Thursday, January 31, 2019

ኢትዮጵያን ያያችሁ “ና ወዲህ” በሉኝ! አሁን የት ናት? ዳግማዊ ጉዱ ካሣ - Ethio Semay


ኢትዮጵያን ያያችሁ “ና ወዲህ” በሉኝ! አሁን የት ናት?
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

በሁሉም ቦታ ውጥረት ነግሦኣል፡፡ ሰላም ያለችው በአንደበትና በመንግሥት ሚዲያዎች ብቻ እንጂ በተግባር የለችም፡፡ ሀገር በከፍተኛ ፍጥነት እየፈራረሰች ባለችበት በአሁኑ ሁኔታ ሕዝቡም ፀጥ ረጭ ብሎ የመርከቢቱን መስመጥ በትግስት እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡  በትብታብ የተያዝን ይመስል (ተይዘንም ሊሆን ይችላል) ሁላችንም ፈዘንና ደንግዘን እንገኛለን፡፡

ተመልከቱ - ስግብግብ ነጋዴዎች በጀሶና በሴጋቱራ እንጀራ ሆዳችንን እየቆዘሩ ላልታወቁ በሽታዎችም እየዳረጉን ሆስፒታሎችንና መቃብር ሥፍራዎችን እያጨናነቅን እንገኛለን፡፡ የግል ሀኪም ቤቶች ወላዶችን እያስፈራሩ በኦፕሬሽን እንዲወልዱ በማድረግ ልጁንም እነሱ የሰጡ ይመስል ሃያና ሠላሣ ሽህ ብር በደቂቃዎች ይዘርፋሉ፡፡ የህክምናው ዘረፋና ማምታታት ወደር አይገኝለትም፡፡ በአንዳንዶች ለካርድ የሚከፈለው ብቻ በሽዎች ነው፡፡ ለአንድ ቀን አዳር የሚያስከፍሉት ከሼራተን የአንድ ቀን መኝታ ይበልጣል፤ ግብር የሚከፍሉት ግን በሆቴል ሣይሆን በህክምና ነው፡፡ ገንዘብን የሚያመልክ ሀገርም ወገንም ማተብም አመዛዛኝ ኅሊናም  የለውም፡፡ ባጭሩ ሥሪቱ ከጅብና ከዓሣማ እንጂ እንደሰው ሰው ከተሠራበት ቀመር አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰው በቁጥር እየበዛ ሀገር የለዬላቸው የሰው ዐውሬዎች መፈንጫ እየሆነች ነው፡፡ በዚያ ላይ በየክልሉ የሚታዬው የወያኔ የዘረኝነት ፍል አድጎና ጎምርቶ መውጫ መግቢያ እያሳጣን ነው፡፡

 በበርበሬ ስም ቀይ ሸክላና ሴጋቱራ ተደባልቆ ይፈጭና ይሸጣል፡፡ በቅቤና በዘይት ስም የማይታወቁ ባዕድ ነገሮች እየተደበላለቁ ይሸጣሉ፤ በነሱም እያለቅን ነን፡፡ በሚበላና በሚጠጣ፣ በመድኃኒት ስም በሚዋጥ - በሚቀባና በሚታሽ ባዕድ ንጥረ ነገር እየተረፈረፍን ነን - በቀጣፊዎች በየሥርቻው በሚመረት “መድኃኒት”፡፡ ማን ይድረስልን? ምን ይዋጠን? ከፈጣሪም ከኅሊናም ከመሪዎቻችንም ከዓለምም ተለይተን የመከራ ዶፍ እየወረደብን እንገኛለን፡፡ (“What swallow me?” አለ አሉ አንዱ እንግሊዝኛ እንደቁምጣ ያጠረው የኔቢጤ ተማሪ - ክፍል ውስጥ እንዲናገር ታዝዞ ሲናገር፡፡ መምህሩም የዋዛ አልነበረምና “Let the Abay river swallow you!”አለው ይባላል፡፡)

የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ በንግድ ማጭበርበርም ሆነ ባዕድ ሸቀጥና ከባህል ያፈነገጠ ሥጋ ሲሸጥ ተገኝቶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሚገባ ወንጀለኛ (ተጠርጣሪ ልበለው ለወጉ ያህል) ወዲያው በጉቦ ይለቀቃል፤ ወንጀለኞች “ብታሰርም ገንዘቤን ይጭነቀው!” በሚል እየተበረታቱ የፈለጉትን ከመሥራት አልተቆጠቡም፡፡ ደርግ በርበሬ ደበቃችሁ ብሎ በጥይት እንዳልቀነሸላቸው አሁን የመንግሥታችን የህግ ባለሟሎች መዝገብ እየሰወሩ ሕዝብን አውዳሚ ወንጀለኞችን በጉቦ ይለቃሉ - የጉድ ሀገር! በዚያን ሰሞን አንድ ጓደኛየ የሚያውቀው ሀብታም ነጋዴ እህል ቅጠል የማይል የቀይ አፈር በርበሬ ሲያመርት እጅ ከፍንጅ ተይዞ አሥር ሽህ ብር ለመርማሪው በመክፈል ፋይሉን አስጠፍቷል - አሁን እንደንጹሕ ሰው በነፃነት ይንቀሳቀሳል፡፡ በሀገራችን ህግ ተደፍጥጧል፤ ሞራል ጠፍቷል፤ የሀገር ፍቅር ርቆ ተቀብሯል፡፡ ሃይማኖታዊ ትውፊት በካህናቱና በጳጳሣቱ ዘንድ ሳይቀር ለይስላሙ እንጂ ድራሹ ጠፍቷል፡፡ መስቀል ረከሰ፤ ሆድ ነገሠ፡፡ ትንቢቱም ደረሰ! - እንኳንስ ደረሰ፡፡ እየጨሱ ከመኖር መገላገሉ ይሻላል፡፡

አሁን ወዴት እንሂድ? ምንስ ይዋጠን? ቆናጃጅቱ ምነው ዘገዩ? ምን እስክንሆን ይሆን ፈጣሪስ እንዲህና እስከዚህ የጨከነብን?
 እግዚዖ እንበል፡፡ ቀኑ ቀርቧል፡፡ ተያይዘን እየጠፋን ነው፡፡ የህግ ጠለላ ከሌለን፣ ባለሥልጣናቱ ዘረኛና ጎጠኛ ሆነው ለዘር ሐረጋቸው ብቻ የሚያደሉና ሌላውን የሚገፉ ከሆነ፣ ቢሮክራሲው ከአንድ ጎሣ ወደሌላ ጎሣ ሽግሽግ በማድረግ የሚመጣው የመንግሥት የሥራ ኃላፊ በአብዛኛው አገልጋይነቱ ለመላው ሕዝብ ሳይሆን እወክለዋለሁ ለሚለው ነገድ ብቻ ከሆነ ኢትዮጵያ ምን ትሁን?

“ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” እንዲሉ በዚህች ድሃ ሀገር የአዲስ አበባ ከንቲባ - ለራስ ፍላጎት እንዲያመች እንደወያኔዎቹ ህግን ለዋውጦ በተደረገ ምደባ ለተሾመ ከንቲባ ሊያውም - በወር ከ140 ሽህ ብር በላይ ለቤት ኪራይ ብቻ የሚመደብ ከሆነ ወዴት እየሄድን ነው? ለመሆኑ የአንድ ሰው ጥቅማ ጥቅም ከወር ደመወዙ ሊበልጥ ይችላል ወይም ይገባል ወይ? ለቤት ኪራይ ይህን ያህል ገንዘብ ከተመደበ የወር ደሞዙ እኮ በሚሊዮን ቤት ውስጥ መሆኑ ነው፡፡ ምን እየተሠራ ነው?  አምባሳደር ሸኝና ተቀባይ ለነበረ አንድ ቅን ታዛዥ የቀድሞ ፕሬዝደንት ከ400 ሽህ ብር በላይ በወር ለቤት ኪራይ መከፈሉስ ምን ያመለከታል? ሀገሪቱን በተራ የማሳደግ ሳይሆን በተራ የመቦጥቦጥና የማኮስመን አባዜ መፍትሔ የሚያገኘው መቼ ነው? በርግጥም እውነተኛው ሕጻን እየተቀበረ እንግዴ ልጁ እያደገ ወደ ሥልጣን እየመጣ ይሆን እንዴ? መጠርጠር ነው፡፡ አለበለዚያ ገበሬው ድሃ ሕዝብ በባዶ እግሩ እየሄደ፣ ቆሻሻ የኩሬና የወንዝ ውኃ እየጠጣ - ያም ከተገኘ - በከፈለው ገንዘብ ይህን ያህል መቀናጣት ዕብደት ወይም ትልቅ የአእምሮ በሽታ መሆን አለበት፡፡ ኅሊና ወዴት ተቀበረ?  እነጠ/ሚኒስትር አብይስ ምን እያደረጉ ነው? ለመሆኑ እየሠሩ ያሉትን ነገር ያውቃሉ ወይንስ እነሱም ጨርሰው ደነቆሩ? ስንትና ስንት ሥራ አጥ ባለባት ሀገር፣ ስንትና ስንት ሚሊዮን ዜጋ በማይምነት ጥቁር መጋረጃ ተጀቡኖ በድህነት አረንቋ ውስጥ በሚዳክርባት የድሆች ድሃ ሀገር፣ ስንትና ስንት ዜጋ በህክምና ዕጦት በቀላል በሽታዎች በሚረግፍባት ሀገር፣ ስንትና ስንት ሚሊዮን ሕዝብ በርሀብ በሚቀጠፍባት ሀገር፤ ስንትና ስንት ሚሊዮን ሕዝብ በመንገድ ዕጥረት ከከተሞች ተቆራርጦ በችግር በሚማቅቅባት ሀገር፣ ስንቶች እየተሰደዱ ከሰውነት በላቾች እንደምንም ቢያመልጡ የባህርና የዱር ዐውሬ ሲሳይ በሚሆኑባት ሀገር…. ለአንድ ከንቲባ፣ ለአንድ ጡረተኛ፣ ለአንድ ተጧሪ ባለሥልጣን ይህን ያህል ገንዘብ በወር መመደብ ምን ዓይነት የአእምሮና የኅሊና ስንኩልነት ነው? በስማም! አዙሮ ማሰብን ምን ወሰደብን? ከሰውነት ተራ ማን ይሆን ያወጣን?

የዚህች ሀገር ዕጣ ፋንታ ያገባናል የምትሉ ተሰሚነት ያላችሁ ወገኖቼ እባካችሁ ሀገራዊ የጸሎትና የምህላ ሱባኤ እንዲጠራ አድርጉ፡፡ ያለንበት ሁኔታ ካምሱሩ የተፈታ ቦምብና ፈንጂ ዓይነት ነውና እንደ ሦርያ ሳንሆን ፈጣሪን እንለምነው፡፡ ሦርያውያን መሰደጃ አገር ጠፍቶ ኢትዮጵያም የሚሰደዱባት ሀገር ሆና - እነግብጽና ሱዳንን አልፈው ወደዚህ የመጡት ለአንዳች ምሥጢራዊ መልእክት ነውና በቶሎ ወደ እግዚአብሔር እንጩህ፡፡ አለበለዚያ በሁሉም ረገድ ጠፍተናልና ወዮልን! ዳኛ የለንም፤ ጠበቃ የለንም፤ የፍትህ ዐይን ድርግም ብሎ ጠፍቷል፤ የፀጥታ ኃይል የለም፤ ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት ሥርዓት የለም - ሀሁን የማይለዩ የተለያየ ደረጃ ተመራቂዎች ናቸው ክፍት የሥራ ቦታዎችን በአብዛኛው እየሞሉ የሚገኙት፤ ሞራልና መልካም ሥነ ምግባር የለም፡፡ ያለው ብቸኛ ነገር የገንዘብ አምልኮትና ስለገንዘብና በገንዘብ ክምችት መሟሟት ነው፡፡ የሁሉም ዐይኖች ወደ ገንዘብ አፍጥጠዋል፡፡ የፈለግኸውን ወንጀል ብትፈጽም ብዙ ብር ካለህ ነፃ ነህ፡፡ ሁሉም ላንተ አሸርጋጅና ተላላኪ ነው፡፡ ገንዘብ የእግዚአብሔርን ቦታ ተክቶ ሕዝቡን እያራኮተው ነው፡፡ በቅርቡ ምናልባት ለገንዘብ ፅላት ሳይቀረጽለት የሚቀር አይመስለኝም፡፡… ሱባሃን! እንዴት ያለ ዘመን ላይ ደረስን ሲላ?! 

Tuesday, January 22, 2019

Is Abey Blessing or a Curse? Ethio Semay


Is Abey Blessing or a Curse?
Ethio Semay
To answer the question, it depends on the issue. I can only tell you Abey is a blessing to the Oromo blood stain criminal leaders and their hatemonger members. The fake Republic of Oromia dreamers slaughtered so many thousands of Ethiopian citizens to death. And millions and millions deported and destabilized their life forever by Oromo criminals.

Many if not all Oromo organization has participated intentionally in the fabrication of history to destroy an ancient country and its people Ethiopian. The OLF lead crime is been recorded in the mind of the many Ethiopian ethnic group, mainly in the mind of the Amhara people for ever. Tigrayans and Oromo criminals intentionally framed a program that lead in the crime to abolish Amhara ethnic from the planet earth.

All Oromo leaders who established an organization called Oromo Liberation Front (several of them in different leadership) are so sickeningly savage minded and uncivilized towards any positive thinking. As you all know according to the political program of the Oromo Liberation Front-OLF-(1976) and various publication related to it, the Oromo are not Ethiopians, but a colonized people: According to the OLF the Oromo were colonized during the last quarter of the 19th century by a black African nation-Abyssinia. As you can see their fabricated lies, the current Oromo society is not an Oromo society. Yes, they speak OromiNNa, but their blood cannot be proved that they are what they called themselves Oromo. There is no such thing in human biology to prove their DNA is Oromo DNA, as if there is a DNA called Oromo DNA. In fact, all of them are obtained from a various mixed ethnic language speaking parents and grandparents. To hide themselves as “pure Oromo blood” they change their parents’ given name to an Oromo names. How smart?! Their mothers are Christian and their fathers are Muslim followers. How do you negate this fact when you see even their different faith is intermingled by marriage. In fact it is difficult to marry a person with a different religious background than the other party than to marry a person with a different ethnic background. Tigrayans are not even better than the Oromo. Starting from Axum (many of them a Jew/Ayhud/ kings, Greece, some unknown ethnic or race...), all the way to Emperor Yohannes down to current living prince Ras Mengesha Seyoum (the treacherous prince who is untrusted, disingenuous and opportunist who speak with two tongues) are all ether half casted Amhara or Oromo, Saho, Beja and Tigrayan background, 

This includes the entire Tigringa speaking Tigray society who are the result of war and Empire which started from the kings themselves who were ruling Axumite Kingdom came from different race and ethnic background. You can see their face featured on their coins (currency) The obvious effect of these kings was to create a glued society of different skin and different feature. The entire Tigray/North- Gojam, Gonder, Baher Negash (eritrea), Wollo and shewa and beyond was the work of these kings and warriors. Those territories are clearly intermingled/mixed with the rest of the different ethnic in Sudan (As we speak today, the Felata Sudanese from Nigeria are living in our territory. Not only them but so many Sudanese ethnic and including Syrian refugees are now starting to flood to Ethiopia- the result of this is clear- mother nature will take its course and half cast breed will emerge). In this case let alone at the beginning of our establishment, starting from the ancient time, the various ethnic groups (Beja,Tigre, Portuguese syria, Italian Jew blood,,,), including with that of the Yemen and Saudi Arabian race is swimming inside the blood of the current Ethiopian society. When it comes to the Axumites, you can read the inscriptions left in stone monuments by the Axumite/Adulis Kings how they were moving one ethnic group to another village or far territories (the entire village mixing with another village after capturing the defeated ethnic/society/). 

This was done openly. When a given territory/village/ethnic refused to be subdued by the king The king goes to war to bring captives of the war and moved them to another territories. As the result nature takes its own course through marriage as the bee works its job inside the flower. The Tigrayan fascist can claim they are "pure" when there is no such "pure' in human biology. In fact Tigrayans are the most mixed/ halfcasted/ trippledcasted/ qudrippledcasted society than any others. Just read the kings' inscriptions left for history to see it.

Let us go back to the criminal OLF group;-

The OLF history as you know cannot cross back beyond their claim (19th century) to the 1st or the 13 century Ethiopia. They know they cant offer to get into it. They know the ¾ Ethiopian territory occupied by the so called Oromo was not their land originally. In fact they are the ones who penetrated from tip south of the Ethiopian territory extended to their current settlement territories that they are now owning as the only ownership of these ¾ Ethiopian territory. Just read the ‘Aba Bahrey Dirsetoch’ documented in the 16 century by a monk name Aba Baherey who was a chief in the Birbir Mariam monastery in Jima during the barbaric Gala occupation, himself a witness and a victim of the gala warriors. They burnt his books and his monastery.  Raping, looting, murdering, burning houses was so brutal, it shocks to your rear end when you read the hand written document left for history to look at it.

So, we know who the Oromo are this time. Their fabrication as occupied people is nothing more than stealing ¾ lands which belong to all of us including to the occupiers themselves. I have to remind that the current Oromo elites including Abey and the OLF leaders demand the current Oromo areas are Oromo territories. These vast land is been handed over on a silver plate by the Tigrayan fascists at the May 1991 conference brokered by the CIA. This was sell-out of Ethiopia. So, this far, it is clear history not hard to understand to any of you my readers.  
  
Now, let us go to the current leader and current opposition leaders how they see regarding the Oromo issue. If you read every one of these so called opposition manifesto/interview/documents/ speeches/ arguments, group discussion…….all of them will tell you “we oppose political organizations based on blood, race, language, religion , etc.. but we will allow and honor their freedom of argument with right of self determination/administration” what does this mean? It means they will allow them to proclaim in front of the Oromo people ‘up to secession” (up to destroying Ethiopia). So, this is the new motto of the new democracy that the opposition Or Dr.Abey’s new reform.

Both of them (the opposition and Abey) agreed in free speech and free arguments up to even destroying, and murdering a nation and its people. Why?  Because, it is the old KGB communist democracy and the new CIA reform democracy style that all oppositions lead by Abey’s reform are said to follow. This is in fact the most dangerous road that legitimizes to murder a nation using “democracy as a tool”. Such reform and belief does not stop only on politics, it also allows even Alshabab type of Extremities group to fight for Islamic/Sharia/ government style as long as there is no gun involved. Do you understand this politics of reform lead by Abey and supported by the so called oppositions? Abey told us that no citizen will be prohibited to air its goal, interest even any Alshabab type of flag if people wanted it, it is allowed to hoist inside the Ethiopian territory under this reform. That far, you can’t prohibit their nihilist agenda, because Abey and the so called opposition agreed in the so called “free speech”. What does free speech mean? Well, God only knows what it means.

This is why the OLF is let free murdering looting, raping and destroying clinics and even to the extent prohibit a wounded captive Ethiopian Oromo soldier from getting treatment in any of the local health hospitals that were occupied by the OLF thugs. This story was told by Abey himself to the Ethiopia people. This far Abey reform allows the OLF and TPLF thugs to do just about anything, any crime they want to carry. Tigrayans told Abey hell with you, we are not going to listen to any of the Ethiopian Federal higher court order to surrender the wanted criminals’ sheltered in Tigray. The blood stained Oromo Liberation groups are also telling Abey hell with you, we have the right to murder, rape, loot banks as we wish, because we are not Ethiopians. So who is the Oromo liberation Front lead by? It is by no one but by a retarded blood stained fellow who is complexly living in the 16 century era still allowed to live in Addis Ababa even ordering the looting, raping and murdering innocent citizens of Ethiopia openly undermining any international or local laws.

Now, we are seeing the so called religious and cultural or community leaders spoiling these Tigrayan and Oromo thugs begging them to mellow down. But, can thugs such as these well organized criminals know what civilized mind means? No. Because these are criminals stained with human blood for many, many years. Murdering is their habit. They are addicted to kill human beings. These are crazy elements, and mentally destabilized elements who are recruiting unemployed and ill informed youngsters using them to run their blood thirsty ego. These Oromo and Tigray gun toting gangs are not use to live without murdering and creating havoc to the life of innocent citizens, so therefore, Abey’s reform is very favorite moment for these thugs to do any they want. Will this reform stop these criminals from shooting at people or will this reform stop from demanding murdering a nation in the name of self administration? Will this reform stop from hoisting Alshabba type of religious extremists’ flag in Ethiopia? The answer is no, because, the reform’s aim is to allow secession, to allow just about anything including homosexuality, faith of 666 Satanism as long as there is no gun toting involved. 

The CIA is behind, leading the flourishing of these types of Democracy up to self administration/self determination/ which started already by TPLF for the last 27 years of Ethiopia agony. seeing these extreme freedom, is Abey a blessing or a curse? It depends who you are asking. But to those dealt on this commentary Abey is a blessing. Do not forget the American democracy and the old communist think of “Freedom of speech, up to self administration/self determination is allowed as long as one does not use a gun’ is catching up in the rest of Africa slowly. So, this trend already killed Ethiopia’s unity in the last 27 years and this trend will continue with its “extreme freedom” in the name of ‘democratic reform’ to solidify tribal territories even worse than ever.

 It is frightening and a concern, that you can easily see this trend, that even the Southern various ethnic territories are now demanding “their own apartheid territories as Kelil”. And harmfully the media and the opposition are all for it, as if,  it is the sign of healthy trend and as if Democracy is flourishing. All these fragmented Apartheid Kelil will later declare their own country and their own flag wich Ethiopia will end up in anarchy state.  Seeing this,will the apartheid trend started 27 years ago by the Tigrayan fascist party going to continue or going to be liquidated once for all? 
The answer is:- as long as criminals who involved in ethnic cleansing and torturing citizens are let free without any accountability still allowed to involve in politics, then I am afraid, Ethiopia will never see the daylight we all wish to see.
Ethio Semay

       

Wednesday, January 16, 2019

ኢሳያስ ወያኔን ይመታልናል ስትሉ የነበራችሁ ነፈዝ ኢትዮጵያውያን ሁላ ይህ እፍ እፍ ፍቅር እዩ’ እና እርማችሁን አውጡ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


ኢሳያስ ወያኔን ይመታልናል ስትሉ የነበራችሁ ነፈዝ ኢትዮጵያውያን ሁላ ይህ እፍ እፍ ፍቅር እዩ’ እና እርማችሁን አውጡ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ትግራይ ትግርኚ ቀስ እያለች በእግሯ እየተራመደች እንደሆነ ለበርካታ አመታት ነግረናል። ትግሬ ለትግሬ አህያ ላህያ ቢራገጥ “ጥርስ አይሰበርም” ሲባል ሰምታችሁ አታውቁም? ከ20 አመት በፊት ሁለቱ ትግሬዎች ተሸክመውት የመጡ የበረሓ ጅኒ ውቃቤአቸው ተነስቶባቸው በባድሜ ሰበብ እርስበርሳቸው ሲራገጡ አንዳቸውም “አለቆች” ሳይጎዱ 
የሙሶሊኒ እና የሂትለር እፍ እፍ ፍቅር በተግባር ሲታይ
የተጎዳው ሳሩ (ሕዝቡ) ነበር። ወያኔ እና ሻዕቢያ ለ80ሺሕ በላይ ሕዝብ የሞት እና የስደት መዘዝ ሆነው ‘አንዳቸውም መሪዎች’ ተጠያቂ ሳይሆኑ እነሆ ከ20 አመት በላ ለብዙዎቻችን ግልጽ ባልሆነልን ግንኙነት መጨረሻ ደብረጽዮን እና ኢሳያስ ሻቢያ እና ወያኔ ‘እጅ ለእጅ’ ተያይዘው እርፍ አሉ!

ስትሉት የነበረውን የተሞኛችሁበት አባባላችሁ ላስታውሳችሁ። እንዲህ ነበር ስትሉ የነበረ፦ “አሁን ኢሳያስ ወያኔን በሰሜን በኩል መክቶ ይይዝል እና የወያኔ ወንጀለኞች በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል፥ወያኔ (ጌታቸው አሰፋ) በሁሉም በኩል ተከብ’ቧል የትግራይ ትግርኚ ሕልማቸውም ይቀጫል የወያኔ ግብኣተ መሬትም ተቃርቧል ፥…ወዘተ.ወተዘ.. ስትሉ የነበራችሁ ነፈዝ ኢትዮጵያውያን ሁላ ይህ የእፍ እፍ የፍቅር ፎቶ ስታዩ እርማችሁን አውጡ!!!ስሜታችሁ ተቆጣጠሩ እና በግድያ በዝርፍያ የተሰማሩ እጃቸው ላይ ደም የተቀቡ ፖለቲከኞችን እትመኑ ስንል አትሰሙንም!! አብይ አሕመድ ጥሩ ተናጋሪ ነው ፤በስሜት ብዙዎቻችሁን ያስመረቅናል ፤ግን ተግባር ላይ “ሙሾ ነው!’ እንዳሉት የጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ የማትረሳ አነጋገር!

      ኢትዮጵያውያን ምሁራንም ሆኑ ወጣቱ ትውልድ ያው ሁሉንም ከፍቶ መስጠት የለመደባቸው “ኮምፕሮማይዘሮች እና አኮመዲተርስ’ መሆናቸው ዓለም ያወቀው ባህርያቸው ስለሆነ ዛሬም ይህንን ሰንገልጽ “ታዲያ ምን አለበት? የምንፈልገው እኮ ይህንን ነው” እንደሚሉኝ መልሳቸው ገና አፋቸው ሳይከፈት አውቀዋለሁ።ስለሆነም ነው ተገንጣዩ እና ሽብርተኛው ጸረ አማራው ኦሮሚያ ነኝ የሚለን ኦነግ አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ ወታደሮችን እና ምስኪን ኦሮሞዎችና ኢትዮጵያውያንን ሲገድል፤ሲዘርፍ ሲያፈናቅል፤ ዳውድ ኢብሳ ለፍርድ ይቅረብ፤ ዳውድ ኢብሳ ወደ አሥመራው ይባረር ብለው ሰላማዊ ሰልፍ የማያደርጉት አኮሞዲሰት ስለሆንን ነው። ምክንያቱም አብይ ፈቅዶላቸዋል እና እንደፈለጉት መሆን ይችላሉ፤ (ኦንሊ ኦን አብይ አሕመድ’ሰ ወርልድ!!!) ።

ኢትዮጵያውያን በባህሪያቸው (እኔን አይጨምርም) “ኣኮመዲተሮች እና ሰነፍ ኮምፕሮማይዘሮች” ናቸው። ጠላትን እና አራጃቸውን በማስተናገድ የታወቁ ራሳቸውን እና ሕዝባቸውን ለእርድ የሚያቀርቡ የጥንቶቹ አይሁዳውያን “አብርሃም እና ሳራዎች” ናቸው። (ይባስ ብሎ ዛሬማ ቀሳወስቱ እና ሼኮቹ ወደ መቀሌ ሄደው ወያኔ እና ብኣዴን ሊያስታርቁ ሄደዋል፤ የጉድ ጉድ ነው! ወደ ድሮአችሁ ተመለሱ እና ሕዝቡን ንደገና ፍጁት ብለው ቁጣቸውን እንዲያበርዱ እና እንደ ጥቱ እንዲሆኑ ነው ተልኡኮው!!)”” ኢትዮጵያውያን በእንደዚህ ያሉ የሃይማኖት ደላላዎች ‘መናፍሰት’ ሲመሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ “እየዘለሉ ኢሳያስን እያነቁ እንዴት ያቅፉ እና ያለቅሱ እንደነበር በቪዲዮ ኣይተናል አይደለም እንዴ?

ይህ ሰው አባታቸውን እናታቸውን በምጽዋ ባሕር ያረደ  ሬሳቸውን ያቀጣለ ፥ ንብረታቸው ዘርፎ “የጥርስ ወርቃቸው ሳይቀር አውልቆ ያባረራቸው ‘አረመኔ ናዚ” መሆኑን ቢነገራቸውም ኢትዮጵያውያን “አስተናጋጆች” ናቸው እና የፈሰሰው ደም ከመጤፍ ሳይቆጥሩት ኢሳያስ ወደ አዲስ አበባ እና ጎንደር ሲመጣ ለመታረድ እንዳማራት ሚዳቋ/ዶሮ ወንዱ ሴቱ ሙሁሩ ያሽካኩ ነበር። ኢትዮጵያውያኖቹ ይባስ ብለው የኢሳያስ ባንዴራ ምልክት ከፊታቸው ቀለም እየቀቡ የመስቀል ደመራን ሲያከብሩ ከናቴራቸው ሁሉ የሻዕቢያ ባንራ ያለው ቀለም ለብሰው እንደ እብድ ሲዘሉ ማየት ሆድ ቁርጠት ከማስነሳቱ አልፎ “ከብትነታቸው” በየትኛው ጠንቋይ ማስቆም እንደሚቻል ሲታሰብ እጅግ የሚያደክም መፍትሄ የታጣለት ጉደኛ ባሕሪ ነው።

ተቃዋሚ የሚባሉት ደደቦች እማ ይህንን የወያኔ እና የሻዕቢያ “እፍ እፍ ፍቅር” ሲመለከቱ በተለይ ግንቦት 7 የተባለው የኦነግ አጎብዳጅ እና የሻዕቢያ ቱልቱላ በደስታ እንደሚፈነድቅ አልጠራጠርም (ሰማያዊ የሚባለው ግም እዛው ደምሩት ያው ከግንቦት 7 ጋር የተደመረ ነውና)። ሌሎቹ (እነ በየነ ጴጥሮስ መረራ ወዘተ….እንደሌሉ ቁጠሩዋቸው፡ ያው የምናውቃቸው ፡”ኮመዲያኖች ናቸው”። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ተቃዋሚው ከደብረጽየን ጋር እንደሚተቃቀፉ ጥርጥር የለኝም። አስመራ ግምጃ ቤቶች ውስጥ ታሽገው የነበሩት እነ ግንቦቴዎች እማ አለቃቸው ተቃቅፏል እና ለነሱ መተቃፉ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ያው የምናየው ይሆናል።

ተቃወሚ ተብየው አብይ እስከፈቀደ ድረስ “አይጎረብጣቸውም”። ከጥቂት ጊዜ በላ የደብረጽዮን እና የኢሳያስ መተቃቀፍ “አርኣያ ነው እና” በዘምባባ እና በጭብጫባ መቀበል አለብን ብሎ እንደሚሰብኩዋችሁ አልጠራጠርም። ሁሉም ስለ ማይጨበጠው “ፍቅርና መደመር” በሚባል ‘ኦፕየም’ ነፍዟልና እንከን የለውም። ሰላም እና እርቅ ሲባል ተቃዋሚው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተገዢነታቸው ለሁለተኛ ጊዜ ለወያኔ እና ለሻዕቢያ የሚያረጋግጡ ናቸው ብየ ነበር ከሁን በፊት ዛሬም በአብይ አሕመድ ወይንም በቀሳውስት እና ሓጂዎቹ  ወኪልነት አደራዳሪነት እነሱም ከደብረጽዮን ጋር እንደሚደመሩ አያከራክርም። ይህንን አትጠራጠሩ! ኢሳያስም አስታረቂ ሊሆን ነው።

ሟቹ ወዳጄ እና መምህሬ ዶ/ር አለሜ እሸቴ The December 18-22 Addis Ababa  Peace & Reconciliation Conference በሚለው ሰፊ ሃተታቸው ውስጥ አንዲት ምዕራፍ የጻፉዋትን ይዤአት እንዲህ ብለው ጽፈው ነበር፦

Again They Tell us lies በሚለው ንኡስ ርዕስ እንዲህ ይላሉ፤-

“Once again, as usual, as we have been used for the last many years, they, those same organizations which never changes as if their existence depends on the non-existence of Ethiopia, as if they are commanded by the stirring of a pay-master, those same organization keep on telling us lies, keep on telling us , we Ethiopians, that they stand for Ethiopia unity while we know, we have known for years, that they have been dissolving Ethiopia, in collaboration with TPLF and EPLF, in the poison of the nihilist super-power imposed dogma of “self-determination up to secession”, to apply only to Ethiopia- stigmatized as on “empire state” made up of “colonies” and “oppressed tribes” or nations and nationalities.

Now while we know, and they know that they have sealed and signed the same nihilist dogma at the Paris Conference of March 11-13, the participants of the so called “peace and Reconciliation Conference” where they sat with such blood-stained ethno cleansers as the OLF of the Arba Gugu, Bedene, Assosa…massacres. OLF which keeps even now telling us that is has not moved an inch from its position of carving out the greater part of Ethiopia to form its Republic of Oromia,” with capital at Finfine-that is Addis Ababa…….”

እያሉ በተንተን ተቃወሚ ተብየው ፓሪስ ውስጥ ባሳለፈው አንቀጽ 6 (VI) ባሳለፈው ውሳኔ ማለትም “”The Conference reaffirms the right of people to self determination in accordance with the united nations Declaration of Human Rights of 1948” ይነበባል በማለት ወያኔ እና እነዚህ ተቃዋሚዎች “ሰልፍ አድምኒሰትረሽን” የሚሉት ትርጉም አንድ መሆኑ እና ተቃዋሚው ፍጹም አገር አቀፍ አጀንዳ እንደሌለው ያስታወሱበት ጽሑፍ ነበር።

ዛሬም በወያኔው ደብረጽዮን እና በኢሳያስ እንዲሁም በበቀለ ገርባ እና በኦነግ ፍልስፍና ተቃዋሚ ተብየው “መለሳለሱ” እንደማይቀርላቸው የቆየ ትዝታችን ትምህርት ነው። ስለዚህ የኢሳያስ አፈወርቂ እና የወያኔ ጥላቻ ለ27 አመት የዘለቀ ከልብ የመነጨ ጥላቻ ነበራቸው የምትሉ “ከብቶች” እባካችሁ ተሳስታችልና እርማችሁን አውጡ። ከወዲሁ አፓርታይዱ ወያኔን ከኢሳያስ እና አብይ ጋር አብረን በማበር ማስወገድ እንችላለን የምትሉ “የዋሆች” ያ “ደሊዥን” እንደማይቻል ከላይ በፎቶ እንዳያችሁት “እፍ እፍ ፍቅር” ትምህርት እንደምትቀስሙ ተስፋ አደርጋለሁ።

ዳዊት ወ/ጊዮጊስ እና ካሳ ከበደ እንዲሁም ንአምን ዘለቀ እና ብርሃኑ ነጋ ከነ አንዳርጋቸው ጋር ሆነው “ኢሳያስ አፈወርቂ” ለኢትዮጵያ በጎ አሳቢ ነው’ ሲሉዋችሁ የነበሩት የፖለቲካ ደላላዎቻችሁ ይኼው በተግባር “በጎ አሳቢነቱን” ከደመኛችሁ ወንጀለኞችን ከሸሸገው ከወያኔው ደብረጽን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው እንደሙሽራ ሲንሸራሸሩ ይኼው በጎ ምኞቱን ለኢትዮጵያ በገሃድ ፎቶግራፉ ላይ እየነገረን ነው!! ደላለቹ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ወንጀለኞችን ወደ እምትደብቅ ወደ ትግራይ ሄደው ያንን አፍ እፍ ፍቅራቸውን ልክ እነደ ኢሳያስ እንደማያሟሙቁላቸው በእርግጠኛነት ማስረገጥ አይቻልም።ምክንያቱም ሁሉም ኢትዮጵያን ተብየ ተቃዋሚዎች በተለያዩ ቡድኖች ሆነው ሲያበላሹ ሲያሳስቱ ሲያጋድሉ እና ሲገድሉ እንዲሁም ሲቦተልኩ የነበሩ ያንድ ስልቻ ዘመን ውጤቶች ናቸው።  

ስለዚህ ኢሳያስ ወያኔን ይመታልናል(ከወደ ሰሜን ወጥሮ ይይዝልናል) ስትሉ የነበራችሁ ነፈዝ ኢትዮጵያውያን ሁላ ይህ እፍ እፍ ፍቅር እዩ’ እና እርማችሁን አውጡ! የወያኔ ጀሌዎች እና ሻዕቢያ ጀሌዎች በተለይም የወያኔ ጀሌዎች (በተለይ የገዛ ተጋሩ ሃፍረተቢስ “እንደርታዎች”) መሪዎቻቸው ተቃቅፈው ስላዩዋቸ በየፓልቶኩ ምን እያሉ ይሳለቁባችሁ እንዳሉ ብትሰሙ መፈጠራችሁ ታቆሙ ነበር።
ጌታቸው ረዳ (ኢት ሰማይ)
   



Monday, January 14, 2019

ኢትዮጵያን ማፍረሱ ለምን ከባድ እንደሆነ በደምብ ገባኝ! ወያኔና መሰሎቹ ተስፋ ቁረጡ!...ነፃነት ዘለቀ


ኢትዮጵያን ማፍረሱ ለምን ከባድ እንደሆነ በደምብ ገባኝ! ወያኔና መሰሎቹ ተስፋ ቁረጡ!...
ነፃነት ዘለቀ
(netsanetz28@gmail.com)


እውነቴን ነው - እኔ ራሴም “ኢትዮጵያውያን እንዲህ እየተናቆርን ከምንኖር ለምን ተለያይተን አንክሞረውም?” ወደሚል የግል ድምዳሜ ደርሼ ነበር፡፡ ይሁንና ያለፉት እሁድና ቅዳሜ ያመላከቱኝ ነገር ሌላና የማልጠብቀው ሆኖ አገኘሁት፡፡ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከጥንት ጀምሮ ቀና ደፋ የሚሉ ወገኖች እነሱ ራሳቸው በተደጋጋሚ ሞክረው ቢያቅታቸው የገዛ ወገኖቻችንን በሤራ መረባቸው እየጠለፉ እኛኑ በኛው ላይ ቢያሰልፉብንና በጊዜው አገላለጽ በሆድ የሚያስቡ የቀን ጅቦችን በየዘመናቱ ቢያሠማሩብንም እኛ ግን እስካሁን አልፈረስንም፤ ወደፊትም አንፈርስም፡፡ በመለስ ዱካ ደብረፅዮን ቢተካም፣ ነገ ደግሞ በዳውድ እግር ሌላ ቢቆምም ኢትዮጵያ ግን እየተንገዳገደችም ቢሆን መኖሯን ትቀጥላለች፤ ከእግዲህም ቢሆን መቼም አትበታተንም፡፡ የኔም ምኞት፣ ያንተም ሥጋት፣ የነሱም ፍርሃት… ሚዛን የማይደፋ እንደሆነና ወቅታዊ ትርምስ ከመፍጠር ውጭ  የኢትዮጵያን ቋሚ ምሠሦዎች ሊያናጋ የሚችል ነገር እንደሌለ አንድ ኅያው ምሣሌ ባይኔ በብረቱ ተመልክቼ ተደንቄያለሁ፤ በተወሰነ ደረጃም ተፅናንቻለሁ፡፡ ስለዚህ ተስፋ አለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ወያኔና መሰል የመከራ ድግስ ደጋሾች ሁሉ ተስፋ ሊቆርጡ ይገባቸዋል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የግፍና በደል ኮማሪ ወር-ተረኞች ሊደንግጡ፣ ተስፋም ቆርጠው ከእስካሁኑ በከፋ ደረጃ ሳንጎዳዳ  ጥጋቸውን ሊይዙ የግድና ታሪካዊም ነው ማለት ነው፡፡ እርግጥ ነው . ሟች ይዞ መሞቱን መዘንጋት የዋህነት ነው፡፡ …

ቅዳሜና እሁድ - ጥር 4 እና 5 / 2011ዓ.ም ሦስት ሠርጎችን ታድሜ ነበር፡፡ አንዱ ቅዳሜ ማታ ሁለቱ ደግሞ እሁድ በተመሳሳይ ሰዓት፡፡ (የሚገርማችሁ ሬሣን ቶሎ ለመቅበር ስንቸኩል ሠርግ ላይ ግን ሰዓት ባለማክር ሰውን እናንቆራጥጣለን፡፡ ለዘጠኝ ሰዓት ቀብር ሬሣ በሰባት ሰዓት ከቤት ሲወጣ ለሰባት ሰዓት ሠርግ ሙሽራ ዘጠኝ ሰዓት ይደርሳል - ያልተፈታ ዕንቆቅልሽ፡፡ አንዱ ለመገላገል - ሌላኛው በሰዎች እንግልት ደስታን ለመሸመት - የሚገርሙ አጋጣሚዎች፡፡)

የቅሜዳው መቼስ ሠርግ አይምሰላችሁ፡፡ ትዝብቴን ለመግለጽ እንጅ አንዱን ከሌላው እያነጻጸርኩ ወይም ፍርድ እየሰጠሁ አይደለምና ፀጉር ሰንጣቂዎች ትንሽ ዕረፍት ቢጤ ውሰዱልኝ፡፡ በመሠረቱ ሁሉም ነገር አንድ ይሁን አይባልም፤ እንዲያ ቢሆን ኖሮ ደግሞ ሕይወት ትርጉም አልባ ናት፡፡ የቀይ ድምቀት በጥቁር ኅልውና ላይ ይመሠረታል፡፡ ረጂምን ካለአጭር ጭራሹን አናውቀውም፡፡ ትልቅ ባይኖር ትንሽ የለም፡፡ በሠንጋ የተደገሰ ድግስ በሙክት የተደገሰን ድግስ ካላከበረ ሠንጋውን ከሰረ፡፡ ትንሽም ብትሆን ልዩነት የሕይወትና የዕድገት መሠረት እንጂ ለጉራና ለትዕቢት የሚዳርግ የዕቡያን የትምክህት ጦር መሆን የለበትም፡፡… በዚያ ሠርግ የመብል መጠጡ ነገር አይነሣ፡፡ ታዳሚዎች ከ600 ቢበልጡ እንጂ አያንሱም፡፡ የተበላው ተበልቶ፣ የተጠጣውም ተጠጥቶ በሠርጉ መጨረሻ የተረፈው የቁርጥ ሥጋ ራሱ በቄራ መኪና ነው የተወሰደው፡፡ ከሠረጉ አይቀር እንደዚያ ነው፡፡ የምትጠራውን ሕዝብ ከድግስህ ጋር አጣጥመህ ከጠራህ አትታማም፡፡ ስትደግስ ደግሞ ሁሉም አይቅርብኝ ብለህና ሁሉንም ነገር ፈልገህ ሳይሆን ሁለንተናዊ አቅምህንና ወቅቱን አገናዝበህ ሊሆን ይገባል - እንደቤትህ እንጂ እንደጎረቤትህ ልሁን ካልክ ትጠፋለህ፡፡ ለአብነት 50 ሰው በሚያምነሸንሽ ድግስ 500 ሰው ብትጠራ ፍላጎትህና ዝግጅትህ አልተጣጣሙምና ከሰው ጋር ትቀያየማለህ፤ በግብዝነትም ትታማለህ፡፡ በዚህ ነጥብ ዙሪያ ብዙ ጊዜ ብዙ ነገር ስለታዘብኩ ነው እንዲህ የምለው፡፡ ተሰልፈን ውለን ጥርግራጊ ጎመን ላይ የምንደርስበት ሠርግ አይሉት ዐርባ ያጋጥማል፡፡ ደግሞም አንዲት ብርጭቆ ጠላ ወይም ድራፍት ብቻ የምትደርስህ ሠርግም አለ - ሊያውም በዘመድና የሚያውቅህን ከሩቅ አይተህ እጅህን እንደባንዲራ አሥሬ አውለብልበህ፡፡ “ይህም ይታሰብበት” ለማለት የደነቀርኩት የእግረ መንገድ መልእክት ነው፡፡ ይህን ለምን እዚህ ገለጽኩ ግን? የሆዳም ነገር…. “ሆዳም ሰው  አይጠድቅም” የሚባለው እውነት ነው፡፡

… ተጋቢዎቹ የአማራና ኦሮሞ ዝርያ ናቸው - በዘመኑ የወያኔ ቋንቋ፡፡ ወያኔዎች ይህን ባይፈቅዱም እኛ ግን ህግ እየጣስን እንጋባላን፡፡ ዐዋጅ እየሻርን እንዋለዳለን፡፡ ሥርዓት እያፈረስን በጋብቻና በአበ ልጅ እንቆራኛለን፡፡ ጠላቶቻችን እንድንዋጋላቸውና እንድነመነቃቀርላቸው ቀን ከሌት ሲማስኑ እኛ በዚህ መልክ ልፋታቸውን መና እናስቀርባቸዋለን - የኅልውናችን መሠረት ይሄውና ይሄው ብቻ በመሆኑ ቢመር ቢጎመዝዛቸውም ይህን ማኅበራዊ ትስስር መቀጠላችን አይቀርምና ይቅርታ ያድርጉልን፡፡ እስካሁን “ያልተንበረከክነው”ም በዚህ ምክንያት ነው፡፡

የሙሽራው ቤተሰብ - ሁሉም ማለት ይቻላል - በሠፈራችን በጭፈራ አንቱ የተባለ ናቸው፤ በተለይ ሸንኮራኛና ምንጃርኛ፡፡ ይህን የምናውቅ ሠፈርተኞች ጭፈራው እስኪጀመር ሳንቸኩል አልቀረንም፡፡ ሁሉም በጨፈገገበት ዘመን እንዲህ ዓይነቱን አጋጣሚ ዘና ለማለት ቢጠቀምበት የሚያስፈርድበት አይመስለኝም፡፡ እንጂ እነዚያ የእፉኝት ልጆች ዕድሜያቸው ይጠርና ዘመናችን የልቅሶና የዋይታ፣ የጭንቀትና የጥበት፣ የርሀብና የሽብር … እንጂ የደስታና የሃሤት እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ቢሆንም እንደባህሉ “ዋ ብሎ ጉርስ” አይቀርምና በዚያ ሠርግ ለተወሰነ ጊዜ ታዳሚዎችም ዓለማችንን ቀጨንበት፡፡

ዲጄው የተለያዩ ሙዚቃዎችን ከመነሻው ጀምሮ ይከፍት ጀመር፡፡ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ጉራግኛ፣ ደቡብኛ … እየተከታተለ መቅረብ ጀመረ፡፡ የወያኔን ቋሚ ህግ ድባቅ የመቱ የሚመስሉትን ታዳሚዎች ዘወር ወር ብዬ ተመለከትኩ፡፡ በግምባር ምልክት፣ በአለባበስ፣ በፀጉር አሠራር፣ በቋንቋና በአነጋገር ቃና፣ አልፎ አልፎም በፊትና በአካል ቅርጽ … ጥሎብኝ …. የዜጎችን ጎሣዊ ማንነት መገመት እንደቅርብ ጊዜ ልማዴ አድርጌዋለሁና ታዳሚዎችን ስታዘብ ከሞላ ጎደል ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን እንደሚወክሉ ተረዳሁ፡፡ ዘፈኖች ሲከፈቱም ምንም እንኳ ብዙዎች ዳንኪረኞች የሁሉንም እኩል ወይም ብዙም በማይተናነስ ሁኔታ ቢጨፍሩም የትኛው ታዳሚ በየትኛው ይበልጥ ፊቱ እንደሚፈካ ስለሚገባኝ ያ ትልቅ አዳራሽ ኢትዮጵያን እስኪመስለኝ የሕዝብ አንድነትና ትስስር ቁልጭ ብሎ ታየኝ፡፡ በአንድ ሠርግ ይህን ያህል የጠበቀ ግንኙነት ማየት ተዓምር ነው፡፡ አንድ ሠርግ ላይ ደግሞ በየትኛውም ወገን የሚጠሩ ሰዎች ቢያንስ ከሁለት ለአንድኛቸው ቀረቤታና ወዳጅነት እንዳላቸው ግልጥ ነው፡፡ ሁለት ሙሽሮች አንድን ሀገር የማያያዝ ችሎታቸው እንግዲህ ሊሠመርበት ይገባል፡፡ ውስጡን ስንመረምረው ቀላል እንዳይመስልሽ እህቴ፡፡  

ትግርኛ ዘግየት ብላ ነበር፡፡ እጠብቃትም ነበር፡፡ የምጠብቃትም ከወቅቱ የፖለቲካ ንዝረት አኳያ የሕዝቡን አጸፋ ለማየት በመጓጓቴ ነበረ፡፡ ዘፈኒቱ መጣች፡፡ መድረኩ እንደሞላ ነበር፡፡ አንድም ሰው አላቋረጠም፡፡ እንዲያውም በእልህ በሚመስል አኳኋን የዳንኪረኛው ብዛት ጨመረ፡፡ አዲስ ገቢውም የነበረውም ሥልት ለውጦ መጨፈሩን ቀጠለ፡፡ ገረመኝ፡፡ ያ ሁሉ ትንግርት መሰል የወያኔ ግፍና በደል በተሰራጨ ሰሞን እንዲህ ያለ የሕዝብ አንድነት ሲታይ፣ እንዲህ ያለ የፍቅር ትስስር ባልተጠበቀ መልክ እውን ሲሆን ብዙ ነገሮች እውነትም ወያኔ ወለድ አርቲፊሻል የሆኑ ያህል ተሰማኝ፡፡ የኔም አመለካከት በአንዴ ተለወጠ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፉ ክፉውን እየረሳ የደጉን ቀን ትውስትታ እንደሚያዳብር ገባኝ፡፡ “ተዋጋ፣ ተጣላ፣ ተገዳደል…” እያሉ ቢወተዉቱትም መሪዎቹን ቀድሞ የሚሄድ እጅግ አስደናቂ ሕዝብ መሆኑን አስተዋልሁ፡፡ ይህን ሕዝብ መናቅ የመጨረሻ ጅልነት እንደሆነም ገባኝ፡፡ የሚንቁን ግን ሞልተዋል - መጨረሻቸው አያምርም እንጂ፡፡ የሚንቅ እኮ ራሱ የተናቀና ራሱንም በራሱ የሚያዋርድ ነው፡፡

ዘፈኑ ቀለጠ፡፡ ኢትዮጵያም በአንድ ማዕድና በአንድ መድረክ ቀለጠች፡፡ ለሙሽሮች መልካም ትዳርንና የኑሮ መሠረትን በዚህ አጋጣሚ ተመኘሁ፡፡ “መጀመር እንዲህ ቀላል ነው፤ ጨርሱት” ብያለሁ፡፡ ወቅቱ ዘመነ መርዓ እንደመሆኑ በነዚህ ሠርጎች የሚጋቡና ከነሱ የሚወለዱም ሁሉ ለኢትዮጵያችን መድኅን እንዲሆኑ በጋራ እንጸልይ፡፡ የእርጉማን ሽንቶች እየተበራከቱ መጥተው ሀገራችንን ወደውድቀት ጫፍ እድረሰዋታልና በቆፈሩት ጉድጓድ ራሳቸው እንዲገቡበት በዚህ አጋጣሚ እንጸልይ፡፡  

ከእሁዱ ሠርጎች አንደኛው የትግሬ፣ የአማራና የኦሮሞ ቅልቅል ሠርግ ነበር - ዳሪዎቹም ተጋቢዎቹም፡፡ ይገርመኛል፡፡ እኛን ኢትዮጵያውያንን እግዜሩ እንዴት አድርጎ እንደሚሸምነን፣ እንዴት አድርጎ ከቆላ ከደጋ አገናኝቶ እንደሚያጠላልፈን ስመለከት “ከቶ እንደኛ የታደለ ሕዝብ አለ ወይ?” እላለሁ - ጨመት ስል ነው ታዲያ፤ ሳብድ ግን አያድርስ ነው፡፡ እግዜሩን እንዴት እንደምራገም አታንሱት፡፡ “የተረገምን ዕድለኞች ነን” ልበል ይሆን?

በዚያ ውብ ሠርግም አንዴ አማርኛው፣ አንዴ ኦሮምኛው፣ አንዴ ትግርኛው በዲጄው እየተቀያየረ ሲጦቅ ጨፋሪውም ሥልቱን እየለዋወጠ ሲጦቅ ያዬ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሩን ይጠራጠራል፤ ምን ማለታችሁ ነው - በተለይ ማኅበራዊ ሚዲያውን ለሚከታተል ሰው አማራና ኦሮሞ፤ ኦሮሞና ትግሬ፣ ትግሬና አማራ  በዚህ ዓይነት ድል ያለ ሠርግ መሀል አብሮ መብላትና መጠጣትም ሆነ አብሮ መጨፈር ይቅርና በአንድ ከተማ ውስጥ የሚኖሩም እኮ አይመስለውም - ሚዲያና እውነታ አንዳንዴ አሁን አሁን ደግሞ ምናልባትም ብዙውን ጊዜ እንደሚለያዩ መገንዘብም ተገቢ ይመስለኛል፤ እንዲህ የምልህ ታዲያ አዲስ አበባ ውስጥ በተወሰነ ደረጃ ስለታዘብኩት ነገር እንጂ ሌላውን አላየሁምና አስዋሽተህ እንዳታስኮንነኝ፡፡ እኛ እንግዲህ እንዲህ ነን - ለማንኛውም፡፡ እነዚያ ሥራ ፈት ፖለቲከኞች ወደነዚህ ቦታዎች መጥተው ቢያዩ ጉዳቸውን ባወቁ ነበር፡፡ ግን ግን የሰይጣን ሽንት የትም ቢገባና ምንም ነገር ቢመለከት ተፈጥሮው አይለወጥምና በድንቁርናቸው መዝለቃቸው እየጎዳን አለን፡፡ እናም እግዜር ይይላቸው፡፡

እንግዲህ ሠርግንና ሀዘንን በመሰሉ ማኅበራዊ ኹነቶች ሕዝባችንን ስናየው አሁንም በአንድነቱ እንደጸና ነው፡፡ “ኦሮሞ ሲሞት አንድም አማራ ቀብሩ ላይ ድርሽ እንዳይል” ተብሎ በነዳውድ ኢብሣ ቢታወጅ እንኳን፣ “ትግሬ ሲሞት አንድም አማራ ዝር እንዳይል” ተብሎ በነአቦይ ስብሃት ቢደነገግም እንኳን ሕዝቡ ግን ዘር ሳይቆጥር እንደውሻ አጥንትና ደም ሳያነፈንፍ ሁሉም ለሁሉም ይሄዳል፤ ይገኛል፤ ያለቅሳል፤ ያዝናል - ከልብ፡፡ በሠርግም አብሮ ይጨፍራል፤ ይጋባል፤ ያጋባል፤ ይዋለዳል፤ ያዋልዳል፡፡ በመከራና በደስታው አንዱ ለሌላው ደጀኑ ነው፤ መከታው ነው፤ ዋስ ጠበቃው ነው፡፡ የተጣላን ለማስማማት በሚደረገው  ሽምግልና፣ በዕድሩ፣ በፅዋ ማኅበሩ፣ በዕቁቡ፣ በፉካው/በሰንበቴው….አብሮ አለ፡፡ አንዳንድ ማፈንገጦች ቢኖሩም ብዙ ሞክረው ስላልተሳካላቸው ተስፋ እየቆረጡ ወደ ብዙኃኑ እየተሳቡ ይገኛሉ፡፡ አፈንጋጭ ደግሞ እንኳንስ በምድር በሰማይም አለ - ሰይጣን በማፈንገጡና ከላይ ወደታች በመጣሉም ነው እኛንም እንዲህ የሚያምሰን፡፡ አይደለም እንዴ? ምቀኛ አታሳጣኝ ነው፡፡ ካወቁበት ምቀኛም የዕድገት በር ከፋች ነው፡፡

ሃይማኖቱ ኖሮ የሃይማኖት መሪዎች ገና ባይፈጠሩም፣  ፖለቲካው ኖሮ የፖለቲካው መሪዎች ገና ባይመጡልንም፣ ሽማግሌዎች ኖረው አመኔታ የሚጣልባቸውና በአርአያነት የምናያቸው ሃቀኛ አዛውንት ባይኖሩንም… እነዚህ ማኅበራዊና ባህላዊ ተቋማት ለሀገር ኅልውናና ለሕዝብ ቁርኝት ያላቸው ፋይዳ ወደር የለውምና በአግባቡ እንጠቀምባቸው፡፡ ከሥጋ ምኞትና ከብልጭልጩ ዓለም ሎሌነት ለመውጣት እየተውተረተራችሁ የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች ካላችሁ ከተዘፈቃችሁበት የሥጋ ባርነትና መንግሥታዊ ሆድ አደርነት ወጥታችሁ ሀገርንና ሕዝብን በቅንነት ለማገልገል ሞክሩ፡፡ በብዙ ነገር ሕዝቡ እንደሚበልጣችሁም ተረዱ፤ ሕዝቡ የሚያከብራችሁ ስለጠመጠማችሁና ሥልጣነ ክህነት ስላላችሁ እንጂ በሥራችሁ እንዳልሆነም ተገንዘቡ፡፡ ሕዝቡ በሁሉም ተስፋ ከመቁረጡ የተነሣ አንዳች ነገር የሚጠብቀው ከላይ እንጂ ከታች እንዳልሆነ በዚህ አጋጣሚ መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ ያለመሪ፣ ያለ ሃይማኖት እረኛ፣ ያለ መንግሥት … እንዲሁ ዕውር ድንበሩን በፈጣሪ ኪነ-ጥበባዊ ሥውር ጣልቃ-ገብነት የሚኖር ብቸኛው ሕዝብ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ በተለይ በአሁኑ ወቅት በስፋት እየታወቀና በአንዳንዶች ዘንድም በድፍረት እየተነገረ ነው፡፡

ይህ ነገር እውነት መሆን አለበት፡፡ ዛሬ ለምሣሌ በአዲስ አበባ ቀውጢ ቀን ነው - 6/5/2011 ፡፡ ነዳጅ የሚባል አንድም ቦታ የለም - ቢኖርም በድብቅ አስወድዶ ለመሸጥ ይቆለፍበታል - በወገን ችግር ማትረፍ - በዜጎች ስቃይ መክበር ደግሞ እንደጮማ ሥጋ የሚወደድ ዘመን አመጣሽ ባህል ሆኗል፡፡ ይህ የሆነው የአንድ ክልል ወጣቶች መንገድ ስለዘጉ ነው ተብሏል፡፡ ልብ አድርግ - ክፉን ያርቅልንና የሦስት ክልል ወጣቶች ለሦስት ቀናት መንገድ ቢዘጉ እህል አጥተን በርሀብ መሞታችን ነው፤ የአምስት ክልል ወጣቶች ተደራጅተው ጦርነት ቢከፍቱ አንዳችንም በሕይወት ላንተርፍ ነው… ካላቆምነው ተጠየቃዊ ትንቢታዊ መጥፎ ጉዞው በዚህ መልክ ይቀጥላል፡፡ ይህን መሰል አቅም ያለው መንግሥት እንግዲህ ራሱን መመርመር/መፈተሸ ይኖርበታል፡፡ አሜሪካ ዛሬ በዓለም ነዳጅ ቢጠፋ ለቀጣዮቹ ሃያና ሠላሣ ዓመታት አንዳችም ችግር አይኖርባትም ይባላል፡፡ መንግሥት ለዜጎቹ ቤዛ እንዲሆን በቅድሚያ ራሱ ተስተካክሎ መቆም አለበት፡፡ ከማንና ከነማን ጋርም በትክክል ቀጥ ብሎ ሊቆም እንደሚችል ካላወቀ እንደተወለጋገደ ይሰነባብትና ለአንዱ ዘመን አመጣሽ ማዕበል ተጋልጦ በተራው ወደ ታሪክነት ይለወጣል - ወዳጅ መስሎ አብሮ ያለን ጠላት አስቀድሞ ማወቅ የለየለትን የሩቅ ጠላት ተዋግቶ ለማሸነፍ ያለውን ዕድል በእጅጉ ያሣምረዋል፡፡ ለዚህ ሁሉ ውስብስብ ችግራችን ዋናው ምክንያት- እንደሚመስለኝ - የዕውቀትና የቆራጥነት ጉድለት ነው፡፡ እንደፀጉራም ውሻ አሉ ሲሉን እንዲህ በቀላሉ ሞተን የምንገኝ ከሆን ዱሮውንም አልነበርንም ማለት ነውና ከእያንዳንዱ የዕለት ገጠመኝ ብዙ ተምረን ነገኣችንን የተሻለ ለማድረግ ታጥቀን መነሣት ይገባናል፡፡ ሰው መሳይ በሸንጎ እንደሆንን ዕድሜያችንን መፍጀት የለብንም፡፡ አንድ ቀን መንገድ ቢዘጋ አንዲትም ቀን የምንግደረደርበት ነገር አጣን - ይህ በራሱ ብዙ ያስተምረናል፤ እጅግ ብዙ ያሳስበናልም፡፡ ለመረጃ ያህል ነው፡፡ 

የሰው ዘር የሰው ዘር ነው፡፡ ዐይጥ ወይም ድመት ወይም ሌላ ዐውሬና እንስሳ  አይደለም፡፡ በተለይ በትላልቅ ከተሞች የወያኔና የኦነግ-ሸኔ አስተሳሰቦች የሽባ ሽባ ናቸው፡፡ አብረኸትን አግብቶ ልጆችን አፍርቶ ከባለቤቱ አባት ከባላምባራስ ዳምጠውና ቤተሰቡ ጋር በሰላምና በፍቅር የሚኖረው አቶ ደቻሣ አጠገቡ ያለውን በሪሁንን ትቶ አምስት ኪሎ ሜትር ርቆ ያለውን ገመቹ የሚባል ዘመዱን ለክፉ ጊዜ እንዲደርስለት ማድረግ አይችልም - እንዲያ ለማድረግ ማሰብ ራሱም ዕብደት ነው፡፡ እነፈይሣ ብቻ እንዲቀባበሩ፣ እነስንሻው ብቻ እርስ በርስ እንዲዳዳሩ/እንዱጋ፣ እነዘበርጋ ብቻ ዕቁብ እንዲጠጣጡ፣ እነጎይቶም ብቻ አገርና ድርጅት እንዲያስተዳድሩ፣ … ማድረግ እንደማይቻል ጊዜው ብዙ ትምህርት እየሰጠን ነውና ሳያመልጠን እንማርበት፡፡ በውነቱ ብዙ ከንቱነት እየተስተዋለ ነውና እባካችን ሁላችንም ማስተዋልን እንዲያድለን፣ በሰው ሰራሽ ነገሮች መለያየትንም እንድንተው በርትተን ቀን ከሌት እንጸልይ፡፡ … ፐ! ያ ሠርግ ግን አሁን ድረስ ዐይኔ ላይ አለ፡፡


Friday, January 11, 2019

የአብይ እና የደብረጽዮን መተሻሸት ሳየው ከኋላቸው የብዙ ሺህ ሰዎች የተቆረጡ ራስ ቅሎች እግር እግራቸው እየተከተሉ “በሕግ አምላክ እያሉ የሚጮሁባቸው ምስሎች ታይተውኛል ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


የአብይ እና የደብረጽዮን መተሻሸት ሳየው ከላቸው የብዙ ሺህ ሰዎች የተቆረጡ ራስ ቅሎች እግር እግራቸው እየተከተሉ “በሕግ አምላክ እያሉ የሚጮሁባቸው ምስሎች ታይተውኛል
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ሰሞኑን ኢሳያስ እና አብይ በኡምሓጀር እና በሑመራ በኩል የኢትዮጵያ እና የሻዕቢያ ኤርትራ ድምበር መተላለፊያ መከፈቱን ሰምተናል። መከፈቱ በጎ ነው። ግን በመክፈቻው ክንውን ካየናቸው ፎቶግራፎች መካከል የፋሺስት ትግራይ ድርጅት መሪው /ክሪሚናል/ ደብረጽዮን ገ/ሚካል እና ኢትዮጵያዊው አብይ አሕመድ መካከል አጅ ለእጅ እየተባበጡ፤ትከሻ ለትከሻ እየተሻሹና ጥርስ ለጥርስ  እየተሳሳቁ የልጅዋን ሠርግ እንዳማረላት እናት ብሉልኝ ጠጡልኝ እንደምትል አይነት “የፊታቸው ገጽ በፍስሃ ተሞልቶ ብርሃን ሲያንጸባርቅ” አይተናል። ከዚያ አልፎ ከሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ ጋርም የውሸት ይሁን የእውነት ከፋሺስት መሪው ከደብረጽዮን ጋርም እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲራመዱ በጀርባቸው የተነሱት ፎቶግራፍ አይተናል። የኢሳያስ እና የደብረጽዮን መተሻሸት ጉዳየ አይደልም፤ እኔ የገረመኝ ግን የአብይ እና የደብረጽዮን መተሻሸት ማየት ሕግ የጣሰ ነው። አብይን ለምን ትቃወማለህ የምትሉኝ ልትኖሩ ትችላለችሁ፡ እኔ አልተቃወምኩትም- እኔ የምለው አሰራሩ መሰረታዊ ለውጥ እየሳተ ትዕግስት ላይ እያተኮረ ሕዝብ እያሰጨረሰ ነው! ነው ክርክሬ። እንደምትረዱኝ ተስፋ አለኝ። ምክንያቴን ላቅርብ።

በየጊዜው ከዚህ ሰው ደብረጽዮን ከሚባል እርኩስ እና ደባሪ ወያኔ የሚያደርገው እሽሩሩ ለአብይ ያለኝ ድጋፍ ሁሉ እየሟሸሸ እንዲሄድ አድርጎታል። መሳሳቃቸው፤መተሻሸታቸው “ፖለቲካ” እና ዲፕሎማሲያዊ ስልት ነው” የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ለኔ “ሁለቱም ሰዎች ክሕደት የፈጸሙ እና የሕግ ንቀት ያሳዩ ናቸው”። ይሕ በሕግ ጥሰት ያየሁት ስዕል፤ እኔ ሳየው ከላቸው በነዚህ ድርጅቶች (ወያኔ እና ኦሕዴድ) ውሳኔ የተፈጸሙ የብዙ ሺህ ሰዎች የተቆረጡ ራስ ቅሎች እግር እግራቸው እየተከተሉ “በሕግ አምላክ እያሉ የሚጮሁባቸው ምስሎች ታይተውኛል”።

ደብረጽዮን በወንጀል ተፈላጊው ጌታቸው አሰፋን አላስረክብህም ብሎ አብይን እቅጩን መንገሩ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን እስከማፍረስ ግልጽ ዛቻ እና ደጋግመን ለማረክናቸው የድሮ ሙርከኞቻችንን የትግሬው ጀግና ጌታቸው አሰፋን አናስረክብም ማለቱ ይታወቃል። ደብረጽዮን እና ተከታዮቹ በዚህ ሳያበቁ፤ አብይ አድሃሪ እና ጸረ ትግራይ ሕዝብ ብሎ ወርፎታል (መሰረተ ቢስ ውንጀላ ቢሆንም)። አንዳንዶቹ’ማ እንደ እነ አሉላ ሰለሞን የመሳሰሉ የታወቁ ወጣት የትግራይ የፋሺዝም ርዕዮት አቀንቃኞች “አብይ በስርቆት/ በሌብነት ነው ከቀድሞ ስራው የተባረረው” ብሎ በትግርኛ በቪዲዮ አውድዮ በይፋ (ዩትና በተባለ የኢንትርኔት ቲቪ) ወንጅሎታል (ማስረጃ ግን አላቀረበም)። ወያኔዎች እና ጭፍራዎቻቸው እንዲህ ያለ ውርደት እያከናነቡት አለቃቸው ደብረጽዮንም “ተጠርጣሪ ወንጀለኛን አላስረክብህም” ብሎ አገር አፈርሳለሁ እያለ ከሚዝት የፋሺሰት ድርጅት ተወካይ ጋር አብይ አሕመድ ተቃቅፎ ምግብ ተጋብዞ በደስታ ሲፈነድቅ የተመለከተ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለምን በሰላማዊ ሰልፍ አብይ አሕመድን መቃወም እንዳልፈለገ ለኔ እንቆቁልሽ ነው። ምክንያቱን የምታውቁ ካላችሁ እባካችሁ ንገሩን። ለአንድ ሰው ስንል ለምን ሰው እንዲሞት እናዛለን ብሎ አበይ አፋችን እንድንይዝ ሲሞክር ፤ጌታቸው አሰፋን እና መሰል ወንጀለኞችን ግን እንዴት ወደ ፍትሕ እንደሚያመጣቸው ግን አልነገረንም። 

በዚህ አይነት ስልት በየ ክልሉ በሚሊዮን ሕዝብ ተፈናቅሏል በመቶዎቹ ሞተዋል። ለምን ተብለው ሲየቁ አንዳንዶቹ የዜና ተንታኞች መንግሥት ሲለወጥ የሚታይ አይቀሬ ነው ብለው እንደ ሕግ አጽድቀው ሊያሰምኑን የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ታግሰህም ቢሆን ሚሊዮን ሕዝብ ከተፈናቀለ እና ከሞተ በሌላ መልኩ ደግሞ እንቅፋቶችን ለማስቆም ግን የሚከፈለው መስዋእት እና ኪሳራ ዕጥፍ ነው ብሎ የሚናገር የፖለቲካ ተንታኝ ሊያሳምነን የሚችል መላምት ሆነ ማስረጃ እስካሁን አልሰማንም። አሸባሪዎቹ እና ወንጀለኞች “በቃችሁ” የሚባሉት ጊዜ መቸ ነው?እያልን አፋችን ደም እስኪያወጣ ድረስ ጠይቀናል። መለስ ግን አላገኘንም።
 

 ዳወድ ኢብሳ አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ፤ ደብረጽዮን ፤ ጌታቸው ረዳ ፤አርከበ ዑቑባይ፤ ፍተለወርቅ (ስንቱን እንጥራ) አዲስ አባባ አለማቸው እየቀጩ ምን እሚሉት “ለውጥ እንደሆነ አላውቅም” እውነትም “የጥገና ለውጥ”!

የሚገርመው ደግሞ፤- አንድ ተጠርጣሪ ተብሎ እስር ውስጥ የሚገኝ ቤተሰብ ላይ ሰነድ ለመሸሽ ወይንም ተጠርጣሪን ለማሸሽ ወይንም ለመደበቅ ተባባሪዎች ናችሁ ተብለው መላ ቤተሰብ የታሰሩበት ሁኔታ በዜና አንብበናል።አዲስ አበባ ወጣቶች በሺዎቹ ተለቅመው ታስረዋል፤ በሌሎች “የፋሺሰት አፓርታይድ ክልል ግዛቶችም” ውስጥም በግለሰቦች ላይ ተመሳሳይ ለቀማ እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ውስጥ “አብይ አሕመድ” ደብረጽዮን እና አጋሮቹ ጋር ሲደርስ ግን ያውም ኢትዮጵያን እየመሩ ካሉት ከ4ቱ ድርጅቶች አንዱ ተወካይ ሆኖ ፌደራል ተብየው መንግሥት ከሚመሩት አንዱ ደብረጽዮን ሆኖ እያለ፤ ፌደራል ፍርድቤት የሚፈልጋቸው ተጠርጠሪዎችን አናስረክብህም እያለ በሕግ እና በአብይ አሕመድ ላይ የሚያላግጠውን ደብረጽዮን ጋር መሞዳሞድ የሚገርም ነው። እንዲያ ከሆነ ባለብረት ያሻውን መስራት ከተፈቀደለት ሁሉም ብረት እየገዛ ወደ ፍርድ ቅረብ ሲባል በቡድን ተደራጅቶ “ፖሊሱን ዞር በል” ማለት ሊጀምር ነው ማለት ነው። እየተሰጠ ያለ ትምሕርት ያ ነው። 

 ያውም “ኢትዮጵያ ምን ታማጣለች” እያለ በትግርኛ የሚዝት ጋጠወጥ የወያኔ ጭፍራ ጋር እየተቃቀፉ እጅ ለእጅ ‘እሸሸ ገዳየ’ ሽር ጉድ ሲል ማየት ጥፋቱ ደብረጽዮን እና ተፈላጊ ጭፍሮቹ ሳይሆኑ “ከእምቢተኞች ጋር አብሮ ሽር! ፏ!” እያለ የምናየው አብይ አሕመድም ነው። በሕግ ሊጠየቅ በተጋባ ነበር (ሕግ ቢኖር ኖሮ!!) ወንጀለኞችን አናስረክብም ብሎ ከደበቀ ግለሰብ ጋር ዊስኪ መጫለጥም ሆነ መተሻሸት አይቶ እንዳላየ ማለፍ ተባባሪነት ነው።

ወያኔ በድርድር እና በዲፕሎማሲ የተጠየቀው ነገር ያስረክባል ብሎ ማለት በ"ፋንታሲ" አለም ገብቶ አጉል ቅዠት መቃዠት ነው። ለፋሺስቶች ድርድር እና ዲፕሎማሲ ይበልጥ ያስቃቸዋል/ያኩራራቸዋል/። ለዚህ ነው ትግሬዎች አብይ ላይ እያላገጡ የምንሰማቸው (ክሩ ሲጠብቅ ግን ድምጻቸው ምን አንደሚሆን ውስጣቸው ለምናውቃቸው ሰዎች እንግዳ አይደለም (የነ ጻድቃን ግበረተንሳይ ወያኔዎችን ጥንካሬ ከሚገባው መካብ የራሱ የማይጨው/ራያ/ ቢራ በማዕቀቡ ፋብሪካው እንዳይዘጋበት ስለሚሰጋ ‘የአብይን ሰዎች ለማስፈራራት’ እንጂ ወያኔ አቅም ኖሯት አይደለም። እኛ ትግሬዎች የምንለው ምሳሌ አለ፤-- ከም ቀደም ይመስለክን ውሕጅ ይወስደክን(እንደ ድሮ መስሎሽ ጎርፍ እንዳይወስድሽ!!!) ይባላል። 


እኔ የገረመኝ የሶሞኑ ሌላ ክስተት ነው።በሽሬ እና ዛላምበሳ ድምበር የሚገኝ መከላከያ ሠራዊት ከምድቡ ሲንቀሳቀስ ወዴት ጥለኸን ትሄዳለህ አትሄድም ብሎ ሕዝቡ ማስቆሙን ሰምተናል። እንዴ!!? ኢትዮጵያ ጋር እገጥማለሁ ፤ድሮ ከማረክናቸው ጋር መግጠም እናውቅበታለን የሚል የወያኔ ጭፍራ እና ጉረኛ ሁላ ዛሬ ደርሶ ለምን መከላከያውን እባክህ ጠብቀን ብሎ ለምን ሊማጸነው ፈለገ? ሻዕቢያ እንዳይመጣ ነው? ሻዕቢያን ከፈራ ከመላዋ ኢትዮጵያ ተዋጊ ጦር እና ኢኮኖሚ ማዕቀብ ሲጣል ታዲያ የትግራይ ወያኔ እንዴት ሊሆን ነው?(እንደ ድሮ መስሎሽ ጎርፍ እንዳይወስድሽ!!!) የምለውም ለዚህ ነው። ትግራዋይ አፍረቃን በመላ ሊቆጣጠር የሚችል የተፈጥሮ ልዩ ዲ ኤን ኤ” አለው እያሉ የትግራይ.ኔት ድረገጽ አጋዚያን ሲፎክሩ የሰማናቸው ያህል “ወታደሩን ትተኸን አትሂድ እባክህ ጠብቀን ብሎ መማጸኑ” አለን ከሚሉን “ዲ ኤን ኤ” ጋር አብሮ አልሄድ ብሎኛል። 

 በደርግ ጊዜ እና አሁን ሁኔታዎች ለየብቻ ናቸው። ድሮም ቢሆን “ጥቂት ቆፍጣና ገበሬዎች ወያኔን ገትረው የይዝዋት ነበር:: ያጠፋቻቻው አድፍጣ በሰላዮችዋ ማታ ሲተኙ ነበር ያጠፋቻቸው ወይንም በሰላዮችዋ በኩል በሚመገቡት መርዝ እያስገባች እንጂ አቅም አግኝታ አልነበረም። ያም ሆነ ይህ  ወያኔ ሁሌም ዕድለኛ ነው፡ መረን የለቀቀ ተለማማጭ ቡድን ሁሌም አያጡም! የሚገርም ዕድል ነው!!)።

ለነገሩ ዝም ብየ ድከም ብሎኝ እንጂ አብይ አሕመድ በወያኔዎች ላይ የሚጨክን ልብ የለውም። አብይ መቀሌ ከተማ ተገኝቶ እንዲህ ብሎ በትግርኛ የተናገረውን ላስታውሳችሁ፦

"ትግራይ ለፍትህና ለእኩልነት ሞትን ተጋፍጠው ክቡር መስዋዕትነት የከፈሉ፤ ለኢትዮጲያን ግንባታ ቤዛ የሆኑ ጀግኖች፣ እንደነስሁል (ወደ ስሁል ፎቶ እየጠቆመ)፣ ሙሴ፣ ዋልታ፣ ሀፍቶም፣ ቀለበት፣ ሀየሎም፣ ብርሀነ መስቀል፣ ቀሽ ገብሩ፣ አሞራ፣ ጥላሁን ግዛው፣ በተለይ እንደ ጓድ መለስ ዜናዊ ያሉ (ጭብጨባ)፤ በአጠቃላይ ደግሞ ተቆጥረው የማያልቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖችና ታጋዮች ሀገር ናት። (ጭብጨባ)"

መለስ ዜናዊ ማነው? እነ መለስ የመሳሰሉ ከጫካ ጀምረው የሰው ፍጡር በተለይ አማራ ምርኮኛ ወታደር “በሳዮናይድ በመርዝ” ሲገድሉ (የታላቁን ሴራ ቃለ መጠይቅ አንብቡ) አንጨት አቀጣጥለው ሳር ከምረው አዛውንቶችን እሳት ውስጥ ቀቅለው ሲያሰቃዩ አገር ሲያፈርሱ ወደብ ሲዘጉ ለሻዕቢያ ወግነው  የኢትዮጵያ ሠራዊትን በጥይት ሲቆሉት የነበሩትን ባንዳዎችን ለኢትዮጵያ ሲሉ ቤዛ የወደቁ ብሎ የሚያሞግሳቸው አብይ አሕመድ አሁን  እንዴት ብሎ ይጨክንባቸው? ትናንት እንደህ ስትለን አልነበረም ወይ እያሉ የፋሺስት ግልገሎች ሊጠይቁት ይችላሉ። መለስ ዜናዊን “በተለይ እንደ ጓድ መለስ ዜናዊ  ለኢትዮጵያ ሲሉ ቤዛ የወደቁ” ብሎ ማለት ?/?/፧! በስመአብ! ለመሆኑ የሃያ ሰባት አመት ጉድ ማን አመነጨው እና ነው?! መለስ ዜናዊ /ህወሓት/እንዲያ ለአገር ቤዛ ሲል የወደቀ ከነበረ ለምን መጀመሪያ ስልጣን ስትይዝ “ሽብርተኞች ነበርን ይቅርታ እንጠይቃለን” ትላለህ? ሽብር እና በሕር ወደብ ማስዘጋት እንዱት ሆኖ ነው ለአገር ቤዛ መውደቅ ሆኖ የሚታይ? እንደው ተከድኖ ይብሰል።

የአብይ አሕመድ ሕግን በማስከበር ላይ ቸልተኛነቱን በወያኔዎች በነ ደብረጽዮን ብቻ እልተወሰነም። አስመራ ከተማ የቀረቺው ዕድሜ በጡሮታ ቁጭ ብሎ ሲቆጥር በነበረው አንድ አርብ የቀረቺው ‘አንድ እግሩ ጉድጓድ ያስገባ’ የኦነጉ መሪ ክሪሚናል ዳውድ ኢብሳ ላይም የሚገርም (ቃላት የሚያሳጣ ግርምት!!) እንዝሕላልነት ሰላሳየ ብዙ ነብስ እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል። አብይ አሕመድ የኦነግ ትግል ተረካቢ/ አስፈጻሚ/ መሆኑንዶ/ር ብርሃነ መስቀል የተባለ እዚሁ አሜሪካ የሚኖር የአብይ አሕመድ ደጋፊ ‘የሕግ ጠበቃ’ ደ/ር ብርሃነ መስቀል አበበ እንዲህ ሲል በግልጽ ነግሮናል፡”አብይ አሕመድ የኦነግ ዓላማ ተረካቢ” ሲል አሞግሶታል። እንግዲህ ኦነግ  ዓላማው እና ተግባሩ ምን እንደነበር እና አሁንም ምን አንደሆነ መግለጫ ከኔ የምትፈልጉ አይመስለኝ (ለበርካታ አመታት ሳጋልጠው ስለነበር)። እንኳን ድሮ ዘሬም በአብይ እና በለማ መገርሳ እገዛ ከሽንፈቱና ከውርደቱ ተገላግሎ በምሕረት አዲስ አበባ እንዲገባ ተፈቅዶለት ገብቶም ቢሆን ኦነግ ምን እየሰራ እንደሆነ የምታዩት ዜና ነው ማለቴ ነው። አብይ እስከዚህ ለኦሮሞ እና ለትግሬ ነፃ አውጪ የነገድ ፌደራሊስቶች ልቡ አይጨክንም።

በተጫማሪም በስፋት አብይ ምን አይነት እንዝሕላልነት እየተጫወተ እንዳለ በጥልቀት ለመረዳት እንዲረዳችሁ ይህንን የአቻም የለህ ታምሩ ጽሑፍ አንብቡ እና ፍርዳችሁን ስጡ!፤
አቻም በሚከተለው ርዕስ እንዲህ ይላል፦

«. . . ማንም ቢመጣ የሚገድለው አማራውን ነው» ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁ ሥላሴ
(Achamyeleh Tamiru)

የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ የፋሽስት ወያኔን የአፓርታይድ አገዛዝ ከተካ ወዲህ [ልክ እንደበፊቱ ሁሉ] ባለፉት ስምንት ወራት ስናያቸው የሰነበትናቸው የጭካኔ አይነትቶች ለመናገር እንኳ የሚሰቀጥጡ ናቸው። ከቡራዩው ጭፍጨፋ የተረፈች አንዲ እናት «በዚህ ዘመን ልጅ ወልዶ ማሳደግ መረገም ነው፤ ሰው ሆኖ መፈጠርም እጅግ ያስጠላል» ያለችው ባሳለፍናቸው ስምነት ወራት ያየናቸውን ጎሰኛነት የወለዳቸው የጭካኔ አይነቶች መጠን የሚገጽ ነው።

በምዕራብ ጎንደር በመከላከያ ጦር ጥይት ተመቶ ህክምና ላይ ከሚገኙ ሃጻናት አንዱ በዐቢይ አሕመድ የአገዛዝ ዘመን ከጅግጅጋው ጭፍጨፋ እስከ ቡራዩው የዘር ማጥፋት፤ ከሻሸመኔ የመንጋ ፍርደኞች ባደባባይ ዘቅዝቀው ከሰቀሉት የድሃ ልጅ በዚያው በሻሸመኔ እስከተካሄደው የአዛውንቶ የልጅ ልጆቻቸው በሚሆኑ አሳዳጊ የበደላቸው ዘረኞች የተካሄደው ዘግናኝ ድብደባ፤ በአዋሳ ከተካሄደው የወላይታና ሲዳማ ያልሆኑ ወገኖች ጭፍጨፋ እስከ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በኦነግ የሚታዱ የአማራ ገበሬ ልጆች ባለፉት ስምንት ወራት ያየናቸው ጎሰኛነት የወለዳቸው ጭካኔዎች ናቸው።

ከመስከረም ወዲህ ደግሞ በዐቢይ አሕመድ አገዛዝ መልካም ፍቃድ ከነትጥቁ እየተንቀሳቀሰ ያለው ኦነግ ምዕራብ ኢትዮጵያን እያተራመሰ ይገኛል። አገዛዙ ራሱ እንደነገረን ከሰላሳ በላይ የአገዛዙ ባለሟሎች በኦነግ ሲገደሉ፣ በወለጋ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተዘግተው የኦነግ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ሲሆኑ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በኦነግ ሲዘረፍ፣ ንጹሐን ዜጎች በኦነግ ሲታፈሱ፣ ዳዎድ ኢብሳ አዲስ አበባ ተቀምጦ የኦነግ ሠራዊት ከመንግሥት ጦር ጋር እንዲዋጋ ትዕዛዝ እንደሰጠ በአደባባይ ሲያውጅ እኛ «የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር» የምንለው ዐቢይ አሕመድ «ኦሮሞ ኦሮሞን አይገድል» በማለት እሱ የሚመራው [የኦሮሞ መንግሥት] ኦሮሞውን ኦነግን ስርዓት ለማስያዝ [መከላከያ] ሰራዊት እንደማያሰማራ ነግሮናል።

በየዩኒቨርሲቲው ካለክልላችሁ መጣችሁ ተብለው የአማራ እንቦቀቅላዎች በኦነግ ሲታረዱ ወለጋ ሄዶ ቢገደል ኦሮሞ ይከፋፈላል ብሎ የሰጋው «ኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ» ዐቢይ አሕመድ ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል መንግሥት ተቋማት እንደመሆናቸው መጠን የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎችን አዝዞ በዩኒቨርሲቲዎች የንጹሐን ሕይዎት በኦነግ እንዳይቀጠፍ ሲያደርግ አልታየም። ጅግጅጋ ቤተ ክርስቲያኖች ሲቃጠሉ፣ ንጹሐን ሲጨፈጨፉ፣ ሕጻናት ሲታረዱ፣ ሴት አያቶች ሲደፈሩ ይህ እንደሚሆን አስቀድሞ መረጃ የነበረው ዐቢይ አሕመድ የሚቆጣጠረውን የፀጥታ ኃይል ልኮ ዜጎች እንዳይታረዱ ማድረግ አልቻለም ወይንም አልፈለገም ነበር።

ፋሽስት ወያኔ አሳልፌ አልሰጠውም ያለችው የቤርሙዳው አዛዥ ጌታቸው አሰፋ መቀሌ በሰላም ተቀምጦ ሕገ መንግሥት ተብዮውን ለማስጠበቅ ቃለ መሀላ የፈጸመው ዐቢይ አሕመድ ግን በከፍተኛ ወንጀል የተከሰሰውን ጌታቸው አሰፋን ለመያዝና ለፍርድ ለማቅረብ ሰራዊት አለማዘዙ ሳያንስ ጌታቸው አሰፋን አሳልፌ አልሰጥም ካለውና ዐቢይ አሕመድ ሊያስፈጽም ቃለ መሀላ የፈጸመበት ሕግ «ለወንጀለኛ ከለላ መስጠት ወንጀል ነው» የሚለው የሕግ አግባብ ወንጀለኛ ካደረገው ከደብረ ጺዮን ጋር ትናንትና እጅ ለእጅ ተያይዞ ሽር ብትን እያለ ነበር።

የጅግጅጋው እልቂት ለማስቀረት፣ የቡራዩውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመቆጣጠር፣ የአዋሳውን ጭፍጨፋ ለስቆም፣ የኦነግን እብሪት ለማስተንፈስ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከመታረድ ለመታደግና በከፍተኛ ወንጀል የተከሰሰውን ጌታቸው አሰፋን ለፍርድ ለማቅረብ ያልተንቀሳቀሰው በዐቢይ አሕመድ የሚታዘዘው የጦር ሰራዊት ጎንደር ፋሽስት ወያኔ ያሰማራው ሱር ኮንስትራክሽን የሚያካሂደውን ቅናንትና አማራን የማጋጨት ፕሮጀክት ለመቃወም በወጡ የአማራ ልጆች ላይ ግን መከላከያ ሰራዊቱን አዝዞ እንቦቀቅላዎችን አስጨፍጭፏል።

የጎባጣ አሽከር አጎምብሶ ይሄዳል ለምን ቢሉት ጌታየን ለመምሰል አለ እንደሚባለው አዲሱን ጌታውን ኦዴፓን ለመምሰል ስም የለወጠው ብአዴን የሚባለው ነውረኛ ድርጅትም የአማራ ጉዳይ ባለጉዳይ ስላልሆነ የትናንትናው የመከላከያ ሰራዊት ጭፍጨፋ ሊያሳስባቸው አይችልም። ባለጉዳይ ቢሆኑ ኖሮ እስካሁን «ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ሳይሆንና ለፌዴራል መንግሥቱ ጥያቄ ሳናቀርብ መከላከያ ገብቶ ጭፍጨፋ አካሂዷል» የሚል ወገንተኝነትና ኤታማጆር ሹሙ ወርዶ እዙን ለግድያ ያሰማሩት ወንጀለኞችና ገዳዮች ለፍርጅ ይቅረቡ ሲሉ እንደማ ነበር።

እንግዲህ! ይህ ሁሉ አርበኛው ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁ ሥላሴ ያሉንን ነው የሚያስታውሰን! አርበኛው ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁ ከዛሬ ስድሳ አመታት በፊት «… ማንም ቢመጣ የሚገድለውና ጠላት የሚያደርገው አማራውን ነው» ብለው ነበር። ፋሽስት ወያኔ ቢመጣ በድሚያ ሰራዊት አሰማርቶ የገደለው አማራውን ነው። ኦነግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ የተመሰረተው ያልታጠቁ ንጹሐን አማሮችን ለመግደል ነው። ይኼው ዛሬ ደግሞ ዐቢይም ቢመጣ «ኦሮሞን ኦሮሞ አይገድለውም» በማለት እስካንፍንጫት የታጠቀውው ኦነግ በሚያሸብርበት ምዕራብ ኢትዮጵያ ጦር ያልላከውን ወደ ጎንደር ግን ሰራዊቱን በብርሃን ፍጥነት በማሰማራት የሚገድለው አማራውን ነው። ስለሆነም ዛሬም ቢሆን አማራው ከሌላው በተለየ መልኩ ሰራዊት እያሰማራ የሚገድለው ጨካኝ አራጅ እንጂ የሚያስተዳድረው መንግሥት የለውም!” ሲል አቻም በጥልቀት የአብይ እንዝሕላልነት ተንትኖታል።
 (አትዮ ሰማይ)