Wednesday, August 15, 2012

የኢሳያስ አፈወረቅ ባለቤት ወ/ሮ ሳባ ሃይለ የጋብቻ ፍች ጠየቀች።

We have three topics for you today:
(2) news from Eritrea and Ethiopia (2) Poem by the popular poet, author and journalist Wondwessen G/kidan from Addis Ababa


1) የወያኔው  አቡነ ጳውሎስ ዛሬ ሌሊት ከዚህ  ዓለም በሞት መለየታቸው ታወቀ።

2) የኢሳያስ አፈወረቅ ባለቤት / ሳባ ሃይለ የጋብቻ ፍች ጠየቀች።
Saba Haile the wife of Isayas Afewerki currently seeking divorce 
Isayas Afewerki of Eritrea with his Arab masters conspiring how to destroy Ethiopia exchange for money and power. Isyas is the shame of our people in history with that shame full foreign mercenary in Ethiopia called Meles Zenawi who is selling Ethiopia to colonialists and racists without fear to history or his God (if he has one)
Isyas Afewrki's daughter Elsa performing a dance infront of her father in Sawa Military Training service center 


ከ1985 ዓ.ም (ኤርትራኖች በሚጠቀሙበት የፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር) በረሃ እያሉ ጋብቻ ከፈጸሙ ጀምሮ እና ለ21 አመት የውሸት እና የሥቃይ ነፃነታቸው ካገኙ በላም  አብረው የኖሩ እና ሁለት ልጆች የወለዱ ቢሆንም ‘አሰና’ የተባለው የኤርትራ ተቃዋሚ የራዲዮ ዜና አገልግሎት እንደገለጠው ወ/ሮ ሳባ በትዳርዋ ደስተኛ እንዳልነበረች አትቷል።

ዜናው እንደገለጸው አቶ ኢሳያስ ነጋ ጠባ ከባለቤቱ ጋር ሰላመዊ የሆነ ግንኙነት

እንደሌላቸው እና ነጋ ጠባ በመጠጥ ተመርዞ ንትርክ እንደሚያበዛ እና ባለቤቱ የሕሊና እረፍት ባለማግኘቷ መቋቋም ባልቻለችበት ደረጃ በመድረሷ ብዙ ጊዜ ምክር እና ማስጠንቀቂያ ብታቀርብለትም ከመጤፍ ባለመቁጠር መንቻካነቱ እና ስካሩ ሊያቆመው ባለመቻሉ ይፋ ሆኖ ሕጋዊ ፍች ከማድረጋቸው በፊት በዘመድ አዝማድ እና በወዳጅ በኩል በምስጢር የጋብቻ ፍች እንዲያደርጉ ብታስጠይቀውም አቶ ኢሳያስ ከመጤፍ ባለመቁጠሩ ፍችውን ይፋ ለማድረግ ሕግ ቦታ ለፍች ቀርቧል።

ወ/ሮ ሳባ ሃይለ፤ ከነፃነታቸው ወዲህ አልፎ አልፎ በትዳርዋ ደስተኛ እንዳልነበረች ወሬ እንደነበሩ ምንጮቹ ገልጸዋል።

የኢሳያስ ቤተሰብ እንኳን ለት ተለት ይቅርና በበዓል ወቅት እንኳ እንደሰው በባህሉ መሰረት በንቡር ህይወት (ተሰባስበው ባንድነት) ተደስተው እንደማያውቁ ለብዙ ሰው  አዲስ ዜና እንዳልነበረ የታወቀ ነው። ይላሉ ምንጮቹ።

አባቴ በባህላችን መሰረት እንደ ባል እና ሚሰት ባንድ ክፍል  አብረው ሲተኙ አይቻቸው አላውቅም። አባቴ አንኳን እና በማንኛውም ተራ ቀን ቀርቶ በታላቁ በዓል ፋሲካ ዕለት እንኳ አባቴ አብሮን ቁጭ ብሎ እኛ ጋር ምግብ ባርኮልን በልቶ አያውቅም።” ሲል  ኣብርሃም ኢሳያስ (የኢሳያስ ልጅ)  ማይ ነፍሒ በሚባለው ኮለጅ ት/ቤት ለት.ቤት ወዳጆቹ ሲናገር ነበር።

ኢሳያስ   ባባ  ገርሰት (የእርሻ ቦታ) ሱኳር ሊዘራልን ነው፤ ይሁን እንጂ  ለሁሉም/ ለሕዝብ ሊያድለው ነው”  ስትል ከነበረቺው ከአንደኛዋ ትንሿ ልጁ ግንኙነት በቀር ከተቀሩት ልጆቹ ጋር በተለይም ከትልቁ ልጁ  ከኣብርሃም ጋር ንትርክና ስድብ ካልሆነ ጤነኛ ግንኙነት አልነበረውም።

በአየር ሃይል ምክትል አዛዥት መዓረግ ተሰጥቶት የወላጁ ስልጣን በመንከባከበረ ላይ ያለው ኮሎኔል አብርሃም ኢሳያስ፤ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በመጥጥ እና በሲጋራ ሱስ የተጠመደ ሱሰኛ ነው። በዚህ ሁሉ ጫና ውስጥ ያለቺው ወ/ሮ ሳባ ሃይለ ከዚህ ሁሉ የሕሊና ጫና ነፃ ለመሆን ባለቤቷ አሲአያስ አፈወርቂ በከባድ የጤና ቀውስ ባለበት ጊዜ የፍች ወረቀት መጠየቅዋ የህይወቷ ውጥረት ከባድነት ያሳያል። ይላሉ ምንጮቹ።

ለብዙ ጊዜ የጋብቻ ፍች ስትጠይቅ የነበረቺው ሳባ ሃይለ ባለቤቷ ኢሳያስ ሲለምናት እና ሲያባብላት ቆይቷል።ፍቹን ካልተስማማህ ይፋ አደርገዋለሁ ስትለው፤ በሁኔታው ተደናግጦ በምስጢር የኢሳያስ ታማኞች ናቸው የሚባሉት በጀኔራል ኤፍሬም ስብሐት የሚመራ የዘመድ ወዳጅ ሽምግልና ቢሞክርም መራራ ህይወት እያሳለፈች ያለቺው ሳባ ሳትስማማ እምቢ ብላ ደርቃለች።

ከዚያም እንደገና ያ አልሳካ ሲለው፤ እራሷም ከባለቤቷ ከሜጀር ጀነራል ተኽላይ ሃብተስላሰ ኣሉታዊ የትዳር ተመኩሮ ያሳለፈቺው የተኽላይ ባለቤት የሆነቺው የ ‘ሃማደኤ’ (ኤርትራ ሴቶች ማሕበር) ሊቀመንበር የሆነቺው / ልኡል ገብረኣብ የምትመራው ታማኝ የሴቶች ሸምጋይ ቡድን ቢልክላትም የእሺታ ተስፋ አልተገኝም።

ኢሳያስ ብቻ ሳይሆን የራሱ ታማኝ ሹሟሙንቶች እና ጀኔራሎች በመጠጥ የተበከሉ እና ከትዳራቸው ውጭ ቅምጥ ሴቶች እና ልጆች የወለዱ እንደሆኑ እና ፤አንዳንዶቹም ሸካራ ጋብቻ አንዳላቸው የታወቀ ሓቅ ነው ሲል ዘጋቢው አስፍሮታል። ዜናው የተገኘው ከውስጥ  አዋቂዎች እንደሆነ እና “አለና ብውሽጢ” (በስርቱ ውስጥ ሰርገን ገብተናል) በሚል ምስጢራዊ የተቃዋሚ የመረጃ ድርጅት እንደሆነ ከዜናው እግርጌ መደምደሚያው ላይ የሚነበበው መፈክር ያሳይል (ኣለና ብውሽጢ)። ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም (ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ /ፌስ ቡክ/ብሎግ) www.ethiopiansemay.blogspot.com
getachre@aol.com

(3)
ጠቅላዩን ጤና ይስጥዎ
በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

በሥነ ምግባር የታነፅኩ - ነኝና ቅን ኢትዮጵያዊ
ጠቅላዩን ጤና ይስጥዎ - ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፡፡
ከወደቁበት ያንሳዎ - ፈጣሪ በቸርነቱ
ይፈውስዎ በአያሌው - ይዳብስዎ በምህረቱ፡፡
እርስዎ“ተማሩ” ማለት - ምህረት ነው ለእኛም ቢሆን
ከ20ዓመት መራር ኑሮ - ከጭንቅና ከሰቀቀን
የመገላገል ያህል ነው - ተስፋ ነው የእፎይታ መቁነን፡፡
ነገር ግን ክቡር ሚኒስትር - እኛን ትንሽ ቅር ያሰኘን
ዕንቆቅልሽ መሆኑ ነው - የእርስዎ መታመም ነገር፤
ለጥየቃ እንኳ ባንበቃ - ክእጃችን ምንም ባይኖረን
የእርስዎን የትልቁን ሰው - መታመም ባዕድ ይንገረን!?
እንዲህ ያለው ንፉግነት - እንዲህ ያለው መመሳጠር
ሕገ-መንግስቱን ከመናድ - በምን ይለያል ከ“ሽብር”!?
ክቡር ሚኒስትር ሐቄን ነው - እግዚአበሔር ያመልክትዎİ
በከፋ ቀን ክፋት ሰሩ - ያመኗቸው ሹሞችዎ፤
እውነት እውነት እልዎታለሁ - ይኼ ነገር ትክክል ነው?
አሁን የእርስዎ መታመም - ከወገን የሚደበቅ ነው!?
ዜናው ለዜጎች ባይተዋር የሚሆነውስ ለምን ነው!?
ይኼስ እንኳ ምንም አይደል - አሉልዎ እንጂ ጉደኞች
ወደቀ ሲሉ ተሰበረ - ታመመ ሲሉ “አርፏል” ባዮች፤
ወትሮስ ሰው የሆነ ሰው - እንዴት እረፍት ይነፈጋል?
የሥራ ሰው መድከሙ አይቀር - ምኑ ብርቅ ሆኖ ይወራል?İ
ነገር ግን ክቡር ሚኒስቴር - እኔን እጅግ ያስደነቀው
“በሐኪም ትዕዛዝ መሰረት - እረፍት ታዘዘላቸው”
ተብሎ ልክ እንደግኝት - በይፋ መነገሩ ነው፡፡
ክቡር ሆይ ልብ ያድርጉልኝ - ሥላቅ ካልሆነ በቀር
“ዕረፍት ይውሰዱ” ለማለት - ሐኪምያስፈልግ ነበር?İ
እርስዎ ባልጋ ሳይወድቁ - እንዲህ ነገሩ ሳይጠና
“እኚህ ሰው በሥራ ብዛት - እጅጉን ደክመዋልና”
“ይረፉ!” ብለን ወትውተን - ነበረ ቀድመን ከጊዜው
ከሀገር ሰው በላይ አዋቂ - ክቡር ሆይ እስቲ አሁን ማነው!?
የሆነው ሆኖ ክቡር ሆይ - አሁንም ቢሆን ይረፉ
ለብቻ ከቶ አይቻልም - ብርቱ ነው የህይወት ሠልፉ፤
እነሆ በሥነምግባር የታነፅኩ - ነኝና ቅን ኢትዮጵያዊ
ጠቅላዩን ጤና ይስጥዎ - ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፡፡
ተፃፈ ነሐሴ 08/2004 ዓ.ም
አዲስ አበባ