Wednesday, December 14, 2016

ቅኝ ገዢዎቻችን ወያኔዎች እና 666 ሰይጣናዊ የኢሉሙናቲ ድርጀቶች በሚያስተዳድሯት ኢትዮጵያ ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ሴት እቶቻችን ላይ እየተሰነዘረ ያለው የሚያሳዝን አገራዊ ጥቃትና ውርደታችን የትግራይ ሕዝብ በልዩ ጥሪ እንዲመለከተው ጋብዣለሁ፡ እነሆ! ጌታቸው ረዳ (Getachew Reda-- Editor Ethiopian Semay)




ቅኝ ገዢዎቻችን ወያኔዎች እና 666 ሰይጣናዊ የኢሉሙናቲ ድርጀቶች በሚያስተዳድሯት ኢትዮጵያ ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ሴት እቶቻችን ላይ እየተሰነዘረ ያለው የሚያሳዝን አገራዊ ጥቃትና ውርደታችን የትግራይ ሕዝብ በልዩ ጥሪ እንዲመለከተው ጋብዣለሁ፡ እነሆ!
ጌታቸው ረዳ (Getachew Reda-- Editor Ethiopian Semay)
666 victim a university Student in Ethiopia under the Satanic Mercenary Weyane/Tigre government in Ethiopia giving her testimony on tears on the crime she suffered.
ሁለት አበይት ርዕሶች በቪዲዮ የተደገፉ ማስረጃዎችን እንመለከታለን። (1) የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተበሎ የሚጠራው የፖለቲካ አቃቂርተኞች “የኢትዮጵያ እና የኦሮሞ አገራዊ ምስረታ ንቅናቄ” ይሉታል፡ ግንቦት 7 እና ኦነግ የሚያሾሩት በአማራ ሕዝብ እና  በኢትዮጵያ አገራዊ ህልውና ላይ ያነጣጠረው ሴራ በማስረጃ እናደምጣለን። (2) ከዚያም በቅኝ ገዢዎቻችን ወያኔዎች እና በ666 ሰይጣናዊ የኢሉሙናቲ ድርጀቶች ኢትዮጵያን ለማጥቃት ከሰነዘሩት ጉንጉን ሴራቸው ውስጥ አንዱ ዘመቻቸው  የኢትዮጵያ   ዩኒቨርሲቲ ወጣት  ሴት ተማሪዎች እየተጠለፉ አዲስ አበባን የግድያ፤የማሰቃያ፤የተገደሉ ሰዎች ስጋ…. (፧?) የሰው ደም ማስጠጪያ፤በሴት እህቶቻችን ላይ እባብ በማህጸናቸው ውስጥ አስግብተው እንዲሰቃዩ የሚደረግበት፤ ክብረ ንጽህናቸው በዓርቦችና በማይታወቁ ሰዎች ጭለማ ውስጥ የሚደፈርሩበት አስደንጋጭ የማፈኛ እና የማጎርያ ህንጻ በቪዲዮ ከተጠቂዎቹ አንዷ ምስክርነቷን የሚያሳይ እንመለከታለን።

ይህ በቅኝ ገዢዎች በወያኔዎች እና በ666 ኢትዮጵያ ዜጎችን የማጥቃት ሴራ በትግራይ ወጣቶችም ሳይቀር (በቪዲየውም የምትሰሙት ይሆናል) እየተፈጸመ ያለው የሚያስለቅስና የሚያበሳጭ ባዕዳን የማይፈጽሙት ጥቃት የትግራይ ሕዝብ ይህ አገራዊ፤ሉአላዊ እና ሰብአዊ የሴቶች እህቶቻችን የጥቃት ዘመቻ በወያኔ ዘመነ መንግሥት ተባባሪትና ተመልካችነት እየተፈጸመ ያለው ወንጀል ተረድቶ ወያኔዎችን የማውገዝ ግዴታው እንዲወጣ ጥሪ አቀርባለሁ። 

ማስጠንቀቂያና ምክር፤-
በቪዲዮው የቀረበው ምስክርነት የሚያስለቅስና የሚያበሳጭ ስለሆነ የደም ግፊት፤የልብ በሽታ፤የጨጓራ በሽታ እና የመሳሰሉ የጤና መታወኮች ያላችሁ ወገኖቼ፤ እባካችሁ እራሳችሁን ሳትጎዱ በትዕግስት ቪዲዮውን አድምጡት። እኔ እራሴ ይህን ማስረጃ ከተመለከትኩ በላ እራሴን ማጋጋም አቅቶኝ እስካሁን ድረስ ከራሴ ጋር ብስጭት እና ትግል አልለቅ ብሎኛል። ስለዚህ እባካችሁ እራሳችሁ ሳትጎዱ  በትዕግስት ቪዲዮውን ተከታተሉት ። ወያኔ አገራችንን ላማዋረድ ባዕዳን ይፈጽሙታል ተብሎ የማይታሰብ ውርደት በራሱ መንግሥታዊ አስተዳዳር የኢሉሙናቲ ዱርየ የናዚ 666 የጉግ ማንጉግ  ሴራ ቅጥረኞች ያለ ምንም ፍርሃት ልቅ ሆነው በሚያምሩ ትላለቅ ማጎርያና ማሰቃያ ህንጻዎች “ማፈኛ” እስርቤት መስርተው ይህ ከዚህ ቀጥሎ ያለው “አስደንጋጭና አስፈሪ ጉድ” እየተፈጸመ ነው። የትግራይ ሕዝብ እና የወያኔ ተከታዮች ይህ ጉድ እንዲመለከቱት ልዩ ጥሪየን አቀርባለሁ። 

እባካችሁ አሁንም የስሜት ህዋሳቶቻችሁ ሳይነኩ በፊት በመጀመሪያ ይህ የግንቦት 7 ሴራ እና የኦነግ ፖለቲካዊ ሴራ ጉድ ተመልከቱ እና ከዚያ ወደ አሳዛኙ የቅኝ ገዢዎቻችን ወንጀል ቪዲዮ ተሸጋገሩ።

ይህ ከዚህ በታች ያለው welkait.com ድረገጽ ላይ የተለጠፈው ግሩም አቀራረብ እንዳለ አቅርቤዋለሁ። የ ግንቦት 7 እና የ ኦነግ ሴራ ሰነድ ለመተንተን አስቤ ነበር ሆኖም ወልቃይት ድረገጽ ከመተንተን ስላዳነኝ የድረገጹ አዘጋጅ አመሰግነዋለሁ። ባለፈው ሰሞን ስለ ግንቦት 7 እና ኦነግ ያዘጋጁት በኢትዮዮጵያ የሴራ ጉንጉን በኢሳቱ ጋዜጠኛ በሲሳይ አገና የተደነቀ እንደነበር እና እኔም የሲሳይ አገና ፖለቲካዊ አታላይነትና የፖለቲካዊ ውሸት ለማጋለጥ ሞክሬ እንደነበር ታስታውሳላችሁ። አሁን እኔ ያልኩትን እውነት ሆኖ መረጃው እነሆ በጽሑፍም፤ በቪዲየው/አውድዮም እየተዋሸ ያለው አስገራሚ ቅጥፈትና አገራዊ ወንጀል ተመልከቱት ይኼውላችሁ።
(1)
የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ የሚጠራው ድርጅትና ያጸደቀው ሰነድ
Ginbot 7 and OLF The anti Amhara mercenary elements organized to destroy Ethiopia 2016-12-
እንደሚታወቀው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአራት የተቃቃሚ ድርጅቶች ማለትም፡-
በግንቦት 7 (G7) በኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ODF) በሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( SNDM ) እና በአፋር ህዝብ ፓርቲ (APP) መካከል በዋሽንግተን ዲሲ ኦክቶበር 30 2016 ..የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) የሚባል ስብስብ ተፈራርመው መመስረታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) የስምምነት ሰነድ ከተካተቱት ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች እና ለህዝብ ያለተገለጡት ጉዳዮች ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን የያዘ ነው።

* የአማራ ህዝብ ተወካይ ባለመኖሩ በስብስቡ አለተካተተም የተባለው ውሸት ነው።

* የንቅናቄው ሰነድ እንዳለ የግንቦት 7 ፕሮግራም የተቀበለ ነው።

* የንቅናቄው ሰነድ በወያኔ መንግስት የወጣውን እና አሁን ወያኔ እየተገበረው ያለውን ህገ መንግስት ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ነው።

* ንቅራቄው በወያኔ መንግስት የተዘረጋውን የአስተዳደር መዋቅር እንዳለ የተቀበለ ነው።
* የንቅናቄው ሰንደ ወያኔ እንደሚለው የኢትዮጵያን ህዝብሕዝቦችእያለ የሚጠራ ነው።

* ይህ በነዚህ በአራቶ ድርጅቶች የጸደቀው ሰነድ ካሁን በኋላ ሰነዱን ማንም ማሻሻም አይችልም የሚል ማሰሪያ አንቀጽ አለው።

* አዲስ ወደ ንቅናቄው የሚገቡ ድርጅቶች በአራቱ ድርጅቶች የጸደቀውን ይህንን ሰንድን እንዳለ ተቀብለው መግባት እንጅ ሰነዱ እንዲሻሻልና እንዲስተካከል የመጠየቅም ሆን የማሻሻል ጥያቄ መብታቸው የተከለከለ ነው።

* ግንቦት 7 ( G7 ) የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ODF ) ማንኛውም የአማራ ድርጅት ተወካይ ወይም በአዛጋጆች ተጋብዞ የነበረው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት በዚህ የንቅናቄ ስብስብ ውስጥ ሊገባ አይገባውም የሚል እገዳ ጥለዋል።

* በንቅናቄ የተገኙት የአፋር እና የሲዳማ ድርጅቶች የአማራ ህዝብ ተወካይ የለለበት የድርጅቶች ስብስብ የትም አይደርስምና የአማራ ህዝብ ተወካይ በንቅናቄው ስብስብ እንዲካተት ከፍተኛ ድምጽ ያሰሙ ቢሆንም  ግንቦት 7 እና ኦዲፍ (ODF) ግን የአማራ ተወካይ በንቅናቄው ውስጥ መገኘት የለበትም በማለት እገዳ ጥለዋል።

በዚህ አጋጣሚ የአፋርና የሲዳማ ህዝብ ድርጅቶች ሃላፊዎች ምንም እንኳ በጉልበተኞቹ በግንቦት 7 እና ኦዲፍ (ODF) መሪዎች ተጽእኖ ምክንያት የአማራ ህዝብ ተወካይ በስብስቡ እንዳይገኝ ቢደረግም እናንተ ግን እውነተኛ የነጻነት ታጋዮች በመሆናችሁ የአማራ ህዝብ ተወካይ የለለበት ስብስብ ዋጋ የለውም ብላችሁ ያነሳችሁት ጥያቄ ለነጻነቱ እየታገለ ላለው የአማራ ህዝብ ያላችሁ ቅን ልብና ወገናዊትነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ለእናንተ ያለው አክብሮት ከፍ ያለ መሆኑን እየገለጽን በዚህ አጋጣሚ ላሳያችሁት አጋርነት እናመሰግናችኋለን።

አቶ ተክሌ የሻው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅትና ሊቀመንበር እና የአማራ ህዝብ ጠባቃየኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ የሚጠራው ድርጅትና ያጸደቀው ሰነድን በሚመለከት የሰጡትን አስተያየት ከዚህ በታች ያድምጡ።

ስለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄን - Ethiopian National Movement የአቶ ተክሌ የሻው አስተያየት

https://youtu.be/j4gLQDvHUM8

 

(2) አሁን በቅኝ ገዢዎቻችን ወያኔዎች እና በ666 ሰይጣናዊ የኢሉሙናቲ ድርጀቶች በኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ አዲስ አበባን የግድያ፤የማሰቃያ፤የሰው ደም ማስጠጪያ፤በሰት እህቶቻችን ላይ እባብ በማህጸናቸው ውስጥ አስግብተው እንዲሰቃዩ የሚደረግበት፤ ክብረ ንጽህናቸው በዓርቦችና በማይታወቁ ሰዎች ጭለማ ውስጥ የሚደፈርሩበት አስደንጋጭ የማፈኛ እና የማጎርያ ህንጻ እየተፈጸመ ያለው የጉግ ማንጉግ ጉድ በቪዲዮ የተደገፈ ከተጠቂዎቹ አንዷ የሆነች ምስክርነቷን የሚያሳይ እንመለከታለን። ፓስተሩ/ቄሱ (ፔንጤ ይመስለኛል) እስላም ኖሮ አሁን ወደ ክርስትና የተመለሰ ኢትዮጵያዊ ነው። በእሱ አማካይነት የተዘጋጀው የጸሎት መድረክ የቀረበ ማስረጃ ነው። እነሆ!
Man of God Prophet Jeremiah Husen Testimony
አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ (Getachew Reda-- Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com



Saturday, December 3, 2016

ምን እየተወራ ነው? ጌታቸው ረዳ Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay)




ምን እየተወራ ነው?
ጌታቸው ረዳ Getachew Reda  (Editor Ethiopian Semay)


መጀመርያ ሰላምታየን አደርሳለሁ። ወደ ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት እንደተለመደው አንዳንድ ነገሮችን ልበል። ወዳጆቼ እና አንባቢዎቼ ለተወሰኑ ሳምንታት ከስልክ እና ከኢመይል ርቄ ስለነበር ለጥሪዎች እና መልዕክቶች መልስ ባለመስጠቴ የተከፋችሁ ወገኖችና የቅርብ ወዳጆቼ እንዳላችሁ ከተቀረጹት መልዕክቶቻችሁ  ማድመጥና ማንበብ ችያለሁ። እጅግ ከፍተኛ የሆነ ልባዊ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ይህ ካልኩኝ ዘንድ፤የኢትዮጵያን ሰማይ (Ethiopian Semay) አንባቢዎች በኖቨምበር ወር ውስጥ በየቀኑ ከ 1385 አንባቢያን ወደ 3061 ከፍ ማለቱ በደስታ ለመቀግለጽ እወዳለሁ።                                                                                                                                                                                                                  
Dr. Merera Gudina wearing the anti Ethiopia flag. If this is not going with the flow of the subversive agenda to downgrade Ethiopian flag I do not know what you will call it. when someone of his caliber, an educated scholar wears banda flags /Fascist Italian or Arab/Egyptian designed flags and symbols for Ethiopia, what will you call such shame? why would someone got into such shame? this is conspiracy against Ethiopian flag designed by OLF and TPLF. What do you think it should be called such shameful act?
                                 
                                                                                                                                                                                                                                                        
ይህም የሚያሳየው፤ “የተገንጣይ ቡድኖች ባንዴራ፤ ግንጠላና ዘረኛ ቅስቀሳቸው” ያለምንም ይሉኝታና ሓላፊነት በድረገጾቻቸው ዘርግተው የወጣቱን ሕሊና የሚበክሉ፤የአብዛኛዎቹ የተቃዋሚ ድረገፆች በብከላ (የሳብቨርዠን) ሥራ ተሰማርተው ብዙ ጉዳቶች እንዳደረሱ ልብ ላለው ሰው የሚስተው አይደለም። ከነኚህ “በካ ድረገጾች” ወጣ ብለው ለየት ያለ አመለካከት ወደሚተላለፍበት ወደ ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ጎራ ብለው ነገሮችን ማገናዘብን ጠቃሚ መሆኑን የተረዱ አንባቢዎች መጨመሩ አበራታች ክስተት ነው። ለዚህም አመሰግናለሁ።

ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ (አንድ እንሁን ወይንም ጥቃቅን አገሮች መስርተን እንለያይ የሚመስል) የሚለው የመረራ ጉዲና ስሜታዊ መፈክር፤ዛሬም ከመቸውም በበለጠ በተቃዋሚ ሊሂቃን ብዕር እየፈለቀ ነው። ወደ ወያነ እንጂ የዘር ማጽዳት ወንጀልና ግፍ ወደ ሰሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች፤ ወይንም የውጭ ቅጥረኞች ጋር አናትኩር፤ወንጀል ከፈጸሙት ጋር ሕብረት ንፍጠር ወዘተ.ወዘተ…..የሚሉ ክርክሮችን አንብቤአለሁ። በመሳሰሉና በሌሎች ርዕሶች ታች እናያለን። ሁሌ የሚያስገርመኝ ግን፤ መተባበር ከማን ጋር? ብሔራዊ ሰደቃላማችንን ጥለው አዲስ ባንዴራ አስሰፍተው ያነገቡ ኦነጎች ወይንስ እስላማዊና  ዓረባዊ ምስል ያነገቡ የዓረብ ባንዴራ ካነገቡ ኦሮሞዎች፤ ኦጋዴኖች? የኦሮሞ ሃበት በኦሮሞና ለኦሮሞ ብቻ’፤ የኦጋዴን ሃብትና መሬት ለሶማሊ ኦጋዴን…ወዘተ ከሚሉ እና በሻዕቢያ ሳምባ ከሚተነፍሱ ወይንስ የአሜሪካ ጥቅም ከወያኔ ይልቅ በይበልጥ እኛ እናስከብርላችለን ከሚሉ ከእነ ብርሃኑ ነጋ የመሳሰሉ ቅጥረኞች እና በካሊ/ሳብቨረሲቭ/ ሃይሎች? 


የማንነታችን ነጋሪ አገራዊ ምልክቶቻችንሉአላዊ ክብራችን ከሚጻረሩ ቡድኖች ጋር የጋራ ትግል ማቀናጀት ኢትዮጵያዊያን ነን የምትሉ ፍፁም እንኳን ለመደራደር ማሰብም የለባችሁም። ዲሞክራሲ እና ሰላም ለማስፈን በሚል ሽፋን እና ማጃጃያ በአገር ሉአላዊነት መደራደር የት እንዳደረሰን 25 አመት ተመክተነዋል።

አሁን ያለችሁ ወጣቶች ያንን ቂልነት ከደገማችሁና ከተደራደራችሁ እኔ ጌታቸው ረዳ ሳይሆን አገር ያጣው እናንተም እዚሁ ትበሰብሳለችሁ፤ አገር ያለችሁም ወጣቶች ስደት ውርደት፤’የጀነሳይድ’/የዘር ፍጅት የቻይና፤ የፈረንጅ ባርያ፤ የዓረብ መጫወቻ፤ የቅኝ ገዢዎች ሲሳይ ትሆናላችሁ።

ወላጆቻችን ያለ ዲሞክራሲ አገራዊ አስተዳደር እና ፈሪሃ ፈጣሪ ያለው ማሕበረሰብ ገንብተው የተንጣለለ አገር አስረክበውናል። በኛ ዘመን ሲደርስ፤ ሶሺያሊዝም፤ዲሞክራሲ፤ሰልፍ አድሚኒስትሬሺን፤ ብር ብረሰብ ወዘተ..ወዘተ.. እየተባለ፤ እርስ በርሱ ምጽዓተ ዓለም ገበቶ ሲገዳዳል፤ የዘር ማጽዳት ተከስቶ በሚሊዮኖች ጠፍተዋል። ዲሞክራሲና ማርክሲዝም ጭራቆችን በገፍ ፈልፍሎ ‘የባሕር ወደቦቿን ለዓረቦች ተሰጥቶ መጨረሻ ላይ ኢትዮጵበባሕልም፤በአለባበስም በመንፈስም የዓረብ ገረድ ሆነች። የዲሞክራሲ ውጤት አይነው!! ሌላ ዲሞክራሲ እትንቢታዊ ዲሞክራሲ እስኪመጣ የፈረንጅ፤የቻይና መጫወቻ ትሆናላችሁ።

ይህ ዕጣ መቅመስ ካልቀረላችሁ ሉአላዊ አገራችሁን እንደ ወላጆቻችሁ አስከብራችሁ መሞት አኩሪ ታሪክ ነውና አስቡበት።አገር በልምምጥ፤በደርድር አልተመሰረትም። ሃይል፤ጽናት፤ገንዘብ የዚህ ዓለም ወሳኝ ሃይሎች ናቸው። እውነት ብቻ አንግባችሁ ኢትዮጵያን ለጠላት ማስረከብ ማብቃት አለበት። ዲሞክራሲ ‘ገለመለ’ ብዙሃን በጥቂቶች እና በግለሰቦች ላይ የሚጫወት የመጨቆኛ መሳሪያ ነው።

 የኛ ምሁራን ጥዝ ነጠቅ ከውጭ እየቀዱ ወንጀል ከሰሩ ቡድኖች ጋር እንተባበር እያሉ ‘ፌዴራል፤ዲሞክራሲ፤ብሔር፤ብረሰብ……..ሊበራሊዘም፤ሰልፍ ዲተርሚነሽን ዊዝ ኢን ኢትዮጵያ…”  ምንትስ፤ገለመለ… እያሉ ሲያጃጅሏችሁ ለሁለተኛ ጊዜ ማነቂያ መድረክ እየተዘጋጀላችሁ እንደሆነ ካሁኑኑ እወቁ። አገራዊ እሴቶች እየጣላችሁ እንደ አሜሪካ ዲሞክራሲ/ዲክታርሺፕ ለመሆን የምትፈልጉ ቡድኖችና ፖለቲከኞች፤ ምን እንደምታገኙ የአሜሪካ ዲሞክራሲ ህያው ምስክር ነው። ዲሞክራሲ ዲክታተር ሺፕ ነው። ናዚዎችን ወደ ሥልጣን የሚያመጣ ልቅ እና አደገኛ የአስተዳደር ክንዋኔ ነው (ሂትለር በዲሞክራሲ ነበር ወደ ፓርላማ ሰገነት የመጣው!!!!)። የትራይ የፋሺስት ግልገሎች በዲሞክራሲ ስም ምለው አሜሪካኖች ምርኩዝ አድርገው ነበር ወደ ሥልጣን የተቆናጠጡት። ፋሺዝምና ዲሞክራሲ አይጨካከኑም፡ በሩ ለሁሉም ጋጠ ወጥ እና ነብሰ ገዳይ ክፍት ነው።

ዲሞክራሲ ማለት ስባሪ/ፍንጣሪ የማሞኛ ጣፋጭ ከረሜላ ምላሳችሁ ውስጥ እንድታላምጡት ካደረገ በላ ሳታስቡት በድንገት መራራውን ክኒን ጉሮራችሁ ውስጥ ሰክቶ ያለ ውሃ እንደትቆረጥሙት የሚያሰስገድድ ማሞኛና የመጨቆኛ መሳሪያ ነው። ኣንድ አገራዊ የፖለቲካ ድርጅት ያገሪቱን አሴቴች ለገበያ እና ለፖለቲካ ድርድር ካቀረበ፤ በመጨረሻ ላይ በሞራል በባህል የበሰበሰ ማሕበረስብን ይፈጥራል።

በኦሮሞች በኦጋዴኖች በኤርትራ ሊሂቃን እያየነው ያለው የበሰበሰ አስተሳሰብ በዓይን የምናየው ሃቅ ነው። መፈክራቸው ሁሉ “ዲሞክራሲ/ ሰልፍ ዲተርሚነሽን” ነው። ለምሳሌ ይህነን የዲሞክራሲ ጅራፍ ከሚያጮሁት ኦሮሞ ሊሂቃን ውስጥ ጸጋየ አራርሳ የተባለ አውስትረሊያ ፡የሚኖር ትምህርት ያሰበደው ዕብድ..... ኢትዮሚዲያ ድረገጽ ደግሞ ፡”መደመጥ ያለበት” እያለ ለወራት ብከላወን ሲያስተዋቃችሁ ከርሞ (እኛ ይህ ጉድ እንደሚፈነዳ አስቀድምን ብናወቅም) ፤ ሳይውል ሳያድር ይህ ነጠላውን የጣለ ሰው ስለ ሚኒሊክ፤ስለ አማራ፤ስለ ትግሬ፤ስለ ኢትዮጵያ፤ስለ አማርኛ፤ስለ አበሻ…….በቆሸሸ ሕሊናው ያለ ሓፍርት ምን እንዳለ ብዙዎቻችሁ እንዳስቆጣ አንብቤአለሁ። ተሻለ መንግቱ የተባሉ ጸሐፊ በትምሕርት( ውስጥ ) እንደሚገኝ  ያለ ድንቁርና የለም” በሚል ርዕስ በግሩም ሁኔታ ያቀረቡትን እንደ ጸጋዬ አራርሳ የመሳሰሉ ነጠላቸውን ባደባባይ የጣሉ የምሁራን ዕብዶች ለማሳየት የጻፉትን እንዲህ ይላሉ፦

ኢትዮጵያ እንደ እስካሁኑ ድረስ ሆደ ሰፊ ሆና የምትቀጥል አትመስለኝም፡፡እንደ እስካሁኑ  የአእምሮ  በሽተኛ ልጆቿን እያስታመመችና ባለጌዎችን በጨዋዎች ላይ እያነገሠች ከአሁን በኋላ በኢዮባዊ ቁስል ለመንፈር ፈቃደኛ የምትሆን አትመስለኝም፡፡እንደ እስካሁኑ አንዱ ከሌላው በሚቀጥል እልህ አስጨራሽ የስቃይ አዙሪት የምትገባና የዋህና ገር ልጆቿን ለተጨማሪ መከራ የምትዳርግ አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም ሁሉም አፈንጋጭ ቆም ብሎ ማሰብ የሚገባበት ዘመን ላይ የደረስን ይመስለኛል፡፡” ይላሉ ‘ኢትዮ ሚዲያ’ ላይ ያስነበቡን አቶ ተሻለ መንግሥቱ። አቶ ተሻለ መንግሥቱ የነ ጸጋዬን ከሃዲና ጎሰኛ የግንጣላ ፕሮፓጋንዳ  “ዕብደትን ለማስፋፋት የሚደረግ ሩጫ” ሲሉ ባጭር አማርኛ ደምድመውታል።

ስለ ኦሮሞዎች ጉዳይ፤ስለ መረራ፤ስለ ሌንጮ ለታ….ስለ አማራው ወጣት አቻምየለህ ታምሩ …….ወዘተ…ወዘተ…. የሚጎረብጡ ትንተናዎች ከወደታች በሰፊው እንመለከታለን።አሁን ወደ ሌላ ርዕስ እንግባ፤

ምጽአተ ዐማራ ተገድሎና ተገዳድሎ የማያልቅ፤ ተነቅሎ የማይደርቅ የሚል በአንደበተ ርቱእ እና በታላቁ ኢትዮጵያዊ ምሁር፤ በአቶ ተክሌ የሻው የሚመራው የሞረሽ ወገኔ ድርጅት ያሳተመው መጽሐፍ ፤ ካሁን በፊት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያልተነገሩና የተደበቁ የአገራችን ታሪኮች በሰነድ አስደግፎ በሰፊው የሚተነትን መጽሐፍ ታትሞ ለሕዝብ መሰራጨቱ የዚህ አምድ አዘጋጅ ለድርጅቱ ሊቀመንበር፤ አመራሮች እንዲሁም አባሎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።

ይህ መጽሐፍ በዓይነቱ ለየት ያለ አቀራርብ ሲኖሮው ፤  መጽሐፉ የፖለቲካ መሪዎችን ፤የኢትዮጵያ ታላላቅ እና ታናናሽ ምሁራን እንዲሁም አሁን ያለውን ማሕበረሰብ ሕሊና በተለይ ወጣቱን ወደ እውነታው ወጥሮ በመጎተት መጽሐፉ ውስጥ በተዘረዘሩት ክንዋኔዎች ውስጥ ራሱ ቆሞ ተመልካች ወይንም ተካፋይ በሆነበት ድርጊት  ምን ያህል አገር አጥፊ ወይንም አልሚ እንደሆነ እራሱን እና መጪውን ትውልድ የሚያይበት ወጣሪ የሆነ ጥልቅ ሰነድ ነው። መጽሐፉ ለታሪክ፤ለማሕበረሰብ ወንጀሎች፤ ለስነልቦና እና ለኣምሮ ተመራማሪዎች የጥናት መስክ የሚሆን፤ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለምርምር የሚረዳ መጽሐፉ እንደሚሆን አልጠራጠርም። መጽሐፉ ወደ ሗላ ታሪካችን ጎትቶ ወስዶ አሁን እስካለንብት ወቅት የተደረጉ በጎ እና መጥፎ ድርጊቶች፤የተለያዩ ጥነታዊ ካርታዎች፤ የዓላማ ጽናቶች፤ ጀግንነቶች፤ ቡድኖች፤ግለሰቦች፤ጦርነቶች፤የስልጣን-ሽሚያዎች፤ክሕደቶች፤ሴራዎች፤ ዘረፋዎች፤ ማሕበራዊና ምጣኔ-ሀብታዊ ንቅዘቶች፤ወንጀሎችና የተፈጸሙ ጠቅላላ ክንዋኔዎችን በሰፊው ይተነትናል።

በመጽሐፉ የተዘገቡ የታሪክ ክንዋኔዎች ከማንኛቸውንም መጽሐፍ አቀራረብ ለየት ያለ እና የታሪክ ጸሐፍትን በማስረጃ እየጠቀሰ የሚያስጠና ወቅታዊ ብቸኛ መጽሐፍ ሲሆን፤ እጅግ ለየት የሚያደረግው ደግሞ በኦነግ፤ በወያኔ እና በአክራሪ እስለማዊ ቡድኖች ሴራና ድርጊት ፤ በአማራ ማሕበረሰብ ላይ የተፈጸመ አሰቃቂ የዘር እልቂት በፎቶግራፎች እና በደብዳቤ የተደገፉ ሰነዶች ስንመረምር ሕሊናን የሚፈታተን እያንዳንዳችን አፍጥጦ የሚጠይቅ መልስ የሚያሳጣ በዘመናችን የተፈጸመ የሰው ልጆች እልቂት በጥልቀት ዘግቦታል።

አስገራሚና የሚያሳፍረው ደግሞ፤ ይህ ሁሉ የአማራ ገበሬ፤ ሽማግሌ፤ አባት፤ እናት፤ጧሪ፤ህጻናት፤ እመጫቶች፤ እርጉዞች፤ወጣቶች፤ነብሰጡሮች፤የገጠርና የከተማ ሃኪሞች፤ ጋዜጠኞች፤መምህራኖች፤ ቄሶች፤መነኮሳትና የቀን ሰራተኞች በሆኑ የአማራ ማሕበረሰብ ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት በላያቸው ላይ ሲፈጸም፤ ከአብራኩ የወጡ የአማራ ማሕበረሰብ ምሁራን፤ ሰምተው እንዳልሰሙ ሆነው ዝምታን በመምረጥ፤ አንዳንዱም በሚያሳፍር ሁኔታ ድርጊቱ እንዳልተፈጸመ ወይንም የተጋነነ ነው በማለት እያስተባበሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የድርጊቱ ተዋናዮች ሆነው ማየት አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን “የአማራ ማሕበረሰብ ምሁራን” ዝምታ ከምን እንደመነጨ ለመግለጽ እንኳን ለኔ ለባለ ሞያ ተመራማሪዎችም የሚከብድ በቃላት ለመግለጽ የሚከብደኝ በማሕበረሰባቸው እና በወላጆቻቸው ላይ “ክህደት” ፈጽመዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ለበርካታ አመታት የጮሁኩበት ስለሆነ እንደገና አልመለስበትም። ምክንያቱም የአማራ ምሁራን ክህደትና ዝማታ ፈልጌ ምክንያታቸው ማግኘት ባልችልም፤ ……. በመኝታና በእረፍት በድሎትና በጥሩ ምግብ የዳበረው ማአዛ ባለው ጽጌረዳዊ ሳሙና እና ቅባት የተሙሎጨለጨው ገላቸው አረፍ ብሎ ይህ መጽሐፍ ሲያነብ እያንዳንዱ የአማራ ምሁር ይህ ወንጀል ሲፈጸም ዝምታን ለምን እንደመረጠ እራሱን ተመልሶ በቁጭት እንደሚጠይቅ ተስፋ አለኝ።

ወጣቶቹም እንዲሁ፡……..የአማራ ማሕበረሰብ ገበሬ፤ እናቶች፤ እርጉዞች፤ አዛውንቶች እና ህጻናት በወንጀለኞች የዘር ማጥፋት ሲፈጸምባቸው ‘የአማራ ወጣቶችም” እንዲሁ ከተጠያቂነት ነፃ መሆን አይችሉም። ምሁራኖቻቻው ዝምታን መርጠው መሪ ሲያጡ ወጣቶቹ ምን ያድርጉ ተብሎ የሚታለፍ ጉዳይም አይደለም። አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ በወላጆቻችሁ እና እህቶቻችሁ ‘ወንጀል’ እየተፈጸመ ነው ብለን የአማራ ወጣቶችን ለማስረዳት ስንጥር “የስድብ ውርጅብኝ ይደረግብን እንደነበረ የአውድዮና የጽሑፍ መረጃዎች አሉ። ሌላው አስገራሚው ግን፤ ብዙዎቹ የአማራ ወጣቶች ሰለባ የሆኑበት ምክንያት፡…  የአማራ ምሁራን ክፍሎች፤ የተቃዋሚዎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች የዝምታ እና የሴራ ሰለባዎች ሆነው ኮቴዎቻቸው ሲከተሉ፤ የትግሬ ወጣቶች ባስገራሚ ሁኔታ የአማራን እልቂት አቀናባሪ እና ቀያሽ/መሃንዲስ የነበረው ቤዛችን/ መድሃኒታችን/ የሚሉትን  መለስ ዜናዊን በማሞካሸት በመለስ እና በዓይናችን አትምጡብን ብለው ለእኩይ መስመር ያለማመንታት ድጋፋቸው ሰጥተዋል። ያም ወጣት ነው፤ያኛውም ወጣት ክፍል ነው። ሁለቱም በአጥፊ ክንዋኔ እና ባጃጃይ አንቅልፍ የተጠመዱ ነበሩ/ናቸው

በዚህ ሁኔታ እያለ የአማራው ወጣት የታሪክ እንፋሎት ለብልቦት ከጥልቅ እንቅልፉ ባንኖ መታገ እንዳለበት ወድዶ ሳይሆን የታሪክ ሃይል ከእንቅልፉ ጎትቶ ከቀሰቀሰው በላም ቢሆን እንደ ወያኔ ወጣቶች ባንድ መስመር ሳይሆን፤ አማራን ከከጨርሶ ጥፋት ለመከላከል በ 5 እና በ6 ድርጅት ገብቶ (ከዚያም በላይ እንደሚሆን ይገመታል) ቅልጥሙ ባንድነት ማስተበባር አልቻለም። አስገራሚ የሚያደርገው ክስተት ደግሞ አንዳንዶቹ “የናዚ” መስመር የተከተሉ (ጠቅላላ ትግሬን ማጥፋት የሚሉ በፓልቶክ ክፍሎቻቸው ውስጥ የሚነገር ተከታታይ አውድዮ መረጃዎች አሉ) እና ከዚያም አልፈው ሌላው “ቤተ አምሃራ“ የተባለው ድርጅት ደግሞ  Independent Amhara is the only salvation to survive the current genocide” አማራን ከጨርሶ ጥፋት ለማዳን “አማራው ኢትዮጵያ ከምትባለዋ አገር ነጥሎ በማሰወጣት የራሱን አገር እና መንግሥት መመስረት አለበት” የሚል በአማራ ስም የተመሰረተ ድርጅትም ለማየት በቅተናል።

ይህ ዕብደት ለምን ተከሰተ? ይህ ድርጅት ሚመሩት እስካሁን ያየቸውና ያዳመጥኳቸው የድርጅቱ አመራሮች “ወጣቶች” ናቸው። አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ የተቀሩት አማራን ለመታደግ ተመስርተናል የሚሉ ድርጅቶች ከዚህ አፍራሽ እና አማራዊ መንግሥት እመሰርታለሁየግንጠላ ትግል አደርጋለሁ ከሚል ድርጅት ጋር አብረው የጋራ ጉዞ  በማድረግ በየአዳራሹ ስብሰባ ሲየደርጉ አይቻለሁ።ለምን? ለዚህ ለዚህ ኦነግ ምን አደረገ? ተሳስቻለሁ ካለም በይፋ ይቅርታ የጠየቀበትና ያስተካከለበት ጽሑፍ አላነበብኩም።

እንዲህ ያለ መላቅጡ የወጣ ትዕይንት ከልብ የተነሱ የአማራ ድርጅቶችን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት ስለሆነ ለመገንጠል በግልጽ የዛተ እና ፖሊሲው በይፋ የተናገረ ድርጅት ጋር የጋራ ንድፍም ሆነ ቃል ኪዳን ማድረግ ታጥቦ ጭቃ እንዳይሆን ከልጆች ጨዋታ ፖለቲካ እንዲርቁ ከወዲሁ ቢታሰብበት መልካም ነው። ገንጣዮቹ የቤተ አምሓራ ምክትል መሪ ለማድመጥ ወደ መጨረሻ አካባቢ ክሩን አሳልፈው የአማራ መንግሥት ምስረታው ዓላማ ለማድመጥ ይህንን  ይጫኑ። Hiber Radio exclusive interview with Bete Amhara Leader, Mesafint Bazezew https://youtu.be/hsn0Z2unFPg   አብርሃ ደስታ ይህ የግንጣለ ቃል በማድመጡ ምክንያት የተነሳ ይመስለኛል፤ በተ አምሃራን “ቤተ አቧራ” ብሎ የጠራው።

ወደ ሌላው ርዕስ ከመሻገራችን በፊት ስለ አማራ ጉዳይ ማንሳቴ ላልቀረ ሁለት ነጥብ ላስቀምጥ።

አማራ በአማራነቱ መደራጀት ጠባብነት ነው ወይንም ኦነግነት/ወያኔነት ነው የሚሉ ምሁራን እና ተንታኞች አሉ። በዚህ ጉዳይ ብዙ ብያለሁ። አሁን አልመለስበትም። አማራ መደራጀት አለበት ያልኩበት ምክንያት በሞረሽ ወገኔ በኩል የተቀመጠ ጥርት ያለ ግልጽ መመሪያ ማንበብ አለባችሁ። አማራውን ከጨርሶ ጥፋት ለመታደግ ሞረሽ ወገኔ /የስቪል/በርጌስ ማሕበረስብ ለምን እንደተደራጀ ከድረጀቱ ሊቀመንበር ቃለመጠይቅ እና ከድርጅቱ መግለጫ እና የራዲዮን ሐተታ ማጤን አማራ ድርጅት እንደሚያስፈልገው በቀላሉ መረዳት እንችላለን።

ሆኖም የሞረሽ ወገኔ መመስረት ጭልሞ የነበረው የአማራ ልቦና ብርሃን ሰጥቶ ወጋገኑ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በበራበት ባሁኑ ሰዓት ጎጎ (ጎንደር /ጎጃም)፤ዳግማዊ መኢአድ፤ቤተ አማራ…. የሚባሉ ድርጅቶች ወደ መድረክ መታየት ጀምሯል። በዚህ ላይ ከኔ ይልቅ ይድረስ ለአራት አማሮች በሚል ርዕስ በድንቅ አቀራረብ ያቀረቡት አቶ መኳንንት ታዬ የተነተኑትን ልጥቀስና ወደ ሁለተኛው እሻገራለሁ።

አንድ አማራ በአውራጃና በክፍለ ሃገር ተከፋፍሎ የእንትና እና የእንትና ድርጅት ማለት ለምን አስፈለገ? ።ለመሆኑ አንድ ቋንቋ አንድ ህዝብ፤ አንድ ስም፤ አንድ… አንድ… ስንት ነገር ያለው ህዝብ እንዴት  የጎጃም… የጎንደር ………ተብሎ በዚህ አንገብጋቢና ጊዜ የማይሰጥ ወቅት በተለያየ ድርጅት መቧደን አስፈለገ? በማለት ይጠይቃሉ። ያውም ይሉ እና…..በዚህ ከቀጠለ…እነ ወሎ እነ ሸዋ  እነ… ብቻ ብዙ አማሮች  ይመጡ ይሆናል። ይላሉ።በመቀጠል ስለ አንድ ህዝብ የምናወራ ከሆነ በአንድነት ስለ አንድ  ነገር የምናወራበት  መልካም ግዜ ከዛሬ የተሻለ መቼ ነው? ጉድ ያለው ገንፎ አድሮ ይፋጃልና ኩታ ገጠም ክፍለሃገሮች  ባለሁለትና ባላ አራት አማራ ሆነው ከላይ እንደገለፀው አይነት ስም ይዘው ሲመጡ መስማት ግን እነማነን  እንበል።በውኑ ለሰሚውስ ለትውልድስ  ስንት አማራ  አለ ተብሎ ይነገር? ጥቅሙና ጉዳቱስ ቁጭ ብሎ ተሰልቷልወይስ እንደነ ጀዋር መሃመድ የስሜት ፖለቲካ ነው ?።ለመሆኑ አማራን  አራትና አምስት  ቦታ መከፋፈል ከወያኔ በምን ተሽሎ ነው? ።ይህ ሁሉ የበላይነት ሽሚያ  ማንን አንግሶ ማንን አኮስሶ ለመለያየት ነው ።አማራው አለም ባወቀው  እና ፀሃይ በሞቀው ሁኔታ ጦርነት ታውጆበት ለምን አማራ ጎጃምና ጎንደር ላይ ብቻ ሆኑ?ለመሆኑ ወሎና ሸዋስ ምን ብሎ ይምጣ ? እሱም ይቅር አማራ ያልተጋባውና ያልተዋለደው  ብሔረስብስ አለ ወይ? ወይስ እንደ እናንተ ስም አዘጋጃችሁለት ? መልካም  የጎንደር እና የጎጃም እንዲህ ነን ተባለ፤እንወክለወላን የሚሉት ያልተስማሙ እንደሁ ምን ብለን እንጥራ ?ጎጃምና ጎንደር ተጣሉ ወይስ አማሮች?ሌላው ባንድነት ስም የተደራጁና  ሁሉንም አማራ አንድ ሊያደርጉ የሚችሉ ድርጅቶች ቀድመው  ተመስርተው  እያሉ ያንኑ ተደግፎ  አንድነት መስረቶ ማጠናከር እያለ ለምን ከላይ በጠቀስናቸው  ስሞች ተመዝግቦ አዲስ ሆኖ መምጣት አስፈለገ? ሲሉ ድንቅ ጥያቄ አቅርበዋል።

ሌሎች ምሁራን ደግሞ በአማራነት መደራጀት ጎሰኝነት ወይንም ጠባብነት ነው ሲሉ ቅዋሜ ያስሰማሉ። ከነዚህ መሃል ለምሳሌ አብርሃ ደስታ የተባለው ምሁር የአማራውን ሕብረተሰብ ከኦነግ፤ከወያኔ እና ከአክራሪ እስላማዊ ቡድኖች ጥቃት ለመከላከል የተደራጁትን አማራዊ ድርጅቶችን፤ ለምን ኢትዮጵያ በሚለው አይደራጁም በማለት፡ ‘በጎሰኛነት’ ሲከሳቸው ወይንም መደራጀታቸውን ሲኮንን እራሱ የራሴ ጎሳ ብሎ የሚናገርለት የትግሬ ሕዝብ ለመቆም ግን ወደ ላ እንደማይል እንዲህ ሲል ይነግረናል።  ትግራይ ህዝብ ላይ የተቃጣ አደጋ ካለ ከትግራይ ህዝብ ጋር መቆሜ አይቀርም።” ይላል አብርሃ ደስታ። በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣ አደጋ አለ። በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣ አደጋ ካለ አማራው ከአማራ ሕዝብ ጋር መቆሙ እንዴት ፍትሃዊ አይሆንም? የሚል ጥያቄ አቀርብለታለሁ።

ቻምየለህ ታምሩ

ሌላው ጉዳይ አቻምየለህ ታምሩ የተባለው የአማራ ማሕበረሰብ ወጣት በቅርቡ ወደ መድረኩ ብቅ ብሎ ብዙ አድማጭና እና አድናቆት ያስገኘ ወጣት ፖለቲከኛ እና ምሁር እንደምታውቁት እገምታለሁ።  በሰፊው እስክመለስበት ጊዜ ለዛሬ ትንሽ ልበል። ይህ ወጣት አንዳንድ እርማቶች ካደረገ ለከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ሊያበቃው የሚችል ብሩሕ እውቀት እንዳለው እርግጠኛ ነኝ። ምን ንደሚሆን ባላወቅም….ማለትም ‘ወጣ ወጣና ንደሸምበቆ…..ተንከባለለ እንደ ….አለሎ እንዳይሆን እና በሂደት ከነ ግንቦት 7 ከነ ኦነጎች፤ከነ ኢሳቶች ካልተሻሸ በዚህ ከቀጠለ ተስፋ ያለው ወጣት ነው። የዚህ ወጣት ጥርጣሬየ ግን እየጎላ መምጣቱ ምቾት አልሰጠኝም።ለምሳሌ ሁለት ነጥቦችን ላቅርብ።

ይህ ወጣት የሻዕቢያው እና የኦነግ ዲስኩር አዳማቂ የሆነው፤ ያልሆነ ታሪክ አጣምሞ ሕዝብን የሚያጃጅል ግንቦት ሰባት የሚያሽከረክረው ኢሳት የተባለ የዜና አውታር ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የኢሳቱ ጋዜጠኛ “ሲሳይ አገና” ን  “ተወዳጁ ሲሳይ አገና” እያለ በሚዲያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አድናቆቱን ሲገልጽ ሰምቼው ተገርሜአለሁ። ሲሳይ አገና፤ታማኝ በየነ እና የመሳሰሉት የሚያካሂዱት ኢሳት የተባለው የመገናኛ አውታር (ሌላውን ጉዳቸውን ሳናነሳ)  ‘ጃራ” የተባለው እስላማዊ የኦነግ ድርጅት መስርቶ በመሪነት በሐረር እና በመሳሰሉ መነኮሳትን እና አማራዎችን የጨፈጨፈ የሰው ጭራቅ ከዚህ ዓለም ሲሰናበት እያቆለጳጰሱ በጣቢያቸው ሲያቅርቡልን እንደነበር ይህ ወጣት “ተወዳጁ” እያለ የሚያስተዋውቀው ሲሳይንም ሆነ ታማኝን  በዚህ ሁኔታ ተወያይቶበት ያውቃል? እነዚህ ሰዎች ስለ አማራ ቆመናል ካሉ፤ ጃራን የሚያክል ትልቁ ጭራቅ በአርበኛ ታጋይነት ሲወሳ፤ነብስ ይማር ሲባልለት፤ በአማራ ነብስ የተጫወተ የቀን ጅብ ሲሳይ እና ታማኝ፤አበበ እና የመሳሰሉ በሚመሩት የዜና አውታር  ሲወደስ እነ ሲሳይን ያስወደሰውና ያስወደሰው ምንድ ነው? ተወዳጅ ምን ማለት ነው?



ይህ ጋዜጠኛ ከሙያው ጋር የተጣረሰ ሰው ነው።በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የነበራቸው ክስ እና በእሱ ምክንያት ወደ ሻዕቢያ መርማሪ ክፍሎች ተላልፈው የተደበደቡ፤የሞቱ፤ደብዛቸው የጠፉ የድርጅቱ የመጀመሪያ ታጋዮች ስሞታቸውን ለሕብ ለማስሰማት እና በብርሃኑ ነጋ እና በመሳሰሉ አመራሮች ጋር ፊት ለፊት ለሕዝብ ዓይን እንዲታዩ እና አንዲከራከሩ “ሕብ አንዲፈርዳቸው” ለኢሳት ቦር፤ ለዜናው አዘጋጆች እና ለነ ሲሳይ አጋና የተጻፈው ደብዳቤ ሲሳይ እና መሰሎቹ እ ብርሃኑ እና አንዳርጋቸውን ለመከላከል ሲሉ ደብዳቤውን አፍነው ድብደባ እና ግፍ የደረሰባቸው የድርጅቱ አባላት ልቅሶ እና እምባ “የወያኔ ሰላዮች ናቸው” ወያኔ  ናቸው በሚል (ነለገሩ የወያኔ መሪዎችን ንደ ስብሐት ጋን የመሳሰሉ እየጋበ 
አስደምጠውናል እኮ! አይደለም እንዴ?) ከጋዜጠኛነት ሙያ ውጭ ለቀጣሪዎቻቸው የፖለቲካ ቡድን አጋር ሆነው መጥፎ ጠባሳ ከጣሉት አንዱ እና ስማቸውን ካጠፋቸው አንዱ “ሲሳይ አገና” ነው። ያ በሰፊው ተወያበታል: አልመለስበትም።  

እስቲ በቅርቡ የአቻምየለህ ተወዳጁ ‘ሲሳይ አገና’ በቅርቡ ሁለት ዶክተሮችን በእንግድነት ሲያወያይ ስለ ጭራቁ ሌንጮ ድርጅት ምን እያለ ሕዝባችንን በውሸት እንደበከለ ልጥቀስ፡


ሲሳይ አገና በአማራ ጭፍጨፋ ተጠያቂና አገርን በመክዳት (ብዙ ሴ በመጎንጎን) ተጠያቂ የሆነው የቀድሞው የኦነግ አማራር እና የዛሬው ኦነግ ግልባጩ  የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዲግ) ምን እንዳለ ልጥቀስ፤

……በጥቅሉ አንተ እንዳስቀመጥከው ሳይሆን .የብሔር ድርጅት ሆነው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ጥያቄ የሌላቸው ድርጅቶች አሉ፤በቅርቡ የተመሰረተው በዶ/ር መረራ የሚመራው ኦፌኮን መውሰድ ይቻላል፡ እንዲሁም በቀድሞ የኦነግ መሪዎች የተመሰረተው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር እነ ነአቶ ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ችግር በኢትዮጵያ አንድነት ሥር ሆኖ መፍታት ይቻላል የሚሉት፤ሌሎችም አገር ውስጥ  ያሉ በነ ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩ ድርጅቶች፤በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ጥያቄ የላቸውም እና እሱን በተዛባ መንግድ እንዳይሄድ ብየ ነው።”  ሲል ስለ እነ ሌንጮ እና መረራ ድርጀት ሕዝብን ለማሳመን ሞክሯል።

እነ መረራ ጉዲና Oromo Studies Association (OSA) በተበላው የገንጣዮች መድረክ ላይ ተገኝቶ በነበረበት ወቅት ያቀረበው “ኦሮሞ ነፃነት መቃረብ” ስለ ኢትዮጵያ ነፃነት መቃረብ አይደለም የለፈለፈው) ስለ ኦሮሞ ራስን በራስ የመወሰን መብትና/ስልፍ ዲተርሚነሽን/ ከሌሎቹ በማይለይ “ቡዱናዊ /ኦሮማዊ ባለቤትነት/ በሌሎች ኗሪዎች ላይ ‘’ማጆሪቲ ሩል” ለማስቀጠል የተውተረተረውን ትንታኔው ለኛ ግልጽ ነው። ቋንቋ ሳይቀር በታሪክ ምጥቀቱ ሳይሆን ‘በማጆሪቲ/በሕዝብ ብዛትነት’ እየታየ ኦፊሴላዊ ይሁን ባይ ነው። በላቲን ፊደልነቱ ማለቱ ነው።  ሚኔሶታ መጥቶ በነበረበት ወቅት ያሸበረቀው ክራባት እና በስሙ የተከፈተው የጽ/ቤት ቢሮ የተሰቀሉት ባንዴራዎች፤አጃቢዎቹ የክብር ቁልፍ ሲያበረክቱለት የለበሱት የባንዴራ ዓይነት ልብ ማለት ያስፈልጋል። መረራ እና ሌሎቹ ገንጣዮች እንዲሁም ወያኔዎች የሚከተሉት የፌደራል ስርዓት የሚለያዩበት ጥቃቅን  ነገር ነው (ያውም ቢኖር ነው)። ሁሉም አንድ የሚያደርጋቸው “ቡድናዊነት” “ፌዴራሊዝምነት” ብዙሃን በጥቂቶች ላይ የሚወስኑበት የግለሰቦችን/የጥቂቶችን መብት የሚገፍፍ “ዲሞክራሲ” የተባለ አምባ ገነን ሥርዓትን ለማምጣት የሚጥሩ ናቸው። ‘የኦሮሞ ክልል ሃይቅ፤ወንዝ፤ሃብት እና  ጫካ በኦሮሞዎች መተዳዳር አለበት’ ባይ ናቸው።እዛ የሚኖር ኦሮሞ አይደለሁም የሚል ዜጋ ፡ጥገኛ እና በብዙሃን ኦሮሞ ሕግ መተዳዳር አለበት ባዮች ናቸው። ይህ ነው የነ መረራ እኩልነትና አንድነት የሚሉት። ቡድናዊ እና ብዙሃዊ የበላይነት!!!!!!! 

መረራ ግንባር የፈጠረው ከነ ማን ነው? ጸረ አማራ ከሆኑት ከነ በቀለ ገርባ እና ቡልቻ ደመቅሳ አይደለም ወይ? ቡልቻ ደመቅሳ ‘ጀርመን ራዲዮ” ላይ ከነ ክቡር ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ጋር ተጋብዞ ስለ ማራ እና ምኒሊክ የተናገረውን መቸውንም አንረሳም። ጎጃም ላይ/ጎንደር ላይ አማራን ለመከላከል ሕይወቱን የሰዋው አርበኛው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ፎቶ ሳይዘከር በሚያስደነግጥ ሁኔታ  በኢሳት ሰርጎ ገብነት ወይንም ባንዳንድ ውጭ አገር ባሉ ግራ በተጋባቸው የአማራ ወጣቶች ነን የሚሉ የበቀለ ገርባ አወዳሾት የተጠነሰሰ ሴራ የበቀለ ገርባን ፎቶ እንደ ‘ማርቲን ሉተርና ጋንዲ” አድርገው ፎቶው ተይዞለት በአማራዎች የተወደሰው ጸረ አማራ በቀለ ገርባ በነ ሲሳይ እና ታማኝ አወዳሽነት አይደለም ወይ ሕዝቡ እንዲደናገር የተደረገው? የበቀለ ገርባ እና የነ መረራ ዲሞክራሲ መመርመር ያስፈልጋል።

በቀለ ገርባ በወያኔ/በኦነግ ፌዴራሊዝም የሚያምን ነው። እንዲህ ይላል፤ it is only through this  (የጎሳ ፌደራሊዘም) way that we can promote our language, our culture, and our identity. ይላል። ስለ ቋንቋ ተጠይቆ ሲመልስ እንዲህ ይላል። የአካባቢ መነጋገርያ ቋንቋ ካልቻልክ ወይንም ኦሮምኛ ካልቻልክ ፤የራስህ ጉዳይ ነው። ባይ ነው። እንዲህ ይላል፡

'I don’t believe in the idea of the unionists….’  ‘For example people complain that we are not able to work in the regions because we don’t know the language. In the first place you are there because you want to sell your knowledge, your skill and your service, is that not? If I went to Tigray to sell my knowledge, my skill or to sell my expertise then I has to interact with the people who want to be served in the language they understand. Nobody is disallowed to work there. But the only thing is serve these people in the language they understand.” አንድ በሉልኝ።

ክልሎች መከበር አለባቸው፤ አጥሮቹ መጥበቅ አለባቸው፤አንዱ ባንዱ ቦርደር መሻገር፤መርገጥ፤መዝለል የተከለከለ ነው ይላል። አንድ ሕዝብ ከሌላው ጋር መደባለቅ የለበትም ይላል። ይህም የኦሮሞ ክልል እንደ አሜካኖች “ሬድ ኢንዲያ” ቀይ ሕንዶች ወይንም እንደ አውስትራሊያኖቹ ኦበርጂነስ ነገዶች ያመሳስለዋል። እንዲህ ይላል፡
 
“there is a shift when you change the population, when you change the social structure, then the culture and the language will be destroyed. This is how the Australian Aborigines lost their languages, lost their identity, lost their history, and lost everything. This is how Red Indians in North America lost their identity, lost their language and lost everything.”“No single region should be allowed to trespass.” “Constitutionally this country is a federal country but as many people think, this is not a gift from the ruling EPRDF. Federalism evolved or it came out of the situation that existed 24 years ago.” Addis Standard ከተባለው የሰጠው ቃለ መጥይቅ ያገኘሁት።

እነ አቻምየለህ እና የጎንደር/የጎጃም አማራ ሰልፈኞች የሚያሞካሹት በቀለ ገርባ አማራ የሚባለው ጎሳ አማራ የተባለ የገዢ መደብ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር አማራ አልተጨቆነም ይላል። እንዲህ ይላል። “ካንድ ብሔር፤ካንድ ሕብረተሰብ ክፍል የወጡ የገዢ መደብ አባላት ከእነሱ ብሔር ወይንም ከነሱ ጎሳ ክፍል ውጪ ያለውን ሁሉ ሲበዱሉ የነበሩበት ሁኔታ ነበር። በፊት የነበረው ሰርዓት አስተዳደር የአማራው ገዢ አስተዳደር እንደነበር ይታወል፡ ከኛ ጎሳ ውጪ፤ከኛ ቋንቋ እና እምነት ውጭ የሆነ ሁሉ እያሉ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ አማራ ገዢ መደቦች ያደረሱት በደል ከፍተኛ  አንደሆነ ይታወቃል። ከነሱ ጎሳ ውጪ የሆነ ሁሉ ሲበድሉት የነበረው ሁኔታ እንክዳለን ከተባለ ዛሬ ላለው ግንኙነት መልከም የማይሆን።ይህነን እውነት ላለመቀበል ደግሞ አብሮ ለመኖርም ለመነጋጋርም አስቸጋሪ ነው። አማራ ገዢ ነበር፤ይህም አማራውን ለይቶ ሌሎችን ብቻ ለምሳሌ ኦሮሞዎችን አልጨቆነም የምትሉ ከሆነ አብረን አንኖርም፤አንነጋገርም” ይ4ላል በቀለ ገርባ፡ ‘ኦሮሚያን አንመሰርታለን” ነው የገርባ ማስፈራርያ። ከእስር ተፈትቶ ወደ አማሪካ እንደመጣ ከኢሳት ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ ያገኘሁት።

ኚህ እና እነ መረራ….. የመሳሰሉ በፌደራል፤በብዙሃን ይመውኡ (ብዙሃን መግዛት አላባቸው የዲሞክራሲ አስከፊ ገጽታ) ባይ ኦሮሞ ኤሊቶች ወጣት አቻምየለህእና የመሳሰሉ አማራ ወጣቶች ሲሳይ አገናን የማድነቅ መብታቸው የተጠበቀ ነው። እኛም የሲሳይን ሴራ እና ውሸት መቃወም መብታችን ነው። ካሁን በፊት ስለ ሲሳይ አገና የጻፍኩበትን ትችቶች ማንበብ በቀላሉ ሲሳይን ከጋዜጠኛነት ሙያው የሚያወርደው ነው። አፈ ጮማነት እና በአድርባይነት እውነት መደበቅ ከጋዜጠኛ አይጠበቅም።

አቻምየለህ በዚህ አልተወሰነም። አስገራሚ የሆነ ሰሞኑ በእንግሊዝኛ የጻፈው አንድ ትችት አለ። መረራ ጉዲና ታሰረ በሚል ርዕስ። መረራ ጉዲና ማለት አገራዊ (ክልላዊ) የሆነ ፓርለማዊም ሆነ ኦሮሞአዊ ሰሚናር ሲያደርግ  የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ሳይሆን በመኪናው ደቅኖ የሚያውለበልበው፤ እና የሚለብሰው ልብስ ፤ ያው ኦሮሚያ የተባለው በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ዘመቻ በሆነው  ኦነጋዊ/ዓረባዊ ባንዴራ ለጥፎ የሚወዳደረው መረራ ጉዲና በመታሰሩ ሃዘኑን እና ንዴቱን በወያኔ ላይ በጻፈው ሐተታ ውስጥ ወጣት አቻምየለህ ታምሩ እናቶቻችንን እንዲህ ይዘልፋል። (ስለ መረራ ሃዘኑን መግለጹን አልተቃወምኩትም) የተቃወምኩት ጽሑፉ እንዲህ የሚለውን ነው፦
Dr. Merera Gudina wearing the anti Ethiopia flag. If this is not going with the flow of the subversive agenda to downgrade Ethiopian flag I do not know what you will call it. when someone of his caliber, an educated scholar wears banda flags /Fascist Italian designed flags and symbols what will you call such shame? why would someone got into such shame? this is conspiracy against Ethiopian flag designed by OLF and TPLF.

እነኚህ ወንድሞች እና እህቶች ግብጾች፤አረቦች ወይስ ኢትዮጵያዊያኖች ናቸው? መለያቸው አርማቸው ምንድ ነው? እውነታው እንነጋገር አንጂ! ማን ማንን እያሞኘ ግምባር አንፍጠር ማለት ይችላል? ሴራው ሳይደበቅ በዓይናችን እያየነው?

How cursed is the womb that conceived the weyyanes!? by Achamyeleh Tamiru በሚል ርዕስ “Over the past month alone they have arrested more than 30,000 Amhara and Oromos teenagers from their homes in the middle of the night. How is cursed is the womb that conceived these. Tigray heinous wild animals, the lunatic called weyyanes, and How cursed are all the evil hands that raised them. Sardonic sadist grin womb!” ሲል ቁጣውን እናቶች ማህጸን ያወርዳል። የወያኔ እናቶች አብዛኛዎቹ ከማሳ እርሻ ፤ከአፈር ጋር የሚታገሉ ‘ፖለቲካ የማያውቁ’ ከድሃ ገበሬዎች እናቶች ማሕጸን የወጡ ናቸው። ብዙዎቹ ደግሞ ተገድደው የተመለመሉ ናቸው። ይህ ተዘንግቶ እናቶችን መዝለፍ ለምን አስፈለገ?

እንዲህ ያለ ቁጣ ለምን እቃወመዋለሁ? ብዙ ሰዎች ዘለፋውን አግባብነት አለው  ሊሉ ይችላሉ። በተለይም የተቈጡ ከፍሎች። ግን አቻምየለህ ብቻ ኣይደለም በወያኔ የተቆጣው። ሁላችንም በወያኔዎች ተጎድተናል፤ ቤተሰቦቻችን ጓደኞቻችን ታፍነው ተሰውረዋል፤ በእሳት ተቃጥለው ሞተዋል፤ተሰቃይተዋል። ግን ቁጣው ወዴት ነው እየዞረ ያለው? እስኪ የአቻም የለህ ቃላቶች እንተርጉማቸው።
 Sardonic ማለት "bitter, scornful, mocking."

Grin ማለት ደግሞ smile broadly, especially in an unrestrained manner and with the mouth open.

A sadist ማለት is someone who enjoys inflicting pain on others, sometimes in a sexual sense. Sadists like seeing other people hurt. A sadist is the opposite of a masochist, who enjoys being in pain. A sadist is all about hurting others, usually to get off sexually. However, this word is about more than sex.

እንግዲህ አቻምየለህ ታምሩ የትግራይ ወያኔ የወለዱ እናቶችን ማህጸን ከላይ በተጠቀመባቸው ቃላቶች ትርጉማቸው ተመልከተናል። የኔ እናትም ሆነ አባት የወለዱን ወንድሞች፤እህቶች ዘመዶች በሁለት ጎራ ተከፍለን ነበር። ወጣት ሆነው ምንም ፊደል ሳይቆጥሩ በልጅነታቸው ወደ ወያኔ በረሃ ገብተው የታገሉ እዛው ያደጉ ወንደሞችና ዘመዶች አሉኝ። ለኔም ለወንድሞቼም/እህቶቼም/የወለደች ማህጸን እና አጥብታ የመገበች እጅ አንድ እናታችን ነች። ይህች እናት ወደ ወያኔ በኮበለሉ ጅሎች ምክንያት “sadist Sardonic እና ቀዳዳ/ክፍት አፍ Grin ተብላ How cursed are all the evil hands that raised them. Sardonic sadist grin womb! ተብላ ትሰደብ ወይንስ እኔን በመውለዷ ትመስገን/ትወደስ? ይህች ማህጸን በማን ፈራጅ እና ዳኛ እጅ ውስጥ ትግባ? ቁጣችን እየተስተዋለ ቢሆን አዋቂነታችን ተቀባይነት ይኖረዋል።

ወደ ወቅቱ ሁኔታ ልውሰዳችሁ። ወደ ኦሮሞዎቹ ፖለቲካ!!!!!!!!!!!!!!!

በወዳጄ በዶክተር አሰፋ ነጋሽ ስለ ጎሰኛነት ምንነት እና መላውን ሕዝብ ልቦና ሰውሮ እንዴት እንደሚያሳውር እና እንደሚያሳብድ ምሁራዊ ትንተናው አንዲህ ሲል ይገልጸዋል ፡

Ethnic nationalism introduces the psychology of collective narcissism that blinds its fanatic followers from becoming aware of the social reality they live in.” አሰፋ ነጋሽ (ዶክተር (ሓኪም እና የስነ ኣእምሮ እስፔሲያሊሰት)

ባጭሩ የመልእክቱ ይዘት ‘የጎሳ (የጎሳ የጥላቻ)ፖለቲካ የመከተል ጠንቁ የማሕበረሱን ጤነኛን አስተሳሰብ በመጋረድ በተከታዩ ማሕበረሰብ ላይ የጋርዮሽ ዕብደትን የሚያስከትል ሕሊናን የሚያሳውር አስተሳሰብ ነው።” ይላል ዶክተር አሰፋ።  ብዙ ሰዎች የኦሮሞዎች ከኢትዮጵያዊነት ማፈንገጥ ያልተዋጣለቸው አሉ። ኦሮሞዎች ካፍንጫቸው ርቀት ማሰብ በማይችሉ ትንንሽ ሰዎችና ወንጀለኞች ተታልለው ከሦስት እና አራት  ዓይነት የራሳቸው ባንዴራ አስሰፍተው፤ ከሕግ ውጭ ወያኔ ጋር ተረሻርከው እንደ ኮሎኒ/የቅኝ ግዛትና ‘የመሬት ንጥቂያ’ አይነት ይዘት ያለው ሴራ በማጽደቅ ‘አገር’ ብለው የሚጠሩት የራሳቸው የሆነ ኦሮሚያ የተባለ ቅዠት ውስጥ እየዋዠቁ እንዳሉ ብዙ ጊዜ እኔ እና ጥቂት አገር ወዳዶች አስቀድምን ለማስጠንቀቅ ሰንጥር ብዙ ጀሮ የሰጥን አልነበርም። በቪዲዮ፤በንግግር፤ በፎቶግራፍ፤በሰርግ፤በስብሰባ ቁልጭ ብሎ በማስረጃ የታየ ነው። አይደለም እንዴ?  ዛሬ ግን ዓይን አፍጥጦ የሚታይ እውነታ እየታየ ስለመጣ “አፋችሁን ዝጉ” ሱሉን የነበሩ “ምሁራን ተብየዎች እና አንዳንዱም አማራው ኦሮሞውን ይቅርታ መጠየቅ አለበት” እያሉ ሲጽፉ የነበሩ (አንዳንዶቹ እንዲህ ከጻፉት ውስጥ አማራዎች ይገኙበታል። ካሁን በፊት ይህንን በሚመለከት ተነጋግረናል) ፤ ዛሬ ግን አንዳንዶቹ ከእንቅልፋቸው በማባነን ወደ እውነታው እየመጡ ነው።

ይህ አስደሳች ቢሆንም፡ በጥቂት ሴረኞች ምሁራን ምክንያት በተለይ እንደ ዶክተር ዜሮ (የግንቦት 7 እና የኦነግ አለቅላቂ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው) እንደ ካሳ ከበደ፤ አንደ የደርጉ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ እና የመሳሰሉ የኦነግና የሻዕቢያ አለቅላቂዎች ኦሮሞዎች ግንጣላን አቁመዋል እያሉ “ኦ ዲ ኤፍ” የተባለ የኦነግ ህቡዕ ቅርንጫፍን በምሳሌ እየጠቀሱ በማታለል ብዙ ሞኝ አሁንም እያንጨበጨበላቸው እያየን ነው። እውነታው እንንጋገር። ሲሳይ አገና ከላይ በአንደበቱ እንደገለጸው ከነሱ አንዱ ዲስኩር ነፊያቸው ነው። ሰሞኑ Ethiopatriots.com ጥሩ የሆነ ስዕላዊ ማስረጃ በድረገጹ አቅርቦልናል። እዚህ ላይ ተውሼ ብለጥፈው ሰዎች የግንቦት7 እና የኦነግ ርካሽነት (በተለይ የግንቦት 7 ርካሽነት) በጉልህ ልትረዱ ትችላላችሁ።

 
The conspiracy of Ginbot 7 and the anti Amhara ethnic cleansing criminal  hatemonger  Lencho Leta

 እንዲህ ያለ ውርደት፤አንዲህ ያለ ሴራ፤ እንዲህ ያለ አሳፋሪ እና የልጆች ጨዋታ አይታችሁ ታውቃላችሁ? አዎን አንዴ ስያትል ላይ ተደርጎ ነበር። ኦነግ ባንዴራ ካልተውለበለበ የኢትጵያ ባንዴራም ከመውለብለብ ይቅር ተብሎ ስብሰባው ያለ ምንም ብሔራዊ ሰንደቃላማ ስብሰባ መካሄዱ ደጋግሜ ከጥቂት አመታት በፊት ገልጬ እንደነበር ታስታውሳላች ። አሁን ያንኑ ዓይን ባወጣ ድፍርት ፖዲዮሙ ላይ መዘርጋት የነበረው የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ሌንጮ እንዳይቀየም፤ ሌንጮ የአቢሲንያዎችና የኮለኒያሊስቶች የሚላትን ሰንደቃላማ እጄ እንዳይነካት ብሏቸዋል መሰለኝ፤ የመነጋገሪያው ሰገነት/ፖዲየም በካርቱን ወረቀት ተሸፍኖአል።ድሃ በሚባለው አፍሪካ ምድር እንኳ በካኪ ወረቀት መነጋገርያ ተሸፍኖ ታይቶ አይታወቅም። ። ይህ የጉድ ጉድ ታሪክ ጸሐፊዎች እና ተቺዎች ብዙ ሊሉበት የሚገባ ድርጊት ይመስለኛል።

 ድሮም ቢሆን ፣የግንቦት ሰባቱ ንዓምን ዘለቀ የተባለው፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እና የኢትዮጵያ አንድነት ብቻ ሲባል ሶፎኬት ያደርገኛል” የሚሉን፤ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስሟ ሲነሳ ትንፋሻቸው ከሚያፍናቸውና ከምያስነጥሳቸው ጉደኛ ሰዎች የሚያዘጋጁት መድረክ ‘ብሔራዊ ሰነደቃላማችን ፖድዮሙ ላይ የወለጋ ናዚው የሌንጮ ቆዳ አንዳይነካ በካርቱን ቢጠቀለል”  ቢገርምንም፤ ከዚህ ሌላ ከግንቦት 7 ምን ገንቢ ታምር ይጠበቃል? 

የሻዕቢያው ቱልቱላ ነፊ ጋዜጠኛ እና ግንቦት 7 መሪው ብርሃኑ ነጋ… ሌንጮ ለታና ድርጅቱ በኢትዮጵያዊነት ምንም ብዥታ የላቸውም ቢሉንም እኛ አንቀበላቸውም። ሌንጮ አንድ ግሩም ጸሐፊ እንዳስቀመጡት ሌንጮ ለታ ከወያኔ ጋር ኢትዮጵያን የገነጠለውን ሕገ መንግሥት ያወጣ ነው፣አሁንም ውስጡ ኦነግ፣ላዩ አስመሳይና አታላይ ዴሞክራት፣እኛን መናጆና አጃቢ አድርጎ የበለጠ ለመበጣጠስ የመጣ እንደሆነ ይግባን።” ሲሉ በትክክል አስቀምጠውታል። አንዲያውም ይሉና........

ሌንጮ ባቲ የተባለው የኦዴፍ አማራር ሌላው አስመሳይም ((ራስን በራስ ከመወሰን እና ከፌደራሊዝም ምንም ንቅንቅ አንልም” የሚለን የዱሮው ኦነግ አማራር ሌንጮ ባቲም የዚህ ድርጅት አመራር ነው)ኢትዮጵያዊነት አለወይ፣የለም’’  ብሎ አፉን ሞልቶ የሚናገር ነው። እነ ብርሀኑ ለሚደግፏቸው ተገንጣይ ቡድኖች አማራውን የሥልጣን መረማመጂያና የህልውናው መጥፊያ ማድረግ ነው። እነኚህን ኢትዮጵያን የከዱ ሰዎች አቅፎ ነውግንቦት ሰባት ነን፣ እንዋጋለንእያሉ፣ከብዙሀኑ የዋህ አማራ ገንዘብ እየወሰዱ በምዕራቡ አማላጅነት ሊወድቅ ከሚንገዳገደው ከነፍሰ ገዳዩ ወያኔ ጋር ሥልጣን ለመቀራመት ላይ ታች ሲሉም የሚሥተዋሉት።ይላሉ እኝህ አስተዋይ ወገን።

ሲሳይ አገና እና ኢሳት/ግንቦት እያደናገሩዋችሁ ያለውን የሌንጮ ባንድ ኢትዮጵያ ጥላ ስር መርሆውን እንመልከት።

አዎ ኦዴፍ ማለት በሌላ ገጽታው ዞር አሉ አልሸሹም ‘ኦነግ’ ማለት  ነው። ኦዴፍ እነማን ናቸው? ዓላማቸውስ ምንድ ነው? አርማቸውስ ምን ይመስላል?  ኦዴፍ የመሰረቱት አብዛኛዎቹ ከላይ የተጠቀሱት አማራን ያስጨፈጨፉና ኢትዮጵያን ‘ቅኝ ገዢ’ እያሉ በመፈከር ብዙ ወጣቶችን ያሳሳቱ ወንጀለኞች ናቸው።  ታዲያ እነ ሲሳይ የሚሰብኩን “በኢትዮጵያ አንድነት ብዥታ የላቸውም” ሲሉን ምን ማለት ነው? ያገሪቱን ሰነደቃላማ የማያምኑ፤የማይቀበሉ፤ ግማሽ አገር ኦሮሞ ብቻ በባለቤትነት የሚሰጥ የኮሎኒ “ሄጂመኒ” (ገፈፋ፤ንጥቅያ፤ዘረፋ፤አመጽ………) ለማስከበር የሚታገል ቡድን “በምን መለኪያ እና ሂሳብ” ብዥታ የላቸውም እያሉ ሕዝብን ያደናግራሉ።

አርማቸውም ከላይ በፎቶ አስደግፎ እየታየ ያለው የኦነግ ባንዴራ ነው። ኦሮሞ ብለው የሚጠሩት ቦታም ከሕግ ውጭ የተሰራ ካርታ/የመሬት ቆዳ በሰፊው የተንጣለለ ‘ኦሮሞ ነን” ለሚሉ ‘ብቻ፤ በባለቤትነትና አዛዥነት የሚሰጥ ነው። እምነታቸውም፤ ከተለያዩ ቃለ መየጠይቅም ሆነ ከድርጅታቸው ደምብ እና አምነት የተገኘም ቢሆን፤ ከላይ የጠቀስኩትን ሁኔታ የሚያጠናክር እና ኦነግ በፕሮግራሙ ለበርካታ አመታት ቀርጾ የታገለላቸው እና “ግብ መትነናል” የሚላቸው አፍራሽ ግቦች ሁሉ ለወደፊቱም አንደሚቀጥሉ የሚታገል ነው። 

ፍንፍኔ’ እያሉ የሚጠሯት አዲስ አበባም ለወያኔው በቅሎ ለሃይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ ሲጽፉለት “ፍንፍኔ/አዲስ አበባ ከተማ የኦሮሞ ሕዝብና መሬት ስለሆነች ወደ ኦሮሞነት ይጠቃለል” ሲ.ል አቤቱታ ያቀረበ መሰሪ ጠባብ ድርጅት ነው። ይህንን አንብቡ  I appeal to you to show leadership by addressing the country and taking the following measures: ü Unequivocally declare that Addis Ababa (Finfinne) is an integral part of the Oromia National State, that also serves as the seat of the federal government;” Open Letter to Ethiopia’s Prime Minister Hailemariam Dessalegn ours truly,Leenco Lata, President
Oromo Democratic Front (ODF) 

እንዲህ ያለ አሁንም በቆሸሸ ጠባብ ጭንቅላትና በመሬት ቀርምትና ነጠቃ የሚታገሉ ግለሰቦችና ድርጅት ነው በኢትኦጵያ አንደነት ተሰልፈዋል፤ ብዥታ የላቸውም እያሉ በብክላ ቅስቀሳ እየተሰማሩ እያሞኟችሁ ያሉት። ልቦናችሁ እና ዓይናችሁ ከጊዜአዊ ስሜት ወጥቶ በጥሞና ሁሉንም መመረምር ያስፈለጋል። እነኚህ ዞር አሉ አልሸሹም ቡድኖች በቡድንተኛነትና ወገንተኛነት የሰከሩ ዕብዶች ናቸው። መፈወስም/መዳንም አይችሉም “የተበከሉ ናቸው” ‘’They are contaminated”.

አሚን ጀንዳይ የተባለው ሌላው የዚህ ድርጅት ቀላማጅ እና በኢትዮ ሚዲያ አዘጋጅ “ብርለያንት” ተብሎ የተወደሰለትም ቢሆን እሱም ኦዴፍን እየወከለ ዛሬ የተናገረው ነገ የሚቃረን በውሸት የተበከለ አደገኛ አሳሳች ሰውም ያው የምታውቁት ነው። ካሁን በፊት ስያትል ላይ እነ አበርሃ በላይን አስቁሞ በስሜት ያስጨበጨበ ከኦዴፍ የውሸት ቀፎዎች መካካል አንዱ ነው።
Abraha Belay at the corner side clubbing his hands approving liars propaganda
 እስኪ ስያትል ውስጥ ከነ ዶክተር አረጋዊ በርሀ ጋር ከእነ ብርሃኑ ነጋ እና የመሳሰሉ ጋር ተጋብዞ የዋዠቀው ከማሕደር መዝዤ እንደገና ላስደምጣችሁ። እነ አበርሃ በላይን ያስጨበጨበ የአሚን ጃንዳይ የውሸት ዲስኩር እንዲህ ይላል።
ኦጋዴኔ፤ ከኦሮሞው፤ኦሮሞው ከትግሬውም ጋር አንድ አገር እንመስርት ብሉ አልተፈራረመም። አንዲህ ያለ አገር እንመሰርት ብኦ የተፈራመበት ወቅት አልነበረም።የተፈራመበት ሰነድ የለም! ታዲያ ኦሮሞ ከማን ነው የሚገነጠለው?! ከማን ጋር ነው የሌለ ፌርማ ለመበጣጠስ የተዘጋጀው? የኖሮው በቄዩ፤ያለው በቄዩ! ማንን ወረረ፤ማን የማንን አገር ወሰደ?        ይልና
 ስለዚህ……..የኦሮሞ ጥያቄ ወደ መገንጠል ጥያቄ የሚወስዱት ሃይሎችም ሆኑ ቡድኖች መሰረታዊ መፍትሔ ላለመስጠት የተደረገ ጉዳይ እንጂ “ኦሮሞ ልገንጠል ብሎ ኦሮሞ ሕዝብም ሆነ የኦሮሞ ነጻነት ደርጅት ጠይቆ  አያወቅም፤አልተናገረም”። የተናገሩትም፤የጻፉትም ካለ አለ የሚሉ ሰዎች ካሉ እስከነመረጃቸው መምጣት ይችላሉ።””

ብሎ ያለምን ይሉኝታ የውሸት አቅማዳው ከከፈተ በሗላ በስሜት የሚነዱት እነ አብርሃ በላይ አዳራሹ ውስጥ ከመቀመጫቸው ተነስተው ሲያንጨበጭቡ ይታያሉ፤ይደመጣሉ።

ታዲያ የ ኦሮሞ ጥያቄ ምነድ ነው ብሎ ከጠየቀ በላ ያው የተለመደው ኦነጋዊ ፖሊሲያቸው ብዙሃን በጥቂቶች ላይ የሚሰብክ ጥያቄ ነው። እንዲህ ይላል፤

“በራሱ ሃብትና መሬት አዛዥና ባለቤት  ሆኖ የመጠቀም መብቱ እንዲከበር ጥያቄ ነው። እነኚህ የተፈጥሮ ሃብቶች የኦሮሞ ባለቤት ብቻ አይደለም ብለው የሚጻረር መንገሥት፤ግለሰብም  ሆነ ድርጅት ‘ጸረ አንድነት፤ጸረ እኩልነት፤ጸረ ነፃነት ነው። ብለን እናምናለን።” እነኚህን እውነታዎችን ሳናከብርና ሳንቀበል ‘ስለ አገራዊ ሉአላዊነት አና ኣነነድት ማውራት ዘበት ነው።” ‘’በእኛ አምነት (በኦሮሞ የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶች በሙሉ ሃበት አሮሞው አዛዥና ባለቤት መሆን)እነዚህን ማክበር ለሃገር ሉዓላዊነትና መብት ዋስትና ናቸው።” ኦሮሞን ጥያቄ ለማሳነስ ‘መገንጠል’ (ተገንጣዮች) የሚሉን ሆን ተብሎ ትክክለኛውን ጥያቄአችን ለመመለስ የማይፈልጉና ሆን ተብሎ ከኢትዮጵያ አንደነትጋር ለማስተባበር የሚሹ ሃይሎች ናቸው ብለን እናምናለን።” ስለሆነም፤ ኦሮሞ በቀዬው ለዘመናት የኖረ እንጂ ከማንም ጋር አንድ አገር ለመመስረት የተፈራረመበት ፎረም የለም።አንዲህ ያለ አገር እንመሰርት ብሎ የተፈራመበት ወቅት አልነበረም።የተፈራመበት ሰነድ የለም! ታዲያ ኦሮሞ ከማን ነው የሚገነጠለው?! ከማን ጋር ነው የሌለ ፌርማ ለመበጣጠስ የተዘጋጀው? የኖሮው በቄዩ፤ያለው በቄዩ! ማንን ወረረ፤ማን የማንን አገር ወሰደ?” ያልሆንነውን ናችሁ ተብለናል፤ያልጻፍነውን ያልተናገርነውን ተናግራችሗል፤ ጽፋችሗል ተብለናል። ኦሮሞን ሕዝብ ብሶት የወለደው ኦነግ ከላይ የተጠቀሱ መብቶች ለመጠየቅ እንጂ የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ ብ አያውቅም።”

ሲል አቶ አሚን ጃንዳይ እነ አብርሃ በላይ ስያትል ውስጥ በስሜት እና በውሸት ካስጨበጨባቸው በላ፤ እኔ በማግስቱ የኦነግ የመገንጠል አጀንዳ ከድረገጹ ላይ የተለጠፈው በመቅዳት በጽሑፍም በቃለም በማስረጃው አስደግፌ ለብዙ ሚዲያዎች እና በኔው ድረገጽ ላይ ከለጠፍኩ በሗላ “ነገሮችን በጥሩ አማርኛ የማደናገር ችሎታ ያለው አምታቺው አሚን ሳይውል ሳያድር ፤ውሸቱ ሳይበርድ፤ ሕብር ለተባለው ቬጋስ ውስጥ እንዲህ ሲል የራሱን ውሸቱን በራሱ ጅራፍ ሲገርፈው ላስደምጣችሁ።

ሕብር ራዲዮ;-       
  “እስኪ ይህ አዲስ የኦነግ አቋም ግልጽ ያድርጉልኝ?”

አሚን፤;-              
 “አነጋጋሪ የሆነው የኦሮሞ የመገንጠል ጉዳይ ነው። ይህ አመለካካት ካሁን በላ (የመገንጠል ጥያቄአችንን አናነሳውም) የኛ ድርጅት ከሌሎች  በሔር  ፤ብሄረሰቦች ጋር በጋራ ሆኖ በመስራት ኦሮሞ ችግር ለመፍታት ይቻላል ወደ ሚለው ሃሳባችንን በመቀየር  አብረን ለመኖር .ወደ እዛ ነው የተቀየረው። ግን…..እስካሁን ድረስ ኦሮሞ ነጸነት ድርጅት ታግሎ ያስገኛቸውን ትላልቅ ድሎች ይዘን በመቀጠል ለሌላ ትልቅ ውጤት እንድናስገኝ እንዲያስችለን ነው ይህ ድርጅት የመሰረትነው።” በማ  የመገንጠል ጥያቄ ጠይቀን አናውቅም ሲል የዋሸውን እና ባለስሜቶችን አስጨበጨበውን ውሸቱን ሳይውል ሳያድር “የመገንጠል ጠይያቄ እንጠይቅ ነበር” ሲል አምኗል። 

በተከታታይ ሰሞን ሁሉም አመራሮቹ “የመገንጠል ጥአቄአችንን አቁመናል” ሲል አስደመጡን። አንዲህ ያሉ በውሸት የተበከሉ፤ተንኮለኞች፤አወናባጆች እና ሐፍረት የማይሰማቸው፤ይሉኝታ ያማያስፈራቸው ግለሰቦች የሚመሩት ደርጅት ነው  አሁን ግንቦት 7ም ሆነ ኢሳት የተባለው ውዥምብራም የዜና ማዕከል ኢትዮጵያዊነታቸው ብዥታ የላቸውም፤ እያሉ የፖለቲካ ግምባር ተፈጥሮ ሕዝብን ለማታታል እየተሞከረ ያለው። ኦነግም፤ኦዴም በሉትሰንደቃላማቸው፤ ላቲናቸው ፖሊሲያቸው፤ግባቸው ፤ወንጀላቸው፤ውሸታቸው፤ተንኮላቸው አልተቀየርም፤ያው ኦነግ ወያኔ፤ወያኔ ኦነግ ነው። እስካሁን ኦነግ ያስገኛቸው ድሎን ሳንጥል ለወደፊቱ የኦነግን ድሎች እናስከብራለን ሲሉ በግልጽ እየነገሩን ነው። በመግለጫቸውም በግልጽ ተቀምጧል። ስለሆነም፤ ሕብረት ከነማን ጋር? ሰንደቅ ከቀየሩት፤ማንነታቸው ከጣሉ? ኢትዮጵያን በጠላትነት ከፈረጁ? በመሰረታዊ እሴቶቻችን ላይ መደራደር የለም!!!!!!!!!!  ካለፈው ቂልነት እአ ኪሳራ እንማር!!! በሚቀጥለው ሰሞን ሌላ አንገብጋቢ የሆነ ርዕስ ይዤ እመለሳለሁ።ሰላም ሰንብቱ ጌታቸው ረዳ Editor Ethiopian Semay    getachre@aol.com