ለጠ/ሚኒስትሩ አድርሱልኝ...
ግርማ በላይ (Ethio Semay) 10/27/2019
Abiy Ahmed the thuggish Hutu look a like leader of the Oromo in Ethiopia. He is a treacherous thug and a clear danger to Ethiopia. |
ለየትኛው ጠ/ሚኒስትር እንደማልባል ተስፋ አለኝ - ለዶ/ር አቢይ
አህመድ ማለቴ ነው፡፡ ሀገራችንን እየመራ ያለው የአጋንንት መንጋ ተቆጥሮ ስለማይዘለቅ ለማን እንደጻፍኩ ግልጥ ይሆን ዘንድ ነው
ይህንን ማለቴ፡፡
ዶ/ር አቢይን በአካል ባገኘው ብዙ
የምጠይቀው ጥያቄ ነበረኝ፡፡ የተወሰኑትን እዚህ ልጠይቅ፤ የሚሰማኝንም ልንገረው፡፡
- ወደ ውጭ ሀገር በተጓዘ ቁጥር ሀገር
ውስጥ ችግር የሚፈጠረው ለምንድን ነው? ይህ ነገር በዕቅድና በተሰናሰለ ጥናት ይደረግ ይሆን? እዚህ እያለ ለምን አይሆንም - መሆን
ካለበት፡፡
- የፖለቲካ ዱላው ከዘር መርጦ አማራን፣
- ከሃይማኖት መርጦ ኦርቶዶክስን፣
- ከዕድሜ መርጦ ትልልቆችን፣
- ከባህል መርጦ የጋራ ዕሤቶችን፣
- ከዓርማ መርጦ አረንጓዴ ቢጫና ቀይን....
- በተለዬ ሁኔታ የሚያጠቃው ለምንድን
ነው?
-
- ይህንንስ አካሄድ አቢይ አያውቅም
ወይ? ካወቀስ ዝምታውና “ትግስቱ” ገደብ ያጣው ለምን ይሆን? የብዙ ስብዕናዎች ባለቤት የሆነው ዶ/ር አቢይ ከገባበት የተዘበራረቀ
ሁኔታ በአፋጣኝ ካልወጣ ተያይዘን እንጠፋለን - ትንሣኤያችን ባይቀርም ብዙ ሊያለፋን ይችላል፡፡
-
-
- ጠ/ሚኒስትሩ ጃዋር ምን እየሠራና
እያሠራ እንደሆነ ጠንቅቆ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአደባባይ እንዲህ አገር ምድር እያነደደ ምንም ሳይሆንና እንዲያውም ጥበቃ
እየተደረገለት ሳለ የአማራን መብት ለማስከበር በሚል የሚንቀሳቀሱ ደካማና አቅመ ቢስ አክቲቪስቶችንና በወፌ ቆመች ደረጃ የሚገኙ
ፖለቲከኞችን በሻማና በኩራዝ እየፈለገ ወደ ዘብጥያ ማውረድ ምን ዓይነት ካርማዊ ጽላሎት በራሱ ላይ ሊያከማችና መጨረሻውን ሊያበላሽ
እንደሚችል አቢይ አያውቅምን? በሀገር ደረጃ ህግና ፍትህ ርትዕ ቢኖሩ ኖሮ ክርስቲያን ታደለ “የአማራ ወጣት መደራጀትና መብቱን
ማስከበር አለበት” በማለቱ ብቻ በሀሰት በተቀነባበረ የክስ መዝገብ ለእሥር ከተዳረገ “ጠ/ሚኒትስሩ ካላነጋገረን ሀገርን ድምጥማጧን
እናጠፋለን፡፡ በአካባቢያችን ክርስቲያን አንገቱን ቀና ቢያደርግ በሜጫ እንቆርጠዋለን፤ ሽማግሌ ልከንም ቢሆን የኢትዮጵያ ገዳዮች
ጋር ታርቀን ይህን ለውጥ እንቀለብሳለን፣....”” የሚል አፄ በጉልበቱ መሀል አዲስ አበባ ላይ በመንግሥት በጀት ሲፏልል ቢገኝ
ምን ይደርስበት ነበር? (የዚህን ታሪካዊ ዕንቆቅልሽና ምፀት አጸፋ ለመቀበል አቢይና ቡድኑ ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምንም
ዕዳ ሳይከፈል አይቀርምና! ከምላሤ ፀጉር ይነቀል በቅርብ ይከፈላሉ፡፡ ደምና ዕንባ በዝቷላ! ፈጣሪ ደግሞ ፍጡራኑን መቼም ቢሆን
አይረሳም፡፡)
- ጠ/ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ከሚያጠፉ
የውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እንዳለው ወይም እንደሌለው እንደምን ማመን ይቻላል? በሌሎች ላይ በግልጽ እንደምናየው በርሱም ላይ
የግብፅና የዐረቦች ጥላ እንዳጠላ ወይ እንዳላጠላ እንዴት እንወቅ? (ለነገሩ ብናውቅ ባናውቅስ ምን ማድረግ እንችላለን! እርግማኑ
ካልከሸፈ ዐይናቸውን እንዳልገለጡ ቡችሎች ነን፡፡)
-
- በናዝሬትና በደብረ ዘይት ዜጎች
በዘራቸውና በእምነታቸው ምክንያት ሲገደሉ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ገዳዮቻቸውን ሊያባርሩ ሲነሱ መንግሥትና የፀጥታ ተቋሙ ተባብሮ
ከቄሮዎች ጋር በመቆም ንጹሑን ዜጋ ለምን ያጠቃል? ይህንን የግፍ
ግፍ አቢይ አያውቅም ወይ? ካወቀ እንዴት አስቻለው? የታሪክ ተወቃሽነትን እንዴት ሊችለው ነው? ይህ ዓይነቱ ፍርደ ገምድልነት እርሱን ከመሰለ የዕውቀት ጌታ ይጠበቃል ወይ?
-
-
- አቢይ የሚሾማቸው ሁሉ በግድ የፕሮቴስታንት
እምነት ተከታዮች መሆን አለባቸው ወይ? ይህች አገር የሁሉም አይደለችምን? እንኳንስ ባለሃይማኖቱ ሃይማኖት የለሹስ የዚህች ሀገር
ዕጣ ፋንታ ይመለከተው የለምን? ዘርና ሃይማኖት ተመርኩዞ የሰው ግርድና አመሳሶ ማውጣት የኋላ ኋላ አጥፊ ነው፡፡ ትምህርትንና ችሎታን
ወደ ጎን ትቶ በሌላ ሌላ ማዳላት ትርፉ ኪሣራ ነው፡፡
በመጨረሻ አንድ መሠረታዊ ነገር ልጠቁም፡፡ በሌሎች ሀገራት እንደምንታዘበው
በሀገር ውስጥ አንድ ችግር ሲፈጠር ለሥራ ወደ ውጭ የሚሄድ መሪ ጉዞውን ይሰርዛል ወይም ለሌላ ጊዜ ያዛውራል፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ
ጉዞውን ጀምሮ ከሆነም አቋርጦ ወዳገሩ ይመለሳል እንጂ በመጣ ይምጣና በትዕቢት ወይም “‹ለሥልጣኑ ፈርቶ ነው የተመለሰው› ይሉኛል”
በሚል የአሉቧልተኞች አቃቂር ተሸንፎ በዚያው ቀልጦ አይቀርም፡፡ ቤቱ እየተቃጠለ ሽርሽር የሚያምረው አባውራ ካለ አባውራነቱ ባፍንጫ
ይውጣ፤ ትልቅ ነውር ነው፡፡ የድሆች ነፍስ ከሀብታሞች ቁጥር የማይገልጸው ዶላር የበለጠ ይመዝናል - ይህን እውነት ብዙ ነገር እንደሚያውቅ
ለምገምተው አቢይ መንገር አይገባኝም ነበር፡፡ ስለሆነም በሰሞኑ የዜጎች ግድያና የንብረት ውድመት ጠ/ሚኒስትሩ በዚያው ሸፍቶ ከርቀት
መከታተልን መምረጡ የሚጠቁመው ብዙ ነገር ቢሆንም ለተራ ታዛቢ ግን ወሰን አልባ ግዴለሽነቱን ነው - አቢይ ደግሞ ለሰዎች ሕይወት
ግዴለሽ ነው ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ይመስለኛል - ይህ ጠባዩ ዕንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ - ሌላው ቀርቶ ባለበት ሀገርም ሆኖ (የሀዘን)
መግለጫ አልሰጠም - ሰጥቶም ከሆነ ይቅርታ፡፡ የራስ መተማመን ገደቡን ሲያልፍ ለከፍተኛ ትዝብት እንደሚዳርግ ጠ/ሚኒስትሩ ሊገነዘብ
ይገባል፡፡ “ማንን ይዞ ጉዞ” ይባላል፡፡
በተረፈ የጃዋር ጉዳይ በፈጣሪም እጅ የተያዘ ስለሆነ ወደዚያ ገብቼ አልዳክርም፡፡
ሀገራችንን ይቅናት፡፡ ከተደገሰላት ዕልቂትም በፍጥነት ይታደጋት፡፡
No comments:
Post a Comment