Sunday, July 18, 2010

በአቶ አማረ አፈለ ብሻው የተጻፉ ድንቅ መጻሕፍቶች

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ getachre@aol.com (408) 561 4836

እኔም ሆነ ሌሎቻችሁ ብዙ ጊዜ የምንለው አንድ ነገር አለ፡ “አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ምሁር ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ በአገሩ ልጆች የተጻፉ መጻሕፍቶችን የማንበብ ልምድ የለውም፡ ቢያነ’ብም በአመስት/አስር ዓመት አንድ መጽሐፍ ያነ’ብ ይሆናል። አንዳንዴም የገዛዉን መጽሐፍ አንብቦ የመጨረስ ልምድ የለዉም፤በደፈናዉ “ግብዝ” ነዉ።” የሚል ድምዳሜ ደርሰናል። መጻሕፍ የማንበብ ጉጉት ያደረባቸዉ አንባቢዎችም ቢሆን የመጻሕፍት መሸጫ መደብሮች አከፋፋዮች/አሰራጮች ስለሌሉን የታተሙ መጽሐፍት በበቂ ማግኘት አልቻሉም። ለዚህ ብዙ ምክንያቶች አሉ። የኢትዮጵያ ሱቅ/መደብሮች/ግሮሰሪዎች/ምግብ ቤቶች… እንደ የሙዚቃ ሸክላ/ክሮች( ይግረም ብለዉ የሻዕቢያ ፖስተሮች/ጌጦች/ሰንደቃላማዎች/የሙዚቃ ሸክላዎች/የሻዕቢያ ሰንደቃላማ ያለባቸዉ ልብሶች ሳይቀሩ በጉግት በጅምላ እየገዙ ለደምበኞቻቸዉ እንደሚያሰራጩት) ጉጉትና ቅድሚያ ሲሰጡ- መጽሐፍቶች፤መጽሄቶች እና ጋዜጦች የመሳሰሉትን ግን በንግድ ዓይን ስለሚመለከቷቸዉ ከአገር ጉዳይ የተያያዙት እንኚህ የአገሪቱ እና የራሳቸዉ ህይወትን የሚጠቁሙ ቋሚ ማሕደሮች/ሰነዶች በቁም ነገር ስለማያይዋቸዉ፤ ደራሲያኑ በኪሳራ ያሳተሟቸዉን መጻሕፍቶች፤መጽሄቶች እና ጋዜጦች ለዜጎች በበቂ እንዲዳረሱ ለማድረግ ከፍተኛ ችግር እየተጋረጠባቸዉ እንደሆነ ለብዙ አመታት የተነጋገርንበት ጉዳይ ይመስለኛል (ብዙዎቹ ባለ መጽሄቶችና ጋዜጦች አገልግሎታቸዉን ለምን እንዳቆሙ እሮሮአቸዉን በስፋት አንብባችሁ ወይንም አድምጣችሁ ይሆናል)።በዚህ ጉዳይ ባለ ሱቆች/ምግብ ቤቶች ለዚህ ዕንቅፋት እንደሆኑ የምታዉቁት ይመሰለኛል። ስለሆነም ደራሲዎች፤የታሪክ እና የዜና ዘጋቢዎች ሕዝቡን ለማስተማር እና ፈር ለማስያዝ ያለባቸዉ ችግር አሁንም እንዳለ ነዉ። እናሰራጫለን የሚሉ ባለ ሱቆችም ቢሆኑ ደራሲያኑ እንዲሸጡላቸዉ ወይንም የመጽሄት እና የጋዜጣ ባለቤቶች የላኩላቸዉን መጽሐፍት እና መጽሄቶች ከሸጣሰቸዉ በሗላ ገንዘቡን በወቅቱ አይሉኩላቸዉም አንዳንዴም ውጠዉት ይቀራሉ። ባለፈዉ ወር በእኔ የተጻፉ ሁለት መጻሕፍቶች ማለትም “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” (አማርኛ) እና “ሓይካማ” (ትግረኛ) ለሕትምት በቅተው ወደ ጥቂት አንባቢዎች መዳረሳቸው ይታወሳል። የአማርኛዉ መጽሐፍ ተሎ በማለቁ አንባቢዎች በብዛት እንዲላኩላቸዉ ስለጠየቁኝ በቅርቡ ተጨማሪ ቅጅ ስላስፈለገ ቅጁ እንደተባዛ ይዳረሳል። ወዳጄ ደራሲና የጉግሳ መጽሄት አዘጋጅ አቶ አማረ አፈለ ብሻው ትውውቃችን ብዙ ዐመት ነዉ። ወንድሜ አማረ ሲኖርበት ከነበረዉ ሎስ አንጀለስ ከተማ ለቅቆ መኖርያው ሌላ ቦታ ካደረገ ወዲህ የስልክ ቁጥር አድራሻ ለዉጥ በማድረጉ መገናኘት አልቻልንም ነበርና ስለኬን በመጽፌ ማስታወቂያ አማካንነት አግኝቶ መጽሃፌን እንድልክለት ደዉሎ ሲያነጋግረኝ ደስ ብሎኝ ስንወያይ ሰባት መጻሕፍት እንደጻፈና በቅርቡ “ከጋምቤላ እስከ ሁመራ”የተባለዉ አዲስ መጽሐፍ እንደጻፈ እና ሌሎቹም በስም ዝርዝራቸዉ ሲነግረኝ እኔ ራሴ “ክዉ” ብየ ነበር የቀረሁት። ምነዉ ይህ ሁሉ መጽሐፍ ስትጽፍ እኔ ላይ ሲደርሱ ተደበቁብኝ? ብየ ስጠይቀዉ ከላይ የጠቀስኩትን እኔ የሚሰማኝን የስርጭት ችግር እና እሱም በአንደኛዉ መጽሐፉ መግቢያ ዉስጥ እንደጠቀሰዉ ሁሉ በዝርዝር የመጽሐፍቱ በበቂ ያልተሰራጨበት ምክንያት እና ህብረተሰቡ ገዝቶ ያነብባል ብሎ ቅጂዎች በብዛት ማሳተም ትርፉ ዕዳ እና ኪሳራ እንደሆነ ተነጋግረን፤ መጽሐፍቶቹ በመታተማቸው ደስ ብሎኝ መጽሐፍቶቹ እንዲልክልኝ ጠይቄዉ ልኮልኝ በማንበብ ላይ ነኝ። እናንተም እነኚህ በሰነድ የተደገፉ መጽሐፍቶቹ ገዝታችሁ እንድታነቧቸዉ አደራ እላለሁ። አሁን ወደ ደራሲዉ አማረ “ከጋምቤላ እስከ ሁመራ”መጽሐፉ መግቢያ ውስጥ ደራሲያን ስለ ስርጭት የሚሰማቸዉን ጉዳይ በራሱ አንደበት ያስተላለፈዉን እነሆ። ደራሲዉ አቶ አማረ አፈለ ከጋምቤላ እስከ ሁመራ መጽሐፉ ለመጻፍ ምን እንዳነሳሳዉ ባጭሩ ካብራራ በሗላ እንዲህ ይላል “ የኢትዮጵያ ጉዳይ ከአደር አደር እየባሰ እንጂ እየተሻለ ባለመምጣቱ የነበራትን ገናና ታሪክ ሳነብ አለቅሳለሁ። በተለይ ነባሩን ታሪኳን ስመለከት ሰላም ይነሳኛል።…አንባቢያን ለማስገንዘብ የምፈልገዉ ነገር ቢኖር እኔ የምጽፈዉ አንዱን ቡድን ለማስደሰት ሌላዉን ቡድን ለማስከፋት አይደለም። መጽሐፉን ብትገዙት ባትገዙት እኔ ግድ የለኝም። እኔ ደስ የሚለኝ ነገር መጽሐፉ ከማተሚያ ቤት ወጥቶ ከተወሰኑ አንባቢዎች እጅ ከገባ በሗላ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል።…የኔ ትርፍ የተሰማኝን መግለጽ የሀገሬን ጉዳይ መግለጽ ነዉ።” ሲል “ከጋምቤላ እስከ ሁመራ” የተባለዉ በሰነድ አስደግፎ በጻፈዉ እጅግ ወቅታዊ ታሪካዊ እና ጠቃሚ መጽሐፍ እንድናነበዉ ሰጥቶናል። ይህ እና ሌሎች ስድስቱ መጻሕፍቶቹን ለማግኘት በሚከተለዉ አድራሻ ብትጠይቁ ማግኘት ትችላላችሁ።ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን ለሙዚቃ ድግስ እስከ $400ዶላር (ለጸጉር ማስርያ፤ አዲስ ልብስ፤ሽቱ/ሽቶ፤ጫማ፤ለመግቢያ ቲኬት…) ለአንድ ምሽት ፈንጠዚያ ያን ያህል ከፍለዉ መዝናናት እንጂ በስሟ የሚጠሩባት ዜግነታቸዉ “ኢትዮጵያዊያን”ነን የሚሉባት አገራቸዉ ምን እየተባለላት፤ምንስ እየደረሰባት እንደሆነ ጉዳያቸዉ ያልሆነ ዜጎች (በተለይም ምሁር የሚባለዉ ክፍል) የ$15 እና የ$20 ዶላር መጽሐፍ ገዝተዉ ለማንበብ ልምዱም ፍላጎቱም እንደሌላቸዉ ሁሌም የሚሰማኝን የኔን እሮሮ ወዳጄ ደራሲዉ አማረ አፈለ ከላይ የገለጸዉን ስሜቱን እንደገና ደራሲያንን ሲያጽናና እንዲህ ይላል“አባ ቀዉስጦስ የሰሜን ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ‘ይግባኝ ለክርስቶስ’ በተባለዉ መጽሐፋቸዉ ገጽ 58 “ምን አልባት ላይሰሙን ምን አደከመን እንል ይሆናል። ነገር ኢግን እነሱ ሰሙም አልሰሙም እኛ መናገር አለብን። ፀሐይ የሚሞቀኝ የለም ብላ ከመዉጣት፤ወንዝም የሚጠጣኝ የለም ብሎ ከመፍሰስ እንደማያቋርጥ ሁሉ መምሕራንም የሚሰማን የለም ብለን ዝም ማለት የለብንም” ሲሉ ጽፈዋል። ሲል ደራሲ አቶ አማረ አፈለ ብሻው ደራሲያን/አስተማሪዎች/የሕዝብ ልሳን አስተጋቢዎች….አንባቢ የለም ብለዉ ከመጻፍ/ከማስተማር/ሃሳባቸዉን ከማሰራጨት/የዘገቡትን ለትዉልድ ከማስተላለፍ እንዳይቆጠቡ አደራዉን አስተላልፏል። እመኑኝ ኢትዮጵያዊያን (ያለንበት ትዉልድ)መጽሐፍ ከማንበብ ይልቅ በሙዚቃ ድግስ እና በየሬስቶራንቱ እየዞሩ መዝናናት የሚደርሳቸዉ በዚህ ዓለም ያለ አይመስለኝም። እንዲሁ በደፈናዉ “ያላለለት ትዉልድ”ብየ ልሰናበታችሁ። የታላቁ ደራሲ አማረ አፈለ ብሻው መጽሐፍቶች ገዝቶ ለማንበብ ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ በሚከተለዉ አድራሻ ማግኘት ትችላላችሁ።የማናዉቀዉ፤የረሳነውና የተነጠቅነዉ ማንነታችን ማፍረስ በማይቻል መረጃ አስደግፎ ያስታውሰናል። የመጻሕፍቱ ስም ዘርዝርም እነሆ ከዚህ በታች ያሉት ናቸው።አመሰግናለሁ። ጌታቸዉ ረዳ Editor www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com የመጻሕፍቶቹ ስም ዝርዝር 1-ከጋምቤላ እስከ ሁመራ! 2-በአባ ጳዉሎስ በጳጳሳት ምክንያት በቤተክርስትያን ላይ የተነሣዉ እሳት! 3-አሰብ የኢትዮጵያ አካል ነች 4-የሁለት ሺህ ዓመታት ውጣ ውረድ በኢትዮጵያ 5-ኢትዮጵያ! የሰው ዘር የተገኘባት የእምነትና የሥልጣኔ ምንጭ ናት! 6-ገድሉስ ገደል ነው! Amare Afele Bishaw P.O.Box 492 Seatle WA 98111 U.S.A

Tuesday, July 13, 2010

እዉን የወያነ ተከታዮች ከዓፋር ግመሎች ባነሰ የኢትዬጵያን ባንዴራ አያዉቋትም?

እዉን የወያነ ተከታዮች ከዓፋር ግመሎች ባነሰ የኢትዬጵያን ባንዴራ አያዉቋትም?
(ጌታቸዉ ረዳ)
Getachew Reda P. O. Box 2219 San Jose, CA. 95109 Telpone 408 561 4836 getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ እዉን የወያነ ተከታዮች ከዓፋር ግመሎች ባነሰ የኢትዬጵያን ባንዴራ አያዉቋትም?
(እያዝናና ልብ የሚሰብረዉ የወያነ ትግራይ ትራጀዲያዊ ተዉኔት!)
ካለፈዉ ግንቦት ወር ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በወያነ ትግራይ ተከታዮች የታዘብኩት ነገር ኢትዮጵያዊነት እና ወያነነት ስሜት እጅግ አደገኛ በሆነ መልኩ እየተፋጨ እንደሆነ ነው። ወያነ ትግራይ ብዙዎቹን የትግራይ ማሕበረሰብ በዉድም በግድም ከዚያም አልፎ ስሜት በሚኮረኩሩ ቅስቀሳዋች ተንተርሶ ወደ ዓላማዉ አሰማርቶ ብዙ አገራዊ ነክ ጉዳዮችን በጎጂ መልኩ አንዳንዴም በአደገኛ መልኩ በግልጽ እና በምስጢር የሚያከናዉናቸዉ ፖሊሲዎቹ ደጋፊዎች እና አድማቂዎቹ ሆነዉ ለብዙ ዓመታት አብረውት ተጉዘዋል። ቁጥራቸዉ ለመገመት ባልችልም በርከት ያሉ የትግራይ ተወላጆች ወያነ ትግራይ ለሁለት ከተሰነጠቀ በሗላ በመለስ ዜናዊ እና በስብሐት ነጋ የሚንቀሳቀሰዉ የህዛባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ቡድንን በመቃወም ተቃዋሚው ወደ ሆነው ወደ ስየ እና ገብሩ (ዓረና ትግራይ)በማንዘበል-“ዞር አሉ አልሸሹም”ብየ ወደ ምጠራዉ የመገንጠል መብት የሚያከብረው እና ለመገንጠል መብትም ቆሚያለሁ ወደ ሚለዉ ወደ ዓረና ትግራይ በመዞር የመልስን ወያነ እየተቃወሙ መሆናቸው ይታወቃል። ዘንድሮ እየተጠናከረ የመጣዉ በጥበት የተበከለው ሌላዉ የወያነ ትግራይ አጨብጫቢዉ ክፍል ደግሞ በጣም ዑወር የሆነ ግን በዓድዋ አሉሙናይ፤ በሽረ አሉሙናይ፤በአክሱም አሉሙናይ፤በንግስተ ሳባ በአጼ ዮሐንስ፤ በምንትስ …በምንትስ….አሉሙናይ እየተሰባሰቡ ለየአካባቢያቸው እና በተማሩበት አዉራጃ/ወረዳ/ትምህርት ቤት ማሳደሻ እና ትምህርት ቤት፤ቤተመጽሕፍት ማሰርያ፤ሽንት ቤት ማሰርያ ወዘተ በሚል መነሻ የዋያነ ትግራይ ተገዢነቱን በግልጽ ማጉላት ጀምረዋል። ይህ የወያነ ትግራይ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ከበረሃ ጀምሮ ምን ዓይነት ኢትዮጵያዊነት ያስተምር እንደነበረ እና ከበረሃ ወደ በትረስልጣን ከወጣ በሗላም በየመጽሔቱ ተደጋግሞ ከሚጠራላቸዉ የበደኖ፤የአርባጉጉ፤የወተር፤የአረካ፤የጎንደር፤የአንዋር መስጊድ ወዘተ…ጭፍጨፋዎች በረሃ እያለ እሱ እና መሰል ተገንጣዮች/ጠባብ ብሄረተኞች እሰራዋለሁ ብሎ በደብተሩ ለኢትዮጵያ ይዞላት የመጣዉ ስብክበትና ሲያስተምርበት የነበረዉን የፖሊሲዉ ውጤት አድናቂዎች በመሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋወሪ የወያነ ትግራይ መሰሪ ወያነነት በመከተል የአገራቸዉን ሰንደቃላማ ከማክበር እና ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ በአገሪቱ ታሪክ ተሰምቶ ታይቶ የማይታወቅ የትግራይ ሕዝብ ሰንደቃላማ በመጣል እና በማናናቅ ወያነ ትግራይ ብሎ ራሱን የሚጠራ ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅት ባንዴራ በማዉለብለብና ቀዳሚ ክብር በመስጠት በየጭፈራ ቤታቸዉና በየስብሰባቸዉ ይህንኑ የድርጅት ባንዴራ አገራዊ ሰንደቃላማ አድርገዉ በመዉሰድ አሳፋሪ የታሪክ ወንጀል በመፈፀም ላይ ናቸው። “እንኳን እኛ ግመሎቻችን የኢትዮጵያ ባንዴራ ያዉቃሉ”የተባለላቸዉ ዓፋሮች ለኢትዮጵያ ያላቸዉ ተሟጋችነት እና ቀናኢነት እንዲህ ሲናገሩ በ“አሉሙናይ ሰበብ” ፤ በ“ልምዓት ዓዲ ብወዲ ዓዲ” ሰብብ “የፖለቲካ ድርጅት” ባንዴራ “የኢትዮጵያ ባንዴራ” መስሏቸዉ ከፊት ለፊታቸዉ በየጠረጴዛቸዉ በክብር የሚያዉለበልቡት የመለስ/ስብሓት ወያነ ትግራይ ፕሮፖጋንዳ ሰለባዎች እዉን ከዓፋር ግምል ባነሰ የኢትዮጵያን ባንዴራ አያውቋትም?ከዚህ ወዲያ የትግራይን ሕዘብ ወዴት ይወስዱትይሆን?እያዝናና ቀስ እያለ ልባቸዉን የሚሰብረዉ የወያነ ትግራይ ትራጀዲያዊ ተዉኔት ውስጥ ገብተዉ ተወናያን መሆናቸዉን ማቆሚያቆሙት መች ይሆን? እንደገና ሌላ ቁጭት አንሰማ ይሆን? ለማንኛዉም መሰንበት ደጉ ይባላል እንሰንብትና ጉዟቸዉን አብረን እንታዘብ። ባህሩ አስነጥቆ ያስነጠቀዉን ቡድን ባንዴራ በክብር ሲያዉለበልብ ማየት አስገራሚ ዘመን እንደዚህ አላየሁም። በታሪክም አላነበብኩም። ልብ የሚሰብር ጥቁር ነጥብ የጣለ የታሪክ ክንዉን። ጌታቸዉ ረዳ (408)-561-4836 getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

Monday, July 5, 2010

Haykama (my new TigriNNa Book)

Haykama (my new TigriNNa Book) ሓይካማ

ይህ ዓምድ ሓይካማ በሚል ርዕስ በትግርኛ የጻፍኩት ሌላዉ አዲሱ መጽሐፌ ነዉ።በዚህ ዓመድ የርዕሱ ትርጉምና ይዘት ለትግርኛ አንባቢዎች ይተነተናል። ከዛ በፊት ግን አንድ ማሳሰቢያ አለኝ። “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” መጽሐፌ ተሽጦ ስላለቀ፡ ሌላ ቅጅ እስኪታተም ድረስ ትንሽ ጊዜ ጠብቁኝ። ለመግዛት የምትፈልጉ- በቼክ ወይም በፖስታ ቤት በማኒ ኦርደር ብትልኩ መጽሐፉ አንዳንድ መጠነኛ እርማት ተደርጎበት ከሕትመት እስኪወጣ ድረስ አይመነዘርም። Getachew Reda p o Box 2219 San Jose, CA 95109 telephone 408) 561-4836 ሆኖም አስቀድማችሁ ብትልኩ ቅድሚያ ስለምታገኙ ተሎ ይላክላችሗል። አሁን ወደ ትግርኛዉ “ሓይካማ” ትንተና እንግባ። ትንተናዉ ለትግርኛ አንባቢዎች በትግርኛ የተዘገበ የመጽሓፉ ርዕስ ትርጉም ነዉ። አዘጋጁ።
ሓይካማ እንታይ ማለት እዩ?
ሓይካማ ዝብል ቃል ”ቶርቸር” ንዝብል ቋንቋ እንግሊዝ ንምትካእ ዝተጠቐምኩሉ ቃል እዩ። ሓደ እሱር ”ናብ ሓይካማ ኣእትየሙኒ” ወይ ድማ ”ብሓይካማ ተመርሚረ” እንተዳኣ ኢሉ”ብከቢድ መርመራ/ቶርች ገይሮሙኒ” ማለት እዩ።ኣብ ጊዜ ደርጊ ብፖለቲካ ተጠርጢሩ ዝተትሓዝ እሱር ዘይተቐጥቀጠ ሰብ ዉሑድ እዩ፡፡ ንምሳሌ ኣብ ክፍለሃገር ትግራይ ኣብ መቐለ ከተማ ብፖለቲካ ተጠርጢሩ ተታሒዙ እንዳተደፍአ ‘ሕዝብ ድርጅት’ ኢሎም ናብቲ ዝጽዉዑዎ ዝነበሩ ቤት ማእሰርቲ ናብ ዝነበረት መመርመሪት ደብሪ/ክፍሊ ዝኣተወ እሱር ብድሕሪ ማዕጾ ብየማን ብጸጋም ተላሒጎም ዝጽበዩዎ “ስፔሻል ፎርስ” ዝተብሃሉ ኮማንዶ “ብቕርዳድ ጽፍዒት” ጉንዲ-እዝኑ ምስ ኣጽመሙዎ፡ሓይካማ ተባሂሉ ብዝፍለጥ ኣላጉማ በቕሊ ብገምድ ተኣሲሩ ጎማ ብዝለበሰ በትሪ እዩ ዝቕጥቀጥ ነይሩ።ናብ ሓይካማ ዝኣተወ ተመርማራይ ብገመድ ክልተ ኢዱ ጠዉዮም ብኣፍ ልቡ ኣደቂሶም፤ክልቲኡ ኢዱ ንድሕሪት ምስ ዓካር ኣእጋሩ ቆርኒዬም ዕጻፍ ሞንኮቡ ምስ ኣጎድጎዱዎ፡-እታ ቀጻሊት ገመድ ኣብ ሞንጎ ኣስናኑ ንመልሓሱ ጸቒጣ ፤ኣፍ ልቡን ማጅራት ክሳዱ ከም ልጓም በቕሊ ንድሕሪት ወጢጣ ምስቆርነየቶ ፤ ከም መሸንቀቕ ከረጢት መንጠልጠሊት ምስ ሰርሐት በታ መተሓዚት መሸንቆቖ “ሓፍ” ኣቢሎም ካብ ባይታ ናብ ኣየር፤ካብ ኣየር ናብ ባይታ ደጋጊሞም ከም ሎቖታ “ሰፍ ኮፍ” ምስ ኣበሉዎ በፍንጭኡ ደም በለል እንዳበለ ትንፋሱ ተጨኒቑ “ቀልቀል ሽንቱ” ኣብ ክቋጻጸር ዘይኽእለሉ ብርኪ< ከናፈር ምንጭሩን ምንጋጋ ሞጉሎጩ> በታ ገመድ “ምስገዝገዙዎ” በፍንጫኡ ደም ቦለል ምስ በለ፤ ብስቅያት ዓቕሊ ጽበት ከም “ታሓራዳይ በጊዕ” ኣካላቱ ብገመድ ተገኒዙ ናይ “ዓዕ!!!! ታ” ድምጺ ካብ’ታ በራኽ ደብሪ ናብ ታሕቲ ገስጊሱ ናብ ኣእዛን ኡሱራት ዘቃልሕ ኣዉያት ፡“ልቢ ዝበልዕ” “ንብዓት ዓይኒ ብዝነቅስ” መሕዘናይ ኣዉያት ታዓጂቡ ዝካየድ እሱር ዝፈልጦ ምስጢር ንክናዘዝ ዝጥቀሙሉ ጨካን ኣማራምራ ስልቲ እዩ። መንእሰይ ትግራይ ምንጋግኡ ከም እንስሳ ብሓይካማ ተሎጚሙ ደም ዓፈራ ክሳብ ዝጎርፍ ኣብ መጉለጩ ዝተሎጎሞ ገመድ ዘይጠፍእ ተለላ ስመብራት ብምጥራይ ብገመድ ተኣሲሩ መስፈር/መዕቀኒ ዘይብሉ ድንጋጸ ምስወረዶ ሕልናኡ ጃጂዉ፡ ሕልናኡ ጥራሕ ዘይኮነስ ኣካላቱ ብበትሪ ብጎማ ብኾርማጅ መግረፍቲ፤ ከናፍር ምንጋግኡ ብገመድ ብስልኪ እንዳተሓርሐረ ደንዚዙ፤ ገጹ ዓምቢሱ፤ዓይንቱ ዓንቁይሎም፣ “ከብዲ እግሩ” ሎቖታ ማይ ሒዙ መግልን ደምን ዓቑይሩ ፣መልሓሱ ተመቲሩ ኣስናኑ ብጭብጢት ዉቅዒት ጎሪፉ፣ ኣፉ ተኣንዲሩ፤ ተላጊቡ ነቒጹ፤ ምሕያኽ ምስትምቓር ኣብዩ፣ ታሕናግ ጎሮሮኡ ምዉሓጥ ኣብዩዎ፣ “ማይ ጥሕኒ በጽቢጹ” ብስቅያት “ሱት” ዝበለሉ ወዙ ተደምሲሱ ጨጎርጎር ኢሉ፣ብጥቑሉል ካልሲ ናብ “ሸምቦቆ ቡምባ መስተንፈሲ ጎሮሩኡ” ተወቲፉ ፤ብምሒር ዓዕታ ድምፁ ሰሊሉ፤ እንትፍታፉ ነቒጹ ብኣዉያት ርእሱ ኣጊሉ፤ ተረዉ ዘብል“መርዘን ርእሲ” ከምረዚን እምኒ ተሸኪሙ፣ ጎሮሮኡ ስለዝቖሰለ ሃፈታ ትንፋሱ ናብ “ጎምዛዝ ዕረ ዝተቐየረሉ ሽብር ዘእቱ ጨካን አማራምራ እዩ። “ሓይካማ” ዝብል ቃል ብመሰረተ ትርጉሙ ክጥቀመሉ ዝደለኹሉ ምኽንያት ብዙሓት መንበብቲ ትርጉሙ ንምፍላጥ ይሽግሮም ይኸዉን። “ካ” ዝብል ፊደል እዉን ላሕሊሑ ክንበብ ኣለዎ።ሓይካማ ማለት ካብ ዕንጨይቲ ዝተፀርበት ኣብ ሞንጎ ኣፍ በቕሊ እትቕርቀር ክልቲኡ ምንጋጋ ፈልያ ኣብ ነዊሕ መገሻ ሳዕሪ ብምጉማም (ብምጥጣም/ብምብላዕ) ጊዜ ከይተቃጽል “ዕርፊ” ትመስል ቅርፂ ዘለዋ ብሜላ ዝተፀርበት “ልጓም በቕሊ” ኢያ። እታ ልጓም ንነዊሕ ሰዓታት ካብ ኣፉ ናይ’ታ በቕሊ ከይለገሰ እንተዳኣ ጸኒሑ “ደም ዓፍራ” ብኣፋ ንክጎርፍ ዝገብር ተሪር ቃንዛ ዘለዎ ሉጓም እዩ። ሓይካማ መብዛሕቱ ጊዜ ዝጥቀሙሉ ጊዜ ነጋዶ “ጌላ-ጨዉ”ናብ ዝምረቶ ኣርሆ/ረገድ/በራሕለ/ዳሉል (ዓዲ ዓፋር) ኣብ ነዊሕ መገሻኦም “ዝተጸርበ እምኒ ጨዉ” (ጌላ) ከምጽኡ እንትኸዱ ኣብቅልቶም ሳዕሪ ንክጎ’ማ ፎቖዶ መንገዲ ደዉ እንዳበላ ከየዳናጉየኦም ዝቋጻጸሩ ኣፈንን ምንጋጋአንን ከይከፍታ ዘጸግመለን ሉጓም እዩ። ቃሉን እቲ ልጓምን (ሓይካማ) ድማ ብነጋዶ እንደርታን ከባቢኣን ዝፍለጥ እዩ። ብ“ሓይካማ” ተለጚሙ ዝምርመር ኡሱር ብዘስምዖ ኣዉያት እትዕጀብ እታ መመርመሪት ክፍሊ ኣብ ርእሲ ርእሲ ብዘይዕረፍቲ እንዳተደፍኡ ብዝኣትዉ ተመርመርቲ ምስ መናብር እንዳተሓላለኹ ተወቒዖም ናብ ጣዋሉ ወዲቖም ደምበርበር ብዝብሉ ኡሱራትን፣-ገልጠምጠም፤ዓነዉነዉ ድምጺታት ናይ ጣዉላ ወናብር፤”ኣዉያት” ዝዓጀባ ክፍሊ “ኡፎይ” እትብለሉ ጊዜ እንተሃሊዩ እቲ ተመርማራይ ህይወቱ ኣካላዊ ስነ ምንቅስቓሳቱ ተፈጥሮዊ ስራሕቶም ምቁጽጻር ምስሳኣኑ፤ኣካላቱ ብመዝበጥቲ ሓቢጡ፤ ኣፍ ልቡ ክዳኑ ብደም ተኣሊኹ፤ዝባኑ ደም ቲፍ-ቲፍ እንዳበለ ገጹ ሓቢጡ ናብ ዘፈርሕ ቅርጺ ተቐይሩ፤ ብቕርዳድ ጽፍዒት የዒንቱ ደም ሰሪቦም፤ኩሊቱ ደም ምስሸነት፤ዝተኸድኖም ነጸላታት ብደም ቆርቢዖም፤ ጠረኑ ቀይሩ ጠቕላላ ናልኡ ናብ “ጽላለ” ተቐይሩ ሽንቱ ምቁጽጻር ምስ ሳሓተ ከላፋለፍ ምእንታን-ዝጥቀሙሉ-ጨካን-ምርመራ-እዩ።getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com

Newer Posts Older Posts Home