Saturday, March 28, 2009

የረሳናቸዉ ሰማዕታት

የረሳናቸዉ ሰማዕታት (ከወያኔ ገበና ማህደር)
ጌታቸዉ ረዳ
“ሞኝና ወረቀት የያዘዉን አይለቅም” እንዲሉ በወረቀት ከመመዝገብ ያመለጡ አያሌ የወያነ ትግራይ ነጻ አዉጪ ድርጅት ወንጀሎች እንዳሉ ሁሉ ፣ወረቀት የመዘገባቸዉ በተባባሪዎቹና በመሪዎቻቸዉ የተፈጸሙ ወንጀሎችም አሉ። ከዚህ የተነሳ፣ ወያኔ የብዙ አመታት ወንጀሎቹን ልደብቅ እንኳ ቢል “ሞኝና ወረቀት የያዘዉን አይለቅም” ነዉና የተዘገበ ስለሆነ ፣ በጊዜ ጉዳይ ይዘገይ እንደሆን እንጂ ይጠየቅበታል። ይልቅኑ የብዙ አመታት በርካታ ወንጀሎቹ በየቀኑ ይፋ ሆነዉ በየሚዲያዉ እንዳይሰራጩ ፣ተቃዋሚ ነን የሚሉን ክፍሎች ፣ በየወቅቱ ከሚቀያየሩ ሁኔታዎችና በአዳዲስ የፖለቲካ ተዋናዮች እየተማረኩ፣አዳዲስ የድርጅት አርበኞቻቸዉን ዝና ለማስቀደም ሲሉ “ለአንድነትና ለሃገሪቱ ክብር ሲሉ መስዋዕት ሆነዉ ብዙ አመታት አልፎአቸዉ በየጉድጓድ እስር ቤቶች ተወርዉረዉ አስቸጋሪ ሕይወት እየገፉ ያሉት እና በሕይወት የሌሉ ከሕዝቡ ሕሊና እየተረሱ-የመጡ ብዙ እጅግ በርካታ የሆኑ ወጣቶችና አዛዉንቶች ኢትዮጵያዉያን እንዲረሱ አስተዋጽኦ እያደረጉ ናቸዉ። በየእስር ቤቱ ሆነዉ የድርጅት አባሎች ያልሆኑ የ“አድኑን” ድምጽ ካስሰሙ ብዙ አመታት ላለፋቸዉ ዜጎች በሻማ መብራት የመዘክር መድረክ ሳያሰታዉሷቸዉ ዛሬ የምናያቸዉ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ክፍሎች ለድርጅታቸዉ ቅርብ የሆኑት መሪዎቻቸዉ ሲታሰሩ ብቻ “ነጋ ጠባ ካለመታከት” ሲጮሁላቸዉ ስንመለከት፣ ይህ “የድርጅት ፍቅርና ወገንተኝነት” *በሽታ* ሳይታወቃቸዉ የወያኔዉን-ያህል “የወገንተኝነት” የስበት ሃይል እነሱም እየተጓዙበት ይመስላሉ።ጎሰኛነት፣ጎጠኛነት ወገንተኛነት “ለነገድ”ፍቅር ብቻ የሚገለጽ ጠባብ የሕሊና ፍቅር ቢሆንም ፣ “የድርጅት ተከታዮች”-ለመሪዎቻቸዉ ካላቸዉ “ልዩ ፍቅር እና አክብሮት” የተነሳ መስዋዕት ለሆኑት ከድረጅታቸዉ ዉጭ ለሆኑ ለሌሎች ዜጎች ያለቸዉ ፍቅር በጣም “ደካማ”ስለሚያደርገዉ “ከድርጅታቸዉ ዉጭ ለሕዝብ መብት ሲሉ ለሚሰቃዩ እና መስዋዕት ለሆኑ ሀገራዊ ዜጎች”እኩል አክብሮት ካልሰጡ፡ በተቃዋሚነት ቢንቀሳቀሱና ቢጮሁም “የድርጅት ወገንተኛነት-ስሜት”-“ከጎሳ ወገንተኛነት ስሜት” ስለማይለይና ለትግሉ ጎጂ ስለሚሆን ፣ ለተወሰኑ የወያኔ ሰለባ ለሆኑ ግለሰቦች ብቻ “ጥብቅና ቆሞ -ወያኔን ከስልጠኑ እስወግዳለሁ ማለት የ ”ፋንታሲ” ጉዞ ስለሚሆን ዛሬም ይታሰብበት እያልኩ ወደ ዛሬዉ ከሰማዕታት ማህደር የመረጥኩላችሁ በወያኔ ትግራይ መንግስት የተገደሉት “መስዋዕቱ ባህታዊ ፈቀደ ስላሴን” በዚህ ዓምድ እናስታዉሳቸዋለን። ኢትዮጵያ በታሪኳ የገደልዋት እንደነበሩ ሁሉ፣ የሞቱላትና ዛሬም የሚሞቱላት አላጣችም። አገራችን በአረመኔዎች በተስፋፊዎች ሴራ ምክንያት ሃይማኖቷን ለማስለወጥ አንድነቷን ለማፈራረስ አያሌ ጊዜ አስቸጋሪ ወቅቶችን ተጋፍጣለች። በዘመናችን እንኳ በግምባር ቀደም የሚታወሱት እፁብ ኢትዮጵያዊያን መካከል መስዋዕቱ “ፕሮፌሰር ዶ/ር አስራት ወልደየስ” እና ከሞት በር በሕዝብ ብርታት ተጎትቶ የወጣዉ አሁንም አርአያነቱ እየቀጠለ ያለዉ ወጣት ሙሁሩ “ፕሮፌሰር ዶ/ር ታየ ወልደሰማያት” ፈታኝ በሆኑ ወቅቶች ያገር ጠላት የሆነዉን ባንዳዉ ወያኔን ተጋፍጠዉ አኩሪ ታሪክ ካስመዘገቡት “ኩሩ” ዜጎቻችን ጥቂቶቹ ናቸዉ። እነ ፊታዉራሪ ጎሪ እና ኤርትራ ኢትዮጵያዊዉ አቶ አበራ የማነአብ እና በሺዎች ሳንረሳ ማለቴ ነዉ። በሃይማኖት መሪዎቻችን በኩል ወያኔን በመቃወም ብዙ ጳጳሳት ካህናትና ድያቆናት ለሞትና ለስደት ተዳርገዋል። ወያኔ የኢትዮጵያን ተዋህዶ ቤተክርስትያን ለማዳከም በረሃ ዉስጥ እያለ በካህናትና በዲያቆናት እንዲሁም በመነኮሳት ላይ አሰቃቂ ግፎችን መፈጸሙ ከአንድ ሁለት ጊዜ በወያኔ የገበና መህደር ላይ ለህዝብ አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል። ጣሊያኖችና ግራኝ መሐመድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ ሲፈጽሟቸዉ የነበሩት ግፎች ዛሬም ወያኔ በግልጽና በተዛዋዋሪ እየፈጸማቸዉ ይገኛል። ጣሊያን “አገሬን አልክድም” ባሉት በመስዋዕቱ ጴጥሮስ ላይ የፈጸመዉን ግፍ፣ ወያኔ ደግሞ ዓለም በቃኝ ብለዉ በመነኮሱ ባህታዊያን ላይ የጥይት ቃታ ስቦ ፋሽስታዊ ግፍ ፈጸሟል። በወያኔ ጥይት ከተረሸኑት መነኮሳት/ባህታዉያን መካከል አንዱ “ብህታዊ ፈቃደ ስላሴ” ናቸዉ። በጥር 1 ቀን 1989 ዓ/ም የኚህ ባህታዊ ሞት በተሰማ ወቅት፣ ለባህታዊዉ ሞት ቀጥተኛ ተጠያቂ የሚሆኑት የወያኔዉ ጳጳስ ጳዉሎስ እና መንግስታቸዉ ፋሽስታዊነታቸዉ ያረጋገጠበት እና የወያኔ ፋሽስታዊ ባሕሪ ሲጠራጠሩ ለነበሩት ሁሉ ማንነቱ ያሳየበት አሳዛኝ ድርጊት ነበር። በወቅቱ ብዙ ጋዜጦችና መጽሄቶች በዚህ አሳዛኝ ድርጊት ላይ ዘግበዉ እንደነበር ይታወሳል። ከዘጋቢዎቹ አያሌ መጽሄቶች መካከል “ላንዳፍታ” ተብሎ ሲጠራ የነበረዉ አሜሪካ አገር ዉስጥ ሲታተም የነበረዉ በወቅቱ የዘገበዉን “ሰላምታ ከወደ አገር ቤት ከወርቃየሁ” በሚል የቋሚ አመደኞቹ የደብዳቤ ልዉውጥ አምድ ላይ ስለ ባህታዊዉ አሟሟት ዘግቦት ነበር። እናስታዉሳችሁ።
“ …ጥር ከመግቢያዉ ጀምሮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንና ምዕመናኑ ሲታመሱ ነዉ የከረሙት። ጥር 1 የልደታ ዕለት ባህታዊ ፈቃደ ሥላሴ በእስጢፋኖስ ቤተክርስትያን መገደል ትልቅ ሽብር ፈጠረ። ጥር-4-ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስትያን በዓሉን ለማክበርና ቃለ ቡራኬ ለመስጠት በፖሊስ ታጅበዉ በቦታዉ የተገኙት አባ ጳዉሎስ “ቡራኬ” ሲሰጡ ሕዘቡ እጁን እያወዛወዘባቸዉ ተቃዉሞዉን በመግለጽ “ሃይል የእዚአብሔር ነዉ ቡራኬዉን አንቀበልም” የሚል ከፍተኛ ጩኸት ተሰምቷል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ብጥብጥ ተነስቶ ብዛት ያላቸዉ ምዕመናን በፖሊስ ታፈሱ። ጥር 7 የሥላሴ ዕለት በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን ከተገኙ ምዕመናን መሐል ፖሊስ ወደ 20 የሚጠጉ የቤተክርስትያኑን ወጣት መዘምራን አፍሶ በመዉሰድ እንዳሰራቸዉ ጋዜጦች ዘግበዋል። ጥር 11 ቀን የጥምቀት ዕለት ጃልሜዳ አባ ጳዉሎስ አሁንም በፖሊስ ታጅበዉ ቡራኬ ለመስጠት ከቦታዉ ሲደርሱ ሕዝቡ ቡራኬያቸዉን ላለመቀበልና ተቃዉሞዉን ለመግለጽ ምዕመናኑ ጠቅላላ ጃንሜዳ ለሳቸዉና ለደቀመዝሙሮቻቸዉ ትቶላቸዉ ሄዷል። እንግዲህ ይህ ሁሉ የሆነዉ በዘህቹ በጥር ወር ግማሽ ጊዜ ነዉ። እንግዲህ ወዳጄ ይግለጡ “ይሰዉረን ከመዓቱ” ብለን እግዚኦታ ከመግባት በቀር ምን ምርጫ አለን። ይሄ በኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እየታየ ባለዉ ሁኔታ አንዳንድ መጤ ሃይማኖት የተደሰቱበት ይመስላል። እንደዉም እንደሚወራ ከሆነማ ያባ ጳዉሎስ የቅርብ አማካሪያቸዉ ጴንጤ ነዉም ይባላል። ምናልባት እሳቱን የሚጭሩ እነሱ ይሁኑ ሌላ ሰይጣን ሁሉም የሚያይ አምላክ ያዉቃል።ለማንኛዉም ያገራችን ነገር፣ ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየከፋ ሄዷል። ሲከፋን ጊዜ ሳንመርጥ ከአምላካችን የምንነጋገርብት ደጀ ሰላም እያስፈራን ከመጣ ሌላ ምንቀረን እንላለን። ቢሆንም የተስፋ አገር ልጆች ነን እና በክረስቶስ ተስፋ አንቆርጥም። አንድ ቀን አንዴ ሁሉ ነገር ይስተካከል ይሆናል። የዛ ሰዉ ይበለን!”
በማለት ሃዘኑን ሲገልጽ፡ በወቅቱ የባህታዊዉ አገዳደል የቀረበዉ ዘገባ በዜና መህደሩ እንደሚከተለዉ ዘግቦት ነበር። ባህታዊ ፈቀደ ሥላሴ በጥይት ተገደሉ
ጥር 1ቀን 1989-ዓ.ም.አዲስ አባባ መስቀል አደባባይ በሚገኘዉ ቅዱስ አስጢፋኖስ ቤተክርስትአን የንግሥ በዓል ይካሄዳል። በመጀመርያ ታቦቱ መጥቶ ሁለት ጊዜ ቤተክርስትያኑን ዞሮ እንደቆመ ያሬዳዊ ዜማና የሰንበት ተማሪዎች ዝማሬ ተሰምቶ እንዳበቃ የደብሩ አለቃ ንግግር በማድረግ የዕለቱን ትምህርት እንዲአደርጉ ፓትርያሪኩ ጋብዘዉ አቡኑ ለንገግርና ለስበከት ሲዘጋጁ አራት ባህታዉያንና ሕዝቡም አብሮ እጅ በማዉጣት “ያቀረብነዉ 21 ጥያቄ ይመለስልን” ሲሉ ይጠይቃሉ። በበዓሉ ላይ የተገኙትን አቡነ ጳዉሎስ፣- የኦርቶዶክስ እምነት መሪነትን የሚቃወሙና የማይቀበሉ ባህታዉያን በወቅቱ በሃይማኖቱ ላይ እየደረሰ ያለዉ መከፋፈል ለመግታት ፣ ‘እምነታችን ላይ ሃይማኖታችን እየተደፈረ ነዉ’-በማለት ‘ማሕበረ ሃዋርያት” በሚል ስም የተቋቋመዉ አዲሱ ማሕበር ያዘጋጀዉን 21 ነጥብ የያዘ የጥያቄ ጽሑፍ ለመስጠት ባህታዉያኑ ቀረብ ለማለት ይሞክራሉ። በዚህን ጊዜ አንድ ፖሊስ “ጥያቄዉን በጽሕፈት ቤታቸዉ እንጂ መጠየቅም መመለስም አይቻልም ብለዋል”። ሲል መልስ ይሰጣቸዋል። ከዚህ በመቀጠልም የማሕበረ ሐዋርያት በአቋም ደረጃ ያስተላለፉትን 10 ገጽ የያዘ ወረቀት ለፖሊሱ ወርዉረዉ ለፓትርያሪኩ ስጥልን እንዳሉትና እንደተቀበላቸዉ ባህታዊ ሃይለሚካኤል የተባሉ ገልጠዋል። ወዲያዉ ግርግርና ጫጫታ ተፈጥሮ- በዚህ ጊዜ ስለተፈጸመዉ ነገር የተለያዩ ነገሮች ተሰምተዋል። ባንድ በኩል ፓትርያሪኩ ከጎናቸዉ ሽጉጥ በማዉጣት በታቦቱ ትክክል ወደ ሰማይ አንድ ጥይት እንደተኮሱና ከዚያም በመቀጠል አጠገባቸዉ የነበሩ ሊቀ ብርሀኑ የተባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትአን የቅርብ አለቃ ሽጉጣቸዉን አዉጥተዉ ሲተኩሱና ሌሎቹም ከየነጠላቸዉ ስር ሽጉጥ በማዉጣት እየተኮሱ ሳለ ባህታዊ ፈቃደ ሥላሴ መዉደቃቸዉ ሲወራ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአባ ጳዉሎስ ጠባቂ የሆነ ፖሊስ ተኩሶ እንደመታቸዉ ተወርቷል።በዚህ መሃከል ባህታዊ አባ ፈቃደ ሥላሴ ፓትርያሪኩ አጠገብ በቅርብ ዕርቀት ተመትተዉ ራሳቸዉ በፅላቱ ስር አግራቸዉ በፓትርያሪኩ ሰር ሆነዉ ወድቀዉ መንጋለላቸዉን ያዩ መሆኑን እኚሁ ባህታዊ ገልጸዋል። እንግዲህ በአሁኑ ጊዜ ይህ ጥያቄ ለማቅረብ ለምን አስፈለገ ተብሎ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ባህታዊዉ ሲመልሱ “በመጀመርያ ጥያቄአችንን በሰላማዊ መንገድ በተለያዩ ወቅት ለፓትርያሪኩ አቅርበን ነበር። ነገር ግን በጥያቄዉ ምክንያት ባህታዉያን ቤተክርስትያን እንዳንገባ እንዳንሳለምም ታግደናል። ፓትርያሪኩ ጽህፈት ቤትም ስንሄድ እያባረሩ ይደበድቡናል።ስለዚህ ጥያቄ ለማቅረብና መስተካከል ያለበትን ለመጠቆም አማራጩ ፓትርያሪኩ የሚገኝትን ክብረ በዓል መጠቀም ብቻ ስለነበር ነዉ” ሲሉ መልሰዋል። በመጨረሻ ላይ ምዕመናን እንዳይንቀሳቀሱ ተደርጎ አባ ጳዉሎስ (“ፓትርያሪኩ”) በጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች ታጅበዉ ከቤተክርስትያኑ መዉጣታቸዉ ተስተዉለዋል። በዚህ ጉዳይ የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም በቅርቡ በአሜሪካ ና አዉሮፓ ጉብኝት አድርገዉ የተመለሱት ባህታዊ ገብረመስቀል በፖሊስ ተይዘዉ በ እስር ላይ ያሉ መሆናቸዉን ዘግይቶ የደረሰን ዜና ገልጿል። ባህታዊ ገብረመስቀል በእስር ላይ እንዳሉ መታመማቸዉና አለመፈታታቸዉንም ተዘግቧል። ሲል በጥር 1 ቀን 1989 ዓ.ም. በወያኔ ጥይት ስለ ተገደሉት ስለ ሰማዕቱ ባህታዊ ፈቃደ ሥላሴ አገዳደል ዘግቦ ነበር። በእኛም የእነኚህ የሃይማኖት መሪዎች ገድልና መስዋዕት ዛሬም በሕሊናችን እና በታሪካችን የሰማዕታት ማህደር ህያዉ ናቸዉ። ኢትዮጵያ በነጻነት ትኑር!ጌታቸዉ ረዳ መጋቢት 2001 ዓ.ም www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Friday, March 27, 2009

Revisiting Ethio-Eritrean issues

Revisiting Ethio-Eritrean issues
On March 15, 2009—San Jose has hosted a discussion forum on the Ethio-Eritrean issues. The honorable invited guests on this topic were Professor Tesfatsion Medhanie from the University of Bremen, Germany and Professor Daniel Kendie from the University of Henderson in Arkansas, United States. Both scholars have written books on the Ethio-Eritrean issue. The meeting has driven lots of participants and it was a successful event. The Amharic version of what the first speaker, Professor Tesfatsion, presented to the audience will soon be posted on the Internet in its entirety. In brief, his presentation focused on confederation as the framework for the closest relations possible between the two countries. He dwelt at length on the difference between confederation and federation. But even for this confederal union to be realized, there are some prerequisites. They include political changes in both Eritrea and Ethiopia; this means, among other things, that there have to be governments of national unity in both countries. Besides, there are also psychological barriers on the part of Eritreans as well as Ethiopians that have to be addressed. The elites of both countries have a big role to play in this regard. Professor Tesfatsion emphasized that if the peoples of both countries are satisfied with the process of the confederation, they can in the future voluntarily decide in favor of a closer relationship including federation. Following that, Professor Daniel Kendie’s presentation focused on the role played by Egypt and other Arab-nations for the secession of Eritrea. He favors not only reinstating the Federal system to Eritrea but also to implement it in other Ethiopia’s sub-regions. In addition, he argued that a confederation allows two countries to sit side by side and is too weak to deal with major issues. Therefore, he stressed that a strong central government is a requirement. His vision of the federal structure also calls for the inclusion of Djibouti, Somalia, and perhaps Sudan. The discussion was really very interesting and a milestone that brought both Ethiopians and Eritreans under one roof for discussions. On the other hand, both lecturers admitted that this vision may be supported by neither the current Eritrean nor Ethiopian governments. A democratic government is a prerequisite for its possible implementation. Therefore, one has to think beyond the era of the present regimes. Professor Daniel also told participants that a meeting between Eritrean and Ethiopian intellectuals will be held in the coming days. It includes 15 participants on each side of the isle and he promised to inform us about its outcome. And finally, on the strength of Professor Danel’s recommendations, 3-people on each side were selected to facilitate at least social interactions between the two communities here in San Jose. It’s actually is the first of its kind since the 1998 major conflict between the two countries or even after the separations for that matter. In sponsoring this discussion forum, we—the event organizes—strongly believe that we’ve brought this crucial issue to the forefront. At the same time, we also know that it’s highly controversial. But taking a step towards peace and reconciliation as well as developing vision is a historical obligation. Let other people take it from here. Forum organizers in San Jose, California

Email sent to VOA Tigringa producer regarding the SJ town hall meeting on the Ethio-Eritria issue This email was suppose to be delivered to VOA Tigringa program. Unfortunately, for reason unknown my emails to them failed so many times in many instances. After I experienced such bouncing emails from VOA using the right address; I used to send my commentaries through the producer’s personal email address. Now, even that seemed to failed. I tried every option to send my commentaries regarding their guests Ato Yako from Eritrean community and Ato Awash from Ethiopian community (though he is ardent supporter of Meles Zenawi) invited to explaining the Ethiopian and Eritrean public discussion forum on the new Ethio-Eritrean issue. As I said it above due to unknown reason my mail kept refused from the VOA webmaster. What ever the reason, till we find out if there is any insider job or not, I will now post my comment in the hope VOA Tigringa producers will see it and air it to their audience via VOA. I ma also surprised how Tigringa VOA producer managed to get TPLF supporter/government supporter as guest to explain about the event in San Jose. It is fishy to say the least! Here is the Tigringa version of my commentary.ሰላም ቪኦኤ ክፍሊ ትግርኛነዋሕ ርኢቶ ስለዝኾነት ሕዝባዊ አድላይነታ ገምጊምኩም ንዉሕ ዝበለ ጊዜ ሂብኩም ቦታ ከም’ትህቡዋ ተስፋ እገብር።ኣብ ዝሓለፈ መደብኩም ብዛዕባ ህዘቢ ኤርትራን ኢትዮጵያን ክንየዉ ዝጥምት ሰላማዊ ፍታሕ ዘምጽእ መንገዲ ንምፍታሽ አብ ሳንሆዘ ካሊፎርኒያ ብፈረንጂ አቋጻጽራ ማርች 15/2009 ኤርትራዉያንን ኢትዮጵያዉያንን ዘሳተፈ ብኢትዮጵያዊን ኤርትራዊን ዶ/ር ተስፋጽየን መድሃንየን ፣ዶ/ር ዳኒኤል ክንዴን ዝተጸወዐ ህዝባዊ ዋዕላ ከመይ ከምዝተኻየደ ንከብራህሩሁልኩም ክልተ አጋይሽ ካብ ኤርትራ “አቶ ያዕቆብ” ካብ ኢትዮጵያ ድማ “አቶ አዋሽ” ዓዲምኩም ነይርኩም።አቶ አዋሽ ማሓዛይን ዘመደይን እንተኾነ’ዉን ነቲ ናይ ክልቲኡ ህዝቢታት ጸገም ተጠያቓይ ዝኾነ “መንግስቲ ወያነ” ደጋፋይ ከም ሙዃኑ መጠን ካብኡ ዝሰማዕኩዎ አዎንታዊ አዛራርባ ግና ፍሉይ ኮይኑ ስለዝረኸብኩዎ ከመስግኖ እፈቱ። ግናኸ ፤ ነቶም ብቅንዕኛ ተሲኦም ነዚ አኼባ እዚ ሱሙር ንክኸዉን ዝጻዓሩ ኢትዮጵያዉን “ሞንጎኛ” አይነበሩን ብምባል ክኸሶም ምፍታኑ ቅንዕኛ ዝጎዶሎን “መንግሰታዊ ድጋፉ” ንምድጓሕ ዝገበሮ ስለዝመስል ክእርማ ይሓቶ። እቶም አዳለዉቲ ካብ ሳዓብቲ ወያኔ ኮነ ካብ ካልኦት ባእታታት ብማዕረ ሓሳባቶም ክህቡ ገይሮም እዮም። ንአባላት ወየንቲ ሓሳባቶም ንክህቡ ምግባሮም ዘመስግኖም እምበር ብወገንተኝነት ከኽስሶም ኣይግባእን።ምሳኣ ግና ከምኡ ዝአመሰሉ ብጾቱን ካልኦትን ንሓዋሩ ነቲ ናይ ክልቲኤን ህዝቢታት ጸገም ዘጋድዱ ባእታት/መንግስቲ ወያኔ ምድጋፎም ድማ ደዉ ከምዘብሉዎ ተስፋ እገብር። ሕዚ ናብ ሓዉ ያዕቆብ እንትንአቱ ድማ ፣- ያዕቆብ ካብ ቀደሙ ቁኑዕ ሙዃኑ ብቐረባ ስለዝፈልጦን ካብቶም ኢትዮጵያዉን ወኪልና ዝተመረጽና ሓደ አነን ካብቶም ኤርትራ ወኪሎም ዝተመርጹ ሓደ ያዕቆብ ስለዝኾንና ንሓዋሩ ሓበራዊ ምርድዳእን ሓለፍነትን ከምዝጽበየና እፈልጥ።በዚ’ዉን ከመስግኖ እፈቱ። እንተኾነ ግና ካብ አዛራርባኡ ዘይጠዓመትኒ ረዛን ቃላት ብምጥቃሙ ፣ሓደ ነገር ክብል እደሊ። ደ/ር ዳኒኤል ክንዴ ንፍተሕ ኤርትራ ኮነ ንኻልኦት ሐጋራት ኮነፈደረሽን ዘይኮነስ ብፌደረሽን እንተተማሓደራ እየን እቲ ዝድለ ሰላምን ምዕብልናን ክመጽ ዝኽእል እምበር፣- “ኮንፌደራል ምምሕዳር”- አመና (ብጣዕሚ) ዱኹም ስለዝኾነ “ንቀጠፍቲን - ንጸሊም ዕዳጋን ከምኡዉን ዉግእ ንከይ ደግስ’ዉን ዝካላኸለሉ *ታኮ* ስለዘይብሉ” -ንቶም ዝተጠቕሱ “በሪ ዝኸፍት” ስለዝኾነ “ሰላምን ምዕብልናን” ከምጽእ አይኽእልን ኢሉ ዳንኤል ንዝሃቦ መርገጽ *-ያዕቆብ “ሓላፍነት ዝጎዶሎ” እንትብል ብረዚን ቃል ምህያሱ አግባብነት ዘይብሉ ሙዃኑ ንሰማዕቲ ክገልጽ እፈቱ። ነክልቲኡ ህዝቢ ብፌደረሽን ምህዋስ’ኮ ህዝቢ ዘዳሚ ምምሕዳር ማለት አይኮነን። ደ/ር ተስፋጽየን እዉን እኮ “ምስቲ ዘሎ ቁሱል ሕልና” ጊዚኡ አይመስለንን ግና ክልቲኦም ህዘቢታት “ዱሉዋት” ኢና ኢሎም “ይሕሸና” “ምድምማይ በዚሑ” ኢሎም እንተዳኣ “ፈዴረሽን መሪጾም” እንኳይዶ ፌደረሽን “ሓደ” እንተኾኑ ዉን *አሰና* ዝቕበሎ ነገር እዩ! ዝብል እዩ ተስፋጽየን ዝተሳማማዓሉ። ፌደረሽን እኮ ናይ ቅድምሕጂ ናይ ተስፋጽየን ደዉታ እዩ ነይሩ። ግና ደዉቱኡ ናብ “ኮን ፌደራሽን” ዝቐየረሉ ምኽንያት በቶም ዝገልጽኩዎም “ህዝባዊ ሕሊና ዘይድሉዊነት” ዝተበገሰ እዩ። ዳኒኤል ዝበሎ ዘሎ ግና፣ ኮንፌደራል ምምሕዳር ከም ፌደራል ምምሕዳር ጠዋት/ጥንኩር ስለዘይኮነ ንቐጠፍቲን ንጸሊም ዕዳጋን፣ ንካሊእ ወራር ዉግእ” ዘቃልዕ ሙዃኑ ብምግላጽ ምሳለታት ሂቡ እዩ። ንአብነት ብኮንፌደራል እንተዳኣ ተኣሳሲረን ኤርትራ መሊሳ “ሸቀጥ ቡን” ብጉሁድን ብጸሊም ዕዳጋን እንዳገፈፈት መበል “ራብዓይ” መፍረይቲ ቡን ኮይና ኣብ ዓለም ንክትምዝገብ ንጸሊም ዕዳጋ መንገዲ ምኽፋት እዩ። እንትብል ገሊጹዎ እዩ። እዚ ድማ “ሓለፍነት ዝስመዖ” እምበር “ሓላፍነት ዝጎዶሎ” አባሃህላ አይኮነን። ናይ ዳኒኤል አባሃህላ ኮን-ፌደራል ምምሕዳር “ፖለቲካዊን ምምሕዳራዊን ምትእስሳር” ክህሉ አለዎ እዩ። ናይ ሓባር ባንክ፣ ሃበራዊ ወታሃደር (common defense)፣ ካብ ክልቲኤን ሃገራት ዝተመዘዙ መንግሰታዊ ስራሓቲ ዘካይዱ ሽማግለታት/ኮሚቲ፤(ፍደራል አሰምብሊ) ፣ ናይ ሓባር ማሪታይን ንገዲ ወዘተ… እዚ ምስ ዘይህሉ ግና “ንዉግእን ንጸሊም ዕዳጋን” መሊሱ መንገዲ ዝኸፍት እዩ፣ ዝብል እዩ ናይ ዳኒኤል ናይ “ፈደረሽን” ደዉታ።ኩሉ ንክትግበር ግና 1- መራሕቲ ብዝፈጠሩዎ ንሕንሕ ዝተለከመ ሕዝቢ አብ ሞንጉኡ ዝተርአየ ጽልኢ አወጊዱ ሕዉነትን ምዝርራብን ክጅምር ምግባር፤ 2- 2- ክልቲኦም መንግስቲ ወያነን መንግስቲ ሻዕቢያን አብ ስልጣን ክሳብ ዘለዉ ጊዜ ሰላም ክህሉ ከምዘይክእል ፈሊጥና ንክልቲኦም ዝኾነ ይኹን ሞራላዊን ንዋታዊን ደገፍ ዘይምሃብ፣ 3- 3- ናይ ወጻእ ባእታታት ኢድ ኣእታዊነት ከቢድ ጽልዋ ስለዘለዎ - ነቲ ባይታ ከየታዓናቕፉዎ ብርቱዕ ጠመተ ምግባር። እዚኦም ክምርመሩ ዝግባኦም ነጥቢታት እዮም፡ ኢሎም ክልቲኦም ሙሁራት ዝተሳማሙዑሎም ነጥብታት እዮም። ጌታቸዉ ረዳ ሳንሆዘ ካሊፎርኒያ ኤዲተር “ኢትዮጵያን ሰማይ”/-/

Saturday, March 21, 2009

ያገር ታሪክ ተጣራሪ፣ የክሕደት በቀል አርማ ይዞ “መሪ!”

ያገር ታሪክ ተጣራሪ፣ የክሕደት በቀል አርማ ይዞ “መሪ!”
ጌታቸዉ ረዳ
ቀደም ብየ በተለያዩ ጽሑፎቼ እንደገለጽኩት፣ ለአንድ አገር ዉርደት ወይንም ኩራት በግለሰብ ወይንም በቡድን ተደራጅተዉ ከፍተኛ ያገሪቱ መንበረ ስልጣን ተቆጣጥረዉ ላገሪቱ ህልዉና በሚነድፉት መመሪያ ምክንያት ነዉ። የአገሪቱ ህልዉናም ሆነ ከበሬታ የሚወስነዉ ግለሰብ መሪዉ ወይንም ቡዱኖቹ ላገሪቱ ባላቸዉ “የፍቅር መጠን” ነዉ። “ፍቕሪ ዑዉር” ይሉታል በትግርኛ። “ፍቅር ኡዉር ነዉ” እንደሚለዉ አማርኛዉ። ፍቅር ኡዉር ሆኖ ለምያፈቅሩት ሰዉ፣ለሚያፈቅሯት አገር የተቻለህን ፣የጠየቀችዉን እንድታደርግ የሚያስገድድ ስሜት ቢሆንም፡በዛዉ አንጻር “ዑወር ጽልኢ”/ “ኡዉር ጥላቻ” ም በተቃራኒ ሰዉን አገርን ያጠፋል።መለስ ዜናዊ ከነድርጅቱ ተከታዮች እየተከተሉት ያለዉን ጎዳና ለኢትዮጵያና ሰንደቃላማዋ ያላቸዉ ክብር ተጻራሪ የሆነ “ኡዉር-ጥላቻ” ነዉ። ከላይ የምትመለከቱት ፎቶግራፍ መለስ ዜናዊ ነዉ። ከጠረፔዛዉ በስተጀርባ ከጎን በኩል የሚታየዉ ባንዴራ “የተሓህት” የመለስ ዜናዊ ፓርቲ/ድርጅት ባንዴራ ነዉ። ፎቶግራፉ የተነሳዉ ወያኔ የተባለዉ “የባንዳ ድርጅት” ጸረ ኢትዮጵያ ሆኖ በትግራይ ክፍለሃገር ተመስርቶ “ለኤርትራ የቆመበት” 33ኛዉን ዓመተ-ልደቱን መለስ ዜናዊ በማክበር “ገባር ሽረ” (የሽሬ ጭሰኛ) በተባለዉ ሆቴል ዉስጥ የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ኗሪዎችን በመሰብሰብ በወያነ ትግራይ ድርጅት “ሽፋን” ስለ ኢትዮጵያ መንበርከክ እና ከኢትዮጵያ “ኮሎኒያሊስቶች”-ኤርትራን ነጻ የማዉጣት ገድል ባሸናፊነት መዉጣቱን ንግግር ሲያደርግ ነዉ።በዚህ ስብሰባ ላይ በክብር ከባንዳዉ ጎን የተቀመጠዉ ባንዴራ የኢትዮጵያ ብሔራዉ ሰንደቃላማ ሳይሆን ከላይ እንደገለጽኩት በአፍዓበት እና ምጽዋ የመጨረሻ የሞት የሸረት ገድል ሲደረግ ፣ምንም እንኳ በአምባገነኑ መንግስቱ ሃይለማርያም ቢመሩም ኢትዮያዉያን ወታደሮች የአባቶቻችን የአሉላን የዮሐንስን የአምደጽዮን የቴዎድሮስ የካሌብ ሕዝብና መሬት ለዉጭ ቅጥረኞች አናስነጥቅም “ኢትዮጵያ ወደብ አልባ አትሆንም” በማለት ደማቸዉን እንደ ጎርፍ ሲፈስስ በነበረበት በዛ አሰቀያሚ የመገዳደል ጦርነት ወያኔዎችና ሻዕቢያዎች በአሜሪካኖች ሳተላይት ፈጣን መረጃ እየተመሩ መጽፅዋን ሲይዙ ፣በኢትዮጵያዉያን ሬሳ ላይ ሲዉለበለብ የነበረዉ የጠላት ባንዴራ ይህ መለስ ዜናዊ ከጎኑ በክብር ተቀምጦ የሚታየዉ “የትሓህት” ባንዴራ ነበር። ይህ አስቀያሚ ትምክህት ስትመለከቱ አንድ የአገር መሪ ነኝ ከሚል ለይስሙላ ተብሎ እንኳ በሰማያዊ ቀለም ያጨማላቃትን ብሄራዊ ባንዴራ ከጎኑ ስታጡ እዉን ይህ ኩታራ ኢትዮጵያዊ ነዉ ወይስ “ሙሶሎኒ” እንደምትሉ ይገባኛል። በአንጋፋዉ ጋዜጠኛ ፀጋየ ገብረመድህን አርአያ የብዕር ጥያቄ ብንጠይቅ “አቶ መለስ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተርነት እንወቃቸዉ ወይስ የትግራይ ጠቅላይ ገዥ አድርገን?” ይህ በአንቱታ የሚጠራዉ፣ የአንቱታ ትርጉም የማያዉቀዉ፣ያገር ክብር ትርጉም ከቶ ያልተማረ “የዓድዋዉ ኩታራ” ኢትዮጵያን የምታከል ታላቅ አገር እየገዛ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሰንደቅ በድርጅት አርማ ለዉጦ ሲኮፈስ “ይህ የትግራይ ልጅ ተወልጄነት፣ ያንጋፋነትና የገዢነት ዕብጠት” ሄዶ ሄዶ አንድ ቦታ ላይ ሲደርስ እንደ ባሉን መተንፈሱ ባይቀርም፣ አስከሚተነፍስ ድረስ ግን የኢትዮጵያን ልጆት አንጀት ማሳረሩ አልቀረም። እያንዳንዳችሁ አገር ወዳዶች እና የ አርበኞች ልጆች ያገራችሁን ሰንደቅ በኩታረዎች ሲናቅ እና ሲወገድ የሚሰማችሁ ንዴትና የዉስጥ ስቃይ ምንኛ አሳማሚ መሆኑን ስለምታዉቁት የቁጭቱ የስቃይ መጠን ለባለቤቶቹ ላናንተ በመግለጽ ጊዜአችሁን አላባክንም። ዛሬ የሚታየዉ የወርቅ ፍልቃቂዎቹ ጉራና ትምክሕቱ፣ ተቆልሎ ሞልቶ “የማን አህሎን” ዕብጠቱ የሰማዩን ጣራ እየነካ ያለዉ ግብር፣ አስቀድሞ ከበራሃ ትግላቸዉ የደም ጥራቱ፣ የአጥንት ንጣቱ፣ ያዉራጃዊነት ወርቃማ ጉልላት ልዩነቱና የበላይነቱ በኢትዮጵያ ትግሬዎችና- በወያኔ ትግሬዎች” የታየዉ ፍጥጫ ወያነ ትግራይ “በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ” ላይ የወያኔ ባንዴራ” የበላይነት ለመስጠት የተደረገዉ ትግል ነበር። ልዩነታችን በጣም ግልጽና የማያሻማ ሲሆን “የወርቅ ፍልቃቂዎዩቹ እና የአጥንተ ንፁሆቹ”-ዓላማ “ብሔራዊ መንደርተኛ ስሜት ያጀበዉ ስልጣንን ማራመድ”-ሲሆን በኛዉ “በኢትዮጵያ ትግሬዎች”-በኩል የነበረዉና ያለዉ አቋም “ኢትዮጵያዊነትን/ሃገራዊነትን እና ኢትዮ አዊ ሰንደቃላማን” ማስቀደም ነበር።
ይህ ሆኖም ፣ድብልቅ የሌላቸዉ “የወረቅ ፍልቃቂዎቹ”፣ አስከ’ዚህ ድረስ ያደረሰዉ መንገዳቸዉ በታሪክ ማሕደር ሲፈተሽ “የተጓዙት ጉዞ”-“የኢትዮጵያ ትግሬዎችን”በማግለል፤ሰም በማጥፋት፤ ትግሬዎች አይደላችሁም በማለት፣ በመግደል፣በማሰቃየት፣በመሰወርና በመደብደብ በኢሰብአዊ ጭካኔ የታጀበ በሰዉ ልጆች (በዜጎች) ህይወት ላይ ወንጀል የፈጸሙበት ጉዞ ነበር። በወንጀል የታጀበ የጠረና የደም ጉዞ!
ኢትዮጵያንና ሰንደቃላማዋን ያከበሩና የድረጅት ባንዴራ አናመልክም ባሉት “በኢትዮጵያ ትግሬዎች” ላይ ባንዳዎቹ (ዩወያኔ ትግሬዎቹ) ያደረሱባቸዉ የግፍ ግፍ የኢድሕ/አዲዩ ታጋይ የነበረዉ የ “አሞራ” መጽሃፍ ደራሲ አቶ ግደይ ባሕሪሹም ሁኔታዉን ላላያችሁና ላልሰማችሁ አዳዲስ ባለጀሮዎች ብትኖሩ እንደሚከተለዉ ያቀርብላችሗል።
\<<…የሻዕቢያ ቅጥረኛ ወያኔም ትግራይ ዉስጥ በገጠሩ ኢትዮጵያዊነቱን ያልካደና እምነታቸዉን ያላመነዉን ገበሬ የከተማ ወዝአደር፣ምሁር “ኮራኹር አምሓሩ” “ሽዋዉያን ተጋሩ” (የአማራ ቡቹሎች ፤ሽዋዉያን ትግሬዎች) እያለች፣ የኢድሕ ታጋይ ቤተሰብ ዘመድና አዝማድ የተባሉትን ሁሉ በጠቅላላ በረና ላሙን፣በግና ፍየሉን፣ አሀያና በቅሎዉን ዶሮና የጎተራ እህሉን፣ማርና ቅቤዉን እየወረሰች ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር… >> ይላል። ከቅርብ አዋቂዉ፣ከወያኔ ትግሬዎች ጋር እጅ ለእጅ ሳንጃ ባፈሙዝ ተሞሻልቆ ኢትዮጵያዊነቱንና የሃገሩን ሰንደቃላማ ላለመዋረድ የታገለዉ ግደይ ባሕሪሹም ምስክርነት የምንረዳዉ ነገር ቢኖረ “ከመጀመሪያ እካሁን በኢትዮጵያዊነት ላይ ያነጣጠረ ነዉ።…”ኢትዮጵያዊ ስያሜ”-የትግራይም ተወላጅ እንዳይጠራበት ለረዥም ዘመን ከነበራቸዉ ስሜት በመነሳት … “ስለትግራይ ሕዝብ ወርቅነት ወዘተ..”ይሆናል አቶ ግደይ ባሕሪሹም “አሞራ”በተባለዉ መጽሐፋቸዉ “ የትግሬና በ አማራ መካከል የከረረ ጠብ ተፈጥሮ የትግራይ ህዝብ ከመሃል አገር የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እየተጋጨና እየተቧጨቀ እንዲኖር ግፋ በል…” የሚሉ የዚህን ጥላቻ አስፋፊ ስድስት ዋነኛ ሰዎችን ይጠቅሳል። የዛሬዉ ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ግን ከነዚህ ተራ ዉስጥ ያሉ ሲሆኑ፣ ግዴይ ባሕሪሹም በህወሓት (TPLF) ዉስጥ በኤርትራዊነት ከተፈረጁትም መካካል አንደኛዉ ያደርጋቸዋል።”) ጸጋየ ገብረመድህን አርአያ (ክቡር ሆይ! ዝንጀሮዉ እያሳቀብን ነዉ…ይበልጥ በእርስዎ! ጦቢያ መጽሄት ሓምሌ 1989)
ኢትዮጵያና ኢትዮጵአዊነትን እየገደሉ ለኤርትራ ሲሉ የሞቱትና የቆሰሉ ለስላሳ ልብ ያሳዩት የትሓት ታጋዮችና መሪዎች ጭካኔአቸዉ በትግራይ ገበሬ ብቻ ሳይወሰን በድያቆናትና በቀሳዉስቱም ጭምር “የባዕድ ብትር”ሰንዝሮባቸዋል።ብርሃነ ገብረህይወት የተባለዉ የወያነ ሰለባ ፣ኢትዮጵያዊነታችን አንክድም ባሉ የትግራይ ድያቆናትና ቀሳዉስት የነበረዉ ግንኙነት እንዲህ ይገልጸዋል፦ “… ቅስና እና ድቁና የተቀበሉ ከ50 በላይ የሆኑ ሰዎች ታስረዉ ነበር። እነሱም ከእስራትና ከቅጣት በሗላ መታወቂያቸዉ ተቀምተዋል። ከዚያ እዚያዉ ቆይተን በ1981 ዓ/ም በግድ ወደ ግንባር ዝመቱ አሉን። …እኛ “አንታገልም፤እናንተ ታገሉ፡ እኛ ድሆች ነን፡ ገና ዳቦ አንኳን አልጠገብንም”ስንላቸዉ፡”ማን አጥንቱን ከስክሶ ሊያኖርህ ፈለግክ?” በማለት በተለይም “ቢሄን” የተባለ ታጋይ አፈር በእጁ ከመሬት ቆንጥሮ በማፈስ ወዳፍንጫችን አስጠግቶ እንድናሸት አስፈራራን። በአገራችን መኖር ካልቻልን ተሰድደን እንሄዳለን፡ ይለፍ ብቻ ስጡን ስንል ስትፈልጉ በሰማይ ሂዱ እንጂ አይሰጣችሁም፡ እያሉ ያፌዙብን ነበር።“ታዲያ የት እንድረስ?” ስንላቸዉ “የራሳችሁ ጉዳይ!ከፈለጋችሁ አገራችሁን ነፃ አዉጡ። ነፃ አናወጣም የምትሉ ከሆነ ግን የዚህችን “ምድር በረት” አትረግጡም። አሉን። “ከማን ነዉ ነፃ የምናወጣት?” ደርግም ኢትዮጵያዊ ነዉ እናንተም ኢትዮጵያዊያን ናችሁ።” ስንል “ከበስተጀርባችሁ የሆነ ነገር አላችሁ!” በማለት ማሰር እና መቅጣት ጀመሩን …(1500 እንሆናለን)።ወላጆቻችን ታሰሩ። የእርሻ ማሳዎቻችንም ተወረሰ። ቀንደኛ አድመኞች ናችሁ በተባልን በተወሰንን ሰዎች ላይ ከባድ ቅጣት ተፈጸመብን። ከ6 ወር አስከ ዓመት በእስራትና በግርፋት ተቀጥተናል። ክንዶቹ ለረዥም ጊዜ በቀጭን ጅማት ነገር በመታሰራቸዉ ምክንያት ጣቶቹ ደም አስከ ማንጠባጠብ የደረሰ ጓደኛችንም ነበረ። በግርፋት አንድ እጁ እና አንድ እግሩ ሽባ የሆነ ጓደኛየ ሃለቃ ሓዲሽ የባላል። ቢዚያን ወቅት ‘ሙሹሮችና ካህናት’ ሳይቀሩ ‘በህማማት ጊዜ ከቤተክርስትያን’ ተወስደዉ ከሽማግሌዎች በቀር ሁሉም ታፍሶ ተወሰደ። ለመሸሽ የሞከረዉን እንደጅግራ እያሯሯጡ በጥይት ያሳድዱት ነበር። ይህ ሁሉ የተፈጸመዉ የካቲት ወር 1981 ዓ.ም ጀምሮ ማለት ነዉ።ትግራይ ነፃ ከወጣች በሗላ ማለት ነዉ:: ከዚያ… ሰዉ እንደ አዉሬ በአካባቢዉ እየተበተነ በአካባቢዉ በቀን ሰዉ የሚባል አይታይም ነበር። እነሱም እንደ ጅግራ እያደኑ ይዉላሉ፤መሬታችንም ለታጋይ ቤተስብ ታድሎ የምንቀምሰዉ የምንልሰዉ አልነበረም።ከቀበሌ ወደ ቀበሌ የሚያስተላልፉ የነሱ ካድሬዎች ካዩን ጥይት ይተኩሱብናል፤ የተኮሱብን ጥይት አልመታንም እንጂ ቁጥር የለዉም። ከዚያ በሗላ እየተንከራተትንና እየተራብን ቆይተን ህዳር 21/1983 ዓ.ም ገረዳ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ለአቶ በርሄ እህል ስንሸከምላቸዉ ዉለን፤ቤት ገብተን ገበታዉ ቀርቦ እህል ልንበላ ስንል ቤቱ ተከበበ። የማይታወቁ ታጣቂዎች ናቸዉ። ከተሰበሰበዉ ሰዉ እኔን ጠሩኝና ዉጣ አሉኝ። መጀመሪያ እህል ይብላ እና ዉሰዱት ብለዉ የቤቱ ባለቤት ቢጠይቁም “አስቸኳይ መልዕክት ስላለን ነዉ፤አሁን ይመለሳል” ብለዉ ወሰዱኝ።ሌሎችም ከያቅጣቻዉ ተሰበሰቡ።ወደ 5 እንሆናለን። ሁላችንም በስብሰባ ላይ የምንከራከራቸዉ ነበርን። “እነዚህ ካልጠፉ ወጣቱ አይታገልም፤በታኞች ናቸዉ፤ከደርግ ለይተን አናያቸዉም” በማለት ከዚያ በፊት እንዳጠፏቸዉ ወጣቶች እኛንም ለማጥፋት ተዘጋችተዉ እየወሰዱን ሳለ፤ እርስ በርሳችን እንነጋገር ነበር። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ይሆናል።…ጫካ ነዉ፤ እኛ አናዉቀዉም። ኢሳ የሚባል በረሃ ነዉ። ምን ይሻላል? ለመሞት ለመሞት እዚሁ እንሙት እየተባባልን እንደገና ጉዞ ጀመርን። አልፎ አልፎ ነዉ እንጂ እኛን ባንድ ላይ አይወስዱንም ነበር። አንድ እዚህ፤ አንድ ደግሞ ራቅ አድርገዉ ሊወስዱን ከፊት ያለዉን ገፍቼ ሸሸሁ። ቁጥር የሌለዉ ጥይት እላየ ላይ ዘነበ። ፀጉሬ ላይ ትንሽ ነካኝ እንጂ አልመታኝም። አምልጬ ሕግ ያለ መስሎኝ ወደ ዋናዉ አለቃ ሄጀ “የማይታወቁ ታጣቂዎች ሌሊት መጥተዉ በደል አደረሱብኝ፤ በነዚህ ሰዎች ላይ ክትትል ይደረግልኝ፤ከየት እንደመጡ ማን እንደላካቸዉ ይጣራልኝ”ብየ አቤቱታ ሳቀርብ፡ “እኛ እናጣራዋለን፤ እንከታተላቸዋለን” የሚል መልስ ሰጡኝ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ ጥር 23 ቀን 1981 ዓ.ም ሥራ አድሬ ከንጋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ወደቤቴ ስሄድ……..(ለመኖርያ ቤት ፤ቤት በደቦ ስንሰራ) ደክሞኝ እዚያ አድሬ ነበር። አባቴ ሞቷል..እናቴ አለች፤ የእናቴ ትንሽ መሬት ነበረችን፡ ቤቴ እንደደረስኩ በረቱን ከፍቼ ለበሬዎቹ ድርቆሽ ልሰጣቸዉ ስል….የ.ማላዉቃቸዉ ሰወች ብትንትን ብለዉ ተኝተዉ አገኘሗቸዉ። ቤቱ ተከቦ ነዉ ያደረዉ። እናንተ እነማን ናችሁ? ስላቸዉ አንዱ እያናገረኝ ሌላኛዉ በሰባት ጥይት መታኝ። በሆዴ እና በአንጀቴ ላይ ደሙ እየተንዠቀዠቀ ሲፈስ እናቴ እንዳታይና እንዳትጮህ ውስጥ ግቢ አሏት። ከዚያ በሗላ “እግሬና እጄን አንጠልጥለዉ ጎትተዉ ጫካ ዉስጥ ጣሉኝ”። አንጀቴ ተበጥሷል። እንጀቴ ይታያል፡ቅጠላቅጠል አልብሰዉኝ ተሰወሩ…” ይህ ከላይ ያነበባችሁት የተለያዩ ምስክርነቶች ፣ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተደረጉ ግፎች ናቸዉ። ዛሬ መለስ ዜናዊ ያ ሁሉ ግፍ “በኢትዮጵያዉያን ትግሬዎች” ላይ ያለ ምንም ተጠያቂነት ሲፈጽም እና ስያስፈጽም ቆይቶ፣ የህዝብ ሥልጣን ከነጠቀ በሗላም በጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ያገሪቷን ሰንደቃላማ ከማክበር ይልቅ ከጎኑ እንዳትታይ በማስወገድ ወይንም አርቆ በማስቀመጥ በምትኳ የራሱን የድርጅቱን ባንዴራ እንደ ብሔራዊ ሰንደቃላማ በመቁጠር እጎኑ በማኖር ብበቱ ስር ታቅፎ በፎቶግራፍ ቀራጮች አማካይነት ሆን ተብሎ የድርጅቱ ባንዴራ በታሪካዊ የፎቶግራፍ ማሕደሮች እንዲቀረጽ በማድረግ የ“መጪዋ” “ሪፑብሊካዊት ዓባይ ትግራይ” /የታላቁዋ ሪፑብሊካዊት ትግራይን ብሄራዊ ሰንደቃላማ እንደምትሆን እና ወያኔ ወልዳ ወያኔ ያሳደገቻቸዉ “ሰገናት/ብርኪ ሰገናት” የተባሉ “ታዳጊ ህጻናትና ወጣቶች” እንዲሰግዱላትና “ኢትዮጵያዉያን የትግራይ አርበኞች”አባቶቻችንና እናቶቻችን የተዉልንን የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ከእነዚህ ታዳጊ ህጻናት ሕሊና ዉስጥ እንድትፋቅ እየተደረገ ያለዉ “ተሓህት ዉስጥ የተሰገሰጉ የባንዳዎች” ሴራ መሆኑን የትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያዉያን በአጽንኦት እንድትረዱት ሳሳስብ፤
በተጨማሪም ካሁን በፊት ታጋያይ አሉላ ካሳ የተባለ የወየነ ትግራይ ታጋይ “ክርቢት” ተብሎ በሚጠራዉ የወያኔ መቺ ሃይል ተምድቦ እየሰራ በነበረበት ጊዜ፤ ጥበቃ በላላባቸዉ ከተሞች ቡዱኔ ተሸሽጎ በድብቅ ወደየ ከተሞቹ ዘልቆ በመግባት፤ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማን በማዉረድ የወያኔን ባንዲራ ሰቅለዉ ይሰወሩ እንደነበር ከድምጺ ወያነ ትግራይ ራዲዮ ጋር ያደረገዉ ቃለ መጠይቅ አቅርቤላችሁ እንደነበረ ስታገናዝቡት፤ መለስ ዜናዊ ዛሬ ከጎኑ ያስቀመጠዉ ባንዴራዉ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ያለዉን ንቀትና ለድርጅቱ ባንዴራ ያለዉ ፍቅርና አክብሮት ምን እንደሆነ እላይ ካቀረብኩላችሁ ፎቶግራፉ መረዳት እንደምትችሉ ተስፋ አለኝ።
ጌታቸዉ ረዳ መጋቢት 2002 ዓ.ም (March 19, 20092009) www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Monday, March 16, 2009

የ“ህወሓቶች” አርአያ ደጃዝማች ገበረስላሴ

የ“ህወሓቶች” አርአያ ደጃዝማች ገበረስላሴ ከታሪክ ሠነድ ጌታቸዉ ረዳ
ኣብዛኛዉን ጊዜ ኢትዮጵያን ያጠቃት ሃይል “የዉጭዉ ወራሪ” ሳይሆን “ከዉስጥ ሆኖ ለጠላት ያደረ፤ እንደ መለስ ዜናዊ ዓይነቱ የቅኝ አዙር ገዢዎች አጎብዳጅ፤ ለዓለማዊ ስልጣኑ ያደረ ዜጋ ነዉ”። በፈረንጆች እና በዓረቦች የሚንቀሳቀሰዉ “ህወሓት” የተባለዉ የባንዳዎችና የዘመናችን የመኳንንት ስብስብ ኢትዮጵያን በማፍረስ ላይ ግምባር ቀደም ሚና የሚጫወተዉ ለብዙ ኣመታት ህወሓት ከተመሰረተበት ጀምሮ በበላይነት እየመራ ያለዉ “የዓድዋዉ ቡድን” እንደ ሆነዉ ሁሉ፤ በጣሊያን ጊዜም በባንዳነት ጣሊያንን ያገለገሉ ምርጥ የዓድዋ ፤የአክሱም እና የእንደርታ መኳንንቶች እንደነበሩበት ታሪክ ያስረዳል። ለዛሬ ከታሪክ ሠነድ መርጬ የማቀርብላችሁ ከትግራይ መኳንንት አንዱ ደጃዝማች ገብረሥላሴ ይሆናሉ።በወቅቱ ኢትዮጵያን ለመዉረር ያኮበኮበዉ አስመራ ይኖር ለነበረዉ ለፋሽስቶቹ ወኪል “ለኮማ ንዳቶረ ማርቲኒ” የጻፉት ደብዳቤ መጬዉ ትዉልድ እንዳይረሳቸዉና ዛሬ ያለነዉ ተቃዋሚ ክፍሎችም ባንዳዎች “በክፉ ቀን” ምን ያህል “ርቀት ተጉዘዉ አገራቸዉን ለግል ጥቅም መሸጥ እንደሚችሉ” ለማሳየት ነዉ። መለስ ዜናዊ ኤርትራን ሲያስገነጥል ከአስገንጣዮች እና ከተገንጣዮች ልቆ ያስሰማዉ የነበረዉ “ለሻዕቢያ/ለ ኤርትራ ፍቅር” ዉክልና ልብ ብላችሁ ብታጤኑት፤ በዛም ምክንያት ‘በብዙ ኢትዮጵያዉያን/ት አገር ወዳዶች ዘንድ ሁሉ እንደተጠላዉ ሁሉ። ደጃዝማች ገብረሥላሴም በደብዳቤአቸዉ የሚሉት ለጣሊያን ፍቅር የተነሳ “የኢትዮጵያ ሞኳንንት ሁሉ ለምን ጣሊያን ወደደ ብለዉ ሁሉም ጠሉኝ፡ ለማጥፋትም ተመኙኝ…” ይላሉ። ደብዳቤዉ እንዲህ ይነበባል። አንዳንድ ቦታዎች በቅንፍ የምታዩት በቅንፍ ከኔ የተጨመረ ቃላት ምን ለማለት አንደሆነ በግድፈት የተዉት ቃላት ወይንም በያኔዉ አነጋገር እና በዛሬዉ አባባል ለማሳየት ነዉ። “ይድረስ ተክቡር ወልዑል ወዳጄ ኮሚንዳቶራ ማርቲኒ። ጌታየ ሆይ አሁን በረሃ ለበረሃ ስዞር እርስዎ የኮሎኒያ መንግሥታ (መንግሥት) ሆኑ ሲሉ ብሰማ አዘኔ ቀለለኝ ተስፋየም እንደገና በረታ። እኔ ተዋጋት (ተዋግቼ) የደረሱበትና ፊትም ድል ማድረጌ ሗላም ድል ከመሆን የደረስኩበት ነገር በኢጣሊያ ፍቅር የተነሳ ነዉ። በኢጣሊያ ፍቅር የተነሳ ባይሆን ግን እርስዎ እንደሚያዉቁት ሹመቱና ማረጌ (ትልቅ) ነበረ። ከኢትዮጵያ ሁሉ መኳንንት በኔ የማይቀና አልነበረም። ሓላ ግን ለምን ኢጣሊያን ወደደ ብለዉ ሁሉም ጠሉኝ። ለማጥፋት ተመኙኝ። ኢጣሊያ የትሪፖሊን ጦርነት በጀመረች ጊዜ ራስ ስብሐት ባሻ ብዙቅ ሁሉ (ባሻ ብዙቅ እያሉ ያሉት ባንዳ ሁሉ ማለታቸዉ ነዉ) ወደ ትሪፖሊ ሄዷልና ይሂን (ይኼኔ) ጊዜ ኢጣሊያን እንዋጋና አገራችንን አስከ ምጽዋ ድረስ መልሰን እንያዝ ብሎ ላዲስ አበባ መንግሥት መከረ። ከዚህ ወዲያ ያበሻ መንግሥት ከራስ ስብሐትና ከደጃች ስዩም ጋራ ሁነህ ኢጣልያን በድንግት ገስግሰህ ዉጋዉና አገራችንን አስለቅቅ፡ እሄን ያደረክ እንደሆነ ኢጣልያ ይዞት የነበረዉን ሁሉ አገር ራስ አሰኝተን ለአንተ እንሰጥሃለን አሉኝ። እኔ ግን አይሆንም እንዋረዳለን ከኢጣልያ አንጣላ ደግሞም ምንም ተከፍሎ ጥቂት ወደ ትሪፖሊ ቢሄድ አሁን ያለዉ የጣሊያ ጦር እልቅ የለዉም ብየ አስፈርቸ (አስፈራርቼ) አስቀረሁ። በዚህ ነገር ሁሉ አቅማማሁ፡ ይልቁንም ራስ ስብሐትና ደጃች ስዩም ለኢጣሊያ አግዞ ነዉ ብለዉ አሳጡኝ። ጠላቴም ባዛ፡ ከዚህ ቀጥለዉ እኔ የጣሊያን ምክር ሰምቶ ሰራዊቱ ሁሉ ወዳገሩ አሰናብቶ ጥቂት ራሴን ሁኜ ወደ አዲስ አበባ እሄዳለሁ ስል ሰራዊቱን ማሰናበቱን አይተዉ አደጋ ጥለዉ ወጉኝ። ነገር ግን በፊት ድል አድርጌ የጣልያን ብርቱ ጠላት ራስ ስብሃትን ገደልሁ። ያስመራ መንግሥት ጥቂት አይዞህ ብሎኝ ቢሆን የጣልያን ጠላት ሁሉ አጠፋዉ ነበርሁ። ድል ታደረግሁ በሗላ ድል መሆኔ ግን እኔ ስለሷ ስዋጋ ኢጣልያ ዝም በማለቷ ነዉ። ኢጣልያ ዝም ስትል ሲያይ ጊዜ፤ለኔ ሊያግዝ ምሎ የነበረዉ ሁሉ የድፍን ትግሬ መኳንንት ፈርቶ ከዳኝ። አሁን አንዲህ በርሃብና በጥማት እየተቆላሁ በረሃ ለበረሃ እንከራተታለሁ። አንድ ነገር ብቻ ደስ ያለን ምሽቴና ሁለት ልዦቸ (ልጆቼ) ከጣልያ እጅ ሁነዉ በደግ ስለተቀመጡልኝ ነዉ አሁን የታመነ ብዙ ጦር አለኝ። ያገዛችሁኝ እንደሆነ እያደረ ይበዛል። ያላገዛችሁኝ እንደሆነ እያደረ ይጠፋል እንጂ አይበዛም። እርስዎ ትልቁ ወዳጄ ምንሰትር ሁነዉ በርግጥ እንዲያስቡልኝና እንዳያስጠቁን አዉቀዋለሁ። የሚቸግርዎ እንዳለ አዉቃለሁ። በርስዎ ሃይል በርስዎ አጋዥ ኢጣልያ አይዞህ ያለኝ እንደሆነ ድፍን ትግሬ ተጸለምት አስከ ስቆጣ አስከ አሸንጌ ያለ ሁሉ መኳንንት እንዲያግዘኝ የታወቀ ነዉ። ነገር ግን መቼም በጥቅምትና በህዳር ጠርነት ላይቀራችሁ ነዉና እሄን ጌዜ ጀምራችሁ አግዙኝ ብየ ብልከ ከሮማ ፈቃድ አልመጣልኝም ብለዉ ምላሽ መለስዩልኝ። አሁንም ጌታየ ወዳጅ ተስፋየ ሁሉ ከርስዎ ላይ ነዉና አደራ አይዞህ ብለዉ ተሎ ይላኩልኝ። መድሃኔ ዓለም ጤናና እድሜ ይስጥልኝ ብየ እጅ እነሳለሁ። ደጃዝማች ገብረስላሴ የጥንት ወዳጅዎ አሁንም የሚያምንዎ።”

Sunday, March 8, 2009

ጥላቻን ማስፋፋት ዓይነተኛ የወያኔ መመርያ ነዉ!

የወያነ ትግራይ ገበና ማሕደር ጥላቻን ማስፋፋት ዓይነተኛ የወያኔ መመርያ ነዉ! ጌታቸዉ ረዳ “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” ዘረኛነት በተደጋጋሚ የተነጋገርንበት ጉዳይ ነዉ። በቅርቡ ዛሬ ዛሬ ደግሞ በተቃዋሚነት ቆመናል የሚሉ የዓረና እና የጉንበት 7 ደጋፊዎች እና የብረቱካን ፓርቲ ደጋፊ አባላት ስለ ወያኔ የገበና መሕደር አንስተን በዘገብን ቁጥር “እጅ እጅ” ያላቸዉ ይመስላሉ። እነሱ ብቻም አይደሉም ጉዳዩን አንስተን በተከራከርንባቸዉ ወቅቶች፤ ብዙ የድርጅቱ አባላት እና አቁዋማቸዉ ነጥሮ ያልወጣ የድርጅቱ “ነበር” አባላት እና አዳዲስ አባላት አፍቃሬ-ወያኔ“የእርጎ ዝምቦች” ክርክራችንን ለማጣጣል ብዙ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች አካሂደዉብናል። በቅርቡም በዚህ “ዌብ ሎግ/በራሴ ዌብ ሎግ” እና በኢትዮፓትሪዮትስ . ካም” ሰሌዳ ዉስጥ ቀርቦ በነበረዉ “የወያኔ ትግሬዎች እና የዓድዋ ድል እይታ”ን በተመለከተ በግል “ኢሜይል” በመላክ “ወያኔ ጸረ አማራ ገዢዉ መደብ እንጂ ጸረ አማራ አልነበርም” ሲሉ “በዚህ ጉዳይ አንስተን ስንከራከር- እኔ ታጋይ እስከነበርኩበት ጊዜ ድረስ ጸረ አማራ ቅስቀሳ ወይንም ዘፈን አልሰማሁም” በማለት ወያኔያቸዉን የመከላከል በሽታ ከቶ ምንም ያልተዋቸዉ ሰዎች ዛሬም ስላሉ - እዉነት እና ንጋት እያደር ይጠራል እንደተባለዉ፣ ምንም ያህል ቢደበቁም ከታሪክ ተደብቆ ለረዥም ጊዜ ማላገጥ ስለማይቻል፣ በራሳችን ክርክር ከመሞገት ይልቅ “ድርጅቱን በግምባር ቀደም በመሰረተዉ በዶ/ር አረጋዊ በርሄ” ብዕር ማስረጃችንን በማቅረብ (ማሌሊት ዘላሊት) ወይንም “ከማገብት እስከ ህወሓት- ጠባብ ብሔረተኝነት ያመናመነዉ ትግላችን” ከሚለዉ ሰነድ ከረዥሙ ዝርዝር ሰነድ መሃል ለይቼ በማዉጣት ለዛሬ የወያኔ የገበና ማሕደር የመረጥኩላችሁን ሰነድ እነሆ። የወያኔ ገባና መዘገባችን ያስፈራቸዉ ሁሉ ብርታቱን ይስጣችሁ እያልን መዘገባችን የምንቀጥል መሆናችነን ስንገልጽ በደስታ ነዉ። ከሰነዱ መግብያ እንጀምር፡ “የዛሬዉ “ማሌሊት”የቀድሞዉ የህወሓት “ኮሚኒስት” ሃይል የዉጭ መልኩ እንጂ ዉስጣዊ ገጽታዉ ምን እንደሚመስል የሚያዉቅ ሰዉ ጥቂት ነዉ። የማንኛዉም ነገር ወሳኝ መልኩ ዉስጣዊ ባሕሪዉ በመሆኑ ለዚያ ለዘመናት ሰላምና ዕድገት እርም ለሆነበት ሕዝባችን ስንል የዚህ ኮሚኒስት ሃይል ነኝ ባይ “ማሌሊት” ዉስጠ ባሕሪ ግልጽ ማድረግ ለትግሉ መፋፋም እጅግ የሚጠቅም በመሆኑ እንደ ታጋይ ይህን ለማድረግ ተገቢ ግዴታዉ ነዉ። “ማሌሊት” በዚያዉ ዘመናዊ መፈክሩ “ግልፅ መድረክ እንጠቀም፤ልዩነታችንን ሁሉም ይወቀዉ” በማለት ፉከራ ስለሚያበዛ በዚህ ጽሁፍ ላይ ቅን ስሜት እንደሚሰዉ የመነመነ ተስፋ አለኝ። የ “ማሌሊት” ወይም የህወሓት “ኮሚኒሰት” ሃይል ዉስጣዊ ማንነት ለማበጠር ብዙ ርዕስ ነገሮችን አንስቶ ለማብራራት የሚቻል ነዉ። ማሌሊትና ዲሞክራሲማሌሊት እና የሕብረት ግምባር ማሌሊት እና የኤርትራ ወያኔ፣ ማሌሊትና የጋራ መግለጫዎቹ፤ወዘተ…የሚሉ ርዕስ ነገሮች ገባጣ መስመሮቹን ለማብራራት ይቻላል። ለጊዜዉ ግን በዚህ የህወሓት ዕድል በራስ የመወሰን መብት ጉዳይ ማለትም በትግራይ ሕዝብ የብሔር ጥያቄ ላይ በማብራራት እንጀምር። ይልና-በአረጋዊ በርሔ እና “ማርከስ የማያዉቀዉ ላምፐን” ተብሎ በቅጽል ስሙ በሚታወቀዉ መለስ ዜናዊ እንዲሁም ሌሎቹ መስፍናዊ ብሔረተንነት የተጠናወታቸዉ የሚላቸዉ ስብሓት ነጋ እና አባይ ፀሃየ መካከል የነበረዉ የተለያዩ ድርጅቱን የሚመለከቱ ክርክሮች በስፋት ሲገልጽ፣ የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ ዓላማ ማለትም መገንጠሉ ዓላማ ማን እንዳቀደዉ እና ያቀደዉ ክፍልም (3 ዋና የዕቅዱ ተላሚዎች እና ሌሎች 3 የነሱ ተባባሪዎች) ስለ ዕቅዱ ተጠይቆ የሰጠዉ መልስ እና ለምንስ እንደታቀደ ሁሉ በዝርዝር ያስቀምጥና፣ ይህ ጠባብ ቡድን ድርጅቱን በጠባብ ብሔረተኛነት ዓላማ ለማራመድ የተጠቀመባቸዉ ዘዴዎች እና መሰሪ ጎዳናዎች በስፋት ካብራራ በሗላ። እንዲሁም ድርጅቱ ለይስሙላ የሕብረት ትግል በማለት ሲያስተጋባዉ የነበረዉ ዉሸት እና መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች አንስተዉ ለጠየቁ የኢሕዴን/ብአዴን አባላት በተሓህት ባለስልጣናት በግል እየተጠሩ “ከፖሊስ መርመራ ባልተናናሰ ምርመራ እና ፍጥጫ” እየተደረገባቸዉ ለወደፊቱ የሚገለጽ ምስጢር በማለት በይደር ያስቆየዉ ሃተታ ከዘረዘረ በሗላ ያ ረዥም ትንተና እና የደርጅቱ ባሕሪ በስፋት ከተነተነ ካስቀመጠ በሗላ፣ ድረጅቱ በጠባብ ብሔረተኛነት እየተጓዘ በጸረ አማራ ቅስቀሳዉ እንዴት ይጓዝ እንደነበር ሰነዱ እስካሁን ድረስ ለሕዝብ ይፋ ከሆኑት ካነበብናቸዉ ከማናቸዉን ሰነዶች በላይ በማያሻማ ግልፅነት እንዲህ ሲል በግልጽ ያስቀምጠዋል። “… ከአንደኛዉ እስከ 2ኛዉ የሕወሓት ጉባኤ ድረስ ለእኩልነታዊ አንድነት ይሁን ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ምስረታ ቅድሚያ ሰጥቶ መታገል ወይም የሕብረት ትግል የሚፈጥርበት መንገድ መፈለግ የሚባል ጉዳይ አልነበረም ብንል ከሃቅ አንርቅም። በህወሓት በኩል የሕብረት ትግልን የማይጋብዙ አደናቀፊ አቀራረቦች ስለነበሩ ብቻ ነዉ። የሕብረት ትግሉ እንዳይፋጠን ብቻ ሳይሆን ይባስ ብሎ የተለያዩ ድርጅቶች ትምክህታዊ አመለካከት እግዶናል፣የሕብረተሰባችን ጠባብ መስፍናዊ አመለካካት የፈጠረዉ ችግር ነዉ”እየተባለ መደባዊ ወገናዊነት አበጥሮ የማይመለከት” “ፀረ አማራ” የሚል ቅስቀሳ ነበር። ባሕላዊ ትርኢቶች፣ትያትሮች፣ቀልዶች፣አባባሎች በዚህ ጠባብ መርዝ እየተለወሰ ቀርበዋል። በዚህ ድርጅት የሚቀርበዉ “ባሕላዊ ትርኢቶች” ጠባብ ብሔረተኝነት የሚያዳምቁ ብቻ ናቸዉ የማያሰኘን አደናጋሪ የሆኑ መደባዊ ወገንነት የሚያንፀባርቁና የሁሉም ጭቁን ኢትዮጵያዊ ጥያቄ የሚያዳምቁ የተለያዩ ዘፈኖች አሉ።ይህ ግን ባንድ ጠባብ ወይም ትምክሕታዊ ዘፈን የሚታይ፣ ድርጅቱ ለእዩልኝ ስሙልኝ የሚያቀርበዉ ማፊያዊ ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ነዉ። “ተራማጅ ነኝ፣ቀድሞዉንም ኮሚኒስት ነበርኩ” የሚለን የህወሓት ቡድን “ጠባብ ብሔረተኝነት የሚያስፋፋ ባሕላዊ ቅስቀሳ” ሲካሄድ “ዝም ብሎ ተመልክቷል” ብቻ ሳይሆን “ይበልጥ ይቀጥል” እያለ “የእደግ ተመንደግ” መመሪያዉን ዉስጥ ዉስጡን ይሰጥ ነበር። ትግላችን ጠባብ ባሕላዊ ቅስቀሳዎችን በሚመለከት የኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አህዴን) አባሎች በተደጋጋሚ ተቃዉሞ ያቀርቡ እንደነበር ጠቅሰን ዝርዝሩን እንተወዉ።ይህ የአመራር ቡድን “የዕደግ ተመንደግ” መመሪያዉን እየሰጠ የሚንቀሳቀስበት የራሱ ምክንያት አለዉ። ጠባብ ማኒፌስቶን አርሜአለሁ በሚልበት በዚያ በሆ-ሆየ ወቅት፣ጠባብ ብሔረተኝነትን ለማዳመቅ ስለከበደዉ ነዉ። ዞሮ ዞሮ ግን ከጠባብ ጓሮዉ ስለማይወጣ ጠባብ መመሪያዉ በግልጽ መዉጣት አይቀርለትም። በሗላ እንመለስበታለን። ከዚያ በረቂቅ መንገድ ከሚካሄዱት ጠባብ ብሔረተኝነት ቅስቀሳዎች አንድ ጠቅሰነዉ ልናልፍ የሚገባ አብነት አለ። አጼ ዮሐነስ እና አጼ ምኒልክ ግዛቶቻቸዉን ለማስፋፋት ሲሉ ህዝቡን እያተራመሱ ከባድ ቅራኔ አሳልፈዋል። ሁለቱም በሚፈጥሩት ትንቅንቅ በዚያ ሗላ ቀር ህብረተሰብ ዘንድ የሚንጸባረቅ ሁኔታ ሊኖር ነዉ። ተራማጆች እና ኮሚኒስቶች ለሕብረተሰብ ቆመናል ካሉ ደግሞ መሳፍንቶች በሕዝቦች መካከል ያደረሱት ክፍፍል እንዲጠፋ እና እንዲታረቅ ሊጥሩ ይገባል።ይህ የህወሓት ኮሚኒሰት ያመራር ቡድን ግን ያንን የስስት ምኞታቸዉን እንዲያገለግላቸዉ ስለሚፈልጉ በዚሁ ታሪክ ላይ ተንተርሰዉ “አማሮች የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች ናቸዉ፣ከአማሮች ጋር መኖር እንዴት ይቻላል ወዘተ…” እያሉ ሲያስፋፉበት ይገኛሉ። የሚኒልክ ሰራዊት አለ ስንቅ ወደ ዓድዋ ጦርነት ስላዘመቱት የትግራይን ሕዝብ ንብረት አጠፉት የሚል ታሪካዊ ትምሕርትም አለ። ይህ አንድ ሐቅ ከሆነ ሌላዉ ሐቅ ደግሞ ከዚሁ ጋር መጠቀስ ነበረበት። ይህ ደግሞ የምኒልክ ሠራዊት ወደ ትግራይ ሲመጣ በአይሮፕላን ስላልነበረ ነፍጠኛ ሠራዊት እንደመሆኑ መጠን የሌላዉን አማራ ገበሬ ንብረትም ዘርፎት እንደመጣ ሊጠቀስ ይገባዉ ነበር። ሌላዉ ደግሞ በመጀመሪያዉ የወያኔ ታሪክ የማዕከላዊ ትግራይ ህዝብ በመሳፍንት ተመርቶ በደቡብ ትግራይ ህዝብ ላይ ከባድ ጥፋት አድርሷል። ይሁን እንጂ የትግራይ ህዝብ ብሔራዊ አንድነት እንዳይላላ እየተባለ ይህን የተከወነ ነገር ተረግጦ የሚታለፍበት ጊዜ ብዙ ስለሆነ ወደ መረሳቱ ደረጃ ተቃርቧል። ግሩም ነዉ። ታሪክ የማይታፈን እንኳ ቢሆንም ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ሲባል ደግሞ ከዚህ በበለጠ መደረግ ተገቢ አልነበረም? በተለይ ከማሌሊት መሪዎች። ጉዳዩ የሕዝቦች መሰረታዊ መደባዊ አንድነት አላልቶ ብሔራዊ ቅራኔ አሁን ካለበት በላይ እንዲቃረንና እንዲሾል በመሆኑ ያን ለጠባብ ዓላማዎቻቸዉ መገንቢያ እየመዘገቡና እያስተማሩ ያን መደባዊ ወገናዊነትን የሚያጎላዉን ግን ማላላትና መቅበር ግድ ሆኖባቸዋል።የዚህ ዓይነት ጠባብ ብሔረተኝነት የሚያስፋፋ ተግባር የሚቋረጥበትን መንገድ እንፈልግ ባልንበት ቁጥር በጥቃቅን ነገሮች ጊዜአችሁን ታባክናላችሁ ተብለን ተኮንነናል።” በማለት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ዋና መስራች አባል እና የድርጅቱ የማአከላዊ አመራር አባል እና የድርጅቱ ወታደራዊ ኮሚቴ ዋና አዛዥ ስለ ድርጅቱ ጠባብ ብሔረተናነት እና ድብቅ ባሕሪዉ እና ተንኮል ከላይ እንዳነበባችሁት ገልጾታል። ትግሉ ይቀጥላል! ትግሉ ረዢም ቢሆንም በጠባብ ብሔረተኞች ሕሊና የሚጓዙ ግብዞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እተጋለጡ ወደ አይቀሬዉ የመጨረሻዉ ዉድቀታቸዉ ያመራሉ። በጠባብ ብሔረተኛነት ስነ ልቦና ዜጎችን ቀስቅሰዉ መጠነ ሰፊ ጥፋት እና ጥላቻ ለፈጠሩት ሁሉ የጊዜ ጉዳይ እነጂ ተጠያቂነታቸዉ አይቀሬ ነዉ።ጉዞአችን ረዢም ቢሆንም ድሉ የማይቀር ነዉ። በአንድነታችን ላይ ጥላቻና መራራቅ የፈጠሩ የህወሓት መሪዎች በዓለም አቀፍ ሕግ ወይንም በዉጭ አገሮች ፍርድ ቤቶች እንዲከሰሱ ኢትዮጵያዉያን የሕግና እንዲሁም የማሕበራዊ ኑሮ ባለሞያዎች ቋሚ የሞያተኞች ማሕበር መስርተዉ በሙያቸዉ ስለሰለባዎች ፍትሕ ማስገኘት ጉዳይ ቢጥሩና ፖለቲካዉ ዉስጥ የዕረጎ ዝምብ እየሆኑ ሓምሳ ገጽ ከመጻፍ በሙያቸዉ ቢሰሩ በንጹሃን ደም እያሾፉ ያሉትን ወንጀለኞች ሁሉ ተጨማሪ ዕልቂትን ትርምስን ለወደፎቱ ከምያመጡ ከማዳን በላይ ጠባብ ብሔረተኞች ዛሬም እየቀጠለበት ያለዉ የሰብአዊ ሕይወትንና ሰብአዊ መብት መረገጥን ከመቀጠል ማስቆም ይችላሉ። በዚህ ላይ አዲስ የትግል ምዕራፍ እንዲጀመር ለሰባዊ መብት የቆሙ የሕግ ባለሞያዎች ሁሉ እንዲወያዩበት አሳስባለሁ። የሰብአዊ ረገጣ እንደዋዛ እንዲታይ እና የሰለባዎች ጥቃት ዛሬ ሳይሆን “ዓረና የተባለ ፓርቲ” ወደ መንግሥትነት ሲመጣ ክሳችሁን አስሰሙ የሚሉን የዘመኑ ፖለቲከኞች ሁሉ እነሱ ቁልቁል በተያያዙት የማራቶን የሗሊት ሩጫ እንዳያስገቡን ሁሉም በያለበት አንደዘወትሩ ከመቸዉም በበለጠ የፖለቲካ ኪሳራቸዉን እንዲያጋልጣቸዉ በዚህ አጋጣሚ አደራየ እንደጥንቱ ደግሜ ሁሉም ጆሮዉን ያቁም ዓይኑን ይክፈት። ለመዉሰድ እያቀዱን ያሉትን ጉዞ አደገኛ እና የሗሊት ፖለቲካ ጨዋታቸዉን ላለመጫወት ነቅቶ ሁሉም ዘብ ይቁም! ወደ መጨረሻዉ እየተቃረብን ስለሆነ ትግሉ እየመረረ መልክ እያጣ ማን ማን እንደሆነ ወገን የሚለይበት እርከን ስለደረስን ብንበታተንም በቁርጠኝነት ከመነሻ ዓላመችን ሳንዛነፍ ለሰለባዎችና ለፍትሕ ቆመን አገርን ለመገነጣጠል የፈሽስትና የኮሚኒስት የግንጠላ መመሪያ አንግበዉ ተመልሰዉ ከተተፉበት ትግል አንሰራርተዉ በመቆም ሳያሟሉት የቀሩት ግንጠላ ከተቀሩ ገንጣይ ጓዶቻቸዉ ጋር ድብቅ ስራቸዉን ለሟሟላት ትግሉን ለመጥለፍ እያጋገሙ ያሉትን የታሪክ እንክርዳዶችን ብልጠቱን እንንፈጋቸዉ። የከፋ ቀን ሲመጣባቸዉ እነ ገብሩ እና እነ ስየ እነ አዉዓሎም ወገንተኝነታቸዉ ከነ መለስ እንጂ ከእኛ ጋር እንደማይሆኑ ለደቂቃም ቢሆን አትጠራጠሩ። የኮሚኒስቶች/ፋሽስቶች የግንጠላ ፖሊሲ ለኢትዮጵያ ግጭት አንጂ አንድነትን አያመጣም! ጌታቸዉ ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com

Tuesday, March 3, 2009

በዓድዋዉ ድል ትግሬዎች እንጂ አማሮች ሊኮሩበት አይገባም?

በዓድዋዉ ድል ትግሬዎች እንጂ አማሮች ሊኮሩበት አይገባም?
ጌታቸዉ ረዳ እንኳን ለ113ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ። እንኳን አደረሰን ማለቱ የአባት ሆኖብን ነዉ እንጂ ፤አያቶቻችን ያስገኙልነን ድል ዛሬ ተመልሰን ኢትዮጵያ የጣልያንን ካርታ እና አስተዳደር በሚያወድሱ እና የሚቀበሉ በሙሶሎኒ መመርያዎች በቋንቋና በነገድ አስተዳደር የሚያምኑ ለቅኝ ገዢዎች ካርታ ቅድሚያ ሰጥተዉ የአባቶቻችነን አንጡራ መረጃዎች በማንኳሰስ በራሳቸዉ አገር የዘመቱ ከትግራይ እና ከኤርትራ የተወለዱ የዘመናችን “ትናንሽ ጣልያኖች” ሥር ወድቃ በምትገኝበት ወቅት “እንኳን ለድል አደረሳችሁ” ማለት አልነበረብኝም። ሆኖም እንዳልኩት ያባቶቻችን ሰናይ ገድል በወያኔ መሰሪ ሳይወደስ እንዳይቀር በማሰብ አባቶች በዚህ ወቅት በሕሊናችን እናስታዉሳቸዋለን። ሰሞኑን የወያኔ የፕሮፖጋንዳ መድረኮች የተመለከታችሁ ሁሉ፤ “ተሾመ ቶጋ” የተባለዉ “የወያኔ አገልጋይ” በዓድዋ ድል መታሰቢያ አበባ ሲየኖር፤ ጌታዉ “የሻዕቢያዉ ሎሌዉ” ‘መለስ ዜናዊ’ ግን ተደብቆ በልቡ “ሲያሾፍ” እንደዋለ ብዙዎቻችን የምናዉቀዉ ነዉ። ወያኔዎች ስለ ዓድዋ በዓል አከባበር “በሙዚቃ ማርሽ” አሳጅበዉ “አክብረነዋል” ቢሉንም በካድሬዎቻቸዉ እና በድርጅቱ መሪዎች በተደጋጋሚ በዓሉ የትግራይ ተወላጆች ድል እንጂ የነፍጠኞች ፤የኢትዮጵያዩያኖች እንዳልሆነ ያዉም (“ነፍጠኛ፤ትምክህተኛ፤የትግራይ ሕዝብ ጠላት፤4ኛዉ ጠላት (ቱርከ፤ግብጢ፤ጣሊያን እና 4ኛዉ ምኒሊክ) የሚኒልክ ተጋድሎ ድል እንዳልሆነ አበስረዉ ደጋግመዉ እንደጻፉ እና እንደተከራረከሩ አብዛኛዎቻችሁ የምታዉቁት በድምጺ ወያኔ ራዲዮ እና በተሓሕት የኪነት ቡድን የተዘፈነበት ፕሮፖጋንዳ ነዉ። ለዚህም ነበር ወያኔዎች {“ትግሬ ከጠገበ እና አንድ ከሆነ አይገዛም} ወይም አይቻልም” የሚል እምነት ነበራቸዉ። በተጨማሪም {የትግራይ ህዝብ “ብዙ ብር” አለዉ፤ተብሎ ስለሚታመን ገበሬዉን “እየዘረፉ” ሃብት ማካበትና ሕዝቡን “ማደሕየትም” “እንደ ስልት” የተያዘ በመሆኑ አስፈላጊ ነበር}። አጼ ምኒልክ ወደ ትግራይ ያደረጉት ዘመቻም እነዚህን “ሁለት ነጥቦች” ለማሳካትና ተግባራዊ ለማድረግ ነዉ”} ምመህር ገብረኪዳን ደስታ (የትግራይ ሕዝብ እና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንት አስከ ዛሬ ገጽ 103) እንግዲህ ከላይ በአህጽሮት የምታኑብቡት የወያኔዎች ያልተገረዘ አንደበት ወያኔዎች የዓድዋን ድል የተገኘዉ በትግራይ ህዝብ እና መኳንንት ብቻ እንደሆነ በማስመሰል፤ በመሪነት ከባለቤታቸዉ ጋር ወደ ረዥም እና አድካሚ የእግር ጉዞ ተጉዘዉ ከአዲስ አበባ ዓድዋ ድረስ ዘምተዉ “አላጄ”፤”እንዳየሱስ” እና “እምባ-ሰሎዳ” ድረስ ገስግሰዉ ራስ መንገሻ ዮሃንስን እየተከታተሉ ሲያባርሯቸዉ የነበሩትን ጣሊያኖች በተጠቀሱ ቦታዎችን የመሸጉት ጣሊያኖችን ከመላ ኢትዮጵያ ያሰባሰቡዋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ተዋጊዎች አያቶቻችን በመምራት ለድል ያበቁትን ምኒልክ መሆናቸዉ ላለማሞገስ ተብሎ “ሚኒልክ ወደ ትግራይ የመጡት “ብዙ” ብር አለዉ ተብሎ የሚገመተዉ የትግራይ ሕዝብ ለመዝረፍ እንደመጡ ነበር እየነገሩን ያሉት። ወያኔዎች ይቀጥሉና {“በአጼ ምኒሊክ ሴራና ሃገራዉ ክህደት ምክንያት (የትግራይ ሕዝብ) የጠላቶቹ መተረቢያና መሳቅያ ሆነ። አስመራ ከተማ ላይ ወድቆ ከኢጣሊያንኖች እጅ ፍርፋሪ ለመነ። በጎዳጉዲ፤በጉራዕ፤በሰሓጢ፤በኩፊትና በዶግዓሊ አዉደ ዉግያዎች አባቶቻችን ያስመዘገቡት የጀግንነት ዉሎ እና አኩሪ ታሪክ በአጼ ሚኒሊልክ ሃገራዊ ክህደት ምክንያት ተደመሰሰ። የአባቶቻችን ደም ፤ደመ ከልብ ሆኖ ቀረ።”} ምመህር ገብረኪዳን ደስታ በተጠቀሰዉ መጽሃፍ ገጽ 104-105) በሃገር ወዳድነት ፤የትግራይን ሕዝብ ከጣሊያን መንጋጋ ያላቀቀዉ፤ የትግራይ መስፍን የነበሩት “ራስ መንገሻ ዮሃንስን” ከጣሊያን እግር ብረት እና ግዞት አልላቅቀዉ ፤ የትግራይ ሕዝብ እንደ “ኤርትራዉያን” ባዶ እግሩ እየሄደ፤ ወይም ከሗላ የከተማ አቡቶበሶች ሲጛዝ ከጣሊያኖች ተከልሎ በመጋረጃ ተጋርዶ ከመጓዝ፤ ከአራተኛ ክፍል ወዲያ እንዳይቀጥል እና እናቶቻችንም የጣሊያን መጫወቻ እና ዲቃላ አምራች እንዳይሆኑ፤ ወንድ አያቶቻችንም የጣሊያን ሰላቶ ሆነዉ ትግራይ ዉስጥ የሰላቶ ባንዴራ እንዳያዉለበልቡ በማለት ከሸዋ፤ ከጎጃም፤ ከወሎ፤ ከአርሲ ከሐረር.. ከመላዋ የኢትዮያ ሕዘብ ክተት ብለዉ በእግር በበቅሎ እየመሩ ጣልይንን አባርረዉ “ለድል ያበቁት” በድል ታሪክ የሚዘከሩትን ጀግናዉ ሚኒልክን “በሃገር ከሃዲነት” ሲከስሱ፤ ያገር ክህደት የፈጸሙት የዘመናችን ከሃዲ “የወያኔ ባንዳዎች” ምኒሊክን ለመዉቀስ የሞራል ብቃት እንደሌላቸዉ መላዉ ሕዝብ እና በክህደቱ ዉስጥ እጃቸዉን ያስገቡ የወያኔ መሪዎች ሳይቀር የራሳቸዉ ክህደት ባያምኑም “ስህትት ፈጽመናል/ችኮላ” የሚሉ ቃላቶች በመተካት ሃጋረቸዉ ኢትዮጵያን እንደበደሉ/እንደካዱ “ያመኑበት ነዉ”። የወላጆቻችን ደም -“ደመ ከልብ” እንዲሆን ያስቀሩት ሚኒልክ ሳይሆኑ፤ ከዛ በሗላ በደማቸዉ ያስመለሱት እና ያስጠበቁት ክፍለሃገር ኤርትራን (ምኒልክ በወያኔ የሚከሰሱበት ጉዳይ) ከመሰል ካሃዲዎቻቸዉ ጋር በመሆን ወላጆቻችን ጣሊያንን በተዋጉበት ስፍራዎች እና የባሕር ወደቦች ላይ ተመልሰዉ የገዛ አገራቸዉ ኢትዮጵያ ያዘመተቻቸዉ ተዋጊ ሃይሎችን ከአሜሪካኖችና እና በዓረቦች አይዟችሁ ባይነት እየተበራቱ “በጠላቶች የሳተላይት መረጃ” እየታገዙ የፈጁት ኢትዮጵያዊ ነብስ ወያኔዎች እንጂ ሚኒልክ እንዳልሆኑ ይታወቃል።
ባገር ክህደት በወደብ መዝጋት፤ ያትዮጵያ ልጆች ደም በማፍስስ የሚከሰሰዉ ወያኔ እንጂ ማንም ሊሆን አይችልም። በዚህ ድረገጽ በአርካኢቭ/በመዛግብት ጓዳ፤ አሁንም የሰፈረዉ “አይ ምፅዋ!” የሚለዉ “ታሪካዊ የጦርነት ሰነድ” ላነበበ ሰዉ ባንዳዎቹ ምንኛ ሕሊና ቢስ ቅጥረኞች መሆናቸዉ ኢትዮጵያዊ ሕሊና ላልተለየዉ ፈራጅ በቀላሉ የሚፈርደዉ ነዉ። ንጉስ ምኒልክ እና (በወያኔዎች ቋንቋ፤በአብራሃም ያየህ በአታኽልቲ ሓጎስ በመምህር ገብረኪዳን ደስታ… ቋንቋ) “ደቂቀ ምኒሊኮች” ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር ከሻዕቢያ ጋር ወግነዉ “ምጽዋ ድረስ አልጌና ድረስ” ‘የትግራይ ልጆች’ ይዘዉ ሄደዉ የ ኢትዮጵያን እና የትግራይን የገበሬዉ ልጆች አስፈጅተዋል? ምኒልክ ከዚህ የባሰ ክህደት ፈጽመዋል? ዮሃንስም ፤ራስ መንገሻም ራስ ሥዩምም፤ራስ አሉላም፤ስብሓትም፤ደብብም ፤ሃይለስላሴ ጉግሳም ሁሉም እንደየሁኔታዉ ለጣሊያንም ለግብጽም እንዲሁም ከእንግሊዝም ተመሳጥረዉ ያገበደዱበት የተሞዳሞዱበት ሰነዶች ትተዉልን ሄደዋል። ሌላ ቀርቶ ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ ሲመለስ እነ ራስ ዳምጤን ማርኮ “ለኮሎኔል ቱቺ” አስረክቦ እንዲረሸኑ ያደረገዉ ማን ነዉ? ራስ ሃይሉ/ጀኔራል ሃይሉ ከበደን ማርኮ ለጣልያኖች በባንዳነት ሀገራቸዉን ከድተዉ የራስ ሃይሉን ራስ ቅላቸዉ በጣልያኖች ቢላዎ መቆረጥ ድረስ ያደረሰዉ የትግራዩ ሰዉ ማን ነዉ? አክሱማዊዉ የትግራይ ሰዉ “ደጃች ተኽሉ መሸሻ” አልነበሩም? ማን በማን ላይ ማማት ያምርበታል? ሁሉም የኛ ነገስታት ናቸዉ፤ሃበሾች ናቸዉ፤ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ።ታዲያ በምኒልክ እና በምኒልክ አድናቂ ኢትዮጵያዉያን እና የታሪክ ጻሃፍቶች ላይ ዘመቻዉ ለምን በረታ? በነገድ የፖለቲካ በሽታ ተለክፎ መስፍናዊነት ሕሊና ተከትሎ መወሻከት ምን የሚሉት ፖለቲካ ነዉ? እንደርታዊዉ ተወላጅ የወያኔዉ ዘፋኝ ኪዳነማርያም ረዳ በወየኔ ፕሮፖጋንዳዉ ምን እያለ ነበር የትግራይን ገበሬ እያሞኘ ሲሰብከን የነበረዉ? “ንአብነት ማይ ጨዉ ዓድዋ እንተዘከርና፤ ተምቤን ዓቢይ ዓዲ ሽረ እንዳባጉና፤ ኩይናት ምስ ገበሩ እቶም ወለድና፤ ጸላኢ ደምሲሶም ታሪኽ ሓደጉልና። ;..ጨቆንትና አምሓሩ ምስ ታሪኽ ፀሓፍቶም ንዓና ዓብሊሎም ታሪኽና ጎቢጦም አለዉ ይምክሑ ብደም ወለድና፤ ንቃለስ ተጋሩ ክንመልስ ቅያና “ (ሓቀኛ ታሪክ ተደብቆ አይቀርም ለምሳሌ የማይጨዉን፤ የዓድዋን፤የሽረ እንዳባጉናን ታሪክ ስንመረምር ወራሪዎችን ድባቅ በምመታት አኩሪ ታሪክ ትተዉልን አልፈዋል። ይሁን እንጂ፤አባቶቻችን ብብዙ ዓዉደ ዉግያዎች ደማቸዉን አፍስሰዉ ያስመዘገቡትን ታሪክ “(ጨቆንትና አምሓሩ ምስታሪኽ ፀሓፍቶም”) “ጨቋኞቻችን አማሮች እና ታሪክ ጸሃፊዎቻቸዉ” በአሁኑ ወቅት እየተኮፈሱበት ነዉ። ታሪካችንን ቀብረዉ በአባቶቻችን ደም/ታሪክ እየተመኩበት ናቸዉ እና የትግራይ ተወላጆች የሆንን በሙላ ታሪካችነን ለማሳደስ በፅናት መታገል አለብን) የሚል መልእክት ነዉ ዘፋኙ ያስተላለፈዉ።
እግዲህ እዚህ ላይ የምንመለከተዉ ልብ ብለን ማሰተዋል ያለብን (1-) ጨቆንትና አምሓሩ የሚለዉ ሐረግ ትግራይን የጨቆነዉ አማራ መሆኑን (2-) ይህ አማራ የተባለዉ ጨቋኝ ነገድ፣ ጉብዝና የሌለዉ፤ለኢትዮጵያም ሆነ ለትግራይ ሕዝብ ሲል ደሙ ያላፈሰሰ፤ በመከራ ጊዜ ለትግራይ ሕዝብ ያልደረሰለት፤የጣሊያን ወራሪ መሪዎቹን እነ ራስ መንገሻ ዮሓንስ እያሳደደ አዲግራትን መቀሌን አልፎ እስከ አላጌ ድረስ ሲያስሸሻቸዉ አማራ የሚባል ክፍል ለወገኑ ለትግራይ ሕዝብ የወገን ደራሽ ሆኖ አምባላጌ፤ እንዳየሱስ፤ በእንዳባጉና፤ በሰለክላካ ጦር ሜዳዎች… ከጎጃም ከሸዋ ከወሎ ከጎንደር ገስግሶ ዘምቶ ደሙን እንደላፈሰሰ፤በመስበክ የታሪክ ዉሸት በጽሁፍ እየመዘገቡ አዲስዩን ትዉልድ ለማወናበድ ጥረዋል። ዘፈኑም የሚያመለክተዉ ይሄንኑ የዉሸት ጸረ-አማራ ስብከት ነዉ። ያዉም-አርበኝነት የሚባል ወኔ አማራዉ ስለሌለዉ ወይንም የትምክህተኞቹ ወላጆች የሚባሉት “አማራዎች” አርበኛ ስላልበቀለባቸዉ “በትግራይ አርበኞች” እየተመኩ “የትግራይ አርበኝነት የአማራዉ በማስመሰል” እየተኮፈሱበት ነዉና “አማሮች በራሳቸዉ አርበኞች (ካሉዋቸዉ!!) ይኩሩ እንጂ በወላጆቻችን በትግራይ አርበኞች መኩራራት መኮፈስ የለባቸዉም።ይላል ዘፋኙ የወያኔዉ የኪነት ክፍል። ይሄ ደግሞ እንዲሆን መፍቀድ የለብንም!! ነዉ መልእክቱ።ይሄን ስታነቡ ብለጭ እንደሚልባችሁ ይገባኛል። ያልበሰሉ ትንንሽ ህሊናዎች አደገኞች በመሆናቸዉ ለምን እንዲያ እንደሚሰማችሁ ይገባኛል። ለመሆኑ አንዳባጉና ፤ሰለክለኻ ማይጨዉ ያልዘመተ አማራ ማን አለ? ትዝታ የሚለዉ የአቶ አዲስ አለማዮህ መጽሃፍ የሚነግረን በአማራ ዘማች እና አዝማች የተካሄደ ጸረ- ጣሊያን ጦርነት ነበር።እነ አዲስ አለማዮህ ፤እነ ራስ እምሩ ትግሬዎች ናቸዉ? ይህ ክህደት የዘለለዉ የክህደት መጠን ስትመለከቱ ጎሰኝነት በዉሸት ሕሊናን አስክሮ ሕዝብ ለሕዝብ እንደሚያባላ ምንኛ ሃይለኛ በሽታ እንደሆነ እንረዳለን። ታሪክን እያጣመሙ ያሉት “ሰዉ መሳይ ባደባባይ” እነማን ናቸዉ? የሰዉ ልጅ እንደ በቀሎ እሸት እሳት ዉስጥ ጨምረዉ የሚቀቅሉ የዘመናችን የወያኔ ጉዶች/ትንንሽ ጣሊያኖች’ አይደሉም? ለመሆኑ አማራ የሚባል ጀግና ታጥቶስ ከትግራይ ጀግኖች እየተፈለጉ በትግራይ ጀግኖች ሰም እንደ “የአማራ ጀግኖች” እየተደረገ፤ አማሮች እየተኩራሩበት ነዉ ማለት ከዚህ ወዲያ የታሪክ ግብዝነት ምን አለ? የአማራ ነገድ ስም የሚያስጠራ የጦር ሜዳ ጀግኖች ስም የለም ብለዉ ማሰብ ከቶዉንም ራሱ የቻለ ልዩ ክህደት ብቻ ሳይሆን “የኩታራ ኩታራ ሕሊና ማራመድ ነዉ”። ደግሞስ አማራዉ በትግራይ ጀግኖች ቢኩራራ እና ቢመካስ የሚያስከፋዉ ምኑ ላይ ነዉ። አማራዉ የትግራይ የሐረግ ዘር አይደለም?።ቢሆንስ፣ በወገኑ ጀግንነት ቢመካ ያስመሰግነዋል እንጂ እንዴት ያስወቅሰዋል? ሚኒልክ ዓድዋ ድረስ መጥተዉ እነ “አይነጥሩ መድፈኛዉ” ሊቀመንኳስ አባተ -“መቀሌ እንዳየሱስ ተራራ” ጣሊያን የመሸገበትን ምሽግ በመነጥር እያዩ ሚዛኑን እየመዘኑ የጣልያንን መድፍ መንኮራኩሩን ሲሰብሩት የነበሩት ጀግኖች በምን መለክያ በክህደት እና በፈሪነት ይመዝገቡ?ትግራይን ከጣሊያን ጥርስ መንጋጋ አላቅቆ “የተከላለከለት” አማራ/ነፍጠኛ ብሎ ወያኔ ሚጠራዉ ክፍል ደሙንና እና አጥንቱን እንዳላፈሰሰ ለምን አኩሪ ስራዉ ለምን ከመ “ደመ ከልብ” ይቆጠራል? ብልግናዉ በጣም አልበዛም?! ወገኖቼ ሆይ- እነኚህ ጉዶች እንኳን በጠላትነት ሚያዩት አማራዉን የኛ የሚሉትን የራሳቸዉ የትግራይን ሕዝብ ሳይቀር “በጠባብ ብሄረተኛ” እና “በመስፍንንት ሕሊና” ይከስሱታል። ለመሆኑ ካሃዲዉ ማን ነዉ? ጠባብ ብሐረተኛ እና መስፍናዊ እና ትምክህተኛ በማለት ስለ የትግራይን ሕዝብ በሕሪ እና ማንነት የገለጸዉ ማን ነዉ? “ወያኔ ወየስ አጼ ሚኒሊክ?” ድርጅቱን በግምባር ቀደም የመሰረተዉ ከድርጅቱ ባላመስማማት የወጣዉ በ“አረጋዊ በርሄ” ብዕር አስደግፌ ስለ ወያኔ ከሃዲ እና ጸረ ኢትዮጵያዊነት ላቅርብ “በዓሰር አመት ግምገማዉ ዉስጥ…” ይላል አረጋዊ በርሄ በእነመለስ እና ስብሓት የሚመራዉ ወያኔ ትግራይ “የትግራይ ሪፑብሊክ” በምን መነሻ ለመመስረት እንደተገፋፉ ተጠይቀዉ ሲመልሱ “የትግራይ ሕዝብ ጠባብ ብሔረተኛነትና መስፍናዊ ሕብረተሰብ ዝንባሌ ስላለዉ፤ ለግንጠላዉ የመነሻ ምክንየት አድርገዉ እንደሆነ እና ሊነጠል እንደሚፈልግ የጻፉት የድርጅቱ ግምገማ ያቀረቡት ክርክር “በ10 ዓመት ግምገማዉ ገጽ 24-25 እንዲህ ይላል “ይህ የጠባብ ብሔራዊ አመለካከት ዝንባሌ የተከሰተዉ በሕዝቡ ላይ የነበረዉ ጠባብ ብሔራዊ ስሜት” እንደነበር ለሪፑብሊክ ምስረታ ዓላማቸዉ ከገፋፋቸዉ ካቀረቧቸዉ ጥቂት ሌሎች ምክንያቶች አንደኛዉ ከላይ የተጠቀሰዉ ምክንያት መሆኑን የ10ዓመቱ የግምገማ ሰነድ ይገልጻሉ። እንግዲህ ሕብረተሰቡም ሆነ እራሱ ተሓትን የሚመሩ መሪዎች ጠባብ ብሄረተኛ ዝንባሌ እንዳለቸዉ ሳይደብቁ ሲነግሩን- ምኒልክን በጠባብ እና ትምክህተኛ ሗላ ቀር በሆነ መስፍናዊ አስተዳደር ሲከስሱ፤ ከሳሾቹ ምኒሊክን የመክሰስ ሞራል ሊኖራቸዉ አይችልም እያሰኘን ያለዉ ሁኔታ ታሪካቸዉንና ሰነዶቻቸዉን በመመርመር ነዉ። በዚያዉ የግንጠላዉ ሁኔታ እና የ10 ዓመቱ ግምገማቸዉ ሰፋ ባለ አረጋዊ በጻፈዉ የቆየ ሰነድ በሚቀጥለዉ ሰሞን ይቀርባል ተከታተሉ።
የዓድዋ ድል የመላ ሀገሪቱ ልጆች ነዉ። በየትኛዉም ጦር ሜዳ ፤አንዱ ካንዱ የበለጠ መስዋእት ከፍሎ ሊሆን ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን ድሉ ለአንድ ሃገር ልጆች የተከፈለ መስዋእትነት በመሆኑ ድሉ የጋራችን ነዉ። በኢትዮጵያ አርበኞች ደም እንኮራለን። ብንኮራም ኢት ዮጵያዉያን አባቶቻችን የሚያስኮራን ደም ስለከፈሉበት ብንኮራም ይገባናል። ከላይ የቀረቡት የ1888 ዓ.ም የ ዓድዋ የኢትዮጵያን የካርታ ምሽጎች የሚያሳዩት በራስ መንገሻ ብቻ የሚመራ የትግራይ ጦር ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ክፍለሃገር ጦር ብዛት በላይ ተዋጊ እና አዋጊ ራሶች መኳንንቶች እና ባላባቶች ከመላ ኢትዮጵያ የተወጣጡ ዘማች ተዋጊ አርበኞች ጠቅላላ የዉግያ ቀጠናዎች/ወረዳዎች የተያዙት በእነዚህ አርበኞች እንደነበር እንድትመለከቱት ለማስረጃ ያቀረብኩት ነዉ (ምንጩ የዓድዋ ድልና የኢትዮጵያ ጀግኖች ዉለታ” ደራሲ አቶ አበበ ሃይለመለኮት ናቸዉ)። በዚህ መረጃ አሌ የሚል የወያኔ ካድሬ ካለ ሜዳዉ ይሄዉ ፈረሱም ይሄዉ! ማስረጃችሁን አምጡ እንከራከር። መስፈናዊ ጠባብ የወያኔዎች የሕሊና አመለካከት ዞሮ ዞሮ የሚጎዳዉ የትግራይን ሕዝብ እንደሆነ ተገንዝባችሁ በጎጠኝነት የተተበተበ ሕሊናችሁ መልሶ ወደ ሃገራዊ እና ሰብአዊነት ሕሊና እንድትመልሱት ደጋግመን ምክራችንን ዛሬም በዚህ የዓድዋ ድል እንለግስላችሗለን። ነገር ካለፈ በሗላ እንደ ደርግ ብትቆጩ ትርፉ መቆጨት እንጂ ጉዳት ካደረሱ በሗላ መቆጨት ላመንም አይፈይድም። የተፈጥሮ ሕግጋት ነዉና ወደ ላይ የወጣ ሁሉ አንድ ቀን ተመልሶ ከወጣበት ሥር ተመልሶ መዉረዱ አይቀሬ ነዉ።ዘረኛነትን ፤ነገድኝነትን እናሰወግድ። የኢትዮጵያ ጠላቶች እና የወያኔ ባንዳዎች ዉድቀት አይቀሬ ነዉ! ትግላችን ረዢም ነዉ ፤ድል ግን አይቀሬ ነዉ! Getachew Reda http://www.ethiopiansemay.blogspot.com

Sunday, March 1, 2009