Thursday, October 10, 2019

ባለቤትህን የተመኘን ልጅህን ወይም እኅትህን ብትድርለት አይመለስም! (አቻምየለህ ታምሩ) Ethio Semay 10/10/19


ባለቤትህን የተመኘን ልጅህን ወይም እኅትህን ብትድርለት አይመለስም! (አቻምየለህ ታምሩ) Ethio Semay

አሁን እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ አብዲ ኢሌ አንድ የሶማሌኛ አባባል በመጥቀስ የተናገረውን ያስታውሰኛል።  አብዲ የነገረን ሶማሌኛ አባባል «ባለቤትህን የተመኘን  ሰውን ልጅን ወይም እኅትህን ብትድርለት አይመለስም፤ ምክንያቱም እሱ የፈለገው ባለቤትህን ነው» የሚል ነበር። ኦነጋውያንም የሚፈልጉት ከተቀሩት ኢትዮጵያውያን ጋር በእኩልነት መኖር አይደለም። እነሱ ቢፈልጉ እንኳ የሚመጻደቁበት ወታደራዊው የገዳ ሥርዓት ያንን አይፈቅድላቸውም። የገዳ ሥርዓት ከኦሮሞ ውጭ ያለውን ከመሬቱ አፈናቅሎ፣ የማንነት እጥበት በማካሄድ ገበሮ፣ ጭሰኛ  ወይም ባርያ አድርጎ የማኖሪያ ሥርዓት ነው። ዐቢይ አሕመድ መደመር የገዳ ውሉድ የኦሮሙማ ቅይጥ እንደሆነ ነገሮናል። የኦሮሙማ ደቀመዝሙሩ አሰፋ ጃለታ  ... 2010 .. «OROMUMMAA: NATIONAL IDENTITY AND POLITICS OF LIBERATION» በሚል ባሳተመው ጽሑፍ ኦሮሙማን ሲያብራራ፤  “Oromummaa emerges from the Oromo cultural and historical foundations, it goes beyond culture and history in providing a liberating narrative for the future of the Oromo nation that suffers under the Ethiopian Empire” ብሏል። 

ሺመልስ ትናንትና  በበረራ/አዲስ አበባ ባደረገው ንግግር ዐቢይ መደመር ኦሮሙማ ነው ያለውን ተርጉሞ  ለሥልጣን የበቁት ከአማራ ጋር ታግለው፤ ከብአዴን ጋር ተባብረው  ሕወሓትን አሸንፈው ሳይሆን በኦሮሙማ መርኅ ተመርተው የአማራን አከርካሪ ሰብረው መሆኑን ነግሮናል። የኦሮሞማ ግብ በኢትዮጵያ እምብርት ላይ የፈጠሩትን «ኦሮምያ» የሚባል እባጭ አገር አድርገው መመስረት ነው። ይህ በኢትዮጵያ እምብርት ላይ የበቀለው እባጭ ግን አባገዳዎች በየስምንት ዓመቱ ከባሌ በታች ካለው አገራቸው ተነስተው ነባሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች ባገራቸው ላይ እያጠፉና ገበሮ እያደረጉ፤ የተጋፈጧቸውን ከርስታቸው እያፈለሱ፣ በትእዛዝ ማንነታቸውን እየቀየሩና የገነቡትን ስልጣኔ ሁሉ እያጠፉ እንደ ዋርካ ተስፋፍተው በወረራ የያዙት የአገራችን ክፍል ነው። በኦሮሙማ እሳቤ እየተመሩ ኦሮምያ የሚባለውን በኢትዮጵያ እምብርት፣ የሁላችን የሆነውን ርስት ቀምተው የነሱ ብቻ አገር ለማድረግ የተነሱ ናዚስት ኦነጋውያንን በመለማመጥ ለማለዘብ እሞክራለሁ ብሎ እየደጋገሙ መታለል ስንዝር ስትሰጣቸው ክንድ እየጠየቁ ሊበላህ የተዘጋጀን አዞ ስጋ ብትመግበው ብትውል በመጨረሻ ላይ  እንደሚበላህ  ሁሉ በስተመጨረሻ እንዲበሉህ፣  ጊዜ እንዲገዙና  ትንፋሽ እንዲያገኙ ማገዝ ብቻ ነው። ምክንያቱም አብዲ ኢሌ  እንዳለው  ባለቤትህን የተመኘን  ሰውን ልጅን ወይም እኅትህን ብትድርለት አይመለስም፤ እሱ የፈለገው ባለቤትህን ነውና። 

ሰው በገዛ ርስቱ፣ ባያት ቅድመ አያቶቹ ባድማ ይህን ያህል ሊዋረድ ከቶ አይገባውም። ባሌ ከተወረረበት ከገዳ ሜልባ ጀምሮ ላለፉት አራት መቶ አመታት ባባቶቻችን ባድማ ሬሳ ስንጎትት፣ በደም አበላ ስንታጠብ ኖረናል። ርስታችንን ሰጥተን  አንድነት ማምጣት ካልቻልን ያለን የመጨረሻ አማራጭ እንደ ዋርካ የተንሰራፉበትን የአባቶቻችን ርስት ለቀው ኦሮምያቸው ከባሌ በታች እንዲፈልጉ ማድረግ ብቻ ነው። ይህን በተፈጥሮ ሕግም በእግዚያብሔር ሕግም መሠረት አለው። የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ አገራቸው የገቡ ነጮች የወረሩትን የጥቁሮቹን መሬት ለቀው እንዲወጡ ሙሉ በሙሉ ወስኗል። 

ደቡብ አፍሪካ በደቾች የተያዘችበት  ዘመን ኢትዮጵያም ከባሌ በታች በተነሱ በአባገዳ በሚመሩ ወራሪዎች  የተወረረችበት ዘመን ነው። በተለይም የመጀመሪያዎቹ የአምስ አባገዳዎች ወረራ ማለትም የሜልባ፣ የሙደና፣ የኪሎሌ፣ የቢፎሌና የምስሌ ወረራ ደቾች ደቡብ አፍሪካን ከተወረሩበት ዘመን ጋር ይገጥማል። የደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተወረረውን ሥርታቸውን ዛሬ ካስመለሱ ደቾች ደቡብ አፍሪካን በወረሩት ዘመን በአባገዳ እየተመራ በተካሄደው ወረራ  የተወረሩት ባሊ[የዛሬው ባሌ]፣ፈጠጋር [የዛሬው አርሲ] ደዋሮ[የዛሬው ሐረርጌ] እናሪያ [የዛሬው ኢሉባቦር] ቢዛሞን [የዛሬ ወለጋን] ወደ ነባር ባለቤቶቹ ሊመለሱ የማይችሉበት ምድራዊ ምክንያት ሊኖር አይችልም። እንዴውም የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ውሳኔ የተወረረብንን የአባቶቻችንን ባድማ ለማስመለስ precedence set አድርጎልናል። የአውሮፓዎቹ ጥንታዊ አገር ስፔንም ዜጎቿ የአገራቸው ባለቤት ሆነው በሰላም የሚኖሩት Reconquista ባሉት እንቅስቃሴ ወራሪዎቻች ለብዙ መቶ ዓመታት የወሰዱባቸውን ርስታቸውን አንድ በአንድ በማስመለስ ነው። እኛም Reconquista በማድረግ የተወረረብንን ርሥታችንን ማስመለስ አለብን። ባጭሩ እነ ሺመልስ ያሻቸውን ሊቀረሹ ይችላሉታዲያ  የሚቀረሹ በሰው ርስት ላይ ተሁኖ አይደለም። ኦሮምያ የሚባለው በወረራ የተፈጠረ ኢምፓዬር ፈርሶ ርስቱ ለባለቤቶቹ መመለስ አለበት።
 posted Ethio Semay

No comments: