Monday, September 26, 2016

በትግራይ ምድር ላይ ጠጅ ሲንቆር ሐዘን እምባ ሆኗል በአማራ ምድር! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopian Semay)


በትግራይ ምድር ላይ ጠጅ ሲንቆረቆር
ሐዘን እምባ ሆኗል በአማራ ምድር!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopian Semay)
Ethiopian Semay- The ugly face of Ethnocentric
በፋሺሰቱ ዘረኛ ‘የወየነ ትግራይ’ ድርጅት የተመራው የትግራይ ብሔረተኛነት፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ “የሳዮናይድ” መርዝ ሆኖበት ለሃዘን፤ለብጥብጥና ለዘር ፍጀት ዳርጎታል።  በመጀመሪያ ሰላም ለሁላችሁ እንደምን አላችሁ? ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት እንደተለመደው አንድ ሁለት አስተያየቶችን ለመሰንዘር እሻለሁ።


በቅድሚያ ለ25 አመት የተደበቀው በአማራ ሕዝብ የደረሰው ሰቆቃና የዘር ጽዳት ጥቃት ገሃድ እንዲሆን በተጨባጭ ማስረጃ አስደግፎ ገሃድ ያደረገው “የጥፋት ዘመን  ከ1983 እስከ 2007 ዓ.ም በዐማራ  ሕዝብ ላይ የተፈጸመ  ዘር ማፅዳት” መጽሐፍ ደራሲ የዘመኑ ምርጥ ጋዜጠኛ (ዲቴክቲቭ ጆርናሊስት) ሆኖ በኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ የተመረጠ ወጣት ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋ የኢትዮጵያ ታሪክ በክብር ዙፋን እንዲመዘግበው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የአማራ ሕዝብ ቀን ወጥቶለት ብርሃን ሲወጣለት ሙሉቀንን የክብር/የኖብል/ሽልማት እንዲሸልመው አሳስባለሁ። ከዚህ ተያይዞ ደራሲው እንደገለጸው በክቡር አቶ ተክሌ የሻው የሚመራው “ሞረሽ ወገኔ” ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ባስቸጋሪ ሁኔታ’ ጥናቱ ሲካሄድ አስፈላጊው የገንዘብ ወጪ እና ምክር በማድረግ በስተጀርባ ሆኖ ጥናቱ እንዲከናወን ቀዳሚው ሚና የነበረው “የሞረሽ ወገኔ” ድርጅት እና ሊቀመንበሩ ምስጋና እና ሽልማት ይገባቸዋል። በመጽሐፉ ዙርያ የተዘገቡት አሰቃቃ የዘር ፍጅት ወንጀሎች ለወደፊቱ እምለስበታለሁ።

ቀጥሎ ለማለት የምፈልገው ሌላ ጉዳይ፤ ሰሞኑ ዋሺንግተን ውስጥ የተካሄደው የኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዘጋጆቹ እና በሰልፈኞቹ እጅግ እንደኮራሁ እና እንደተደሰትኩ ለመግለጽ እወዳለሁ። ለምን ለመጀመሪያ ጊዜ? የሚል ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል። ሰልፈኛው ያሸበረቀበትና ያስተጋባው መፈክር “ካሁን በፊት ስተችበት የነበረው ዝብርቅርቅ ያለ የጠላቶቻችን ባንዴራዎች፤ የኦነግ (የግብፅ/ዐረቦች ባንዴራ የያዘ ቀለም)፤ የሻዕቢያና የኦብነግ ባንዴራዎች ከኢትዮጵያ ሰንደቅዓለማ ጋር እያዳቀሉ  ኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማን ክብር የሚያንኳስስ ለበርካታ አመታት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረግ እንደነበር ባለፈው ሰሞን ክፍል ሁለት (ሳብቨርዥን/ብከላ) በሚል የጻፍኩትን ትችቶቼና ፎቶግራፎችን በማሳየት ‘አምርሬ በተደጋጋሜ ለበርካታ አመታት መቃወሜን ታስታውሳላችሁ።” ዛሬ የኔን ትችት እና ምሬት ሰምተው ለመጀመሪያ ጊዜ የጠላቶች ባንደራዎችን በማስወገድ “ኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማን ክብር ብቻ ከፍ አድርጎ ያንጸባረቀ ሰላማዊ ሰልፍ በመደረጉ እጅግ ደስ ብሎኛል።” ለመጀመሪያ ጊዜ የጠላት ባንዴራ እንዳይቀላቀል አግዳችሁ የሚያኮራ አሸብራቂ ኢትዮጵያዊነትን ስላንጸባረቃችሁና ምሬቴን ስላዳመጣችሁኝ አዘጋጆች አጅግ አመሰግናለሁ።

ሌላው በድረገጾች የተዘረጋው መነበብ ያለበት ጽሑፍ ልጠቁማችሁ። ካሁን በፊት ስማቸው ሰምተናቸው የማናውቅ አዲስ መጤ ጸሐፊዎች ተወሽቀውበት ከነበረው የምቾት ማማቸው ወጥተው በረካታ ጽሑፎችን ለዓይናችን ንባብ እያበረከቱ ነው። ጠቀሚ ትችቶም ናቸው። ሆኖም አጠንክሬ አንባቢዎቼ እንድታነቡት የምመከራችሁ በጣም አስፈላጊና የወደፊቷ ኢትዮጵያ መከተል ያለባት አስተዳደርና የመፍትሄ ሃሰባች ከሰነዘሩት ጠቃሚ (እኔ የወደድኩት) ጽሑፍ ‘ገለታው ዘለቀ’ የተባሉ ጸሓፊ የኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓት ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች- እንደመግቢያ - ገለታው ዘለቀ”  የጻፉትን ጽሑፍ ብታነብቡ ብዙ ቁም ነገሮችን ታገኙበታላችሁ ስለሆነም እንድታነብቡት እጠቁማለሁ።

እንዲሁም፦ ወያኔ የመኢአድን አባላት እና አመራሮች ሲያፍን ኢሳት ደግሞ መኢአድ ላይ የሚደርሰዉን የግፍ በደል ያፍናል። በመላዉ አለም እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለዉ ሕዝብ ስለ መኢአድ ተጋድሎ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ብሎ የምንልክለትን መረጃ ሁሉ ወደ ቅርጫት ይወረውረዋል።” በማለት አምርሮታቸው በሻዕቢያ አሞጋሹ ‘ኢሳት’ ቲ/ቪ እና ራዲዮ ወቀሳቸውን የሰነዘሩት የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት /ሀላፊ አቶ ለገሰ /ሃና በምሬት ኢሳትን አምርረው  የወቀሱበትን ሰነድ ለማንበብ “ኢሳት ቴሌቪዥን ጣቢያ ከመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ከፍተኛ ወቀሳ ደረሰበት” የሚለውን ዜና  ለማንበብ  
ወልቃይት.ካም welkait.com ድረገጽ በመግባት http://welkait.com/?p=6227 በመጠቆም ያንብቡ።

አሁን ወደ ርዕሳችን ንግባ።
ሄንሪክ ሄደን የተባሉ ሊቅ እንዲህ ይላሉ፦ “እንደሰው የሚያስብ አህያ እንኳን አይቼ ባላውቅም፤ እንደ አህያ የሚያስቡ ሰዎች ግን አጋጥመውኛል” ይላሉ። ይህ አባባል የዘመናችን አስገራሚ ሰዎችን የሚያመላክት ነው። ባሕላችን፤ይሉኝታችን በ25 አማታት እንዴት አንደተበከለ ባለፈው ከፍል ሁለት (ክፍል ) ኢትዮጵያዊያኖች ‘በዘረኛነት ባሕር እየዋኙ ነው’! ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ? ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ  Ethiopian Semay)  በሚል የተቸሁበት ትንታኔ ስታጤኑት፤ ዜጎቻችን ይሉኝታን ጥለው ከሰብአዊ አስተሳሰብ ውጭ በሆነ መንገድ ወገኖቻቸው በፋሺስቶቹ አረመኔአዊ የወያኔ ጥይት ሲቆሉ፤እናቶች በልጆቻቸው ሬሳ ላይ ተጋድመው በወረባላ አረመኔ የወያኔ ‘ጎስታፖ’ ፖሊሶች በዱላ ሲደበደቡ ደንታ የማይሰማቸው ወገኖች እያየን ነው።ይህ ደግሞ  ኢትዮጵያ ውስጥ የታየ ነው። 
The Tigre Fascism & the suffering of the Amhara  Ethiopians- Ethiopian Semay
የአማራ መሕበረሰብ ለ25 አመታት እጅግ አሳዛኝ በሆነ የዘር ማጽዳት ሲከናወንበት ቆይቶ በመጨረሻ በቅርቡ፤ ‘በቃኝ ብሎ’ በአጥቂዎቹ ላይ ሲያምጽ የትግራይ ወያኔ ‘ጎስታፖ’ ነብሰገዳዮች፤ “የአማራን ወጣቶች፤ታዳጊ ህጻናት እና አዛውንቶች” በጥይት እየቆሉ የተቀሩትም ማታ ማታ ወደ እየመንደሩ እየሄዱ በጭለማ እያፈኑ ብዙ  አማራዎችን እያጠፉ ባለበት ወቅት፤ ትግራይ ውስጥ ለቅዱስ ዮሐንስ እና ለመስቀል በዓል አከባብር ጠጅ እየተንቆረቆረ፤ ሽግ በርቶ፤ ከበሮ እየተነተረ ፤ቀጤማ ተጎዝጉዞ፤ ነጭ ልብስ ተለብሶ እስክስታ ወርዶ፤የትግራይ አደባባዮች በዕልልታ ሲቀልጡ ማየት አጅግ አሳዘኝ ክስተት መሆኑን እኔ እንደ ትግሬነቴ እጅግ አሳፍሮኛል፤ አሳስቦኛል። ይህ መወገዝ ያለበት እጅግ አስገራሚ ክስተት የትግራይ ማሕበረሰብ ለወደፊቱ ከተቀሩት ወገኖቻችን ያለንን ቁርኝት ወዴት እያመራ እንዳለ በጥሞና እንዲያጤኑት አሳስባለሁ። ብሔረተኛ ይህን ተሎ የሚገነዘብ አይመስለኝም። ታረክ ነፃ እንዲያጣን ግን እያሳሰብን ነው።

ዜጎች በጥይት እየተቆሉ፤ ከየቤታቸው እየታደኑ መግቢያ መውጫ አጥተው ባሉበት ወቅት ‘አረመኔ’ የወያኔ መሪዎች ካድሬዎቻቸው፤የዜና አውታሮቻቸው እና አዝማሪዎቻቸው ሌሊቱ ሙሉ እስከንጋቱ የሚቆይ የጭፈራ፤የደስታ እና የጥጋብ ማስታወቂያ እየዘረጉ ይጨፍራሉ፤ አማሮች ሌሊት ሙሉ እስከንጋቱ የሃዘን እምባ ያቀርራሉ። ይህ አሳዛኝ ክስተት ለመግለጽ የሚያዳግት ክስተት በታሪካችን ይከሰታል ብሎ የገመተ ይኖር ይሆን?
Partying and dying the outcome of  TPLF Fascism in Ethiopia
የሰሞኑነን የሰማነው እና የነበብነው አናቋሪ የወያኔ ሴራ እልከት።
የትግራይ ወላጆቻችን፤ወንድሞቻችን እና ዘመዶቻችንን ሳት እና በዘይት እየጠበሰ፤ ሰውን በማሰቃያት ሲባልግ የነበረ ደም የጠማው በጎስታፖ ቅኝት የተገነባ ድረጅት መሆኑን በተደጋጋሚ በብዙ ማስረጃዎች ተነጋግረንበታል። ወያኔ “ክርስትያን/ አማራ/ነፍጠኛ/ ትምክሕተኛ..” በማለት የመደበው የአማራ ማሕበረሰብ ወያኔ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ወደ ሥልጣን ጎበጣው/ሄጂመኒ ለማድረግ በሽግግሩ ወቅት ያደረገው አክራሪ ‘ሶማሌና ዓፋርን” በፓርላማው ውስጥ አሰባስቦ ወደ እየካባቢቸውም ባለሥልጣኖችና ካድሬዎቻቸውን በመላክ በአማራ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ያደረገው ቅስቀሳ፤ ‘በማሕደረ በቪዲዮና አውድዮ’ የተቀረጹ ዘገባዎች አሉ። አማራው ለሶማሌው፤ ለዓፋሩ፤ ለኤርትራው ሰቆቃ፤ግድያና መከራ ተጣያቂ አድርጎ በውሸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማካሄድ “አማራ ወክለዋል፡ ብሎ እራሱ ያደራጃቸው “ባንዳ ግለሰቦችን” በማሰማራት ወደ ኤርትራና ወደ ሶማሌ እንዲሁም ዓፋር እና በመሳሰሉ ቦታዎች በመላክ “በዐማራ ማሕበረሰብ ስም” ይቅርታ እንዲጠይቅ ማድረጉ የሁላችንም የቅርብ ትዝታ እና በቪዲዮ ተቀርጾ ለታሪክ የተመዘገበ የወያኔዎች “ቆሻሸ’ ባሕሪ ሁላችሁም ታስታውሱታላችሁ። 

ዛሬም አማራው ሲገደል፤ እነዚህን ማሕበረሰብ ወክለናል የሚሉ ሰዎችን አሰባስቦ ያንኑ የለመደበትን ሕዝብን ከሕዝብ የማለያየት  ‘ሰይጣነዊ ሥራው’ አገርሽቶበታል (ሶማሌዎች እና ዐፋሮች ለትግራይ ተፈናቃዮች ይህ ለገሱ……እያለ የዋሃን ሶማሌዎች እና  ፋሮችን በለመደው የሕዝብ ማናቆር ፋሺስታዊ ተንኮሉ ለጎሰኛ ፕሮፓጋንዳው ሰለባዎች እያደረጋቸው ነው)። ችግሮችን ለመፍታት የወያኔ የጫካ እውቀቱና አቅሙ ያ ብቻ ነው። የተካነበትና የሚያውቀውም ያው ሕብረተሰብን ‘ማናከስ/ማቀያየም/ማፋጀት’ ነው። ፋሺስቱ የወያኔ ድርጅት በአማራ ማሕበረሰብ ላይ የትግራይ ማሕበረሰብ ሲያደራጅ በዓለም የታዩ ፋሺስቶች ያደረጉት፤ወያኔም ያንን ባሕሪ አድርጎታል። ወያነ ትግራይ በአማራ ማሕበረስብ ላይ ፋሺስታዊና የጅምላ ፍጅት ሲያካሂድ፤ “ወያኔ ማለት ትግራይ ሕዝብ ማለት ነው” በሚል መርሕ ተደግፎ ወያኔ ትግራይ በአማራ ላይ ያንጸባረቀው ባሕሪ ዶ/ር አሰፋ እንዲህ ይገልጸዋል።

“በዓለም ላይ የተካሄዱ የጅምላ ፍጅቶች ሁሉ የሚያመሳስሏቸው ነገሮች አሉ። ከእነዚህም አንዱ የጅምላ ፍጅት የሚያካሂዱት ወገኖች የፍጅት ሰለባ የሆነውን ነጥለው ከለዩ በላ በማንንቱ ላይ የሥነ ሉቦና ዘመቻ ማድረጋቸው ነው። የሥነ ሉቦናው ዘመቻ ግብ አንድን ለጅምላ ፍጅት ሰለባነት የታጨን ሕዝብ ማንነት በሰይጣንንት ምስል መሳልና ጥላሸት መቀባት ነው። የሥነ ሉቦና ዘመቻ የጥቃት ሰለባ የተዳረገው ሕዝብ ራሱን እንደ በደለኛ አድርጎ በመቁጠር ጥቃቱን ንዲቀበል ሲያደርግ፤አጥቂው ወግን እና ራቅ ብለው ይህንኑ ጥቃት የሚያዩትን ወገኖች ፍጅቱን እንደ ተራ ነገር እንዲመለከቱት እና ለተጠቂው ማሕበረሰብ አንዳችም ዓይነት የርህራሄ አመለካካት እንዳይኖራቸው ያደርጋል።…..” (ስርዝ የተጨመረ- የኔ) ይላል ደ/ር አሰፋ  የጥፋት ዘመን ከ1983 እስከ 2007 ዓ.ም በዐማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመ ዘር ማጽዳት” በሚል በወጣት ሙሉቀን ተስፋው የተጻፈ ወያኔዎችና ኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ንዲሁም የመሳሰሉት “በአማራ ማሕበረሰብ ላይ” የተፈጸመው ፍጅት በጻፈው መጽሐፍ የቀረበ የመጽሐፉ ጀርባ።

ሶማሌዎች ትግራይ ወደ ትግራይ በመጓዝ በሚሊዮን የሚገመት ብር ለትግራይ ተፈናቃዮች ለግሰዋል የሚለው ዜና ፤ ስታደምጡ እጅግ የሚያስገርም የወያኔ ፋሺስታዊ ተንኮል ምን ያህል ተራምዶ ሶማሌዎች በአማራ ማሕበረሰብ ‘ፍጅትና ሐዘን’ ምንም ደንታ እንደሌላቸው “አማራው” በሶማሌው እና በዓፋሩ ቂም እንዲይዝ ለማናከስ የለኮሰው “ተንኮል” መሆኑን በቃላሉ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ሶማሌው ከአማራው ማሕበረሰብ ፍጅት ይልቅ የትግሬዎች መፈናቀል እንደቆረቆረቆረው ለማሳየት ያልጣረው ፕሮፓጋንዳ የለም።

ሆኖም ይህ ሶማሌዎች ናቸው የሚባሉት ሰዎች የሶማል ወያኔ ያደራጃቸው ካድሬ ስብስቦች እና ባለስልጣን ሶማሌዎች ያሰባሰቡዋቸው ናቸው። እነዚህ ደግሞ እማን እንደሆኑ በቪዲዮ የተቀረጸው በድጋሚ ለማሕደራችሁ ይህንን አድምጡ፤Somali region president hate statements about Amhara https://youtu.be/6lpronBiUZ4 እዚህ ላይ ግልጽ የሚሆነው ነገር፡ ሶማሌዎች ትግሬዎችን እንደ ወዳጅ “አማራ ማሕበረሰብ” ግን የሶማሌ ጠላት ነው ሲል የሶማሌ ክልል መሪው ሲናገር ታደምጣላችሁ። ስለሆነም ሶማሌዎች ወደ ትግሬ ተጉዘው ለትግሬ ተፈናቃዮች ሚሊዮን ብር ለገሱ፡ ሲለን ወያኔ፤ ሶማሌዎች የአማራውን ፍጅት እንደተደሰቱ እየነገረን ነው። ሶማሌዎችም ያረጋገጡልን ይህንኑ መሪያቸው የነገራቸውን ነው። ታሪክ እራሱን ባስከፊው ገጽታው ሲደግም ዛሬም እያየን ነው!

ዛሬ እየታየ ያለው ትግራይ ውስጥ፡ጭፈራ እና ቀረርቶ ዕልልታ፤ አብሮነትን የሚያደፈርስ ፤እየከፋ በመምጣት ላይ ያለው እየሻከረ ያለው የትግሬና የአማራ ማሕበረሰብ ግንኙነት የትግራይ ማሕበረሰብ በብረቱ አጢነው የወያኔ እና ካድሬዎቻቸው የሚደሰኩሩላቸው የደንቆሮዎች ፋሺስታዊ እና የሚያፋልስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ “ሳይቀበሉ” ወያኔ በአማራ ላይ እያካሄደው እና የፈጸመው የሚገኘው ፍጅት/እልቂት/ዘር ማጽዳት ወንጀል ‘አቁም’ ብላችሁ ትብብራችሁ ለአማራ ሕዝብ ካላሳያችሁ፤ የወደፊት አብሮነት እንደማይጥም እና ኢትዮጵያም እንደ ኢትዮጵያ እንደማትቀጥል ማወቅ ይኖርባችሗል።

 የወያኔ ፖሊሲ ጎሳዎችን የመለያ መታወቂያ አድሎ እንደ ሩዋንዳ ለማፋጀት ያቀደ፤ የውጭ ትልዕኮ እና የማደፍረስ፤የማበጣበጥ፤የፍጅት ወንጀል ይዞ የመጣ መልዕክታኛ መሆኑን ለ25 አመት በክርስትያኑ በአማራው፤ በሉዓላዊ መሬታችን እና ባሕራችን እንዲሁም ሰንደቃላማችን የፈጸመው ወንጀል እና ክሕደት አውቃችሁ አደፍራሽ እና ፋሺስታዊ ዘመቻው ባስቾኳይ እንዲቆም ጥሪ አንድታቀርቡለት ጥሪየን አቀርባለሁ። እኛ እየነገርን ነው! ወያኔን የምንቃወም እኛ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች ነገ ታሪክ ነፃ ያወጣናል። ታሪክ እናንተም ከኛ ጋር ነፃ እንዲያወጣችሁ አስቸጋሪውን የሕሊና ተራራ መውጣት ይጠበቅባችል። ወጣትነት፤ውበት፤ገንዘብ፤ሃብት፤ፍቅር፤ ሥልጣን ፤ፎቅ፤እስክስታ፤ዳንኪራ ጊዜአዊ ናቸው፡ የታሪክ ጉልበት ነው እና ታሪክን ማገድ ስለማይቻል፤ ባንድ ወቅት ባንድ የታሪክ መድረክ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በታሪክና በጊዜ ቅይይር “በተራቸው” ይሰወራሉ። እኛ ሰዎች ነን፤ እንደ አህያ ሳይሆን እንደ ሰው ማሰብ ይጠበቅብናል። እንደ ሰው ካሰብን፤ አማራዎች ሐዘን ላይ ሲቀመጡ እኛ የምንጨፍርበትን ሕሊና መቆጠጣርን ይጠበቅብናል።

አመሰግናለሁ፡

ጌታቸው ረዳ(ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopian Semay)getachre@aol.co

 

 

 

 Tuesday, September 13, 2016

(ክፍል ፪) ኢትዮጵያዊያኖች ‘በዘረኛነት ባሕር እየዋኙ ነው’! ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ? ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Editor Ethiopian Semay ካለፈው የቀጠለ(ክፍል ) ኢትዮጵያዊያኖች ‘በዘረኛነት ባሕር እየዋኙ ነው’! ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ?

ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Editor Ethiopian Semay

ካለፈው የቀጠለ
Ethiopian/Tigrayan government police woman torturing protesters like animals (Photo edited by Ethiopian Semay)

ወደ ርዕሴ ከመግባቱ በፊት አንዳንድ አስፈላጊና አሳሳቢ ጉዳዮችን ላነሳ ነው። በመጀመሪያ በርከት ያሉ የተለያዩ የድጋፍ ደብዳቤዎች፤ጥያቄዎችና አስተያየቶች ለላካችሁልኝ አንባቢዎቼ አመሰግናለሁ። በድረገጼ ከፍተኛ የሆነ የጎብኚዎች ቁጥር እያደገ መሄዱ ሳበስር በደስታ ነው። ትችቴን ለማፈን የሞከሩ ከወያኔ የማይሻሉ የተቃዋሚ ሚዲያዎች፤ በሁሉም ድረገፆቻቻው የሚያቀርቡት “የተኮራረጀ” ዜና እና የተቺዎች ጽሑፍ አንድ በመሆኑ፤ ለየት ያለ ትችት ለማግኘት አንባቢ አጥራቸውን እየሰበረ ወደ ተለየ ሃሳብ ፍለጋ መምጣቱ አበራታች ክስተት ነው። የኔም የ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እና የደ/ር አባባ ፈቃደ ከማንኛቸውም ጸሐፍትና ተቺዎች የተለዩ ሃሳቦች ለማድምጥ ለምትፈልጉ በhttp://welkait.com/ ታገኙናላችሁ። 


ባለፈው ሳምንት በክፍል 1 ትችቴ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ለመጣል እያደረገ ያለው የሞት የሽረት ትግል ብሩህ ተስፋ እየተከሰተ ነው በተባለበት ወቅት፤ ጣልቃ በመግባት ዓይኑን አፍጥጦ እየገሰገሰብን ያለው ዘረኛነት በገሃድ እንዲሰበክና የተሰበከውም ባንዳንድ ቦታዎችም እንደተፈጸመ በማስረጃ አስደግፌ በወንድሜ ላይ የተፈጸመውን ጎሳን ለይቶ የማጥቃት ክስተት ለማብራራት ሞክሬአለሁ። ይህ አደጋ ካሁኑ እንዲቆምና ትኩረት ካልተደረገለት፤ ምንም ዓይነት የፖለቲካ መፍትሄና ትንተና ቢደረደር ከአሰቃቂው የርዋንዳ እልቂት አገራችን አታመልጥም። ስሜትና መሬት ላይ እየታየና እየተደመጠ ያለው አመላካች ጭስና ቁጣ ማየት በቂ ነው።  


የወያኔ ትግሬዎች ገና ጫካ እያሉ በነደፉት ማረክሳዊ/ፋሺስታዊ/ ርእዮት ከውጭ ሃይላት ጋር በመመሳጠር የነደፉት ኢትዮጵያን የማበጣበጥ እቅድ ዜጎች በዜግነታቸው ሳይሆን በመታወቂያ/አይደንትፈኬሽን ካርድ/ በጎሳቸው ‘እንዲለዩ’ በማድረግ  ‘የሁቱ እና የቱትሲ’ መተላለቅ እንዲከሰት የተደረገ ጥናት መሆኑን ሕዝቡ ይዞት የሚገኘው መታወቂያ ህያው ምስክር ነው። ሰሞኑን እነ አባይ ፀሐየ እየነገሩን ያለው ፍንጭም ይህንኑ አደጋ ያጠናክረዋል።ስለሆነም እንነጋገርበታለን።

 ወደ ትንተናዬ ከምግባቴ በፊት፤ አንባቢዎቼን ለማስጨበጥ የምፈልገው በዚህ ውጭ አገር ከምንኖር ወገኖች የታዘብኩት እየተንጸባረቀ ያለ አንድ ክስተት አለ። የታዘብኩትንም ክስተት የሚከተለው ነው። ዘረኛ ግለሰቦች/ቡድኖች አስነዋሪ ስራቸው እንዳለ ሆኖ፤ አጅግ የገረመኝ ነገር፤ ብዙ ሰዎች፤ የየራሳቸው ጎሳዎችን ጥቃት እያጎሉ በጎሳቸው ላይ የደረሰውን በደል በበቻ በየሚዲያው እየላኩ ሰው እንዲመለከተው ሲያሰራጩ፤ በሌላው ወገን ላይ የደረሰው የጎሰኛነት ዘለፋ እና ዛቻ እና ጥቃት ግን ከማሰራጨት ወይንም ከመተቸት መቆጠባቸው ሳይ ያስገርመኛል። እነኚህ ሰዎች ዘረኛነትን እየተቃወሙ፤ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ እራሳቸው በዛው የወገንተኛነት ጨዋታ የመግባታቸው ከስተት ስታዘብ፤ የጎሰኛነት ጭቃ ሁሉንም ያዳረሰ ይመስላል። ይህ ለጎሳው ብቻ ማድላት ወገንተኛነት ነው። ክስተቱ ብዙ ምሁራንም ጭምር ያካተተ ነው። አማራ ከሆነ የአማራ ጥቃት ነው የሚሰማውና የሚያስተጋባው ፤ትግሬ ከሆነ የትግሬ ጥቃት ነው የሚሰማውና የሚያስተጋባው። 


ይህን አንድ ምሳሌ ሰጥቼ ወደ ዋናው ትችቴ ልግባ። ብዙ ጸሐፊዎች ባንድ ፈለግ የሚጓዙበት ባሕሪ እያስተዋልኩ ነው። ይህ ደግሞ እርማት ያስፈልገዋል የሚል አስተያየት አለኝ። አስተያቴን ብትቀበሉትም ባትቀበሉት እንደ ሃሳብ ለግሻለሁ። ለምሳሌ አንድ የማደንቀው ወጣት ጋዜጠኛ የሰው ልጆችን የአፈጣጠር ባሕሪ ‘አንድ ወጥ ሆኖ’ የተፈጠረ በማስመሰል፤ የአማራ ማሕበረሰብ ዘረኞች አልተፈጠሩበትም አይነት አገላጽ ባንድ ጸሑፉ እንዲህ ሲል ይጠቅሳል፤


“…ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ ነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን አማራ ክልል በሚኖሩ ትግሬዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል እያለ መሠረተ ቢስ አሉባልታ እያወራና እናንተም ይህንን በሬ ወለደ እንድታስተጋቡ…” ይላል። ይህ አይነት አባባል ካደነቅኩትና ከምጠብቀው ጋዜጠኛ ሳደምጥ ትንሽ አሳሰበኝ። ይህ እንደምታ የተወሰነ ማሕበረሰብ እንጂ “አማራ ማሕበረሰብ ሲፈጠር ዘረኞች አልበቀሉበትም” ዓይነቱ አባባል በወቱ ጋዜጠኛ ብቻ አልተወሰነም። አንዳንድ ምሑራን እንዲህ ዓይነት አባባል ሲጽፉና ሲናገሩ አደምጬአለሁ። ይህ “ፍጹምነት” መታረም የሚገባው ነው። 


ባለፈው ጽሑፌ የጠቀስኩት፤ “የዚያች የመቀሌ የትግሬ የአምበጣ ለቃሚ ልጅ” የሚል ጥላቻና ትምክሕተኛነትን የሚያንጸባርቅ በአገር ውስጥ በአማራው ማሕበረሰብ አካባቢ የተቀረጸ “ገበሬዎች” በቀረርቶ መልክ ሲያቅራሩ የሚያሳይ ‘በዩ ቱብ’ በሚዲያ ላይ የተለጠፈ አይተናል። ይህ የገበሬ ‘ቀረርቶ’ በድንቁርና፤ በስሜት፤ በጥላቻ እና ትምክሕት ተነሳስቶ እንዲህ ያለ ሕዝብን የሚዘልፍ ቀረርቶ ካስተጋባ፤ ‘ትግሬ በመሆናቸው የተደበደቡ/ጥቃት የተፈጸመባቸው ሰዎች ንፀሓን ዜጎች የሉም’ የሚለው ሙግት የሚያስኬድ ክርክር አያስኬድም፤ እርማት ያስፈልገዋል።


ሌላው፤ ባለፈው ሁለት ሳምንት በፊት በሲያትል ከተማ ‘የጎንደር ማሕበር ለኢትዮጵያ’ በሚባል ማሕበር ላይ የተጋበዘው ታማኝ በየነ፤ ጎሰኛነትን ለማውገዝ ለተሰብሳቢው ማስተማሪያ የሚሆን ባሳየው የቪዲዮ/ክሊፕ/ ላይ ስለ አንዲት “የኩናማ ጎሳ ተወላጅ ነኝ” ብላ የነገረችን ‘የትግራይ ወጣት’ እዚህ አሜሪካ ውስጥ ‘ሥራ ቦታ’ ላይ ሆና አማራውን ማሕበረሰብ የሚዘልፍ ዘረኛ ንግግሯን አሳይቷል። እሷን የሚመስሉ ጎሰኛ ትግሬዎችም እንደዚሁ ጎሰኛ ባሕሪያቸውንና ንግግራቸውን ‘በስዕለ ድምጹ’ ተሰብሳቢውን ለማስተማር ጥሯል። በሌላ በኩል ግን የትግሬን ሕዝብ አምበጣ ለቃሚ፤ የትግሬ እናቶች ሁሉም ሸርሙጦች ናቸው፤ትግሬዎች በዚህ አለም መኖር አይገባቸውም፤ከአጋሜዎች፤ከትግሬ ጋር መጋባት የለባችሁም………ወዘተ…..ወዘተ … እያሉ ሕዝብን የሚዘልፍና የሚያስቆጣ ቅስቀሳ በየ ‘ዩ-ቱብ’ ድረገጽ በጸረ ትግሬ ጎሰኞች ካሁን በፊት የተሰራጩ እና ዛሬም  በሚዲያዎች በገፍ እየተሰራጨ እንዳለ ታማኝ ያውቃል። ለምን ባንድ ጎሳ ብቻ ትምህርቱን ለማስተላለፍ ፈለገ? የሚለውን ጥያቄ ላስተላልፍለት እሻለሁ።


 ይህንን ስል ‘ታማኝ  ጸረ ትግሬ ነው’ ማለት እንዳልሆነ ግን አንባቢዎቼ አንድትረዱልኝ እሻለሁ። ይህ ክስተት በታማኝ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ እኔ የማውቃቸው ምሁራን የቅርብ ወዳጆቼም የሚያንጸባርቁትና የሚልኩልኝ ተሰራጪ (ፎርዋርድ) ቪዲዮ ‘የአንድ ወገን ጥቃት ብቻ’ የሚያንጸባርቅ የታማኝ አይነት “ዴሞንስትረሽን’/ማስረጃ/ ይልኩልኛል። 


ትግሬዎችም በራሳቸው ሕብረተሰብ ብቻ የታየ ጥቃት/ዘለፋ ብቻ እያንጸባረቁና እያወገዙ፤ በሌላው ወገን ላይ በመንግሥታዊ ባለስልጣኖቻቸውም ሆነ በጎሰኞች ትግሬዎች እና ወያኔዎችን በሚያገለግሉ ሚዲያዎች በኩል በአማራውም ሆነ  በሌላው ማሕበረሰብ ጎሳ ላይ የሚፈጸም ጥቃትና ዘለፋ አያሳዩም


ጎሰኛነት ስንቃወም፤ ሁሉንም ዘረኞች መቃወም ሕዝብን ማስተማር ይጠበቅብናል። በአንዱ ዘረኛ ክፍል ብቻ አትኩሮታችን ስንሰጥ፤በጉያችን ላይ ያለው ሌላው ጎሰኛ ወደ ዘንዶነት እየተለወጠ ቀስ በቀስ የሌላውን ባሕሪ ይወርስና አገሪቷ ሲኦል ትሆናለች ማለት ነው። ይህ ባሕሪ ለኦሮሞው፤ ከለጉራጌው፤ ለትግሬው አማራው፤ሶማሌው….የሚመለከት ነው። 


ብዙዎቹ የተቃዋሚ ሚዲያዎች ትችቶቼን ለማፈን የሞከሩበት ዋናው ምክንያታቸውም፤ የፖለቲካ መሪዎቻቸውን እና በአራቱ መአዝናት በኩል ያሉት ጎሰኞ ወገኖቻቸውንም አድልዎ በሌለበት ትችት ስለምተችላቸው እንደሆነ የኔን ጽሁፍ የተከታተላችሁ የምታውቁት ነው። ስለሆነም ትችቴ ባፈኑት ቁጥር አንባቢ አጥራቸውን እየጣሰ ወደ ድረገጼ እና የኔን ትችት በመለጠፍ ወደ እሚተባበሩ ድረገጾች እየተመመ ነው። በዚህም ደስተኛ ነኝ። አመሰግናለሁ።


ስለ ጎሰኛነት ላነሳን አይቀር ወደ ዋናው ርዕስ ከመገብታቸን በፊት አንድ ማሳሰቢያ ልግልጽ የምፈልገው ነገር አለ። 


በ ‘ዩቱብ’ ላይ በሕዝብ ላይ መቃቃር  ሊያስከትል የሚችል ብዙ የጎሰኞች ቅስቀሳ እየተካሄደ/እየተለጠፈ ነው። ከነዚህ ጎሰኞች መካካል ዩቱብ የተለጠፈውን፤የትግሬን ሕዝብ የሚዘልፍ “ዮኒ ማኛ” በሚል ስም ራሱን የሚጠራ፤ እዚህ እኔ ከምኖርበት ሳንሆዜ ከተማ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ያስተላለፈውን መልእክት እንዳደምጥ ሁለት ወዳጆቼ በጠቆሙኝ መሰረት፤ አደመጥኩት። እውነትም እጅግ የሚያስገርም፤የሚያስቀይም ዘለፋ በትግራይ ሕዝብ ላይ ዘለፋ ሲያካሄድ አደመጥኩት። ክስተቱ የሕብረተሰቡ ንቃትና ግንዛቤ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ የተገነዘብኩበት አጋጣሚ ነበር። ለዚህ ነበር ደጋግሜ ‘ሕዝብን መዝለፍ እንደ ቀላል ነገረ የታየበት ዘመን ደርሰናል’ ስናገር የነበረው። ከባሕላችን ባሕሪ ውጭ የሆኑ እንዲህ አይነት አዳዲስ ክስተቶች ሲከሰቱ አመንጪ ምክንያቶች አሏቸው። ከታች የምገልጻቸው የሕብረተሰብ የሞራል ድቀት/መበስበስ ምክንያቶች በዘርዘር ተገልጸዋልና አነሱን ከታች እንመለከታቸዋለን።


ዋናው ነገር፤ ስለ ዮኒ ማኛ ለመግለጽ የምፈልገው፤ባለፈው ጽሁፌ በየ ዩቱብ ሚዲያዎች/ፓል ቶክ ክፍሎች የሚሰራጩ  ሕዝብን የሚያራርቁ ቅስቀሳዎች ከማንኛውም ማሕበረሰብ በግልም ሆነ በማሕበር ተደራጅተው የሚገኙ ክፍሎች በነዚህ የጥላቻ ክፍሎች ክስ እንዲያቀርቡ ባሳሰብኩት መሰረት አንዳንድ ማሕበራት ሂደቱን እንደጀመሩት በድረገጻቸው አንብቤአለሁ። ሁኔታውን ለመግታት የሚረዳ ስለሆነ፤ ቅዋሜአችሁ በሕግ እንድትቀጥሉበት እያሳሰብኩ፤ የሌሎቹን ባላውቀም፤  “ዮኒ ማኛ” ባልወጠነው ድንገተኛ ስሜት (ካነጋገሩ እንደገባኝ ከሆነ) የትግራይን ሕዝብ ዘልፎ በማስቀየሙ ለዚህም በይፋ “ይቅርታ ስለጠየቀ”፤ እኔ እንደ ትግሬነቴ ይቅር ብየዋለሁ፡ ማንኛችሁም ትግሬዎች ይቀር እንድትሉት እጠይቃለሁ።


ሰው በቁጣ ስሜት/ወይንም በሕሊና ድክመት ተገፋፍቶ ሰውን ካስቀየመ በላ ተጸጽቶ ይቅርታ ከጠየቀ፤ አዋቂነቱና ቀና ሰው መሆኑ ምልክት ስለሆነ፤ ሁላችሁም የተቀየማችሁት የትግራይ ማሕበረሰብ እንደኔው ይቅርታውን ተቀበሉት። አገሪቱ በዚህ የይቅርታ ፈለግ እንድትራመድ ሁላችንም መግፋት ይኖርብናል። ማሕበረሰብ የሰዎች ስብስብ ነውና ማሕበረሰቡን ለማስተካከል የግለሰዎችን ይቅርታም ሆነ መጥፎ እርምጃ ለጥፋትም ለገምቢም አስተዋጽኦነቱ ቀዳሚ ረድፍ አለው።። ሌሎቹም “የዮኒ ማኛ’ ቅጽበታዊ እርማት እና አርአያ እንደሚከተሉ ተስፋ አለኝ። ‘ዮኒ ማኛ’ ስለ ወያኔ እና መሰል ጠባቦችን መቃወምክን ግን መቀጥል አስፈለጊ ነው፤ መቀጠል አለብህ እላለሁ። በዚህ አጋጣሚ አማራን የምትዘልፉ የትግራይ ጎሰኞችም “አማራውን ማሕበረሰብ” ይቅርታ መጠቅ ይጠበቅባችል። 


አሁን ወደ ርዕሳችን።


ባለፈው ሳምንት በክፍል 1 ትችቴ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ለመጣል እያደረገ ያለው የሞት የሽረት ትግል ብሩህ ተስፋ እየተከሰተ ነው በተባለበት ወቅት፤ ጣልቃ በመግባት ዓይኑን አፍጥጦ እየገሰገሰብን ያለው ዘረኛነት በገሃድ እንዲሰበክና ውጤቱም ባንዳንድ ቦታዎችም እንደተፈጸመ በማስረጃ አስደግፌ በወንድሜ ላይ የተፈጸመውን ጎሳን ለይቶ የማጥቃት ክስተት ለማብራራት ሞክሬአለሁ። ባጠቃላይ ማሕበረሰባችን በለውጥ ሂደት ላይ ነው። በአገራችን ላይ እየታየ ያለው የባሕል ለውጥ በሂደት ላይ እየገሰገሰ ነው። አንዳንዱም ፍጻሜውን በማገባደድ ላይ ነው። የሕብረተሰቡ ባሕል፤ አኗኗር፤ አስተሳሰብ፤ መልክአ ምድር፤ሰንደቃላማ፤ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ የተከሰተ ሂደት አለ። ለውጡ እንዴት ሊከሰት ቻለ?


ለውጡ የተከናወነው በሳብቨርዥን ‘በብከላ’ /Subversion/ በኩል ነው። Subversion ምንድ ነው? የእንግሊዝኛው ትርጉሙ “Corrupting someon’s personal moral” ይላል። አንድ ሰው ወይንም ማሕበረሰብ ሲከተለው የነበረው እምነት/ባሕል/ሃይማኖት/አገራዊ ፍቅር/መተሳሰብ…የመሳሰሉ ባሕሪያቶችን በተንኮለኞች አስተሳሰቡን እንዲቀይር ማስደረግ ማለት ነው። 


ምን ማለት ነው? ቀላል ምሳሌ ልስጥ። ፍራፍሬ ወይንም ጎመን ብቻ ሲመገብ የነበረን ሰው በተንኮል (ትሪክ) ስጋ  እንዲበላ እና እምነቱን እንዲለውጥ ቀስ በቀስ ማስለመድ ማለት ነው። ከሃይማኖት ወደ ሌላ ሃይማኖት፤ ከራሳቸው ባሕል ወደ ባዕድ ባሕል፤ በየጊዜው የሚዋዥቁበት ባሕሪ በዚህ ጥቃት ስለሚጠቁ ነው። ማሕበራዊ አገራዊ፤ባሕላዊ እና ሉአላዊ እሴቶችም እንዲናቁ ወይንም በሌላ አስተሳብ እንዲለወጡ/እንዲተኩ፤እንዲሁም ሰው ከሰው ጋር የነበሩት ማሕበራዊ ግንኙነቶችና መተሳሰቦች እንዲሰበሩ፤ ማሕበረሰቡ እያጃጃሉ አቅጣጫውን ማስለውጥ የሳብቨርሲቭ ቡድኖች ትኩረት ነው።


ክቡራን እና ክቡራት ኢትዮጵያዊያን ወንድሞች እና እህቶች፤ ኢትዮጵያ በአደጋ ላይ ነች ስል የነበረው አሁን አይደለም፤እጅግ ቆይቷል። የተለያዩ ጠላቶች ኢትዮጵያን  ለማንበርከክ በነፍጥ ሞክረዋታል።አልቻሉም። የተቀራቸው ዘዴ ከነፍጥ የተለየ ዘዴ በመጠቀም አደጋ ላይ እንድትወድቅ ማድረግ ነበር። ይኼውም እራሱን በሚያፈርስ መልኩ አስተሳሰቡን ‘መበከል’ ‘ሳብቨርት’ የማድርግ ዕቅዳቸው ተሳክቶላቸዋል። 


የአገሬው ጠንካራ ምሰሶዎችን ለማናጋት ጠላቶች የተጠቀሙባቸው ስልቶች አንዱ እና ቀዳሚው አደጋ ‘አክራሪ ሃይማኖት ወይንም ጎሰኛነትን’ ማስፋፋት ነው። ይህ ተንኮል በብዙ አገሮች ተከናውነዋል። ሕብረተሰቡ በጠባብ መነጽራዊ አስተሳሰብ ተበከሎ አብሮነትን በማናናቅ (አብሮነትን የተለያዩ ትርጉሞችን ስሞችን እየሰጡ ጥላሸት በመቀባት) በጎሰኛ ማሕበር ተደራጅቶ ሌላውን በጥላቻ መንፈስ ሰክሮ ራሱን እንዲያፈርስ በማድረግ የራሱን ግብአተ መሬት ያፋጥናል። ዛሬ እየገሰገሰ ያለው  የጥላቻ አየር ምንጮቹ እንዲዘጉ ካልተደረገ ብርቱ ነው የተባለለት ማሕበረሰብ የራሱን ሞት በቅርቡ ይደግሳል። 


በምዕራፍ 1 የገልጸኩት ስጋት አንብበው ከአዲስ አባባ የሚል ደብዳቤ ደርሶኛል። ባነበብኩት ደብዳቤዩ የወሰድኩት ግንዛቤ የተከበሩ አንባቢዬ እጅግ የመጠቀ ሕሊና ያላቸው፤አርቆ ተመልካች ቢሆኑም በደብደቤአቸው ላይ የተከበሩ አንባቢ የሩዋንዳ አይንት ብጥብጥ እንደማይከሰት ሊያብራሩልኝ ሞክረዋል። ለመከራከርያ ማስረጃ ያቀረቡልኝ ነጥብም የሕብረተሰቡ የተከበረ የማይናድ ጨዋ ባሕሪ መሆኑን ነግረውኛል። እኔ በዚህ አልቃወምም። 


ሁላችንም የምንስማማበት አንድ ማሰርያ ነጥብ አለ። ለ25 አመት የታየ የጨዋ ባሕሪው አገረቷን እስካሁን ድረስ እንዳትናጋ የደገፋት የሕብረተሰቡ ጨዋ ባሕል መሆኑን ጥርጥ የለውም። ምክንያቱም በወያኔ ምኞት፤ ቅስቀሳና በወያኔ ሕገመንግስት እና አፓርተይድ አስተዳዳር ሌላ አገር ቢሆን ድሮ በተበታተነ ነበር።፡የሕዝቡ አብሮነት ‘ሙጫው’ ተሎ በተላቀቀ ነበር። ይህ በዚህ ብንስማማም ጉዳት አልደረሰም አንልም። ሁላችሁም ልትገነዘቡልኝ የምፈልገው በነዚያ ሃያ አምስት አመታት አዝጋሚ የሆነ ‘ሙጫውን’ እያስለቀቁ የሄደ የተለያዩ የጥፋት እርምጃዎችና “የጥፋት ዘመን” የተከናወኑበት ሂደት እንደነበር ምሳሌዎች-መስጠት ይቻላል።
   የወጣት ሙሉቀን ተስፋው ‘የጥፋት ዘምን’ ከ1983-2007 የሚለው መጽሐፍ ስታነብቡ፤ ከእኛ ጋር አለ እያልን ስንመካበት የነበረውን የሕዝባችን “ድሩ እና ማጉ” በጥላቻ ቡድኖች ቅስቀሳ ተበጣጥሶ በዐማራ  ሕብረተሰብ እናቶች፤አባት ገበሬዎች፤እመጫቶች ከህጻነት ልጆቻቸው በሺዎቹ የሚቆጠሩ በሩዋንዳ የተፈጸሙ አራዊታዊ እልቂቶች በሙሉ ተፈጽመዋል። እደግመዋለሁ!!!!!!!!!!! በሩዋንዳ የተፈጸሙ አራዊታዊ እልቂቶች በሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ማሕበረሰብ ሕይወት ላይ ተፈጽመዋል”።
ስለሆነም ውድ አንባቢዬ፤ ከሚኖሩበት አዲስ አባባ ውስጥ ይህ መጽሐፍ አፈላልገው ቢያነብቡ “ሕዝባችን ጨዋ ነው፤ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ጨዋ ባሕል ስላላው እንደ ሩዋንዳ ዕልቂት አይፈጽምም” ብሎ አፍ ሞልቶ መናገር አይቻልም። በግል ስለጻፉልኝ ደብዳቤ አክብሮት እየሰጠሁ፤ በግል መልስ ከማጸፍ ይህንን ጹሑፍ እንድያነብቡ ልኬለዋተለሁ እና ያንብቡት። ስላከበሩኝ እና ስለ ወንድሜ ሁኔታ ድጋፍዎን ስለገለጹልኝም እጅግ አመሰግናለሁ።  

ሌላ ልጨምርለዎት የምፈልግ ማስረጃ፤ የሚከተለውን ፎቶግራፍ ይመልከቱ።

Ethiopian police beating protesters in Amhara and Oromo region


 በፎቶግራፉ ላይ የምትታይ ‘አንስት ፖሊስ’ ሁለት ዜጎችን ቁልቅል ዘቅዝቃ በብትር ስትደበድብ ይታያል። ሴቶች እህቶቻችን/እናቶቻችን በባህላችን በጣም ርህሩህ አንጀት ያላቸው መሆናቸውን የሚያከራክር አይደለም። በአገራችን ታሪክ ሴቶች እህቶቻችን በእንደዚህ ያለ የጭካኔ ገራፊነት ባሕሪ የተሰለፉበት ወቅት እኔ አላውቅም። እንዲህ አይነት ባሕሪ ፍጹም የማይታለም እንደነበር አውቃለሁ። ጨዋ ባሕል ተሰርዞ፤ በምትኩ ዛሬ እንዲህ ያለ የጭካኔ እና አረመኔአዊ ‘የባሕል ለውጥ’ እንዴት ሊከሰት ቻለ? የሚለውን ክቡር አንባቢየ እንዲመራመሩበት እጠይቃለሁ። ይህም ወደ ዋናው መነጋገሪያችን የሚወስደን ማስረጃ ነው። ይሕ የተረጋጋ ማሕበረሰብ በተዋናይ ቡድኖች እንዴት ሊናጋ ቻለ? የሚለውን አይነተኛውን ነጥብ አንስቼ ለመወያየት እሻለሁ።(1ኛው) የውጭ እና የውስጥ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማጥቃት የተጠቀሙባቸው አራት የጥቃት ስልቶችን/ዘዴዎች/ እንመለከታለን። ስለ እነዚህ አራት የጥቃት ዘመቻዎች አንስተን “መወያየት” ስለ አገራችን መሰረታዊ “ግንዛቤዎች” እንዲኖሩን ይረዱናል።መጀመሪያ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጡ አራቱ የጥቃት ስልቶች ያልኳቸው ምንድ ናቸው?


“የአሁኑዋ” የወያኔ ጊዜ “ኢትዮጵያ” እና “ድሮ” የምናውቃት ኢትዮጵያ በጣም የተለየች ኢትዮጵያ ነች። ልዩነታቸው ለማስረዳት መጽሐፍ ተጽፎም አይበቃም። ጫዋ እና የተረጋጋ ባሕል አለን ያልነውን አንድነት እና ሉዓላዊነታችን ጥቃት ላይ መውደቁን እንመልከት። ባጭሩ ልግለጽ ፤

(1)          “የሕዝቧ አንድነት ደፍርሷል፡

(2)         ግዛቷ/ድምበሯ ተቆራርሶ ለጠላት ተሰጥቷል፤

(3)        ቋንቋን መሰረት ባደረገ ስርዓት እየተገዛች “ሕዝቡ” በጎሳ ተከፋፍሎ ባንድ ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደ “ሩዋንዳ”  ዕልቂት ተፈጽሟል። ዕልቂቱም ተደብቆ ለ25 አመት ቆይቷል። ብዙዎቹ ተቃወሚዎችም “መ ኢ አ ድ”ን ሳይጨምር (‘መ ኢ አ ድ’  ስለ አማራው መጠቃት ብዙ አቤቱታና ጨኸት አሰምቷል)።  ሆኖም የኢትዮጵያ ምሁራን ሊያነሱት ያልፈለጉት እንዲረሳ እና በየመድረኩ አንዳይወሳ ሆን ብለው የተረባረቡበት ሁኔታም እስኪመስል ድረስ የጋዜጠኞች እና ግለሰቦች መታሰርና መብት ረገጣ ብቻ ሲጮኹ የአማራው ሰቆቃ ተደብቆ አንዲቀር ተደርጓል/በተዘዋዋሪ ከጠላት ጋር ተረባርበዋል ማለት ይቻላል። ማሕበረሰቡ በሁለም ቦታ አዝጋሚ በሆነ ግጭት በአፓርታይድ ክልል ምክንያት “እየተጋደለ እና እየተጋጨ” ነው። ዛሬም ቶሎ ብሎ ሂደቱ እርማት ካልገጠመው ወደ ‘ሁቱ እና ቱትሲ’ ዓይነቱ የእርስ በርሱ መጠፋፋት እንደሚያመራ ብዙ ምልክቶች እያየን ነው።

(4)        አክራሪ ሃይማኖቶች ተስፋፍቷል፤

(5)            አዲስ መጤ የሆነ የዘረኞቹና አለምን ለመግዛት የተነሱ በሰይጣን እና በአለም ፍጅት የሚያምኑ “የኤሊሙናቲ” ሃይማኖት ተከታዮች ኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ ተመስርተዋል።

Illuminati religion invading Ethiopian society during the Tigrayan ruling system through subversion
በትግሬዎች ሥርኣተ መንግሥት
የሃይማኖት ብከላ/የሳብቨርዥን/ ውጤት በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ(6)ሕዝቧ ለስደት እና ለባርነት ተዳርጓል፤

         (7)  ወጣቶቿ ለግበረሰዶም፤ እና እህቶቻችንም ዕርቃናቸው እያሳዩ ጎዳና ላይ ቆመው የሚታዩ የእህቶቻችን ባሕሪ ተቀባይነት አግኝቶ  ለሽርሙጥና፤ ለሱሰኛ እጽ ተዳርጓል፤

        (8)    የዛሬ ወጣቶቻችን ብርታት በአንዳንድ ጸሓፍት ግምገማ ‘በቺታ/በግስላ፤ በነብር…’ ቢመሰሉዋቸውም አሁን ያለው ትግል በጀግንንት ቢጋፈጡም ግንዛቤአቸው አጠያያቂ ነው።ካንድ የምወደው የቅርብ ወዳጄ በዚህ ጉዳይ አንስተን “አለው የለውም” ሰፊ ውይይት አድረገናል። አገራዊ ራዕይ ያለው ሩቅ ተሻግሮ የሚራመድ ግንዛቤ የላቸውም የሚል የራሴን ክርክር ላስምርበት። ለዚህ እዘረዝራለሁ። “በቲት ፎር ታት” ( blw for blow) የሚነዳ የስሜት ተጓዥ ነው። (በተለይ እውጭ አገር ያለው)ላሰምርበት የምፈልገው፡ ወጣቶች ሲባሉ እንደክራር በጠባብ  ሕሊና የተቃኙ የኦሮሞ፤ የሶማሌ፤ የትግሬ… ወጣቶችን ግምት ውስጥ ማስገባት አሁን ለምከራከርበት ነጥብ ግንዛቤ ይሰጣችኋል። የአማራ ወጣቶችም ለ25 አመት ማሕበረሰባቸው ሲጨፈጨፍ፤ሲፈናቀል፤ ለምን እንዳንቀላፉ እና ይባስ ብሎ የማይናቁ በሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ ብዙ አማራ ወጣቶች እና ምሁራን አማራዎች በጨፍጫፊዎቹ ብዱኖች ተሰግስገው የሚዲያ አገልጋዮቻቻው፤ ሚኒስተሮቻቸው፤ ዘፋኞቻቸው፤ ካድሬዎቻቸው፤ ሰላዮቻቻው፤ ተወካዮቻቸው … ሆነው ለምን እንደቆዩ ግንዛቤአቸውን ለማየት ይረዳል። በገለልተኛነት ቆመው ለ25 አመት ሕዝባቸው ሲታረድ ያላመማቸው ብዙ ሚሊዮን አማራ ወጣትም ሆነ ምሁሩ ክፍል  እዛው መደርደሪያ ውስጥ ብታሰልፏቸው፤ለግንዛቤ ይረዳል።(9)ዜጎች  ከመኖርያቸው እየተባረሩ የአገሪቱ ለም መሬቶችና ሜዳዎች ለባእድ አገር ዜጎች በስፋት ተሰጥቷል።

(10)ሴት እህቶቻችን የዓረቦች መጫወቻ ግዑዝ ዕቃ ተደርገው በወያኔ ጊዜ የውርደት ውርደታቸው እንድያዩ ሆኗል። ወንዶች ወንድሞቻችንም በየበረሃው እና በየባሕሩ እየገቡ በጣም በርካታ ወጣቶች ለስደት ተዳርገው ሰው ለሚያርዱ አክራሪ እስላሞች ተዳርገዋል። አዲስ አበባ ውስጥ ሃዘናቸውን ለመግለጽ ባደባባይ የተሰበሰቡ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችም የወያኔ ባለስልጣናት በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት  ቅልብ ወታደሮቹን በመላክ ተጨማሪ ሃዘን በማውረድ “የድበደባ እና የእስራት ቅጣት” በዜጎቻችን ላይ  ፈጽሞባቸዋል። ወዘተ…ወዘተ… ወዘተ…


ባጭሩ የሕዝባችን ሕይወት ለክፉ ሕይወት ተዳርጓል፤ ቀስ በቀስ እየተገዘገዘ ነው ማለት ነው። ይህ እንዴት ተከሰተ? ማንስ ነው የዚህ ሴራ አቀነባባሪ? የሚለው በጥልቅ መመርመር አለብን።

ባለንበት ዘመን፤አገሮች እየተናጉ ነው።  ከመጠነኛ መረጋጋት ወደ የከፋ የሕዝብ እና የአገሮች መደፍረስ ያለ ምክንያት አይከሰትም። ምክንያት አለው ማለት ነው። ምክንያቱን እንፈልገው እና እንወያይበት።


ለኢትዮጵያ መናጋት ምክንያቶች እና የተሰነዘሩብንን ጥቃቶች ወይንም ሌሎች አገሮች ሲደፈርሱ ከመጋረጃ ሆኖ “ድፍረሳውን” ወይንም የመናጋቱ ትዕይንት የሚያንቀሳቅሰው ክፍል ማን ነው? እንዴትስ ይከናወናል? የኢትዮጵያ ጥቃት ዓለም አቀፍ ተዋናዮች እና በውስጥ ወኪሎቻቸው በኩል የተከናወነ፤የተሰነዘረ ጥቃት አለ። ያ ጥቃት ምንድ ነው?


 አገሮች ሲደፈርሱ በአራት ‘4’ ደረጃዎች ውስጥ ማለፍ ይኖርባቸዋል። እነዚህ የድፍረሳ ደረጃዎች  “ዩሪ ቢዝኖቭ” የተባለ የድሮ የሶቭየት ሕብረት የስለላ ክፍል ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረው፤ በ1970 ዎቹ አካባቢ ወደ አሜሪካኖች እጁ በሰጠበት ወቅት እና በቃለ መጠይቁ ጊዜ “የአሜሪካን ማሕበረስብ ለማፍረስ ሶቭየቶች የተጠቀሙባቸው ስልቶች በጠመንጃ ሳይሆን “ideological-subversion" ወይንም “የርዕዮተዓለማዊ አስተሳሰብን መበከል” የሚል የመንፈስ ጦርነት በማካሄድ ነበር። ይህ “መንፈስን የማጥቃት ጦርነት” ከአገራችን ሁኔታ ተመሳሳይነት ስላለው ግንዛቤ እንዲኖረን እንደ መረጃ አቀርባለሁ።


 ኢትዮጵያ ውስጥ  የሕብረተሰቡን ነባር፤ የቆየ፤የተረጋጋውን ሰላማዊ ሕሊና፤ አሁን ካለው ከደፈረሰው የማሕበረሰባችን ሕሊና ሲተያይ  “ዩሪ” ከተናገረው ጋር  ባስገራሚ ክስተት “መቶ በመቶ” ተመሳሳይነት አለው። 


ይህ “ideological subversion” ይህ “ሕሊናን የማደፍረስ” ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ፡ ያለ ጠመንጃ ፤ያለ ጦርነት “ቀስ በቀስ/ በዝግታ” አንድ አገር ለማፍረስ የሚከተሉት አራት መከናወን ያለባቸው የሂደት ደረጃዎች ማለፍ አለበት

1.    Demoralization የሞራል ዝቅጠት

2.    Destabilization አገርን ማናጋት

3.    Crisis አገርን በቀውስ ሂደት ማስገባት

4.    Normalization የውሸት እርጋታ የመጨረሻው የአገሪቱ ሕልፈተ ሞት (ልክ ወያኔ ወይንም ኒው ወርልድ ኦርደር የተባለው “አዲስ ሴራ” አገሪቱን/አለምን “ኖርማላይዝ” አድርገናታል (አረጋግተናታል) እያለ ሕብረተሰቡ “በጎሳ ጽዳት” እንዲፋጅ እና አገሪቱ እንዳትኖር የማድረግ የመጨረሻው የአገሪቱን “ግብአተ መሬት” አንዲጠናቀቅ የሚደረግ የመጨረሻው ዘዴ ማለት ነው።


እነዚህ አራት ደረጃዎች በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ሕይወት በመከናወን ላይ ናቸው። የመጀመሪያው “ዲሞራላይዘሽን”( የሞራል ዝቅጠት) ሂደቱን ስንመለከት፡ ዩሪ የሚለን አንድ ነገር አለ። በእንግሊዝኛው ልጥቀስ “You are what you eat, and your brain is the product of its perceptions.  Americans consume data bits from television each night.፡ ሲተረጐም ካላበላሸሁት በቀር፡ እሱ የሚለው “ አንተነትህ የሚወስደው ቅርጽ አንተ በምትመገበው ምግብ የሚሰጥህ የአከላት ቅርጽ ሲሆን፤ ሕሊናህም የሚቀረጸው “ሆን ተብሎ” ያለ አማራጭ ሌት ተቀን  ወደ ኣእምሮህ “በሚቀዳ” የቴሌቪዥን መረጃዎችን ነው።” ይላል። ይህ ዲሞራላይዘሽን (የሕሊና/የሞራል ዝቅጠት) ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን በማጥቃት ላይ ነው። 
 
ወጣቱ በምዕራቡ እና በዓረቡ ኣለም ባሕል፤ቋንቋ፤አስተሳሰብ ተዘፍቋል። ወያኔ በሚመድብላቸው ሥራ ማስኬጃ በጀት ተደግፈው በቲቪ/በትያትር ቤቶች/በመዝናኛ ማእከሎች/በስፖርት እና በሙዚቀኞች፤ በፊልምተዋናዮች፤ በሚለብሱት፤ በሚናገሩት፤ በሚያጨሱት እና በሚያመነዥጉት፤ በሚጫሙዋቸው ጫማዎች እና ልብሶች በኩል የሕብረተሰቡን ሕሊና በመለወጥ አገራዊ ባህሉን እና ቋንቋው እንዲነጠቅ ተደርጋል። 


“አንደበቱ እና አእምሮው” ኢትዮጵያዊ ሳይሆን “አረባዊ ወይንም ምዕራባዊ” ባህል አንጸባራቂ ሆኗል። ብታምኑም ባታምኑም፤ ከኔው ጋር ላትስማሙ ትችላላችሁ፤ ነባራዊው እውነታ ግን ይኼው ነው።


የታሪክ ተንታኞች እንደሚሉት ‘ባሕሉ የተነጠቀ ማሕበረስብ “ጥዋት የወጣበትን ቤት” ማታ ሲመለስ ‘ጥዋት የወጣበትን’ ቤት አያውቀውም እንደ ማለት ነው ይላሉ። ጥቃቱ የሚነጣጠረው ኢላማ አብዛኘው በወጣቱ ስለሆነ ወጣት አገር ተረካቢ እንደመሆኑ መጠን ‘የተምታታ ሕሊና’ ያለው ወጣት ደግሞ “አገሩን ብቻ ሳይሆን፤ማንነቱን አያውቅም” ማለት ነው። ማንነቱን የሳተ ሕሊና ደግሞ ስለ አገሩ ጥቃት ግንዛቤ የጐደለው ይሆናል ማለት ነው።


የዲሞራላይዘሽኑ/የሞራል ዝቅጠት/ ሂደት በአንድ አገር ለማከናወን የሚወስደው እድሜ ከ 15 እስከ 20 አመት ይፈጃል። ይህ ሂደት ኢትዮጵያ ውስጥ ተጠናቋል።ዩሪ እንዲህ ይላል። “Why that many years? መልሱን ይሰጠናል፦ Because this is the minimum number of years required to educate one generation of students in the country of your enemy exposed to the ideology of [their] enemy.” ለምን ያንን ሁሉ አመት ይፈጃል? ይላል እራሱን በመጠየቅ፤ ምክንያቱም ይላል ሲመልስ፡ ለማጥቃት የፈለግከውን አገር የተማሪዎቿን/የተቀባዩ/ ሕሊና ለመለወጥ፤ የራስክን አስተሳሰብ በሕሊናቸው ለማስረጽ የሚፈጀው ጊዜ ያንን ያህል አመት እየተጓዘ መጠናቀቅ ስላለበት ነው።” ይላል።    ይህንን በምሳሌ ለማየት ከፈለጋችሁ

በደርግ ጊዜ

በወያኔ ጊዜ

በጣሊያን ፋሺስቶች ጊዜ የተከሰቱ የሕሊና ጥምዘዛዎችን/ጥቃቶችን ስንመለከት

በደርግ ጊዜ የማርከሲዝም የሌኒኒዝም ርዕተ አለም ማለትም “የሶቭየቶች/የቻይናዎች ፍልስፍና በማስገባት የማሕበረሰቡን ሕሊና በመጠምዘዝ ለቀውስ የዳረገውን ሁኔታ ስንመለከት ፤-


ወይንም በወያኔ ጊዜ የከፋፍለህ ግዛ፤ አክራሪ የሃይማኖት እና የጎሳ ብሔረተኛነት ማለትም “ከደቡብ አፍሪካው’ ክልላዊው ዘረኛ አስተዳዳር የማይተናነሰው የቋንቋ አስተዳደር ተግባራዊ በማድረግ ጐሳዎችን በተለይ አማራውን በግፍ ለጥቃት የተጋለጠበት ሁኔታ ስንመለከት፤-   


ወይንም የፋሺስት ጣሊያኖች ሴራ” በኦነጎችና በወየኔዎች ቅየሳና አስፈጻሚነት አገርን የማፍረስ ሴራ “ኤትኒክ ፌደራሊዝም” (የጎሳ ብሔረተኛ ፌደራሊዝም) ተግባራዊ እንዲሆን በዝግታ ከ17 እስከ 25 አመት ፈጅቷል። ( የሕዝቡ ባሕላዊ ጥንካሬ እንጂ ሌላ አገር ቢሆን የኸኔ አገሩ በሙሉ እንዳለ ፈርሶ ነበር)። ሆኖም መጠነ ሰፊ የሆነ ጥቃት ደርሷል። ሁኔታውም አስፈሪ ነው።ይህ የሳብቨርዥን/’የብከላ ጥቃት’ ሲፈጸም ያለ ምንም ጠንካራ አገራዊ/አርበኛዊ ወይንም ፓትርዮቲክ ተቃውሞ ተከናውኗል። እርግጥ መጠነኛ ተቃውሞች ተደርገዋል፤እየተደረጉም ነው፡ ግን በቸልተኛነት ስለተለቀቀ “ዲሞራላይዘሺኑ/የሞራል ዝቅጠቱ” በውስጥ ተዋናዮች በጠምነጃ እና ያለ ምንም ጠመንጃ ስለተከናወነ “በሁለት ትውልዶች እድሜ ሂደት” ውስጥ ተከናውኗል ማለት ነው(በደረግ እና በወያኔ ወቅት)።


 የአገራችን ወጣት “ማርክሲዝም” ወይንም ያንን ካላወቀ ደግሞ፤ በአለም ውስጥ የሌለ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በገዛ ልጆቿ የተቀየሰው አደገኛው “ኤትኒክ ፌደራሊዝምን/የቋንቋ/” አስተዳዳር ተዋውቋል ማለት ነው። ሁለቱንም ‘ርዕዮት’ በውጭ አገር የአይዲዮሎጂካል ሳብቨርዢን ተዋናዮች የተሰነዘሩበት የሕሊና አጠባዎች ተቀባይ ሆኗል። 


የዲሞራላይዘሺኑን ዝቅጠት ባጭሩ በ15 እስከ 20 አመት ያሉት ወቅቶች ሲጠናቀቅ፤አሁን ያለው ሕብረተሰብም ይሁን በመወለድ ላይ ያሉ አዳዲስ  ትውልዶች፤ያስተሳሰባቸው ሕሊና ከተቀየረ አገራዊ ፍቅር ስለማይኖራቸው ሁለተኛውን ደረጃ ማለትም “ዲስታብላይዘሽን” አገርን የማናገቱ ሂደት በቀላላሉ እንዲከናወን ይረዳል ማለት ነው። (የኦሮሞዎች እና የትግራይ ወጣቶች ለዚህ ብቁ ማሳያ ሆነው እናያቸዋለን)። 


2ኛው የ Destabilization አገርን የማናጋት ሂደት ወጥመድ ደግሞ ምን እንደያዘ እንመልከተው፡


የሕብረተሰቡን የተረጋጋ ሕይወት (የተረጋጋ አገር) ለማናጋት የሕዝቡን ቫልዩ/አቅጣጫን/ቀልብን በማሳት የሚከናውን ብቻ ሳይሆን ባገሪቱ ውስጥ ያሉት አርበኞቿ፤አገር ወዳዶቻ፤ምሁራኖቻን በዝግታ ማስወገድ ለመናጋቱ ከፍተኛ ክፍተት ስለሚኖሮው በነዚህ ላይ ጥቃት መከናወን ስለነበረበት ጥቃት ተፈጽሟል። ከሕሊና አጠባ የተሸጋጋረው የዲስታቢላይዘሽን ሂደት በጣም አስፈሪ እና የአገሪቱን ማሰርያ /መልሕቅ የሚበጠስበት ወቅት ነው ማለት ነው። አገር ሲናጋ ማሰሪያ፤ሉጓም የሌለው ፈረስ ይሆናል ማለት ነው። 


ሊቃውንቶች፤ምሁራኖች፤አገር ወዳዶች እና አርበኞች የአገሪቱ መሪዎች እና ሉጓሞች ናቸው።እነዚህ “እሴቶች/ የአገሪቱ ውድ ዋስትናዎች” ናቸው። ማለትም “ዋናው የአገሪቱ አንጡራ ሃብት ናቸው”። ካፒታል /አሴት የሌለው ባንክ “ባንክራፕት/የከሰረ እንደሚሆነው ሁሉ” አገሪቱም ምሁራኖቿ ስታጣ “አገሪቱ ትናጋለች” ማለት ነው። ዱሩየዎች ቦታቸውን ይነጥቁዋቸዋል ማለት ነው።


 እነዚህ በሰበብ አስባቡ በውጭ እና በውስጥ ተዋናያች አጥቂነት እየተጠቁ ከስራ እንዲፈናቀሉ፤ እንዲታሰሩ፤እንዲሰደዱ፤ አካላቸው እንዲጎድል ከተደረገ፡ አገሪቷ ጠባቂ አልባ ሆና ፤ ጠበቃ፤ ተሟጋች፤ተዋጊ፤ተከራካሪ፤አስተማሪ፡ ስለማይኖራት “አገሪቱን ለማናጋት” ለአጥቂዎቹ ስለሚቀል፤ አጥቂዎቹ የወጠኑትን የማናጋት፤የማፍረስ ሂደት በቀላሉ ይጠናቀቃል ማለት ነው። 


የሕብረተሰቡ “ኤክሶዳስ” ስደት ከተለመደው ቁጥር በላይ ፤ሞት፤ባርነት፤ውርደት፤ ባይተዋርነት ውስጥ  ይገባል ማለት ነው። እዚህ ደረጃ ሲደርስ “አገርን የማናጋት” ሴራው ተከናውኗል ማለት ነው። እኛ ከአገራችን ወጥተን እዚህ ያለንብት ዋና ምክንያት የማናጋቱ ሂደት ሰለባዎች መሆናችንን ግንዛቤ ውስጥ አስገቡት።  


ይህ ሲጠናቀቅ ተጫዋቾች አሉ። ተጫዋቾቹ በማወቅም ባለማውቅም በማናጋቱ ሴራ ውስጥ የየራሳቸው መጥረቢያ ይዘው በማናጋቱ ሂደት የሚተውኑ ተዋናዮች አሉ። እነማን ናቸው?

የሃይማኖት ድርጅቶች፤ ነጋዴዎች፤ ሚዲያዎች፤ የሴት/የወጣት/የምሁራን፤ እና የፖቲካ ድርጅቶች ወዘተ ወዘተ….ይጨምራል። አነዚህ ተዋናዮች የአገሪቱ ዜጎች ስለሆኑ፤ የያራሳቸው ዓላማ/አጀንዳ ግብ ለማድረስ የሚጓዙበት መንገድ አቀበቱን በጥንቃቄ ካልተጓዙት እራሳቸውን በማናጋቱ ሂደት ጠልፈው የማናጋቱ ሴራ ተጫዋቾች የሚሆኑበት ጊዜ አለ።


ባጭሩ እንመልከት። እውነታው የሚከተለው ነው፡ ላብራራ። ሕዝቡ/ድርጅቶች/ አጥቂዎቹ በሚሰጡት የፖለቲካ ጫዋታ/ካርድ እየተጠቀመ እርስ በርሱ በጣላትነት እየተፈራራጀ፤ የየራሱን ባንዴራ እያሰራ በማውለብለብ “ኢትዮጵያን” ማአከላዊ የጋራ ጠላት በማድረግ የተሰጣቸው የማናጋት ሴራ የየራሳቸው መጥረቢያ ይዘው በመገዝገዝ ላይ ናቸው።በፋሺስቶቹ የተሰጣቸው “የኤትኒክ ፌደራሊዝም አስተዳዳር” አገርን የማናጋት ሴራ ለማከናወን “ጎሳዎች” የሌለን “የጋራ ጠላት” መፍጠር ነበረባቸው።  የጋራ ጣላት የተባሉት ደግሞ “ኢትዮጵያ፤አማራ፤ኦርቶዶክስ” የሚባሉ እስቶች ወይንም ማሕበረሰቦች በጠላትንት ተፈርጀው ከፍተኛ “ጥቃት” ተፈጽሞባቸዋል። ይህ ሴራ በጣሊያን እና ከዚያም በፊት የተሰነዘረ የጥቃት ዘመቻ ስለሆነ “ጥቃቱ” አሁን በወያኔ ጊዜ ደንዳና መሰረት ጥሎ የአገሪቱን ማዕከላዊ ምሰሶ ተነቃንቆ ለመውደቅ በመንገዳገድ  ሂደት ላይ ይገኛል ማለት ነው።


የወስጥ ተዋናዮቹ ‘የነፍጠኛ፤የጡት ቆራጭ አገር፤ ላ ቀር አገር፤የመቶ አመት አገር’ በማለት ኢትዮጵያን ‘በማዋረድ፣በማንኳሰስ’ የማናጋቱ ሂደት “ስሎው ፕሮሰሱ” (በዝግታ) እንዲከናወን እየተደረገ ነው። ኦሮሞዎችና እና ትግሬዎች የአገሪቱን መሰረታዊ ምሰሶዎች ለማፍረስ ለ25 አመት አፍራሽ ሚና ተጫውተዋል። ለወደፊቱም አገሪቱ እንደትፈርስ መሪ ተዋናዮች የነበሩ እና ለወደፊቱም የሚሆኑትና ለማፍረሱም ሆን ብለው ዛሬም እያሰፈሰፉ ያሉ በጎሰኛ ጠባብ ማርክሳዊና ፋሺስታዊ ፌደራሊዝማዊ ርዕዮት” የተበከሉት የሁለቱ ማሕበረሰብ ወጣቶችና ምሁራን ክፍሎች እንደሆኑ በልበ ሙሉነት ስነግራችሁ ቅር የሚላችሁ ካላችሁ፤ ነባራዊን ሁኔታ ግንዛቤ ያላችሁም ማለት ነው። የወያኔ ስርዓት ቢወገድም የተቀሩት በኦሮሞና በትግሬ ዙርያ አጎራባች አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማሕበረሰቦች፤ መራራ እና ስከፊ ትግል የሚፋጠጡት በፋሺስታዊ ጠባባ ጎሰኛ ርዕዮት ከነዚህ ሁለት ማሕበረሰቦች ጋር ነው። አንዳንድ አንባቢዎቼ ከሆሆታ ስሜት ወጥታችሁ ትችቴን በርቀት ብታጤኑት የወደፊት ጉዞአችሁ ወዴት እያመራ እንደሆነ ይረዳችል።

ግንዛቤአችን ስናሰፋ፤ የማናጋቱን ሂደት ለማከናወን “በሕግ የተፈቀደ” የጥላቻ ቅስቀሳ በኢትዮጵያ ላይ፤ በክረስትያን ማሕበረሰብ ላይ፤በአማራ ሕብረተሰብ ላይ እንዲጻፍ፤እንዲነገር ፤የጥላቻ ሃውልቶች በኦሮሞ እና ትግሬ ክ/ሀገሮች እንዲቆሙ፤ በድርጅት ፖሊሲ ተጽፎ፤ የመንግሥት ሥልጣን በተቆጣተሩ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እና መሪዎች የተፈቀደ የማናቆርና የጥላቻ ቅስቀሳ ያለማቋረጥ አድምጠናል። 

መሪዎችም በይፋ  በቴሌቪዥን፤ በራዲዮ፤ በጋዜጦች ይህንኑ የጥላቻ ንግግር በመናገር ወይንም ሲነገር ቸል በማለታቸው ሕብረተሰቡ እንዲሸማቀቅ እና ውረድቱ እንዲለማመደው ሕጋዊ እንዲሆን ተደርጓዋል።መለስ ዜናዊ፤ስብሓት ነጋ፤(ዳዊት ዮሐንስን አትርሱ) እና በርካታ የኦሮሞ፤የሶማሌ እና የትግሬ መንግሥታዊ ባለሥልጣኖች ወዘተ……ወዘተ… በይፋ አገሪቱን እና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማን በመዝለፍ የታወቁበት የፖለቲካ ማስታወቂያቸው እንደነበር እና ዛሬም እንደሆነ የግዝገዛው  መሪ ተዋናዮች ናቸው። የኢትዮጵያ ወጣቶች በሳብቨርዢኑ/በብከላው ስለተለከፉ፤ ጉልህ የሆነ ‘ተቃውሞ’ ሲያሳዩ አልታዩም። ወጣቶቹ ጆሮአቸውን ከፍተው ከ25 አመት በኋላ ጩኸታችን በዝግታ ማድመጥ የጀመሩት ገና አሁን ነው። ለዚህ ደግሞ ምሁራን እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች አብረው ከማሕበረሰቡ ላይ ተበክለው ስለነበር ጊዜ ፈጅቷል።
 
አጥቂዎቹን እየተከተሉ፤ የሃይማኖት፤የጎሳ መሪዎች ነን የሚሉም እንደ አሸን በመፍላት፤ አገሪቱን እንደ ባዕድ አገር ቆጥረው፤ ራሳቸውንም እንደ ባእድ ዜጋ ቆጥረው “ኢትዮጵያ አገራችን አይደለችም” እያሉ ያልወረወሩት ነውረኛ ቃላት የለም።የብከላው ሰንጠረዥ ጣራ ነክቷል።

‘የሳይኮሎጂካል ሳብቨርዥን/የስነ ኣእምሮው የብረዛ/ ዘመቻ  “መንግሥት” ነን በሚሉ አካሎች ያለ ምንም ዩሉኝታና ፍርሃት በድፍረት በአገራችን ሕዝብ ሃይማኖታዊ እምነት ላይ በቴ/ቪዥን እንዲተላለፍ አድርገዋል።  አጥቂዎቹ- የሕዝቡ ጨዋዊ ሞራል፤አብሮነት፤የተረጋጋ ማሕበረሰብ እንዳይኖር፤ፈሪሃ እግዚአብሔር ቦታ እንዳይኖረው፤የወያኔ መሪዎች በሕዝቡ ሃይማኖት ላይ በፈጣሪ እየተሳለቁ በፓርላማ መድረካቸው ላይ በአምላክ ላይ የተሳለቁበት/ያፌዙበትን መድረክ ከቶ አይረሳም።

ትንተናዬን በማስረጃ ላስደግፍ

አንድ በወያኔ ፓርላማ ውስጥ የሚገኙ ብቸኛ ተቃዋሚ (ስማቸው አቶ ግርማ ሰይፉ ይመስሉኛል ባልሳሳት) “አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ” ብለው ንግግራቸው ሲደመድሙ “አባ ዱላ ገመዳ” የተባለው (የወያኔ የጭነት አጋሰስ’) ብለው ሰዎች የሚሳለቁበት “የወያኔ ፓርላማ አፈ ጉባኤ”  ላንቃው እስኪሰነጠቅ የሳቀበትን እና የወያኔ ፓርላማ አባሎችም እሱን በመከተል አዳራሹን ሳቅ በሳቅ እንዴት እንዳስተጋቡት በቴሌቪዥናቸው የተላለፈውን የውስጥ ገመናቸውን ያሳዩንን አስታውሱ።


ሆን ተብሎ የአገሪቱን ሃይማኖቶች በማዋረድ የሕዝቡን አምላክ እና በሃይማኖት አስተማሪዎቹ ላይ በመሳለቅ የሕዝቡን “ኤቲክስ/ግብረገብነት” እንዲሰበር በማድረግ ማሕበረሰቡ ወደ አረመኔነት ከተለወጠ፤አስቀድመን የተነጋገርንበት የሳብቨርዥን/የብከላው ዘመቻ ይሳካል ማለት ነው። ሕብረሰተብ የነበረው ገብረገብ እና ሃይማኖት እያንኳሰሰ  በተጓዘ ቁጥር ሕብረተሰቡ አረመኔ እየሆነ በሄደ ቁጥር “ግድያ፤ ስርቆት፤ ውሸት፤ ይሉኝታ፤ ክሕደት” ይሰፍናል። ስለሆነም ‘ሆን ብለው’ ያቀዱት የማናጋቱ ሴራ ለማቃናት ይቀ’ላቸዋል ማለት ነው። አንደ ኢትዮጵያ ያለ በፈሪሃ እግዚአብሔር የሚጓዝ ማሕበረስብ፤ ወደ አረመኔነት ሲለወጥ “ሰውን በቁመናው ወደ ገደል መወርወር፤ሰው ገድሎ ቆዳውን መግፈፍ፤ ነብሰ ጡር የጸነሰቺውን ሕፃን ከማሕጸንዋ ከነ ሕይወቱ በቢላዋ ቀድዶ እሱን እና ልጇን መግደል” የመሳሰሉትን አረመኔያዊ ባሕሪዎች እንዲታዩ ክፍተት ይሰጣል። 


ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጽሟል። የበደኖ የመሳሰሉ እልቂቶች እና አሁንም በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የጎሳ ጽዳት ዘመቻ እየተከናወነ ያለው ሂደት “የአረመኔነት” ባሕሪ በወያኔ ጊዜ “በዲስታብላያዘሺኑ” /በማናጋቱ ሂደት ውስጥ የተፈጸመ ሴራ ነው ማለት ነው። ለዚህ ነው “የሕዝብ ተጠሪዎች” ነን እያሉ “የአምላክ ስም” በጠራ የፓርላማ ተቃዋሚ አባል ላይ የወያኔ ፓርላማ አባሎች እና አፈጉባኤው “የተሳለቁበት”።


ባጭሩ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ የምፈልገው “የተረጋጋ ሃይማኖት” እንዳይኖር ሴራው በዚህ እና በመሳሰሉት ዘዴዎች በማከናወን ሕብረተሰቡ ፈጣሪው እንዲንቅ እና “ዲሲፕሊን” ወይንም “ግብረገብ” አንዲጎድለው በማድረግ፡ “ክሕደት እና ግድያ” የመሳሰሉ ሕብረተሰቡ በነውርነት ሲመለከታቸው የነበሩትን “ነውሮች” እንደ “ነውር” እንዳያያቸው አድርጓል ማለት ነው። ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን “ካት ትሮት ሜንታሊቲ”/cut-throat mentality (ይሉኝታ የሌለው) ዘረፋ/ኰራፕሽን/ንቅዘት” እና “አንተ የኔ ጎሳ ቋንቋ ተናጋሪ ስላልሆንክ ከክልሌ ውጣ” እየተባለ፤ አገሪቱ በማናጋት ሂደት ውስጥ “እየተናጠች” የምናያት።


ከላይ የጠቀስኳቸው የፖለቲካ፤ የሚዲያ፤ የሃይማኖት፤የጎሳ ወዘተ..ወዘተ….ተቋማት “ያገሪቱን ግንድ” በመገዝገዙ፤በማናጋቱ ትእይንት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት በሳብቨርሲቡ/ በጥቃቱ ዘመቻ በመሪዎቻቸው “ማለትም” በወያኔ እና በኦነግ ፕሮፓጋንዳ እየተመሩ ወደ አስፈሪው ሂደት እየወሰዱን ነው። የሃይማኖት ተዋናዮችን ስትመለከቱ የተዘረጉላቸው የ“ideological subversion” ሴራ እየተመሩ ‘ከዓረቦች’ በአላህ ስም፤ በዋሃቢም ስም፤ ከምዕራቡ ዓለም ደግሞ በጴንጤ፤ በአይሁድ ወዘተ….. እየተጠመደ በማያውቀው መርዝ እየተመረዘ “በማናጋቱ ሂደት” ውስጥ እየተጓዘ ነው ማለት ነው። 


 ፈላሻዎች ኢትየጵያዊነታቸው፤ አፍሪካዊነታቸው እንዲክዱ ተደርጐ፤ አይሁዶች ነን በማለት የገዛ አጋራቸውን አውግዘው ወደ አይሁዶቹ አገር ወደ እስራል በገፍ በሕጋዊ ሴራ ወደ አዲስ ባርነት እራሰቸውን በማዘጋጀት “ባርነትን” ተቀብለዋል። በርካታ እህቶች እና ወንድሞች በአረብ አገር በወያኔ አስፈጻሚነት ወደ ባርነት እየተላኩ ለመገልጽ በሚያዳግት ግፍ እየተገደሉ እና እየተረገጡ ይገኛሉ። ግልፅ የሆነ ንግግር ነው እየተናገርኳችሁ ያለሁት።


የሳብቨርዢኑ/ብከላው ጥቃት፤ ‘ከውጭ’ የሞሳዶች፤የሲአይ ኤ እና የመላ አረቦች ሴራ እና ቅንብር፤- “ከውስጥ ተዋናዮች” ደግሞ ወያኔዎች እና ኦነጎች ሆነው በመተባባር የሕብረተሰቡን እና የተረጋጋውን ማሕበረሰብ “በማናጋቱ ሂደት” የሰነዘሩብንን ጥቃቶች ስትመለከቱ ጥቃቱ በግልጽ ይታያቹሃል። 


እስላሞቹም ቢሆን ካሁን በፊት ያላየነው በክርስትያኑ ማሕበረሰብ ላይ፤ በቤተክርስትያን እና በገደማት፤በመነኮሳት ግድያና ቃጠሎ መፈጸም። አለፍ ብሎም በመስጊዶችና የተቀደሱ የእስላም መሪዎችን መቃብሮችንም አስነዋሪ የማፍረስ ተግባሮች ታይተዋል። እስላሞቹ ሴቶችም ወንዶችም ዓረባዊ ባሕል እያጠቃቸው በግልጽ ይታያሉ። አለባበሳቸው ቋንቋቸው፤ስማቸው ጺማቸው ኢትዮጵያዊ ሳይሆን “አረባዊ” ወይንም “ፓኪስታናዊ” አስመስሏቸዋል። 


አንዳንዶቹ በዲሞክራሲ ጥያቄ እየተነሱ “አገራቸውን” በሁለተኛ ደረጃ በማስቀመጥ “ሃይማኖታቸው እስላም አገራቸው እና መሪያቸው አላህ” በማለት ኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤታቸው እንጂ ደም እና አጥንታቸው እንዳልሆነች በመስበክ፤ እራሳቸውን “የሃይማኖት ብሔረተኞች” አድርገው በማስሰለፍ “ከጎሳ ብሔረተኞች” ጋር ፍጥጫ ገብተው አገሪቱን በማናጋት ሂደት ላይ ይገኛሉ።የsocial code of behavior የማሕበረሰቡ የመለያ ባሕሪዎች/ቁልፎች ተለወጧል ማለት ነው።

ሚዲያዎቹም ስንመለከት።

 የዜና እና የትችት ድረገፆች ከምሁራን እና የአገር ሉአላዊነትና አንድንትን ከሚበርዙ ተቃዋሚዎች የጋራ ስምምነት በመፍጠር፤ የፐርኦፓጋንዳቸው አሰራጮች በመሆን ግራ ቀኙ ሳይደስሱ እየተጓዙ፤ እራሳቸውን በጤነኛ ተቃዋሚነት ሽፋን ገብተው የደበቁ ተገንጣዮች እና የመሳሰሉ ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት በብእራቸው እና በየዌብሳይታቸው እየቀባቡ ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሕዝቡን ሕሊና በማጠብ በጥቃቱ ዘመቻ እጃቸውን አስገብተዋል። ኢትዮጵያዊያን እጅግ ሲበዛ ተጃጅለዋል ስላችሁ በእርግጠኛነት ነው። በየስብሰባው አዳራሽም ሆነ በሰላማዊ ሰልፎች የሻዕቢያ፤ የኦነግ፤ የኦብነግ ባንዴራዎች ከትዮጵያ ሰንደቃላማ ጋር እየቀላቀሉ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ ማየት የጥቃቱ ዘመቻ ተቀባዮች ሆነው በግዝገዛው ላይ ሳያተወቃቸው ተዋናይ ሆነዋል። ይህ ከፍተኛ የውርደት ውርደት እና ለጠላት መንበርከክን ያሳያል።

 ሚዲያዎቹ ከፍተኛ የብከላ ሜዳዎች/መናኸርያ ሆነዋል። ሚዲያዎችን እየተመለከቱ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችም አብረው ከንፈዋል። የሻዕቢያ፤ የኦነግ፤የኦብነግ የወያኔ… ባንዴራዎች እንዲውለበለቡ ፈቅደዋል። ይህ ካልቀፈፋቸው የወያኔን ባንዴራ ለምን ማውለብለብና በየቦታው መቃወምና ከተሰቀለበት ማውረድ ወይንም ትግሬዎች የወያኔ ባንዴራ ለብሰው ወይንም እያውለበለቡ ሲያዩ ለምን እንደሚያወግዟቸው እጅግ አስገራሚ የሕሊና ንቅዘትን ያመላክታል። የኢትዮጵያ ወጣቶች በሚዲያዎች የሚተላለፉትን የብረዛ ፖለቲካ ተበክለው የአገራዊ ሉአላዊ ዕይታ ግንዛቤአቸው መበስበሱ አይነተኛው ምልክት ነው። 


ሚዲያዎቹ ወጣቱን በሳብቨርዢኑ ዘመቻ ለማጥቃት እሩቅ ተራምደዋል። በዚህ ሳይወሰኑ፤ ኢትዮጵያዊያን ነን የሚሉን የነዚህ ሚዲያ ጋዜጠኞ “ኢሳያስ አፈወርቂን” የአመቱ ሰው፤ በማለት በሚዲያዎቻቸው በማውጣት ፤ በሕዝባችን ላይ ያፌዙ የተቃዋሚ የዜና አውታሮች አሉ። ኤርትራ ውስጥ የመሸገው እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ የመሳሰሉት የግንቦት 7 መሪዎችም “የኢሳያስ ሰብአዊነትና ዲሞክራሲነት” ለሕዝባችን ለመሸጥ በኢሳት ቲቪ ቀርበው በፕሮፓጋንዳ ገበያ በማሻሻጥ ስራ ላይ ተጠምደው፤ የዲስታብላይዘሺኑ ዘመቻ ተዋናዮች በመሆን የራሳቸውን መጥረቢያ ይዘው በግዝገዛው ስራ ላይ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።በሙሉ እንኳ ባይሆኑ አንዳንድ ጋዜጠኞች የተቃዋሚውን አንድነት (በተለይ በቅንጅት ወቅት) በማፍረሱ ሂደት ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን አንዘጋውም።

የፖለቲካ ድርጅቶችም

 ወያኔ እና የውጭ አገር ተዋናዮች በሚሰጧቸው የዲሞክራሲ ጨዋታ ገብተው እራሳቸውን በማስገመት 22 አመት የረባ ስራ ሳይሰሩ የታሰሩትንም ሳያስፈቱ እራሳቸውንም “ወንጀል ሳይሰሩ” ወንጀል ሰርተናል በማለት ወያኔ ባዘጋጀላቸው የይቅርታ ማስፈረሚያ ፎርም (ቅጽ) ፈርመው ከእስር ወጥተው “ሕዝባዊ ማዕበሉን” በሚገርም አሳፋሪ ብልሽት አኮላሹት። ሊወለድ እራሱን ከማሕጸኑ ያስወጣ አብዮት ጎትትተው ከማስወለድ ይልቅ፤ እንዳይወለድ ወደ ማሕጸኑ እንዲገባ ገፍተው ወደ ሗላ ወሸቁት። ወያኔ የልብ ልብ ተሰምቶት እነሆ የማናጋቱ ሂደት እየቀጠለበት ይገኛል።      


 ይህ ሁሉ ስንመለከት ሁሉም በወያኔዎች እየተመሩ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የየራሳቸውን መጥረብያ በመያዝ አገሪቱን በመገዝገዝ በቆረጣ ሂደት ላይ ናቸው። ስለዚህም የማናጋቱ ሂደት እየተጠናቀቀ ሲሄድ ወደ ሦስተኛው ምዕራፍ ማለትም ወደ Crisis” አገርን በቀውስ ሂደት ማስገባት ወደ ሚለው ደረጃ እያመራ ይገኛል።


3ኛው ሂደት ማለትም Crisis ቀውስ ሲከሰት

 “አናርኪ” ስርዓተ አልባነት ይከሰታል። ለነገሩ የተገባደደ አንኳ ባይሆንም በከፊል ስርዓተ አልባነቱ እየተካሄደ ነው። ሁሉም የየክልሉ ጎሰኛ ሃላፊ፤ፖሊስ፤የሕግ ዘርፎች ሁሉ፤ የየራሳቸው ስልጣን በመያዝ ማእከላዊው ከፌደራሉ መንግሥት ተብየው ቁጥጥር ውጭ ናቸው። ተበደልኩ ብሎ አንድ ዜጋ ወይንም ማሕበረሰብ/ቡድን/ተቋም ወዘተ…ወደ ፌደራል መንግስት አቤት ሲል፤ የፌደራሉ መንግስት የክልሉን ስልጣን መጋፋት ስላማንችል እንደፈረደብህ እዛው “ተጋፈጥ” ይሉታል።


 ማስረጃ ልስጥ።
  ወያኔ በሥልጣን አፍላው አመት፤ የጎጃም ገበሬዎች በብአዴን ወረበላ ባለሥልጣኖች መሬታቸው እየተጠቁ ለብእዴን ደጋፊዎች ሲሰጥ ለደረሰባቸው በደል አቤት ለማለት አዲስ አበባ ድረስ በእግር ተጉዘው (አንዳይጓዙም ተከልክለው በድብቅ ነበር የተጓዙት) አቤት ሲሉ እነ መለስ ዜናዊ አይናችሁን አናይም ብለው “ይክልሉ ባለሥልጣኖች ጋር ተጋፈጡ’ ብለው ነበር የመለሿቸው። የሚበላ ምግብ እንኳ አጥተው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‘ተክለሃይማኖት ቤተክረስትያን’ ቅጥር ግቢ ወስጥ ተጠልለው የነበሩት ምስኪን ገበሬዎች ከሚመገቡት ዳቦ ይዘውላቸው እንደሄዱ በወቅቱ ፎቶግራፎቻቸው እና ዜናውን በኢትዮፕያን ረጅስተር“ መጽሄት መውጣቱ ይታወሳል።

ለዚህም ነው የቀውሱ/የ Crisis” ሂደት ስፋት ስንመለከት፤ “በሺዎቹ የሚቆጠሩ የአማራ ሕብረተሰብ ገበሬዎች፤ሽማግሌዎች፤ሕፃናት እና እናቶች ከጉራ ፈርዳ፤ ከጋምቤላ ከኦሮሞ ክልሎች እየተጨፈጨፉ፤ንብረታቸው እየተነጠቀ እንዲወጡ ተደርጐ “የጎሳ ጽዳት” /ኤትኒክ ክሊንሲክ” ሲፈጸምባቸው ለማየት የበቃንብት ክስተት የቀውሱ/የ Crisis” ሂደት ግስጋሴ ላይ መሆኑ ምልከት ነው ።


ይህ ክራይሲስ/ቀውስ ቀደም ብየ እንዳልኩት “አስቸኳይ እርማት ካልተደረገለት” ፤በሌላው ወገን ያለው ተጠቂው ክፍል ትእግስቱ እያለቀ በሄደ ቁጥር “የመልስ ምት” ለማጥቃት ሲገደድ፤ ሩዋንዳ ውስጥ ያየነውን አስከፊ የእርስ በርስ/ሲቪል ኮንፍሊክት/እልቂት (ጦርነት) ሊነሳ ይችላል በማለት ከጥቂት አመታት በፊት በአሲምባ የውይት መድረክ ፓልቶክ ክፍል  ተጋብዤ የሰጠሁት አስተያት ዛሬ ያልኩትን ምልክት ቀስ በቀስ እየታየ ነው። ለዚህም ቀውስ እንዲከሰት የወያኔ መሪዎች እና በወያኔ ሥር ተጠልለው የመገንጠል ዓላማ ለማካሄድ ያደፈጡ የተገንጣይ አባሎች አማካይነት ቀውሱ እንዲከሰት በመግፋት ላይ ናቸው።


4) አራተኛው ዲስታብላየዘሽን 
 

የሚለው የመጨረሻው ሂደት “አገር ተበታትኖ” እህት እናት ወንድም ዘመድ ተለያይቶ የመጨረሻው የአገሪቱ ግብዓተ መሬት የሚከናውነብት ደረጃ ነው ማለት ነው። ኤርትራ በዛው ደረጃ ትገኛለች። የኤርትራ ሕዝብ በዲስታብላይዘሽን ሂደት እየተራመደ (በማረጋጋት ስም) ሕይወቱ ተናግቶ ቀውስ ውስጥ ገብቶ አበባ ይዘው ሆ ሲሉ የነበሩ ጉረኞች ዜጎቿ ወደ ሲኦል ገብተው “እራሳቸው እና ቤተሰቦቻቸው” ቀውስ ውስጥ ገብተው ለሲናይ በደዊን ዘላን ዓረቦች መጫወጫ ሆነዋል።  ኢትዮጵያም በዚህ ሂደት ላይ በወያኔ ምክንያት በ2ኛውም በ3ኛውም ደረጃ ሂደት ላይ ትገኛለች።
 

አብዛኛው ጽሑፌ ለወደፊቱ ለማሳተም እያሰብኩ ካለሁት መጽሐፍ የተቀነጨበ ነው። የሳይኮሎጂካል ሳብቨርሲቭ ጥቃቱ ያለ ጠመንጃ በፕሮፓጋንዳ አማካይነት እንዴት እንደተከናወነ ለማሳየት የሞከርኩትን እዚህ ልግታና፤ በመጨረሻ ከዚህ ጽሑፍ ላይ ተያያዢነት ያለው የአርበኛዋና የምህርትዋ የ ዶ/ር አበባ ፈቃደ የምንፈልገውን ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉን ነገሮች ምንድን ናቸው?”  የሚለውን ጽሑፍ ጉግል አድረጋችሁ ብታነብቡ የኢትዮጵያዊነት ሕሊናችን እንዴት ቀስ በቀስ እንደተሸረሸረ/erode/ እንደሆነ ምክንያቶቹን አስቀምጣቸዋለች እና እሱን እንድታነቡ እያሳሰብኩ፤ እዚህ ላቁም።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ Editor Ethiopian Semay (getachre@aol.com)