Monday, July 23, 2012

በሽተኛው መለስና በሽተኛው ስርዓቱ፤ የሰሞኑን ውሎየን ላወያያችሁ።

Meles Zenawi of TPLF drafting a plan how to destroy Ethiopia to establish Tigray Republic

በሽተኛው መለስና በሽተኛው ስርዓቱ፤ የሰሞኑን ውሎየን ላወያያችሁ።


ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)


ለመልእክት አስተያየት getachre@aol.com

ሰላም እንደምን አላችሁ። እኔን የማንበብ ልምድ ያላችሁ ቅዱሳን ወገኖቼ ለቅዱስ ዮሓንስ የሚደርስ አዲስ መጽሐፍ እየጻፍኩ ስለሆነ በየጊዜው ካላነበባችሁኝ ይቅር በሉኝ፤አደራ።

መለስ ሞቷል፤ ታሟል የሚለው ዓለም አነጋግሯል። መለስ ባይሞትም መለስ መጥፎ ነውና ከመልካም የታሪክ ሕሊና ከሞተ ብዙ ቆይቷል። መለስ መጥፎ ብቻ ሳይሆን፤ጠማማ፤ መሰሪ (የውጭ ልኡክ)፤ኢትዮጵያን የማውቅ እና ኢትዮጵያን የሚጠላ (ወያኔው ብስራት አማረ በሃዋርያ ጋዜጣ ጽፎ የነገረን) የወያኔዎች መሪ ነው። መጥፎ መሪ የአንድ አገር የወደፊት ዕድል ብቻ ሳይሆን የሚያበላሸው፤የሕዝቡ ሞራል እና ባሕልም ጭምር ነው።

እዚሁ በምንኖርባት አገር አሜሪካ እንኳ መጥፎ መሪዎቻ ከጠንካራና ሃብታም አገር ወደ ከሰረች አገር መርተው የወደፊት ዕጣ ፈንታዋን አበላሽተውባታል። የመንግሥት ስልጣን ከያዙት ትልልቅ መሪዎች ጀምሮ እስከ “ዎል ሰትሪት” ተብሎ ከሚታወቀው ዓለም አቀፍ የባንክ፤ የንግድ መልህቅና ማእከል የሚመሩ መሪዎች አገሪቷን ከኩሩ እና አበዳሪነት ወደ “ተበዳሪ እና ኮስማና ባዶ ኪስነት/ቺስታ”(ባንክራብት) ወለል አውርደው የአገሪቱ የትምህርት፤የጤና፤የእርሻ እና የመገናኛ አውታሮች በመንቀሳቀሻ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ሠራተኞችን  በማሰናበት እንዲዘጉ አድርገዋል። ይህ አሳዘኝ ክስተት የመሪዎች መጥፎ አመራር እና የመሪዎች በትክክል ባለማሰብ፤የገንዘብ እና የሃብት፤የሥልጣን አልጠግብ ባይነት የሕሊና መቀቃዋስ ያመጣው ውጤት ነው።

ናምንም ባናምንም መቀበል የሚያስገድደን ሁኔታ፤ በእንደዚህ ዓይነት የፖለቲካ፤የመንግስት እና ተራራ የሚያክሉ የንግድ ተቋማት ገብተው በመምራት ላይ የነበሩና ያሉት ኩሯን አገር ወደ ተመጽዋች እና ወደ ፍርክስክስነት (ክራይስ) ከሚመሩ ጎዶሎ መሪዎች እና ያለ መሪ ሕይወትን መምራት ብናነፃጽረው ምንም ለውጥ የለውም።

እንደዚህ ዓይነት መጥፎ መሪዎች መላዋን ዓለም ሞልተዋታል።በዛው አንፃር የሕዝቦች ኑሮ ተቃውሶ ጭለማ ሕይወት እንዲመሩ ተገዷል። አገራችን ኢትዮጵያ “ኩሩ” ተብለው ከሚጠሩ አገሮች ምናልባትም በቅድሚያ የምትወሳ አገር ነች።እርግጥ ኩራቷ ለሕሊና ቀውስተኞች አይስማማም። ልብ ብሎ በሰከነ ሕሊና የአገሪቷ ታሪክ፤ሕይውት እና ውስብስብ መሰናክሎች በዘዴና በመጋፈጥ አልፋ ራሷን አሁን ወደ አለችበት እርከን ለብዙ ሺሕ አመታት እንዴት እንደጠበቀች ላሰላ ሰው አስገራሚ እና ኩሩ አገር መሆኗን ይደመድማል።

የኮራች ኢትዮጵያ የሚል መዓረግ ሲሰሙ “ትግርኛን መጻፍ አግዳ አማርኛ እንዳውቅ በግድ አስተማረቺኝ” ስለዚህ ኩራቷ ገደል ይግባ” የሚሉ የጣሊያን ቡችሎች ተበራክተዋል። አገር በስሜት የሚገነባ በስሜት እንደ ጭቃ የሚፈርስ የሚመስላቸው አሻንጉሊቶች እንደ አሸን ፈልተዋል። ይህ ሁሉ የሕዝብ ባሕል እና ሞራል መላሸቅ ተጠያቂዎቹ እንደ መሰል ዜናዊ የመሳሰሉ የኮሞኒሰት እና የፋሺስት ብሄር ብሐረሰብ….ልክፍት አቀንቃኞች የሚያላዝኑ ሕሙማን መሪዎች እንደሆኑ መሰመር አለበት።

አገር ሕዝብ ነው፤ብዙ ባህሪ የያዘ አስፈሪና አዳጋች ደን ነው። የብዙ ሕዝብ ባሕሪ ለመምራት ጤነኛ የመንፈስ የስነምግባር እና አገራዊ ፍቅር መታጠቅ መለኪያው ነው።”ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” ብሎ ራሱን የሚጠራ “ትግራይ ነፃ አውጪ” ድርጅት ከመነሻው ሲነሳ አነሳሱ የትግራይን ችግር ለመቅረፍ በሚል ነው የተደራጀው እና ተዋግቶ “በለስ ቀንቶት” የመንግስትን መንበር የነጠቀው። ወደ ስልጣን ሲሸጋገር ኢትዮጵያዊነት ሕሊናው አልነበረውም እና ዘርፎ አድበስብሶ “ትግራይን በልማት” ገንብቶ አንቀጽ 39ን በመጠቀም ትግራይን ገንጥሎ ጠላት በሚላቸው አማራዎች (ጎንደር ጎጃም ወሎ፤ ምናልባትም አፋሮች) እና ነፃ አገር ንነ ብለው “አጋሜ” ብለው በሚሰድቡን ኤርትራዊያኖች ተከብቦ “የአክሱም የእንቅልፍ ዘምን” ተከናንቦ ሕዝቡን ‘ፓራያ’ (የቁም እስር መንግስት ለማድረግ ነው።

ያንን ከማድረጉ በፊት ግን መለስ ዜናዊ በተጠናወተው በሽታ አገሪቷን በየዛው የጎሳ በሽታ በክሎ ፍርክስክሷን ለማውጣት እቅዱ እየተሳካለት ነው። ነገር ግን ብዙ ይቀረዋል። ያንን የመጨረሻው ዝርፍያን እና አገሪቷን ወደ አመድነት የመቀየር ሁኔታ ሳያጠናቅቅ ሲሰቃይበት ከነበረው የጎሳ በሽታ ከእግዚሃር የተላከበት በባሰ በሽታ ተይዞ ወደ በልጅየም ሄዶ  በሚሊዮኖች የሚቆጠር የኢትዮጵያ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ከሞት ለመዳን “ውጪ ነብሲ ግቢ ነብሲ” ጣረሞት ውስጥ እንዳለ አውቀናል።

የዚህ ከንቱ ግለሰብ ጤና ብዙዎቻችን “ይዞህ ይሂድ” ስንል ወያኔዎች ግን “ተንቀጥቅጠዋል”። ከመንቀጥቀጥ አልፎ ተናደዋል። “ይዞህ ይሂድ” ያሉትን እየኮነኑ ያለ የሌለ ስድብ በማውረድ “ኢትዮጵያዊነት ባሕሪ ያልተላበሱ፤ ርሕሩህ ልብ የጎደላቸው” ሲሉ ጩሆታቸውን አሰምተዋል። ባለፈው ሰሞን የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ክፍል የድሮ የወያኔ መስራች እና መሪ የነበረው አቶ ግደይ ዘርአጽዮንን በመጋበዝ ስለ መለስ መታመም አስመልክቶ አስተያየቱን እንዲሰጥ እንዳደመጣችሁት ተስፋ አለኝ። በወቅቱ አቶ ግደይ ዘርአጽዮን የመለስ መታመም ሲተነትን መለስ በያዘው በሽታ እግዚሃር ቢያሰወግደው ለአገራችን ሕዝብ የሚበጅ እንደሆነ አስተያየቱን ሲገልጽ፡ ወያኔዎች ግን ኩፉኛ በመቆጣት “ዓይጋ ፎረም” በተባለው የወያኔዎች ድረገጽ የሚከተለው ብሎ ነበር::
  

Comment on Gidey’s remarks on PM Meles’ health!
Zeru Hagos July 20, 2012-- The secret behind TPLF’ssuccess is one and simple. The organization simply trusted the people to nurture and defend it against its adversaries. And boy did they!...On hindsight it seems that not all TPLFites knew this secret! The latest news about PM Meles’health has opened a window for many Diaspora talking heads to spew their venomous hateful analysis on the air. One among them is Gidey Zeratsion...”

በማለት የመነጋገሪያ መድረክ በመክፍት ወያኔዎች መለስ ዜናዊ በሞት አፋፍ በመገኘቱ ድንገተኛ “ርሕሩሕ ልብ፤ሰብአዊነትን የተላበሰ ኢትዮጵያዊ አዛኝነት” ተላብሰው ግደይ ዘርአጽዮንን “ኤርትራዊ እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለም፤ በማለት ኤርትራዊነቱን በመጠቆም ኤርትራዊ ባህልና ልብ እንጂ ርህሩሕ የሆነው ኢትዮጵያዊነት ያልተላበሰ….” በማለት በጣም አስቀያሚ እና ጎሰኛ/ዘረኛ ባህሪያቸው አንጸባርቀዋል። እኔ እና ግደይ አብረን በአንድ ከተማ ያደግን ብንሆንም እና ካየሁት የቆየ ቢሆንም ኢትዮጵያዊ እንጂ ኤርትራዊ ዜጋ ነኝ ብሎ አያውቅም። ወያኔዎች ግደይን በዚህ መወንጀላቸው በጣም አስቀያሚ የሆነ ምልክታቸው የሆነ ዘረኝነትን አንጸባርቀዋል።
መለስ ቢሞት ደስታውን አንችለውም “በዛው ይዞት ይሂድ!” ስለተባለ አንዳንዶቹ በዚህ ተቆጥተው “አንቀጽ 39 የተባለው የፋሺስቶች እና የኮሚኒሰት መርሆ አንቀጽን በመጥቀስ “ትግራይ ሪፑብሊክን” አንመሰርታለን በማለት አስቂኝ እና ማስፈራሪያ የህፃን ቁጣቸውን አሰምተዋል። ከዚያ ሁሉ የሕጻን ቁጣቸው ይልቁንስ ያስገረመኝ “የወያኔ ጀሌዎች” በሰው ልጆች ላይ “ሞትን አትመኙ” በማለት ኢትዮጵያዊ ሰብአዊነትን ተላብሰው “ድንገተኛ ሰብአዊ ርህራሄ” አቀንቃኞች መሆናቸውን ሳነብ እጅግ ነው የገረመኝ። ለዚህ ሁሉ የመለስ እርግማን ደግሞ ተጠያቂ ያደረጉት፤መለስ ዜናዊ እና ካድሬዎቹ በአእምሮአቸው ውስጥ የከተቱባቸው የማመካኛ ጎዳናቸው የሆነው የፈረደበት “አማራውን” ነው። እዛው ከመድረኩ የተሰነዘሩት አስተያየቶች ታገኟቸዋላችሁ።
 እዛው መድረክ ገብቼ ከነዚህ “በድንገት፡ ወደ ሰብአዊነት ወደተለወጡት የወያኔ ጅሎች እና ጀሌዎች ጋር ለመነጋር ገብቼ ነበር። ከመለስ ጀሌዎች የሚሰነዘረው አስተያት እና ቁጣ በጣም አስገራሚ ነው። የድረገጹ አዘጋጅ “Uncivilized and Unlike any Ethiopian!” የሚለው ለግደይ የተሰነዘረው ርእስ ሳነብብ ድንገት የተደቀነብኝ ነገር “እነዚህ ሰዎች አርቆ አሳቢነት እና ኢትዮጵያዊነት፤ለሰው ልጅ አዛኝነት የሚባሉት በጎ ስነምግባሮች አሁን እንዴት ተገለጸለቸው?” ነበር ያልኩት። ይህ ከመከሰቱ በፊት  እውነት እንዚህ ሰዎች ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ እና ተቃዋሚ ሰው ሲሞት እና ሲታመም አዛኞች ነበሩ ይህ ጉዳይ ሳንሸፋፍን መነጋገር አለብን።  አልነበሩም። እነዚህ ሰዎች እና የፖለቲካ ድርጅታቸው እጅግ በተወሰነ የድርጅት ፍቅር እና ክልል እይታ የታጠሩ ርህራሄ የሌላቸው እጅግ ጠባብ እና ለተወሰነ ሕዝብ ብቻ የሚያዝኑ እና የሚቆረቆሩ ናቸው።
ታስታውሱ እንደሆነ እዛው በመላው ዓለም ውስጥ የተበተኑት ትግሬዎች ተሰባስበው ቴሌ ቶን’ በመባል የሚታወቀው የመሰባሰቢያ ጥሪ በማድረግ በወቅቱ 9.6 ሚሊዮን ሕዝብ በረሃብ ተሰቃይቶ የወያኔ መንግስት የልመና ኮሮጆ ዘርግቶ ሹሟሙንቶቹ አሰማርቶ በየዓለማቱ ለማስመሰያ ሲለምን (ለዘርፊያም ሊሆን ይችላል) በሌላ ጎኑ ደግሞ የትግራይ ተወላጆች ለትግራይ ትምህርት ቤቶች መገንቢያ ሲያሰበሳስቡ ነበር። ይህ የምታስታውሱ ብዙዎች ናችሁ የሚል ግምት አለኝ።
በዛች አንድ ቀን በተደረገው የገንዘብ መዋጮ 60 ትምህርት ቤቶች የሚያሳንፅ ገንዘብ በማሰባሰብ “ሰብዓዊ ሕሊና እና ኢትዮጵያዊነት ቸርነት” ጥለውት እንደነበር የምታስታውሱት እንደሆነ ተስፋ አለኝ። በዛው ወቅት ከዘጠኝ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ለተራበ ሕዝብ እና በረሃብ በበሽታ ሲሞት ፤ሕጻናት በእናቶቻቸው ክንድ ለዘላለሙ አሸልበው ሲያልፉ፤እናቶች በሃዘን ተወግቶ አምባቸው ሲያወርዱ፤ትግራይ ግን ረሃብ ተወግዶ፤ ለትግራይ ሕዝብ ልጆች ለትምህርት ቤት ማስገንቢያ የሚሯሯጥ ለትግራይ ሕዝብ ልቡ ተንጠልጥሎ የሚንገበገብ፤ አሁን ድንገት በመለስ ዜናዊ በሽታ እና ስቃይ “አልቅሱ፤ ተጨነቁ” እያሉ መለስን ያወገዙትን “ኢትዮጵያዊነት-ያልተላበሰ-ልብ”-ሲሉ-ገርሞኝ-በፎሮሙ http://aigaforum.com/blog1/2012/07/21/uncivilized-and-unlike-any-ethiopian/comment-page-2/#comments ላይ ሰሞኑን የጻፉትን የሰጠሁት መልስ ላስነብባችሁ።

Do you remember the “Tigrayan telethon” a campaign to collect money for Tigray school constructions? Do you remember the event? Do you remember what was taking place in Ethiopia particularly in the Eastern part of our country Ethiopia? Let me put it in short to remind your memory “incase”. The event that Telethon was conducting was a period of terrible starvation taking place by millions in the eastern and Amhara region as well.

The Eritrean Hilawe Yosef on Behalf of the people who he said represents Amhara ethnic (as if he or his family born Amhara)  contributed $2,000,000 for school in Tembiyen Awaraja  money snached from the starved and unemployed Amhara farmer, He donated the money for Tigrayan because Hilawe said it is a “payback” for they supported ADM during the struggle (literally for hiring them as a puppet to steal money from the Amahara society,and live lavish and as TPLF's Amharic Department).

The other contributor was a government branch called “Ethiopian Electric Power” which donate money to built 2 schools in Tigray (remember at this moment when the event is taking place, millions were starving, the world is in a hot perused of contribution to help the starved in Ethiopia).


The next was Ethiopian Telecommunication donated huge sum of money to built several schools in Tigray.

The other contributor was . Ministry of Ethiopian defense (department of Industries/engineering) contributed huge sum of money for MatChew Awraja in Wereda “MoKoni” to build a preparatory school.

Many numbers of Tigre individuals contributed by millions and hundreds of thousands in single contribution. To mention the few;- Ato Selama Gebru (100,000ብር) (this fellow lives in Nazret and made his fortune in Nazret- unfortunately his son died and said "my son is dead, from now the replacement for my son are the Tigray children and will donate one fully facillitated school in Adi Aferom village and aslo money for a road constraction in that village. He (in other words the kids in Nazret are not his replacment kids, but the Tigrayan kids. Now figure that out, how narrow nationalism is dangerous!!!) 

The next contributers was TPLF member Mr. Alamoudi who donated money for being baptized by the TPLF Ambassador Tewelde Ageme and Assefa Mamo as a pay back for baptizing him to be TPLF member, Mahber LimAt Tigray, ……..many of them in massive and  each of them contributed huge sum of money. To the extent money to built 1 and 2 schools (this is from individual donation). Let me remind you again, 9.6 Million Ethiopoan was starved at that moment when this Tele tone was running.

The point that you need to take a note of it is – that, we the Diaspora opposition and Ethiopian citizens were contributing money for the starved people. Our representatives went to Ethiopia with our contribution with the knowledge of Ethiopian government/TPLF government agreement just to give access for them to donate it to the starved people. It was a tense and repressive momment for patriotic nationalist Ethiopians to hear a starvation again while these TPLF tycoons are sending money to Tigray for school constraxtion. All the TPLF Ministers/officials were all over the world begging for donation to help the starved while Telethon was held for school construction in Tigray!!! At one day- money was collected enough to built 60 new schools in Tigray!!

Note;- The starvation the hunger was bad and broadcasted by german radio and VOA Amharic programs. At that week one dry Enjera was $3.oo that was sold $1.25. some people on VOA and German radio told $10.00 ብር.

Mr. Gezaee tell us your memory, if such is fair, when Ethiopian Electric power corporation (there was power frailer in Addis remember!? it was called LIGHT BEFEREKA) and other government agencies involved in such from its badget and employees and was sending money for Tigray Scool constraction while the people starved, while we the Diaspora also sending money for starved people in Ethiopia from here. Where was the heart of these new “HUMANITARIANS of MELES ZENAWI’s at that time?

This telethon campaign was held in Sheraton Addis in a city where millions of homeless and starved people live where few coraupt individuals and exploiters dance and enjoyed., and where the starved lower government workers and others eat once or twice a day and code was given to it "11 and 5" (no breakfast in the morning you eat if "possible" your lunch and breakfast at 11 and eat your dinner at 11 Alamoudi was thanking TPLF Tewelde Agame of TDA for baptizing him as TPLF for for the first time by coming to his house and allowing his capital to invest his money in Ethiopia. He donated huge money for his Tigray to glorify TPLF. At that moment children and domestic animals (camel, cows….) were dying (evidence was on TV throughout the world) in the Eastern part and some areas as well.

It was the corrupt and narrow nationalist "Iyasu Berhe" (the singer who passed away last year) leading the Telethon. Many of those Tigrayan are milliners who made their investment in Nazret and Amhara and other regions, but they were building school for Tigray not for Nazret or Harar. Ogaden where millions were starved in that week. Is it fair? This telethon campaign was held in Sheraton Addis in a city where millions of homeless and starved people live. Where was your Ethiopiawinet heart at the time? Now you have the nerve to attack Gidey or anyone for wishing Meles’s death?

በማለት ነበር ሊሸሽጉት የሞከሩትን  ያደፈውን መስተዋታቸውን አውጥተው እንዲመለከቱት የጠየቅኳቸው። ቀጥየም ስለ ማሕበር ተጋሩ ሰሜን አሜሪካ የሚባለው በቅንጅት መሪዎች ላይ ያስተላለፈውን ለመለስ ዜናዊ የጻፉትን ደብዳቤ በጨረፍታ እንዲህ ስል አስታወስኳቸው።

“Those who of you who now are sorry for Meles Zenawis ailment and felt as if you have humanity to all human being is a fake so to speak. If indeed those are crying with sympathy too much for Meles Zenawi should have shown similar sympathy to those TPLF/Meles victims as the result whom some are dead and disappeared and some are crippled and their life destabilizedsome languishing in known and unknown horrible prison cells.

Are not those same elements who wrote a letter of appeal to their Prime Minister to execute opposition “extremists” /the terminology that should belong to TPLF) with “YEMAYADAGIM IRMIJA” Do you know who they are? They are members of the “UTNA” (Union Tigrayan in North America), now this like members and individuals are trying to attacking Gidey ZeraTsion for his personal view (because Gidey similarly labeled Meles Zenawi worst extremist individual and wish him to go away for good).

 How is that the TPLF sympathizers have all rights to seek death to the opposition with the “YemaYadagim Irmija”, but not Gidey when it comes to wish Meles’s God’s YemaYadagim Irmija ordered by God? They are telling Gidey to be polite to all human creation/ You mean to tell us all in a sudden TPLFiets are now coming with Human face after their leader is caught by God’s power?

If you are now wearing human heart and felt humanity to all humans, then what I want TPLF followers to do is not what Meles Zenawi’s admirer Gezaee.H is advocating like the following


(I think Meles Zenawi is doing a good job lately. TPLF has to implement the article 39 now. So that people can live in peace in their respective region becoming countries. They have aleady called Tigray. Let it be Tigray republic now.” Gezaee H. July 21, 2012 at 2:04 pm Aigaforum discussionforum,)
I was not shock by such silly elements. But, I said, nstead what I am asking you all is the following if you are for human rights and kind heart as you all TPLF followers are now demanding from Gidey ZerAsion and others,  the opposition to change. Here is what I said about change and kindness that you primary need to do first before demanding change of heart from the opposition towards your leader Meles Zenawi;-

“If change to come and vengeance to replace by Christian concept of pardoning the sinner- the abuser in power have to admit he sinned and asked for forgiveness in detail what he did as a sinner without reasons of walls or barbed wire or armed guards to hide from the eye of the people/justice. Mr.Gezaee.H – I want to tell you this- I am not for bloodshed or vengeance but will speak out for the rights of my people . If you are asking people to change – you take the role of being reconciler and that is to urge your leader to establish special prosecution for TPLF victims. Change will come immediately.”

 ይህ ነበር የሳምነቱ ውሎየ ባጭሩ።የሞሶለኒ ተወካይ ግራዚያኒ ኢትዮጵያን ሲረግጥ ሲያበጣብጥ አንድ ሰሞን ወሬው ሲሰወር’ እርጉሙ ግራዚያኒ ሞተ፤ተጠለፈ፤ታመመ፤ የት ሄደ? አረ በዚያው ይዞት ይሂድ! ብለው ሲመኙ እና ሲጠይቁ “ግራዚያኒን ወድደውት ሳይሆን ያችን የናፈቋትን ነፃነት ከማስተንፈስ አኳያ ነበር።  አሁንም መለስ ዜናዊ የት ሄደ? ሞተ? ጠፋ፤ታመመ፤ታሰረ፤ ምን ነካው?  አረ በዛው ይዞት ይሂድ! ብለው ሲሉ እና ሲጠቁ  የግራዚያኒን ታሪክ እና ሁኔታ ስላስታወሳቸው መሆኑን ልብ በሉ። መጥፎ መሪ የአንድ አገር የወደፊት ዕድል ብቻ ሳይሆን የሚያበላሸው፤የሕዝቡ ሞራል እና ባሕልም ጭምር ነው፡ያልኩበት ምክንያትም ከዚህ አኳያ ነው።

ሕዝቡ ሲራብ የመለስ ተከታዮች ስለ ትግራይ ትምህርት ግምባታ ገንዘብ ሲያዋጡ የሕዝቡ ሞራል እና ባሕል፤ አርቆ የመመለክት ክብደታቸው አበላሽቶታል። ስለዚህ ብዙ ሰዎች የመለስን መወገድ የሚመኙት ለኢትዮጵያ ወጣቶች እና ለሕዝቡ ሞራል እና ባሕል መበላሸት ተጠያቂው ብልሹው እና ጠማማው መለስ ዜናዊ ስለሆነ ነው።

“ስለ ኢትዮጵያ የሚያስብ ሁሉ በሰላም ይክረም” ነው ያለው የ“ቀለበትዬን ስጧት” ደራሲ ወንድሜ በልጅግ አሊ!  ሓምሌ 2004 ዓ.ም  ለመለስ አልሆነችም እና ክረምቱን ይከርማል ብላችሁ ነው? ወንድሞቼ ሁሉም የእግዚሃር ጥበብ ነውና “ይዞሕ ይሂድ” ከመባል ያድነን።

ወንድሜ አበበ ገላውም “መለስ ዜናዊን አስደንግጠህ ለክፉ በሽታ ጣልክብን ተብለህ ከመከሰስ ያድንህ። ድሮም ያልኩህ ይኼው ነበር፤ እንኳን አዳራሹ ላይ አልሞተብህ። ከዚያ ወዲያ ግን ጠበቃ መፈለጉ ለኛ ቀላል ነው። አስደንግጠህ በልጄም የሚባል ሀገር እንዲሄድ ማድረግህ ግን ያገሪቱን ገንዘብ እንዲባክን ምክንያት ሆነሃል; ቢሆንም ይቀር ብለነሃል; ገንዘብ የታባቱ!”
 ”በልጅግ እንዳለው በሉ ደህና እንክረም። ጌታቸው ረዳ (አትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) www.ethiopiansemay.blogspot.com












Sunday, July 15, 2012

ቆንጆዋን ልጅ በተሰበረ መነጽር


Note from the Editor;----
It is obvious that TPLF's hate monger propaganda against EPRP which TPLF sees EPRP as NewTeNga and  Amhara/Neftenga party (though some of the founders and many of the leaders and members and fighters of the party "EPRP" are from Tigray!!) for the last 21 years misguided the thinking of many youngsters and even the young journalist those of the opposition journalists like that of Fitih GazeTa Mr.Temesgen Desaleng trusted TPLF's filthy propaganda.  Simply sad to read Mr.Temesgen the way TPLF and Derg referred EPRP! What was Temesgen's intention to use such filthy terminology he learned it from TPLF?  To Join the Joiner.....? If that is the case, well, EPRP as a Party or as individual is not allowed to  live in Ethiopia and write as Temesgen is allowed and licenced to be a commentator of any paper in Ethiopia to defend all sorts of true or false propaganda against EPRP. What makes you think EPRP is dead and no one will correct your young mind?  Well, here is Beljig Ali's response to you if you are ready to re correct yourself.

ቆንጆዋን ልጅ በተሰበረ መነጽር
በልጅግ ዓሊ

ተከታታይ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የሚያቀርባቸውን ጽሁፎች አነባለሁ። በብዙዎቹ ብስማማም በመሃል ጣልቃ በሚያስገባቸው አንዳንድ ትንታኔዎች ላይ አልስማማም። አለመስማማትም ሳይሆን መታረም አለባቸው የሚል እምነት አለኝ።

ተመስገን <<የኔ ትውልድ>> የሚለውና <<ያ ትውልድ>> የሚለው ነገር አለው። ከብዙ ጽሁፎቹ እንደምንረዳው “የእሱ ትውልድ” ከቀይ ሽብር በኋላ የተፈጠረው ሲሆን፣ “ያ ትውልድ” የሚለው ደግሞ ከቀይ ሽብር በፊት ያለው ይመስላል። ብዙውን ትንታኔው የሚያተኩረው “ያ ትውልድ” ሞኝ፣ ለማይረባ ነገር መስዋትነት የከፈለ፣ ቅራኔዎችን በሚገባ ባለማያዙ የተጋደለ አስመስሎ ያቀርብና . . . የእሱ ትውልድ ግን “አርቆ አሳቢ ፣ በእንቶ ፈንቶ የማይጣላ፣ ቅራኔን በበሰለ ሁኔታ የሚመለከት” አድርጎ ለመሳል ይሞክራል። ይህ የእሱ ትንተና ከእሱ ጽሁፍነት አልፎ እውነት ቢሆን በጣም አስደሳች ነበር። እውነቱ ግን ሌላ ነው።

ተመስገን ትውልድ በአብዛኛው በእኔ ትንታኔ <<የድጋፍ ወረቀት ሠራዊት>>ነው ። ይህ ደግሞ ካለ ምክንያት አይደለም። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ትግል የግል ጥቅም ከፖለቲካ መድረክ ላይ ማጋበስ የተጀመረውም ከቀይ ሽብር በኋላ ሆኖ እናገኘዋለን። ቀይ ሽብር በኅብረተስብ ውስጥ የፈጠረው ፍርሃት ዜጎች የፖለቲካ ጥያቄ ቢያነሱ ሊደርስባቸው የሚችለው አሰቃቂ ሥቃይ በእውን እንዲያዩት ስለተደረገ ሃገርን ከሚመለከት ማናቸውም ጉዳይ መራቅን የመርጠ ትውልድ ነው። ይህንንም አያይዞ ለግል ጥቅም መሮጥ በሰፊው ተጀመረ። ከቀይ ሽብር በኋላ ለሃገር መሞት ማስከበሩ ቀርቶ፣ የድህንነት ሠራተኛ፣ የአየር በአየር ነጋዴ፣ “የሕዝባዊ ድርጅቶች” (የአኢወማ፣ አኢሴማ ፣ መኢሠማ . . .ወዘተ) መሪ ሆኖ መመረጥ ወይም መሳተፍ ጥቅም እንዳለው እየታወቀ መጣ።

በዚህም ምክንያት አብዮታዊ አስተዋፆ የሥራ፣የትምህርት(በሃገርም ይሁን በውጭ )፣ አልፎም ተርፎ ሕይወትን ለማሰንበት አስፈላጊ ሆነ። አብዮታዊ አስተዋፆ የማይጠየቅበት ቦታ ቢኖር ብሔራዊ ውትድርና ነበር። ለዚህም ነው በዘመኑ የነበሩ ወጣቶች ለጦላይ (ብሔራዊ ወታደር ማሰልጠኛ ጣብያ ) የድጋፍ ወረቀት አያስፈልግም ብለው የተሳለቁት። ለሃገር፣ ለሕዝብ፣ ለዴሞክራሲ መሞት የተዋረደውና ለግል ጥቅም መሮጥ በሰፊው የተጀመረው ያኔ ነው።

ይህ “የድጋፍ ወረቀት ሠራዊት” በደርግ አብዮቱ ውስጥ የሚያደርገው ተሳትፎ እየታየ የሚያገኘውን ጥቅም ከሃገር ፍቅር ይበልጥ ሲያሳድድ የነበረ ነው። አልፎ ተርፎ ንቅዘቱ በሠራዊቱ ውስጥ ሳይቀር በጉልህ ይታይ ነበር። ታላላቅ የጦር መኮንኖች በተራ አለብላቢ ካድሬዎች ይታዘዙ እንደነበር የሚረሳም አይደለም። ከዛም አልፎ የሃገሪቷን ጥቅም በገንዘብ የለወጡ ስንት ናቸው? ታሪክ ይፍረደው!

ከዚህ የግል ጥቅም ሩጫ ጋር ለሃገሩ የተስውትን ጅግኖች ማዋረድ በደርግ እንደ አብዮተኝነት ሲያስቆጥር በሌላ በኩል ደግሞ ለግል የሞራል ማካካሻ፣ በሃገር ላይ የሚደረገውን ክህደት ማሳመኛ ሆኖ ማገልገል የጀመረው ከቀይ ሽብር በኋላም ቢሆን እስከ አሁን በሰፊው እንደቀጠለ ይገኛል። ለዚህ ነው የዘንድሮ ፖለቲከኛ በአንድ ወገኑ ኢንቨስትር በሌላው የተቃዋሚ ድርጅት መሪ ሆኖ የምናገኘው። አስረጅ የምጠየቅ አይመስለኝም። <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> በሚል መፈክር ላይ ተነስቶ የዛን ትውልድ ያበረከተውን ከፍተኛ አስተዋፆ ማጣጣል የተጀመረው በደርግ ወቅት ቢሆንም አሁንም በሰፊው እንደቀጠለ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ በቂ ምክንያት አለው።

በዚህ ወቅት በአብዮታዊ ተሳትፎ ጥቅም ያጋባሱ ግለሰቦች ከቀይ ሽብር ማግስት ያ ቆራጥ ትውልድ ያለቀው አልቆ የተረፈው በእሥር ተንገላቶ፣ ሞራሉ በቀይ ሽብር ተጎድቶ፣ እንዳይሰራ፣ እንዳይማር ያጠቆርከው የአብዮት ሸማ እጠብ እየተባለ የድጋፍ ወረቀት ተክልክሎ በነበረበት ወቅት አብዮታዊነታቸውን በማሳየት

ጥቅም ያገኙ ግለሰቦች፣ በተሰጣቸው ሰፊ የትምህርት እድል በመጠቀም ዛሬ ምሁራን እየተባሉ ይገኛሉ። እነዚህ ግለሰቦችም ይህንን <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> የሚለውን መፈክራቸውን ለመሸጥ በሚያደርጉት ጥረት የዛን ትውልድ የዴሞክራሲ ትግል ወደ ታች በማውረድ የቃላት ጦርነት እንደነበር ሲያስረዱ ይታያሉ። ሌሎችም ይህንን የተሳሳተ አመለካከት ይዘው ያስተጋቡ። ሃቁ ይህ አይደለም ሊላቸው የሚችለው ትውልድ

ግማሹም ከመቃብር በታች ነው። ሌላውም በሃገር ውስጥ ስደት የድጎማ መምህር ሆኖ ቀርቷል። የተረፈው ደግሞ ከድርጅት ድርጅት እየቀያየረ ያንን ትውልድ መስደብ የፖለቲካ አዋቂነት መጀመሪያ አድርጎ ሲመጻደቅ ይታያል።

 እውን ያ ትውልድ የተሰዋው በቃላት ልዩነት ነበር?
ተመስገን “‹‹ይቅርታ›› የኢህአዴግ ቃጭል? ወይስ…” በሚለው ጽሁፉ ውስጥ

“ የዚህ ትውልድ ፖለቲካ አንድምታ፣ ከያ ትውልድ የፖለቲካ አንድምታ እንደወረደ የተተገበረ ነው፡፡ በመጠፋፋት ሳጋ እና ማገር የቆመ ማለቴ ነው፡፡ ሀቅ ነው! ያ ትውልድ ከፍ ሲል በርዕዮት አለም ልዩነት እርስ በእርሱ ተጠፋፍቷል፡፡ ዝቅ ሲልም ‹‹በቃላት አጠቃቀም›› ተገዳድሏል፡፡ ለምሳሌ አንዱ

‹‹ወዛደር›› ሲል ሌላኛው ‹‹ላብአደር ነው የሚባለው›› ብሎ ጦርነት ሲያውጅበት አይተናል፡፡ ‹‹ኢህአፓ›› የተሰኘው ነውጠኛ ድርጅት ‹‹እናቸንፋለን!›› ሲል በመፈከሩ ብቻ፣ መኢሶን የተባለ ሌላ ነውጠኛ ‹‹አብዮተኛ እናሸንፋለን!› እንጂ እናቸንፋለንአይልም››

ሲል በፈጠረው የሆሄያት ልዩነት ወደጎዳና ላይ መገዳደል መሸጋገራቸው የትላንት ታሪክ ነው።” ዛሬ ተመስገን በ”ላ” በ “ቸ” ፊደሎች ተላለቁ ብሎ የሚሳለሰቅባቸው ወጣቶች የተሰውበትን ራዕይ በዘንድሮ የነጻ ገበያ ፖለቲካ አንጻር( የግል ጥቅም የለውምና) ለማይረባ ነገር የተደረገ መስዋዕትነት ተብሎ ሊታይ ይችላል። ውስጡ ለነበሩት ግን ምን ያህል ከግል ጥቅም በላይ የሃገር ፍቅር ጎልቶ ይታይ እንደነበር እውነትና ታሪክ ይመሰክራሉ።

 በኢሕአፓና በመኢሶን መካከል የነበረውን ልዩነት ወደ ቃላት አውርዶ፣ ጉዳዩን አልከስክሶ መተንተን የሚሰጠውን ጥቅም (ከሞራል ማካካሻ ባሻገር) ሊገባኝ ባይችልም፣ ከተራ የፖለቲካ ትንተና በላይ ሊሆን እንደማይችል እረዳዋለሁ። ይህን ትንተና ሄዶ ሄዶ ለሃገራቸው የተሻለ ሥርዓትን እናመጣለን ብለው <<ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ፣ የዴሞክራሲ መብት ያለገድብ . . . >> ሌሎች መፈክሮችን አንግበው የተሰውቱን ወጣቶች በ“ቸ” ና በ”ሸ” ልዩነት ተላለቁ ብሎ መደምደም ተገቢ አይደለም።

 ዛሬ ከወያኔ ጋር መስራትና አለመስራት የሚለው ጥያቄ ጉልህ እንደሆነ ሁሉ ከደርግ ጋር መስራት አለመስራት የሚለውም በዚያ ወቅት ገሃድ ነበር። ዛሬ ሕዝባዊ መንግሥት የሕዝብ ጥያቄ እንደነበር ያኔም የወጣቱ መፈክር ነበር ፣ ያኔ የዴሞክራሲ አለገደብ ጥያቄ ያስገድል ያሳስር እንደ ነበር ዛሬም አያሸልምም። ያኔ ደርግን የሚቃወሙትን አናርኪስት ፣ ፀረ ሕዝብ ተብለው ይገደሉ እንደነበር ዛሬም አሸባሪ ፣ ፀረ ሰላም . . . እየተባሉ አይለቀቁም። እንዲህ ከሆነ ታዲያ የዛን ወቅት ትግል ለቃላት የዘንድሮውን ለዴሞክራሲ የሚደርገው ምኑ ነው? ምንአልባት ትግል ነውና የተሠሩ ስህተቶች ይኖራሉ። እንዚያን በትክክል ካልተተነተኑና ያንን ትውልድ ለመውቀስ ብቻ ሲባል <<ጽንፈኛ>> የሚል ቃል መጠቀም ቆንጆዋን ልጅ በተሰባበረ መነጽር ተመልክተው አስቀያሚ ነች ከማለት ተለይቶ አይታይም።

 ዛሬ ለሃገሩ ቆሞ የሚታገል እያነስ በመጣበትና የግል ጥቅም ጎልቶ የሚታይበትን ምክንያት አበጥሮ ማየት ያስፈልጋል ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሃገሩ ሟች ትውልድ ለማፍራት ከተፈለገ ቀደም ለሃገራቸው በንጽሁ ዓላማ የተስውትን ጀግኖች ታሪክ የጠጅ ቤት የአግዳሚ ወንበር ጨዋታ አለማድረግ አስፈላጊ ነው።

እኔ በማምንበት በጀግኖች ታሪክ ላይ ጀግንነት ይፈጠራል። ጀግኖችን አዋርዶ ፣ የሞቱበትን ግዙፍ ዓላማ አጣጥሎ በቃላት ልዩነት እንደሆነ አድርጎ መተንተን ነገም ለሃገር የምንሰዋበት ምክንያት ሊጣጣል እንሚችልና እንደ ዘንድሮ ደልቃቃ ፖለቲከኛ <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> በሚል መፈክር ሥር ተሰባስቦ አነስተኛ የሆነውን መስዋትነት ለመክፈል አለመዘጋጀትን ያመጣል። ተመስገን ከላይ በጠቀስኩት ጽሁፉ እንደገለጸውም መታሰርን እንደ ታላቅ መስዋእትነት ተቆጥሮ በወያኔ የፊርማ ስነ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ በራስ ላይ የእንጥልጥል ፍርድ አስፈርዶ መፈታትንም ያስከትላል። ለሃገር፣ ለሕዝብ መሞት ከገለባ የቀለለ ለግል ጥቅም መቆም ደግሞ ከተራራ የገዘፈ ሲደረግ እንዲዚህ ነው።

 ውድ ታናሽ ወንድም ተመስገን . . . ለዓላማ መሞት ከባድ ነው። መሣሪያ ይዞ ሊገድል የቆመን ፋሽሽት ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ፣ የዲሞክራሲ መብቶች አለገደብ እያሉ መሞት "ቸ ቸ ቸ" ወይም "ላ ላ ላ" እያሉ መሞት አይደለም። የመጻፍ መብት ስትከለከል “አደፍርስ “ የሚባል የማባዣ መሣሪያ ሠርቶ

በድብቅ የሚያምኑበትን ጽፎ መበተንና ከዚያም ተይዞ መገደል “ቸ” ና የ”ላ” ትግል ውጤት አይመስለኝም። የተገፈፉትን ነጻነት በትግል የማግኘት የዴሞክራሲ ጥያቄ እንጂ!

በእነዚያ የዴሞክራሲ ጥያቄ አንግበው በተስዉ ጀግኖች ልቦና ውስጥ ምን እንደነበረ ከኢዲስ ዘመን ወይም ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተገኘም ንቃት አይተነትነውም። ያንን ለመገንዘብ በእነሱ ቦታ ራስን ማስቀመጥ ያስፈልጋል። ዛሬ በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ብዙ ቅጽል ስም ከመንግሥት ደጋፊዎች ይወጣላቸዋል። ይህንን ስም ማጥፈት የሚያምኑ ይኖራሉ። ከሁለት አስርተ ዓመታት በኋላ አንድ የደላው ጋዜጠኛ በአሁኑ ወቅት ያለው ትግል “ዓባይ ይገደብ አይገደብ ነበር” ብሎ ቢጽፍ የዘንድሮውን ሁኔታ ተነተነ ማለት አይቻልም። እነሽብሬም ፣እነ ተስፋዬም ፣ እነ አስፋ ማሩም፣ እነ ጋይምም በዚህ ምክንያት ተሰዉ ማለት አይደለም። ትግል ሙሉውን ሳይሆን በቅንጣቢ መተንተን የሚመጣው ስህተት ይህንን ይመስላል።

 ጽሁፌን ለማጠቃለል ያህል ታላቁ ደራሲ ዩሐንስ አድማሱ ከዚህ ዓለም የተለየው በእድገት በኅብረት መጀመሪያ ወቅት ላይ ነበር። ከዚህ ከሚባለው ክፍፍል በፊት በመሆኑ እድለኛ ነው። እዚህ ውስጥ በቃላት አጠቃቀምም ቢሆን እንኳን ለመዶል መሞከሩም አስፋላጊ አይደለም። ይህም ቢሆን ቁንጽል የሆነ ጽሁፍ ጠልቆ ታሪኩን ለማያውቅ ግለስብ ሌላ ትርጉም ይሰጣል። ዮሐንስ አድማሱን ለመጥቀስ ከተፈለገ ውብ የሆኑ ሥራዎችን ከዚህ ክፍፍል ውጭ ለብቻቸው አንስቶ መወያየትን በግሌ እመርጣለሁ።

ስለ ያ ትውልድ የሚያስብ ሁሉ በሰላም ይክረም !
በልጅግ ዓሊ Beljig.ali@gmail.com








Thursday, July 12, 2012

“አለባብሰው ቢያርሱ ……….”


I have two topics for you all. One is for the Diaspora Ethiopian Lawyers

This is Home Work for Ethiopian Lawyers living in the Diaspora. I want all the so called Ethiopian Lawyers to do something about these Animals in Saudi Arabia who are still in their barbaric stage. Ask us financial contribution to sue the Saudi beasts in the world court. Send an investigation now!!!!!!!!! At least try

(1) !!!!!!!!! Meles is killing our people inside and outside Ethiopia intentionally to destroy Ethiopia for ever its pride.

I like all my readers to see the following video how the Saudi Arab Human Animals in Jedha collaborated with the mercenary Meles Zenawi of Ethiopia caught on Camera abusing Ethiopian Woman. How long are these beasts who look like human, but worst beasts than the God created Animals of the jungle on this civilized world continue to abuse Ethiopian Women? How long is Meles Zenawi selling Ethiopian Women to his Arab masters for such sad situation? Let the Arabs remind their memory when that time comes of accounting. It is time a change to come to Saudi Arabia as the rest of the Arab world. It should have come first before any of them. These are 16 police officers of Saudi calling themselves Men struggling to chock one poor woman's neck as if she is a Tiger or a lion that intimidates these so called themselves MEN. There is time for all said King Solomon!!!!!!! Editor Ethiopian Semay.

ከአዘጋጁ ማስታወሻ፦

ከዚህ በታች የሚቀርበው ጽሑፍ “አብረሃ በላይ” በሚያዘጋጀው  “ኢትዮሚዲያ” ተብሎ በሚታወቀው የነ ብርሃኑ ነጋ እና መሰል ግለሰዎች እና ቡድኖች የሚለቀልቁበት እና የሚለቃለቁበት ድረገጽ ላይ በሕዝብ እንዳይነበብ “የታገደ” ለኢሳቱ ጋዜጠኛ ለፋሲል የኔዓለም ከእውቁ ገጣሚና ጋዜጠኛ “ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን” የተሰጠ መልስ ነው። መልካም ንባብ። (ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
Fasil YeneAlem of ESAT

 “አለባብሰው ቢያርሱ ……….”
ከወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

                 አሀዱ

ዕለተ ሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2004 ዓም አመሻሹ ላይ ሞባይሌ ተንጫረረች፡፡አንስቼ ወደ ጆሮዬ አስጠጋኋት፡፡ ጓደኛዬ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰለሞን ነው፡፡

"ሳይቸግርህ ሰዎቹን ካክተህ...." ያለ መሰለኝ፡፡ "ምን አልከኝ?" አልኩት የተናገረ ማረጋገጥ "የቀድሞው አለቃህ ፋሲል የኔዓለም በቃሊቲ ምስጢሮች የተነሳ የፃፈውን ኢንተርኔት ላይ ተመልከት" አለኝ፡፡

በማግስቱ ማክሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2004 ዓም ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ሌላው ጓደኛዬ አለማየሁ ባዘዘው "ፋሲል ወንዱ ልክ ልኬን" እንደነገረኝ ደግሞ አበሰረኝ፡፡ ወዲያው ወደኢንተርኔት ቤት ጎራ አልኩ፡፡ እናም የፌስ ቡክ ገፄን ከፈትኩት፡፡ ሁለት መልዕክቶች አሉኝ፡፡ በየተራ ከፈትኳቸው፡፡ አንደኛው ቅዱስ ያሬድ ኤፍሬም የተባለ ሰው የላከልኝ ነው፡፡ ሰባት ጊዜ ወድቆ የተነሳውን "ቅዱስ ያሬድ" እያሰብኩ መጠቆሚያ ቀስቱን ወደፖስታው መራሁት፡፡

የፋሲል የኔዓለም ፅሁፍ ከፊቴ ተዘረጋ፡፡ አነበብኩት፡፡ ሁለት ዓይነት ሥሜት ተሰማኝ አንድም ደስ አለኝ፡፡ መፅሐፌ በዓለም ዙሪያ እየተነበበ ነውና፡፡ አንድም አዘንኩ፡፡ ፋሲል የኔዓለም በእያንዳንዱ የፅሁፉ መስመር ውስጥ ሲንጨረጨር ታየኝከልብ አዘንኩለት!!

                     ክልዔቱ

እያዘንኩ ሁለተኛውን መልዕክቴን ለማየት መጠቆሚያ ቀስቱን ወደ ፌስ-ቡኬ ፖስታ ሰደድኩት፡፡ የፖስታው መሸፈኛ ተነሳልኝ፡፡ የጋዜጠኛ ተስፋዬ /አብ ፅሁፍ በኮምፒውተሩ ስክሪን ላይ ፈሰሰ፡፡

ተስፋዬ "የቃሊቲ ምስጢሮች" መፅሐፍ ውስጥ ካነበባቸው ታሪኮች መሀል በዝዋይ ማረሚያ ቤት 14 ዓመት ሙሉ የታሰረውና የመፈቻውን ቀን ናፍቀውን ሁሴን (የኦነግ ወታደር የነበረ) ታሪክ ነቅሶ አውጥቷል፡፡ እናም እጥር ምጥን ባለው ፅሁፉ እንዲህ ብሎ አሳርጓል፡-

"...እነሆ እኔም ተክዤአለሁ፡፡ ሁሴን በኦነግነት ተይዞ የታሰረው ሌንጮ ለታ እና ዲማ ነገዎ መራ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ ልክ እንደሁሴን በአስር ሺህዎች በወያኔ ማጎሪያ ተወርውረዋል፡፡ የት እንደደረሱ ማይታወቅ የተረሱ እስረኞች ቁጥር ዳርቻ የለውም ይህንን እያሰብኩ የወሰንሰገድን መፅሐፍ አጥፌ ተከዝኩ፡፡...."

እኔም ልክ እንደተስፋዬ ተክዤ የፌስቡክ ገፄን ከረቸምኩት፡፡ ሆኖም የተከዝኩትና ያዘንኩት ለእኔ አልነበረም፡፡ ለቀድሞው "አለቃዬ" የእስር ቤት ጓደኛዬ የአሁኑ የኢሳት ፊታውራሪ ለሆነው ፋሲል የኔዓለም ነው

                     ሠለስቱ

አንጋፋው ምፃ ተሾመ ምትኩ "አስራት" ሚል ርዕስ ባሳተመው ካሴት ሁሌም ሳደምጠው ሚመስጠኝ አንድ ዘፈን አለ፡፡ "እሹሩሩ ማሞ" የሚል፡፡

".....እሹሩሩ ማሞ እሹሩ ማሙዬ

ዘመን አሳለፍኩኝ አንተን ተሸክሜ አንተን አንጠልጥዬ..."

ይላል ምፃዊው፡፡ ልጁን እያባበለ ወይም እያጫወተ አይመስለኝም፡፡ ሚያድግና ከትከሻ ማይወርድ ልጅ በመሆኑ እየተማረረ እንጂ፡፡ እኔም እንዲሁ እሹሩሩ ማለ የምችል አይመስለኝም እነፋሲል የኔዓለም ግን አሁንም እሹሩሩን ይሻሉ መሰለኝ ማለቃቀስ ጀምረዋል

እንደመሰለኝ ለፋሲል ማለቃቀስ ምክንያት ሆነ የኔው መፅሐፍ ነው አንድ አንባቢ መፅሐፌን አንብበው ግምማዊ ፅሁፋቸውን ኢትዮ-ሚዲ እና ኢኤም ኤፍ በተባሉ ድረገፆች አውጥተዋል፡፡ ሆኖም ገምጋሚው ስማቸውን አልገለፁም፡፡ ፋሲል የኔዓለም "ጎንትለውኛል" ባይ ነው በእሱ አባባል "ስብዕናውን ማጨቅየት" ነው በግምገ ሰበብ ብዕራቸውን ያነሱት፡፡ ፋሲል ለእኚህ "ሥም የለሽና ሥም አጥፊ" ገምጋሚ ምላሽ ባይሰጥ ደስ እንደሚለው፣ ግን ደግሞ እንዳልስቻለው በመጀመሪያው አንቀፅ ያትታል

"...በህይወቴ ሙሉ ደስ ሳይለኝ ከፃፍኳቸው ፅሁፎች መሃል አንዱ ይህ ነው፡፡.." ብሎ ይቀጥላል፡፡ እናም ሶስት ገፅ ሙሉ የመልስ ምት ያለውን ፅሁፍ ያስነብበናል፡፡

የእስር ቤት ጓደኛዬና የቀድሞ "አለቃዬ" ችግርም ከዚሁ ከመንደርደሪያው አንቀፅ ይጀምራል፡፡ ደስ ሳይለው ሚፅ ሰው፣ ደሰታውን ሚነጠቀው በራሱ ዕጅ ነውና፡፡ ስለዚህም አዘንኩለት፡፡ ደስ ያለውን ትቶ ደስ ያለውን ማድረጉ፡፡ ነው? ቢሉ መነውን ያላወቀ መድረሻውን እንደማያውቅ ሳይታለም የተፈታ ሐቅ ነውና፡፡ የፋሲልም መል ፅሁፍ እንደዚያው ነው። ዒላማውን የሳተ "ለስም የለሹ" መፅሐፍ ገምጋሚ መልስ ብሎ ከቸከቸው 3 ገፅ ፅሁፍ ሚሱ ነጣጠረው በእኔ "የቃሊቲ ምስጢሮች" ደራሲ ላይ ነውና። ስለዚህ የፋሲል መል ምት ገና መነሻው ነው የከሸፈው ዓላማ ሲከሽፍ ደግሞ ያሳዝናል ቢሆንም......

አርባዕቱ

የሆኖ ሆና ፋሰል የኔዓለም ለስም አልባው ገምጋሚ በሰጠው ምላሽ ማለ የፈለገው “በማተ ልዳኝ!"ነው በማተቤ ዳኙኝ እንጂ ካለሥም ስም አትስጡኝ ነው። እንዲያ ከሆነ ዘንዳ ጥያቄው አንድና አንድ ነው ሚሆነው። ማነው ባለማተብ!? ማነው ማተቡን የበጠሰ!? ማነ የተበጠሰ ናተቡኑን ለመቀጠል ባህር ማዶ የተሻገረ!? ማነ ከነማተቡ ያለ!? መል ከባድ አይደለም ቀላልም አይደለም ሁሉም የማተቡን ልክ ሚመጥነው በአንገቱ ልክ ነውና። ቢሆንም ያገሬ ሰው “አንገት የተፈጠረው አዙሮ ለማየት ነው” ሚለው እንዲሁ ለይምሰል አይደለም አንገት ለማተብም አዙሮ ማየትም ይጠቅማል ነው እናም እስ የ”አፄ ፋሲል”ን መልስ ተብዬ ፅሁፍ ዞር ዞር ብለን እንፈትሸው በየተራ፡-

"....የቃሊቲ ባልደረባዬ የነበረው ወሰንሰገድ /ኪዳን መፅሐፍ ማሳተሙ እጅጉን ተደሰቻለሁ ወሰን ብዙ ተሰቃይቷልአብዛኛውን ጊዜ እሱ ባልፃፋቸው ፅሁፎች /በዋና አዘጋጅነት ስሙ ስለተቀመጠ/ ፍርድ ቤት መላልሷል፡፡… ይላል ፋሲል ስለእኔ

ይገርማል! ፋሲል ማለ የፈለገው ጋዜጠኛ አይደለም፤ አይፅፍም፤ ሌሎች በፃፉት ነው ሲከሰስ የኖረው ነው እንደእውነቱ ከሆነ አንድ ጋዜጣ ከዳር እስከዳር ብቻ (በዋናአዘጋጁ) እንደማይለቀለቅ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው። በጋዜጣው ለወጡ ፅሁሮች ደግሞ ሙሉ ኃላፊነቱን ሚወስደው ዋና አዘጋጁ ነው። እኔ ለበርካታ ዓመታት ይህንን ኃላፊነት በፅናትና በቁርጠኝነት ተወጥቻለሁ ኃላፊነት ከበደኝ ብዬ አላፈገፈግኩም አልሸሸሁም የፈረንጅን እርጥባን ለመቃረም ባህር ማዶ አልተሻገርኩም ግንባሬን አላጠፍኩም። ለፋሲል የኔዓለም ምስጢር የሆነበት ታዲያ ምኑ ነው!? ቀድሞ ነገር ፋሲል ይህንን ማለ ምን የሞራ ብቃት አለው!?  መቼ ወደነፃው ፕሬስ መጥቶ፣ መቼ ጋዜጠኛ ሆኖ ነው!?  "”መቼ መጣሽ ሙሽራ መቼ ቀነጠስሽ ሽምብራ” ሚባለው እንዲህ ያለ ነገር ሲገጥም መሰለኝ፡፡ ደርሶ ጀግና መምሰል፣ እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ ማለት ትርፉ ዘበት ነው። ጎበዝ ሰው ይታዘባል!!

                   አምስቱ

…"...ወሰንን በሥራ ዓለም ብዙ አላውቀውም። አዲስ ዜና ከሁለት ወር በላይ የሰራ አይመስለኝም ከአራት ቀናት የበለጠ ቢሮ ውስጥ ተገናኝተን የምናውቅ አይመስለኝም…ብዙ ጋዜጠኞቻችንን የሚያዘናጋብን የ‹ጀበና› ቤት ደንበኛ መሆኑም ብዙ እንዳላውቀው አድርጎኛል፡፡…” ይላይ ፋሲል፡፡

አባባሉ ሞላ ጎደል ውነ አለው ጭቦ ይጎላበታል እንጂ፡፡ እርግጥ ነው አዲስ ዜናን ስንሰራ ብዙ አንተዋዋቅም፡፡ ልንተዋወቅም የምንችልበት ሁኔታ አልነበረም እሱ ከዶ/ ብርሃኑ አፍ የሚንጠባጠብ የሥልጣን ፍርፋሪ ለመለቃቀም ውሎ አመሻሹን ሲባዝን እኔ ቢሮ ነኝእሱ ከፖለቲከኞቹ በላይ ፖለቲከኛ መስሎ ለመታየት ሲንደፋደፍ እኔ ከሕዝብ ጋር ነኝ ሕዝብ ውስጥ የሕዝቡን የልብ ትርታ እያዳመጥኩ

አንድ አብነት ብቻ ልጥቀስ፡- ፋሲል የኔዓለም የዶ/ ብርሃኑ ነጋ ነጠላ አቀባይ ነኝ እያለ ሲያሸረግድ (በወርሃ ነሐሴ 97 ዓም ሁለቱን ሳምንታት)  እኔ ባህርዳር እና ጎንደር ከተማ ውስጥ ዘገባ ላይ ነበርኩ፡፡ ጋዜጠኝነት ሕዝብ ውስጥ እንጂ ፖለቲከኞች ቢሮ ውስጥ ብቻ ሚገ አይደለም ያለመተዋወቃችን ምክንያት ይኸው ነው እኔ የሕዝብ እሱ የሹመኞች ወገን መሆናችን፡፡

ይልቅስ የገረመኝ "ወሰን የጀበናቤት ደንበኛ መሆኑ አልተዋወቅንም" ያለው ነው ጫት ቤት ማለቱ ነው ጫት ይቅማል ለማለት ነው እንዲህ ፍርጥ ፍርጥርጥ አድርጎ መናገር እያለ እንደ"ሥራቤት" የምን ነገር ማዟዟር ነው!? ቢሆንስ ችግሩ ምንድነው? አንድ ሰው ቢጠጣ፣ ቢያጨስጮማ ቢቆርጥ ጋዜጠኝነቱን ምን ይከለክልዋል? "ጋዜጠኞቻችንን ያዘናጋብን" የሚለውስ  የተዘናጉት ጋዜጠኞች™‹የትኞቹ ናቸው!? የነቃሁና የበቃሁ ጋዜጠኛ እኔ ብቻ ነበርኩ ማለ ነው!? ማን መስዋዕትነት ማነው ጉራ ሚነፋው? ኧረ ጎበዝ! ሌላው ቢቀር ህሊና ሚባ ነገር አለ፡፡ ወይስ ባህር ማዶ ሄደው መሽጉ ህሊና ባል ነገር ይጠፋል ማለ ነው!? አድነነ ከማአቱ ማለት ኼኔ ነው፡፡

              ስድስቱ

"....እስር ቤት ወሰንን ማወቅ ችያለሁ፤ ጥቃትን ማይወድ ደፋር  በመሆኑ እወደዋለሁ፡፡ አዛኝና ለማንም የማይጨነቅ ነው /የሥነፅሁፍ ችሎታውን ሳንጠቀምበት ቀርተናል/ ...." ይላል ፋሲል፡፡

እንደእውነ ከሆነ እነዚህ ውዳሴዎች አስፈላጊ አልነበሩም ስለችሎታዬ የፋሲል መወድስ ሚያሻኝም አይደለሁም "ችሎታው ሳንጠቀምበት" ያለው ግን በመጠኑ አስፈግጎኛል፡፡ የእኔ ችሎታ ለእነፋሲል አይነቱ መጠቀሚያ ውል አይችልም፡፡ ችሎታዬን ሚውለው ለሕዝብ ጥቅም ብቻ ነው፡፡ "መጣፍ" ሳይሆን መፃ እንደምችል ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እንደፋሲል አልጥፍም፤ ነገር አልደርትም፡፡ የፋሲል ውዳሴ ማያስፈልገኝ ለዚህ ነው። የፋሲል ከንቱ ውዳሴ አሰስ ገሰሱን አስከትሎ እንደሚመጣም አውቃለሁ፡፡ እንደሚከተለው ያለ ዝባዝንኬ፡-

"....የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከቅንጅት መሪዎች የተሻለ ሥነ ምግባር እንደተላበሱ አድርጎ ያቀረበበት ክፍልወሰን የትግል ታሪኩን ለጀበና ውጦት ይሆን የሚል ጥያቄ አሳድሮብኛል፡፡ ሰዎች ለመኖር ሲሉ እምነታቸውን ይሸጣሉ፤ ወሰን ግን እንዲህ በቀላሉ ህሊናውን እንደማይሸጥ እመሰክራለሁ፡፡....ወሰን ባላወቀው ወይም ሆን ብሎ የአሳዳጆቹ መጠቀሚያ ሊሆን እንደማይች እገምታለሁ፡፡... " ይላል ፋሲል፡፡

የምን መዘላበድ ነው እሱ!? አንድ ሰው ማለት የፈለገውን በግልፅና ፊትለፊት ተናግሮ ቢወጣለት ነው ሚሻለው። እዚህና እዚያ እየረገጡ መውሸልሸል ህሊና አለኝ ብሎ ከሚያምን ሰው ሚጠበቅ ተግባር አይደለምእንዲያ ከሆነ ደግሞ ፋሲል ስለህሊና ነፃነት የመናገር ብቃት የለውም ማለት ነው ህሊና ጫካ አይደለም በራስ ላይ መሸፈት አያስችልም፡፡ አይሸፍጥምም፡፡ ህሊና ለእውነት ከእውነ ጋር ነው ሚኖው። እኔም "በቃሊቲ ምስጢሮች" መፅሐፍ ውስጥ የከተብኩት ያየሁትን፣ ያስተዋልኩትን፣ ማውቀውን ሐቅ ብቻ ው። አንዲትም ቃል ሃሰት የለበትም

ፋሲል ከየት እንዳመጣው ላውቅም እንጂ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከቅንጅት መሪዎች የተሻለ ሥነ ምግባር እንደተላበሱ አድርጌ አልፃፍኩም ምክንያቱም የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከእኔ ጋር አልታሰሩም ከእኔ ጋር ስለታሰሩት የቅንጅት መሪዎችና ጋዜጠኞችን ውሎና አዳር እንዲሁም አመለካከት ብቻ ነው የፃፍኩት ሕዝብ ያላየውን ነገር ግን ማየት የሚገባውን እውነት ነው የገላለፅኩት፡፡ የፋሲል መንጨርጨር ገበናዬ ለምን ተገለጠ የመነጨ ካልሆነ በቀር፡፡

በነገራችን ላይ ማንበብና ማነብነብ ሁለት የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን ለፋሲል መናገር ያለብኝ አይመስለኝም ገበናው የተጋለጠ ሰው ከማንበብ ይልቅ ሚቀናው ማነነብ ከሆነ ችግሩ ሌላ ነው፡፡ ፋሲል ያላነበበውን ማነነቡ ችግሩ የከፋ መስሎ ታይቶኛል፡፡

እዚች ላይ አዛኝ ቅቤ አንጓቹ ፋሲል የኔዓለም "ወሰን ሳያውቀው ወይም ሆን ብሎ የአሳዳጆቹ መጠቀሚያ ሆኗል" ያለወግ ላርመው እሻለሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እኔ አሳዳጅ የለኝም፡፡ ጠላት የለኝም የሚያሳድደኝ ካለ እሱ እውነ ብቻ ነው። እውነትን ከመናገር ደግሞ ወደኋላ አልልም፡፡ "የቃሊቲ ሚስጥሮች" የፃፍኩት ለመኖር ስል አይደለም ምክንያቱም 97 ዓም በፊት እኖር የነበረውን ኑሮ ሚከለክለኝ ማንም የለም መፅሐፉን በመፃፌ ዩማገኘውም ማጣው የተለየ ነገር የለም። እስር ቤት ስጥ የሆነውን የተፈጠረው "ቁጭ" ነው ያደረግኩት፡፡ ያውም በአክብሮት ጭምር። የማንንም ስብዕና ሳልነካ፡፡ በአጭሩ "የቃሊቲ ምስጢሮ" የፃፍኩት የታሪካችንን ሌላ ገፅታ ለማሳየት ነው፡፡ የሀገር ታሪክ ስለሆነ ነው። ታሪክ ደግሞ ታሪክ ሊባል ሚችለ በጎውን መጥፎንም ማሳየት ሲችል ነው ለትውልድ አስተምህሮት ሚኖረው። ከዚህ የዘለለ ዓላማም ዒላማም የለኝም "አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ" ነውና

              
      ሰባ


ፋሲል የኔዓለም "የቃሊቲ ምሰጢሮች" አሁን በመፅሐፍ መልክ ታትሞ ለአንባቢያን መቅረቡ ለምን እንዳንገበገበው አልገባኝም ምክንያቱም 2002 . በእኔ አሳታሚነት ለንባብ ይቀርብ በነበረው "ሐራምቤ" ጋዜጣ 24 ሳምንታት በተከታታይ ተተርኳል፡፡ በተለይ እሱን የሚመለከተው ክፍል ከየካቲት እስከ ነሐሴ ወር 2002 . ነው በምድረ-ኢትዮጵያ ለንባብ የበቃው አሁን "ሐራምቤ" ጋዜጣ ለህትመት ያልበቃው ክፍል ታክሎበት ነው መፅሐፍ ሆኖ የመጣው፡፡

የሆነ ሆኖ እኔን ከሁሉ በላይ የገረመኝ ፋሲል የኔዓለም ".... ወሰን በእኔ ላይ ያቀረበው ወቀሳ ለምንበገንዘብ አልደገፈኝም› የሚል በመሆኑ ለሞራሉ መጎዳት አስተዋፅኦ አድርጌ ይሆናል.." ብሎ መዘላበዱ ነው፡፡

ቀድሞ ነገር ፋሲል የኔዓለም ምን ሆኖ፣ ምን አለውና ነው እኔን በገንዘብ የሚረዳኝ? የምን አጉል መኮፈስ ነው እርግጥ ነው እስር ቤት ውስጥ ስድስት ወር ሳይሞላን ከእስር ተፈትቶ፣ የስደተኝነት ሊቼንሳ አግኝቶ፣ "ሳይገድሉ ጎፈሬ" እንዲሉ ያልኖረበትን የጀግንነት ካባ ደርቦ፣ ከምስኪኑ ዲያስፖራ በትግል ስም ዶላር አሰባስቦ ለመኖር ሲቋምጥ የነበረው ፋሲል የኔዓለም ነው እንጂ እኔ አይደለሁም እናም ታጋይ ፋሲል ገና ምኑም ከምኑ ሳይያዝ ያለመው ተሳክቶለታል "ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ላይ ቂጥጥ" ብሏል፡፡ ይመቸው!!

ፋሲል ከእስር ቤት ሳይወጣ ባህር ማዶ ዘልቆ ጀግና ለመሆን ሲያልም፣ የእኔ ምኞት አንድ ብቻ ነበረ ከእስር የመፈታት ዕድል ካገኘሁ ለአንድ ጊዜም ቢሆን በሙያዬ ላይ መገኘት፣ ለአንድ ጊዜም ቢሆን ጋዜጣ ማሳተም ነበር ማልመው፡፡ ህልሜንም አሳክቻለሁ "ሐራምቤ" ጋዜጣን 6ወር አሳትሙአለሁ"ሐራምቤ" እንደገና ተከስሼ፣ እንደገና ቃሊቲን ጎብኝቼአለሁ ይህንንም ፍሷን ማር "አውራምባ" ጋዜጣ ላይ ፅፌዋለሁ፡፡ የዋስትና ገንዘብ ከፍለው ከዳግም እስራት ያስወጡኝ "አዲስነገር" እና "አውራምባ" ጋዜጠኞች መሆናቸውን የምናገረው በኩራት ጭምር ነው፡፡ ይህ ማለት የምፅፈው እነፋሲል የኔዓለም ከምስኪኑ ዲያስፖራ ሚሰበስቡት ገንዘብ እንጥብጣቢ ይወድቅልኛል ብዬ አይደለም ማለ ነው

ያኔ ብቻ አይደለም፤ አሁንም እየፃፍኩ ነው ወደፊትም እፅፋለሁ፡፡ የምፅፈው ማስመሰል፣ አጉል ታጋይ መባል፣ መመፃደቅ፣ ለከንቱ ውዳሴ አይደለም፡፡ የምፅፈው ለሕዝብና ለሃገር የተሻለ ምኞት ስላለኝ ነው  የምፅፈው ማንንም ተመክቼ፣ ማንንም ተገን አድርጌ አይደለም፡፡ የእኔ ተገን እና መመኪያ ውነትና ውነ ብቻ ነው የምፅፈው ሳላፈገፈግ ው። የሥነምግባር ትጥቅ መታጠቅ ማለ ደግሞ ይኼ ነው። እንጂ ያልተረዱትን ነገር ማንዴላ ምናምን እያሉ መደስኮር አይደለም በዚሁ ባበቃ ነው ሚሻው። በመጨረሻ ግን....

                   በመጨረሻ

"....ገምጋሚው ፋሲል በእስረኞች የተጠላ መሆኑን ከየት አመጡት? ምናልባት ወደፊት ሚወ የወሰን መፅሐፍ አግኝተውት ይሆን?" ሲል በፅሁፉ ውስጥ ላቀረበው ስጋታዊ መጠይቁ ምላሽ ሰጥቼ ይህንን ፅሁፍ ልደምድም፡፡

የኢሳት ፊታውራሪ ፋሲል የኔዓለም ሆይ!! ሥጋትህ ከንቱ ነው ወደፊት የሚታተም መፅሐፍ ቢኖረኝም እናንተን ስለማይለከት አትስጋ፡፡ ለዚህ ቃል እገባልሃለሁ፡፡ የሥጋትህ ምንጭ ግን ይገባኛል፡፡ አሁን "የቃሊቲ ምሰጢሮች" ብዬ ባሳተምኩት መፅሐፍ ውስጥ ያላካተትኳቸው እጅግ አሳፋሪ ታሪኮች እጄ ላይ እንዳሉ ጠንቅቀህ ስለምታውቅ ነው። ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮ የመኖር ባህል፣ ታሪክ፣ ምነ ጋር በእጅጉ የሚጣረሱ እና የወረዱ ተግባሮችን "ሕዝብ ላይ መትፋት ነው" በሚል አጭር አገላለፅ ትቼዋለሁ፡፡ ከዚህ በላይ መውረድ ከዚህ በላይ መዝቀጥ ሞት፣ የሞት ሞት ነውና፡፡

ቢሆንም ምናልባት ገንዘብ ካገኘሁ አንተ "እጅግ ውብ" ብለህ የመሰከርክላቸው ግጥሞቼን ናሳተሜ አይቀርም፡፡ ላኢጮኛህ ጭምር ማስታወሻነት ያበረከትኩላትን ግጥም ጭምር፡፡ በነገራችን ላይ ዘንግተህ ካልሆነ እስር ቤት የፃፍኳቸው ግጥሞች ሁለት ብቻ አይደሉም ብዙ ናቸው ትዝ ይልህ እንደሆነ ሁላችንም እስረኞች በምንታደምባቸው ምሽቶች "አጭር ፀሎት" የሚል ግጥም አንብቤ ነበረ፡፡ "ያቺ ፀሎቴ" በእርግጥም ሰምራልኛለችና ግጥሟን ጋብዤ ልሰናበትህ፡፡ ግጥሟ ውስጥ በእርግጥም እኔን፣ በእርግጥም ምኞቴን፣ በእርግጥም ፅናቴን፣ በእርግጥም እምነቴን ታገኘዋለህ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ በእርግጠኝነትም ታውቀኛለህ፡፡ እነሆኝ ግጥሟን ለስንብት፡-
አጭር ፀሎት
ፈጣሪ ሆይ
ረዥም ፀሎት የለኝም፣ ልፀልይ ብልም አልችልም
ለትንሣኤ ሞት አብቃኝ ብዬ አጓጉል አላስቸግርም
ይህቺኑ ዕድሜዬን በወጉ ፅናቱን ብርታቱን ስጣት
ከተገፉ ጋር አቁማት የደሀ ፍቅር ሸልማት
ይህቺኑ ዕድሜዬን አጣፍጣት - ከታሪክ መዝገብ አኑራት፡፡
ቁምነገር ማይገኝበት ረዥምና ዘልዛላ ዕድሜ አልለምንህም ቆሜ።
በትንሳዔ ለው ህይወት በጭራሽ ቁብ አይሰጠኝም
ከሞት በኋላ ለመኖር ናፍቆት ጉጉቱ የለኝም
እንኳንስ ሁለቴ ህይወት አንዱንም መኖር ታክቶኛል
የሰው ልጅ ሥቃይ ሰቆቃ ጩኸቱ አደንዝዞኛል፡፡
ሰው በሞላበት ምድር ላይ ሰው የሚሆን ሰው ጠፍቶ
ግፍና በደል በርክቶ ሕግ ስብዕናው ሞቶ
ሎሄ ዋይታ እየናኘ
ሀዘን እየተቃኘ
በትንሳዔ ህይወት ፈጥረህ ዳግመኛ ከምታኖረኝ
ለድሆች አጋር መከታ እዚሁ አንደዜ ሰው አርገኝ 
አሁን ባለው ህይወቴ ሰው መሀል ለሰው አቁመኝ፡፡
ይኸው ነው አጭር ፀሎቴ- ረዥም ፀሎት የለኝም
ልፀልይ ብልም አልችልም - ጌታ ሆይ አላስቸግርም
ጌታ ሆይ ሰው አርገኝ አንዴ - ይህቺኑ ህይወቴን ሸልመኝ
ንኛው ህይወት ይቅርብኝ - ለሰው ስለሰው አኑረኝ፡፡
ወሰብ ሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

Posted at www.ethiopisnsemay.blogspot.com
Email getachre@aol.com