Sunday, May 24, 2009

የተባረሩት የህወሓት ማእከላዊ ኮመቴ አባላት ሲባረሩ የክብር ጠባቂ፣ ደሞዝ እና መኖርያ ቤቶቻቸዉ እንዳይነጠቁ ተደርጓል

የተባረሩት የህወሓት ማእከላዊ ኮመቴ አባላት ሲባረሩ የክብር ጠባቂ፣ ደሞዝ እና መኖርያ ቤቶቻቸዉ እንዳይነጠቁ ተደርጓል ጌታቸዉ ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ምክንያት፣ባለፈዉ ሰሞን በአቶ አበበ በለዉ የአዲስ ድምፅ ራዲዮ ፕሮግራም ከሦስት የትግራይ ተወላጆች ጋር የተደረገዉ ቃለ መጠይቅ ቅጅዉን ሳዳምጥ፣ ከእንግዶቹ አንደኛዉ የመለስ ዜናዊ አመራር አረመኔነት ከዘረዘረ በሗላ የስርዓቱ ጨካኝነት ለማሳየት ምሳሌ የተጠቀመበት በእነ ገብሩ በእነ አረጋሽ እና ጓዶቻቸዉ የተደረገዉ ኢሰብአዊ እርምጃ በማዉሳት “እንኳን ሌላዉ አብረዋቸዉ ለታገሉት የቅርብ ጓዶቻቸዉ እንኳ ከድርጅቱ ሲያስወጧቸዉ ያለ ምንም መጠለያ እና ደሞዝ ነበር መሃል ሜዳ የጣሏቸዉ”የሚል ዓይነት እንደምታ ሲነገር በመስማቴ፣ እኔ ከያዝኩት ሰነድ ጋር ሳገናዝብ ታሪኩ ተቃራኒ እንደሆነ ስለተገነዘብኩ፣ በእጄ ላይ የሚገኝ በቴፕ/በደምፅ የተቀረጸ ስለ ጉዳዩ የሚያስረዳ ማለትም እነ ጸጋይ በርሄ እና ዓባይ ወልዱ የተባሉት የትግራይ የወያኔ ከፍተኛ ሹሞች “በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማሕበር”ብሎ ራሱን የሚጠራ የመለስ ዜናዊ ደጋፊ አካል ባዘጋጀዉ “የወያኔ ባዓል”ለማክበር በእንግዳነት ተጠርተዉ በ2005(በፈረንጅ) ወደ አሜሪካ መጥተዉ በነበሩበት ወቅት የተባረሩት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሲባረሩ የክብር ጠባቂዎቻቸዉ እና ደሞዝ እንዲሁም በነጻ ሲኖሩባቸዉ የነበሩባቸዉን መኖርያ ቤቶቻቸዉ እንደያዙ ሳይነጠቁ እንዲባረሩ እንደተደረገ ለተሰብሳቢዉ በቃላቸዉ አረጋግጠዋላቸዉ እንደነበር ማስረጃዉ ያረጋግጣል። .የወያኔ ሹሞች ጉዳዩን አስመልክተዉ ሲያብራሩ፤ ይህም እንዲደረግ የሆነበት አንደኛዉ ምክንያት ይላሉ ‘ምናልባትም ከጊዜ በሗላ ወደ ልቦናቸዉ ይመለሳሉ የሚል እምነት ስለነበረ፣ ባይመለሱም “አብረዋቸዉ የታገሉ እና አብረዉ ብዙ ዉጣ ዉረድ ያዩ ጛዶቻቸዉ ስለሆኑ በሌላ ተቃዋሚ ሃይል እንዳይገደሉ ወይንም ላስቸጋሪ ኑሮ እንዳየይጋለጡ በሚል ድርጅታዊ ሰብአዊ እና ጓዳዊ ርህራሄ መሰረት በማድረግ እንደተወሰነ የሚገልጽ እንግዶቹ እዚሁ ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ እና ዋሺንግተን-ዲሲ ድረስም መጥተዉ ያረጋገጡትን ከሁለቱም የዕለቱ እንግዶች የተገለጸዉ ገለጻ በትግርኛ የተቀረጸዉ የቴፕ ድምፅ (ሰነድ) ወደ አማርኛ ተርጉሜ ከዚህ በታች ሳቀርብ፣- ‘የፀጋይ በርሄ አነጋገር ሁሌም ለጽሁፍ ቅንብር የማይመች ዝርክርክና የተተበተበ አነጋገር ስለሚጠቀም ለፅሁፍ አንባቢ እንደሚገባ በመጠኑ ተስተካክሎ እንዲቀርብ አድረጌአለሁ፣፣ የተስተካከለዉ ግን የአረፍተ ነገሮቹን ቅደም ተከተል አሰካክ እንጂ ቁም ነገሮቹ እንዳሉ የተናጋሪዎቹ መልሶች ናቸዉ፣፣ ከዚህ በተጨማሪ፣- “እነ ገብሩ….” እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከስራ ሲባረር ደሞዙ እንዳጣዉ ሁሉ እኛም ከህወሓት ድርጅታዊ ስራ ስንሰራ ቆይተን ስንባረር መንግስት ምንም የተለየ ጠቀሜታ አላደረገልንም፣ አልተንከባከበንም፣ የሚሉ ከሆነ ያዲስ ድምፅ አዘጋጅ ሁለቱንም ተቃራኒ ክፍሎች (እነ ፀጋይ በርሄ እና እነ ገብሩ) በእንገድነት ጠርቶ ትክክለኛ ታሪኩን ለሕዝቡ እንዲያስደምጡን አጋጣሚዉን በመጠቀም አደራ እላለሁ። ይህ ጎሰኛ አድልዎ የሚያሳየዉ ጎሰኞች ምንም ያህል ቢራራቁና ቢጣሉ በመከራ ሰዓት እርስበርሳቸዉ ጥለዉ እንደማይጣጣሉ ህያዉ ማስጃ ነዉ፣፣ ለዚህም ነዉ ጎሰኝነትን አጥብቀን የምንዋጋዉ፣፣ ሰነዱም እነሆ።- የመድረኩ አዘጋጅ ከተሰብሳቢዎቹ የተሰጠዉ ጥያቄ እነ ጸጋይ በርሄን (ሃለቃ ፀጋይ) እና ዓባይ ወልዱን (ዓባይ ዴራ) እንዲመልሱት ባቀረበላቸዉ ጥያቄ ልጀምር። ጥያቄ፣- የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራር አባሎች የነበሩ በተፈጠረዉ ሁኔታ ከድርጅቱ ተባሯል፣፣ ሲባረሩ ለደህንነታቸዉ ጥበቃ፣ መኖርያ እና ደሞወዛቸዉን በሚመለከት የተወሰደ እርምጃ ካለ ብትገልጹልን? ዓባይ ወልዱ፣- …..ጥያቄዉ በተደጋጋሚ ለኛም ቢሆን ትግራይ ድረስ መቀሌ ድረስ ዉጭ የሚኖሩ አንዳንድ ወንድሞች ስልክ እየደወሉ ለምን ባዶ ሜዳ ላይ ያለምንም መተዳደርያ ጣላችሗቸዉ እያሉ ይጠይቁናል። ሁኔታቸዉን በሁለት መንገድ በመመለከት ዉሳኔ አድርገናል። አንደኛዉ ለደህንነታቸዉ ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ አስፈላጊነት ነዉ። ይኼዉም እንደምናየዉ “መጥፎ ትካል” (የተጠቀመበት ትግርኛ )/ (ከወያኔ ዉጭ ሌሎች “መጥፎ” ድርጅቶች/ቡድኖች) አደጋ እንዳያደርሱባቸዉ በማሰብ ጥበቃቸዉ ልክ እንደ ድሮዉ “ሴኪሪቲዉ” በቦታዉ እንዳለ ሆኖ “የትም ይኑሩ የትም ( የተግርኛዉ “አብዝሃለዉ ይሃሉዉ”)በሚኖሩበት አካባቢ ስጋት እንዳያድርባቸዉ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ጥበቃ ይደረግላቸዋል። ሁለተኛ “መኪኖቻቸዉ ተነጥቀዉ በእግራቸዉ እንዲጓዙ ተደርጓል” “መኖርያ ቤቶቻቸዉ ተነጥቀዉ አልባሌ ቦታ ወድቀዋል… ወዘተረፈ”የሚል እሮሮ እንሰማለን። ይሄ ለፕሮፖጋንዳ እንዲጠቀሙበት ራሳቸዉ የሚያወሩት ካልሆነ በስተቀር በእኛ በኩል የምናዉቀዉ እና የሚወራዉ ዉሸት ለየብቻ ነዉ። በጣም የሚገርመዉ በመንግሥት የተሰጣቸዉ መኪና እቤታቸዉ ግቢ ትተዉ በእግር ሲጓዙ የሚታዩበት ሁኔታ እኛም ታዝበናል። ይሄ ግን ሆን ብለዉ ራሳቸዉ ያደረጉት ነዉ። መኖርያ ቤት በሚመለከትም ከተጠበቀላቸዉ ከሌሎቹ ጥቅማጥቅሞች የተለየ አይደለም። መኖርያ ቤቶቻቸዉም ቢሆን ሁሉም ሲኖሩባቸዉ የነበሩት መኖርያዎች ሁሉ እንዲኖሩበት ተደረጓል።መኪናቸዉ፣መኖርያ ቤቶቻቸዉ የነበራቸዉ ጥበቃ እና ደሞዝ ከቦታዉ ላይ እንዳለ ነዉ።ከሚኖሩባቸዉ ቤቶች አንድም ሰዉ ልቀቅ የተባለ የለም። እነሱም እንዲናፈስ የሚፈልጉት ወሬ ነዉ። ለምሳሌ እንቅስቃሴአቸዉን በሚመለከት ብንመለከትም፣ እንደማንኛዉም ዜጋ በነፃ የትም መዘዋወር መንቀሳቀስ ይችላሉ፣ እየተንቀሳቀሱም ነዉ። ወደ ፈለጉበት ቦታ/ አገር ስልክ መደወል ይችላሉ፣በፈለጉበት መዉጣት መግባት ዉጭ አገር መሄድ መመላለስ ችለዋል። እኛ የምናዉቀዉ ሙሉ ነፃነታቸዉ እቦታዉ ላይ እንዳለ ነዉ የምናዉቀዉ። አገር ዉስጥ ያለ ሰዉ በዓይኑ የሚያየዉ ጉዳይ ነዉ። ለምሳሌ ከዚህ ከዉጭ ወደ እኛ እየደወሉ”መኪኖቻቸዉ ደሞዛቸዉ መኖርያ ቤቶቻቸዉ ነጠቃችሗቸዉ!ለምን እንደዚህ ታደርጋላችሁ?”እያሉ ይደዉሉሉናል። ይህ ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ዉሸት ዉጭ አገር ላሉ ዜጎች ሆን ተብሎ እንዲራባ እና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀሙበት እንዳሉ ነዉ እንየተገነዘብን ያለነዉ። ስለዚህ ወሬዉ ዉሸት ነዉ። ኑሮአቸዉ ድሮ ከነበሩበት የተለወጠ ወይንም የተቀነሰ ነገር የለም። የመድረኩ አስተናጋጅ -ጥያቄ፣- ጓድ ፀጋይ! ጓድ ዓባይ ባለዉ ላይ ተጨማሪ ካለህ? ፀጋይ በርሄ.- ቡዱኑ (አንጃዉ) ከመገንጠሉ በፊት እያንዳንደቸዉ ሲኖሩበት ከነበረዉ ኑሮ የተቀነሰባቸዉ ነገር የለም፣፣ እንዳለ ነዉ፣፣ ጥበቃዉ፣መኖርያ ቤታቸዉ፣ደሞዛቸዉ እንዳለ ነዉ፣ አልተነካም፣፣ ለምሳሌ የገብሩ አስራትን ሁኔታ ብንመለከት “ወደ ሌላ ስራ ተዛዉሮ እንዲሰራ ሆኖ” ደሞዙም፣ጥበቃዉም፣ መኖርያዉም እንዳለ፣ እንደነበረ መሆኑ ይታወቃል፣፣ ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ በማሃሉ “መኖርያዉን ነጠቁት!የሚል ወሬ ተነዛ፣፣ ይህ ሲሆን ግን ለምሳሌ ገብሩ በቅርብ ጊዜ ከነበረበት መኖርያዉ ለቅቆ በራሱ ፍላጎት ወደ ሌላ መኖርያ ሄዷል የሚል ወሬ ሰምተናል፣፣ ገብሩ ከሚኖርበት መኖርያዉ “ዉጣ” ያለዉ ሰዉ ወይንም አካል የለም፣፣ በጥበቃዉም በኩል አሁን የምኖርበት መኖርያ ጠበብ ያለ ስለሆነ ከጠባቂዎቼ መርጬ የሚሰናበቱ አሰናብቼ የማስቀራቸዉንም አስቀራለሁ ብሎ ደህንነቱን ከሚጠብቁ የደህንነት ጥበቃ ዘቦቹ መሃል መርጦ የሚፈልጋቸዉ አስቀርቶ ያልፈለጋቸዉ ጠባቂዎቹን ያሰናበታቸዉ ሁኔታዎች አሉ፣፣ ስለዚህ ቦታ ጠበበኝ ወዘተ…እያሉ ራሳቸዉ ከሚኖሩበት ሁኔታ የሚለቁበት ሁኔታ እንዳለ እናዉቃለን፣፣ ያም ሆነ ይህ በዚህ በኩል እኛ የወሰድነዉ ቀና እርምጃ እነኚህ ሰዎች ባለፈዉ ትግል ዘመን ጓዶቻችን የነበሩ ናቸዉ፣ እንደሰዉ (እንደሰባዊ ፍጡርነታቸዉም)መጠንም እንዲጎዱ የሚፈልግ ግለሰብም ሆነ መንግሥት የለም፣፣ ስለዚህ አሁን የያዙት አካሄድ ግን ሕዝባችንና ድርጅታቸን የሚበትን አካሄድ ነዉ እየተከተሉት ያሉት፣፣ ስለሆነም፣ ሁለት አማራጮች አስቀምጠናል-አንደኛዉ አማራጭ አሁንም የነበረዉ ትግል ፈር ተከትለዉ ወደ ህዝባቸዉ እንዲመለሱ ወደ ሕሊናቸዉ እንዲመለሱ ፣ ከስህተታቸዉ ተምረዉ እንዲቀላቀሉና ልዩነታችንን ይዘን አብረን እንድንጓዝ የማድረግ ጥረታችን ይቀጥላል፣፣ ሁለተኛዉ አማራጭ-እኔ እንደምረዳዉ እየተከተሉት ያለዉን መንገድ ድርጅታችንና ሕዝባችንን ወደ አደገኛ ጉዞ የሚያስገባ ሁኔታ እተከተሉ ስለሆነ እንታገለዋለን፣፣ እየታዘብነዉ/እያስተዋልነዉ ያለዉ ግን የተዛባ የጨለማ ጉዞ ግን ይበልጥኑ ወደ ዉስጥ እየገቡበት እንዳሉ ነዉ እየታዘብነዉ ያለነዉ፣፣ ስለዚህ ከዚህ ጉዟቸዉ ወደ ቀና መንገድ እንዲመለሱ እንጥራለን፣፣ ያ ክልሆነ ግን ሕዝቡም ካድሬዉም መታገሉ የማይቀር ነዉ፣፣ እየታገላቸዉም ነዉ፣፣”በማለት የነገብሩ፣ ተወልደ፣አረጋሽ አዳነ፣ ዓለምሰገድ ገብራምላክና የመሳሰሉት ወያኔ ለሁለት ተከፍሎ ሲባረሩ አንደማንኛቸዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለ ምንም መጦርያ እንደሚባረረዉ ሳይሆን የነበራቸዉ ጥበቃ እና ክብር ከነ ደሞዛቸዉና ነጻ መኖርያ ተለግሶላቸዉ ነበር የተሰናበቱት፣፣ በኔ በኩል ይኼዉ የያዝኩትን ማሕደር ይሄዉና በእናንተ በኩል በጉዳዩ ተቹበት፣፣ጎሰኛ እርስ በርስ ምን ያህል መጨካከን እንደማያስችለዉ ይህ በቂ መረጃ ነዉ እንላለን፣፣ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

የተባረሩት የህወሓት ማእከላዊ ኮመቴ አባላት ሲባረሩ የክብር ጠባቂ፣ ደሞዝ እና መኖርያ ቤቶቻቸዉ እንዳይነጠቁ ተደርጓል

የተባረሩት የህወሓት ማእከላዊ ኮመቴ አባላት ሲባረሩ የክብር ጠባቂ፣ ደሞዝ እና መኖርያ ቤቶቻቸዉ እንዳይነጠቁ ተደርጓል ጌታቸዉ ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ምክንያት፣ባለፈዉ ሰሞን በአቶ አበበ በለዉ የአዲስ ድምፅ ራዲዮ ፕሮግራም ከሦስት የትግራይ ተወላጆች ጋር የተደረገዉ ቃለ መጠይቅ ቅጅዉን ሳዳምጥ፣ ከእንግዶቹ አንደኛዉ የመለስ ዜናዊ አመራር አረመኔነት ካወሳ በሗላ የስርዓቱ ጨካኝነት ለማሳየት ምሳሌ የተጠቀመበት በእነ ገብሩ በእነ አረጋሽ እና ጓዶቻቸዉ የተደረገዉ ኢሰብአዊ እርምጃ በማዉሳት “እንኳን ሌላዉ አብረዋቸዉ ለታገሉት የቅርብ ጓዶቻቸዉ እንኳ ከድርጅቱ ሲያስወጧቸዉ ያለ ምንም መጠለያ እና ደሞዝ ነበር መሃል ሜዳ የጣሏቸዉ” የሚል ዓይነት እንደምታ ሲነገር በመስማቴ፣ እኔ ከያዝኩት ሰነድ ጋር ሳገናዝብ ታሪኩ ተቃራኒ እንደሆነ ስለተገነዘብኩ፣ በእጄ ላይ የሚገኝ በቴፕ/በደምፅ የተቀረጸ ስለ ጉዳዩ የሚያስረዳ ማለትም እነ ጸጋይ በርሄ እና ዓባይ ወልዱ የተባሉት የትግራይ የወያኔ ከፍተኛ ሹሞች “በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማሕበር” ብሎ ራሱን የሚጠራ የመለስ ዜናዊ ደጋፊ አካል ባዘጋጀዉ “የወያኔ ባዓል” ለማክበር በእንግዳነት ተጠርተዉ በ2005 (በፈረንጅ) ወደ አሜሪካ መጥተዉ በነበሩበት ወቅት የተባረሩት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሲባረሩ የክብር ጠባቂዎቻቸዉ እና ደሞዝ እንዲሁም በነጻ ሲኖሩባቸዉ የነበሩባቸዉን መኖርያ ቤቶቻቸዉ እንደያዙ ሳይነጠቁ እንዲባረሩ እንደተደረገ እና ይህም እንዲደረግ የሆነበት አንደኛዉ ምክንያት ምናልባትም ከጊዜ በሗላ ወደ ልቦናቸዉ ይመለሳሉ የሚል እምነት ስለነበረ፣ ባይመለሱም “አብረዋቸዉ የታገሉ እና አብረዉ ብዙ ዉጣ ዉረድ ያዩ ጛዶቻቸዉ ስለሆኑ በሌላ ተቃዋሚ ሃይል እንዳይገደሉ ወይንም ላስቸጋሪ ኑሮ እንዳየይጋለጡ በሚል ድርጅታዊ ሰብአዊ እና ጓዳዊ ርህራሄ መሰረት በማድረግ እንደተወሰነ የሚገልጽ እንግዶቹ እዚሁ ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ እና ዋሺንግተን-ዲሲ ድረስም መጥተዉ ያረጋገጡትን ከሁለቱም የዕለቱ እንግዶች የተገለጸዉ ገለጻ በትግርኛ የተቀረጸዉ የቴፕ ድምፅ (ሰነድ) ወደ አማርኛ ተርጉሜ ከዚህ በታች ሳቀርብ፣- ‘የፀጋይ በርሄ አነጋገር ሁሌም ለጽሁፍ ቅንብር የማይመች ዝርክርክና የተተበተበ አነጋገር ስለሚጠቀም ለፅሁፍ አንባቢ እንደሚገባ በመጠኑ ተስተካክሎ እንዲቀርብ አድረጌአለሁ፣፣ የተስተካከለዉ ግን የአረፍተ ነገሮቹን ቅደም ተከተል አሰካክ እንጂ ቁም ነገሮቹ እንዳሉ የተናጋሪዎቹ መልሶች ናቸዉ፣፣ ከዚህ በተጨማሪ፣- “እነ ገብሩ….” እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከስራ ሲባረር ደሞዙ እንዳጣዉ ሁሉ እኛም ከህወሓት ድርጅታዊ ስራ ስንሰራ ቆይተን ስንባረር መንግስት ምንም የተለየ ጠቀሜታ አላደረገልንም፣ አልተንከባከበንም፣ የሚሉ ከሆነ ያዲስ ድምፅ አዘጋጅ ሁለቱንም ተቃራኒ ክፍሎች (እነ ፀጋይ በርሄ እና እነ ገብሩ) በእንገድነት ጠርቶ ትክክለኛ ታሪኩን ለሕዝቡ እንዲያስደምጡን አጋጣሚዉን በመጠቀም አደራ እላለሁ። ይህ ጎሰኛ አድልዎ የሚያሳየዉ ጎሰኞች ምንም ያህል ቢራራቁና ቢጣሉ በመከራ ሰዓት እርስበርሳቸዉ ጥለዉ እንደማይጣጣሉ ህያዉ ማስጃ ነዉ፣፣ ለዚህም ነዉ ጎሰኝነትን አጥብቀን የምንዋጋዉ፣፣ ሰነዱም እነሆ።- የመድረኩ አዘጋጅ ከተሰብሳቢዎቹ የተሰጠዉ ጥያቄ እነ ጸጋይ በርሄን (ሃለቃ ፀጋይ) እና ዓባይ ወልዱን (ዓባይ ዴራ) እንዲመልሱት ባቀረበላቸዉ ጥያቄ ልጀምር። ጥያቄ፣- የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራር አባሎች የነበሩ በተፈጠረዉ ሁኔታ ከድርጅቱ ተባሯል፣፣ ሲባረሩ ለደህንነታቸዉ ጥበቃ፣ መኖርያ እና ደሞወዛቸዉን በሚመለከት የተወሰደ እርምጃ ካለ ብትገልጹልን? ዓባይ ወልዱ፣- …..ጥያቄዉ በተደጋጋሚ ለኛም ቢሆን ትግራይ ድረስ መቀሌ ድረስ ዉጭ የሚኖሩ አንዳንድ ወንድሞች ስልክ እየደወሉ ለምን ባዶ ሜዳ ላይ ያለምንም መተዳደርያ ጣላችሗቸዉ እያሉ ይጠይቁናል። ሁኔታቸዉን በሁለት መንገድ በመመለከት ዉሳኔ አድርገናል። አንደኛዉ ለደህንነታቸዉ ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ አስፈላጊነት ነዉ። ይኼዉም እንደምናየዉ “መጥፎ ትካል” (የተጠቀመበት ትግርኛ )/ (ከወያኔ ዉጭ ሌሎች “መጥፎ” ድርጅቶች/ቡድኖች) አደጋ እንዳያደርሱባቸዉ በማሰብ ጥበቃቸዉ ልክ እንደ ድሮዉ “ሴኪሪቲዉ” በቦታዉ እንዳለ ሆኖ “የትም ይኑሩ የትም ( የተግርኛዉ “አብዝሃለዉ ይሃሉዉ”) በሚኖሩበት አካባቢ ስጋት እንዳያድርባቸዉ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ጥበቃ ይደረግላቸዋል። ሁለተኛ “መኪኖቻቸዉ ተነጥቀዉ በእግራቸዉ እንዲጓዙ ተደርጓል” “መኖርያ ቤቶቻቸዉ ተነጥቀዉ አልባሌ ቦታ ወድቀዋል… ወዘተረፈ” የሚል እሮሮ እንሰማለን። ይሄ ለፕሮፖጋንዳ እንዲጠቀሙበት ራሳቸዉ የሚያወሩት ካልሆነ በስተቀር በእኛ በኩል የምናዉቀዉ እና የሚወራዉ ዉሸት ለየብቻ ነዉ። በጣም የሚገርመዉ በመንግሥት የተሰጣቸዉ መኪና እቤታቸዉ ግቢ ትተዉ በእግር ሲጓዙ የሚታዩበት ሁኔታ እኛም ታዝበናል። ይሄ ግን ሆን ብለዉ ራሳቸዉ ያደረጉት ነዉ። መኖርያ ቤት በሚመለከትም ከተጠበቀላቸዉ ከሌሎቹ ጥቅማጥቅሞች የተለየ አይደለም። መኖርያ ቤቶቻቸዉም ቢሆን ሁሉም ሲኖሩባቸዉ የነበሩት መኖርያዎች ሁሉ እንዲኖሩበት ተደረጓል።መኪናቸዉ፣መኖርያ ቤቶቻቸዉ የነበራቸዉ ጥበቃ እና ደሞዝ ከቦታዉ ላይ እንዳለ ነዉ ። ከሚኖሩባቸዉ ቤቶች አንድም ሰዉ ልቀቅ የተባለ የለም። እነሱም እንዲናፈስ የሚፈልጉት ወሬ ነዉ። ለምሳሌ እንቅስቃሴአቸዉን በሚመለከት ብንመለከትም፣ እንደማንኛዉም ዜጋ በነፃ የትም መዘዋወር መንቀሳቀስ ይችላሉ፣ እየተንቀሳቀሱም ነዉ። ወደ ፈለጉበት ቦታ/ አገር ስልክ መደወል ይችላሉ፣በፈለጉበት መዉጣት መግባት ዉጭ አገር መሄድ መመላለስ ችለዋል። እኛ የምናዉቀዉ ሙሉ ነፃነታቸዉ እቦታዉ ላይ እንዳለ ነዉ የምናዉቀዉ። አገር ዉስጥ ያለ ሰዉ በዓይኑ የሚያየዉ ጉዳይ ነዉ። ለምሳሌ ከዚህ ከዉጭ ወደ እኛ እየደወሉ”መኪኖቻቸዉ ደሞዛቸዉ መኖርያ ቤቶቻቸዉ ነጠቃችሗቸዉ! ለምን እንደዚህ ታደርጋላችሁ?” እያሉ ይደዉሉሉናል። ይህ ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ዉሸት ዉጭ አገር ላሉ ዜጎች ሆን ተብሎ እንዲራባ እና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀሙበት እንዳሉ ነዉ እንየተገነዘብን ያለነዉ። ስለዚህ ወሬዉ ዉሸት ነዉ። ኑሮአቸዉ ድሮ ከነበሩበት የተለወጠ ወይንም የተቀነሰ ነገር የለም። የመድረኩ አስተናጋጅ -ጥያቄ፣- ጓድ ፀጋይ! ጓድ ዓባይ ባለዉ ላይ ተጨማሪ ካለህ? ፀጋይ በርሄ.- ቡዱኑ (አንጃዉ) ከመገንጠሉ በፊት እያንዳንደቸዉ ሲኖሩበት ከነበረዉ ኑሮ የተቀነሰባቸዉ ነገር የለም፣፣ እንዳለ ነዉ፣፣ ጥበቃዉ፣መኖርያ ቤታቸዉ፣ደሞዛቸዉ እንዳለ ነዉ፣ አልተነካም፣፣ ለምሳሌ የገብሩ አስራትን ሁኔታ ብንመለከት “ወደ ሌላ ስራ ተዛዉሮ እንዲሰራ ሆኖ” ደሞዙም፣ጥበቃዉም፣ መኖርያዉም እንዳለ፣ እንደነበረ መሆኑ ይታወቃል፣፣ ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ በማሃሉ “መኖርያዉን ነጠቁት! የሚል ወሬ ተነዛ፣፣ ይህ ሲሆን ግን ለምሳሌ ገብሩ በቅርብ ጊዜ ከነበረበት መኖርያዉ ለቅቆ በራሱ ፍላጎት ወደ ሌላ መኖርያ ሄዷል የሚል ወሬ ሰምተናል፣፣ ገብሩ ከሚኖርበት መኖርያዉ “ዉጣ” ያለዉ ሰዉ ወይንም አካል የለም፣፣ በጥበቃዉም በኩል አሁን የምኖርበት መኖርያ ጠበብ ያለ ስለሆነ ከጠባቂዎቼ መርጬ የሚሰናበቱ አሰናብቼ የማስቀራቸዉንም አስቀራለሁ ብሎ ደህንነቱን ከሚጠብቁ የደህንነት ጥበቃ ዘቦቹ መሃል መርጦ የሚፈልጋቸዉ አስቀርቶ ያልፈለጋቸዉ ጠባቂዎቹን ያሰናበታቸዉ ሁኔታዎች አሉ፣፣ ስለዚህ ቦታ ጠበበኝ ወዘተ… እያሉ ራሳቸዉ ከሚኖሩበት ሁኔታ የሚለቁበት ሁኔታ እንዳለ እናዉቃለን፣፣ ያም ሆነ ይህ በዚህ በኩል እኛ የወሰድነዉ ቀና እርምጃ እነኚህ ሰዎች ባለፈዉ ትግል ዘመን ጓዶቻችን የነበሩ ናቸዉ፣ እንደሰዉ (እንደሰባዊ ፍጡርነታቸዉም) መጠንም እንዲጎዱ የሚፈልግ ግለሰብም ሆነ መንግሥት የለም፣፣ ስለዚህ አሁን የያዙት አካሄድ ግን ሕዝባችንና ድርጅታቸን የሚበትን አካሄድ ነዉ እየተከተሉት ያሉት፣፣ ስለሆነም፣ ሁለት አማራጮች አስቀምጠናል- አንደኛዉ አማራጭ አሁንም የነበረዉ ትግል ፈር ተከትለዉ ወደ ህዝባቸዉ እንዲመለሱ ወደ ሕሊናቸዉ እንዲመለሱ ፣ ከስህተታቸዉ ተምረዉ እንዲቀላቀሉና ልዩነታችንን ይዘን አብረን እንድንጓዝ የማድረግ ጥረታችን ይቀጥላል፣፣ ሁለተኛዉ አማራጭ- እኔ እንደምረዳዉ እየተከተሉት ያለዉን መንገድ ድርጅታችንና ሕዝባችንን ወደ አደገኛ ጉዞ የሚያስገባ ሁኔታ እተከተሉ ስለሆነ እንታገለዋለን፣፣ እየታዘብነዉ/እያስተዋልነዉ ያለዉ ግን የተዛባ የጨለማ ጉዞ ግን ይበልጥኑ ወደ ዉስጥ እየገቡበት እንዳሉ ነዉ እየታዘብነዉ ያለነዉ፣፣ ስለዚህ ከዚህ ጉዟቸዉ ወደ ቀና መንገድ እንዲመለሱ እንጥራለን፣፣ ያ ክልሆነ ግን ሕዝቡም ካድሬዉም መታገሉ የማይቀር ነዉ፣፣ እየታገላቸዉም ነዉ፣፣” በማለት የነገብሩ፣ ተወልደ ፣ አረጋሽ አዳነ፣ ዓለምሰገድ ገብራምላክና የመሳሰሉት ወያኔ ለሁለት ተከፍሎ ሲባረሩ አንደማንኛቸዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለ ምንም መጦርያ እንደሚባረረዉ ሳይሆን የነበራቸዉ ጥበቃ እና ክብር ከነ ደሞዛቸዉና ነጻ መኖርያ ተለግሶላቸዉ ነበር የተሰናበቱት፣፣ በኔ በኩል ይኼዉ የያዝኩትን ማሕደር ይሄዉና በእናንተ በኩል በጉዳዩ ተቹበት፣፣ጎሰኛ እርስ በርስ ምን ያህል መጨካከን እንደማያስችለዉ ይህ በቂ መረጃ ነዉ እንላለን፣፣ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

Tuesday, May 19, 2009

የሓሰት ሰነድ አቀናባሪዉ ደብረጽየን ገብረሚካኢል

የሓሰት ሰነድ አቀናባሪዉ ደብረጽየን ገብረሚካኢል (ከወያኔ የገበና ማሕደር) ጌታቸዉ ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
የህዝባዊ ሓርነት ወያነ ትግራይ መንግስት በማለት ራሱን የሚጠራ ለባዕድ አገሮች ያደረ ትግራይ ዉስጥ የተመሰረተ ጸረ ኢትዮጵያ ወራዳ ቡድን “ፕሮፌሰር-አስራት-ወልደየስን”የሐሰት-ክስ-በመመስረት-ባልሰሩትና-ባልተሳተፉበት ወንጀል ተሳትፈዋል በማለት “ከአራት ዓመት”በላይ አስሮአቸዉ በወቅቱ ሲታመሙ መታከም የሚገባዉን የሕክምና ደረጃ ምርመራ-ተነፍገዉ በመቆየታቸዉ ሕመማቸዉ ጠንቶባቸዉ መዳን እንደማይችሉ “ወያኔ” ሲያዉቅ፣ ሆን ብሎ ለፕሮፖጋንዳ ዉጭ አገር ሄደዉ እንዲታከሙ ከፈቀደ በሗላ ለሞት መዳረጋቸዉ ይታወቃል፣፣ በሃሰት የተወነጀሉበት ምስጢር በወያኔ ሲቀነባበር ድርጊቱ በዓይኑ የተመለከተዉ የቀድሞዉ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ታጋይ እና የወያኔ/ኢሕአዴግ የህዝብ ደህንነት ሰራተኛ “ፍስሃ ሃይለማርያም”-ምስጢሩን ለህዝብ ይፋ አዉጥቶ ወያኔንን ያጋለጠበትን የቃለ መጠይቅ “አዉዲዮ-ቪዲዮ” ለማየትና ለማዳመጥ ከበስተቀኝ በኩል የተለጠፈዉ ቪድዮ ይመልከቱ፣፣ ፍስሃ ሃይለማርያም ትዉልዱ ትግራይ ዉስጥ ተምቤን አዉራጃ ዓብይ ዓዲ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ማይ ሎሚን ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ነዉ የተወለደዉ፣፣ ወያኔ በመጨረሻዉ ሰዓትደርግን ለማሸነፍ ሲቃረብ በስለላ ስራ መድቦት ይህንኑ ስራዉ ሲያከናዉን ከቆየ በሗላ የደርግ ስልጣን ሲወገድ፣ ፍስሃ እና 20 የሚሆኑ የህወሓት አባላት ለስለላ ስልጠና ሱዳን አገር ተልከዉ ወደ 10 ወር ገደማ ሰልጥነዉ ሲመለሱ ፣ ፍስሃም በቀጥታ አዲስ አበባ ዉስጥ ተመድቦ ከ1984 እስከ 1992 ዓ.ም. በአገር ደህንነት መከላከያ በልዩ ጽ/ቤት ዋና መምርያ ሓላፈ ሆኖ ቆይቷል፣፣ ከስለላ ስራ ጎን ለጎንም የህወሓት መሰረታዊ ማሕበራት ዋና ጸሃፊም ነበር፣፣ ፍስሃ ሃይለማርያም ወያኔን ከድቶ ወደ ኤርትራ እጁን በመስጠት “የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ”(TPDM) ተብሎ በሚጠራ በኤርትራ ይደገፋል የሚባለዉ ጸረ ህወሓት ድርጅት መሪ ሆኖ ከቆየ በሗላ ምስጢሩ እስካሁን ለኛ ግልጽ ባልሆነ መንገድ “የላይኛዉ ጋሽ ባርካ” ተብሎ በሚጠራዉ የኤርትራ ድምበር አካባቢ “በወያኔ ክትትል እንደተገደለ ይነገራል፣፣ የአገዳደሉ ቅንብርና ምስጢር ለወደፊቱ ብዙ ምስጢር እንደሚወጣ ይጠበቃል፣፣” ለማንኛቸዉም በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተጠነጠነዉ የሓሰት ወንጀል እንዴት እንደተጎነጎነ እና ማንስ በዛዉ የፈጠራ ወንጀል ልዩ መሪ ሆኖ እንደተሳተፈ ምስጢሩ ከመሞቱ በፊት ከኤርትራ ሚዲያዎች በኩል የሰጠዉ የምስክርነት ቃል እነሆ፣፣ ቃሉ የተጨመረ ወይንም የተቀነሰ የለም፤ እንደወረደ ነዉ። “እኔ በዓይኔ ያየሁት አንድ ነገር ነበር! ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ አንድ ጊዜ በዚህ ደብረብርሃን እስረኞችን ለማስፈታት በተደረገዉ ኦፔረሽን ተሳትፈዋል ብሎ አስወንጅሎ ከባድ ፍርድ እንዲፈረድባቸዉ በማሰብ፣ ባገር ዉስጥ ሚኒሰትር ምክትል ሚኒስተር የነበረ ደብረጽየን ገብረሚካኤል የሚባል የሰረዉን ስራ እኔ በዓኔ ያየሁት ነበር፣፣ ፕሪፌሰር በዚህ ዓይነት ሕገ ወጥ ስራ ተሰማርተዋል ብሎ በታይፕ አርጎ ጽፎ፣ ፌርማቸዉን የፕሮፌሰር በሌላ ወረቀት የፈረሙት ፌርማ ኮፒ አደርጎ አስመስሎ በመፈረም እሳቸዉ ወደ እስርቤት ከገቡ በሗላ፣ ጽ/ቤታቸዉ የማአድ ጽ/ት እንዳለ ዘግቶ ማሕተም አምጥቶ አትሞ በቀጥታ እንደመስረጃ ብሎ ለፍርድ ቤት አቀረበዉ፣፣ ያ ወረቀት እንደ ዶክዩመንት ተቆጥሮ፣ ፍርድ ቤት ይሄ ጽሑፍ፣ የሄ ፌርማ፣ ይሄ ማሕተም የርስዎ ነዉ ብሎ….ምንም ባልፈጸሙት ወንጀል በእስር ቤት ተሰቃይተዉ ለሞት ተዳረጉ፣፣ እንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ግፍ እየተፈጸመ ይህ የታገልክበት ዓላማ በግልባጩ ሲተገበር እያህ…እኔ በግሌ ለሕሊናየ በጣም ቁስል ነዉ የፈጠረብኝ፣፣ በታሪክም ተጠያቂ የሚያደርግ ስለሆነ የነበረኝም ሁኔታ ከግምት ሳላስገባ የታገልኩለትን ዓላማ የትግራይ ህዝብ በመሆኔ ሌላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የታገለበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የተሰዉ ታጋዮች ወንድሞቻችንና ጓዶቻችን አደራ ያሉንን ዓላማ ከግብ እንዲደርስ ዳግም መታገሉን መረጥኩ፣፣”(ፍስሃ ሃይለማርያም -የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የስለላ ሰራተኛ፤ በሓላም “የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” ሽምጥ ተዋጊ ሊቀመንበር)
በዚህ ሁኔታ ነበር ፕሮፌሰር አስራት በሃሰት ተወንጅለዉ ለሞት ተዳረጉት። ወያኔም ሆን ብሎ ፍስሃን ተከታትሎ እንዲገደል ያስደረገበት ዋናዉ ምክንያት ይህ በጣም አስገራሚ ጉድ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ስላጋለጠዉ እና ለወደፊቱም ፍስሃ በምስክርነት እንዳይቀርብ ባጭሩ ህይወቱ እንዲቀጭ አደርጎታል። ፍስሃ ሃይለማርአም ስጋዉ ቢሞትም ቃሉ ህያዉ በመሆኑ የወኔ ጥይት የማይሞት የምስክርነት ቃሉን መግደል አይቻለዉም።/-/www.Ethiopiansemay.blogspot.com

የሓሰት ሰነድ አቀናባሪዉ ደብረጽየን ገብረሚካኢል

የሓሰት ሰነድ አቀናባሪዉ ደብረጽየን ገብረሚካኢል (ከወያኔ የገበና ማሕደር) ጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com
የህዝባዊ ሓርነት ወያነ ትግራይ መንግስት በማለት ራሱን የሚጠራ ለባዕድ አገሮች ያደረ ትግራይ ዉስጥ የተመሰረተ ጸረ ኢትዮጵያ ወራዳ ቡድን “ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን” የሐሰት ክስ በመመስረት ባልሰሩትና ባልተሳተፉበት ወንጀል ተሳትፈዋል በማለት “ከአራት ዓመት” በላይ አስሮአቸዉ በወቅቱ ሲታመሙ መታከም የሚገባዉን የሕክምና ደረጃ ምርመራ ተነፍገዉ በመቆየታቸዉ ሕመማቸዉ ጠንቶባቸዉ መዳን እንደማይችሉ “ወያኔ” ሲያዉቅ፣ ሆን ብሎ ለፕሮፖጋንዳ ዉጭ አገር ሄደዉ እንዲታከሙ ከፈቀደ በሗላ ለሞት መዳረጋቸዉ ይታወቃል፣፣ በሃሰት የተወነጀሉበት ምስጢር በወያኔ ሲቀነባበር ድርጊቱ በዓይኑ የተመለከተዉ የቀድሞዉ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ታጋይ እና የወያኔ/ኢሕአዴግ የህዝብ ደህንነት ሰራተኛ “ፍስሃ ሃይለማርያም” ምስጢሩን ለህዝብ ይፋ አዉጥቶ ወያኔንን ያጋለጠበትን የቃለ መጠይቅ “አዉዲዮ-ቪዲዮ” ለማየትና ለማዳመጥ ከበስተቀኝ በኩል የተለጠፈዉ ቪድዮ ይመልከቱ፣፣ ፍስሃ ሃይለማርያም ትዉልዱ ትግራይ ዉስጥ ተምቤን አዉራጃ ዓብይ ዓዲ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ማይ ሎሚን ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ነዉ የተወለደዉ፣፣ ወያኔ በመጨረሻዉ ሰዓትደርግን ለማሸነፍ ሲቃረብ በስለላ ስራ መድቦት ይህንኑ ስራዉ ሲያከናዉን ከቆየ በሗላ የደርግ ስልጣን ሲወገድ፣ ፍስሃ እና 20 የሚሆኑ የህወሓት አባላት ለስለላ ስልጠና ሱዳን አገር ተልከዉ ወደ 10 ወር ገደማ ሰልጥነዉ ሲመለሱ ፣ ፍስሃም በቀጥታ አዲስ አበባ ዉስጥ ተመድቦ ከ1984 እስከ 1992 ዓ.ም. በአገር ደህንነት መከላከያ በልዩ ጽ/ቤት ዋና መምርያ ሓላፈ ሆኖ ቆይቷል፣፣ ከስለላ ስራ ጎን ለጎንም የህወሓት መሰረታዊ ማሕበራት ዋና ጸሃፊም ነበር፣፣ ፍስሃ ሃይለማርያም ወያኔን ከድቶ ወደ ኤርትራ እጁን በመስጠት “የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ”(TPDM) ተብሎ በሚጠራ በኤርትራ ይደገፋል የሚባለዉ ጸረ ህወሓት ድርጅት መሪ ሆኖ ከቆየ በሗላ ምስጢሩ እስካሁን ለኛ ግልጽ ባልሆነ መንገድ “የላይኛዉ ጋሽ ባርካ” ተብሎ በሚጠራዉ የኤርትራ ድምበር አካባቢ “በወያኔ ክትትል እንደተገደለ ይነገራል፣፣ የአገዳደሉ ቅንብርና ምስጢር ለወደፊቱ ብዙ ምስጢር እንደሚወጣ ይጠበቃል፣፣” ለማንኛቸዉም በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተጠነጠነዉ የሓሰት ወንጀል እንዴት እንደተጎነጎነ እና ማንስ በዛዉ የፈጠራ ወንጀል ልዩ መሪ ሆኖ እንደተሳተፈ ምስጢሩ ከመሞቱ በፊት ከኤርትራ ሚዲያዎች በኩል የሰጠዉ የምስክርነት ቃል እነሆ፣፣ ቃሉ የተጨመረ ወይንም የተቀነሰ የለም፤ እንደወረደ ነዉ። “እኔ በዓይኔ ያየሁት አንድ ነገር ነበር! ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ አንድ ጊዜ በዚህ ደብረብርሃን እስረኞችን ለማስፈታት በተደረገዉ ኦፔረሽን ተሳትፈዋል ብሎ አስወንጅሎ ከባድ ፍርድ እንዲፈረድባቸዉ በማሰብ፣ ባገር ዉስጥ ሚኒሰትር ምክትል ሚኒስተር የነበረ ደብረጽየን ገብረሚካኤል የሚባል የሰረዉን ስራ እኔ በዓኔ ያየሁት ነበር፣፣ ፕሪፌሰር በዚህ ዓይነት ሕገ ወጥ ስራ ተሰማርተዋል ብሎ በታይፕ አርጎ ጽፎ፣ ፌርማቸዉን የፕሮፌሰር በሌላ ወረቀት የፈረሙት ፌርማ ኮፒ አደርጎ አስመስሎ በመፈረም እሳቸዉ ወደ እስርቤት ከገቡ በሗላ፣ ጽ/ቤታቸዉ የማአድ ጽ/ት እንዳለ ዘግቶ ማሕተም አምጥቶ አትሞ በቀጥታ እንደመስረጃ ብሎ ለፍርድ ቤት አቀረበዉ፣፣ ያ ወረቀት እንደ ዶክዩመንት ተቆጥሮ፣ ፍርድ ቤት ይሄ ጽሑፍ፣ የሄ ፌርማ፣ ይሄ ማሕተም የርስዎ ነዉ ብሎ….ምንም ባልፈጸሙት ወንጀል በእስር ቤት ተሰቃይተዉ ለሞት ተዳረጉ፣፣ እንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ግፍ እየተፈጸመ ይህ የታገልክበት ዓላማ በግልባጩ ሲተገበር እያህ…እኔ በግሌ ለሕሊናየ በጣም ቁስል ነዉ የፈጠረብኝ፣፣ በታሪክም ተጠያቂ የሚያደርግ ስለሆነ የነበረኝም ሁኔታ ከግምት ሳላስገባ የታገልኩለትን ዓላማ የትግራይ ህዝብ በመሆኔ ሌላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የታገለበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የተሰዉ ታጋዮች ወንድሞቻችንና ጓዶቻችን አደራ ያሉንን ዓላማ ከግብ እንዲደርስ ዳግም መታገሉን መረጥኩ፣፣ ” (ፍስሃ ሃይለማርያም -የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የስለላ ሰራተኛ፤ በሓላም “የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” ሽምጥ ተዋጊ ሊቀመንበር)
በዚህ ሁኔታ ነበር ፕሮፌሰር አስራት በሃሰት ተወንጅለዉ ለሞት ተዳረጉት። ወያኔም ሆን ብሎ ፍስሃን ተከታትሎ እንዲገደል ያስደረገበት ዋናዉ ምክንያት ይህ በጣም አስገራሚ ጉድ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ስላጋለጠዉ እና ለወደፊቱም ፍስሃ በምስክርነት እንዳይቀርብ ባጭሩ ህይወቱ እንዲቀጭ አደርጎታል። ፍስሃ ሃይለማርአም ስጋዉ ቢሞትም ቃሉ ህያዉ በመሆኑ የወኔ ጥይት የማይሞት የምስክርነት ቃሉን መግደል አይቻለዉም።/-/www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Saturday, May 16, 2009

ለእኔ ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ የኖረች አገር አይደለችም

ለእኔ ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ የኖረች አገር አይደለችም ለፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የመት ዓመት መዘክር የተዘጋጀ ዓምድ ጌታቸዉ-ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ ፕሮፌሰር ዶ/ር አስራት ወልደየስ ከተናገሯቸዉ ጠቃሚ ንግግሮች ለጻፍትና ለታሪክ ተመራማሪዎች እንዲሁም ለአንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በየሳምንቱ በጥቅስ አቀርብላችሗለሁ። በጣም አስገራሚና ጠቃሚ ንግግሮቻቸዉ እንድታነብቧቸዉ እጋብዛለሁ። ወደ ዋናዉ ርዕስ ከማምራታችን በፊት ከኢትዮጵያን ረጅስተር በእንግሊዝኛ ቋንቋ ካደረጉት ቃለ ምልልስ ያነበብኩትነ በጥቅስ ጠቅሼ ልለፍ። “…It is not only many other opposition parties, but also the TPLF/EPRDF that supports a federal state structure. Western government, too, support and advance such a form of government. Federalism is a burden that is being imposed on the people by those who claim to know what is best for us, and this is being done without assessing the advantage and disadvantage of federalism or without the Ethiopian people expressing their wish. If the west had advocated a monarch form of government and Mr. Paul Henze had written an article on this, the agenda would be different today. The foundation of federal structure is a nation divided along linguistic, ethnic, and religious lines in the name of democracy. We believe that a federal structure of regional administrations that are based on national unity, sovereignty, equality, economic and social benefits, and popular consent will be useful for advancement. But installing a federal government without foundation and especially at a time Ethiopia is being wrecked is like constructing a house in the midst of a violent earthquake. Even the much-lauded American federal system of government had to engage in civil war to ensure national unity…” ፕሮፌሰር አስራት በወያኔ የዉሸት ዉንጀላ ተወንጅለዉ ለጨካኝ እስር ተዳርገዉ ለሕይወታቸዉ ሕልፈት ምክንያት ሆኖ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰዉ እንድታጣ ሆኗል። “ለእኔ ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ የኖረች አገር አይደለችም” በማለት የተናገሩት የወያኔ እስርኛ ሆነዉ እስር ዉስጥ እያሉ ታመዉ ሕክምና ተነፍገዉ ለረዢም ጊዜ ከቆዩ በሗላ ሕመማቸዉ እየበረታ ሲሄድ በጠና በመታመማቸዉ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለሕክምና ተወስደዉ ሆስፒታሉ ዉስጥ ተኝተዉ በሕክምና ላይ እንዳሉ አሜሪካን አገር ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘዉ አንድ ኢትዮጵያ የተባለዉ “አፍቃሬ ወያኔ/ኢሕአዴግ”ራዲዮ በተኙበት ሆስፒታል ክፍል ዉስጥ በመግባት ካደረገላቸዉ ቃለ ምልልስ የሰነዘርዋቸዉ አንዳንድ ጠቃሚ ሃሳቦች ዋና ዋናዎቹን አቀርብላችሗለሁ። አገር ወዳዱ አረጋዊዉ ፕሮፌሰር ቃለ መጠይቁ ሲያደርጉ ኢሕአዴግ መላ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ልክ ሰባት ዓመት ሆኖት ነበር። ያኔ ከሰባት ዓመት በፊት ሰኔ ዉስጥ ኢሕአዴግ ባዘጋጀዉ ኮንፈረንስ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲን ወክለዉ በመገኘት በኢትዮጵያ ላይ የታለመዉን የመገንጠል አደጋ ብቻቸዉን በቆራጥነት በመቃወም ተጋፍጠዋል። በወቅቱ ጦቢያ ጋዜጣ ቀጠሮ በሚል ዓምዱ ላይ ቃለ መጠይቁን በሚመለከት እንዲህ ሲል ዘግቦት ነበር “ …በኮንፈረንሱ ላይ በቆራጥነት ሲቃወሙት የነበረዉን የፈሩት የጎሳ ፖለቲካም አገሪቱ በማመሱ በአማራዉ ሕዝብ ለይ ደረሰዉን አደጋ በሰላማዊ ትግል ለመከላከል ወደ ፖለቲካዉ ዓለም ገቡ። ከአራት ዓመት በፊት “ለጦርነት የሚያስነሳ ንግግር አድርገሃል”-በመባል ወህኒ ተጥለዉ ይገኛሉ።የጤና እና የዕድሜ ጫና ሳይበግራቸዉ አሁን፣ም ለሚወዷት አገራቸዉ እየተጨነቁ ናቸዉ።በርካታ ኢትዮጵያዉያን፣የዓለም ሕብረተሰብና የሰብኣዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅቶች እኒህን አገር ወዳድ አረጋዊ ከእስር እንዲፈቱ ቢጪኹም ሰርዓቱ ርህራሄ አላሳየም። ከሰባት ዓመት በፊት የተቃወሙትና የፈሩት የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕጋዊነት የሌለዉ ፍቺ አገሪቱን ባስጨነቀበት ሰዓት ሰባኛ ዓመታቸዉን በርካታ ዓመታት ባገለገሉበት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተኝተዉ ሲተክዙ አሜሪካ ዉስጥ ዋስንገተን የሚገኘዉ “የአንድ ኢትዮጵያ”-ድርጅት ሪፖርተር አልጋቸዉ ድረስ ገብቶ ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። እኛም የፕሮፌሰር አሥራት ወልዴስን ቃለ ምልልስ በአሜሪካን አገር ከተሰራጨዉ ራዲዮ በማግኘት የመጀመሪያዉን ክፍል ለ አንባቢዎቻችን ስናቀርብ ለፕሮፌሰሩ ጤናን፣ ለአሠራቸዉ አካልም ልቦና እንዲሰጣቸዉ እየተመኘን ነዉ። አንድ ኢትዮጵያ፣- ኢትዮጵያ ከሦስት ሺህ ዓመት በላይ ታሪክ ያላት ሀገር ናት። የዓለም ታሪክ የመዘገበዉ ሀቅ ይህ ሆኖ ሳለ እድገቷ ሗላ-ቀር ሊሆን የቻለዉ በምን ምክንያት ይመስለዎታል? ፕሮፌሰር አስራት፣- የኢትዮጵያ ዕድገት ሗላ ቀር ነዉ የምንለዉ ያሁኑኑ ዘመናችንን ወይም ያለፉትን ጥቂት ዓመታት በመገንዘብ ነዉ። ሆኖም አዋቂዎች ጭምር በዓለም ደረጃ ሗላ ቀርነቷ ቢመሰክሩም በበኩሌ ኢትዮጵአን ሗላ ቀር ብየ የምመዘግባት አይደለችም። ለምሳሌ ቶይንቢ የሚባለዉ የዓልመ ታሪክ ሊቅ ስለ አፍሪካ ታሪክ በጻፈበት ጊዜ “ኢትዮጵያ ዓለምን በመርሳትና በዓለም በመረሳት አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ ኖራለች።”ብሏል-"ለኔ ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ የኖረች አገር አይደለችም። ኢትዮጵያ አጋጣሚ ሆኖ ብዙ መሰናክሎች በታሪኳ እያጋጠሟት ብዙ የዉጭ ጠላቶች እያደከሟት፣ እየተነሳች እየቆመች በመምጣቷ እርግጥ በአሁኑ ጊዜ ሗላ ቀር ከተባሉ አገሮች ተራ ተሠልፋለች። እስከ አስራስድሰተኛ ክፍለ ዘመን በማያጠራጥር ሁናቴ የኢትዮ ጵያ እንቅስቃሴና ዕሰድገቷ ከአብዛኛዉ ከአዉሮፓ አገሮች እንኳ የማይተናነስ ነበር።ነገር ግን በገራኝ ወረራ …..። (ይቅርታ ቅጁ ከጋዜጣዉ ህትምት ስህተት ሳይታተም ተቋርጣል፣) አንድ ኢትዮጵያ፣- ለኢትዮጵያ ምን ዓይነት አስተዳደር የሚበጃት ይመስለዎታል? ፕሮፌሰር አስራት፣- ዛሬ አስተዳደር ስንል አስተሳሰብ ማስገባት ያለብን ይመስለኛል። በዚህ መሠረት አንድ ቁንጽል የሆነ የዚህ ዓይነት አስተዳደር ብል ትርፉ አለመግባባት ብቻ ይሆናል። መሠረት መሆን ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱ ማነዉ? ባለዉ ሁኔታ ዉስጥ ፍላጎቱና ችግሩ ምንድነዉ? ብሎ ለራሱ ተስፋ ለራስ በራሱ ልክ የሚሆንና ደግፎ ሚያስኬደዉ ዓይነት አስተዳደር መመሥረት አለበት። እንጂ እንዲያዉ ዝም ብለን ከአንዱ ጎራ ብቻ አምጥተን በፈረንጅ ቋንቋ እንናገራለን፣እናነባለን ብለን ያንን ወስደን ፈረንጅ አገር በተሠራ መሣሪያ እሱን አስገድደን እላዩ ላይ ስንችንበት የሚገኘዉ ዉጤት ታይቷል። ባለፈዉ ሰላሰ ዓመታት ይህንን ነዉ ስናይ የኖርነዉ። ይሄ አይመስለኝም ትልቁ ነገር።አፍሪካዉያን እንኳ በያሉበት በልባቸዉና በጉጉት ሲጠብቁን የኖሩት ሁሉንም ሞክረዉ ስላቃታቸዉና ስላልሆነላቸዉና ስላልበጃቸዉ እንደ ኢትዮጵያ ያለች ጥንታዊት አፍሪካዊት አገር መሀላችን እያለች እርሷ እኮ ምስጢሩን ይዛ ይሆናል የሚል ጉጉት ነበራቸዉ። ብዙዎቹን ሳገኛቸዉና ሳነጋግር ይሄ ምኞት በዉስጣቸዉ ይገኛል። ግን እኛ በበኩላችን የበለጠ ዝም ብሎ የፈረንጅ ስም በመከተል የምናመጣዉና በኢትዮጵያ ህዝብ የምንጭነዉ ነገር ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎሉበት አልሆነም።በተሠራበት አገር እንኳ ሊሠራ ያልቻለ ለስሙ ብቻ “እዛ ዲሞክራሲ ሲወራ ነበር፣ እዚህኛዉ የሶሻሊስት ይሠራ ነበር፣- እያልን የማይሠራዉን አምጥተን ህዝቡ ላይ በግድ በመጫናችን ሥርዓት ያጣንና ምንም ለአገራችን ማመንጨት የማንችል ሆነን ተገኝተናል። አሁን ሁሉንም ሞክረነዋልና እኔ በበኩሌ ከኢትዮጵያ ሰዉነት ጋር የሚሄድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር፣ከሁሉም ሕዝብ ጋር የሚሆንና የሚያራምደዉን ዓይነት ሥርዓት ዓላማ ነዉ ማስማማት ያለብን። አንድ ኢትዮጵያ፣- ኢትዮጵያን በዘር መከፋፈሉ አንድነቷን ያጠናክራል ወይንስ ይበታትናል ይላሉ? ፕሮፌሰር አስራት፣- በእኔ እምነት ብቻ ሳይሆን የትም ሥፍራ የታየ ነዉ። ለኢትዮያ ምንም አይበጃትም። የሚበታትናት እንጂ አንድነቷን የሚጠብቅ ነዉ ብየ አላምንም።ሩቅ እንኳ መሄድ ሳያስፈልገን እዚቺዉ ቅርባችን ወደ ደቡብ ብንሄድና ሱማሌዎችን ብንወስድ ይህን ያህል የሚለያዩበት ምንም ነገር የላቸዉም። አንድ ቋንቋ አንድ ባሕልና አንድ ሃይማኖት ቢኖራቸዉም እዚያች ዉስጥ በቁንጽል በጎሳ እንለያያለን ብለዉ ፍርክስክሳቸዉ ወጥተዋል። ወደ ሰሜን የሄድን እንደሆነ. ኤርትራን አንደምሳሌ መዉሰድ ይቻላል። እዚያ በምንም ዓይነት በጎሳ አይለያዩም።ጎሳ ማለት ይለያየናል ፣ያፈርሰናል ብለዉ እነሱ ጎሳን የማይቀበሉ ናቸዉ።ከላይም ከታችም ያሉት ጥሩ ምሳሌዎቻችን ሆነዉን እያለ ነዉ ጎሳ ይበጀናል የምንለዉ።እርግጥ በበኩሌ ጊዜያዊ አድርጌ ነዉ የምወስደዉ። ይህን ያሉት ወገኖች ለኢትዮጵያ ይበጃል ብለዉ ሳይሆን በአንድ በኩል የዉጪ ግፊትም አለበት። ሌላዉ ደግሞ በዚህ አመካኝቶ የተረሳን አካባቢ ለመጥቀም እንዲያመች የተደረገ ነዉ። አንድ ኢትዮጵያ፣- ፓርቲዎች ተለያይተዉ የየበኩላቸዉን ፕሮግራም ማካሄድ ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጎዳና ይጠቅማል ወይስ ሁሉም ለአንዲት ኢትዮጵያ የሚያስቡ ከሆነ ባንድነት ተወሃደዉና ተጠናከረዉ ቢሰሩ ይመረጣል?ከዚሁ ጋር በቅርቡ ፓሪስ ላይ ለሚሰበሰበዉ የተቃዋሚዎች ጉባኤ አባታዊ ምክር አለ? ፕሮፌሰር አስራት፣- እኔ እዚያ ለተሰበሰቡት ለማስተማር አልችልም። እንዳልሁህ ላለፉት ዓመታት ከሁሉ ነገር የተገለልሁና ተጨባጭ መረጃዎች የሌሉኝ ስለሆነ የእኔ ሃሳብ ለእነሱ አስተላልፋለሁ ብየ እንኳ አልሞክርም።ግን አንዳንድ ሃሳብ ልሰነዝር እችላለሁ። በየጊዜዉ አነብባለሁ፣እሰማለሁም። ኢትዮጵያዉያን ባንድ ድርጀት ወይም ባንድ ስብሰባ ባለመሰብሰባቸዉ ምክንያት ወቀሳ ከያለበት ይሰነዘራል::ይህንን እኔ በበኩሌ የምደግፈዉ አይደለም።ምን ተይዞ ጉዞ! አባቶቻችን “ድር ብያድር አንበሳ ያስር”ብለዋል። ድር ቢያብር አንበሳ የሚያስር እኮ እያንዳንዷ ድር ደንበኛ ድር ስትሆን ነዉ። እንዳዉ ዝም ብለዉ አጥመልምለዉ ቢሰበስቡት አበረ ማለት አይደለም። በተፈጠረዉ አዲስ የኢትዮጵያ ሁኔታ ዉስጥ ድርጅቶች መቋቋም አንዳንድ ጂምናስቲክ መስራት፣መፍጨርጨር ራሱ ለኢትዮጵያ አዲስ ነዉ።አንዳንዱ ድርጅት ለምሳሌ ፣ሁለት ሦስት ሰዉ ብቻ ያለበት ነዉ በድርጅት ስም የተቀመጠዉ።አሁን ያ ተጨፍልቆ እንድ ድርጅትስ ቢሆን ጠነከረ ማለት ነዉ? እያንዳንዷ ድር ሲጠነክር ነዉ ሕብረቱ የሚጠነክረዉ። ስለዚህ ያ ሲጨፈለቅ ምንድ ነዉ የሚሆነዉ?ልክ ከአንድ ድርጅት የማይሻል ጥርቅም ይሆናል። ምክንያቱም የሙከራ ባሕል የለዉም።ስለዚህ የግለሰቦች ጥርቅም ይሆንና ተመልሶ እዚያዉ ነዉ ። እኔ በበኩሌ በበጎን አላየዉም።ሲበስል ችግሩ ሲደርስ የኛ መተባበር የግድ ይመጣል።ከተቻለማ የኛ ትብብር ነገ ጥዋት ቢፈጠር ጥሩ ነበር።በተጨባጭ ስናየዉ ግን ባዶ ነዉ። ስለዚህ አሁን ያለዉ ሁኔታ ለዚህ አመችቶ አላየዉም። አሁን የኤርትራ ሁኔታ የተፈጠረዉን እንመልከት፣-ህዝቡ ማንም ሳይጠራዉ ከያለበት በገራ ተነስቷል፣ ችግሩን ለመቋቋም ጠንካራ ገመድ መሆን የሚችለዉ እያንዳንዱ የራሱን ጥንካሬ ሲጠብቅ ነዉ። ስለዚህ በያለበት ጥረት በዉነቱ ጥሩ ነዉ። ስለዚህ እየተገናኙ መወያየት፣ በሃሳብ መፋጨት እንደዚህ ያለዉ ባህል እንዲጠነክር ማድረግ አለበት። አንድ ኢትዮጵያ፣- መገንጠልን ከመሠረቱ በጥብቅ እንደሚቃወሙ እናዉቃለን ይቀጥላል ዛሬ በኢትዮጵያ የሚታየዉ ሁኔታ ወደ የት እንደሚያመራ ቢገልጡልን? ፕሮፌሰር አስራት፣- አዎ እኔ በበኩሌ መቼም ይህንን የመገንጠል ነገር ለማንሳት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ኢሕአዴግ ባዘጋጀዉ የመጀመሪያዉ የሰኔ ኮንፈረንስ ላይ ተካፍየ ነበር።የተካፈልሁበትን ጉዳይ ይህን ያህል አዉቃለሁ ብየ አይደለም። ግን በወቅቱ ያጋጠሙኝ ልቋቋመዉ ያልቻልሁት ሆኖ ስላገኘሁት በዚያዉ ላይ የመገንጠል ነገር ተነሳ። የኤርትራ መገንጠል እንዲሁም ደግሞ አዝማሚያዉ የሌሎችንም መከተል ፍራቻ ስለነበር በተቻለ መጠን የኢትዮጵያ አንድነት የሚጠበቅበትና በኤርትራ የነበረ ችግር እንዳለ እንዲታረም እንጂ ዞሮ ዞሮ ኢትዮጵያን ወደ ማፈራረስ እንዳይኬድ የኢትዮጵያን አንድነት የሚጠበቅበት ሁናቴ እንዲፈጠር አሳስቤ ነበር። ነገር ግን አዝማሚያዉ ስላላማረኝ “ኤርትራ ትገንጠል ከተባለ አገነጣጠሏ በደምብ በሕግ ስርዓትና በ አስተዳደር በሚገባ አንዲሰራ የመለያየቱ ፍቺ በደንብ እንዲፈጸም አለበለዚያ መዘዝ ነዉ የሚመጣዉ። በማለት በዚያን ጊዜ ተናግሬ ነበር። ይህም አነጋገሬ ነበር ሰዉ ጥርስ ዉስጥ አስገብቶኝ አስከዛሬ ድረስ ለማየዉ ፍዳ አስተዋጽኦ ያደረገዉ። አሁን የተከሰተዉ ነገር ታይቶኛል ብየ እንኳን ባልል ነገር ግን ፍጹም ከፍተኛ ችግር እንደሚፈጠር አምኜበት ነበር። ምክንያቱም አገር ይቅርና ሁለት ባልና ሚስቶች ተፋትተዋል ከተባለና ተድበስብሶ ከታለፈ ነገ ጠዋት መነታረካቸዉ አይቀርም። ያ ንትርክ ደግሞ መዘዙ እየተባዛ እንጂ እየበረደ አይሄድም።የፈራሁት በሁለቱ መካከል ከፍተኛ ቅራኔ የተፈጠረ እንደሆነ የዚያ ቅራኔ ዉጤት ዘላቂ የሆነ ጥላቻ ነዉ በማለት ነዉ። ባልና ሚስት እንኳ ደህና ሕጋዊ ፍቺ ከፈፀሙ እንኚህ ሰዎች አልተጣሉም። እንደገና ሊታረቁ ይችላሉ። የዚያን ጊዜ ፍቺዉ ካልቀረ በደንብ ይሠራ ያልሁበት ዋናዉ ምክንያት ኤርትራዉያን ተገንጥለዉ ሲያዩት የሚለያዩበት ምክንያት አያስፈልግም በሚሉበት ጊዜ ተመልሶ ለመዋሃድ የሚያሳፍራቸዉ ነገር አይኖርም ። ኢትዮጵያዉያኖችም እንደዚሁ። ይህን በማሰብ ነዉ። www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Tuesday, May 12, 2009

ቤተ መንግሥትም ቤተክህነትም በምንደኞች ይመራሉ

ቤተ መንግሥትም ቤተክህነትም በምንደኞች ይመራሉ
( ትችቴ በአቶ ኤፍሬም ማዴቦ)
ከጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com
ይህ ትችት ለኢትዮሜድያ አዘጋጅ በደብዳቤ መልክ ለአንባቢዎች እንዲነበብ በግማሽ ገጽ ቀለል ባለ ምዕዳን /ትችት ልኬ እንደዘወትሩ አዘጋጁ ካልወደዱት አንባቢዎቻቸዉ ትችቱን የማንበብ ዕድል እና መብቱ ታግደዋልና በደብዳቤ መልክ የተላከዉ ትችት ሰፋ ባለ መልኩ እንዲቀርብ በመወሰን ሰፋ ባለ መልኩ አቅርቤዋለሁ። እነሆ። ቅንጅትን በማፈራረስ እና በዉጭ ያለነዉ ኢትዮጵያዊያንን በማራራቅ ከፍተኛ ሚና የተጫወተዉ ካገር ፈርጥጦ አሜሪካ እና ለንደን መቀመጫቸዉ ባደረጉ ጥቂት ግለሰቦች የሚመራ ለዉጥን ባጭር ጊዜ በብረት ታግየ አዲስ ስርዓት አመጣለሁ የሚለዉ ግንቦት 7 የተባለዉ አዲስ ድርጅት፣ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ዉስጥ በጠራዉ ስብሰባ በእንግዳነት ይሁን ወይንም በአባልነታቸዉ፣ በመድረክ ተናጋሪነት ከጠሩት ሰዎች መሃከል አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ዳኛ ፍረህይወት ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አቶ ሙሉነህ እዮኤል ተባሉ ሲሆኑ ፣ የእለቱ የመድረክ አዘጋጁ አቶ አበበ በለዉ ነበር ። በወቅቱ ተነጋሪዎቹ ለተሰብሳቢዎቻቸዉ-ያቀረቡት-ንግግርበአዉዲዮድምጽተቀርጾ “www.Ethiomedia.comየህዋ ሰሌዳ ተለጥፎ ሕዝቡ እንዲያደምጠዉ ቀርቦ ነበር። እኔም አድመጬዉ- ከተናጋሪዎቹ አንዱ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ያቀረቡትን ሃይመኖትና ፖለቲካን በሚመለከት ባቀረቡት ንግግር/ትችት ላይ አንድ ለማለት እፈልጋለሁ። አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ብዙዎቻችሁ ጽሁፎቻቸዉ ካሁን በፊት አንብባችሗልና አዲስ እንግዳ አይሆኑባችሁም ብየ እገምታለሁ። አቶ ኤፍሬም የሚከተሉት ሃይማኖት የየትኛዉ አማኒ ወይንም የሃይማኖት ሰባኪ ወይም የሃይማኖት ምሁር ይሁኑ አይሁኑ ባለዉቅም ፖለቲካ እና ሃይመኖትን በሚመለከት አንስተዉ የተቹባቸዉ ጉዳዮች አብዛኛዉ እሳቸዉ ስማቸዉ ባልጠቀሱዋቸዉ “ሦስቱ ሃይማኖቶች”በሚሉዋቸዉ ላይ ጠንከር ያለ የተዛባ ወቀሳቸዉ ሲያነጣጥሩ “የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያንን”ግን በበጎ አርአያነት ሲያሞግሷት ተደምጠዋል። በተለይም ትችታቸዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ያነጣጠረ በመሆኑ እኔም የዚሁ ሃይማኖት ተከታይ በመሆኔ ቅሬታየን በተቹት ላይ ለማቅረብ መብቴ ነዉና አብረን አንመለከት። አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እስኪ ከተናገሩት አንዳንዶቹን መበጥቀስ ለ አንባቢዎቼ ላስነብብና ልተችበት።ስጠቅስ እሳቸዉ ባቀረቡት ቃላት እና አባባል ቃል በቃል ነዉ። አንዳንድ ቦተዋችም አባባለቸዉ ግልጽ ለማድረግ በቅንፍ ስተች ታነብቡኛላችሁ። ልጥቀስ፣- “…ኢትዮጵያ ዉስጥ የሃይመኖት ነፃነት/ኢንዲፔንደንስ አለመኖሩ ነዉ። ለምሳሌ በ2005 (በፈረንጅ አቆጣጠር) ሠልፍ በወጣበት ጊዜ ትናንሽ ልጆች በጥይት እሩምታ ሸሽተዉ ያመለጡበት አካባቢ እንዱ የቤተክርስትያን አካባቢ ነበር። እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲፈጸም እጅዋን ዘርግታ ምትቀበል ቤተክርስትያን ነች። ነገር ግን ባወጣ ያዉጣ ብላ የጥይት እሩምታ የሚወርድባቸዉ ልጆች…አጋልጣቸዋለች። ይህ ሲፈጸም የሃይማኖት መሪዎች ማዉገዝና ፊት ለፊት ሲገባቸዉ፣ይሀንን ማድረግ አልቻሉም። በተሌይም ሦስቱ ትላልቆቹ የሃይማኖት ድርጅቶች ይህንን ማድረግ አልቻሉም።…” አቶ ኤፍም ንግራቸዉን በመቀጠል“…ፊት ለፊት በግልጽ ጥፋት ተፈጽሟል በግልጽ፣ የተናገረችዉ አንዲት ብቻ “የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ብቻ ናት”። ይሄ ደግሞ እንዲሁ ብቻ አይደለም።ምክንያቱም በኢትዮጵያ ዉስጥ ነፃነት ያላት ድርጅት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ብቻ በመሆኗ ነዉ።ምክንያታዩም …ጳጳሱ የፈለጉት ቢናገሩ (የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ጳጳስ ማለታቸዉ ነዉ)፣ ነገ ጳጳስ አይደሉም። ይወርዳሉ ካቶሊክ ቤተክርስትያን በሚመለከት ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ካርዲናል ሊሾምባቸዉ አይችልም። ካርዲናል ሊሾምባቸዉ የሚችለዉ አንዲት ቫቲካን ብቻ ነች። ያንን “እንዲፔንደንት”ተጠቅመዉ ድምጻቸዉን አሰምተዋል። ስለዚህ ነፃነት እንዴት ዓይነት የድምፅ ማስሰሚያ ሃይል መሆኑ ያሳየናል። ይህ ሃይል ነዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የታመቀዉ።የሃይማኖት መሪዎች ሚናቸዉ ሊጫወቱ ያልቻሉበት ምክንያት (ይሄ ነዉ)።” ብለዋል። ወንድም አቶ ኤፍሬም ( ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንደ ጥንቱ በግብፅ እጅ አዙር አገዛዝ አይነት “ድፔንዳንት/ጥገኛ በመሆን”በዉጭ ሃይል ጳጳስ እንዲሾም ቢደረግ “ነጻነቱ ተጠቅመዉ”እንደካቶሊኮቹ መንግሥትን ያወግዙ ነበር ማለታቸዉ ይመስላል።ያ ደግሞ ወደ እጅ አዙር ጥገኛነት እንጂ ወደ ነፃነት እንደማያመራ ብናዉቅም፣በግብጽ/ምሥር መንግሥት የሚሾሙት የኤርትራ ፓትርያሪኩም ከኢሳያስ በትር እንዳላመለጡ ዜናዎቹ የተከታተላችሁ ይመስለኛል። “አስማሪኖ ዳት ካም” በሚባለዉ የኤርትራዊያኖች ሰሌዳ መመልከት ትችላላችሁ። ኣቶ ኤፍሬም ማዴቦ እንደ ካቶሊኮቹ በዉጭ ሃይል ስለማይሾሙ “ነጻነቱ ስለሌላቸዉ” መንግሥት በዜጎች የሚፈጽማቸዉ በደሎች መቃወም/ማዉገዝ አይችሉም፣ ባሉበት አንደበታቸዉ ዞር ሳይሉ በሴኮንድ ዉስጥ “ሊያወግዙ ያልቻሉበት ምክንያት እንደገና በነሱ ላይ ዉግዘቱን እንዲህ በማለት ያወርዱባቸዋል“የሃይማኖት መሪዎች ሚናቸዉ ሊጫወቱ ያልቻሉበት ምክንያት “እኛ ፖለቲካ አይመለከተንም የሚል ነዉ”፣ በማለት ያወግዟቸዋል። ይቀጥሉና እንደ ደቡብ አፍሪካዊዉ ካቶሊኩ “ዲስሞን -ቱቱ” ለዘረኛ መንግሥት አልገዛም ብሎ መቆም አልያም እንደ ኢትዮጵያዊዉ ፕሮቴስታንቱ/ጴንጤዉ(?) “ቄስ ጉዲና ቱምባ” አልገዛም ብሎ ካገር እንደወጡ መቅረት በማለት አቡነ ቴዎፍሎስንና አቡነ ጴጥሮስን በአርአያነት በመጥቀስ ከ35 ዓመት ወዲህ ያሉትን የሃይማኖት ግንመሪዎች ግን ሕዝብ ሲበደል አያገባንም ብለዉ አፋቸዉ ዘግተዋል በማለት እንደሚከተለዉ ይተቻሉ።ልጥቀስ። “ መሪዎቹ ሚናቸዉን ሊጫወቱ ያልቻሉበት ምክንያት እኛ ፖለተካ ዉስጥ አያገባንም በሚል ነዉ። ሃይማኖትና ፖለቲካ ይቀላቀል ሚል እምነት ባይኖረኝም እንደ ቄስ “ዲስሞን ቱቱ” በነጭ አልረገጥ ብሎ ለሕዝብ መቆም እንደ “አቡነ ቴዎፍሎስ” እና እንደ “ቄስ ጉዲና ቱምባ” እዉነትን በዉሸት አልለዉጥም ብለዉ “እንደወጡ መቅረት”፣እንደ “አቡነ ጴጥሮስ” አገሬ በፋሺስት አትገዛም ብሎ በጥይት ተደብድቦ መሞት ለእዉነትና ለአገርና ለሕዝብ መቆም ነዉ እንጂ ፖለቲካ መሆን አለመሆን የሃይማኖት መሪዎች አጥብቀዉ ሊረዱ ይገባል።” በማለት እንደካቶሊኮች ነጻነት ስለሌላቸዉ መናገር አልቻሉም ያሉዋቸዉን ምስኪኖች ተመልሰዉ “ፖለቲካ ዉስጥ አንገባም ብለዉ የሕዝብን ግፍ እያዩ ባይተዋር ሆነዉ ጥግ ሆነዉ የሕዝቡን ግፍ እየተመለከቱ ነዉ በማለት ልክ ተመችቶአቸዉ እንዳሉ በማድረግ አቶ ኤፍሬም በዉሸት በመመርኮዝ “አይመለከተንም” እያሉ ነዉ ሲሉ አላግባብ ሁሉንም በጥቅል ሲተቿዋቸዉ ማድመጥ ፣እጅግ በጣምኑ ነበር የገረመኝ። ከተነጋሪዉ ይልቅ የገረመኝ ደግሞ “የግንቦት 7 ታዳሚዎች የደመቀ ጭብጨባ ሲለግሷቸዉ በመስማቴ ዉሸትን እዉነትንም ቢደባለቅ ባይደባለቅ የጭብጨባ ሱሰኞች የሆኑት የዚህ ቡድን አምላኪዎች እንደዘወትሩ ለዉሸት ትችት በማንጨብጨብ ዛሬም እንደ ትናንቱ ያዉ አድሮ ቃርያ መሆናቸዉን ያመለክታል።እዉነት እዉነት እላችሗለሁ -አዘንኩ! አቶ ኤፍሬም ምሁር ናቸዉ።ያቀረቡት ያልተመጣጠነ ለሕዝብ የሚተላለፍ ትችት ግን የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንም ሆነ ሌሎች በስም ያልጠቀስዋቸዉ ሁለት “ትላልቅ ሃይማኖቶች” በተለይም ወያኔ በተዋሕዶ ቤተክርስትያን ላይ ያደረገዉ ግፍ ያወቁት አልመሰለኝም፣ ካወቁት ደግሞ ለካቶሊክ ካረዲናሉ እና የካቶሊክ ሰባኪያን ምእመናኖች ብቻ አርአያነቱን በመጥቀስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከ35 ዓመት ወዲህ ቤተክርስትያኒቱ ማንም መሪ “በአርአያነት” ሊጠቀስ የሚችል ካህን/ሰባኪ/መሪ/ቄስ እንዳላወጣች አድርገዉ የተዛባ ትችት መተቸቱ ከአንድ ምሁር የሚጠበቅ አይደለም። እንኳን እና እየሞቱ እየታሰሩ እየተሰደዱ ያሉት ምዕመናን እና መሪዎቻቸዉ፣ እንደ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እንደ ቄስ ጉዲና ተሰድደዉ እንደማንም ዜጋ ዉጭ ቢቀሩና ቢኖሩ ለብቻቸዉ ልዩ ታምር ይስሩ የሚለዉ ሕግ ማነዉ ያወጣዉ? አገሪቱ ለካህናቱም ሆነ ለማንም ዜጋ ዕኩል ስለምትደርስ ለብቻቸዉ ልዩ ሸክም ይሸከሙ፣ይሙቱ፣ይታሰሩ፣ እኔ ግን ልተችባቸዉ የሚል ትችት ሚዛናዊ አይመስለኝም። እኛ ያላደረግነዉ አንዳንዶቹ የቤተክርስትያኒቱ መነኮሳት/መሪዎች /ባሕታዊያን ግንባራቸዉን ለአረር አጋልጠዉ ሰጥተዋል።እዉነት ለመናገር ከሆነ እኛ ተቺዎችም የተተቹት ነገሮች በአርአያነት ማሳየት ይጠበቅብናልና፣ እነሱም ያንኑ አደርገዋል ፣ከማደረግም ወደ ሗላ ያሉበት ጊዜ የለም። በመሰረቱ ወያኔ እንደገባ በአንዋር መስጊድ ያደረሰዉ ግድያ ያስታዉሱታል? በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያን እና ገዳማት ቅጥር ግቢ የተፈጸሙት ግድያዎችስ ያዉቁት ይሆን?የሚል ጥያቄ አድሮብኛል። ያገሪቱ ሕጋዊ ፓትርያሪክ አቡነ መርቀሬዎስ እና ካህናቱ ከስደት አስከ ሞት እንግልትና ግፍ ደርሶባቸዋል። ባይተዋር፣ ዳር የቆሙ አይደሉም። ሰለባዎች ናቸዉ ። በባሕታዊ ፈቀደ ስላሴ እና አባ አማሃ እየሱስ እና በመቶዎቹ መምህራን ሰባኪያንና ካሕናት ላይ የደረሰዉ ግፍ የሕዝቡንና የቤተክርስትያኒቱን መብት ለመጠበቅ አልገዛም በማለት ከሕዝቡ ጎን በመቆም እንደሆነ አቶ ኤፍሬም ያዉቁታል የሚል ግምት አለኝ። የካቶሊኮቹ ትግል ካወቁ ያኦርቶዶክሶቹና የሌሎቹ መስዋዕትነት የሚያጡት አይመስለኝም። የተዋሕዶ ኦርቶዶክስ መሪዎች ስለ ሕዝብ እና ቤተክርስትያኒቱ መብት በመናገራቸዉ ስደትና ሞት እንግልት ከሥራ መፈናቀል ሲደርስባቸዉ (አቶ ኤፍሬም ቢዘነጉትም)ካቶሊኮቹ ሙሉ ነጻነት ስላላቸዉ የደረሰባቸዉ በደል እንደሌለ በራሳቸዉ አንደበት አረጋግጠዋል።ታዲያ ሦስቱ ትላልቆቹ ሃይማኖቶች በተዛባ ትችት እና በማይገባ ፖለቲካ አያገባንም እያሉ ግፍ ሲፈጸም እያዩ ቆሞ ተመልካች ሆነዋል ማለታቸዉ ከምሁር አንደበት ሊወጣ የማይገባ በመሆኑ፣ በላይ ላንዲት ደቂቃ እና እንዲት ሃረግ እንኳ “በዚህ መጥፎ ሚና የሚጫወቱና ተጠያቂ የሆኑትን የወያኔዉ ጳጳስ አባ ገብረመድህን/አባ ጳዉሎስ አልጠቀሱዋቸዉም። ሰማቸዉ አንኳ በካሃዲነት ወይንም በግፍ ሰራቸዉ አንስተዉ ሲያወግዟቸዉ አልሰማንም።ለምን? ሃይሞኖቱ ተቅዋሙ በደፈና ከመተቸት ለዚህ ጥፋት ተጠያቂ የሆኑትን በስም መጥቀስ ለምን አልቻሉም?ለማንኛዉም ስለ ወጣት ተማሪዎች የደረሰባቸዉ በደል አንስተዉ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ተጠያቂ በማድረግ /ለመዉቀስ “አያገባኝም አለች”የሚሉን አባባል፣ቤተክርስትያንና አባ ጳዉሎስ ለየብቻ መሆናቸዉ ካወቁ (እንደሚያዉቁት ተስፋ አለኝ) እሳቸዉን በስም እየጠቀሱ ከማጋለጥ እና ከመተቸት ይልቅ በገፈኞች መሪዎች ላይ 35 ዓመት ምንም ያለቺዉ ነገር የለም በማለት እራስዋ እግቢዋ ዉስጥ በመግባት የራስዋን ካህናትና ምዕመናን በጥይት ሲቆሉባት አቅም እንደሌላትና “እንደማንኛችን ዜጎች”ሁሉ እስዋም ተጠቂ እንጂ ቆማ በባይተዋር በምን አገባኝነት ግፍን እንዳላስተናገደች እያወቁ በጠቅላላ የሦስቱ ትላልቅ ሃይሞናት መሪዎችን መተቸት አግባብነት የለዉም። አብዛኛዎቹ ካህናትም ፖለቲከኞችም እንደሚሉት አባ ጳዉሎስ የመንግሥቱ ካድሬ አንጂ የቤተክርስትያኒቱ ሕጋዊ ተወካይ እንዳልሆኑ እየታወቀ ስማቸዉን ላለማንሳት እየሸሹ በደፈናዉ ሁሉንም በዉግዘት መቀጥቀጡ አይገባም ። አንግዲህ ነገርን በማስረጃ ነዉና ፣እኔ ተራዉ ሰዉ ታሪኩን ከምነግር የችግሩ የእንግልቱ የሞቱና ስደቱ ተጠቂዎች እና ቀማሾች የሆኑት በቤተክርስትያኒቱ መሪዎች አንደበት ካደረጉዋቸዉ ቃለ መጠይቆች አቶ ኤፍሬም ማዴቦን ላስተናግድ እና አንባቢ በቂ ግንዛቤ እንዲያደርግና የግንቦት7-የጭብጨባ ሱሰኞችም ትንሽ ቢማሩበት (የሚያዳምጥ ልቦና ካላቸዉ) እነሆ። ቤተ ክህነትም ቤተ መንግሥትም በምንደኞች እየተመሩ ስለሆነ ቤተክርስትያኒቱን በጥቅል እንዳለ መዉቀስ አይቻልም፣የሚሉት በአሀገረ አሜሪካ በስደት የሚኖሩ ብጹእ አቡነ መልከፄዴቅ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ምክትል ፓትሪያሪክ ናቸዉ (ስለ ማዕረጋቸዉ ከተሳሳትኩ ይቅርታ እጠይቃለሁ እርምቱን ላኩልኝ)፣ ሕጋዊዉ ፓትርያሪኩ ደግሞ ከላይ በፎቶግራፋቸዉ የሚታዩት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቀሬዎስ ናቸዉ። ብፁእ አቡነ መልከፄዴቅ ሕዳር ወር 1993ዓ.ም ኢትኦጵ ከሚባለዉ መጽሄት ጋር አድረገዉት የነበረዉን ቃለ ምልልስ አንኳር አንኳሩን ላስነብባችሁ። አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ቄስ ጉዱና ቱምባን አልገዛም ብለዉ እንደወጡ መቅረት በማለት ያሞገሷዋቸዉን ቄስ አንገዛም ብለዉ ብለዉ ከመንበረስልጣነቸዉ የተገለበጡና የግፍ ተባባሪ አንሆንም ያሉት ምእመናኖች የሞት ስደት ሰለባዎችም እንዲያዉቁዋቸዉ ምእመናኖቻችንም እነሆ ላስነብበዎት። አቡነ መልከፄዴቅ፣- “በርካታ ዉሳኔዎችን አሳልፈናል። አንደኛ አዲስ አበባ ያለዉ ሲኖዶስ አለመሆኑን ምዕመናን ሁሉ እንዲያዉቁና ቤተክርስትአን በስደት ላይ እንዳለች እንዲረዱ በአገር ቤት የምትገኘዉን ቤተክርስትያን ደግሞ ባላባቱ ወንዱ ሴቱ ሕዝቡ እንዲጠብቅ ምንደኞች ቤተክርስትያንዋን የማይወክሉ መሆናቸዉን ሁለት ሦስት ጊዜ ባደረግነዉ ስብሰባ ገልጠናል። ሁለተኛ፣- በዉጭ አገር በምንደኞቹ የሚደፈርሰዉ የምእመናን አንድነት አንድ እንዲሆን ምእመናንን በማስተባበር ሲኖዶሱ ራስ እንዲኖረዉ የተለያየ ራስ አንዳይኖረዉ ለማድግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን።ሦስተኛ፣-ባገሪቱ ዉስጥ የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሳቅርሶች እየተሸጡ እየተለወጡ ካገር እየወጡ ይገኛሉ።የህንን ከፍተኛ ሓላፊነት ሕዝቡን ለማስተማርና ለማስጠንቀቅ ብዙ ሊሰሩ የሚገባቸዉ ዉሳኔዎችን አሳልፈናል። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚያሰኛት ቢሔራዊ ቅርስዋ ነዉ። አሁን የመጣዉ መንገሥትና አሁን ያለቺዉ ቤተክርስትያን መሪ ነኝ የሚሉ ምንደኞች ስለሆኑ ለጥፋቱ ግድ የሌላቸዉ ስለሆኑ ሕዝቡ በአትኩሮት እንዲመለከተዉና እንዲጠብቅ መላልሰን ዉሳኔዎችን አሳልፈናል ፣አሳስበናል። ኢትኦጵ፣- በአገር ቤት በተለይ በጎንደር አደባባይ ኢየሱስ፣ በ አሰቦት ገዳም በአርሲ እንዲሁም በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርሰትያን (በአባ ፈቃደስላሴ ላይ የደረሰዉ)አሳዛኝ ጭፍጨፋዎችና ግድያዎች ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰደዉ አ ቋም ምን ነበር? ድርጊቱንስ አዉግዞ በአጠቃላይ ያደረገዉ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? አቡነ መልከፄዴቅ.- በአሰቦት።፣ በአርሲ፣ በሐረር ስለደረሰዉ በደረሰበት ወቅት እንዲሁ ተበታትነን በያገሩ ስለነበርን በዚሁ ላይ በሲኖዶሱ ዉስጥ ዉሳኔ ማሳለፍ አልቻልም ፣ እኔም በግሌ ከስራ ዉጭ ሆኜ በሀዘን ላይ ስለነበርኩ፣-ሥራ ፈትቼ (ተግዤ ልበለዉ)የነበረ ስሆን፣ ሲሆን ደረሰዉን የወገን እልቂት ግን በጣም አሳዛኝ ነበርና ሠላም አይሰጥምና ቤተክህነት እየሄድኩ “አረ ባይሆን ፍትሃት ይደረግላቸዉ” እል ነበር። ተቀባይነት አላገኘሁም።ተቀባይ አላገኘሁም እንጂ።አንድም ለስደት የዳረገን ቤተክርስትያንዋም ቤተክርስትያን አይደለችም። አገሪቱ ከእንግዲህ ወዲህ ወገን የሚከበርባት አገር አይደለችም ብየ ነዉ! ስለዚህ በወቅቱ እዚያዉ አዲስ አበባ ስላልነበርኩ በሲኖዶስ መልክ ለማየት አልቻልኩም ። ስለ አደባባይ ኢየሱስና ስለ አባ ፈቃደ ስላሴ በእዉነቱ በጠም የሚያሳዝን ነዉ። አሁንም ደግሜ የምናገረዉ ጣሊያን እንኳ በቤተክርስትያን ዉስጥ ሰዉ አልፈጀም፣ አልገደለም ፣- በእርግጥ በአንድ ቦታ ላይ በጦርነት የተነሳ ቦምብ እየጣለ ቤተክርስትያን አቃጥሏል፣ሰዎችም ሊሞቱ ችለዋል። አላማ አድርጎ ግን በመትረየስ ቤተክርስትያን ዉስጥ ፍጅት አላደረገም። የደብረሊባኖስ መነኮሳት ቢፈጅ ወደ ሰላሌ ወስዶ ሜዳ ላይ ነዉ፣ የዙቋላ መነኮሳትም ቢገድል ሞጆ ወስዶ ነዉ። ወያኔ ግን ቤተክርስትያን እንዳሉ ነዉ የገደላቸዉ። ቤተክርስትያን የሚፀለይበት፣ የፈራ የሚሸሸግበት ፣የሚጠለልበት ቦታ ሲሆን፣-ተደፍሮ የሬሳ ማከማቻ አድርገዉታል። ያንን አዉግዘናል፣አስተላልፈናል እንደዉም እኔ ራሴ በግሌ ሕዝብ ሰብስቤ፣ሰልፍ አድርጌ በዲስኩር ኢሕአዴግንና ያለዉን ፓትርያረክ ነኝ ባዩን አወግዣለሁ፣ እንዲወገዝም አድርጌአለሁ። ምክንያቱም የቤተክርስትያን ጠባቂ በመሆን ፈንታ በጎንደር የደረሰዉን ዕልቂት ከ “ዴቪድ ኮረሽ”-አሟሟት በማመሳሰል አንድ በ “ካልት””ተቃጥሎ የሞተ ሰዉንና ወያኔ የገደላቸዉን ባሕታዊ አነፃፅሮ ተናግሯል።እንደገና ምንም ሰዉ እንዳልተጎዳ ተናግሯል። የሞቱትስ አረፉ።የሚገርመዉ ደግሞ ከዛ ጊዜ ጀምሮ የታሰሩት ናቸዉ። አንዱ አባ አምሃ እሱስ የሚባሉ ናቸዉ።ከእርሳቸዉ ጋር የታሰሩት ወጣቶች እስካሁን ድረስ እንደታሰሩ አሉ። ፍርድም አላገኙም፣የሚጮህላቸዉ የሚናገርላቸዉም የለም።ወያኔ ደግሞ ለዚህ ደንታ የለዉም።አስሮ አስቀምጧቸዋል። ይህንን መላልሰን ጽፈናል አዉግዘናል። አስካሁን ድረስ ምንም የተደረገ ነገር የለም።በአባ ፈቃደ ስላሴ ሞት ደግሞ ዓለም ነዉ ያዘነዉ። የኛ ቤተክርስትያን ሆን ብላ ያደረገችዉ ስለሆነ ተገቢ ሞት እንደሆነ ሲናገሩ ይሰማል። በቀድሞዉ የኢትዮጵያ ነገሥታት ጊዜ ቋንጃ የቆረጠ፣ነፍስ የገደለ ቤተክርስትያን ገብቶ “ደወል” ከደወለ ማንም አይነካዉም ነበር።በተለይ “ዳሩ እሳት መካከሉ ገነት” ተብሎ የሚነገርላቸዉ የታወቁ ደብሮች አሉ። እዛ ሄዶ ከደወለ “እገሌ ደዉሏል አይነካም” ተብሎ ከዚያ ቦታ እንዳይወጣ ይታገዳል እንጂ አይነካም ነበር ከዚያ ቦታ ሲወጣ ደግሞ መንኩሶ የሚወጣ ከሆነ ሞቷልና አይነካም ይባላል።ዝም ብሎ ሸልኮ ከወጣ ነዉ የሚያዘዉ ይያዛል ከነዚህ ሁሉ ለመዳን የነብስ ገዳይ ቋንጃ ቆራጅ ሰዉየዉን ይዞ ንጉሡ ዘንድ ሄዶ ያስታርቃል ወይም በፍርድ እንዲቀጣ ያስደረጋል። ንጉሠነገሥቱ እንኳን ደፍሮ ሠራዊት ልኮ ቤተክርስትያን አያስደበድብም፣ ሕዝብም አያስጨርስም ነበር። ይሄ ሁሉ ታሪክ ባላት ኢትዮጵያ በዚህ በወያኔ ጊዜ መኖክሴ ቤተክርስትያን አገልጋይን በአዉደ ምሕረት አስገደሉ ገዳዩም የፓትርያሪክ ሰዎች ወይም ራሳቸዉ ናቸዉ እየተባለ ነዉ የሚነገረዉ ። በሕታዊዉ የሞቱት በቤተክርስትያን ቅፅር በአዉደ-ምህረቱ፣ታቦቱ ካለበት ከመጋረጃዉ ላይ መሆኑ ለሰሚዉ ግራ ነዉ። እግዚኦ! በዘመኔ እኔ ባለሁበት ወንድሜ ተገደለብኝ” ብሉ ሙሾ ማዉረድ የሚገባቸዉ አባ ጳዉሎስ ነበሩ። እዉነተኛ ክርስትያን ቢሆኑ እሳቸዉም ሆነ ግብራበሮቻቸዉ አንድ እርምጃ ሳይወስዱ ለጊዜዉ አንድ ግለሰብን “ገዳዩ እሱ ነዉ” ብለዉ እንዲታሰር አደረጉ። በሗላ ደግሞ አለፍርድ ፈትተዉ ለቀቁት። ሆን ተብሎ በትዕዛዝ የተደረገ ይመስላል። የሚያሳዝነዉ ባእነሱ ላይ ሳይሆን በቤተክርስትያኒቱ ላይ ጥቁር ነጥብ ማረፉ ነዉ። ቄሶች እንዲህ አደረጉ እየተባለ እኛንም ሁሉ በስመ ቄስ ሊያስተቸን በቅቷል ይህ የተፈጸመዉ ግን በምንደኛዉ ሲኖዶስ እንጂ በስደተኛዉና በእዉነተኛዉ ሲኖዶስ ባለመሆኑ የእኛን ነፃነት አላሳጣም ። ኢትኦጵ፣- እርሰዎበመላ ሐገሪቱ በተለይም በቤተክርስትያኒቱ የሚሰራዉ ትከክል አይደለም ብለዉ ተሰድደዋል። ይሁን እንጂ በስደት ላይ ባሉበት ጊዜ በተደጋጋሚ አማላጅ እንደተላከበዎ ይሰማል በርግጥ ተልኳል? አባ መልከፄዴቅ፣- ሳልሰደድ ከስራ ዉጭ ካለሁበት ወቅት ነዉ ዘጠኝ ጊዜ አማላጅ የተላከብኝ።የመጡበት ምክንያት “ያባ ጳዉሎስን ሹመት ተቀበል፣የወያኔ መንግሥት አትክሰስ፣ አትዉቀስ፣ ተባብረህ ሥራ ወደ ቀድሞ ሥልጣንህ ትመለሳለህ” የሚል ነበር ። የኔ ምላሽ ደግሞ “እኔ አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ነኝ፣ብሞትም ብኖርም ምንም ዋጋ የለዉ፣የምጠይቀዉ ስላገሬ ነዉ፣ሕዝብ በነፃ እርምጃ አይገደልም፣ቁጥቋጥ አይደለም አይጨፈጨፍም” የሚል ነበር። በመቀጠልም “ሕግ አይፈርስም በአንድ ራስ ሁለት ምላስ አይኮንም በአንዲት ቤተክርስትያን ሁለት ፓትርያሪክ አይሾምም”-እያልኩ ሁሉንም መልሻቸዋለሁ። ሽማግሌ የሚባሉትም የኔን፣ምላሽ አይናገሩም፣ እዛ የሚጫኑትን ብቻ አምጥተዉ “ምን ቸገረህ? መስለህ ተመሳስለህ ኑር” ሲሉኝ ቆዩ “እንዴት አይቸግረኝም? ቸግሮኝ እኮ ነዉ ከናንተ ጋር የማልሆነዉ፣ እናንተ ባይቸግራችሁ እኔ ይቸግሮኛል”-እያልኩ እመልሳቸዉ ነበር።ከተሰደድኩም በሗላ መምጣቱ ይመጣሉ፣፣ ፊት ለፊት አይናገሩንም እንጂ “እሱ ነገር ያከርራል፣እሱን ትተን በዙርያዉ ያሉትን እናነጋግር እያሉ ሌሎችን እያነጋገሩ ይሄዳሉ። ያነጋገሯቸዉ ባልደረቦቼም “እሱ ከሌለ መልስ አንሰጥም” እያሏቸዉ ይመለሳሉ እንጂ አስከ መጨረሻዉ ወደ እኔ አልቀረቡም።” በማለት ሰፊዉን ያላቀረብኩላችሁ ቃለ መጠይቁ በዚች ብፁእ አባታችን በተናገሯት ሐረግ ልዝጋ “… በዚህ ወቅት ተወላጅ ንን ብለዉ ኢትዮጵያዉአኖቹ ኢትዮጵያን ሊአጠፉ ሲነሱ ግራኝን ይበልጣሉ፣ ጉዲተን ይበልጣሉ ነዉ ምለዉ፣፣ እነዚያ ባይማሩ የሃገር ፍቅር ባይኖራቸዉ ነዉ፣፣ እነዚህ ግን ተምረዉ የሀገር ፍቅር በመያዝ ፈንታ የሃገር ጥላቻ፣ የወገን ጥላቻ ያደረባቸዉ ከነዚያ የባሱ አረመኔዎች ናቸዉ ብየ እናገራለሁ።”በማለት የወያኔ ጨቋኝ እና ጨካኝ መንግሰሥት ወያኔ ከሾማቸዉ የራሱ የቤተክርስቲያኒቱ ሕገ ወጥ ሹማምንትን በማዉገዝ ቃላቸዉን ጮክ አድረገዉ በማሰማት ከሕዝብ ቆን ከቆሙት ከሺዎቹ ካሕናት እና መነኮሳት ጳጳሳት መካከል አንዱ አቡነ መልከፄዴቅ የቤተክርስቲያኒቱ አቁዋምና ኑሮ ፣እንግልት ፣እየደረሰባት ያለዉ ግፍ አስረድተዋል። ወንድሜ አቶ ኤፍሬም ማዴቦም ከዚህ ቃለ መጠይቅ ምን ትምርት እንደሚቀስሙ ባላዉቅም ፣ በደፈናዉ ቤተክርስትያኒቱን ከመኮነን ፣ አጥፊዎችን በስም እየጠቀሱ ትችቱን ወደ መተቸት የሚገባዉ ክፈልና ግለሰብ ብያደርጉ ለወደፊቱ የተሻለ ነዉ ብየ ወንድማዊ ምዕዳኔን ለመለገስ እወዳለሁ። ተጠቂዎችን እንደ ቆሞ ተመልካች ማድረጉና መወንጀሉን ይቅርብን ማለቴ ነዉ። በቤተክርስትያን አለቆችና ምዕመናን እየደረሰ ያለዉ ግፍ ከሕዝቡ የቀለለ ሳይሆን የከፋ መሆንና ግፉን እየቀመሰች እና እያወገዘች መሆኑን ሕዝቡ እንዲያዉቀዉ ማድረግ የምሀራን ሓላፊነት ነዉና፤ በሁኔታዉም ታሪክ እየመዘገበን ነዉና ; “ከቄስ ጉዲና” ወይንም “በባቲካን ከመሾሙት ከካቶሊኩ ዲስሞን ቱቱ” ባልተናነሰ ያዉም በደመቀ አኩሪ አርአያነት ህይወታቸዉ ለፍትህ የሰጡ ባህታዊ መሪዎቻችንና ቀሳዉስቶች መነኮሳትና ካህናት ኢትዮጵያዉያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አገልጋይ ዜጎቻችንም ስላሉን በዚህ አጋጣሚ ዕዉነት በዕዉነት እየመስከርን ዉለታቸዉን እና መስዋዕትነታቸዉን በክብር እንዲዘከር የተማረዉ ክፍል ልብ እንዲለዉ አደራ እላለሁ። አመሰግናለሁ። የአቶ ኤፍሬም ማዴቦ ንግግር ለማዳመጥ በተጠቀሰዉ በwww.Ethiomedia.com ድረገጽ ወይንም www.Ecadforum.com በተባለዉ የግንቦት 7 እና መሰሎቹ ድረገጽ ደጋፊ በመጎብኘት ያድምጡ። ጌታቸዉ ረዳ (ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ) www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Friday, May 8, 2009

የወያኔ መኢሰኖችና የኩዴታዉ አስቂኝ ተዉኔት

የወያኔ መኢሰኖችና የኩዴታዉ አስቂኝ ተዉኔት ጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com “ወያነ ትግራይ” በማለት ራሱን የሚጠራ “የታሪክ ነቀዝ”- ግንቦት 7 የተባለዉ (የወያኔ መኢሶን )መንሥትነቴን ለመጣል መፈንቅለ መንግሥት ሊያካሄድብኝ ያቀደዉን ሴራ አከሸፍኩባቸዉ ሲል በራሱ ጋዜጦች ይፋ ማድረጉን ይታወሳል። እዛዉ በዛዉ የዋሸዉን ዉሸት ሳይደርቅ- የተወጠነዉ ሴራ መንፈንቅለ መንግሥት ሳይሆን ባለሥልጣናቶቼን ለመግደል የታቀደ ሴራ ነበር ሲል እንደገና ተመልሶ ራሱ በራሱ ሲያምታታ ተደምጧል። ላማስረጃም ከአባሎቹ በብርበራ ተገኘ ብሎ በእግዝቢት የያዛቸዉ ልዩ ልዩ ጠመንጃዎችና ቦምቦች በራሱ ቴሌቪዥን ለሕዝብ እንዲታይ አድርጓል። ዕድሜ በረዘመ ቁጥር አንድ ድርጅት/መንግሥት/ቡድን… “በፊት” ሲከተላቸዉ ከነበሩት ከተጋለጠበት ተራ ብልጣብልጥ አሰራሩ በሚቀጥለዉ የዉሸት/የቅጥፈት/ያጭበርባሪነት እና የብልጣብልጥነት አሰራሩ ልቀጥልበት ካለም ፣“መንገዱ ስልቱና ዓይነቱን”ቀይሮ የተቀናቃኞቹን የፖለቲካ ፊኛ ማስተንፈስ ማዳከም፣ ማሳጣት(ማጋለጥ-) ሲችል ወያኔ ግን ለ34ዓመታት ሙሉ የተከተለዉ “የዉሸት-መንገድ”ዛሬም ስልቱና ዓይነቱን ሳይቀይር በተለያዩ ተቀናቃኞቹ ላይ በዛዉ በለመደበት የዉሸት ስልቱ ሲወነጅላቸዉ ስናይ እዉነትም የጫካ ሕሊናዉ አሁንም እዛዉ እንደጫጨ መሆኑን አመላካች መረጃ ነዉ። ለብዙ ዓመታት ከበረሃ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተቀናቃኞቼ ሲዶሉቱብኝ ደረስኩባቸዉ ያለባቸዉን መረጃዎቹ 95%በዉሸት ያቀነባበራቸዉ መረጃዎች ናቸዉ። የጫካ ባሕሪዉ በቅርብ የተከታተሉና ማሕደሮቹን ያነበበ ሁሉ በቀላሉ መገንዘብ ይችላል። ለምሳሌ ህወሓት በጫካ ዘመኑ “ጃሱስ ማንጁስ ዴማ”(ማንጁስ እና ጃሱስ የሚሉ ቃላቶች የዓረብ ቃላቶች ሲሆኑ ወያኔ ቀልቡ በኤርትራ ቡዱኖች “ፕሮፖጋንዳ፣አሰራር አነጋገርና አጻጻፍ” ሰክሮ ስለነበረ ከነሱ ተበድሮ እስካሁን የሚጠቀምባቸዉ ከበርካታዎቹ የዓረብ ቃላቶች ጥቂቶቹ ናቸዉ- ማንጁስ ማለት “ትንሽ ልጅ/አሽከር’ያልጠና’/ኩታራ” ማለት ሲሆን “ጃሱስ” ደግሞ “ሰላይ”ማለት ሆኖ “ዴማ/ዳይማ”ደግሞ ትግራይ ዉስጥ በዓዲግራት አካባቢ/አሲምባ…. እና ዕዳጋሓሙስ የተባሉ ቦታዎችን ያማከለ ተራራማ ቦታ ነዉ- ቦታዉ ከደደቢት ቀጥሎ ወያኔ ለስልጠና ጣቢያ ያዘጋጀበት ቦታ ነበር-የመጀመሪያዉ ጠቅላላ ጉባኤዉ ያደረገበትም እዚህ ነበር)- በማለት ወያኔ የሚጠራዉ የዴማዉ ሰላይ “የ12 ዓመት ወጣት ህጻን ልጅ” ነዉ። ይህ ህጻን (1) በደርግ ተልኮ በስለላ ተግባር ተሰማርቶ የህወሐትታጋዮች ከሚጠቀሙባቸዉ የዉሃ ኩሬዎች መርዝ እንዲጨምር የተላከ ነዉ፤ በማለት እየደበደቡ ‘አዎ ተልኬ ነዉ የመጣሁት በል” እያሉ በማሰቃየት፣- (2) ታጋዮቻችን ወደ ደርግ ዓላማ ለመሳብ በስለላ ተግባር ተሰማርቶ ሲያደራጅ ያዝነዉ በማለት፣ ሸዊት በተባለዉ ታጋይ እና በወያኔዎቹ አባት ስብሓት ነጋ ታጋዮቹ በሙሉ ሲመረመሩ ምንም ማስረጃ ማግኘት ስላልቻሉ ገበሬዉንም በክሎታል በማለት ገበሬዎች እና ቄሶች ሳይቀሩ በሰበቡ የድብደባ ምርመራ ከተካሄደባቸዉ በሗላ ምንም ምንጭ ስላላገኙ በመጨረሻ እንዲረሸን የፈረዱበት “መሓመድ”የተባለዉ ይህ ህጻን እና ሌላዉ ወጣት በሃሰት እንዴት እንደረሸንዋቸዉ ካሁን በፊት በፊታዉራሪ ገዛ ረዳ ቃለ መጠይቅ እንዳስነበብኳችሁ ይታወሳል። ከተማ ገብቶ የመንግሥት ሥልጣን እንደነጠቀም ደ/ር ታየ ወልደሰማያትን ከዉጭ አገር ጉብኘት እንደተመለሰ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ሲመለስ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ላይ ያያዘዉ ሻንጣ ሲፈተሽ ታጣፊ መሳርያ አገኘንበት በማለት ለ6ዓመት በሃሰት አስሮ እንደለቀቀዉ የምታዉቁት ታሪክ ነዉ። የሓሰት ምስክሮቹም በማናቀዉ ጉዳይ ላይ በሓሰት አንመሰክርም በማለታቸዉ የደረሰባቸዉ ስቃይ በወቅቱ የተለያዩ ጋዜጦች ዘግበዉት እንደነበር ይታወቃል። ሌላዉ ስለ የወያኔ የዉሸት ቀፎነት በዚህ “በኢትዮጵያን ሰማይ- በሎግ” ላይ ያቀረብኩላችሁ የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የሰጡትን የወያኔ አሰራር እና ሰዉን ፣ድርጅትን እንዴት አድረጎ በሓት እንደሚወነጅል በሰፊዉ ተመልክተናል። ከዚህ ሌላ በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ላይ የደረሰዉ በመንግሥት ግልበጣ የሓሰት ዉንጀላ (በሙት ዓመታቸዉ በዚህ ወር ዝርዝሩ አቀርብላችሗለሁ)-ታሪክ ወያኔ የሓሰት ምስክሮች እንዴት እንዳዘጋጀ የራሱ የወያኔ ታጋይ እና የደህንነት ሰራተኛ የነበረዉ በሗላ ከድቶት ወደ ኤርትራ እጁን በመስጠት ይህ ጉዱ ስላጋለጠዉ እና ለወደፊቱም በምስክርነት እንዳይቀርብ በማለት ስለሰጋ - ወያኔ ተከታትሎ በ2000 ዓ.ም ላይ ጋሽ- ባርካ ላይ እንዳስገደለዉ የሚወራዉ “ፍስሃ ሃይለማርያም””-የተባለዉ በሁኔታዉ እራሱ የተሳተፈበት የምርመራ ቅንብር የሰጠዉ ምስክርነት በYou Tube” ቴሌ ቪዥን የቀረበዉ ማስረጃ በማየት የወያኔ ማንነት መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ ወያኔ በዉሸት የፋፋ የዉሸት ቡድን እንደሆነ የሚታወቅ ነዉና ስለ ወያኔ የመፈንቅለ መንግሥት አስቂኙ ተዉኔት እዚህ ትትን ይልቁን እኔ የገረመኝ “ሙሉነህ እዮኤል” የተባለዉ ሌላዉ የግንቦት 7 አመራር አባል ነዉ የሚባልለት ወጣት በዚሁ የሰሞኑ አስቂኝ የመፈንቅለ መንግሥቱ ጋር የተያያዘ ስለ የድርጅት አለቆቹ እነ ብርሃኑ እና “አንዳርጋቸዉ ጽጌ” (በትናቸዉ ጽጌ) የጻፈላቸዉ የአርበኛነት ምስክርነት ገርሞኝ እሱን አንድ ለማለት ነዉ። ከዚህ መፈንቅለ መንገሥት የተባለለት የዉሸት ቅንብር ተያይዞ በር ተከፈተልን በማለት የግንቦት 7-ሰዎች ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀሙበትም እንደሆነ ግልፅ ነዉ። በግረመንገዳቸዉም የገንዘብ ማሰባሰብያ በር ከፍቶላቸዉ እንደለመዱበት መከረኛዉ የአዉሮጳ እና የዲ.ሲ ስብሰባ 6 እና 7 ሰብሰባዎች እናካሂዳለን በማለት ጥሪ እያስተጋቡ ነዉ። ከዚህ በተያያዘ ሰሞኑ ደግሞ ታክቲኩ ሁሉ አልሰራ ሲል “አርበኛ”-የሚለዉ ቃል- “የሰሞኑ ባለ ተራ ቅመም” ሆኖ “እገሌ አርበኛ” በማለት በየመድረኩ ማንበብ ጀምረናል። ሁለት የወያኔ ተቃዋሚ ነን የሚሉን ጠንካራ ድርጅትን እና በጋራ የመስረሳትን ጅማሮ ያደፈረሱት “የዛኛዉ ጎራ” ታዋቂ ሁለት ሰዎች በተከታታይ ባጋጣሚም ይሁን በተጠና መንገድ የየራሳቸዉ ሰዎች “በአርበኛነት”-በማቆላጰስ ወደ ሚዲያዉ መድረክ አቅርበዋቸዋል። አንደኛዉ እዚህ የተቸሁበት ፕሮፌሰር አለማዮሁ ገብረማርያም ስለ ደ/ር ሃይሉ አርአያ አርበኝነት ሲሆን፣ በተከታታይ ደግሞ “የግንቦት 7”-ሦሰተኛ ሰዉ ነዉ የሚባልለት “ሙሉነህ እዮኤል”የተባለዉ በጸረ አማራነት የታወቀዉ ፣አማራን ለመበተን የኢትዮጵያን አንድነት ለማደፍረስ ለወያኔ አድሮ “የአማራ ሕዝብ ከየት ወደየት” በማጻፍ የታወቀዉ በብዙ ወገኖች “በትናቸዉ ጽጌ” በመባል የሚታወቀዉ “አንዳርጋቸዉ ጽጌ”ን “የአርበኛ ልጅ አርበኛ” በማለት ሲያቆላጵሰዉ አንብበናል። የ80ዓመት አዛዉንት ናቸዉ የሚባሉት የአንዳርጋቸዉ ወላጅ አባት አቶ ጽጌ ሰሞኑን መንግሥቴን ለማወክ ያዝኳቸዉ በማለት ትግራይ ዉስጥ አዛዉንት ወላጆቻችን እና ወንድሞቻችንን ያስር ይደበድብ ይረሽናቸዉ እንደነበረዉ ሁሉ ዛሬም ጉደኛዉ እና ዉሸታሙ ወያኔ እኝህ አዛዉንት ካሰራቸዉ ዜጎች አንዱ ሲሆኑ መሆናቸዉን ከልብ እናዝናለን።ጉዳቱ ካሁን በፊት በኛ በቤተሰቦቻችን እና ወንድሞቻችን ትግራይ ዉስጥ ደርሶብናል እና የሕሊና ቁስሉ እና ከባድነቱ ይገባናል።በዚህም በአንዳርጋቸዉም ሆነ በብርሃኑ ቤተሶበቻቸዉ የሚደርሰዉ እንግልት እንቃወመዋለን። ሆኖም፣-ይህችን ቀዳዳ በመጠቀም “ለወያኔ በማደር ያገሪቱ ሰራዊት ሜዳ ላይ ሲበተን፣ ዜጎቻችን ከኤርትራ ተባርረዉ በባዶ እግራቸዉ ተጉዘዉ አዲስ አበባ መጠለያ አልባ ሆነዉ ሲንከራተቱ አፋቸዉ የከደኑ ብቻ ሳይሆን ለመከራዉ አስተወጽኦ ያደረጉ፣ በሺዎቹ ታፍነዉ እነሱ ባዘጋጁት እስር ሲሰቃዩ ፣ በወቅቱ በስቃዩ ላይ ደስታን የጎነጩ፣ የኢትዮጵያን አንድነት በማፈራረስ ከፍተኛ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳና አስተዋጽኦ በማድረግና በመዲናይቱ ምክትል ከንቲባነት እና በመሳሰሉት ከፍተኛ ስልጣን በመመደብ ወያኔን እና ራሳቸዉን በመንግሥትነት አደላድለዉ ከታወቀዉ የኢትዮጵያ ጠላት ባንዳዉ መለስ እና ታምራት ላይኔ አፍላፍ ገጥመዉ ዊስኪ እና መጽሃፍ ሲዋዋሱና ሲጫለጡ የነበሩት አንዳርጋቸዉ እና ለስየ አብርሃ የመታሰቢያ መጽሀፍ የከተበዉ “ብርሃኑ ነጋን” በአርበኝነት ማቆላጰስ መቼም “ጋኖች አለቁና ምንቸት ጋኖች ሆኑ” ይባል የለ?። ሙሉነህ እዮኤል ሰሞኑን ያንዳርጋቸዉ ጽጌ ወላጅ አባት “በአስቂኙ መፈንቅለ መንግሥቱ”-የተያያዘ በመታሰራቸዉ ወላጅ አባትየዉ “አርበኛ”-ሲላቸዉ ለልጃቸዉ አንዳርጋቸዉን “የአርበኛ ልጅ አርበኛ”-በማለት የወላጅ አባቱን የአርበኛነት ማዕረግ ሲሸልመዉ እኔኑን ደነቀኝ። በተለይ-የመለስ ዜናዊ ወላጅ አባት “አቶ ዜናዊ አስረስን” “ባንዳ” ሲላቸዉ ልጃቸዉ መለስ ዜናዊን “የባንዳ ልጅ “ባንዳ” ብሏቸዋል። ይህ መቸስ በሽታ ነዉ። በሽታ ስላችሁ ሕክምና የማይፈዉሰዉ “የዘረኝነት በሽታ” ማለቴ ነዉ። እንዴት ነዉ ነገሩ ጭልጥ ያለ ነገር!? የአርበኛ ልጅ አርበኛ ይወልዳል ያለ ማነዉ? ብዙ ያርበኞች ልጆች ልጆቻቸዉ “ባንዳ” ሆነዉ አገራቸዉና ታሪካቸዉ ሲያበላሹ ታሪክ የተዘገበ ነዉ። ሙሉነህ እዮኤል ለፕሮፖጋንዳ ስራ ካልሆነ ወይንም የፖለቲካ አለቃዉን አንዳረጋቸዉ ጽጌን ለማስደሰት ካልሆነ ፣እንዳርጋቸዉ ጽጌ በአርበኝነት የሚያስጠራዉ አንድም ማስረጃ አላቀረበልንም። ታድያ እንዴት እንዴት ሲኮን ነዉ ያለ ማስረጃ አርበኛ ብለን አንዳርጋቸዉን የምንጠራለት? ሙሉነህ እዮኤል ወየኔን “ባንዳ” ነዉ ብሎታል፣- ወያኔ ባንዳ መሆኑን ካመነ- እንዴት ሲሆን ነዉ ያርበኛ ልጅ ለወያኔ ለባንዳዉ አድሮ ከሚገባዉ በላይ ወገቡን ለዘረኝነት ብቅል ሰጥቶ ዘረኝነት እንዲበቅልበት ፈቅዶ “የኦሮሞ ትዉልድ ሐረጉ እየመዘዘ -አማርኛ መናገሩን አንጂ አማራ እንዳልሆነ መጽሐፍ ጽፎ እየዘረዘረ አማራንና ኢትዮጵያዊነትን ያጥላላ ግለሰብ ያዉም’ኮ “ኢትዮጵያዊነት-የዘረ-ቢሶች መሸሸጊያ”-በማለት መጽሐፍ የጻፈ ፣ አማራ ሳይሆን “ስለ አማራ ሕብረተሰብ በመጥፎ ጎኑ መጽሐፍ የጻፈ”-መጪዉን ትዉልድ ሊያባላ የሚችል አደገኛ ጽሑፍ የተወልንን ሰዉ በምን ሂሳብ ነዉ በአርበኛነት ሊመደብ የሚችለዉ? የአርበኛ ልጅ በእንደዚህ ያለ ጉደኛ ታሪክ ራሱን ሲነክር አርበኛዉ አባቱ አይቀየሙትም ወይ? ሙሉነህ እዮኤል አማራ ቢሰደብ ባይሰደብ፤ ጉዳዩ አላለዉም፤ አለቃዉ “ኢትዮጵያዊያን ንነ የምንል ሁሉ “ብሔር የሌላቸዉ ዘረ-ቢስ ቢለንም” ሙሉነህ ጉዳይ አላለዉም። የሙሉነህ እዮኤል ሁለተኛዉ ያስገረመኝ ጽሑፉ ደግሞ ወያኔን “አምባ ገነን ቡድን” ማለቱ ነዉ።ለመሆኑ መኢሶን ደርግን “አምባገነን”-እንዲሆን “እንዳርጋቸዉ እና ጓዶኞቹ”” ወያኔንን “አምባገነን” እንዲሆን ዕድሉን የሰጧቸዉ አይደሉምን? ታዲያ ወያኔ አምባ ገነን እንዲሆን በከፍተኛ የፖለቲካ ቦታ ተመድቦ ያገለገለዉ አንዳረጋቸዉ “አርበኛ”-ማለት ዜጎችን አያስቆጣም? ሙሉነህ እዮኤል ወያኔ ትምህርት መቀጠል አለብኝ ካልክ ሂድ ቀጥል በሎ እንደተቀሩት በኬኒያና በባሌ በመከራ ተሸሽገዉ እና ተሰቃይተዉ ሳይሆን “በቦሌ” በክብር የሸኘዉን ወያኔን ምስጋና አይግባዉና እዚህ ድረስ አሸጋግሮ ፈቅዶ የጓደኛዉን የአንዳርጋቸዉ ጽጌን (ጓድ/ጓድ ቁልጵስ) አርበኛነት ማዕረግ ሊያስሰማን መብቃቱ እዉነት ወያኔ “ዉለህ አትግባ” ከማለት ምን ማለት ይቻላል? ሙሉነህ - አስቲ እንደዉ፣ እንደ ብጻዩ/ጓዱ እንደ ብርሃኑ መዋ ድምጹን አጥፍቶ ዉስጥ ለዉስጥ ስራዉ ቢሰራ ምን አለበት? በዚህ ጉዳይ እህቴ “አያልነሽ” በሚጣፍጠዉ አማርኛዋ በሚገባ ገልጻዋለችና ብዙም ለማለት አልፈልግም። ስለ አስቂኙ መፈንቅለ መንገሥቱ ግን አንድ ሁለት ብየ ልዝጋ። ለመሆኑ ብርሃኑ ነጋ በምን ሃሞቱ ነዉ አሜሪካ ተቀምጦ ጦር እያስላከ ወያኔን ለማስወገድ የሚሞክረዉ? ነገሩ ነገር ቢኖረዉም (መፈንቅለ መንግሥት ባይሆንም)-ከብርሃኑ ነጋ የተጠነሰሰ ሴራ እንዳልሆነ ብዙ ሰዉ ይገምታል ።ወያኔ አገዛዙ እየከፋ ስለሄደ በወታደሩም በሲቪሉም ወያኔን በሚችለዉ መንገድ ላለመታዘዝ መሞከሩ አያሌ የማይባል ነዉ። አዲስ ነገርም አይደለም። የብርሃኑ ሃሞት ግን ያየነዉ ነዉ። ድሮ በኢሕአፓ ታሪኩም ሆነ ዛሬ ሴት ልጅቷን ብርቱካንን አጋልጦ ካዲስ አበባ ሸሽቶ በዋሽንግተን -ዲሲ እና በአዉሮፓ በካናዳ የትኩሳቱ መልቀቂያ እና የጉራ መድፈቂያ መድረክ ተዋናይ ከመሆን ሌላ በምን መራራ ሃሞቱ ነዉ እንዲህ ዓይነቱ ስራ የሚሰራዉ? አይሞክርም ሳይሆን ብርሃኑ እና አንዳረጋቸዉ ለእነደዚያ ዓይነት ተልእኮ ዘሎ የሚገባ ሕሊና እና ሃሞት የላቸዉም! እመኑኝ! ከነሱ ይልቅ ሴቲቱ ብርቱካን መቶ በመቶ በወንድነቷ ምረጥ ቢሉኝ አማራጭ ካጣሁ እሷን እምርጥ ነበር። ወያኔ ዋሽቶ መወንጀሉ ላይቀር ዉሸቱን አሳምሮ ቢዋሽ እና የመኢሶኑ የ ዶ/ር ነገደ ጎበዜን የኩባዉና የየመን ሪፑብሊክ አምባሲዎች ትብብር በሌተናል ኮሎነል መንግሥቱ ሃይለማርያም የታቀደዉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ዓይነት ሲደረግ እጅ ከፍንጅ ደረስኩባቸዉ፣ ቢልና ብርሃኑ ነጋ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወርዶ በደህንነት ጥበቃ ሰራተኛችን በመታየቱ -ለምን እንደመጣ ደህንነት ሰራተኛዉ ቢጠይቀዉ “የእርቅና የሰላም” ድርድር በሚመለከት ስብሰባ ለማድረግ በመንግሥት መጋበዙን ገልጾለት-ሲያበቃ ደህንነቱ ይሄንኑ ለማስታወቅ ወደ አለቃዉ ሄዶ ሲመለስ አጅሬ “ብርሃኑ ነጋ”-ስሙን ለጊዜዉ ለመግለጽ ያልፈለግነዉ በአንዱ በ----------አዉሮጳ አምባሲ አጃቢዎች ታጅቦ በምስጢር በመኪና ተወስዶ መደበቁን ደርሰንበት ደረግ ዶ/ር ነገደ ጎበዜን እንደሸኘዉ እኛም በድርድር አገር እንዲለቅ ሆኗል። ብሎ አሳምሮ ቢዋሽ ምንኛ ታሪኩ ተደማጭነት ባገኘ ነበር። ግን አልቻለበትም! · ብርሃኑም-አንዳርጋቸዉም-ወያኔንና መለስ ዜናዊን አገልገለዋል፣ አክብረዋል፣ አቆላጵሰዋል ዊስኪ ተጫልጠዋል።ሃይለ ፊዳ እና ጓዶኞቹም ሌተናል ኮሎኔል መንግሥቱን አገልገለዋል፣ አክብረዋል፣ አቆላጵሰዋል ዊስኪም ተጫልጠዋል። ስለዚህ እነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳረጋቸዉ “ግንቦት 7”ብለዉ ራሳቸዉን ቢጠሩም ሰዎቹ “የወያኔ-መኢሰኖች”ናቸዉና ከጓዳቸዉ ከበረከት ስሞን ጋር ሲማከሩ፣ ሲለሳለሱ እና ሲያቅማሙ የግንቦቱን ሕዝባዊ እሮሮ አክሸፉት (የቤት መቀመጥ አድማዉን ልብ ይለዋል)። ከወያኔ መኢሰኖች ብዙም አልጠበቅንም ትናንትም ዛሬም ነገም ። የደርጉ የሃይለ ፊዳ መኢሰኖችና እና የወያኔዎቹ የአንዳርጋቸዉ/ብርሃኑ “የወያኔ መኢሰኖች”-ልዩነታቸዉ የደረጎቹ መ ኢሰኖች ሃገራዊ አንድነት እንዳይላላ የታገሉ ኢትዮጵያዊነትን ያስቀደሙ ከዘረኝነት የጸዱ ሲሆኑ፣ የደርግን መነግሥት በጥበብ ለመጣል ደርግን የተደባለቁ ጊዜዉን ያላገናዘቡ ፖለቲከኞችና የደርግን ዙፋን የገነቡ ሲሆኑ”። የእነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳረጋቸዉ “የወያኔ-መኢሰኖች” ግን አማራን የሚጠሉ ዘረኞች፣ ለወያኔ ያደሩ ፣ ካለ ወያኔ በቀር በራሳቸዉ ህልዉና እና ፖሊሲ መቆም ያልቻሉ፣ ጥገኞችና፣ አገር ሲፈርስ ሮጠዉ አገር ገብተዉ ኩት… ኩት.. እያሉ የወያኔ አለቆችን ባሽከርነት እየተከተሉ “ባንዳዎች” ብለን ከምንጠራቸዉ የወያኔ መሳፍንት አለቆች ጋር ዊስኪ ሲያንቃርሩ “ፎቶ መነሳት” እንደኩራት የሚቆጥሩት “አሳፈሪዎች”፣ የባሕር በሮቻችን ሲዘጉብን ኡኡ ስንል ያማራ ትምክህተኞች እሮሮ እያሉ “ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ”-ሆነዉ የወያኔን ዉሳኔ ተቀብለዉ ያስተጋቡ ናቸዉ ። · ዋ! ዋ! ያዉም እኮ ፣ “የአርበኝነት የምስክር ወረቀት” በ$500 ዶላር እንሸጣለን በማለት በታሪክ ያልተሰማ. ያልተደረገ “ምጻእተ ዓለም / ጉድ!” አርበኝነትን ማዕረግ ችርቻሮ ገበያ ንግድ ዉስጥ የገቡ እኮ ናቸዉ!እናንት ወንድሞቼ/እህቶቼ፣-በኢሕአፓ አባሎችና ደጋፊዎቻቸዉ ጥረት.፣ መስተንገዶነት፣ ጽ/ቤት ቅርንጫፎቻቸዉ በአዉሮጳም በአሜሪካም ክፍት አድርገዉ እነ ሃይሉ አርአያም እነ ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዉልም እነ ልደቱ አያሌዉን አሰባስበዉ አስከ ቅንጅት ሕብረት ድረስ እንዲጎለብሱ እና ተበታትነን የነበርነዉን ህብረተሰቦች ጸረ ወያኔ ቆመን እንድንታገል ከጅምሩ የተተከለዉ የሕብረት ችግኝ ዉሃ አየርና እና ማዳበርያ ሆነዉ በማሳደግ፣ በማጠናከር ያደረጉት በታሪክ የማይረሱ ሸጋዎቹ “ኢሕአፓዎች” ከማመስገን ይልቅ (የብርሃኑ መዋ እና የአንዳርጋቸዉ ሴራ እንዳለ ሆኖ) ብርሃኑ ነጋ ከእስር እንደተፈታ ዉጭ አገር መጥቶ ዋሽንገተን ዲሲ አዳራሽ ገብቶ ከአፍዓበት የመጣ አርበኛ ይመስል “አበባ እና ዘምባባ ሲጎነጎንለት”-የመጀመርያ ዲስኩሩ ዘለፋ የጀመረዉ በወያኔ ሳይሆን “በኢሕአፓ”-ላይ ነበር ያነጣጠረዉ (ስልጡንና የፋራ ፖለቲካ በማለት-የስድቡ የሽርደዳዉ ጉንጉን ምን ይል እና ለማን ይዘልፍ እንደነበር የምናዉቀዉ እናዉቀዋለን)። በዚህ ዘዴ ነበር “የብተና ስራቸዉ የጀመሩት” ። · ቀጥሎ በወያኔ እና በኢሕአፓ ላይ እያደባለቀ ተደጋጋሚ የብተና ፕሮፖጋንዳዉ እና ስድቡ እንዳጦፈዉ በኢንጅነር ሃይሉ ላይ በተቀነባበሩ ዘረኞች በየመድረኩ እና በየሚድያዉ አስሰልፎ ጅላጅል ብርቱካንን ፊት-ፊት በማስቀደም እሱ ከሗላ ምን ማለት እንዳለባት እያጣደፈ ሕብረቱን በትኖ ሲያበቃ፣--ልጅቷንም ጥሎ አሜሪካኖች ገንዘብና ቀለብ ሰጥተዉት ሳትሰራ ሳትለፋ “ተራራ ላይ ወጥተህ ቁጭ ብለህ ተፈላስፍ” ብለዉኛል ብሎ እዚህ “ፋራዎች”-ከሚለን የፖለቲካ አዛዉንቶች ጋር ቀረ። የምስኪኒቷ ድርጅትም አስዋን ለእስር ዳርገዉ ኢንጅነር ሃይሉን አምባገነን ባሉበት አፋቸዉ ዛሬም በፕሮፌሰር መስፍን አፍ እርስ በረስሳቸዉ “አምባገነንነት እና ስርዓተ አልበኝነት ማን ያዘኛልነት እና ገለልኝነት” አዲሱን ፓርቲዋን ዉጦታል እያሉ በገዛ ብዕራቸዉ እየነገሩን ነዉ! · አንግዲህ ይህ ሁሉ አፍራሽ ተግባርና ባሕሪ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ተጋግሎ የነበረዉ የሕዝቡ ወኔ እና ሕብረት ላይ “ቀዝቃዘ ዉሃ ሲቸልሱበት”ያረርነዉን እንዳይበቃ መላልሰዉ የሚጽፉት ፕሮፖጋንዳ እና ጉራ “ቁጣችንን የሚያበረድ ሆኖ አላገኘሁትም!”አሁንም አሁንም ጉራቸዉ ሰንጢ የማይበጣዉ ሆኖ አሜሪካ እና አዉሮጳ በመዞር እየተንገዋለሉ እነ አንዳርጋቸዉን “አርበኞች” በሉልን ሲሉን- በ እውነት እላችሗለሁ በመንገስቱ ሃይለማርያም ፊት ቆመዉ አንድ “ቄሱ”-እንዳሉት የዚህ ዕብጠት ትርጉም “እኔ- እየጠበበኝ መጥቷል”። በቻ ለማንኛዉም በወሎየዉ በሸኽ ጅበሪል ምርቃን/ሀድራ “አላህ ይሁናችሁ አላህ ይሁነና” ከማለት ምን ማለት ይቻላል?

የወያኔ መኢሰኖችና የኩዴታዉ አስቂኝ ተዉኔት

የወያኔ መኢሰኖችና የኩዴታዉ አስቂኝ ተዉኔ
“ወያነ ትግራይ” በማለት ራሱን የሚጠራ “የታሪክ ነቀዝ”- ግንቦት 7 የተባለዉ (የወያኔ መኢሶን ) መንሥትነቴን ለመጣል መፈንቅለ መንግሥት ሊያካሄድብኝ ያቀደዉን ሴራ አከሸፍኩባቸዉ ሲል በራሱ ጋዜጦች ይፋ ማድረጉን ይታወሳል። እዛዉ በዛዉ የዋሸዉን ዉሸት ሳይደርቅ- የተወጠነዉ ሴራ መንፈንቅለ መንግሥት ሳይሆን ባለሥልጣናቶቼን ለመግደል የታቀደ ሴራ ነበር ሲል እንደገና ተመልሶ ራሱ በራሱ ሲያምታታ ተደምጧል። ላማስረጃም ከአባሎቹ በብርበራ ተገኘ ብሎ በእግዝቢት የያዛቸዉ ልዩ ልዩ ጠመንጃዎችና ቦምቦች በራሱ ቴሌቪዥን ለሕዝብ እንዲታይ አድርጓል። ዕድሜ በረዘመ ቁጥር አንድ ድርጅት/መንግሥት/ቡድን…“በፊት”-ሲከተላቸዉ ከነበሩት ከተጋለጠበት ተራ ብልጣብልጥ አሰራሩ-በሚቀጥለዉ የዉሸት/የቅጥፈት/ያጭበርባሪነት እና የብልጣብልጥነት አሰራሩ ልቀጥልበት ካለም ፣ “መንገዱ ስልቱና ዓይነቱን”-ቀይሮ የተቀናቃኞቹን የፖለቲካ ፊኛ ማስተንፈስ ማዳከም፣ ማሳጣት(ማጋለጥ-) ሲችል ወያኔ ግን ለ34 ዓመታት ሙሉ የተከተለዉ “የዉሸት-መንገድ”-ዛሬም ስልቱና ዓይነቱን ሳይቀይር በተለያዩ ተቀናቃኞቹ ላይ በዛዉ በለመደበት የዉሸት ስልቱ ሲወነጅላቸዉ ስናይ እዉነትም የጫካ ሕሊናዉ አሁንም እዛዉ እንደጫጨ መሆኑን አመላካች መረጃ ነዉ። ለብዙ ዓመታት ከበረሃ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተቀናቃኞቼ ሲዶሉቱብኝ ደረስኩባቸዉ ያለባቸዉን መረጃዎቹ 95%በዉሸት ያቀነባበራቸዉ መረጃዎች ናቸዉ። የጫካ ባሕሪዉ በቅርብ የተከታተሉና ማሕደሮቹን ያነበበ ሁሉ በቀላሉ መገንዘብ ይችላል። ለምሳሌ ህወሓት በጫካ ዘመኑ “ጃሱስ ማንጁስ ዴማ”(ማንጁስ እና ጃሱስ የሚሉ ቃላቶች የዓረብ ቃላቶች ሲሆኑ ወያኔ ቀልቡ በኤርትራ ቡዱኖች “ፕሮፖጋንዳ፣አሰራር አነጋገርና አጻጻፍ”-ሰክሮ ስለነበረ ከነሱ ተበድሮ እስካሁን የሚጠቀምባቸዉ ከበርካታዎቹ የዓረብ ቃላቶች ጥቂቶቹ ናቸዉ- ማንጁስ ማለት “ትንሽ ልጅ/አሽከር’ያልጠና’/ኩታራ” ማለት ሲሆን “ጃሱስ” ደግሞ “ሰላይ” ማለት ሆኖ “ዴማ/ዳይማ”-- ትግራይ ዉስጥ በዓዲግራት አካባቢ/አሲምባ….እና ዕዳጋሓሙስ የተባሉ ቦታዎችን ያማከለ ተራራማ ቦታ ነዉ-ቦታዉ ከደደቢት ቀጥሎ ወያኔ ለስልጠና ጣቢያ ያዘጋጀበት ቦታ ነበር-የመጀመሪያዉ ጠቅላላ ጉባኤዉ ያደረገበትም እዚህ ነበር)-በማለት ወያኔ የሚጠራዉ የዴማዉ ሰላይ “የ12 ዓመት ወጣት ህጻን ልጅ” ነዉ። ይህ ህጻን (1) በደርግ ተልኮ በስለላ ተግባር ተሰማርቶ የህወሐትታጋዮች ከሚጠቀሙባቸዉ የዉሃ ኩሬዎች መርዝ እንዲጨምር የተላከ ነዉ፤ በማለት እየደበደቡ ‘አዎ ተልኬ ነዉ የመጣሁት በል” እያሉ በማሰቃየት፣- (2) ታጋዮቻችን ወደ ደርግ ዓላማ ለመሳብ በስለላ ተግባር ተሰማርቶ ሲያደራጅ ያዝነዉ በማለት፣ ሸዊት በተባለዉ ታጋይ እና በወያኔዎቹ አባት ስብሓት ነጋ ታጋዮቹ በሙሉ ሲመረመሩ ምንም ማስረጃ ማግኘት ስላልቻሉ ገበሬዉንም በክሎታል በማለት ገበሬዎች እና ቄሶች ሳይቀሩ በሰበቡ የድብደባ ምርመራ ከተካሄደባቸዉ በሗላ ምንም ምንጭ ስላላገኙ በመጨረሻ እንዲረሸን የፈረዱበት “መሓመድ” የተባለዉ ይህ ህጻን እና ሌላዉ ወጣት በሃሰት እንዴት እንደረሸንዋቸዉ ካሁን በፊት በፊታዉራሪ ገዛ ረዳ ቃለ መጠይቅ እንዳስነበብኳችሁ ይታወሳል። ከተማ ገብቶ የመንግሥት ሥልጣን እንደነጠቀም ደ/ር ታየ ወልደሰማያትን ከዉጭ አገር ጉብኘት እንደተመለሰ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ሲመለስ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ላይ ያያዘዉ ሻንጣ ሲፈተሽ ታጣፊ መሳርያ አገኘንበት በማለት ለ6 ዓመት በሃሰት አስሮ እንደለቀቀዉ የምታዉቁት ታሪክ ነዉ። የሓሰት ምስክሮቹም በማናቀዉ ጉዳይ ላይ በሓሰት አንመሰክርም በማለታቸዉ የደረሰባቸዉ ስቃይ በወቅቱ የተለያዩ ጋዜጦች ዘግበዉት እንደነበር ይታወቃል። ሌላዉ ስለ የወያኔ የዉሸት ቀፎነት በዚህ “በኢትዮጵያን ሰማይ-በሎግ-”ላይ ያቀረብኩላችሁ የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የሰጡትን የወያኔ አሰራር እና ሰዉን ፣ድርጅትን እንዴት አድረጎ በሓት እንደሚወነጅል በሰፊዉ ተመልክተናል። ከዚህ ሌላ በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ላይ የደረሰዉ በመንግሥት ግልበጣ የሓሰት ዉንጀላ (በሙት ዓመታቸዉ በዚህ ወር ዝርዝሩ አቀርብላችሗለሁ) ታሪክ ወያኔ የሓሰት ምስክሮች እንዴት እንዳዘጋጀ የራሱ የወያኔ ታጋይ እና የደህንነት ሰራተኛ የነበረዉ በሗላ ከድቶት ወደ ኤርትራ እጁን በመስጠት ይህ ጉዱ ስላጋለጠዉ እና ለወደፊቱም በምስክርነት እንዳይቀርብ በማለት ስለሰጋ -ወያኔ ተከታትሎ በ2000 ዓ.ም ላይ ጋሽ- ባርካ ላይ እንዳስገደለዉ የሚወራዉ “ፍስሃ ሃይለማርያም””-የተባለዉ በሁኔታዉ እራሱ የተሳተፈበት የምርመራ ቅንብር የሰጠዉ ምስክርነት በYou Tube” ቴሌ ቪዥን የቀረበዉ ማስረጃ በማየት የወያኔ ማንነት መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ ወያኔ በዉሸት የፋፋ የዉሸት ቡድን እንደሆነ የሚታወቅ ነዉና ስለ ወያኔ የመፈንቅለ መንግሥት አስቂኙ ተዉኔት እዚህ ትትን ይልቁን እኔ የገረመኝ “ሙሉነህ እዮኤል” የተባለዉ ሌላዉ የግንቦት 7 አመራር አባል ነዉ የሚባልለት ወጣት በዚሁ የሰሞኑ አስቂኝ የመፈንቅለ መንግሥቱ ጋር የተያያዘ ስለ የድርጅት አለቆቹ እነ ብርሃኑ እና “አንዳርጋቸዉ ጽጌ” (በትናቸዉ ጽጌ) የጻፈላቸዉ የአርበኛነት ምስክርነት ገርሞኝ እሱን አንድ ለማለት ነዉ። ከዚህ መፈንቅለ መንግሥት የተባለለት የዉሸት ቅንብር ተያይዞ በር ተከፈተልን በማለት የግንቦት 7 ሰዎች ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀሙበትም እንደሆነ ግልፅ ነዉ። በግረመንገዳቸዉም የገንዘብ ማሰባሰብያ በር ከፍቶላቸዉ እንደለመዱበት መከረኛዉ የአዉሮጳ እና የዲ.ሲ ስብሰባ 6 እና 7 ሰብሰባዎች እናካሂዳለን በማለት ጥሪ እያስተጋቡ ነዉ። ከዚህ በተያያዘ ሰሞኑ ደግሞ ታክቲኩ ሁሉ አልሰራ ሲል “አርበኛ” የሚለዉ ቃል- “የሰሞኑ ባለ ተራ ቅመም” ሆኖ “እገሌ አርበኛ” በማለት በየመድረኩ ማንበብ ጀምረናል። ሁለት የወያኔ ተቃዋሚ ነን የሚሉን ጠንካራ ድርጅትን እና በጋራ የመስረሳትን ጅማሮ ያደፈረሱት “የዛኛዉ ጎራ”ታዋቂ ሁለት ሰዎች በተከታታይ ባጋጣሚም ይሁን በተጠና መንገድ የየራሳቸዉ ሰዎች “በአርበኛነት” በማቆላጰስ ወደ ሚዲያዉ መድረክ አቅርበዋቸዋል። አንደኛዉ እዚህ የተቸሁበት ፕሮፌሰር አለማዮሁ ገብረማርያም ስለ ደ/ር ሃይሉ አርአያ አርበኝነት ሲሆን፣ በተከታታይ ደግሞ “የግንቦት 7” ሦሰተኛ ሰዉ ነዉ የሚባልለት “ሙሉነህ እዮኤል” የተባለዉ በጸረ አማራነት የታወቀዉ ፣አማራን ለመበተን የኢትዮጵያን አንድነት ለማደፍረስ ለወያኔ አድሮ “የአማራ ሕዝብ ከየት ወደየት” በማጻፍ የታወቀዉ በብዙ ወገኖች “በትናቸዉ ጽጌ” በመባል የሚታወቀዉ “አንዳርጋቸዉ ጽጌ”ን “የአርበኛ ልጅ አርበኛ” በማለት ሲያቆላጵሰዉ አንብበናል። የ80ዓመት አዛዉንት ናቸዉ የሚባሉት የአንዳርጋቸዉ ወላጅ አባት አቶ ጽጌ ሰሞኑን መንግሥቴን ለማወክ ያዝኳቸዉ በማለት ትግራይ ዉስጥ አዛዉንት ወላጆቻችን እና ወንድሞቻችንን ያስር ይደበድብ ይረሽናቸዉ እንደነበረዉ ሁሉ ዛሬም ጉደኛዉ እና ዉሸታሙ ወያኔ እኝህ አዛዉንት ካሰራቸዉ ዜጎች አንዱ ሲሆኑ መሆናቸዉን ከልብ እናዝናለን።ጉዳቱ ካሁን በፊት በኛ በቤተሰቦቻችን እና ወንድሞቻችን ትግራይ ዉስጥ ደርሶብናል እና የሕሊና ቁስሉ እና ከባድነቱ ይገባናል።በዚህም በአንዳርጋቸዉም ሆነ በብርሃኑ ቤተሶበቻቸዉ የሚደርሰዉ እንግልት እንቃወመዋለን። ሆኖም፣-ይህችን ቀዳዳ በመጠቀም “ለወያኔ በማደር ያገሪቱ ሰራዊት ሜዳ ላይ ሲበተን፣ ዜጎቻችን ከኤርትራ ተባርረዉ በባዶ እግራቸዉ ተጉዘዉ አዲስ አበባ መጠለያ አልባ ሆነዉ ሲንከራተቱ አፋቸዉ የከደኑ ብቻ ሳይሆን ለመከራዉ አስተወጽኦ ያደረጉ፣ በሺዎቹ ታፍነዉ እነሱ ባዘጋጁት እስር ሲሰቃዩ ፣ በወቅቱ በስቃዩ ላይ ደስታን የጎነጩ፣ የኢትዮጵያን አንድነት በማፈራረስ ከፍተኛ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳና አስተዋጽኦ በማድረግና በመዲናይቱ ምክትል ከንቲባነት እና በመሳሰሉት ከፍተኛ ስልጣን በመመደብ ወያኔን እና ራሳቸዉን በመንግሥትነት አደላድለዉ ከታወቀዉ የኢትዮጵያ ጠላት ባንዳዉ መለስ እና ታምራት ላይኔ አፍላፍ ገጥመዉ ዊስኪ እና መጽሃፍ ሲዋዋሱና ሲጫለጡ የነበሩት አንዳርጋቸዉ እና ለስየ አብርሃ የመታሰቢያ መጽሀፍ የከተበዉ “ብርሃኑ ነጋን” በአርበኝነት ማቆላጰስ መቼም “ጋኖች አለቁና ምንቸት ጋኖች ሆኑ” ይባል የለ?። ሙሉነህ እዮኤል ሰሞኑን ያንዳርጋቸዉ ጽጌ ወላጅ አባት “በአስቂኙ መፈንቅለ መንግሥቱ”-የተያያዘ በመታሰራቸዉ ወላጅ አባትየዉ “አርበኛ”-ሲላቸዉ ለልጃቸዉ አንዳርጋቸዉን “የአርበኛ ልጅ አርበኛ”-በማለት የወላጅ አባቱን የአርበኛነት ማዕረግ ሲሸልመዉ እኔኑን ደነቀኝ። በተለይ-የመለስ ዜናዊ ወላጅ አባት “አቶ ዜናዊ አስረስን” “ባንዳ” ሲላቸዉ ልጃቸዉ መለስ ዜናዊን “የባንዳ ልጅ “ባንዳ” ብሏቸዋል። ይህ መቸስ በሽታ ነዉ። በሽታ ስላችሁ ሕክምና የማይፈዉሰዉ “የዘረኝነት በሽታ” ማለቴ ነዉ። እንዴት ነዉ ነገሩ ጭልጥ ያለ ነገር!?-የአርበኛ ልጅ አርበኛ ይወልዳል ያለ ማነዉ? ብዙ ያርበኞች ልጆች ልጆቻቸዉ “ባንዳ” ሆነዉ አገራቸዉና ታሪካቸዉ ሲያበላሹ ታሪክ የተዘገበ ነዉ። ሙሉነህ እዮኤል ለፕሮፖጋንዳ ስራ ካልሆነ ወይንም የፖለቲካ አለቃዉን አንዳረጋቸዉ ጽጌን ለማስደሰት ካልሆነ ፣እንዳርጋቸዉ ጽጌ በአርበኝነት የሚያስጠራዉ አንድም ማስረጃ አላቀረበልንም። ታድያ እንዴት እንዴት ሲኮን ነዉ ያለ ማስረጃ አርበኛ ብለን አንዳርጋቸዉን የምንጠራለት? ሙሉነህ እዮኤል ወየኔን “ባንዳ” ነዉ ብሎታል፣- ወያኔ ባንዳ መሆኑን ካመነ- እንዴት ሲሆን ነዉ ያርበኛ ልጅ ለወያኔ ለባንዳዉ አድሮ ከሚገባዉ በላይ ወገቡን ለዘረኝነት ብቅል ሰጥቶ ዘረኝነት እንዲበቅልበት ፈቅዶ “የኦሮሞ ትዉልድ ሐረጉ እየመዘዘ - አማርኛ መናገሩን አንጂ አማራ እንዳልሆነ መጽሐፍ ጽፎ እየዘረዘረ አማራንና ኢትዮጵያዊነትን ያጥላላ ግለሰብ ያዉም’ኮ “ኢትዮጵያዊነት- የዘረ-ቢሶች መሸሸጊያ” በማለት መጽሐፍ የጻፈ ፣ አማራ ሳይሆን “ስለ አማራ ሕብረተሰብ በመጥፎ ጎኑ መጽሐፍ የጻፈ” መጪዉን ትዉልድ ሊያባላ የሚችል አደገኛ ጽሑፍ የተወልንን ሰዉ በምን ሂሳብ ነዉ በአርበኛነት ሊመደብ የሚችለዉ? የአርበኛ ልጅ በእንደዚህ ያለ ጉደኛ ታሪክ ራሱን ሲነክር አርበኛዉ አባቱ አይቀየሙትም ወይ?-ሙሉነህ እዮኤል አማራ ቢሰደብ ባይሰደብ፤ ጉዳዩ አላለዉም፤ አለቃዉ “ኢትዮጵያዊያን ንነ የምንል ሁሉ “ብሔር የሌላቸዉ ዘረ-ቢስ ቢለንም” ሙሉነህ ጉዳይ አላለዉም። የሙሉነህ እዮኤል ሁለተኛዉ ያስገረመኝ ጽሑፉ ደግሞ ወያኔን “አምባ ገነን ቡድን”-ማለቱ ነዉ።ለመሆኑ መኢሶን ደርግን “አምባገነን”-እንዲሆን “እንዳርጋቸዉ እና ጓዶኞቹ”” ወያኔንን “አምባገነን” እንዲሆን ዕድሉን የሰጧቸዉ አይደሉምን?-ታዲያ ወያኔ አምባ ገነን እንዲሆን በከፍተኛ የፖለቲካ ቦታ ተመድቦ ያገለገለዉ አንዳረጋቸዉ “አርበኛ” ማለት ዜጎችን አያስቆጣም? ሙሉነህ እዮኤል ወያኔ ትምህርት መቀጠል አለብኝ ካልክ ሂድ ቀጥል በሎ እንደተቀሩት በኬኒያና በባሌ በመከራ ተሸሽገዉ እና ተሰቃይተዉ ሳይሆን “በቦሌ”በክብር የሸኘዉን ወያኔን ምስጋና አይግባዉና እዚህ ድረስ አሸጋግሮ ፈቅዶ የጓደኛዉን የአንዳርጋቸዉ ጽጌን (ጓድ/ጓድ ቁልጵስ) አርበኛነት ማዕረግ ሊያስሰማን መብቃቱ እዉነት ወያኔ “ዉለህ አትግባ” ከማለት ምን ማለት ይቻላል? ሙሉነህ - አስቲ እንደዉ፣ እንደ ብጻዩ/ጓዱ እንደ ብርሃኑ መዋ ድምጹን አጥፍቶ ዉስጥ ለዉስጥ ስራዉ ቢሰራ ምን አለበት? በዚህ ጉዳይ እህቴ “አያልነሽ” በሚጣፍጠዉ አማርኛዋ በሚገባ ገልጻዋለችና ብዙም ለማለት አልፈልግም። ስለ አስቂኙ መፈንቅለ መንገሥቱ ግን አንድ ሁለት ብየ ልዝጋ። ለመሆኑ ብርሃኑ ነጋ በምን ሃሞቱ ነዉ አሜሪካ ተቀምጦ ጦር እያስላከ ወያኔን ለማስወገድ የሚሞክረዉ? ነገሩ ነገር ቢኖረዉም (መፈንቅለ መንግሥት ባይሆንም) ከብርሃኑ ነጋ የተጠነሰሰ ሴራ እንዳልሆነ ብዙ ሰዉ ይገምታል ።ወያኔ አገዛዙ እየከፋ ስለሄደ በወታደሩም በሲቪሉም ወያኔን በሚችለዉ መንገድ ላለመታዘዝ መሞከሩ አያሌ የማይባል ነዉ። አዲስ ነገርም አይደለም። የብርሃኑ ሃሞት ግን ያየነዉ ነዉ። ድሮ በኢሕአፓ ታሪኩም ሆነ ዛሬ ሴት ልጅቷን ብርቱካንን አጋልጦ ካዲስ አበባ ሸሽቶ በዋሽንግተን -ዲሲ እና በአዉሮፓ በካናዳ የትኩሳቱ መልቀቂያ እና የጉራ መድፈቂያ መድረክ ተዋናይ ከመሆን ሌላ በምን መራራ ሃሞቱ ነዉ እንዲህ ዓይነቱ ስራ የሚሰራዉ? አይሞክርም ሳይሆን ብርሃኑ እና አንዳረጋቸዉ ለእነደዚያ ዓይነት ተልእኮ ዘሎ የሚገባ ሕሊና እና ሃሞት የላቸዉም! እመኑኝ! ከነሱ ይልቅ ሴቲቱ ብርቱካን መቶ በመቶ በወንድነቷ ምረጥ ቢሉኝ አማራጭ ካጣሁ እሷን እምርጥ ነበር። ወያኔ ዋሽቶ መወንጀሉ ላይቀር ዉሸቱን አሳምሮ ቢዋሽ እና የመኢሶኑ የ ዶ/ር ነገደ ጎበዜን የኩባዉና የየመን ሪፑብሊክ አምባሲዎች ትብብር በሌተናል ኮሎነል መንግሥቱ ሃይለማርያም የታቀደዉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ዓይነት ሲደረግ እጅ ከፍንጅ ደረስኩባቸዉ፣ ቢልና ብርሃኑ ነጋ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወርዶ በደህንነት ጥበቃ ሰራተኛችን በመታየቱ -ለምን እንደመጣ ደህንነት ሰራተኛዉ ቢጠይቀዉ “የእርቅና የሰላም” ድርድር በሚመለከት ስብሰባ ለማድረግ በመንግሥት መጋበዙን ገልጾለት-ሲያበቃ ደህንነቱ ይሄንኑ ለማስታወቅ ወደ አለቃዉ ሄዶ ሲመለስ አጅሬ “ብርሃኑ ነጋ”-ስሙን ለጊዜዉ ለመግለጽ ያልፈለግነዉ በአንዱ በ----------አዉሮጳ አምባሲ አጃቢዎች ታጅቦ በምስጢር በመኪና ተወስዶ መደበቁን ደርሰንበት ደረግ ዶ/ር ነገደ ጎበዜን እንደሸኘዉ እኛም በድርድር አገር እንዲለቅ ሆኗል። ብሎ አሳምሮ ቢዋሽ ምንኛ ታሪኩ ተደማጭነት ባገኘ ነበር። ግን አልቻለበትም! · ብርሃኑም አንዳርጋቸዉም ወያኔንና መለስ ዜናዊን አገልገለዋል፣ አክብረዋል፣ አቆላጵሰዋል ዊስኪ ተጫልጠዋል።ሃይለ ፊዳ እና ጓዶኞቹም ሌተናል ኮሎኔል መንግሥቱን አገልገለዋል፣ አክብረዋል፣ አቆላጵሰዋል ዊስኪም ተጫልጠዋል። ስለዚህ እነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳረጋቸዉ “ግንቦት 7” ብለዉ ራሳቸዉን ቢጠሩም ሰዎቹ “የወያኔ-መኢሰኖች”-ናቸዉና ከጓዳቸዉ ከበረከት ስሞን ጋር ሲማከሩ፣ ሲለሳለሱ እና ሲያቅማሙ የግንቦቱን ሕዝባዊ እሮሮ አክሸፉት (የቤት መቀመጥ አድማዉን ልብ ይለዋል)። ከወያኔ መኢሰኖች ብዙም አልጠበቅንም ትናንትም ዛሬም ነገም ። የደርጉ የሃይለ ፊዳ መኢሰኖችና እና የወያኔዎቹ የአንዳርጋቸዉ/ብርሃኑ “የወያኔ መኢሰኖች”ልዩነታቸዉ የደረጎቹ መ ኢሰኖች ሃገራዊ አንድነት እንዳይላላ የታገሉ ኢትዮጵያዊነትን ያስቀደሙ ከዘረኝነት የጸዱ ሲሆኑ፣ የደርግን መነግሥት በጥበብ ለመጣል ደርግን የተደባለቁ ጊዜዉን ያላገናዘቡ ፖለቲከኞችና የደርግን ዙፋን የገነቡ ሲሆኑ”። የእነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳረጋቸዉ “የወያኔ-መኢሰኖች”ግን አማራን የሚጠሉ ዘረኞች፣ ለወያኔ ያደሩ ፣ ካለ ወያኔ በቀር በራሳቸዉ ህልዉና እና ፖሊሲ መቆም ያልቻሉ፣ ጥገኞችና፣ አገር ሲፈርስ ሮጠዉ አገር ገብተዉ ኩት…ኩት..እያሉ የወያኔ አለቆችን ባሽከርነት እየተከተሉ “ባንዳዎች”ብለን ከምንጠራቸዉ የወያኔ መሳፍንት አለቆች ጋር ዊስኪ ሲያንቃርሩ “ፎቶ መነሳት”እንደኩራት የሚቆጥሩት “አሳፈሪዎች”፣ የባሕር በሮቻችን ሲዘጉብን ኡኡ ስንል ያማራ ትምክህተኞች እሮሮ እያሉ “ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ” ሆነዉ የወያኔን ዉሳኔ ተቀብለዉ ያስተጋቡ ናቸዉ ። · ዋ! ዋ! ያዉም እኮ ፣ “የአርበኝነት የምስክር ወረቀት” በ$500 ዶላር እንሸጣለን በማለት በታሪክ ያልተሰማ.-ያልተደረገ “ምጻእተ ዓለም /ጉድ!”አርበኝነትን ማዕረግ ችርቻሮ ገበያ ንግድ ዉስጥ የገቡ እኮ ናቸዉ!እናንት ወንድሞቼ/እህቶቼ፣- በኢሕአፓ አባሎችና ደጋፊዎቻቸዉ ጥረት.፣ መስተንገዶነት፣ ጽ/ቤት ቅርንጫፎቻቸዉ በአዉሮጳም በአሜሪካም ክፍት አድርገዉ እነ ሃይሉ አርአያም እነ ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዉልም እነ ልደቱ አያሌዉን አሰባስበዉ አስከ ቅንጅት ሕብረት ድረስ እንዲጎለብሱ እና ተበታትነን የነበርነዉን ህብረተሰቦች ጸረ ወያኔ ቆመን እንድንታገል ከጅምሩ የተተከለዉ የሕብረት ችግኝ ዉሃ አየርና እና ማዳበርያ ሆነዉ በማሳደግ፣ በማጠናከር ያደረጉት በታሪክ የማይረሱ ሸጋዎቹ “ኢሕአፓዎች” ከማመስገን ይልቅ (የብርሃኑ መዋ እና የአንዳርጋቸዉ ሴራ እንዳለ ሆኖ) ብርሃኑ ነጋ ከእስር እንደተፈታ ዉጭ አገር መጥቶ ዋሽንገተን ዲሲ አዳራሽ ገብቶ ከአፍዓበት የመጣ አርበኛ ይመስል “አበባ እና ዘምባባ ሲጎነጎንለት”-የመጀመርያ ዲስኩሩ ዘለፋ የጀመረዉ በወያኔ ሳይሆን “በኢሕአፓ” ላይ ነበር ያነጣጠረዉ (ስልጡንና የፋራ ፖለቲካ በማለት-የስድቡ የሽርደዳዉ ጉንጉን ምን ይል እና ለማን ይዘልፍ እንደነበር የምናዉቀዉ እናዉቀዋለን)። በዚህ ዘዴ ነበር “የብተና ስራቸዉ የጀመሩት” ። · ቀጥሎ በወያኔ እና በኢሕአፓ ላይ እያደባለቀ ተደጋጋሚ የብተና ፕሮፖጋንዳዉ እና ስድቡ እንዳጦፈዉ በኢንጅነር ሃይሉ ላይ በተቀነባበሩ ዘረኞች በየመድረኩ እና በየሚድያዉ አስሰልፎ ጅላጅል ብርቱካንን ፊት-ፊት በማስቀደም እሱ ከሗላ ምን ማለት እንዳለባት እያጣደፈ ሕብረቱን በትኖ ሲያበቃ፣-ልጅቷንም ጥሎ አሜሪካኖች ገንዘብና ቀለብ ሰጥተዉት ሳትሰራ ሳትለፋ “ተራራ ላይ ወጥተህ ቁጭ ብለህ ተፈላስፍ”-ብለዉኛል ብሎ እዚህ “ፋራዎች-ከሚለን የፖለቲካ አዛዉንቶች ጋር ቀረ። የምስኪኒቷ ድርጅትም አስዋን ለእስር ዳርገዉ ኢንጅነር ሃይሉን አምባገነን ባሉበት አፋቸዉ ዛሬም በፕሮፌሰር መስፍን አፍ እርስ በረስሳቸዉ “አምባገነንነት እና ስርዓተ አልበኝነት ማን ያዘኛልነት እና ገለልኝነት” አዲሱን ፓርቲዋን ዉጦታል እያሉ በገዛ ብዕራቸዉ እየነገሩን ነዉ! · አንግዲህ ይህ ሁሉ አፍራሽ ተግባርና ባሕሪ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ተጋግሎ የነበረዉ የሕዝቡ ወኔ እና ሕብረት ላይ “ቀዝቃዘ ዉሃ ሲቸልሱበት” ያረርነዉን እንዳይበቃ መላልሰዉ የሚጽፉት ፕሮፖጋንዳ እና-ጉራ“ቁጣችንን የሚያበረድ ሆኖ አላገኘሁትም!”-አሁንም አሁንም ጉራቸዉ ሰንጢ የማይበጣዉ ሆኖ አሜሪካ እና አዉሮጳ በመዞር እየተንገዋለሉ እነ አንዳርጋቸዉን “አርበኞች” በሉልን ሲሉን- በ እውነት እላችሗለሁ በመንገስቱ ሃይለማርያም ፊት ቆመዉ አንድ “ቄሱ” እንዳሉት የዚህ ዕብጠት ትርጉም “እኔ- እየጠበበኝ መጥቷል”። በቻ ለማንኛዉም በወሎየዉ በሸኽ ጅበሪል ምርቃን/ሀድራ “አላህ ይሁናችሁ አላህ ይሁነና” ከማለት ምን ማለት ይቻላል?