Saturday, October 7, 2017

አዲስ መጽሐፍ ደራሲ ጌታቸው ረዳ
አዲስ መጽሐፍ ደራሲ ጌታቸው ረዳ
የገጽ ብዛት 457
2010 ዓ.ም

መግቢያ

26 አመት አላላውስ ብለው ጨምቀው የያዝዋት በኢትዮጵያ ገላ የተጠመጠሙት ከጫካ የወጡ አስደንጋጭ የደራጎን እባቦች፤ የመጨረሻውን መርዛቸው በመርጨት ላይ ናቸው። በደራጎኖቹ ላለመነደፍ ሁሉም በሩቅ እየሸሸ ነው። የገዳማት፤ የቤተክርስትያንና የመስጊዶቿ በሮች ሁሉ ተበረጋግደው በሚያሳዝን ሁኔታ አጋንንቶቹ ተቆጣጥሮዋቸዋል፤ ፈጣሪዋም አገር ጥሎ ሄዷል። አማልክቶቿም በብርቱ ሐዘን ላይ ተቀምጠዋል። በምናኔ የሚኖሩ ቅጠል እየበሉ ከእግዚአብሔር ጋር በፀሎት የሚገናኙ የገዳማት አንስት መኖክሲቶች በአጋንንቶቹ መደፈራቸው ነግረውናል። አግዚኦ ተሳሃለነ!!

 ላለመሞት ትንፈራገጣለች፤ ደራጎኖቹ ግን አልለቅ ብለው ጨምቀው ሊገድልዋት ይታገላሉ። ልጆቿ ከአጽናፍ አጽናፍ ተደናግጠዋል። አንዳንዶቻችን ከተመደብንበት ከመከላከያው የቀጠና ሰረገላ ወርደናል። ምን እየተደረገ እንደሆነም አናውቅም። አገራችን ጊዜ በሰጣቸው ትግሬዎች እየታመሰች ነች። እናቶቻችን፤ እህቶቻችን፤ ወንድሞቻችን፤ ዜጎቻችን ተደፍረዋል። ደጋግ ሰዎች ያለማቋረጥ ወደ ጭለማ ክፍል እየተገፈተሩ ነው። ይሙቱ ይታሰሩ ይደብደቡ ይዋረዱ እኛን አስካልነካን ጉዳያችን አይመስልም። ለማወቅም ፍላጎት አላሳየንም። ነቢቦቻችን ተለቅመው ጠፍተዋል። የቀሩትም የማያፈሩ የበሰበሱ ዕጽዋት ሆነዋል። 26 አመት ሙሉ ‘ክፉም ሆነ ደግ ሰው መርዝ ሰጪ የሆነበት፤ እገሌ ከእገሌ ሳይባል ማንኛውም ሰው ማንነቱን የሚያጣበት፤ ሰው ሁሉ ቀስ በቀስ ራሱን መግደል የያዘበት አገር ተችሮልናል’። ሰዎች የመሆን ባሕሪ ጥለው ወደ ድራጎን እና አጋንንትነት የተለወጡት የትግራይ ወያኔዎች አገሪቷን እያስጨነቁዋት ናቸው። ገበያ ላይ ወርደው የሚሸጡት ብቀላቸውና ክፋታቸው እንደ ፍም እሳት ይንቀለቀላል። ከገበያቸው ለመሸሽ ስንሞክር መላ ቅጡ ጠፍቶን ለረዢም ጊዜ በጭለማው መደናበሩን አማራጭ አድርገን ይዘነዋል። እናት በልጇ ሬሳ ተቀምጣ የረዳት ያለህ ታለቅሳለች። ፍርሐታችን አንደኛውን እግራችን አስበልቶ ሁለተኛውን እግራችንም ለመበላት እያመቻቸላቸው ነው። እስከመቸ?  

ኢትዮጵያ ለ26 አመት ሞት፤ ስደት፤ ውርደት፤ አመጽ፤ እንግልት፤ እስራት፤ ድብደባ፤ ጦርነት፤ ግድያ፤ ዘረፋ፤ ክሕደት፤ግብረሰዶማዊ ዝሙት በተዘጋጀላት ሞገደኛ’ማዕበል ውስጥ ገብታ ትንገላታለች። ትዕቢት ባሳበዳቸው ብሔራዊ ስሜት በራቃቸው ‘የቀወሱ’ ሰዎች የአገራችን ሕይወት ሸምቀው ይዘውታል። ባዘጋጇቸው የጭለማ እስርቤቶች እርግብ ወጣት ሴቶችን መድፈር ሳያንሳቸው ተባዕትም ጭምር  ይደፍራሉ። አውላላ ሜዳላይ በቆሙ የኢትዮጵያ ሸበላ ወጣቶች ከሰማዩም ከፎቁም ጥይት ያዘንቡባቸዋል፤ በእያሪኮ ጩኸት እስከ መቸ?

በለስ ቀንቷቸው ይህ ሁሉ ሽብር የሚያካሂዱብን የወያኔ ትግሬዎች የመጡበት ክፍለሃገር’ እኔም ከተወለድኩበት ክ/ሃገር ነው። ብዙዎቹ መሪዎች በትምህርት ወይንም በትውውቅ ወይንም በጉርብትና በጓደኝነት፤ አስቀድሰን ተጫውተን ስቀን፤ በቅርብ የምንተዋወቅ አብሮ አደግ ነን። እንዲህ ያለ አስደንጋጭ ዘመን ያመጣሉ ብየ ገምቼ አላውቅም። እንዴት ተከሰተ? እንዴትስ ተዳራጁ? ሰምታችኋቸው የማታውቋቸው አዳዲስ ታሪኮችና ስለ ትግራይ ሕዝብ በየደረጃው በዚህ መጽሐፍ የምታዩት ዝርዝር ነው።

ወያኔዎች ለ26 ዓመታት ኢትዮጵያን ከመቆጣጠራቸው በፊት በሥጋ ዘመድ አዝማድነትና በጋብቻ በቤተሰብነት እዛው በዛው መተሳሰራቸው ለሚቆጣጠሯት ኢትዮጵያ ቀላል እንደሚሆንላቸው በማሰብ የድሮ የትግራይ መሣፍንትና ነገሥታትን ቅጂ በመከተል ነበር የመጡት። ዘጠኝ የፖሊት ቢሮ አባሎች እና ወደ 30 የሚጠጉ ማዕከላዊ አባላት አብዛኛዎቹ በትዳር እና በዘመድ አዝማድ የተቆላለፉ ናቸው። ሌሎቹ በወያኔ ጥላ የተሰባሰቡ የብአዴን እና የመሳሰሉ አሽከሮቻቸውም ልክ እንደ ወያኔዎች እርስ በርስ በጋብቻ ተጠላልፈው የመጡ ናቸው። አስተዳደሩን የከፋ ካደረገው አንዱ የሥርዓቱ መሪዎች እና አስፈጻሚ አሽከሮቻቸው በዘመድና በጋብቻ ሐረግ ተቆላፈው ስለሠሩ እነ መለስ ዜናዊ ይዘውት የመጡትን ጸረ ኢትዮጵያ ፖሊሲ ለማስፈጸም እጅግ የቀለለ ነበር።

ኢትዮጵያ  ከዓለም ሙሉ የተለየ መሪ ታይቶባታል። የአገሪቱ መሪ ሆኖ የአገሪቱን ዳር-ድምበር፤ ክብር፤ ታሪክና ሰንደቃላማ በዓለም መድረክ ፊት ቆሞ የሚያንቋሽሽና የሚቃወም፤ አገሪቱን ለማፍረስ በሕግ የተደነገጉ 44 የጎሳ ባንዴራዎች አዘጋጅቶ፤ ለሚገነጠሉ ጎሳዎች አንቀጽ አዘጋጅቶ አገር ለማፍረስና ያገሪቷን ጥንታዊ የባሕር በሮቿን ለጠላት በማስረከብ የሚኩራራ ርዕሰ ብሔር የታየው በኢትዮጵያ ብቻ ነው። በዚህ ግለሰብ መመሪያ የሚመሩ ባለጊዜዎቹ ‘እኛ  መንግሥት ነን፤ መንግሥት ማለት ሕዝብ ማለት ነው ይሉናል። ፈላስፋው ፍሬዴሪክ ኒቺ “መንግሥት የክፉዎቹ ሁሉ ክፉ አውሬ ነው።” ይለናል።  መንግሥት በሁሉም ቋንቋዎች የሚዋሽ አፍ ነው። መንግሥት የተፈጠረው ለኒህ እልፍ አእላፍ ሰዎች ነው። እንዴት እንዴት እንደሚያባብላቸው ብቻ ተመልከቱልኝ። ሲያላምጣቸው፤መልሶ’መላልሶ’ሲያኝካው አያችሁልኝ?“ ይላል ‘ኒቺ’። አዎን በአውሬዎች መሃል ተከብበን እያላመጡ መልሰው መላልሰው አኝከውናል። “ኒቺ” በታምራታዊ ትንቢቱ “መንግሥት ሲሞት ቀስተደማና ይወለዳል” ይላል። ኢትዮጵያም በቀስተዳመና መቀነትዋ ዙርያ ብቅ ብላ እንደጥንቱ ሰንደቃላማዋን ይዛ የዚህ ስርዓት ሞት ታበስራለች። አንድ ቀን! 

ወገኖች ሆይ! እስከዚያው ግን ዜግነታችንን በዘመናዮቹ በትግሬዎች መንግሥት በወያኔ ተነጥቀናል። በትዕቢት የተወጠሩ አብሮ አደጎቼ <<ትግሬዎች ወዳሉበት አትዝመት፤ ትግሬዎች ሳትይዝ አትዝመት>> የሚለውን የሰማይ ጣራ ለማፍረስ በሚንጠራራው ትዕቢታቸው እየተመሩ ሲራመዱ መሬቲቱ አፍ አውጥታ እስክትጮህ ይደበድቧታል። አገር ቤት ደርሶ ሲመጣ የታዘበውን የአንድ ወዳጄ ወዳጅ የላከለትን፤ የዘመኖኞቹ ጥጋብ እንዲህ ይገልጸዋል፡

“...እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወንድሜ። ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር የተወሰነ ወር ቆይቼ ነው የመጣሁት። የሰውን ፊት አይተው ይለያሉ ሊቃወመን ይችላል ብለው የሚያስቡትን ኤርፓርት ኢሚግሬሽን ቡት/ኪዮስክ/ ውስጥ ከሚቀመጡት ዘረኛ ትግሬዎች ጀምሮ። በተለይ ቦሌ መድሐኒአለም ፊት ለፊት በኤድና ሞል ዝቅ ብሎ ብዙ ዘመናዊ ባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ተከፍተዋል ሁሉም የትግሬ ናቸው። ነጮቹ “ሆቴል ዲስትሪክት” ይሉታል። የኛ ህዝብ “መቀሌ” እና “አፓርታይድ” ይለዋል ሰፈሩን። በተለይ ቬኒሺያን የሚባለው የትግሬ ሆቴል ገብተን 10 ዲቂቃ እንደተቀመጥን ካውንተሩ ላይ የሚቀመጠው እጅግ በጣም የጠገበ ሲራመድ መሬት የሚነቀንቅ ትግሬ የተቀመጥንበት ድረስ መጥቶ ያፈጣል። አስተያየቱ ሀሉ በጣም ነው የሚከብድው። ህዝቡ ኪሱ ውስጥ ያለውን ብር ቶሎ አራግፎ እንዲወጣ ነው የሚፈልጉት። ጥላቻቸው በግልፅ የሚታይ ነው። በዘረኝነት እና በጥላቻ ከተመረዘ ህዝብ ጋር መኖር በጣም ነው የሚከብደው። ህዝባችን በገዛ አገሩ ላይ እንዲሸማቀቅ እየተደረገ ነው። ባካባቢው ባሉት ሌሎች የትግሬ ሆቴሎች ውስጥም ተመሳሳይ ዘረኝነት ነው ያየሁት።” ይላል። “ይህ እጅግ በጣም የጠገበ ሲራመድ መሬት የሚነቀንቅ ትግሬ የተቀመጥንበት ድረስ መጥቶ ያፈጣል” ብሎ የነገረን በወጣትነት ዕድሜ ያለ የሆቴል ደምብ-ልብስ የለበሰ ዕብድ የሚያክል ሽጉጥ በእጁ ይዞ ደጅ ወጥቶ መኪና ላይ ተደግፎ ምድሩም ነፋሱንም ሲያስፈራራ በቪዲዮ የተቀዳ ልኮልኝ አይቼው፤ የትግራይ ሕዝብ እንዲህ ያለ የልጆቹ ዕብደት ተሎ ካላስቆሞው ዛሬ ‘ ነገ ’ ሲሆን አስቸጋሪ ፈተና ላይ ይወድቃል።  ሲበዛ ጥጋብ ሰንጥቋቸዋል። በገዛ አገራችን መቆሚያ መቀመጫ አሳጥተውናል። አገሪቷ ጠመንጃ ለያዙ ከትግሬ የመጡ ወሮበላዎችና ለልጆቻቸው እንጂ ለኛ ለዜጎች መኖሪያ እንድትሆን አልተፈቀደም። ይህን ቡድን በግልጽ መውቀስ ወይንም ተከታዮቹን መተቸት ለችግር ይዳርጋል። ጸሎታችን  ተቀይሯል። “ጌታ ሆይ ከጀርመን Gestapo (ጌስታፖ)፤ ከኢጣሊያው squadrist ፤ ከወያኔው ‘አጋአዚ’ ማረን” ማለት የዕለት ተለት የኢትዮጵያዊያን ጸሎት ሆኗል። ከጫካ የመጣ ዐውሬያዊ ተፈጥሯቸው ትችት አያውቅም፤ በድርጅታቸው እና በመሪዎቻቸው የሚነጣጠረውን ሂስና ትችት በፖለቲካ ዓይን አይመለከቱትም። ወያኔ ትግሬዎች ለምን ተተቸን በሚል ክፉ ቂም ያሳድራሉ። ቂማቸው እስከዕለተ ሞታቸው ለረዢም ጊዜ አብሮአቸው ይጓዛል። በዚህ መጽሐፍ የምታነቡት የቂማቸው መጠን ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘ ወይም ሊጓዝ እንደሚችል የሚጠቁም ነው። 

አገር ለነሱ ብቻ የተሰጠች ግዑዝ ዕቃ ነች። ሊቆርሷት፣ ወደብ አልባ ሊያደርጓት፣ ሊሸጧት፤ ሊለውጧት፤ ብጥስጥስዋን ሊያወጧት፤ በስጦታ ሊያበረክቷት ባለ ሙሉ ሥልጣን ናቸው። ቻይናዎች ሰው ሲገድሉ ለዲፕሎማሲ ግንኙነት ሲሉ ገዳዩን በሕግ ላለመጠየቅ በነፃ ይለቋቸዋል። የቻይና “ኢንቨስተሮች’ ‘የራሳቸው እስር ቤት’ መሥርተው ዜጎችን መደብደብና ማሰር፣ ደሞዝ ያለመክፈል መብት አላቸው  “በኢትዮጵያ ምድር!!”። የምድሪቱ ሉዓላዊ የጠረፍና የምድር አካላትዋ በውጭ ኃይላት በ “ድሮን” (በሰው አልባ አውሮፕላን) ተደፍራ እንድትሰለል ፈቃድ የመስጠት መብታቸው ጥያቄ ውስጥ አይገባም። ምንነታቸው የማይታወቁ ዓረቦችና የውጭ አገር ፈረንጆች በአገሪቷ የቆዳ ስፋት ውስጥ ተዘርግተው ያለምንም ቁጥጥርና ስጋት አንደ አሸን ተበራክተው የአገሪቷ ሉዓላዊ ገላ ይፈትሻሉ። በውስጧ የሚንቀሳቀሱ ፍጡራን ሉዓላዊ ክብራቸው በባዕድ ይረገጥ አይረገጥ ለትግሬዎቹ መንግሥታዊ መሳፍንቶች የተፈጠሩ ንብረቶች ናቸውና ዜጎች ምንም ዓይነት መብት የላቸውም። በሺዎች ሕይወት መስዋዕት  የተገኘ የጦር ሜዳ ድል እና ድምበር መልሰው ለታሪካዊ ጠላት የማስረከብ መብታቸው የተረጋገጠ ነው፡፡ ያን ሲያደርጉ አይከሰሱም፤ ማን ያበደ አለ የሚጠይቃቸው? ተጠያቂዎችም  ከሳሾችም፤ ፈራጆችም እነሱ ናቸውና ያለመጠየቅ የማይገሰስ መብት አላቸው።

ኢትዮጵያ በትግሬዎች ብቻ እንደተገነባች  አድራጊ ፈጣሪ አድርገው እራሳቸው ራሳቸውን ሰማይ በመስቀል ስለሚክቡ ዜጎች በነሱ ፈቃድ ብቻ ይንቀሳቀሳሉ፤ ሲፈልጉ ያድኗቸዋል፤ ሲፈልጉ  ይገድሏቸዋል፤ ሲፈልጉ ያሰድዷቸዋል፤ ሲፈልጉ-ያባርሯቸዋል፤ይዘርፏቸዋል፤ ይደበድቧቸዋል።
ወዳጄ ነፃነት በላከልኝ ባንድ ጹሑፉ ወያኔዎችን “ክፉ ዕብዶች’ ይላቸዋል። 4የታወቁ የዕብደት ዓይነቶች አሉ ይላል። Badmad, Mad-mad, Sad-mad, and Glad-mad. የሚባሉ። እነዚህ ሁሉ የዕብደት ዓይነቶች ወያኔ የተያዘበትን የአእምሮ ደዌ ለማወቅ ሞክሬ በመጠኑ የተጠጋጋልኝ የመጀመሪያው የዕብደት ዓይነት ነው – “ክፉ ዕብድ” ወይም “መጥፎ ዕብድ” የሚለው  ይላል። መጥፎ ዕብድ እየሣቀ መጥቶ በደቦል ድንጋይ ደረትህን ወይም ማጅራትህን መትቶ ሲጥ ያደርግህና በሞትህ እየሳቀና እየተዝናና በመጣበት መንገድ ሊመለስ ይችላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ዕብድ ቀድሞውን የተለከፈበት የአእምሮ ህመም ከግድያና ስቃይ ጋር የተያያዘ በመሆኑ የሚያስደስተው ነገር ግድያና ስቃይ ነው፡፡ ለዚህ ዕብድ ሰዎችን ማሰቃየት ብቸኛው የደስታ ምንጩ ነው’እንደ ህወሓት!:“ዕብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል” ይባላል። አንድ ሰው ካላበደ መቼም በአንድ ጊዜ ጨለማና ብርሃን ለመሆን አይሞክርም፡- ዕብዱ ወያኔ አንዴ “የፍቅር ዓመት ይሁንልን” ይልና በዚያው አንደበት ስለፍቅር ብቻ የሚያዜመውን ብላቴና የሙዚቃ ምረቃውን መከልከሉ አላንስ ብሎ ልጁን በአሸባሪነት መፈረጁና በጦር ለመውጋት ሲዘጋጅ ማየቱ ስም የማይገኝለት ዕብደት ነው፡፡ በአንዲት ትልቅ ሀገር ውስጥ አንድ ግዙፍ መንግሥት ከአንድ ተራ ዜጋ ጋር የእልህ ግብግብ ውስጥ ገብቶ ሲዳክር ማየት ዓለምን ሳያስገርምና የመጀመሪያው ትንግርት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ቴዎድሮስ ካሣሁን ከጊታርና ከማሲንቆ ያለፈ መሣሪያ ሳይኖረው ወያኔን በፍቅር ስብከቱ ብቻ እንዲያ ሲያንበጨብጨው መታዘብ አስደማሚ ከመሆን አልፎ የወያኔን ሰብኣዊ ተፈጥሮ እንድንጠራጠር የሚያደርግ ልዩ ክስተት ነው፡፡ ወያኔ እንደሚመስለኝ ከጦር መሣሪያና ከባዶ ጉራና ፉከራ  ይልቅ ይህን  መሰሉን እንደሐምሌ ዝናብ እየሰረሰረ የሚገባን የፍቅር መዓዛ በጣም ይፈራል፡፡ ፍቅር የሚያርደውና የሚያሸብረው ደግሞ ሰይጣንንና የሰይጣን የሆነን ብቻ ነው፡፡ እናም ወያኔ ባጭር ቃል ሰይጣን ነው፡፡ ይላል ወዳጄ ነፃነት። በነዚህ ጤና በራቃቸው በቀወሱ ጎስታፖዎች   ዜጎች ያለማቋረጥ ፤ ይጠለፋሉ፤ ይዘለፋሉ፤ ይሰወራሉ፤ ዜጎችን ያለ ነገዳቸው የግዴታ ነገድ ይሰጧቸዋል ። ከ500 በላይ ሶዶማውያን ጌይ/ ለዝቢያን) በሽርሙጥና ተዳዳሪነት ተደራጅተው የርዕሰ ከተማዋ ጎዳናዎች “በሃይ ሂል” የግብረሰዶማዊ  ጫማዎች  ይረገጣሉ። የኢሉሙናቲ ሃይማኖት አስገብተው የገበሬው ቤተሰብ  እንዲበክሉ አደርገዋል (በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱ ፎቶግራፎችን ይመልከቱ)። የአህያ ሉካንዳ መርቀው ከፍተዋል። “በሬ ከበላህ የአህያ ሥጋ ምን ከፋህ?” እያሉ በሬ እና አህያን እያነጻጸሩ አህያ መብላት ነውር እንዳልሆነ ሳያፍሩ ይሰብኩናል። አገሪቱ  በሃይማኖት ሕግ አትተዳደርምና ከአህያ ሥጋ ጋር ተለማመዱ ብለውናል። “ቆሻሻ የሚበላ ሕዝብ ይዘን አህያ ለምን ስትሉ አታፍሩም? እሱን በልታችሁ ከረሃብ በወጣችሁ በማን ዕድላችሁ!” ይሉናል ባለጌዜዎቹ። እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ!!

ጉራቸውና ድንፋታቸው መጠን ስለሌለው፤ እነሱ አምበሳ ሌለው ጥንቸል አድርገው በመሳል፤ “እንኳን ሰው፤ ግዑዝ ያስገረመ” በሚል አስካሪ ሙዚቃ እየጨፈሩ ከሰውነት ደረጃ ወጥተው ከመንጋዎቻቸው ጋር በሚበሉበት አፋቸው ግፍ እየተናገሩበት አብረው በማይጨበጥ ዓለም ውስጥ ገብተው አስደንጋጭ ደወል ይደውላሉ።

እንኳን ከዜጋ ከጠላት አንደበት ይወጣሉ ተብለው በማይታሰቡ አስደንጋጭ ዘለፋዎች አገርን፤ ሰንደቃላማንና ሕዝብን በተናዳፊ ምላሳቸው ሲዘልፉ ለነገ አይሉም። ታሪክን አይፈሩም። አረጋዊያንን በአለንጋ ይገርፋሉ፤ በልጆቻቸው ሬሣ ጎን ተቀምጠው የሚያለቅሱ እናቶችን በዱላ ይደባደባሉ፡፡ የአሸናፊነትና የጊዜ  ትርጉም አያውቁም። በሚውረገረገው የዕብደት መስተዋት በCollective Narcissism ታውረዋልና ጊዜ እንደሚጥል  አይረዱም። ጸሐፊው ዳግማዊ ጉዱ ‘አሸናፊነትን ከማያወቅ አሸናፊ ይሰውረን!” ይላሉ፤ እውነትም ይሰውረን!

የሚያረጉት ሲያጡ፤ ትንሿ ትግራይን  በ‘ሲም-ካርድ’ (Sim Card ) ሰይመው፤ ትልቋ ኢትዮጵያ ‘ግዑዝ’ የቴሌፎን ቀፎ ብለዋታል። ያለ ትንሺትዋ ትግራይ ትልቋ ኢትዮጵያ ሕይወት ሊኖራት አይችልም የሚለው ትዕቢታቸው አብጦ ፈንድቷል። ትግራይ የኢትዮጵያ ‘ሲም ካርድ’ ነች። “እኛ ትግሬዎች ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳንሆን፤ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያደረግንና የመሠረትን ነን። ምስክር የምንሆንለት ካልሆነ በቀር የእኛ ኢትዮጵያዊነት ምስክር አያስፈልገንም፤ ብታምኑም ባያምኑም፤ ሃቁ ያ ነው” ይሉናል በልዕለነት የሚመኩ የትግራይ ፋሺስት ምሁራን። ሰዎቹ ከምድሪቱ እትብት ተለይተው ብቻቸውን ርቀው የሚጓዙ አስፈሪ ፍጡራን ሆነዋል።በቅኝ ግዛት ያልተገዛው ይህ ኩሩ ሕዝብ የሚቀጠቅጡት የወታደሮቹ ማዕረግ ስም፣ ንግድ ቤቶቹ፣ ትምህርት ተቋማቱ፣ከ/ሀገሮቹ(ዞን/ስቴት....፤) አብዛኛዎቹ ጎዳናዎቹ በባዕድ ቋንቋ ተሰይመዋል። የወታደሮቻቸው ማዕረግ ኮማንደርኮንስታብልኢንስፔክተርሱፐር ኢንስፔክተርሱፐር ኢንቴንዳንትነው። ለምን? ብለን በአግራሞት ስንጠይቅ የሚመልሱልን መልስ ‘ሻምበልሻለቃመቶ አለቃ፣ ሃምሳ አለቃ፣ አሥር አለቃ…. የሚሉ አገር በቀል ወታደራዊ መጠሪያዎች የአማራዎች ነውና ከኬኒያ ከናይጀሪያ ወስደን ሰይመናቸዋል ይሉናል። አማራና አማርኛን ለማጥፋት የተነሳንበት ዓላማ ነውና ስትፈልጉ አልቅሱ ይሉናል። አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ የማናጋቱን ሂደት ለማከናወን “በሕግ የተፈቀደ” የጥላቻ ቅስቀሳ በኢትዮጵያ ላይ፣ በክርስትያን ማኅበረሰብ ላይ፣ በአማራ ኅብረተሰብ ላይ እንዲጻፍና እንዲነገር በሕግ ተፈቅዷል። የጥላቻ ሃውልቶች ተመርቀው ተተክለው ይታያሉ። ባለጊዜዎቹ በይፋ በቴሌቪዥን፣ በራዲዮ፣ በጋዜጦች ወዘተ. ይህንኑ የጥላቻ ንግግር በመናገር ኅብረተሰቡ እንዲሸማቀቅ እና ውርደቱ ሕጋዊ እንዲሆን አድርገዋል። አብዛኛው ዜጋ አጥቂዎቹ በሚሰጡት የመጠላለፊያ ፖለቲካ  ወጥመድ ውስጥ ገብቶ፣ እርስ በርሱ በጠላትነት እየተፈራራጀ፣ የየራሱን ባንዴራ እያሠራ በማውለብለብ “ኢትዮጵያን” ማዕከላዊ የጋራ ጠላት በማድረግ የተሰጠውን የማናጋት ሤራ የየራሱን መጥረቢያ ይዞ በመገዝገዝ ላይ ነው። በፋሺስቶቹ የተሰጣቸው “የኤትኒክ ፌደራሊዝም አስተዳዳር” አገርን የማናጋት ሤራ ለማከናወን “ጎሣዎች” የተነገራቸው የጋራ ጠላት ተብለው የተሰየሙ ‘ተዋህዶ ሃይማኖትን፣ አማርኛንና አማራን’ በመጻረር ጎሣዎች አጥቂዎች የጠነሰሱላቸው መርዝ በጥብጠው እየጠጡ ሀገርን በማናጋቱ ሂደት ተዋናይ ሆነው የየራሳቸውብ ምሣር ይዘው አገሪቱን በመገዝገዝ ተጠምደው ራሳቸውን በማጥፋቱ ሂደት ላይ ይገኛሉ። የፖለቲካ፣ የሚዲያ፣የሃይማኖት፣የጎሣ ወዘተ.. ወዘተ…. ተቋማት “ያገሪቱን ግንድ” በመገዝገዙ፣ በማናጋቱ ትዕይንት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት በሳብቨርሲቡ/ በጥቃቱ ዘመቻ አቀነባባሪ በወያኔ  እየተመሩ ወደ አስፈሪው ሂደት እየወሰዱን ነው። የሃይማኖት ተዋናዮችን ስትመለከቱ በተዘረጉላቸው “ideological/subversion (የእምነት ብከላ) ወጥመዶች ገብተው ከዓረቦች በአላህ ስም በዋሃቢም ስም፣ ከምዕራቡ ዓለም ደግሞ በጴንጤና አይሁድ ስም  እየተጠመደ በማያውቀው መርዝ እየተመረዘ “በማናጋቱ ሂደት” ውስጥ እየተጓዘ  ነው ማለት ነው። የኦሮሞ ፋሺሰቶች አማራን <አማርቲቲን ነማ ሚቲ> “አማራ ከሰው በታች ነው” የሚለውን ዘፈን እየዘፈኑ ቁጥራቸውን ለማወቅ በሚያስቸግር አማራዎች ከነ ነብሳቸው ወደ ገደል እየተጨመሩ፣ ሴቶች ከጡታቸው የተቆረጠ ሥጋቸውን እንዲጎርሱ እየተደረገ አሰቃቂ ግድያ ሲፈጸም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማራዎች ከምድር ሰውረናል ብለው ሲኩራሩ፣ ዓለም ምን አለ እንጂ እኛስ ምን አልን!? የሚል ጠያቂ አልተገኝም። ይህም ሆኖ ‘የመቻቻል ፖለቲካ” በተቃዋሚዎች እየተሰበከ የዘመኑ ማደንዘዣ ዕፅ ሆኖ ሙታን እንዳይዘከሩ ለገዳዮች ምቹ ሽፋን ሆኖላቸዋል። አንድ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል “መለስ ዜናዊ ሞቷልና የሞተን ሰው ስም እያነሳን ሙትን መውቀስ  እናቁም” ብለው በሚሰብኩን የፖለቲካ ቀሳውስት እየተሰበክን አረሙን መረማመድ አልቻልንም።

የደናቁርት አክሊል የደፉ የባለጊዜዎቹ ጥጋባቸው ሞልቶ መቋጠሪያ አጥቷልና የባህል ቅኝ ተገዥ አድርገውናል። ስማችን፣ ዜግነታችን፣ አርማችን፣ መታወቂያችንንና እኛነታችንን የመቀየር ሥልጣናቸው የማይገሰስ ‘ምሉዕ’ ነው። እነሱ ወደ ፈጣሪነት እኛ ወደነሱ ፍጡርነት ተቀይረናል። በዛች አገር ውበትና ነፃነት የቀኑ፤ ክፋት የተጠናወታቸው የሩቅና  የቅርብ ጠላቶች ባጠመዱላት ወጥመድ፤ ጤና ባጡት ዕብድ ልጆቿ ተባባሪነት በለኮሱት ሴራና ጦርነት ውብና ክቡር ገላዋ እርቃንዋ ወጥታ ለጠላቶቿ ተገልጣ በሐፍረት ተኮማትራ ትታያለች።  ወላጆች ችግር ውሰጥ ገብተዋል። አባት ልጁን ወደ ዓረብ አገር ወደ ሽርሙጥና ልኮ በሚላከለት ‘የሆር ሞንገር” ገንዘብ እህል ሸምቶ ቆርሶ እንጀራ ሲበላ “የእርም ገንዘብ” አልበላ ብሎት ከጉሮሮው ጋር ውረድ አልወርድም ትግል ገጥሞ እምባ ይተናነቀዋል። አንዳንዱም እራሱን ገድሏል። ባለጊዜዎቹ ብዙውን ዜጋ ቁጭት ውስጥ ከትተውታል። ቁጭታችን በታረክ ማኅደር እንድናስመዘግብ ይኼው ተገድደናል። የሕይወት አሳዛኙ ክስተት ሞት ሳይሆን ሳንሞት የቀበርነው ቁጭት ነው። እንደ ትግሬነቴ የትግራይ ፋሺስቶችን ተፋልሜአቸዋለሁ በአገሬ ሞት ያደረብኝ ቁጭት ከመሞቴ በፊት ቀድሞኝ እንዲቀበር አልፈቀድኩም። ስለሆነም እነሆ ቁጭቴ ከናንተው ጋር ቆሞ ይነጋገራል።  ………….
መልካም ንባብ !
መጽሐፉን ለማግኘት $30.00 የፖስታ አገልግሎት ደራሲው ይሸፍነዋል።
getachre@aol.com (408) 561-4836

ጌታቸው ረዳ
p.o box 2219
 San Jose, CA 95109Wednesday, September 6, 2017

ካላበዱ ወይ ካልነገዱ… ነፃነት ዘለቀEditorial Note- quote from the article
<ከነዚህ ሁሉ የዕብደት ዓይነቶች ወያኔ የተያዘበትን የአእምሮ ደዌ ለማወቅ ሞክሬ በመጠኑ የተጠጋጋልኝ የመጀመሪያው የዕብደት ዓይነት ነው - “ክፉ ዕብድ” ወይም “መጥፎ ዕብድ” የሚለው፡፡ መጥፎ ዕብድ እየሣቀ መጥቶ በደቦል ድንጋይ ደረትህን ወይም ማጅርህን መትቶ ሲጥ ያደርግህና በሞትህ እየሳቀና እየተዝናና በመጣበት መንገድ ሊመለስ ይችላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ዕብድ ቀድሞውን የተለከፈበት የአእምሮ ህመም ከግድያና ስቃይ ጋር የተያያዘ በመሆኑ የሚያስደስተው ነገር ግድያና ስቃይ ነው፡፡ ለዚህ ዕብድ ሰዎችን ማሰቃየት ብቸኛው የደስታ ምንጩ ነው - እንደሕወሓት::> Posted at Ethiopian Semay 

ካላበዱ ወይ ካልነገዱ…
ነፃነት ዘለቀ

Obama's Democracy in Action in Ethiopia. How the Tricky, the Liar, Ruthless and shameful Obama
 Enjoyed the Brutal Repression of the Ethiopian People by his Mad Men 
ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓመተ ፍዳ ነው፤ በእስካሁኑ ጉዞ ከቀጠልን አዲሱንና ግፍና በደል ተባብሶ በወያኔዎች የሚወርድብንን የመከራ ዘመን ልንቀበል አራት ቀናት ብቻ ቀርተዋል፡፡ ለማንኛውም “ደግ ተመኝ ደግ እንድታገኝ” ይባላልና  መጪው ዓመት የኢትዮጵያ ጠላቶች ድል የሚሆኑበት፣ ሀገራችን ከገባችበት ማጥ ነፃ የምትወጣበት፣ የወያኔው ዘረኛ አገዛዝ አብቅቶ ለሁላችንም እኩል የምትሆን ኢትዮጵያ የምትመሠረትበት፣ ጉግማንጉጎች ከነሰንኮፋው ተነቃቅለው የሚጠፉበት፣ ሃይማኖት ለግብር ይውጣ ሳይሆን በሃቅ እውን የሚሆንበት፣ የጠፉብንን የፖለቲካና የእምነት እረኞች የምናገኝበት … እንዲሆንልን አምላካችን ይርዳን፡፡  የዕዳ ደብዳቤያችን የሚቀደድበት ዘመን ይሁንልን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት፡፡

ዕብደት ዓይነቱ ብዙ እንደሆነ የሙያ ዘርፉ ባለቤቶች ሲናገሩ ይሰማል፤ ከትበውትም ይነበባል፡፡ የአእምሮ መቃወስ ዓይነቱና ደረጃው ከሰው ሰውና ከሀገር ሀገር ሊለያይ ቢችልም ማንኛውም ሰው ከነዚህ በመዝገብ ከሚታወቁ የዕብደት ዓይነቶች በአንዱ ወይ በሌላው ቢያንስ ለተወሰነ አጭር ቅጽበት - አንድ ጊዜ ብቻም ሳይሆን በሚመላለስ መልኩ - እንደሚጠቃ ጠቢባኑ ያስረዳሉ፤ እኛ የዘርፉ ማይምናንም በተግባራዊ ኑሯችን ሳንረዳው የምንቀር አይመስለኝም፡፡ ለጠቅላላ ግንዛቤያችን ያህል በፈረንጅኛው ስያሜ እነዚህን መሰል የዕብደት ዓይነቶች በሥነ ልቦናው የትምህርት ዘርፍ በአራት ተከፍለው እንደሚጠኑ ክፋት ያለው አይመስለኝም - Bad-mad, Mad-mad, Sad-mad, and Glad-mad.

በግርድፍ ንባባዊ ግንዛቤየ የሰው ልጅ እስካሁን መቶ በመቶ ማበዱ እንዳልተረጋገጠ መረዳት ችያለሁ፡፡ የመቶ በመቶ ዕብደት የተመዘገበው በውሻ ነው ይባላል፡፡ ልብስን ሽክ አድርጎ ለብሶ በመሄድ ከሰው ጋር ተደባልቆ ማውራትና መጫወት አእምሮን ጨለፍ የሚያደርግ ነገር ሲመጣ ደግሞ ግምኛ ነገር በመናገር ወይም ከርዕስ የወጣን ነገር በመዘብዘብ ሰዎችን ማስደመም የዐውቆ አበዶች ወይም የንኮች ጠባይ ሲሆን ለይቶለት ጨርቁን የጣለና የትሚናውን የሚያድር ግን የዕብደት ደረጃው አርባና ሃምሳን አልፎ ወደ ሰማንያና ዘጠና በመቶ የተጠጋ “ጥሩ” ዕብድ ነው፡፡ በውሻ ዕብደት ግና አንዴ አይጀምር እንጂ ከጀመረ ራስን ያስትና መብላት፣ መጠጣት፣ አቅጣጫን ለይቶ መጓዝ፣ መራብና መጠማት የመሳሰሉ የባሕርይና የስሜት መገለጫዎች የሉም፡፡ ስለሆነም ሂደትን ጠብቆ መሞት ብቻ ነው፡፡ የሰው ዕብድ ግን ይርበዋልና ይበላል፤ ይበርደዋልና ይለብሳል ወይም ጥጋት ላይ ቁጭ ብሎ በብርድ ይንቀጠቀጣልል፡፡ ስለዚህ ዕውቀቱንና ሙሉ ስሜቱን አልተገፈፈምና ወሰድ መለስ እያደረገው እንደምንም ይኖራል - መኖር ተብሎ፡፡
በተለምዶ ጤነኛ የሚባሉ ሰዎች (ዕብደታቸውን ማወቅ የማይፈልጉ ብላቸውም ግዴለኝም) ዕብዶችን በጣም ይፈራሉ፡፡ ሁሉም ዕብዶች ሊፈሩ እንደማይገባ ግን ከፍ ሲል የተጠቀሱትን የዕብደት ዓይነቶች ዝቅ ሲል በተቀመጠው አድራሻ ሄዶ ማንበብ ጠቃሚ ነው፡፡ አንዳንድ ዕብዶች አዛኝና ሩህሩህ ናቸው - ያላቸውን የሚያካፍሉና ለተቸገረ የሚንሰፈሰፉ፡፡ ያገኙትን ነገር እያነሱ አጠገባቸው ወደሚገኝ ሰው የሚወረዉሩና አደጋ የሚያስከትሉ አንዳንድ ዕብዶችም አሉ፡፡ አንዳንዶች በሣቅ እየተንከረከሩ ራሳቸው ለራሳቸው በሚፈጥሩት ደስታ የሚዝናኑ አሉ፡፡ አንዳንዶች በሀዘን ድባብ ተውጠው ዘላለማቸውን እንደቆዘሙና እንደጨፈገጋቸው የሚኖሩ አሉ፡፡ አያድርስ ነው …

ከነዚህ ሁሉ የዕብደት ዓይነቶች ወያኔ የተያዘበትን የአእምሮ ደዌ ለማወቅ ሞክሬ በመጠኑ የተጠጋጋልኝ የመጀመሪያው የዕብደት ዓይነት ነው - “ክፉ ዕብድ” ወይም “መጥፎ ዕብድ” የሚለው፡፡ መጥፎ ዕብድ እየሣቀ መጥቶ በደቦል ድንጋይ ደረትህን ወይም ማጅርህን መትቶ ሲጥ ያደርግህና በሞትህ እየሳቀና እየተዝናና በመጣበት መንገድ ሊመለስ ይችላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ዕብድ ቀድሞውን የተለከፈበት የአእምሮ ህመም ከግድያና ስቃይ ጋር የተያያዘ በመሆኑ የሚያስደስተው ነገር ግድያና ስቃይ ነው፡፡ ለዚህ ዕብድ ሰዎችን ማሰቃየት ብቸኛው የደስታ ምንጩ ነው - እንደሕወሓት፡፡
መጥፎ ዕብድ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ መረጃ ያጋራኝ ሰነድ ስለነዚህ ዕብዶች እንዲህ ይላል- 
If you meet a bad-mad person, especially when on your own, your priority must be to protect yourself. When self-defence is impossible, you should flee. ( [እንደሕወሓት ያለ]መጥፎ ዕብድ አያጋጥምህ እንጂ ካጋጠመህ - በተለይ ደግሞ ብቻህን ሆነህ - የመጀመሪያው እርምጃህ መሆን ያለበት ራስህን ከአደጋ መከላከል ነው፡፡ ራስህን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ ውስጥ የምትገኝ ከሆነ ደግሞ አጥብቀህ ሽሽ፡፡)

ትክክለኛ የባለሙያ ምክርና አስተያየት ነው፡፡ የተራ ዕብድን ጥቃት ታግለህም ሆነ ሮጠህ ትከላከላለህ፡፡ ይሁንና በመንግሥት መልክ ተደራጅቶ የመጣብህን ጎጠኛ ዕብድ እንዴት ትጋፈጠዋለህ? ከዚህ ዓይነቱ በጠላት ድጋፍ ከተደራጀ ዕብደት እንዴት ታመልጣለህ ? በቀላሉ መልስ የማይገኝለት ከባድ ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህ ነው እንግዲህ ኢትዮጵያውያን ከዕብዶቹ ሕወሓታውያን የሲዖል ግርፋት ይልቅ በበረሃ አውሬዎች መበላትን እስከመምረጥ የደረሱት፡፡ ለዚህ ነው ኢትዮጵያውያን ውብ ሀገራቸውን በቀንና በሌሊት እየለቀቁ የባሕር እንስሳት ሲሳይ ሆነው መቅረትን የመረጡት፡፡ ለዚህ ነው ውድ የሀገሬ ወጣቶች ከዕብዱ የወያኔ አፓርታይድ አገዛዝ ይልቅ የዐረብ ጀማላ የቤት ውስጥ ገረድ መሆንን የሚመርጡት፡፡ ለዚህ ነው ሀገራቸው የማትበርድ እቶን የሆነችባው ኢትዮጵያውያን በሚሊዮኖች እየተሰደዱ በሰው ሀገር እንደሁለተኛና ሦስተኛ ዜጋ ሆነው መኖርን የሚመኙትና በተግባርም እየሄዱ የሚማገዱበት፡፡ ለዚህ ነው ወገኖቻችን ከዚህ ከወያኔዎች የዕብደት ሥራ ለመዳን ሲሉ የአይሲሶች ካራ ሰለባ የሚሆኑት፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ከመኖር የለየለት ገሃነምም ሳይሻል አይቀርም፡፡ መብላት መጠጣት፣ መጥገብ መራብ፣ ማግኘት ማጣት ሌላ ጉዳይ ሆኖ ሰው ሆነህ እንደሰው መኖር የማትችልባት ሀገር ሆናለች - ኢትዮጵያ (የምለው ግልጽ ከሆነልህ በገንዘብ ሀብታም ሆነህም ወያኔ ካልሆንክ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አትችልም እያልኩህ ነው ወዳጄ፡፡) እንደሰው ለመኖር ቢያንስ በቅድሚያ የማሰብ ነፃነትህ ሊገፈፍ አይገባም፤ እንደዜጋ ይቅርና ቢያንስ እንደሰው የሚቆጥርህ የራሴ ነው የምትለው መንግሥት ሊኖርህ ይገባል፡፡ የራሴ ነው የምትለው የፖሊስ፣ የፀጥታና ደኅንነት፣ የመከላከያ ወዘተ. ኃይል መኖር አለበት፡፡ አንዱን የእንጀራ ሌላውን የሠይፍ ልጅ አድርጎ ማኛውንና ቁርጡን ለዘሩ፣ ዘንጋዳውንና ሳላይሰጡን ለአሽከሩ የሚሰጥ የመንግሥት መዋቅር ስታይ ምን ሊሰማህ ይችላል? እነዚህን ዓይት የተንሻፈፉ አካሄዶች ሲስተካከሉ ያኔ  ነው ሀገሬ ልትል የምትችለው፡፡ እንጂ ስታየው የሚያቅርህ ባንዴራና እንደጠላት እያዬ የሚደበድብህ መለዮ ለባሽ ይዘህ በየትኛው አእምሮህ የሀገር ስሜት ይመጣልሃል?   ምን መናገርና መጻፍ ቀርቶ ምን ማሰብ እንዳለብህ ተለክቶ የሚሰጥህ በወያኔዎች ነው፡፡ ኧረ ባይገርምህ ይህ መንግሥታችን ማመልከቻም የሚጽፍልህ ራሱ ሆኖ አርፎልሃል! ንቀት ሲበዛ እንዲህ ነው፡፡ በየቀበሌው ለጉዳይ ስንሄድ እኛ እንደምንፈልገው ሣይሆን እነሱ እንደሚፈልጉት ተጽፎ “ማመልከቻችን” ግርጌ ላይ እንደ ቅጽ ፈርመን እንድናስገባ እንገደዳለን፤ ራስህ መጻፍ አትችልም፤ በዚህስ ተገላግለናል - ሰሜን ኮሪያንም ሳናስንቅ አንቀርም ( እነሱ የሞተውን መሪ ትተው ልጁን ሲያመልኩ እኛ በሞተ ባምስት ዓመቱ በዐፅም እንገዛለን - ለዐፅምም እንድንሰግድ እንገደዳለን! ይቺ ናት የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ንቃትና ዕውቀት ማለት! ዱሮ መፈክራችን “ወደፊት!” ነበር፤ አሁን ደግሞ “ወደኋላ!” ሆኗል፤ የማመልከቻውን ናሙናው ከሥር ተመልከት) ዜጎች በሁለት ጎራ ተከፍለው አንዱ ነዋሪ ሌላው አኗኗሪ የሆነባት ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ የዕብደት ውጤት እንደዚህ ነው፡፡ ዕብደት ማለት አእምሮን በአግባቡ ያለመጠቀም እስከሆነ ድረስ በሆዳቸው የሚያስቡት ደናቁር ወያኔዎች ሀገራችንን እንዳታንሰራራ አድርገው እየገደሏት ነው፡፡ የዕብድ ገላጋዩ ድንጋይ አቀባይም ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር እጅግ በዝቷል፡፡ መጨረሻችንን እንዲያሳምረው ለአንድዬ መጸለይ ነው፡፡

በርዕሴ ከጠቀስኩት “ካላበዱ ወይ ካልነገዱ…” ከሚለው ሀገርኛ ብሂል በተጨማሪ  ስለዕብድ ሌላም አባባል አለ፡፡ እሱም “ዕብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል” የሚለው ነው፡፡ አንድ ሰው ካላበደ መቼም በአንድ ጊዜ ጨለማና ብርሃን ለመሆን አይሞክርም፡- ዕብዱ ወያኔ አንዴ “የፍቅር ዓመት ይሁንልን” ይልና በዚያው አንደበት ስለፍቅር ብቻ የሚያዜመውን ብላቴና የሙዚቃ ምረቃውን መከልከሉ አላንስ ብሎ ልጁን በአሸባሪነት መፈረጁና በጦር ለመውጋት ሲዘጋጅ ማየቱ ስም የማይገኝለት ዕብደት ነው፡፡ በአንዲት ትልቅ ሀገር ውስጥ አንድ ግዙፍ መንግሥት ከአንድ ተራ ዜጋ ጋር የእልህ ግብግብ ውስጥ ገብቶ ሲዳክር ማየት ዓለምን ሳያስገርምና የመጀመሪያው ትንግርት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ቴዎድሮስ ካሣሁን ከጊታርና ከማሲንቆ ያለፈ መሣሪያ ሳይኖረው ወያኔን በፍቅር ስብከቱ ብቻ እንዲያ ሲያንበጨብጨው መታዘብ አስደማሚ ከመሆን አልፎ የወያኔን ሰብኣዊ ተፈጥሮ እንድንጠራጠር የሚያደርግ ልዩ ክስተት ነው፡፡ ወያኔ እንደሚመስለኝ ከጦር መሣሪያና ከጉራ ይልቅ ይህን  መሰሉን እንደሐምሌ ዝናብ እየሰረሰረ የሚገባን የፍቅር መዓዛና ጠረን በጣም ይፈራል፡፡ ፍቅር የሚያርደውና የሚያሸብረው ደግሞ ሰይጣንንና የሰይጣን የሆነን ብቻ ነው፡፡ እናም ወያኔ ባጭር ቃል ሰይጣን ነው፡፡

ከሰሞነኛ ጉዳዮች ጥቂት ልበልና ላብቃ፡፡ የወያኔው ጉጅሌ ያማረውን ሁሉ በዐዋጅ እየቀማ 26 ዓመታትን በመንግሥትነት ዘልቋል፡፡ ፈጣሪም መጨረሻውን ሊያጃጅልለት ያቀደ ይመስላል እስካሁን እንደልቡ እንዲፈነጭ ሜዳውንም ፈረሱንም ሰጥቶታል፡፡ እነሂትለርም፣ እነሙሶሊኒም፣ የኛው ማፈሪያ ጉድ መንግሥቱም እንዲሁ ቅጥ አምባራቸው የጠፋ ባለጌዎችና ቅል ራሶች ነበሩ፡፡ መጨረሻቸው ግን አላማረም፡፡ አምባገነኖች ዋልጌዎች ናቸው፤ አምባገነኖች ታህተ-ሰብዕ (sub-humans) ናቸው - ለዚህ አባባሌ እነኢዲያሚን ዳዳና እነአፄ ቦካሣ ምሥክሮቼ ናቸው፡፡ ሁሉ ነገር በጉልበትና በወኔ የሚያልቅ ይመስላቸዋል፤ ጭንቅላታቸው የገማ ነጭ ጭቃ እንጂ የሰው ልጅ አንጎል የለበትም፡፡ እውነቱ ታዲያ ሌላ ነው፡፡ ሥልጣንና ዝና የሚቆየው ወይም የማይቆየው በመሣሪያ ብዛት አይደለም፤ በዕውቀት ብዛትም አይደለም፤ በወታደር ብዛትም አይደለም፤ በዓላማ ጽናትም አይደለም፡፡ በሀብትና በገንዘብ ብዛትም አይደለም፡፡ ይህን ምሥጢር አምባገነኖች አያውቁትም፤ ለምን ቢባል ድንጋይ ራስ ናቸውና፡፡ ቀኑ ሲደርስ ሁሉም ነገር ይከዳቸውና እንደወጡ ተንኮታኩተው ይወርዳሉ፤ እንደወፈሩ ሟሽሸው ይኮሰምናሉ፤ እንደታበቱ በሀፍረት ተሸማቀው ይዋረዳሉ፡፡ ቀኑ ነው፤ አለቀኑ ዝናብ አይጥልም፡፡ አለቀኑ እህል አይበቅልም፤ አያፈራምም፡፡ አለቀኑ ሽልም አይወለድም፡፡ “ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” ይላል መጽሐፉም፡፡….

ወያኔዎች በሁሉም ረገድ ትግራይን አሳብጠው ወደሚቃዡበት “የትግራይ ሪፓፕሊክ” የሚያደርጉትን ጉዞ ቀጥለዋል - ያላንዳች ሀፍረትና ይሉኝታ፤ ክፉ ዕብድ ሀፍረትም ሆነ ይሉኝታ የለውምና፡፡ ኢትዮጵያውንን ርስ በርስ አባልተው እነሱ ጎጆ ለመቀለስ ሽር ጉድ እያሉ ናቸው፡፡ ይህ ግን ቅዠት ነው፡፡ የቅዠት ቅዠት፡፡ እኔ ትንሹ ሰው እንዴት እንደምስቅባቸው ቢያዩ ምናልባት እነሱም እኔን ዐበደ ይሉኝ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን ገድለው እነሱ በሰላም የሚኖሩ ከሆነ በርግጥም እግዚአብሔር በመንበሩ የለም፡፡ የአማራን ሕዝብ ጨርሰውና የአማራን መሬት ለሱዳንና ለ”ትግራይ ሪፓፕሊክ” ሰጥተው እነሱ በሰላም እንኖራለን ብለው አስበው ከሆነ ይህም ሃሳባቸው ደረጃ ሊወጣለት የማይችል ዕብደት ውስጥ መግባታቸውን በግልጽ የሚናገር ነው፡፡ የሚያደርጉትን ሁሉ ስታዘብ የወያኔነት ቫይረስ የሌለብኝ ጤናማ ትግሬ ነኝ የሚለውም ሆነ ሌላው ሕዝብ ቁጭ ብሎ እህህ ማለቱን ስቃኝ እነዚህ ሰዎች በዚህች ሀገር ሊያመጡ የፈለጉትን መቅሰፍት አስባለሁ፡፡ እነዚህ ዕብዶች የሚያስቡትንና የሚያደርጉትን ነገር የሕጻን አእምሮ እንኳን ይጠየፈዋል፤ ይንቀዋል፡፡ የማይምነታቸው አሰቃቂነት የሚገዝፈው ደግሞ ብሔረሰቦችን ለማናከስ አዲስና ያልነበረ የማንነት ጥያቄ በነሱው ሠርጎ ገቦችና በገንዘብ ኃይል በማስነሳት የረጋውን ኩሬ ለማደፍረስ የሚያደርጉትን ጥረት ስንታዘብ ነው፡፡
ቅማንት የሚል ሕዝብ የለም አልተባለም፡፡ ግን ግን በቅማንት የማንነት ጥያቄ ሰበብ 12 ቀበሌዎችን ወደ ትግራይ ለመውሰድ ማለም - አሁን ሕዝበ ውሳኔም ሳያስፈልጋቸው እንዲሁ ሊወስዱትም ይችላሉ - “አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ” ያለችውን ተረት ያስታውሰናል፡፡ ሥራቸው ሁሉ የሚገርም ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የፊታችን መስከረም ሰባት ሊካሄድ ዕቅድ የተያዘለት የቅማንት የማንነት ጥያቄ ተብዬና የሕወሓት መፍትሔ ለትግራይ ተጨማሪ የእቶን እሳት የሚያወርድባት እንጂ አንድም ዕድገትና ብልጽና አያስገኝላትም፡፡ ወያኔ ዕድገቱን ጨርሶ ሊሰናበት የቀረው ጊዜ ትንሽ ነው፡፡ በዚህችን አጭር ጊዜ እንኳን አደብ ሊገዛ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ወያኔ ማለት ለኢትዮጵያ  ውድመት ሲባል በፈረንጆች ተረግዞ በፈረንጆች የተወለደና ለወግ ማዕረግ የበቃ የድውያን ቡድን በመሆኑ ግብዓተ መሬቱ እስካልተፈጸመ ድረስ ከጥፋት ሊቆጠብ አይችልም፡፡

 የነጋበት ጅብ ያገኘውን እየዘነጠለ ወደ ጎሬው እንደሚገባ ወያኔም ያገኘውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከምድር በታች ሳያስገባ ማንንም ፈርቶ ከጥፋት ተልእኮው ይታቀባል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ በየጊዜው ችግር እየተፈጠረለት ለስቃይ የሚዳረገው የትግራይም ሆነ ሌላው ሕዝብ ግን ቆም ብሎ ማሰብ አለበት፡፡ ለምሣሌ የወያኔን ችግር ፈጣሪነት ይረዳዋል ብዬ የምገምተው ሰፊው የትግራይ ሕዝብ በራያና በወልቃይት ሰበብ የተጠመቀው መርዘኛ ጠላ ተጠጥቶ ሳያልቅ ሌላ አስካሪ መጠጥ ሊያስተናግድ  እንደማይገባው ማወቅ ይኖርበታል፡፡ የዛሬ ገናናነት ነገ አይኖርም፤ የዛሬ ሁሉን አዛዥነት ነገ አይደገምም፤ የዛሬ እዩኝ እዩኝ ማለት ለነገ ሀፍረትና አንገት መድፋት እንደሚዳርግ የማይረዳ ሰው ባይፈጠር ይሻለዋል፡፡ አንገት የተፈጠረው አዙሮ ለማየት ነበር፡፡ አሁን ግን ብዙ ወንድሞቻችንን ስናይ አንገታቸው ቦርጫቸው ውስጥ ተወሽቆ ሁሉን ነገር የሚመለከቱት በሆዳቸው ሆነና ከሰብኣዊ የይሉኝታ ማዕቀፍ በፀሐይ ብርሃን ፍጥነት እየራቁ ሄዱ፡፡ ስለዚህ ጤናማ ነኝ የሚል የትግራይ ሰው ልጆቹ ጥጋባቸውን በልክ እንዲያደርጉት በጸሎትም በምክርም ሊሣተፍ ይባል፡፡ ነገር ከተበላሸ በኋላ - እስካሁን ተበላሽቶ ካልሆነ - ቢጸጸቱ ዋጋ የለውም፡፡ የፈሰሰ አይታፈስምና፡፡ በወያኔ ጥጋብ ትግራይ ብትነድ ጉዳቱ የሁሉም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ እንዲህ የምለው ማንንም ለማስፈራራት አይደለም፡፡ “የተሸነፈ” አያስፈራራም፤ የዕልቂት ዐዋጅ ታውጆበት “ጅራቱን ወትፎ” እግር አውጭኝ የሚል አያስፈራራም፡፡ ከሥር ያለ ከላይ ያለ የሚመስልን አያስፈራራም፡፡ ግን ግን ቀኝ ኋላ ዙር መኖሩን አለማሰብ የለዬለት ድንቁርና ነው፡፡ መጽሐፉም “ፊተኞች ኋለኞች፣ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ” ይላል፡፡ ግን ማን ሲያስተውለው!  

ወያኔዎችን እኔ ልምከራቸው፡፡ ምንም ወጪና አታካራ ሳያበዙ ኢትዮጵያን በሙሉ ትግራይ ይበሏትና በአንዴ ይገላገሉ፡፡ ዕብድ የያዘው ገንዘብ አንዴውኑ የተረገመ ነውና ሰውንም ገንዘቡንም ተቆጣጥረው እንዲህ አበሳችንን ከሚያሳዩን ከተቻለ ሁላችንንም እንዳወጣን ሸጠው ይረፉ፡፡ እኛም እንረፍ፡፡ ከመጥፎ አሸናፊ የማይሻል ክፉ ነገር የለም፡፡
“የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” ይባላል የነሱ ዓይነት ልብ አውልቅ፡፡ የሚፈልጉትን ለማድረግ የሚከለክቸው ህግም ሆነ ሌላ ኃይል በሌለበት ሁኔታ ማንን ለማታለል እንዲህ እንደሚቸገሩና እንደሚለፉ አይገባኝም፡፡ ምርጫውን እንደሚያጭበረብሩ ሁሉ ምንም ነገር ከማጭበርበር አይመለሱምና ለታይታና ለይስሙላ የሚያደርጉትን ክርክርና ህዝበ ውሳኔ ተብዬ የሚባል ጡት ያልጣለን ሕጻን ሳይቀር ማታለል የማይችል ቁጩ ነገር ትተው መውሰድ የሚፈልጉትን ተራራም ይሁን ሜዳ፣ ህንጻም ይሁን አስፋልት መንገድ፣ ከተማም ይሁን ገጠር በወሬ ቱማታ ሳያደነቁሩን ዝም ብለው ይውሰዱ፡፡ የተቸገሩትም በዚህ ጉዳይ ይመስለኛል - ሕንጻና መንገድ ዘርፎ መውሰድ የሚያስችል ዘዴ ባለመገኘቱ ሳይናደዱ አይቀሩም፡፡ ሌላውንማ አጓጉዘው ጨርሰዋል፡፡ ለነገሩ  ማጓጓዝ ለማይችሉት መሬትንና ምርጥ የሀብት ምንጭን ለመቀራመት ሰዎቻቸውን ከትግራይ እያመጡ በመላው ሀገራችን አስፍረዋል  - ሌላውንና ባለመብቱን እያፈናቀሉና እየገደሉ፡፡ የማስመሰያ ቲያትር ሳያስፈልጋቸው ያሻቸውን እያደረጉ እንደኖሩት አሁንም እንደዛው ማድረግ ይችላሉ፡፡ የማንም ቡራኬም አያስፈልጋቸውም፡፡ በቀሺም ድራማ ሰውን ይበልጥ ከማናደድ ቢቆጠቡ ለኛም አንድ ዕርዳታ ነው፡፡ በጣም ያንገሸገሽን ወዝ የሌለው ቲያትራቸው ነው፡፡ በነገራችን ላይ መሬትና ሕንፃ እንዲሁም መንገድ ተነቅሎ ቢወሰድ ኖሮ ይሄኔ ኢትዮጵያ ባድማ ሆና ነበር - ምን ዓይነት ስግብግብ ናቸው በእግዚአብሔር! የማይጠግቡ እምብርት የለሾች፡፡…

ለማንቻውም መስከረም 7 2010 ጎንደር ላይ ሊያካሂዱት ያቀዱትን የቅማንት ማንነት ህዝበ ውሳኔ ተብዬ ነገር ይተውትና የሚፈልጓቸውን መንደሮች እንዲሁ ይውሰዱ፡፡ ከፈለጉ ሸዋሮቢትንም፣ ደብረ ብርሃንንም፣ ሞላሌንም፣ የኔይቱን ቅምብቢትንም … ወስደው ትግራይ ላይ ይለጥፏቸው፡፡ ማን ይቆጣቸዋል? እነዚህንና ሌሎችንም ቦታዎች ከመሬት ሰቅስቆ ማንሳትና ማዛወር የሚችል ክሬን ካገኙ አዲስ አበባንም ወስደው መቀሌ ላይ ይለጥፏት፡፡ እንጂ አንዴ ፊንፊኔ ሌላ ጊዜ አዲስ አበባ እያሉ ልባችንን አያውልቁ፡፡ ለትግራይ ትልቅነት ስንል መከራችንን በላን - አንዳንዶቻችን ያልበላንን አከክን፤ አንዳንዶቻችን ባልገባንና በማይገባን  ነገር ከወዳጆቻችን ጋር ተቆራረጥን፤ አንዳንዶቻችን እንደኤሣው ለቁራሽ እንጀራ ስንል ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀልና ምሕረትን የሚያስከለክል ኃጢኣት ሠራን፡፡ ግልብነታችንን በገሃድ ያወጅን በሚሊዮን የምነቆጠር ተማርን የምንል ወገኖች አገር ምድሩን ሞልተናል፡፡

 ፌዴራል ተብዬ የሌለ መዋቅር እንዳለ በማስመሰል በዚህ ወያኔ ብቻ በሚቀናጣበት የማስመሰያ ጭምብል ኢትዮጵያ መታመስ ከጀመረች ጀምሮ ሁላችንም መቅኖ አጥተን፣ ሰላምና የአምላክ በረከትም ርቆን በስቃይ እንኖራለን፡፡ እምብርት የሌላቸው ወያኔዎችን ተሸክመን የድቅድቅ ጨለማውን መንገድ እየተጓዝን ነው፡፡ መቼ እንደሚያልቅ ዕንቆቅልሽ ሆኖብናል፡፡ ( netsanetz28@gmail.com)

ማመልከቻ

እኔ ነፃነት ዘለቀ የክ/ከ 75 ወረዳ 128 የቤት ቁጥር 1219 ነዋሪ ስሆን ያለኝን መኖሪያ ቤት መንግሥት በፈለገው ጊዜ ለቅቄ ለመሄድ የተስማማሁ መሆኔን በፊርማየ አረጋግጣለሁ፡፡
                                    ፊርማ

ዋቢ - https://www.psychologytoday.com/blog/spiritual-wisdom-secular-times/201501/four-types-madness

Saturday, August 26, 2017

ዝምታ ሁሉ እንደማስማማት አለመቆጠሩን ለመግለጽ ስል ብቻ?…

Note- from the Editor:
As Ethio Semay repeatedly challenged and exposed the Oromo movement inside or outside Ethiopia, you can see from the so called 'Kero' (Oromo youth) movement an organization made to destroy the speedy revolt of the Ethiopian people. It is premature, mercenary orchestrated by TPLF itself and some extremist Islamist Oromo leaders in the Diaspora(USA and Europe) in order to drag the speed of the revolution and create confusions among Ethiopian society. This organization is nothing but nihilist movement. Therefor, such organization is a branch for the nihilist and fascist OLF, therefore, Ethiopians need to isolate such organization and labeled it as OLF. These group are simply outdated and fascistic in nature.


ዝምታ ሁሉ እንደማስማማት አለመቆጠሩን ለመግለጽ ስል ብቻ?

                                                          ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com)ይህን አጭር ማስታወሻ የምጽፈው በርዕሴ ለመጠቆም እንደሞከርኩት አንድን የተነገረ ወይ የተጻፈ ነገር በዝምታ ብቻ ታዝቦ ማለፍ ስምምነትን እንደመግለጽ የሚቆጠር እንዳልሆነ ለማስገንዘብ ስል ብቻ ነው፡፡እንጂ ሰዎች ባበዱና በሰከሩ ቁጥር ብዕር እናንሳ ብንል በቀን ውስጥ ያለው 24ቱ ሰዓትም  በጭራሽ አይበቃንም፡፡ ይሄ የተለከፈ ዘመን ደግሞ በየቀኑ የማያሰማንና የማያሳየን ነገር ባለመኖሩ ብዙው ነገር አስገራሚና አስደንጋጭም እየሆነ መጥቷል፤ በሁሉም ረገድ - በሃይማኖቱም በፖለቲካውም፣ በማኅበራዊ ሕይወቱም… በእያንዳንዱ የሕይወት መስመር የምንሰማውና የምንታዘበው ነገር ሁሉ በአብዛኛው አስፈሪ ነው፤ የምንጽናናበት ነገር እየቀነሰ የምንደነግጥበት ነገር ደግሞ እየበዛ የመሄዱ ምሥጢር አልገለጥ ብሎናል፡፡ ስለዚህም በያለንበት ባማርኛው ትርጉሙ “ጉድ!” እያልን መጨረሻውን መጠበቅን የመረጥን በርካታ ዜጎች አለን - ባገር ቤትም በውጪው ዓለምም፡፡ ጊዜ ያመጣውን ጊዜ እስኪሽረው አንድ ተገን ይዞ ፈጣሪንና የታሪክ ፍርድን በተስፋ መጠባበቅ ደግሞ የነበረና ያለ ምናልባትም ወደፊትም የሚኖር ነው፡፡ እናም ያበዳችሁና በዘመን ድፍርስ የእንክርዳድ ጠላ የሰከራችሁ ወንድም እህቶቻችን አቅል አጥታችሁ የምትናገሩትንና የምታደርጉትን ሁሉ የሚታዘብና ለነገው ትውልድ የሚያደርስ ጤናማ ሰው እንደማይኖር አስባችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል፡፡ ጥንታውያን ዕብዶች አሁን የቡና መጣጫ እንደሆኑት ሁሉ የዛሬዎቹ ዘረኞችና ልበ ሥውራን ጎጠኞችም በነገው ታሪካችን እንደጭራቅ የልጅ ማስፈራሪያ እንደምትሆኑ አሁኑኑ መረዳት አለባችሁ፡፡ የሰከረ የሚበርድበት፣ ያበደም የሚጨምትበት (ካልሞተ በቀር) ዘመን መምጣቱና የተንጨባረረ ማንነቱን በዘመን መስታወት ማየቱ አይቀርምና ጊዜ ሰጠን ብላችሁ የምትሆኑትን ያጣችሁ ወገኖች ጥጋባችሁንና ዕብሪታችሁን ልክ እንድታስይዙት የወንድምነቴን እመክራለሁ፡፡ እውነቱን ለመናገር እንደ እናንተ ለማበድ ብንፈልግ ኖሮ ከእናንተ በላይ እያበድንና እየሰከርን የፈለግነውን መሆን የሚያስችለን ዕድሉ የነበረን ብዙ ነገን ዐዋቂ ዜጎች አለን - በዘርም፣ በቋንቋም የተሟላ ወቅታዊ የመርገምት መሣሪያ እያለን በወፍ ዘራሽ አስተሳሰብ አንበከልም ብለን ግን ዳር የቆምን፣ ከዚያም ባለፈ ለነፃነት ትግሉ የበኩላችንን አስተዋፅዖ የምናደርግ ትግሬዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ጉራጌዎችና ሌሎችም ብርቅዬ ኢትዮጵያውያን ሞልተናል - በዚህስ ወላድ በድባብ ትሂድ፡፡ ዝም ያልነው ባለታክሲዎች በመኪኖቻው ውስጥ “ከላይ ነው ትዛዙ” እንደሚሉት የማይቀር ታሪካዊ ፍርድን ከታች ብቻ ሣይሆን በዋናነት ከላይም ጭምር እየጠበቅን ስለሆነ ነው፡፡ ለመግቢያ ያህል ይህን ካልኩ ወደ ዋና ነጥቤ ላምራ፡፡


“ቄሮ በኦሮሚያ ክልል የጠራውን የአምስት ቀን አድማ ግቡን ስለመታ በሦስተኛው ቀን አቋርጫለሁ አለ/ከቄሮ የተላለፈው አስቸኳይ መግለጫ (ምንጭ  http://www.zehabesha.com/amharic/?p=79730

ከዚህ በላይ በተመለከተው ርዕስ ዘሃበሻ ላይ የተለጠፈውን ዜና ዛሬ ጧት አነበብኩ፡፡ ማለፊያ ዜና ነው፡፡ ሕዝባዊ ዐመፅ አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ማንም ይዘዘው፣ ከየትም ይታዘዝ ዋናው ዓላማው ነውና ሁሉም ዜጋ ሊያከብረው ሊታዘዘውም ይገባል፡፡ እናም ላለፉት ጥቂት ቀናት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች የተካሄዱ ሕዝባዊ ዐመፆች የወያኔውን የወሮበሎች መንግሥት ማስደንገጡን ስናነብ ቆይተናልና በርግጥም የታሰበው ድል ተገኝቶ ከሆነ አድማው መቆሙ በጎ ነው፡፡ ተገኘ የተባለው ድል በርግጥም ተገኝቶ ከሆነ ደስታው የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው፡፡ ይሁንና መከራን ተካፍለን እንደምንኖር ደስታንም ለመካፈል የሚያስችል የአንድነት መንፈስን ብናዳብር ጥሩ ነው፡፡

በዚህ የቄሮዎች ትዕዛዝ በተባለለት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያልገቡኝ አንዳንድ ነገሮች መኖራቸውን መደበቅ ግን አልፈልግም፡፡ ስሜቴን ሳልገልጽ ይህን ዜና በሽፍኑ ወድዶ መቀበልም ኅሊናየ አልፈቀደልኝም፡፡ የዐመፁ ዓላማ ይህን ሀገራችንን ምድራዊ ሲዖል ያደረገውን ግፈኛ፣ ዘረኛና አጋንንታዊ የማፊያ ጉጅሌ(ቡድን)  ለማስወገድ እስከሆነ ድረስ የቄሮዎች ትዕዛዝና የትዕዛዙ አፈጻጸም ሂደት የተጎጂ ወገኖችን አካታችነት በቅጡ የዳሰሰ አልመሰለኝም፡፡ በዚህ ጉዞ የትም መድረስ እንደማይቻልም መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ በማያዛልቅ መንገድ - ጫፉ ድፍን በሆነ ዋሻ - የመጓዝን አደገኝነት ከጅምሩ ካልተረዱ ደግሞ ውጤቱ ዜሮን በዜሮ እንደማባዛት ነው - በዜሮ ፍቅር የመለከፍ አባዜ፡፡ አንዳንድ ኹነቶች ደግሞ በዱባ ጥጋብ በሚመሰል ጊዜያዊ የድል እርካታ ዐይንን ይጋርዳሉ፤ ያኔ መጠንቀቅ ነው፡፡ በዱባ ጥጋብ የቱንም ዓይነት ዘመቻ ድል ማድረግ ቀርቶ በአጭር ርቀት ውስጥ የሚገኝን ኮረብታ መውጣት አይቻልም፡፡ አንዲት ክር አንበሣን አታስርም፤ አንዲት ጠጠርም ጋንን አትደግፍም፡፡ ዘላቂ ድል እንጂ ጊዜያዊ ድል ካንጀት አያስጨፍርም፡፡ ሦስተኛ ዐይናችንን ካልገለጥን ዞረን ዞረን ወደ ድጡ እንመለሳለን፡፡….

በነገራችን ላይ ቄሮ ሲባል ብዙዎቻችን በግልጽ በምንረዳው አገላለጽ “የጎበዝ አለቃ” ለማለት መሰለኝ፡፡ የጎበዝ አለቃ እና ቄሮ መገናኘት ካቃታቸው ወይም እንዳይገናኙ አንዳች ደንቃራ ከተፈጠረ በመሃላቸው የሆነ ወያኔዊ ንፋስ ገብቷል ማለት ነው፡፡ የወያኔን ንፋስ ሳያስወጡ ደግሞ በቄሮና በጎበዝ አለቃ ያልተጣጣመ የተናጠል የትግል ጉዞ የወያኔን ዕድሜ ማርዘም እንጂ የሕዝብን ሰቆቃ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስቆም አይቻልም፡፡ ህልም ነው፡፡ ዛሬ የኦሮሞ ቄሮ ይነሳና አንድ ነገር ያዛል፤ ነገ ደግሞ የአማራ የጎበዝ አለቃ ይነሳና ሌላ ነገር ያዛል፡፡ በዚህ መሀል ወያኔ ሠርግና ምላሽ ይሆንለታል፡፡ ከዚህ አንጻር እነዚህ የአማራና የኦሮሞ እንቅስቃሴዎች - እንደ ድፍረት አይቆጠርብኝና - በሕወሓት የበላይነት የሚታዘዙ አለመሆናቸውን መረዳት እስከሚያቅተኝ ድረስ እየተቸገርኩ ነኝ፡፡ ምን ላድርግ - “እባብን ያዬ በልጥ በረዬ” እንደምንለው እኮ ሆኖብኝ ነው፡፡ ቄሮዎችን የሚያሰማሩት ኃይላት ማዘዣ ጣቢያቸው አንጨቆረር መሆኑ እንዳለ ሆኖ ሕዝብን እየከፋፈሉ ድራሽዋ የጠፋችን የጋራ ነፃነት ለማስገኘት በተፈናጅራ የትግል ሥልት ማታገል ህልም እንኳን መሆን የሚያቅተው ጭልጥ ያለ ቅዠትና ቅብዥር ነው፡፡ ለነገሩ ወያኔ በሕዝባዊ ዐመፅና በሰላማዊ ትግል (ሲቪል ዲስኦቢዲየንስ) የሚወድቅ ቀላል ቡድን አይደለም፡፡ ዓለም አቀፉ የፀረ ኢትዮጵያ ኃይል ከጎኑ የተሰለፉለት ከባድ የኢትዮጵያ ጠላት በመሆኑ በሰላማዊና በተበታተነ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሕወሓት ይወድቃል ብሎ ማሰብ በትንሹ ቂልነት ነው፡፡ ሕወሓት ልክ እንደ እስካሁኑ ሁሉንም ተቃዋሚ ተራ በተራ እንደዘንዶ ይውጣል እንጂ በመለያየትና እርስ በርስ በመነታረክ ለውጥ አናመጣም፤ ደግሞም ከተቃዋሚዎች አለመስማማትና በቃላት ጦርነት ከመጠዛጠዝ በተጓዳኝ እንኳንስ ከ14 እና ከ15 ሺህ ማይሎች በሚታዘዝ የሳይበር ጦር እዚሁ ሆነን በአካልና በቅርበት ታግለን ከጣልነውም እሰዬው ነው፡፡ አያያዛችንን እያዩ ወያኔዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ጭብጦዎቻችንን ቀምተውናል፤ እናም በመንጌ አማርኛ ወያኔዎች ንቀውናል - ሊንቁንም ይገባል፡፡ የተናቀ ኃይል ደግሞ ሲከፋፈል የበለጠ ይናቃል፡፡ መሣቂያ መሣለቂያም ይሆናል፡፡ ጥረታችን ሁሉ በግልጽ የሚናገረው የወያኔ መሣቂያ እንደሆንን ዕድሜ ይፍታህ ለመቆየት መወሰናችንን ነው፡፡ የብዙዎቻችን ምርጫ “በተናጠል ታግለን የግል ፍላጎታችንን በሕዝብ ጫንቃ ላይ መጣል ካልቻልን ወያኔ ዕድሜ ልኩን ይግዛ!” የሚል ይመስላል፡፡ ይህ ደግሞ ባልጠጣው ላደፍርሰው ዓይነት የጥጋበኛ አውራ ዶሮ አስተሳሰብ ነው፡፡ ከዶሮነት እንውጣ!

የምቃወማቸውን አንዳንድ ነጥቦች ቀጥዬ ላስቀምጥና በርግጥም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውን የምታስቡና የምትጨነቁ ወገኖች ይህን ትግል የምታራምዱ ከሆነ ጊዜ ሳያልፍባችሁ መንገዳችሁን አስተካክሉ፤ ከወያኔያዊ ተፅኖዕም በአፋጣኝ ውጡ፡፡ እንዲህ የምለው የትግሉን ዕድሜ አታንዘላዝሉት ለማለት ፈልጌ እንጂ ሀገራችን ከነዚህ ነቀዞችና ምሥጦች ነፃ አትወጣም የሚል ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ኖሮኝ አይደለም፡፡ አንገቱ በሠይፍ የተቀላው፣ ደረቱ በጦር የተወጋው፣ ትውልዱ በመርዝ የተበከለው የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላኩ በሶ አልጨበጠምና በቅርብ የራሱን “መሲሆች” ይልካል ብዬ በሙሉ ልብ አምናሁ፤ ነፃነታችን የቀን ጉዳይ እንጂ እንደተሰወረ የሚቀር አይደለም፡፡ ካነበብኩት ዜና በአንድ ወይ በሌላ መልክ የመሰጠኝን ሃሳብ መጥቀሴን ልቀጥል ፡-


እናም የቄሮው የተቀናጀ አድማ ዛሬ በ3ኛው ቀን እነዚህን ግቦች መምታቱን ገምግመን ተገንዝበናል። የአድማው ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ በጎረቤት ሃገር ከተሞች ጭምር ሳይቀር መታየቱን ገምግመናል። ስለሆነም የአድማው ውጤት በሶስተኛው ቀን አጥጋቢና በ5ኘው ቀን ይጠበቅ ከነበረው ውጤትም በላይ ሆኖ በመገኘቱ፤በዚሁ በ3ኛው ቀን በተደረገው ግምገማ መርሃ ግብሩን መከለስ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። (አጽንኦት የተጨመረ)

ይህን መግለጫ የጻፈና ያጻፈ ወገን ያላገናዘበው ብዙ ነገር አለ፡፡ በመጀመሪያ እንደወያኔ የስሜት ፈረስ መጋለብ የት እንደሚያደርስ አላወቀም፡፡ የጸሐፊው ዓላማ በጣም ግልጽ ነው - ‹ግልብ‹ ነው አላልኩም፡፡  የጎረቤት ሀገር የሚባለው ኬንያንና ሱዳንን በመሰሉ ከተሞች ላይ የዚህ ዐመፅ ተፅዕኖ ጥላውን አሣርፎ ቢሆን ነው፡፡ እዚህ ላይ መባል የተፈለገው በወያኔ አከላለል በአማራውና በሌሎች የሀገራችን ከተሞች ለማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የአንዲት እናት ልጆች መካከል ልዩነትን ለመፍጠር ታስቦ የተቀመረ ሽል መንጣሪ  አነጋገር ነው፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ይህን መግለጫ የከተበ ሰው አባይ ፀሐዬ ወይም አባይ ወልዱ አለዚያም አርከበ ዕቁባይ መሆን አለበት፡፡ በአማራና በኦሮሞ እንዲሁም በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ በወያኔ አማካይት የሚወርደውን የመከራ ዶፍ የሚያውቅ ኦሮሞ ታጋይ ይህን ከፋፋይ ጽሑፍ ወደ ሚዲያ ይልካል ብዬ ማመን በበኩሌ ይከብደኛል፤ ምን ጥቅም ሊያገኝ? እርግጥ ነው - የሕዝቡን ቁስል የማይረዳ፣ በውጭ እየኖረ ከመከራና ከስቃያችን የማይጋራ ቅንጡ ዜጋ ከዚህም በላይ ሕዝብን ለመከፋፈል ቢሞክር ሌላ ዓላማ ሰንቆ ሊሆን ይችላልና ብዙም አይፈረድበትም፡፡ ለማንኛውም  እውነቱን የምታውቁ ወገኖች በአፋጣኝ ጣልቃ ግቡና ከነዚህ መሰል ቅንጦተኞች ሤራና ደባ ገላግሉን፡፡ አንዱ ሌላውን ያገለለ የግል ሩጫ ስሜትን ከመግለጽና  በግል ጥቅምና ፍላጎት ላይ ያነጣጠረ ምኞትን ከማንጸባረቅ ባለፈ ኢትዮጵያ ውስጥ ፋይዳ ያለው ነገር አያመጣም፡፡
እኔ እውነቱን ልንገራችሁ፡፡ ይህን ጽሑፍ የምትጽፉ ወይም የጻፋችሁ ወገኖች በዕድሜ ምናልባት ልጆቼ ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ እናም በዕድሜ ትንሽነታችሁ ምክንያት ሊሆን ይችላል ሕዝቡን በፍጹም አታውቁትም፡፡ ሕዝቡ አሁንም አንድ ነው፡፡ የሚቁነጠነጡትና የሚረብሹት የወያኔን አብሾ ሳይወዱ በግዳቸው የተጋቱ ጥቂት ወጣቶችና ጎልማሣዎች ናቸው፤ ከእውነቱ ብዙ በመራቃቸውና በሚጥበረብር የራሳቸው ዓለም ውስጥ የሚኖሩ በመሆናቸው እነሱም ያሳዝናሉ - ከመርገም ይልቅ ታዲያ “እግዚአብሔር ወደ አቅላቸው ይመልሳቸው” ብለን መጸለይ አለብን፡፡ ለዚህን መሰሉ ቅዠታቸው መሠረትም በርግጥ ለሕዝብ አስበውና ተጨንቀው ሳይሆን ያቺው ሥልጣንና ሥልጣን ቢይዙ የሚፋጠን የሚመስላቸው ወደ ሀብቱ የሚደረግ ጉዞ ናቸው፡፡ እንጂ መገንጠል ምን ያህል ተምኔታዊና ቅስምን ሰባሪ እንደሆነ ከቅርብ እስከ ሩቅ በሚታዩ ነባራዊ እውነታዎች ሳይገነዘቡት ቀርተው አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ዋና የሀገራችን ራስ ምታት አንፃር በዚህ የዘር ልክፍት ያልተጠመዳችሁ  እነ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣና መሰል ብርቅዬ ኢትዮጵያውያን የበኩላችሁን እንድታደርጉ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡


የኦሮሞ ትግል ግቡን የሚመታው ህዝቡን ራሱ በመረጣቸው መሪዎቹ አማካይነት መተዳደር ሲጀምርና ፊንፊኔን ጨምሮ ሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች ከህዝቡ የወጡ በወጣ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ስር ሲዋቀሩ ነው።


የኦሮሞ ትግል ግቡን የሚመታው ኢትዮጵያ በጠቅላላው ከወያኔ ናቡከደነፆራዊ አገዛዝ ነፃ ስትወጣ ነው፡፡ ከ80 በላይ የሚገመት ብሄርና ብሔረሰብ አቅፋ በያዘች ሀገር ውስጥ አማራ ወይ ኦሮሞ ነፃ ወጥቶ ሌላው ትግሉን የሚቀጥልበት ሁኔታ በፍጹም የለም፡፡ ይህን መሰሉን ወያኔያዊ አካሄድ በአፋጣኝ መለወጥ ይገባል፡፡ በምንም መንገድ እውን ስለማይሆን፡፡ እንተዋወቃለን፡፡ ኦሮሞና አማራ፣ ትግሬና ጉራጌ፣ ከምባታና ወላይታ ሁላችንም በተለይ ማታ ማታ አንድ ነን፡፡ በትዳር፣ በመሸታ ቤት፣ በሀዘንና በደስታ፣ ወዘተ. በእስካሁኑ ሁኔታ የሚነጣጥለን ያልተገኘ የእግዚአብሔር ውህዶች ነን፡፡ ከአሁን በኋላም ማንም አይነጣጥለንም - ከወያኔ ወዲያ ነጣጣይ ላሳር ነበርና በዚህ ከአሁን በኋላ ያለመነጣጠል ተፈጥሯዊ ቁርኝታችን መተማመን እንችላለን፡፡ ተስፋ መቁረጥ የሚፈልግ መብቱ ነው - እኛን መለያየት የማይቻልና ህልምም መሆኑን ተረድቶ ተስፋውን ጎማምዶ ይጣል፡፡ ቁርቁስ ደግሞ የትም አለ፤ እንኳንስ ሁለት ሰዎች የአንድ ሰው ሁለት እግሮችም እየተጣለፉ ጊዜያዊ ግርንጭት ይከሰታል፡፡ ግጭት በተፈጠረ ጊዜ ሁሉ ግን ሀገር አይገነጣጠልም፤ ሕዝብም አይበታተንም፡፡ መበታተን የሚጠቅመው ግለሰቦችን እንጂ ማኅበረሰብን እንዳልሆነ ከሩቅም ከቅርብም የዓለማችን ታሪክ ብዙ ተምረናል፡፡
ድል ለኦሮሞ  ህዝብ !
ኦሮሞ  ቄሮ
የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አይነጠልም፤ ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ፈጣሪዎች አንዱና ዋናው ግንድ ነው፡፡ ኦሮሞ ያልተቀላቀለበት የኢትዮጵያ ጎሣና ነገድ የለም፡፡ ይህን በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ውስጥ የሰረጸ ደም ነጥሎ የተለዬ ኅልውና ለማላበስ መሞከር ደግሞ የዘፍጥረትን መጽሐፍ ለመለወጥ እንደመሞከር ያለ ጀብደኝነት ነው፡፡ በማንኛውም መሥፈርት የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተለዬ አይደለም፡፡ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ዋና ገዢና አስተዳዳሪ ሆኖ እስከ ደርግ ውድቀት ድረስ የዘለቀው ኦሮሞ ከአጋሩ ሌላው የሀገራችን ሕዝብ የተለዬ ጥቅምም ሆነ ፍላጎት የለውም፡፡ ለዚህ ቅንና ሀገሩን ወዳድ ሕዝብ እውነተኛ ዴሞክራሲን እንጂ አዲስ መጥ ብሔርኝነትን በግድ ጭኖ ከወንድምና እህቶቹ ጋር ለዳግም ግጭትና ዕልቂት የሚጋብዘው መሠሪ ኃይል -  አዛኝ ቅቤ አንጓች  አያስፈልገውም፡፡ ኦሮሞው ከሌላው ወገኑ የተለዬ ድልም ሆነ ሽንፈት አጋጥሞት አያውቅም፡፡ የዘፈን ዳር ዳሩ እስክስታ ነው ይባላልና ይህን ተዋልዶና ተዋህዶ የኖረ ሕዝብ ከሌላው ጋር ቅራኔ እንዲገባ ከሚያደርግ ቅስቀሳና ስብከት እንቆጠብ፡፡ “ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጢጥ” እንዲሉ ሆኖ ገና ለገና የሕወሓት መንበር የተነቃነቀ ስለመሰለ ብቻ ሌላ እሳት ውስጥ የሚሞጅረንን ትልም አንከተል፡፡ ከመነሻው ወያኔ በዚህ ዓይነት የትግል ሥልት የበለጠ ሥር እየሰደደ ዘላለማዊነቱን ያጸናል እንጂ አይወድቅም፡፡ በዘር እየተደራጁ ወያኔን ለማስወገድ መሞከር ያቺን የበሬው እንትን ይወድቅልኛል ብላ እሰው በረት ደጅ ድረስ እየተጃጃለች የሄደችዋን ቀበሮ መሆን ነው፡፡ ልብ ይስጠን፡፡ ከአንታጀችን ለፈጣሪ እንጸልይ፡፡ ቀኑ ቀርቧል፤ ለቀኑ ምቹ እንሁን፡፡ ባንመች እንደ አረም ተነቅለን የምንጣለው እኛው ነን፡፡ ሳይለወጥ እንዳ የሚያረጅ ድንጋይ ብቻ ይመስለኛል፡፡ ሰው ደግሞ በሥ ተፈጥሮው ከድንጋይ በብዙ እጅ የተሸለ ነው፡፡ ጥላቻንና ቂምን ከሰውነታችን አውጥተን በፍቅር ጠበል ራሳችንን እናድስ፡፡ ክፋትን ለክፉው እንተወው፤ ለኛ ግን ደግነትንና ፍቅርን፣ መተዛዘንንና መተሳሰብን ገንዘባችን እናድርግ፡፡ ያኔ የጨለማው ኃይል ከኛ በሺዎች ኪሎ ሜትሮች ይርቃል፤ አሁንም ያኔ የፈጣሪ በረከትና ቸርነት በየደጃችን ሞልቶ ይፈሳል፡፡ በቃ፡፡
 Posted at Ethio Semay