ሰሞኑን ከተሰሙ አስገራሚ ንግግሮች
እና ዜናዎች
ኢትዮጵያን ሰማይ
ሰሞን የአማራ ራዲዮ ድምፅ ዋና
አዘጋጅ እና በላስቬገስ ዩኒቨርሲቲ መምህር የጋዜጠኛነት ሙያ አስተማሪ የነበረው የወንድማችን ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ድንገተኛ ሞት
መራራ ሓዘኑን ለቤተሰቡ እና ለሥራ ባልደረቦቹ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ የሓዘን መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። ለጋዜጠኛው መሞት ምክንያት እየተጣራ ቢሆንም አንዳንድ በሙያው
ስልጠና የወሰዱ ባለሞያዎች አስተያየት አሟሟቱ ብዙ ፍተሻ እንደሚያስፈልገው ለዚህ ድረገጽ አዘጋጅ ጥርጣሬአቸውን ገልጸዋል።
ወደ ሌሎቹ ዜናዎች ስንሻገር የሚከተሉት
ለጀሮ የሚስቡ አጫጭር ዜናዎችን እንመልከት።
የኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አገና
የኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አገና “ዕለታዊ”
በተባለው የቴ/ቪዢኑ ክፍለ ጊዜ በDec/24/2018 የሚከተለው “እስቱፒዲቲ” (የአማርኛ ቃል ፈልጌ ስላጣሁ ነው) አባባሉ እኔንም
ሆነ አብረውት በውይይቱ የተካፈሉ ባልደረቦቹ “ቅንድባቸውን” ያስቆመ አግራሞት የሚጭር አባባል እንዲህ ይላል፡-
“በመንግሥት በኩል መደረግ አለበት
ብየ የማምነው እኔ ማንም ድርጅት የተጋደለለትን ዓላማ ለኢትዮጵያ
ነው “ለሰፈሩ” ነው (ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለግንጠላ ነው…የሚለውን ጭምር- በዚህ ጸሐፊ ለማብራራት የተጨመረ ማብራሪያ) እንተወው ፤ ግን
ለምንም ይሁን ለምን “ለመብት፤ለነፃነት” ብለው ሲታገሉ ዕድሜአቸውን ሙሉ “በረሃ ውስጥ ለተንከራተቱ” በተለያዩ ትግል የቆዩ፤ እጅ
ላልሰጡ ሰዎች ተገቢውን ክብር የሚሰጥበት ቢኖር ብየ በግሌ አምናለሁ። የኦነግ መሪዎች ፥ የታንድ መሪዎች ፥ የኢሕአፓ መሪዎች ፥
የመኢሶን መሪዎች .. ፥ እንዲህ እያልን የቀድሞ ታጋዮች 70ዎቹ 80ዎቹ ዕድሜ ክልል ገብተው ከመከራ
ኑሮ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በምን ሁኔታ ነው የሚኖሩት? …እነዚህ ሰዎች ለአገራቸው አስተዋጽኦ ሲያደርጉ
የነበሩ ሰዎች ናቸው እና በመንግሥት በኩል እንዲህ ያለ ክፍተት ቢያይ ለኔ ጥሩ ይመስለኛል።” (ሲሳይ አገና ዕለታዊ ከተባለ የትንተና ክፍለ ጊዜ በDec/24/2018
ከተናገረው ያደመጥኩት የተወሰደ)።
እንዲህ ያለ በኮሚዩኒዝም፤ በናዚፊኬሽን
እና በፋሺዝም ርዕዮት አስጠምቀው የኢትዮጵያን ባሕል፥ ቋንቋ፥ ሃይማኖት፥ መተሳሰብን
እና ታሪክ “አመድ ዱቀት አድርገው” ኢትዮጵያን አንደ ባዕድ የቅኝ ገዢ ስለው/አስተምረው፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ በነዚህ በተጠቀሱት
ርዕዮት አስጠምቀው ፥ አታልለው ፥ ዋሽተው ፥ አሳስተው ፥
አስተምረው ፥ ሕዝባችን እርስ በርሱ እንዲባላ አድርገው ፥
በጠቅላላ ለዚህ ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረጉን በአገራዊ
ክሕደት እና በወንጀል ተግባር በሕግ ሊጠየቁ የሚገባ ሰዎች ናቸው ብሎ ወደ ሕግ እንዲቀርቡ ከመስበክ ይልቅ ከነዚህ መሪዎች
ውስጥ በዘር ማጥፋት የሚጠየቁ ነብሰ ገዳዮች እና በአገር ክሕደት ሊጠየቁ የሚገባቸውን ሰዎች “ክብር እንዲያገኙ” ስለ “ኑሮአቸው
ሲጨነቅ” የሰሙት እጅግ አስገራሚ ስብከቱን ያደመጡት ባልደረቦችም ገርሞአቸው “መልሰው እንዴት?! ብለው ይጠይቀውታል።
ገርሞአቸው ሲጠይቁት የባሰውኑ ሓሳቡን
አጠናክሮ እንዲህ ሲል መልሶላቸዋል፦
”ዓላማቸው “ለአገር ይሁን ለመንደር”
አንድ በጎ ነገራቸው ምንድነው ፤ በሕዝብ ላይ ‘የመብት የነፃነት” የሚደርሰው መከራ አንቀበልም ብለው የግል ምቾትም ቢሆን እነዚህ
ሰዎች ከሌላውም (ደርግም) ከቲ ፒ ኤል ኤፍም ሥልጣን ተደራድረው የኖሩ አይደሉም……..” ሲል ከአፈርኩ አይመልስኝ በሚል “ገታራ
መልስ” ይመስላል “ለሕዝብ የቆሙ የነፃነት እና የመብት ተሟጋቾች ስለነበሩ እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ተከራክሯል።
ባልደረቦቹም በዚህ ሊወጥሩት ይሁን አይሁን ባላውቅም መልስ ሊሰጡ ሲሉ የውይይቱ ክ/ጊዜ ስላለቀ በዚህ ቆመ።
እነ ሲሳይ አገና እንዲህ ያለ ስብከት
እየሰበኩ ኦነጎችን እና ወዘተ ….ለኢትዮጵያ ሕዝብ “የነፃነትና የመብት ታጋዮች” ነበሩ ብለው ሲያስተምሩ የፍትሕ ጉዳይ እንዳይነሳ
፥ ቦታ ላይሰጠው በአገራችን ሉኣላዊ ነፃነት እና በሕዝብ እና በግለሰብ ህይወት ላይ ሰቆቃ
እና የዘር ማጥፋት የፈጸሙ ሲሳይ የጠቀሳቸው ለድርጅት መሪዎች ኑሮ
ሲጨነቅ ማድመጥ “ፍትሕ” በኢትዮጵያ ለምን እየተረገጠ እንደመጣ ወይንም ለወደፊቱ ፍትሕ መብት የሚባል ከሕግ አንጻር
ቦታ እና ከነጭራሹ የፍትሕ ማስከበር ጠቀሜታ ቦታ እንደማይኖረው የዚህ ጋዜጠኛ ስብከት አመላካች ነው ብየ እከራከራለሁ።
የድርጅት መሪዎች ተጠያቂነት እንዳይኖር
‘ልሂቃን/ኢሊቶች/ እና ጋዜጠኞች ብዙዎቹ በቀጥታም በተዘዋዋሪም አስበውም ይሁን ሳያስቡት ሽፋን በመስጠት ሚና እንደነበራቸው ለ27
አመት ስሟገትብት የነበረ ጉዳይ መሆኑን አንባቢዎቼ የምታስታውሱት ጉዳይ ነው። ይህ ባህሪ ዛሬም ይህንኑ እየተደገመ ነው።
አስገራሚ፡የሚያደርገው ደግሞ ሲሳይ
አገና ለዘላቂ ኑሮአቸው ይታሰብበት ሲል ለመንግሥት ቢማጸንም ሲሳይ ከመማጸኑ በፊት አብይ አሕመድ ለነዚህ ድርጅት መሪዎች በግብር
ከፋዩ የተሰበሰበውን የድሃ ሕዝብ ገንዘብ “ለሆቴል፥ ለምግብ ለመጓጓዣ ወጪ እና የተመቻቸ
ጽ/ቤት” ከፍቶላቸውም ቢሆን ፡እዛው አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው “ኢትዮጵያን ለማፍረስም ሆነ በሰው መግደል ፥ በዘረፋ እና በዘር ማጥፋት እየተሰማራ ያለው የጥላቻ ቁንጮ እና የብጥብጥ ድርጅት የሆነው “የኦነግን ሠራዊትን” እራሳችሁ
ተከላከሉ” ወዘተ…..እያልኩ ትዕዛዝ አስተላልፌላቸዋለሁ” እያለ የጥላቻ መሪው ዳውድ ኢብሳ ትጥቅ ሳይፈታ “በሚገደለው ሕዝብ
ገንዘብ” እንዲቀለብ የተደላደለ የጥላቻ ስነ ልብ እንዲያገኝ የሲሳይ አገና አወዳሹ “አብይ አሕመድ” የሚጨነቅላቸው
መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለሲሳይ አገና መልዕክት ላስተላልፍለት እፈልጋለሁ።
ጋዜጠኞች እባካችሁ የዚህ ሕዝብ
ሰቆቃ ፍትሕ እና ተጠያቂነት ኖሮ ጩኸቱ እንዲደመጥ በነዚህ ሰዎች
ትዕዛዝ እና በነዚህ ሰዎች በራሳቸው እጅ ጥይት የተረሸኑትን የሙታን ጩኸት እንዲደመጥ እና ፍትሕ አንዲሰራ ብትሰብኩ
የተሻለ ነውና ፍትሕን እያጣጣላችሁ ስብከት ከመስበክ ጠንቀቅ በሉ። ወንጀለኞች ደጋግመው ሥልጣን ላይ እየወጡ “ፖለቲካውን እያደፈረሱት”
አስቸግረውናል፡ ባንድ ቦታ ላይ እልባት ይኑሮው። ዕልባቱም ተይዘው የፍትሕ አለንጋ መቅመስ አለባቸው እንጂ ፍትሕ ከማየታቸው በፊት አስመራ ተቀምጦ “አኒቼ አረቂ’ ሲጋት የነበረ የጥላቻ መሪ ሁላ ከሃገሩ
ወጥቶ አስመራ፥ የመን ፥ ሱዳን ፥ ግብፅ ፥
ሚኔሶታ፥ ሲዊዲን፥ጀርምን… እየኖረ ጥላቻ ፥
ግድያ እና አገራዊ ብተና ሲሰብክ የነበረ “አየማራ ነብስ ሲያጠፋ የነበረ ነብሰ ገዳይ ሁላ” “የነፃነት ታጋይ ነበሩ እያሉ
ማሽሞነሞኑ” ይቁም። ጋዜጠኞች አፋችሁ ከፈሪሃ እግዚአብሔር ልጓም ጋር ይተዋወቅ!!! የሙታኖች ነብስ ጩኸት ሚዛኑ አንዲቀንስ የምታደርጉት
ሃላፊነት የጎደለው “ፌዝ” ይቁም!!
ሦስተኛው
ዜና፡
በትግራይ
ፋሺዝም የተጠመቁ የትግራይ ታጋይ ሠራዊት የመራው የትግራይ ፋሺስት ብሔረተኛው ሌ/ጀኔራል ጻድቃን እና በድሮ የኢትዮጵያ ወታደራዊ
ከፍተኛ የሠራዊት አዛዥ የነበሩት ሌ/ጄነራል ካሳየ ጨመዳ የተደረገ ውይት
ኤል ቲቪ በተባለ ቴ/ቪዥን ጣቢያ
በድሮ የኢትዮጵያ ወታደር ውስጥ የሌ/ጄኔራል ማዕረግ የነበራቸው ሌ/ጄነራል ካሳየ ጨመዳ እና በወያኔው ሌ/ጄነራል በትግራይ ፋሺዝም
የተጠመቁ የትግራይ ታጋይ ሠራዊት የመራው የትግራይ ፋሺስት ብሔረተኛው ሌ/ጀኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይ እሱ እና የወያኔ ፋሺሰት
አመራሮች የበተኑዋቸው በድሮ ወታደሮች ህይወት ላይ ውይይት ተደርጎ ያደመጥኩት ቃለ መጠይቅ/ውይይት/ ቅንድብ የሚያስቆም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
የድሮ ወታደሮች ተበትነው ለጎዳና
ተዳዳሪነት ለልመና ህይወት መዳረጋቸው ስናስታውስ “በጀኔሳይድ/ በዘር ማጥፋት/” ስልት የተፈጸመ ወንጀል መሆኑ ለጥያቄ የሚቀርብ እንዳልሆነ
ከኔ ጋር የምትስማሙ እንዳላችሁ አምናለሁ። ሆኖም የቃለ መጠይቁ አዘጋጅ “የፋሺሰት ብሔረተኛ ሠራዊት የመራው ጻድቃን ገ/ተንሳይ
ለበተናቸው የድሮ የኢትዮጵያ ወታደሮች “ይቅርታ” መጠየቅ ያስፈልጋል የሚሉ ጠያቂዎች አሉ እርስዎ እንዴት ይመልሳሉ ብሎ ጋዜጠኛው
ሲጠይቀው “የደርግ ወታደር ለመበተኑ ይቅርታ መጠየቅ ዋናው ጉዳይ አይደለም!“ ይቅርታ አንጠይቅም ከማለቱ አልፎ “ዋና ጉዳይ አይደለም” በማለት እርሱ እና የተቀሩት የፋሺሰት ጓዶቹ “የፈጸሙትን ወንጀል አጣጥሎታል”።
ቅር ያሰኘኝ ግን ጻድቃንን ወጥሮ ልይዝ የሚችል ተከራካሪ ባለመጋበዙ “ሌ/ጄነራል ካሳየ ጨመዳ” ወንጀል በማጋለጡ በኩል ለስላሳ እና ጥልቀት በሌለው ችሎታቸው የቀረበው መልስ አልተደሰትኩም። ከካሳየ ጨመዳ ይልቅ የቴ/ቪዥን አዘጋጅ ጋዜጠኛው “እጅግ በሳላ እና በመረጃ የታጠቀ
ወጣት ጋዜጠኛ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከካሳየ ጨመዳ ይልቅ ‘ሌላ ጥልቅ ተመጓች ሰው ቢጋበዝ በመርጥኩ ነበር።
ሌላው ዜና፡ ስለ ኤርትራ ነው።
ከ7 ቀን በፊት ኤርትራ ውስጥ ስብሓት
ኤፍሬም ተባለ የሻዕቢያ ጀኔራል በዲሰምበር 19 /2018 ዕሮብ በ11 ሰዓት ላይ ወደ ቤቱ ሲመለስ እቤቱ በራፍ አጠገብ ሲደርስ
ማንነቱ ባልታወቀ በወቅቱ በቁጥጥር የዋለ ተኳሽ ‘በድምጽ ኣልባ ሽጉጥ’ ጭንቅላቱ ላይ ኩፉኛ ስለተመታ ‘ወዲ ምሕፁን’
በተባለ ኤርትራዊ ዶክተር ሸኚነት እና ተንከባካቢነት ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ዱባይ ባስቸኳይ እንዲሄድ ተደርጓል።
የቶኩሶ መግደል ሙከራ ሲደረግ
‘ኣሌክስ’ የተባለ የስብሓት ኤፍሬም ልጅ አብሮት እንደነበር ተገልጿል። ስብሓት በጥይት ተመትቶ ሲወድቅ በአካባቢው የቤተሰብ እና
የጎረቤቶች የድንጋጤ የድረሱ ኡኡታ ተሰምቷል።
ለግድያው መነሾ ምክንያት ግንባር
ሃገራዊ ድሕነት ኤርትራ “የኤርትራ ሃገራዊ ደህንነት” በመባል የሚታወቅ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚከተለው ዜና በትግርኛ አሰራጭቶታል።
ስብሓት ኤፈሬም እና ከታች የተዘረዘሩት ባለሥልጣኖች አብሮ በመመሳጠር በኢሳያስ አፈወርቂ ላይ የመፈንቅለ መንግሥት አከናውኖ ከባድሜ ጦርነት ሽንፈት
በኋላ “ኢሳያስን ተቃውመው” እስር ላይ የሚገኙ G-15 በመባል የሚታወቁት ኤርትራውያኖችን
እና መሰል እስረኞችን ለማስፈታት የታቀደ የመንግሥት ግልበጣ ሴራ በመጨረሻው ሰዓት ጓዶቹን ከድቶ ምስጢሩ ለኢሳያስ በማስተላለፉ
አብረውት የዶሎቱት ጓዶቹ በማስያዙ ምስጢር በማውጣቱ የተደረገ የመግደል ሙከራ እንደሆነ ይገለጻል።
ዱሎታውን ያቀነባበሩ የሻዕቢያ ባለሠልጣኖች
“ብርሃነ ሃይለ (ወዲ ውነሽ) ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ፣ ኮሎኔል ደረስ
ገብረ ኣምላኽ የፋይናንስ ሓላፊ፡ ኮሎኔል ባንተ የራዲዮ መገናኛ ጠለፋ ከፍተኛ ባለሥልጣን ፣ እና ሌሎቹ የመሳሰሉት የመግደል ሙከራው
ከመደረጉ በፊት ከሦስት ቀን በፊት ማለትም ዕሁድ በዲሴምበር 16ተለቃቅመው መታሰራቸው ተገልጿል። የመግደል ሙከራው የተደረገው በ19
ሲሆን በ16 ደግሞ ተለቃቅመው ታስረዋል።
አመሰግናለሁ!
ኢትዮጵያን ሰማይ getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment