Wednesday, September 2, 2026

የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በእኔ ዕይታ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 9/2/26

 

የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በእኔ ዕይታ

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

9/2/26

ቲክቶክን ጨምሮ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ ከመከታተልና አልፎ አልፎም በአስተያየት መስጫዎች ከመሣተፍ ባለፈ ለበርካታ ወራት ከመጣጥፍ አስተዋፅዖ ተቆጥቤ ቆይቻለሁ - የሚገርመው “ያ ሰው ወዴት ጠፋ?” ብሎ አንድስ እንኳ የጠየቀ የለም፡፡ ይህም በራሱ አለመታደል ነው፡፡ ምን አዚም እንደወደቀብን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ የሚያጨካክንና ከዚያም ባለፈ እርስ በርስ እንደበግ የሚያስተራርድ ድግምትማ ተደግሞብናል፡፡ ለነገሩ እንኳንስ በወረቀት ለጮኸ ለሀገርና ለሕዝብ ነፃነት ትግል ደረቱንና ግምባሩን የሰጠ ሰማዕትም በማይታወስባትና ቤተሰቡ በርሀብና በዕርዛት በሚማቅቅባት የአይሞቄ-አይበርዴዎች ምድር እኔ ያነሳሁትን ነጥብ ማንሳትና አጥጋቢ መልስም መጠበቅ ቅንጦት ነው፡፡ አብዛኛው ሰው የተቀፈደደው “ሀ ራስህን አድን” በሚለው የፈሪዎች መርኅ ነው፡፡ ስንቶች ጭዳ ሆነው ቤተሰባቸው ተበትኗል፤ በብዙ ነገር ተሰቃይቷል፡፡ በቃችሁ ካላለን መፃኢ ሁኔታችን ከአሁኑም በእጅጉ አሳሳቢ ነው፡፡

ሀገራችን ከድጥ ወደማጥ እየተንከባለለች መጥታ ዛሬ ላይ ደርሳለች - ነሐሴ ወር መጨረሻ አካባቢ 2018 ኢ.አ ማለትም ዓ.ሂ … የዘመን አቆጣጠሩም እንደጊዜው ተወነባበደብኝ - ለማንኛውም ዓመተ ምሕረት ማለቴ ነው፡፡ (ኦህዲዳችን የሰጠንን አዲሱን የቀን መቁጠሪያ በሾርኒ ማስተዋወቄ እኮ ነው፡- ኢ.አ - እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር፤ ዓ.ሂ - ዓመተ ሂጅራ የሚሉ አማራጮችን በምክክር ኮሚሽን ተብዬው አጸድቀዋል አሉ፡፡) ኢትዮጵያ አሁን የተናጋሪ እንስሳት ማጎሪያ ሆናለች፡፡ ግሩም ጭራቅ መሪ ተሰጥቶናል፡፡ አቢይ ባይኖር ምን ይውጠን ነበር? በሀገራችን የተቸገረው አንድ ሰው ብቻ እስኪመስልና የመቶ ሚሊዮኖች ችግርና ብሶት በአንድ ሰው ሰላማዊ ሰልፍ እስኪወከል ድረስ ዝምታችን መጽናቱ ግን እጅግ አስደንጋጭ ነው፡፡ የቁም ሞት ከዚህ በላይ የለም፡፡

አለሁ ለማለት ያህል እንግዲህ ከዚህም ከዚያም አንዳንድ ነጥቦችን ላንሳ፡፡ በርዕሴ ላይ ያለውን ላስቀድም፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን ኦነግ/ኦህዲድ የሚባል የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐውሬ የኢትዮጵያን መናገሻ አዲስ አበባንና መላውን የሀገሪቱን ሀብት ንብረት ተቆጣጥሮ የምዕተ ዓመታት ቅዠቱን እውን ሊያደርግ ጫፍ ላይ የደረሰበት ዘመን ነው፡፡ ስለዚህን ዓይነቱ አደጋ ብዙዎቻችን ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ ብንለፈልፍም ታይታኒካውያን ኢትዮጵያውያን ግን ከጭፈራቸውና ከዳንኪራቸው ቆም ብለው ሊሰሙ አልቻሉም፡፡ በኦሮሙማና ቅጥረኞቹ አማካይነት አማራ አንገቱ በሠይፍ እየተቀላ ሀብት ንብረቱ ደግሞ በዘረፋ እየተቀማና በእሳት እየጋዬ ባለበት በዚህ የሰቆቃ ዘመን ደስታን ቀነስ ጸሎትን ጨመር እንደማድረግ “ጎጃሞች ዘነጡ” በሚል ዘፈን በአረግራጊ መኪና አደባባይ ወጥቶ ጮቤ መርገጥ በርግጥም የኛን የኢትዮጵያውያንን ሥነ ተፈጥሮ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፤ አንጎላችን መፈተሸ አለበት፡፡ የተነገረውና የተባለው ሁሉ እውነት ሆኖ መርከቢቷ ልትሰምጥ ወይም በአንዳች ተዓምር ልትተርፍ የመጨረሻ ቅጽበት ላይ ትገኛለች፡፡ ያ ቅዠታም አክራሪ ኦሮሙማ ከ500 ዓመታት በኋላ ቤተ መንግሥቱን ማን ሰጠው ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀደም ሲል በመለስ ዜናዊና እርሱ ካለፈ በኋላ ደግሞ በሙት መንፈሱ የሚመራው ሕወሓት የተባለ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል መሆኑን እንረዳለን፡፡

አዎ፣ ለጥፋት የተፈጠረ ከጥፋት ውጪ አይጠበቅበትም፡፡ ለምሣሌ እሳት የተፈጠረው ለማቃጠል … ምግብ ለማብሰል… ብርድን ለማጥፋት ነው፡፡ ከዚህ ተፈጥሮው እንዲያፈነግጥና የውኃ ጥማችንን እንዲቆርጥ ልናደርግ ብንሞክር የእሳትን ተፈጥሮ ካለመረዳት የሚመነጭ ሞኝነት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ሕወሓት በማኒፌስቶው ጭምር በድፍረትና በማንአለብኝነት ያሠፈረውን አማራንና ኦርቶዶክስን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዓላማና ግብ ሰርዞ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን መመኘት የቂልነቶች ሁሉ ቁንጮ መሆን አለበት - እርግጥ ነው ለውጥ አለ፤ ለለውጥ የሚገዛ አካል ግን ያስታውቃል፤ ሕወሓት ለውጥን ራሷን ቢያገኛት አይለቃትም - በጥይት ይደፋታል፡፡ እኔ የምለው ታዲያ አክራሪውን ሕወሓትን ነው፡፡ እኔ በዚህ መልክ አምርሬ የማነሳው የኢትዮጵያ መሠረት የሆነውን የትግራይን ሕዝብ በፀረ-አማራነትና በፀረ-ኢትዮጵያነት የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ አእምሮውን በርዞ ከልሶ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራውን እንዲረግጥና እንዲያቃጥል፣ ኢትዮያዊነትንም አምርሮ እንዲጠላ ያደረገውን የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጠባብ ቡድንን ነው፡፡

 

ኢትዮጵያን ያህል ሰፊ ሀገር ተቆጣጥሮ እየገዛ ባለበት በዚያን የ27 ዓመታት የመንግሥትነት ዘመኑ እንኳን ከትግራይ ነጻ አውጪነት ስሙ ሊላቀቅ ያልፈቀደ የልዩ አጋንንታዊ ተፈጥሮ ሰለባ ነው፡፡ ይህ ቡድን ጥቂት ግለሰቦችን ብቻ ይዞ ቢጠፋ ዕዳው ቀላል ነበር፡፡ ነገር ግን ከሞላ ጎደል የመላውን ትግራይ ሕዝብ አበከተው፤ ለማያባራ መከራም ዳረገው፡፡ እልኸኛና ሰይጣን የሆነ ሰው ዓላማው ከሚኮላሽ ዓለም ብትጠፋ ደስታው ነው፡፡ ሕወሓትን ጤናማ አስተሳሰብ እንዲኖረው መምከርም ሆነ መመኘት ፍሬቢስ ነው፡፡ ለብዙ አሠርት ዓመታት አየነው፤ በተስፋም ጠበቅነው፤ እውነቱ ግን ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡ አዲስ ትውልድ መጥቶ ነባሩን ካልተካና ዘረኝነት ከትግራይ ካልተወገደ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ባመጣው ጣጣ ሲባላ መኖሩ ሊካድ አይገባም፡፡

 

ይህ ቡድን እስካለ ድረስ ኢትዮጵያም አማራም ኦርቶዶክስም ከመጥፋት የሚያድናቸው አንድም ኃይል የለም፡፡ ለ500 ዓመታት ያህል ውስጥ ውስጡን ሲያደባ የነበረው ዐውሬው ኦሮሙማ ኢትዮጵያን የመዋጥና የሚቃዥበትን የታላቋ ኦሮምያ ኢምፓየር ምሥረታ የተቃረበውም በዚህ ሕወሓት በሚባል ቡድን አማካይነት ነው - እርግጥ ነው ኦሮምያን የመመሥረት ሤራ ገሃድ ወጥቶ ሥራ ላይ መዋል የጀመረው ከደርግ ዘመን መባቻ ወዲህ መሆኑ ብዙ መረጃዎችና ማስረጃዎች አሉ፡፡ ለኦሮሙማ መንሰራፋትም ሆነ ለኢትዮጵያ ውድቀት የአማራ ጅልነትና በዋል ፈሰስነትም ቀላል ሚና አልተጫወተም፡፡ አማራን ማታለል ከምንም ነገር በላይ ቀላል ነው፡፡ ገንዘብ፣ ሴት፣ መጠጥ፣ ጨዋታና ድልቂያ ካገኘ አብዛኛው አማራ የማይተውልህ ነገር አታገኝም፡፡ አማራ “ኢትዮያ ኢትዮጵያ” ካልክለት በቂው ነው፡፡ ኢትዮጵያን እስከጠራህለት ድረስ ዝንጀሮም አራት ኪሎ ቢገባ ጉዳዩ አይደለም፡፡ በብዛቱ አይኮራ፤ በሥልጣኔው አይመጻደቅ፤ በምልዓቱ አይጀነን፤ … ምሥኪን ግን ምሥኪንነቱ ክፉኛ የሚያስደፍረውና የሚያስጠቃው ሕዝብ ነው አማራ፡፡ ተባብሮ ቢነሣ እኮ እንኳን ለኢትዮጵያ ለአፍሪካም የሚበቃ ብዙ ነገርና እምቅ ኃይል አለው፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው  - የት ይደርሳል ያሉት ጥጃ ማረፊያው ሉካንዳ ቤት ሆነና አማራን ያህል ታላቅ ሕዝብ እዚህ ግባ በማይባል የበሻሻ ጩልሌ ጉድ ተሠራ፡፡ የአማራ አፈጣጠር ግን በርግጥም ይገርማል … አምስት ቀጣፊ ሆነህ አንድ ሺውን አማራ እንደከብት ልትነዳው ትችላለህ፡፡ አንድ እረኛ አሥር ሺህ በጎችን እንደሚነዳው ማለት ነው፡፡ እቅጭ እቅጩን ነው የምናገረው፤ መንቆለጳጰስ አይጠቅምም፡፡ እንዲህ ባይሆን ኖሮ የአማራን ዘር ለማጥፋት የሚደፍር ግልጽና ድብቅ ኃይል ባልተፈጠረ፤ ኢትዮጵያም ኅልውናዋ ሊከስም ጀምበሯ ባላዘቀዘቀ፡፡

 እንጂ ሕወሓት ባይኖርና ትክክለኛ የትግራይ ኢትዮጵያዊ ቢኖርማ ኖሮ በአሁኑ ወቅት አማራ ትግሬ፣ ሳሆ ብሌን፣ አድዋ ተምቤን፣ ኦቆርዳት ተሰነይ፣ አሥመራ መቀሌ፣ ጎንደር ባሕር ዳር፣ ጎጃም ወሎ፣ ሸዋ ወለጋ … ሳይል መላውን የሰሜን ሕዝብ አርዶ ጨርሶ የዋቄ ፈታ ገዳ ሥርዓት ሊመሠርት አንድ ሐሙስ የቀረው ዐውሬ ኦሮሙማ አማራና ትግሬ በተገኘበት አንገቱ እየተቀላ፣ ሀብት ንብረቱ እየተዘረፈና እየተቃጠለ ባለበት ወቅት ወልቃይትና ሰቲት ሁመራ ላይ ሕወጣት ቀን ከሌት እያላዘነ የጋራ ትግልን ባላጓተተ ነበር፡፡ እንደኔ ወልቃይትና ራያን ማንም ቀቅሎ ሊበላቸው ይችላል፡፡ እነዚህ ቁርጥራጭ የግጦሽም ይሁኑ የሰብል መሬቶች ከ70 እና 80 ሚሊዮኑ የአማራና ትግሬ ሕይወት አይበልጡም፡፡ እዬዬም ሲደላ ነው ይባላል፡፡ የሰው ልጅ ከውሾች እንኳን መማር ካልቻለ ከንቱነት ነው፡፡ ውሾች በአንድ አጥንት እየተጣሉ ጅብን የመሰለ የጋራ ጠላት ቢመጣባቸው አጥንቱን ጥለው ያን የጋራ አጥፊ ይፋለማሉ፡፡ ትልቅ ዕውቀት ነው፡፡ አጥንቱ የት ይሄድባቸዋል? ሕወሓትነት ምን ያህል መረገም መሆኑን የምረዳው ከዚህ ነጥብ አኳያ ነው፡፡ ዋሸሁ?

በነገራችን ላይ አማራ እያደረገ ያለው ትግል ፍትኃዊ መሆኑን ማንም ይረዳዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ሆዳሙና ባንዳው እንዲሁም ለንግሥና የሚሻማው ጅላጅል አማራ በዝቶ ትግሉ በሚፈለገው ፍጥነት አልሄደም እንጂ “አትግደሉኝ ሀገር አታሳጡኝ” ብሎ የነፃነት ትግል ማካሄድ በሰማይም ሆነ በምድር ኩነኔም ወንጀልም አይደለም፡፡ ችግሩ የአማራ ተፈጥሮ ለዬት አለና አደናቃፊው በዛ፡፡ ባልተጨበጠ የአራት ኪሎ ወንበር ገና ከአሁኑ የሚራኮተውንና በሸርና በሤራ እየተጠላለፈ ከኩራዝና ፋኖስ ወጥቶ ሻል ያለች ከተማ እንኳን ሳያይ የሚረግፈውን የሰው ብዛት ስንሰማ በሰው ልጅ ሞኝነትና ከንቱነት እየሣቅን ባላስፈላጊ የኃይል ብክነቱ ግን እናለቅሳለን፡፡ አማራ ውስጣዊና ውጫዊ መሰናክሎች ባይኖሩበት ኖሮ ይሄኔ ኢትዮጵያ ከቡርኪና ፋሶ ይበልጥ በነፃነትና በምቾት በተንደላቀቀች ነበር፡፡ አንድ ወጣት ብቅ ብሎ ነው በዚያች ሀገር የዘመናት ብሶትንና ኋላ ቀርነትን በሦስት ዓመት ውስጥ ብቻ ጠራርጎ ቤት አጥነትንና ርሀብን ታሪክ ያደረገው፡፡ ከ24 ሚሊዮን ሕዝብ አንድ ትራኦሬ ሲገኝ ከ139 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል ደግሞ ሰይጣን የሚቀናበት አንድ አቢይ የሚባል አጭበርባሪ ሉጢ ተገኘና አሣራችንን ያበላናል፤ በጎሣና በነገድም ተከፋፍለን በማን አባት ገደል ገባ የሕጻናት ጨዋታ ተጠምደን አንዳችን ሌላኛችንን በሰላ ጎራዴና ሜንጫ ያስተራርደናል፡፡ ፊደል የቆጠረው ሁሉ ከእሱ ጋር ወይም ከእሱ በተቃራኒ በመሰለፍ ያልበላንን እያከከ በቃላት ጦርነት በመተጋተግ መቀመቅ ይከተናል፡፡ ምን ያልሆንነው አለ …

ጥሩ ጥሩ ትግሬዎች ካሉ ካለፈ መጥፎ ታሪክ ተምረው ከአማራ ጋር ቢተባበሩና ይህን ትግሬንና አማራን ካልጨረሰና ካላጨራረሰ ዕረፍት የሌለው ኦሮሙማ ቢገጥሙት ድላቸው የቀናት ግፋ ቢል የጥቂት ሣምንታት ጉዳይ ነው፡፡ የጋራ ገዳያቸው ከተወገደ በኋላ ደግሞ በሠለጠነ መንገድ ተነጋግረውና ተወያይተው አለን የሚሉትን ችግር ማስወገድ ይችላሉ፡፡ የካንሰርና የጉንፋን ህመሞች ያሉበት ሰው ቅድሚያ የሚሰጠው ለጉንፋኑ ሳይሆን ለካንሰሩ ነው፡፡ አሁን ባለው አስጠሊታ የፖለቲካ ሁኔታ ከአቢይ በቀር አሸናፊ የለም፡፡ የአቢይ እጅ ረጂም ነው፡፡

ከማሕጸን ጀምሮ ሲማር የነበረው ስለተንኮልና ሤራ ነው፡፡ ተፈጥሮው ነው፤ ተልእኮውም - ማን እንደላከውና የማንን አጀንዳ ኢትዮጵያ ላይ እያስፈጸመ እንደሆነ እዚህ መናገሩ ጊዜ ማባከን ነው፤ በዋናነት ግን ኢትዮጵያ ደህና መሪ እንዳታገኝ የውጪ ጣልቃ ገብነት ከዱሮ ጀምሮ መኖሩ መረሳት የለበትም፡፡ ከፍ ሲል ገልጫለሁ፡፡ አንድ ነገር ከተፈጠረበት ውጪ እንዲሆን መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ በፊት በፊት አቢይን እንቀው ነበር - በጣም፡፡ አሁን ግን በዓለማችን ያለፈም ይሁን የወደፊት ታሪክ ማንም ሊስተካከለው በማይችለው ሰይጣናዊ ተፈጥሮው አደንቀዋለሁ፡፡

ዓላማውን ለማሣካትና ወንበሩን ላለማጣት የማይፈጽመው የሤራና የሸፍጥ ዓይነት የለም፡፡ እሱ አንድ ሰው በቻ አይደለም፡፡ አንዱ አቢይ ከሚሊዮንም ይበልጣል - ምንም የማይፎርሽ ልዩ አጋንንታዊ ተሰጥዖ አለው፡፡ አንድ ሰው ንቀህ ደግሞ የምታመጣው መፍትሔ የለም - ከነተረቱ “የናቁት ያደርጋል ራቁት” ነው - እየሆነ ያለውም ይሄው ነው፡፡

በስምንት ዓመታት ውስጥ የዋሸውን፣ ያስመሰለውን፣ የጨፈጨፈውንና ያስጨፈጨፈውን የሰው ብዛት፣ ያታለለውን፣ የቀላመደውን፣ በመሳም ወይም በመጨበጥና በማቀፍ ያበከተውን የምሁርና የታዋቂ ሰው ግትልትል … ስንመለከት የዚህ ሰው ተፈጥሮ ልዩ መሆኑን እንረዳለን (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም በሕይወት አለ ግን?)፡፡ በትምህርት ዜሮ፣ በወታደራዊ ሥልጠናና ግንዛቤ ዜሮ፣ በአይኪውና በመሳሰለው የዕውቀትና የችሎታ መለኪያ ዜሮ ሊሆን ቢችል እንኳን በተንኮልና በሸፍጥ፣ በክህደትና በጥላቻ፣ በአንዳች ነገር የጠረጠረውን ሁሉ በመግደልና በማዋረድ አንድም የሚስተካከለለው የለም፡፡ ታሪክ የሚያውቃቸው እነሂትለተርንና ሙሶሊኒን፣ እነጆሴፍ ስታሊንንና ፒኖሼን የመሰሉ ጨካኞች በጭካኔያቸው የአቢይን አንድ አሥረኛ አይሆኑም፡፡

እነዚያ ቢያንስ የማይገድሉት የማኅበረሰብ አባል ወይም ክፍል ነበራቸው፡፡ ይሉኝታና ርህራሄም ነበራቸው፡፡ አቢይ ግን የግል ጠንቋዩ ከጠቆመው ለምን ልጁን አይሆንም ይደፋታል፡፡ ሚስትና ውሽሞቹንም አይራራላቸውም ያርዳቸዋል፡፡ (የቴሌዋ ፍርዬ ግን ደህና ናት? አልደገመች(ለት)ም ይሆን?) አቢቹ በወንበሩ ቀልድ አያውቅም፤ እንቅልፍ አጥቶ ሲባዝን የሚያድረው ለማን ሆነና! ለዚህም ነው ባገኘሁት አዲስ የድረ ገፅ መረጃ መሠረት 139 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአቢይ ወንበር በጭዳነት ተዘጋጅቶ በየቀኑ ለመታረድ ዝግጁ የሆነው፡፡

ብዙ ሰሞነኛ ወሬዎች ነበሩ፡፡ የምክክር ኮሚሽኑ ማለቂያ፣ የነሐሴን ወር ጠብቆ የአቢይ መጥፋት፣ የእስክንድር ነጋ የቢቢሲ ንግግር፣ የአዲስ አበባ ወደኦህዲድ ግዛት መግባት፣ ኦህዲድ ጋር ተሰልፈው አማራን ስለሚያጠፉ ሆዳም አማሮች ወዘተ. ብዙ መናገር በተቻለ፡፡ ሳልጠቁም ማለፍ የማፈልገው ግን አዲስ አበባ ወደዚህ ወደዚያ ተካለለች የሚሉት የቂሎች ፈሊጥ ነው፡፡ ስለዚህ ነገር ሲንጨረጨሩ ሳይ ይገርመኛል፡፡ ሽንት ቤት ተቀምጦ ፈስ ገማኝ ይባላል? አይባልም፡፡ እያንዳንዱ የአገዛዝ ዘመን ሲመጣ የመሰለውን ሁሉ ያውጃል፡፡ ሲገለበጥ ደግሞ መጪው አገዛዝ የነበረውን እንዳልበር ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ኦህዲድ አዲስ አበባን ወደ ኦሮሙማ በህግ ሰበብ ወሰዳት ብሎ መንጨርጨርን ምን አመጣው? አሁንስ የማን ሆነችና ነው? አዲስ አበባ ውስጥ አሁን አማራና ትግሬ የሚረባ ሥልጣን አላቸው? የላቸውም፡፡ የመንግሥት ቢሮ ሁሉ የተሞላው በማን ሆነና ነው? ስለዚህ ስለነገ ራሱ ይጨነቃልና አትድከሙ፡፡ ቀድሞ የመቀመጫየን ብላለች ዝንጀሮ፡፡ ዛሬን በደህና ባደርን - ነገን ተውትና፡፡ ለአሥር ሺህ ብር ገቢህ ከገቢዎች የተላከ ደቻሣ ፈይሣ 100 ሺህ ብር እንድትከፍል እያስገደደህ አንተ አዲስ አበባን ወሰዱ ትላለህ፡፡ ቢወስዳት ቢወስዳት ባሌን አሳልፎ ኬንያና ማዳጋስካር አይወስዳት፡፡ ዋናው ትኩረት መሆን ያለበት ነቀርሣን ማስወገድ ነው፡፡ ከዚያ ጤናማነት ይመለሳል፡፡

መጻፍ ሳልጀምር ቦታ አለቀብኝና መጻፌን ላቆም ነው፡፡ ለማንቻውም የተመረጡ ይመጣሉ፤ በጸሎትና በቻልነው ሁሉ እናግዛቸው፡፡ እነሱ በደም ሲዋጁን እኛ በስንቅና በትጥቅ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል፡፡ በዚህ ሥርዓት በተለይ በዘር ሐረጋችሁ ምክንያት የምትንገላቱና ሀብት ንብረታችሁን የምትቀሙ ወገኖች ማስረጃችሁን በጥንቃቄ ያዙ፡፡ ትክክለኛ የፍትኅ ሚዛን አደባባይ የምትወጣበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርምና ተስፋ ቆርጦ ማስረጃውን የትም የሚጥል ሰው እንዳይኖር ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ የሚመጣው መንግሥት ጆሮና ዐይን እንደሚኖረው ተስፋ እናደርጋለንና ፍትኅን እንደሚያሰፍን በበኩሌ አምናለሁ፤ የተበደለን የሚክስ - የተጣላን የሚያስታርቅ - የወደቀን የሚያነሣ ትክክለኛ መንግሥት ይመጣል ብዬ እጠብቃለሁ፡፡ ሁሉ ነገር እንዳለ አይቀጥልም፡፡ በቦሌም ይሁን በባሌ የሚመጣ መልካም ነገር እንደሚኖር ይሰማኛል፤ ሁሉም ነገር በወያኔና በልጁ ኦህዲድ እንደተጨመላለቀና እንደበከተ አይቀጥልም፡፡ ፖለቲካውም ሃይማኖቱም ባህልና ወግ ሥራቱም በቅርቡ በአንድዬ ይጎበኛል የሚል ጽኑ ተስፋ አለኝ፡፡

 መልካም ትግሬዎች ታሪክ ሥሩ፡፡ ሆዳም አማሮች ተመለሱ፡፡ ለእናንተ ሳይሆን ለትውልዳችሁም አስቡ፡፡ ተጸጽቶ ከጥፋት መመለስ አያሳፍርም፤ ትልቅነት ነው፡፡ መጥፎው ነገር በካፈርኩ አይመልሰኝ መምጣቱ የማይቀርን ነገር ለማገድ መንደፋደፍ ነው፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ማንንም ላሳስብ የምወደው ለአንደበታችን ልጓም እናብጅለት፡፡ ከጥይት ይልቅ አንደበት ይበልጥ ያደማል፤ ያቆስላል፡፡ አማራ ላይ ስድ አፋችሁን የምትከፍቱ ወገኖች ወደራሳችሁ ተመለሱ፡፡ ትግሬዎች አማራን እንድትጠሉ ያደረገውን የቆዬውን የወያኔ የጥላቻ ስብከት እርሱት፡፡ አማራ ወንድማችሁ እንጂ ጠላታችሁ አይደለም፡፡ ካልተባበራችሁ በኔ ግምት በሁለትና በሦስት ዓመታት ውስጥ ሁለታችሁም ትጠፋላችሁ - ምላሤ ጥቁር ነው፡፡ ግን ግን ሌላ ትንቢትም አለ፡፡ ብናገር ያሳንፋችኋልና ይቅርብኝ፡፡ በሌላም በኩል ያንን ትንቢት ብናገር ኦሮሞ ወዳጆቼን ማስከፋት ይሆንብኛል፡፡ የተዘራው ሁሉ ሲታጨድ ኦሮሞ ያሳዝነኛል፡፡ ኢትዮጵያ ነገረኛና ሸረኛ ሀገር ናት - ወዳጆቿን አትክስም፤ አትጠቅምምም፡፡ ጠላቶቿን ግን አወፍራና አስብታ ስታበቃ በመጨረሻ ባላሰቡበት ሰዓት እገቡበት ገብታ እንደ እንቧይ አንስታ ታፈርጣቸዋለች፡፡ ይህን ከራሴ በላይ አውቃለሁ፡፡ ቀኑን ጠብቅ፡፡ “ዕድሜ ስጠኝ” ብለህ ጸልይ እንድታየው ከፈለግህ - አዲስ ነገር አልነገርኩህም፤ የዐዋጁን በጆሮ ዓይነት ነው፡፡ ሰላም፡፡

 Ethiopian Semay

Wednesday, August 26, 2026

እውን ትግሬዎች ወያኔን ይቃወማሉ? ያንን ለማመን የሚከተሉት የማሳመኛ መመዘኛዎች ማለፍ አለባቸው ጌታቸው ረዳ 8/26/26 ዓ.ም Ethiopian Semay

 

እውን ትግሬዎች ወያኔን ይቃወማሉ? ያንን ለማመን የሚከተሉት የማሳመኛ መመዘኛዎች ማለፍ አለባቸው

ጌታቸው ረዳ

8/26/26 ዓ.ም

Ethiopian Semay

ከየዓረብ አገሮች ምስል የተቀዳ መቀሌ ከተማ የቆመው ለእነ መለስ ዜናዊና የፋሺት ድርጅት (ህወሓት) ታጋዮች ለነበሩት መታሰቢያ ሓውልት ለምን ዓላማ ቆመ? 

ወያኔዎች ኤርትራን ለማስገንጠል፤ኢትዮጵያን ባሕር-አልባ ለማድረግና ኢትዮጵያን በቋንቋ ሸንሽኖ <<ራስ ገዝ አፓርታይድ ክልሎችን>> እና አምሐራንና አርኛን እንዲሁም ዓድዋ ላይ ጣሊያን ሲሸነፍ የተውለበለበቺው ሰንደቅዓላማችንን ለማጥፋት የተመሠረቱበት አመተ ልደታቸው በየአውራጃዎችና ወረዳዎች በየአመቱ እስከ ዛሬ ድረድ ጥቂቶች ቢቃውሙትም በርካታው ሕዝብ ግን እያከበረው ይገኛል

ትናንት “ቴዲ አዋሳ” በሚባል ሚዲያ አንድ ሰው እንዳደምጠው “ዩ-ትዩብ” ልኮልኝ ሳደምጥ አንድ የትግራይ ወጣት ስለ “አቶ ገዱ አንዳርጋቸው” ጉዳይ እና “ጽምዶ” የሚባለው መሳለቂያ አንስቶ ተናግሮ ሲጨርስ ፣ አወያዩ “ይህ ዛሬ በቅርቡ  እየተፈጠረ ያለው አዲሱ የትግራይ ወጣት ልዩ ነው፤ ወያኔን በደምብ አርጎ ይቃወማል...” በሚመስል አባባል ሲናገር ሰምቸው፤ ይህ እምነት በብዙ ሰዎች ሲነገር የምሰማው እምነት ነው። ይህ እምነት ያልተፈተሸ አይደለም። እኛ ጥቂቶች በየወቅቱ ወያኔን እንቃወማለን ብለው ብቅ ሲሉ የፈተሽናቸው ክስተቶች ናቸው።

 በተለያዩ ወቅቶች ካሁን በፊት ትግራይ ውስጥ የተነሱ ምናልባትም ክ9 ያላነሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች ወያኔን ለመቃወም ሲመሰረቱ አስኳላቸው ገልጠን ስንፈትሸው ሃውልቱንም ይሁን የፋሺስት ድርጅት ሆኖ ያገለገለው ወያነ የተባለው “ርዕዮት” የሚቀበሉ እና አክባሪዎች መሆናቸውን ሲናገሩ እና ሲከራከሩ አይተናል አድምጠናል አንብበናል። አንዳንዶቹ እማ ጭራሽኑ ወያኔ ያሰመረላቸው የመገንጠል መብት አክብረው ትግራይን ለመገንጠል የሚንቀሳቀሱ እንደ አሸን የፈሉ ፋሺስት ድርጅቶች ተፈጥረዋል። ሰለዚህም ይህ በዚህ 1 አመት ብቅ ያለው “የወያኔ ተቃዋሚ ወጣት” የሚባለው ክፍል የሚከተለው ፈተና ማለፉን አለማለፉን እናረጋግጥ ዘንድ እነሆ እነዚህን መመዘኛዎች እንፈትሽ።

ጥያቄዎችም እነሆ

1ኛ ጥይቄ - “እንደሚታወቀው የሱዳን ፕረዚዳንት የነበረው “ፕረዚዳንት ዑመር አል በሺር (Omar al-Bashir) እና የሱዳን የስለላ ድርጅት National Intelligence and Security Service (NISS) ( ጂሓዝ ኣል ዓምን ዋል ሙኻበራት ኣል ወተኒ) የተባለው የስለላ እና የደህንነት ጽ/ቤት ዋና ሓላፊ የነበረው የወያ አባል እና ከፈተኛ ስራ ለወያኔ የዋለላቸው ሱዳናዊው «ጀነራል አልፋታሕ ማርዋን” (General alfataH Marwan) በተገኙበት  መቀሌ ከተማ የቆመው ለእነ መለስ ዜናዊና የፋሺት ድርጅት (ህወሓት) ታጋዮች ለነበሩት መታሰቢያ ሓውልት መፍረስ አለበት ብለው  ያምናሉ ወይ? 

2ኛው ጥያቄ -ወያኔዎች ኤርትራን ለማስገንጠል፤ኢትዮጵያን ባሕር-አልባ ለማድረግና ኢትዮጵያን በቋንቋ ሸንሽኖ <<ራስ ገዝ አፓርታይድ ክልሎችን>> እና አምሐራንና አማርኛን ለማጥፋት የተዋቀረው አሁን ያለው የአፓርታይድ አወቃቀር ይቃወማሉ ወይንስ ይቀበላሉ?

3ኛው ጥያቄ- እንዲሁም ዓድዋ ላይ ጣሊያን ሲሸነፍ የተውለበለበቺው ሰንደቅዓላማችንን በነበረቺበት ክብር እንድትውለበለብ ይታገላሉ?

4ኛው ጥያቄ- “ተጋዳላይ ትግራይ ኣርኪብካ በሎ ነቲ ዓሻ አምሓራይ” እያሉ እየጨፈሩ በማኒፍስቶ ላይ ያስቀመጡት « አማራ ገዢያችን ነው፤ የአማራ ሕይወት ዕረፍት እሰክታጣ ድረስ እንታገላለን” እያሉ የጻፉትን ዛቻ እነሆ 35 አመት ሙሉ የአማራ ሕይወት ዕረፍት እያጣ እነሆ እሰካሁንዋ ደቂቃ ድረስ አለ። ይህንን ለማስቆም የመጀመሪያ ማሳያ “የአማራን ህይወት ዕረፍት ለመስጠት ያመች ዘንድ” ፋሺስቶቹ የተመሠረቱበት «አመተ ልደታቸው» በየአውራጃዎችና ወረዳዎች በየአመቱ እንዳይከበር ይጥራሉ?

5ኛው ጥያቄ- ‘’አማራ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች” የሚባሉ የፖለቲካ ትንግርቶች ጨቋኝ ነበር ወይስ አልነበረም ብለው ያምናሉ?

6ኛው ጥያቄ- የዘር ፍጅት (ጀንሳይድ) በመፈጸም በጉልበት ወደ ትግራይ የተጠቃለለው የወልቃይትና አካባቢው ቦታዎች ቅድመ የካቲት 67 የነበረውን የጎንደር መስተዳድር ወደ ቦታው እንዲመለስ ይስማማሉ ወይ?

7ኛው ጥያቄ- በቤተክርስትያናት እና መስጊዶች፤ ትምሕርት ቤቶች፥ ተራራዎች፤ ሕክምና ቤቶች እና የታሪክ ቦታዎች ሁሉ፤ እንዲሁም በየ በዓላት እና ሓይማኖታዊ በዓላት ወቅት ዘማሪዎች ፤ የቀሳውስት /ካሕናት ልብሶች፤ ጃንጥላዎች፤ እና ሕዝቡ የሚያውለበልበው እና የሚለብሰው የወያነ ድርጅት ባንዴራ መሆኑን ግልጽ ነው። ታዲያ ወጣቱ ይህ ባንዴራ የፖለቲካ ድርጅት ምልክት ሰለሆነ ሁሉንም የሚወክል የወላጆቻችን ዓድዋ የተውለበለበቺው የነፃነት ምልክት በኢትዮጵያ ባንዴራ መተካት አለባት ብሎ ይቀሰቅሳል? እነኚህ እና የመሳሰሉ ፈተናዎች ማለፍ ይችላል? የሚሉ ፈተናዎች መፈተሽ አለባቸው።

ርዕሱ ላይ እንዳያችሁት |ብዙዎቹ| ትግሬዎች ይህንን ሲያነቡ እሳት ላይ እንደሚጠበስ ስጋ መንጨርጨራቸው አይቀርም። ምክንያቱም ፋሺሰቶች ሲነኩ የሚያሳዩት ባሕሪ ስለሆነ አይገርምም። የጥላቻ እና የቂም ሃውልት ቀርጾ ለትውልድ የሚያስተላልፉ ሕዝብ ለሕዝብ ቀጣይ ጦርነቶችን የሚጭሩ በየገጠሩና ከተሞች የተተከሉ ትግራይ ወስጥ የቆሙት ሃውልቶቻቸው ካልፈረሱ “ከቂም ወደ ቂም” “ከጦርነት ወደ ጦርነት” ፤ ከውሸት ወደ ዘላቂ የውሸት ትርክት የሚያስቀጥል ምልክት ሰለሆነ የግድ መፍረስ አለበትመመዘኛ አድርጌ የማቀርበውም ይህንኑ ነው። ፈተናው ለአኖሌ ሃውልት አምላኪዎች ለኦሮሞ ወጣቶች እና ለኦሮሞ መሁራን ጭምርም ነው

እነ መለሰ ዜናዊ እና እነ ሥዩም መስፍን የመሳሰሉት የተሰው ታጋዮቻችን እያሉ የሚጠርዋቸውና ሃውልት ያቆሙላቸው ታጋዮቻቸው ያልሆኑትን <ነበሩ> እያሉ በውሸት እንደሚክቡዋቸው ለዲሞክራሲና ለእኩልት የተሰው ሳይሆኑ የወያኔና የሻዕቢያ ተዋጊዎች ከትግራይ እና ኤርትራ ተራሮች ጀምረው በጋራ” ኢትዮጵያዊያንን እየገደሉ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢትዮጵያ ሠራዊትን ወራሪ” “አምሐራይ እያሉ ከጣሊያን በባሰ መልኩ ኢትዮጵያዊውን ሠራዊት 1ሚሊዮን የሚገመት “ሠራዊት እና ቤተሰቦቻቸው” ያለምንም መጠለያና ምግብ ወደ ጎዳና በትኖ ባለማዕርግ መኮንኖች “ኮከባቸው መለዮአቸውን መሬት ላይ አንጥፈው” ሳንቲም እንዲለምኑ ያደረጉ የፋሺስት አለቆቻቸው ድርጊት ፈጻሚ ታጋዮች የነበሩ ናቸው።

ያለተሰውት የተቀሩት በህይወት ያሉት በየ ዓለማቱም ይሁን በሃገር ውስጥ ያሉ ታጋዮችም ፋሺቱ መሪያቸው መለስ ዜናዊ ሲሞት ደም ዕምባ ያለቀሱ ፡ በፋሺሰት የደህንነት አለቆቻቸው እየታዘዙ አምሐራ የተባለው ምሁር እና ኢትዮጵያዊነቱ በጽናት የያዘ የትግራይ ተወላጅ “ጸረ ወያኔ ነው እያሉ” ለቁጥር የሚያዳግት ግድያና ድብደባ በመፈጸምተሳዳጁን እንደ ጅግራ በየገጠሩ እና ጫካ እያደኑ ትግራይ የፍርሐት እና የሽብር መድረክ አድርገው ያንን ሲፈጽሙ፡

ወደ አዲሰ አበባ እንደገቡም እንደ እነ አሰፋ ማሩ የመሳሰሉትም ኢትዮጵያዊያን በጠራራ ጸሐይ አደባባይ ላይ ነጻ እርምጃ ሲወስዱ የነበሩ የግድያና የእስር ድርጊት ፈጻሚዎች እንጂ ለሕዝብ መብት ተሰው የሚሉዋቸውም ሆኑ በህይወት ያሉት ተጋዮች ካንድ ኩሬ “ከትግራይ የፋሺሰት ርዕዮት” የተቀዱ የፋሺስቶች ታዛዥ ተዋጊዎች እንጂ <<ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ>> የታገሉ ታጋዮች አልነበሩም

እነዚህን ታጣቂዎች አሰማርቶ ኢትዮጵያ የተሰራቺበት ድር እና ማግዋን ጥንታዊ ክሮችዋን እንዲበጣጠስና እርስ በርስ እንዲፋጅ ኢትዮጵያ አሁን ላለቺበት መከራ የዳረጉ ይህንን የፈጸሙ የወያኔ ትግሬ መሪዎችና ተዋጊዎች ቢያስ ራሳቸውን ለፍርድ አቅርበው ይቅታ ባይጠይቁም ራሳቸው እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው የሚቆጥሩ ከሆነየተጓዙት መንገድና ድርጊት አውግዘው ታጋዮች ብቻ ሳይሆኑ አሁን ያሉት ወያኔን ይቃወማሉ ተብሎ በየሚዲያው የሚነገርላቸው አዳዲስ የወኔ ተቃዋሚዎች አምነናቸው ለምቀበል «መቀሌ ላይ የቆመው ሃውልትና በየከተማውና ገጠር ጋራ ሸንተረሩ ያቆሙዋቸው የጥላቻ ቀስቃሽ ሃውልቶች እንዲፈርሱ አቋም መያዝ አለባቸው።

የኤርትራ የሽምቅ ተዋጊ ቡድኖች ስሜት በመኮረጅ ቀ.ሃ.ስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አክራሪ የትግራዋይነት ስሜት በማጎልበት 7ቱ የትግሬ ወጣት ተማሪዎች የመሠረቱት የ1967 ዓ.ም የትሓህት ሽምቅ ተዋጊ ድርጅት መሰረታዊ መነሻው ምንድ ነው?

መነሻቸው ልክ እንደ ኤርትራኖቹ ለግንጣላ በድምጽ ብልጫ የትግራይ ሕዝብ አስፈቅዶ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል- (ሬፈረንደምና ፈቃድ እንደምታውቁት “ሽፋን” እንጂ ወያኔ አድርግ ያሉት የሚያደርግ ሕዝብ እንደነበርና አሁንም እንደሆነ የምታውቁት ነው። ሆኖም ሥልጣኑንና ሃብቱን ተቆጣጠሩና ያንን ዕቅድ አዘገዩት) ለዚህም መነሻቸው በዙ ጸረ አማራ መጻሕፍትና ሰነዶችን የጻፉ፤ <<አምሐራንና ኢትዮጵያን ከነ ሰንደቅዓላማዋ እንደ ጠላት ቆጥረው>> ወደ ደደቢት በረሃ የወጡ ፤ ትምህርታቸው በቅጡ ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ነበሩ

መስራቾቹ እነማን ነበሩ?

<<ልባቸው በኤርትራነት ፍቅር የተማረከ ፤ ሙሉ በሙሉ ከኤርትራ ወላጆች የተወለዱ ፤ ወይንም ግማሽ በግማሽ ትግሬና ኤርትራ ፤ እንዲሁም የድርጅቱ ዋና ሐንዲስ የነበረው ከጊዜ በኋላ ወደ “ትግሬነት” የተለወጠው <<ከአምሐራው ጎጃሜው የደ/ዝማች አስረስ ተሰማ ልጅ ከሆኑት አቶ ዜናዊ አስረስ እና ከኤርትራዊትዋ ወ/ሮ አለማሽ ገብረልዑል የተወለደ ሟቹ መለስ ዜናዊ የመሳሰሉ ጸረ አምሐራ የሆኑ ፋሺስቶች የመሰረቱት ፣ የገነቡትና የመሩት ድርጅት ነው።

ሃውልቱ ለነ መለስ ዜናዊ ቆየት ብሎም ሞት እየጎተታቸው ለሚገኙት በትግራይ ወጣቶች ነብስ ሲጫወቱ የነበሩት ለወንጀለኞቹ ለነ ስብሐት ነጋ እና ዛሬም “ሸዋ” የሚል ቃል ከምላሳቸው የማይለየው (የሚዲያ ሰዎች) እና የወያኔ ታጣቂ “አዋጊዎች” እና የፋሺዝም ትግራዋይነት ፖለቲካውን የሚዘውሩት ለነ ስብሓት ነጋ ፥ ለእነ ደብረጽዮን፤ ጌታቸው ረዳ ፤ ሞንጆሪኖ ፤ ቴድሮስ ሐጎስ፤ ዓለም ገብረዋህድ… የመሳሰሉ ጸረ አምሐራ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ግለሰቦች ሲሞቱ በማስታወሻነት ፎቶግራፋቸው የሚለጠፍበት የፋሺቶች ሐውልት ነው። ለነዚህ ነው የተተከለው።

ሃውልቱ የቆመላቸው ታጋዮቹም መሪዎችም <<ገመናቸው>> ስንፈትሽና ትግላቸው ስንመረምር <<በወንጀል የተጨማለቁ፤ በጭፍጨፋ ፤ ሃገር በመክዳት ፤ ኤርትራን በማስገንጠል እቦታው ድረስ ሄደው የተገደሉና የገደሉ ፤ ለኢትዮጵያዊነት ሳይሆን የወያኔ ድርጅት ባንዴራ እያውለበለቡ ኢትዮጵያዊነታቸው ከድተው ለትግራዋይነት የበላይነት ዓላማ “የተሰው” የነ ስብሓት እና የነመለስ ዜናዊ  ሎሌዎች ነበሩ

በአመለካከት የተቃወማቸው ሁሉ በየገጠሩና በየከተማው እየገቡ እንደ ጅግራ እያደኑ ዜጎችን ሲያሸብሩ የነበሩ <<ማፊዮዚ>> ‘የነብሰገዳይ ድርጅት’ ተዋጊዎችና ተላላኪዎች የነበሩ ናቸው (የራሴው የሥጋ ዘመዶቼም ጭምር) ።

ኢትዮጵያ ወታደሮችን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነታቸውን አጥብቀው ያደመቁ ሃገር ወዳድ ኤርትራዊያን ከከሓዲዎቹና አምሐራን በጠላትነትን ከፈረጁ በስሜት ከሚጋልቡ ደናቁርት የኤርትራ ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር አብረው መረጃ በመስጠትና በማሳፈን አሳልፈው ሲሰጡ የነበሩ ፤ እንዲሁም ዓድዋ ከጣሊያኖች ጋር ጦርነት ሲደረግ በድል የተወጣችውን ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ያውለበለቡዋት ሰንደቅዓላማችንን ጨርቅ ነው ብሎ ኮከባዊ የሰይጣን አምልኮ ያለበትን ምልክት በማድረግ ሃገሪቱ ውስጥ 44 ባንዴራዎች እንዲወለበሉና “እንድትዋጥ” በማድረግ የሃገራችን ኩራት የሆነቺውን የወላጆቻችን ዓርማ ከኢትዮጵያዊያን ገላ የገፈፉ ባንዳዎች እንጂ ኢትዮጵያዊ ታጋዮች አልነበሩም ሰለዚህም ሐውልቱ መፍረስ ቀዳሚ መለኪያ መሆን አለበት።

ጀርመንን እንመልከት

አስተዋይ ጀርመኖች ሃገራቸው ከናዚ አመለካከት እንድትጸዳ ለናዚ ታጋዮችና መሪዎች የተተከሉ ሃውልቶች እንዲገረሰሱ ወይንም ወደ ሚዚዮም እንዲታሸጉና ናዚያዊነትን ከሕዝቡ ሕሊና ለማፅዳት ሞክረዋል።

ቤተ መፃህፍቶች ሁሉየያዙዋቸውን መጽሃፍቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉንም የናዚ ፕሮፓጋንዳ ቁሳቁሶችን እንዲያስረክቡ ጠይቀዋል።

ትግራይን እንመልከት

በተመሳሳይ ትግራይ ውስጥ በየትምህርት ቤቶችና መዋዕለ ህጻናት፤ በየሕክምና ተቋማትና ቤተ እምነቶች የወያኔ ናዚ ፓርቲ የሚያወድሱ መጽሐፈቶች፤ ግጥሞች፤ ዘፈኖች፤ መጽሔቶች፤ ጋዜጦች፤ ፖስተሮች፣ ሐውልቶች፣ በማን አለኝነት ጥንታዊ ስሞችን በመሰረዝ በምትካቸው በታጋዮቻቸ ስም የተሰየሙት ሃውልቶች ትምህርት ቤቶች ፥ የመንገድ፤ የወንዝ፤ የተራራ፤ የቅርሳቅርስ አካባቢዎች ስሞች ምልክቶች እና አርማዎች በሙሉ ተሰብስበው ወደ ማጎርያ ሙዚየም ወይንም መታጎር ወይንም መፍረስ ወይንም መቃጠል አለባቸው።

በሚያሳዝን ሁኔታ ጥንታዊ ጥናት ለማካሄድ ወደ ትግራይ የሚሄዱ የውጭና የሃገር የታሪክ ተመራማሪዎችና ጸሐፍቶች በሚያደናግር መልኩ “በአዳዲስ ስሞች” ብዙ ሸለቆች፤ መንደሮች፤ ገጠሮች ፤ ተራሮች፤ ሜዳዎችና ወንዞች” በታጋዮቻቸው ስም በመሰየማቸው ተመራማሪዎቹ ችግር እንደሚገጥማቸው እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ለወደፊቱ አዲስ ትውልዶች እና ተመራማሪዎችን ከማደናገሩ በፊት ያንን ችግር ከማስከተሉ በፊት የተሰየሙት ተጠንተው እንደገና ወደ ጥንታዊ ስሞቻቸው መለወጥ አለባቸው።

ትግራይ የወያኔ ድርጅት ተከታዮች ንብረት ብቻ አይደለችም፡ የወያኔ ተቃዋሚዎች የሆንን የኛም የትውልድ ቦታችንም ነችና ድምጻችን መሰማት አለበት!

ከተሰውት ታጋዮቻቸው ደምቆ በግዙፍ ፎቶግራፍ በሃውልቱ አዳራሽ የተለጠፈለት የዚህ ድርጅት መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ያለ ባሕር በር እንድትቀር ማመልከቻ ጽፎ ለእናት መንደሩ ለኤርትራ ወግኖ የተጫወተው ወንጀለኛው መለስ ዜናዊና መሰሎቹ እንዴት ሲሆን ነው ለነዚህ ከሃዲዎች ሃውል ቆሞላቸው “ሰማዕታት” ተብለው መዘከር የሚኖርባቸው?

የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ከሆነ <<ሃገር ያስደፈሩ ባንዳ ነብሰገዳዮችና ዘራፊዎችን ማውገዝ አለበት>> ካልሆነ አይደለሁም ካለም ወያነ ማለት እኛ ነን እኛ ማለት ወያኔ ማለት ነው፤ ስለዚህ የወንጀሉ ተባባሪ ነን የሚለው እውን ሊሆን ነው።የሆነውም ያ ነው።

ሃውልቱ ቆሞላቸዋል የተባለላቸው ታጋዮች ምንም የታሪክና የፖለቲካ ምጥቀት ያልነበራቸው ታጋዮቻቸውም በውሸት <<ለዲሞክራሲና እኩልነት ሲሉ የተሰው ናቸው>> እየተባለ ለነ መለስ ዜናዊና ለታጋይ አሽከሮቹ ሲዋሽላቸው ስሰማ የትግሬዎቹ እውነታን የማዛባት ባሕሪ መቸ እንደሚቆም ሁሌም ይገረምኛል።

ታጋዮች ሲባልላቸው የነበሩት እኮ ብዙዎቹ እናውቃቸዋለን። ዲሞክራሲና እኩልነት ምን ማለት እንደሆነ የማያውቁ በህጻንነታቸው ወደ ትግሉ የገቡ “ሰው ሲገድሉና ሲገርፉ” የነበሩ የፋሺሰቱ የነ ስብሓትና የመለስ ዜናዊ ታዛዥ ተዋጋዎች ሲፈጽሟቸውና ሲዘፍኑዋቸው ከነበሩት መልዕክቶች አኳያ የዲሞክራሲና የዕኩልነት የሚያስተላልፍ መልዕክት አልነበረም።

ይህ አጽንኦት የሚሰጠው ለዲሞክራሲና ለዕኩልነት ነበር የተዋጉት የሚባልላቸው ተዋጊዎች ምን ሲያደርጉ እንደነበር እኮ እናውቃለን። ታሪካቸው አንብበናል፤ በአካል አይተናቸዋል፤ አወያይተናቸዋል፤ ስሜታቸው አንብበናል፤ አምሐራ ማለት ምን ማለት አንደሆነ ሲተረጉሙት፤ካንደበታቸው የሚወጣ አስጸያፊ ቃል አድምጠናል፤ ፍጹም ፤ እየተባለላቸው የነበረው ያልነበሩ ፤ “ግደል ሲባሉ የሚገድሉ፤ ደብድብ ፤ እሰር ፤ አሰቃይ” ሲባሉ የሚፈጽሙ፤ አባት እህት ወንድም ግደሉ ሲባሉ ቤተሰቦቻው ሲገድሉ የነበሩ Cambodia’s Khmer Rouge; የካምቦዲያ ኸመሩዥ ኮሚኒሰትና ፋሺስት ተዋጊ ዓይነት ገራፊዎችና በየገጠሩና በየከተማው በሕዝቡ ሕይወት ላይ ሽብር የሚለቁ የፋሺሰት ድርጅት የሽብርና የጥፋት ታጋዮች የነበሩ ናቸው።

እዚህ ሥልጣን ከያዙ አዲስ አበባ እንኳ ኢትዮጵያዊነታቸው አጥብቀው ለያዙ ዶ/ር ሃይሉ አርአያ ስለ ትግሬ መርማሪዎችና ፖሊሶች ምን እንዳሉ ታስታውሳላችሁ።

<<…ከቤቴ እየደበደቡና እየተሳደቡ የወሰዱኝ የትግራይ ልጆች ነበሩ። ማዕከላዊ እንደደረስኩ ቀበቶዬን ያስፈታኝ የትግራይ ሰው ነው። ከእርሱ ተቀብሎ አንድ የፍሪጅ ያህል የሚቀዘቅዝ ክፍል አስገብቶ የቆለፈብኝ የትግራይ ሰው ነው። ሲመሽ ሽንት ቤት ወስዶ ያሸናኝ ሰው የትግራይ ሰው ነው።እየተሳደበ ቃሌን የተቀበለኝ የትግራይ ሰው ነው።በእርግጥ እኔ የትግራይ ሰው ሆኜ ከአንድ አካባቢ በወጡ ሰዎች ጥቃት እየደረሰብኝ እንደሆነ ከተሰማኝ ሌላው ሰው ምን ሊሰማው እንደሚችል አስቤ ለትግራይ ህዝብ ከልቤ አዘንኩለት። ይሄ ሁሉ የሚደረገው ለትግራይ ህዝብ ሲባል ነው መባሉ ደግሞ የበለጠ ሰላሜን ነሳው።>>

ይህን ምስክርነት የሰጡት የትግራይ ተወላጁ የቅንጅት ፓርቲ አመራር የነበሩት ዶክተር ሃይሉ አርአያ ናቸው ። ተሰው ተብለው ሃውልት የቆመላቸው ታጋዮች በሕይወት ዛሬ ቢኖሩ ኖሮ ከነዚህ አረመኔ ፖሊሶችና መርማሪዎች የሚለዩ አይሆኑም ነበር።

መቀሌ ውስጥ የቆመው ጸረ ኢትዮጵያ የጥላቻ ሃውልት ለታጋዮቹ መዘክር በሚል ሽፋን የተገነባ ይሁን እንጂ ዋና ተልዕኮው <<በትግሬና ኢትዮጵያ አስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ በታጠቁ ታጋዮች፤ በትግራይ  ምሁራን እና ጋዜጠኞች “ሸዋ” የሚለው ቃል ዛሬም በየንግግራቸው ሲደነቅሩት የሚታይ የማይበርድ ቀጣይ የአምሐራ ሕዝብ ጥላቻና ጸረ <<ብሔረ ኢትዮጵያ>> የሆነ “ግጭትና ጦርነት በዘላቂ ለማስቀጠል የቆመ” የወያኔ መሪዎች ያቆሙት የጥላቻ ሃውልት ነው።

 ሃውልት አቁማናል፤ በየሰልፉ ለታጋዮች የደቂቃ ጸሎት እናድርግ እያሉ ሕዝብን ለማታለል የሚጠቀሙበት ማታለያ ዘዴ ካልሆነ በቀር በሕይወት ያሉ በትግሉ ቆስለው እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ ጥይት ከገላቸው ውስጥ ተሰክቶ የቀረ “ስራ የሌላቸው” የራሴ ወንደሞችና ዘመዶች ፤ በየስብስባው ለፕሮፓጋንዳ ማሳመርያ የሚያደርጉት <ዝኽሪ ንስውኣትና> (ለታጋዮቻችን የሕሊና ፀሎት) እያሉ በውሸት የሚጸልዩት ማታለያ “ፀሎት” የሚያደርሱትም ሆኑ እነ ስብሓትና እነ ደብረጽዮን” ሳይሆኑ የሚረድዋቸው እኔ ካለኝ ጥቂት ገንዘብ እየላኩኝ ነው ኑሮአቸው የሚገፉት።

የነዚህ ፀሎት አድራሾች እውነታ ግን <<ዛሬም ሂድና ሙት ቁሰል ትግራይ ትዕወት>> እያሉ ወጣቱን ማስጨረስ ነው። በመሪነት የተቀመጡትም የመሪዎቹ ልጆችና ዘመዶች ግን በየፈረንጅ እና ቻይና ሃገር እያላኩ በምቾት አስተምረዋል፤ሃብት ገንብተዋል። <<ለማያውቅሽ ታጠኚ>> የሚባለውም ለዚህ ነው።

ለዚህ ነው ድሕረ ናዚ “ጀርመን እንዳደረገቺው” ኢትዮጵያም <<ኢትዮጵያዊ መሪ ስታገኝ>> ሃውልቱ ከስሩ ተደርምሶና ደቅቆ ወደ ቆሻሻ መጣያ መጣል እንዳለበት ለብዙ አመት የምወተውተው።

አንድ ዘመዶቹ በግፍ የገደሉበት እስከዛሬ ድረስ ምንም ፍትሕ ያላገኘና ወያኔዎችን መከስስ የማይቻልባት ትግራይ ውስጥ የሚኖር ስሙን ለመግለጽ የማልፈልገው ሰው ፤ ባንድ አጋጣሚ ለጉብኝት እዚህ አሜሪካ መጥቶ ያነጋገርኩት አንድ የትግራይ ልጅ ስለ ሃውልቱ አንስቶ ሲያጫውተኝ፤ እንዲህ ይላል፡

 <<መቀሌ ጎዳናዎች ስዘዋወር የማያቸው የወያኔ አርማዎችና በተለይ ሃውልቱን ስመለከት በቦምብ የማጋየት ስሜት ይጫነኛል።የቤተሰበቼ ደም ከንቱ ቀርቶ ገዳዮቹ ሃውልተ ቆሞላቸው ሳይ ብሶቴ ያስቸግረኛልበተለይ ደግሞ እዚህ ውጭ አገር ሆነው የሃወልቱ ምስል በየ ዩቱባቸው ለጥፈው ስመለከት የቤተሰቦቼ ገዳይ ድርጅት ተባባሪዎች ሆነው ሳያቸው በሰለጠነ ሃገር የመኖር ትርጉሙ  “ኮንሴፕቱ” ሊገባ አልችል ብሎኝ ሁሌም አስባለሁ>> ሲል ምሬቱን አጫውቶኛል።

በሚያስገርም ሁኔታ ይህ ድርጅት ላለፉት 50 አመት ያመጣልን ምን በጎ ነገር አለ? ብሎ የጠየቀ የትግራይ ሕዝብና ምሁር አላየሁም (ካሉም ጥቂቶች ናቸው)። ሞት፤አካለ ስንኩልነት ፤ ብጥብጥ፤ እርዛት፤ ውርደት፤ የባሕር-በር ማጣት፤ ዘረኛነት፤ ሃገር አልባነትና ስደተኛነት “የወያነ ትግራይ” የትግል ውጤት እንደሆነ ፍጹም ሊታያቸው አልቻለም

በቅርቡ ከስንት ውርደትና አካለ ስንኩልነት በኋላ ፤ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ ድርጅት ጋር ላለመቀጠል ዛሬ በቅርቡ አንዳንድ ትንሽየ ነጸብራቅ እንኳ ቢታይም 99.9% ሕዝቡ የድርጅቱ “ባርያ” ሆኖ ለመቀጠል የወሰነ ነው የምልበትም ምክንያት ያቀረብኩዋቸው የማለፊያ ፈተናዎች እስካላለፉ ድረስ ነው

 ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ተቃወመ እያሉ ሕዝቡ ለሁለት ስለተከፈሉት የወያኔ መሪዎች ደጋፊና ተቃዋሚ ሆኖ በመታየቱ ብቻ <<ወያኔን የተቃወመ እየመሰላቸው ብዙ የሚያስጮሁት ሚዲያዎች ስሰማ የትግራይ ማሕበረሰብ ዛሬም የወያኔ ባንዴራ እየለበሰ በየአደባባዩ ሲወጣ መልዕክቱ ምን እንደሆነ እንኳ ሚዲያዎች ሊረዱት አልቻሉም።

ማሕበረሰቡ በብዛት ወጣት ነው። ይህ ወጣት ደግሞ የወያኔ ጡት (ፖለቲካ) እየጠባ ማደጉና ወያኔ ማለት የማይረሳ የናቱ ጡት መሆኑን ምን እንደሚል ላስደምጣችሁና ልደምድም

መቀሌ ውስጥ በትምክሕት ሲጨፈር የነበረውን የተለመደው የመቀሌ የእንደርታዎቹ የዘፈን ጭፈራ ንግግር በቪዲዮ የተቀረጸው በደስታ የቀለጠው ትምክሕታዊ የደስታ ጭፈራ እንዲህ ይላል፦

 

ናዓና ዝመስል የለን(እኛን የሚመስል ተወዳዳሪ የለም) ትግራዋይ ዝመስል ባዓል ስረ የለን(ትግሬን የሚያክል ባለ ሱሪ ወንድ የለም) ! ! ምስ ወየነ እየ ዝዓበኹ) (! ! ከወያኔ ጉያ ነው ያደጉት!) “! ~ ወያነ እንዳበልኩ እየ ዝዐበኹ( ! ! ወያኔ እያልኩ ነው ያደግኩት)መቐለ ፤መቐለ!!! (መቀሌ! መቀሌ!) “ናይና! ናይና ናይና!!” (የኛ ነች የኛ!!)ኣየኹም ናይና!!” (የኛዎቹ ኣይዝዋችሁ!!)”” ሲል ነበር ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት።

ይህ ወጣት ነው ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ሚዲያዎች በተሳሰተ ድምዳሜ ደርሰው <<የትግራይ ሕዝብ ጦርነት ይብቃን አለ፤ ወያኔ ተቃወመ>> እያሉ የሚዘግቡት፤ ጦርነት ይብቃን ስላለ ብቻ “የወያኔ ርዕዮት” ተቃወመ ወይንም የወያኔ መለያና አርማ ጣለ አወገዘ ማለት አይደለም። የናዚ ወጣቶች ጦርነት ይብቃ ብለው የስዋስቲካ ምልክትና የሂትለር ዓርማ ካልጣሉ “ዞር አሉ አልሸሹም ነው”

ናዚ ወይንም ፋሺዝም የሚኖርበት ፍልስፍና ትዕቢትና እኛ ማን አህሎኝነትና ጦርነት በመቀስቆስ ነው። ስለሆነም ትግሬዎች ፍኖተ ካርታቸው ካላስወገዱት፤ ጦርነት ስለተቃወሙ ብቻ ፤ እስኪደላደሉ እንጂ ያ ጊዜያዊ እን ዘላቂ አይሆንም (አዲሰ አበባ ከተማ የሚኖረው የአባዲ ዘሞ ልጅ-  የመዘክር አባዲ ያስነበብኩዋችሁ ጽሑፍ እና ንግግር አስታውሱ)። ፈረንጆች እንደሚሉት ፖለቲካቸው ካላስተካከሉት <<ጋርቤጅ ኢን ጋርቤጅ አውት garbage in garbage  out>> (ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ) ዓይነት ነው።

ስለሆነም ነው ይህ የወያኔ ጡት እየጠባ ያደገ የወያኔ ሎሌ እራሱን ለማዳን ስንጥርና ስንታገልለት እጅግ ከባድ የሆነብን።

ይህ ትግራይ መቀሌ ውስጥ የተተከለው የነ መለስ ዜናዊ ሐውልት መታሰቢያነቱ <<ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትን የሚያስታውስ>> ሳይሆን በጣሊያን እና በትግዎች መካከል የተካሄደ ጦርነተና የቆመ መታሰቢያ ሆኖ የተመሰለ ተምሳሌት ነው። ይህንን የናዚ ፋሺቶችና ወንጅለኞች ሃውልት እንደ ቤተ ጸሎት ሰጊድ ሰላም የሚሰግዱ በርካታ “የድርጅቱ ካልቶች” እያየን ነው። የተለጠፈው ቪዲዮ የሚያሳየን መረጃም ይህ ነው።

 

ሃውልት ይኑር ከተባለም

 <በወያኔዎች ግፍ የተገደሉና ደብዛቸው የጠፋ>> የሚል ሃውልት እና ሚዚየም በየገጠሩ እና  መቀሌ ውስጥ ይቁም። ሃውልቱ ማጠቃለል ያለበት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብት የተዋደቁ የባሕር ወደቦችን ለማስከበር ኤርትራ ሳሕል ተራሮች ላይ መስዋዕት ለከፈሉ በወያኔ ታጋዮች የተገደሉ ጀግኖች እና በመለስ ዜናዊና በትሕነግ አመራር አባሎችና የድርጅቱ “ሓለዋ ወያነ እና ክርቢት በተባለው የገዳይና አሸባሪ ቡድን አባላት ምክንያት በየገጠሩና በየከተማው በግፍ ለተገደሉ ንብረታቸው የተነጠቁ ፥ ደብዛቸው ለጠፋ ወጣት የትግራይ ታጋዮችሆኑ ድርጅቱን የተቃወሙ አረጋውያን እና ወጣት ምሁራን የትግራይ ተወላጆች፤

እንዲሁም በወያኔዎች ግፍ የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳንፈልጋቸው 27 አመታቸው!” ብሎ የተፋቸው ሥልጣን ላይ በቆየባቸው 27 አመት ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ በወያኔ የደህንነት አባላት የተሰወሩ፤ አሰቃቂ ድብደባ ፤ ግድያና ጭፍጨፋ ለተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን ጭምር ከወያኔ ሃውልት ጎን ለጎን ሌላ ሃውልት ይቁም።

ስለዚህም ነው ሃውልታቸው “ፀረ መብት፤ ፀረ አምሐራና ፀረ ኢትዮጵያ ትግላቸው” መልሶ መላልሶ የሚያስታውሰን፤ ለሃገር አንድነት ያልቆሙ ፤ <<ተጋዳላይ ትግራይ አርኪብካ በሎ ነቲ ዓሻ አምሓራይ>> የሚለው ፤ ጭፈራቸውና መራራ ጥላቻቸው ወደ ትውስታችን አምጥቶ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ዳግም የውስጥ ምሬትና ቁጭት ስለሚቀሰቅስ እርስ በርስ ዳግም ጸብ ላለመቀስቀስ መፍረስ አለበት። በዚህ አንደ አመት ውስጥ ወያነ የተቃወሙ ወጣቶች እየመጡ ነው ከተባለ ይህንን ፈተና ማለፍ አለባቸው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)