Tuesday, September 25, 2012

ውራጅ ፖለቲካ በኢሳት ቲቪ

Isayas Stoog Amanuel Beidemariam

ውራጅ ፖለቲካ በኢሳት ቲቪ


ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ www.ethiopiansemay.blogspot.com

በአማርኛ ቋንቋችን ‘ተጠግቶ የሚያጠቃ’ ነብስ  « ተውሳክ »  ይባላል። አረቦቹ ‘አልጀዝማ ‘ይሉታል። እንዳውም የዓረቦቹ አጠቃቀም እኛ ‘ተውሳክ’ ከምንለው በበለጠ ያብራራዋል። የተጠቂውን የሰውነት ክፍል አካል ተመስሎ በመጣበቅ ተጠቂውን ‘ቀስ’ እያለ የሚያጠቃ እንደሆነ ነው የዓረብኛው ትርጉም ተውሳኮችን በበለጠ የሚያብራራው። የሰው ተውሳኮች ደግሞ አልጀዚሞችን በጥልቅ ለመግለጽ ሲፈልጉ ‘ጃሱስ’ ይሏቸዋል፤ (በኤርትራዊያን የናቅፋ የበረሃ ቋንቋ ደግሞ (ጃንዳ/አገልጋይ) « ሰላይ » ማለት ነው።  በዚህ ቃል ብንረጋ ፤ እራሱ ሻዕቢያ እና የሻዕቢያ ሰላዮች በተቃዋሚ ድረገጾች ፕሮፓጋንዳቸውን እንዲነዙ አንዳንድ ተቃዋሚ ድረገጾች ለብዙ አመታት ሲተባበሩ መቆየታቸው ማስረጃ ማቅረብ አይቸግርም።
 ‘ኢሳት’ የተባለው በበጎ አድራጊዎች (እራሱ እንደሚነግረን ከሆነ) የሚተዳደር ጣቢያ  ጋዜጠኞች ናቸው ብሎ ያሰባሰባቸው አንዳንድ ጋዜጠኞቹ የሚነዙት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እና ክብር በሚያሳንስ መንገድ ዛሬም እየቀጠለበት ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪ ይህ ጣቢያ በጸረ ትግሬ ቅስቀሳ የታወቀው « ECADF/ድረገጽ » ወይንም Ethiopian Current Affairs የተባለው ፓል ቶክ ጋር በመተባበር  (የብዙ ኢትዮጵያዊያን ጽሑፍ እና ቃለ መጠይቅ ሕዝብ እንዳያዳምጣቸው/ እንዳያነባቸው እያገዱ) የየሻቢያ ወኪሎች እና ጃንዳዎቻቸውን የሚናገሩት እና የሚጽፉት ጸረ ኢትዮጵያ አጀንዳ ያለ ምንም ገደብ ያስተናግዳሉ።

ሰሞኑን እንዳያችሁት ሦሰት የሻዕቢያ ሰላዮች እና ወኪሎች በነዚህ “የኢትዖጵያ ተቃወሚ ድረገጸች” እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩ ድረገጸች እና ቴቪዢን ጣቢያ ሲስተናገዱ ታዝበናል። ለምሳሌ ከነዚህ  ውስጥ ሶፍያ ተስፋማርያም ፤ አማኑኤል በእደማርያም እና ተስፋየ ገብረአብ ናቸው። እነኚህ ሁለቱ ኤርትራዊያን ሶፍያ እና አማኑኤል ‘ለአለም አቀፍ ኮንቶሮባንዲስቱና ባርያ ፈንጋዩ ለኢሳያስ አፈወርቅ” ያደሩ የታወቁ “ጅንዳዎች” ናቸው።  የማንነት ፍለጋ ውስጥ  ገብተው ማንነታቸውን ማግኘት የተሳናቸው  እነዚህ  ሁለቱ “ጃንዳዎች” ሕሊናቸው በማንንት ፍለጋ ሲጋጭ  “ወጣት ኤርትራዊያን ሴቶችና ወንዶች እየታፈሱ ኢሳያስ አፈወርቅ ባዘጋጃቸው “የሻዕቢያ ጠላፊ ቡድን/ጐስታፖ” እየተጠለፉ “ጭለማ እስር ቤቶች ውስጥ” እየተቀጠቀጡ መላው አከላታቸው ‘ተልቶ እና ቆስሎ’ በሚገማው ሽታ የሚመረቅኑ “በወገኖቻቸው ስቃይ እና እምባ” የሚደሰቱ’ የአረመኔ መንጋ ቡድን አገልጋዮች ናቸው።  


ውጭ አገር ከሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ቡድኖች ብለው ራሳቸው ከሚጠሩ ከእነ “ንአምን ዘለቀ እና ግንቦት 7” ጋር በመተባበር  የሻዕቢያ ወኪል አማኑኤል ባእደማርያም የተካፈለበት’ “Ethiopia & the Horn of Africa Conferenece on Governance, Peace, Security and Sustainable Development” በሚል የመወያያ ጉዳይ  በApril 9 እስከ 11 / 2010 (አውሮጳ አቆጣጠር) አርሊንግተን ቨርጂኒያ ውስጥ ከላይ የተጠቀሱ ኢትዮጵዊያን አድርባይ ቡድኖች ከሻዕቢያ ጋር ሕብረት በመፍጠር ‘የሻዕቢያ’ አውሬነት የማናውቅ መስሏቸው ዛሬ ደግሞ  የሰውነት ባሕሪ ለማላበስ ሻዕቢያ የሰው መብትና የስነ መንግስታዊ  አስተዳደር ተምሳሌ ይመስል አማኑኤል ባእደማርያምን ከአዘጋጆቹ ጋር በመመካከር ኢትዮጵያ አገራችን መግባ፤ በነፃ አስተምራ ለዚህ ያበቃቺውን ኢትዮጵያን  በኮሎኒያሊሰትንት እየከሰሰ የዘለፈበትን ሰፊ መድረክ አንደሰጡት የሚታወስ ነው
 

ከዚህ በተጨማሪ “ሶፍያ ተስፋማሪያም” ያዘጋጀቺውን የሻዕቢያ ማንነት የማያውቁ  እንደ እርሷ የመሳሰሉት ውጭ አገር ያደጉ “የሻዕቢያ ወጣት ማሕበር በማሰሰብ ”የዓለም ሕብረተሰብ በኢሳያስ እና በነብሰገዳይ አገልጋይ ወታደራዊ አሽከሮቹ የጣለውን ማዕቀብ በመቃወም የተዘጋጀው “ሻዕቢያዊ ሰላማዊ ሰልፍ” ንአምን ዘለቀ እና መሰል ‘ጃሱሶች’ ተቃቅፈው አብረው ተስልፈው ይጨሁ እንደነበረ በሚያሳፈር ሁኔታ የተነሱት ዩቱብ ቪዲዮው ካሁን በፊት አሳይቼአችሁ እንደነበረ ይታወሳል። ተስፋየ ገብራብም በደምብ ስለምታውቁት ብዙ መዘርዘር አያሻውም።  ኢትዮጵያ ወታደር እንጂ አምላክ አያድናትም ሲል እየተሳለቀብን ቆይቶ፤ ይህ ብሎ በጻፈ እኔ በተቃወምኩት መሰሪ  ምላሱ “የኢትዖጵያ አምላክ” ትንግርታዊ ስራው ለማሳየት “የድሮ አለቃው “መለስ ዜናዊ”ን መንቅሮ ወሰደው። ተስፋየ ሻዕቢያም ምላሱ ቀርጥሞ  አምላክ እንዲያፍር አደረገው 
 «ሁለቱ የፋሺስቱ ኢሳያስ» ወኪሎች  የተለያየ ጸረ ኢትዮጵያ ክብር የሚያዋርድ ቅስቀሳ በድረገጻቸው እና በተለይ ሰሞኑን በኢሳት ቲቪና  በራዲዮን ጣቢያው ጋብዞ  ሻዕቢያዊ ተልዕኮ ሲያስተላልፉ መስማት ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እጅግ መራራ እሬት ነው።
 
ዛሬ አገራችንን በከባድ ፈተና ተወጥራ እንድትያዝ ያደረጉት የሕዝባችንን ክብር፤ታሪክ እና አንድነት ለማፍረስ  በጠላትንት የፈረጅናቸው እና የፈረጁን ኦነጎች እና ሻዕቢያዎች የመሳሰሉ ብቻ አይደሉም። በተቃዋሚነት የተሰለፉ አንዳንድ አድርባዮችም ጭምር የጠላቶቻችን ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆነው ሲያገለግሏቸው የታዘባችሁ አገር ወዳዶች እንዳላችሁ በሚደርሱኝ ደብዳቤዎች ማወቅ ችያለሁ።

ተመችቶአቸው ወደ ተቋሚው ጎራ ሰርገው በመግባት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ሴራቸውን የሚያራምዱት ተቃዋሚም እራሱ ለጊዘያዊ ጥቅሙ ሲል ከነዚህ ጸረ ኢትዮጵያ አሸባሪዎች እና ነብሰገዳይ ወሮበላ ቡድኖች ጋር በመሞዳሞድ አንዳንዱም እስከ ኤርትራ ምድር ድረስ በመሄድ ኢትዮጵያዊነቱን/ትግሬነቱን ክዶ « ኤርትራ » የሚባል ምንነቱ የማይታወቅ « ማንነት » በመፍጠር በጸረ ኢትዮጵያ ስራው የታወቀው ኢሳያስ አፈወርቂ ጽ/ቤቱ ድረስ በመሄድ አርዳታ እንዲያደርግላቸው የተማጸኑ ኢትዮጵ ውያን በጃሱስነት እያገለገሉ ለኦነግ እና ለሻዕቢያ መጠቀሚያ እየሆኑ ሕዝባችንን ለማወናበድ በግልጽ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ በሚያሳዩት ትብብር መረዳት ችለናል። ተክለሚካኤል አበበ  ወይንም « ተክሌ » እያለ ራሱን የሚጠራ በቅርቡ ወደ ኢሳት ቲቪ የተቀላቀለው የኢሳቱ ጋዜጠኛ በሚያካሂደው በጸረ ትግሬው « ኢካድ ፎረም/ካረንት አፌርስ » ድረገጹ ዛሬ የተለጠፈው ደግሞ ካናዳ ውስጥ  የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ (የትግራይ ተወላጅ) ጳጳስ፤  ኤርትራ ጠላት መንደር ውስጥ ድረስ  ሄደው « ለ21 አመት የኤርትራ ድምበር ጠባቂ » ሆነው እያገለገሉ ያሉት የተለያዩ  ሻዕቢያ ያስታጠቃቸው ‘ምስኪኖች’ ኢትዮጵያዊያን (ከዚህ ጋር የተያያዘ አሰና.ካም በተባለዉ የሻዕብያ ተቃዋሚ ራዲዮ ጣብያ ሮብዕ መጋቢት 23 ቀን 2001 ዓ.ም በፈረንጅ March 24/2009 ባስተላለፈዉ የዜና ዘገባው ኢሳያስ ያስተላለፈላቸው ትዕዛዝ በኢትዮጵያ ሰማይ ብሎግ ዝርዝር መቅረቡ ይታወሳል) ታጣቂዎች በረሃ ድረስ ሄደው ያነጋገሩበትን አስገራሚ ቪዲዮ እንደተመከታችሁ ተስፋ አለኝ።

አባ ጰውሎስ ወዲዚያው ዘልለው ኢሳያስን አነጋግረው ነበር፤ ከተቃዋሚም እኚህ ጳጳፓስ ማን እንዳሳሳታቸው አላውቅም ኢሳያሰን ሄደው አነጋግረዋል (እስረኞች ሊያስፈቱ ሄደው ካልሆነ በቀር ድርጊቱ ለታጣቂዎቹ ለጉብኝት ከሆነ አስገራሚ ነው)።  የነዚህ ምሰኪን ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በሻዕቢያ  መንደር መታገል አሳዛኝ ገጽታው ቢሆንም፤ ያሳቀኝ ነገር ግን ‘ቪዲዮው ላይ አንዳርጋቸው ጽጌን ተመልክታችሁ የዚህ ጉደኛ ጸረ አማራ ተክለሰውነት እና የሻዕቢያን ተክለሰውነት የምታውቁ ሰዎች ስታዩ እንደኔ የሳቃችሁ ሰዎች ስንት ትሆናላችሁ ? እስቲ እጃችሁን አውጡ ! ወይ አገሬ !)
ዛሬ ሁለት ጉዳዮችን እነካካለሁ። ተቃዋሚው ክፍል እና ሚዲያው በሚመለከት። ተቃዋሚውም ሆነ ሚዲያቸው (ሁሉም አይመለከትም) የሚዘባርቁት  ውሸት፤ ወገንተኝነት፤ አሳሳች ቅስቀሳም ሆነ  አገርን እና ሰንደቃላማን በሚከዳ እና በሚያዋርድ መንገድ ሲጓዙ እየታዘብን  ብንተቻቸው የጋራ ጠላታችን እንዳይጠቀምበት፤ጠላት ደስ አይበለው፤ እስቲ ዛሬስ እንታገሳቸው እያልን መተቸት የሚገባንን ትችት ጠልቀን ከመተችት የተቆጠብንበት ወቅት ብዙ ነው።
 
« ላይ ላዩን » ብቻ እየነካካን ከዛሬ ነገ ይሻላቸው ይሆን ስንል እያደሩ ቃርያ  በመሆን ‘ማአዛ’ እያጡ መኮምጠጣቸውን ቀጥለውበታል። ለድክመታቸውም ሆነ አውቀው ለሚሰሩዋቸው አስነዋሪ  ኢትዮጵያዊ የማንነት ክብር የሚያናንቅ ቅስቀሳ ሲያሰራጩ ሰምተው እንዳልሰሙ፤አንብበው እንዳላነበቡ የመቀጠሉ የይሉኝታ ባሕሪ ከእንግዲህ መቀጠል የለበትም።

በዚህ ርዕስ ተጠቅሜ ትችቴን ላነጣጥርበት የፈለግኩት ክፍል፤ እዚሁ ውጭ አገር አሜሪካ ውስጥ የሚገኝ « ኢሳት ቲቪ » ብሎ ራሱን በሚጠራ በዜና አውታር ላይ ነው።ወደ ርዕሱ ከመግባታችን በፊት ግን ስለ ሰሞኑ የወያኔ ተክለሰውነትን አንድ ብየ ወደ ዋናው ርዕስ እሻገራለሁ።
 
የመለስ ሞት ተከትሎ የመጣው “የሙት ሹሞት ወራሽ » ሁላችንም እንደገመትነው ወያኔዎች ከሗላ « ቻዕ !!! ያዓውሽ !!!« እያሉ ከሚነዷቸው አጋሰሶቻቸው ውስጥ አንዱ እንደሚሆን የታወቀ ነበር። እንደተገመተው የመለስ ዜናዊ ቦታ «በመያዝ » ከድሮ በበለጠ ለወያኔዎች ጭነት ወገቡን አለጥልጦ  በማመቻቸት ፈቃደኝነቱን ገልጾ የተቀበለው ሃይለማርያም ደሳለኝ ነው። ወያኔ ጫካ ውስጥ በነበረበት ወቅት « ደሳለኝ »  የሚባል ከባድ ጭነት የሚሸከም፤ የአህዮች አለቃ ተብሎ  “ብፃይ ደሳለኝ” በሚል ማአረግ የተሾመ  ከወያኔ ታጋዮች ጋር አብሮ  የሚጓዝ  ‘ሲቆሙ የሚቆም ፤ ሲቀመጡ የሚንጋለል፤ ጠላት ሲመጣ « በማናፋት » ምልክት የሚሰጥ፤ ስናር አህያ ነበራቸው (ይህ አህያ አስገደ ገብረስላሴ ነው በወቅቱ በ $45 ብር ገዝቶ ወያኔ ገና እግር ሲተክል ለድርጅቱ መጓጓዣ እንዲሆን ያበረከተው) ። አጋጣሚ ሆኖላቸው ወያኔዎች ዛሬም ስልጣን ላይ ከወጡ በሗላ ‘የጫካው ደሳለኝን’ የሚተኩ በርካታ « የክልል ደሳለኞችን» አፍርተዋል። ጥላሁን ገሰሰ እንዳለው በመፈንቅለ መንግሥት በመገዳደል የመጡ  እንደ « ሦስቱ አልማዞች » (ጀኔራል ተፈሪ ባንቲ፤ ኰሎኔል አጥናፉ አባተ እና ኰሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም) ሳይሆኑ ‘የብፃይ ደሳለኝን‘ ቦታ  ለመተካት ወገባቸው አለጥልጠው ለጭነት  ከታጩት «የየክልሉ ደሳለኞች »  ወስጥ  ‘ብፃይ ደሳለኝን’  የሚተካ ወያኔዎች እና የወያኔ ጀሌዎች በትግርኛ እያቆላመጡ  «ወዲ ደስ ደሳለኝ»  የሚሉት የደሳለኝ  ልጅ  ማግኘታቸው በጣም አስገራሚ አጋጣሚ ነው።
ሦስቱ አልማዞች
 አልማዝን አይቼ አልማዝን ሳያት
 ሦስተኛዋ አልማዝ ብትመጣ ድንገት 
 ሁለቱም አልማዞች ብቅ ቢሉብኝ
 ምርጫዬ ከምርጫ ተበላሸብኝ።
 ሦስቱም አልማዞች ባያቸው ባያቸው
 ይችም ያቺም አልማዝ ሁሉም አልማዝ ናቸው።
አልማዝን ከአልማዝ መምረጥ አቅቶኝ
ምክራችሁ ለግሱኝ ምርጫው ቸገረኝ።
 (የግጥሙ ደራሲ አቶ ተስፋዬ ለማ ፤ ሙዚቃውን የተጫወተው ጥላሁን ገሰሰ)
ተብሎ የተገጠመው ለካ ‘የዝንጀሮ ቆንጆ’ ምርጫ ውስጥ ተገብቶ ለሕሊና የሚያስቸግር እንደዚህ ዓይነቱ ጉደኛ  ዘመን ስላጋጠመ ነበር።  
 በጣም የሚገርመው ደግሞ በደርግ የስልጣን ምስቅልቅ  አሰራር እንዳልተገረምን ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ  አህያን ‘ብፃይ’ (ጓድ) ብሎ የሚጠራ ጉደኛ ጉጅለ ወደ ስልጣን ወጥቶ የአህዮች መንጋን አሰባስቦ  ኢትዮጵያን ምስቅልቅሏን ሲያወጣት፤የታወቀው ድምጸ መረዋው ጥላሁን ገሰሰ « ዘንድሮ » የሚለው ዜማውን እንድናስታውስ አድርጐናል።
 ዘንድሮ
 «በዚያኛው ተገርመን ብዙ ሳንቆይ
  የዚህኛው መባስ አያስቅም ወይ ?
  ይኸ ሁሉ ነገር ስንት ዘመን ኖሮ
          በጣም ያስገርማል ጉድ አየን ዘንድሮ»
እንዲህ ያሉ የኪነት ባለሞያ  ሰዎች  ነበሩን። አሁን ያሉት « አጋሰስ አዝማሪዎች እና ጋዜጠኞች»  ከነዚያ ደፋሮች ጋር ስናወዳድር  እነዚያ ድንቅ ከያኒዎች በተጠሩበት ሙያ መጥራት  በጣም  ይቀፋል።
በዛው ቆራጥ ትውልድ ያለፍን ቆፍጣና ትውልዶች የዛሬዎቹ ተቃዋሚዎች፤ከያኒው ጋዜጠኛው….. (ሁሉም እንኳ ባይሆኑ) አብዛኛዎቹ በዚህ ፈታኝ ወቅት ፈተናውን ማለፍ አቅቷቸው ራሳቸውን በአጓጉል ትንተናዎች ሲሸፋፈኑ ማየት እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ነው።  የጣሊያን አስተዳደር ፖሊሲ (ሊገ ኦረጋኒካ/መሠረታዊ ሕግ/በሙሶኒ አገላለጽ) ተግባራዊ በማድረግ በቋንቋ/በጐሳ ከልሎ እያንዳንዱ የራሱ ብሔራዊ « ባንዴራ » እንዲኖሮው ያደረገ «ግልገል ፋሺስቱ »  መለስ ዜናዊ ሞተ ሲባል ተቃዋሚ ነኝ የሚለውም ሆነ በአጋሰስ ዓለም የተሰለፈው የኪነት ሞያተኛ ሁሉ ግማሹ ልቡ በሐዘን ሲታጠፍ፤ግማሹ ደግሞ  በፍቅር ሰግጣ ይዛው የነበረቺውን ፍቅረኛው  ድንገት ገፍትራ እንደተለየቺው እስከሚመስለው ድረስ የመለስ ሞት ሰምቶ « ልቡ » ባዶ ክፍል ሆኖበት « ጭር » ባለ የናፍቆት ዓለም ተውጦ ሲተክዝ ፤ ለሐዘኑ መግለጫ ቃላት እስኪያጥራቸው ሐረግ እና ቃላት ፍለጋ ዓይኖቻቸው  ሲያማትሩ  አስተውለን የኪነት ባለሞያዎች የታዘብንበት የሚገርም  ዘመን ደርሰናል። የዘመኑ ጉደኛነት (ዊርድ ኢፖች/ ይሉታል ፈረንጆቹ) ለመግለጽ ቃላት ሊገልጸው አይችልም። የሚመቸው የጥላሁን ዜማ ነው።
 «በዚያኛው ተገርመን ብዙ ሳንቆይ
የዚህኛው መባስ አያስቅም ወይ?»
 
በዚያኛዎቹ በመለስ ዜናዊ ሰበካ የተጠለፉ ምስኪን የኪነት ሰዎች እና ጋዜጠኞች ልቅሶ እና አሳፋሪ « ዋይታቸው » ተገርመን ብዙ ሳንቆይ፡ በተቃዋሚው ጎራ የቆሙት የኛ ብለን የምንላቸው የዚህኛው ጎራ የኪነት እና የፖለቲካ ሰዎች በፋሺስት ግልገል መለየት ሰመመኑ ብሶባቸው ከመገረም አልፈን፤ሕዝብን ከማሳወቅ አልፈን ምን እንበል ? እውነትም ይኸ ሁሉ ነገር ስንት ዘመን ኖሮ፤ በጣም ያስገርማል ጉድ አየን ዘንድሮ» የሚለው  ዜማ ለዛኛው ዘመን ብቻ ሳይሆን ለዚህኛው ዘመንም ገላጭ ስንኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በየአዳራሹ ላንቃው እስኪታይ ድረስ ስሜተኛውን ታዳሚ እያስጨበጨበ የሚለፈልፈው « ፍየል ተቃዋሚ » በዚህ ጉድ ተይዞ ሲጋለጥ ማየት ‘ተቃዋሚ ነው ማለት አያስደፍርም’ ። በጣም የሚገርመው ግን ይህ አሳፋሪ ሞራል በውስጣቸው ዘንድ ሲከሰት እርስ በርሳቸው በሚዲያቸው አይወቃቀሱም። የዜና አውታሮቻቸው በወያኔ አልቃሽ ደጋፊዎች ብቻ ሲተቹ ይደመጣሉ። ተቃዋሚውም በወገንተኛነት/ቡድንተኛነት (ጎሰኛ) በሽታ የተለከፈ መሆኑንም ማስረጃ ነው።
የዜና እና የሐተታ ድረገጽና ራዲዮን  አገልጋዮችስ ? ሻዕቢያ የወያኔ እንጂ የኢትዮጵ  ጠላት አይደለም ብለው በመደምደም  ከሻዕቢያ ጋር እየተሞዳሞዱ ሳያፍሩ በግልጽ የሕብረት አጀንዳቸውን አሳትውቀዋል።እስኪ እንፈትሻቸው። ከላይ በመግቢያዬ የጠቀስኳቸው እነዚህ ቡድኖች/ግለሰዎች ከሻዕቢያ ጋር  የተለያዩ ግንኙነታቸውን እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ ሰሞኑን ደግሞ በጣም አድርጎ ያስገረመኝ ያበሳጨኝ እና ያወከኝ ነገር ላውጋችሁ። ኢሳት የሚባል « የስእለ ድምፅ » የዜና አውታር (ተቃዋሚ እንዳልለው እራሱ « ገለልተኛ የዜና አውታር ነኝ ስለሚል ፤ « የተቃወሚዎች የዜና አውታር « ብየ ልጠራው አልችልም እና «ገለልተኛ የዜና አውታር ልበለው»። ሆኖም ይህ የዜና አውታር እርሱ እንደሚቀደደው « ገለልተኛ ነው ? » መልሱ በኔ እይታ « ወገንተኛ ነው »። ወገንተኛነቱ ለማን ነው ? የሚያናፋው ቱልቱላ በጥንቃቄ የተከታተልን ሰዎች የታዘብነው ነገር ቢኖር ብዙ ጊዜ ለኢትዮጵያ ጠላቶች ፕሮፓጋንዳ ስራ ሲሰራ በተጨባጭ አይተናልና ይህ ጣቢያ ‘ውሸታም፤ አድርባይ እና ለጊዜአዊ ጥቅም ብሎ የጠላት ፕሮፓጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጀሮ የሚያደርስ  ጣቢያ  ስለሆነ አገር ወዳዶች ጣቢያው አደብ እንዲገዛ « ሀ » በሉት።
 
 ተክለሚካኤል አበበ/ተክሌ የተባለ  የኢሳት ባልደረባ; ዓለም ያወቀው የሻዕቢያው ወረበላ መንግስት  አጨብጫቢት ሶፊያ ተስፋማርያምን በመጋበዝ የፕሮፓጋንዳ ስርጭት ማስተላለፉ ብቻ ሳይወሰን አዘጋጁም ከእንግዳው ጋር በመወገን የኢትዮጵያን ክብር እና ሉአላዊ መንደርን ለሻዕቢያ በሚወግን መልኩ ድጋፍ በመስጠት የአገራችንን ሉአላዊነትን የሚዳፈር ከወያኔ ቱልቱላ የማይለይ ለኤርትራዊያኖቹ የሚደግፍ አጉዳፊ ቅስቀሳ አድርጓል። ይህንን ለማዳመጥ ESAT Insight Mrs Sophia Tesfamariam 05 September
2012  (http://youtu.be/J2Yyj1GsZ7Q
አድምጡ። ዝግጅቱ ስካሁን ድረስ 30 ሺሕ ሕዝብ አድምጦታል። አዘጋጁ እና ጣቢያው ምን አንድናገኝ ተብሎ ይህች በወንድሞእና እህቶ ኤርትራዊያን ስቃይ የምትመረቅን የኢሳያስ  ጃንዳ ወደ ጣቢያው ጋብዞ እንዳመጣት ባይገባኝም፤ ኤርትራ ድረስ እየሄደ እና እየመጣ ተከታቹን የሚያታልለው የግንቦት 7ቱ አንዳርጋቸው ጽጌ ፤ በበርሃኑ ነጋ አማካይነት ጣቢያው  የሻቢያ ወዳጅነቱን ለማሳየት ያዘጋጀው መጥፎ/treasenous መድረክ ነው።
 
ብርሃኑ ነጋ የሚጨፍርበት ወደ 3000 የሚጠጉ ‘ምሰኪኖች’  ኢትዮጵያዊያን በየወሩ $20.00 እያዋጡ ያካሂዱታል የሚባለው ይህ ጣቢያ ያቀፋቸው ሰዎች (ሁሉንም አይመለከትም- አንዳንዶቹን ነው) ለጊዜአዊ ጥቅም ሲሉ የአገራቸው እና የሕዝባቸውን አንድነት ቁም ነገር  ሳያስገቡ በጠላቶች  ፕሮፓጋንዳ  ተጠምደው ጠላቶች የሚነዙትን ቅስቀሳ ተቀባይ እንዲኖሮው ወደ ሕዝባችን በአጎብዳጅነት ጸባይ ያስተላልፋሉ (የ ኦነግን፤የ ሻዕቢያን፤ ኦጋዴን፤…..ውሸቶቻቸውን፤ባንዴሮቻቸውን….እያውለበለቡላቸው በስርጭቱ  ይደሰኩራሉ/ይተባበሯቸዋል)። አጐብዳጆቹ  ለአጎብዳጅነታቸው ሽፋን ሲሰጡ የሚሰጡት መልስ ”ጠላቶቻችን ናቸው አንበላቸው፤ እናስጠጋቸው፤ የጠላትን ቅስቀሳ በፕሮቮክ መልክ ደግፎ ማስተላለፍ ነውር የለውም፤…"  በማለት በፖለቲካ የሽፋን መጠሪያ ስሙ “ፕሮቨካቲቭ  ፖለቲካን መፍራት የለብንም” ይላሉ።

 በመሰረቱ  እንዲህ ያለ የሉአላዊ ክብርን በፕሮቮካቲቭነት ስራ ውስጥ የሚጠመዱ ሰዎች እና ቡድኖች/የዜና አውታሮች የቅጥረኛነት እና አጎብዳጅነት  እንግሊዞች “ኮላቦራቶር” የሚሉት ባሕሪ ነው። ኮላቦራቶርም መብት ነው የሚሉ አሉ። ልክ የኢሳቱ “ፖለቲከኛ/አክቲቪሰት”  እና “ተራቢው” ‘ለመለስ ዜናዊ ለምን አዘንክ ተብሎ ሲጠየቅ፤ ለምን አዘንክ ብለው ቅሬታና/እግዚኦታ ያስሰሙ ክፍሎች ልነግራቸው የምፈልገው ሌሎች የማልቀስ መብታቸው እንደሆነ ሁሉ እኔም ካለቀሱት ጋር አብሬ የማዘን መብቴ የተጠበቀ ነው” ምን ትሆኑ (የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ!) እንዳለን ሁሉ (ESAT Tamagne Beyene September 2012 http://youtu.be/xxE-v_t-Z-0 ) እና ሌሎቹ ባለመብቶችም “ምንም ቢሆን እንጀራ ቢያምራችሁም በየሱቁ እየሄዳችሁ የወያኔ እንጀራ አትግዙ!” እያሉ  በራዲዮናቸው የሚቀሰቅሱ፤ ነገር ግን“አንድ ሚሊዪን ተኩል ብር የሚፈጅ ያማረ ቪላ አዲስ አበባ ውስጥ ማስራት አማረኝ” ብለው አዲስ አበባ ውስጥ የናጠጠ ቪላ ወኪሎቻቸውን “በወያኔ” አየር መንገድ (በጀርመን በጣሊያን በዓረብ አየር መንገድ እንጂ በወያኔ አየር መንገድ ወደ አገርቤት እንዳትጓዙ ብለው ቢቀሰቅሱም) እየተጓዙ ቪላ ማስገንባትም መብታችን ነው እያሉ እንደሚሉን ሁሉ  “ኮላቦራቶሮችም”  የጠላትን ወኪሎች  ወደ መድረካችን ስንጋብዝ “ኩራት” ይሰማናል ማለትም “መብታችን” ነው ይላሉ። ('ወይለየኸ! ለካ ተሸሚምና ኢና' አለ ትግሬ/ እንዴ.. እንዴ! ይህ ሁሉ የመብት ጥበቃ ሲካሄድ ለካ ጀሮና ዓይናችን ተሸፍኖ ነበር፤ ወሬውም የለንም! ማለት ነው)።”እውነት እውነት እላችሗለሁ” አለ እየሱስ ክርስቶስ። ለካ ይሄ መብት የሚባል የማይታይ “ዓንደ ረቢ/ጐስት” ሁሉንም በየፈርጁ የሚያገለግል እምቢታ የማያውቅ ሁለገብ ዘበኛ ነው። እሺ ይሁን! ለመሆኑ “ኮላቦራቶር/ተባባሪ” ምንድነው?
 
ከሳንሆዘ’ ሲሰራጭ የነበረው ተወዳጁ የኢጵያዊያኖች “ኢታር/ER” መጽሄት አጎብዳጅነት/አባሪ ተባባሪ ማለት ‘የዘቀጠ ፖለቲካ አድርባይነት ማለት ነው’ ይላል። “Collaborationism is the worst form of political opportunism in which the collaborator/s willingly participate in the destruction of their country….” Collaborators can only aspired can become politically sub servant foot soldiers for the enemy  bent on annihilating Ethiopia, and yet because of their block aspirations, their unscrupulous morals and their convoluted conscience, they will do anything to achieve  their fifteen minutes of fame.” ይላል።
  ይህ ትንተና ሥልጣን ካለው ሃይለኛ ቡድን ጋር  በመሞዳመድ ጊዜያዊ ጥቅም ለማካበት በአድርባይ የሚያታየው ባህሪ ነው። በሌላ መልኩ ግን አንድ ደካማ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅት ወይንም ግለሰብ ደካማ አቅም ኖሮት ለማጥቃት የሚፈልገው ቡድን ማጥቃት ሳይችል በሚቀርበት ወቅት ከሱ የበለጠ ጉልበት ያለው ሌላ ተቀናቃኝ ሃይል በመፈለግ (የጠላቴ ጠላት ወዳጄ/ከሰይጣንም/ከጠላትም ጋር ቢሆን በሚል የኮሚኒስቶች ስልት እነ አርበኞች ግምባር እና ግንቦት 7….ከሻዕቢያ ጋር እንደሚሞዳሞዱት ዓይነት) ጥገኛ ሆኖ አገሪቷ ያስቀመጠቻቸው መሰረታዊ መርሆዎች ለድርድር በማቅረብ፤ (ባያቀርብም) የተጠጋበትን ቡድን መርሆ እና ቅስቀሳ በማራገብ ወዶም/ሳይወድም ወደ አገልጋይነት በመለወጥ፤ አገሬ ብሎ ወደ እሚጠራት አገር የሚኖር ሕዝብ ስለ እዛው ቡድን (ጠላት) በጎ ባሕሪ ወይንም የተለያዩ አጀንዳ የያዙ የሰበካ ዘመቻ መልእክቶችን በማስተላለፍ በቀጥታ (እራሱ ጥገኛው) ወይንም በተዘዋዋሪ የተጠጋበትን የዛው አገር/ቡድን ጠላት “አፈቀላጤ” በመጋበዝ ያለ አንዳች “ቁጥጥር”/ቻለንጅ ወደ አገሩ (ኢትዮጵያ) በማስተላለፍ በእኩይ ስራ ውስጥ ይሳተፍል።
የህች ማንነቷ ከድታ ጣሊያን የሰጣትን ‘ኤርትራ’ በሚል የዜግነት መጠሪያ ተቀብላ “ኤርትራዊት በሉኝ” የምትል የዞረባት ፍጡር፤ ምስኪን ኢትዮጵያዊያን የፈረንጅ ወለል እየጠረጉ ባጠራቀሙት የገንዘብ መዋጮ በሚካሄደው በኢሳት ቲቪ ተገኝታ ስትነሰንሰው የነበረው ጸረ ኢትዮጵያ የውሸት ክምር ‘ማረም ቀርቶ’ የክፍለ ጊዜው ዋና አስተናጋጅ የሆነው “ተክለሚካኤል(ተክሌ)አበበ የተባለው “ጸረ አማራ” (መረጃው ወደ ታች አቀርባለሁ) የቅስቀሳዋ “ተባባሪ’ በመሆን የሻዕቢያ እምባ ጠራጊ እና አናፋሽ መሆኑን ‘የኢሳትን ግዴለሽነትና ላልበሰሉ ጋዜጠኞች መድረክ መለገሱ አስገራሚ ነው።’
ይህች የሻዕቢያ ‘ገለባ” ዘሯን ለማታውቁ ሰዎች ሁሉ የማን ዘር መሆኗን ብነግራችሁ በጣም ታዝናላችሁ። ይች ሴት የጀግናው ኢትዮጵያዊው የሓማሴኑ ተወላጅ “የዘርአይ ደረስ” የቅርብ ስጋ (የእናትዋ አባት እና ዘርአይ ደረስ ወንድማማቾች ናቸው) ነች። አማርኛውን ስተረጉም ተሳስቼ እንዳልሆን በእንግሊዚኛው ትርጉም ዘርአይ ደረስ “ግራንድ አንክል” ማለት ነው።ከዚያ ኢትዮጵያዊ የጀግና ሐረግ የተፈጠረች “ዘርና አገር አሰዳቢ” ግለሰብ ነች። ዘርአይ ደረስ ማን መሆኑን እና ለኢትዮጵያዊነቱ ቀናኢነት እና በፋሺስቶች ላይ ምን ዓይነት አቋም እንደነበረው ታላላቅ ምሁራን እና ሮማ ውስጥ በአካል አግኝተው ያነጋገሩት ኢትዮጵያዊያን የዘገቧቸው የታሪክ ምስክርነት ያነበባችሁ ሰዎች ስታገናዝቡ፤ ዛሬ “የፋሺስት ባሕሪ የተላበሰው፤ ባሕረ ምድር/ኤርራን ወደ ወታደራዊ መደብር በመለወጥ የኤርትራ ወጣቶች በባሪያ ስርዓተ ማሕበር “አፍኖ” በመያዝ ስደት፤እስራት፤ ጦርነት፤ ሞትና ሽብር በመዳረግ አዲስ የስቃይ ህይወት የፈጠረ ወንጀለኛው የኢሳያስ አፈወርቂ ስርዓት ተጣበቂ ሆና ስትቀርብ በጣም አሳዛኝ ክስተት ነው። ያውም “ከ21 አመት” ነፃነትም በሗላ መሰረታዊ የተባሉት እንደ መብራትና ውሃ ለሕዝቡ መለገስ እቅቶት በፈረቃ የሚከፋፈልበት ጨለማ አገር!!!!!
ታዲያ ለይህች ሴት ነች ተክለሚካኤል አበበ በመደነቅ የሽፍቶች አገርና የራሷን ተቃዋሚዎች አንድ ያላደረገች; ኢሳየስ 7 ገጠራማ አውራጃዎች ማስተዳደር አቅቶት የሌሊት መብራት እንኳ የሌላት ጭለማ “አገር”፤ ለኢትዮጵያዊያን እርዳታ እንድትለግሰልን ተክሌ ያለ ሐፍረት የጠየቃት። ያውም ከሷ ጋር መነጋገሩ ኩራት ተሰምቶት “በኢሳት ቴ/ቪዥን አንችን ለቃለ መጠይቅ በማቅረቤ ከፍተኛ ኩራትና ክብር ይሰማኛል” በማለት ከሻዕቢያ አገልጋይ ጋር መነጋጋሩ “ክብር” ተሰምቶት፤ወጣቱ ከድሰታው የተነሳ ከሻዕቢያ ማሕበረሰብ ጋር በመተባበር ለወደፊቱ የጭፈራ “ፈስቲቫል” እንደሚያዘጋጁ ምኞቱን እና ፍላጎቱንም ቃል ገብቶላታል።
ይህ ተክሌ የተባለው ወጣት ማን ነው? ካለይ እንደገለጽኩት (ካረንት አፌርስ ዋና አዘጋጅና
የኢሳት አዲስ ጋዜጠኛ ከመሆኑ ሌላ) ግለሰብ በተለያዩ ወቅቶች የሚጽፋቸውና በየራዲዮኑና/ፓልቶክ ሰለ የኢትዮጵያ ሉኣላዊነት የሚጻረር ቅስቀሳዎቹን በአገር ወዳዶች መፈተሽ አስፈላጊ ነው። ኦፖርቱኒዝም/አጎብዳጅነት (ኮላቦራቲዝም) በትከክለኛ ትርጉሙ ኢሳት ውስጥ በዚህ ወጣት ተንጸባረቋል።እኛ ሻዕቢያን የሕዝባችን ጠላት; ወገኖቻችንን የጨፈጨፈ ብለን ስንፈርጅ እነ ተክሌ እና ኢሳት ግን “ከሻዕቢያ ጋር የጋራ ፈስቲቫል” ለማዘጋጀት ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ይህ ልጅ ኢሳት ውስጥ ተጠግቶ ለሻዕቢያ እና ገንጣይ ቡድኖች ማቀንቀኑ ሰንደቃላማን ማንኳሰሱ ………ወዘተ…..ወዘተ ስንመለከት ብዙ ታሪክ ሸፋን ስለሚያስፈልገው ከሶፊያ ተስፋማርያም ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቁን አንብባችሁ ፍረዱ::  ይህ ልጅ ከላይ እስቀድሜ “በጸረ አማራነት” ለምን አንደፈረጅኩት እና ማን እንደሆነ አሁን በአፕሪል 2011 ዓ.ም (በአውሮጳ ዘመን አቆጣጠር) (ቅንጅት ስዊዘርላን ከተባለው በቅርቡ የፋሺስቱ ወያኔው መሪ የመለስ ዜናዊ አፈቀላጤ ወደ መሆን የተለወጠው ፓል ቶክ ክፍል)እና “ዓድዋ ለአረጋሽ አዳነ” በሚል ለወያኔዋ አረጋሽ  አዳነ ነፃ እንድታወጣን በምትመረጥበት አውራጃ የሚረዳት የገንዘብ እርዳታ እናድርግላት በማለት የጻፈውን እና ከአንደበቱ የተገኘ ጸረ አማራ ንግግሩን አስነብቤአችሁ ልደምድም።
የወጣት ተክለሚካኤል አበበ እና የወያነ ወይንም ትግራይ ጠባብ ብሔረተኞች አጀንዳ እና ቅስቀሳ እንዴት እንደሚመሳሰሉ ለማነጻጸር እንዲመቻችሁ፤ መጀመሪያ በ60ዎቹ አካባቢ የትግራይ ብሔረተኞች ሲቀሰቅሱት የነበረው የአማራ ስም ጥላቻ ምን ይሉ እንደነበረ በትግራውያን ልጀምር እና ከዚያ የተክሌን አባባል እወስዳችሗለሁ።
"...የትግሬ ጠቅላይ ግዛት ትምህርት ቤት መምህራን እና ተማሪዎች የትግራይን ሕዝብ ብሔራዊ ማንነት የሸዋ አማራ ገዢ መደቦች አካሄድ እና የአገሪቱን አጠቃላይ ጭቆና ለሕዝቡ በማሳወቅ እና ብሔረተኝነትን በማቀንቀን ዋነኛ ተዋናዮች ነበሩ። በተለይ ትምሕርት ቤት አካባቢ የባህል ክበባትን በማቋቋም ተማሪዎች እና አልፎ አልፎ ወላጆች ስለ ትግራይ ብሔረተኝነት ስለ ሸዋ አማራ ልሂቃን አካሄድና አድልዎ በትግርኛ መናገርና መጻፍ ምን ያህል የሕዝቡን ማንነት እንደሚያጠናክር እና እንደማያሳፍር...ወዘተ ይቀሰቅሱ ነበር። የአማርኛ ስም ለልጆች መሰየም እና መጥራት መቅረት እንዳለበት ሕዝቡን እያዋዙ ይቀሰቅሱ ነበር።" (ጋላህቲ ሠጊ ገጽ 42)(ምንጭ የወያኔ ገበና ማህደር- ደራሲ ጌታቸው ረዳ መስከረም 1/ 2004 ዓ.ም)
ክሌ ደግሞ ያንኑን መፈክር በመድገም እንዲህ ይላል፡
“ግዛቸው፤ሃይላቸው፤ጌታቸው፤አለባቸው....የሚሉ አማራ ቀመስ ስሞች  ከአመራር አስወግደን ይልቁንስ “አብርሃ ፤አጽብሃ፤ነመራ፤መረራ፤ነጋሶ…..” የሚሉ ስሞችን የያዙ ወደ አማራር መተካትና ማምጣት አለብን”  (ተክለሚካል አበበ - የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቦረድ ሰብሳቢ የነበረ ዛሬ በሰሜን ሜሪካ ኢሳት በተባለው ቲቪ ጋዜጠኛ፡ (የተናገረበት ቦታ እና ወቅት ኤፕሪል 2011 ቅንጅት ኔዘርላድ ፓልቶክ ቃለ መጠይቅ ከተደረገለት የተገኘ)።
ሌሎች የተክለሚካል አበበ  (ርዕሶቹ) ጽሑፎቹስ ምን ይላሉ?
(1)  “ የተሸነፍነው በትግራይ ነው፤ የምንድነውም በትግራይ ነው። አረጋሽ  ለአድዋ ፤አድዋ ለአረጋሽ….”(ዣንጥራር ተክሌ (ከቫንኩቨር ካናዳ)
(2) የምንድነው በኤርትራ በቀር የኢትዮጵያ መዳን በማንም የለም! (ኢትየጵያን የምታድናት ኤርትራ እንጂ ኢትዮጵያ እራሷን የመዳን አቅም የላትም)
(3) አረጋሽ አዳነ ጣይቱ ቡጡልን ብትሆንስ? ሚያዚያ 2000 ዓ.ም ምንጭ ኢትዮ ፎረም) ሰፋ ባለ ግልጽ ጽሑፉ እንዲህ ሲል ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልእክቱን እንዲህ ያስተላልፋል:

    “የዛሬዋ መቶ አስራ አራት አመት አካባቢ ምኒሊክ ጣሊያንና ባንዳውን ሲረቱ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ቡጡልም ጦር እየመሩ የድሉ ተካፋይ ነበሩ። እነሆ ዛሬም ታሪክ ራሱን ሊደግም ነው። ያኔ በታንክ ነበር አሁን ግን አረጋሽ በሾኬ ብላለች። ታንኩንም ቢሆን ገና በሃያዎቹ እያለች እኩያዎቿ ከተማ ውስጥ ሲዳሩ እሷ በጫካ አስኪዳዋለች። (አረጋሽን) ያልደገፈና ለብሩ የሰሰተ እጁንም አፉንም ይሰብስብ”። በማለት አረጋሽ ዳግማዊት ጣይቱ ለኢትዮጵያ መጥታለች እልል!! እልል!!!! በሉ ብሎናል።
ዛሬም ይህ የኢሳት ወጣት ጋዜጠኛ 'የኢሳያስ ተቃዋሚ ኤርትራዊያን  ቡድኖች “የጭራቆች ፈስቲቫል” ብለው በሚጠሩት በየአመቱ ሲዘጋጅ እየሄደ በሻዕቢያ ፈስቲቫል በመገኘቱ ደስታውን በመግለጽ የሻዕቢያዋ “ሶፍያ ተስፋማርያም” እና “አማኑኤል በእደማርያም” ለተባሉ የኢሳያስ አረመኔ ግፍ ደጋፊዎች እያጎበደደ፤ ኢትዮጵያ እራሷ የመዳን አቅም ስሌላት ኤርትራ የምትመጸውተንን የመዳኛችንን ምክር ጠይቋታል።

እንግዲህ ወዲህ እንደ እነ ተክሌ የመሳሰሉ በአፍቃሬ  ሻዕቢያ ወኪሎች የተላለፈላችሁ ምክር በተለይ ደግሞ የአማርኛ ስም ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችም ሆናችሁ ሌሎች ወደ መሪነት ወይንም ወደ መንግስታዊ ስለጣን እና ስራ ፍላጋ የምትፈልጉ  ወጣቶች ካላችሁ በቅድሚያ ስማችሁ “ጐይተኦም፤ አብርሃ ፤ሐጎስ፤መረራ፤ጊዳዳ፤ፈሪሳ፤ደነቹ፤ፈይሳ……ወዘተ..” ወደ መሳሰሉት ስሞች ተሎ ካልቀየራችሁ የመምረጥ እና የመመረጥ ወይንም የመምራት መብታችሁ “በጠባብ ብሔረተኞች” ኮታ እንደሚታገድ  ካሁኑኑ እንድታውቁት የድሮ የአዲስ አበባ ተማሪዎች ማሕበር መሪ የነበረው የዛሬው የኢሳት ጋዜጠኛ “ወጣት ተክለሚካል አበበ” አስታወቆአችሓል። አንለውጥም የምትሉ ካላችሁም ዓረብ አገር ሄዳችሁ “ስዒድ፤ጃዋር.ዓሊ፤ሙስጦፋ…” የሚለው የስም የለውጥ ግዳጅም ስለማይቀርባችሁ፤ መቀየር መቀየሩ ላይቀር እዛው አገራችሁ ባገራችሁ ልጆች ስም ወደ አብርሃ፤አጽብሃ እና ፈሪሳ ጊዳዳ እና ደነቹ ወደ ሚለው ቀይሩ። አማራ እና የአማራ ስም ካሁን ወዲህ “አይፈቀድም” ብሎ ወያኔ እንዳወጀው፤ በአባቴ የኦሮሞ ደም አለኝ የሚለን ተክሌ በሚመራት የወደፊቷ ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወዲህ ቦታ አይኖራችሁም።ውራጅ ፖለቲካ አገሩን አጥለቅልቆታልና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ እዘኑ።የወያኔ አማርኛ እና አማራ ስም መጥላት አንዳይበቃን አነኚህ አዲስ መጤ ፖለቲከኞች በስማችን እንዲህ ሲያሴሩብን አይገርምም? አሁን አሁን በነዚህ ጅላጅል ተቃዋሚዎች እና ጎሰኛ ቡድኖች ፖለቲካው ተስፋ እያስቆረጠኝ ስለሄደ ሕሊናየ በግድ ነው እየነዳሁ እየመራሁት ያለሁት። በጣም ይገርማል። በነኚያ ስንገረም እነኚህ ደገሙን።
«በዚያኛው ተገርመን ብዙ ሳንቆይ
የዚህኛው መባስ አያስቅም ወይ ?
ይኸ ሁሉ ነገር ስንት ዘመን ኖሮ
በጣም ያስገርማል ጉድ አየን ዘንድሮ»
ተብሎ የተገጠመው ለ ለዋዛ አልነበረም።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)www.ethiopiansemay.blogspot.com

Sunday, September 9, 2012

በመለስ ሞት ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!

                ለተወሰኑ
ደቂቃዎች ሰውነቴን መቆጣጠር አቃተኝ!
 
በመለስ ሞት  ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!ታቸው-ረዳ  (Ethiopian Semay) ዲክታተሮች-ንቅላትን የመቆጣጠር ሃይላቸው በጣም የላቀ ነው።የከያያኖቹ ቁንጮ ታማኝ በየነ በመለስ ሞት የተሰማው የስቶክሆልም ሲንድሮም ድንጋጤ እና እሱ ሳይታወቀው ከሕሊናው ውስጥ ገብቶ የተለማመደው፡አንዳች ነገር ከሕሊናው የተነጠቀ ነገር የመሰለው የተሰማው “ባዶነት፡  በሚገርም ሁኔታ በመራር ሐዘን እንዲህ ሲል ስሜቱን ሳይደብቅ ገልጿል::


 ታማኝ እንዲህ ላይል::
"አውነቴን ነው የምለው ደነገጥኩ፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰውነቴን መቆጣጠር አቃተኝ።(ከው ብየ) አዘንኩ። አውነት እንዴት እንደምገልጸው አላውቅም፤በጣም ደነገጥኩ።አዘንኩ።ምንም ይሁን ምንም ባደግንበት ሠፈርም ይሁን “የለመድነውን ነገር ስናጣ” የተሰማኝ ስሜት አለ።ለሃያ አንድ ዐመት በእኚህ ሰውየ ዙርያ ብዙ ነገር አይቻለሁ፤አድምጫለሁ፤ብዙ ብዙ ነገር ….እና….በጣም ለምጃቸዋለሁ፡ እና ሞቱ ሲባል የተሰማኝ ነገር ቀላል አይደለም።…..የተሰማኝ ስሜት ሐዘን ነበር። “ ታማኝ በየነ (ስለ ጸረ አማራው ጐሰኛው መለስ ዜናዊ ሞት ከኢሳት ጋር የደረገው ቃለ መጠይቅ)፡
እንግዲህ ልብ በሉ። ያልኩዋችሁ የስቶክሆልም ሲንድሮም ምልክቱ ታማኝ የሚከተለውን ንግግሩ በጥንቃቄ ብትመረምሯቸው በሕሊናው የተያዘ ነገር እና ስሜት እንዲህ የገለጻትን ነጥብ እስቲ ልድገምላችሁ እና የሲንድረሙ ክብደት ምርምሩት። ታማኝ በየነ  እንዲህ ይላል፦  
““የለመድነውን ነገር ስናጣ” የተሰማኝ ስሜት አለ።ለሃያ አንድ ዐመት በእኚህ ሰውየ ዙርያ ብዙ ነገር አይቻለሁ፤አድምጫለሁ፤ብዙ ብዙ ነገር ….እና….በጣም ለምጃቸዋለሁ፡ እና ሞቱ ሲባል የተሰማኝ ነገር ቀላል አይደለም።…..የተሰማኝ ስሜት ሐዘን ነበር።” ብሏል ታማኝ።
ታማኝ የለመደውን የማጣት ስሜት “ከጨቋኝ መሪ ጋር መጨቃጨቅ/ክርክር የቃላት መወራወር ሱስ ድንገት የተለከሰተ የማጣት  ባዶነት” (ልክ ልደቱ ዓያሌው እንደገለጸው የተሰማውን የማጣት ባዶነት ስሜት ማለት ነው) :: ታማኝ በዚሁ ቃለ መጠይቁ ቀጠል ያደርግና “ሕዝቡ ተገድዶ/ ነው ያዘነው/ያለቀሰው” ሲል ታማኝ ከተጠናወተው የስቶክሆልም ሲንድሮም/ ልክፍት ዲናያሉን በመታገል  ወደ “ዲፌንሲቭ”/ወደ መክላከያ መስመር በማፈግፈግ ወድያውኑ የተጣመመው ስሜት ወደ ሌሎቹ አዛኞች/አልቃሾች በማላከክ/በመወርወር ከሕሊናው ሲታገል ታደምጡታላችሁ።

ስትመለከቱ የስቶክሆልም ሲንድረም ደምበኛው ምልክት ከታማኝ ጭንቅላት አነጋጋር በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁ። ሰዎች ከዲክታተሮች ለብዙ ጊዜ ሲኖሩ ይለማመዷቸዋል። እነሱ ሲለዩ ልክ ታማኝ እንደተሰማው “ከውስጣቸው ባዶነት ይሰማቸዋል”” ሲደበድባት የነበረው ፍቅረኛዋ ድንገት ሲለያት እያደረ “ባዶነት” ይሰማታል። ታማኝም የዚህ ሲንድሮም መገለጫ “ስቶክ” (ከጥቅሎቹ አንዱ ነው)።

 


እባካችሁን፤ ላሳስባችሁ የምፈልገው ልታተኩሩበት የሚገባ ነገር፤ አንዳንድ ምሁራኖች ለምን ተቃዋሚ መሪዎች ሐዘኔታቸው በመራራ ሐዘን እንደገለጹ መላምታቸው ሲነግሩን “የፐለቲካ ሰዎች ስለሆዩ፤ ዲፕሎማቲክ ቋንቋ ወይንም ለሽፋን/ዘዴ መጠቀማቸው ነው” ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ በጣም የተሳሳተ መላምት በአውራ ገነኖች እና በሕዝብ ሕሊና ውስጥ የተዘረጉ የስነ ኣእምሮ ክሮችን ባለመፈተሽ፤ ነገሮችን ካመረዳት የመጣ ድምዳሜ ስለሆነ በዚህ እኔ በምላችሁ አትኩሮታችሁን አገናዝቡት። ተቃዋሚ መሪዎች ለክስተቱ (መለስ ለዘብተኛ ዲክታቶረ ብቻ አድርገው በማስተማር፤ ትክክለኛ ማንነቱን፤ ማን መሆኑን በሚገባ በሕዝቡ ላይ ጠለቅ ያለ ትምህርት ባለመስጠታቸው በራሳቸው እና በሕዝቡ ውስ  የታየው አሳፋሪ “ትሬይት”/ባሕሪ) ተጠያቂዎች ናቸው።
ዚህ ሌላ ቀን እንነጋገርበታለን ፤ወደ ሚቀጥለው እናምራ።

በመለስ ሞት ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!
Birtukan cults fooling themselves as she was wrongly depicted on the above cartoon, the fact is her heart towards the Ethiopian enemy Meles Zenawi never  was as her cults thought she was. What a shameless cults using religious symbol in a such disgraceful politic. This was how some opposition leaders and their followers were fooling themselves as well the people. The fact is clear now on Bertukan's and other so called opposition politicians on their interview after Meles died. The Stockholm syndrome is clearly playing its effect on each of those sorry A.. elements!

Mengistu killed Ethiopians: Meles is killing Ethiopia” The not-so late Historian Dr.Aleme Eshete.
 *The name rendition—“seleM iwaneZ”--in the title of this article, is a mild metaphor for this Ethiopian writer’s indignation over the sacred Ethiopian flag held upside down by the ruler of the country at a summit event in Kenya (March 2, 2012) in the presence of the heads of states of Kenya and South Sudan. That said “seleM iwaneZ” is otherwise known as Meles Zenawi.” (Historian Professor Negussay Ayele)

"When they (TPLF) entered Addis Ababa on May 28, 1991 Meles and his gang had taken down the Ethiopian flag at the Ministry of Foreign Affairs located right across from the Hilton hotel, and hoisted the TPLF flag for at least twenty-four hours. Later on, none other than Meles himself uttered that he is tired of sound bites about the Ethiopian flag as nothing but Cherq, which accurately translates to ‘rag.’ " (professor Negussay Ayele)
“ዶ/ ቴዎድሮስ የበለጠ እንዲረዱልኝ፣ 1993 . የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር በቀጥታ የኢትዮጵያ ሀብት የወያኔ ካድሬዎች ቁጥጥር ስር ውስጥ ነው መውደቅ የጀመረው። ምርታማነትንና ውድድርን ለማሳደግና ለመጨመር እየተባለ ወደ ግላዊነት የተዘዋወረው የመንግስት ሀብት የወያኔን ካድሬዎች ያደለበ ነው። በአቶ መለስና በግብረ-አበሮቻቸው ዕምነት ኢትዮጵያን መቆጣጠር የሚችሉት ሀብቷን ሲቆጣጠሩ ብቻ ነው። ስለዚህም ድርጊታቸው ሁሉ በኢንዱስትሪ ተከላና በቴክኖሎጂ ምጥቀት ላይ ያተኮረ ሳይሆን ቶሎ ቶሎ ትርፍን ወደ ሚያመጣ ወደ ንግድና ወደ አንዳንድ አገልግሎት መስኮች ላይ መሰማራት ነበር። ይህንን ለማድረግ ደግሞ የሚቀናቀኗቸውን በሙሉ ማጥፋት፣ ወይም ደግሞ እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ብቻ እንዲሄዱ በማድረግ በሙስና ዓለም ውስጥ እንዲዘፍቁ ማድረግ ነበር። በዚህ ዐይነት የሞነቴሪ ፖሊሲ ላይ የተመረኮዘ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተ የሀብት ዘረፋን አስከትሏል።” (የአቶ መለስ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን ዘመናዊ ማድረግ ወይስ ማወላገድና ማዘበራረቅ ነበር” በሚል ርዕስ Dr. ፈቃዱ በቀለ መልስ / ቴዎድሮስ ኪሮስ Ethiopian Observer ላይ “Meles Zenawi and the unfinished project of Ethiopian Modernity” ለሚለው ጽሑፍ ከተሰጠ  የተቀነጨበ)
 
 እንደምን አላችሁ? በምን ልጀምር? ግንቦት 7 ብሎ ራሱን በሰየመ “ፎሽ -ፎሽ” ተቃዋሚ ልጀምር? ወይንስ በሻዕቢያው ጋዜጠኛ ተስፋየ ገብረአብ የሰሞኑን ዓይን ባወጣው ውሸቱ?
እስኪ በተስፋየ ልጀምር። የአክሱም ጽዮን ቤተመቅደሳችንን የሚዘልፍ ሳሞራ የኑስን ምክንያት ተጠቅሞ ጂሃዳዊ ተልዕኮውን በማስተላለፍ ሳሞራን  የሚከስስ የፈጠራ ውሸቱን ሳነብ የዚህ ልጅ ሕሊና ምን ያህል የቆሰለ ግማታም ሕሊና እንዳለው ይገርማል። ይህ ሻዕቢያ ወኪል እያመጣ የሚያስነብበን “የኢሳቱ” ካረንተ አፈይርስ ‘ተክሌ” በኢካዴፍ ዌብ ሳይት የለጠፈለትን እንዲህ ይነበባል፤፡

“ሳሞራ የኑስ ልጅ እያለ አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተክርስቲያን እየገባ፣አላሁ ዋአክበር!!” እያለ ቄሶችን ማበሳጨት ይወድ ነበር አሉ። ይህችን ታሪክ ስሰማ በጣም ነው የሳቅሁት። እንዲህ ያሉ ኮሚክ ብሽሽቆች ቀልቤን ይሰርቁታል። ሳሞራ ደግ አደረገ። እነሱስ ቢሆኑ አክሱም ላይ መስጊድ እንዳይሰራ ለምን ይከለክላሉ? የሆነው ሆኖ ጀብደኛው ሳሞራ ይብቃው። ደክሞታል፣ ይረፍ።” ይላል ይህ ቁስላም ሻዕቢያ።

ሳሞራ እና እኔ አብረን ነው ያደግነው። ተስፋየ ሻዕቢያ የፈጠረው ወሬ “ይህ ታሪክ ስሰማ” ብሏል፤። ይህ “ታሪክ” ብሎ የጠቀሰው ደግሞ “አስደስቶታል። በሳቅም ፈንድቷል። ለወጥወጥ አድርጎ ደግሞ “ብሽሽቅ፤ ኮሞዲ” ይለዋል። አለፍ ብሎ ደግሞ የአክሱም ታሪክ ጠለቅ ብሎ ባለማወቁ  ክርስትያኑ እና አስላሙ ለማጋጨት የሞኞች ፖለቲካ ለመጠቀም ሞክሯል። እንኳን ሳሞራ እኔ በግል የማውቀው አብሮ አደግ ጓደኛችን ይቅር እና ሌሎች እስላሞችም ቢሆን እንዲህ ያለ ብልግና አስበውትም ተሰምቶም አይታወቅም። ታዲያ ይህ ሻዕቢያ “ታሪክ” አገኘሁ ብሎ የቅድስት ጽላቷን ክብር በእንደዚህ  ይነት አዋራጅ “ቀልድ እና ታሪክ” የሚለው እሱ መቅደሳችንን ጂሃዳዊ የመዝለፉ ዘመቻው ተስፋየ ማን ነው የላከው?  

ሻዕቢያው “ፕሮተስታንት አማኝ” ሊሆን  ወይንም ንደ የቀድሞ ጌታው ሃይማኖተ ቢስም ሊሆን ይችላል ነገር ግን ያዘዙት እነማን መሆናቸው ከናንተ የሚሰወር አይመስለኝም። እሱ ምን አደረገ፡ አላጠፍም እኮ? ቅድስት ቤተክርስትያናችን፤ ኢትዮጵያዊያን ነገሥታቶቻችንን ፤የታሪክ አዋቂዎቻችን እና አዛውንቶችን እያስሰደቡብን ያሉት በስመ ኢትዮጵያ የሚበርዙትን የኢሳት ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው የካረንት አፈይርስ ፓል ቶክ እና ዌብሳይት ባለቤት ተክለ የተባለው ለሰንደቃላማ ክብር የሌለው “ጸረ አማራ እና ጸረ ትግሬ” አፍቃሬ ሻዕቢያ እና ኦነግ የሆነ ጋጠ ወጥ ነው ይህ ሁሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ውርደት አንዲዘመትብን እያደረገ ያለው።

“ሳሞራ የኑስ አክሱም ቤተመቅደስ ገብቶ እንዲህ ያለ የአክራሪዎች እና የጃሃዲስቶቹ ጋጠ ወጥ ባሕሪ መሳለቁ  አስደስቶኛል፤ ደግ አደረገ” እያለ ያለየው፤ያልሰማው፤የማያውቀውን የጸረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሻዕቢያ የፈጠራ የመንደር ወሬ ጽፎ ሲልክለት ይህ ጉደኛ ዌብሳይት በኢትዮጵያዊያን እንዲነበብ መፍቀዱ የመጀመሪያው  አይደለም። ካሁን በፊትም እኮ “ሁለት ሦስት ተቃዋሚ መሪዎች ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ግብረ ሰዶም ተፈጽሞባቸዋል” ሲል አስነብቦናል። ስያትል ውስጥ “ሰንደቃላማችን የኦነጎቹ ባንዴራ ካልተውለበለበ ብሔራዊ ሰንደቃላማችን ቢደበቅ ባይደበቅ ስሜት አይሰጠኝም፤ ቢቃጠልም ባይቃጠልም ጉዳየ አይደለም “ዊ አር ኢን አሜሪካ ኖት ኢን ኢትዮጵያ” በማለት በራዲዮ ተናግሯል። ይህ ደግሞ ካሁን በፊት  እቅርቤላችሗለሁ። ይህ የጂሃዲስት  ጋጠ ወጥነት ጽሑፍ ግን  ዓይን ያወጣ ድፍረት የአክሱም ልጆች እና የተዋህዶ ቤተክርስትያን ተከታዮች  ይህ ጉድ ካነበባችሁት በሗላ ትዕግስት ይኑራችሁ እላለሁ። ድረገጹ ጽሑፉን እንዲያነሳ መጠየቅ ይቻል ነበር፤ (አዘጋጁ የኢሳት ጋዜጠኛው ‘ተክሌ’ ነው) ሆኖም እሱም ሰንደቃላማችንም ሆነ የትግሬ ሕዝብ ጠቅላላ የሚዘልፍ ፓል ቶክ (የካረንት አፈይረስ) ባለቤት ስለሆነ ስሜት አይሰጠውም እና ጊዜአችሁን አታባክኑ። ብቻ ለታሪክ ማስታወሻችሁ እንዲሆን መዝግቡት።

ወደ ሁለተኛው ጉደኛ የመንደር ዜና እንሸጋገር እናንተየ! የግንቦት 7  ትኩስ “ፎሽ ፎሽ” ሰምታችሁልኛል? (ደግሞ “ፎሽ ፎሽ” ምንድ ነው እንዳትሉኝ (እናቴ እንደ ነገረቺኝ/እኔም ገብገብ ተብሎ በሚጠራ ከከተማው ትንሽ ወጣ ብሎ በሚገኘው ገጠር “ተበብ” “ችቦ ጭራ  “ጭዕንዶግ” “እሸት”  እና  “ሃምባሃምቦ” ለቀማ ስሄድ ንዳየሁት ማሳ ላይ ተጥሎ የሚታይ ስትይዘው “ቡን ቡን”  የሚል “የቡና ዱቄት” የሚመስል "የቀበሮ ፈስ የያዘ ትንሽ የዱቄት ከረጢት" ነው)። ዜናውን ካልሰማችሁ የግንቦት 7  “ፎሽ ፎሽ”  ወሬ አዳማቂ የሆነው አሁንም ያው ከላይ የጠቀስኩት “ተከሌ” በሚያዘጋጀው “ካረንት አፌርስ” (ኢካዴፍ) የተባለው ድረገፅ እና ፓልቶክ” የለጠፈውን ሌላው አስቂኙ ዜና አንብባችሁልኟል? ካላነበባችሁት እነሆ፤-

“Senior leaders of Ginbot7, Abebe Bogale and Dr. Tadesse Biru, disclosed to ESAT that their movement is working expeditiously to bring EPRDF to the negotiation table or remove it from power altogether.” “…Ginbot7 of today is a movement with a strong and efficient organizational structure said the confident duo.

ESAT will broadcast the full interview in the coming days.”

አየ ኢሳት፡ ምን ያሰማን ይሆን ደግሞ ብርሃኑን ጎትቶ? እርግጠኛ ነኝ የግንቦት 7 መሪዎችን ሰውነት  የምታውቁ ዜናውን ስታነብቡ ያስቃል። ግን እባካችሁ እንዳትስቁ። የሄውላችሁ ወያኔ ዕድሜውን እንዴት ልያስረዝሙብን እንደተዘጋጁ እና የሕዝቡን ተቃዋሚነት ስሜት  እንዴት ዛሬም እምነት እንዲያጣ  እያደረጉ እንዳሉ ማንም ተራ ሕሊና ሊገምተው በሚችለው ተራ ወሬያቸው ተቃዋሚው  ዋጋ ቢስ እያደረጉት እንደሆነ አሳፋሪ ዜናቸውን ይሄውላችሁ።አሁን በዚህ ብዙ ማለት አልችልም፡ ግንቦት 7 የፊታችን ቅዳሜ ወያኔንን ጠራርጎ በማስወገድ “ሥልጣኑን ስለሚይዝ” እሱ እና መሰሎቹ “መንግሥት ለመሆን” የመሃላ ቀን ሲፈጽሙ ጋዜጠኛቸው የሆነው የብርሃኑ ነጋ ወዳጅ ሻዕቢያው ተስፋየ ገብረአብ “ዝርዝር ዜናው” ሲዘግብልን ለእዛው ሰሞን ላቆይላችሁ እና  ርዕሱ በተመለከተ ላይ ላተኩር። ወይ አገሬ ሓጢያትሽ በዛ እኮ!

ትግላችን ከወያኔ ጋርም ብቻ ሳይሆን ዛሬም በተቃዋሚ ስም ገብተው ትግሉን ከሚበርዙት በመለስ ዜናዊ ሕልፈት ልባቸው የደማ፤ ወያኔን ለክፋት የማይሰጡት፤ ልባቸው የሚቀልጥ ፈሪዎች፤ ውሸታሞች፤ አድርባዮች እና አክራሪዎች ጋር እንደሚሆን ከብዙ አመት በፊት የጻፍኩትን ታስታውሱ እንደሆነ ዛሬም ይህንኑ ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ።  ይህ ቃሌ እንደትንቢት ዘግቡት። ልብ እና ድፈረቱ አንሷት በሬን እየተከተለች የበሬን ቆለጥ ይወድቅልኝ ይሆናል ብላ በመቋመጥ እየተከተለች  ምራቋ ሞልቶ “የከረጢት ፈስ እንደምትለቀው” ሃሞተ ቢስ ቀበሮ፡ ዛሬም ምንም  ሳያፍሩ የነፈሰውን ያረጀ ያፈጀ  “ፎሽ ፎሻቸውን” ሲረጩ ማየት መቸ ልብ እንደሚገዙ ለኔ በጣም እየገረመኝ ነው።

የፎሽ  ፎሾቹ የሰሞኑ ዜና ምን ይመስል እንደነበር ከላይ አስነብቤአችለሁ፡
ይሄ ዩኒቨርሲቲ የሚባል ጉደኛ አዳራሽ ምን እያስተማረ ዶከተርነት እንደሚሰጣቸው እኔ ግራ እየገባኝ መጥቷል::
አሁን በመለስ ሞት  ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!
 ወደ እሚለው ርዕስ እንግባ
ተቃዋሚ ሓዘንተኞች ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ምንስ ሆነው ነው ልባቸው የተነካው? እንዴትስ በመለስ ሞት  ልባቸሁ ጥቁር የለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን! ለምንስ ነው የመለስ ሐዘን እየገለጹ ያሉት?
 Eric Niller የተባለ ጸሐፊ “How Dictators Keep Control” በሚለው ትችቱ ውስጥ “አምባገነኖች” ሕብረተሰቡን በፍርሃት ማዕበል ውስጥ በመክተት ፤የሚታየው ግልጽ እና ስውር የሕብረተሰቡ የሕሊና አለመመቻቸት ደረጃ በደረጃ በመከታተል መረጃዎችን እየተቆጣጠረ የሕብረተሰቡን ጤናማ ሕሊና ቀውስ ውስጥ በመክተት አምባ ገነኑ በራሱ ላይ አንዳች የተፈጥሮ አደጋ ሲደርስበት የሕልውናቸው ምሰሶ  እንደነበር በመዘከር ከእርሱ ሕልፈት በሗላ የሚመጣው ህይወት የተደረመሰ ገደል መስሎ እንደሚታያቸው እስከመምሰል ደረጃ የሚያደርስ የሕሊና ብልሽት በግለሰብም ሆነ በጣምራ እንዲንፀባረቅ የማድርግ ልዩ ባሕሪ እንዳለው ይናገራል።

ኤሪክ ናይለር  “How Dictators Keep Control” በሚለው ጽሑፉ እንዲህ ይላል፡ …..Dictators also exploit a well-known instinct for most people to seek protection from a strong leader, according to Alice LoCicero, a Cambridge, Mass.-based clinical psychologist and researcher on leadership and terrorism

"Our behavior is still affected by what went on thousands of years ago," LoCicero said. "It's easier to understand why it's adaptive and common for people to bond to powerful leaders. In Darwinian evolution, the people who bonded with the leader survived. That instinct got passed along." ትላለች በማለት፤-

አብዛኛው የዛሬዋ የዓለም ሕብረተሰብ ከሺ አመታት በፊት ከነበሩት ሕብረተሰቦች ለአምባገነኖች አዘኔታም ሆነ አምልኮት ሲያሳየው ከነበረው ባሕሪ ብዙ የማይለይ መሆኑን እና በዳርዊንያን ዘገምተኛ ለውጥ እንደተመለከተውም ከአምባገነኖች/ከሃይለኞች ጋር የተጠጋ ቡድን/ሕዝብ/ግለሰብ ባጭር የመቀጨት ሕይወቱ የመነመነ በመሆኑ፤ ተለሳልሶም፤ተሞዳሙዶም ሆነ ካንገት በላይ እያጎነበሰም ቢሆን ሕየወቱን የማቆየት ዕድል ስለሚኖረው ነፃነቱን ከሚገፈው አምባገነን ጋር የመጠጋት ባሕሪው ጥንትም ዛሬም በሰፊው የታየ እና የሚታይ የሕብረተሰብ ባሕሪ ነው። ይላል በግርድፍ ይዘቱ ሲተረጐም።

ባለፈው ሰሞን ከአምባገነን ወይንም መብቱን ከገፈፈው ግለሰብም ሆነ ቡድን ሰዎች ለምን እንደሚቆራኙ እና በከፋው መልኩም ለምን እንደሚወዷቸው ወይንም በዳያቸው ክፍት ሲደርስበት የፈለገው ሽፋን ይስጡት ለምን በሃዘን እንደሚወረሩ  “ሰቶክሆልም ሲንድሮም” በተባለ የሕሊና የአስተሳሰብ ንቅዘት የመነጨ መሆኑን ከሞላ ጎደል እንድትመለከቱት አቅርቤው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ካለፈው ሰሞን የቀጠለው የዚያ ክፍል 2 ዛሬ እናጠቃልላለን። ዛሬ የምንመለከተው በታወቁት የተቃዋሚ ግለሰዎች በብርቱካን መዲቅሳ፤በልደቱ አያሌው፤ እና አንድነት በወከሉ አንድ ግለሰብ መለስን አስመለክተው በተደጋጋሚ በየዜናው ማሰራጫ ሲጠየቁ የሰጡት መልስ የኢትዮጵያን ሕብረተሰብ ከወያኔ ካድሬዎች በከፋ መልኩ የሚበክል አፍራሽ መስመር ሲናገሩ በመቅረጸ ድምፅ የተመዘገበው ለታሪክ ዘጋቢዎችም ሆነ ለፖለቲካ ተንታኞች እንዲሁም ለማድመጥ ዕድሉን ያላገኙ አንባቢዎቼ እንዲመለከቱት እና እንዲዘግቡት የተናገሩትን አንኳር አንኳር ንግግሮቻቸውን አቀርብላችሗለሁ።

እንዚህ ግለሰዎች በመለስ ዜናዎ ሞት ማዘን “ባሕላችን ነው፤ ጨዋነት ነው”…ከገባንበት አዘቅት ለመውጣት...
ግልጽ በሆኑ  ለድረድር በማይገቡ አገራዊ እሴቶች ላይ መገበርም ካለብን ገብሮ መቻቻል፤ የፋሺስቶች እቅድ የሚተገብር ጸረ አማራ የወያኔ አስተማሪ እና መሪ የነበረ ግለሰብ  የቀሩትን በደብተሩ የዘገባቸው ብዙ አገራዊ ጥፋቶችን ሳያስከትል በፈጣሪ ቅጣት በሞት ሲለይ “ሰው ነውና እንደሰው እንዘን፤ አገራዊ ባሕላችን ስለሆነም  ከመካከላችን በመለየቱ የተሰማን ሓዘን ጥልቅ ነው” ወዘተ.. የሚሏቸው ማመካኛ ምክንያቶቻቸው ቢላበሱም ሰዎቹ በመለስ ዜናዊ የሕሊና ነጠቃ እንደተጠቁ ግልጽ ነው።

የወያኔ ነገር ሲነሳ ልባቸው ጨክኖ የማይጨክነው፤ ወያኔን ለክፋት የማይሰጡ  አንዳንድ ታዋቂ ተቃዋሚዎች እያሉን ያሉት፤ መለስ ዜናዊ የዲሞክራሲ “ጉድለት” የታየበት ቢሆንም የምጣኔ ዕድገት አስገኝቶልናል እና (በፋሺስታዊ) በአስተዳደሩ ወቅት ያስመዘገበው የምጣኔ ዕድገት ውጤት ምስጋናውን እየቸርን ከኛ በመለየቱ ልባችና አዝኗል። እያሉን ነው። ለመሆኑ ከወያኔ/መለስ የባሱ ፋሺስቶች አገራቸውን ሲገዙ ከመለስ ዜናዊ በበለጠ ዕድገት ዘርግተው እንደነበር ያውቃሉ? ሌላ ቀርቶ ጣሊያን አገራችን ሲወር በ 5 ዓመት ውስጥ አንዳንድ ነገሮች ገንብቶ እንደነበር ያውቁታል? ኤርትራኖችን በመካኒክነት እና በሕንጻ ግመበኛነት ስራ ፤ፋቭሪካ….ጨርቃጨርቅ በመሳሰሉት አስተምሮ የሄደው ፋሺስት ነው። ታዲያ ለሙሶሎ ምሳጋና ይቸረው ማለት አስነዋሪ መሆኑን አያውቁትም ወይስ አማራን እና አማርኛ ቋንቋን እንዲሁም ቤተክርስትያንን በጠላትነት ፈርጆ በቋንቋ አስተዳዳር ከልሎ አንድ አገር በ5 ኮሎኒ ከፍሎ፤ባንዴራ ለማሰራት ያዋቀረው ፋሺስቱ የሙሶሎኒ መርሆ ከመለስ ዜናዊ የቋንቋ ክልል /አቶኖሚ እንዴት አይመሳሰልም? ለመሆኑ አመርኛ የተናገረ የአዲስ ኣበባ አንደኛ ደረጃ ታዳጊ ሕፃናት ትምህርት ቤት “I am stupid!!!!I am Stupid!!! ደደብበ ነኝ!!! ደደብበ ነኝ!!! በማለት 100 ጊዜ በደብተሩ ላይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲጽፍ ወይንም “ጀርባውን ወደ ተማሪ ፤ፊቱን ወደ ግድግዳ አድርጎ በቅጣት እንዲቆም  መደረጉ አዲስ አበባ ውስጥ በተደረጉት 4 የትምህርት ተቋማት ውስጥ ድርጊቱ እንደተፈጸመ ያዲስ አበባ ኗሪ የሆኑት በዚህ ጥናት ያደረጉ  ከትምህርት ተቋም ተመራማሪ እና መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊ ዜጋ የጀርመን ራዲዩን የአማርኛ ዝግጅት ክፍል ካዲስ አበባ ስልክ ደውሎ ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸው በጥናት እንደተረጋገጠ ያውቃሉ? አንድ ተማሪ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ከ1ኛ ደረጃ እስከ 9/10 (ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) እስኪደርስ  ድረስ እንዳይማር እና ከአፀደ ሕፃናት ት/ቤት ጀምሮ እንግሊዝኛ እና ትግርኛ ብቻ እንዲማሩ ሃያ አንድ አመት ሙሉ  አማርኛ በሕግ ታግዶ በምትኩ ባገሪቱ በመላ እንግሊዝኛ መተካቱ ያወቃሉ? ይህ ሁሉ የማን ፖሊሲ ነው? ፏሺስት ከዚህ ወዲያ ምን ፈጸመ?
ለሞሶሊ እና ለግራዘያኒ/ሂትለር/ለኪም ኤል ሱንግ/ለመለስ ዜናዊ የሚያዝን የሚያለቅስ ኢትዮጵያዊም ሆነ ማንኛውም ፍጡር በሕሊና ቀውስ ውስጥ የተጠመደ ሕብረተሰ ብቻ ነው። (ለምሳሌ የትግራይ የኪነት አባሎች ያሳዩትን አስገራሚ ጉድ ብትመለከቱ  እንደ "ፆመ አርብዓ" ባሕታዊ በጉልበታቸው ተምበርክከው መሬት ለመሬት እየተሳቡ እያለቀሱ ግምባራቸው ወደ መሬት እያጋጩ  እየተንፏቀቁ ወደ ዛርነት/ውቃቢ/ዳልቻ (ሂሥቴሪክ) ተለውጠው የማሰብ ሕሊናቸው ተገፍፎ ማየት አሳሳቢ በሆነ የሕሊና ቀውስ የገባ ሕብረተሰብ መሆኑን አጋጣሚውን ማጤን ያስፈልጋል)።

 መለስ ዜናዊ ከሂትለር ጋር ከሙሶሎኒ ጋር የሚያመሳስሉት ብዙ ባሕሪዎች አሉት። ያውም የናዚው ፓርቲ/ሂትለር ጀርመን ገብታበት ከነበረቺው ጥልቅ የምጣኔ ቀውስ አውጥቶ በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሦስት አመቶች የዕድገት እምርታ በማሳየት የሕዝቡ ሕሊና ሰልቦ እንደገና ያልታዩ የስልጣኔ ዘመናዊ ጥበቦችን (ቅመሞችን፤የራዲዮ ምስጢሮችን፤መገናኛዎችን ሕንጻዎችን… የዓለም ዓቀፍ የስፖርት እና የንግድ ትዕይንቶችን በማስተናገድ፤ዘመናዊ  መኪኖችን……የመሳሰሉ) በማስተዋወቅ የሕዝቡን ሕሊና ሰልቧል (እንደ መለስ በቢሊዮን ዶላሮች ለሃያ ዓመታት ከጌቶቹ በብድርም ሆነ በምፅዋት “ትልልቆቹ የመንግሥት ሌቦች” የሚላቸውን እራሱ ያስቀመጣቸው ሌቦቹ  እንደሚያድላቸው ሳይሆን) ። ሥልጣንም ለመያዝ  የጀርመን ናዚ የሕዝብ ድምፅ መርጫን አስመልክቶ እንኳ ብንመለከት ሂትለር በሕዳር 1932 (34.1%) ከማንኛቸውም ተቀናቃኞቹ በላይ የሕዝብ ድምፅ በማግኘት “በሕጋዊ” መንገድ ነበር ወደ ፓርላማው ገብቶ  አምባገነናዊ ስራው የፈጸመው። የወያኔው መሪ “የነበረው” መለስ ዜናዊ ግን የሕዝብ ድምፅ በመስረቅ 99.6%  ድምፅ አገኘሁ ብሎ ወጣት እና አዛውንቶችን ባንክ ዘራፊዎች ናቸው ብሎ በጥይት አስጨፍጭፎ “ፖሊሶቻችን የሰላማዊ ሰልፈኞች አድማ አያያዝ ስልጠና ስላልወሰዱ ነው ይህ ሁሉ ግድያ ሊከሰት የቻለው” ብሎ ሳያፍር ለአልጀዚራ ነበር የተናገረው።

 ይህ ጉደኛ ሰው ሲሞት ልባችን ለሁለት ታጠፈ፤አዘነ፤ለቀብሩ ባለመገኘታችን እጅግ ይቆጨናል፤ እናዝናለን….እንግዲህ ወዲህ ጠቅላይ ምኒስትሩ በሞት ስለተለዩን ስለ እሳቸው አምባገነንነት፤ሃጢያት ወዘተ…..ለሃያ አመት ስለተናገርን፤እሳቸው በሌሉበት መናገር ተገቢ ስላላሆነ እንገዲህ አፋችን እንዝጋ…….ይበቃል…..ወዘተ…..የሚሉን የተቃዋሚ ተብየ ሰዎችን አንደበት ለታሪክ ዘገባ (ለማስታወሻችሁ) እንዲሆን እነሆ አንብቡ እና ኢትዮጵያ ለሃያ አመት በእነዚ የፋሺሰት 9 (ዘጠኝ)ባንዴራ አውለብላቢ የዘመናችን ሶላተቶዎች  ስትረገጥ ተቃዋሚ ነን የሚሉ አንዳንድ ግለሰቦች በቀደዱት የሽንፈት እና የተጐንባሽነት መንገድ ሕዝቡ እንደበታቸውን እየተከተለ ለዚህ አሳፋሪ የሕሊና ነጠቃ እንዴት አንደበቃ መረጃው እነሆ።

የቶኒ ብሌር ሊበራልና ዲሞክራቶች (“ላብ- ላብ” ይሏቸዋል አንግሊዞች) ለመጪዋ ኢትዮጵያ እያዘጋጁልን ያለውን እንግሊዝ ሰራሽ “ኢትዮጵያዊው-ሊበራል ፓርቲ” ልደቱ አያሌው ስለ መለስ ዜናዊ የሚለንን አድምጡልኝ። እርግጥ ልደቱ ተቃዋሚ አይደለም ከ“ሰለሞን ስቶክሆልም” (ሰለሞን ተካልኝ) የሚለየው ምን ነገር አለ? ልትሉኝ ይሆናል፤ ነገር ግን ልደቱ አያሌው ተቃዋሚ ለመሆን የሚፈልግ “የመሟገቻ ነጥቦቹ  የመቀመር ችሎታ ያለው” ቢሆንም።  መለስ ዜናዊ ሰው እየረሸነም ቢሆን ፤እያሰረንም፤ እያንገላታን እና እየሸጠን እና እያስሰደደንም ቢሆን “መለስን አመስግኑ” “በክፉ አይን አትዩት” የሚለን ሕሊናው የተነጠቀ፤ “በመለስ ዘመን ተወልዶ(?እንበለው ) ያደገ” ግራ የተጋባ ወጣት ስለሆነ ለማንኛውም ዋናው “ሞተራቸው ተነጥቀው” ባዶ የቀሩት ወያኔዎች ሥልጣን እንደሚሰጡት ስለምገምት እሱ እና ከእርሱ ጋር ያሉት ቡድኖቹ በጥንቃቄ እንድታጤኗቸው ለታሪክ ይመቻችሁ ዘንድ እነሆ። (ስየ አብርሃን እና የተቀሩት የወያኔ ትርፍ ጭነቶች ‘አንዳንዶቹ’ በወያኔ አዲስ የስልጣን ሽግሽግ እንደሚቀመሩ አትጠራጠሩ።የጊዜ ጉዳይ እንጂ) ምምዕርራ/ ምትዕርራይ ይለዋል ወያኔ “ማሸጋሸግ” ማለት ነው። ሰለጠንኩ ካለ ደግሞ “ምትሕንፋጽ” ይለዋል (ማዳቀል ማለት ነው። ለክፋት የማይሰጡ ከዚህም ከዚያም ማለት ነው።  ልክ በየነ ጴጥሮስ ለትምህርት ሚኒስቴር ሾሞ እንደተጠቀመበት ስልት ማለት ነው። ይሄ “በኢሕአዴግ” (ወያኔ) ውስጥ እርስ በርስ ፍጥኛ መሳሳብ አለ የሚሏችሁ አትመኗቸው፤ “ፌሶ” ወሬ ነው። ወያኔ እንኳን አሁን አንድነታቸውን በበለጠ በሚፈልጉበት ሰዓት እና ሞተራቸውን አጥተው ቀርቶ ድሮም ብሔረተኛ በክፉ ቀን የራሱን ሙጫ (ማስቲሺ./ ክሬዚ ግሉ) በማጠናከር የታወቀ ነው። በዛው የሚቋምጡ ካሉ የበሬ ቆለጥ እራሱ ይወድቅልኛል ብላ የበሬን ሗሊት ሗሊት እንደምትከተል ገራ ገር ቀበሮነት ይቅር።

ልደቱ ምንድ ነው የሚለው?

"ድሬ ቱብ" የተባለው የወያኔ የድምፀ ስዕል ድረገጽ ልደቱ አያሌውን (ወይንም በቅጽል ስሙ እንደሚጠሩት “ልድቱ ክህደቱ”) በፋሺስቱ የወያኔ ትግራይ መሪ በመለስ ዜናዊ ሞት ምክንያት ምን እንደተሰማው ለማወቅ የሚከተለው ጥያቄ አቅርቦለት ነበር።

አቶ ልደቱ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ሕልፈተ ሞት በግልህ የተሰማህ ስሜት ምንድነው?
ልደቱ አያሌው ፡
እንግዲህ አዳምጠህ ከሆነ ታመውም እያለ፤ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ  ተጠይቄ ያኔ ነው አቋሜን ግልጽ ያደረግኩ። ያኔ ከሕመማቸው ተሽሎአቸው ከሕመማቸው እንዲፈወሱ እና ደህና እንዲሆኑ ነው ያኔ ምኞቴ የነበረው።…ውጭ አገር በመሆኔ በቀብራቸው ለመገኘት ባለመገኘቴ በጣም አዝኛለሁ። ከሦስት ዓመት በፊት የጻፍኩት መጽሐፌን አየተህ ከሆነ ተቃዋሚው ከሚያያቸው ዓይን ለየት ባለ ነበር  ሳያቸው የነበረ።….ለኢትዮጵያ ሕዝብም መንግሥትም መጽናናት እንዲሠጣቸው እመኛለሁ።

በዚህ ወቅት ባይታጡ ምናልባት በሃገሪቱ በጐ ነገር ለወደፊት በተሻለ ሁኔታ ለማበርከት ዕድል ይኖራቸው ነበር ብየ አስባለሁ። ….”ኢትዮጵያ አንድ ሰው” አጣች “ ብየ አስባለሁ። በጣም ነው ያዘንኩት።

ልደቱ አያሌው ስለ የመለስ የፓርለማ ባሕሪ ፤ተጠይቆ  (ሰብአዊነቱን “ሰውነታቸው” ይለዋል በእሱ አገላለጽ) በፓርላማ ክርክር ከሚያሳየው "ብልግና" (ልደቱ በቃል ሊገልጸው የፈራው የመለስ የስድብ እና መድረክ ለብቻ የመያዝ ጠባይ…..) እንዲህ ይገልጸዋል።

“ከዚያ  ይነት መድረክ ውጭ ስታገኛቸው “ሰውነታቸውን” (ሰብአዊነቱን “ቀናነቱን፤ደግነቱን ፤ተግባቢነቱን፤የዋህነቱን….) የምታይበት ወቅት ያኔ ነው።  እና ያኔ እሳቸውን የምናይበትን ዓይን ቀደም ብሎ ቢለወጥ ኖሮ ምናልባትም ያገሪቱ ችግር አካል  ሳይሆን የመፍተሔ አካልም አድርገናቸው አይተናቸው ቢሆን ኖሮ “ተገቢውን እውቅና እና ምስጋና ሰጥተናቸው ቦሆን ኖሮ”  ላመበት ዓላማ ሙሉ ሕይወታቸውን፤ጊዜያቸውን፤ጉልበታቸውን ፤እውቀታቸውን የሰጡ ሰው ናቸው። ይሄ ማንም ሰው ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ አይደለም። ይሄ የሚያስቀና ነገር ነው

ባንድ በኩል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በልማት መልክ የሰሯቸው ስራዎች ቀላል አይደሉም።..የኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት ረገድ፡(ልብ በሉ አላደገም፤ በወያኔ ተቋማት የተሰነገ ምጣኔ ሃብት ነው… ሲለን የነበረውን አስታውሱ፤ (ከደጀን ራዲዮ (ትግርኛ ጣቢያ) በአማርኛ ያደረገው ቃለ ምልልስ ልብ ይለዋል።) ከምርጫው በሗላ ነው እንዲህ ያለው።) በአካባቢ እና በዓለም አቀፍም ኢትዮጵያ ተቀባይነት እንዲኖራት የበለጠ እንዲያድግ በማድረግ ረገድ ያደረጓቸው አስተዋጽኦዎች፤ ቀላሎች ናቸው ብየ አላምንም። በሰብአዊነት እና በዲሞክራሲ ያለው "ጉድለት" እንደተበቀ ሆኖ (ልደቱ “ጉድለት” ነው የሚለው እንጂ በዲሞክራሲ እና በሰብአዊ መብቶች ላይ የተፈጸሙ “የግድያ ወንጀሎች፤የጎሳ ማጽዳት ወንጀሎች…)” እንደወንጀል ሳይሆን እንደ “ጉድለት” ነው የሚመለከታቸው።) በጐ ስራዎች በሰሩት ስራዎቻቸው ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብዙ ጠቅመዋል ብየ ነው የማምነው።

እና (መለስ ዜናዊን ለማወቅ )በነበሩኝ አጋጣሚዎች ቀላል የማይባል እውቀት የነበራቸው ሰው እንደነበሩ፤ ፖለቲካ (?) የሚያወቁ እንደሆነ፤ ያመራር (ብቃታቸው (?)) በጣም የላቀ እንደሆነ በጣም አይቻለሁ።….በነበራቸው እምነት በነረበራቸው ጊዜ እና ሁኔታ ቀላል የማይባል ስራ ለኢትዮጵያ ሰርተዋል።ሕዝቡም በፖለቲካ የሚደግፋቸውም የማይደግፋቸውም ሐዘኑን እየገለጸ ያለው ያለምክንያት አይመስለኝም።ጥሩ ነገር እንደሰሩ በማየት ነው ብየ አምናለሁ።

ድሬ ቱብ፤ ጥያቄ፤-

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማረፋቸው ምክንያት የዚች አገር የወደፊት  ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል ብለህ ታምናለህ?

ልደቱ አያሌው፦

እኔ እንግዲህ መጽሐፌን አንብበኸው መሆንክን አለመሆንክን አለውቅም፡ ኢሕአዴግ በስልጣን እስከቀጠለ ድረስ እሳቸው ኖሮ ቢኖሩ ለአገሪቱ  የተሻለ ይሆን ነበር ብየ አምናለሁ። ዛሬ የምገልጸው አቋሜ አይደለም የዛሬ ሦስት አመት የገለጽኩት አቋሜ ነው። …..አስቀድሜ ይህ ይፈጠራል ብየ ልልህ አልችልም። ……

ጥያቄ ፤-በመጨረሻ የምትለው ካለ?

ተቃዋሚው ከጽንፈኛነት አመለካከቱ መውጣት አለበት።  ኢሕአዴግን ስናይበት የኖርንበትን  አይን መቀየር አለበት። ይህ በማለታችን ብዙ ዋጋ ከፍለናል። መሞታቸው የማይፈለግ እና ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ነው። አውነትም  ….የሕዝቡ ምክንያተዊነት (ብስለት እያደገ ስለመጣ) የሚደግፈው ፖሊተካ ይቃወመኛል ብሎ ሳይፈራ   እሕዝቡ የተሰሩት ስራዎች አይቶ በጨዋነት በመግለጹ “ያ እኛ ስናራምደው የነበረ አስተሳሰብ አሁን እየሰፋ እና ቦታ እያገኘ መሄዱን” ሕዝቡ መንቃቱን ነው የሚያሳየው። ይሄ ትልቅ ነገር ነው፤ ይሄ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነገር ነው።

ኢትዮጵያ መሪዋን አልቅሳ የቀበረችበት ዘምን በታሪክ አልነበረም፤ይሄ የመጀመሪያ ነው። ኢሕአዴግ በአየር የተንጠለጠለ ፓረቲ ነው፤ አልቆለታል እያልን የምናወራው ነገር ከሕዝብ አስተሳሰብ የራቀ መሆኑን ያሳየን ይመሰልኛል። ሕዝቡ ተገዶ ነው እያዘነ ያለው ከማለት ይልቅ፤ከዚህ ሂደት ምን ተምረን አካሄዳችንን ልናስተካከል እንችላለን በማለት ልንማርበት ይገባል።ከዚህ በተረፈ  ቤተሰቦቻቸው፤ የኢትዮጵያም ሕዝብ፤መንግሥትና አባሎቻቸው፤ጽናቱን ይስጣቸው። እሳቸውም ነብሳቸው እግዚአብሔር በጥሩ ቦታ ያስቀምጥ ነው ለማለት የምንችለው።

አሁን ደግሞ  ወደ ዳኛ ብርቱካን መዲቅሳ  ከጀርመን ራዲዮ  አማርኛው ክፈለ ጊዜ ጋር ያደረገችው ቃለ መጠይቅ ምን እያለች አንደሆነ ልውሰዳችሁ እና አድምጡ። ቃለ መጠይቁ የተካሄደው ከዶቸ ቨለ የአማርኛው ክፍል ነው። ወ/ሪት ብርቱካን የምትኖረው አሜሪካ ውስጥ ሃርቨርድ ዩኒቨርሲቲ ነው። (እኔ የገረመኝ የዚምባቡዌም፤የኢትዮጵያም እና የመሳሰሉ አገር ፡ ”እስር ውስጥ የነበሩ ፖለቲከኞች” ከታሰሩ በሗላ ወደ እዚሁ ጉደኛው ሐርቨርድ በቀጥታ እንዴት መግባት ዕድል እያገኙ እንደሆነ እናንተም እንደ እኔው እንቆቁልሹ እየገረማችሁ ይሆን?)

ብርቱካን እንዲህ ትላለች፡

“አውነት ለመናገር የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት ስሰማ በጣም….ነው ያዘንኩት።በጣም ተደራራቢ ሐዘን ነው የተሰማኝ። አንደኛ እንደ ሰው ፤እንደ አገሬ ዜጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አለ ዕድሜአቸው በሚባል ሁኔታ ማለፋቸው አዝኛለሁ።ለቤተሰባቸው አዝኛለሁ ፤ለሳቸው አዝኛለሁ።” “በሐዘን ድባብ ውስጥ ሆኜ ያሰብኩት ነገር” እያለች ወደ ምክንያተዊ ሽፋን ስትተነትን አድምጠናታል።
 
ስየ አብርሃ ደግሞ እያለ ያለው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራ በምጣኔ ሐብቱ ከፍተኛ ዕድገት የታየው በፖለቲካው ላይ አስተማማኝ መደላድል አድርገው ባለማለፋቸው አሳዝኖኛል። ብሏል። የመለስ መሞት በስልክ ደወል ሲሰማ “ልቡ ደንግጦ ተረብሾ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሕሊናው እና ማስተዋሉ ጽጥ ብሎ እንደነበረ” ሳይደብቅ የተሰማውን ሓዝን ገልጿል። ሆኖም የብርቱካን እና የስየ አባባል ስትመለከቱት ሁለቱም በተለያዩ ዜና ማሰራጫዎች ያስተላለፉት መልዕክት “በጎም መጥፎም አንደማንኛውም ሰው አድርገዋል” (የብርቱካን) ጀምረውት በሗላ የዘጉት የዲሞክራሲ መንገድ መክፈቱን ቢቀጥሉበት ኖሮ…..(ብርቱካን በ ቪ ኦ ኤ አማርኛ ክ/ጊዜ) የምትለውን እና ስየ የፖለቲካ መደላድሉን ሳያረጋጋ ማለፉን’ የሚለው  “ምኞች” ስትመለከቱት ፤እነዚህ ሰዎች መለስ (የወያኔ ትልቁ የጦር መሪ የነበረው የስየን አስተያየት ወደ ጎን ትተን፤ ብርቱካንን እና መሰሎቻ ማለቴ ነው) ማን መሆኑን ፤የተከተለው የፖለቲካ ፖሊሲ ምን እንደነበረ ጭራሽኑ የገባቸው አይመስልም። ጎሰኛ ወይንም ሙሶሎኒ ወይንም ሂትለር “እንዲህ ቢሆን ኖሮ” በዚህ የጀመረው በዚህ እንዲህ ቢቀጥልበት ኖሮ የሚሉት የፖለቲካ አላዋቂነት ምን ያህል ያገሪቱ ተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች የተቃዋሚያቸው የፖለቲካ መመሪያ እንዳልተረዱት የሚያሳይ መስተዋት ነው።  የማዘናቸው መሰረቱም በጠላት እና በወዳጅ መካከል ያለው የዓይን ሚዛን ደካማ ነው። መለስ እንደሚሉት አገራዊ ፖለቲከኛ ሳይሆን ኢትዮጵያን በጥፋት ጐዳና እንደትጓዝ ቀይሶ የመጣበትን መመሪያው በጣለትንት ካለመፈረጃቸው የመጣ ደካማነት ነው። እንዲህ ቢሆን ኖሮ ብሎ የሚተነብይ ፖለቲከኛ “የወያኔ ምንነት እና ፖሊሲው” እንደገና መመርመር ያስፈልገዋል እላለሁ።

 አሁን ደግሞ ወደ አቶ ግርማ ሰይፉ የአንድነት  ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ እና የምክር ቤት አባል እንዲህ ብለዋል። የሰውየው አጀማማር “ያበሻ ሲንድሮም” ብየ የምጠራው “እንደ ሰው” የሚለው አጀማመር ነው እሳቸውም እንደ ብርቱካን እና የመሳሰሉት “እንደሰው” እያሉ ለሐዘናቸው የመሸፈኛ ጥበብ የሚጠቀሙት። ሂትለርም ፤ሙሶሎኒም “ሰው ነበር” ግን እንደሰው እናልቅስላቸው?
ሰውየው እንዲህ ይላሉ።
“እንደሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት ያሳዝነኛል።ካሁን በሗላ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ነበር እንዲህ ነበር ብሎ “ማውራት” ተገቢ አይደለም። ከዚህ በፊት የምናወራው ወሬ “እንዲህ ናቸው እንዲህ ናቸው” ብለን የምናወራው ወሬ ይማራሉ ብለን መልዕክት የምናስተላልፋቸው ነገሮች ነበሩ አሁን ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገር ካሁን በሗላ በታሪክ እሳቢ የሚያገኝ ስለሆነ (መውቀሳችን  “ወሬያችን” ማቆም) እና ጠቅላይ  ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመት ያገለገሉ ስለሆነ ማረፋቸው ያሳዝናል።”
ይህ አባባል አልገረማችሁም? “ለ21 ዓመት ኢትዮጵያን የጣሩ፤ ያገለገሉ መሪያችን ስለሆነ ማረፋቸው በጣም ያሳዝናል”? ምን እሱ ብቻ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ነበሩእንዲህ በደል ነበራቸው ሕዝቡን እንዲህ አደርገውት ነበር የምንለው ወሬ ካሁን በሗላ ማቆም ለብን “ የሚለውስ አልገረማችሁም? እነዚህ ናቸው ተቃዋሚዎች የሚባሉት? ሕዝቡ በነቂስ አልቅሷል፤አዝኗል ብሎ ሕዝብን መውቀስ እንዴት ሊመች ይቻላል? የተቃዋሚ ጅላጅሎች እና አድርባይ የሕሊና በሽተኞች እንደዚህ ዓይነቱ ለፋሺስት መሪ ማላዘን ፤ማዘን፤ልባቸው ሲታጠፍ የተመለከተ እና ያደመጠ ሕዝብ  ለመለስ ዜናዊ ቢያለቅስ ምን ይጠበቅበታል ብለን ነው የምንወቅሰው? ይህ ተቃዋሚ የሚባል ሌሎች መሪዎች ከሰማይ እግዚአብሔር በጥበቡ መለስን እንደወሰደው ከሰማይ ለተቃዋሚው ቢልክለት እንጂ ይህ አድር ባይ እና ለፋሺሰት አልቃሽ ተቃዋሚ ለውጥ ያመጣል ፤ወያኔ ያስወግዳል ብላችሁ አትጠብቁ። በዚህ አጋጣሚ የመኢአዱ ኢንጂኔር ሃይሉ ሻውል በፋሺስቱ በመለስ ዜናዊ ሞት የሰጡትን መልስ እና ያሳዩት ጠንካራ እና ሕጋዊ (ጃስቲፋያብል) አቋም ሳላመሰግናቸው አላልፍም። ምስጋናየ-ይድረሳቸው።ታቸው-ረዳ(ኢትዮጵያን-ሰማይ-አዘጋጅ) አሜሪካ www.ethiopiansemay.blogspot.com          email getachre@aol.com