Sunday, September 9, 2012

በመለስ ሞት ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!

                ለተወሰኑ
ደቂቃዎች ሰውነቴን መቆጣጠር አቃተኝ!
 
በመለስ ሞት  ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!ታቸው-ረዳ  (Ethiopian Semay)



 ዲክታተሮች-ንቅላትን የመቆጣጠር ሃይላቸው በጣም የላቀ ነው።የከያያኖቹ ቁንጮ ታማኝ በየነ በመለስ ሞት የተሰማው የስቶክሆልም ሲንድሮም ድንጋጤ እና እሱ ሳይታወቀው ከሕሊናው ውስጥ ገብቶ የተለማመደው፡አንዳች ነገር ከሕሊናው የተነጠቀ ነገር የመሰለው የተሰማው “ባዶነት፡  በሚገርም ሁኔታ በመራር ሐዘን እንዲህ ሲል ስሜቱን ሳይደብቅ ገልጿል::


 ታማኝ እንዲህ ላይል::
"አውነቴን ነው የምለው ደነገጥኩ፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰውነቴን መቆጣጠር አቃተኝ።(ከው ብየ) አዘንኩ። አውነት እንዴት እንደምገልጸው አላውቅም፤በጣም ደነገጥኩ።አዘንኩ።ምንም ይሁን ምንም ባደግንበት ሠፈርም ይሁን “የለመድነውን ነገር ስናጣ” የተሰማኝ ስሜት አለ።ለሃያ አንድ ዐመት በእኚህ ሰውየ ዙርያ ብዙ ነገር አይቻለሁ፤አድምጫለሁ፤ብዙ ብዙ ነገር ….እና….በጣም ለምጃቸዋለሁ፡ እና ሞቱ ሲባል የተሰማኝ ነገር ቀላል አይደለም።…..የተሰማኝ ስሜት ሐዘን ነበር። “ ታማኝ በየነ (ስለ ጸረ አማራው ጐሰኛው መለስ ዜናዊ ሞት ከኢሳት ጋር የደረገው ቃለ መጠይቅ)፡
እንግዲህ ልብ በሉ። ያልኩዋችሁ የስቶክሆልም ሲንድሮም ምልክቱ ታማኝ የሚከተለውን ንግግሩ በጥንቃቄ ብትመረምሯቸው በሕሊናው የተያዘ ነገር እና ስሜት እንዲህ የገለጻትን ነጥብ እስቲ ልድገምላችሁ እና የሲንድረሙ ክብደት ምርምሩት። ታማኝ በየነ  እንዲህ ይላል፦  
““የለመድነውን ነገር ስናጣ” የተሰማኝ ስሜት አለ።ለሃያ አንድ ዐመት በእኚህ ሰውየ ዙርያ ብዙ ነገር አይቻለሁ፤አድምጫለሁ፤ብዙ ብዙ ነገር ….እና….በጣም ለምጃቸዋለሁ፡ እና ሞቱ ሲባል የተሰማኝ ነገር ቀላል አይደለም።…..የተሰማኝ ስሜት ሐዘን ነበር።” ብሏል ታማኝ።
ታማኝ የለመደውን የማጣት ስሜት “ከጨቋኝ መሪ ጋር መጨቃጨቅ/ክርክር የቃላት መወራወር ሱስ ድንገት የተለከሰተ የማጣት  ባዶነት” (ልክ ልደቱ ዓያሌው እንደገለጸው የተሰማውን የማጣት ባዶነት ስሜት ማለት ነው) :: ታማኝ በዚሁ ቃለ መጠይቁ ቀጠል ያደርግና “ሕዝቡ ተገድዶ/ ነው ያዘነው/ያለቀሰው” ሲል ታማኝ ከተጠናወተው የስቶክሆልም ሲንድሮም/ ልክፍት ዲናያሉን በመታገል  ወደ “ዲፌንሲቭ”/ወደ መክላከያ መስመር በማፈግፈግ ወድያውኑ የተጣመመው ስሜት ወደ ሌሎቹ አዛኞች/አልቃሾች በማላከክ/በመወርወር ከሕሊናው ሲታገል ታደምጡታላችሁ።

ስትመለከቱ የስቶክሆልም ሲንድረም ደምበኛው ምልክት ከታማኝ ጭንቅላት አነጋጋር በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁ። ሰዎች ከዲክታተሮች ለብዙ ጊዜ ሲኖሩ ይለማመዷቸዋል። እነሱ ሲለዩ ልክ ታማኝ እንደተሰማው “ከውስጣቸው ባዶነት ይሰማቸዋል”” ሲደበድባት የነበረው ፍቅረኛዋ ድንገት ሲለያት እያደረ “ባዶነት” ይሰማታል። ታማኝም የዚህ ሲንድሮም መገለጫ “ስቶክ” (ከጥቅሎቹ አንዱ ነው)።

 


እባካችሁን፤ ላሳስባችሁ የምፈልገው ልታተኩሩበት የሚገባ ነገር፤ አንዳንድ ምሁራኖች ለምን ተቃዋሚ መሪዎች ሐዘኔታቸው በመራራ ሐዘን እንደገለጹ መላምታቸው ሲነግሩን “የፐለቲካ ሰዎች ስለሆዩ፤ ዲፕሎማቲክ ቋንቋ ወይንም ለሽፋን/ዘዴ መጠቀማቸው ነው” ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ በጣም የተሳሳተ መላምት በአውራ ገነኖች እና በሕዝብ ሕሊና ውስጥ የተዘረጉ የስነ ኣእምሮ ክሮችን ባለመፈተሽ፤ ነገሮችን ካመረዳት የመጣ ድምዳሜ ስለሆነ በዚህ እኔ በምላችሁ አትኩሮታችሁን አገናዝቡት። ተቃዋሚ መሪዎች ለክስተቱ (መለስ ለዘብተኛ ዲክታቶረ ብቻ አድርገው በማስተማር፤ ትክክለኛ ማንነቱን፤ ማን መሆኑን በሚገባ በሕዝቡ ላይ ጠለቅ ያለ ትምህርት ባለመስጠታቸው በራሳቸው እና በሕዝቡ ውስ  የታየው አሳፋሪ “ትሬይት”/ባሕሪ) ተጠያቂዎች ናቸው።
ዚህ ሌላ ቀን እንነጋገርበታለን ፤ወደ ሚቀጥለው እናምራ።

በመለስ ሞት ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!
Birtukan cults fooling themselves as she was wrongly depicted on the above cartoon, the fact is her heart towards the Ethiopian enemy Meles Zenawi never  was as her cults thought she was. What a shameless cults using religious symbol in a such disgraceful politic. This was how some opposition leaders and their followers were fooling themselves as well the people. The fact is clear now on Bertukan's and other so called opposition politicians on their interview after Meles died. The Stockholm syndrome is clearly playing its effect on each of those sorry A.. elements!

Mengistu killed Ethiopians: Meles is killing Ethiopia” The not-so late Historian Dr.Aleme Eshete.
 *The name rendition—“seleM iwaneZ”--in the title of this article, is a mild metaphor for this Ethiopian writer’s indignation over the sacred Ethiopian flag held upside down by the ruler of the country at a summit event in Kenya (March 2, 2012) in the presence of the heads of states of Kenya and South Sudan. That said “seleM iwaneZ” is otherwise known as Meles Zenawi.” (Historian Professor Negussay Ayele)

"When they (TPLF) entered Addis Ababa on May 28, 1991 Meles and his gang had taken down the Ethiopian flag at the Ministry of Foreign Affairs located right across from the Hilton hotel, and hoisted the TPLF flag for at least twenty-four hours. Later on, none other than Meles himself uttered that he is tired of sound bites about the Ethiopian flag as nothing but Cherq, which accurately translates to ‘rag.’ " (professor Negussay Ayele)
“ዶ/ ቴዎድሮስ የበለጠ እንዲረዱልኝ፣ 1993 . የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር በቀጥታ የኢትዮጵያ ሀብት የወያኔ ካድሬዎች ቁጥጥር ስር ውስጥ ነው መውደቅ የጀመረው። ምርታማነትንና ውድድርን ለማሳደግና ለመጨመር እየተባለ ወደ ግላዊነት የተዘዋወረው የመንግስት ሀብት የወያኔን ካድሬዎች ያደለበ ነው። በአቶ መለስና በግብረ-አበሮቻቸው ዕምነት ኢትዮጵያን መቆጣጠር የሚችሉት ሀብቷን ሲቆጣጠሩ ብቻ ነው። ስለዚህም ድርጊታቸው ሁሉ በኢንዱስትሪ ተከላና በቴክኖሎጂ ምጥቀት ላይ ያተኮረ ሳይሆን ቶሎ ቶሎ ትርፍን ወደ ሚያመጣ ወደ ንግድና ወደ አንዳንድ አገልግሎት መስኮች ላይ መሰማራት ነበር። ይህንን ለማድረግ ደግሞ የሚቀናቀኗቸውን በሙሉ ማጥፋት፣ ወይም ደግሞ እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ብቻ እንዲሄዱ በማድረግ በሙስና ዓለም ውስጥ እንዲዘፍቁ ማድረግ ነበር። በዚህ ዐይነት የሞነቴሪ ፖሊሲ ላይ የተመረኮዘ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተ የሀብት ዘረፋን አስከትሏል።” (የአቶ መለስ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን ዘመናዊ ማድረግ ወይስ ማወላገድና ማዘበራረቅ ነበር” በሚል ርዕስ Dr. ፈቃዱ በቀለ መልስ / ቴዎድሮስ ኪሮስ Ethiopian Observer ላይ “Meles Zenawi and the unfinished project of Ethiopian Modernity” ለሚለው ጽሑፍ ከተሰጠ  የተቀነጨበ)
 
 እንደምን አላችሁ? በምን ልጀምር? ግንቦት 7 ብሎ ራሱን በሰየመ “ፎሽ -ፎሽ” ተቃዋሚ ልጀምር? ወይንስ በሻዕቢያው ጋዜጠኛ ተስፋየ ገብረአብ የሰሞኑን ዓይን ባወጣው ውሸቱ?
እስኪ በተስፋየ ልጀምር። የአክሱም ጽዮን ቤተመቅደሳችንን የሚዘልፍ ሳሞራ የኑስን ምክንያት ተጠቅሞ ጂሃዳዊ ተልዕኮውን በማስተላለፍ ሳሞራን  የሚከስስ የፈጠራ ውሸቱን ሳነብ የዚህ ልጅ ሕሊና ምን ያህል የቆሰለ ግማታም ሕሊና እንዳለው ይገርማል። ይህ ሻዕቢያ ወኪል እያመጣ የሚያስነብበን “የኢሳቱ” ካረንተ አፈይርስ ‘ተክሌ” በኢካዴፍ ዌብ ሳይት የለጠፈለትን እንዲህ ይነበባል፤፡

“ሳሞራ የኑስ ልጅ እያለ አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተክርስቲያን እየገባ፣አላሁ ዋአክበር!!” እያለ ቄሶችን ማበሳጨት ይወድ ነበር አሉ። ይህችን ታሪክ ስሰማ በጣም ነው የሳቅሁት። እንዲህ ያሉ ኮሚክ ብሽሽቆች ቀልቤን ይሰርቁታል። ሳሞራ ደግ አደረገ። እነሱስ ቢሆኑ አክሱም ላይ መስጊድ እንዳይሰራ ለምን ይከለክላሉ? የሆነው ሆኖ ጀብደኛው ሳሞራ ይብቃው። ደክሞታል፣ ይረፍ።” ይላል ይህ ቁስላም ሻዕቢያ።

ሳሞራ እና እኔ አብረን ነው ያደግነው። ተስፋየ ሻዕቢያ የፈጠረው ወሬ “ይህ ታሪክ ስሰማ” ብሏል፤። ይህ “ታሪክ” ብሎ የጠቀሰው ደግሞ “አስደስቶታል። በሳቅም ፈንድቷል። ለወጥወጥ አድርጎ ደግሞ “ብሽሽቅ፤ ኮሞዲ” ይለዋል። አለፍ ብሎ ደግሞ የአክሱም ታሪክ ጠለቅ ብሎ ባለማወቁ  ክርስትያኑ እና አስላሙ ለማጋጨት የሞኞች ፖለቲካ ለመጠቀም ሞክሯል። እንኳን ሳሞራ እኔ በግል የማውቀው አብሮ አደግ ጓደኛችን ይቅር እና ሌሎች እስላሞችም ቢሆን እንዲህ ያለ ብልግና አስበውትም ተሰምቶም አይታወቅም። ታዲያ ይህ ሻዕቢያ “ታሪክ” አገኘሁ ብሎ የቅድስት ጽላቷን ክብር በእንደዚህ  ይነት አዋራጅ “ቀልድ እና ታሪክ” የሚለው እሱ መቅደሳችንን ጂሃዳዊ የመዝለፉ ዘመቻው ተስፋየ ማን ነው የላከው?  

ሻዕቢያው “ፕሮተስታንት አማኝ” ሊሆን  ወይንም ንደ የቀድሞ ጌታው ሃይማኖተ ቢስም ሊሆን ይችላል ነገር ግን ያዘዙት እነማን መሆናቸው ከናንተ የሚሰወር አይመስለኝም። እሱ ምን አደረገ፡ አላጠፍም እኮ? ቅድስት ቤተክርስትያናችን፤ ኢትዮጵያዊያን ነገሥታቶቻችንን ፤የታሪክ አዋቂዎቻችን እና አዛውንቶችን እያስሰደቡብን ያሉት በስመ ኢትዮጵያ የሚበርዙትን የኢሳት ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው የካረንት አፈይርስ ፓል ቶክ እና ዌብሳይት ባለቤት ተክለ የተባለው ለሰንደቃላማ ክብር የሌለው “ጸረ አማራ እና ጸረ ትግሬ” አፍቃሬ ሻዕቢያ እና ኦነግ የሆነ ጋጠ ወጥ ነው ይህ ሁሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ውርደት አንዲዘመትብን እያደረገ ያለው።

“ሳሞራ የኑስ አክሱም ቤተመቅደስ ገብቶ እንዲህ ያለ የአክራሪዎች እና የጃሃዲስቶቹ ጋጠ ወጥ ባሕሪ መሳለቁ  አስደስቶኛል፤ ደግ አደረገ” እያለ ያለየው፤ያልሰማው፤የማያውቀውን የጸረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሻዕቢያ የፈጠራ የመንደር ወሬ ጽፎ ሲልክለት ይህ ጉደኛ ዌብሳይት በኢትዮጵያዊያን እንዲነበብ መፍቀዱ የመጀመሪያው  አይደለም። ካሁን በፊትም እኮ “ሁለት ሦስት ተቃዋሚ መሪዎች ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ግብረ ሰዶም ተፈጽሞባቸዋል” ሲል አስነብቦናል። ስያትል ውስጥ “ሰንደቃላማችን የኦነጎቹ ባንዴራ ካልተውለበለበ ብሔራዊ ሰንደቃላማችን ቢደበቅ ባይደበቅ ስሜት አይሰጠኝም፤ ቢቃጠልም ባይቃጠልም ጉዳየ አይደለም “ዊ አር ኢን አሜሪካ ኖት ኢን ኢትዮጵያ” በማለት በራዲዮ ተናግሯል። ይህ ደግሞ ካሁን በፊት  እቅርቤላችሗለሁ። ይህ የጂሃዲስት  ጋጠ ወጥነት ጽሑፍ ግን  ዓይን ያወጣ ድፍረት የአክሱም ልጆች እና የተዋህዶ ቤተክርስትያን ተከታዮች  ይህ ጉድ ካነበባችሁት በሗላ ትዕግስት ይኑራችሁ እላለሁ። ድረገጹ ጽሑፉን እንዲያነሳ መጠየቅ ይቻል ነበር፤ (አዘጋጁ የኢሳት ጋዜጠኛው ‘ተክሌ’ ነው) ሆኖም እሱም ሰንደቃላማችንም ሆነ የትግሬ ሕዝብ ጠቅላላ የሚዘልፍ ፓል ቶክ (የካረንት አፈይረስ) ባለቤት ስለሆነ ስሜት አይሰጠውም እና ጊዜአችሁን አታባክኑ። ብቻ ለታሪክ ማስታወሻችሁ እንዲሆን መዝግቡት።

ወደ ሁለተኛው ጉደኛ የመንደር ዜና እንሸጋገር እናንተየ! የግንቦት 7  ትኩስ “ፎሽ ፎሽ” ሰምታችሁልኛል? (ደግሞ “ፎሽ ፎሽ” ምንድ ነው እንዳትሉኝ (እናቴ እንደ ነገረቺኝ/እኔም ገብገብ ተብሎ በሚጠራ ከከተማው ትንሽ ወጣ ብሎ በሚገኘው ገጠር “ተበብ” “ችቦ ጭራ  “ጭዕንዶግ” “እሸት”  እና  “ሃምባሃምቦ” ለቀማ ስሄድ ንዳየሁት ማሳ ላይ ተጥሎ የሚታይ ስትይዘው “ቡን ቡን”  የሚል “የቡና ዱቄት” የሚመስል "የቀበሮ ፈስ የያዘ ትንሽ የዱቄት ከረጢት" ነው)። ዜናውን ካልሰማችሁ የግንቦት 7  “ፎሽ ፎሽ”  ወሬ አዳማቂ የሆነው አሁንም ያው ከላይ የጠቀስኩት “ተከሌ” በሚያዘጋጀው “ካረንት አፌርስ” (ኢካዴፍ) የተባለው ድረገፅ እና ፓልቶክ” የለጠፈውን ሌላው አስቂኙ ዜና አንብባችሁልኟል? ካላነበባችሁት እነሆ፤-

“Senior leaders of Ginbot7, Abebe Bogale and Dr. Tadesse Biru, disclosed to ESAT that their movement is working expeditiously to bring EPRDF to the negotiation table or remove it from power altogether.” “…Ginbot7 of today is a movement with a strong and efficient organizational structure said the confident duo.

ESAT will broadcast the full interview in the coming days.”

አየ ኢሳት፡ ምን ያሰማን ይሆን ደግሞ ብርሃኑን ጎትቶ? እርግጠኛ ነኝ የግንቦት 7 መሪዎችን ሰውነት  የምታውቁ ዜናውን ስታነብቡ ያስቃል። ግን እባካችሁ እንዳትስቁ። የሄውላችሁ ወያኔ ዕድሜውን እንዴት ልያስረዝሙብን እንደተዘጋጁ እና የሕዝቡን ተቃዋሚነት ስሜት  እንዴት ዛሬም እምነት እንዲያጣ  እያደረጉ እንዳሉ ማንም ተራ ሕሊና ሊገምተው በሚችለው ተራ ወሬያቸው ተቃዋሚው  ዋጋ ቢስ እያደረጉት እንደሆነ አሳፋሪ ዜናቸውን ይሄውላችሁ።አሁን በዚህ ብዙ ማለት አልችልም፡ ግንቦት 7 የፊታችን ቅዳሜ ወያኔንን ጠራርጎ በማስወገድ “ሥልጣኑን ስለሚይዝ” እሱ እና መሰሎቹ “መንግሥት ለመሆን” የመሃላ ቀን ሲፈጽሙ ጋዜጠኛቸው የሆነው የብርሃኑ ነጋ ወዳጅ ሻዕቢያው ተስፋየ ገብረአብ “ዝርዝር ዜናው” ሲዘግብልን ለእዛው ሰሞን ላቆይላችሁ እና  ርዕሱ በተመለከተ ላይ ላተኩር። ወይ አገሬ ሓጢያትሽ በዛ እኮ!

ትግላችን ከወያኔ ጋርም ብቻ ሳይሆን ዛሬም በተቃዋሚ ስም ገብተው ትግሉን ከሚበርዙት በመለስ ዜናዊ ሕልፈት ልባቸው የደማ፤ ወያኔን ለክፋት የማይሰጡት፤ ልባቸው የሚቀልጥ ፈሪዎች፤ ውሸታሞች፤ አድርባዮች እና አክራሪዎች ጋር እንደሚሆን ከብዙ አመት በፊት የጻፍኩትን ታስታውሱ እንደሆነ ዛሬም ይህንኑ ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ።  ይህ ቃሌ እንደትንቢት ዘግቡት። ልብ እና ድፈረቱ አንሷት በሬን እየተከተለች የበሬን ቆለጥ ይወድቅልኝ ይሆናል ብላ በመቋመጥ እየተከተለች  ምራቋ ሞልቶ “የከረጢት ፈስ እንደምትለቀው” ሃሞተ ቢስ ቀበሮ፡ ዛሬም ምንም  ሳያፍሩ የነፈሰውን ያረጀ ያፈጀ  “ፎሽ ፎሻቸውን” ሲረጩ ማየት መቸ ልብ እንደሚገዙ ለኔ በጣም እየገረመኝ ነው።

የፎሽ  ፎሾቹ የሰሞኑ ዜና ምን ይመስል እንደነበር ከላይ አስነብቤአችለሁ፡
ይሄ ዩኒቨርሲቲ የሚባል ጉደኛ አዳራሽ ምን እያስተማረ ዶከተርነት እንደሚሰጣቸው እኔ ግራ እየገባኝ መጥቷል::
አሁን በመለስ ሞት  ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!
 ወደ እሚለው ርዕስ እንግባ
ተቃዋሚ ሓዘንተኞች ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ምንስ ሆነው ነው ልባቸው የተነካው? እንዴትስ በመለስ ሞት  ልባቸሁ ጥቁር የለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን! ለምንስ ነው የመለስ ሐዘን እየገለጹ ያሉት?
 Eric Niller የተባለ ጸሐፊ “How Dictators Keep Control” በሚለው ትችቱ ውስጥ “አምባገነኖች” ሕብረተሰቡን በፍርሃት ማዕበል ውስጥ በመክተት ፤የሚታየው ግልጽ እና ስውር የሕብረተሰቡ የሕሊና አለመመቻቸት ደረጃ በደረጃ በመከታተል መረጃዎችን እየተቆጣጠረ የሕብረተሰቡን ጤናማ ሕሊና ቀውስ ውስጥ በመክተት አምባ ገነኑ በራሱ ላይ አንዳች የተፈጥሮ አደጋ ሲደርስበት የሕልውናቸው ምሰሶ  እንደነበር በመዘከር ከእርሱ ሕልፈት በሗላ የሚመጣው ህይወት የተደረመሰ ገደል መስሎ እንደሚታያቸው እስከመምሰል ደረጃ የሚያደርስ የሕሊና ብልሽት በግለሰብም ሆነ በጣምራ እንዲንፀባረቅ የማድርግ ልዩ ባሕሪ እንዳለው ይናገራል።

ኤሪክ ናይለር  “How Dictators Keep Control” በሚለው ጽሑፉ እንዲህ ይላል፡ …..Dictators also exploit a well-known instinct for most people to seek protection from a strong leader, according to Alice LoCicero, a Cambridge, Mass.-based clinical psychologist and researcher on leadership and terrorism

"Our behavior is still affected by what went on thousands of years ago," LoCicero said. "It's easier to understand why it's adaptive and common for people to bond to powerful leaders. In Darwinian evolution, the people who bonded with the leader survived. That instinct got passed along." ትላለች በማለት፤-

አብዛኛው የዛሬዋ የዓለም ሕብረተሰብ ከሺ አመታት በፊት ከነበሩት ሕብረተሰቦች ለአምባገነኖች አዘኔታም ሆነ አምልኮት ሲያሳየው ከነበረው ባሕሪ ብዙ የማይለይ መሆኑን እና በዳርዊንያን ዘገምተኛ ለውጥ እንደተመለከተውም ከአምባገነኖች/ከሃይለኞች ጋር የተጠጋ ቡድን/ሕዝብ/ግለሰብ ባጭር የመቀጨት ሕይወቱ የመነመነ በመሆኑ፤ ተለሳልሶም፤ተሞዳሙዶም ሆነ ካንገት በላይ እያጎነበሰም ቢሆን ሕየወቱን የማቆየት ዕድል ስለሚኖረው ነፃነቱን ከሚገፈው አምባገነን ጋር የመጠጋት ባሕሪው ጥንትም ዛሬም በሰፊው የታየ እና የሚታይ የሕብረተሰብ ባሕሪ ነው። ይላል በግርድፍ ይዘቱ ሲተረጐም።

ባለፈው ሰሞን ከአምባገነን ወይንም መብቱን ከገፈፈው ግለሰብም ሆነ ቡድን ሰዎች ለምን እንደሚቆራኙ እና በከፋው መልኩም ለምን እንደሚወዷቸው ወይንም በዳያቸው ክፍት ሲደርስበት የፈለገው ሽፋን ይስጡት ለምን በሃዘን እንደሚወረሩ  “ሰቶክሆልም ሲንድሮም” በተባለ የሕሊና የአስተሳሰብ ንቅዘት የመነጨ መሆኑን ከሞላ ጎደል እንድትመለከቱት አቅርቤው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ካለፈው ሰሞን የቀጠለው የዚያ ክፍል 2 ዛሬ እናጠቃልላለን። ዛሬ የምንመለከተው በታወቁት የተቃዋሚ ግለሰዎች በብርቱካን መዲቅሳ፤በልደቱ አያሌው፤ እና አንድነት በወከሉ አንድ ግለሰብ መለስን አስመለክተው በተደጋጋሚ በየዜናው ማሰራጫ ሲጠየቁ የሰጡት መልስ የኢትዮጵያን ሕብረተሰብ ከወያኔ ካድሬዎች በከፋ መልኩ የሚበክል አፍራሽ መስመር ሲናገሩ በመቅረጸ ድምፅ የተመዘገበው ለታሪክ ዘጋቢዎችም ሆነ ለፖለቲካ ተንታኞች እንዲሁም ለማድመጥ ዕድሉን ያላገኙ አንባቢዎቼ እንዲመለከቱት እና እንዲዘግቡት የተናገሩትን አንኳር አንኳር ንግግሮቻቸውን አቀርብላችሗለሁ።

እንዚህ ግለሰዎች በመለስ ዜናዎ ሞት ማዘን “ባሕላችን ነው፤ ጨዋነት ነው”…ከገባንበት አዘቅት ለመውጣት...
ግልጽ በሆኑ  ለድረድር በማይገቡ አገራዊ እሴቶች ላይ መገበርም ካለብን ገብሮ መቻቻል፤ የፋሺስቶች እቅድ የሚተገብር ጸረ አማራ የወያኔ አስተማሪ እና መሪ የነበረ ግለሰብ  የቀሩትን በደብተሩ የዘገባቸው ብዙ አገራዊ ጥፋቶችን ሳያስከትል በፈጣሪ ቅጣት በሞት ሲለይ “ሰው ነውና እንደሰው እንዘን፤ አገራዊ ባሕላችን ስለሆነም  ከመካከላችን በመለየቱ የተሰማን ሓዘን ጥልቅ ነው” ወዘተ.. የሚሏቸው ማመካኛ ምክንያቶቻቸው ቢላበሱም ሰዎቹ በመለስ ዜናዊ የሕሊና ነጠቃ እንደተጠቁ ግልጽ ነው።

የወያኔ ነገር ሲነሳ ልባቸው ጨክኖ የማይጨክነው፤ ወያኔን ለክፋት የማይሰጡ  አንዳንድ ታዋቂ ተቃዋሚዎች እያሉን ያሉት፤ መለስ ዜናዊ የዲሞክራሲ “ጉድለት” የታየበት ቢሆንም የምጣኔ ዕድገት አስገኝቶልናል እና (በፋሺስታዊ) በአስተዳደሩ ወቅት ያስመዘገበው የምጣኔ ዕድገት ውጤት ምስጋናውን እየቸርን ከኛ በመለየቱ ልባችና አዝኗል። እያሉን ነው። ለመሆኑ ከወያኔ/መለስ የባሱ ፋሺስቶች አገራቸውን ሲገዙ ከመለስ ዜናዊ በበለጠ ዕድገት ዘርግተው እንደነበር ያውቃሉ? ሌላ ቀርቶ ጣሊያን አገራችን ሲወር በ 5 ዓመት ውስጥ አንዳንድ ነገሮች ገንብቶ እንደነበር ያውቁታል? ኤርትራኖችን በመካኒክነት እና በሕንጻ ግመበኛነት ስራ ፤ፋቭሪካ….ጨርቃጨርቅ በመሳሰሉት አስተምሮ የሄደው ፋሺስት ነው። ታዲያ ለሙሶሎ ምሳጋና ይቸረው ማለት አስነዋሪ መሆኑን አያውቁትም ወይስ አማራን እና አማርኛ ቋንቋን እንዲሁም ቤተክርስትያንን በጠላትነት ፈርጆ በቋንቋ አስተዳዳር ከልሎ አንድ አገር በ5 ኮሎኒ ከፍሎ፤ባንዴራ ለማሰራት ያዋቀረው ፋሺስቱ የሙሶሎኒ መርሆ ከመለስ ዜናዊ የቋንቋ ክልል /አቶኖሚ እንዴት አይመሳሰልም? ለመሆኑ አመርኛ የተናገረ የአዲስ ኣበባ አንደኛ ደረጃ ታዳጊ ሕፃናት ትምህርት ቤት “I am stupid!!!!I am Stupid!!! ደደብበ ነኝ!!! ደደብበ ነኝ!!! በማለት 100 ጊዜ በደብተሩ ላይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲጽፍ ወይንም “ጀርባውን ወደ ተማሪ ፤ፊቱን ወደ ግድግዳ አድርጎ በቅጣት እንዲቆም  መደረጉ አዲስ አበባ ውስጥ በተደረጉት 4 የትምህርት ተቋማት ውስጥ ድርጊቱ እንደተፈጸመ ያዲስ አበባ ኗሪ የሆኑት በዚህ ጥናት ያደረጉ  ከትምህርት ተቋም ተመራማሪ እና መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊ ዜጋ የጀርመን ራዲዩን የአማርኛ ዝግጅት ክፍል ካዲስ አበባ ስልክ ደውሎ ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸው በጥናት እንደተረጋገጠ ያውቃሉ? አንድ ተማሪ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ከ1ኛ ደረጃ እስከ 9/10 (ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) እስኪደርስ  ድረስ እንዳይማር እና ከአፀደ ሕፃናት ት/ቤት ጀምሮ እንግሊዝኛ እና ትግርኛ ብቻ እንዲማሩ ሃያ አንድ አመት ሙሉ  አማርኛ በሕግ ታግዶ በምትኩ ባገሪቱ በመላ እንግሊዝኛ መተካቱ ያወቃሉ? ይህ ሁሉ የማን ፖሊሲ ነው? ፏሺስት ከዚህ ወዲያ ምን ፈጸመ?
ለሞሶሊ እና ለግራዘያኒ/ሂትለር/ለኪም ኤል ሱንግ/ለመለስ ዜናዊ የሚያዝን የሚያለቅስ ኢትዮጵያዊም ሆነ ማንኛውም ፍጡር በሕሊና ቀውስ ውስጥ የተጠመደ ሕብረተሰ ብቻ ነው። (ለምሳሌ የትግራይ የኪነት አባሎች ያሳዩትን አስገራሚ ጉድ ብትመለከቱ  እንደ "ፆመ አርብዓ" ባሕታዊ በጉልበታቸው ተምበርክከው መሬት ለመሬት እየተሳቡ እያለቀሱ ግምባራቸው ወደ መሬት እያጋጩ  እየተንፏቀቁ ወደ ዛርነት/ውቃቢ/ዳልቻ (ሂሥቴሪክ) ተለውጠው የማሰብ ሕሊናቸው ተገፍፎ ማየት አሳሳቢ በሆነ የሕሊና ቀውስ የገባ ሕብረተሰብ መሆኑን አጋጣሚውን ማጤን ያስፈልጋል)።

 መለስ ዜናዊ ከሂትለር ጋር ከሙሶሎኒ ጋር የሚያመሳስሉት ብዙ ባሕሪዎች አሉት። ያውም የናዚው ፓርቲ/ሂትለር ጀርመን ገብታበት ከነበረቺው ጥልቅ የምጣኔ ቀውስ አውጥቶ በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሦስት አመቶች የዕድገት እምርታ በማሳየት የሕዝቡ ሕሊና ሰልቦ እንደገና ያልታዩ የስልጣኔ ዘመናዊ ጥበቦችን (ቅመሞችን፤የራዲዮ ምስጢሮችን፤መገናኛዎችን ሕንጻዎችን… የዓለም ዓቀፍ የስፖርት እና የንግድ ትዕይንቶችን በማስተናገድ፤ዘመናዊ  መኪኖችን……የመሳሰሉ) በማስተዋወቅ የሕዝቡን ሕሊና ሰልቧል (እንደ መለስ በቢሊዮን ዶላሮች ለሃያ ዓመታት ከጌቶቹ በብድርም ሆነ በምፅዋት “ትልልቆቹ የመንግሥት ሌቦች” የሚላቸውን እራሱ ያስቀመጣቸው ሌቦቹ  እንደሚያድላቸው ሳይሆን) ። ሥልጣንም ለመያዝ  የጀርመን ናዚ የሕዝብ ድምፅ መርጫን አስመልክቶ እንኳ ብንመለከት ሂትለር በሕዳር 1932 (34.1%) ከማንኛቸውም ተቀናቃኞቹ በላይ የሕዝብ ድምፅ በማግኘት “በሕጋዊ” መንገድ ነበር ወደ ፓርላማው ገብቶ  አምባገነናዊ ስራው የፈጸመው። የወያኔው መሪ “የነበረው” መለስ ዜናዊ ግን የሕዝብ ድምፅ በመስረቅ 99.6%  ድምፅ አገኘሁ ብሎ ወጣት እና አዛውንቶችን ባንክ ዘራፊዎች ናቸው ብሎ በጥይት አስጨፍጭፎ “ፖሊሶቻችን የሰላማዊ ሰልፈኞች አድማ አያያዝ ስልጠና ስላልወሰዱ ነው ይህ ሁሉ ግድያ ሊከሰት የቻለው” ብሎ ሳያፍር ለአልጀዚራ ነበር የተናገረው።

 ይህ ጉደኛ ሰው ሲሞት ልባችን ለሁለት ታጠፈ፤አዘነ፤ለቀብሩ ባለመገኘታችን እጅግ ይቆጨናል፤ እናዝናለን….እንግዲህ ወዲህ ጠቅላይ ምኒስትሩ በሞት ስለተለዩን ስለ እሳቸው አምባገነንነት፤ሃጢያት ወዘተ…..ለሃያ አመት ስለተናገርን፤እሳቸው በሌሉበት መናገር ተገቢ ስላላሆነ እንገዲህ አፋችን እንዝጋ…….ይበቃል…..ወዘተ…..የሚሉን የተቃዋሚ ተብየ ሰዎችን አንደበት ለታሪክ ዘገባ (ለማስታወሻችሁ) እንዲሆን እነሆ አንብቡ እና ኢትዮጵያ ለሃያ አመት በእነዚ የፋሺሰት 9 (ዘጠኝ)ባንዴራ አውለብላቢ የዘመናችን ሶላተቶዎች  ስትረገጥ ተቃዋሚ ነን የሚሉ አንዳንድ ግለሰቦች በቀደዱት የሽንፈት እና የተጐንባሽነት መንገድ ሕዝቡ እንደበታቸውን እየተከተለ ለዚህ አሳፋሪ የሕሊና ነጠቃ እንዴት አንደበቃ መረጃው እነሆ።

የቶኒ ብሌር ሊበራልና ዲሞክራቶች (“ላብ- ላብ” ይሏቸዋል አንግሊዞች) ለመጪዋ ኢትዮጵያ እያዘጋጁልን ያለውን እንግሊዝ ሰራሽ “ኢትዮጵያዊው-ሊበራል ፓርቲ” ልደቱ አያሌው ስለ መለስ ዜናዊ የሚለንን አድምጡልኝ። እርግጥ ልደቱ ተቃዋሚ አይደለም ከ“ሰለሞን ስቶክሆልም” (ሰለሞን ተካልኝ) የሚለየው ምን ነገር አለ? ልትሉኝ ይሆናል፤ ነገር ግን ልደቱ አያሌው ተቃዋሚ ለመሆን የሚፈልግ “የመሟገቻ ነጥቦቹ  የመቀመር ችሎታ ያለው” ቢሆንም።  መለስ ዜናዊ ሰው እየረሸነም ቢሆን ፤እያሰረንም፤ እያንገላታን እና እየሸጠን እና እያስሰደደንም ቢሆን “መለስን አመስግኑ” “በክፉ አይን አትዩት” የሚለን ሕሊናው የተነጠቀ፤ “በመለስ ዘመን ተወልዶ(?እንበለው ) ያደገ” ግራ የተጋባ ወጣት ስለሆነ ለማንኛውም ዋናው “ሞተራቸው ተነጥቀው” ባዶ የቀሩት ወያኔዎች ሥልጣን እንደሚሰጡት ስለምገምት እሱ እና ከእርሱ ጋር ያሉት ቡድኖቹ በጥንቃቄ እንድታጤኗቸው ለታሪክ ይመቻችሁ ዘንድ እነሆ። (ስየ አብርሃን እና የተቀሩት የወያኔ ትርፍ ጭነቶች ‘አንዳንዶቹ’ በወያኔ አዲስ የስልጣን ሽግሽግ እንደሚቀመሩ አትጠራጠሩ።የጊዜ ጉዳይ እንጂ) ምምዕርራ/ ምትዕርራይ ይለዋል ወያኔ “ማሸጋሸግ” ማለት ነው። ሰለጠንኩ ካለ ደግሞ “ምትሕንፋጽ” ይለዋል (ማዳቀል ማለት ነው። ለክፋት የማይሰጡ ከዚህም ከዚያም ማለት ነው።  ልክ በየነ ጴጥሮስ ለትምህርት ሚኒስቴር ሾሞ እንደተጠቀመበት ስልት ማለት ነው። ይሄ “በኢሕአዴግ” (ወያኔ) ውስጥ እርስ በርስ ፍጥኛ መሳሳብ አለ የሚሏችሁ አትመኗቸው፤ “ፌሶ” ወሬ ነው። ወያኔ እንኳን አሁን አንድነታቸውን በበለጠ በሚፈልጉበት ሰዓት እና ሞተራቸውን አጥተው ቀርቶ ድሮም ብሔረተኛ በክፉ ቀን የራሱን ሙጫ (ማስቲሺ./ ክሬዚ ግሉ) በማጠናከር የታወቀ ነው። በዛው የሚቋምጡ ካሉ የበሬ ቆለጥ እራሱ ይወድቅልኛል ብላ የበሬን ሗሊት ሗሊት እንደምትከተል ገራ ገር ቀበሮነት ይቅር።

ልደቱ ምንድ ነው የሚለው?

"ድሬ ቱብ" የተባለው የወያኔ የድምፀ ስዕል ድረገጽ ልደቱ አያሌውን (ወይንም በቅጽል ስሙ እንደሚጠሩት “ልድቱ ክህደቱ”) በፋሺስቱ የወያኔ ትግራይ መሪ በመለስ ዜናዊ ሞት ምክንያት ምን እንደተሰማው ለማወቅ የሚከተለው ጥያቄ አቅርቦለት ነበር።

አቶ ልደቱ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ሕልፈተ ሞት በግልህ የተሰማህ ስሜት ምንድነው?
ልደቱ አያሌው ፡
እንግዲህ አዳምጠህ ከሆነ ታመውም እያለ፤ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ  ተጠይቄ ያኔ ነው አቋሜን ግልጽ ያደረግኩ። ያኔ ከሕመማቸው ተሽሎአቸው ከሕመማቸው እንዲፈወሱ እና ደህና እንዲሆኑ ነው ያኔ ምኞቴ የነበረው።…ውጭ አገር በመሆኔ በቀብራቸው ለመገኘት ባለመገኘቴ በጣም አዝኛለሁ። ከሦስት ዓመት በፊት የጻፍኩት መጽሐፌን አየተህ ከሆነ ተቃዋሚው ከሚያያቸው ዓይን ለየት ባለ ነበር  ሳያቸው የነበረ።….ለኢትዮጵያ ሕዝብም መንግሥትም መጽናናት እንዲሠጣቸው እመኛለሁ።

በዚህ ወቅት ባይታጡ ምናልባት በሃገሪቱ በጐ ነገር ለወደፊት በተሻለ ሁኔታ ለማበርከት ዕድል ይኖራቸው ነበር ብየ አስባለሁ። ….”ኢትዮጵያ አንድ ሰው” አጣች “ ብየ አስባለሁ። በጣም ነው ያዘንኩት።

ልደቱ አያሌው ስለ የመለስ የፓርለማ ባሕሪ ፤ተጠይቆ  (ሰብአዊነቱን “ሰውነታቸው” ይለዋል በእሱ አገላለጽ) በፓርላማ ክርክር ከሚያሳየው "ብልግና" (ልደቱ በቃል ሊገልጸው የፈራው የመለስ የስድብ እና መድረክ ለብቻ የመያዝ ጠባይ…..) እንዲህ ይገልጸዋል።

“ከዚያ  ይነት መድረክ ውጭ ስታገኛቸው “ሰውነታቸውን” (ሰብአዊነቱን “ቀናነቱን፤ደግነቱን ፤ተግባቢነቱን፤የዋህነቱን….) የምታይበት ወቅት ያኔ ነው።  እና ያኔ እሳቸውን የምናይበትን ዓይን ቀደም ብሎ ቢለወጥ ኖሮ ምናልባትም ያገሪቱ ችግር አካል  ሳይሆን የመፍተሔ አካልም አድርገናቸው አይተናቸው ቢሆን ኖሮ “ተገቢውን እውቅና እና ምስጋና ሰጥተናቸው ቦሆን ኖሮ”  ላመበት ዓላማ ሙሉ ሕይወታቸውን፤ጊዜያቸውን፤ጉልበታቸውን ፤እውቀታቸውን የሰጡ ሰው ናቸው። ይሄ ማንም ሰው ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ አይደለም። ይሄ የሚያስቀና ነገር ነው

ባንድ በኩል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በልማት መልክ የሰሯቸው ስራዎች ቀላል አይደሉም።..የኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት ረገድ፡(ልብ በሉ አላደገም፤ በወያኔ ተቋማት የተሰነገ ምጣኔ ሃብት ነው… ሲለን የነበረውን አስታውሱ፤ (ከደጀን ራዲዮ (ትግርኛ ጣቢያ) በአማርኛ ያደረገው ቃለ ምልልስ ልብ ይለዋል።) ከምርጫው በሗላ ነው እንዲህ ያለው።) በአካባቢ እና በዓለም አቀፍም ኢትዮጵያ ተቀባይነት እንዲኖራት የበለጠ እንዲያድግ በማድረግ ረገድ ያደረጓቸው አስተዋጽኦዎች፤ ቀላሎች ናቸው ብየ አላምንም። በሰብአዊነት እና በዲሞክራሲ ያለው "ጉድለት" እንደተበቀ ሆኖ (ልደቱ “ጉድለት” ነው የሚለው እንጂ በዲሞክራሲ እና በሰብአዊ መብቶች ላይ የተፈጸሙ “የግድያ ወንጀሎች፤የጎሳ ማጽዳት ወንጀሎች…)” እንደወንጀል ሳይሆን እንደ “ጉድለት” ነው የሚመለከታቸው።) በጐ ስራዎች በሰሩት ስራዎቻቸው ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብዙ ጠቅመዋል ብየ ነው የማምነው።

እና (መለስ ዜናዊን ለማወቅ )በነበሩኝ አጋጣሚዎች ቀላል የማይባል እውቀት የነበራቸው ሰው እንደነበሩ፤ ፖለቲካ (?) የሚያወቁ እንደሆነ፤ ያመራር (ብቃታቸው (?)) በጣም የላቀ እንደሆነ በጣም አይቻለሁ።….በነበራቸው እምነት በነረበራቸው ጊዜ እና ሁኔታ ቀላል የማይባል ስራ ለኢትዮጵያ ሰርተዋል።ሕዝቡም በፖለቲካ የሚደግፋቸውም የማይደግፋቸውም ሐዘኑን እየገለጸ ያለው ያለምክንያት አይመስለኝም።ጥሩ ነገር እንደሰሩ በማየት ነው ብየ አምናለሁ።

ድሬ ቱብ፤ ጥያቄ፤-

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማረፋቸው ምክንያት የዚች አገር የወደፊት  ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል ብለህ ታምናለህ?

ልደቱ አያሌው፦

እኔ እንግዲህ መጽሐፌን አንብበኸው መሆንክን አለመሆንክን አለውቅም፡ ኢሕአዴግ በስልጣን እስከቀጠለ ድረስ እሳቸው ኖሮ ቢኖሩ ለአገሪቱ  የተሻለ ይሆን ነበር ብየ አምናለሁ። ዛሬ የምገልጸው አቋሜ አይደለም የዛሬ ሦስት አመት የገለጽኩት አቋሜ ነው። …..አስቀድሜ ይህ ይፈጠራል ብየ ልልህ አልችልም። ……

ጥያቄ ፤-በመጨረሻ የምትለው ካለ?

ተቃዋሚው ከጽንፈኛነት አመለካከቱ መውጣት አለበት።  ኢሕአዴግን ስናይበት የኖርንበትን  አይን መቀየር አለበት። ይህ በማለታችን ብዙ ዋጋ ከፍለናል። መሞታቸው የማይፈለግ እና ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ነው። አውነትም  ….የሕዝቡ ምክንያተዊነት (ብስለት እያደገ ስለመጣ) የሚደግፈው ፖሊተካ ይቃወመኛል ብሎ ሳይፈራ   እሕዝቡ የተሰሩት ስራዎች አይቶ በጨዋነት በመግለጹ “ያ እኛ ስናራምደው የነበረ አስተሳሰብ አሁን እየሰፋ እና ቦታ እያገኘ መሄዱን” ሕዝቡ መንቃቱን ነው የሚያሳየው። ይሄ ትልቅ ነገር ነው፤ ይሄ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነገር ነው።

ኢትዮጵያ መሪዋን አልቅሳ የቀበረችበት ዘምን በታሪክ አልነበረም፤ይሄ የመጀመሪያ ነው። ኢሕአዴግ በአየር የተንጠለጠለ ፓረቲ ነው፤ አልቆለታል እያልን የምናወራው ነገር ከሕዝብ አስተሳሰብ የራቀ መሆኑን ያሳየን ይመሰልኛል። ሕዝቡ ተገዶ ነው እያዘነ ያለው ከማለት ይልቅ፤ከዚህ ሂደት ምን ተምረን አካሄዳችንን ልናስተካከል እንችላለን በማለት ልንማርበት ይገባል።ከዚህ በተረፈ  ቤተሰቦቻቸው፤ የኢትዮጵያም ሕዝብ፤መንግሥትና አባሎቻቸው፤ጽናቱን ይስጣቸው። እሳቸውም ነብሳቸው እግዚአብሔር በጥሩ ቦታ ያስቀምጥ ነው ለማለት የምንችለው።

አሁን ደግሞ  ወደ ዳኛ ብርቱካን መዲቅሳ  ከጀርመን ራዲዮ  አማርኛው ክፈለ ጊዜ ጋር ያደረገችው ቃለ መጠይቅ ምን እያለች አንደሆነ ልውሰዳችሁ እና አድምጡ። ቃለ መጠይቁ የተካሄደው ከዶቸ ቨለ የአማርኛው ክፍል ነው። ወ/ሪት ብርቱካን የምትኖረው አሜሪካ ውስጥ ሃርቨርድ ዩኒቨርሲቲ ነው። (እኔ የገረመኝ የዚምባቡዌም፤የኢትዮጵያም እና የመሳሰሉ አገር ፡ ”እስር ውስጥ የነበሩ ፖለቲከኞች” ከታሰሩ በሗላ ወደ እዚሁ ጉደኛው ሐርቨርድ በቀጥታ እንዴት መግባት ዕድል እያገኙ እንደሆነ እናንተም እንደ እኔው እንቆቁልሹ እየገረማችሁ ይሆን?)

ብርቱካን እንዲህ ትላለች፡

“አውነት ለመናገር የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት ስሰማ በጣም….ነው ያዘንኩት።በጣም ተደራራቢ ሐዘን ነው የተሰማኝ። አንደኛ እንደ ሰው ፤እንደ አገሬ ዜጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አለ ዕድሜአቸው በሚባል ሁኔታ ማለፋቸው አዝኛለሁ።ለቤተሰባቸው አዝኛለሁ ፤ለሳቸው አዝኛለሁ።” “በሐዘን ድባብ ውስጥ ሆኜ ያሰብኩት ነገር” እያለች ወደ ምክንያተዊ ሽፋን ስትተነትን አድምጠናታል።
 
ስየ አብርሃ ደግሞ እያለ ያለው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራ በምጣኔ ሐብቱ ከፍተኛ ዕድገት የታየው በፖለቲካው ላይ አስተማማኝ መደላድል አድርገው ባለማለፋቸው አሳዝኖኛል። ብሏል። የመለስ መሞት በስልክ ደወል ሲሰማ “ልቡ ደንግጦ ተረብሾ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሕሊናው እና ማስተዋሉ ጽጥ ብሎ እንደነበረ” ሳይደብቅ የተሰማውን ሓዝን ገልጿል። ሆኖም የብርቱካን እና የስየ አባባል ስትመለከቱት ሁለቱም በተለያዩ ዜና ማሰራጫዎች ያስተላለፉት መልዕክት “በጎም መጥፎም አንደማንኛውም ሰው አድርገዋል” (የብርቱካን) ጀምረውት በሗላ የዘጉት የዲሞክራሲ መንገድ መክፈቱን ቢቀጥሉበት ኖሮ…..(ብርቱካን በ ቪ ኦ ኤ አማርኛ ክ/ጊዜ) የምትለውን እና ስየ የፖለቲካ መደላድሉን ሳያረጋጋ ማለፉን’ የሚለው  “ምኞች” ስትመለከቱት ፤እነዚህ ሰዎች መለስ (የወያኔ ትልቁ የጦር መሪ የነበረው የስየን አስተያየት ወደ ጎን ትተን፤ ብርቱካንን እና መሰሎቻ ማለቴ ነው) ማን መሆኑን ፤የተከተለው የፖለቲካ ፖሊሲ ምን እንደነበረ ጭራሽኑ የገባቸው አይመስልም። ጎሰኛ ወይንም ሙሶሎኒ ወይንም ሂትለር “እንዲህ ቢሆን ኖሮ” በዚህ የጀመረው በዚህ እንዲህ ቢቀጥልበት ኖሮ የሚሉት የፖለቲካ አላዋቂነት ምን ያህል ያገሪቱ ተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች የተቃዋሚያቸው የፖለቲካ መመሪያ እንዳልተረዱት የሚያሳይ መስተዋት ነው።  የማዘናቸው መሰረቱም በጠላት እና በወዳጅ መካከል ያለው የዓይን ሚዛን ደካማ ነው። መለስ እንደሚሉት አገራዊ ፖለቲከኛ ሳይሆን ኢትዮጵያን በጥፋት ጐዳና እንደትጓዝ ቀይሶ የመጣበትን መመሪያው በጣለትንት ካለመፈረጃቸው የመጣ ደካማነት ነው። እንዲህ ቢሆን ኖሮ ብሎ የሚተነብይ ፖለቲከኛ “የወያኔ ምንነት እና ፖሊሲው” እንደገና መመርመር ያስፈልገዋል እላለሁ።

 አሁን ደግሞ ወደ አቶ ግርማ ሰይፉ የአንድነት  ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ እና የምክር ቤት አባል እንዲህ ብለዋል። የሰውየው አጀማማር “ያበሻ ሲንድሮም” ብየ የምጠራው “እንደ ሰው” የሚለው አጀማመር ነው እሳቸውም እንደ ብርቱካን እና የመሳሰሉት “እንደሰው” እያሉ ለሐዘናቸው የመሸፈኛ ጥበብ የሚጠቀሙት። ሂትለርም ፤ሙሶሎኒም “ሰው ነበር” ግን እንደሰው እናልቅስላቸው?
ሰውየው እንዲህ ይላሉ።
“እንደሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት ያሳዝነኛል።ካሁን በሗላ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ነበር እንዲህ ነበር ብሎ “ማውራት” ተገቢ አይደለም። ከዚህ በፊት የምናወራው ወሬ “እንዲህ ናቸው እንዲህ ናቸው” ብለን የምናወራው ወሬ ይማራሉ ብለን መልዕክት የምናስተላልፋቸው ነገሮች ነበሩ አሁን ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገር ካሁን በሗላ በታሪክ እሳቢ የሚያገኝ ስለሆነ (መውቀሳችን  “ወሬያችን” ማቆም) እና ጠቅላይ  ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመት ያገለገሉ ስለሆነ ማረፋቸው ያሳዝናል።”
ይህ አባባል አልገረማችሁም? “ለ21 ዓመት ኢትዮጵያን የጣሩ፤ ያገለገሉ መሪያችን ስለሆነ ማረፋቸው በጣም ያሳዝናል”? ምን እሱ ብቻ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ነበሩእንዲህ በደል ነበራቸው ሕዝቡን እንዲህ አደርገውት ነበር የምንለው ወሬ ካሁን በሗላ ማቆም ለብን “ የሚለውስ አልገረማችሁም? እነዚህ ናቸው ተቃዋሚዎች የሚባሉት? ሕዝቡ በነቂስ አልቅሷል፤አዝኗል ብሎ ሕዝብን መውቀስ እንዴት ሊመች ይቻላል? የተቃዋሚ ጅላጅሎች እና አድርባይ የሕሊና በሽተኞች እንደዚህ ዓይነቱ ለፋሺስት መሪ ማላዘን ፤ማዘን፤ልባቸው ሲታጠፍ የተመለከተ እና ያደመጠ ሕዝብ  ለመለስ ዜናዊ ቢያለቅስ ምን ይጠበቅበታል ብለን ነው የምንወቅሰው? ይህ ተቃዋሚ የሚባል ሌሎች መሪዎች ከሰማይ እግዚአብሔር በጥበቡ መለስን እንደወሰደው ከሰማይ ለተቃዋሚው ቢልክለት እንጂ ይህ አድር ባይ እና ለፋሺሰት አልቃሽ ተቃዋሚ ለውጥ ያመጣል ፤ወያኔ ያስወግዳል ብላችሁ አትጠብቁ። በዚህ አጋጣሚ የመኢአዱ ኢንጂኔር ሃይሉ ሻውል በፋሺስቱ በመለስ ዜናዊ ሞት የሰጡትን መልስ እና ያሳዩት ጠንካራ እና ሕጋዊ (ጃስቲፋያብል) አቋም ሳላመሰግናቸው አላልፍም። ምስጋናየ-ይድረሳቸው።ታቸው-ረዳ(ኢትዮጵያን-ሰማይ-አዘጋጅ) አሜሪካ www.ethiopiansemay.blogspot.com          email getachre@aol.com

    

 

No comments: