Sunday, June 30, 2013


     Notice from Ethiopian Semay Editor:-

Stay tune for new commentary that revealed the new secret and tactic of OLF, some Diaspora opposition websites, and individual elements from the opposition who are in the new campaign of blackened our good names in campaigning of labeling bad names (such as naming recognized and hard core patriotic nationalist Ethiopians as "Weyane" and also blackmailing patriotic Ethiopian nationalists names illegally on their webistes in order to kill the spirit of patriotic Ethiopians when fighting TPLF/OLF propaganda. Their names with evidence will be listed on the upcoming commentary for all to see and judge these elements of distortion who these individuals are from the opposition and from the enemy camps as well. As I told you before right after the split of TPLF and Kinijit , our struggle will be overlapped due to the new element from those groups , who now are on the front line of campaign of sabotaging the struggle since then. Their primary goal is to rehabilitate and promote  the agenda of OLF and EPLF with all their crime . Stay tune for the commentary.

Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.co
June 30/2013

ኢትዮጵያዊው ዑሴይን ቦልት የራሱን ሪከርድ አሻሻለ!
 ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 

ለለውጥ ያህል ለምን አንባቢን ፈገግ ልታደርግ በምትችል የአዲስ አበባ ዘመነኛ ቀልድ አልጀምርም?

     አንድ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሲዝናና ያመሻል፡፡ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ወደቤቱ ሊሄድ ቄንጠኛ ፕራዶ መኪናውን ሊያስነሳ ቢሞክር ያልታሰበ ብልሽት ያጋጥመውና ሞተሩ ለመነሣት እምቢዬው ይለዋል፡፡ ቢለው፣ ቢለው አልሆነለትም፡፡ ከዚያም ሌላ ምርጫ ሲያጣ ላዳ ታክሲ ያስጠራና ወደቤቱ እንዲያደርሰው ሹፌሩን ይጠይቀዋል፡፡ በቅድሚያ ግን በስንት እንደሚያደርሰው ሒሳቡን ለማወቅ ይፈልግና “ለቡልጋሪያ ማዞሪያ ነው ቤቴን፣ በስንት ነው እንዴ’ምታደርሰኝ?” ይለዋል፡፡ ይህ ባለታክሲም ብዙም ሳያቅማማ “150 ብር ይከፍላሉ፤ ይግቡ” ይልና ጋቢናውን ይከፍትለታል፡፡ ይሄኔ ባለሥልጣኑ ተገርሞ “ቧይ! ለቡልጋሪያ ማዞሪያ ለዚህን ያህል ቡዙ ገንዘብ ማለተይ ለሞቶ ሃምሳ ብር ከጠየቅኸኝ መለ ብልህ ስንት ልትለኝ ነው እንዴ?” ይለዋል፡፡ ያ አራዳ የአዲስ አበባ ላዳ ታክሲ ሹፌር ቀበል ያደርግና “ ጌታዬ፣ የማይመለሱ ከሆነ በ50 ብርም ቢሆን እወስደወታለሁ!” አይለው መሰላችሁ? ባለጌ ሹፌር፡፡ አሸባሪ ብሎ ዘብጥያ ማውረድ እሱን ነበር፡፡ “በዚህ ዚቅ ፈገግ ካላሉ ወያኔ ነዎ” የሚል ቅብጠት የሌለብኝ መሆኔን በታላቅ ትህትና ከመግለፅ በተጓዳኝ የሐሳብ ፈረሴን ልኮልኩልና ንቅድሚት ልሸምጥጥ - ማሣቅና መሣቅ ዱሮ ቀረ፡፡ ዛሬ ሁሉ ነገር አርቲፊሻል ሆኖ እውነተኛ ፈገግታ ጠፍቷል ወዳጄ፡፡ እንዲያው ነው የምናገጥ፡፡

    
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያው መቶ ብር መጠሪያ ዑሴይን ቦልት(Usain Bolt) መባሉን ሳትሰሙ አትቀሩም ብዬ ልገምት፡፡ ዑሴይን ቦልት ደግሞ በ(እዚች ቦታ ስደርስ ባለቤቴ ‹አሁንም ደገሙልህ› አለችኝ፤ ምን? እነማን? እመለስበታለሁ፡፡ አላበዙትም?) ዑሴይን ቦልት ደግሞ በዓለም የመቶ ሜትር ሩጫ ቀዳሚውን ሥፍራ የሚይይዝ የሰው ቺታ(አቦሸማኔ?) ነው፡፡ የሀገራችን መቶ ብር ከኪስ ከመውጣቱ እንደወፍ እየበረረ አንዳችም ፋይዳ ያለው ነገር ሳያከናውን በቅጽበት ስለሚያልቅ ስም ማውጣት የማይገደው የሀገሬ ሰው በተለይ ወጣቱ መቶ ብሩን በዚያ ጃማይካዊ የመቶ ሜትር ሯጭ ስም ሰየመው፡፡ ግሩም ተመሳስሎ ነው፡፡ አሁን አሁን ደግሞ መቶ ብራችን እንደቦልት በ9 እና 10 ሴኮንዶች ብቻ ሳይሆን በሁለትና ሦስት ሴከንዶች ድራሹ ሊጠፋ ይዟል፡፡ እንትና እሚባል ተራ ባር ውስጥ አንድ ሻይ 8 ብር መግባቱን ታውቃለህ? ተራ ሽሮ 50 ብር የገባባቸው ባለምንም ኮከብ ሆቴሎች እንዳሉ ታውቃለህ? ብርህ ከኪስህ ሾልኮ የጠፋብህ የሚመስልህ ጊዜ መሙላቱንስ ልብ ብለህ ታውቃለህ? ሪከርዱን አሻሻለ ማለት እንግዲህ ይህን የገንዘብ ዕብደት ለመግለጽ ነው፡፡

    

ሀገራችን ውስጥ ጉድ እየንተከተከላችሁ ነው ጎበዝ፡፡ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው መቶ ብር ማለት ከጥንቱ አንድ ብር ፊት ሊቆም የማይቻለው የማሽላ እንጀራ ሆኗል፡፡ በዘመነ ኃይለ ሥላሤ አንድ ኩንታል ነጭ ጤፍ ከነማስፈጫው 12 ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም እንደነበረ ትናንት አንድ ሰውዬ አጫውቶኛል፡፡ ይህ ሰው 62 እና 63 ዓመተ ምሕረቶችን በማጣቀስ እንደነገረኝ ከሆነ የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ ላምባ፣ ሥጋ፣ ቅቤ፣ የሰላሱት እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣ ልብስ፣… በኪሎም ይሁን በሊትር ወይም በሥፍርና በሜትር በዝቅተኛ የመነሻ አሃዳቸው ከአንድ ብር እጅግ በሚያንስ ቁርጥራጭ ሣንቲሞች ይገዙ እንደነበረና ነገር ግን ሣንቲሞቹን ለማግኘት ለብዙዎች ዜጎች ይከብድ እንደነበረ ቁጭት በሚነበብበት ትዝታ ተውጦ አውግቶኛል፡፡ ዛሬ እንኳን አንድ ብር መቶ ብር ራሱ ግርማ ሞገሱን አጥቶ የተሙን(አንድ ሣንቲም) ያህል ወድቋል፡፡ ዱሮ በአንድ ወይ በሁለት ተሙኖች የሚገዛ ዕቃ ነበር - በተለይ አሥመራ  ላይ፡፡ ተሙን አይናቅም ነበር፡፡ በልጅነታችን ተሙኖችን እያጠራቀምን አራትና አምስት ሲደርሱ እንጠቀምባቸው እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡(በነገራችን ላይ ከደርግ ጀምሮ ሥራ ላይ በዋለው የአሁኑ አንድ ብር ላይ ምስሉ የሚታየው ባለፈገግታው እረኛ ከዚህ ዓለም እንደተገላገለ ዛሬ ሰማሁ፡፡ ነፍሱን ይማር፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከመኖር ይልቅ መሞት እሚያስቀናበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡)


     ዛሬ ኑሮው ሰማይ ደርሷል፡፡ ድሃ መኖር አልቻለም፡፡ የተፈጠረው ሁለት መደብ ብቻ ነው - ሦስት መደብ የነበረው ቀረ፡፡ ያለውና የሌለው ተብሎ በሁለት ሊከፈል የሚችል መደብ ነው ዛሬ የተፈጠረው፡፡ ሕንድ ወደኢትዮጵያ ገባች፡፡ ይህ ዓይነት የኑሮ ውድነት እንዳለ እንሰማ የነበረው በሕንድ ሀገር ነበር፡፡ የጥንቱ ንዑስ ከበርቴ እየተባለ ሲንቆላጰስ የነበረው መደብ(class) ዛሬ ጠፍቷል፡፡ አንድም ኅሊናውን እየሸጠ ወደላይኛው የአጭበርባሪዎች ጎራ ተቀላቅሏል አለዚያም ወደለየላቸው ያጡ የነጡ ድሆች ወርዶ ተመሳስሏል፡፡ በደህናው ዘመን ከኮሌጅ እንደወጣ በወር የቀስ በቀስ ክፍያ (installment)  አዲስ ኦፔልና ከሴፈሪያን ኩባንያ ውኃ ያልነካት ቮልስዋገን እየገዛ በራሱ መኖሪያ ቤት እየኖረ ሠርክ በግሩም የሎንዶን ሱፍ ይሽሞነሞን የነበረው የዚያኔው ንዑስ ከበርቴ ዛሬና አሁን በተራ የመንደር ጉሊት ገብቶ ግማሽ ኪሎ ቲማቲምና የሁለት ብር በቁጥር ሦስት ወይ አራት የሚሆን ቃሪያ ከጥቂት ቀይ ሽንኩርትና አንድ የጠወለገ ሎሚ በመግዛት(አንድ ሎሚ እንኳን ሁለት ብር ሲገባ?) ሰላጣ ሠርቶ የሚበላበት ዱዲ የሌለው ሙልጭ የወጣ ድሃ ሆኗል(የአለባበሱ ነገርማ አይነሣ!)፡፡ ያኔ በሃምሳ ሳንቲም  ‹ከዚህ መልስ ቁረጥልኝ› እያለ ቤተሰቡን በሥጋ ያሰለች የነበረው ንዑስ ከበርቴ ዛሬ የቲማቲም ቁርጥ ብርቅ ሆኖበት ስታዩት አለመፈጠሩን ትመኙለታላችሁ፡፡ ያኔ የአንድ ወር ደመወዙን አብቃቅቶ መላዋን ኢትዮጵያ ሊጎበኝ ይችል የነበረው ንዑስ ከበርቴ ዛሬ የወር ደመወዙ እንኳንስ ሀገር ሊያስጎበኘው ከደረጃ በታች የሆነ የጥቁር ጤፍ እንጀራ በእንደነገሩ የሽሮ ወጥ በልቶም ከወር እወር ሊያደርሰው አልቻለም፡፡ ትልቁ የሀገርና የማኅበረሰብ ኪሣራ ደግሞ በሚገኝ የወር ገቢ ቢያንስ ከወር እወር መድረስ አለመቻል ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን መረገም ግዘፍ ነስቶ የጭራቅን ያህል አስፈሪ ሆኖ የታየበት ብቸኛው ዘመን ይህ የኛው ዘመን ነው፡፡ እርግማኔን ጀመርኩ - ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ!!


ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ሸልለህ ለመኖር ያለህ ምርጫ አንድ ነው - ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መካድ - በቃ፡፡ ያኔ ዘንጠህ ትኖራለህ - ተንደላቅቀህ፡፡ ኢትዮጵያዊነትህን በካድህ ማግስት ሁሉም ማቴሪያላዊ ችግሮችህ ተጠራርገው ከነሰንኮፋቸው ይነቀሉልሃል፡፡ ያኔ ታዲያ ኅሊና የሚባለው አመዛዛኝ ፍጡር ሊኖርህ በጭራሽ አይገባም፡፡ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልህምና አንዱን መምረጥ ይኖርብሃል፡፡ ኅሊናህን መጠቀም ከፈለግህ ድህነትን መምረጥ ሊኖርብህ ነው፤ ባለጠግነትን መምረጥ ከፈለግህ አቅልህን ስተህ ቀልብህን ወደቁሣዊ አብረቅራቂው ዓለም ሰብሰብ በማድረግ ቀን ከሌት ገንዘብ ሊገኝ የሚችልበትን መንገድ ማውጠንጠን ነው፡፡ እሱም ቀላል ነው፡፡ በዚህ ሂደት እንደነገርኩህ ወያኔ መሆን ከሁሉም መንገዶች የመጨረሻው ቀላል መንገድ ነው፡፡ በዚያ መንደር አእምሮ እንጂ ሀብት በሽበሽ ነው፤ ጤንነት እንጂ መብልና መጠጥ እንደጉድ ነው፡፡ ፍቅር እንጂ ጥላቻና ይሉኝታቢስነት እንደልብ ነው፡፡

    
ወያኔ ሁንና ወይም የወያኔን የአጥፍቶ መጥፋት ፖሊሲ ደግፍና ወደንግዱ ሰተት ብለህ ግባ፡፡ በአንድ ቀን አዳር ትከብራለህ፡፡ አንድም ባለሥልጣን - እደግመዋለሁ - አንድም ባለሥልጣን ለሀገርና ለወገን የሚጨነቅ የለም፤ የሚጨነቅ ከሆነ የሲስተሙን -የሥርዓቱን ማለት ነው - ፍሰት ስለሚያጨናጉል በአፋጣኝ እንዲወገድ ይደረጋልና በዚህ አባባሌ ቅር የሚለው ሰው እንዳይኖር አደራየ የጠበቀ ነው፡፡ በቆሻሻ ቱቦ ውስጥ በአጋጣሚም ይሁን በሌላ መንገድ የሚገኝ ንጹሕ ነገር ያለው አማራጭ ሁለት ብቻ ነው - አንድም ከቆሻሻው ጋር አብሮ ቆሻሻ መሆን አንድም ተለይቶ መውጣት፡፡ ስለዚህ በወያኔ ውስጥ ሆኖ ንጹሕ ነኝ ማለት መፀዳጃ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ፈስ ገማኝ እንደማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዐዋጁ የጸና ነው - ‹በወያኔ ውስጥ የሚገኝ ባለሥልጣን ሁሉ ቆሻሻ ነው› - ቢያንስ እስኪጣራ እንኳን ‹ቆሻሻ› ነው›፡፡ እያንዳንዱ ባለሥልጣንና ካድሬ በሙስና ኃጢያት ያመነዘረ ወይም ከአመንዝራዎች ጋር የተባበረ በመሆኑ ለንስሐ ሕፅበት መትጋት ያለበት ኃጥዕ ወአባሲ ነው - በቃ! እየተዋወቅን?

    

ስለዚህ ከቆሻሻዎቹ ባለሥልጣናት ጋር እየተመሳጠርክ በንግድና በልዩ ልዩ ሙስና ውስጥ መዘፈቅና በአንዴ መክበር ወያኔያዊ መብትህ ነው፡፡ የመክበሪያ ቁልፍ ግን ከፍ ሲል እንደተናገርኩት ኅሊናቢስነት  ነው፡፡ ኅሊናህን ሆድህ ውስጥ ሸጉጠህ ተመሳስለህ መኖር ነው፡፡ ሃቲማህ ግን አያምርም፡፡

 

ኅሊናቢስነት በምን በምን ይገለጻል?


ባለሥልጣንና ካድሬ ከሆንክ የመንግሥትንና የሕዝብን ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ባወጣልህ ዋጋ መቸብቸብ ነው፡፡ እንደየሥልጣንህ ተዋረድ ገንዘቡ አንድም በቦርሣ ታጭቆ በፈለግኸው ቦታ ይመጣልሃል፤ አሊያም በፈለግኸው ዓለም አቀፍ ባንክ በስምህ ይገባልሃል - ዕድሜ ከሰጠህ ትበላዋለህ - ባጭር ከተቀጨህም አይዞህ በይ አይጠፋም - ቢያንስ ጎባንህ ያልፍለታል፡፡ ለጊዜው ግን የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ኪስ ቦታዎችን በቃፊሮችህ እያፈላለግህ ለኢንቬስተርና ለዲያስፖራ በመሸጥ፣ ከነጋዴዎች ጋር በሚደረግ ግልጽም ሆነ ሥውር መመሳጠር ከፍተኛ ጉቦ በመቀበል፣ የመንግሥትን ሀብትና ንብረት ‹ሌላ ዘዴ ከተገኘ በጨረታው አንገደድም› በምትለዋ ቀጣፊ አንቀጽ ሰበብ በሙስና በርካሽ ዋጋ በመሸጥ፣ ገበሬዎችንና ነባር ነዋሪዎችን እያፈናቀሉ የሀገርንና የወገንን መሬት ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሀብት ባወጣ በመቸርቸር፣ ስንቱ ተነግሮ … በነዚህ ሁሉ መንገዶች መክበር ቀላል ነው፡፡ እያየነው? ወያኔዎች ግን ጥቁር ውሻ ይውለዱ!!

    

መክበሩ ይሁን፡፡ ማንም በምንም መንገድ ይክበር፡፡ ኋላ የሚያልፍበት ራሱ ነው፡፡ ነገር ግን የሕዝብ ኑሮ እንዲህ ሰማይ እንዲደርስ የሚደረገው ለምንድነው? ለምን የግፍ ግፍ ይሠራል? ጥቂቶች እየኖሩ ሚሊዮኖች በቀን አንዴ እንኳ እንዳይመገቡ የሚደረገው ለምንድነው? ዜጎችን አልልም - ዜጋን በዜግነቱ የሚቀበል መንግሥትም ሆነ የመንግሥት አካል ስለሌለ፤ ነገር ግን ሰዎችን በማስራብ የሚገኝ ደስታ ምን ዓይነት ደስታ ይሆን? የዚህ ሁሉ የሕዝብ ሥቃይ የሚያመጣው የዞረ ድምር እንዴት አልታየም? በእውነቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን እየኖረ ነውን? ሆድ ሲጠግብ አንጎል በሞራ የሚሸፈነው ለምን ይሆን? ሥነ ቃላችን እንደሚለው ከተራበ ለጠገበ መታዘኑ ለዚህ ይሆን?

    

ደመወዝና ኑሮ ቻው ቻው ከተባባሉ ቆይተዋል፡፡ በደመወዝ መኖር የሚችል ዓለም አቀፍ ደረጃ የደመወዝ ክፍያን በሚከተሉ ተቋማት አንጂ በሲፒኤ ተብዬው የኢትዮጵያ መንግሥት የደመወዝ እስኬል የሚከፈል ሠራተኛ እስትንፋሱ ተንጠልጥላ የምትገኘው በተራድዖና በልዩ ልዩ ድጎማ ነው፡፡ ልጁን ወደዐረብ ሀገርና ወደሌላው ዓለም የላከ፣ በደህናው ዘመን የሠራትን ጎጆ እየሸጠና እየለወጠ ላለመሞት የሚንደፋደፍ፣ በደጉ ዘመን በሠራት ቤቱ የሚከራይና ለሱቅ የሚሆን ቤት ያለው፣ በትርፍ ሰዓቱ አለባበሱንና ገጽታውን ለዋውጦ በልመና ‹ሙያ› የተሠማራ፣ አሁንም በትርፍ ሰዓቱ ሥርቆትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ‹ሥራዎች› ላይ የተጠመደ… የዛሬ ነፍሱን ለነገ ያደርሳል፡፡ አለበለዚያ እመኑኝ በመንግሥት ደመወዝ እንኳንስ 30 ቀናትን ለመቆየት ይቅርና 3 ቀናትም ይከብዳሉ፡፡ ምን ተበልቶ? በምን ተጉዞ? ምን ተለብሶ? በምን ታክሞ? ለማንኛውም ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ!!

     ሀኪሙ ሌባ፣ ሆስፒታሉ ሁላ ሌባ፣ ዶክተሩ አጭበርባሪ፣ ፖሊሱ ሌባ፣ ዳኛው ሌባ፣ ጠበቃው ሌባ፣ ዐቃቤ ሕጉ ሌባ፣ ወታደሩ ሌባ፣ መንግሥቱ ማፊያ፣ ባለሥልጣኑ ሌባ፣ ነጋዴው ሌባ፣ ሲቪል ሰርቫንቱ እጅ እጅህን የሚያይ ሌባ፣ ቀበሌው ሌባ፣ … ሁሉም ሌባ በሆነባት ሀገር እንዴት መኖር ይቻላል? እንዴ! ለእግርህ ወለምታ ወደ አንድ የግል ሕክምና ተቋም ብትሄድ ካርዱ አምስት መቶ ብር ይሆንና ጭንቅላትህ ራጅ ይነሳ፣ አክታህ ይመርመር፣ እርግዝናህ እግርህን ሊኮደኩደው ስለሚችል ሽንትህ ይመርመር፣ የአንጀትህ መታጠፍ ለእግር ወለምታ መቀስቀስ ሰበብ ሊሆን ስለሚችል በአልትራሳውንድ ውስጠ ዕቃህ ይታይ፣ በሲቲ ስካን ሁለመናህ ይፈተሸ፣ 11 ዓይነት የደም ምርመራ ይደረግልህ … የማትባለው እኮ የለም - ለወለምታ፡፡ ኤቲክስ፣ ሞራል፣ ሃይማኖት፣ ይሉኝታ፣ግዛዕ ምዛ የለም፡፡ ሆድ ነው ንጉሠ ነገሥቱ በሀገራችን፡፡  የግል ሆስፒታል አልጋ ከሼራተንና ሒልተን አልጋ በልጦ ብታገኘው እንዳይደንቅህ - ምክንያቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የምትገኘው፡፡ አብዛኛው ሰው የለየለት ጅብና ዓሣማ ሆኖ ዐረፈው፡፡ ምን ይሆን ግን ወደዚህ የለየለት ሀገራዊ ቀውስ ውስጥ የዘፈቀን? በነገራችን ላይ ከንፍሮ ጥሬ አይታጣምና ምናልባት በዚህ አንቀጽም ሆነ በቀደሙትና በሚለጥቁት አንቀጾች ከምለው ነገር ነጻ ልትሆኑ የምትችሉ ዜጎች ካላችሁ መሬት ላይ ወድቄ ይቅርታችሁን እለምናለሁና ይቅር በሉኝ፡፡ ወድጄን እንዳይመስላችሁ፡፡ ግን ግን አሁንም ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ!!

    

ነጋዴው ጨርቁን ጥሎ አብዷል፡፡ በገንዘብ ፍቅር ናላው ዞሯል፡፡ በገንዘብ ብቻም አይደለም፡፡ በሀገራችን ብዙው ሰው በሥልጣን ፍቅር ቅንጭላቱ ናውዟል(እንዲያ ባይሆን ኖሮ መቶ ታምሳ ፓርቲና የፖለቲካ ድርጅት በውጪም ባገር ውስጥም ይኖር ነበር? - በሬው ሳይገዛ ሌባው በረት ሞላ አሉ! አለመታደል ነው!)፤ ብዙ ሰው በፍቅረ ንዋይ ታውሯል፤ በወሲብ አራራም አቅሉን የሳተው የትዬለሌ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሥሪያውን ያያችሁ እንደሆነ ‹እንዴ፣ ዓለም የምታልፍበት ቀን በቁርጥ ተነገረ እንዴ?› ብላችሁ ልትገረሙ ትችላላችሁ፡፡ የሃይማኖት መላላትና የማኅበረሰብኣዊ ዕሤቶች ደብዛ መጥፋት ምን ዓይነት ሀገራዊ ቀውስና የትውልድ ዝቅጠት ሊያስከትል እንደሚችል እኛን ያየ ታዛቢ በቀላሉ ይረዳል፡፡ በቁማችን መሞታችንን ለመታዘብ አዲስ አበባ መምጣትና በቀንና በሌሊት የሚሠሩ ሰይጣናዊ ድርጊቶችንና በተቃራኒው ደግሞ የአብዛኛውን ሕዝብ የርሀብ ሰቆቃ፣ የዜጎችን የለየለት ዕብደትና ለብቻ እየተናገሩ እንደወፈፌ ሲጓዙ ማየት በቂ ነው - ዛሬ ካበደው ደግሞ ነገ ለማበድ የተዘጋጀው ይበልጣል፡፡ የሶዶምና ገሞራ የዕልቂት ዘመን በጣም ተቃርቧል ብዬ ለማመን የተገደድኩበት ሁኔታ ተፈጥሯል ማለት እችላለሁ - እንደ አካሄድ፡፡ የቀረን የፊሽካው መነፋት ብቻ ይመስለኛል፡፡

    

ነጋዴዎች በኪሎ ይሸቅቡሃል፤ ጥራት የጎደለው ብቻ ሳይሆን ለጤንነት ፀር የሆነ የምግብና ምብግ ነክ ሸቀጦችን ያቀርቡልሃል፤ሱስ እንዲይዝህ በሻይ ቅጠል ሳይቀር ትምባሆ ጨምረው ያሽጉልህና ሲያስፋሽግህ እንዲውል ያደርጉሃል፤ በመጠጦችም ውስጥ ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገሮችን እየጨመሩ መሸተኛ ሆነህ እንድትቀርና በሰበቡም ቤተሰብህን እንድትበትን ያደርጉሃል፤ ሦስት ቀን ለማያገለግሉ የቻይና ትርኪ ምርኪ ሸቀጦች ያጋልጡሃል - ከገንዘብህም ከዕቃውም ላትሆን፤ ሰውነትህን ለሚኮደኩድ የየመን ስምየለሽ የመብል ዘይት ያጋልጡሃል፤ ለሆነ ጉዳይህ አሥር ኪሎ ብለህ የገዛኸው ሥጋ የኪሎ ሚዛኑ ሰባት ሆኖ በዚያም ላይ አጥንትና ልፋጭ አሸክመው ቢልኩህ ብቸኛው ምርጫህ ከሚስትህ ጋር እቤትህ ሀዘን መቀመጥ ነው፡፡ ሸክላና ሴጋቱራ ከመናኛ የበርበሬ ዛላ ጋር ፈጭተው በበርበሬ ስም ቢያበሉህ ለጤንነትህ አንድዬን ብቻ መለመን ነው፡፡ ከሥነ ልቦናህና ከባህልህ ከምግብ ሥርዓትህም ያልተለማመዱ የቤትና የዱር እንስሳትን አርደው ሊመግቡህ ቢችሉ መታገስ ነው፡፡ የበከተ ዶሮና ከብትማ የዘወትር ቀለብህ ነው - ዶሮ ወይ በግ ሳትታረድ ሞተች ብሎ መጣል ታሪክ ሆኗል ልጄ - አከፋፋይና ተቀባይ አላቸው፡፡ ዘይቱ፣ ቅቤው ከምን እንደሚሠራ አታውቅም - ያን እየተመገብክ የቀብርህን ጊዜ ማሣጠር ነው፡፡ ጤፉን ግማሽ በግማሽ ከአሸዋና አፈር ቢቀላቅሉት ነፍተህ መጠቀም እንጂ ቅሬታ ማሰማት በሞኝነት ያስፈርጅሃል፡፡ ብዙ ነገር ከመስመር ወጥቷል፡፡ ነጋዴው የሚታየው ብቸኛ ነገር ገንዘብ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ብዙው ነጋዴ ከሰውነት ተራ ወጥቶ ገንዘብን አምላኪ ሆኗል - ከጣዖትነት በዘለለ ሁኔታ፡፡ በጥቀሉ ያልሆንነው የለም፡፡ ‹ብታምኑም ባታምኑም ወያኔ ቀልዶብናል› ነበር ያለው መንግሥቱ ኃ/ማርያም? የሥራቸውን ይስጣቸው እንጂ ነጋዴዎችና ወያኔዎች ቀልደውብናል፡፡ አንድዬ ዋጋቸውን አይነሳቸው፡፡   

    

የኑሮው ልዩነት አይወራም፡፡ ስንትና ስንት ቤተሰብ የቀድሞ የነተበ ሱፉን ከነክራቫቱ ግጥም አድርጎ ከሆቴሎች የተሰባሰበ - ወጣቶች ቱሩ ይሉታል - ትርፍራፊ በቅናሽ ዋጋ ለመግዛት ከ‹አከፋፋዮች› ደጅ ተሰልፎ ስታዩት ልታለቅሱ ትችላላችሁ፡፡ ትራፊን ለውሻ ማከራየት ዱሮ ቀረ፤ አሁን ‹ዛሬ ከምሞት ነገ ልሙት› ከሚል የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ የተነሣ ያ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ዕድሜ ለወያኔ ክብሩን አዋርዶ ለሆቴል ትራፊ መሰለፍ ከጀመረ ዋል አደር አለ - ይሄው ትራፊ በጉርሻ ደረጃም  ይሸጣል - ያም እየጠፋ ነው፤ ኩራት እራት የሚሆነው የሚንጫጫ ወስፋት ሳይኖር ነው - እዬዬም ሲደላ ነውና፡፡ ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ!!

    

ልመናውና ዘረፋው ቀልጧል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች የቀን ዘረፋም እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ በዘረፋውም የፖሊስ ኃይሉ አባላት እንደሚተባበሩበት እንሰማለን - እነሱስ ማን አላቸው? በሰባት መቶ ብር ደመወዝ እንዴት ይኑሩ? ይሄም ብቻ አይደለም - በ12 ብር ሒሳብ አራት ኪሎ ሙዝ የሚገዛ የጡረታ አበል የሚከፈልባት ደናቁርት የመንግሥት ባለሥልጣናት የሚገኙባት ብቸኛ የዓለም ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ ወፍራም የምትሉት የመንግሥት ደሞዝ በሙስና ወይም በሌላ መንገድ ካልተደጎመ አያኖርም፡፡ … የኔ የወንድማችሁ ደመወዝ - የእህታችሁ ብልም ግዴለኝም - (ውኃን ለመክፈልና ጥቂት ኩታራዎችን ከማፍራት ውጪ ምን ጠቀመኝ? የተጠቀሙበትስ ባሉበት አሉ! መንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት ሕንፃ ላይ ሳይቀር ገትረውት የለም እንዴ! ግን እኮ በዚያ ቦታ ነውር መሆን ነበረበት፤ በክርስቶስ ቦታ የወንድነትን ልክ ማሳያ ጥንታዊ ሀውልት ሳይሆን የላሊበላው የመስቀል ምልክት ቢሆን ይሻል ነበር፤ መሃንዲሱ አክሱማዊ መሆን አለበት! ) - የኔ የ‹ንዑስ ከበርቴ›ው ወርኃዊ የተጣራ ደመወዝ ከባለቤቴ ወይም ከአንድ ጓደኛየ ጋር ኪሎውን በ150 ሒሳብ በወር ሃያ ጊዜ(20ኪ.ግ) ጥብስ ወይም ቁርጥ ከማብላት አያልፍም - ሻይና ማወራረጃ አምቦ ወይ ለስላሳ እንኳን ሳይጨምር፡፡ ሕዝብ በፍትህ ዕጦት ብቻ ሳይሆን በርሀብም እያለቀ ነው፡፡ ወያኔዎችም ግፍን በግፍ ላይ እየቆለሉ የራሳቸውን ጉድጓድ አርቀው እየቆፈሩ ናቸው - ምን ቸገረን - ይቆፍሩ፡፡ እርግማኔን ግን እቀጥላለሁ፤ እናም ልጅ አይውጣላቸው!! እስከዚህ እንዳዋረዱን ሳያስቡት በላ ይላክባቸው!! ዕጣቸው ጥርስ ማፋጨትና በሲዖል የዕቶን እሳት መለብለብ ይሁን፡፡


ኢትዮጵያ ስሟ ያጸይፋል እንዴ?
     ነገርን ቢዘበዝቡት አያልቅም፡፡ ከፍ ሲል በጅምር ወደተዉኳት በመሀል የተሸረጠች ሃሳብ ልግባና ቁጭቴን ልቋጭ፡፡ ሆድ ለባሰው ማጭድህን አውሰው ይባላል- (ሳላውቅ አዟዟርሁት ልበል?)፡፡ አሁንስ ከሆድም አልፎ አንጀትም ብሶኛል፡፡

     ባለቤቴ ‹ደገሙልህ!› አልነበር ያለችኝ? አዎ፣ እንዲያ ነበር ያለችኝ፤ የደገሙት ኢሣቶች ናቸው፤ ዛሬ ጧት ለአራተኛ ጊዜ የደገሙትም(ማለትም ያቀረቡት) ትናንት ለሦስት ጊዜያት ያህል በአንድ ቀን ጀምበር ለአየር ያበቁትን ከአንዱፌ ጅራ(ዳዊት መኮንን) ጋር ያደረጉትን ግሩም ቃለ መጠይቅ ነው፡፡ ‹እንዴት ነው ኖገሩ? ለአንድ ሞቶ ሃምሣ ብር ከፍዬ ከዐረብሣት ወደናይልሣት የጎለበጥኩት ለዚሁ ነው እንዴ?› አይ፣ ግዴላችሁም ይስተካከል፡፡ በፓርትታይም እየተሠራ ከሆነ አስቸጋሪ ነው፡፡ ለውጥ የሕይወት ቅመም ነውና አቀራረቡ ለወጥወጥ ማለት አለበት፡፡ በመሠረቱ ብዙ ነገሮች ጥሩ ናቸው፡፡ ከፍተኛ መሻሻልም እየታዬ ነው፡፡ ግን ግን አሁንም ብዙ ይቀራል፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ዲያስፖራ ቢያንስ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀጥ አድርጎ መያዝ ካቃተው አሳፋሪ ነገር ይመስለኛል - የኛን የብዙኃኑን ያገር ቤት ዜጎች ነገር ተውት፤ ከሞቱትም ካሉትም በታች ሆነናልና የኛ ጉዳይ ተከድኖ ይብሰል፡፡ ብል ለሚበላው ሀብትና የዓለም ንብረት እጅን ማሳጠር ደግ አይደለም፡፡ የኢሣት ሰዎችም ብቻቸውን እንዲፍጨረጨሩ መተው የለባቸውም፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ ለጥቂቶች ብቻ እንደፍጥርጥራቸው ይወጡት ተብሎ የሚተው ነገር አይደለም፡፡ ነገ እንተዛዘባለን፡፡ በእርግጠኝነት ነጻነታችን በባሌም ይሁን በቦሌ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ያኔ ሀገራችን ‹አላውቃችሁም› ብትለን ምን ይውጠናል? የክርስቶስን አስተምህሮ አስታውሱ፡፡ ‹ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማይ አይገባም› ያለው ምንን ሊያስተምር እንደሆነ አንዘንጋ፡፡ እየቻልን ሀገራችንን ከረሳን ነውር ነው፡፡ ሁሉም ከተባበረ ኢሣት የሚወቀስባቸውን ቀዳዳ ጎኖች ለመድፈን አያቅተውም፡፡ አንራቀው - እንቅረበው፡፡ ጦራችን ነው፤ የሕዝብ አለኝታ ነው፡፡ ኢሣት የወቅቱ የጭቁኖች እስትንፋስ ነው፡፡ እርግጥ ነው - በሁለገብ ትግል ካልታገዘ ቲቪም ሆነ ማንኛውም ሚዲያ ብቻውን ነጻነትን ያመጣል ማለትም አይደለም፡፡ ስለዚህ ሀቀኛ ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን ጋብ አድርገው አዲስ ታሪክ መሥራት ይገባቸዋል - በየፈርጁ፡፡ እግዚአብሔር የኛን ጦርነት አይዋጋም - እንዲዋጋልን መጠበቅም የዋህነት ነው፤ ምክንያት ፈጥሮ ግን ሀገርንና ሕዝብን ከጨቋኝ ሥርዓት ሊታደግ እንደሚችል የታወቀ ነው - ዕቅዱን ማፋጠን የሚቻለን ይመስለኛል፤ ‹አንኳኩ ይከፈትላችኋል› አለ እንጂ እደጅ ቆማችሁ አላዝኑ ወይ አንቀላፉ አላለምና እንወቅበት፡፡… በደረቅ አበሳ እርጥብ ይቃጠላል፡፡ ለኃጥኣን የመጣ ለጻድቃን ይተርፋል፤ ለጻድቃን የመጣም ለኃጥኣን ይተርፋል፡፡ የሆኖ ሆኖ ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ!!


ያን ቃለ መጠይቅ በተመለከተ ግን የተሰማኝን ቅሬታ ሳልጠቁም ማለፍ አልወድም፡፡ ይሉኝታ ዱሮ ቀረ ምዕመናን፡፡ ጫካ አይደለሁምና የተሰማኝን እናገራለሁ - የፈለገ ይውሰደው ያልፈለገ ይተወው፤ ገበያና ንግግር የጋራ ነው - የስምምነት ጉዳይ ነው፡፡ እና ዳዊት መኮንን እጅግ የሚመስጥ ቃለ መጠይቅ የማድረጉን ያህል በዚያ ሰፊ ንግግሩ ውስጥ ተስቶት እንኳን አንድም ጊዜ ‹ኢትዮጵያ› የሚል ቃል አለመናገሩን ሳጤን በጣም ከፋኝ - ይህን ጽሑፍ ከጀመርኩ በኋላ አንድ ከጉራጌ ብሔረሰብ የሚወለድ ጓደኛየ ይህን የኔን ትዝብት ራሱ አስታውሶኝ ቅር እንዳለው ሲያጫውተኝ በኢትዮጵያዊነታችን የጸናን ነን የምንል ምዝብር ዜጎች ምን ያህል የአእምሮ መናበብ እንዳለን ተገነዘብኩ - ይቅርታ ሰውን በዘር ቋጠሮ መለያየትና መናገርም አልወድም - በመሠረቱ - ነገር ግን እዚህ ላይ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቴ ነው፡፡ ኢትዮጵያን መጥላት የማንም መብት ነው፡፡ ይሁንና የዚህ አርቲስት ‹ኦሮሚያ› ላይ ማጥበቅና ኢትዮጵያን ገሸሽ ማድረግ በአብሮነታችን ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ሳስበው ልጁ ያልገባው ነገር እንዳለ  ተረዳሁ፡፡ በኋላ የወጣ ቀንድ በፊት የወጣ ጆሮን ጣል ጣል ማድረግ እንደማይኖርበትም ላስታውስ ፈለግሁ፡፡

    
ከ22 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ባንዲራና አንዲት ሉዓላዊት ሀገር ከአንድ ሕዝብና ከአንድ መንግሥት ጋር ነበሩ - ምንም እንኳን መንግሥታቱ ጨቋኝና አምባገነን ቢሆኑም - ስትፈልጉ ዘውድ ናፋቂ ወይም ደርግ ኢሠፓ በሉኝ (ሁለቱንም እንዳልሆንኩ  የማሳወቅ መብቴ ግን ባልተሸራረፈ መልኩ እንደተጠበቀ ነው)፡፡ ወያኔ ለዘዴዋ ስትል ሠላሣ ባንዲራና እውናዊ ኅልውናቸው ከላም አለኝ በሰማይ ያልዘለሉ ሠላሣ ክልላዊ መንግሥታት ፈጠረችና ለየዋሃን አደለች፡፡ የዋሃን ያን የመከፋፈያ ሥልት እንዳለ ተቀብለው ይንከረፈፉ ገቡ፡፡ እሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል እንዲሉ ከደደቢት - ትግራይ ሲገሰግስ የመጣው የመለስ ዜናዊ የጥፋት ሠራዊት ለሕዝብ ያዘነ መስሎ የዐዞ ዕንባ እያነባ ሀገሪቱን በዘርና በቋንቋ ተልትሎ  ራሱ ለጠፈጠፋቸውና ቀድመው ለተፈጠሩ ተቃዋሚዎች የባንዲራ መዓት በማደል በውስጡ እዬሣቀ የልቡን ይሠራ ያዘ - ከእውነት ያታለለ መስሎት(በመንጌ አማርኛ - ብታምኑም ባታምኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኒት ለቅጣት እንደመጣች ጠንቅቆ ያውቃልና ማንንም ሊያታልሉ አይችሉም!)፡፡ ሁለገብ ሟርትና ደንቃራው ይዞለት ዋናው የሠራዊተ አጋንንት መሪ መለስ ዜናዊ በቃህ ተብሎ በአምላከ ኢትዮጵያ እስኪጠራ ድረስ ትርምሱና ዋይታው በርትቶ ቀጠለ - አሁን ድረስ፡፡…

    
ይህ ትውልድ ከሸፍጥና ሸፍጠኞች ካጠመዱለት ቀረቀር በአፋጣኝ ካልወጣ የጉዳቱ ሰለባ ራሱ እንጂ ሌላ ማንም አይሆንም፡፡ አንድን ችግር ለማስወገድ ችግሩ የተፈጠረበትን የአስተሳሰብ ጎዳና መከተል እንደማያዋጣ አልበርት አነስታይን አስቀድሞ ተናግሯል - የክርስቶስ ስብከተ ፍቅር ‹ጠላትህን ውደድ›ም ከዚህ የተለዬ አይደለም፡፡ ችግሩ ከተፈጠረበት አእምሮ የበለጠና የሰላ አእምሮ ባለቤት መሆንን ይጠይቃል - ተፈጠረ የተባለን ችግር በማያዳግም ሁኔታ ለመፍታት፡፡ እናም ወያኔ በተጓዘበት መንገድ ተጉዞ የሕዝብን ነጻነት አመጣለሁ ማለት ዘበት ነው - ወደትፋቱ እንደሚመለስ እሪያ(ዓሣማ) መሆንም ነው፤ አንገት ለምን ተፈጠረ - አዙሮ ለማየት አይደለምን? መቶ ሃምሳው ተቃዋሚ በመቶ ሃምሳ ባንዲራና ሰንደቅ ሥር ተሰልፎ ቢመጣ ቂልነት እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም፡፡ በሌላ በኩልም ዘመደ ብዙ ጠላው ቀጭን እንደሚሆንበት በመረዳት ለማያዋጡ አካሄዶች ከማጎንበስና ጥቁርና ነጭን ተቀላቅለው ላይቀላቀሉ ለማቀላቀል በመሞከር በቡራቡሬ ግንጥል ጌጥም ለመዋብ ከመድከም ይልቅ የሚያዛልቁ አካሄዶች ላይ መላ ትኩረትን ጥሎ ለትዝብት በሚዳርግ ሁኔታ ሳይንጋለሉ አዋጪውን ልጅ ብቻ በመምረጥ ማጥባትን መለማመድ ክፋት ያለው አይመስለኝም - በዚህች ዐረፍተ ነገር ምን ለማለት እንደፈለግሁ ለኔ ለራሴ ላቲን ሆኖብኛልና የገባው ወደፊት ቢያስረዳኝ ደስ ይለኛል - አልሰርዛትም ደግሞ፡፡ … ስለሆነም ወደ እውነቱ መቅረብ ያስፈልጋል፡፡ አዳሜ በየብሔሩና በየጎሣው እየተመሰገ በመጤ ባንዲራና በፍልሱፍ ማንነት ሕዝብን ሊያታልል ቢሞክር ዕድሜው ብዙ አይደለም፤[ ሰውን ግን ምን እየነካው ነው?  ባንዲራን ያህል ትልቅ ነገር በቤተ ሙከራ ፈልስፎ የቡና ቁርስ ይመስል እንዴት ለሕዝብ ያድላል? ወያኔዎች እኔ ለተገኘሁበት የሕዝብ ክፍልም የፈለሰፉት ባንዲራና ብሔራዊ የማንነት መገለጫ አለ አሉኝ - ግን ሁለቱንም አላውቃቸውም፤ ማንነቴ ኢትዮጵያዊነቴ - ባንዲራየም የሰይጣን ዓርማ የሌለበቱ ንጹሑ አረንጓዴ - ቢጫ - ቀይ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊነት የሚያኮራ ማንነት እንጂ የሚያሣፍር አይደለም፡፡ በጊዜ እንመለስ ጎበዝ!]

    
በተረቱ ‹የሞኝ ፍልጥ ካላንድ ቀን አይበልጥ› ይባላልና  አሁን ለጊዜው ሕዝቡ አማራጭ አጥቶ ከላይ የተወረወረው ቁዝምዝም መሬት እስኪያርፍለት ዝም ስላለ ብቻ ለዕልቂትና ውድመት የሚዳርግን  የመሠሪዎች ሸቀጥ የዘር ፖለቲካ ከእንግዲህ ወዲያ ይቀበላል ማለት እንዳልሆነ ሁላችን ልንገነዘብ ይገባል - ቋቅ እስኪለንና እስኪያንገሸግሸን አየነውም አይደል? ማንን ጠቀመ? ማንንስ እንጦርጦስ አወረደ? በመሠረቱ ይህን ወይ ያን መጥላት ይኖራል፡፡ በተቀያየምክ ቁጥር ወይም የጓደኛህ የ‹ዐይን ቀለም› ባስጠላህ ቁጥር ግን  ከሜዳ ተነስተህ በሞቅታም ይሁን በለብታ የጋራ ቤትን ሊያርስ የሚችል የተለዬ ነገር አታደርግም፡፡  ባሏን የጎዳች መስሏት ሰውነቷን በእንጨት እንደቦጫጨረችው ቂላቂል ሴት ለመሆን እስካልተፈለገ ድረስ የበሬ ግምባር በማታህል ሀገር ሰማንያ ባንዲራና ሰማንያ ማንነት ለማቆጥቆጥና ሕዝብን ለማወናበድ መነሳት በተለይ ከአሁን ወዲያ አያዋጣም ብቻ ሳይሆን የለየለት ጅልነት ነው፡፡ ሊሣካ ቢችል ኖሮ እስካሁን ነበር የሚሳካው፡፡ ባጭሩ አይሆንም ነው - የሚወጣና የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ በቅርቡ ሁሉንም ነገር ‹አፖስቶ› ያደርገዋል የሚል ሥጋዊ ግምትና መንፈሳዊ ጠንካራ እምነት አለኝ - ያስተካክለዋል ማለቴ ነው በሶላቶኛ፡፡ አሁን ማን ይሙት በሰው ኃይልና በመንግሥት ጥበቃ የምንኖር ይመስላችኋል? አይደለም! በኪነ ጥበቡ ነው እየኖርን ያለን - መንግሥት ለስሙ - ጠ/ሚንስትር ለስሙ - ፖሊስ ለስሙ - ጤንነት ለስሙ … ሁሉም ለስሙ እንጂ ከእውነት የለንም፡፡ አንዱ ገድሎህ ቢሄድ ዋስትና የለህም፡፡ አውላላ ሜዳ ላይ ያለ እረኛ የተበተነ ከ80 – 90 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ! አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ዓለማቀፋዊ ኹነት! የሚገርም ሕይወት እኮ ነው እየመራን ያለነው በውነቱ!

    
ይህን ጉዳይ ለብቻው ብመለስበት ይሻለኛል፡፡ ለዛሬ ጣፈጠም መረረም እዚህ ላይ ላብቃ፡፡ አጎቴ አባ ዘባሪቆ እንዲህ ይሉ ነበር - እጠቅሳለሁ፡- አንድ ጽሑፍ የምትፈልገውንም የማትፈልገውንም የምታገኝበት ብፌ ማለት ነው፡፡ የማትፈልገው የምትፈልገውን እንዳያጠይምብህ በአስተውሎት አንብብ፡፡ ሁሉን ማስደሰት የሚቻለው አንድም ፍጡር የለም፤ ፍቅር ግን ቻይና ታጋሽ ናት፡፡ ከችኩል ፍርድ ተቆጠብ፡፡ ልዩነትን  ‘enjoy’ ማድረግ ያልለመደ ሰው፣ ሰው ሳይሆን ያረጅና እንደፊጋ በሬ ዙሪያ ገባውን በነገር ቀንዱ እንደደሰቀና ከሁሉም ጋር እንደተጣላ ሰው ሳይሆን ያልፋል፡፡ የጥቅሱ መጨረሻ፡፡ “ይህን ጽሑፍ ያነበበ፣ ያስነበበና ያናበበ የዘላለም ሕይወት አለው፡፡” ብል በ‹plagiarism› እከሰስ ይሆን? ለማንኛውም እርግማኔን ሳልረሳው “ወያኔ ጥቁር ውሻ ይውለድ ልበል”ና ከ‹አየር› ልውጣ፡፡ ቻው!

 

ነገር የሚፈልገኝ ሰው ይኖር ይሆን እንዴ?

Monday, June 17, 2013

የኢትዮጵያዊያን ትግል - ( ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት )

Notice from Ethiopian Semay Editor:-
Stay tune for new commentary that revealed the new secret and tactic of OLF, some Diaspora opposition websites, and individual elements from the opposition who are in the new campaign of blackened our good names in campaigning of labeling bad names (such as naming recognized and hard core patriotic nationalist Ethiopians as "Weyane" and also blackmailing patriotic Ethiopian nationalists names illegally on their webistes in order to kill the spirit of patriotic Ethiopians when fighting TPLF/OLF propaganda. Their names with evidence will be listed on the upcoming commentary for all to see and judge these elements of distortion who these individuals are from the opposition and from the enemy camps as well. As I told you before right after the split of TPLF and Kinijit , our struggle will be overlapped due to the new element from those groups , who now are on the front line of campaign of sabotaging the struggle since then. Their primary goal is to rehabilitate and promote  the agenda of OLF and EPLF with all their crime . Stay tune for the commentary.
Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com



Ethiopians holding on to their flag priding themselves encountering the TPLF's rug thug flag shown below
 
The effect of Italian Mussolini's teaching in Tigray. Tigrayans confronting Ethiopian Flag

Note from the Editor:- Part one and Part two are attached here on this page
 
የኢትዮጵያዊያን ትግል - ( ክፍል ሁለት )

“ለየብቻችን ተማክለን እንጂ በአንድነት ተዋሕደን አንኖርም።” የሚለው ቅኝት፤

ሰኔ ፲፪ ቀን ፳ ፭ ዓመተ ምህረት - June 19, 2013

ከአንዱ ዓለም ተፈራ - የእስከመቼ አዘጋጅ፤ http://nigatu.wordpress.com/

ከሁሉ በፊት ያለው ጥያቄ፤ ኢትዮጵያዊ ነዎት ወይ? ነው። መልስዎ አዎ ከሆነ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲሉ፤ ምን ማለትዎ ነው? ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? እርስዎ ኢትዮጵያዊነትዎን ሲያስቡ፤ ለግል፣ ለራስዎ የሚሰማዎ ምንድን ነው? ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ነው። ለማናችንም ቢሆን መነሻ ወለላችን ይህ ነው። ይኼን ስናጤንና አጢነን ለዚህ የምንሠጠው መልስ፤ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ያለንንና የሚኖረንን ግንኙነት ይወስናል። እናም በአንድነት ለምናደርገው ተግባር፤ ተርጓሚ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ለአንድ ኢትዮጵያዊ፤ ጊዜ የማይቀይረው፣ ሁኔታ የማይለውጠው፣ የግል ጥቅም የማያነቃንቀውና ቦታ የማያርቀው የምንነት አካል ነው። ዜግነቱ ብቻ አይደለም። ከዚያ በላይ ነው። ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል በኢትዮጵያዊነቱ የመኖር መብት አለው። ይኼ ደግሞ ሊተገበር የሚችለው፤ አንድ ግለሰብ፤ በኅብረተሰብ የፖለቲካ ተሳትፎው መመዘኛው ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ሆኖ ሲገኝ ነው። ኢትዮጵያዊ በመሆኑ፤ መብቶቹ ሁሉ ይከበራሉ። አንዱ ኢትዮጵያዊ ከሌላው ኢትዮጵያዊ በማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ብልጫ ወይንም አነስተኛ ድርሻ ሊኖረው አይገባም። የታሪክ አንድነታችን፣ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ያበጀልን ያካባቢ ማነቆ፣ ታሪክን በደንብ መረዳት ግዴታችን መሆኑ፤ ኃላፊነታችን፣ የሌሎች ተመክሮና የዚህ ክፍል ማሳረጊያ እነሆ!

የታሪክ አንድነታችን፤

የእንግሊዝ፣ የጣሊያን፣ የቱርክ፣ የግብፅ፣ የሱዳንና የፈረንሳይ ወራሪዎችን በተለያዩ የታሪካችን ወቅቶች የተጋፈጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ፋሽስት ጣሊያን በኛ ላይ ያደረገውን ተደጋጋሚ ጦርነቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ነበር ገትሮ የተቋቋመው። በነዚህ ውጊያዎች ቆራጥ የሆኑ አያቶቻችን፤ ከዘርዓይ ድረስ እስከ አብቹ፣ ከበላይ ዘለቀ እስከ ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ከአብረሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም እስከ ጣይቱ ብጡል፣ ከታከለ ወልደ ኃዋሪያት እስከ አዳነ አባ ደፋር በአንድነት አኩሪ ተግባር ፈፅመው አልፈዋል። በኤርትራ በኩል፣ በሱማሌ በኩል፣ በሱዳን በኩል ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲመጡብን የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተሠልፏል። ሽብሬ ደሳለኝ ለአማራ ወይንም ለኦሮሞ፣ ለትግሬ ወይንም ለወላይታ፣ ለሲዳማ ወይንም ለአኙዋክ ሳትል፤ ለኛ ለሁላችን ለኢትዮጵያዊያን ነፃነት ሕይወቷን የሰጠች ኢትዮጵያዊት ነበረች። ከየትኛው የኢትዮጵያ ክልል ከሚኖሩ ወገኖች መወለዷን የሚናገር እስካሁን አላገኘሁም፤ አስፈላጊ አይደለምና! የኔሰው ገብሬ የተናገረው፤ በነበረባት ኢትዮጵያ ያለው በደል፤ ለማንም ኢትዮጵያዊ የማይቻል መሆኑን ነበር። በተጨማሪ ረሃብና እርዛት በአንድ ወገን ሲደርስ፤ ወደ ሌላው አካባቢ በመሄድ ተጠግተዋል። ተመሳሳይ የባህልና የኅብረተሰብ ግንኙነቶችን መጥቀስ ይቻላል። እስኪ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የፈጠረልንን ያካባቢ ማነቆ እንመርምር።


የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ያበጀልን ያካባቢ ማነቆ፤

አሁን ችግራችን፤ ሀገሬን ነፃ አወጣለሁ የሚሉ ኢትዮጵያዊያና የኢትዮጵያን ክፍል አንድ ቆርጠው ነፃ አውጣለሁ በሚሉት መካከል ሊኖር የሚችል ግንኙነት ካለ፤ ምንድን ነው? የሚለው ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለትግሬዎች ቆሜያለሁ እያለ ኢትዮጵያን እየገዛ ነው። አንዳንዶች ለትግሬዎች አዳላ እያሉ ማሰረጃቸውን በመደርደር ይናገራሉ። በትግራይ ያሉ ወገኖቻችን ደግሞ፤ የለም የራሳቸውን ቤተሰብና ዘመዶች እንጂ በሙሉ የትግራይን ወገን አልጠቀሙም ይላሉ። ማጣፊያው፤ ለእነዚህ መሪዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ጉዳያቸው እንዳልሆነ ነው። እዚህ ላይ የትግራይ ወገናችን የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል በመሆናቸው የችግሩና የመፍትሔው ክፍል ናቸው። ይህ የሚያሳየን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ለራሱና ለዘመዶቹ ጥቅም፤ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል መነሳቱን ነው። በየክልሉ ያስቀመጧቸው ተቀጥላዎቻቸው የግልና የዘመዶቻቸውን ኪሶች ማሳበጣቸው አብሮ የሚሄድ ነው። በኢትዮጵያዊነታችን የምናምን ደግሞ፤ የምንታገልለትን ማወቅና በግልፅ ማስቀመጥ አለብን። በተጨማሪም ከማን ጋር እንደምንሠለፍ መተለም አለብን። የራሴን ወገኖች ቆርሼ ነፃ ላወጣ ነው የሚል ግንባር፤ ከተቃዋሚ ኢትዮጵያዊያን ይልቅ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ይቀርበዋል። ሲመሽ ከዚህ ቡድን ጋር መቀላቀል ይቀለዋል። ምክንያቱም፤ ሁለቱም ላካባቢያቸው ጉዳይ ቅድሚያ ሠጥተው ነው በኋላ ኢትዮጵያን በያሉበት ተደራጅተው መቀላቀል የሚለው ትርጉም የሚሠጣቸው። ታሪካችን በደንብ መረዳት ከዚህ እንድንጠነቀቅ ይረዳናል።

ታሪክን በደንብ መረዳት ግዴታችን ነው፤

አሁን ባለንበት ዘመን፤ በተለይም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በፈጠረው የክፍፍል ቀመር እኛ ተመርዘን የቀድሞ አባቶቻችንና ነገሥታትን እንደኛ ያሰሉ ነበር የሚለው ጥሬ አስተሳሰብ ግንዛቤያችንን አሸውርሮታል። በቀድሞ መንግሥታት መካከል የነበረው አመዛኝ አመለካከት፤ ጠንካራ የሆነውን ወገን ማቸነፍ፤ ማቸነፍ ካልቻሉ ደግሞ በጋብቻ ማሰርና መዛመድ ነበር። ለዚህ ነው አጋዚ፣ አገው፣ አማራ፣ ትግሬና ኦሮሞ ነገሥታቶች የነበሩት። የዘር ግንዳቸውን በአባታቸው ቆጠሩት በናታቸው፤ ደማቸው የተደበላለቀ ለመሆኑ ማናችንም ልንጠራጠር አይገባም። በታሪክ የተመዘገበውን የነገሥታት የጋብቻ ትስስር ብናጤን፤ መዛመዱ ሀገር አቀፍ ነበር። ወደ ኋላ ራቅ ብሎ ማየት ይቻላል፤ እስኪ በዘመነ መሣፍንት ጊዜ በጎንደር ብንጀምር፤ ራስ አሊ ልጃቸውን ለካሣ ሲድሩ፣ ካሣ አማራ መሆኑን ጥያቄ ውስጥ አላስገቡትም። ጠንካራ ጎበዝ መሆኑንና በጎናቸው ቢያሰልፉት እንደሚጠቅማቸው ተረድተው ነበር። አፄ ዮሐንስ የወሎውን ራስ አሊ ንጉሥ አድርገው በጋብቻ ሲጠምዱ ዘራቸውን አልቆጠሩም። አፄ ሚኒልክም ደግመውታል። አፄ ኃይለሥላሴም እንዲሁ። በትግሬ፣ በኦሮሞና በአማራ ነገሥታት መካከል፤ በግለሰብ ሥልጣናቸውን የሚያጠናክሩበትን መንገድ እንጂ፤ የደም ቁጥር ተሳስበው ያገለሉበት ወቅት ጎልቶ አይታይም። አሁን እኛ በገባንበት ማንቆ እነሱም ይግቡ ብለን የምናደርገው ትንንቅ፤ ብስለት የጎደለው የግንዛቤ ልልነት ነው። የትግራይ፣ የኦሮሞም ሆነ የአማራ ደም አላቸው ብለን ብንፈርጃቸውም፤ ነገሥታቱ ኢትዮጵያዊ ነበሩ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪ የነበሩት፤ “የአክሱም ሐውልት ለወላይታው፤ የጎንደሩ ግንብ ለኦሮሞው ምን ያደርግለታል?” ያሉ ጊዜ፤ የሀገርን ምንነት ግንዛቤያቸውን ተረዳን። ይህ አባባል፤ በዘመነ መሣፍንት ጊዜ እንኳን፤ የራስን ኃይል ለማጠናከርና ወታደር ለመመልመል መሣሪያ ከመሆን አልፎ ትርጉም አልነበረውም። በአሁኑ ዘመን ሲነገር ደግሞ፤ ተናጋሪው ከዘመነ መሣፍንት በፊት መኖርና መሞት የነበረባቸው፤ ጊዜያቸውን አልፈው የተገኙ ተብለው እንዲወሰዱ ያደርጋል። ይኼን የመሰሉ መሪ ምን ዕቅድ እንዳላቸው ግልፅ ነበር። ከክልሉ ውጪ ያለው ማንኛውም ነገር የሱ አይደለም ማለት ነው። የአክሱም ሐውልት የአሁኑ የትግሬ ነዋሪዎች ነው ብሎ ማሰብ ታሪክን አለማወቅ ነው። ያኔ በዚያ ይኖሩ የነበሩት ማን እንደነበሩ ታሪክን ማገላበጥ ይረዳል። ያኔ በአክሱምና በጠቅላላው የሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል፤ ከአማሮችና ከትግሬዎች በፊት አብዛኛው ነዋሪ አገው እንደነበር ማስረጃዎች ብዙ ናቸው። በመካከላቸው በተደረጉት የጋብቻ ግንኙነቶች፤ የአገው ደም የሌለውን ኢትዮጵያዊ በዚህ ክፍል ማግኘት፤ የአማራ ደም የሌለበት ኢትዮጵያዊ ማግኘት፣ የኦሮሞ ዝንቅ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ማግኘት ቀላል አይደለም። የጎንደር ግንብም ሲሠራ ምን ያህል የኦሮሞ ባለሥልጣኖች በወቅቱ በዚያ ከተማ ይኖሩ እንደነበር ማገናዘብ ያስፈልጋል። አማራዎች ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ኦሮሞዎች ከሰሜን እስከ ደቡብ በተለያዩ ወቅቶች ኖረዋልና! ደም መቁጠሩ የት እንደሚያደርሰን በርጋታ እናስብ። የእኛ ኃላፊነት ምንድን ነው? እንመልከት።

ኃላፊነታችን፤

ኃላፊነታችን የነበረውን ታሪካችንን ተቀብለን፤ ከስኬቱ ሆነ ከስህተቱ ትምህርት ወስደን፣ የወደፊቱን ማስተካከል ነው። እኛ ለትናንቱ ሳይሆን ላለንበት ወቅትና ለነገው ሁኔታ ነው ተጠያቂነታችን። ኢትዮጵያዊ ነኝ ስንልና በኢትዮጵያዊነታችን ስንኮራ፤ በታሪካችን ሁሉም ጥሩ ሥራ እንጂ መጥፎ አልነበረም ብለን አይደለም። እኛ ኢትዮጵያዊ ስለሆን ብቻ ነው። መጥፎም ተደረገ ጥሩ፤ ታሪካችን ነው፤ ኢትዮጵያዊያን ነን። መጥፎ ስለተደረገ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም፣ ዴሞክራሲያዊ መብቴ ስላልተከበረ ሀገሬ ለኔ ምን ታደርግልኛለች፣ የነበረው የኔ አይደለምና አዲስ መጀመር እፈልጋለሁ የሚለው ቁንፅልና ያልበሰለ ግንዛቤ ራሳችንን ጎጂ ነው። አንዳንዶች ከነገሥታቱ እየመረጡ አንዱን ኢትዮጵያዊ ሌላውን የአንድ አካባቢ ተጠሪ ያደርጋሉ። ሌሎች ደግሞ አንዱን አረመኔ ጨፍጫፊ ሌላውን መልዓክ የሚያደርጉ አሉ። ኢትዮጵያዊነትን በአንገት ላይ እንደሚንጠለጠል ጌጥ አድርጎ መመልከት ጎጂ ነው። ኢትዮጵያዊነት የምንነት አካል ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አይደለሁም እንጂ፤ ኢትዮጵያዊነትን በኪሴ ያያዝኩት ንብረት ነው፤ ስፈልግ ባንገቴ አንጠለጥለዋለሁ አለያም ደብቄ በኪሴ እይዘዋለሁ የምንለው ጉዳይ አይደለም። በመሆንና ባለመሆን መካከል መቆሚያ አጥር የለም። ነህ ወይንም አይደለህም ብቻ ነው። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ታሪካችን በብዙ ቢሆን ኖሮዎች የተሞላ ነው። አፄ ቴዎድሮስ እንዲህ ቢያደርጉ ኖሮ፣ በዚያ ቦታ እንዲህ ቢወስኑ ኖሮ፣ በዚያ ጊዜ ይኼን ባያደርጉ ኖሮ፣ . . . የምንላቸው ተትረፍርፈዋል። በአፄ ዮሐንስም ዘመን፣ በአፄ ሚኒሊክም ዘመን፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴም ዘመን። የሀገራችንን ታሪክ አጥፊዎቹ ሌሎች ናቸው እኛ አይደለንም ለማለት፤ እነሱ ይኼንን ባለማደረጋቸው ነው ወይንም ያንን በመድረጋቸው ነው እያልን፤ ሀገራችን ላለችበት ሁኔታ ወቃሾች ብዙዎቻችን ነን። እስኪ ከ፲ ፮ ዓመተ ምህረት ጀምሮ፤ ስንት አጎምዢ አጋጣሚዎች በዓይኖቻችን ሥር አልፈዋል? ይኼ ቢሆን ኖሮ፣ ያ ቢደረግ ኖሮ፣ . . . የምንላቸው ብዙ ናቸው። አሁንም ከመቼውም የበለጠ አጋጣሚ ከፊታችን ተዘርግቷል። ይኼን አጋጣሚ እንደሌሎቹ ሁሉ አሳልፈን፤ ለነገአዎቹ ቢሆን ኖሮ ካሳለፍንላቸው፤ በታሪክና በነገ ከተወቃሽነት አንወጣም። በሥልጣን ላይ ያለው ቡድን በውስጡ በጣም የተወጠረበት ሰዓት ነው። አንዱ ሌሎቹን ገድሎ ብቻዉን በአቸናፊነት እንስኪወጣ ድረስ፤ በመካከላቸው ትርምስ አለ። ተቀምጠን እነሱ ተባልተው እንስጨርሱ ስንጠብቅ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ እጅ ሊገባ የሚችለውን ድል አስልፈን እንሠታለን። ተቃዋሚ ክፍሉ በአንድነት፤ የውስጥ መበላላቱን ትቶ፣ በአንድ አጀንዳ፣ በአንድ ድርጅት፣ በአንድ ራዕይ፤ ሥልጣኑንና ምርጫውን ለጠቅላላው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትቶ፤ ከሕዝቡ ጎን ቢሠለፍ፤ የታሪክ፤ የትውልድና የሀገር ኃላፊነቱን ከመወጣት ሌላ፤ እያንዳንዳችን ልባችን ሞልቶ በፈገግታ ቀሪውን የሕይወታችን ጊዜ ማሳለፍ እንችላለን። የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደእስካሁኑ ሁሉ ድርጅቶችን ቀድሞ ከፊት ቆሟል። እሁድ ግንቦት ፳ ፭ ቀን ፳ ፭ ዓመተ ምህረት የተደረገው ሰልፍ ትልቁ ምስከር ነው። የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ቢሆንም፤ ጠቅላላ ሕዝቡ የመራውና የሕዝቡ ለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ያን ያህል እንዳልነበሩ ዕውቅ ነውና! ስለዚህ ተጀምሯል። እኛ ተባበርንም አልተባበርንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ደወሉን አስምቷል። ይልቁንስ በትልቁ የሀገራችን ጉዳይ እናተኩር። ኢትዮጵያዊ ሆነን እንቆጠር። እስኪ ሌሎች የራሳቸውን ታሪክ በተመለከተ ተመክሯቸውን እንመልከት።

የሌሎች ተመክሮ፤

በአሜሪካ መሥራች አባቶች በመባል የሚታወቁትን መሪዎቻቸው ብናጤን፤ በባርያ ፈንጋይነታቸውና ሠራተኛን በመበዝበዝ የሚታወቁት ባለፀጎች ነበሩ። ዛሬ እኒህ መሥራቾች በነጮችና በአፍሪካዊያን አሜሪካዊያን ዘንድ የማይነኩ ጣዖት ሆነዋል። እኛ የቀድሞ ነገሥታትን እንዴት ነው የምንመለከታቸው? ሪቻርድ ኒክሰን በአሜሪካ የስነ-አስተዳደር ቅጥፈት ተገኝቶባቸው፤ ከፕሬዘዳንትነት ተዋርደው የወረዱ መሪ ነበሩ። የሪቻርድ ኒክሰን የቀብር ስነ ሥርዓት ሲፈፀም፤ የነበረው ድምቀትና አዘኔታ፤ ልክ እንደ አንድ ታላቅ መሪ ነበር። መጥፎ ተግባራቸው የመሪነት የቀብር ስነ ሥርዓቱን አላጓደለባቸውም። ምን ጊዜም የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ነበሩ መባልን አያስቀረውም። ጆርጅ ቡሽ ለብዙ ሺህ አሜሪካዊ ወታደሮችና በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የኢራቅ ተወላጆች እልቀት ምክንያት የሆነውን የኢራቅ ወረራ በውሽት መረጃ አመካኝተው እዝ አስተላልፈዋል። አሜሪካ ከፍተኛ ወጪ በማድረግ ያካሄደችው ይህ ወረራ፤ ምንአልባት ቀጥሎ ለመጣው የምጣኔ ሀብቷ ቀውስ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ሳያደርግ አልቀረም። በዚህ ወረራ ከጠፋው ሕይወት ሌላ፤ የጠፋው ንብረት ቀላል አልነበረም። በተጨማሪም የሕዝቡን መብት በመጋፋት፤ ሕጋዊ ያልሆኑ ፍተሻዎችን፣ እስር ቤቶችን ማቋቋምና ግለሰቦችን ማሰር አከናውነዋል። ይኼን ሁሉ በአሜሪካን በዓለም ዙሪያ ለፈፀሙ መሪ፤ በአሜሪካ ውስጥ፤ ዳላስ ከተማ ከፈተኛ የሆነውን የቡሽ ቤተ መጽሐፍት ወዳጆቻቸው አቋቁመዉላቸዋል። እኛ የራሳችንን እንዴት እያየን ነው?

የዚህ ክፍል ማሳረጊያ፤

“ለየብቻችን ተማክለን እንጂ በአንድነት ተዋሕደን አንኖርም” የሚለውን ቅኝት ዘማሪዎች ከሁለት ወንዝ ይቀዳሉ። የመጀመሪያዎቹ በክፍፍሉ የራሳቸው ሥልጣን ስለታያቸው፤ ከግል የጥቅም ጉጉት አንፃር የሚያከሩ ናቸው። ሁለተኛዎቹ ደግሞ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ ካለመፈለግም ሆነ ዕድሉን ስላላገኙ የማያውቁ ናቸው። በማንኛውም መንገድ ቢሆን ራሳቸውን ያላወቁ ናቸው ማለት ይቻላል። አንዳንድ ታሪክ ጸሐፊዎችና ጸሓፊዎችን የሚያዙ ባለጉልበቶች ታሪካቸው እንደፍላጎታቸው እንዲተረክላቸው መጣራቸው አዲስ አይደለም። እኒህ ወገኖች ግን ሁሉን በቁጥጥራቸው ሥር ማድረግ ባለመቻላቸው፤ ታሪክ ከየቦታው እየሠረፀ በመውጣቱ፤ ተመራማሪዎች እያጠናቀሩ አቅርበውልናል። እናም በብዙ ድካም ከተለቃቀሙት ክፍሎች ታሪኩን መረዳት ችለናል። አሁን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የበላይ በሆነበት ወቅት፤ ይህ ቡድን የነበረውን ሆነ አሁን ያለውን በፈለገው እንዲቀረፅለት እየሞከረ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። በሂደቱም ደግሞ የነበረውን ታሪክ መለወጥ የፈለገበት ምክንያት፤ አንድም የራሱን ሕልውና ሕጋዊና ዘለዓለማዊ ለማድረግ፤ ሁለትም የስነ ልቡና ለውጥ ለማምጣት ያለው ጥረት ነው። ስለተጻፈ ግን እውነት አይሆንም። የነበረው ነበር። አሁን ያለንበትን እንጂ የትናንቱን ሀቅ መለወጥ አንችልም። የትናንቱ ሀቅ ደግሞ፤ ትምህርት እንድናገኝበት ከተለያዩ ማዕዘናት መመርመርና መጠናት አለበት እንጂ፤ እንለውጠው ብሎ መነሳት፤ የአምባገነኖች ዓይነተኛ ባህርይ ነው። እኛ የምንታገለው በሀገራችን አሁን ያለው የአስተዳደር ጉድለት፤ ከዕርማት በላይ ስለሆነ መለወጥ አለበት ብለን ነው። ስለታሪካችን የታሪክ ተመራማሪዎች በመስካቸው እንዲከራከሩበት ነፃነቱ እንዲሠጣቸው እንታገልላቸው። ስላሁን ነፃነታችን አሁን እንታገላለን።

 (ክፍል ሶስት የቀጥላል)

የኢትዮጵያዊያን ትግል - ( ክፍል አንድ )


የመድረክ የአደባባይ ውይይትን በመንተራስ

ሰኔ ፯ ቀን ፳፻፭ ዓመተ ምህረት

ከአንዱ ዓለም ተፈራ - የእስከመቼ አዘጋጅ

http://nigatu.wordpress.com/

የአንድነት ፓርቲ ግምገማዉንና የመድረክ አመራር መልሱን በአደባባይ ማቅረባቸው ታላቅ በር ከፋች ጥረት ነው። አንድነት መድረክን ብቻ ሳይሆን፤ የራሱን አመራር አካላትም ገምግሞ ለኢትዮጵያዊያን ማሳየቱ፤ ብስለቱንና ጥንካሬውን አመልካች ነው። ከመድረክ በኩል የተሠጠውም መልስ፤ በድብቅ ሳይሆን በአደባባይ መውጣቱ የሚያኮራ ነው። እዚህ ላይ አንዱም ሆነ ሁለቱ ትክክል ናቸው ወይንም ስህተተኞች ናቸው ማለቴ አይደለም። ጥረታቸው የሚያኮራ መሆኑን ለመጠቆም ነው። በዴሞክራሲያዊ ማዕከልነት ስምና በፓርቲ አባልነት ግዴታ ማነቆ ልሳናቸው ሳይዘጋ የተጻጻፉበት ምልልስ፤ ትልቅ ትምህርት ለሁላችን ሠጥቷል። እስከዛሬ ያልተለመደው ግልፅነት በሩ ተከፈተለት። ራሳችንን መገምገም ራሳችንን ዝቅ እንደማድረግ ስለሚወሰድና ይኼን ማድረግ እንደተቸናፊነት ስለሚወሰድ፤ ከትናንት ትምህርት የመውሰዱ ሂደት በሩ ዝግ ነበር። አሁን በሩ ተከፈተ። ሀቅ ይረዳል እንጂ ማንንም አይጎዳም። ይኼ ግን ባህላችን አልነበረም። ጥሩ ነገር ስናይ ደግሞ፤ ማንም ይሥራው ማንም ይበል ማለት ተገቢ ነው።

ጉዳዩ የሁላችን ነው

የተወያዩባቸው ጉዳዮች የግላቸው ሳይሆኑ፤ ሁላችን ኢትዮጵያዊያንን የሚነኩና እኩል እንደነሱ ልንወያይባቸው የሚገባ ነው። ትኩረቱ እከሌ እንዲህ አለ፤ ሌላው ደግሞ ይኼን መለሰለት ለማለት ሳይሆን፤ ባደረጉት ምልልስ የተነሱት ነጥቦች በሁላችንም ዘንድ መልስ ፈላጊ በመሆናቸው፤ በየበኩላችን እንድንወያይበት ይገፋናልና የበኩሌን ለመለገስ ነው። አሁንም እንደገና፤ ግልፅ ውይይት ማድረግ በማንኛውም ወቅት የጥንካሬ፣ በተጨማሪም ራስን ደግሞ ደጋግሞ በየደረሱበት ደረጃ መመርመር፤ ለትግሉ ውጤት ያለንን ቁርጠኝነት መለኪያ መሣሪያዎች ናቸው።

ጉዳዩ እንዲህ ነው። መድረክ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዋቀረ የፖለቲካ ድርጅት ነው። የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ተንትነው አንድ መፍትሔ በማቅረብ፤ የርዕዩተ ዓለም አመለካከታቸው አንድ የሆነ አባላት ያሉበት ድርጅት ነው። በሌላው በኩል በአካባቢ ወገኖቻቸውን በማሰባሰብ የተዋቀሩ ድርጅቶች አሉ። እኒህ ድርጅቶች የአካባቢያቸው ተቆርቋሪ በመሆን አጀንዳቸውን ያማከሉ ድርጅቶች ናቸው። መድረክን ለመፍጠር በሁለቱ ወገን ያሉ ክፍሎች ወይይት አድርገው፤ በኢትዮጵያ በነበረው ሀቅ ተገደው፤ የተወሰነ ስምምነት ላይ ደረሱ። ይህ መድረክ ወደፊት ምን ሊሆን እንደሚችል ያኔ በደንብ ያጤኑት ላለመሆኑ፤ የአንድነት ፓርቲ ግምገማ ግልፅ አድርጎልናል። አሁን ዕድገታቸውን አስመልክቶ ወደፊት ሲሉ፤ በወቅቱ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አስረው ያዟቸውና፤ ከፊታችን ለተደቀነው ውይይት በቁ። ታዲያ ከዚህ ምን እንማራለን?

እውነት ስትፈተን

እያንዳንዳችን መብትና ግዴታችን የሚመነጨው ከኢትዮጵያዊነታችን ነው። መብታችን ሊከበር፣ ኃላፊነታችን ሊጠየቅ የሚገባው፤ በኢትዮጵያዊነታችን ነው። ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በምንኖርባት ኢትዮጵያ፤ ከኢትዮጵያዊነት የተለዬ መብትና ግዴታ የለንም። አማራ ሆኜ በአማራነቴ መብቴና ግዴታዬ፤ በኢትዮጵያ፤ እንደ ትግሬ ወይንም እንደ ኦሮሞ ወይንም እንደ ሶማሌ ሳይሆን እንደ አማራ ይከበርልኝ ብል፤ የምናገረውን የማላውቅ መብት ፈላጊ እሆናለሁ። አማራ መሆኔ የኔ ጉዳይ ነው። ከአማራና ከኦሮሞ መወለዴ የራሴ ቤተሰብ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ ስኖር፤ አማራ ወይንም ኦሮሞ፣ ሶማሌ ወይንም አፋር፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ መሆን የለብኝም። ኢትዮጵያዊ ብቻ መሆኔ ነው መለኪያው። ከአንዱ ወይንም ከአንዱ በላይ ከሆኑ ቤተሰብ መወለዱ፤ የግለሰቡ የቤተሰብ ትስስር ጉዳይ ነው። ይህ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብቱ ሊጨምርለት ወይንም ሊያስቀርበት አይችልም። ታዲያ ምኑ ላይ ነው ችግሩ? ችግሩ የተከሰተው፤ ከዚህ ወይንም ከዚያ በመወለዴ የቀረብኝ ወይንም የደረሰብኝ ወይንም የሚቀርብኝ ወይንም የሚደርስብኝ ጥቅም ወይንም በደል ነው። ይህ ያለአንዳች ጥያቄ በሀገራችን የተከሰተ ችግር ነው። መለያየት የሚመጣው መፍትሔ ሲታሰብ ነው። መፍትሔው ደግሞ፤ ላንድ ወቅት ወይንም ላንድ ክፍል የሚሰራ ሳይሆን፤ ሁሌም ለሁሉም የሚሠራ መሆን አለበት። ይህ ደግሞ፤ በሕገ-መንግሥቱ፣ በመንግሥቱና በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊከበርና ሊጠበቅ የሚገባው መሆኑ ነው። በዚህ ላይ በአንድነት መነሳት አለብን። በውጭ ሀገር በየተሰደድንበት ቦታ፤ መብታችን በሀገሩ ካሉ ነዋሪዎች በአንዲት ጠብታ ሳታንስ እንዲከበርልን ሽንጣችንን ገትረን እንቆማለን። የሀገሩን ዜግነት ተቀበልንም አልተቀበልንም ልዩነት አናይበትም። ታዲያ ኢትዮጵያ ላይ ምን ልዩነት ተፈጠረ? የሀገሩ ዜጋ በሙሉ እኩልነታቸው የሚመዘገበው፤ የሀገሩ ዜጎች በመሆናቸው ብቻ ነው።

የትግላችን ግብ

ኢትዮጵያዊያን ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር የምናደርገው ትግል፤ ይኼን በጉልበቱ በሥልጣን ላይ ያለን ቡድን ስሙን ስለጠላን ለማስወገድና ሌላ ስም ያለው በቦታው ለመተካት አይደለም። መሠረታዊ የትግሉ መነሻው የዚህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የፖለቲካ ፍልስፍናውና የአስተዳደር መመሪያው ናቸው። እኒህ የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያዎቹ በሀገራችን ተዘርፍጠው መቀመጥ ቀርቶ ባንዣበቡበት ሁኔታ፤ ወደፊት መሄድ የሚባል ጉዳይ የለም። የትግል እሽክርክሪቱ ተወግዶ ወደፊት እንድንሄድ ከተፈለገ፤ ግልፅ የሆነ ውይይት ማድረግ አለብን። በአሥራ ዘጠኝ መቶ ስድሳዎቹ የነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ዋናው የትግል መስመሩ፤ በገዢዎችና በተገዢዎች መካከል የነበረው ቅራኔ ነበር። በዚህ የተጠቃለሉት የዴሞክራሲያ ጥያቄዎች፤ መሬት ላራሹ፣ የትምህርት ዕድል ለብዙኀኑ፤ ሕክምና ለገጠሬው፣ ኃላፊነት ለፓርላማው፣ የሴቶች እኩልነት፣ በወቅቱ ትክክለኛ ትኩረት ያልተደረገበትና የዘመኑ የሶቪየት ኅብረት ሶሺያሊዝምን መስመር ያንፀባረቀው የብሔሮች እኩልነት ነበሩ ከሞላ ጎደል ሰንደቆቻቸው። በመደብ ትግሉ ጠንካራ አቋም ከነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተገንጥለው፤ “በኢትዮጵያ የብሔሮች ነፃ መውጣት ነው ቅድሚያ ያለው” ብለው የተነሱ ጥቂት ቡድኖች ነበሩ። በዚህ የተመሩ የብሔር ነፃ አውጪ ቡድኖች በሀገራችን ግራ ቀኙን ተሯሯጡበት። ተጨባጭ የነበረው የአድልዖና የጭቆና ክስተት፤ ለትንንሽ መንግሥታት መፍጠሪያ መንገዱን ከፈተ። ለነበረው ሀቅ አንድ ብቻ መፍትሔ ሳይሆን ብዙ መንገዶች ቀረቡ። አንድ ሀገር የሚለው ጉዳይ በአንዳንዶች ዘንድ ተቀባይነት አጣ። በዕርግጥ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ መፍትሔ የፈለገው በሀገራችን ውስጥ የነበረውን የገዢዎችና የተገዢዎች ቅራኔ መፍታት ሲሆን፤ ጥቂቶች ደግሞ የተለዬ መፍትሔ ብለው የያዙት የራሳቸውን ሀገር የመመሥረት አጀንዳ ነበር።

አጀንዳ ያልለወጠ ነፃ አውጪ

ይኼን የመጨረሻውን መንገድ የመረጡት የነፃ አውጪ ግንባሮችን በመመሥረት ጠመጃቸውን አነሱ። በባንዳነት ጣሊያንን በማገልገል የታወቁ የትግራይና የኤርትራ ተወላጆች ልጆች፤ ጠንካራ የሆነ ፀረ-ኢትዮጵያ መርኀ-ግብር ይዘው፤ ኢትዮጵያን የማፈራረስ አጀንዳቸውን በራሳቸውና በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች መመሪያቸው አደረጉ። በከፍተኛ ደረጃ ለዚህ የረዳው ደግሞ፤ የደርግ ደርጋማ ማንነትና የተከተለው መመሪያ ነበር። ሥልጣን ለብቻው መያዝ ዋናው ዓላማው ያደረገው የመንግሥቱ ኃይለማርያም አረመኔ ደርግ፤ ወጣቶችን በመጨፍጨፍ፤ በእውነትና በሕልሙ ጠላቶቼ ናቸው ብሎ የፈረጃቸውን በማሳደድና የራሱ ሰው በላ ቡችሎችን በከፍተኛ ቦታ በማስቀመጥ፤ ሀገራችንን ወደ አዘቅት ከተታት። የዚህ ውጤቱ ለትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሀገሪቱን ወለል አድርጎ ከፍቶ ሀገር ለቆ መሽምጠጥ ሆኗል። ታዲያ የብሔሮች ነፃ መውጣትን ያነገበው ይኼ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ትግራይን ነፃ ከማውጣት ይልቅ፤ በተፈጠረለት ቀዳዳ ገብቶ ሀገሪቱን ተቆጣጠረ። አጀንዳውን ሳይለውጥ፤ አሁንም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ሆኖ አዲስ አበባ ተዘርፍጧል። ባለበት ቦታ ደግሞ የሚሠራው ሀገራችንን መበጣጠስ ነው። ሀገራችንን ሀገር የሚባል ነገር ጠፍቶ፤ የየራሳቸው ብሔር የሚኖራቸው ሕዝቦች ያሉበት ቦታ አድርጓታል። ይህ ነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ አጀንዳ። ይኼን ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚታገለው። ታዲያ በየአካባቢያቸው የተዳራጁት የፖለቲካ ድርጅቶች ዓላማቸው ምንድን ነው? የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚከተለውን ዓላማ ማራመድ ነው ወይንስ መለወጥ? ሀገራችንን በጋራ ነፃ አውጥተን ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እኩል የምትሆን ሀገር ማድረግ ነው? ይህ ነው መሠረታዊው የመድረክ ምስቅልቅል።

“አትከፋፍሉን። አንድ ነን።”

አንድነት የፖለቲካ ግኘታ ቋምጦ ነበር ከአካባቢ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የተቧደነው። አሁን ጠዘጠዘው። የግድ ከዚህ መላቀቅ አለበት። በአዲስ አበባ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ፤ “አትከፋፍሉን። አንድ ነን።” ነበር ያለው። የኢትዮጵያ የወደፊት ዕድል በሰማያዊ ፓርቲና በመሰሎቹ ወደፊት መጪ ፓርቲዎች እንጂ፤ በነበሩት የነፃ አውጪና የማያፈሩ የቆዩ ፓርቲዎች እጅ አይደለም። የአካባቢ የፖለቲካ ድርጅቶችን ከሀገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች በዋናነት የሚለያቸው፤ የአካባቢ የፖለቲካ ድርጅቶች ሌሎችን አግላይ መሆናቸው ነው። በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ፤ በሌሎች አካባቢ የሚኖሩ የሀገሪቱ ዜጎች፤ አባል ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ ዴሞክራሲያዊም ሆነ ኢትዮጵያዊ አይደሉም ማለት ነው። ከዚህ ተነስተውም፤ እንንቀሳቀስበታለን በሚሉት የራሳቸው ክልል፤ የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶችን መንቀሳቀስ በድፍኑ ይቃወማሉ። የርዕዩተ ዓለም ልዩነት ሳይሆን፤ የዚህ አካባቢ ሕጋዊ ተወካዮች እኛ ብቻ ነን ስለሚሉ፤ ከነዚህ ድርጅቶች ጋር ማንኛውንም ዓይነት ስምምነት ለመድረስ፤ በነሱ አካባቢ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያለማድረግ ቅድመ-ግዴታ ይሆናል። ይኼን የተቀበለ ሀገር አቀፍ ድርጅት፤ አንድም በነዚህ አካባቢ ያሉትን ደጋፊዎቹ የሀገሪቱ ነዋሪዎች ሸጧል ማለት ነው፤ አለያም የሚያደርገውን የማያውቅ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ማኅደር፤ በአካባቢ በተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶችና በሀገር አቀፍ በተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ቅንጣት ታክል ፍቅር የለም። ግንባርማ ቅዠት ነው። ኢሕአዴግም ውሎ አድሮ ሲበጣጠስ፤ ይኼኑ ያሳየናል።

ውሃ ቢያጥቡት

ሥር የሰደደ ቂም ካለው የትግራይ ታሪክ የተያያዘ መነሻ ያለው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ድርጅት፤*1 ኢትዮጵያን ማፈራረስ ዋና ዓላማው ነው። እንደ ኢትዮጵያዊያ ሳይሆን፤ የተገነጣጠልን ሆነን ራሳችንን እንድንመለከት ነው መርሁ። አንዳንድ የአካባቢ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ለምን ሀገር አቀፍ የሆነ ድርጅት እንዳልመሠረቱ ወይንም ሀገር አቀፍ ከሆኑ ድርጅቶች እንዳልተቀላቀሉ ሲጠየቁ፤ የሠጡት መልስ ወንዝ አያሻግርም። ዶክተር መራራ መልሳቸው፤ “እኛ ለኦሮሞ ሕዝብ የቆመ ድርጅት ይዘን ካልተገኘን፤ ሕዝቡ ወደ ኦነግ (የኦሮሞ ነፃነት ግንባር) ይነጉዳል።” ነበር። እንግዲህ የዶክተር መራራ ድርጅት የሚፎካከረው ኦሮሞዎችን ከኦነግ ጋር እንዳይሠለፉ ገንጥሎ፤ በሥሩ ለማድረግ ብቻ ነው። አቶ ገብሩ አሥራትም በበኩላቸው፤ “የትግራይ ሕዝብ የራሱ የሆነ ድርጅት ካላቀረብንለት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብቸኛ ወኪላቸው በመሆን ያጠቃልላቸዋል።” ይላሉ። በዕርግጥ ቃል በቃል አልተጠቀሱም። መልሳቸው ግን ማንነታቸውን በግልፅ ያሳያል። የአቶ ገብሩ አሥራት አረና የሚፎካከረው ትግሬዎችን በሥሩ ለማድረግ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር ነው። የዶክተር አረጋዊ በርሄና የአቶ ግደይ ዘርዓፂዮን ታንድም እንዲሁ።

የግለሰብ መብትና የቡድን መብት - በግልፅ ከተነጋገርን

በግለሰብና በቡድን መብቶች ዙሪያ ብዙ ስለተጻፈ እዚህ ላይ መተንተኑ አስፈላጊ አይደለም። እግረ መንገዴን ግን የቡድን የምንለው መብት በግለሰብ መብት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተጠቃለለና በትክክለኛ የዴሞክራሲያዊ ሂደት ብቻውን መቆም የማይችል መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ። አቶ ገብሩ አሥራት፣ ዶክተር አረጋዊ በርሄና አቶ ግደይ ዘርዓፂዮን ትግሬዎችን ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለመውሰድ ከሆነ የሚታገሉት ለምን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በከለለው በትግራይ ምድር ብቻ ተመዝግበው አይታገሉም? በእውነት ለመናገር፤ ለትግሬዎች ከሀገር አቀፍ በርዕዩተ ዓለም የተመሠረተ የፖለቲካ ድርጅት ሌላ፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የበለጠ አረናና ታንድ ይጠቅማሉ? ይኼ ያጠራጥራል። ይልቁንም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሲወድቅ፤ ትግሬዎች በደል እንዳይደርስባቸው ቦታ መያዣ የተቋቋሙ ድርጅቶች ናቸው። ዶክተር መራራም ሀገራዊ ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን፤ ለሥልጣን ሊያቀርባቸው የሚችለው፤ የአካባቢ የፖለቲካ ድርጅት በመመሥረት ስለሆነ ነው። በተመሳሳይ መልኩ ዶክተር በየነ ጴጥሮስም የዚሁ አባዜ ተጠቂ ናቸው። ታዲያ ዶክተር መራራም ሆኑ ዶክተር በየነ ለምን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በከለለው የኦሮሚያና የደቡብ ክፍል ተመዝግበው አይታገሉም? ይህ እንግዲህ በግልፅ እንነጋገር ከተባለ ነው። ታዲያ ለኔ፤ በመድረክ ውስጥ የታዬው ድራማ ከዚህ በላይ የተገለፀው ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ማኅደር የሚሳተፍና በሕዝቡ ላይ እምነት ያለው ግለሰብም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ቀርቦ ሃሳቡን መግለፅና አሳምኖ ተከታዮችን ማግኘት እንጂ፤ በአንድ የተለዬ አካባቢ ቀርቦ፤ ለዚያ አካባቢ ተከላካይና የዚያ አካባቢ ጠባቂ ለመሆን አያስብም።

የመገንጠል ግብ

መገንዘብ ያለብን፤ በሥልጣን ላይ ያለውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መጣል ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን ለመገነጣጠል ዓላማቸው አድርገው የሚታገሉ የአካባቢ ድርጅቶች እንዳሉ ነው። እነኚህን ለይቶ ማስቀመጥና ከነዚህ ጋር ሊኖር የሚችለውን ግንኙነት ማጥናት ግዴታ ነው። በዕውነት ግን ከነዚህ ጋር ምን ዓይነት ቅርርብ ሊደረግ ይቻላል? ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተነሱ ድርጅቶች ጋር የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ለማስወገድ መሠለፍ፤ የራስን አንገት ለማስቆረጥ፤ ከጎራዴ መዛዡ ጋር መስማማት ነው።

(ክፍል ሁለት ይቀጥላል)
 * የዶክተር አረጋዊ በርሄን የማስተርስና የዶርትሬት ጽሑፍና መጽሐፋቸውን ይመልከቱ። በአፄ ሚኒሊክ ላይ ያስቀመጡት ውንጀላ በግልፅ ተቀምጧል።
(Ethiopian Semay)

Monday, June 10, 2013

The OLF letter to UN - translated by Yinegal belachew





The OLF letter  to UN - (translated by Yinegal belachew)

Note from the editor;_ (Ethiopian Semay)

First thank you for our dearest brother “Yinegal Belachew” for translating the OLF English letter written to the UN by OLF to cheat the world as its master EPLF leader Isyas always deny anything including no prisoners in Eritrea, including denying that there are no Eritrean refugees in any world…… always lie. OLF and EPLF are the most liars ever heard or seen in the recent history.

The OLF denied participated in any bombing. The pathetic US embassy can also misinform any country as it has special mission to misinform Africans in many instances at times sending intentional wrong reports. The fact is of the Evidence OLF participated in planting explosions in Addis Aababa during the African Union gatherings is true.

My evidence is not based on TPLF video document- my evidence is direct information obtained from an Eritrean secret service who later expose the joint work of EPLF/PFDJ (Eritrean Government) and “OLF” (which is an Ethiopian Oromo ethnic; a secessionist  and dangerous terrorist organization responsible for Amhara ethnic cleansing). The Eritrean secret service agent photo above shown has witnessed from the preparation stage all the way up to when the OLF fighters were lead by Eritrean special troops to cross the Eritrean border to snick to Ethiopian border for their terrorism mission. Those of you who can listen Tigringa- here is the audio source from an Eritrean opposition radio called “Radio Wegahta” just write the address on Google or You tube; or click it here

          Former Eritrean Secret Service Exposes PFDJ (P-1)


Ali Abdou the Eritrean x spokes person is aso in the Diaspora after leaving EPLF government/Eritrea. He will expose some sensitive secrets he new about it , hope fully one day after settled down. No secret remain hidden for ever, it is all a mater of time. here is the translation.

            

አዳ ቢሉስማ ኦሮሞ (ኦነግ)

ይነጋል በላቸው

 

ሰሞኑን ለድረገፆች የላክኋትን አንዲት ትርጉም ቢጤ ተመርኩዘው ብዙዎች ሲቆራቆሱባት ታዘብኩ፡፡ የኢሣቱ ልጅ ተክሌ የሚላት ነገር ትዝ አለችኝና በዚህ አጋጣሚ እሷን አስታውሼ ወደድኩለት፤ በቀጥታ ላልጠቅሰው እችላለሁ - የምጽፈው ነገር አቧራ ካላስነሳ የጻፍኩ አይመስለኝም - ይላል ልጅ ተክሌ፤ እውነቱን ነው፡፡ እየበሉ እየጠጡ ዝም… የሚባለው የመደሰቻ ድግስ ብሂል እንኳን መብላት መጠጣታቸው ስለሚታይ ነው፡፡ የአንድ ጽሑፍ መነበብና አለመነበብ የሚለካው ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ሰላማዊ ውርክብ ሲታይ ነው፡፡ በነገር መነታረክ መጥፎ አይደለም፤ ከብዙ ተጨቃጫቂ መካከል አንድና ሁለት የሚማማር ሰው ማግኘት ቀላል አይደለምና፡፡ ፍሬና ገለባ ከሚለይባቸው መንገዶችም አንዱ ይሄኛው ነው፡፡ ‹ከአነጋገር ይፈረዳል፤ከአያያዝ ይቀደዳል› እንደምንል፡፡

   ዛሬ ደግሞ በ‹ጠዓመኒ ድግመኒ› የትግርኛ ብሂል መሠረት አንዲት ነገር ተርጉሜ ማስነበብን ወደድኩ፡፡ የዛሬው ወደአማርኛ በከፊል የተመለሰ ጽሑፍ ቀደም ሲል ከድረ ገፅ ያወረድኩትና ለክፉ ቀን ሳይሆነኝ አይቀርም ብዬ እንዳይዘነጋኝ በ‹ሾርት ከት› የኮምቡጦሬ ደስክቶፕ ላይ ያኖርኩት አንድ አስደናቂ የኦነግ ደብዳቤ ነው፡፡ የደብዳቤ መለያውን ፍርማት(head letter) በኦሮምኛ፣ በዐረብኛና በእንግሊዝኛ  ቋንቋዎች ያዘጋጀው ይህ ግምባር የጌቶቹንና የጃዝ ባዮቹን የኤሪዎች ትግርኛ - የኛም ነው ለነገሩ - አለመጨመሩ ገርሞኛል፡፡ (ሰዎች እየተጃጃሉ የማያስፈልግ ግጭት ውስጥ የሚዘፈቁት እኮ ቋንቋን ልክ እንደ አንድ የምርት መገልገያ መሣሪያ ወይም ልክ እንደሸሚዝና ከናቴራ ከመቁጠር አልፈው በዘር ሐረግ ባሕርያዊ ውርስ ከአባት ወደ ልጅ እንደሚተላለፍ ትልቅ ቁም ነገር እየቆጠሩ ሥነ ልቦናዊ ቀውስ በመግባታቸው ነው - እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህም ላይ እመለስበታለሁ)፡፡

   ትግርኛን አለመጨመሩ ድርጅቱ ዕድሜ ጠገብ በመሆኑ ሊሆን ይችላል ከወያኔ በተሻለ ይሉኝታን ያውቃል ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም ግምባሩ ለተቦረቦሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ለሚስተር ባን ኪ ሙን የላከውን ደብዳቤ ሙሉ ቃል ሳይሆን የተወሰነውንና ከሀገራችን ወቅታዊ የመጋኛ ምች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውን ይህን የተላላኪዎች ጦማር ተርጉሜ ላስቃኛችሁ ፈልጌያለሁና ለማንበብ ትብብራችሁን አትንፈጉኝ፡፡ ሁሉንም ያልተረጎምኩት ረጂም ስለሆነና ከወቅታዊነት አንጻር አስፈላጊ መስሎ ስላልታየኝ ነው፡፡ ለሁላችሁም መልካም ንባብና ለአንዳንዶቻችሁ በተለይ መልካም መናደድ ይሁንላችሁ፡፡

 

                              OROMO LIBERATION FRONT
Gaafa: 09-08-2011 Date:

ﺗﺎرﺦﻳ رﻢﻢ

His Excellency Ban Ki-moon

Secretary General of the United Nations,
The United Nations Organization,
New York, N. Y.

 
( በቀጥታ ለዋና ጸሐፊው ስለተጻፈ Your Excellency ቢባል ይሻል ይመስለኛል - ለማንኛውም እንደገባኝ ልቀጥል - በቅንፍ የሚገኙ ጭማሪዎችና ደብተራ የጫጫረው አሸንክታብ ያስመሰልኩበት ልዩ የቀለም አፅንዖት የኔ ናቸው፡፡)

ለተከበሩ ባን ኪ ሙን

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ

 

   ይህን ደብዳቤ የምጽፍልዎ ሶማሊያንና ኢትዮጵያን የሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት (ከአሁን በኋላ የተ.መ.ድ በሚል አሳጥረዋለሁ) የቁጥጥር ቡድን ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ በጁን 21/2012 የተደረገውን የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ለማደናቀፍ ታስቦ ተጠነሰሰ የተባለለትን ሤራ (የኢሕአዲግ መንግሥት) አከሸፍኩ ማለቱን ተከትሎ ኦነግን በዚህ የሽብር ድርጊት ውስጥ ከሌሎች ኃይላት ጋር ለማካተት ሙከራ የተደረገበትን ሪፖርት በመቃወም ነው፡፡

        ይህ ዜና በልዩ ልዩ ሚዲያዎች በወጣበት ወቅት ኦነግ  የአፍሪካ ኅብረትን ስብሰባ በቦምብ ለማጋየት ተጠንስሷል በተባለ በዚህ የሽብር ጥቃት ውስጥ (ከእውነት ተሞክሮና ከሽፎም ከሆነ) እጁ እንደሌለበትና እንዲያውም ይህን ዓይነቶችን ንጹሓን ዜጎችን ለዕልቂት የሚዳርጉ ተግባራትን እንደሚቃወም በጊዜው በማያወላውል ሁኔታ አስታውቋል፡፡   በብሉምበርግ የዜና ማዕከል የዜና ዕወጃ እንደተገለጸው  “ኦነግ የአፍሪካ ኅብረትን ለማፈንዳት አላለመም ወደፊትም አያልምም”፡፡ እንደድርጅቱ ፖሊሲም “ኦነግ ሲቪሎችን፣ የሲቪል ተቋማትንና ንብረቶቻቸውን በጥቃት ዒላማው የዕቅድ ዝርዝር ውስጥ አይጨምርም፡፡”

   እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ የኢትዮጵያን መንግሥት በኃይል የተቆጣጠረው የመለስ (ዜናዊ) አገዛዝ ኦነግን በተለያዩ የሽብር ተግባራት ሲከስ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ እነዚህም ማለቂያ የሌላቸው የሽብር እንቅስቃሴ ተብዬዎች በእውን የሚታዩ ሳይሆኑ በራሱ በኢሕአዲግ መንግሥት የፕሮፓጋንዳ ክፍል አማካይነት በቤተ ሙከራ እየተፈበረኩ መንግሥትን በሚቃወሙ ኃይሎች ላይ የሚለጠፉ መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ በቅርቡ በዚሁ የወያኔ መንግሥት የደኅንነት ሰዎች የተሠራውንና “ አዲስ አበባን እንደባግዳድ” በሚል ርዕስ ለዕይታ የበቃውን በዶኩመንተሪ ፊልምነት የቀረበ የቤተ ሙከራ ሥሪት ብንመለከት ኦነግን ከሽብር ተግባር ጋር ለማቆራኘት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ይህ የተ.መ.ድ የሶማሊያና ኢትዮጵያ ተቆጣጣሪ ቡድን ይህን የመንግሥት የውሸት ፕሮፓጋንዳ እንዳለ ገልብጦ በሪፖርትነት ማቅረቡ ድርጅታችንን ኦነግን በእጅጉ አሳስቦታል፡፡ /ያን ቪዲዮ ለማየት ይህን አድራሻ ይጠቀሙ - http://www.diretube.com/etv-special/addis-like-baghdad-documentary-video_58f9ec467.html/. …

 

/የድርጅታችንን የኦነግን [የምሥራቅ አፍሪካ] አድራሻ ከፈለጉ ይሄውልዎ፡- P.O.Box 6973 Asmara, Eritrea Tel 2911 110236 Email: abamilki@gemel.com.er, www.oromoliberationfront.org /

 

   ይህ የተ.መ.ድ ተቆጣጣሪ ቡድን (The MGSE group) ድርጅታችንን ከዚህ የሽብር ጥቃት ጋር በዕብለት ከማነካካቱም በተጨማሪ  የኤርትራን መንግሥት ከኦነግ ጋር አንዳች ግንኙነት እንዳለው ለማስመሰል ማለትም የኦነግን ዓላማዎች በማስፈጸም ረገድ የኤርትራ መንግሥት እንደሚሠራ ለማሳመን በተሳሳተ ሁኔታ ብዙ ርቀት ተጉዟል፡፡  (ለኢትዮጵያው የወያኔ መንግሥት የሚያዳላው) ይህ ቡድን የኤርትራ መንግሥት የኦሮሞን (ሕዝብ) ትግል በበላይነት እንደሚመራ ለማስመሰል ባደረገው ጥረት የተሳሳተ ግንዛቤን ሊፈጥር የሚችል ሪፖርት አሰራጭቷል፡፡ በበኩላችን ይህን ቡድኑ እያወቀም ይሁን ሳያውቅ ያሰራጨውን ስምና ዝናን የሚያጠለሽ ሪፖርት በተመለከተ የኤርትራ መንግሥት በራሱ መንገድ እንደሚሄድበትና ራሱን እንደሚከላከል ሙሉ እምነታችን ነው፡፡ ነገር ግን የኤርትራ መንግሥት በጉዳያችን ፈጽሞውን ጣልቃ እንደማይገባና የድርጅታችንን ነጻነት እንደሚጠብቅ ለሚመለከተው ወገን ሁሉ ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በሌላም በኩል የኤርትራና የኦሮሞ ሕዝቦች ከመቶ ዓመታት በላይ የዘለቀ ረጂም የጋራ ታሪክና መልካም ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እንሻለን፡፡ የኤርትራ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ለሚገኝበት ሁኔታ ያለው ራሮትና ድጋፍም ከዚህ የረጂም ዘመን ትስስር የሚመነጭ ነው፡፡

 ክቡር ዋና ጸሐፊ

   ደግመን ደጋግመን ለመላው ዓለም እንዳሳወቅነው ኦነግ ማለት የኦሮሞን ሕዝብ ብሔራዊ ትግል በማስተባበር ኦሮሞንና ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ለማውጣት ቆርጦ የተነሣ ሕጋዊ ድርጅት መሆኑን አሁንም በዚህ አጋጣሚ ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ የኦነግ ግብ የኦሮሞ ሕዝብ ማንኛቸውም የዓለም ሀገራትና የተ.መ.ድ ራሱ የሚያምኑበትን መሠረታዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዲጎናጸፍ ማስቻል ነው፡፡ በተጨማሪም ኦነግ በአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦችና ሀገሮች ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር አበክሮ ይጥራል፡፡ …

የተከበሩ ዋና ጸሐፊ፤

 

   ኦሮሞዎች፣ በአፍሪካ ቅርምት ዘመን የአውሮፓ ቅኝ ግዛት የፈጠሯት የቅርብ ጊዜይቱ አፍሪካዊት ቅኝ ገዢ ሀገር አቢሲኒያ ወይም ኢትዮጵያና አውሮፓውያን ራሳቸው በጫኑባቸው አስከፊ ጭቆናና መሪር ቅኝ አገዛዝ ካለፉት አንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ጀምሮ ስቃይ ላይ የነበሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ዛሬ ኦሮሞዎች በምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው ሕዝቦች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የኦሮሞዎች ቁጥር 40 ሚሊዮን አካባቢ ይደርሳል፤ ይህ ደግሞ የጠቅላላውን ነዋሪዎች ቁጥር 40 በመቶ ያህል ነው፡፡ የኦሮሞዎች ሀገር - ኦሮሚያ - በተለይ ለኢትዮጵያና በአጠቃላይ ደግሞ ለአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ናት፡፡ ኦሮሞዎች ከማንም ሕዝብ በተለዬ ሁኔታ አንድ ዓይነት ባህል፣ አንድ የጋራ ቋንቋ፣ አንድ የጋራ ታሪክ፣ እንዲሁም አንድ ዓይነት የዘር ሐረግና ልዩ የመኖሪያ ግዛት ያላቸው ሕዝቦች ናቸው፡፡ ኦሮሞዎች ከኢትዮጵያውያንና ከሌሎች የአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች ጋር ሰፊ የባህልና የኢኮኖሚ ትስስር ያላቸው ከመሆናቸውም በላይ ከኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥታትና ከሌሎች በርካታ የቀንዱ ሀገራት ጋር በድንበር ይገናኛሉ፡፡

   የሀበሻ ገዢዎችና የፖለቲካ ምጡቃን(ኤሊቶች) በኦሮሞዎችና በሌሎች ተገዢዎች አጠቃላይ ሕይወት ላይ መድሎን፣ አስገድዶ መግዛትን፣ አፈናና ጭቆናንና ብዝበዛን ጨምሮ ያልጣሉባቸው የክፉ አገዛዝ ቀምበር የለም፡፡ እነዚህ የሀበሻ ቅኝ ገዢዎች የኦሮሞን ባህል፣ ቋንቋ፣ ወግና ልማድ ወዘተ. ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ በወራሪ የቅኝ ገዢ ኃይል ሥር እንደመገኘታቸው ኦሮሞዎች ሀበሾች በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ እንደሁለተኛ ዜጋ ይቆጠራሉ፡፡

   የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምጡቃን ዘረኛ አመለካከትና መናኛ አስተሳሰብ እንዲሁም ሥልጣናቸውን በእጃቸው እንዳለ ለማቆየት ያደረባቸው ጉጉትና ቅዠት ዴሞክራሲንና ልማትን እውን ለማድረግ እንዳይቻል እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ዘረኝነትንና መድሎን አስወጋጅ የተ.መ.ድ ኮሚቴ በአንደኛው ሪፖርቱ “ … ከ1995 እስከከ 2005 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከታዩ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች አብዛኞቹ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የተከሰቱ ናቸው፡፡ ከነዚህ ዓመታት ውስጥ ከአንደኛው በስተቀር በሁሉም ዓመቶች ከፍርድ ቤት ትዕዛዝና ብይን ውጪ ግድያና እሥር ተፈጽሟል፤ በነዚህ ዓመታት  ውስጥ በኦሮሞ የተፈጸመውን ያህል ግፍና በደል በሌሎች ክልላዊ መንግሥታት ውስጥ መፈጸሙን የሚያመለክት ዘገባ ወይም ሪፖርት አልቀረበም፡፡ …”ሲል ገልጾኣል፡፡

   በተጨማሪም በሰብኣዊ መብቶች መጠበቅ ዙሪያ የሚንቀሳቀስ አንድ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በዘገባው እንደገለጸው “የርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ተከታታይ የአማራ-ትግሬ ገዢ መደቦች የኦሮሞን ሕዝብ ነጥለው የጥቃት ዒላማ ማድረጋቸውን በተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፎ ማቅረብ ይቻላል፡፡” ከዚህና ከሌሎችም ሪፖርቶች መረዳት እንደሚቻለው የአሁኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞን ሕዝብ በተለያዩ አጋጣሚዎችና ሰበቦች የጥቃት ሰለባ አድርጎ እያሰቃየው እንደሆነ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ … (የአማራውን ማለቅ ለመሸፋፈን ኢሣይያስ በኦነግ በኩል ለወያኔ የሰጠው ፖለቲካዊ ድጋፍና የዕርቅ መጎናበሻ ገጸ በረከት  ይሆን?)

    የኦሮሞ ሕዝብ የነጻነት ትግል ከቅኝ ገዢው የኢትዮጵያ መንግሥት ነጻ የመውጣት ፍላጎት የወለደው ተፈጥሯዊ የመብት ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ከውጭ ወራሪ ኃይል ራስን ነጻ የማውጣት ትግልና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ደግሞ የተ.መ.ድን ጨምሮ በሁሉም ሀገራት ዕውቅና የተሰጠው ዓለም አቀፍ መብት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይህን መብት ለኦሮሞ ሕዝብ ይነፍጋል፡፡ መንግሥት ይህን ሕገ ወጥ ድርጊት በመፈጸሙም የተባበሩት መንግሥታትን ሕገ ደንብ አንቀጽ አንድ፣ ንዑስ አንቀጽ አንድ  ይጻረራል፡፡ ይህ ሕግ እንዲህ ይላል፡- “ሁሉም ሕዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብት አላቸው፤ ይህን መብታቸውን አለገደብ በመጠቀምም የራሳቸውን የፖለቲካ ሥርዓት በነጻነት የመወሰን፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ዕድገታቸውን በፈለጉት አቅጣጫ የመምራትና የማሳደግ መብት አላቸው፡፡” …

ዳውድ ኢብሣ፤ የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ብሔራዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር

______________________________________________

 

   እንደተለመደው የራሴን ጥቂት ሃሳቦች በመናጆነት መለጠፌ አልቀረም፡፡ አንጋፋውና የእንጨት ሽበቱ ኦነግ ይህን አስገራሚ ደብዳቤ ከአሥመራ በላከ ሰሞን በአድራሻው ‹አንጀት የሚበላ› አጭር ኢሜይል ብልክም ሣንሱር አድራጊው ሕግሓኤ በቅድሚያ ስለሚያነበው ይመስለኛል መልስ የሰጠኝ አልነበረም፤ ለነገሩ እኔም አልኩ ለማለትና ለኅሊናዊ ውርድ ከራስ እንጂ ዐውቆ የተደበቀ ቢጠሩት እንዳለመስማቱ ከእሥረኛው ኦነግ መልስ መጠበቁ የዋህነት መሆኑን አጥቼው አልነበረም፡፡ የኢትዮጵያን ነጻነትና ሉዓላዊነት ከገፈፈ አካል ነጻነትንና ሉዓላዊነትን በምፅዋት መልክ መለመን የለዬለት ጅልነት መሆኑንም ብዙዎች ከበፊቱ ጠንቅቀን እንረዳ ነበር፡፡ በመሠረቱም ነጻነትን ከሚደፈጥጥ ወገን፣ ኢትዮጵያውያንን  በኤርትራ ታዳጊ ሕጻናት አእምሮ ውስጥ በማስፈራሪያነት ከሚያሰርጽና በተለይ አማሮችን ለተዋጊዎቹ የዒላማ ተኩስ መለማመጃ ከሚያደርግ፣ የጦር ምርኮኞችን ጨፍጭፍ ራሳቸው በቆፈሩት ጉድጓድ አፈር የሚያለብስ፣ በሕይወት ካሉ ሰዎች የወርቅ ጥርስን በጉጠት እያወለቀ ከሚቀማ …  የክፉዎች ክፉ የበላኤሰብ ቡድን ነጻነትን መጠበቅ ከብት ባልዋለበት ኩበት ፍለጋ እንደመሰማራት ነው፤ ይህን በጎ ነገር ከዚህ ዕኩይ ድርጅት መቀላወጥም ‹የጨነቀው ዱቄት ወደ ንፋስ ይጠጋል› እንደሚባለው የተስፋ መቁረጥ ምልክት ነው - ያበጠው ይፈንዳ የሚሰማኝን እውነት እናገራለሁ፡፡ እንዴት ተደርጎ ነው ሻዕቢያ የኢትዮጵያ ነጻነት ሐዋርያ ሊሆን የሚችለው? የችግር መፈልፈያ ቋት በየትኛው ሒሣባዊ ቀመር ተገልብጦ ነው የመፍትሔ ምንጭ የሚሆነው?...

   አሁን ኦነግ ፈራርሷል ተብሏል፤ ቢዘገይም ከቅሪቶቹ የተወሰኑት እየተጀነኑና በአስደግዳጊ ቅድመ ሁኔታም ታጥረው የኢትዮጵያን አንድነት ለመቀበል እየተዘጋጁ ነው ተብሏል፡፡ እውነቱን ለመናገር ኦነግ የፈረሰው ዛሬ ወይ ትናንት አልነበረም፡፡ የፈረሰው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ቆርጠው ከተነሱ ወገኖች ትዕዛዝ እየተቀበለ በሰው ሣምባ እየተነፈሰ በብዙ የሞኝ ተግባራቱ ምክንያት ቀስ በቀስ ግን በሂደት ከኦሮሞ ሕዝብ ልብ መውጣት ሲጀምር ነው፡፡ ኦነግ ኖረ ከተባለ አንድ ጥጋት ላይ ቁጭ ብሎ ይህን መሰል መግለጫና ደብዳቤ በሚለቀልቅ የወረቀት ላይ ነብር የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ አማካይነት እንጂ በተግባር የኖረበትን ጊዜ ማስታወስ ያቅተኛል፤ እርግጥ ነው ድርጊቱ የተፈጸመው በበላይ ትዕዛዝም ቢሆን በበደኖና በአሰቦት ገዳም በጊነሰ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ሊመዘገብለት የሚገባው ሕጻናትና አእሩግ እንዲሁም መሣሪያ ያልታጠቁ ምሥኪን አማሮችን የመጨፍጨፍ ታላቅ ጀብድ ሠርቷል - በዚያ ድርጊቱ አለቆቹና ያን ግፍ የፈጸሙ የራሱ የኦነግ አባላት ተገቢ ዋጋቸውን ያገኛሉ - ዋናውን ፈላጭ ቆራጭ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ብዙዎቹ ወንጀለኞች ከአሁን በፊት ፍርዳቸውን እንዳገኙ ይገመታል፡፡ ከዚያ በመለስ ግን አንዲት የታወቀች መንደር እንኳን ይዞ ‹እዚህ አለሁ! ማን ነው ወንዱ! አካኪ ዘራፍ› ማለት ያልቻለና ሕይወቱን በስደት ኖሮ በዚያው በስደት ሕይወቱ ያለፈ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አንደኛው ተላላኪ እንጂ እውናዊ የነጻነት ፋኖ አልነበረም - መሪ ተብዬዎቹ የፈረንጅ ፓስቲ ሲገምጡና በዕርዳታና የውጭጭ ገንዘብ በቅንጦት ሲምነሸነሹ ኖረው በመጨረሻው በ’mission accomplished’ ፈረንጃዊ የቃቃ ጨዋታ ኦነግ ከጨዋታ ሜዳ መውጣቱን ለመሸፋፈን ቢሞከርም የኢትዮጵያ ትንሣኤ በሚበሰርበት ቅርብ ጊዜ ውስጥ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ጠላት የሥራውን እንደሚያገኝ ጥርጥር የለውም፡፡

   እናም ኦነግ ለማያውቁት ይታጠን፤ ቋንቋን ማሣመር የኅልውና ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም - ደግሞም ወግ አይቀርምና ‹ሲቪል ዜጎችና ንብረቶቻቸው ከኦነግ የዒላማ ጥቃቶች ውጪ ናቸው› ይባልልኛል፡፡ ለመሆኑ ደካሞችንና መሸሻ መጠለያ የሌላቸውን ዜጎችን ከመግደል ያለፈ የጦር ሜዳ ውሎ አለው እንዴ ኦነግ? የምን ንገሩኝ ባይነት ነው? የሌሎች ሀገሮች ተቃዋሚዎችና አማጺያን በጥቂት ወራትና ዓመታት ውስጥ ግባቸውን ሲመቱና በተናጠል ወይም በሽርክና መንግሥት ሲመሠርቱ ኦነግ በግማሽ ምዕተ ዓመት አንዲትም ወረዳ ሳይቆጣጠር በወሬ ኖሮ በወሬ የተፈታው በአቅም ማነስና በአመራር ጉድለት ሳይሆን በዓላማ ተልካሻነት ነው፡፡ ወንዝ የማያሻግር እንቶ ፈንቶ ዓላማ አንግቦ፣ ያንንም የጥላቻ ዘፈን አይሉት መዝሙር በጠላት አማካይነት እንደቴፕ ሪከርደር ተሞልቶ አሥመራ ላይ ሆኖ እንደጣቃ መቀደድ ድል እንደማያስገኝ እናውቅ ነበር፡፡ ወያኔንና ሻዕቢያን ያመነና ጉም የዘገነ አንድ መሆናቸውንም እናውቅ ነበር፡፡  ሻዕቢያና ወያኔም ባቅማቸው የአፍሪካ ሞሳድና ኬጂቢ ወይም ኤም አይሲክስና ሲአይኤ ሆነው (በሥልት መመሳሰል ማለቴ ነው) ኢትዮጵያን ለመበታተን ይህን ጅላጅል ድርጅት መጠቀማቸውን ልብ ለምንል ወገኖች ለመጥፎ ዓላማም ቢሆን ተግተው ከሠሩ የማይቻል ነገር አለመኖሩን መገንዘብ ይቻለናል፡፡

   ይሁንና እውነት ሁልጊዜም እውነት ስለሆነች በመጨረሻ ማሸነፏ አይቀርምና የኢትዮጵያ ጠላቶች አንድ ባንድ ግን በርግጠኝነት ወደ ከርሠ መቃብራቸው የሚነጉዱበት ዘመን እየመጣ ነው፡፡ ይህን የምንለው ይህኛውን ወይም ያኛውን የተቃዋሚ ቡድን አለኝታ አድርገን ሳይሆን ፈጣሪን ተመክተን  ነው፡፡ ከሰው የምንጠብቀው ነገር ብዙም አይደለም፤ ያልታዘዘ ምንም ነገር አያደርግም፡፡ ከታዘዘ ግን ሣምንትም፣ ቀንም፣ ሰዓትም፣ ደቂቃና ሴከንድም የማድረጊያ ጊዜ ናቸው፡፡ የነጻነት ጎሕ ሲቀድ፣ እውነተኛው ሙሤ ሲላክ፣ … ያኔ የቁርጥ ቀን ሲመጣ አጭበርባሪውና ሆድ አምላኪው ሁላ የሚገባበትን ያጣል፡፡ …

   በበኩሌ ይታየኛል፤ የሌቦች ዘመን እየተጠቀለለ ነው፡፡ የብርሃን ዘመን እየባተ ነው፡፡ ብዙ እንዳየን ብዙ እናያለን፡፡ እስካሁን ያየነው ሁሉ ባሳለፍነው አጭር ግን አስደንጋጭና አሰቃቂ ጊዜ ውስጥ እናያለን ብለን ካሰብነውና ከጠበቅነው በላይ ነው፡፡ የፈጣሪ ቀን አንዲት ብቻ አይደለችም፤ ቀናት ሁሉ የርሱው ናቸው፡፡ ነገን የማያውቁ ትናንትን የማያስቡና ማስታወስም የማይችሉ ወይም የማይፈልጉ ናቸው፡፡ ዛሬ አብዛኛው ዜጋ ለሆዱ ተሸንፎ ስለሆዱ አድሮ በሆዱ እያሰበ ቢያድር ቢውልም ፈጣሪ ይህን የእበላ ባይነትና የስግብግብነት ዘመን ሲገፍፈው፣ ኅሊናም ትክክለኛ የዳኝነት ሥፍራውን ሲይዝ የሀገራችን ቅርጽ በቅጽበት ይለወጣል፡፡  ያኔ የጠፋው ሃይማኖት ይመጣል፤ ያኔ የጠፋው መተሳሰባችንና መተዛዘናችን ይመጣል፤ ያኔ ቁሣዊነት ይጫጫና ሰብኣዊነት ይፋፋል፡፡ ያኔ ይሉኝታና ሀፍረት ይወለዳሉ፡፡  

   በነገራችን ላይ “አንበሣን ፈርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ” እንዲሉ አንዱን ፈርተን ወደ ሌላኛው ልንሸሽ ስንሞክር የኋለኛው ከፊተኛው የባሰ እየሆነብን ስንሰቃይ መቆየታችንን ስናስብ የሀገራችን ነገር የእግር እሳት ይሆንብናል፡፡ እናም እንዳለመታደል ሆኖ ኦነግ ትልቅ ደረጃ መድረስ እየቻለ ባነገበው ውራጅ ዓላማና ግብ እንዲሁም የሰው አሽከር ለመሆን በመቁረጡ ሣቢያ ከስሜትና ከልብ ወጥቶ መሬት ሊቆነጥጥ የሚችል ድል ሊጎናጸፍ አልቻለም፡፡ ይህ ሰባራ ዕድላችን ደግሞ ኦሮሞ ነን ለምንል ወገኖች ትልቅ የልብ ስብራትን ያስከትልብናል - የምትወደውን በማትወድለት ጠባዩ ምክንያት ማጣት ሌላው የእግር እሳት ነው - እየተወደዱ ከመጠላት ይሠውር፡፡ እኔ በኦሮሞነቴ ከማፍርባቸው ነገሮች አንዱ ይህ የኦነግ አይረቤነትና ለአሰለጦች ዓላማ ማስፈጸሚያ የመሆኑ ክፉ ዕጣ ነው፡፡

   እኔ ኦሮሞ ነኝ ብያለሁ - እስካሁን ካላልኩም አሁን ነኝ እያልኳችሁ ነው፡፡ ኦሮሞ ለመሆን ደግሞ የማንም ፈቃድና ይሁንታ አያስፈልገኝም - የማንነት ጥያቄ እንደንግድ ሊቼንሳ ግድግዳ ላይ ለጥፈው የተቆጣጣሪ ባለሥልጣንን ተግሣጽና ግልምጫ የሚያስወግዱበት ቁሣዊ ነገር አይደለም፤ ብዙ ምሥጢር አለው፡፡ ኦነግም ሆነ በኦሮሞ ስም የተቋቋሙ ኆልቁ መሣፍርት የሌላቸው ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ኦሮሞነትን ለማንም ሊሰጡ ወይ ሊነሱ አይችሉም፤ ከሞከሩ ድፍረትና ብልግናም ነው፡፡ በምርጫቸው ኢትዮጵያዊ መሆንን የወደዱ ነጮች መኖራቸውን ስንረዳ የነኦነግ ኢትዮጵያን የመጥላት አባዜ አልገባችሁ ሊለን ይችላል፡፡ ሌላው ሁሉ ይቅር - ኦሮሞው መንግሥቱ ኃ/ማርያም ምን ይላቸዋል? የኦሮሞው የአጼ ኃይለ ሥላሤ አፅም ምን ይላቸዋል? የሌሎች ኢትዮጵያን አንቀጥቅጠው የገዙ የኦሮሞ ነገሥታት ዐፅሞች ምን ይሏቸዋል? እንደኦሮሞነቴ ቢቻለኝ አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ የሚናገረውን ቋንቋና የሚኖርበትን ባህል ባውቅ መልካምና ተጨማሪ ዕሤት በሆነልኝ፡፡ ያም ቢሆን የግድ ያህል አይደለም፡፡ በተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች የተነሣ ቋንቋውንና ባህሉን ላላውቅ እችላለሁ፤ ኦሮሞነትን ግን በማንም በጎ ፈቃድ እንደማላገኘው ወይም እንደማላጣው አስረግጬ ልነግራችሁ እችላለሁ - ኦሮሞ ለመሆን ኢትዮጵያዊነቴ ብቻ ይበቃኛል፤ የኔ ደም የኦሮሞን ደም እንደማይመስልና ኦሮሞነቴን ሊያስከለክለኝ የሚችል ብቸኛው መንገድ ናሙና ደሜ ተመርምሮ ‹አንተ አጭበርባሪ! የኦሮሞ ደም የሚባል በደምህ ውስጥ የለም!› የሚል የምሥክር ወረቀት ከታወቀ የዘረመል ጥናት የሕክምና ማዕከል ሲሰጠኝ ብቻ ነው፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ኦሮሞ፣ የኢትዮጵያ ትግሬ፣ የኢትዮጵያ አማራ… የሚባለው ምናልባትም ከጭንቀት የሚመነጭ የማደናገሪያም ይሁን የማባበያ ፈሊጥም ትክክል አይደለም፡፡ ራሱን በሺህ ቦታ ይበጣጥሰው ብዬ እንዳልረግመው ከኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ከሃይማኖታዊ ቀኖና አንጻር ይከብደኛልና ‹ኦሮሞነቴን ያልተቀበለች ኢትዮጵያ በሺህ ቦታ ትበጣጠስ› በማለት ይህችን የሚሊዮናትን ሀገር የነገር ማጣፈጫ ለማድረግ የሞከረው ሰውዬም ልብ ሰጥቶት ወደኅሊናው እንዲመለስና በአንድ የጋራ ማንነት ውስጥ አብረን ኢትዮጵያዊነትን እንድንዘምር እጸልያለሁ፡፡

   በተረፈ ኦሮሞ ለመሆን ኢትዮጵያዊነት ብቻውን በቂ ብያለሁ - አሁን አልደግመውም፡፡ በመሠረቱ ኦሮሞ መሆን ጮቤ የሚያስረግጥ አይደለም፤ አማራ መሆንም በሀዘን ማቅ እሚያስለብስ ወይም በደስታ ቱልቱላ እሚያስነፋ አይደለም፤ ትግሬ መሆን በከበሮና ክራር ጮቤ እሚያስረግጥ አይደለም፡፡ ምንም መሆን ምንም ማለት አይደለም - ትግሬ ወይም ጉራጌ ሆነህ ለመፈጠር አንተ ወይም አንቺ ምን ቤት ናችሁና? አንዳንዴ እኮ ማፈርም ጥሩ ነው፤ አመኑበትም አላመኑበትም የሃይማኖት መጻሕፍትንም መዳበስ አይከፋም - ሁሉም የአዳምና የሔዋን ዘር አይደለም እንዴ? ታዲያ ቄሱንና ኢማሙን ምን ነካቸው? በጎቻቸው በዘረኝነት ተጠልፈው ከፈጣሪ ትዕዛዝ ሲወጡ እነሱ የት አሉ? ወይንስ ካለበት የተጋባበት እንዲሉ በነሱም ብሶ ተገኘና ተያይዘው ጠፉ? ባልሠራነው ሥራና በማይመለከተን ጉዳይ ዘው ብለን ገብተን ለምንድነው ከሣሽና ፈራጅ ዳኛ መሆን የሚቃጣን? መጀመሪያ እኛነታችን ሰብኣዊነታችን እንጂ የሰው ዘር በሙሉ አንድ መሆኑን መረዳት ተገቢና ከጤናማ ማኅበረሰብም የሚጠበቅ ነው፤ ሰው አበደ ተብሎ ደግሞ ጨርቅ እንደማይጣል ሁሉ የተወሰኑ ሰሜነኛ ወንድምና እህቶቻችን በዘር ልክፍት አበዱ ብለን አብረን ተባብረን ማበድ አይጠበቅብንም፡፡ ማግኘትና ማጣት ባመጡብን ጣጣዎች ተከፋፍለን ሰብኣዊነትን መረጋገጥ አይገባም፡፡ ብዙ ነገሮች የወረት ናቸው፤ ወረት ደግሞ ያልፋልና በማያልፍ የታሪክ መዝገብ ላይ በጉልህ ፊደላት የሚሠፍር የታሪክ ጠባሳ መተው አይኖርብንም፡፡ አንድ ሁላችንም በጥልቀት ልናስብበት ነገር ልናገርና ላብቃ፡፡

   እኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ስፈጠር የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 25 ሚሊዮን ገደማ ነበር፡፡ አሁን ያ ቁጥር ተገቢው መንግሥት ስለሌለን ክፉኛ አሻቅቦ ወደ 87 ሚሊዮን አካባቢ ደርሰናል አሉ - ይህን አስደንጋጭ የሕዝብ ቁጥር ስናሰላው የያኔውን ሦስት ነጥብ አምስት ገደማ አጥፏል ማለት ነው ፡፡ ከእኔ ዕድሜ ወደኋላ ጥቂትና ብዙ ዓመታትን ለምሳሌ 50፣ 100፣ 200፣ 500… ሄደን ማየትም እንችላለን፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በነዚያን ዓመታት ስንት ሊሆን እንደሚችልም በምናባችን መቃኘት እንችላለን፡፡ ምናልባት 100 ሚሊዮን፣ 5 ሚሊዮን፣ 2 ሚሊዮን፣ ግማሽ ሚሊዮን… ይህ ሒሳባዊ ፖስቱሌትም እንበለው ቴኦረም እያለ እያለ ወደ ጥቂቶች ቀደምት ዝርያዎቻችን ይወስደናል፡፡ ታዲያን በጣት ከሚቆጠሩ አባት እናቶች ተነስተን 87 ሚሊዮን የገባነው ዘር እየተቋጠርን በመዋለድ ይሆን እንዴ? ብለን ደግሞ እናስበው፡፡ እርግጥ ነው - በአንድ አካባቢ ሰው ሲበዛ በተፈጥሮ ሀብት መሳሳትና ማለቅ እንዲሁም በቦታ ጥበት የተነሣ ወደሌላ አካባቢ ተዛውሮ መሥፈር የነበረና ያለ ነው፡፡ በዚያም የረጂም ዘመን ሂደት ውስጥ የቋንቋና የባህል መለያየት መከሰቱ የማይቀር ነው፡፡ ለዚህም ነው የሰዎች ባህልና ቋንቋ በብዙ መንገድ የሚመሳሰለው፡፡ … እግዚአብሔር አንድ አድርጎ የፈጠረውን ሰው ዘመንና መልክዓ ምድራዊ ልዩነቶች ሊለዩት ደግሞ አይቻላቸውም፡፡ መቅላት መጥቆርም፣ ማጠር መርዘምም… በአንድ ቤተሰብ ሳይቀር የሚታዩ ልዩነቶች በመሆናቸው ያን ያህል ጉባኤ የሚያስቀምጡ የልዩነት መንስኤዎች አይደሉም፡፡

   በኔ በዚህች የግማሽ ምዕተ ዓመት በምትሆን ዕድሜየ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ25 ሚሊዮን ወደ 87 ሚሊዮን የደረሰው ኦሮሞ ከኦሮሞ፣ ትግሬ ከትግሬ፣ ኮንሶ ከኮንሶ፣ ከፊቾ ከከፊቾ፣ ጠምባሮ ከጠምባሮ፣ ዳዋሮ ከዳዋሮ፣ ጉራጌ ከጉራጌ ደራሳ ከደራሳ፣ ወላይታ ከወላይታ፣ ሃዲያ ከሃዲያ፣ ከምባታ ከከምባታ፣ አደሬ ከአደሬ፣ ቆቱ ከቆቱ፣ አማራ ከአማራ፣ አገው ከአገው፣ ወይጦ ከወይጦ… እንዲጋባ ሕግና ሥርዓት ተበጅቶ በዚያ ቀጭንና ኢተፈጥሯዊ ሕግ ተጉዘን ሣይሆን ሁሉም እንዳመቸው ካፈቀራትና ካፈቀረችው ጋር እየተጋቡና አንሶላና ጋቢ እየተጋፈፉ ነው - ያኔ እኮ ‹የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ፤ የሐረር ልጅ ነኝ፤ የደሴ ልጅ ነኝ፤ የአዋሣ ልጅ ነኝ፣ የቦንጋ ልጅ ነኝ…› እንጂ ‹የኦሮሞ ልጅ፣ የትግሬ ልጅ፣ የአማራ ልጅ…› የሚባል እንዲህ እንደዛሬው ዐይን ያወጣ የዘረኝነት ልክፍት አልነበረብንም፤ ይህ ዓይነቱ ነገር የመጣብን በተለይ ካለፉት 22 ዓመታት ወዲህ ወያኔ መርዙን ከረጨብን በኋላ ነው፤(አሁንስ ቢሆን እስኪ በየትምህርት ቤቱ ሂዱና እዩ … ተማሪዎች በዘፈቀደ ተበሰጣጥረው እንጂ በይሁንታ በዘር ኩይሣ ነው እንዴ የሚማሩትና በፍቅር ዓለምም የሚመላለሱት?)፡፡ አንዳንድ በስተቀሮችን ወደ ጎን እንተዋቸውና - በአብዛኛው - ጥንት ያኔ ኦሮሞው አማራዋን ያገባል፤ ትግሬው ይፋቴዋን ያገባል፤ አማራዋ ከጀምጀሙ ትወልዳለች፣ ሽናሻይቱ አገውን ታገባለች፤ ቢለኑ ሳሆዋን ያገባል፣ ትግረዋ ትግሬውን ታገባለች፣ ኢሮቡ አፋሯን ያገባል… ምኑ ቅጡ… በዚህ የአሥረሽ ምቺው የፍቅርና የጋብቻ ትስስር ‹ብዝሁ ተባዝሁ ወምሉዕዋ ለምድር› በሚለው ሕገ እግዚአብሔር ተመርተን ኢትዮጵያን ሞላናት - ምን አጠፋንና ነው ታዲያ ወያኔና ኦነግ ከአባታቸው ከሻዕቢያ ጋር በሃሳብ አንድነት ሥሙር ሆነው ሽል ምንጠራ ውስጥ የገቡትና በማን አባት ገደል ገባ ሊያመነቃቅሩን የሚሹት? እኔ አሁን ታዲያ ምንድነኝ ልበል? የትኛው ነው የኔ ‹ጥርት› ያለው ዘር? ‹እኔ የጎንደሬይቱ ልጅ! እኔ የጎጃሜይቱ ልጅ…› የሚለውን መንደርኛ ፈሊጥ ተውት፡፡ ይህ ዓይነቱ ከጠላ ቤት ድንፋታ ሊያልፍ የማይገባውን ተራ ጨዋታና ከዚህ ባስ የሚለውንም ተራ የቀልድ ልውውጥም ከምር አትውሰዱት፡፡ በእናቴ በኩል የምዛመዳቸውን ወንድሞቼንና እህቶቼን አስታውሰህ በቀልድ መልክ ‹ከወሎ ጎረቤት ይሻላል ባዶ ቤት› ብትለኝ እስቅ ይሆናል እንጅ ምንም አልልህም - በዚህ ዓይነቱ ተራ ቧልትም መነካከስ አይገባም፡፡ በአባቴ በኩል የምዛመዳቸውን እህቶቼን አስበህ ‹አንት ግድርድር ጎንደሬ› ብትለኝ ይብስ እየተኮፈስኩ በቀልድ አናድድህ ይሆናል እንጂ በዚህም ምንም አይሰማኝም፡፡ ኧረ ለመሆኑ ወሎስ የማን ሆነና? ስሙ ራሱ የኦሮሞ ስም አይደል እንዴ? ኦሮሞ ያልገባበትና ያልተዋለደው ኢትዮጵያዊ ግዛት ይኖር ይሆን? በኦሮሞነት ብዙም በማይታሙት ኤርትራና ትግራይ እንኳን ዕድሜ ለዚያ የደርግ ዘመን የርስ በርስ ጦርነት ሁላችንም በሁላችንም ውስጥ እንድንቀልጥ ተደርገን የለምን? ከሌላ ጋር የማይዋለድ መንወሳቀስ የማይችል ዛፍና ግንድ ብቻ ነው፡፡ ሰው በተፈጥሮው ተንቀሳቃሽ በመሆኑ ሌላ መሰል ፍጡር እስካገኘ ድረስ ይተኛል፤ ይዋለዳልም፡፡ ስለዚህ የጠራ ዘር ማግነት በነኦነጎችና መሰሎቹ አእምሮ ውስጥ ህልምና ቅዠት ሆኖ የሚቀር እንጂ እውን ሊሆን አይችልም - የነዚህ የበጥባጮቹ የዘር ሐረግ ሲታይ በአብዛኛው የዚህ የመጢቃነት ‹ሰለባ› ናቸው- ለምሳሌ የሕወሓቱን አዲስ ዓለም ባሌማን ብናይ የኦሮሞና የትግሬ መጢቃ ነው - በዚህ ረገድ መረጃው ያላችሁ እባካችሁን የበጥባጮቹን የዘር ሀረግ (pedigree) አሳዩን - እንድንማርበት፡፡ እኔን ታዲያ ማን ነው ከማን ነጻ የሚያወጣኝ? ራስን አለማወቅ ይሏል ይሄኔ ነው፡፡ ኦነግ ራሱን ሳያውቅ በስሜ እየማለና እየተገዘተ ድፍን ግማሽ ምዕተ ዓመት ቀለደብኝ፡፡ እሱ ሩጫውን እንደጨረሰ እኔም አሁን በሃሳብ መዳከሩ ቢበቃኝስ ወገኖቼ፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋየ መሆኑን ታውቃላችሁ፡፡ እናም በትምህርት ብዙም ያልገፋሁና በ‹መሠረተ ትምህርት› ብቻ ተወስኜ የቀረሁ ከመሆኔም በተጨማሪ አማተር ተርጓሚ እንጂ ፕሮፌሽናል አለመሆኔን ተረድታችሁ በሚኖርብኝ የትርጉም ስህተት ከመሣለቅ ይልቅ እናንተው በጎደለ እየሞላችሁ በተጣመመ እያቃናችሁ እውነታውን ብቻ እንድትገነዘቡልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ በተጨማሪም ይህን ወረቀት ለማንበብም ሆነ ለማስነበብ የምትጓደዱ ወገኖቼ ኃያሉ አምላክ ጭንቀቴን ያስርፅባችሁና እውነቱን ተረድታችሁ … በቃ እናንተ እውነቱን  ከተረዳችሁልኝ ያ ብቻ  ለጊዜው በቂየ ነው፡፡