Monday, July 21, 2014

ውድ ሰዓሊ ስዕልዎን ያስተካክሉ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
ውድ ሰዓሊ ስዕልዎን ያስተካክሉ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
(Ethiopian Semay) getachre@aol.com

ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን ጉዲት የአክሱም ስልጣኔን  ያወደመቺው  ትግሬውን ለማስደሰት እና አማራውን ለማበሳጨት ነው” ይለናል!

ስለ ጉንቦት 7 ተከታዮች ጸረ ትግሬ ዘመቻቸው ጽሑፍ በመረጃ ለማዘጋጀት ስዘጋጅ፤ ድንገት ሳለስበው ይህ ጉደኛ ነገር ከመሃሉ ተከሰተብኝ እና ቀዳሚነት ሰጠሁት። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ተድላ አስፋው ሳለስበው በድንገት የላከልኝ የተሰራጨ (ፎዋድ) ጽሑፍ መልስ መስጠቴ ነው። ያንን የግንቦት 7 (3ኛው ክፍል) ረዢም ሐተታየ በማቆየት የተጠቀሱት ሁለቱም ቅደም ተከተል መልስ ለመጻፍ ወሰንኩኝ። የተድላ አስፋው ራሱን የቻለ መልስ በሌላ ርዐስ/ጉዳይ እገልጸዋለሁ፤ የሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን ግን ይኸው። ሁለቱም ለየቅል ይቀርባሉ ተከታተሉኝ።በኚህ ቁጡ ሰው ልጀምር።ንባባችን ከመቀጠላችን በፊት ማሳሰቢያ አለኝ። (የኔ ብሎግ ባንድ ጊዜ ከአንድ ርዕስ በላይ መለጠፍ ስለማይችል ይድረስ ለውድ በልጅግ ዓሊ፤ እርስዎም አንደሌሎች? የሚለውንም የመሳሰሉ ዛሬ የጻፍኳቸው ወቅታዊ ትችቶችም  ስላሉ፡ ለማንበብ በሚከተሉት ድረገፆች(Ethiopatriots.com )  (welkait.com ) ይጐብኙ።)

ህ ሰው ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን ይባላሉ። አንገታቸው ላይ ማተብ ያጠለቁ ክርስትያን ይመስላሉ። ክርሰትናውን ለእኛ ለትግሬዎች የሰጡን አማራው እሳቸው አንደሆኑ እየነገሩንም ይመስላል። በማተቤ ልዳኝ! ነበር ያሉት አቶ አሰፋ ጫቦ?

በምን ልጀምር? አንዳንዴ ከመገረሜ ብዛት በምን አንደምጀምር አግሩም እጁም መያዣ መጨበጪያው ያጥረኛል። ብቻ መሞታችን ብናውቅም እንደ አልአዛር ሞቶ የመነሳትን ዕድል ለተቻረን ወገኖች አስጀምሮ ለማስጨረስ የሚሳነው አምላክ የለም  እና ሐተታየ ወያኔነን ውለህ አትግባ ብየ ልጀምር። ለምን አልልም?  “ወያኔ ውለህ አትግባ” የምለው እኮ የምሬን ነው። እኛ ትግሬዎች በወያኔ እየተሰደብን አንዳይበቃ አንደገና በሌሎች ወገኖች ተጨማሪ ዱላ እያረፈብን ነው።  እወነቴን ነኝ። እኛ ትግሬዎች ወያኔን ካልተራገምን ማን ይራገምልን?

አሁን አሁን’ማ ጭራሽኑ “ትግሬ የሚባል አክሱም አይወለድም እያሉን ነው። ትግሬ የአማራዎች አንጂ የትግሬዎች አይደለም። የሚሉ ጉደኛ ጻሐፊዎች በግልጽ ሳያፍሩ ብቅ እያሉ ነው። ሰሞኑን!!! በዘሃበሻ ድረገጽ!!!

አክሱም የክርስትያኖቹ የአማራዎች ነው፡ ሃይማኖት የሌለው የትግሬ ማሕበረስብ ከየት አንደመጣ አይታወቅም፤ ዮዲት አማራውን ከመሬቱ ከትውልድ አገሩ ከአክሱም በዩዲት ጉዲት ተባርሮ፤ ክርስያን ላልነበረው የክርስትያኖቹ “የአማራዎቹን” የአክሱም መሬት በዪዲት ጉልበት ተሰጥቶ’ታል።  ሃይማኖተ ቢሱ ትግሬ “የራሱ ያልሆነውን አክሱም የኔ ነው” ብሎ ከያዘ በሗላ ፤አማራ ወደ ጐንደር፤ ወደ ጎጃም፤ ወደ ሸዋ፤ ወደ ወሎ በዩዲት ተሰድዶ አክሱምን ከየት አንደ መጡ ለማይታወቁ ትግሬዎች አክሱም ለትግሬዎች ተሰጠ“።  የሚል ናላው የዞሮው  የሚመሰል “ሰዓሊ“አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው   amsalugkidan@gmail.com ” የተባለ  “ዘር የማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ፤ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ July 15, 2014” የሚለውን ጽሑፍ Ze-Habesha በተባለው ድረገጽ የተለጠፈውን ያንብቡ።

አምሳሉ ገ/ኪዳን ማለት ግንቦቴ 7ቶች ሲያስነጥሳቸው መሃረም የሚያቀርብ  ጸረ ትግሬ ”ዘረኛ” ግለሰብ ነው። “ኩርኩር!” (የግንቦት 7 ሰባት ተሰላፊዎች “ኩርኩር” ፤ምን ማለት አንደሆነ ኤርትራኖቻችሁን ጠይቁ )።፡ ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን እያለን ያለው፤ የአክሱም ጥበብ እና ቅርስ የክርስትያኖቹ አማራዎች የገነቡት ስለሆነ፤ የአክሱም ጥበብ፤ መጻሕፈት እና ሃውልቶች ያፈረሰቺው “ክርስትያን ያልሆኑ ከየት አንደመጡ የማይታወቁ ትግሬዎችን ለማስደሰት አማራውን ለማበሳጨት” ብላ ነው ያወደመቺው። ይለናል ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን።  ወይ ቱ ጉዱ!

ስለዚህም ይልና “አክሱማዊው አማራው ከመሰደድ በመለስ የነበራቸው ብቸኛ አማራጭ አማራነታቸውን ማስተባበል ወይም አማራ እንዳልሆኑና ትግሬ እንደሆኑ ለአጥፊዎቻቸው ለዮዲት ጉዲት ሠራዊት መግለጽ ነበር።” ይላል ሰአሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን።  የዘመናችን “መጻጉእ ፍጡራን” አማራን አንከላከላለን እያሉ አማራውን እና ትግሬውን ይበልጥ በማራራቅ ቅራኔ ለመፍጠር የማይከጅሉት “አማራዎች ወይንም አማራ ተመስለው የሚጠጉ አማራ ያልሆኑ “እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ” የማሳሉ ስለ አማራ “ከየት ወዴት የሚጽፉ” ፍጡራን አሉ።

አምሳሉ ግን በአይነቱ እና በዘረኛነቱ ለየት ያለ እኔንም መጀመርያ ያጃጃለኝ በሗላ በደምብ ጽሑፉን ሳነበው ግለሰቡ ካስገረመኝ ግለሰብ ይህ ለየት ያለ ዓይን ያወጣ የዘር በሽታ የተጠናወተው ሕክምና የሚሻው ግለሰብ ነው። እውነትም ይህ በምናምን …. ገብረኪዳን የሚያልቅ እና የሚጀምር ነገር ጉደኛ ነው (ተመሳሳይነት ያላች እናንተን አይመለከትም)።አምሳሉ ገ/ኪዳን- ትግሬው ገ/ኪዳን ደስታ በአምሳያው የፈጠረው ይመስላል። ያኛው አማራን ነክሶ ሲይዝ፤ ይህ ደግሞ ጭራሽኑ “ዩዲት አክሱምን ስታቃጥል ትግሬውን እየተወች፤ ትግሬወን ለማስደስት አማራውን እየጨፈጨፈች አንዲሰደድ አድርጋ አክሱም ለትግሬዎች ሰጠታቻቸው ሄደች” ይለናል።  ኢኽ!  ትግሬ ጭራሽኑ ጥረስ ውስጥ ገባ እኰ። ምን ይሻላል! መቸም አንዲህ ያለ አየር የማይችለው የገማ ጠረን ለወዳጅም ለጠላትም የሚበጅ አይደለም።
  
ጠባቦች ሆይ! እባካችሁ፤ በቁጥር ጥቂት የቀረናችሁ ተቃዋሚ ጋር የቆምን ትግሬዎችን ባታስቀይሙን እና ተጨማሪ ዱላ አንዳንሆንባችሁ ራሳችሁ ባትጋብዙን ይመረጣል። እጅግ የማደንቀው የአዲስ ነገር ኪያንቲ ጋዜጠኛ የነበረው “መሐመድ ሰልማን” አንዲህ ይላል:-

“ ኢትዮጵያ ውስጥ እግር ኳስ ያደገችው በፒያሳ ነው። በነ ፍቅሩ ኪዳኔ ዘመን፤ የያኔዎቹ የፒያሳ አራዳዎች ኳስ በካልሲ እየሰሩ ይጫወቱ ነበር። ድሮም አሁንም የፒያሳ ልጅ የሆኑት የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በተከላካይ ስፍራ ይጫወቱ ነበር። አሪፍ ተከላካይ ነበሩ። አብረዋቸው ይተጫወቱት አቶ ፍቅሩ ለዚህ ጉዳይ “የፒያሳ ልጅ” በተሰኘው መፅሐፋቸው እንዲህ ይቀልዳሉ፦

“ ወዳጄ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በተከላካይ መስመር ይጫወት ስለነበረ አሁንም የመከላከል ተግባሩን ቀጥሏል። ምንም አንኳ አርቢትሩ ቀይ ካርድ እያሳየ ቃሊቲ ቢከተውም፤ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የፖለቲካ ቡድን መጫወቱን አላቋረጠም።” ይላል።


እናም፤ በተቃዋሚ የቆምን እኔ እና መሰል ጥቂት ትግሬ ወንድሞቼ ከሰዓሊ አምሳሉ እና መሰል ጸረ ትግሬ ግለሰቦች እኛን ከትግሉ አግልለው ትግሉ የዘረኞች ሜዳ አንዲሆን እና አንዲፈነጩበት፤ “ተስፋ ቆርጠን” የወያኔ ወገኖች፤አንድንሆን እየገፈተሩ ወደ ወያኔ ካምፕ ሊከቱን  እና የተፈለገው ጸያፍ ጉም በዙርያችን ላይ አንዲያንዣብብ ቢጥሩም፤ ለኢትዮጵያ ቡደን መጫወታችንን ለእነ ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን እና መሰል መሰሪ ቡድኖቹ አንዲያውቁት በዚህ አጋጣሚ መልእክቴ አስተላልፍላችለሁ። አማራን ከጠባቦች ጥፋት መከላከል ስንል “ትግሬዎችን የዮዲት ፍቅረኛ ማድረግ”፤ “አክሱምን ለአማራዎች መሸልም” ፤ ትግሬዎች ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ስደተኞች እያሉ መቃዠት ማለት አይደለም። ወድ ሰዓሊ ስዕሎን ያስተካክሉ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትየጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com