Tuesday, September 28, 2010

ውጥንቅጥ ነፃ አውጪዎቻችንና ሻዕቢያ (ክፍል 2)

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com

ውጥንቅጥ ነፃ አውጪዎቻችንና ሻዕቢያ (ክፍል 2)(Getachew Reda ጌታቸው ረዳ) ይህ ጽሑፍ “በአልጌና በምፅዋ በዓይደር የተዘሩ ዓጥነቶች ዕሾህ ሆነው ይውጓችሁ”ከሚለው የቀጠለ ተመሳሳይ ትችት ነው። ጽሑፉ የቀረበበት ምክንያት “አሁንም ኤርትራ መዳኛችንም መጥፊያችንም ትመስላለች:ኤርትራ፤ አርበኞች ግንባር፤ ግንቦት7”በሚል በልጅ ተክሌ (ኢጋድ ፎረም/ካረንት አፈይርስ ዌብሳይት/ፓል ቶክ ባለቤት)ለቀረበው ጽሑፍ ቀጣይ ትችት ነው። ካናዳ አገር የሚኖረው ተክሌ (ልጅ ተክሌ/ፊታውራሪ ተክሌ……)በማለት ራሱን የሚጠራ ወጣት ኤርትራ ድረስ በመሄድ ተዋጊ ሃይል እንዲያሰለጥንልን ሻዕቢያን ካልተማጸንን መለስን ማስወገድ አንችልም ባይ ነው። በማያሻማ አገላለጽ “በዚህ ዘመን በኛ ዕዴሜ በቀጣዮቹ ጥቂት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በአመጽ ለውጥ መምጣት ካለበት፤ ቢከፋም ቢለማም ያንን የማሳካት አቅም ያለው ግንቦት ሰባት ብቻ ነው ባይ ነኝ።” ብሎ ነበር። ለዚህ አባባሉ ነበር ክፍል አንድ ጽሑፌ ነካ ነካ አድርጌ የተቸሁበት። በዚህ ክፍል ሁለትም የዛኛው ቀጣይ መደምደሚያ ሆኖ በሌላ ሳምንት ሌላ ወቅታዊ ጉዳይ መጥቶ ከላስተላለፍኩት በቀር በቀጣዩ የሚቀርብ ጽሑፌም የግንቦት7 ጥብቅ ወዳጅ የሆነው ተስፋየ ገብረአብ የተባለው የሻዕቢያ ሰላይ በሚመለከት እንዳስሳለን። የተክሌ አማራጭ ብቸኛ ነፃ አውጪዎቼ ናቸው ብሎ የሚመካባቸው ውጭ አገር ስራ እየሰሩ ሕይወታቸው የሚመሩት የግንቦት7መሪዎችን መተማመኑ የገንዘብና የፕሮፓጋንዳ ድጋፉን ምኞቱን መግለጹ መብቱ ተጠበቀ ቢሆንም፤ እኔ ከተክሌ ጋር ያለኝ ችግር “ግንቦት ሰባት በግልጽ ባደባባይ ከኤርትራ መንግስት ጋር መነጋገርና መስራት ካልጀመረ፡ሌሎች የስራ መንገዶች ሁሉ ተዘግተዋልና ትግላችን እዚያው ባለበት መርገጥ ነው ባይ ነኝ።” “በጸረ ወያኔ ትግል ውስጥ የጎረቤት መንግስት እገዛ ካስፈለገን፡ ያለችን ብቸኛ አጋር ኤርትራ ብቻ ነች።”ስላለው አባባሉ ክፉኛ ይጎረብጠኛል። ለምን? የሚከተለውን እንመለከት። ተክሌም ሆነ እኔ እና በሚሊዮን የምንቆጠር ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አገራችንን የማጣቱ ምክንያት ወያኔ ብቻ ሳይሆን ሻዕቢያም ጭምር መሆኑን በድጋሜ ማስታወስ ሊኖርብኝ ነው። “ማየት ማመን ነው” የሚሉት የወያኔዎች ደንቆሮ ፖለቲካ (“የሶፊስቶች ፍልስፍና” የሚከተሉ) “ማሰብ ያቆሙ” ነብሳት ዛሬም ለወያኔም ሆነ ለሻዕቢያ ያላቸው አመለካከት በጎ መሆኑን ስመለከት ያንዳንዳችን አፈጣጠር የሰው ልጅ ሕሊና ዛሬም ከእንሰሳ ጭምትነት ያልመጠቀ በኤሊ የጉዞ ፍጥነት ሂደቱ እያዘገመ እንደሆነ ስመለከት ለዳተኛው ጉዞአቸው እንዲህ እንዲያዘግሙ ምክንያታቸውን ለማወቅ ብሞክርም አለትን ለማርጠብ የሚደረግ ፈተና ያህል ይከብደኛል። እዚህ በዲያስፖራም/ውጭ አገር እየኖሩም ለወያነም ሆነ ለሻዕቢያ መሪዎች ያላቸው አመለካከት የተለሳለሰና በጎ መሆኑን ስታዘብ የእኛነታችን ውጥንቅጥነት (ናቲ ጊቲ) እኛነታችንን በጉልህ የማየት ችግራችን ማጣት ተደማምሮ ነፃነት የመቃረቡ ዕድሜው ይበልጥኑ ረዢምና ውስብስብ አድርጎታል። ጎረቤቶቻችን ለኛ በጎነት አልተሰለፉም። የኼ የምናውቀው ሓቅ ነው።ለዚህም ምክንያቱ መለስ ዜናዊ ያገሪቱን መሬቶች እና ውሃ ነክ ጥቅማ ጥቅሞች ለጎረቤት አገሮች በነፃ እየለገሰ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን፤ለም የእርሻ መሬቶችን ያለ ምንም ገድብ ለጎረቤት አገሮች በመለገስ በልዋጩ መለስን የሚቃወሙ ተቃዋሚ ድርጅቶችና ግለሰቦች እየተያዙ ከተጠለሉበት የጎረቤት አገሮች እየተያዙ ወደ መለስ ዜናዊ እስር ቤቶች እየተወረወሩ መሆኑን ለትግሉ አመቺ እንዳልሆነ ሁላችንም እንስማማበታለን። ያለን አማራጭ ዛሬም ነገም ለውጥ መምጣት ካለበት አገር ውስጥ በሚደረጉ ትግሎች ነው፡ እላለሁ። ይህ ለማድረግ ያለፈው የትግል አካሄድና አካሄዱን የመሩት አመራሮች በጥልቅ መመርመር አለበት። ሥልጣን በሚፈልጉ ግለሰቦችና በጭፍን ስሜት በሚጓዙ አመራሮችና ተከታዮች ምክንያት ተጠናክሮ የነበረው የተቃዋሚ አንድነት ፈርሶ ለመለስ ዜናዊ ለምለም (ለም) መስክ ሆኖለት ይኼው እስከ ዛሬ ድረስ ያገሪቱ ሕዝብ ችግር ውስጥ ገብቶ የመናገር የመውቀስ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች ተዘግተው አገሪቱ የውስጥ እና የውጭ አገር (neo-colonialist)የጥቂት ዘራፊ ግለሰቦችና ኩባንያዎች በቧረቂያ ገነት (ሴፍ ሔቨን)ሆና ሕዝቧም “በቀይ ቢጫ ለባሽ”ፋሽስቶች ያስተዳደር ቀንበር ስር እየተረገጠ ይገኛል። ለምክንያቶቹ ዝርዝር ለተቃዋሚዎች አንድነት መፍረስ ምክንያት ብዙ ትችቶች የተካሄዱ ስለሆነ አሁን አልመለስበትም። አዲስ አበባ ያክል ትልቅ ከተማ፤የነቃ እና የተለያዩ አስተሳሰቦች ያያዘ ሕሊና ያለው ኗሪ ሕዝብ ወያኔን ባንድ የምርጫ ቀን “አክ እንትፍ” ብሎ ተፍቶ ትብያ ላይ ጥሎ ተቃዋሚዎቹን በመምረጥ “ቀይ-ቢጫ” ለባሾችን የሓፍረት ማቅ አስለብሶ ጥፍራቸው ውስጥ እንዲገቡ ያደረገበትን ያንድነት ትግል ዛሬ በፋሸስቶች ቀንበር ዳግም እንደገና የመረገጡን ጉዳይ ሁላችንም አሳስቦናል። ይህ ደግሞ እጅግ አሳዛኙ ክፍል ነው።ሕዝቡ ለትግሉ ያለውን ዝግጁነት ሲገልጽ፤በተፃራሪ የተቃዋሚ መሪዎች “በሙሉ” ሃላፊነታቸውን በመጣል “ሰላማዊ ሰልፍ/የተቃውሞ ሰልፍ እንዳያደረግ በመወስን በመለስ ጉራና ዛቻ ተደናግጠው ትግሉን ከመመምራት ይልቅ ያለ መሪ በመተው ሕዝቡ በፋሽስቶች ጥይት እንዲቆላ ምክንያት መሆናቸው የምንስማማበት ነው።ባለፈው አምስት ዓመት በፊት ቀይ ለባሽ የወያኔ ፋሽሰት ግልገል ወታደሮችም ሴት ህፃን ሽማግሌ ሳይል ረሽኗቸዋል። ወጣቱ እና ታዳጊ ህፃናቱንም የባንክ ዘራፊ በማለት ሌባ እና ወረበላ አድርገው የፖለቲካው ተቃዋሚውን በመትረየስ አጨዱት።አሁን እዚህ ላይ እንገኛለን።የዛሬውንም ምርጫ እንደዚሁ አገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ መሪዎች አንድ ሁለት ሳይባል “ሁሉም”በፍርሃት ተሸማቅቀው ትግሉን በመተው ለወያኔ ሰጡት። እጅግ አስገራሚ እና ካለፈው የባሰ አስገራሚ ጉድ! እነኚህ የተቃዋሚ መሪዎች፤ትግሉን እስከ መጨረሻው መግፋት ካልቻሉ ወይ ካገር ለቆ እንደ ግንቦት7 መሪዎች ኑሯቸውን ውጭ ማደላደል፤ ከመጀመርያውኑ ምርጫ ውስጥ መሪ ሆኖ አለመመዝገብ፤አለመፎከር፤አለመወዳደር፤አለመከራረከር!ከገቡም የተጭበረበረውን ምርጫ ለማጋለጥ እና የሕዝቡን መብት ላለማስረገጥ ሕዝቡን ለመጨረሻ ወሳኝ ትግል አመጽ አስነስቶ የለየለት የታሪክ መሰነድ/ማስመዝገብ ነበረባቸው። ያ አላደረጉም፤፡ ይበልጥኑ ለፏሲስቶቹ ጥቃት ራሳቸውንም ሆነ ሕዝቡ አመች ሆነው ይገኛሉ። ከዚህ ወዲያ ወዴት እንሂድ?ለሚለው ጥያቄ ብዙ ተጽፎበታል ዛሬም በቀጣይ እየተጻፈ ነው። እንቅልፍ አጥተው መፍትሔ ለመፈለግ የሚጥሩ በተከታታይ ሃሳቦችን በየሚዲያው እየቀረቡ ነው። በየትም ወገን ይሁኑ ለጥረታቸው ምስጋና ይገባቸዋል። ወሳኙ ጥያቄ ግን “በሻዕቢያ በኩል አድርገን መለስን እናስወግድ?” ወይስ “አገር ውስጥ ያለው ሕዝብ በመቀስቀስ ሕዝባዊ አመጽ አስነስቶ መብቱን ማስከበር?” የሚሉ ሁለት አማራጮች ላይ ደረስናል። የመጀመሪያው መፍትሔ “የጨነቀው ዕርጉዝ ያገባል” ነውና መፍትሔ አይደለም (በተለይም ከወያኔ ያልተናነሰ ተፃባኢ)።ሁለተኛው ግን አማራጭ የሌላው 17 ዓመት ሙሉ በደምብ ያልተገራ፤መሪ ያጣ፤ በፈታኝ ትግል ተፈትነው የወደቁ መሪዎች የተገራ ትግል ስለሆነ ያንኑ አትኩሮት በመስጠት የፋሽስቶችን ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጭቆና እና ብዝበዛ በሕዝብ አመጽ የሞት የሽረት ትግል እንዲያደርግ የችግሩ ምክንያቶች ከድርጅት ወገንተኛነት ስሜት የራቀ ምርመራ (ዲያግኖስቲክ/ትራብል ሹተር) የሚቀየስበት ጥናት እንደገና መታየት ያስፈልገዋል እላለሁ። ሕዝብ ሲያምጽ መሳርያ እንደማይገታው የትግል ታሪኮች ህያው ምስክሮች ናቸው። (መሣርያ ታጥቆ ጎሰኛ/ፋሺስቶቹን ከስልጣን ማስወገድ ባልተጠላ፤ ነገር ግን ተክሌም ሆኑ ሌሎቹ በገለጿቸው ምክንያቶች አልተቻለም። ያም ቢሆን/ፍላጎቱ ካለም ኤርትራ የሚያስኬድ የለም። አገር ውስጥ የትጥቅ ትግል ማድረግ ይቻላል ባይ ነኝ) ያ ለማድረግ ሕዝቡ የግድ መሣርያ መታጠቅ አለበት ማለት አይደለም። ሕዝቡን በማዕበል ለማስነሳት የፕሮፓጋንዳው ስራ እጅግ በስፋት በመቀጠል እና በፋሺስቶቹ ወጥመድ “ማሰብ ላቆመ ሕብረተስብ”አዳዲስ የማታለያ ወጥመዶች ሲያጠምዱለት በወቅቱ ተከታትሎ ማጋለጥ የመጀመርያውና ቅድሚያ የሚሰጥ ትግል ሲሆን። ቀጥሎ አገር ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ መሪዎች በሌሎች በሳልና ፈጣን እጅግ ደፋር እና ፍርሃት የማይበግራቸው በጥበብ የሚጓዙ መሪዎች መተካት አማራጭ የለውም። እስካሁን ያየናቸው መሪዎች መሸጋገርያ እንጂ “ፈታኝ” ፈተና ሲጋረጥባቸው ሸርተት የሚሉ ደካሞች እና ፈሪዎች ሀኖው ትግሉን ስላበላሹት የድክመታቸው ስፋት ሰፊ በመሆኑ፤ጊዜ ሳይወስድ እነሱን የሚተካ ሃይል አማራጭ የለውም። የሚተካቸው እስከሌለ ድረስ ፖለቲካው በተቆጣጠሩት ቁጥር ይበልጥ ትግሉን እየጎተቱ ፤መለስ ዜናዊ በደነፋ ቁጥርም “ጭራቸው እየቆሉ”እርስ በርስ እኔ አይደለሁም “ሃይሉ ነው፤ግዛቸው ነው፤ መስፍን ነው፤ልደቱ ነው፤ያዕቀብ ነው፤….”በሚል የማምለጫ ምክንያት “ሸብረክ”እያሉ የጉዞ ጉቶዎች/መሰናክል/ሃርድል የመሆናቸውን ጨዋታ ይቀጥሉበታል (ምክንያቱም አይተናቸዋል፡ what you see is what you get) ይላል ፈረንጁ።በዚህ መንገድ “ቀይ ቢጫ ለባሽ” ፋሺስቶቹም ያገሪቱ አንድነት በቦረቦሩት የልጆች እና የቅጥረኞች የጨዋታ ትልም መቀጣላቸው እውን ነው። ስለዚህ ትልሙ አሁንም በመለስ ዜናው ብቻ ማትኮሩ ሳይሆን በተቃዋሚው የመምራት ችሎታ ላይ ማትኮርና ጥራት ያላቸው መሪዎች ለማውጣት ዘዴ መፈለግ አለበት። የጫት መደብሮች በመላ አገሪቱ እንደ ወረርሺኝ በተስፋፋበት “ግደ ቢስ”ስርዓት አልበቃ ብሎ፤ ወያኔ (ኢትዮጵያን አይድል) ሻዕቢያ ደግሞ (ሽንግርዋ) የሚሏቸው የወጣቱን የማሰብ ሕሊና በመዝናኛ መድረኮች ፍጥኝ የማሰርያ ዘዴያቸው እንደሚያደርጉት ሁሉ እኛ ተቃዋሚዎችም በተለይ አገር ውስጥ ያሉት ዜጎች አገርን “ከቀይ ቢጫ ለባሽ” ፋሽሰቶች ፕሮፓጋንዳ ለመስበር የፖለቲካ ዲቤት/ክርክር የሚደረግበት መድረክ ከፍቶ ሕብረተሰቡ የማሰብ ችሎታው በወያኔዎች የማዘናጊያ ሱስ እንዳይጠመድ ማዘጋጀት አዲስ የትግል ረድፍ መክፈት ነው። በጥንቷ ግሪክ ተደርጓል። ክርክሮች በየገበያው በየአደባባዩ ሲደረጉ ገበያተኛው እና ኟሪ አላፊ አግዳሚ ተሰብስቦ እንደ ሲነማ ያዳምጥ ነበር።እርግጥ ለዛ ሲሉ ፈላስፎቹ ሕይታቸው ገብረዋል። እርግጥ ወያኔ ይፈቅዳል ወይ የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ። ትግል ነውና አይፈቅድም። ከጭንቅላቴ በስብሻለሁ ብሎ ኑዛዜ የተናዘዘ “ግም” “ግም” የሚሸት ቡድን ግማቱ እንዲነገረው አይፈቅድም። ቢሆንም ወያኔን በጋዜጣ በራዲዮን በመጽሔት በየጠላ ቤቱ በየክለቡ በአዝማሪ አሽሙረኛ-(በማሲንቆ/በሃረሚኒካ እየተሸኘ) (በመጠኑም ቢሆን-እየታሰሩም እየተፈቱም) ማጋለጥና መግጠም ከተቻለ “የፖለቲካ-አይድል” መድረክ ለመክፈት ጠይቆ ማስፈቀድና ወያኔን እልክ ማስጨረስ አንዱ ትግል ነው።ወያኔ የተቃዋሚዎች የክርክር መድረክ ብሎ ለስሙም ቢሆን መድረክ ከፍቶ የራሱን ቆሻሻነት ሳይወድ እንዲያደምጥ የተገደደበትን መድረክ ማስከፈት/መክፈት አንዱ ትግል ነው።በወያኔ መንግሥት በየአምስት አመቱ አንዴ የሚካሄድ ሳይሆን በተቃዋሚዎች ወይንም በገለልተኛ ባለሃብቶች ድጋፍ መድረክ ከፍቶ በቀጣይነት በማዘጋጀት ለሚቀጥለው ትግል ተረካቢው ትውልድ (ወጣቱ)ዝግጁ ለማድረግና ወጣቱ ማሰቡን እንዳያቆምና ያገሩን መቦርበር፤ውድቀት፤አንደነት መላላት፤ያገሪቱ መጪ ዕጣ ፈንታ ምን ላይ ሊወድቅ እንደሚችል፤የጎሰኛ ፖለቲካ አደጋ ለማጋለጥ ወጣቶች የሚገኙበትና የሚከራከሩባቸው መድረኮች ቢዘጋጁ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።(በተለይ ውጭ ያሉት ሚዲያዎች ጥሩ አርአያ ሊሆኑ ይችላሉ)። ወጣቱ የታሪክ ተረካቢ እና ወሳኝ ሃይል ሊሆን ስለሚችል ወጣቱ የትግሉ ትኩረት ጎሰኛ/ፋሺስት ከመሆን እንዲጠነቀቅ (ጎሰኛነት ለወያኔ ትኩስ ዳቦ ነውና)የፖለቲካ አይድል (ትኩስና ፈጣን፤ብልህና አገር ወዳድ ወጣት የሚያስገኝ መድረክ)ተከራካሪዎች የሚከራከሩበት መድረኮች መዘጋጀት አለባቸው። የኮመዲ/የቀልድ/መዝናኛ መድረክ ባለቤቶች ትብብር ቢያደርጉ “ፓን ኢትዮጵያኒሰት” ወጣቶች በማፈላለግ አዲስ/ተኪ ሃይል በማፍራት ክፍተቱን ማሟላት ይቻላል። ውጭ አገር የሚኖሩ ግንቦት7ውስጥ የተደራጁ አንዳንድ ወጣቶች በሻዕቢያ እርድታ ነፃ ካልወጣን ሌላው ሁሉ ተስፋችን የተዘጋ ነው የሚለው አባባል በጽኑ መቃወም ይኖርባችሗል። በሻዕቢያ መንደር የተሰራ የነፃነት መንኮራኩር ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት በበረራ ላይ ስለሚገኝ ለነፃነት እንዘጋጅ! የሚለው የሰከረ የካልቶች ሰበካ ሞኝነት መገታት አለበት። ሻዕቢያ ጠላት እንጂ ከቶ ወዳጅ ሊሆን ወይንም አዳኝ/ረዳት ሊሆን እንደማይችል የግንቦት7 ደጋፊዎችና ወጣቶች መረዳት ይኖርባቸዋል (በቅርቡ የግንቦት7 “ሸሪክ”የነበረው ኮሎኔል አለበል የተባለ አስመራ ከሻዕቢያ ጋር ያደረገው አሳፋሪ ቃለ መጠይቅ ማድመጡ የሻዕቢያ /ብላሰፎሚ/ይቅር የማይባልበት እርኩስ ሓጢአት በቂ መረጃ ነው። የአማራ ነፃ አውጪ አድርጎ አደራጅቶታል!!)። ውጭ አገር ውስጥ በሚኖሩ የሻዕቢያ ባለስልጣኖች እየተታለሉ (አቶ አብርም ያየህ ሞክረውታል)እንደ እነ ብርሃኑ ነጋ እንደ እነ ወጣት ተክሌ እንደ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ ኤልያስ ... የመሳሰሉት የዋሆች ሻዕቢያ ላገራችን በጎ አሳቢ ስለሆነ፤አማራጭ ስለሌለን አማራጩን ተጠቅመን መለስን እናስወግዳለን (ከሰይጣንም ቢሆን እንደራደራለን የሚል የከሰሩ ሰዎች አማራጮች)የምትሉት አማራጭ “ከንቱ ኡቱ” ልፋት ነው። ልፋታችሁ ከንቱ እንደሚሆን እና የሻዕቢያ ባሕሪ እኔ ከምነግራችሁ የኤርትራ መሪዎች ምንነት በሚገባ የሚተነትኑ በሳል ያገራችን ጻሓፊዎች አንዱ ከሆኑት ጸጋየ ገብረመድህን “አርአያ (ዛሬ ከናንተ ጋር ሙጫ ዓይነት ፍቅር እንዳላቸው እገምታለሁ -ከታዘብኳቸው አንዳንድ የድክመት ምልከቶቻቸው እንደታዘብኩት) “አፍቃሪ- ኢትዮጵያዊነትን ማረጋገጥ-ከባዱ ሸክም”በሚለው በጦቢያ አምደኝነታቸው ሲያስተምሩን ከነበሯቸው ጽሑፎቻቸው አንዱ “ኢትዮጵያና ኤርትራ ያልተጠናቀቀ ፍቺ፤ያልተሳካ ጉርበትና” (ሌላው የሓሰን ዑመር አብደላ ትችትም ፈልጋችሁ ብታነቡ ይጠቅማል)ያሉትን ከዚህ በታች ልጥቀስና የሻዕቢያ ጠላትነትና ስለ ኢትዮጵያ ያለው ጥላቻ ካነበብን በሗላ ሁለቱ ማለት ሻዕቢያም ሆነ መለስ ዜናዊ ዙሮው ዙሮው መታረቃቸው የማይቀር መሆኑና አንዱ ሌላውን እየናፈቀው መሆኑን በተለይም ከመለስ ዜናዊ አንደበት የተናገረውን ጠቅሼ ጽሁፌን ልግለጽና፤ሁለቱ ሲታረቁ ሻዕቢያን አምነው ሳዋ/ተሰነይ ስልጠና የሚወስዱ ኢትዮጵያዊያን ታጣቂ ሰልጣኞች (መሪዎቹ ማለቴ ነው።አብረው ከተራው ምስኪኑ ተጋይ ጋር እየኖሩ ከሆነ ለማት ነው።)፤እንዲሁም ሻዕቢያን እንጥላለን ብለው መቀሌ እና ሽሬ በመሰብሰብ ብሔር ብሔረሰብ እስከ መገንጠል የሚለው ፋሺስታዊ ኮሚኒሰት መመርያ ይዘው የሚፎክሩ ኤርትራዊያን በሁለቱም ስምምነት ተቃዋሚዎቻቸው እንዲያስረክቡ/እንዲለዋወጡ ስምመነት ቢገቡ ዕጣ ፈንታችሁ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ግምት ውስጥ አስገብታችሁት ታውቃላችሁ?። መጀመርያ ስለ ሻዕቢያ ማንነት ለማታውቁ ወጣቶች ጸጋየ ገብረመድህን አርአያ “አፍቃሪ- ኢትዮጵያዊነትን ማረጋገጥ-ከባዱ ሸክም” በሚል የጻፉት ትምህርታዊ ጽሑፍ ልጥቀስና ከዚያ መለስ ዜናዊ ከስምንት ወራት በፊት ከሻዕቢያ ጋር የሚፈልገው ወዳጅነት ምን አይነት መሆኑን በትግርኛ ቃለ መጠይቁ የተናዘዘውን ልጠቅስና ልሰናበት። “አፍቃሪ ኢትዮጵያዊነትን ማረጋገጥ ከባዱ ሸክም“ ባለፉት ሰባት አመታት የሻዕቢያ ግልገሎች በአገራችን ተቀምጠውና በአገራችንም አምጸው የበኩር ልጅ ድርሻ እየወሰዱ መልሰው ሲዘልፉን ነበር። ኢሳያሳቸው በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ቤተመንግሥትና መንግሥቱ ሃይለማርያም ባሰራው ሰፊ አዳራሽ ፈነጩ። ሽማግሌዎቻችንን በደፋር ቋንቋ ደፈረ። ታሪካችንን ተረት ተረት አለው። አሰኘው።የዚህን አገር ቅድስና ዘለፈብን። እንደሚባለው አምላክ በመለኮቱ ላይ ለሚመጡበት ሥርየት ሌለው ሃጢአት (Blasphemy) እንደ ፈጸሙ በማመን ይበቀላቸዋል።የአገርን ክብርና የሕዝብን ማንነት የሚደፍሩ በተመሳሳይ ዓይን መታየት ይገባቸዋል።ይኸ ነው የደረሰብን።…” በማለት የጦቢያው አምደኛ ጸጋየ ገብረመድህን አርአያ አፍቃሪ- ኢትዮጵያዊነትን ማረጋገጥ-ከባዱ ሸክም” በሚል የጻፉት ሻዕቢያ ላገራችን ያለው ንቀት እንጂ በጎነት እንደሌለው ማንነቱን ገልጸውልናል። መለስ ዜናዊም በበኩሉ የሻዕቢያ ፍቅሩ አሁንም እንዳለው አስረግጦ በቃለ መጠይቁ የተናገረውን በመረጃ ልጥቀስ። ንግግሩ የተገኘው አዝማሪኖ.ካም ተብሎ በሚታወቀው የኤርትራ ተቃዋሚ የሕዋ-ሰሌዳ (ዌብ ሳይት) አዘጋጅ አዲስ አበባ ቤተመንግሥት ድረስ በመሄድ መለስ ዜናዊን ለቃለ መጠይቅ ጠይቆ ከመለስ ጋር ያደረገው የትግርኛ ሰፊ የአውዲዮ-ቪዲዮ ቃለ ምልልስ Meles Zenawi's interview with Asmarino.com - part 3” በሚል ርዕስ ጉጉል ቪዲዮ ውስጥ የተገኘው ማስረጃ እነሆ።ከትግርኛው ቃለ መጠይቅ ወደ አማርኛ የተረጎምኩትን አንዲህ ይነበባል። ““የድምበር ኮሚሽን የወሰነው ውሳኔ ወደን ሳይሆን ሕግ ስለሆነ ባንወደውም ሳንወድ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመተግበር ተቀብለነዋል።የድምበር ኮሚሽኑ በሰጠው ውሳኔ መሠረት መፈታት አለበት። ይሁን እንጂ ነገ ጥዋት የሁለቱም አገሮች ድምበር በኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት ተግባራዊ ከሆነ በሗላም ቢሆን ሰላም አናገኝም። በተደጋጋሚ የኤርትራ መንግሥት ያወጀው ነገር አለ “የወያኔ መንግሥት የኢትዮጵያ መንግሥት ካልፈረሰ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ሰላም መረጋጋት የሚባል ነገር አይኖርም።ስለዚህ አማራጭ ነገር ስለሌለ የኢትዮጵያ መንግሥት ማፍረስ ነው፡ የሚል ነው አጀንዳው። በበኩላችን የኤርትራ ሕዝብ መሪያችን ብሎ ያስቀመጠው መንግሥት/ሃይል ወደድነውም ጠላነውም የኤርትራ ሕዝብ መሪ ነው። እንደ መሪ እና እንደ መንግሥትም ከእርሱ ጋር ተነጋግረን በሰላም ለመኖር ዝግጁ ነን። የጎረቤት አገር መሪዎችና መንግሥታት የመውደድ ግዴታ የለብንም፡ወደድናቸውም ጠላናቸውም የጎረቤት መንግሥታት ስለሆኑ ከነሱ ጋር ተከባብረን ተስማምተን እንኖራለን ከሚለው የመተከል/መስመራችን እምነት እንከተላለን። በነዚህ መተከላችን መሃል ያለው ጋግ ወይንም ክፍተት ባልኩት መሠረት ካልተሸጋግርነው ከኤርትራ ጋር ዘላቂ ሠላም አይኖርም።ስለዚህ ዋናው መደረግ ያለበት ትኩረት የኤርትራ መንግሥትም ቢሆን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ ጣልቃ የመግባት ወይንም የመወሰን ሓላፊነትና መብት እንደሌላው አምኖ ከጎረቤት አገሮች ጋር በሰላም ተግባብቶ መኖር (ይጠበቅበታል)።በበኩላችን በኢትዮጵያ ማለት በኛ በኩልም ቢሆን ተመሳሳይ ዝግጁነታችንን ለሰላም ያለንን ዝግጁነቱ ዛሬም ቦታው ላይ ነው ያለው እንላለን።በኛ በኩል በተግባር ለማሳየት ዝግጁ ነን። እንደዚህ ስንል ደግሞ በኤርትራ መንግሥት በኩል ተግባራዊ ለማድረግ ተመሳሳይ አጀንዳ ይዞ ቢጠጋን ኖሮ ዝግጅነቱ “ከልቡም ይሁን አይሁን”ለማወቅ በቻልን።እንዲህ ቢያደርግ(ቢጠጋን/ልቡ ቢያሳየን) ያኔ እኛም ከሱ ጋር የሰላም ዕርቅ ለማድረግ ያለንን ብርቱ ጉግት(ለማሳየት ያስችለን ነበር)።እሱ “ትያትራዊ” ነው በማለት ሁሌም እንደሚወነጅለን “ትያትራዊ”መሆኑን ወይንም ከልባችን የምር መሆናችንን እቅጩ በታወቀ ነበር። ይህ እስካልሆነ ጊዜ ድረስ (ሁለታችን እስካልታረቅን ድረስ)ድምበሩ ቢካለል፤ባይካለል መፍትሔ አይሆንም የሚል እምነት ነው ያለኝ።” Meles Zenawi's interview with Asmarino.com - part 3 ይላል “የቀይ ቢጫ ለባሽ ቡድን” መሪ የሆነው መለስ ዜናዊ ለሻዕቢያ ያለው ፍቅርና የሰላም ጉጉት ሳይደብቅ ሲገልጽ። በመለስ ፍላጎትና ጉጉት ድንገተኛ የናፍቆት ትቅቅፍና ዕርቀ ሰላም በሁለቱም ሽፍቶች ቢወርድ ነፃነታችን ይዛ አዲስ አበባ ልታደረሰን ነው የምትሏት የነፃነት መንኮራኩር አቅጣጫዋን ቀይራ ወድየትኛው የማረፊያ ግቢ አንደምታወስዳችሁ የምትስቱት አይመስለኝም። ካሁን በፊት በመለስ ዜናዊ ከዳተኛ እና እስስተኛ አቋም ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ በኤርትራ ተቃዋሚ ሃይሎች ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ዕልቂትና ሽብር ሳታስታውሱት የቀራችሁ አይመስለኝም።አጥብቄ አደራ የምላችሁ ግን ፖለቲካችሁ እንዳይበላሽ ከፈለጋችሁ “መለስ (ትግሬዎች ለማለት ነው) እንዴት ጮማውን ለመድከው ተብሎ ሲጠየቅ በመከራ” አለ አሉ፡ ብሎ የትግሬ ጠሊታነቱና የሻዕቢያ ዘረኛ ባሕሪው በመለስ በኩል አሳብቦ የትግራይን ሕዝብ መዝለፍ አንድ ብሎ እንደ አጀንዳ የጀመረው ሰላዩ ተስፋየ ገብረአብን ከሚዲያችሁና ከመሪዎቻችሁ ጓዳ መርመስመሱ እንዲያቆም ማስራቁ ብልሕነት ነው። በተረፈ ውጥንቅጥ ነፃ አውጪ ሆኖ ከሻዕቢያና ከመለስ ዜናዊ ተጎዳኝቶ ነፃነትን መመኘት በራስ ላይ እና በአገር ላይ ሐዘን መጨመር ነው።ከሁለቱም በጋሚዶዎች/ወረበሎች ጭካኔ አምላክ በጥበቡ ከመዓቱ ይሰውራችሁ። ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ ሰማይ ዘገባ አዘጋጅ። www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com ይደረስ ለጎጠኛው መምህር( አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሓፎቼን ለመግዛት የምትሹ አማርኛው $25.00 ሲሆን ትግርኛው $15 ነው (ይኼኛው አምስት ዶላር የፓስታ መላኪያ ሳይጨምር ነው።አሜሪካ ላሉት ብቻ)። የፖስታ ቤት አገልግሎት እየጨመረ ስለሚሄድ ዋጋው ሳይጨምር ካሁኑኑ ብትገበዩ እና ማን እየገዛን እንደሆነ ለማወቅ ራሳችሁ እንድትመረምሩ ይረዳችሗል የሚል ግምት አለኝ።አመሰግናለሁ።(408) 561-4836 (Getachew Reda p.o.Box 2219 San Jose, CA 95109 U.S.A )

Tuesday, September 21, 2010

የምፅዋ፤የአልጌና እና የዓይደር አጥንቶች እሾህ ሆኖው ይውጉዋችሁ!

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ የምፅዋ፤የአልጌና እና የዓይደር አጥንቶች እሾህ ሆኖው ይውጉዋችሁ! ጌታቸው ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ “ኢካድ ፎረም.ካም” እና “ኢትዮሚድያ.ካም” እና በመሰል ድረገፆች ሰሞኑን ተጠናክሮ እየወጣ ያለው የፖለቲካ ሰበካ (ፕሮፓጋንዳ)አስገራሚ ነው። “ግንቦት7”የተባለው ጎጠኞች የሚመሩት ድርጅት ኤርትራ ድረስ ሄዶ የሻዕቢያ እርዳታ በመጠየቅ ኢትዮጵያን ከመለስ ዜናዊ አስተዳደር ነፃ እናወጣለን ብሎ መሄዱን የሚነግሩን ፅሁፎች መለጠፍ ጀምረዋል።በዚህ ላይ ሁለት ጽሁፎች ቀርበዋል። አንዱ ጥቁር ጫካ የተባሉ ጸሓፊ የአርበኞች ግምባር ደጋፊ ሲሆኑ ሌላው ጸሓፊ ደግሞ የግንቦት7 ደጋፊ የሆነው “የኢትዮጵያን ሕዝብ በመጨፍጨፍ፤በማባረር አሁንም ብዙ ምርኮኛ በባርነት በሳህል ተራራዎችና በተቀሩት ምድረበዳዎች በልማት ሥራ ከደቡብ አፍሪካ ሮቢን ሁድ እስር ቤት ባልተናነሰ በሰንሰለት ታስረው ጉድጓድ ውስጥ ታፍነው ለሸቅል ብቻ ሊወጡ የሚፈቀድላቸው ዛሬም እንዳሉ ከኤርትራኖቹ ራሳቸው የተዘገበ ጉዳይ ሆኖ እያለ፡ “ጭራቆቹ”የሻዕቢያ ባለሥልጣኖች “ለኢትዮጵያ ሕዝብ በጎ አመለካከት አላቸው” እያለ መወትወት ያልሰለቸው ያለ ማባራት ሁሌም “ጸረ ትግራይ ሕዝብ” ቅስቀሳ የሚካኼድበት “ካረንት አፌርስ” የተባለው “ፓልቶክ” እና “ኢካድ ፎረም” የተባለው ድረገጽ ባለቤት ነኝ የሚለን የግንቦት7አፍላ/ወጣት “ተክሌ”የተጻፉ ጽሁፎች በሚመከት በዚህ ዓምድ አንመለከታቸዋለን። እንኚህ ሁለት ጽሁፎች ስለ ግንቦት7አማራጭ የለሽነት የሚሰብኩን ቢሆኑም በፋሽስቱ “በኤርትራ ህዝባዊ ሓርነት ኤርትራ”ግምባር/ወታደራዊ የሽምቅ መንግሥት ያላቸው አመለካከት ግን ተቃራኒዎች ናቸው። “አርበኞች ግምባር፤ግንቦት7፤የሻዕቢያ ሰላዩ ተስፋዬ ገብረአብ ከፍል 4”በጥቁር ጫካ የቀረበው የግንቦት7 አመራር (አንዳርጋቸው ጽጌ)እና የኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥት ግንኙነትና ለዓመታት አስመራ ከተማ የመሸገው “አርበኞች ግምባር” ተብሎ የሚጠራ ድርጅት የሚተነትነው ጽሑፍ በመረጃ የተደገፈ ጠቃሚ ዘገባ ቢሆንም ግንቦት7ን በጎንደር፤በወሎ እና በጎጃም ሕዝብ የሚደገፍ ድርጅት መሆኑና እነኚህ ሦስት (የሸዋ አማራ ሕዝብን አልጨመረም) የአማራ ሕዘብ አካባቢ ተብለው የሚታወቁት ክፍለሃገሮች “ግንቦት7ን” /መንፈስ/ ብለው እንደሚጠሩትና ነፃ የሚያወጣቸው ድርጅትም “ግንቦት7 መሆኑን” በጉጉት እየተጠባበቁት እንዳለ ጎንደር ድረስ አንድ ቤተሰብ ጋር ደውለው መረጃውን እንዳገኙትና እሳቸውም ቢሆኑ የአርበኞች ግምባር አባል ሆነው “ግንቦት7”እንደሚደግፉ ሳይሸሽጉ ገልጸውልናል። ጉድ ነው!!! የሻዕቢያ እና የተጠቀሱት ድርጅቶች ግንኙነት ባጭሩ በመረጃ አስደግፈው ያቀረቡት ትንተና ተቀባይነት ያለው ቢሆንም አሳማኝ ዘገባቸው በሚከተለው ሁኔታ ጭቃ እንዲቀባ አድርገውታል።ስለ አርበኞች ግምባር ልባቸው ሲደማ ለግንቦት7ም እንዲህ ሲሉ ግሩም ሲገቡልን የነበረውን ዘገባቸው በዘገባው መደምደምያ ላይ ድነገት በጭቃ ቀቡት ያልኩትን ልጥቀስ እነሆ። “ጽሁፌን ወደ ማጠቃለሉ ስገባ ባሁኑ ሰአት በውጭ አገርም በውስ አገርም ሁሉም ሕዝብ ያለ ግንቦት7 ሌላ ወሬ መስማት አይፈልግም። ትልቅ ተቀባይነት አግኝታችሗል። ሕዝቡ እምነቱ በናንተ ነው። ስለዚህ መታገል ያለባችሁ የሕዝቡን ጠላት ነው። ከዚህ ከሚደግፋችሁ ሕዝብ ውስጥ ደግሞ አማራው አንዱ ነው። ባሁኑ ሰአት በጎንደርም በጎጃምም በወሎም ያለ ሕዝብ ትኩረቱና ፍላጎቱ ከናንተው ጋር ነው። ቤተሰቦቼን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ጎንደር ስደውል ዘመቼ ገና የናፍቆት ሰላምታዬን ሳልጨርስ “ስለ ግንት7ላወራቸው ፈለጉ”(ቅንፍ የኔ)፡ይህ ማለት ታለቋ መሪያችን ብርቱካን ቅንጅት መንፈስ ነው እንዳለችው አሁንም ግንቦት7 “መንፈስ ነው፤ በሁሉም ቤት ገብቷል” (ቅንፍ የኔ) አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀውን ሳታስጠጉ “አማራው ምን ይሰማዋል? ምን ይለናል? ብላችሁ አስቡ” (ቅንፍ የኔ)” ጸሐፊው ግንቦት7 ዋርካ ፤ጥላ ነው… በማለት ፕሮፓጋንዳቸውን ያደመቁበት ጽሑፍ ነው። ስለ እኚህ ፀሐፊ ስለ አስመራው ዘገባቸው አክብሮት ቢኖረኝም ከላይ እንደገለጽኩት የግንቦት7 ቅስቀሳቸው በውሸት መዳከራቸው ከምራቸው ተነሳስተው በሃገራዊ ቁጭት የዘገቡትን ዘገባቸው ታጠቦ ጭቃ አደረጉት። በጽሑፋቸው ላይ ብዙ የተሳሳቱ ትንተናዎችን ዘግበወዋል። ከላይ የጠቀስኩትን ስለ ግንቦት7 አባባላቸው የምመለስበት ስሆን፡ ለምሳሌ ለምሳሌ በሻዕቢያ አቀነባባሪነት ባኦነግ መሪነትና ተሳታፊነት የተካሄደው ዘግናኙ የወለጋው ዕልቂት ኦነግ ሳይሆን ሻዕቢያ ነው በማለት ድርቅ ሲሉ፤ ለዚህም “ኮሎኔል ጎሹ ወልዴን”ጠይቁ በማለት በማስረጃነት ይጠቅሳሉ (ኮሎኔል ዶ/ር ጎሹ ወልዴ ጥሩ ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ተወላጅ፤ጠንካራ አገር ወዳድ መሆናቸውን ባውቅም-ዋሺንግተን በአሜሪካን ኮንግረስ ቀርበው ከነ ፕሮሰር መስፍን ጋር በመሆን በወንበዴዎቹ በወያኔ እና በሻዕቢያ ተወካዮች ላይ (በሻዕቢያው በርሐ እና በወያኔው አሰፋ አብርሃ) የሴናተሮችን አፍ በተፈጥሮ የተሰጡት አፍዝዝ አደንዝዝ አስደናቂና አኩሪ የንግግር ችሎታቸው መቸም የማልረሳው እና የሚያኮሩኝ ዜጋ ቢሆኑም) ኮለኔሉ ስለ ወለጋ እልቂት እና ስለ ሻዕቢያ ምን እንደሚያውቁ ባላውቅም እኔ ያለኝን መረጃ እና ሻዕቢያ በወቅቱ በራዲዮኑ ያስተላለፈው የትግርኛ ዜና እና ኦነግ በጋራ የተሳተፉበት ግዳጅ መሆኑን መረጃው በእጄ እንደነበር አስታውሳለሁ (በ ኢ-ኢ ዲ ኤን የውይይት መድረክም ቅጂው ለጥፌው እንደነበር አስታውሳለሁ)።(በዚህም ተጨማሪ ይህን አስመልክቶ የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር አለሜ እሸቴ የዘገቡትን ጉግል ፈልጎ ማንበብ ጠቃሚነት አለው።) ሌላ በተጨማሪ 2008 (በሻዕቢያ ዘመን አቆጣጠር) የሻዕቢያው ጀነራል ኤፍሬም (ወዲ ስብሓት) ያደረገው ቃለ መጠይቅ (“ተዓጠቕ” በሚለው የትግርኛ መጽሔታቸው)ላይ ታጋይ መኮንን የተባለው የግዳጁ የኮማንዶ መሪ ከኦነግ ጋር መበሆን ያደረገው የወቅቱ ጥቃት እነሱ ዓወት/ግዳይ (ድል/ግዳጅ)ይሉታል እኛ “ዕልቂት/ጭፍጨፋ”እንለዋለን፦ የሚጠቅሱ መረጃዎች እንዳሉ የታወቀ ነው። የህ የጠቀስኩት ምክንያት ኢትዮጵያዊ አይደለሁም የሚለው የሰለቸኝን ጭራቁን ኦነግ ለመተቸት ሳይሆን ጸሐፊው ሻዕቢያ እንጂ ኦነግ የለበትም በማለት ሲያስተምሩን ውሸት ከሆነ ደግሞ በግልፅ ወጥታችሁ ሞግቱኝ ስላሉት ሁኔታ በጨረፍታ ለመግለጽ ነው። አሁን በዚህ ብዙ አልገፋበትም። አሁን ከላይ የገለጽኩት ጥቅስ (ስለ ግንቦት7) ያሉትን ልመለስና ወደ ሁለተኛው ጸሓፊ እገባለሁ። ጥቁር ጫካ ስለ ግንቦት7ፍቅራቸውና ሦስቱ የአማራው አካባቢ ክፍለሃገሮች መረን የለቀቀ ፍቅር እንዳለው እንደሚከተለው ገልጸውታል። “ከዚህ ከሚደግፋችሁ ሕዝብ ውስጥ ደግሞ አማራው አንዱ ነው። ባሁኑ ሰአት በጎንደርም በጎጃምም በወሎም ያለ ሕዝብ ትኩረቱና ፍላጎቱ ከናንተው ጋር ነው። ቤተሰቦቼን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ጎንደር ስደውል ዘመቼ ገና የናፍቆት ሰላምታዬን ሳልጨርስ “ስለ ግንት7 ላወራቸው ፈለጉ” (ቅንፍ የኔ)፡ይህ ማለት ታለቋ መሪያችን ብርቱካን ቅንጅት መንፈስ ነው እንዳለችው አሁንም ግንቦት7 “መንፈስ ነው፤ በሁሉም ቤት ገብቷል” (ቅንፍ የኔ) አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀውን ተስፋዬን ሳታስጠጉ “አማራው ምን ይሰማዋል?ምን ይለናል?ብላችሁ አስቡ” (ቅንፍ የኔ)” ወንድሜ አቶ ጥቁር ጫካን ልጠይቅ፦ በጨረፍታም “በኢመይል ደብዳቤ”እንደላኩለዎት አሁንም በድጋሚ በይፋ እዚህ ልጠይቀዎት። የጠቀሱት ሦስቱ የአማራ ክፍለሃገር አካባቢዎች ፍቅሩ፤ፍላጎቱና ትኩረቱ ከግንቦት7 “መንፈስ ነው” ጋር ነው ሲሉን በወያኔ መሳፍንቶች ዓይን ውስጥ የገባው የሸዋው አማራ ለግንቦት7 ያለው ፍላጎት ፍቅርና ትኩረት ምን እንደ በላው አልነገሩንም። የሸዋ አማራ ብቻውን ተነጥሎ የነ ብርሃኑ የነ አንዳርጋቸው የነተመስገን ማዴቦ “መንፈስ”ለምን እንዳልማረከው የጎንደር ቤተሰብዎ በዚህ ያለዎት ነገር ቢኖር አንድ ቢሉን?ለመሆኑ ቤተሰቦችዎ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ላዲሱ ዓመት ሲደውሉ “ገና የናፍቆት ሰላምታዬን ሳልጨርስ “ስለ ግንት7 ላወራቸው ፈለጉ” ሲሉን እውን ከእርስዎ ይልቅ ለግንቦት7 ናፍቆት አይሎባቸው ነው የርስዎን ናፍቆት ሳያስጨርሱ ስለ ግንቦት7 ፍቅርና ነፍቆት ትኩረታቸው ሊስበው የቻለው?በጣም አስገራሚ የናፍቆት ሰላምታ ነበር የተለዋወጡት። አገር ጥሎ፤ባሕር ተሻግሮ በናፍቆት የሚቃጠለው ቤተሰብዎን ለማነጋገር ሲደውሉ የፖለቲካ ድርጅት ቅድሚያ ሰጥቶ የርስዎን የናፍወቆት ሰላምታ አቋርጦ ለድረጅት ፍቅርና ናፍቆት ቅድሚያ የሚሰጥ የሰላምታ ልውውጥ (ያውም ኑሮአቸውና ልጆቻቸው በምቾት ውጭ አገር እያስተማሩ የሚገኙ የግንቦት7 መሪዎችና ድርጅታቸው! ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋንም አላይ!) ስሰማ የመጀመርያ ጀሮየ ነው። በጣም አስገራሚ መንፈስ~! እውነትም መንፈስ! ለመሆኑ አማራው ብቻ ለግንቦት7 ፍቅሩ የለገሰው በምን የትግል ማሕደሩ ይሆን? ለመሆኑ የርስዎ መረጃ ከአንድ የስልክ ጥሪ እና ከአንድ ቤተሰብ ጋር ያደረጉት ውይይት መላውን (ሦስቱን) አብዛኛው አማርኛ ተናጋሪ አካባቢዎች ያሉበትን ክፍለሃገሮች እንደ የሕዝብ ጥናት (ሪሰርች) አድርገው ለኛ ሲያቀርቡ ተቀባይነቱ ምን ያህል ተአማኒነት እንደሚሆን መዝነው ነበር? ለግንቦት7መልክትዎን ሲያስተላልፉም አስገራሚው ምክርዎ እንዲህ ይላል፡ “አሁንም ግንቦት7 “መንፈስ ነው፤ በሁሉም ቤት ገብቷል” (ቅንፍ የኔ) አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀውን ተስፋዬን ሳታስጠጉ “አማራው ምን ይሰማዋል? ምን ይለናል? ብላችሁ አስቡ” (ቅንፍ የኔ)” ብለዋል። ወንድሜ አቶ ጥቁር ጫካ፡ ምክርዎ እንከን የለውም። ተስፋዬ ገብረአብ የተባለው የሻዐቢያ እና የኦነግ ነገረፈጅ መሆኑ እውን ነው። እሱን እያቀበጡት ያሉት በትልቁ “ግንቦት7የተባለው መሪ ብርሃኑ ነጋ እና ተከታዮቹ፤ እነ ክንፉ አሰፋ (ኢትዮ -ፎረም.ኦርግ)ኢካድ ፎረም.ካም (ተክሌ)፤ካረንት አፈይርስ ፓልቶክ (የሻዕቢያ፤የኦነግ እና በስሜት የሚከንፉ ፀረ ትግራይ ሕዝብ የሆኑ ግራ የተጋቡ አንዳንድ ውዥምብራም ኢትዮጵያዊያን/ኢትዮጵያዉያት የመለስ ዜናዊ ተቃወሚዎች ነን የሚሉ ስብስቦች እና የግንቦት7 ደጋፊዎች በሙሉ) እንዲሁም ኢሳት የተባለ አዲሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ከሻዕቢያ ደጋፊዎች ጋር የሻዕቢያ ባንዴራና እና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አብረው በማውለብለብ ለሻዕቢያ ድጋፍ ባደባባይ ሰልፍ የወጡ እነ ንአምን ዘለቀ የሚመሩት የቴሌቪዢን ጣቢያ/መደብር…)እና የሻዕቢያው ወኪል ኤልያስ ክፍሌ እና አገር ውስጥ የሚታተም “አውራምባ ታይመስ”ተብሎ የሚታወቀው ሌላኛው ውዥምብራም ጋዜጣ)ተስፋዮ ገብረአብ የተባለው የወያኔ፤የኦነግና የመሳሰሉ ያን የሻዕብያ ውሻ እያቀለጳጰሱብን ያሉት እነኚህ ናቸው። ሌላ ቀርቶ የስዬ አብርሃን እናት “አንቺ”እያለ በመዘርጠጥ ሲጽፍ ሆን ብሎ እንደጻፈው ዋለጌነቱ ቢረዳውም ትላልቁን፤ አረጋዊውን፤ ቄሱን፤ባሕታዊውን፤እናቶችን፤ያገር መሪዎችን፤ነገሥታትን ባንቱታ ሳይሆን በአንቺና በአንተታ ባንድ ጆሮዋቸው የማንጠልጠሉን የባንዳዎቹ የሻዕቢያ ባሕል መላበሱን በፖለቲካ ውስጥ የሌሉበትን የስዬ አብርሃ ወላጅ እናት (ያውም በዕድሜ በጣም አረጋዊ የሆኑትን እናት) አንቺ እያለ ሲዘልፍ ሻዕቢያነቱ ያስታውቅበታል። ያላነበባችሁ እንዳትኖሩ ለሬከርዱ እነሆ እንዲህ ነበር ያለው፡ (“ፍርድ ቤት ስቀርብ እናቴ በትምኒት ተደግፋ መጥታ ነበር…”(ስዬ አብርሃ ነው እንዲህ እያለ ያለው በአዲሱ መጽሃፉ ውስጥ)በዚህ አያበቃም (ተስፋዬ ገብረአብ ነው በዙሁ አላበቃም እያለ ያለው)። ከመታሰሩ በፊት እናቱን ከወንድሙ ከምህረተአብ ቤት (ምህረተአብ የታሰረ ቀን) አጊኝቷት እንደነበርና ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ እንደነበር ጭምር ይነግረናል።”) ስለዛ የሻዕቢያ ሰላይ አዛውንትን የመዝለፍ ዋልጌነቱን እዚህ ልተውና አቶ ጥቁር ጫካ “አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀውን ተስፋዬን ሳታስጠጉ “አማራው ምን ይሰማዋል? ምን ይለናል? ብላችሁ አስቡ” (ቅንፍ የኔ)” ስለሚሉት ትንሽ ልበል። አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀው ሰላዩ ተስፋዬ ገብራብ ብቻ አይደለም። እርስዎ “መንፈስ” የሚሉትን ግንቦት7 የሚመራው የእስላሞች ኮፍያት/ኮፊያ አጥልቆ አሥመራ ኮምቢሽታቶ ላይ የሚሞላቀቀው አንዳርጋቸው ጽጌም በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የዕልቂት ጥሪ አውጆ ለትውልድ የሚተላለፍ መጽሐፍ ከትቦ አስተላልፏል። በተለይም ደግሞ “ብሔሬ/አገሬ/ፋዘር ላንድ/ማዘር ላንድ- በትግርኛው “ዓዲ አቦ” ኢትዮጵያ ነው” ያለውን ሁሉ በጠላትነት እንዲታይ የሕሊና ከበባ እንዲደረግበት ከሻዕቢያዎቹ/ከጀብሃዎቹ…ከእነ ተስፋዬ ገብረ አብ ፤ከእነ መለስ ዜናዊ፤በረከት ስማኦን፤አርከበ ዑቁባይ፤ቴድሮስ ሐጎስ፤ስዩም መስፍን፤ስብሓት ነጋ…እና ከመሰል የወያኔ ቡችላዎች ጋር ሆኖ ከባድ ቅስቀሳ አድርጓል። አንዳርጋቸው “ኦሮሞ ነኝ” ብሎ በመጽሐፉ ይፋ ቢያደርግም አሁንም እርስዎ እንደሚነግሩን “አንዳርጋቸው ተስፋዬ ገብረአብ የሻዕቢያ ሰላይ/መረጃ መሆኑን ያውቃል ነገር ግን እርስዎ እንዳሉት አስመራ ውስጥ ኢትዮጵያዊያኖቹን እየራቀ የእስላም ቆብ አጥልቆ ከቀንደኛው የኢትዮጵያ ጠላት ጋር አሥመራ ውስጥ ከተስፋዬ ገብረአብ ቤት ውስጥ ዕቃውን ጠቅልሎ ገባ። ብለውናል። አስገራሚ ታሪክ ነው የነገሩን። ሁለቱም አንድ ናቸው።አንዳርጋቸው ከተስፋዬ ገብረአብ ምን ይለየዋል? ፍቅራቸው የጸና ነው። አሁንም ከጠላታችን ጋር ነው እየተሻሸ ያለው። ብርሃኑም አንዳረጋቸውም ለሰላዩ ያላቸው አክብሮትና ፍቅር በጣም የናረ ነው። ያ ፀረ አማራ የሚቀሰቅስ መጽሐፍ ጻፈ፤ ያም እንደዚሁ ጸረ አማራ የሚያነሳሳ መጽሐፍ ከተበ! ከሁለት መልከ ጥፉ ዝንጀሮ ማን ይመርጧል? ግንቦት7ን የሚያደንቁ እንደርስዎ ያሉ የግንቦት 7አድናቂ የአርበኞች ግምባር አባሎች ከዚህ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ግለሰብ ጋር በእፍ-እፍ ፍቅር የተለከፉት አንዳርጋቸውና ብርሃኑ ስለሚመሩት ድርጅት ማድነቅ/መደገፍ የአማራው ሕዝብ ምን ይለናል ማለት የነበረበት ይልቁንስ እንደርስዎ አይነት ሰው ነበር። ያውም እርስዎ በጽሑፍዎ እንደነገሩን ከሆነ የተስፋየ ገብረአብ አዲሱ መጽሐፍ (እስካሁን አላነበብኩትም)አማራው ከአደሬውና ከትግሬው ቂም እንዳለውና እንዲጨፋጨፍ ፕሮፓጋንዳ እንደጻፈ” ያ የጥላቻ መጽሐፍም ግንቦት7 አሳትሞ ለገበያ እንዳዳረሰው ገልጸውታል። ታዲያ ግንቦት7 በአማራው ሕዝብ የሚደገፍ እና የአማራው ሕዝብ ትኩረት እንደሳበ የሚነግሩን አማራው የሚጨፈጨፍበት ሰበካ የሚቀሰቅስ መጽሐፍ ከተሸጠ እና ለገበያ ይፋ ከሆነ ቆይቷል፡ ታዲያ የሸዋው አማራ ሕብረተሰብ ክፍል የተስፋዬ ገብረአብ ተንኮልና የግንቦት7መሪዎች (ያውም አንዳርጋቸውና ብርሃኑ መጽሐፉን በአራሚነት እንደተሳተፉበትም ይነገራል) በማከፋፈሉ/በሕትመቱ/በማስታወቅያው የተሳተፉበትን “የጥላቻ መጽሐፍ” አንብቦት ሆኖ ይሆን ትኩረቱን ሳይስበው ቀርቶ፡ የጎጃም የጎንደር እና የወሎ አማራ ሕዝብ መጽሐፉ አልደረሰውም ሆኖ ይሆን ወይስ ስለ’ዛው “የጥላቻ መጽሐፍ” የሚነግረው አጥቶ? እንደው “ማን ይሙት!” ለመሆኑ አንዳርጋቸው ጽጌ ማን እንደነበር የዚህ ክፍል ሕዝብ አያውቀውም ማለት ነው? እስኪ መልሱን ከእርስዎ ልስማ? ወደ ሌላኛው ግንቦት7 አዳማቂ፤ደጋፊ እና ሰባኪው ወጣት ተክሌ ጽሑፍ እናምራ። “አሁንም፤ ኤርትራ መዳኚያችንም መጥፊያችንም ትመስላለች-..ክፍል አንድ ኤርትራ፣ አርበኞች ግንባር፣ ግንቦት ሰባት” በሚል ርዕስ የቀረበው የተክሌ ጽሁፍ “ግንቦት ሰባት በግሌ ባደባባይ ከኤርትራ መንግስት ጋር መነጋገርና መስራት ካልጀመረ፡ሌሎች የስራ መንገዶች ሁሉ ተዘግተዋልና ትግላችን እዚያው ባለበት መርገጥ ነው ባይ ነኝ።”የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻ ማውጣት በሚደረግ ትግል ውስጥ ግንቦት ሰባትም ይሁኑ ሌሎች ሀይሎች ከኤርትራ ጋር በኢትዮጵያ ስምም ቢዋዋሉ፡ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈው እስካልሰጡ ድረስ ምንም ጥፋትም ክፋትም የለውም። ባህሩንም የባህሩንም በር አሳሌፎ የሰጠ መንግስት አዱስ አበባ ቁጭ ብሎ የለ፡ ያውም እኛ በኢትዮጵያ ዘሊቂ ጥቅም ላይ ከሌሎች ሀይላት ጋር አንዋዋልም፡ ሌላ ሽሽት ነው።መንገዳችን ኤርትራ ብቻ ነች። እነሆ ምክንያቶቼ።” ሲል ምክንያቶቹን ይዘረዝራል። ወይ ጉድ! ሻዕቢያ ድረስ ሄደን ፤ እግር ስመን ተዋጊ ሃይል እንዲያሰለጥንልን በቁሳቁስና በሞራል እገዛ ቢያደርግልን ኢትዮጵያን ከወያኔ ጦር ነፃ ማውጣት ይቻላል ነው የሚሉት እኒህ ወገኖች። ልጁ የሚለን የኢትዮጵያ ጥቅም አሳልፈው እስካልሰጡ ድረስ ምንም ጥፋትም ክፋትም የለውም ነው። እያለን ያለው። ልጁ የጣሳቸው ሕጎች አሉ። እጠቅሰዋለሁ። አንደኛ ሻዕቢያ የኛ ጠላት ነው። የኤርትራኖችም ጠላት ነው። ቡድኑ ፋሺስት ነው። መሪውዬውም ሕግ ቢኖር ኖሮ በተለያዩ ወቅቶች በዓለም አቀፍ ሕግጋት የሚያስጠይቀው ወንጀል የፈጽመ የጦር ወንጀለኛ ነው። ከሃይለስላሴ፤ከደርግ እስከ ወያኔ ድረስ ያሉት ወቅቶች የፈጸማቸው ወንጀሎችን ይጠቅሰዋል። በሗላ እምለስበታለሁ። “ለመታገል ኤርትራ የሚሄድ ሁሉ የሸቀጥ ነጋዴዎች ሳይሆኑ እራሱ ሸቀጥ ነው አለኝ።”ሲሉ ጥቁር ጫካ የተባሉት ጸሐፊ አስመራ ውስጥ ከሚገኝ አንድ የአርበኞች ግምባር አባል በሚገባ አብራርተውታል። “ኤርትራ ውስጥ በራስህ፤በወገንህ ዓላማ/አጀንዳ መታገል አይቻልም።በግድ በሻዕቢያ ጥቅም እየተደለልክ፤በሻዕቢያ ዓላማና ስልት ነው መታገል ያለብህ። እሱ በፈቀደው! ይኼን የማይቀበል ወደ መጣበት እምቢ ብሎ መመለስ ነው። አቅም የለውማ!!!! ባዶ እጅ ተይዞ ሸዕቢያን በምኑ ነው ወደ ጠረጴዛ አስጠግቶ እኩያ አድርጎ መደራደር የሚቻለው!?እምቢ አልስማማም ያለ ቀኝ ሗላ ዙሮ ወደ ለንደን ይሄዳል፤ የሚቀበል ደግሞ በሆዱ እየተገዛ ናቅፋና ዶላር እየፈሰሰለት ያገለግላል። ስለዚህ ሸቀጥ ሆነ ማለት ነው። ይኸ ደግሞ ጥቁር ጫካ ቁልጭ ባለ ሁኔታ አብራርተውልናል። ይኼን በሚመለከት ለመረዳት ሲል ኤርትራ ውስጥ ያለ ወዳጃቸው እቅጩን ነግሯቸው እንደነበር አቶ ጥቁር ጫካ ከላይ በጠቀስኩት ክፍል አራት ዘገባቸው ላይ ዘግበውታል፡ ያን ማንበብ ነው። ስለዚህ ወጣት ተክሌ የሚያምታተው “የሻዕቢያ መኳንንት/ባለስልጣኖች ለኢትዮጵያ በጎ የሚመኙ ናቸው” ግንቦት7 በሕዝብ ስም ከሻዕቢያ ሹማምነት ጋር የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈው እስካለሰጡ ድረስ ቢዋዋሉ ምንም ክፋት የለውም” ይለናል። የፖለቲካ ጌኞነት ካልሆነ በቀር ግንቦት7ም ይሁን ሌሎቹ ወደ ፋሸስቶቹ መንደር ሲገሰግሱ ከሻዕቢያ ጋር ሲደራደሩ “እራሳቸው የሚሸጡ ሸቀጦች”ናቸውና የሚደራደሩበት ካርታ/ቺፕ/ጠጠር፤መደራደርያ የላቸውም።የባሕር ወደብ መጠየቅ አይችሉም፤ በስታሊናዊ/ሞኦይስት/ማርክሲሰት/ኮሚኒስት/ፋሺስታዊ የብሔር አደረጃጀት ስልት ካልተደራጁ ዕጣቸው ተመልሰው ወደ መጡበት አገር ባዶ እጅ መጓዝ ነው። ከሻዕቢያ ልሳን የማይጠፋ “ዓጋሜዎች ጠግበዋል1”ሲሉ ዝም ብሎ ማዳመጥ ነው። አማራ/ነፍጠኛ/አድጊ ቦታውን አስይዘነዋል!ሲሉም ዝም ብሎ ማድመጥ ነው። ይኼንና እነኚህን የመሳሰሉ ሞሶሊናዊ ትምክህቶች አርፈው ማድመጥ ካልቻሉ፤ ዕጣቸው ባዶ እግር ወደ እንግሊዝ፤ዴንማርክ፤ አሜሪካ… መመለስ ነው። ኢትዮጵያዊን ነን የሚሉ ሻዕቢያን በጦርነት ከሚዋጉ የቀይ ባሕር ዓፋሮች (ዓሰብና ምፅዋ ተወላጆች)ኢትዮጵያዊያ አፋሮች እና ሌሎቹ ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም። እነኚህ ሁሉ የሻዕቢያ መደራደርያዎች ናቸውና ‘የማይነኩ-ለድርድር የማይቀርቡ ሕጎች ናቸው። ታዲያ አስመራ ድረስ እየሮጡ ዕርዳን ብለው ፋሺስቶቹን የሚማጠኑ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ድርጅቶች የሚደራደሩባቸው ምን የመደራደርያ መቁጠርያዎች ይዘው ነው አንድ ሁለት ብለው ሻዕቢያን ሊደራደሩ የሚችሉት። ምንም! እራሳቸው ሸቀጦች ናቸውና የመደራደር መብት የላቸውም! ሻዕቢያን የሚጠይቁት “ጠመንጃ፤ማሰልጠኛ ቦታ፤ስንቅ፤ትጥቅ፤ መጠለያ፤ አሰልጣኝ፤መሸጋገርያ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ቪዛ….” ሲሉት ፡ ሻዕቢያ ደግሞ ይህንነ ለማግኘት “በብሔር ተደራጁ፤የባሕር ወደብ መብት አትጠይቁ፤መንግሥትነት ስትረከቡም ለወደፊቱ እንዳትጠይቁ በፌርማችሁ አረጋግጡ ቢላቸውስ? (ተክሌ የሚለውን “ሕዝብ ባይፈቅድም ድርጅቶች የመደራደር መብት አላቸው” የሚለውን ማለት ነው ድረድር ማለት?) ተክሌ ያልገባው (ወይንም ገብቶት ነገር ግን ሆን ብሎ የጀሌ ሰበካ/ፕሮፓጋንዳ እያዳመቀም ሊሆን ይችልል) ነገር “ዘላቂ የኢትዮጵያ ጥቅም እስካልተደራደሩ ድረስ ማንም ድርጅት/ግንቦት7… በሕዝብ ስም መደራደር መፈራረም ይችልል” ሲል ተክሌ ነገሩ እጅግ አልገባውም። “ተመጽዋች ተደራዳሪ ስላልሆነ አቅም ስለሌለው ደካማ ወገን የሚደራደረው በዘላቂ ያገሪቱ ምስጢሮችና ሉዓላዊነት ነው! (ይኼ ደግሞ ባለፈው ታሪካችን ታይቷል) ወያኔ ለሱዳን አስቀድሞ እንደሸጠን አይነት!። ወጣት ተክሌ ያልገባው ነገር እያልኩት ያለሁት ጉዳይ “ከሻዕቢያ ጋር ድርድር ሲደረግ “ሻዕቢያ እንደማንም አገር/ጎረቤት/ሕብረተሰብ/መንግሥት ሰላማዊ የኢትዮጵያ አጋር/ወዳጅ/መልካም በጎ እይታ ያለው ሳይሆን “ጠላት ነው”! ጠላት ሆኖ ከሚታይና በግብርም የታየና በመታየት ላይ ያለ ጠላት የሚመደራደርህ ዘለቄታ ባለው በብሔራዊ ጥቅምህ እና ደካመ ጎንህ ነው! ሻዕቢያ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ዘለቄታ ጥቅም መቆጣጠር ቅድሚያ አጀንዳው እና የሕይወቱ ዋስትናው ነው! ያ ካልሆነ ኤርትራ የምትባል አገር በሻዕቢያ ቁጥጥር ስር መኖር አትችልም! ስለዚህ ነው ሻዕቢያ ማንንም ከኢትዮጵያ የሚመጣ ቡድን የኢትዮጵያን ዘላቂ ዕድገትና ጠቀሜታ ላስጠብቅ የሚል ቡድን ድጋፍ የማይሰጠው! ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የሚባለው አጀንዳ ራሱ ቃላቱ “ከኤርትራ ጋር ጦርነት የሚቀሰቅስ ነው!” ስለሆነወም ሻቢያ በራሱ ላይ ለመዝመት የሚመጣ (ዘለቄታው የሚጻረር ቡድንን) ለመርዳት የማይፈልገው! ተቃዋሚዎቹም ቢሆን እንዳልኩት የሕዝብ መብት ለመደራደር መብቱስ ይቅርና “የሚደራደሩበት አቅምም የላቸውም”! ስለዚህ ተክሌ ራሱን ማታለል ካልሆነ ግንቦት7 አንድ አንዳርጋቸውና 15 ሰዎች በስድስት አመት ውስጥ ተሰነይ ውስጥ/ሳዋ ውስጥ (? በጥቁር ጫካ ዘገባ መሰረት) ጦር እያሰለጠነ ማለት (ራሱን ባልዘረጋበት ሁኔታ ሆኖ) የሕዝቡን ዘለቄታ ለመደራደር ይችላል ማለት ሓማ ቱማ “ቃለ አጋኖ” የሚለው ወይንም ጉረኛ ፖለቲካ ከማስተጋባት ሌላ የሚፈይደው የለም! በማለት የምከራከረው ለዚህ ነው። ወገኖቼ ሆይ! ባለፈው ታሪካችን ስናስታውስ ከሻዕቢያ ጋር ተዳብለው የሰለጠኑ እና የተጎዳኙ ወይንም ዛሬ እንደ እነ ተክሌ እና ንአምን ዘለቀ እንደ እነ ክንፉ አሰፋ እና የግንቦት7 መሪዎች እና ምሁራን ወዘተ ወዘተ… ስለ ሻዕቢያና ወያኔ መሪዎች ሰብአዊነት፤በጎነት፤ነፃ አውጪነት፤አሳቢነት ሲሰብኩና የዋሁን ሕብረተሰብ ሲያደናግሩ ኖሮው መጨረሻ ላይ ተው ልክ አይደለም ሲባሉ አንሰማም ብለው፤ ሁለቱ ወረበሎች አስመራና አዲስ አባባ ሲቆጣጠሩ “”ዋሽንግተን ኮነግረስ ውስጥ አሰፋ አብራሃ የተባለው የወያኔ አፈቀላጤ/ቱልቱላ (ከ እንግሊዝ አገር/ለንደን) “ኢምፔርያል ኢትዮጵያ” “ኮሎኒያሊስት ኢትዮጵያ’ ሲል ፕሮፌሰር በርሐ ወልደገርግስ የተባለው ሌላኛው የሻዕቢያ ጡሩምባ ነፊም ኤርትራኖች ከኢትዮጵያ ነፃ መውጣታቸው ጥቁር አሜሪካኖች ከባርነት ቀንብር ነፃ በመውጣት “ፍሪ አትላስ”እንዳሉት ሁሉ፤ የእስራል አይሁዶችም ከናዚዎቹ ቀንበር ነፃ እንደወጡት ሁሉ ኤርትራኖችም ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ኮሎኒያሊስቶች ከባርነት ቀንበር ሰንሰለቱን በጥሰው ነፃ በመውጣታቸው ከበሮ እየደለቁ ደስታቸውን በመላው ዓለም በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ዓለም የዓይን ምሰስክር ነው! ብሎ ነበር። እንኚህን ሓሰተኞች፤ከዳተኞችና ጭራቆ ድርጅቶች እየካቡ ታዝበን ስንገጥማቸው “ተውዋቸው”“አትውቀሱዋቸው” ሰንደቃላመይቷን ቢያበሻቅጡም ታሪክ ቢዘልፉም ’አትቃወሙዋቸው፡ ደርግን የጣሉልን አዳኞቻችን ናቸው፤የብሐረሰብ መብት ተማጓቾች ናቸው…..ሲሊን የነበሩ ሁሉ አንድ ሳምንት ሳይቆዩ “በተናገሩት ምላስ አፍረው የገዛ ምላሳቸው ቀረጠሙት” አንዳንዶቹ ዛሬ ከኛ በባሰ ሲጮኹ ይታያሉ (አንዳንዶቹ’ማ የፏስሰቶቹ ቀንደኛ የናዚ “ጉበል” ሆነው መጽሐፍ ሲጽፉ የነበሩ ናቸው)። ዛሬም ያ ታሪክ በተጠቀሱት ቡድኖች ካለፈው ትምህርት ሳይቀስሙ እንደ አህያ ያ ስንፍና ዛሬም እየደገሙ “ኤርትራ ገዳያችን/አዳኛችን” ነች ወደ ሻዕቢያ እንንበርከክ ሲሉ ወደ ፋሽስቶቹ እንሸብረክ እያሉ አሳፋሪ ሰበካ በመስበክ ሰሞኑን የውርደት ሰበካ በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ። ይህ የተቀነባበረ ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ መልከ ብዙ ቢሆንም በተጠቀሱት ሚዲያዎችና የሚዲያ በለቤቶች የሚዘረጉት የኤሊቲሲዝም ክበብ/ቡድን ሰበካዎች ለመቋቋም ዛሬም በድጋሚ እንዳለፉት ሁሉ ትግሉ መጦፍ አለበት እላለሁ። ትግላችን በጸረ ኢትዮጵያ ቡድኖች፤ጠባብ ትምክህተኞች፤ኤሊቲሲዝም’የሊሂቅ/የፈርሳም ክለብ ፖለቲካ አራማጆች የሚነዙት ሰበካ ላይ ማነጣጠር ወቅታዊ ነው። በደርግ ወቅት ደርግ ወቅት ወያኔ፤ሻዕቢያ ኦነግና ወያኔዎች እንደነበሩ ሁሉ ዛሬም ጠላት የሚባሉት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ ከሻዕቢያ ከጭራቆቹ ከነ ኦነግ ጋር እንጠጋ “ሻዕቢያ አዳኛችን ወይንም ገዳያችን” ነው፤ ከሱ ጋር ካልተደራደርን፤ካልተጠጋን የኢትዮጵያ ሕልውና ለዘላለሙ ያከትማል። ፈጣሪያችን ሻዕቢያ ነው፤ ሊገድለንም ሊያድነንም የሚችለው እሱ አንድ ሻዕቢያ/ኤርትራ ነው!! እንጠፋለን! ብሎናል ተክሌ የተባለው የግንቦት7 ሰባኪ ወጣት። እኛ በጭካኔ ያደጉ የሻዕቢያ ወጣቶችና መሪዎቻቸው አብረን ስላደግን እናውቃቸዋለን፡ ተክሌ ባህሪያቸው አያውቃቸውም። በዕድሜም የበሰለ አልመሰለኝም።ያደገው ቦረና ይመስለኛል። ስለዚህ የተስፋዬ ገብረአብ ሰበካ እንደ ጋቢ ሲከናነበው ሙቀት እንደሚጥማት እንቁራሪቷ ለጊዜውም ተመችቶት “ገዳያችንና አደኛቺን ሻዕቢያ/ኤርትራ ነው/ነች” እያለን ያለው የኢካድ ፎረም ባለቤት ወጣቱ ተክሌ ኤርትራ በማን እጅ እንዳለች መንገሩ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ኤርትራ የትግራይን ወጣት፤እናቶች፤አባቶች፤መምህራን እና ህጻናት ዓይደር ላይ በክላስተር ቦምብ በአይሮፕላን የፈጀ በፋሽስቶች በወረበላ (ራግ ስቴት) እጅ በሻዕቢያዊያኖች እጅ ነች። ተክሌ እና ግንቦት7 መሪዎች ስለ ትግራይ ህፃናትና ስለ ኢትዮጵያ ሰላማዊና ወታደራዊ ነብሳት መጨፍጨፍ በሕሊናቸው ማሕደር ውስጥ አልተዘገበም። ቢኖርም ጉዳይ አላሉትም። እኛ ግን አልረሳነውም፡ በወቅቱ አነጋገር “ኤርትራ ማለት ሻዕቢያ መሆኑን ተረዱልን”። በደመኛ ጠላታችን የተያዘቺው ኤርትራ (ሻዕቢያ)ገዳይ እንጂ አዳኛችን ልትሆን ከቶ አይቻላትም። ስትገድለን መሸብረክን ዳግም የሚሰብኩ ተሸብረኩ የሚሉን ሃፈረት ትርጉም የማያውቁ ነብሳት ማወቅ ያለባቸው በኛ እና በኤርትራ ሻዕቢያ መካከል ያለው ነባራዊ ሁኔታ “የጥይት ዝናም እንደ ማባራት ቢልም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የቆየው ጦርነት አበቃ ምዕራፉም ተዘጋ ለማለት አያስደፍርም። “የተኩሱ ድምፅ እየሞተ መሄድ ወይም የጥይት ማጓራት ማቆም፤በተጨማሪ፣ የተሟሟቀ ውጊያ ወሬ ጊዚያዊ ዝምታ የሰላም መገኘት ምልክት አይደለም”(አምባገነኖችን እንዴት እንቀላቀላቸው?) ጦቢያ ቁጥር 12 ቅፅ 7 ቁጥር 12 1992 ዓ.ም.) የምንለው አሁንም ግንቦት ሰባትና ሌሎቹ ወደ አስመራ በመገስገስ የሻዕቢያን መሪ በርና የሻዕቢያ “ባይቶ” በማንኳኳት የሚማጸኑትንም ሆነ “ሻዕቢያ አዳኛችንም ገዳያችንም ነው” በማለት የአዳኝና የገዳይነት መለኮታዊ ኦምኒፖተንስነት የሚሰብኩን የሻዕቢያ ቱልቱላ ኢትዮጵያዊያኖች (ስዬ አብርሃ በምርጫው የክርክር መድረክ ወቅት የሻዕቢያን ቱልቱላ አርከበ ዑቁባይን “የሻዕቢያን ሚሊዮን ሕዝብ (ሕጻንት…አረጋዊያን..ነብሰ ጡሮችን…) ነብሰገዳይነት እያነሳችሁ ባታስፈራሩን ይሻላል!!” እንዳለው እውነታ ሁሉ) ከገዳዮቻችን ጋር ጦርነቱ ስላባራ ሞተናል እና እንንበርከክ የሚሉ “የመንፈስ ሙታኖች” “የሻዕቢያ ጌታነት አሰልጣኝነትና ገዳይነትና አዳኝነት እየነገሩን”አንድንባንን የሚማጸኑን የዘመናችን ሰባኪዎች ሊያውቁት የሚገባ መልዕክት የጦርነቱ ምዕራፉ እንዳልተዘጋ ያውቁልን ዘንድ በዚህ አጋጣሚ መልክቱ ይድረሳችሁ። የኛ የውሻ ልጅ (አወር ሳን ኦፍ ኤ ቢች) ገዳያችን እንጂ አዳኛችን ሊሆን የማይችልበት ምክንያት ዘርዝሩ በክፍል ሁለት ይቀጥላል………….. ሻዕቢያ ስለ ኢትዮጵያ በጎ አሳቢነትና አዳኝነት አትስበኩን! ክፍል 2 ይቀጥላል…. ጌታቸው ረዳ “ኢትዮጵያን ሰማይ” ብሎግ አዘጋጅ። www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com

Tuesday, September 14, 2010

የትግራይ ትግርኚ ዓላማ መሠረተ ድንጋይ እየተጣለ ነው እንበል?


ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109)
የትግራይ ትግርኚ ዓላማ መሠረተ ድንጋይ እየተጣለ ነው እንበል?
ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com (መስከረም 3/ 2003 ዓ.ም.)
ስድራ ቤታት ትግርኛ ወይንም (የትግርኛ ተናጋሪ ቤተሰቦች) መተዳደርያ ሕገ ደምብ በሚል ቀን እና ዓመተምሕረት የማይጠቅስ “ለሰላም ፈላጊዎች ሁሉ” በሚል ርዕስ ስምና አድራሻ የሌለው ነገር ግን የኢመይል አድራሻ ተደርጎበትselamin_hiwinetn@yahoo.com የሰላምና የወንድማማችነት ምስረታ (የትግርኛ ተናጋሪ ቤተሰቦች) ተግባራዊ እንዲሆን ከጥቅምት መጨረሻ እስከ ሕዳር ወር አጋማሽ ድረስ (ብግሮጎርያን - ኤውሮጳ ኣቆጻጽራ) መስራች ጉባኤ ለመጥራት ቀነ ቀጠሮ ( ዓላማ) ስላለው ለዚህ ዓላማ መሳካት ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ ለማግኘት በደስታ እንጠባበቃለን። በማለት- የትግርኛ ተናጋሪ ቤተሰቦች የሰላምና የወንድማማቾች ማሕበር የሚባል አዲስ ድርጅት ለመመስረት እንደታሰበና ድርጅቱም ከትግርኛ ተናጋሪ “ቤተሰቦች” (የትግራይና የኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪዎች) ብቻ ሳይሆን ከትግርኛ ተናጋሪው ብሄር ጋር አጎራባች የሆኑት (የኩናማ/ዓፋር…) ጋርም ወንድማዊ የሰላምና የአብሮ መኖር ትብብር እንደሚያደርግ ይህ “ማሕበር ሰላምን ሕውነትን ትግርኛ ስድራቤታትን ተዳወብቲ ብሄራትን” በሚል ራሱን የሰየመ አዲስ ድርጅት ሲደራጅ ዋና ጽ’ቤቶቹ ሽሬና እና መቀሌ እንደሚሆን ይገልጻል።

የዚህ ድርጅት መስራች ማን እንደሆነ በግልጽ ባይታወቅም ግምታዊ ቢመስልም በእርግጠኝነት ማን እና እነማን ይህ አዲስ “ቤተሰባዊ የትግርኛ ተናጋሪዎች ሕብረት” ለመመስረት እንዳቀዱ ለማወቅ አያስቸግርም ። ወደ ዝርዝር ከመግባቴ በፊት የድርጅቱ ፖለቲካዊ እምነት “የቤተሰብ መብት” (ክላን) እና “የብሔር መብት” (አካባቢ) አንደሚከተል ግልጽ ሲያደርግ ከብሔር (ጎሳ?) ይልቅ ቅድሚያ “ለቤተሰባዊ ማሕበር” ቅድሚያ እንደሚሰጥ እና ለዚህም ምክንያት ሲገልጽ ቤተሰባዊ ማሕበር ሲከበር የብሔሮች መከበር ማለት ስለሆነ የብሔሮች መብት ሲከበር ደግሞ “የሕዝቦች” መብት መከበር ማለት ስለሆነ የዚህ ማሕበር መመስረት “ስድራቤታት ቅሳነት” (የስጋ ዝምድና፤የጋብቻ ትስስር) ያለው የቤተሰብ ሕይወት መብትና ግንኙነት በዘላቂነት የሚረጋገጥበት ምክንያትም ቀበሌ፤ወረዳ፤አውራጃ የሚባሉ ቤተሰብ የሰፈረባቸው አካባቢዎች የቤተሰብ (ፋሚሊ/ክላን) መሰረት ስለሆኑ ይህ የቤተሰብ ክፍል (ክላን) ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የአያቶቹ ያስረዳደር ደምብ ስላሉት፤ ሕገ ደምቡ ሲጥስም ሆነ ፍትህ ሲፈልግ በአባቶቹ ስርአት እንዲተዳደር ስለሚገደድ ራሱ አስተዳዳሪና ፍትህ ሰጪ ስለሆነ ከውጭ አስዳዳሪና አቀነባባሪ ስለማይኖረው ማንነቱ የሚያረጋግጥበት ፍጹም ዘላቂ ሰላማዊ ሕይወት የሚረጋገጥበት ስለሆነ ቤተሰባዊ ማሕበር የብሄሮች ሁሉ መሰረቶች ናቸው። ይላል።
ባጭሩ የብሔር ፖለቲካ አንድ ብሔር የውስጥም የውጭው ፍላጎቱ በመሰለው መንገድ ገደብ የለሽ የመሰለው መወሰን መተክያ የለውም ይላል፡(ይህ በራሪ ወረቀት የወደፊት “ግልጽ” አቋሙ ግልጽ ላለመድረግ በድብብቆሽ ሲገልጸው)። መልዕክቱ ደጋግሞ የሚያነሳው የብሔሮች መብት (ግልጽ ባያደርገውም እሰከ መገንጠል ድረስ ሊሄድ ይችላል) መከበር የሕዝቦች መብት መከበር ማለት ነውና ይላል።

የዚህ ማሕበር ዓይነተኛ መመስረት በሚከተለው ዓረፍተነገር ግልጽ ያደርገዋል። “ማሕበር ሰላምን ሕውነትን ንዘረጋግጾ ሸቶ ሕውነትን ሰላምን ናይ ብሄረ ትግርኛ
ኤርትራን ኢትዮጵያን ኣረኣያ ኾይኑ ናብ ኩለን ተዳወብቲ ብሄራት ክሰፍን
ኽከባበር
ዕቱብ ቅዱስ ጻዕርታቱ የከናውን፡፡””(የሰላምና የወንድማማቾች ማሕበር ዋናው ትኩረት የኤርትራና የትግራይ ትግርኛ ተናጋሪ ማሕበረሰብ ወንድማማችነትና ሰላማዊ ግንኙነት በአርአያነት መመስረት ሲሆን ሊያረጋግጠው ያቀደው ዕቅድም ወደ እነኚህ ተጎራባች ብሄሮችም እንዲሰፍንና እንዲከባበርያልተቆጠበ ቅዱስ ጥረት ያከናውናል። ይላል።
የሚከተሉት ጥያቅዎች ጭሮብኛል።የኢትዮጵያና የኤርትራ ወንድማማችነት ለምን ወደ ጎን ተውት? የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝብ ሰላማዊና ወንድማዊ ግንኙነት ለመመስረት አቀበት ነው ብለው ነው የተውት ወይንስ ወደ ታች ቆይቼ በምገልጸው የትግራይ ትግርኚ ምስረታ መሰረተ ድንግያ እንዲጥሉ ስለተፈለገ”? ግንኙነቱ እንመሰርተዋለን ዋናው መቀመጫ ቢሮዎቹም (ሁኔታው ሲመቻች ለወደፊቱ አስመራ፤ዓሰብ ባረንቱ እንዲሆን እንመኛለን) ሽሬ እና መቀሌ ይሆናሉ ሲል አስመራ ዓሰብ…ሲል የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ከወያኔዎች ጋር ሲታረቅ ማለት ነው ወይስ በዚህ ጉዳይ በጉዳዩ በምስጢር እጁ አስገብቶበታል? ኢሳያስ ከተወገደ ማለት ከሆነ ለምን በሁለቱ ብቻ ዕርቅ እንዲደረግ ተፈለገ? ሁለቱም ትግርኛ ተናጋሪዎች በተለያዩ አገሮች ማለትም (በኤርትራና በኢትዮጵያ) ተብሎ በሚታወቀው በዛሬው አነጋጋር በጠላትነት በሚተያዩበት እና ደም በተፋሰሱበት ሁኔታ አሁንም በደም በሚፈላለጉበት ሁኔታ ላይ የሚኖሩ መሆናቸውን እየታወቀ “ሁለቱ ትግርኛ ተናጋሪዎች” ለማቀራረብ ቀላል የሆነበትና ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለማገናኘት የከበደበት ምክንያት ምን ይሆን? የደም መፋሰሱ ከተነሳ ጠቡ እና ደም መፋሰሱ በሁለቱ ትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ሳይሆን ጠቡና ጦርነቱ ከመላው የኤርትራ ሕዝብ ጋር እና ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሆነ ዓለም የሚያውቀው ነው። ታዲያ እነኚህ መቀሌ ውስጥ መሠረታቸው የጣሉ አንዳንዶቹም እዛው የሚኖሩና አንዳንዶቹም ውጭ አገር የሚኖሩ የወያኔ አፍቃሪ ኤርትራዊያን ምሁራን እና በጠባብ ጎጠኛ ሕሊና የሰከሩ የወያነ ትግራይ ምሁራን ቡቹላዎች “ጠቡ/ጦርነቱ” በሁለቱ ትግርኛ ተናጋሪ ማሕበረሰቦች የተወሰነ ጦርነትና ጥላቻ ነው ብለው መወሰናቸው መሠረቱ ምን ይሆን? ሁሉም ያካተተው ጦርነት ወያኔዎች ገና ሳይፈጠሩ እየተካሄደ እንደነበር እየታወቀ በትግርኛ ተነጋሪው ማሕበረሰብ ብቻ ሰላምና ወንድማማችነት ሲመሰረት ዋናው ቢሮው አስመራ፤ሽሬ አና መቀሌ እንዲሆን በማሕበሩ ሕገ ደምብ መቀየስ “ጣሊያንና እንግሊዞች የጣሉት” ፖለቲካ ትግርኛ ውልድ (ኦፍስፕሪንግ) መጣል ወየስ ………….? ማሕበሩ ሰላምና ወንድማማችነት በሁለቱም ትግርኛ ተነጋሪዎች ከተረጋገጠ በመላይቷ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ኤርትራዊ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር ሰላም ያውርድ አያውርድ የመኖር ዋስትናው በሸሬ፤ በአስመራና በመቀሌ በሚመሰረተው ቢሮ በኩል የመኖር ዋስትናውና ግንኙነቱ ይረጋገጥለታል ማለት ኢትዮጵያን ለዝንተ ዓለም የማስተዳደሩ ሕልም የተመደበ ክፍል አለ ማለት ነው? ከተቀረው ጋር ሰላም እንዲፈጠርለት ካልተመቻቸ ትግራይ ትግርኚ ሲመሰረትስ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ኤርትራዊ ዕጣ ፈንታው ምን ይሆን? ወይስ ትግርኛ ተናጋሪዎቹ ብቻ ከታረቁ የተቀረው በትግርኛ ተነጋሪ ክፍሎች የሚወሰንለት ዕቅርቀ ሰላም ዕድል መቸም ቢሆን በሊሂቅ ማሕበረሰብነቱ/ ኤሊትነቱ ወሳኝ ስለሆነ ወሳኝነቱ ለትግርኛ ተናጋሪው ክፍል ነው ማለት ነው?
ይህ ንቀት ብቻ ሳይሆን፤ለትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነትም ኤርትራ ውስጥና ትግራይ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ጎሳዎች አደገኛ ፤ጠንቀኛ እና ከፋፋይ የፖለቲካ ተልዕኮ እንዳለው በምንም ሁኔታ አልጠራጠርም። ባለፈው ወር ትግራይ ውስጥ እና በሌሎቹ የኢትዮጵያ ከተሞች የተደረጉ ስብሰባዎች የጎሳ ፖለቲካ ኤርትራ ውስጥ በነበረውና አሁንም በቆላ እና በከበሳ በአውራጃዊነትና እና በሃይማኖት ልዩነት እየሰፋ ያለው ቁስል እንደገና ለማስፋት ኤርትራ ውስጥ እስከ መገንጠል የሚል የጎሳ ፖለቲካ ታቅፎ ብቅ ማለቱ በተጨባጭ የዚህ በር ከፋችነትና ወያኔዎች ሆን ብለው እየቀየሱት ያለው የጎሰ ፖለቲካ አደገኛ ምልክት ይዞ ብቅ እንዳለ ከስበሰባዎቹ የተሰጡ የድርጅቶቹ መግለጫዎች መረዳት ይቻላል። ይህ አዲስ ድርጅት ደግሞ “በቤተሰብነት/በቋንቋ/በስጋ ዝምድና እና ባምቻ ጋብቻ”ሰላማዊ እና ውንድማዊ ግንኙነት ለመመስረት እስከ ተባበሩት መንግሥታት የሚሄድ ዕቅድ ምን ማለት እንደሆነ ለወደፊቱ የምናየው ክስተት ሲሆን፤ ድርጅቱ ከዚህ ሂስ ተምሮ ራሱን ካላስተካከለ የጎሳ ፖለቲካዊ ተልዕኮው ወደ 1940ዎቹ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ሕዝብን በጎሳ የሚሸነሽን ፖለቲካ በስፋት እድሜው እንዲራዘም የተደረገ የጎሰኞች/የፋሺስቶች አዲስ ሴራ ነው የሚል አምነት አለኝ።
ባለፉት የጦርነት ታሪኮች ትግርኛ ተናጋሪው ብቻ ተዋግቶ ደም የተቃባ እና የመበዳደሉ ሁኔታ ጥላቸው ቅሬታው በሁለቱ ወንድማማቾች ብቻ ነው ብሎ የተወሰነ ቋንቋ ተናጋሪ ለማገናኘት መጣር ከፖለቲካዊ ተልዕኮ ሌላ መልዕክት የለውም። እኔኑ በጣም ያስገረመኝ “የማሕበሩ አባላት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ትግርኛ ተናጋሪ ትግሬዎችና ኤርትራ ውስጥ የሚገኙ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራዊያኖች ናቸው። ምክንያቱም ይልና “በሁለት የተለያዩ ሉአላዊ አገሮች ተለያይተው ይኑሩ እንጂ ከጥንት ጀምሮ አያቶቹ ያቆዩለትን ቤተሰባዊ ሕግ እና ግንኙነት በጋብቻ ቃል ኪዳን በአጥንት ሰጋ ዝምድና እና በባሕል አንድ ስለሆኑ ናቸው። ከእንግዲህ ወዲህ ጥላቻ ጠፍቶ ሰላምና ፍቕር በመሃላቸው የሚሰፍንበት፤ይቅር፤ይቅር ለእግዚአብሔር ተባብለው የሚሳሳሙበት፤ካሁን ወዲህ እንዳለፈው ሳይፈልጉት ያለፈቃዳቸው እንዳይጎዳዱ ፤ወንዳማዊ ዝምድናቸው እንዳይራከስ መሰረት የሚጥሉበት ማሕበር ነው። የትግርኛ ተናጋሪው ብሔር ነባራዊ እንዲሆንና የፍቅር አርአያ እንዲሆን በሁለቱ ማሕበረሰቦች ሰላም እንዲሰፍን ፍቅሩም ከትውልድ ትውልድ ነባራዊ ሆኖ እንዲተላለፍ መሰረት መጣል ዋነኛው የማሕበሩ ዓላማ ነው።” ይልና - ቀጥሎም በአንቀጽ 9 ላይ ስለ ማሕበሩ ጽ/ቤት ምቹ ከተማ/ቦታ እስኪያገኝ ድረስ ዋና ጊዜያዊ መንቀሳቀሻ ጽሕፈት ኣዲስ ኣበባ፤ ሽረ እና መቐለ/መቀሌ ይሆናል፡፡እኒህ ቦታዎች የተመረጡበት ምክንያት ሲገልጽ “ሽረ/ሽሬና መቐለ/መቀሌ ለትግርኛ ተናጋሪዎቹ ሁኔታዎችን በቅርብ ለመከታተል ቅርብና አመች ስለሆኑ፤በተጨማሪም በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ንብረቶች ለመጠገን የተፈናቀሉ ቤተሰቦች ተከታትሎ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲያገኝ ለማድረግ እንዲመቸው የተመረጡ ናቸው። ኣዲስ ኣበባ ጽሕፈት እንዲኖረው የሆነበት ምክንያትም ከውጭው ዓለም ጋር ግንኙነት ለማድረግ እንዲያመችና ግንኙነትና የድጋፍ በር የሚያገኝበት መሰረት ለመፍጠር ሲሆን ሁኔታው ሲፈቅድም ኤርትራ ውስጥም አስመራ፤በረንቱ፤ዓሰብ ውስጥ ጽ/ቡቶች ለመክፈት ምኞት

(ቃል ኪዳን ይገባል)
አለው።ይላል።
ከላይ ባጭሩ የተረጎምኩላችሁ አንዳንድ የማሕበሩ አባባሎች በክፍል ሁለት በሰፊው “ስለ ትግራይ ትግርኚ መሰረተ ድንጋይ የመጣል አዝማሚያ” መሆኑ በሰፊው ስለማብራራው ማሕበሩ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጎጠኛ ማሕበር መሆኑ የሚያመለክተው ትግርኛው ተናጋሪው ክፍል በተለያዩ ወቅቶች እርስ በርሱ የሚናናቅና የሚጋደል የተጋደለና የተዋሃደ አብሮ የኖረ አንዴ ሲዋጋ አንዴ ሲዋደድ የኖረ መሆኑ ቢታወቅም፤ ያገሪቱ ርዕሰ ከተማ አዲስ አባባ በወያኔ ቁጥጥር ስለሆነች አስፈላጊው ለማሕበሩ የሚያስፈልገው የውጭ ዲፕሎማሲያዊና ቁሳዊ ድጋፍ ለማግኘት ያመቸው ዘንድ ያለ ምንም ቀረጥና በውጭ ዕርዳታ ስም ሌላ የመበዝበዣና የመዝረፍያ ቦይ እንዲሆነው ዕቅድ ማውጣቱ ሲሆን፤ እጅግ የሚያሳዘነው ግን ባድሜ፤ዓሰብ፤ዛላምበሳ እና በደርግ ሰርም ሆነው በወታደራዊ ግዳጅ ተሰልፈው ሕይወታቸው ያጡ፤ጧሪ ያጡ፤ዜጎች ግን አስታዋሽ የሌላቸው መቅረታቸው ያሳዝናል። ይህ ማሕበር በዚህ ጠባብ ጎጠኛ ባሕሪው ሳይወሰን ይግረማችሁ ብሎ ለሁለቱ ትግርኛ ተናጋሪዎች አመቺ በሆነ ቦታ ከዓለም ግብረ ሰናይ ማሕበራት፤ከተባበሩት መንግሥታት፤ከደጋፊ አባላት…የሚገኝ ገንዘብ ሃወልትና ሆስፒታል እንዲቋቋም ዕቅድ ውስጥ አስገብቶታተል።

በዚህ አላቆመም፦ የማሕበሩ ሕገደምብና ዝርዝር ሁኔታ ሕጋዊነት በቅጂ ለተባበሩት መንግሥታት ያሳውቃል ይላል። የማሕበሩ ሕገደምብና ዝርዝር ሁኔታ ሕጋዊነት በቅጂ ለተባበሩት መንግሥታት ያሳውቃል ሲል ራስ ተሰማ በ1947 ዓ.ም አካባቢ የመሰረቱት በእንግሊዝ ቅየሳ የተደራጀ የሊበራል ፓርቲ መርሃ ግብር ለተባበሩት መንግሥታት ኮሚሽን ልኡካን ያሰሙት የትግራይ ትግርኞ መንግሥት ማመልከቻ ተግባራዊ ለማድረግ ይሆን? ማሕበሩስ የራሱ ወይንም የትግራይ ትግርኚ ዕቅድ ባንዴራስ ይኖረው ይሆን? ራስ ተሰማ አስበሮም በተባበሩት መንግሥታት ኮሚሽን ምን ብለው ነበር?

……..በአፄ ዮሐንስ ዘመን የባዕድ መንግሥት ከውጪ መጥቶ ከኢትዮጵያ ላይ ቆርሶ የወሰደው አገር የለም። ጣልያን ኤርትራን ቅኝ ግዛቱ ያደረገው፤ አጼ ዮሐንስ ከሞቱ በሗላ የኢትዮጵያን ሥልጣን የተረከቡት ንጉሥ ሚኒልክ በገንዘብ ስለሸጡት ነው።…እንደሚታወቀው የተሸጠ ዕቃ በማናቸውም መንገድ እንደማይመለስ ሁሉ፤ዛሬም የኢትዮጵያ መንግሥት ከሃምሳ ዓመት በፊት የሸጥኩት አገር ይመለስልኝ ማለት አይችልም፡… የኢትዮጵያ መንግሥት ኤርትራን በግዴታ ካልወሰድኩ ብሎ የሚታገል መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው።ይህ መንግሥት በትግራይ ወንድሞቻችን ላይ የመሰረተው የግፍ አስተዳደር በጣም የሚያሳዝን ስለሆነ፤ይህ አስከፊ ዕድል በኛም በኤርትራውያኖች ላይ እንዲደርስብን አንፈልግም።….የትግራይ ሕዝቦች አንድ ዓኢነት ዘርና አንድ ዓይነት ባሕል ያላቸው፤አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ ስለሆኑ፤ በአንድነት ተዋህደው ነፃ መንግሥት ለማቋቋምእንዲወስንላቸው
አጥብቀን እንፈልጋለን::
” ብለው ነበር።



ህ በዘመነ ወያነ ትግራይ ተንከባካቢነትና በአንዳንድ አድርባይ ጎጠኛ ኤርትራኖች “የሰላምና የወንድሞች የትግርኛ ተናጋሪ የቤተሰብ ማሕበር” በማለት የተመሰረተ አዲስ ቅኝት በእንግሊዝ ቅየሳ እና በራስ ተሰማ ግምባር ቀደም ጥረት ተወጥኖ የነበረው ውጥን ለመቀጠል ይሆን? ታላቋ ትግራይ የተባለው የፖለቲካ ስታረተጂ በመቅረጽ የትግራይ ኢትዮጵያዊነት ለሁለተኛ (ለሦስተኛ) ጊዜ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርግ ይሆን?
ወያነ ትግራይ በየትኛው ማህደሩ ማመን ይቻላል?
ታሪኩን በዝርዝር እንመልከት። ይቀጥላል….. ጌታቸው ረዳ - ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ www.ethiopiansemay.blogspot.com










Friday, September 3, 2010

አረጋሽ አዳነ፤ሐስን ሽፋ፤ቢተው በላይ “የዝጉልኝ ቤታቸው” ታሪካና እና የትግራይ ገበሬ “የማጎርያ ቤት” ወንጀላቸው

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 begin_of_the_skype_highlighting (408) 561 4836 end_of_the_skype_highlighting አረጋሽ አዳነ፤ሐስን ሽፋ፤ቢተው በላይ “የዝጉልኝ ቤታቸው” ታሪካና እና የትግራይ ገበሬ “የማጎርያ ቤት” ወንጀላቸው ከየወያኔ ገበና ማህደር (ጌታቸው ረዳ) Septemebere 6/2010 www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com

ለቅዱስ ዮሐንስ የማስነብባችሁ የወያኔ ገበና ማሕደር የሚከተለው ነው።ይህ ታሪክ የተገኘው ከጋህዲ ቁጥር 3 የትግርኛ መጽሐፍ ውስጥ ወያኔን ከመሠረቱት 11 ሰዎች አንዱ ከሆነው በአቶ አስገደ ገብረስላሴ ከጻፈው መጽሐፍ ነው። ታሪኩ የሚተነትነው ”ስታራተጂ መጥቃዕቲ” ተብሎ በሚታወቀው ወያነ ትግራይ በደርግ ሥርዓት ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ያወጣው ወሳኝ ወታደራዊ የጥቃት/የፍልሚያ (ዕቅድ) ለማጠናከር ሲባል ወያነ ትግራይ በትግራይ አርሶ አደር ሕይወት ላይ ያደረሰው አሳዛኝ ታሪክ ነው። ታሪኩ ረዢም በመሆኑ አሳጥሬ በማቅረብ ትግርኛ ለማታነቡ ዜጎች ሁኔታውን ባጭሩ እንድትረዱት ይረዳ ዘንድ አሳጥሬ በመተርጎም ለዛሬ የወያኔ ገበና ማህደር ዓምዳችን ወያኔዋ አረጋሽ አዳነ ዓረና ትግራይ ለፍትሕ ፤ለዲሞክራሲና ለሉኣላዊነት በሚል መጠርያ ድርጅት መስርታ ብቅ ስትል ፀረ መለስ ዜናዊ ነችና መለስን ታስወግድልናለች ብለው ብዙ የዋሃን ዜጎች ሲሰብኩን አንዳንድ ”አቃጣሪ/ደላላ” ጋዜጠኞችና ዌብሳይት ባለቤቶች ድንቅ ታጋይነቷንና ለፍትሕ ለሰብአዊነት ህይወቷ በሙሉ እንደቆመች አስመስለው ውሸትን ሲለቀልቁና ሊያስተዋውቁንና (ሲያቃጥሩ) እንደንደነበር ይታወሳል (አሁንም ይሰብኩናል)። ይግረም ብሎም ከወደ ካናዳ በኩል የሚደመጡ መለስ ዜናዊን እንቃወማለን ገብሩና አረጋሽ እናከብራለን/እንከተላለን የሚሉ እንዳንድ የፖለቲካ ኩታራዎች፡ ሥልጣን ውስጥ በነበረችበትና በረሃም እያለች ስትፈጽማቸው የነበረው የሥልጣን ብልግናዋን ስናጋልጥ በየዜናው ማሰራጫ የምትዋሸንን ስብዕናዋን ለማጋለጥ የምናደርገው ጥረት እየተከላከሉ እና እያሾፉብን ”ሳትጠራቸው አቤት ሳትላከቸው ወዴት” የሚሉላት ቡችሎቿ መለስ ዜናዊን የምትጥልልን ታጋይ ነፃ አውጪያችን ነችና (ለድርጅቷ ለዓረና ትግራይ) ዕርዳታ ገንዘብ እናዋጣላት እያሉ ታሪክ ምን ይለናል ሳይሉ ቡቹላነታቸው ለማስመዝገብ በገንዘብና በሞራል ፍቅራቸውን እንደገለጹላት ውጭ አገር የተመሠረቱት የተቃዋሚዎች ዌብሳይት የምታነቡ ሁሉ የታሪክ ምስክሮች ናችሁ። ጉዷን የሚያውቁ የዓይን ምስክሮች ግን የፍትሕ ረጋጭ እና በስልጣን የባለገች በከርሰ መቃብር ውስጥ ሆነው የፍትሕ ያለህ እያሉ በእርሷ ምክንያት ሕይወታቸው ያጡ፤የተፈናቀሉ፤ንብረታቸው ተበትኖ የትም የቀረ፤ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ በጠቅላላ ለፈፀመቺው ወንጀልና ዲክታተርያላዊ ጸባይዋ/ትዕቢቷ በሠራቺው ግፍ ሳትቆጭ የተገላቢጦሽ ዛሬም ስትኩራራ አድምጠናል።

የመለስ ዜናዊ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የትግራይን ገበሬ/ኗሪ ስቃይ ከእሚንት የማይቆጥሩት “ሳትጠራቸው አቤት -ሳትልካቸው ወዴት” የሚሏት አዳዲስ ጀሌዎችዋ በግፍ የቆረፈደው የታሪክ ዕድፏን አጥበው ውድነቷን እያብራሩ ወደ ፖለቲካው ገበያ ሊሸጡልን ቢሞክሩም፤ “የዘንድሮ” ደላላ “ጋዜጠኞችም” ከመለስ ዜናዊ በምን ትሸልያለሽ ሲሏት “Because people know what I have been through, what I have given up for the truth. They know that power had not corrupted me. (Welcome to Ethiopia's election 2010: The case of Adwa By Eskinder Nega April 2, 2010) ብትለንም ”የምሯ፤ከልቧ ነው የምትናገረው” እያሉ ወደ ኮከብነት /ወደ ጣይቱነት በመለወጥ ለውሸቷ ሽፋን የሚሰጧት አለቅላቂ ጋዜጠኞችም የለበሰቺውን የታሪክ እድፍ ሲያደንቁላት አይተናል። እነ አረጋሽ እነ ስየ እነ ገብሩ እነ ተወልደ እነ ዓለምሰገድ እነ ቢተው እነ አውዓሎም… በየዱሩ በየጉድጓዱ ውስጥ ጥለውት የመጡት የገበሬው፤የከተማው፤የምሁሩ ኗሪ ሕይወት ፍትሕ በማጣት ወደኛ ጮኾ ስሞታውን ስንመዘግበለት ውጭ አገር የሚገኙት አንዳንድ የተቃዋሚ ሚዲያዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች ለሙታኖች በመቆምችን ለምን ይጠሉናል? ምናቸው ስለሚነካቸው ነው የሙታንና የተገፉ ዜጎች ስሞታ ስንመዘግብ እየጎረበጣቸው የሚገኘው? እውን አረጋሽ አዳነ “they (voters) know that power had never corrupted me” “ስልጣን አላበላሸኝም” ስትል እውነት ከልቧ ነው እያሉ የታሪክ እድፏን የሚጠራርጉላት ደላላ ጋዜጠኞች አስገደ ገብረስላሴ እያጋለጠው ያለው የነ አረጋሽ እና የወያነ ትግራይ መሪዎች ምስጢር ከማጋለጥ ለምን ወደ ሗላ አሉ? የአስገደ ገብረስላሴ፤የገብረመድህን አርአያን ፈለግ አንከተልም ብለው ያደፈጡ የተደበቁ ሚስጢሮች እንዳይጋለጡ የሚጥሩ ወንጀለኞችና ተባባሪዎቻቸው ለጊዜው ከቅጣት ቢያመልጡም ከታሪክ ተጠያቂነት ግን አያመልጡም። አስገደን ከልብ አመሰግናለሁ። ወደ አስገደ ሰነድ ከመግባቴ በፊት ከዚህ በታች የሚቀርበው ሰነድ ”ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ” የሚል በተከታታይ ስለምታገኙ ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ምን እንደሆነ ልግለጽና በቀጥታ ወደ ሰነዱ እንገባለን። ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ለወሳኝ ምዕራፍ የሚያደርስ የመጨረሻ የውግያ ዝግጅት ነው። ”ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ” ተብሎ የሚታቀው የወያነ ትግራይ የጦርነት ዕቅድ ብዙ ሃላፊዎችን በየዘርፉ ያካተተ ሲሆን ሰዎቹ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ሃላፊነት ወስደዋል።ስንቅ፤ነዳጅ፤መጓጓዧ፤ትጥቅ፤ሕክምና የመሳሰሉት በተቀናጀ አሰራር እንዲቀነባበር የተደረገ ጥናት ነው። በዚህ ዘመቻ ወሳኝ ሆኖ የተገኘው ደግሞ የተዋጊው ሃይል ቁጥር በብዛት መኖር ወሳኝነት ስለነበረው፤በወቅቱ ወያነ ትግራይ የሻዕቢያ ባርያ ስለነበረ ጌታውን ሻዕቢያን ከኢትዮጵያ ሠራዊት ለማዳን ሲል በብዙ ሺሕ ትግራይ ታጋዮች ወደ ኤርትራ በመላክ እንዲያልቁ በማድረጉ፤ ”ስተራተጂካዊ መጥቃዕቲ” ስለተባለው ዝግጅት ከመደረጉ በፊት ከቀረው እጅግ አድካሚ እና ወሳኝ ፍልሚያ ሲነፃፀር በሰው ሃይል እጅግ ቀንሶ እና ተመናምኖ ነበር። ለዚህ አንድ ሁለት ምክንያቶች ነበሩት። አንዱ ቀደም ብየ እንደገለጽኩት ወደ ኤርተራ እንዲሄድ ተደርጎ በሺዎች ተሰውተዋል።ሌላው ታጋዮቹ ከደርግ ሰራዊት ይዘት ትግራይን ነፃ እንዳወጡ ወዲያውኑ እንዲተገብረው የተማረው ጠባብነት በተግባር በማዋል ”ትግራይን ነፃ አውጥተናል፤ አማራው ነፃ ለመውጣት ከፈለገ እራሱ ነፃ ያውጣ፤ እኛ ላማራዎች ስንል የምንሰዋበት ምክንያት የለንም፤ ስለዚህ ከአለውሃ ምላሽ ወዲያ እንዲሁም ከደብረታቦር ወዲያ አናልፍም በማለት ከነ ትጥቃቸው ምሽጋቸውን እየለቀቁ ወደየ መንደራቸው ስለሄዱ የወያኔ ታጋይ በቁጥር የተመናመነ ስለነበር የግድ እሱን ለመተካት ሲል የትግራይ ገበሬ ወጣት በግድ ወደ ማስልጠኛ ጣቢያ በመትመም ወታደራዊ ስልጠና ተገድዶ እንዲወስድ ተደርጓል። ከየመንደሩ በገፍ እየታፈሰ ሲሄድ እምቢ ያለ ደግሞ ከዚህ በታች ያለውን ድርጊት ተፈጽሞበታል። ባንድ ወቅት በግድ እየተገፋ አፅቢ በተባለው ማሰልጠኛ ውስጥ 79 ሺህ አዲስ ምልምል ታጋዮች እንደነበር አስገደ ይገልፃል።ይኸ አሃዝ እንድ ቦታ የነበረ እንጂ በየገጠሩ ማስለጠኛ የያዘዘቸው ብዛቶች በርካታ ናቸው።ከዚህ ቀጥሎ የምታነቡት አስገደ የዘገበው ታሪክ አምቢ አልታገልም ያለ ሰው በአሳዛኝ ሁኔታ የትግራይ ገበሬ እና የከተማ ኗሪ ሕዝብ በወያነ ክፍሊ ሕዝቢ (ካድሬዎች/የህዝብ ግንኙነት ሓለፊዎች) እየተጎተተ ወደ ማጎርያ (ኮንሰንትረሺን ካምፕ) እስርቤቶቸ ተወስዶ የደረሰበት ስቃይ ትመለከታላችሁ። ወደ ታሪኩ ልውሰዳችሁ። አስፈገደ ገ/ሥላሴ እንዲህ ይላል። ”የአዲስ ምልምሎች ሥልጠና ጉዳይ በበላይነት የሚመሩ ከማዕከላዊ የደጀን አስተዳደር ክፍል የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባላት ስምዝርዝር የሚከተሉት ናቸው። 1 ገብሩ አስራት 2 አረጋሽ አዳነ 3 ተወልደ ወልደማርያም 4 ቢተው በላይ የምልመላው የህዝብ ግንኙነት (ክፍሊ ሕዝቢ 08)ሃላፊው ተወልደ ወልደማርያም ሲሆን ከተወልደ ሥር በትግራይ ውስጥ በየአውራጃው ለምሳሌ በወልቃይት፤ፀገደ፤አርማጭሆ፤ፀለምቲ፤ላሬ፤በየዳ፤ጃን አሞራ፤በለሳ ሰቆጣ፤ወሎ ሰሜን ሸዋ 500 የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነበሩ። በስትራተጂካዊ የማጥቃት ዘመቻ ዕቅድ ለማሳካት አዲስ ሰልጣኝ ለማብዛት ሁለቱም ማለትም የሕዝብ ግንኙነትና የደጀን አስተዳደር ክፍል ከፍተኛ ሓለፊነት ተጥሎባታፀቸዋል። ምክንያቱም ተመልማይ ብብዛትና በወቅቱ ሰልጥነው ወደ ጦር ግምባሩ ካልዘመቱ ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ሚባለው ወሳኝ ፍልሚያ ግቡ አይመታም። የታሰበው ግብ ካልመታ ”ሙሽራ ሳይዙ ሚዜ ፍለጋ ዓይነት” እንዳይሆንበት በማሰብ ካሁን በፊት በግድም ሆነ በውዴታ ልጆቹን ወደ ጦር ሜዳ አስልኮ አታግሎ የነበረ ወላጅ ወይንም ቤተሰብ ልጆቻቸውን ወደ ታጋይ ምልመላ ያልላኩ ቤተሰቦች/ጎረቤቶች ካሉ ልጆቻቸው እንዲያታግሉ ”ዛሬ ያልከተተ በቁሙ የበከተ” የሚል መፈክር እንዲያሰሙዋቸው በመገፋፋት በሁለቱም ላይ ቅራኔ እንዲፈጠር አድርገው ለጆቻቸው ያልላኩ ሰዎች በግድ እንዲሄዱ በመጫን በርካታ ምልምሎች ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ጎረፉ። በተለይም በ1981 ዓ.ም ደርግ የለቀቃቸው በሗላ ነፃ የወጡ ቦታዎች ያልተነካ ወጣት ስለነበር መጀመርያው ዙር ላይ 30,000 ወጣት በግድ ተመልምሎ ሰልጥኖ ታጋይ ሆነ። ያ በ1982 ዓ.ም በጠባብነት ስሜት (ፀረ ኢትዮጵያዊነት /ፀረ አማራነት) የተማረውን ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ምሽጉን እየጣለ ወደ የቤቱ የሄደው ታጋይ ከነ ብረቱ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ መመለስ ጀመረ። የመጀመርያው ዙር በእንዲህ ቢከናወንም የተጠበቀው ቁጥር ከተገመተው በታች ስለሆነ እና የመታገል ስሜት ስለቀዘቀዘ ሰሜቱን ለማነሳሳት የኪነት ቡድኖች እነ እያሱ በርሐ እና እነ ገብረመድህን ስቡሕ (ጠርጣራው) ወደየ ገጠሩ ወደየ አውራጃው ተሠማሩ። የኪነት ትርዒት ባሳዩ ቁጥር ባንድ መድረክ ውስጥ ወደ 300 ሰዎች ለትግል ዝግጁነታቸው ይገልፁ ነበር። ያም ሆኖ አሁንም የተፈለገው ሃይል ማግኘት አልተቻለም። በቂ የታጋይ ቁጥር ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተላለፈ። ወደ ትግል ለመሄድ ዝግጁነቱ ያላሳየ ሁሉ በታጋዮችና በሚሊሺያ ወያኔዎች እየተጎተተ ወደ ማሰልጠኛ ጣቢያ እንዲወሰድ። አልታገልም ብሎ አሻፈረኝ ያለ ወጣት ደግሞ ሚሰቱ፤ወላጆቹ፤እህት ወንድም ዘመድ አዝማድ እየተገደዱ እስር ቤት እንዲገቡ፤ንበረታቸው፤በግ፤ፍየል ላም በሬ ደሮ እንሰሳት በሙሉ ተወርሰው ለድርጅቱ ገቢና ጥቅማጥቅም ይውላል። በነፃ በወጡት ገጠሮችም ሆነ ከተማዎች እምቢ እያሉ የሚያንገራግሩ፤የሚያውኩ፤የሚሰብኩ በማንቁርታቸው እያታነቁ ወደ 06 እስር ቤት ተወርውረው እንዲቀጡ። ቅጣቱም ወደ አፅቢ ማሰልጠኛ ቦታ በመሄድ ሠልጣኙ የሚወስንላቸው የቅጣት ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ሙሉ ስልጣን ተሰጣቸው። የዚህ ምልመላ ቅጣት ውሳኔ አመንጪዎች፤ፈፃሚዎችና አስፈፃሚ አካላት ሥም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው። ተወልደ ወልደማርያም የሕዝብ ግንኙነት አስተዳደር ሐላፊና አደራጅ ገብሩ አስራት የትግራይ ደጀን አስተዳዳሪ አረጋሽ አዳነ ትግራይ ደጀን ምክትል አስተዳዳሪት ቢተው በላይ ሕዝብ ድርጅትና አስተዳደር (ምክትል) ሃለቃ ፀጋይ በርሀ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሐሰን ሽፋ ደጀን ትግራይ የፀጥታ ጉዳይ ሐላፊ ቁዱሳን ነጋ የምዕራብ ትግራይ የሕዝብ ጉዳይ ሐላፊ ትርፉ ኪዳነ የትገራይ ማዕከላዊ አስተዳደር የሕዝብ ክፍል አደራጅ ሓላፊት አብርሃ ማንጁስ የድርጅት ጉዳይ ፀሐፊ ዘርአይ አስገዶም መቀሌ የሕዝብ ጉዳይ ሐላፊ ዓለምሰገድ ውረታ ውቅሮ የህዝብ ጉዳይ ሃላፊ እና የውቅሮ አስተዳዳሪ ምሩፅ የዛላምበሳ እና አካባቢዋ ሕዝብ ጉዳይ ሓላፊ ሃረያ ስባጋድስ ዓድዋ የሕዝብ ጉዳይ ሓለፊት (ልጅቷ በህይወት የለችም፡ የተወልደ ወ/ማ ባለቤት የነበረች ነች (ከተርጓሚው) አቶ ሙሉ ሰንደቕ የህዝብ ጉዳይ ሸዊት ገብረክርስቶስ የሕዝብ ጉዳይ ዓባዲ ወልዱ የሕዝብ ጉዳይ ካሕሳይ ቆራይ የእስርቤቶች (06) ጉዳይ ሓላፊ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ የሕዝብ ጉዳይ ሓላፊዎችና ካድሬዎች ሲካሄድ በነበረው የሕዝብ ዓፈና ተጠያቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ዓፈናውን በግምባር ቀደምትንት ፈፃሚዎችና አስፈፃሚዎች የነበሩ ናቸው። ለዛ ዓፋኝ እና አስገዳጅ የምልመላ መርሃ ግብርና ዓፈናውንም ግብር ላይ መዋሉን የሚከታተል ፖሊት ቢሮ ማአከላዊ አባላት ሲሆን በተለይም ደግሞ የማአከላዊው አመራር ኣባል (ሰንትራል ኮማንድ)በቀጥታ ምልመላውን በምን ሁኔታ መካሄድ እንዳለበት ይቆጣጠረው ነበር። ከላይ ተጠቀሱት ሰዎች ምድብ ሥራቸው ተሰማርተው ዓፈናውን ማጧጧፍ ከጀመሩ በሗላ በጣም በርካታ የከተማና የገጠር ወጣቶች ካአፈናው ለማምለጥ ሲሉ ወደ ሱዳን (ጂዛን) እና ወደ ደርግ መሸሽ ጀመሩ። በተላለፈው መመርያ መሠረት ከዚያ በሗላ የሸሹትን ወጣቶች ቤተሰቦች ንብረታቸው እየተቀሙ/እየተወረሰ ሚሰት፤ባለቤት፤አባት፤እናት፤ወንድም፤አጎት....ሁሉ እየተለቀሙ ፅዳት በጎደላቸው፤ምግብ በሌለበት፤ሕክምና በሌለበት ትናንሽ እስር ቤቶች እና የእስረኛ ማጎርያ ስፍራዎች ታጉረው እንዲሰቃዩ በመደረጉ ለታይፎይድና ልዩ ልዩ ለተላላፊ በሽታዎች እና ለተቅማጥ በሽታ ተጋለጡ። ከገጠር የተወረሰ የቤተሰብ እህልም ወደ ከተማ እየተጫነ የአሳሪዎቻቸው ባለሥልጣኖች መሽሞንሞንያ ሆነ። ክፍሊ ህዝቢ (የሕዝብ ጉዳይ) የሚሉዋቸው እነዚህ ክፍሎች ባለ ሙሉ ሥልጣን ሆነው ያለ ተቆጣጣሪ ሕዝቡን አበሻቀጡት። 17 ዓመት ሸሽጎ፤ አዝሎ ወደ ሰሜን ሸዋ ያሸጋገረን እሽርሩ ብሎ ተንከባክቦ ያሳደገን ሕዝብ ካሳው/ወረታው ዓፈና ሆነ! አሳዛኝ! በአስገዳጅ እየታፈነ ወደ ህወሓት ትግል እንዲገባ የተደረገው ይህ አሳዛኝ ድርጊትና ግፍ ለማስረጃ እንድትሆናችሁ እኔ የማውቀው በዓይኔ ያየሁዋት አንዲት ማስረጃ በማቅረብ ልመስክር። ሐቁን ገልጬ ለናንተው ለፍረድ ልተወው። በወቅቱ ምድብ የሥራ ቦታየ ሽሬ ውስጥ ነበር። አዲስ መመርያ ስለሚተላለፍ ወደ ሃገረሰላምና (ተምቤን) ባስቸኳይ እንድትመጣ ተብየ ትዛዝ ተላልፎልኝ በመመርያው መሠረት ከሽሬ ተንቀሳቅሼ መንገድ ስጀምር መውጫ በር ላይ በሺሕ የሚቆጠሩ ፍየሎች፤ በጎች፤ላሞች፤በቅሎና ደሮዎች በወያኔ ታጋዮችና ሚሊሽያዎች እየተገሩ ወደ ከተማው ሲገቡ አገኘሗቸው። ግራዝማች በላይ ሃይሉ የተባሉ አንድ አዛውንት አባት ከከብቶቹ ሗላ ሗላ በአዝግሞት ሩጫ እየተከተሉ ንብረቴ ዘረፉኝ እያሉ እየጮኹ ሰማሗቸው። እንዴ! ምን ጉድ ነው ብየ፤ ምን የሆኑ አባት ናቸው? ብየ ታጋዮቹን ስጠይቅ ”አይ ተዋቸው ሕሊናቸው ተቃውሶባቸው ነው” አሉኝ። አብረውኝ ከኔው ጋር በመኪና ሲጓዙ የነበሩ 8 ታጋዮች ነበሩኝ። መኪናዋን አስቁመን ”አቦ! (አባባ) ምንድነው ችግሩ? ብለን ጠየቅናቸው። ”ንብረቴ ተወረርኩኝ! ወያኔ ፀባይዋ ቀይራለች! አዲስ ጠባይ አምጥታለች!” አሉን። እኚህ አባት ታጋይ ዘነበ በላይ የሚባል ልጃቸው በ1968 ዓ.ም ተጋይ ሆኖ እስከ የሃይል መሪነት እና አዋጊ ሆኖ ውጊያ ላይ ተሰውቷል።ሌሎች ሁለት ልጆቻቸውም እንደዚሁ ታጋዮች ሆነው በክብር ተሰውተዋባቸዋል። ይህ ሁሉ አስተዋፅኦ አድርገው ልጆቻቸውን ያጡ አዛውንት አባት መሆናቸውን እየታወቀ አንድ የቀራቸው ልጃቸውን ታገል ተብሎ አልታገልም ብሎ ስለተሰወረ፡ የኚህ አባት ንብረት የሆነ 30 ፍየሎች 42 ከብቶች አንድ በቅሎ6 አህዮች 10 ኩንታል እህል ወረሷቸው። እኛም ታሪካቸውን ሰምተን በማዘናችን የሳቸውና የሌሎች ሰዎች ፍየሎችና ከብቶች በጎች ቀላቅለው ሲነዷቸው የነበሩ እነኛ 3 ታጋዮችና 10 የሚሆኑ ጀሌዎች (ሚሊሽያዎች) ጠርተን የሚመለከታቸው ክፍሎች እስክናነጋገር ድረስ እየነዳችሗቸው ያሉትን እንሰሳት በሙሉ ካመጣችሗቸው መልሳችሁ ውሰዷቸው፡ ብለን አዘዝናቸው። ትዛዙን ላለመቀበል ብያጉረመሩሙም ሳይወዱ መለሷቸው። ጉዟችንን ቀጠልን። በለስ ከተባለች ትንሽ ከተማ ደረስን። በዛች ትንሽ ከተማ ውስጥ ከላይ ቆራሮ እና ከታች ቆራሮ የተለቀሙ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች ህፃናት ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ልጆቻችሁ/ቤተሰቦቻችሁ ከተሸሸጉበት ቦታ አምጧቸው ተብለው መጠለያ በሌለው አውላላ ሜዳ ላይ ልክ እንደ አውጫጭ በጥበቃ ተከብበው ታጉረው ታስረው አየን። ራቅ ብለህ በሺ የሚቆጠሩ የታሳሪዎቹ ንብረት የሆኑ ላሞች፤ከብቶች የቤት እንሳሰት ጠባቂ አልባ ሆነው የሌባ ቀለብና እና የጅብ እራት ሆነው ለአደጋ ተጋልጠው ይቀራመቷቸዋል።ያ አልበቃ ብሎ በሌሎች ቦታዎችም በሰለኽለኻ በኩል ስናልፍ የታዘብናቸውም ቢሆን በለስ ውስጥ ካየነው የባሰ በየጠባብ ማጎርያ እስር ቤት ክፍል ውስጥ በብዛት ታጭቀው፤ምግብ ውሃ ተከልክለው፤ንፅህና በጎደላቸው ክፍሎቸ ታጉረው በቅማል በላብ በእድፍ ምክንያት በታይፎይድ (በተላላፊ በሽታ በአር ኤፍ) በወባ በሽታና በተቅማጥ እየተሰቃዩ ጠረኑ ለህዋሳት የሚዘገንን ሽታው የማያስጠጋ ማጎርያ እስር ቤት ታጉረው አየን። ይህን ስመለከት በስልጣኔ እንድፈታቸው ፈልጌ ነበር፡የሰለኽለኻ ሕዝብም እርምጃው በጣም ስለተቃወመው እንዲፈቱ ግፊት ያደርግ ስለነበር ድርጊቱ በውስጤ እጅግ አስቆጣኝ። ይሕ ግፍ የተመከተ ሰብአዊነት የተላበሰ ሰውም ምን እንደሚሰማው የታወቀ ነው። እኔም የተወለድኩባት መንደሬ በመሆኗ ለመንደሩ ተቆርቁሮ ነው ፤አድልዎ በማድረግ ነው የፈታቸው እንዳልባል ”ነብሴ ላዘሬ ብለሽ ታገሺ” ብየ ውስጤ እሳት እየነደደበት ወደ ውቅሮ ማራይ (አክሱም አጠገብ) ተጓዝን። ውቅሮ ማራይም በሺ የሚቆጠሩ እንሰሳት እና ሰዎች የታሰሩ ገጠመኝ። አክሱም ከተማም አንደዚሁ በሺዎቹ የሚቆጠሩ እስረኞች አንዳሉ ተገነዘብኩ። ዓድዋ/ዓዲ አቡን እንደደረስንም ባካባቢውና ከተማው ውስጥ የነበረው የእህል ማከማቻ ጎተራ በሺዎቹ የሚገመቱ እስረኞች ታጉረውበት እንዳሉ ካገኘናቸው ገበሬዎችና ታጋዮች በኩል እንዲህ ያለ አሳዛኝ የእስራት አስገዳጅ ዘመቻ በመላ ትግራይ ውስጥ በሰፊው እየተጧጧፍን እንደሆነ እና በተለይም አልታገልም ወይም ልጄ የት እንደሸሸ/ሸሸች አላውቅም ያለ ሁሉ ንብረቱ እየተቀማ እየተጎተተ ፍዳውን አየ። ኩፍኛ የተጧጧፉባቸው ማጎርያ እስር ቤቶች የተባሉት በዓድዋ፤አክሱምና ሽሬና ተምቤን ውስጥ የከፋ እንደሆነ ነገሩን። ጉዟችን ወደ ሃገርሰላም ነው። ያ ከሽሬ ጀምሮ አክሱም እስከ ዓድዋ ድረስ ያየነውና የሰማነው በሕዝብ ላይ የደረሰው ግፍ ጉዟችን የከፋና በሃሳብ እንድንዋጥ አድርጎት ነበር። ጉዟችን ወደ ሀገረሰላም ከማቅናታችን በፊት የተመለከትነው አሳዛኝ ድርጊት ዓድዋ ውስጥ ለነበሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለሥልጣኖች ስለ ሁኔታው አሳሳቢነት መንገር እንዳለብኝ ወሰንኩ። ስለሆነም ሁኔታውን ለመንገር የማአከላዊ ኮሚቴ አባላት ወደ ሆኑት ወደ አረጋሽ አዳነ፤ቢተው በላይ፤ሓሰን ሽፋ፤ አብርሃ ማንጁስ፤ካሕሳይ ቆራይ ወደ ሚተኙበት ቤት አመራን። እነኚህ የደጀን መሪዎች ቤት ዘግተው በኮንትሮባንድ የመጣ መጠጥና ከውጭ አገር የመጣ የቆርቆሮ ቢራ እየተጎነጩ በውጭ አገር ቪዲዮ ካሴቶች እየተዝናኑ ሲመለከቱ ደረስንባቸው። መጀመርያ በሩን ስናንኳኳ እኛ መሆናችንን ካወቁ በሗላ ግቡ፤አረፍ በሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ቤት ለእንግዳ ከማለት እና እንደታጋይ ጓዶቻቸው ከማስተናገድ ይልቅ ”ጉዳቸውን” እንዳናይባቸው በማለት በሩን ከፍተው ሐሰን ሽፋና ቢተው በላይ ወደ ደጅ በመውጣት እንደማንም ሰው ከደጅ አነጋግረው ሊመልሱን ዳዳቸው። ዘግናኙ ሁኔታ በዝርዝር ነገርናቸው። በማይገባ ውሳኔ ወላጆቻችን ፤ሕዝባችን በቁር በበሽታ በረሃብ በሙቀት በጠባብ ክፍል ታጉሮ ለተላላፊ በሽታ ለስቃይ ተዳርጎ ንብረቱና ከብቱ በድርጅታችን እየተወረሰ ታስረው ተሰቃይተው እየሞቱ፤ እህሉ ከብት፤በግ ፍየሉ ንብረቱ ሁሉ ወርሳችሁ ለስቃይ ዳርጋችሁት በወረሳችሀት ገንዘብ በመፈንጨት ትጠጣላችሁ ትበላላችሁ። ጭራሽኑ ይህ የተበደለ ሕዝብ ልጅ ከወላጁ ተሰብስቦ አንድ ቀን ይበላችሗል፡ጭራሽኑ ለምናካሂደው ትግል እንቅፋት ነው። እያልን ስንነግራቸው፤ ሓሰን ሽፋ በማሾፍ ገጽታ ተመለከተን፡ ቢተው በላይም ”ተደፈርን” ብሎ ተቆጣ። ቆየት ብላ አረጋሽ አዳነ መጣች። እየነገርናቸው ያለውን ጉዳይ አዳመጠች። ብዙ ከተጨቃጨቅን በሗላ ወደ ነበሩበት ክፍላቸው ተመልሰው በመግባት ስብሰባ ካደረጉ በሗላ ”ሁሉም ይፈቱ ነገር ግን 150 ብር እየተቀጡ ይውጡ” የሚል ውሳኔ አሳለፉ። አሁንም ጭቅጭቅ ገባን። ገንዘብ እየከፈሉ ይፈቱ አሉ እንጂ መቸ መፈታት እንዳለባቸው ላቀረብነው ጥያቄ አልመለሱትም። መጨረሻ አክርረን ስናጠብቅባቸው እስረኛ በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ እንዲፈታ፤ የታመሙትንም ሕክምና እንዲያገኙ ሓኪሞች እንዲሰማሩ እናደርጋለን አሉ። እኛም ከምድብ ቦታችን ተነስተን ለአስቸኳይ ስብሰባ ለመሄድ አስበነው የነበረውን ጉዞ ሠርዘን ወደ ሗላ በመመለስ ያስተላለፋችሁትን ማዘዣ መልዕክት ይዘን እንድንመለስ የመፍቻ ወረቀት ትእዛዝ ስጡን አልናቸው። እነሱም በስምምነታችን መሠረት ወረቀት ሰጥተውን የወደፊት ጉዟችን ሰርዘን ወደ ሗላ በመመለስ በሌሊት ገስግሰን ወደ አክሱም፤ሰለኽለኻ፤ሽሬ አድያቦ ወረዳዎች ውስጥ ላሉ እስር ቤቶች እንዲዳረሱ አደረግን። እኛ ባሰማነው ተቃዉሞ በመላይቱ ትግራይ ውስጥ ታጉሮ በግፍ ታስሮ ሲሰቃይ የነበረ በሺዎች የሚገመት እስረኛ እንዲፈቱ ተደረገ። የተወረሰው ንብረትም ሆነ ላም ከብት ፍየል በግ እንዲመለስለት ትዕዛዝ ይተላለፍ እንጂ ብዙ እንሰሳ እና ንብረት የክፍሊ ሕዝቢ (በየገጠሩና በየከተማው የተመደቡ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ሓላፊዎች) ሓላፊዎችና የወያኔ ሚሊሺያዎች ምግብ ሆነው የተቀሩትም ያለ እንክብካቤ በዘራፊና በአራዊት እየተበሉ የትም ቀርተዋል። እኛም ውሳኔውን እንዲፈፀም ካደረግን በሗላ ወደ መድረሺያችን ወደ ሃገረሰላም (ተምቤን) ጉዟችን በቀን ቀጠልን። ሃገረሰላምም በሰላም ገብተን ጉዳየችንን እንደፈፀምን ወደ ምድብ ቦታችን ከመመለሳችን በፊት ወዲያውኑ አከታትለን በሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ለተወልደ ወልደማርያም፤ለመለስ ዜናዊ፤ለዓባይ ፀሃየ፤ለስየ አብርሃ እና ለስብሐት ነጋ ነገርናቸው። በጣም አሳዛኝና አሳሳቢ ሁኔታ እንደሆነም በሰፊው አስረዳናቸው። እነሱም ወደ የሕዝብ ጉዳይ ክፍል ሓላፊዎችና የትግራይ ደጀን ሓላፊዎች በመጻፍ የታሰረው ሕዝብ እንዲፈታ ተጨማሪ ትእዛዝ በጽሑፍ ጽፈው ሰጡን። ቀደም ብየ እንደገለጽኩት ሰዎቹ በኛ አቤቱታ በማዘዣ እንዲፈቱ ይደረግ እንጂ የቤት ንብረታቸው ላምና ፈየል ደሮ እና በግ ተወርሰው አብዛኛው የትም ባክኖ ቀረቷል። ይህ በ1983 ዓ.ም ከሽሬ እስከ ዓድዋ ድረስ ባጋጣሚ ስጓዝ ድንገት ያየሁት በሕዝብ ላይ የደረሰ ግፍ እንጂ በሌሎች ወረዳ ጣቢያዎች ከተሞች ገጠሮች በሰው ልጆች ሲፈፀም የነበረ ኢሰብአዊ ግፍ ቢገለጥ ተጽፎም አያልቅ፤ ብዙ መጻሕፍቶችም በወጡት ነበር።በዚህ መጽሐፍ ላይ በጨረፍታ እንደማስረጃ የጠቀስኩት ባይኔ ያጋጠመኝ በሕብ በጅምላ በድርጅታችን የተፈጸመ ግፍ ለታሪክ ፃሐፍት መነሻ እንደሚሆናቸው በማሰብ ነው።” (አስገደ ገብረስላሴ -ጋህዲ ቁ 3 የትግርኛው ቅፅ 289-293) አንግዲህ ከላይ እንዳነበብነው የወያኔ ትግራይ የገበና ማሕደር መሠረት ድርጅቱ እጅግ የከፋ አረመኔ ቡድን ሲመራው በትግራይ ኗሪ ላይ ያደረሰው አሰቃቂ ግፍ ነበር። ስትራቴጂካዊ መጥቃዕቲ (ወሳኝ/ዘላቂ የማጥቃት ዘመቻ) በሚል የጦርነት ትልም ሲያቅዱ የጠበቁትን የሰው ሃይል ጌቶቻቸው ሻዕቢያን ለማዳን ወደ ኤርትራ በመላክ ብዙ ሺሕ የትግራይ ታጋይ በማለቁ ምክንያት ስለተማናመኑ፤ በግድም በውድም 80,000 አዲስ ወጣት ታጋይ ያስፈልገናል ስላሉ ለወታደራዊ ስልጣና በማንቁርቱ እየታነቀ ወደ ማሰልጠኛ ጣቢያ ሲወረወር፤ የሸሸውም የቤተሰቡን ንብረትና የቤት እንሰሳ እየተወረሰ እየታጎረ በተላላፊ በሽታ በተቅማጥ በወባ በቅማል በመሳሰሉት ለስቃይ ተዳርጎ በኮንሰንትሬሽን ካምፕ/በማጎርያ እስርቤቶችና አውላላ ሜዳ ላይ ተከብቦ የደረሰበት ግፍ ፤-አሳሪዎቹና አድራጊ ፈጣሪ የወያኔ ማአከላዊ ኮሚቴዎቹ ግን ቢራና ዊስኪ እየጎነጩ፤በውጭ አገር ፊልሞች እየተዝናኑ ዓለማቸው ሲቀጩ እንደነበር ከውስጥ አዋቂ በይፋ ሲገለጥ የሚሰማችሁ ስሜት ለናንተው ለሰው ልጆች መብት የቆማችሁ ዜጎች ሁሉ ለሕሊና ፍርድ ልተውና ልሰናበታችሁ። እውን እንዲህ ያለ ግፍ እየፈፀሙ የነበሩት እነ አረጋሽ እነ ገብሩ እነ ስየ ምነዋ አንዲት ቀን ተሳስተውም ቢሆን በሕዝብ ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አንዲት ገጽ እንኳ ቢናዘዙ ምን አለበት? እነኚህ ደሞተራዎች ናቸው የአዲሲቱ የኢትዮጵያ ነፃ አውጪዎች እያሉ አቃጣሪ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ስደልሉን የከረሙት። አንቺ መሬት ስንቱን ጉደኛ ጫንቃሽ ላይ ተሸክሽ ትዞርያለሽ! አምላኬ ሆይ ይቅር በላቸው! ጌታቸው ረዳ። መጽሐፌን ለማንበብ ዕድል ያላገኛችሁ $25.00 ብቻ በመላክ (ለአሜሪካ አገር ብቻ) በስልክ ቁጥር 408 561 4536 ወይንም P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109 በመላክ ልታገኙ ትችላላችሁ። መልካም 2003 አዲስ ዓመት!