Thursday, December 21, 2017

ዶጋሊ ላይ የአሉላን ሃውልት በቦምብ አፍርሶ በጣሊያኖች የመታሰቢያ ሓውልት ላይ የጣሊያኞችን ባንዴራ እንድውለበለብ ያደረገ ትግሬው ኢሳያስ አፈውርቂ “ፒያሳ ዴ ቺንኩዌ ቼንቶ” አደባባይ ላይ ጣሊያኞችን ያራወጠ ጀግናው ኤርትራዊው ዘርአይ ደረስ ከመቃብር ተነስቶ ቢያየው ምን ይለው ነበር?



ዶጋሊ ላይ የአሉላን ሃውልት በቦምብ አፍርሶ በጣሊያኖች የመታሰቢያ ሓውልት  ላይ የጣሊያኞችን ባንዴራ  እንድውለበለብ ያደረገ ትግሬው ኢሳያስ አፈውርቂ “ፒያሳ ቺንኩዌ ቼንቶ” አደባባይ ላይ ጣሊያኞችን ያራወጠ ጀግናው
ኤርትራዊው ዘርአይ  ደረስ ከመቃብር ተነስቶ ቢያየው  ምን ይለው ነበር?
ጌታቸው ረዳ

ራስ አሉላ እና ደጃዝማች  ዘርአይ ደረስ (የፎቶውን ምንጭ ያገኘሁት  ክቡር ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ስለ ግል ህይወታቸው በጻፉት ማስታወሻ መጽሐፍ ከወዳጅ የተላከልኝ::

ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት ለዚህ ትችት መነሻ ሊሆነኝ የቻለ የኔን ጽሁፎች የሚከታተሉ አንባቢዬ ወዳጄ አቶ ዳኜ ታደሰ ከሚኖሩት አገር የሚከለተውን መልእክት በደብዳቤ ስለላኩልኝ መነሻ ሆኖኛል። እንዲህ ሲሉ ባጭሩ ቁጭታቸውን ይገልጻሉ። ሰላም ውድ አርበኛው ጌታቸው ረዳ ሰላምታዬና ምስጋናዬ ይድረስህ። ዛሬ የምልክልህ አንጀቴ ያሳረረኝ እና ሁሌም ዕረፍት የነሳኝ ነገር የኢትዮጵያ ጀግኖች፤ የአፍሪካ ሕዝብ መመኪያ የሆነው የዶጋሊ ጦርነትና ታሪክ በማንኳሰስ ለጣሊያኖች አድሮ የራሱን ማንነት ያራከሰ ወራዳውና  ባንዳው ኢሳያስ አፈወርቂ “ዶጋሊ” ላይ ወራሪ ጣሊያኖችን ድል የነሱበትን የራስ አሉላን ሃውልት መታሰቢያ በቦምብ አፍርሶ በምትኩ የጣሊያኖችን መታሰቢያ ሃውልት ላይ የጣሊያን ባንዴራ እንዲውለበለብ ያደረገው ፎቶ ስመለከት መላ ሰውነቴ በንዴት ይቃጠላል፡ ይኸው እስኪ ይህንን ንደቴን አብረህ ተካፈለኝ። ብለው ከላይ የሚታየው የጣሊያኖች ሃውልት በዶጋሊ ልከውልኝ ስመለከት ንደቴ እኔንም ስለቀሰቀሰብኝ አንባቢዎቼም አብራችሁን እንድትመለከቱት እና በጣም አስገራሚ ቅጥረኛነትና ራስን የመክዳት በሽታ ምንነት እያሰቃየው ያለው መነሻው ምክንያቱን ለመፈለግ  የአእምሮ ሃኪሞች በኢሳያስ አፈወርቂ ባሕሪና ሕሊና ላይ ጥናት እንዲያካሂዱበት ይህ መልእክት እያስተላለፍኩ፤ እውነት ሃኪሞች የዚህ ሰው በሽታ ቢመራመሩ ትልቅ “ሪሰርች’ ግኝት ይሆናል ብየ እገምታለሁ። አንደኛው ፎቶ “ከረን” ውስጥ የሚገኘው የጣሊያኖች መካነ መቃብር ነው። ኢሳያስ ይህንን መካነ መቃብር አትክልቶችን በመትከል፤ውሃ እያጣጣ ሰራተኞች ተቀጥረውበት በእንክብካቤ እየተጠበቀ ያለው የወራሪዎች መካነ መቃብር ነው። ከላይ አናቱ ላይ ያለው ደግሞ 500 ጣልያኖች አሉላ የፈጁዋቸው የወራሪዎቹ የጣሊያኖች መካነ መቃበር ነው። በስተግራ በኩል የጣሊያን ባንዴራ ሲውለበለብ፤በቀኝ በኩል ደግሞ የሻዕቢያ ባንዴራ አማክለውታል። አካባቢው ዙርያ ሃውልቱ ንጣፍ በኢሳያስ ትእዘዝ የገንዘብ ወጪ ተደርጎ ኤርትራዉያን የህንጻ ሥራ ባለሞያዎች ተመድበው አስፈላጊው እድሳት እና አንክብካቤ ተደርጎለታል። እግዚኦ ተሳሃለነ ክርስቶስ!!!

ፈረንጆች  “ባድ ኣፕል” የሚሉት ነገር አላቸው።  ወላጆቻችን “የተረገመ ሽንት” እንደሚሉት አባባል። ኢሳያስ ትግሬ ነው። ራስ አሉላም ትግሬ ናቸው። ያውም የኢሳያስ አባት  ከሚወለዱበት አውራጃ “ተምቤን”። ሮማ ፒያሳ ቺንኩዌ ቼንቶ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ በተባለው ዶጋሊ ላለቁት የኢጣልያ ወታደሮች መታሰቢያ በተሰየመው አደባባይ ላይ ሦስት የጣሊያን ከፍተኛ ወታደራዊ ባለ ማዕረጎችን አንገት አንገታቸውን ቀልቶ “በዓለም ውስ  ፍጹም ያለተደረገ፤ዓለም ያስገረመ ታሪክ” የሰራ በኢትዮጵያዊነቱ እየፎከረ በሕዝቡ ፊት ቆሞ ጎራዴው ሲያወዛውዝ የጣሊያን ሕዝብን ወታደሮች  በየቦታው እገሬ አውጭን እያለ ሲሸሽ አንድ ፈሪ ጣሊያን ከሩቅ አነጣጥሮ በጥይት ቶኩሶ እግሩ ያቆሰለውን ሌላው አራተኛውን ጣሊያናዊው ሲጠጋው በጎራዴው ቀልቶ የራስ አሉላን ጅብዱ በጣሊያን 2ኛው ዶጋሊ አደባባይ ላይ የተቀዳጀው የ21 አመቱ ጎልማሳ ወጣት ኤርትራዊው ደጃዝማች “ዘርአይ ደረስ” መካካል ያለውን ልዩነት ላጤነ ተመራማሪ “ኢሳያስ አፈወርቂን” የተረገሙ ሽንቶች” ብለው ወላጆቻችን ከሚጠሩዋቸው ፍጡራን አንዱ እና ግምባር ቀደም ተጠቃሽ ሰው ነው። ይህ ባህሪ እንዴት ሊከሰት ቻለ? የሚለው ለአአምሮ ሓኪሞችና የልቦና ተመራማሪዎች ሊነግሩን የሚገባ ይመስለኛል። በዚህ ሙያ ያሉ ምሁራን ይህ የኔን ርዕስ መነሻ አድርገው እንደያብራሩልን ጥሪ አደርጋለሁ።

ኢትዮጵያ የተለያዩ ሽንቶች ወልዳለች። የተባረኩ እና የተረገሙ። ብዙውን ጊዜ የነዚህ ብሩካን ጅግንነት ሲያረክሱ የምናያቸው ደግሞ የገዛ ልጆጯ ናቸው። ይባስ ብሎ እንዲህ ያለ ክህደት ውስጥ የሚገቡት ብዙዎቹ ኤርትራኖች ሳይሆኑ “ትግሬዎች” መሆናቸው ሃቅ ነው። ለዛሬዋ ኤርትራ መከራ ምክንያት የሆኑት ወልደ አብ ወ/ማርያም፤ ኢሳያስ አፈወርቂ ሙሉ በሙሉ ትግሬዎች ናቸው። ዘርኣይ ደረስ ፤ ንቡርእድ ዲሞጥሮስ፤አስፍሃ ወ/ሚካል፤ ሎሬንሶ ታእዛዝ፤ ደ/ች አፈወርቅ ወ/ሰማያት ስማቸው ለመጥራት የሚበዛብኝ የመሳሰሉ በርካታ ጀግኖች “ኤርትራዉያን”  ናቸው። በሁለቱም ቡድኖች ያለው ባህሪና ታሪክ ስንመለከት እጅግ የሚርም ነው። የተገላቢጦሽ ሆኖ እናገኘዋለን።

ወያኔዎች ሻዕቢያን ለመርዳት ከኢትኦጵያ ጦር ሃይሎች ጋር ለመዋጋት ምጽዋ ከመሻገራቸው በፊት፤ አያቶቻቸው አገራቸውን ከጣሊያን ወራሪዎች ለመከላከል ዶጋሊ ላይ የወደቁትን የአያቶቻቸውን አጥንትና የደረቀው ደም እየረገጡ በማራከስ ተረማምደውበት ነበር ምጽዋ ወደብ ላይ ሄደው  የወንጀል ጦርነት ከፍተው አሳፋሪ የባንዳነታቸው ታሪክ ያስጻፉት። በዳግማይ ወያኔ ተዋጊዎች ምጽዋ ላይ የተካሄደው አሳፋሪ የትግሬዎች ታሪክ፤ ዶጋሊ ላይ በትግሬው አሉላ የሚመራው የትግሬዎች ታሪክ ሲነጻጻር፤እነኚህ የተረገሙ ሽንቶች ምን ያህል ርቀት ሄደው የአያቶቻቸውን አኩሪ ታሪክ እንደደመሰሱትና እንዳራከሱት ለወደፊቱ ዘመን ሲለወጥ መጪው ትውልድ በሰፊው አንደሚዘግበው ጥርጥር የለኝም።

ዓለም የዘገባቸው ታላላቅ የአበሻ ጀብዶች በታሪክ ከሚጠቀሱት  

ከልዑል ጌታዬና ከልዕልት እመቤቴ ጋር በግዞት የመጣነው ወደ ሃያ የምንሆን ሰዎች ነበርን። ቪያሌ ካሜሎቻየሚባል ቦታ ላይ እና ፎሮ ሙሶሊኒየሚባለው ቦታ ላይ አንድ ወደ ሦስት ፎቅ የሆነ ሕንፃ፣ መኪና፣ ሥንቅ በየቀኑ በቁጥራችን ልክ ይቀርብልናል። ከዚያ በኋላ ደግሞ፣ እነ ራስ ጌታቸው፣ ራስ ከበደ፣ አቡነ ይስሐቅ፣ እነዚህ ሁሉ ልዑል ጌታዬ ይምጡልኝእያሉ ከእኛ ጋር ተደባለቁ። ልዕልት እመቤቴ ሥንቁንም ምኑንም ጭነው በመርከብ ነበርየተጓዝነው። ከምፅዋ ወደ ናፖሊ፣ ከዚያ ደግሞ በባቡር።

ልዕልት በጣም አዋቂ ነበሩና የሚያስፈልገውን አደራጅተው አስጭነው ነበር። ሥንቅ በሙሉ ከአገራችን በስደት አገር በነበርንበት ጊዜ ምግብ ምንም የጎደለ ነገር አልነበረም። እነዚያም እኛ ጋር የተጨመሩት በዚሁ በእኛ ሥንቅ ብዙ ጊዜ ተገልግለዋል። የዕለቱን ሥንቅ ደግሞ ከዚያው አገር ታዝዞልን በቀን በቀን ይመጣልን ነበር።ለሥንቃችን አመላላሽም ሆነ ባልደረባ አንድ የኤርትራ ወንድማችን ተመድቦልን ነበረ። እሱም ዘርዓይ ደረስ የሚባለው ነው። ዘርዓይ ደረስ በዚያን ጊዜ ወደ ሃያ አንድ ዓመት ዕድሜ የሚሆነው ወጣት ነበረ። እሱ እዚያ ሲመጣ እኔ ገና የዘጠኝ ዓመት ልጅ ነበርኩ። የጣልያን ትምህርት ፊደል መጀመሪያ ያስቆጠረኝ እሱ ነው። እልዑል ጌታዬ ዘንድ ከሰዓት በኋላ ደብተሩን ይዞ ይመጣና ሲጽፍና ሲወያይ ይውል ነበርና ከእሳቸው የማይለይ መሆኑን እመለከት ነበር። እንግዲህ አሁን ስገምት ታሪክ የማጥናት ባሕርይ እንደነበረው ነው። ታዲያ ከዕለታት በአንዱ ቀን ወደ ናፖሊ ተልኬ መሄዴ ነውየሚል ነገር ለልዑል ጌታዬ ይነግራል፤ ለካ መሰናበቱ ነው። ለአንድ ሳምንት ያህል መሄዴ ነውሲላቸው፤ ምን ልታደርግ ነው የምትሄደው?ይሉታል። እኛን የሚያስተዳድረው ኮማንዳቶሬ እስከዲዬሬ የሚባለው የውጭ ጕዳይ ሚኒስትሩ 'ለእናቴ ከኢትዮጵያ የመጣ ጐራዴ አለና እሱን ይዘህልኝ ሂድ፣ ለመታሰቢያ ይሁናል' ብሎኝ እሱን ይዤ እየሄድኩ ነኝአላቸው። ዓርብ ማታ እንደዚህ ተሰናብቶን በማግሥቱ ቅዳሜ የደረሰው ነገር አይረሳም። ከሰዓት በኋላ ነው። እኔ በቢስክሌት እዚያ ሜዳው ላይ እየተጫወትኩ አንድ ሻለቃ ቶሬዛኔ የሚባል የጣልያን ዋና ኃላፊ፣ የእኛ ባልደረባ ለጥበቃ እኛ ዘንድ የሚቀመጥ፣ እሱ ጮሆ መንገሻብሎ ሲጠራኝ ሄድኩኝ። ሮጬ ስሄድ፣ በትእዛዝና በቁጣበአስቸኳይ ቶሎ ግባ! ግባ!ግባ!ይለኛል።


(በግዞት ወደ ጣሊያን አገር እንዲጋዙ የተደረጉት ክቡር ራስ ሥዩም መንገሻ ከነቤተሰቦቻቸው እና ሌሎች መኳንንት፤ልዕልቶችና ወይዛዝርት ጋር  በናፖሊ ጣሊያን አገር በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ጊዜ )


ወደቤት ሮጬ ገብቼ በመስኮት በኩል ሳይ፣ እሱ ወደ በር ይሮጣል። በራችን ትልቅ የብረት አጥር ነበር። እዚያ ላይ ብረት ይብለጨለጫል፤ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይታየኛል። ከዚያ በፊት ምንም የሰማነው ነገር ስለሌለ ምን ሆነው ነው? ምን የደረሰ ነገር አለ?እልና ኧረ እዚህ ግድም አንድ ነገር ደርሷል፤ እኔን ግባ!ብሎ ነው ያበረረኝ ብዬ ልዑል ጌታዬን አስጠነቅቃቸዋለሁ። አሁን ግን ሳይ እሱ ራሱ ፊት ለፊት ሄዶ ከዚያ ከበሩ ውጭ ደግሞ ሌሎች ብዙዎች አሉእላቸዋለሁ። ከዚያ ሁላችንም ተደናግጠን ዝም ብለን እናያለን። አንድ ሰዓት ያህል ፈጅቶበት ከዚያ እነሱንም አሰናብቶ ወደ እኛ መጣ። የዚያን ጊዜ ትንሽ ትንሽ ጣልያን ቋንቋ መናገር ጀምሬአለሁ፣ ምንድነው የሆነው?አሉና ልዑል ጌታዬ ወደ ሳሎኑ ወርደው ጠየቁት። አይ ዛሬ እኮ አንድ ትልቅ ነገር ደረሰ፤ በጣም ያሳዝናልአለ።ምን?”“ የእናንተ ባልደረባ፣ እዚህ የነበረው ዘርዓይ ደረስ ሮማ ፒያሳ ቺንኩዌ ቼንቶ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ የተባለውና ዶጋሊ ላለቁት የኢጣልያ ወታደሮች መታሰቢያ የተሰየመው ለገሐር ወደ ናፖሊ የሚሄድ ባቡር ካፖርቱን ለብሶ ይጠብቃል። ባጋጣሚ ከአዲስ አበባ የመጣውን የይሁዳ አንበሳ ሐውልት እዚያ እንዲቆም አድርገውታል። ፔዲስትራሊ እየተሠራ ቆይቶ እዚያች እሱ የቆመባት ቅዳሜ የሚመረቅበት፣ በዓል የሚደረግበት ቀን ነበረ። ያኔ ያልመጣ ጦር፣ ያልመጣ ሕዝብ የለም። ዘፈናቸውም ጭፈራቸውም የሚደንቅ ነበረ። የኢትዮጵያው አንበሳ በሮማውያኑ ተኩላ ተረገጠ! ድሉ የእኛ ነው! ፋሺዝም ለዘላለም ይኑር!እየተባለ በየዓይነቱ ይዘፈናል እያለ እየተነተነ አጫወተን።

እዚያው ላይ እሱ ዝም ብሎ ቆሞ እያለ፣ አንድ ኮሎኔልና ሦስት ሻለቆች ተጠጉት። እዚያ ምን እንደተነጋገሩ አይታወቅም፤ ብቻ የታየው ግን ይኼው ሰው ጐራዴውን ሲመዝዝ ነው። ለእናንተ ነግሮ ነበር፣ ተሰናብቷችኋል መሰለኝ፤ አይደለም? አዎ”“ እንግዲህ አስቀድሞም ጐራዴውን የተሸከመው ካፖርቱ ውስጥ ነበረ ማለት ነው። በቀጥታ ነው የቆመው አይታይም። እዚያ እነሱ ተጠግተውት ሲነጋገሩ በደረሰው ንግግርና ሁናቴ ሊሆን ይችላል፣ ጐራዴውን መዝዞ የኮሎኔሉንም፣ የሦስቱን ሻለቆችም አንገት አንገታቸውን በቁመናቸው እያሉ እየቀላ ጣላቸው። እዚያ ላይ ደማቸው! መቼም የቆመ ሰው አንገቱ ሲቀላ የሚሆነው ይታወቃል። ሁሉ ሕዝብ እዚያ ቦታ ዶጋአሊ 500ዎቹ ያለቁበት መታሰቢያ ነው። ታሪካቸውን ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቁትበጐራዴና በጦር ነው፤ አሁን አንድ ጥቁር ጐራዴ ይዞ የሚቀላ ሲገኝ፣ አንበሳ እዚያ ቆሞ ቁልቁል እያየ፣ ምድር ቁና ሆነች። ሽሽቱ፣ ትርምሱ፣ ድንጋጤው ቁጣው ቀውጢ ሆነ! እንደምንም ብለው በሩቁ እሱን ጠመንጃ ተኲሰው እግሩን መትተውት ወደቀ። እዚያ በወደቀበት ቦታ ላይ የጣለው ሲመጣ እንደዚሁ እሱንም ይዞ አሰናበተው። በኋላ እንደምንም ብለው በዓሣ መያዣ መረብ ተብትበው ይዘው፣ የአንበሳ ፍርግርግ ብረት አምጥተው፣ እዚያ ውስጥ አስገብተው፣ ሮማን በሙሉ እየዞሩ 'አብዶ ነው እንጂ፣ የነፃነት ጥማት አይደለም!' የሚል ስብከት ለማስተጋባት ሞከሩአለና ነገራቸው። አባባም በእውነቱ በጣም በጣም አዝነው፣ እንባ እያነቃቸው አንገታቸውን ወደታች ቀልሰው ዝም አሉ። እኔም ለራሴ ደነገጥኩ። በእርሱ ሕይወት ላይ በደረሰው እያዘንን ቆየን። ሌሊቱኑ ዘርዓይን ከዚያ ቦታ ማጥፋት አለብን ብለው ሳይሆን አይቀርም ያለ የሌለውን እኛ እዚያ ውስጥ የነበርነውን ሰዎች በሙሉ እንዳለን በመኪና ጭነው፣ ሌሊት 30 ኪሎ ሜትር ያህል ከሮማ አርቀው፣ ሰው እማይሰማበት ቦታ ወስደው አገለሉን። ቦታው ቲቮሊ የሚባል በጣም ጥሩ ነበር እንዳጋጣሚ። ግን እንደ ምሽግ ዓይነት ነው። እኛን ለመጠበቅ ሕዝቡ እንዳይጎዳን ለማድረግ አስበው ነው ወደዚያ የወሰዱን። እንግዲህ ማንም ቢሆን የራሱ ወገን ሲጎዳበት መናደዱና ለመበቀል መነሣቱ የታወቀ ነው። በዚያን ቀን የተፈጸመውን ድርጊት ታሪክ በጋዜጣው ሁሉ ስናየው በጣም ተበጣብጠው ነበር። አንድ ሰው እንደዚህ አድርጎ፣ በጐራዴ፣ እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ እንዴት ነው? እኛ ያሳደግነው፣ ያስተማርነው፣ የእኛ ታማኝ ነው ብለን ያልነው፣ እንደዚህ አድርጎ ተጫወተብን፤ ለካ እንደዚህ ያሉ እባቦች ናቸው ወዘተምንም ያላሉት ነገር አልነበረም። እሱ ግን እንደዚህ ያለ ጀግንነት መፈጸሙን በታላቅ አድናቆት አስታውሳለሁ።
 
ርዓይ ደረስ ወደ እስር ቤት ተወስዶ በቂ ሕክምና ስላልተደረገለት በቍስሉ ምክንያት ከጥቂት ወራት በኋላ ሞቷል። ከነፃነት መመለስ በኋላ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የደጃዝማችነት ማዕረግ ሰጥተውታል።
       ክቡር ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም በጣሊያን አገር ዘርኣይ ደረስ ጣሊያንኛ እንዲያስተምራቸው ተመድቦላቸው በነበረበት ዕድሜአቸው።
የኢሳያስ አፈወርቅ ጉድ በዚህ ልደምድም እና የምትበሻጩም፤የምትገረሙም ሁሉ ለምን እንዲህ ያለ ጉድ በትግሬው ተወላጅ በኢሳያስ አፈወርቅ ያውም አሉላ “ወዲቑቡ” የተገኙበት አውራጃ ተምቤን የተገኘ ዘር እንዴት ወደ “የተረገመ ሽንት” ሊለወጥ አንደቻለ ትንታኔአችሁን ለናንተው ትቼ በዚህ በጣም አስገራሚ የወዲ አፈወርቂ ትንሽ ሕሊናነት አስነብቤ እዚህ ልሰናበታችሁ።

ከዚህ በታች የማስነብባችሁ ታሪክ ያደመጥኩት እና አውዲዮውንም የቀዳሁት ባንድ የኤርትራኖች ሚዲያ ሲያስተላልፉት የቀዳሁትን አውድዮ ነው ይህ ታሪክ የማስነብባችሁ። ቃል በቃሉ ነው ወደ ጽሑፍ የማቀርብላችሁ።

<< ኤርትራ ነፃ ወጣች በተባለ ከጥቂት አመታት በኋላ ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ጣሊያን አገር በሄደበት ወቅት፤የጣሊያን መንግስት አስጎብኚዎች ከማን ጋር እንድናገናኝህ ትፈልጋለህ ብለው ለጉብኝቱ ዝርዝር እንዲሰጣቸው ጠየቁት። እሱም ከፋሺስቱ አርሜዶ ጉሌድ አንዲገናኝ በቀጥታ ጠየቃቸው። አርሜዶ ጉሌድም ተጠርቶ አርሜዶ ጉሌድ ጋር ተገናኝቶ ሁለቱም ፎቶግራፍ ተነሱ።አርሜዶ ጉሌድ ማነው? አርሜዶ ጉሌድ ግራዚያኒ ኢትዮጵያዊያንን እና ሊቢያውያንን እያረደ ሲያሰቃይ የነበረ ከዓሰብ ጀምሮ አስከ መላ ኤርትራ ያሉ መንደሮች አልታዘዝም የሚለውን በጭካኔ ሲያርድ ሲያሳንቅ ሲረሽን፤ ሲደበደብ የነበረ በጣም ጨካኝ ፋሺሰት መሪ የነበረ ነው።

የሚገርማችሁ ነገር፤ ምናልባት ሌሎች የአፍሪቃ መሪዎች እንዲህ ያለ አጋጣሚ ቢያገኙ ኖሮ ዘርአይ ደረስ ጀግንንት የሰራበትን አደባባይ (ሮማ ፒያሳ ቺንኩዌ ቼንቶ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ ማለቱ ነው ተናጋሪው) አሳዩኝ ይሉ ነበር።እኔ ብሆን ያንን ነበር ለማየት የምፈልገው እላቸው ነበር እንደ ሰው እና እንደ መሪ። ኢሳያስ ግን የአፍሪካነት፤የጥቁርነት፤የአበሻነት ክብርና ነጻነት ስለማይቀበል በቀጥታ ከአርሜዶ ጉሌድ ጋር አገናኙኝ አላቸው፤እነሱም ደስ ብሏቸው ወይንም “ግርሟቸውም ሊሆን ይችላል” አገናኙት።

አብሮ ካርሞቺ ጋር ፎቶ ተነስቶ ወደ አስመራ እንዲመጣ ግብዣ አደረገለት። አርሜዶ ወደ 90 ዎቹ አመቱ ነበር በወቅቱ። በዛ ዕድሜው ኢሳያስ ባደረገለት ግብዣ መሰረት ወደ አስመራ ለሁለተኛ ጊዜ ዕድል አግኝቶ ሕዘብ ሲጨፈጭፍና ሲያሰቃይ፤ሲያዋርድባት ወደ ነበረቺው መሬት በክብር አንግድነት የኤርትራን መሬት በኩራት እየተረገጣት አስመራ ከተማ ገባ። ይህ ነው ኢሳያስ እና የኢሳያስ ገድል። ምናልባት እናንተ እዚህ እኔን የምታደምጡ አድማጮች “ጊዜው አሁን አይደለም ምናምን ልትሉ ትችሉ ይሆናል። ግዜው አሁን ነው። ኤርትራን እየመራ ያለው ሰው ማንነት ካላወቃችሁ፤ በተለይ በተቃዋሚነት እና በወጣትነት ዕድሜ ክልል ያለ ወጣት ታሪኩና አገሩቱን እየመራ ያለው የሰውየው ባህሪ ካላወቅን እየታገልን ያለነው የዕውር ሩጫ እና ትግል መነሻችን እና ወዴትስ እና በማን መሪነት እንጓዛለን?አሁን ላለንበት ውርድትስ ለምን ተጋረጥን? ብለን መመርመር ካልቻልን፡ የባሰ ውድቀት ውስጥ እያዘገምን ነው እላለሁ። …. ይል እና በመቀጥልም

<….ስለዚህ ኢሳያስ አፈወርቂ የመራው ገድልም ሆነ ስለ ጥቁር ሕዝብም ሆነ ስለ ኤርትራ ሕዝብ ክብር ፈጽሞ የማይቆረቆር አደገኛ ማፊያ እና ለሥልጣን ሲል የአገር እና ሕዝብ ክብርና ነጻነት አሳልፎ ለመሸጥ ሁሉንም ነገር ከማድረግ የማይመሰል እርኩስ ፍጥረት ነው እላለሁ።>> ሲል አንድ ኤርትራዊ በፓልቶክ ሚዲያ ሲናገር የቀዳሁትን የኢሳያሰ አፈወርቂን ጉደኛ ታሪክ፤ አብራችሁኝ እንድትካፈሉ አድርጌአለሁ።

 ይህ ትንሽ ሰው፤ እንኳን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ክብር እና መቆርቆር ይቅር “እመራሃለሁ ብሎት በክብር ይዞት እንደ ፈጣሪያቸው ሲያመልኩት ለነበሩት የኤርትራ ሕዝብም ቢሆን ክብር ያልቆመ ከመለስ ዜናዊ ጋር አብረው  በክሕደት በታሪክ የተዘገቡ የዘመናችን ትንንሽ ሰዎች ናቸው። የልዑል ራስ መንገሻ የሕይወት ታሪክ የላከልኝ የቅርብ ወዳጄ እጅግ አመሰግናለሁ። ጤና ይስጥልኝ።አበቃሁ።  
ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com




                                          

No comments: