካላነባችሁት ጠይቁኝ እና ካለኝ ካልሆነ ደግሞ  አፈላልጌ እልክላችለሁ ። ስለዚህ የምስራቅ አፍሪካ መደመር ግልጽ የቤት ስራ ነው። አብይ የለበሰው አረንጓዴ ከናቲራ የአፍሪካ ካርታው ‘አናቱ ላይ’ ምን ስዕል እንዳለው እዩልኝ። መደመር ማለት ያ ነው።
በባድሜ ጉዳይ የስትራቴጂና የስልት ጥያቄዎች” (መለስ ዜናዊ የተዘጋጀ ሰነድ ‘ባለ 10 ገጽ’) ትዝ ይላችሗል? መለስ ምን ብሎ ነበር የጻፈው ጥቂቶቹን ላስታውሳችሁ፡

“ባድመ የመሬት ወይንም የክብር ጉዳይ አይደለችም” የሕግ የበላይነት የማረጋገጥ ጉዳይ ናት ትክክለኛ መንገድ ላይ ቆመን” (ገጽ 4)      

መሬታችን ነው ብለው ለሞቱ የሺዎቹ ኣእላፍ ሕይወት እና በዛው በ1000 ኪ.ሜ ድምበር የሚኖሩ ባለመሬቶቹ “መሬታችን’ ነው ብለው ሲዋደቁ ፤ቤተሶቦቻችን በኢሳያስ ወራሪ ወታደሮች ተደፍረናል፤ ብሎ ስለ ክብሩ እና መሬቱ የተዋደቀውን ሕዝብ እና ኗሪውን ነው “የመሬት ወይንም የክብር ጉዳይ አይደለም” እያለ ትግሬዎችን ሲያሞኝ የነበረው። ያ የሕግ የበላይነት እያለ ሲያታልል የነበረው ሕግ የሚለው ደግሞ ኢሳያስ እና መለስ አልጄሪስ ሄደው በደላሎቹ ዓረቦች እና ኢምፔሪያሊስቶች አስማሚነት የፈረሙበት ቀን እና ፌርማው የፀደቀበት ቀን  ታህሳስ 03/1993 ዓ.ም (እ.አ.አ. 12th December, 2000) ሲሆን
የአልጄርስ ስምምነትን ተብሎ  በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የታወጀው ደግሞ ህዳር 29/1993 ዓ.ም (እ.አ.አ. 8th December, 2000) ነው።  

አያችሁ ሕግ ማለት? ሻዕቢያ መለስ እና ስዪም መስፍን… የመሳሰሉ የሻዕቢያ  ቅጥረኞችን  አስሰርገው እንዴት አንደተጫወቱብን?

በሚገርም ሁኔታ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ሲያታልል እንዲህ ብሎ ነበር፦

 “ጥያቄአችን የሕግ እንጂ የመሬት ስላልነበረ ሻዕቢያ በሃል ካዳከምነው በላ ደግሞ አሻፈረኝ ያለውን ሕግ የበላይነት እሬት እሬት እያለው እንዲውጠው  አስገድደነዋል” ( መለስ ዜናዊ ገጽ 4) አያችሁ ወያኔዎች እንዴት ሲጫወቱብን እንደነበር?

በመቀጠል እንዲህ ይላል፤

“የመጣ ቢመጣ  መሬታችንን አሳልፈን አንሰጥም የሚለው ፀረ ሕዝብም ነው” (መለስ ዜናው ገጽ 7)።

በዚህ ቅስቀሳ የተነሳ ብዙ ጅሎችና የመለስ አሽቃባጭ ምሁራን ጭምር ያንን ፕሮፓጋንዳ ተቀብለው “ሕግ ሕግ” እያሉ አሁን ወደ አለው “ሕግ አልባ” እና ሻዕቢያን በአሸናፊነት ያጎናጸፈውን ክስተት አድርሰውናል። ዛሬም ወደባችን ሕጋዊ እና ክርክራችን መሰረት ያለው ስለሆነ በሕግ ካልሆነም በሃይል ወደባችንን እናስመልሳለን የምንል ሁሉ ዛሬ በአብይ “የመደመር ፍቅር” ሰክረው እና ተጃጅለው እየተወላገዱ ከእንግዲህ ወዲህ “ጦርነት እና የጦርነት ወሬ ሁሉ በመደመር ፍቅር ተሽሯል

እና

“ተዘወሪ አመኪና ተዘወሪ

አስመራን ሽዋን ኮይኑ መዛወሪ”
ተብሏል
 እና

አየር መንገዳችን ጀምሯል ፤ምፅዋ ‘ጉርጉሱም’ እንድናዋኝ ስለተፈቀደልን “ጦርነት ናፋቂዎች” አፋችሁ ዝጉ እያሉን ነው።

 አሽቃባች ሁሉ- ወደዳችሁ ጠላችሁ ጦርነት የሰው ልጆች መፈጠሪያ እና ሕግ አስከባሪ ስለሆነ አይጠፋም። ሕግ አላስከብርላችሁም ያለውን ክርክራችን ጦርነት እና ሃይል በግድ ያመጣዋል። ስለሆነም ቅዠት አቁማችሁ “መጃጃላችሁን አቁሙ”። ኢሳያስ “ዓሰብም ሆነ ኤርትራ በብር ማንኪያ ያጎረስን ሕግ ሳይሆን “ በሃይል” ነው ያጎረሰን” ፡ ብሎ ነግሮናል። ጌታቸው ረዳም “በሃይል የሄደ ባሃይል ይመጣል” ይላል የዘወትር ክርክሩ።

 አብይ አሕመድ “ጦርነት እና የጦርነት መንገድ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ተዘግቷል” በማለት እንደ መለስ ዜናዊ “በፍቅር ቅዠት’ ቢናገርም “የባሕር ወደባችን ሕጋዊ ባለቤቶች እስካላደረገን ድረስ”  *በምጣኔ ሃብት ልውውጥ* የሚባለው “የአዲሱ አለም” “የቺፕስ” መገበያያ እና “የሕዝቦች ድመራ” ስልታዊ ቁጥጥር ከመሆን አያልፍም። የዘላለማዊ ባርነታችንን የፈረሙብንን ሴረኞችን እንቃወማለን፡በሃይል እና በሴራ የተነጠቁት የባሕር በሮቻችንን ጉልበት እንደተወሰዱት ሁሉ በሃይል እና በመራራ ረዢም እልክ እናስመልሳለን

አብይ ካላደረገው ሌላ ነብይ ሌላው “አፄ ሠርፀ ድንግል”  ከኢትዮጵያ ሰማየ ሰማያት ወርዶ ‘የዘመናችን የባሕረ ነጋሽ ቱረኮችን’ ተዋግቶ ከማሃይማን ባንዳዎች እጅ ባሕሮቻችንን ያስለቅቃል። ሩጫው፤ ገራ ገርነቱ እና ፍጥነቱ ስመለከተው የባሕር በራችንን  እስከ  ዘላለሙ ሊያስነጥቀን የመጣው ሌላው መለስ ዜናዊ አብይ አሕመድ እንደሆነ አልጠራጠርም። ይህ ውሸት ሆኖ ከተገኘ ይፋው ይቅርታ እንደምጠይቀው ቃል እገባለሁ። ከአብይ ይልቅ  እኔን የጨነቀኝ በጊዜያዊ መደለያዎች እየተጃጃልክ ከገዳዩም ከጨፍጫፊውም ከቀጣፊውም ከገንጣዩም ከወንጀለኛውም፤ ከገራፊውም ሁሉ እየዶለትክ እና አብረህ እየዞርክ የምትደሰኩር “ፍቅር ፈቅር” እያልክ ‘ሕዝባችንን የምታጃጅል’ የኢትዮጵያ ምሁር ምን አባቴ እንደማደርግህ ጭንቅ ይለኛል። ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) getachre@aol.com

Sunday, July 8, 2018

አብይ ወደ አስመራ ሄዶ ለደረስው ጥፋት እና ግድያ በኢትዮጵያ ስም ለኤርትራኖች ሓዘኑን መግለጹ በኤርትራኖቹ ዓይን ጥፋተኞች አስደርጎናል! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


አብይ ወደ አስመራ ሄዶ ለደረስው ጥፋት እና ግድያ በኢትዮጵያ ስም ለኤርትራኖች ሓዘኑን መግለጹ በኤርትራኖቹ ዓይን ጥፋተኞች አስደርጎናል! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት በመከታተል እያቀረብከት ያለውን ወያኔ እና ትግሬዎች አንድ ናቸው አይደሉም? ትግሬዎች በዘመነ ወያኔ ተጠቃሚዎች ናቸው አይደሉም? ወያኔ አፓርታይድ ነው አይደለም? … የሚለው ክርክሬ ባለፈው ሰሞን ክፍል አንድ ገልጫለሁ። ሁለተኛው እየሰራሁ ባለሁበት ወቅት ነው ይህ ወቅታዊ ዜና ፊቴን እንዳዞር ያደረገኝ ስለዚህ በሚቀጥለው ሰሞን ይቀርባል ተከታተሉኝ።

አብይ አስመራ ሄዶ ሁለቱም ሕዝብ ኢትዮጵያ እና መረብ ምላሽ እንደልባቸው እንዲዘዋወሩ አደርጋለሁ ብሏል። እኔ የተሰማኝ “ተዘወሪ ማኪና ተዘወሪየ አስመራን ሽዋን ኮይኑ መዛወሪየ” የሚል ጥንት የቆየ የዘፈን አስታወሰኝ። ገጣሚና ዘፋኙ ታዋቂው ኤርትራዊው አብራሃም ሰጊድ ናቸው። ገናናው ሃይለስላሴ አስመራና አዲስ አባባ ባቆራኙት ዕለት ሕዝቡ እንደልቡ አስመራ አዲስ አባባ መዘዋወር በቻለበት ወቅት ደስታውን ለመግለጽ የተዘፈነ ዘፈን ነበር። ዛሬም ያንን እደግማለሁ እያለ ነው አብይ አህመድ።  ወደ “ሪል ዲል” (እውነታዊ ድርድር) ስንገባ ‘ግን ግን…..’ የምንለው ወደ ላ የምንመዘው “ግን… ግን...ጥርጣሬአዊ ካርዳችን” እንዳለ በቀረጢታችን አስቀምጠን ለዛሬ ግን “እሰየው” ብለናል። ፖለቲከኞች ነን እና ኣትጠርጥሩ’ አትበሉን። ያውም በኢሳያስ እና በወያኔ የተጎዳች አገር ይዘን።

ዛሬ አብይ ወደ አስመራ ስለ መሄዱ ነው የምንወያየው። ስለ አብይ ኣሕመድ መተቸት ቀርቶ ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ባንዴራው መተቸት በኢትዮጵያውያን ምሁራን እና ተራ ሰዎች የሚያስወቅስ እና የሚያስሰድብ ብሎም ገለል የሚያስደርግ እና በጠላትነት የሚያስፈርጅ ስለሆነ ዛሬ ዛሬ ተቺዎች ከመሰደብ እና ከመወቀስ እያሉ ብዕራቸውን ማስታገስ ጀምረዋል። ከአዲስ አባባ አንድ ታዋቂ ጸሐፊው አምሳሉ ገ/ኪዳን ብቻ ነው የተሰማውን ከመግለጽ ወደ ላ የማይለው እንጂ የተቀረነው መሸማቀቅ ይዘናል።

ከማይሸማቀቁት አንዱ “Yours Truly” እኔ ብቻ ነኝ እና የሚሰማኝን ከማለት አልተቆጠብኩም፤ የሚገድበኝም አንዳችም ሃይል የለም። ስለሆነም ስለ ኢሳያስና እና አብይ ጉዳይ አንስተን እንወያያለን። እውጭ አገር ያሉት የከሰሩት የተቃዋሚ ሚዲያዎች ጽሑፋችንን ሊያግዱት ቢሞክሩም አፍነው ሊያፍኑት ስለማይቻላቸው ለሕዝብ ይደርሳል። ጸሎቴ እነዚህ የውጭ ተቃዋሚ ሚዲያዎች (አክራሪዎቹም ሆኑ ቡድንተኞቹ ፓርቲዎቻቸም ጭምር) ወደ አገር አንዳይገቡ እና እዚህ እንደሚያደርጉት በለመዱት ቡዱናዊ ባሕሪያቸው አገራችንም እነደዚያ እንዳያበላሹት ብቻ ነው ጸሎት የማደርገው። 

አብይ በሚከተለው እጅግ መረን የለቀቀ ሰለማዊ ባሕሪው በፖለቲካው ሜዳ ላይ ‘ሪል ዲል’ ብለን በምንጠራው ድርድር ላይ ሊያደርሰን ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሁሌም ይጭርብኛል።  የተጀመረው የተስፋ ጭላንጭል ወደ እዚያው የሚያደርሰንን መንገድስ ‘ጅቦቹ’ እንዳይነጥቁን የመዝጊያ በሮችን የሚዘጉ እርምጃዎች ለመዝጋት እያፋጠናቸው ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ ሁሌም የሚረብሸኝ ሁኔታ ነው። ወያኔዎች ፋሺስቶች ስለሆኑ እና ተሎ አጅ መስጠት የማይፈልጉ፤ ያልሰለጠኑ “ያልለመዱ የበረሃ አራዊቶች” ስለሆኑ አገሪቷ ወደ ጠምንጃ ፍትግያ እንዳያስገብዋት የሁሌም ስጋቴ ስለሆነ አብይ ጋር ያለኝ ስጋት ይህ ነው። ስጋቴ ባጭር አገላለጽ “አገሪቷ የተረጋጋች አይደለችም” ለማለት ነው። ይህ ካልኩኝ ዘንድ አሁን ወደ አስመራ እንገስግስ።

አብይ ወደ አስመራ ሄዶ ከሃያ አመት በፊት ለደረስው ጥፋት ግድያ በኢትዮጵያውያን ስም ኤርትራውያኖችን ሓዘኑን ገልጿል። ይህ ምን ማለት ነው? ይቅርታ እየተየቀ ነው ማለት ነው። ተመሳሳይ እና ቀጥተኛም ባይሆን ዛሬም የወያኔ ታሪክ ደግሞታል፡ የሚያስብል ነው። ለምን? ይህ መልስ ለማግኘት ከመባዘኔ በፊት እንዲሕ ያለ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው “ሰላማዊ’ አገላለ እሳት እየተንቦገቦገ ባለበት የሁለቱ ፖለቲካ ግንኙነት ጥንቃቄ መደረግ ነበረበት።

ይህ እራሱ ቀጥተኛ ይቅርታ ነው አይደለም የሚለው ክፍት ሆኖ ለክርክር ብንተወውም፡ አብይ ያደርገዋል ብየ ባልልም በእርሱ ትዕዛዝ መሰረት ወደ አስመራ አብረውት የሚሄዱትን ይቅርታ እንዲጠይቁ  እንደሚያደርግ ጥርጣሬየን ወደ አስመራ ከመሄዱ በፊት ገልጫለሁ። ወቅቱም እነ የማነ አዲስ አባባ ገብተው ንግግር ሲያደርግለቸው አብይ ወደ አስመረራ ከመሄዱ በፊት ቀደም ብየ በጽሑፍ ይህንን ጥርጣሬዬን እውን እንደሚሆን ጽፌ ነበር። ይህን ስለ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ አስመልክቼ ስለ ጻፍኩት ትችት ተነተርሼ የጻፍኩት እውነተኛ ጥርጣሬየን በገለጽኩበት ወቅት ነበር። ይህንንም ዋሽተሃል እንዳትሉኝ ልጠቅስ እና ላስታውሳችሁ፡

ከጉብኝቱ የምንጠብቀው ግን ምናልባት መለስ ዜናዊ አማራ ያልሆኑትን ሰብስቦአስመራ እና ከረንድረስ ሄደው አማራ ለኤርትራ ሕዝብ ስቃይ ተጠያቂ ስለሆነ  የአማራ ሕዝብ ወክሎን ይቅርታ እንድንጠይቅ መጥተናል፡ ብለው እንዳሉት ቅጥረኞች ዛሬምአብይ ወደ አስመራሲሄድ አብረውት የሚሞሸሩት እነ ዳዊት /ጊዮርጊስ  አስመራ ሄደው ያንን ይደግሙ ይሆን? ወይንስ የቀድሞ ወታደር ይቅርታ እንድጠይቅ ልኮኛል ብሎለነፃነታችን፤ ላንድነታችን፤ ለፍትሕ እና ለዲሞክራሲ ላደረጋችሁልን ትብብርበወታደሩ ስም ይቅርታ ሊጠይቅ መጥቻለሁሊል  ይሆን ወይንስ ሌላ ያልሰማነው አሳዛኝ ልሳን ልንሰማ ይሆን?” (ወታደሮቹን ከድቶ ከሻዕቢያ ጋር የወገነው ዳዊት /ጊዮርጊስ ዛሬም ሳያፍር ለኢሳያስ ማሽቃበጡን ብሶበታል! (June 30/2018) ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን Ethiopian Semay) ብየ ነበር።

አሁን እናዝናለን የሚለው የአብይ አገላለጽ ለክርክር የሚቀርብ ቢሆንም እኔ የገለጽኩት ጥርጣሬየን እውን ሆኖ ይኼው ዛሬ አብይ በሌሎች ተላላኪዎች ሳይሆን በራሱ አንደበት እንዲህ ሲል ያልጠየቅነውን በስማችን ያላልነውን የሓዘን አቅራቢነት  እንዲህ ጠይቆአቸዋል።

“ የኤርትራ ሕዝብ ከሃያ አመት በፊት ባጋጠመው ግጭት ህይታቸውን ላጡ አካላቸው ለጎደለ ኤርትራውያን የተሰማኝን ጥልቅ ሓዘን ለቤተሶባቻቸው ማድረስ እፈልጋለሁ።”
ይኼ ምን ማለት ነው? ገዳዮቻቸው  እኛ ነን እና  ስለገደልናችው እና አካላታችሁ ስላጎደልናቸው ጥልቅ ሓዘኔን ለማድረስ እፈልጋለሁ፡ ማለት እንግዲህ አብይ አህመድ ለኤርትራኖች ያዘነበው የፍቅር ዝናብ ይህ እና ዋነኛው ሓላፊነት የጎደለው የሓዘን አድርሱልኝ መልእክት ነው። ይህ አባባል ለትችት የቀረበው በኢሳያስ በኩል ተመሳሳይ የሐዘን መግለጫ ቢቀርብ ኖሮ ለትችት አይቀርብም ነበር። ግን ባንድ በኩል የቀረበ ስለሆነ ኤርትራኖቹ በሚገርም ሁኔታ በሚከተለው ሁኔታ ‘መስከረም” በተባለው የሻዕብያ ታማኝ ድረገጽ ጋዜጣ አብይ እንዲህ ከለማለቱ በፊት አብይን አንዲህ ሲል ጠይቆ ነበር፦

Meskerem 07/08/2018 10:46:19 PM
As Eritrea welcomes the Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed, the honorable guest is called upon to apologize for the atrocities and crimes committed against the Eritrean people by the last three ruthless Ethiopian administrations…

እዚህ ለመዘርዘር ሰፊየሆነው መግለጫው ባጭሩ ይህ ድረገጽ እየነገረን ያለው፤ ኢትዮጵያውያኖች ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከፈለጉ ይህ የታሪክ አጋጣሚ የተገኘው የጉብኝት ዕድል ተጠቅሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር አብይ አሕመድ በሦስት የኢትዮጵያ ስርዓቶች በኤርትራ ሕዝብ ላይ የደረሰው እና የተፈጸመው የጭፍጨፋ ወንጀል (አትሮሲቲ) ይቅርታ መጠየቁ የኤርትራ እናቶች እና አባቶች ልብ አለሳልሶ ለዘላቂ ሰላም መፍትሄ ስለሚየስገኝ ይርታ እንዲጠይቅ እንጠይቃለን፡” በማለት አስቀድሞ አብይን ጠይቀውታል። ስለሆነ ይሆን ሓዘኑን ሊገልጽ ያነሳሳው እንዲህ ያሉ ጥያቄዎች አስቀድመው ቀርበውለት ስለነበር ይሆን? የሚል ጥያቄ ይጭራል። ሐዘኑን በመግለጹም ሌሎች ድረገጾች በዚሁ በተመሳሳይ “ቀጥተኛ” ይቅርታ እንደጠየቀ አድረገው ሓተታቸውን በሰፊው አስተጋብተውታል። ያውም እኮ ጦርነቱን የለኮሰው ኢሳያስ መሆኑን የድምበር ኮሚሽኑ ያረጋገጠው ሃቅ ሆኖ እያለ ነው።

ይህ እንዳይበቃ ደግሞ “ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አድርጎ ሹሞኛል”ብሎ እርፍ! ወይ ጉድ! ቀልደም ለካ ቦታ የለውም ሲባል የሰማነው ልክ ነው። ትንሽ ቆየት ብሎ ኢሳያስም ኢትዮጵያን እንዲስተዳድር ስለተፈቀደልኝ መሪያችሁ ነኝ ሊለን ይሆን። ጊዜ መስተዋቱ የሚባለው ይኼው ነው።  ዶናልድ ትራምፕ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኝየ ተሹሜአለሁ፤ ቢል በቀልድም ቢሆን ፕሮቶኮሉ ይፈቅድለታል? ያምርበታል?

ይህም ሆኖ ጉብኝቱ ደስ ይላል። ፋሺስቱ ኢሳያስ ባለፈው በአንድ ሕዝባዊ ንግግሩ የ60 አመትዋ ዕድሜ ያላት ኢትዮጵያ ብሎ በቆሸሸው አንደበቱ ያሳነሳት የገዛ አገሩ (አገራችንን) ያፈለቀቺው ሰላማዊው ሰው ዶ/ር አብይ አሕመድ አስመራ ከተማ ድረስ ሄዶ ሲጎበኘው ታፍኖ የነበረው ብዙ የኤርትራ ሕዝብ በደስታ እያቀፈ ሲሳለመው ማየት እጅግ ደስ ይላል። ሰንደቃላምችን ምንም እንኳ የወያኔ የሰይጣን ኮከብ ምልክት ያረፈባት ብትሆንም ‘በኢትዮጵያ ሰንደቃላማነትዋ’ በየአመቱ ኤርትራኖች የነፃነት (የባርነት) በዓላቸው ሲያከብሩ ሲጠየፍዋት፤ በእግራቸው ሲረግጧት እና ምራቃቸው ሲተፉባት የነበሩዋትን ሰንደቃላማችን ብትሆንም በክብር ሲያብለበልቡዋት ማየት ደስ የሚል ነው።

እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን፤ ሰንደቃላማ እንደትረገጥ ያዘዘው ፋሽስቱ ኢሳያስ እንደሆነ ካሁን በፊት ደጋግሜ በጽሑፎቼ ገልጬ እንደነበር ታስታውሳላችሁ። አሁን ግን በራሱ ትዕዛዝ መሰረት የረገጥዋትን ሰንደቃላማ በክብር አንዲያውለበልቡዋት ትዕዛዝ በማሳለፉ በክብር ሲያውለበልቡዋት አይተናል። መሪዎች ሕዝባቸው በፈለጉት መንገድ እንደ ወንዝ ውሃ መጠማዘዝ እንደሚችሉ ማስረጃ ነው። ለዚህ ነው መሪዎች ካልተለወጡ ሕዝብ ሊለወጥ አይችልም፤መጀመሪያ የመሪዎች ባሕሪ መለወጥ አለበት ስል የነበርኩት። ዋና ተዋናዮቹ መሪዎቹ ሳይለወጡ ሕዝብ ለሕዝብ እናገናኝ እያላችሁ ከንቱ አትድከሙ ስል የነበርኩት ለዚህ ነው። በሕዝብ ላይ ብዙም የሚተኮር ነገር ቢኖር በመሪዎች ላይ ነው።

ስለ እኔ ስሜት ለማወቅ ለምትፈልጉ ዜጎች እንድታውቁልኝ የምፈልገው  ግንኙነቱን መፍጠር አልቃወመውም፡ ግን “የጠላታችን ሻዕቢያ ባንዴራ ትናንትም፤ዛሬም ነገም ለወደፊቱም ብንሞት አናውለበልባትም”። የወያኔን ባንዴራ ለማውለብልብ እንደምጠየፈው ሁሉ የሻዕቢያ ባንዴራም ለኔ እኩል ናቸው እና አሽቃባጮች ይንን እወቁልኝ። ያ ብቻ አይደለም፡ አብይ አሕመድ ምጽዋ ሄዳችሁ መዋኘት ላማራችሁም ሄዳችሁ መዋኘት ትችላላችሁ ብሎ ቢናገርም እነ ጀኔራል ተሾመ እና እነ ሺዎቹ ስንት ሺ ኣእላፍ “እምየ ኢትዮጵያ” እያሉ ሰንደቃላማውን ለብሰው እራሳቸውን በጥይት እያጠፉ፤ በድን ሬሳቸው ወደ ባሕሩ እየዘለለ ቀዩ ደማቸው የምጽዋን የባሕር ባቀለመው ውሃ ውስጥ ሄጄ ኢሳያስ በሥልጣን ላይ እያለ እየዋኘሁ ደማቸውን መጠጣት የጀግኖችን ደም ማርከስ እንደማልፈቅድ ካሁኑኑ ስገልጽ የሻዕቢያ አሽቃባጮች የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን ሃቁን ስንነግራችሁ ከመራራው እውነታ ጋር ነው። ከወያኔ ጋር አብሮ ሲዘርፍ የነበረው ምድረ “ፔቲ ቦርዥዋው” ይኼኔ ምጽዋ ሄዶ ለመዋኘት ክንፎቹን እያኮበኮበ እንደሚገኝ እርግጠኛ ነኝ። ምድረ አቃጣሪ ከያኒም እፍ እፍ ፍቅሩን ከመጠን ያለፈ እያቀነቀነ የዘመዶቹ  አጥንት በተረጨበት ምድር ላይ ቆሞ በላያቸው ላይ እየጨፈረ ጭፈራው እልልታው ሰማይ ያደርሰዋል። ያዝማሪ ነገር!

ስለ አብይ አሕመድ አንድ ነገር ብየ ወደ ኢሳያስ እገባለሁ። በተለያዩ ውቅቶች እንደገለጽኩት አብይ አዋቂ፤ ጥሩ ሰው እና የዋህ ሰላማዊ ሰው ነው። በገራገርነቱም ወያኔዎች እና ተንኮለኞች እንዳይገድሉት ስጋቴን በገለጽኩ ሰሞን አብዮት አደባባይ (አዲስ አበባ ስታድዮም ?) ተገኝቶ ንግግር ሲያደርግ የተሞከረው አስነዋሪ ግድያ ስጋቴን ትክክል እንደነበር ማሳያ ነበር። ዛሬም ጠንካራ ጥንቃቄ እንዲደረግለት የተሻለ ነው። ምክንያቱም ጅቦቹ ዛሬም በዙርያው እያየናቸው ነው፤ ከፍተኛ  የወታደር አመራሮች፤ አማካሪዎቹ፤ አጃቢዎቹ፤አምባሳደሮቹ እነሱ ናቸው:: ስለሆነም በቀላሉ ለጥቃት የተጋለጠ ነው። እግዚሓር ይጠብቀው ከማለት ሌላ ‘አማራጭ ምክር’ የለም።

ዶ/ር አብይ አስመራ አየር ማረፊያ ከደረሰበት ጀምሮ እስከ መሃል ከተማዋ ድረስ ተሰልፎ የነበረው ሕዝብ በጭፈራ፤ በዕልልታ አልፎም እስኪደክመው ድረስ እየሳቡ ሲስሙት ማየት የሚያስታውሰን አንድ ነገር ቢኖር ጥንታዊው የመረብ ምላሽ ሕዝብ እንደ አምላክ ሲመለከታቸው እና ሲወዳቸው የነበሩትን የኢትዮጵያ ንገሠ ነገሥት መሪ የነበሩት ኤርትራን ሲጎበኙ የተቀበላቸው ቀዳማዊ ሃይለስላሴን ያስታውሰናል። ልዩ ማራኪ ባሕሪ ያለው አብይ አሕመድ ክርስትያኑ እና አስላሙ ኤርትራ ሕዝብ በሚገርም ሁኔታ በፍቅር ጥሎአቸዋል። ይህም ለኢትዮጵያቀ የተሰጣት አለፍ ብሎ የሚወርድላት ታአምራታዊ ስጦታዋ እና ክስተት መሆኑንም ተጠራጥረን አናውቅም። መለስን እና አባት ነብሱን አብሮ በአንድ ወር ወደ ሰማየ ሰማያት ድንገት ሲጠራቸው ያሳየን ተአምር፤ በዛው ፈንታ የተበደልነውን ያህል  “ኢትዮጵያ ወደ ፈጣሪዋ እጆችዋን ትዘረጋለች” የተባለው ሃቅ ሆኖ ይህ ታምር እንድናይ በቅተናል።

ስለ አብይ ይህ ካልኩ ስለ ፋሺስቱ ኢሳያስ አንድ ለበል። ከዚያ በፊት ግን ማወቅ ያለባችሁ ስለ ጉብኝቱ ስንነጋገር ተጠቃሚዎቹ ኤርትራኖች ዕልል ቢሉ ያምርባቸዋል። እኛ ግን የሰማነው ነገር ስለሌለ “በግን .. ግን” መቆየታችን የሚጠበቅ ነው። ምክንያቴን እገልጻለሁ።

እየሳቀ የሚገድል ጨካኙ እና ፋሺስቱን ኢሳያስ ስቆ የማያውቀው ልቡ እስኪፈነዳ ድረስ በአብይ ልዩ ባሕሪና ተዋዛይነት (ቀልደኛነት) እያሳቀ ሳያስበው ተመርኳል። የአብይ ያልተዘጋ የበር ልብ ተማርኮ ግባ ሲለው ሳያስበው እያንጨበጨበ ሲገባ እየተነዋል። ይህ ግን ምን ማለት ነው? አብይ ወደ አስመራ ሲመጣ ለዓለም እና ለሁለቱም ሕዝብ የሚገልጽ ፖሊሲ የሚከተለው የምጣኔ ሃብት፤ የፖለቲካ እና ማሕበራዊ መርሃ ግብር በጽሑፍ አዘጋጅቶ የመጣበትን ዓላማ እያነበበ ነግሮናል። በኢትዮጵያ በኩል የቀረበው ሰለማዊ መርሃ ግብር አውቀናል። ያላወቅነው ግን ያው የኢሳያስ ድብብቆሽ ባሕሪው በአጸፋው ኤርትራ ምትሰጥንን ወይንም የምትከተለው መርሃ ግብር አልገለጸልንም፤ ግልጽ አልሆነልንም።
 
በሚገርም ንቀት ወይንም ደደብነቱ ብቻ ሁኔታው በማናውቀው ምክንያት ‘ኢሳያስ’ የነገረን ነገር “ለጽሑፍ ንግግር ስላልተዘጋጀሁ እንዲሁ በቃሌ አንዳንድ ነገር ልብል’ ብሎ የራሱን እና የሕዝቡን ደስታ ብቻ ነበር የገለጸው።

ከዚህ አልፎ አብይ የወሰደው ምርጫ/እርምጃ ‘ቀላል የሚባል እንዳለሆነ’ እንጂ ኢሳያስ በበኩሉ ‘ቀላል የማይባል ምርጫ የወሰደበት መርሃ ግብር ግን አልነገረንም”። አብይ ሙሉውን መድረክ በአማርኛ እና ትግርኛ ኢትዮጵያ ልትተገብራቸው ያቀደቻቸው ውሳኔዎች አንድ ባንድ ሲገልጽ ኢሳያስ በሚከተለው የዘወትር ድብቅ ባሕሪው የተነሳ እንኳን በጽሑፍ በቃልም የወሰደበት የንግግር ርዝማኔ በደቂቃዎች ብቻ የተወሰኑ ነበሩ። ለምን?

ምክንያቱም አንደኛ ነገር ኢሳያስ በተቃዋሚዎቹ እና አሽከሮቹ በኩል ‘ተምበርካኪ’ ተብሎ እንዳይታይ ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ እራስዋ ለምና ለዕርቅ እንደመጣች እና አመራሩ (ኢሳያስ) በአሸናፊነት መወጣቱን ለማሳየት የወሰደው ድብቅ ተንኮል ነው። የትዕግስት ውጤቱ ይኼው ኢሳያስ አሳይቶናል እያሉ ኤርትራኖች በሰልፉ ላይ በተጠየቁበት ቃለ መጠይቅ ሲናገሩ ሰምተናል፤ (በትግርኛ)። የኢሳያስ ብዙ ያለመናገር እና ምን አንደሚሰጠን ያለመግለጹ ወይንም አብይ በተናገረው ላይ ዝርዝር ነጥቦች አንስቶ ያለመግለጹ የሚያሳየን “ክፋት እና አሸናፊነቱን” ለማሳየት የተጠቀመበት አጉል ተንኮሉ እና የዘወትር ባሕሪው ነው። ይህ የሳይኮሎጂ ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች የምታውቁት ነው ብየ እገምታለሁ።

እንኳን ለሃያ ምናምን አመት ተራርቆ የነበረ፤ በጦርነት እና በጥላቻ የተቋሰለ ሕዝብ ቀርቶ ‘ለሦስት ቀን’ የስራ ጉብኝት ላመድረግ የሱዳን፤ የካታር፤ የ….. አገር መሪዎች ለሚመጡ እንግዶች የሚያደርገው ንግግር በጽሑፍ የተዘጋጀ ንግግር ነው። እዚህ ደርሶ አብይ የሚያክል ትልቅ እንግዳ መምጣቱ እያወቀ “በጽሑፍ አልተዘጋጀሁም ነበር” ብሎ አጭር ንግግር ማድረጉ ግን ለአሽቃባጮች ግልጽ ባይሆንም ለኛ ግን ያው የተካነበት የተንኮል እና የትዕቢት ባሕሪው መሆኑን ለምናውቀው የአካባቢው ሰዎች ድብቅ አይደለም። አጉል ኩራቱ በምናውቀው ሰዎች እንጂ ባሽቃባጮች ለነሱ ትልቅ ደስታ እና ፈንጠዚያ ነው (የሚያውቁትም አይመስለኝም)። መሪያችን ያንተ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ነኝ ሲለው ኤርትራን ሴቶች “ወዲ አፎም…የ… እያሉ ነበር እያሞካሹ ሲዘፍኑለት የነበረው። የስነ ልቦና ተመራማሪዎች ካልሆኑ በስተቀር አሽቃባጮቹ (ኢትዮጵያውያን) ግን የኢሳያስ ስነ ልቦና አያውቁትም እና በፈንጠዚያ ሲያሞካሹት እና ባንዴራውንም ሲያውለበልቡለት አይተናል። አሁን ጥያቄው አብይ የሚሰጣቸው ነገሮች ነግሮአቸዋል፤ ኢሳየስ ግን ምን አንደሚሰጠን አስካሁን የነገረን ነገር የለም። ለወደፊቱ ሲገለጽልን የዚያ ሰው ይበለን እና “ሪል ዲሉ” እንቀበለዋለን አንቀበለውም የሚለውን ያኔ እናየዋለን።
ምን ጊዜም የናንተው ጌታቸው ረዳ ነኝ Ethiopian semay     Sunday, July 1, 2018

የዲሲ ግበረሃይል ዱርየዎች በአሜሪካ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


የዲሲ ግበረሃይል ዱርየዎች በአሜሪካ
ታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)This fellow is the DC Gibrehayl gangster
ዲሲ ግበረሃይል እየተባለ የሚጠራ የሆነ ተቃዋሚ ክፍል እንዳለ በተለያዩ ዜናዎች አደምጥ ነበር። ይህ ሃይል ማን እንዳደራጀው ማንስ እንደሚመራው የማውቀው ነገር ባይኖርም፤ በቪዲዮ እየተቀረጹ ከዋሺንግተን ዲሲ ሲተላለፉ የነበሩት በተለያዩ ዜናዎችና ወቅቶች ያየናቸው የማውቃቸው አንዳንድ ሰዎች አይቻለሁ። ባለፉት ጊዜያት በዚህ ግብረሃይል ስም ሚጠራ በዜና ያየሁት ሰው የኢሕአፓ ራዲዮ ተነጋሪ /አዘጋጅ የነበረ (አሁንም ያለ ይመስለኛል) ዮሃንስ የተባለ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት በተለያዩ ጊዜያት አይቸዋለሁ። አንዳንዶቹ ደግሞ የግንቦት 7 አባላት አሉበት ይባላል (በመልክ አላውቃቸውም)

ማንም ይሁን ማን ያደራጀው ይህ የዲሲ ግብረሃይል የተባለ (ይህ ትችት የማይመለከተው ሌላ ቡድን ከሌለ በቀር) ይህ ቡድን ባለፈው ሰሞን/ አብይ አሕመድን ወደ ዲሲ ለመጋበዝ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግተብሎ በዚህቡድን የተዘጋጀ ይመስለኛል” (ካልተሳሳትኩ) በተጠራው ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ / ፍስሐ እሸቱ የተባሉት ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከተቀመጡበት ወንበር ድረስ በመሄድሁለት ሰዎች ከጀርባ እና ከጎንሆነው (በስተጀርባ ጎን ቆሞ የነበረው ፀበኛ መልኩ አይታይም ሁለተኛው ከዶ/ ፍስሓ ወደ ግራ ተቀምጦ እጁን ከዶክተሩ አንገት በማጅራት በኩል አዙሮ በመጠጋት ሲያስጨንቃቸው የነበረው እጅግአግረሲቭ” (ፀበኛ) የሆነው መልኩ በደምብ ማየት የሚቻል ሞገደኛው ወጣት ዶክተሩን ከብበውበማገትእየሰደቡ የተረጋጋውን መንፈሳቸውን ሲያስጨነቁ ሲዘልፏቸው፤ሲያስፈራርዋቸው በቪዲዮ ተቀድቶ ለመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ የተላለፈው ከሕግ ውጭ የሆነ የሚያበሳጭ፤ የሚያሳዝን እና የሕግ ሞራል የሚፈታተን፤ አንጀት የሚበላ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊነታችንን የሚፈታተን አሳዛኝ ክስተት እንድናይ ተደርጓል።

 ይግረማችሁ ብሎ ይህ ሞገደኛ ወጣትየድፍረቱ እና የንቀቱ ብዛትይህ የዱርየነት ወንጀልእንደ ጀግንነት ቆጥሮትቪዲዮውን ያሰራጨው ደግሞ ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮው ውስጥ የሚታየው ከሞገደኞቹ አንዱ እና ዋነኛውሞገደኛውወጣት ነው።


ሁለቱን ቪዲዮዎች ተመልክቱዋቸው። የመጀመርያው ቪዲዮ ዶክተሩን ከብበው ሲያስጨንቁት የሚያሳይ ቪዲዮ ሲሆን ፤ሁለተኛው ቪዲዮ ደግሞ እራሱ ሞገደኛው ወጣት (ጋንጉ) ስለ ግብረሃይሉ መግለጫ እያብራራ የሚያሳይ ነው። በዛው ቪዲዮ ዶክተሩንበቁጥጥር ስር” (አብዳክት) በማድረግ ለምን እንዲያስጨንቅዋቸው እና እንዲያስፈራርዋቸው  ምክንያት ሲያብራራየዲሲ ግበረሀይል ሙሉ መግለጫበሚል በቪዲዮ ቀርጾ ሞገደኛው ወጣት ለረዢም ደቂቃዎች የሚያብራራበት ቪዲዮ ነው።

ሰበር ዜና የዲሲ ግብረ ሀይል / ፍሰሀን በቁጥጥር ስር አውሎ አናገራቸውከዶ/ ፍሰሀ ጋር ያለው ፀብ ምንድነው የዲሲ ግብረሀይ ሙሉ መግለጫ ያስረዳልእንዲህ ያለ ነውርነት የወያኔ ማጅራት መቺዎች ከፈጸሙት የባሰ ነው። ያውም በሰለጠነው ዓለም፤ ለሰላም ህይወት ለምኖ፤ “መንግሰቴን በሰላም አላኖር አለኝ ተብሎ ማመለክቻ አቅርቦ” እባካችሁ አስጠጉኝ ተብሎ አሜሪካኖችን ተማጽኖ፤ በስደተኛነት ተመዝግቦ እኮ ነው ይህ ሁሉ ሞገደኛነት ዲሲ ውስጥ እያን ያለነው።

 በፖለቲካ እያሳበቡ ዜጎችን የሚያስፈራሩ ፤ የሚደበድቡ የሚገድሉ የሚያሸብሩ ግለሰቦች ፖለቲካውን እየተንተራሱ ዜጎችን የሚያስፈራሩ እና የሚያስጨንቁ ሕግ እንዲጎበኛቸው ማድረግ ተገቢ መሆኑን ከመነጋገራችን በፊት እነኚህ መጎደኞች ዶክተሩን “በቁጥጥር ስር (አብዳክት) ለማድረግ ምክንያታቸው ሲገልጽ በቪዲዮው ላይ የተዘገበው ግልጽ ነው። “ለምንድ ነው አንተ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር እንዲፈታ ያልጠየቅከው…..” የሚል ነው። በጣም አስገራሚ ነው! አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ ድምጽ ስላለሰሙ ዶከተሩ በነዚህ ጋንጎች “ቊጥጥር ስር” እንዲውሉ ተደርጓል። ለተወሰነ ጊዜ አስረዋቸዋል ማለት ነው። ብዙ ሰዎች ይህ ሞገደኛ ሰውየ የግንቦት 7 ኣባል እና ዲሲ ውስጥ ካሁን በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎችን በማወክ የሚታወቅ ሆኖ ሌላም ጉድ ሰርቶ ሕግ ፊት እንደነበረ ይነገራል።

የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህ ወጣት አንገቱ ላይ ያንጠለጠለው የክርሰቶስ የሰላም መስቀል ነው። ያ ብቻ እንዳይመስላችሁ፤ የዘውድ መንግሥት ሥርዓት ማሕተም እና ምልክት የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በመስቀል ምልክት የተሸከመ አንበሳ መስቀል ምስል ያለበት የባሕል ልብስ የለበሰ ወጣት ነው። አንዲህ ያሉ የሰላም ምልክቶች ለብሰው ሰላማዊ ዜጎች በፖለቲካ እያሳበቡ ልክ እንደማጅራት መቺ በቀን ጸሓይ ሕዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ ውስጥ የፈለገው የፖለቲካ ልዩነት ዶክተሩ ቢይዙም “በቊጥጥር አሰረው/አግተው/ በአካል እና በመንፈስ ለጥቂት ጊዘያት አንዳይንቀሳቀሱ አስሮ ግራ እና ቀኝ ከለብበው ዜጋን ማገት ከፍተኛ የሕግ ጥሰት እና የሚያስጠይቅ ነው። ሕግ ቦታ ሰርቻለሁ። ሕጉን ስለማውቀው። ለመሆኑ የሕግ ባለሞያዎች ምን እያደረጋችሁ ነው? አያገባንም ልትሉ? ስራችሁ ስለማትሰሩ እኮ ነው ይህ ሁሉ የወያኔ  ገራፊ  ዘራፊና ሞገደኛ የነበረ ሁሉ እኛ ጋር እየኖረ እየናቀን ያለው።

እኔ ያበሳጨኝ አብዳክት (በቊጥጥር ስር ) ያደረጉዋቸው ሞገደኞቹን (ጋንጎችን) አይደለም ትኩረቴ፤ እኔ ቅር ያለኝ እነ ግርማ ሰይፉ የተባሉ እና የአዳራሹ አስተናጋጆች እና ለዜጎች ጸጥታ ሓላፊነት የወሰዱ አዘጋጆች ያሳዩት እጅግ አሳፋሪ  ትዕይንት ነው።

በቪዲዮው “ስክሪን ሻት” የተወሰደው ከታች እንደትመለከቱት ምስል የወያኔ ፓርላማ አባል ‘ግርማ ሰይፉ” ነው። ስለ ግርማ ልተች አይደለም; ስለ እሱ ሌላ ጊዜ መተቸት እችላለሁ። እዚህ ላይ የሚታየው ግርማ ሰይፉ እና ሌሎች ፖሊስ ጠርተው ሞገደኛውን ከማሳሰር ይልቅ (ሰለማዊ ተጋባዥ እንግዳ ሳያስበው በመጎደኞች ኣብዳክት (በቁጥጥር) በመደረጉ /ሰላማዊ ታዳሚ በሞገደኛ ወጣቶች ቁጥጥር ስር በመዋሉ) ሞገደኞችን ሲያሽሞነሙኑ ሲያባብሉት ይታያሉ።
Girma Seyfu and others comforting  the gang
አንድ ዜጋ በሞገደኞች ሲታገት ወደ ፖሊስ ማቅረብ ‘ስልክ ደውሎ’ ማስያዝ ፤ ቢያንስ ሞገደኛውን ከአዳራሹ ማስወገድ የአዘጋጆች እና የዜጎች ግዴታ አይደለም ወይ? ያውም እኮ “ለጠ/ሚ አብይ አሕመድ የሰላም የፍቅር መስተንግዶ ለማድረግ እየተከናወነ ባለበት የፍቅር (?) አዳረሽ ውስጥ እኮ ነው እኚህ ዜጋ በሕዝብ ፊት ‘በፓብሊክ’ በቪዲዮ እየተቀረጸ ሊታገቱ የቻሉት!

እንዲህ ያሉ ሞገደኞች በሕዝባዊ አዳራሾች ዜጎች ‘ማገት’ (አብዳክት) ማድረግ ከቻሉ ይህንን ስጋት በማየት ተጋባዦች መኪናቸው ውስጥ መሳርያ ይዘው በመምጣት አጋቾቻቸውን ጠብቀው ሲወጡ መግደል ሊጀመር ነው ማለት ነው። ያኔ ታጋቾቹ ግድያ ስለፈጸሙ ፖሊስ እንዲጠራ ይደረጋል። ሰው ሲገደል ፖሊስ መጥራት ሰው ሲታገት ግን ፖሊስ ከመጥራት ይልቅ ወይንም ሞገደኛውን አንቆ ከማስወጣት ይልቅ ‘አጋቾችን’ ማሽሞንመን፤ማባበል ፍጹም ከሞራልም ከሰብአዊነትም ከዜግነትም ከሃይማኖትም እጅግ የሚጣረስ ነው።

ዶክተር ፍስሃ እሸቱ በፖለቲካ መስመራቸው አልደግፋቸውም። ስለ እሳቸው አቁዋም ካሁን በፊት በምሬት ተቺቻቸዋለሁ። ሆኖም ሰብአዊ እና ዜግነታዊ ሰላመዊ እና አካላዊ መብታቸው በሞገደኞች ሲረበሽ ቆሜ የማይበት ስብእና የለኝም። ወገኖች ቪዲዮውን አይታችሁታል? ደጋግማችሁ እስቲ እዩት? የአዳራሹ “ፔቲ ቡርዣ” ታዳሚ ሁሉ ቁጭ ብሎ ይህንን “የማገት ትዕይንት” (አብዳክሽን) ተረጋግተው ተዝናንተው ተቀምጠው እያያ ‘ዶክተሩ በነዚህ ጋጠ ወጦች ሲጨነቁ ስድቡ ማስፈራሪያው ማገቱ ሁሉ ‘በትዕግስት’ ተቀብለው ሲጨነቁ’ አይቼ  ለጀመሪያ ጊዜ እምባየ በብስጭት አቅርሬለሁ። ሰው በብስጨት ተነሳስቶ ሰውን በሽጉጥ ጀሮ ግንዱን የሚያነድደው እኮ እንደዚህ ያለ ክብርን የሚዳፈር ጋጠ ወጥ ፍጡራን ሲተናኮሉ ነው።  እንዴት ዜጎች ይህንን ተመለክተው ጋጠወጦቹን ለሕግ አያቀርብም?    

ሞገዶኞቹ እንኳ “ሰበር ዜና ብለውታል” ተዳሚው እና መነኛ አዘጋጆቹ ግን እንደ ዜና ቀርቶ ምንም አንዳልተፈጸመ አልፈውታል። የሚገርመው ደግሞ የቪ ኦኤ ተብየው ሁለት ወይንም ሦስት ጋዜጠኞች እዛው ወስጥ ተቀምጠዋል። ጉድ እኮ ነው። ሞገደኛው እራሱ  የዲሲ ግብረ ሀይል / ፍሰሀን በቁጥጥር ስር አውሎ አናገራቸው” ብሎ ዜና ሲያሰራጭ ጋዜጠኞቹ ግን ጀሮ ዳባ ነበር የሉት። “አበዳክሽን” እኮ ነው! የዲሲ ግብረ ሀይል / ፍሰሀን በቁጥጥር ስር አውሎ አናገራቸው እኮ ነው ዜናው! እንዴት አንድ የሰው ልጅ ኢትዮጵያዊ ምሁር ቀርቶ  ድመት እና ውሻ ‘የእንሰሳዎች” ክብር በሚከበርበት አገር ውስጥ በሕዝብ ፊት በሞገደኞች ታግቶ ቁጥጥር ስር ሲውል፤  እንዲህ ያለ የክብር መዳፈር ሲገጥመው የአዳራሹ ሞገደኞች እና አዘጋጆች ፖሊስ ከመጥራት ይልቅ እያባባሉ ማሽሞንሞን ምን ይባላል? ውጭ አገር ያለው ፖለቲካ እና ተከታይ ወዴት እየተጓዘ ነው? በፖለቲካ ያልተስማማህን በአካል ማስፈራራት፤ መደብደብ፤ ማገት? ለምን?

የሚገርመው ደግሞ ሞገደኛው የሰላም የፍቅር ምልክት የሆነው የእየሱስ ክርስቶስ የክርስትያን መስቀል አንገቱ ላይ አንጥለጥሏል እኮ! ይህ ፖለቲካ አይደለም ፡ የማጅራት መቺ ባሕሪ ነው። ሰውን ማገት፤ በቁጥጥር ስር ማድረግ ይቅር የማይባል ነው።

ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com (ኢትዮጵያን ሰማይ)