Sunday, December 28, 2008

ዜጎች ሲገደሉ ወደ ዲሞክራሲ የሚወስድ የሽግግር ሂደት ገበያዉ ሲንርም የዕድገት ምልክት ነዉ ይሉና ኩርር ኩርርር! ጀሮ ያሳምማል።

ዜጎች ሲገደሉ ወደ ዲሞክራሲ የሚወስድ የሽግግር ሂደት

ገበያዉ ሲንርም የዕድገት ምልክት ነዉ ይሉናል!
ኩርር ኩርርር! ጀሮ ያሳምማል
ጌታቸዉ ረዳ
ትችቱ ለቀድሞዉ የወያኔ መስራች ዛሬ በአሜሪካን ሀገር በሎስ አንጀለስ ከተማ ለሚኖሩ ለአቶ ሃይሉ መንገሻ ነዉ።
ወደ መነሻ ጉዳየ ከመግባቴ በፊት ዓምና የሰማሁት ሁላችሁም የምታዉቋት ዶክተር ሙሉወርቅ ቀጸላ የተባለችዋ “ወያኔ” (የትዉልድዋ ከተማ -“አክሱም”) ይግረማችሁ ብላን “ሃያ የአፍሪካ ድሃ አገሮችን በልማት ማፋጠን ጉዳይ እወክላለሁኝ”-የምትለዋ ስለ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዕድገት ምጥቀት “ገዛ ተጋሩ” (የትግሬዎች ቤት) ተብሎ በሚጠራዉ ብዛታቸዉ ከ10 እሰከ 20 የተሰብሳቢ ብዛት አድጎ የማያዉቀዉ “የወያኔ-ኩታራዎች እና ወፈፍተኞች”–የሚጯጯሁበት “የኢንተርኔት ገበታ” በእንግዳነት ተጠርታ ስታወራ፦”ከጨቅላዎቹ” አንደኛዉ የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት እንዳደገ ከተስማማ በሗላ እንዲያም ሆኖ ገበያዉ “ለምን አልቀመስ”-እንዳለ እንድታብራራለት ሲጠይቃት “ማደጉን በተለመደዉ በወያኔአዊ ዉሸቷ “በመቶኛዉ”-የተወሰ ስሌት በየአመቱ ያደገዉን መጠን ካስቀመጠችለት በሗላ -ለዋጋዉ ንረት ምክንያት “የሕዝቡ ኑሮ እየተሻሻለ በመምጣቱ እና የመግዛት አቅሙና ፍላጎቱም በዛዉ መጠን እያደገ በመምጣቱ ዋጋዉ *ሊንር* ችሏል” ስትል-
በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔን ከመሰረቱት አንዱ የሆነዉ “አቶ ሃይሉ መንገሻ” የተባለዉ፤ከ7 ዓመት በፊት እነ ስየ አብርሃ ከመለስ ዜናዊ ጋር ተጣልተዉ ለሁለት ሲከፈሉ መለስ ዜናዊ የሚመራዉ ስርዓት *ዘረኛ/አፓርታይድ/ከፋፍለህ ግዛ እና ጎጠኛ እና አምባገነን* ስርዓትን ነዉ ብሎ የሰየመዉን የወያኔ መንግሥት ዛሬ ግን ዶክተር ሃይሉ መንገሻ በቪኦኤዉ የትግርኛ ፕሮግራም ቀርቦ “የወያኔ መንግስት ሰዉ መግደሉን ማሰሩን ማፈኑን፤ዜጎችን አፍኖ ማጥፋቱን የሚታማዉ እዉን ከሆነ (ወያኔ ጥፋተኛ ይሁን አይሁን የማዉቀዉ ነገር የለኝም ይል እና፤-ያዉም ባሁኑ ሰዓት ወንጀለኛዉ ፤ጥፋተኛዉ “እየተጣራ” መሆኑን መረጃ አለኝ ሲለን) እንደችግር ሆኖ- ድርጊቱ ብቃወመዉም የዲሞክራሲ ሂደት ፕሮሰስ ነዉ” ሲሉ ለመለስ ዜናዊ ስርዓት ጥብቅና በመቆም ለትግርኛ ተነጋሪዉ የትግራይ ህዝብ አቋሙን ይፋ አድርጎልናል።
- ዶክተር ሙሉወርቅ ቀጸላ እና ዶክተር ሃይሉ መንገሻ የተማሩት ዱክትርና የሗሊት ሩጫን እንደ ዕድገት መቁጠራቸዉ ከማስገረሙ በላይ ለኩታሮቻቸዉ የሚያስተምሩትን ግብዝነታቸዉን እና ዉሸታቸዉን ወደ ህዝቡ ለማሸጋገር ሲሞክሩ ዝም ማለት ስለማይገባ በዚህ አንድ ልበላችሁ።
ወደ አቶ ሃይሉ ከመግባቴ በፊት የሙሉ ቀጸላን አባባል እንመልከት። ዕደገት ገበያ አስወድዶ ንረት የሚያስከትል ከሆነ “የማደግ ትርጉሙ” *ድህነት* እንጂ እንዴት አደግን ሊባል ይቻላል? ድህነት እና ዕድገት ደግሞ በትርጉምም በሚሰጡት ዉጤትም የተለያዩ ናቸዉ። *የገበያ ዉድነት* በሰዉ ልጆች ኣእምሮ ከባድ ጫና የሚያስከትል ሕሊናን ወጥሮ ዕረፍት ነስቶ ኑሮን የሚያቃዉስ፤ጭንቀትና ብስጭት ጥበት እና ንዴት የሚያስከትል ክስተት መሆኑ እየታወቀ “አንድ አገር በምጣኔ ሃብት አድጓል ከተባለ እና የሕዝቡ የመግዛት አቅም እና ፍላጎትም አድጓል ከተባለ ፤በአንጻሩ ግን የገዡዉ አቅም አድጎ የመግዛቱንም ፍላጎት በዛዉ መጠን አድጎ *ገበያዉን” የሚያስወድደዉ ከሆነ *ከማደግ* ይልቅ *መደህየቱ* ቢመረጥ ጥፋቱ እምኑ ላይ ነዉ? የዕድገት ዋነኛ ፍላጎቱ ህዝቡ በተመጣጣኝ በለዘብተኛ እርከን እቃዎችን ሸምቶ ቤተሰቡን አስተዳድሮ በልቶ ጠጥቶ *ጭንቀት እና ብስጭትን ጥበት እና ንዴትን* ከሕሊናዉ እና እህል አምሯቸዉ በመወደደዱ ምሳ ባለማግኝታቸዉ ከሚያለቅሱ ልጆቹ ሕሊና ለማስወገድ ነዉ። የወያኔ ካድሬዎች የሚሉን ግን “ዕድገት አለ- ነገር ግን ዋጋዉ አልቀመስ አለ” ይሉናል። ለምን ቢባሉ ደግሞ ሕዝቡ “በገንዘብ ስለተምበሸበሸ” “የሕዝቡ የመግዛት አቅም ስለጎለበተ” “ሃብታም ስለሆነ” “ዕቃ መግዘት ስላማረዉ” እቃዉ ተወደደ ይሉናል። የመግዛት አቅም መጎልበት እና የፍላጎት ጉግት የእቃ እና የገበያ ንረት አስከትሎ የሚያስወድድልን ከሆነ “ዕድገት” የሚሉት “ገደል ይግባ” ማለታችን እንዴት ስተተኞች መሆን እንችላለን? ኢኮኖሚዉ ብቻ መሰላችሁ በተሳሳተ የትርጉም ሃዲድ የሚያስኬዱት ፖለቲካዉም ጨምሮ፤ሰብአዊ ረገጣዉንም ጨምሮ ያዉም እኮ *መግደል፤ማፈን፤መደብደብ፤አፍኖ ማጥፋት* የሰብአዊ መብት መርሆ መረገጥን *የዲሞክራሲ መሸጋገርያ ምልክት ነዉ* ይሉናል። ዜጎችን መረሸን ማሰር መደብደብ ጋዜጠኛን ማዋከብ ፍርድ ቤቶችን በመዳፍ ማሽከርከር በሽግግር ወቅት የሚከሰቱት የዲሞክራሰቲክ ሂደቶች ናቸዉ እና ዲሞክራሲ ባንድ ቀን ስላማይገነባ *ስንገድላችሁ፤ስናንገላታችሁ ‘ዋጥ’ አርጉት* ይሉናል።
“ወያኔ በሩን ገርበብ አድርጓል እና እናንተ ዉጭ ሀገር ሆናችሁ አትጨሁበት አትዉቀሱት አትክሰሱት” የሚሉንን እንደ እነ ሃይሉ መንገሻ ዓይነቶቹ “ግርምቢጥ ፖለቲከኞች” እና ደም የጠማዉ ቡድን አፈቀላጤዎች ላለመወቀስ ላለመከሰስ የሚሰጡን *የወንጀል ማምለጫ* ምክንያታቸዉ ‘ግድያ እና የመብት ረጋጣ’ “ወደ ዲሚክራሲ ሚሸኘን የሽግግር ምልክት ነዉ” ይሉናል።ኩርር ኩርርር! ለጀሮ ይቀፋል።
ባለፈዉ ሁለት ሳምንታት በተከታታይ የቪኦኤዉ የትግርኛዉ ክፍል-አራት ኢትዮጵያዉያን ትግርኛ ተናጋሪዎችን ስለ ሰብአዊ መብት መረገጥ ወይንም አለመረገጥ እና ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት ማደግ በወያኔ ስርዓተ ዘመን የሚታዩት ክስተቶች ለአድማጮች እንዲያሰሙ ጋብዟቸዉ ነበር።በ እንግድነት የቀረቡት ሦሰት የህወሓት መስራቾች “ዶክተር አረጋዊ በርሄ” “አቶ ግደይ ዘርአጽዮን” “ዶክተር ሃይሉ መንገሻ” እና አራተኛዉ “መስፍን አየለ” የተባሉ ካሁን በፊት ሰምቻቸዉ የማላዉቃቸዉ እንግዳ ተጋብዘዉ ተከራክረዋል። አራተኛዉ እንግዳ ሙሉ በሙሉ ወያኔዊ ድጋፍ ስላሳዩ አሳቸዉን ትተን እኛ በምናዉቃቸዉ በሦስቱ የወያኔ መስራቾች ክርክር አናትኩር።
ሦስቱም የወያኔ ገበና ያጋልጣሉ ብየ ጠብቄ ነበር። ከግምቴ ዉስጥ ቃላቸዉ ጠብቀዉ ያገኘሗቸዉ ሁለቱም ዶክተር አረጋዊ በርሔ እና አቶ ግደይ ዘርአጽዮን ሲሆኑ ዶክተር ሃይሉ መንገሻ ግን አገር ከማስተዳደሩ በፊት የአእምሮ ጠንነቱ በአእምሮ ሃኪም መመርመር አለበት” በማለት የመለስ ዜናዊ “ንክነት” Who is Meles Zenawi? በሚለዉ ሃይሉ በጻፈዉ ጽሁፉ ድሮ “ንክ” ያሉዉን ‘ሰዉ በላዉ’ የመለስ ዜናዊን “የንክ” ስርአት እንደገና ሲደግፉ ተደምጠዋል ። እስኪ ሦስቱም ሰዎች ከተናገሯቸዉ ጥቂቱን ላስነብባችሁ እና የአቶ ሃይሉ መንገሻ አስተያየት ወደ መጨረሻዉ እንሄድበታለን። አነሆ-
ቪኦኤ- ጥያቄ፦በኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብአዊ መብት ረገጣ አለ የምትሉት ነገር ካለ ከያንዳንዳችሁ ብታብራሩልን? አቶ ግደይ ዘርአጽዮን
* በኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብአዊ መብት ረጋጣ እንዳለ በሰፊዉ ከተለያዩ የኢንተርናሽናል ድርጅቶች የሰብአዊ መብት ረገጣ በከፋ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ተረጋግጧል። * ስርአቱ ፍረድቤቶቹን ወደ ፈለገበት አቅጣጫ በመጠምዘዝ “ሆን ብሎ” ነጻ ዳኝነት እና ነጻ ዳኞች እንዳይኖሩ የሚያግድ ነዉ። * በሺዎቹ ታፍሰዉ እና ታፍነዉ አስካሁን ድረስ የት እንዳሉ ድራሻቸዉ የማይታወቁ አሉ። * ሲቪክ ተቋማት ሆን ብሎ የሚዘጋ፤ጋዜጠኞች ሚያስር፤የሚያፍን ስርዓት ነዉ። * ሕዘብ የመረጣቸዉ ተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች ያለ ምክንያት የሚያስር ነዉ።
ዶክተር አረጋዊ በርሄም በተማሳሳይ የመለስን ስርዓት ኩፍኛ የተጠናወተዉ አምባገነን ለመሆኑ እንደሚከተለዉ በማስረዳት ተከራክረዋል። * ሰብአዊን መብት በሚመለከት ጉዳይ ካነሳን ዘንዳ እንደዚህ ዓይነቱ መንግሥት የከፋ መንገሥት ከቶ ተፈልጎ አይገኝም። ለምሳሌ ጋዜጠኞች በማፈን እና በማሰር ከአፍሪቃ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 2ኛ ደረጃ የጋዜጠኞች መብት ረጋጭና አፋኝ ተብሎ ተሰይሟል። ከዚህ የከፋ ስም ምን አለ? የመናገር የመደራጀት መብት የሚረግጥ መሆኑን ተረጋግጧል።
* ይህ መንግሥት ከመሰረቱ ስንመለከተዉ በማፈን ብቻ ሳይሆን በመግደልም ያምናል።ለምንድነዉ ተቃዋሚዎቹንን የሚገድላቸዉ? ከእርሱ የተለየዉን ሃሳባቸዉ ስለገለጹ *ብቻ*።ዜጎች በማሰር እና በማፈን አጥፍቷቸዋል ስንል በሺዎቹ የሚቆጠሩ ናቸዉ።የለ ፍትህ ይይዛል፤ ያስራል፤ ይሰዉራቸዋል።ስየ አብርሃም ሆነ የቅንጅት መሪዎች ሲያስራቸዉ ያለ ምንም የወንጀል ጥፋት ነበር ያሰራቸዉ።ሲያስራቸዉ ሕግ ያልተከተለ የማን አለብኝ ያምባገነንነኖች ስራ ነዉ።
ቪ ኦ ኤ፦ ዶክተር ሃይሉ መንገሻ በዚህ ረገድ ያለዎትን አስተያት?
+++ይህ መንግሥት በአንድ ጀምበር በአንድ ንጋት አዉሮፓዊ እና አሜሪካዊ አይነት ዲሞክራሲ መልክ መያዝ አለበት ብሎ መከራከር ተገቢ አይደለም። ይህ መንግሥት “ፖዚትቭ” መንገድ እየተከተለ ነዉ ወይ? Yes! ፕሮሰሱን Processን ነዉ ማየት ያለብን እንጂ በአንድ ሌሊት “ዲሞክራቲክ” መሆን አለበት ብሎ መከራረከር ልክ አይደለም።እኔ የኢትዮጵያን መንግሥት የምመለከተዉ የዲሞክራሲዉ “ፕሮሰስ” የችግሮች አፈታት “ካልቸር” ከተቀሩት የአፍሪካ አገሮች ከሚከተሉት አስተዳደር የማወዳድረዉ እንጂ “ግደይ” ኖርወይ ሆኖ ወይም “አረጋዊ” ሀላንድ ሆኖ “እኔ” አሜሪካ ሆኘ በምንለዉ ወይንም በምናየዉ የኢትዮጵያን አስተዳደር መፍረድ አንችልም። በእርግጥ “ግደይ” እንዳለዉ በምርጫዉ ጊዜ ብዙ ሰዉ አልቋል።ቢሆንም ለእልቂቱ ለወንጀሉ ተጠያቂዉ እና ጥፋተኛዉ ማን ነዉ ለሚለዉ ለመለየት “ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አዉቃለሁ”peace and order ለማምጣት የግድ አንድ ነገር ለማድረግ ትገደዳለህ (ልብ በሉ- ‘ፒስ ኤንድ ኦርደር’ ለማምጣት ወደዳችሁም ጠላችሁም የመግደል አማራጭ የለዉም እያለን ነዉ። እሱ በሚያስተዳድረዉ በአሜሪካ ት/ቤት ረብሻ ቢነሳ የ197 ሰዎች ሕይወት በፖሊስ ጥይት ቢጠፋ “ፒስ ኤንድ ኦርደር” ለማስያዝ “የግድ /መግደል/ ነበረባቸዉ ማለት ነዉ።ወታደሮቼ ከጫካ ስለመጡ ትምርት ስላነሳቸዉ የስብሰባ መበተኛ መሳሪያ ስላልነበራቸዉ የግድ “መግደል ነበረባቸዉ” ብሎ ያለንን መለስ ዜናዊ ነዉ ዛሬም ሃይሉ መንገሻ በደመቀ መልኩ በደማቅ ቅብ ቀብቶ እያቀረበልን ያለዉ።- /ሃይሉ መንገሻ ወያኔ መስርቶ “ዓዲ ሃገራይ” (ሽሬ አዉራጃ ዉስጥ) ሲፈልጥ ሲገዛ አሰቃይቶናል ያሉትን ሰዎች ልያስታዉሰን ነዉ/አንዳንዶቹ እማ የተሰወሩት ሰዎች ስም እየጠሩ አፍኖ ያጠፋቸዉ ዜጎች እና በከባድ የጭካኔ ምርመራና ዉሳኔዉ ይከስሱታል- “ይሄነን በይደር እናቆዉ”)። ይቀጥል እና ሃይሉ መንገሻ እንዲህ ይላል <“ይህ ማለት አፍኖ መዉሰድ መግደል ተደርጓል የሚባለዉ እንዲያ እንዲአደርግ አልደግፈዉም፦ነገር ግን “የዲሞክራቲክ ሂደት process ነዉ”።ይህ መንግሥት የዲሞክራቲክ ሂደት ፕሮሰስ ከጀመረ በግምት ከ15/16 ባጠቃላይ ከ12 ዓመት አይበልጥም። in fact እኔ የማየዉ በሚከተለዉ መንገድ ነዉ፡_ “ኢንስቲትዩሽኖች አሉ ወይ? ተከሳሾች በሕግ ፊት ቀርበዉ ጠበቃ ቁሞላቸዉ እንዲሞግትላቸዉ የፈቅዳል ወይ? የሄ መንግሥት accommodating /አኮመደቲንግ ነዉ ወይ? ዲፈረንስስ ወይም ያለ መረዳዳት ሲከሰት ልዩነቶች ለመፍታት በሰለማዊ መንገድ ይሞክራል ወይ? ሌላ ቀርቶ *ጠላቶቼ የሚላቸዉ ሞገደኞች/አመጸኞች የሆኑት እነ ቅንጅት ጋር ሆኖ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት የሞከረ ምንግሥት ነዉ*። ተቃዋሚዎች እንደልባቸዉ እየተሳደቡ ዉጭ አገር እየሄዱ ወደ አገር ዉስጥ እየገቡ በነጻነት እየወጡ እየገቡ መዉጣት እና መግባት የሚችሉ ከሆነ “አስተያታቸዉ” መግለጽ ከቻሉ “ወደ ጤነኛ” መንገድ እየመራን ነዉ ማለት ነዉ የሚል እምነት ነዉ ያለኝ።ለኔ የዲሞክራቲክ በር መክፈቱ ቢቂ ነዉ። እነኚህ ለዉጥ የለም የሚሉን ሰዎች “ጭፍኖች” ናቸዉ። እኔ ካልገዛሁ እሾህ ይብቀልበት የሚሉ ሰዎች ናቸዉ።>>
ዉድ ወገኖቼ እንግዲህ አቶ ሃይሉ መንገሻ ያነበነበዉ የወያነ መጽሃፍ ቅዱስ አንድ ባንድ ስህተቱን ለማሳየት ብንሞክር መጽሃፍ ሊያስጽፍ ነዉ እና ካሁን በፊት ወደ መለስ ዜናዊ አጋርነት ከመጠምዘዙ በፊት መለስ ዜናዊን ይተች በነበረበት ወቅት፡ የገዛ ብዕሩ እና ካደረጋቸዉ ቃለ መጠይቅ ምን ብሎ ይነግረን እንደነበር አንዳንዶቹን ለማስረጃ እንሂድባቸዉ።
ዛሬ በ ቪኦ-ኤ ቀርቦ አቶ ሃይሉ እየነገረን ያለዉን የመለስ ዜናዊ ዲሞክራትነት መሆን የጀመረዉ ቀደም ብሎ 15 እና 16 ዓመት በጠራ መንገድ ግን የዲሞክራቲክ ፕሮሰስ ከጀመረ 12 ዓመት ሆኖታል ብሎናል። አቶ ሃይሉ መንገሻ መለስ ዜናዊን - “ንክ” ወይም የአእምሮ በሽተኛ ስለሆነ አገር ማስተዳደሩን ትቶ መጀመሪያ “የአእምሮ ሃኪም ማየት አለበት” በማለት Who is Meles Zenawi? በሚለዉ ጽሁፉ ብዙ ብዙ የነገረንን ዘንግቶ ያዉም ከነገረን 6 ዓመት ባልሞላዉ ጊዜ ዉስጥ ዛሬ እየነገረን ያለዉ ደግሞ የ “ንኩ” ሥርዓት *ዲሞክራቲክ ፕሮሰስ* እየሆነ ዲሞክራቲክ መሆን ከጀመረ “ነገሮችን በሰላም መፍታት ከጀመረ፤ተከሳሾችን በነጻ ዳኛ በነጻ ፍርድ ቤት ያለ ጣልቃ ገብነት መዳኘት ከጀመረ እና መግደል ካቆመ ተከሳሾች በፍትህ ማሰር ከጀመረ… 12 ዓመቱ ሆኖታል፤ ዉጭ አገር ምትኖሩ“ጭፍኖች” የት ነበራችሁ 12 ዓመት “ጭፍንተኞች” ሆናችሗል። እያለን ነዉ ሃይሉ መንገሻ። (ስለ ስየ መታሰር ከ12 ዓመት በፊት ሳይሆን ከ6 ዓመት በፊት ግን ስለ ፍትህ አንስቶ እራሱ ሃይሉ መንገሻ ምን እንደተናገረ ዘንግቶታተል)
አሁን እያሞገሰዉ ያለዉን መለስ ዜናዊን የአእምሮ በሽተኛ ስለሆነ አገር ከማስተዳደሩ በፊት የአእምሮ ሃኪም ማየት አለበት ብለዉ ያዘዘለትን ሕክምና አጠናቅቆ መቸ እንደተመለሰ ማን ወደ ሚሉት “ሓኪም” ሄዶ ታክሞ ድኖ መምጣቱ የምስክር ወረቀት መያዙን ባይነግረንም፤ዛሬ “ቀዊሳዉ” መለስ ዜናዊ “ሙሉ ጤንነቱ” እንደተጎናጸፈ አቶ ሃይሉ እየነገረን ነዉ። አቶ ሃይሉ “እንኳን ደስ አለህ!”
አስኪ እነ ስየ አብርሃ ከመለስ ዜናዊ ጋር ሲለያዩ አቶ ሃይሉ “ኢትኦፕ” ከሚባለዉ መጽሄት ጋር ያደረገዉ ቃለ መጠይቅ በራሱ አንደበቶች እና ቃላቶች አሁን እያሞገሰዉ ላለዉ የ“ንኮች” እና “የከፋፍለህ ግዛ/አፓርታይድ ስርዓት” (የሃይሉ መንገሻ ቃል ነዉ) ምን ይለዉ እንደንደነበረ ልጥቀስ እና በትዝብት እቺ መጥፎ የዋሾች ዓለም እንለያት።ከዚህ ወደ ታች ያለዉ ቃለ መጠይቅ የተገኘዉ ከ ኢትኦጵ መጽሄት ከቅጽ 3ቁጥር 027ነሓሴ 1993 ዓ.ም/ በኢትዮጵያችን አቆጣጣር ነዉ።
ኢትኦጵ፦አሜሪካ በሚመራዉ የምዕራበዊ ምነግሥታት አሁንም አቶ መለስ በተሃድሶ ፕሮግራማቸዉ አማካይነት እንደገና ሁሉም እያስተባበረ ማንንም ገለልተኛ የማያደርግ አዲስ የሽግግር ጅማሬ ላይ እንዳሉ በመግለጽ አገሪቱን በመምራት ሃላፊነት መሸከም የሚችሉት ጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ብቻ ናቸዉ የሚሉ ይመስላሉ_ እረስዎ ይህንን ይጋራሉ?
አቶ ሃይሉ መንገሻ _ይህነን አስተያየት አልጋራም።የመለስ የመምራት ብቃት አጠያያቂ ደረጃ ከደረሰ ቆይቷል።ምዕራባዊያን አገሮች መለስን የሚመርጡት በተቃዋሚነት የቆሙት የፖለቲካ ድርጅቶች አንድ ጠንካራ ግምባር ባለመፍጠራቸዉ ነዉ።>>
ዛሬ ደግሞ አቶ ሃይሉ እያለን አለዉ “የመለስ ዜናዊ አገርን የመምራት ብቃት አጠያያቂ አይደለም- ዲሞክራቲክ ፕሮሰሱ ከጀመረዉ 12 ዓመቱ ሆኖታል>> እናንተ ጭፍኖች ናችሁ አይታያችሁም ይለናል። ቃለ መጠይቁ ከማድረጉ በፊት ከ5 ዓመት በፊት መለስ ዲሞክራቲክ ፕሮሰስ ጀመሮት ነበር በዛሬዉ በሃይሉ መንገሻ አባባል። ያኔ “ንክ” እና “ብቃት የጎደለዉ ፤አጠያያቂ” ብሎት በነበረበት ወቅት ነዉ። ኩርር ርርር!
ይህ ዲሞክራቲክ እያለዉ ያለዉን ስርዓት ከበረሃ ጀምሮ “ዘረኛ” እንደነበረ እና አሱን በዘረኝነት/ በ አዉራጃዊነት ግፊት ምክንያት ከበረሃዉ ትግል እንዲገለል የተጫነዉን ዘረኛ ቡድን በአንድ ጀምበር ከዲሞከራሲ፤ከፍትሕ እና ከአንድነት ጋር መቸ ወዳጅነት እንደፈጠረ አልነገረንም። አንደገና ከቃለ መጠይቁ ልጥቀስ። << በ1969 አጋማሽ የታየዉ ሕምፍሽፍሽ/ትርምስ በሚባል የሚታወቀዉ በታጋይ አባሎች እና በአመራሩ የታየዉ ልዩነት መንስኤዉ አመራሩ ይፈጽም ነበረዉ “ጎጠኛ” አመለካከት “አድልዎ” የበዛበት አሰራር በመቃወም የተከሰተ ነበር>> <<ህወሓት በትጥቅ ትግል 17 ዓመት መታገሉ ሳይሆን ስሕተቱ በትረ መንግስት ከጨበጠ በሗላ የሕዝብን መብት መግፈፍ እና የኢትዮጵያን ህዝብ በከፋፍለህ ግዛ ማተራመሱ ነዉ።>> ጎጠኛዉ እና አፓርታይድ ስርዓት ያለዉን ቡድን “ሃይሉ መንገሻ አዲስ አበባ ትግራይ ደርሶ ከመጣ በሗላ “የኢያን ስሚዝ” ጎጠኛነት እና አገሪቱን በከፋፍለህ ግዛ እያተራመሳት ነዉ ያለንን ዛሬ ደግሞ “አሌ” ብሎ “አኮመዴቲንግ” ነዉ እያለን ነዉ።>>
ወገኖቼ፡ አይሰልቻችሁ ትንሽ ትግስት ስጡኝ እና ጉዳችንን አንብቡት፤- ልቀጥል፡ <<የስብሓት ነጋ የ10 ዓመታት (በ1971-1981) የህወሓት ሊቀ መንበርነት ዘመን እንኳ የመገንጠሉን ፍላጎት በትግራይ ሕዝብ እና በታጋዩ ኣእምሮ ዉስጥ ማስረጽ ስላልቻለ በኢሕአዴግ ስም ሚኒሊክ ቤተመንግስት ዉስጥ ሆኖ *አገሪቱን ማተራመስ* መርጧል>>ብሎን ነበር ሃይሉ መንገሻ ያኔ አዲስ አበባ ደርሶ ከመምጣቱ በፊት።
ጥያቄዉ፤ ስብሓት ነጋ ወዴት ሄደ እና ነዉ አገሪቱን ከመተራመስ የዳነችዉ? አቶ ሃይሉ ሲነግረን የነበረዉ እና ዛሬ እየነገረን ያለዉ ልዩነት እየገባዉ ነዉ? ነዉ ወይስ ስብሓት ነጋ እንደ መለስ ዜናዊ በሃይሉ መንገሻ የአእምሮ ጠበብትንት ታክሞ ከጎጠኝነት በሽታዉ ተፈዉሶ “የምስክር ወረቀት” ይዟል? ወይ ጉድ- ወይ አገሬ! እቺ አገር ምን ይሻላት ይሆን! ወይ አትሞት ወይ አትድን!
<<እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለዉ የህወሓት አመራር አሱ የማይመራዉ የአንድነት ትግል እንዲኖር አይፈልግም>> ሲል ሃይሉ መንገሻ የወያኔ ዲሞክራቲክ መሆን እና አኮሞዴቲንግ ባህሪ መኖሩን እቅጩን ነግሮን ነበር እኮ! ወንድሞቼ ካሁን በፊት እና ዛሬ እየነገረንን ያለዉን እያዳመጣችሁት ነዉ?ልቀጥል!_ስለ ታንድ (ትደግ)<<ታንድ ይህን በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ያለዉን ጎጠኛ ስርዓት እንደማይደግፍ ለማሳየት የቆመ ነዉ>> በሎንም ነበር። “ጎጠኛ” የሚለዉ ቃል ስንት ገዜ በሃይሉ መንገሻ እንደተደጋገመ ልብ በሉ። ጎጠኛዉ ቡድን ዛሬ ማን እሚሉት ሃኪም ዘንድ ሄዶ እንደተፈወሰ ሃይሉ መንገሻ ሊነግረን ይገባዋል።
ሃይሉ መንገሻ አያይዞም <<ቋሚ የሆነ የዲሞክራቲክ አሰራር በሌለዉ ዘር እና ጎጠኝነትን የችሎታ መመዘኛ አድርጎ በሚወስደዉ የአጎት እና የአክስት ልጅ ድርጅት ከስድሳ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የሆነዉን ሰፊዉን የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዳድሮ ለረጅም ጊዜ አይቆይም ብሎ መገመት እመብዛም ነብይነትን የሚጠይቅ አይደለም።>> ይህ እንደ ሮዴሽያዉ እና እንደ ደቡብ አፍሪቃዉ አፓርታይድ ስርዓት “ዘረኝነትን እና ጎጠኝነትን የመመዘኛ ችሎታ አድርጎ- በአጎት እና በአክስት ልጅ ተተብትቦ አገር የሚመመራ ድርጅት ነዉ ብሎ የነገረንን ዛሬ አቶ ሃይሉ ምላሱን በመቆርጠም የ አጎት የ አክስት ልጆች የሚመሩት መንግሥት “አኮመዴቲነግ” ነዉ። እያለን ነዉ። ይግረም ብሎ ደግሞ አናንት መብት የላችሁም ዉጭ ሆየኖራችሁ መለስ ዜናዊ የሚያሽከረክረዉ የወያነኔን መንገሥት “አትክሰሱት፤አትዉቀሱት፤አትዝለፉት” እያለን ነዉ። የ አክስት እና የ አጎት ልጅ የወያኔ ልኡላን እና ንጉሳዉያን ቤተሰቦች ከመንግስት ስልጣን ከህዝቡ ጫንቃ ይብቃን ብለዉ ወርደዋል እና “አትንጫጩ” አታጉረምርሙ እያለን ነዉ።እየተከታተላችሁኝ ነዉ?! የሚያስፈልጋትን ያህል ከፈጨች በሗላ “በዓለማርያም ነዉ” ትላለች ይላሉ የትግራይ እናቶች እና አዛዉነቶች ሲተርኩ። አሱ ዉጭ አገር እየኖረ ሲፈልግ “ቋሚ የሆነ የዲሞክራሲ አሰራር በሌለዉ “ዘር እና ጎጠኝነት መመዘኛ” በሆነዉ የአክስትና የአጎት ልጅ ድርጅት አገር እየመራ ነዉ” “ጎጠኛ ነዉ” “አፓርታይድ ነዉ” የማለት መብት ሲኖረዉ እኛ ጋር ሲደርስ ግን “ዉጭ እየኖራችሁ ቃል መወርወር አትችሉም” ይለናል። ወይ “ትጉዱ!” ምኑ ዘመን ደረስነዉ እባካችሁ?
<<የድርጅቱ አሰራር ቁንጽል የፖለቲካ ፕሮግራም ገና ከጅምሩ የኢትዮጵያ ሰፊ ሕዝብን ዲሞክራሲን የማያጎናጽፍና አንድነትን የማያጠናክር መሆኑን ድምጻችነን ስናስተጋባ ቆይተናል።>> ዛሬ ደግሞ ከመቅጸበት ዲሞክራሲን አኮመዴት እያደረገ ነዉ ይለናል። ከቶ ወያኔን አክሞ ያዳነልን ሃኪም ስሙ እንደዉ ማን ይባል ይሆን? ወያኔን አክሞ የሚያድን ሃኪም እያለ እንዴት ሌሎች አገሮች በጎጠኞች አና በአምባገነኖች እያታመሱ ይዝለቁት? አረ ጎበዝ ሃኪሙን ፈልጉት እና ሌሎችም እንዲድኑ እንድንጠቁማቸዉ አቶ ሃይሉ የሃኪሙን ስም እና አድራሻ እንዲነግራቸዉ ጠ ይቁት!
<<እነዚህ አስር የህወሓት መአከላዊ ኮሚቲ አባለት በሙስና መፈረጃቸዉ ሃቅ እንደሌለዉ እና የመለስ/ስብሓት ሳይቀድሙኝ ልቅደም ፕላን ነዉ>> ይሄ ሰዉ ዘሬስ በቪ-ኦ-ኤ ምን እያለን ነዉ_? ልጥቀስ << ስየ ተከስሶ ታስሮ ነበር ጥፋት ፈጽሟል አልፈጸመም እኔ አላዉቅም። “ችግሮችን በሰላም ለመፍታት የሞከረ ምንግሥት ነዉ- አኮመዴት ያደርጋል (ይህን አዉቃለሁ)።” ባንድ እራስ ሁለት ምላስ_ይሉታል ይሄ ነዉ።
<<ፖለቲካዊ ችግሮች በተወሳሰበበት የሥራ አጡ ቁጥር በየዕለቱ በሚጨምርበት ኢኮኖሚዉ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ባሽቆለቆለበት በዚሁ በቀዉጢ ሰዓት የመለስ መንግስት አማረጭ እየጠበበ እንደሄደ የፖለቲካ ጠበብት በግልጽ ሚያዩት ነዉ።>> ዛሬ ደግሞ ኢኮኖሚ አድጓል እያለ ነግሮናል። ከሰብአዊ ነክ ጉዳኦች ሌላዉ በ ቪ ኦ ኤ ተከራከሩበት ጉዳይ የኢኮኖሚዉ ማደግ ጉዳይ ነበር። ባኮኖሚዉም በሰብአዊ ነክ ጉዳይም “ለዉጡ የማይታያቸዉ የወያኔን መትፎ ጎን ብቻ የሚያዩ ጭፍኖች”-ብሎናል። (ድሮ የባሪያ ጌቶች ባሪያቸዉን ምሳ እንዲቀምስ ሲፈቅዱለት፦ ይሄዉ ሲርብህ ምሳ እያበለሁህ ነዉ እና ነጻ እወጣለሁ ተጨቁኛለሁ አትበል_ አታማርር! የምገርፍህን ብቻ ሳይሆን ማበላህንም ምሳ ጥሩ ጎነኔንም አስተዉል!) አይነቱ ነዉ ሃይሉ የወያኔ “በጎ ጎኑንም” ጭምር አዉሱለት እያለ አጓጉለኛዉን ፍልስፍናዉን ወደ ህዝቡ የረጨዉ።
<<ይህ አንደነቱን ወዳድ የሆነ ቻይ ሕዝብ ለብዙ ዘመናት ያካበተዉን አምባገነኖችን ጠባቦችን አሽቀንጥሮ የመጣል ልምዱን እንዲቀጥልበት እስገነዝባለሁ>>---ዛሬ ደግሞ “ማሽቀንጠሩን እንተወዉ እና “ዝም በሉ” “አትክሰሱት አትዉቀሱት” ይለናል። ብረት ያላነገበዉ ቅንጅትን “አመጸኛ” በማለት ሲኮንነዉ “ለዘመናት ያካበተዉን አምባገነኖችን አሽቀንጥሮ የመጣል ልምዱን እንዲቀጥልበት” እየመከረዉ የነበረዉን “ህዝቡ ያካበተዉ ልምድ “ብረት አንግቶ” አመጽ አስነስቶ እመቢተኝነት ማሳት አንጂ ሌላ ከዚህ ዉጭ ምንም ልምድ እንዳልነበር እያወቀ “አምጹ- አሽቀንጥሩት” ሲለን ከርሞ ዛሬ ዞር ብሎ ደግሞ ሃይሉ ዉጭ አገር ኖርወይ ሆላንድ አሜሪካ ስለምንኖር “አፋችሁ ክደኑ” ይለናል።
በመጨረሻ ሁለት አስገገራሚ አባባሎቹን ልጥቀስ እና ልሰናበታችሁ_
<<የመለስ መንግስት በአንድ እግሩ ብቻ መቆሙን መገንዘብ እና ካሁኑ ለመጻኢዉ መዘጋጀት ነወ!>> ሃይሉ መንገሻ ተናገረዉ ቃል ነዉ። የመለስ መንገስት ከ12 ዓመት በፊት የዲሞክራሲ እና የፍትህ ፕሮሰስ /ሂደት በር ከፍቶልናል ሲል በ ቪ ኦ ኤ የተነፈሰዉ የዛሬዉ ወያኔአዊ ፕሮፖጋንዳዉ ከ7ዓመት በፊት በ አንድ እግሩ መቆሙን ተገንዘቡ ያለንን ከ 7 ዓመት በፊት ደግሞ እንዲህ ብሎ ነግሮዋል <<አሁን ያለዉ ስርዓት ለከፋፍለህ ግዛና ከእዚያም አልፎ ወደ ጥፋት እልቂት እየመራን መሆኑን እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ነዉ>> በማለት በ1993 ዓ.ም ሲነግረን ዛሬ ግድያዉ አፈሳዉ ክብደት አትስጡት ወደ ዲሞክራሲ የሚወስደን የሽግግር ምልከቱንም አትኩሩ “ያ ለእኔ በቂ ነዉ” ይለናል። እኛ ደግሞ የምንለዉ “ቁስላችን ዘወትር ለማስፋት የምትፈልጉ ወገኖች ግድያ ሲፈጸም የገበያ ንረት ጣራ ሲነካ “እያደግን ነዉ”-“ወደ ዲሞክራሲ የሚያመራን የሽግግር ጊዜ ምልክት ነዉ” እያላቸሁ ከተጠያቂነት እየሸሻችሁ በዜጎች ሕይወት እና ሰብአዊ መብቶች አታላግጡብን መለስ ነጻ አወጣችሁ አትበሉን እንላችሗለን።
እስቲ ቢገባቸሁ በዝነኛዉ በጦቢያዉ ጸሃፊ በጸጋየ ገ/መድህን አርአያ ብዕር ልሰናበተችሁ፦ “….ሩረሲያን ከሶቪየት ክንድ አዉጥተዉ ነፃ ወጣች-አሉ።ኢትዮጵያን ከኢትዮጵያዉያን መዳብ ዉስጥ ፈልቅቀዉ በማዉጣትና ኢትዮጵያን ዘላለም በሕይወት እና በደም ካስከበሯት ጀግኖች ልጆቿ ብብት ዉስጥ በመስረቅ መለስ ነፃ አወጣናችሁ ይሉናል።
እልቂትን ትርምስን የሰብአዊ መብት መረገጥን “በሽግግር ወቅት የሚያጋጥም ምልክት ነዉ” ይሉናል። የሗሊት የማራቶን ሩጫዉን የብሔራዊ ልዕልና አጀንዳ፤ ድህነቱን የፍትሕና ርትእ ዉድቆ መሰበርን ፤የአንድነትን የፍትህ መኮስመንን እኛ ዉርደት እንለዋለን፡እነሱ ዕድገት እና ግስጋሴ ይሉታል፤ ሁላችንም በየጀሮአችን የሚጮህ ድምፅ እንሰማለን ኩርር ኩርርርር! ተዋርደናል!>> ጸጋየ ገ/መድህን አርአያ/ጦቢያ። <ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!-ጌታቸዉ ረዳ ethiopiansemay.blogspot.com>

Saturday, December 27, 2008

Ethiopia: Former OLF leader exposes OLF and TPLF propaganda

Ethiopia: Former OLF leader exposes OLF and TPLF propaganda By Kirkos
In an interview, another former OLF leader shocked and destroyed the biggest propaganda schemes of the OLF and the TPLF separatist organizations. Mr. Ababiya Abajobir was the former OLF External Relations director, the face of the Oromo Liberation Front (OLF) to the world for many years, before he finally gave up the tough job of misinforming the world and chose to expose the historical lies the OLF has been shoving down the ears and hearts of our Oromo people.
Groups like OLF and TPLF have been throwing the propaganda that Ethiopia colonized southern people and other groups which these separatists threatened to divide (secede) from Ethiopia. For many years, our Oromo people have been insulted by OLF supporters as “Neftenya” just because they challenged the propaganda of OLF. Oromos have been insulted by OLF just because we talked about Oromo heroes like Ras Gobena and Dejazmach Balcha, who united our country and made Ethiopia stronger while defending it from foreign aggression. But today is the big day for all Oromos around the world who have been persecuted by OLF supporters because the former OLF leader himself has admitted what we have been saying for many years. Mr. Ababiya Abajobir admitted that Ras Gobena and Dejazmach Balcha were the Oromo-Ethiopian heroes who created modern Ethiopia. After many years of denial, this OLF leader admitted what our heroes like Emperor Haile Selassie told us for decades. Mr. Ababiya Abajobir admitted and said in an interview:
“Oromo nationality is a pillar of the country. So, we have to ask ourselves not only how a pillar can secede but also who created or cemented the unity? During the time of Menilik II, people like Dejazmatch Balcha and Ras Gobena Dachew expanded the territory through military actions and created the unity. Oromo people like others paid sacrifices in the battles of Adwa and Maichew.”
This is the second time a person from the highest level of OLF leadership has admitted historical realities which the OLF has been rejecting for almost 40 years. A few weeks ago, one of the OLF’s founders, Mr. Lencho Lata, shocked many OLF circles in the Diaspora by talking in favor of the Ethiopian state that the OLF propagandists hated deeply.
In addition to admitting the fact that the modern Ethiopian State was developed, created, expanded and united by brave Oromo-Ethiopians like Ras Gobena, the former OLF leader Mr. Ababiya Abajobir also said that some ancient Oromo communities like the Gibe Kingdom of Jimma shared the dreams of Ras Gobena and Menelik, which they showed by willingly uniting.
He admitted in the same interview by saying:
“In my birthplace, Gibe area, Aba Jifar consented to the idea of unity willingly and peacefully.” At the end of the day, whether OLF leaders, founders or former leaders admit history does not make history truer because history can not be changed, added, subtracted or ignored. But the former OLF leaders and founders, Mr. Lencho Leta and Mr. Ababiya Abajobir, finally exposing the OLF 40 years old ideological propaganda is a symbolic victory to the millions of Oromos and other Ethiopians.
Sadly, these OLF leaders admitted history very late because thousands of Oromos around the world are already brainwashed to hate their mother country Ethiopia. Especially thousands of Oromos in the Diaspora, like in Europe and America, like in Minnesota, have been brainwashed to think that so-called “Abyssinians” colonized Oromos. Thousands of Oromos in the Diaspora are brainwashed to think in simplicity, in Black and White. But OLF leaders like Lencho Leta and Ababiya Abajobir are finally telling the truth and accepting historical facts, which will eventually bring victory to the truth and bring victory to the millions of Oromos who love their country Ethiopia.
The facts are, there was no single united entity “Abyssinia” that colonized Oromos because ancient Oromo leaders like Ras Gobena united Oromos and created modern Ethiopia, alongside other heroes like Menelik I. In those days when Oromo communities were divided as Gibe Kingdoms for instance ended up in civil wars and as some Oromo communities raided into Sidama communities; semetic speaking peoples were also divided between regions like Gondar, Gojjam, Wollo, Tigray, Shewa etc. In fact, there were various conflicts between these people, including the Gojjam King Teklehaimanot with his Oromo ally Ras Derasu whose armies fought against another Oromo leader Ras Gobena Dache and his Shewan Amhara allies. But the Shewans Ras Gobena and Negus Menelik easily defeated the Gojjam army and continued to unite the rest of Ethiopia. This battle between the Teklehaimanot-Deresu alliance against the Gobena-Menelik alliance was one of the biggest examples in Ethiopian history of a multi-ethnic alliance which exposes OLF’s propaganda of Oromo vs Amhara simplifications. Similarly, there were examples of infighting between Oromo speaking communities, one historic instance being the Oromo Kingdom of Limmu-Ennarea, which not only fought against other Oromo communities, but also created suffering for Oromo people due to the bloody internal power struggles. In fact, according to the historian Donald Levine, many ancient Oromo communities supported their Oromo hero Ras Gobena who united Ethiopians in every region and ended the “intertribal fighting” which was causing destruction and bloodshed as Oromos were fighting other Oromos. While Emperor Menelik (who spoke both Afaan Oromo and Amharic languages) was busy uniting northern Ethiopians, Ras Gobena (who was gaining more and more fame inside his Oromo communities) was uniting southern Ethiopians. Some historians even confirm that the Oromo Ras Gobena’s success was not limited inside his Oromo communities because Gobena also helped the southern people of Sidama and Gurage after he defeated rebellion forces of the Muslim Gurage warlord Hassen Injamo and united all southern Ethiopians.
It is important to remember that Ras Gobena and other Ethiopian heroes were very revolutionary and smart leaders who understood that Africans needed to unite for many reasons, including for solving their internal issues, to be able to defeat European aggressors and to be a powerful player globally. So it was not surprising that many smart Oromo leaders united with Amhara leaders and other Ethiopians to create a powerful Ethiopian state that defeated the better equipped European invaders like the Italians. In this sense, Menelik, Gobena and other Ethiopian heroes were foresighted African leaders who – in an era when the motto of the white race was that the black race was a “backward race” that is “less than human” with “no civilization, language or achievement” – stepped up to stop bloody inter-clan, intertribal fightings in order to create a multi-ethnic powerful black nation that we call Ethiopia. This reminds us that Gobena and other Oromo heroes and their allies like Menelik were revolutionaries who were ahead of their time and created a “united states” of African people while the western Europeans were developing their “united states” of America (albeit the incorporation of blacks across the Atlantic Ocean under slavery). So It is no wonder that historian Donald Levine confirmed the support Oromo heroes like Ras Gobena received when he concluded that the Gobena-Menelik mission of expanding, uniting Ethiopians and strengthening the country was “welcomed as a way to put an end” to the bloody Oromo vs Oromo wars of the century.
Even though Ras Gobena is one of the biggest Oromo heroes in Ethiopian history, there are many other Oromo heroes and famous Oromo leaders, including Fitawrari Geresu Duki, Dejazmach Balcha Safo, Dejazmach Jagama Kelo, Iyasu V, Fitawrari Abba Gomol, King Ali AbaJiffar and the famous head of Ethiopia’s Ministry of Defense Fitawrari Habte Giorgis (Dinagde) who ruled Ethiopia together with Emperor Menelik. Meanwhile, various Oromo entities like the Yejju Oromo Dynasty, ruled Ethiopia in different stages, while many other Ethiopian leaders were of mixed descent with ethnically mixed Oromo-Amhara or other ancestry – including the various Fitawraris and Emperors. Another historian Paul Henze also exposed the TPLF’s propaganda of pure ethnic identities by saying that “pure Amhara can be found today only in isolated northern regions, such as Manz and Tegulet. All other Shoan Amhara have a sizable Oromo strain in their ancestry.” http://www.rand.org/pubs/reports/2006/R3347.pdf
This is the reason why today, millions of brave Ethiopians from Shewa and other Ethiopian regions have rejected Woyane’s ethnocentric census and refuse to simplify their complex historical identities by saying “Amhara” and “Oromo.” These failed TPLF classifications have ridiculed the ethnic politics agenda of separatists like TPLF and OLF, for these classifications indicate mere linguistic identities with no historical, cultural, religious, ancestral homogeny since a Wellega Oromo has very small non-linguistic similarity with a Shewan Oromo; nor does the multi-ethnic Shewans have a magical capability to claim they are pure one “ethnic” group. Therefore, Meles Zenawi’s current population statistics have been based on imposed tribalism, where an Ethiopian is forced to randomly choose one "ethnicity" that seems to be his/her most likely categorization and where the Ethiopian must blank out his/her memory and delete his/her unique, proud and complex history that led to the making of this multi-ethnic beautiful nation we call Ethiopia.
But simplification and propaganda is used not only by Meles Zenawi's TPLF dictatorship in Ethiopia today because the OLF is also equally experienced at this evil tactic. In fact, simplification and propaganda have become an accepted norm of the OLF organization that even one of the head ideological OLF “scholars” Mr. Asafa Jalata recently advised the OLF to increase the amount of its “propaganda” that is needed to “mobilize” the Oromo people who are suffering from “low level of the political consciousness,” according to this shameful OLF “scholar.” This is why our Oromo Diaspora communities need to confront OLF “scholars” like these who put down and demean the intelligence of our Oromo people who are beginning to think independently instead of having to parrot the OLF.
The last couple of decades, our Oromo people and fellow mixed Oromos have been attacked by OLF propagandists and labeled “Neftenya” for holding high the flag of Oromo heroes like Ras Gobena. The OLF used all its tools to make Oromos look at the world as “black & white,” in its simplest (though emotive) form, which brainwashed some innocent Oromo children to accept that these and these people are your enemies, and the OLF is your friend or your only “hope and shield” that will free you from “colonization” by non-Oromos. As the result, some Oromos have been forced to remain silent while the OLF propagandists claimed that Oromos were simply colonized by some type of Empire that was led by non-Oromos. But, the current admission by top former OLF figures like Lencho Leta and Ababiya Abajobir is the breakthrough Oromo people worldwide have been waiting for, to end the persecution of Oromos by the OLF mobs. The TPLF and the OLFs preying on innocent Oromos is coming to an end and the ideologically bankrupt Oromo separatists can not impose their will and propaganda on us anymore.

Wednesday, December 24, 2008

ከወያኔ የገበና ፋይል-ክፍል 2 ካለፈዉ የቀጠለ

ከወያኔ የገበና ፋይል-ክፍል 2 ካለፈዉ የቀጠለ የወያኔዉ ጀነራል ሓየሎም አርአያ ግድያ እና የአብዱል መጂድ የግድያ ሙከራ በመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን በፖሊስ የሞያ እይታቸዉ የደረሱበት ድምዳሜ፦ ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
ባለፈዉ ሰሞን ከመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የተገኘ ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያዉ ክፍል የወያኔ ያገሪቱ ከፍተኛ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነረሮች፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነሮች እና የአገሪቱ የደህንነት ሃለፊዎች እና የወንጀል መከላለክል እና የምርመራ ክፍል ሹሞች ከተራ ሌቦች እና ከግምጃ ቤት ዘበጆች ጋር በመመሳጠር ሕዝቡን እንዴት ይዘርፉት እና ያሽሸብሩት እንደንበር፤- እንዲሁም ወያኔ የመንግሥስልጣነ መንበር ከሕዝብ ነጥቆ የወንጀል መከላከል እና የምርመራዉ ሕግ ክፍል በ ቁጥጥሩ አድርጎ፤ ለግል ፖለቲካና ለማህበራዊ ጠቀሜታዉ እንዴት ይጠቀምባቸዉ እንደነበር አንብበናል። እነ ተስፋይ አብርሃ እና እነ ረዳኢ ገብረአነንያ የተባሉት የወያኔ ፖሊስ ኮሚሽነሮች እና ህዝብ ደህንነት ባለስልጣኖች በስማቸዉ የተመዘገዉን መሳሪያ ሌቦች እና ዘራፊ አሸባሪዎችን እያስታጠቁ ዝረፍያዉ እና ሰላማዊዉን ሕዝብ እንዴት ያሽሸብሩት እንደነበር አይተናል።ይህ ሁሉ ሲሆን -አንዳቸዉም እንኳ ለፍርድ አልቀረቡም። እዛዉ ክፍል እያለን፤ በይቀጥላል በአዳሪ ተሰናብተን ነበር።
ለቀጣዩ አቀርብላችሗለሁ ብየ የነበረዉን የአገሪቱ የመንገድ ሥራ ባለስልጣን መ/ቤት ባለስልጣኖች በተራ ዝርፍያ እና ንብረቶችን ማለትም ቡልደዘሮች፤ ትራክተሮች፤ ትላልቅ እና ትናንሽ የመንገድ እና የህንጻ አጋዥ መኪናዎች የመሳሰሉት በእነ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በእነ አቶ ተስፋየ ናሁ ሰናይ (የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ሹም) ተባባሪነት ዕቃዎቹ ከዉጭ አገር በግዢ ወይንም በመሳሰሉት ዕርዳታ የተገኙ ንበረቶች በመርከብ ተጭነዉ ከጅቡቲ ወደብ ላይ ተመዝግበዉ እንዳረፉ ፤- ከጅቡቲ ግምጃ ቤት በቀጥታ ወደ ትግራይ አንዲተላለፉ እንዴት ይደረግ እንደነበረ ሙሉ ታሪኩ እና ነገር ግን ቡልደዞሮቹ እና ትራክተሮች እና የመሳሰሉት ከባድ ንብረቶች ከመነሻዉ ለግዢ ወይንም በ እርዳታ መጠ ይቅ ሲመዘገቡ በሌሎች ክልሎች ስም የግዢ ቅጽ ይሞላ እንደነበር እና፤ ከተገዙ በሗላ ግን በቀጥታ ወደ ትግራይ እንዲመዘገቡ ተደርጎ እንዴት ወደ ትግራይ ይተላለፉ እንደነበር እና እነዚህ ሰዎች ያገሪቱ ትላልቅ መስሪያቤቶች እና የሕግ ክፍሎች ለግል መጠቀሚያ ያደርጉት የበነበረዉን የማጭበርበሪያ ስልቶችን የገለጹበት ክፍል ነበር።
በአጋጣሚ ቴፑ የት እንዳኖርኩት ማግኘት ስላልቻልኩ ላቀርበዉ አልቻልኩም። ለዚህም ይቅርታ እጠይቃለሁ። ቴፑ ያላችሁ ሰዎች ብትልኩልኝ ቀሪዉን ማስነበብ ይቻላል።ካገኘሁት ለወደፊቱ አስነብባችሗለሁ። እስከዛዉ በእዛዉ ፈንታ ያገኘሁት ሦስተኛዉን ክፍል አቀርብላችሗለሁ።
አሁን በቀጥታ ከላይ በርዕሱ ወደ ተጠቀሱት ሁለት አበይት ጉዳዮች የመቶ አለቃዉ በሞያቸዉ የደረሱበት መደምደሚያ ለጥያቄዉ የሰጡትን መልስ እና ሌላዉ በርዕሱ መርዘም ምክንያት ያልጠቀስኩት፦ ድሮ የወያኔ ታጋዮች ነበሩ - በሗላ ወያኔ ራሱ “ሞቡላይዘሽን/መልሶ ማቋቋም፤- የሚለዉን የመልሶ ማቋቋሚያ መመሪያዉን/ፕሮጀክቱን ሲያካሂድ የተከናወነዉን አድልዎ እና አናስፈጽምም በሚሉ አንዳንድ በአዲስ አበባ ፖሊስ ጽ/ቤቶች እና በአዲስ አበባ መስተዳድር (ከተፈራ ዋልዋ ጋር) የተደረጉትን ጠቦች እንመለከታለን። ሦስቱም ጉዳዮች እነሆ።
ጥያቄ- ከሙያስ አኳያ ወ ያኔ በተጨባጭ አብዱል መጂድን ለመግደል ሙከራ አደረገ ለማለት ነዉ የፈለጉት? “..ከሙያ አንጻር መመለስ ይቻላል ይህነን ጥያቄ ። ወያኔ አብዱል መጂድን ለመግደል ሙከራ አድርጓል አላደረገም ከማለቴ በፊት እስቲ አንዳንድ ነገሮችን ማለት ልቻል። ወንጀል ሲፈጸም ወምጀል መንስኤ የሚባል ነገር አለ። በወንጀል ተመራማሪ ሊቃዉንቶች መሰረት የወነጀል ሦስት የወንጀል መንስኤዎች አሉ። አንዱ ማህበራዊ ጉዳይ ነዉ፤ሌላዉ ኢኮኖሚአዊ ጉዳይ ነዉ።ሌላዉ ደግሞ ፖለቲካዊ ጉዳይ ነዉ። ከነዚህ ሦስቱ ተተቀሱት ነገሮች ዉች አስካሁን ድረስ ሌላ የታወቁ መንሲኤዎች የሉም። ወደ አበዱል መጂድ ሑሴን የግድአ ሙከራ ስንመጣ፦በቀትታ ሙከራዉ “ፖለቲካዊ ነዉ”። አብዱል መጂስ ሑሴንን በማህበራዊ ጉዳኢ ሚፈልጋቸዉ ሰዉ የለም፦ “የተጣሉት ጎረቤት የላቸዉም፤ ወይም ያደረጉት የእምነት ማጉደል ወንጀል የለም”። አብዱል መጂድ ሚኒስቴር ነበሩ። በቀጥታ የመግደል ሙከራዉ ሙከራዉ በቀትታ የተያያዘዉ ከፖቲካ ዩዳይ ነዉ።
ምናልባት እሳቸዉን በመግደል ወይም በእርሳቸዉ ላይ የመግደል ሙከራ በማድረግ ወያኔ ሊያገኘዉ የፈለገዉ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ነበረ። ስለዚህም ይህነን ጉዳይ ያደረገዉ ራሱ ወያኔ ነዉ የሚል ብዙዎቻችን በተለይም በሙያዉ ላይ የበሰሉ ከእኔም በላይ አስከ ዉጭ አገር ድረስ ሄደዉ የተማሩ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ተነጋግረን የደረስንበት ድምዳሜ አለ። ለጊዜዉ ስማቸዉን መጥቀሱ ስለማልፈልግ ነዉ። በቀጥታ በአብዱል መጂድ ላይ የተፈጸመ የመግደል ሙከራ በራሱ በኢሕአዴግ ነዉ። ምክንያቱም ኢሕአዴግ ባይሆን ኖሮ እነዚህ ሰዎች ማምለጥ አይችሉም። ቅድም በጠቀስኩልህ ቦታ መኪና አስቁመን እዛዉ ፖሊስ እያለ፤ ያዉም የአብዱል መጂድ አጋሮች አብረዉ እያሉ ቢያንስ አንድ ሰዉ እንኳ እንዲመታ አልተሞከረም። ይሄ በጣም ፤በረቀቀ መንገድ እራሱ ወያኔ ነዉ የፈጸመዉ የሚል ነዉ በሙያችን የደመደምነዉ። እኔ ብቻ ሳልሆን ከእኔ በላይ በምርመራ ስራ ለ10 ዓመታት ከዛም በላይ ለሰራ ዉጭም አገር ሄደዉ የዉጭ አገር የአመራመር ስርዓት፤ትምርት እና ስልት ብዙ ልምድ ካላቸዉ መኮንኖች ጋር አብረን ይሄነን ጉዳይ አንስተን ነበር ስንወያይ የነበረዉ። ስለዚህ በአብደል መጂድ ሑሴን ላይ የተደረገዉ የመግደል ሙካራ እራሱ ወያኔ ነዉ የሚል ነዉ በእኛ በሙያችን ግንዛቤ ላይ የደረስንበት።
ከዚህ ሌላ ወያኔ በአመራመር እና በፍርድ አፈጻጸም ለፖለቲካ መጠቀሚያዉ እንዴት እንደሚያዉለዉ ልጥቀስልህ። ለምሳሌ ጀሚል ያሲን የተባለ ጀኔራል ሓየሎምን ገድሏል።በእርግጥም ገድሏል። ያ የተረጋገጠ ነገር ነዉ። አገዳደሉ እንዴት ነበረ? በጀሚል ያሲን የተሰጠዉ ፍርድ ዉሳኔወ እና ጀሚል ያሲን ጀኔራል ሓየሎም ለምን እንደገደለዉ እንዴት እንደገደለዉ እና የነበረዉ የወንጀል አፈጻጸም ዘዴዉ፤ ከተሰጠዉ የፍርድ አፈጻጸም ጋር በፍጹም የማይጣጣም ነበር። ብዙ ባለሙያዎች አስተያየታቸዉን ይሰጡ ነበር።
“አገዳደሉ እንዴት ነበር?” በመሰረቱ እኛም ወደ እዛዉ እንድንጠጋ አልተፈለገም። ለምሳሌ መቶ አለቃ አድያምሰገድ የሚባል ነበር ( ለማስታወሳችሁ -ከጌታቸዉ ረዳ- መቶ አለቃ በሗላ ሻምበል አድያም ሰገድ የተባለዉ ትዉልዱ አክሱም ሆኖ በቀ/ሃይለስላሴ ዘመነ መንገሥት ጀምሮ በ ወህኒቤቶች እና በፖሊስ ሰራዊት ያገለገለ ነበር በሗላም በደርግ እንዲሁም ም በወያኔዉ ዘመን ያዲስ አበባ ፖሊስ የምርመራ ሹም ነበር። ወያኔ ከተጠቀመበት በሗላ ሌሎችን እንዳደደርገዉ ሁሉ ‘ከደርግ ጋር የተየያዘ ወንጀል ፈልስፎ በሃሰት ከስሶ ለአመታት አስሮ መቀሌ ወህኒ እያሰቃየዉ እስካሁን ድረስ እሮሮዉን እያአሰማ መቀሌ ወህኒ /እስር ቤት የሚገኝ ነዉ) - በእዛዉ ጊዜ የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል መከላከል እና መርመራ ክፍል ሃላፊ የነበረዉ Even እሱንም እንኳ ወደ እዛዉ እንዲጠጋ አላደረጉትም። ጀሚል ያሲን ጀኔራል ሓለፎም አርአያን እንዴት እንደገደለዉ ለማጣራት የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽኑ ረዳት ኮሚሽነር የነበረዉ መቶ አለቃ አድያም-ሰገድ እንኳ ወደዛዉ እንዲጠጋ አልተፈቀደለትም። በመጨረሻ እንዲያዉም አራንሺ ገብረተኽለ ራሱም እንዳይጠጋ ተደርጓል። አራንሺ ገብረተኽለ የክለልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበረ ነዉ። እንዲያዉም ከኮሚሽነርነቱ ያወረዱት ከዛ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነዉ። እነዚህ ሰዎች ብያንስ ሓየሎም አርአያ በጀሚል ያሲን እንዴት እንደተገደለ First hand information ቀጥተኛ የሆነ ማስረጃ ነበራቸዉ። ያ ቀጥተኛ “ፈረስት ሃንድ ኢንፎርሜሽን” ያልተበረዘ ያልተከለሰ ማስረጃ ስለነበራቸዉ፤ያንን እንዳትተነፍሱ ተብለዉ ከሃላፊነታቸዉም ወርደዉ ምርመራዉን በቀጥታ ወደ “ተስፋይ አብርሃ ” ቢሮ ነዉ የተወሰደዉ።
ግልጽ ነዉ ከአካባቢዉ የሰማነዉ ፤-- የያሲን እና …. (በደምብ ያልተሰማ የሰዉ ስም ይጠቅሳሉ) መጠጥ ቤት ነበሩ፦ በመጠጠጥ አልተግባቡም ፤- ተነጋገሩ-፤ከዚያም ሓየሎም አርአያ ተነስቶ ጀሚል ያሲንን መታዉ፤ “በካልቾም በጥፊም”- ከዚያ በሗላ የስካር መንፈስ ነበር በሁለቱም ላይ። የማይካድ ነዉ። ስካራቸዉ እዚያዉ አብረዉ የነበሩት ሰዎች የሚያዉቁት ጉዳይ ነዉ።
አንድ ወንድ ልጅ “በጥፊ ሲመታ” “በካልቺ ሲመታ” ራሱን ለመከላከል የሚወስደዉ እርምጃ አለ። ሕጉም ይላል። ራስን ለመከላከል። አልሞት ባይ ተጋዳይ ነዉ የሚለዉ።ሕጉ አለ እኮ! ሕጉን ያሰስተማሩኝ እኮ ሌላ አይደለም፦ ሕጉን ያስተማሩኝ- ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር የሆኑት ሻለቃ ፈቃዱ ቶሌራ ናቸዉ። እሳቸዉ ይሄንን ቢጠየቁ ምን መልስ እንደሚሰጡ አላዉቅም! ዛሬ ኮሚሽነር ሆነዋል ሲባል ሰምቻለሁኝ። እኔ እያለሁ አልነበሩም፡ ራሰቸዉ ከስርአቱ ጋር ችግር ነበረባቸዉ፦ ባንድ ወቅት ላይ”። ዛሬ ምን ተገኝቶ ነዉ ኮሚሽነር የሆኑት እንግዲህ አሳቸዉ የሚመልስት የሚያዉቁት ነዉ የሚሆነዉ።
ስለዚህ በእንደዚህ ዓይነት የተፈጸመን ወንጀል፤ እንደ ግፍ አገዳደል ተብሎ በጀሚል ያሲን ላይ የስቅላት ብያኔ ሲበየን ያላዘነ ፖሊስ ያላዘነ ዳኛ አልነበረም። የፍትህ ሰዉ/አካል አቃቤ ሕጎች ፍረድ ቤቶች ራሳቸዉ ሳይቀር! እንዴት በስካር መንፈስ የተፈጸመን ወንጀል ወደ ፖለቲካ ይላከካል ?……..
የቅጣት ማቅለያ እና የቅጣት ማክበጃ የሚባል አንቀጽ አለ። ለጀሚል ያሲን ሊጠቀስለት የሚችል ሕግ “የቅጣት ማቅለያ” ነዉ። ሰዉ ገድሏል ወይ? በእርግጥ! ወንጀል ፈጽሟል ወይ? አዎ ተፈጽሟል! ለምን ተፈጸመ ለሚለዉ እንነጋገርበት። ጀኔራል ሓየሎም አርያ እና ጀሚል ያሲን በወዳጅነት የተሳሰሩ ሰዎች ነበሩ ወይ? ጠብ ነበራቸዉ ወይ? ጀሚል ያሲን ሓየሎም አርአያን ለመግደል ሆን ብሎ ነዉ ወይ? -ተዘጋጅቶ ነዉ ወይ? አስቦ ነዉ ወይ? እነዚህ ነጥቦች ሁሉ እዛ የሕግ ክፍል ዉስጥ ስንገባ አይሟሉም።
አንድ ወንጀል በትከክል ተፈጽማል ለማለት እና ያሰዉየ በትከክል ሆን ብሎ መፈጸሙን ለማረጋገጥ እነዚህ ጥያቄዎች መመለስ አለባቸዉ። አቶ ጀሚል ያሲን ሆን ብለዉ ተዘጋጅተዉ ነዉ ወይ ሄደዉ ሓየሎም አርአያን የገደሉት? በቂም በቀል ነዉ ወይ? እነዚህ ሁሉ የሉም። ምንም ቂም አልነበራቸዉም። ጠጥተዋል፤ ሁለቱም ሰክረዋል። ሁለቱም ከጠጡ ደግሞ መስከር አለ።መስከር ካለ ደግሞ -የሰዉ ሕሊናዉ ትከክል አልነበረም ማለት ነዉ።
የሃሳብ ክፍል የሚባል የአይምሮ ክፍል አለ። ወንጀል ለመፈጸም ሦስት ነገሮች መሟላት አለባቸዉ የሚል የሕግ ደፍኒሽን definition /ትርጉም አለ። አንደኛዉ የሃሳብ ክፍል ነዉ -“እእምሮአችን ማለት ነዉ”” አንድ ሰዉ ወንጀል ፈጽሟል ለማለት አእምሮዉ ጤነኛ መሆን አለበት። የሃሳብ ክፍል የሚባለዉ ይሄ ነዉ። ሁለተኛ የህግ ክፍል የሚባል አለ። አታድርግ ወይንም አድርግ የሚል ድንጋጌ መኖር አለበት።ያ ድንጋጌ ተጥሷል ወይ? ያ መታየት አለበት። ሦስተኛዉ “የድርጊት ክፍል” የሚባል አለ። ድረጊቱ “Action” ኑ “ድረጊቱ ተፈጽሟል ወይ?” ተፈጽሟል ማለት አለበት። በነዚህ ሦስት ነገሮች በጀኔራል ሓየሎም የተፈጸመዉ አገዳደል ብንሄድባቸዉ፤-ሕግ አለ? አዎ ሕግ አለ።- አትግደል የሚል ሕግ አለ። ነገር ግን “ሕግ” ተጥሷል። ምክንያቱም “ግድያ ተፈጽሟል”። አታድርግ የሚል ክፍል ደግሞ አለ። ድረጊረት ተደርጓል። ምክንያቱም የድርጊቱ አፈጻጸም በጥይት ግድያ ተደርጓል። ይሄ አክሽኑ ነዉ -ድርጊቱ ማለት ነዉ።
ወደ ሃሰብ ክፍሉ ወደ ሦስተኛዉ ክፍል ስንመጣ ነዉ እንግዲህ የምንከራከረዉ። አቶ ያሲን ጀሚል ጤነኛ ናቸዉ? አዎ ጤነኛ ናቸዉ።በወቅቱ ግን ጠጥተዋል። አንድ ሰዉ ጠጥቶ ወይ ይሄ ድራግ/አደንዛዥ እጽ የሚባለዉ ወስዶ ወይም በደም ፍላት ተነስቶ ደሙን የሚያፈላ ነገር ከተፈጸመበት Cause and Effect “መንስኤ እና ዉጤት” የሚባል ነገር አለ። እነዚያ ነገሮች በሕግ ዉስጥ ሲተነተኑ የሕግ ባለሞያዎች ከኔ ይበልጥ ይተነትኑታል። እነዚያ ነገሮች በአቶ ጀሚል ያሲን አእምሮ ተሟልተዉ ነበሩ ዎይ?የሚለዉ የሕግ ጥያቄ ስንመልስ - አቶ ጀሚል ያሲን ጠጥተዉ ነበር። ሐየሎም አርአያም ጠጥተዋል።አንድ ሰዉ ሞቅታ ላይ ነዉ፤መጠጡ ሰዉየዉን ተቆጣጥሮታል- በተጨማሪም በላዩ ላይ ጥፊ ሲጨምርለት፤ካልሲ ሲጨምርለት ከመጠጡ ላይ በባሰ እንዲናደድ፤ደሙ የባሰ እንዲፈላ የሚያደርግ ነገር ነዉ። በዚህ ሁኔታ የተነሳ አንድ ሰዉ ወንጀል ቢፈጽም፦ ይህ ሰዉ ወንጀሉ ለምን ፈጸመዉ ወደ ሚል እንመጣለን። በደም ፍላት እና በስካር መንፈስ። በደም ፍላት እና በመጠጥ መንፈስ ወደ እሚል ከመጣን ደግሞ ወደ ሕግ አንቀጽ ስንሄድ ወደ ቅጣት ማጥርያ ነዉ የመንሄደዉ። ያ የቅጣት ማጥሪያ ሲጠቀስ ደግሞ “ሰዉ የገደለ ሰዉ ከ5 ዓመት አስከ ሞት ነዉ እሚለዉ ገደቡ”። 5/22 5/26 ወዘተ የሚሉ ህጎች አሉ (Actualy አሁን አላስታዉሳቸዉም የህግ አንቀጾቹን ቁጥሮቹን- የሕግ ባለ ሞያዎች ያዉቁታል ይሄንን) የትኛዉ አንቀጽ ሊያስጠቅስ እንደሚችል የቅጣት ማጥሪያ ጠቅሶ ነዉ በዚህ ሰዉየ ላይ አቃቤ ህግ ክስ ሊመሰርት የሚችለዉ።
በአቶ ጀሚል ያሲን ላይ ግን የተወሰደዉ የህግ አሰጣጥ የህግ ዉሳኔ ሁሉንም ያላገናዘበ ግን ከጀነራል ሓየሎም አርአያ ለወያኔ ወይንም ለስርአቱ አስፈላጊነት ጋር የተያያዘ ነዉ።
እኔ የጀነራል ሓየሎም አርአያ ስም እና ክብር መንካት አልፈልግም። በትግሉ ወቅት ብዙ ነገር አድርገዉ ሊሆኑ ይችላል። አደርገዋልም “ለወያኔ”። ጀግና ሊሆኑ ይችላሉ፡ አሟሟታቸዉ ግን ከነበራቸዉ ክብር እና ከነበራቸዉ ማዕረግ ሲታይ መጠጥ ቤት ሞቱ።ሰዉ ተማትተዉ ነዉ የሞቱት።ሰዉን በጥፊ መትተዋል።ሰዉ በጥፊ መምታት እኮ ሰብአዊ መብት መርገጥ ነዉ።መሳደብም ሰባዊ መብት መርገጥ ነዉ። ትግሉ የታገሉት ደግሞ”ሰብአዊ መብት ለማሰከበር ነዉ የታገልነዉ ነበር ሲሉ የነበረዉ ካድሬዎቻቸዉ”። ከእዛ አንጻር ሲታይ ወያኔ የተጠቀመበትን ጀሚል ያሲንን በመስቀል የቀጣዉ አቀጣጥ ዘዴ ግን አጠያያቂ ነዉ ። ራሱ የጀሚል ያሲን አሰቃቀል-በስቅላት እንዲቀጣ ሲደረግ ጀሚል ያሲን ኤርትራዊ ነዉ ሲባል ነበር የምንሰማዉ። ናቸዉ አይደሉም ‘እኔ የማዉቀዉ ነገር የለም’ እርገጠኛ አይደለሁም። በወያኔ እና በኤርትራ መካከል ግጭት ተፈጥሮ ጦርነት ሊካሄድ ነዉ በሚባልበት ሰዓት ነዉ ጀሚል ያሲንን የሰቀለዉ። ምክር ቤቱ ‘ኤርትራ ወረረን” ብሎ በቴሌቪዥን መግለጫ አወጣ። በሁለተኛዉ ይሁን በሦስተኛዉ ቀን ደግሞ የጀሚል ያሲን በስቅላት የሞት ቅጣት ደግሞ ያ ቴለቪዥን መልሶ ነገረን።
የጀሚል ያሲን ስቅላት ከኤርትራ ወረራ እና ከወያኔ ጦርነት ጋር የሚያያይዘዉ ነገር የለም! ያ ተራ ወንጀል ነዉ!ተራ ወንጀል ነበር! ነብስ ግድያ ነዉ የተፈጸመዉ።ነብስ ግድያ ደግሞ “ማሕበራዊ ነዉ”። ቅድም የጠቀስኳቸዉ ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ የወንጀል መንስኤዎች ብየ ከገለጽኳቸዉ ዉስጥ ነዉ። ሌሎች ሰዎች “ፖለቲካዊ” ነዉ ሊሉ ይችላሉ። እኔ በሙያየ የደረስኩበት ግን አፈጻጸሙ አካሄዱ “ሞዳስ ኦፔራስ” የሚባለዉ ግን “ማህበራዊ ነዉ”።መጠጥ ጠጥተህ ከተገዳደልክ “ማሕበራዊ” ነዉ “የወንጀሉ መንሲኤዉ”። የማሕበራዊ ግጭት ነዉ።
ስለዚህ ያ ዓይነት አገዳደል ከአገር መወረር እና ከሉአላዊነት ጋራ አያይዘዉ የትግራይ ሕዝብ ሓየሎም አርአያ ይወድድ ስለነበር፡ እስካሁንም ይወዳቸዋል፡ እኔም አከብራቸዋለሁ፤ ነገር ግን ያንን የትግራይን ሕዝብ ለማነሳሳት፤ ሌላዉንም የኢትዮጵያ የዋህ ሕዝብ ለማነሻሻነት ለመጠቀም “ኤርትራ ባድመን ሲወርር -እኛ ደግሞ እዚህ ጀሚል ያሲንን ሰቀልነዉ” በማለት ለመቀስቀሻነት ነበር የተጠቀሙበት። ይህ ማጭበርበር አስከመቸ ድረስ ነዉ ሕግን እና የፖሊስን ሃይል እየተጠቀሙ ህዝብን ማታለል እና መዋሸት የሚቻለዉ? የሚል የራሳችን ድምዳሜ ደረስን። በሙያችን አዘንን፤ተክዘናል።ምክንያቱም ሕግ ሲረገጥ ይከነክናል፤ያበሳጫል፤ዕረፈት ሰላም ይነሳል። ባጠቃላይ ለባለሞያዎቹ ለኛ ይህ አሰራር የሚያሳየዉ ኢሕአዴግ ያገሪቱን ፖሊስ ሃይል ሕግ እና የወንጀል ምርማራ ዘርፎችን ለመቀስቀሻ ለፕሮፖጋንዳ ህዝብን ‘ሞቢላይዝ’ ለማድረግያ እንዴት በተካነ ጥበብ እንደሚጠቀምበት ለመግለጽ ነበር ይሄነን ለመግለጽ የሞከርኩት።
ጥያቄ፦የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን- እስኪ የሕግ የበላይነት “Rule of Law” የሚባለዉ እና የሰብአዊ ጉዳዮች ሁንታ በምን አይነት መልኩ ነዉ የሚመለከቱት በሙያዎ አኳያ? ወደ ሚለዉ ጥያቄ በሚቀጥለዉ መልሳቸዉ በቀጣዩ 3ኛዉ ክፍል በመግባት በመልሶ ማቋቋም ያሰማራቸዉ የወያኔ የድሮ የበረሃ ታጋዮች በአዲስ አበባ ከተማ የንጋዴዉ ሕብረተሰብና ሰላማዊ ዜጎች ሱቆቻቸዉ አና ዉድ ዉድ የሆኑ ቤቶች በተፈራ ዋሉዋ አስፈጻሚነት በመለስ ዜናዊ እና ጥቂት የምስጢር ጓዶቹ ባወጡት ማንም የላጸደቀዉ እና ያላወቀዉ ምስጢራዊ አዋጅ “ቀጭን” ትዕዛዝ እያስተላለፉ እየነጠቁ እንዲኖሩበት እንዴት እንደተደረገ እና ይህ ሕገ ወጥ እና አድልዎ ያለበት አሰራር አናስፈጽምም ባሉት በአንዳንድ የአዲስ አበባ የፖሊስ ወረዳ ጸ/ቤቶች እና የከተማዉን አስተዳደር ሲመራ በነበረዉ በተፈራ ዋሉዋ መካከል የታየዉ ጠብ በሚቀጥለዉ 3ኛዉ ክፍል ይቀርባል። ተከታተሉ:: www.ethiopiansemay.blogspot.com

Sunday, December 14, 2008

የወያኔ የፖሊስ እና የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሌቦችን በማስተባበር ወንጀል ሲፈጽሙ የሚያመለክት ማህደር

ከወያኔ የገበና ማሕደር የወያኔ የፖሊስ እና የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣኖች
ሌቦችን በማስተባበር ወንጀል ሲፈጽሙ የሚያመለክት ማህደር ጌታቸዉ ረዳ ከጥቂት ዓመታት በፊት የመቶአለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የተባሉ በወያኔዉ መንግስት በፖሊስ ሰራዊት የመቶአለቅነት ማዕረግ የነበራቸዉ በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ 21 ፖሊስ ሹም እና የምርመራዉ ክፍል ሹም በመሆን አገራቸዉን በቀና ለማገልገል በሙያቸዉ ተሰልፈዉ እንደነበር እና የሗላ-ሗላ ግን የወያኔ ባለስልጣኖች በጎሰኝነት እና በዘረፋ በተራ ስርቆት ሌቦችን አሰማርተዉ ሕዘቡን ሲያሸብሩ እና ሰላም ሲነሱ በመታዘባቸዉ እና በምርመራዉም ላይ ግምባር ቀደም ሚና በ አካልም ዘራፊዎቹ እና አስዘራፊዎቹን የሚያሰማሩ አንዳንድ የደህንነት እና የፖሊስ ከፍተኛ ባለስለጣኖችን ሰለ ፍትሕ እና ስለተማሩበት ሙያ ሲሉ በሙያቸዉ ጸንተዉ ሲጋፈጧቸ እና እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሌቦችን እየለቁቁ ካለ ቦታቸዉ ጣልቃ እየገቡ አላሰራም ስላሏቸዉ የነበራቸዉን ስራ እና የሚወዷት አገራቸዉ እና ቤተሳባቸዉን ጥለዉ ወደ ስደት በማምራት የሻዕቢያ ራዲዮ አሳቸዉን አፈላልጎ ከአዉሮጳ የስልክ ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዉ እንደነበር ይታዋሳል። መኮንኑ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ እና ያጋለጡት ምስጢራዊ ሰነዶችን በዚህ ለናንተ “ከወያኔዎች የገበና ማሕደር” ርዕስ ቀርቧል።
“ምናልባትም ካልተሳሳትኩ” የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን- አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በየትኛዉ የ አርበኞች ግምባር ጦር መሆናቸዉን አላዉቅም እንጂ በኤርትራ መንግስት ሲደገፉት ከነበሩት የአርበኞች ግምባር በአንደኛቸዉ ዉስጥ መሰለፋቸዉ ትዝ ይለኛል። ጽሁፋቸዉም በየትናዉ የህዋ ሰሌዳ እነደሆነ ትዝ አይለኝም እነጂ ስለ ግምባሮቹን በሚመለከት ስለ አንድነት እና መተባበር የጻፉት የ አማርኛ ጽሑፍ አንብቤአለሁ። ምናልባትም ይህ ዝግጅት ማንበብ ከቻሉ በ እኔ እና በ ኢትዮጵያን ሰማይ ዳት ብሎግ ሰፖት.ካም (Ethiopiansemay.blogspot.com) አንባቢዎቼ ስም ከፍተና ምስጋናን አቀርባሉ። ባሉበት ምድ እና ትግልም ተቃና ኢትዮጵያዊ ግዳጅዎ እንዲቃና እመኝለዎታለሁ።አምላክ ከ እርስዎ እና መላ ቤተሰቦ በሰላም ይጠብቀዎት እአልኩ በቀጥታ ወደ ቃለ መጠይቁ ማህደር ወደ ወያኔ የስረቆት እና ዝርፊያ ገበና እናምራ።
በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳዉ ምርመራ ሹም እነደነበሩ እና የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሌቦችን በቡድን እና በግለሰብ በማሰማራት በዘረፋ ስራ እንደተሰማሩና የሚዘርፉበትም መሳሪያ በ ባለስልታኖች ስም ተመዘገበ ማሳሪያ እነደነበር በምርመራዉ እንደረሱበት እና ሌሎች ዝርዝር ታሪኮችን ያጋለጡበት አነሆ፡-
የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን
"በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 21 የፖሊስ ምርመራ ክፍል ሹም እንደመኖሬ መጠን በዛች ወረዳ ብቻ የተፈጸሙትን እኔ የተከታተልኳቸዉ መንግስታዊ ወንጀሎችን ነዉ በማስረጃ አስደግፌ ማቀርበዉ። ካገሬ ብወጣ እና በሰደድም ፖሊስ እንደመሆኔ መጠን ሙያየም ስለሚያስገድደኝ ከሕግ ዉጭ የተፈጸሙ መንግስታዊ ደባዎችን ህዝቡን የማስረዳት ግዴታ አለብኝ።
ለምሳሌ ብጠቅስ፣ በወረዳ 21 ቀበሌ 01 ሳህለስላሴ ህንጻ የሚባል አንድ ህነጻ አለ። ህንጻዉ ዉስጥ “ኢሰመጉ” የሚባል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅት ጽ/ቤት የነበረበት ነዉ።የጽ/ቤቱ በር ተሰብሮ ተዘረፈ።የተሰረቀዉ ምነድ ነዉ!ሰነዶች፤ፋይሎች መጽሐፍቶች እና የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶች ናቸዉ ተሰረቁት።በመሰረቱ ቢሮዉን እንዲዘረፍ የተፈለገበት ምክንያት ሰነዶችን ለመዉሰድ ነበር። እኔ በዛዉ ወቅት የወረዳዉ ሸም ስለነበርኩ፤በአካባቢዉ የተፈጸሙ የወንጀል ድረጊቶችና ፈጻሚዉን ተከታትሎ ወደ ሕግ ማቅረብ ሃለፊነት አለብኝ። ኢሕአዴግ አይደልም ይህነን ሐላፊነት የሰጠኝ።አንደኛ የተማርኩበት ት/ቤት ኮርሴን አጠናቅቄ ስመረቅ ለእዉነት እና ለሕግ ተገዝቼ ሕዘቡን ለማገልገል አስምሎ ነዉ ያስመረቀኝ።ሁለተኛ ሕገ መንግስቱ ራሱ ይህነን እንድከታተል ያስገድዳል።በዚህ መሰረት ክትትል በማድረግ ይሄነን ኢሰመጉን ቢሮ ሰብሮ የሰረቀዉን ሌባ፤ከሌሎች የስራ ባልደረቦቼ ጋር ሆኜ (አሁን ስማቸዉን ለመትቀስ አልፈልግም) ከነሱ ጋር ሆነን ተከታትለን ነዉ ግለሰቡን የያዝነዉ “ኤርሚያስ መብራህቱ” ይባላል።
የኢሰመጉ ጽ/ቤት የያዘዉ የማመለክቻ ፋይል ከተለያዩ ቦታዎች ከደቡብ፤ ከአማራ፤ ከኦሮሚያ ክልል፤ ከትግሬ ክልል እንኳን ሳይቀር ወዘተ ያለ ሕግ ከስራ አባረሩኝ፤ ተደበደቡኩኝ ወዘተ የሚሉ ሰብአዊ ነክ ጉዳዮችን ለዚህ ለኢሰመጉ ቢሮ እሮሯቸዉን ያስገቡበት የግለሰቦች ማመልከቻ ነበር የተዘረፈዉ።የነሱ ፋይል ነዉ የተሰረቀዉ።ኤርሚያስ መብራቱ ፋይሎቹን ዘርፎ ለማን ይሰጠዋል፤ በዞን 2 የኢሕአዴግ ሐለፊ ሆኖ ብዙ መስሪያ ቤቶችን የሚቆጣጠር “ገብረ እግዚአብሔር” ሚባል ከፍተኛ ካድሬ አለ።ሰነዶቹን ለእረሱ ነዉ የሰጠዉ። ገብረእግዚአብሔር … “ኤርሚያስ መብራህቱ” መያዛችንን ሲሰማ፤ ባስቸኳይ ምርመራዉ እንዲቆም ብሎ ነዉ ትዕዛዝ መመሪያ ለእኔ የሰጠኝ። አይ- ምረመራዉንም እማ አላቆምም! ምክንያቱም ወንጀል ተፈጽሟል።”ወንጀል ከተፈጸመ ደግሞ ፈጻመዉ ወደ ሕግ መቅረብ አለበት” የሚል መልስ በምሰጥበት ሰዓት፤ ከእኔ ጋር ሆኖ ሲሰራ የነበረ የጣቢያ አዛዥ አስጠንቅቀዉ (ለሱ ነበር ማስጠንቀቅአዉ የተሰጠዉ) መዝገቡን ወደ እኛ ባስቸኳይ ላክ ተባለ።መዝገቡ ወደ ክልል እንዲላክ ተደረገ። አሁን በዚህ ሰዓት ላይ እዛዉ ከኔዉ ጋር ሲሰሩ ነበሩ የክፍል ሃላፊዎች አሉ፡አነዚህ በቀጥታ መዝገቡን አንሰጥም ማለት ይችላሉ። ይህ አቋም ከያዙ ደግሞ በቀጥታ ከኢሕአዴግ ጋር ተጋጩ ማለት ነዉ።ምክንያቱም ወንጀሉን የፈጸመዉ ኢሕአዴግ ነዉ (ኤርሚያስ መብራህቱ ነዉ)። ኤርሚያስ መብራህቱ ቃሉን ሲገልጽ ምነድ ነዉ ያለዉ_”ገብረእግዚአብሔር ነዉ ሂድ ስረቅ ያለኝ። ሂድ እና መዝገቦቹን ሰርቀህ አምጣ ያለኝ ምክንያት እኔ ሌባ መሆኔን ያዉቃል።እንዲያዉም ይረዳኛል።መዝገቦቹን ብቻ ስጠን ብሎ መዝገቡን ስጥቼዋለሁ” አለን። የግድግዳ ሰዓቶችን እና ሌላ ሌላ የተዘረፉት ንብረቶች ግን ሄዶ ከመረካቶ ነዉ የሸጠዉ።የሸጠዉን ዕቃ ደግሞ አስመልሰን በእግዚቢት ይዘነዋል።
ጥያቄ፦ የመቶ አለቃ አሁን እርሰዎ ያሉት ያሉት ፤ወያኔ ገንዘብ እየከፈለ ወንጀል ያስፈጽማል ነዉ የሚሉት ።ልከ ነዉ?
የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን-
በሚገባ እንጂ! ይሄ ኤርሚያስ መብራሕቱ የምልህ ከወላጅ አባቱ ጋር ተጣልቶ የወጣ ስርዓተ አልበኛ ዱርየ ነዉ።የሚኖረዉ በመስረቅ ነዉ። አበዛኛዉ በዋናነት የቅርብ ጓደነኝቱ ግን ገብረ እግዚአብሔር ካልኩህ ጋር ነዉ። የሚያመሹትም ሚዉሉትም አበረዉ ከገብረእግዚአብሔር ጋር ነዉ።ገብረእዝግዚአብሄር ማለት ደግሞ በዞን ሁለት የኢህአዴግ ባለስልጣን ነዉ።የዞን አስተዳደር፤የዞን የትምህርት የጤና ወዘተ በዉስጡ ብዙ ዘርፍ የያዘ ክፍል ነዉ። ጠቅላላ ኢህአዴግን ወክሎ በእነዚህ እና በመሳሰሉት ሕዝባዊ ነክ ዘርፎች የሚቆጣጠረዉ ይህ ክፍል ነዉ።ይህ ክፍል ደግሞ የሚቆጣጠረዉ “ግብረእግዚአብሔር” ነዉ። ስለዚህ ሂድ እና ይሄነን ተግባር ፈጽም እያለ የሚያዘዉ “ገብረእግዚአብሄር፡ ነዉ።ይህ ልጅ ፍላጎቱ በመሰረቱ የሚሸጥ ነገር መስረቅ ነዉ። ምክንያቱም “ኢሰመጉ” ቦሮ ዉስጥ ገብቶ “ሰነዶችን” ሰርቆ ልሽጥ ቢል ማንም አይገዛዉም።ገንዘብ የሚያስገኝለትን ስርቆት እና ዕቃ አጥንቶ ነዉ የሚሰርቀዉ። አነጋግረነዋል።በሚገባ እንዲሰርቅ ማን እንዳዘዘዉ ግልጹን ነግሮናል። ይህነን የወረዳ 21 መርማሪ ፖሊሶች በሚገባ ያዉቁታል።የሰጠዉም ቃል በወረዳዉ ዕለት ሁኔታ መዝገብ ተመዝግቦ ይገኛል። ኢሕአዴግ ብቃቱ እና ሞራሉ ካለዉ እና ልከታተለዉ ካለ ‘እዛዉ ሄዶ መዝገቡን ማየት ይችላል፤ ዉሸት ከሆነ። ስለዚህ ኢህአዴግ የሚያሰማራቸዉ ወንጀለኞች አሉ።
ሌላዉ ልጥቀስ። አንድ የቀድሞ ሰራዊት አባል በሻምበልነት ማዕረግ የነበረ፤በወረዳ 21 ቀበሌ 22 እና 24 መካከል ስሙን ዘንግቼዋለሁ ማዕረጉን ነዉ የማስታዉሰዉ (ማስታወሳን ስለወሰዱብኝ)።
ጥያቄ፡- ማነዉ መስታወሻዎን የወሰደበዎት?
የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን-
ኢሕአዴግ።ቤቴን ሰብረዉ ስኖርባት ነበረችዉን አንዲት ክፈል እኔ በሌለሁበት ሰብረዉ ማስታወሻዎቼን ወሰዱት። ይህ ድረጊት የፈጸመዉ “ጀማል” የሚባል መጀመሪያ የአዲስ አበባ የደህንነት ሃለፊ የነበረ በሗላ ደግሞ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል እና መርመራ ክፍል ሹም የነበረ፤- እሱ ነዉ ማስታወሻ ሰነዶቼን በሙሉ የወሰዳቸዉ።
ጥያቄ፦ ይገርማል! በዚህ ጉዳይ ወደ ሗላ እንመለስበታለን እና ስለ ሻምበሉ ጉዳይ አስኪ ይቀጥሉ
..ሻምበሉ፤በድሮ ሰራዊት አባል ሰራዊት የነበረ ነዉ።በወረዳ 21 እና በቀበሌ 22 መካከል ከቀኑ ስድት ሰዓት አካባቢ ክላሽ በታጠቀ ግለሰብ ተተኩሶበት ተገደለ።ይሄ ግለሰብ ተገድሎ፤ገዳዩ ሻምበሉን ገድሎ እየሮጠ ወዴት ነዉ የገባዉ (?) በወረዳ 21 ቀበሌ 04 “ገነት ሆቴል” የሚባል አንድ ሆቴል ፊት ለፊት ካለዉ የደህንነት ህንጻ ጸ/ቤት በቀጥታ ሮጦ ገባ። ሕዘቡ ተከተታትሎ ሪፖርት አደረገ። ከዛ እኛም ደረስን። ከዚያ በሗላ ደህንነት ጽ/ቤት አባሎችን በማነጋገር “ሰዉ ገድሎ ከእናንተዉ ቢሮ ዉስጥ ሸሽቶ አምልጦ ገብቶ የተደበቀ ሰዉ አለ እና ስጡን ወይንም እንግባ እና እንፈትሸዉ ብለን ስንል፡ “በቀጥታ ከዚህ ጥፉ!” ነዉ የተባልነዉ።
በሬድዮ “ልዩ ሃይል” ተጠርቶ በነሱ እንድንባረር ተደረገ። “ልዩ ሃይል” የሚባል አለ ስለ እሱ ወደ ሗላ አነሳዋለሁ። ልዩ ሃይል ማለት የሰዉን ጭንቅላት ለመቀጥቀጥ የተሰራ “መዶሻ” ነዉ ማለት ይቻላል። እና ከነሱ ጋር ተጋጭተን ስለነበረ ወዲያዉ ከክልሉ ፖሊስ -ፖሊስ ኮሚሽነር “ተስፋይ አብርሃ” በተባለ ግለሰብ ወደ መ/ቤታችን እንድንመለስ ትዕዛዝ ተሰጠን እናም ወደ ቢሮአችን ተመልሰን ሄድን። ወደ አካባቢዉ ስንሄድ የሰዉየዉ አስከሬን ወደ ሆስፒታል ተላከ።ከዚያ በሗላ በክልል ደረጃ ይጣራል ተባለ እና የሰዉየዉ አስከሬን በምኒሊክ ሆስፒታል ሃኪሞች እንዲመረመር ተደረገ። የነበረዉ መረጃ ወደ ክልል ስጡ ተባለ። እነ መቶአለቃ ተማም ኑር ከኔ ጋር ሲሰራ የነበረ ነዉ፦ ከላይ ክልል ደግሞ እነ መቶ አለቃ ዘላለም የሚባሉ በክለል ነብስ ግድያ ወንጀል ምርመራ ቡድን መሪ ነበሩ፤- ጉዳዩ እነሱ ሁሉ ያወቁታል።ሻምበሉ የተገደለዉ ከፖለቲካ ንክኪ ነዉ።የተገደለዉ ደግሞ በጠራራ ጸሐይ ነዉ። ገድሎት ወደ ደህንነት ገብቶ ገዳዩ ሳይጠየቅ ቀረ።
ሌላዉ የወንጀል ዓይነት ደግሞ ልንገርህቡድን አደራጅቶ ወንጀልን የመፈጸም ድርጊታቸዉን ልግለጽ።
ለምሳሌ አንዴጸሐየ” አንዴ “በየ” አንዴ “እያሱ”፤አንዴ ገብረእግዚአብሔር አንዴ … በተለያዩ ስሞች የሚጠራ የ“ተስፋይ አብርሃ” የእህቱ ልጅ ነዉ።እሱ ነዉ ቡዱኑን የሚመራዉ።ተስፋይ አብርሃ በዛ ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊስ ፖሊስ ኮሚሽነር ነበር።በሗላ ደግሞ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ግጭት ሲፈጠር “ጌታቸዉ አሰፋ” (የማዕከላዊ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበረዉ) ወደ ጦሩ ሲሄድ የሱን ቦታ ተክቶ ሲሰራ የነበረዉ ነዉ። ተስፋይ አብርሃ የነጌታቸዉ አሰፋ፤የነክንፈ ገብረመድህን ቡድን ነዉ ‘ተስፋይ አብርሃ” ማለት። ተስፋይ አብርሃ የሚታወቀዉ “ተስፋይ አፍረሶም” በመባል የሚታወቀዉ ነዉ።ተስፋይ አፍረሶም ብለዉ በአብዛኛዉ የሚጠሩት “ተስፋይ አብርሃ” ማለት ነዉ። እንግዲህ “በየነ፤እያሱ…ወዘተ በሚል ስም የሚጠራዉ ለተስፋይ አብርሃ የ የእህቱ ልጅ ነዉ። በዚህ ግንኙነት በመሳሪያ ታጥቀዉ ሃብታም ነጋዴ ቤት ወይንም ድርጅቱ ድረስ ሄደዉ እያስፈራሩ “በደህንነት ትፈለጋለህ” “በፖሊስ ትፈለጋለህ” እያሉ እና ሚፈልጉዋቸዉን ሃብታሞች በመኪና ጠልፈዉ ይዟቸዉ ይሄዳሉ። ወያኔ ነጋዴ ስለሆነ የሚጫረቱትን ነጋዴዎች ማስፈራራት ማዋከብ ይፈልገዋል እና ነጋዴዎቹም ይህ ባህሪዉ ስለሚአዉቁት ነጋዴዎቹ ስጋት ላይ ናቸዉ። ሰዎቹ ወደ ንግድ ቦታቸዉ ወይንም ከሆነ ካገኙዋቸዉ ቦታ ተልፈዉ በመኪና ለምሳሌ ወደ ባምቢስ የድህንነት ቢሮ አለ ካዛንቺስ ዉስጥ “አንደር ግራዉንድ” አስርቤት ወዳለበት አንድ ድህንነት ኦፊስ አለ ወደ ማዕከላዊ እ…. ወደ ሜክሲኮ ወዳለዉ ልዪ ኦፊስ አለ …ወደ ተላያዩ ወደ እነዚህ ቦታዎች እየወሰዱ በማሳየት ያስፈራሯቸዋል።
ወደ እነዚህ ደህንነት ጽ/ቤቶች ይወስዱ እና አስፈራርተዉ በሺዎች ብር የሚቆጠር ገንዘብ እተቀበሉ ይለቋቸዋል።ለምሳሌ በኔ በ21 ወረዳ ልዩ ቦታዉ “ባክሻፍት” (?) ተብሎ በሚጠራ አጠገብ አንድ ህንዳዊ ዜጋ ነገዴ ነበር። ያ ሕንድ ነጋዴ በተከታታይ ወደ 60 ሺህ ብር በእነ “ጸሃየ” ተወስዶበታል።ይህ የምርመራ ወንጀል እኔ እና ባልደረቦቼ ደርሰንበታል።ይህ ወንጀል ስናዉቅ ሰዉየዉን ሄደን አነጋገርናቸዉ። እንደዚህ ዓይነት ወንጀል ተፈጽመዎበታል፤ ለምንድ ነዉ ወደ እኛ ድረስ መጥተዉ ወንጀሉን ያላመለከቱበት ምክንያት? ብለን ጠየቅናቸዉ። እንግዲህ ካሁን ወዲህ ወንጀለኞቹ እንደልማዳቸዉ ወደ እርስዎ ሲመጡ እኛኑን ወዲያዉኑ ይጥሩን አልናቸዉ። “ታስገድሉናላችሁ” አሉን። ግዴየለዎትም፣ ብለን ቃል ገባንላቸዉ። በመጨረሻ ኦኬ (እሺ) አሉ።
አሁንም ያ “ጸሃየ” የተባለዉ ሰዉየ ደወለላቸዉ።መደወሉን ለእኔ ነገሩኝ። ሲደዉሉ አኔ እና ባለደረቦቼ ወደ ድርጅታቸዉ ስንሄድ 3ሺህ ብር አስፈራርቶ ካሳቸዉ ተቀበለዉን ገንዘብ ይዞ ሲወጣ ወዲያዉኑ እጅ ከፍንጅ ደጃፋቹ ላይ ያዝነዉ። መሳሪያ ታጥቋል።ፎርጂድ የሆነ የታጋይ መታወቂያ ይዟል። ታጋይም ሁን- ሌላም ሁን ምን የምተሄደዉ መንግሥት ቦታ ነዉ፤ ፖሊስ ጣቢያ ነዉ። እዛ ሄደን እነንጋገራለን፡ እና አንሂድ ብለን ከነ ማሳሪያዉ እና 3ሺህ ብሩን ሁሉ ያዝነዉ። የሚገርመዉ ደግሞ ከኪሱ ደግሞ “ካገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር” የሚል ለነጋዴዉ የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ በማሕተም የታተመ የተጻፈ የማስፈራሪያ ደብዳቤ ይዟል። ሻምበል (የሻምበሉ ስም ይጠቅሳሉ- ከቴፑ ጥራት ግን ስሙን በትክክል መለየት ያስቸግራል) ሻምበል (ጥሃፌ/ጸሀፌ (?) ከተባለ ተወካያችን የተለካ ደብዳቤ ነዉ የሚል ማህተም ያለበት ደብዳቤ ሁሉ ይዟል።ከደህንነቱ ተጻፈ አስመስሎ ማለት ነዉ።ይሄን ሁሉ ያዝን እና ወደ ጣቢያ ሄድን።
እኔ ወደ ቢሮ ገብቼ፤ የዕለት ሁኔታ መዝጋቢዎች የተያዛወን ንብረት እግዝቢት እየመዘገቡ እያሉ፡እኔም ይሄን “ጸሃየ” የተባለዉ ሰዉ እያነጋገርኩት እንደለሁ ወዲያዉኑ ከክልል ምመሪያ “ረዳኢ ገ/አነንያ” የተባለ በፖሊስ ሬንጀር መኪና እበረረ ወደ እኔ ቢሮ መጣ። ማን እንደነገረዉ፤እንዴት እንደሰማም አይታወቅም። መጣ። የታያዘዉ ሰዉ አለ ወይ? አለኝ። አዎ አለ፡ አልኩት። ከዚያ ሲያዉ ሰዉየዉን በትግርኛ ተነጋገሩ። እኔ ትግርኛ አልችልም- ግን ፍሬ ነገሩ የተረዳሁት ምንድነዉ፦ለምን አባትክ በየወረዳዉ ትልከሰከሳለህ! የሚል ነዉ።መጨረሻ ሁለቱም ከተነጋገሩ በሗላ “ይህ ጉዳይ በክልል ደረጃ መታየት ስላለበት በክልል ደረጃ እንዲጣራ እኔ ይዤዉ እሄዳሉ አለኝ። እኔም “አይሆንም” ብየዉ ጭቅጭቅ አድረገን፤ ወዲያዉኑ “በላይ የሚባል ካገር ዉስጥ ደህንነት “በላይ” እባላለሁ ነኝ ያለኝ፦ደዉሎ “ይሄ አሁን የያዝከዉ ኬዝ እኛም እየተከታተልነዉ የነበረ ስለሆነ እና በስፋት ለማጣራት ስለምንፈልግ ለረዳኢ ስጠዉ፡ ረዳኢ ይዉስደዉ!” አለኝ። ማነህ አንተ? ስለዉ- እኔ ከደህንነት ነኝ እደወልኩ ያለሁት። አለኝ። እንዴ ታድያ ደህንነት ከሆንክ የደህንነት ስራ ስራ እንጂ ይሄ እኮ የፖሊስ ስራ ነዉ፡ እርግጥ ሚያገናኘን ስራ ዘርፍ ቢኖርም፤ይሄ የወጣለት፤የለየለት ደረቅ የማጭበርበር ወንጀል ስለሆነ-ግለሰቡ እና ማስረጃዎች “ኦልሬዲ” የተያዘ ስለሆነ ማስረጃዎች ተጣርቶ ወደ ሚመለከተዉ ሕግ ይቀርባል እንጂ እንዴት ወደ የበላይ ይሂድ ትለኛለህ? ስለዉ “ስጠዉ ማለት - ስጠዉ ነዉ “ስጠዉ ብየሃለሁ! ስጠዉ ብየሃለሁ!” አለኝ።
በመጨረሻ ተስፋይ አብርሃ (አፍረሶም) (ቅድም የፀሃየ የእህቱ ልጅ ነዉ ብየ የጠቀሰውኩት ባለስልጣን ደዉሎ ለረዳኢ አስረክበዉ ብየሃለሁ ብሎ ደዉሎ አሱም ከኔ ጋር ንትርክ አድርጎ የተያዘዉን መሳርያ እና የመሳሪያዉ መለያ ቁጥር፤ እንደዚሁም 3ሺህ የተያዘዉ ገንዘብ ረዳኢ ይዞት ሄደ። ለታሪክም መዝገቡ ካልጠፋ ወይም ካልቀደዱት በወረዳ 21 የዕለት ሁኔታ መዝገብ አስከ እነ ቁጥሩ ቀን ዓ/ም ይገኛል።መሳሪያዉ ቁጥር፤ የሐሰት የደህንነት ደብዳቤ ከነ ሸኚ ቁጥሩ ሳይቀር ሁሉ ተመዝግቦ ይገኛል።ተጠያቂዉም አብሮ ከነ መዝገቡ ይዞት ሄደ። አንድ ሰዓት አልቆየም ይሄ ይዞት የሄደዉ ‘በየነ’ ‘እአሱ’ ‘ጸሃየ…እገሌ እገሌ እያለ በተለያየ ስም የሚያጭበረብረዉ ወንጀለኛ ስልክ በቀጥታ ወደ እኔ ደወለ። ደዉሎ ምንድ ነዉ ያለኝ- “ከማን ጋር እየታገልክ እንደሆንክ እወቅ! ለምድነዉ አርፈህ እንጀራህን በሰላም እየበላህ የማትኖር? ካስፈለገ እኮ የአንተ ጉዳይ የደቂቃ ስራ ጉዳይ ነዉ! ብሎ በስልክ ደዉሎ አስጠነቀቀኝ። እኔም ስመልስ_ አንተ ምትችለዉን አድርግ እኔም አለሁኝ! አልኩት እና በዚህ ተለያን።
አንግዲህ በነ ተስፋይ አብርሃ በእነ ረዳኢ ገብረአነንያ በኩል ነዉ መሳሪያዉን የሚያገኘዉ። ይዞት የነበረዉን ያጭበረበረበትን መሳሪያ ፈቃድ አሳየን ብለን ስንጠይቀዉ የማሳሪያዉ መለያ ፈቃድ የሚያሳየዉ “”ረዳኢ ገብረአነንያ” ይላል።ረዳኢ ገብርአነንያ ማለት ደግሞ ‘የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ሃለፊ” ነዉ። ሌሎች ትግሬ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን ግን በሆነ አጋጣሚ መሳሪ ይዘዉ ከተገኙ ተይዘዉ ይታሰራሉ።ወይ ኦነግ ነዉ ወይ መኢአድ ነዉ ወይ የኦሮሞ ኮንግረስ ወይ የደቡብ ህዝቦች አባል ነዉ የሚል የፖለቲካ ስም ይለጠፍበት እና “ጀርባዉ ይጣራ” የሚሉት ቋንቋ አላቸዉ። ይሄ ጸረ ኢሕአዴግ ነዉ፡መሳሪያ ከየት ሊያመጣ ይችላል? ተብሎ ስቃዩን ያያል። የትግራይ ተወላጆች ግን 3 አራት ማሳርያ አላቸዉ። ይሄ የሚደረግዉ እንግዲህ ወያኔ ራሱ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” እንደሚባለዉ “ራሱ ዳኛ ነዉ” ራሱም “ይዘርፋል ወይም ያስዘርፋል” ።ስለዚህ በቡድን በእጅ አዙር በመንግስት ባለስልታኖች የሚሰራ የወንጀል መተባበር ተግባር እና ትስስር ተለመደ ነዉ።
ሌላ ዓይነት ቡድን ደግሞ አለ
አንድ ቀን ታጋይ ሐዱሽ፤ታጋይ ጀማል፤ታጋይ ዜናዊ የተባሉ በቀን መኪና አስቁመዉ ከዛዉ ከእነ ተስፋይ አበርሃ ቢሮ ትንሽ ዝቅ ብሎ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ (የተስፋይ አበርሃ ቢሮ ነዉ) ከዚየዉ ዝቅ ብሎ ከጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ጀምሮ አስከ መክሲኮ ድረስ በአንድ መኪና እየበረሩ መጥተዉ፤ ክላሽን ጠመንጃ ይዘዋል፤ሽጉጥ ታጥቀዋል፤የመከላከያ ደምብ ልብስ ዩኒፎረም ነዉ የለበሱት፤ሦስት ናቸዉ፡ አንዱ ሾፌር ነዉ-ከደጅ ሆኖ ይጠብቃል፤ ሁለቱ በመደዳ በወቅቱ ክፍት በነበሩ ቡናቤቶች ገብተዉ ለመዝናናት የመጡ ደምበኞችን ሁሉ ወለል ላይ በሆዳቸዉ አስተኝተዉ -ሰዓት ያለዉ ሰዓቱን፤ወርቅ ያለዉ ወርቁን፤ የቡና ቤቱ ቴፕ ሪኮርደር እና ከመጠጥ ሽያጭ የተገኘዉ የቡና ቤቱ ባለቤት ገንዘብ ካለም ገንዘቡን ዘርፈዉ መኪናቸዉ ይሰወራሉ። እንግዲህ እንደዚህ እያደረጉ ከላይ ከ እዛ… እንግዲ አዲስ አበባ ለሚያዉቅ ሰዉ ግልጽ ነዉ፤-ከፕያሳ ጀምረዉ በቴድሮስ አደባባይ አድርገዉ በመስቀል አደባባይ አድርገዉ እንደገና እየዞሩ አስከ ሜክሲኮ አደባባይ ድረስ ሲመጡ መደዳዉን ስላዳረሱት ህዝብ ተዘርፏል እና ለእርዳታ ድረስ ተብሎ ለክልሉ በስልክ ሲነገር_ የክልሉ ተረኛ ፖሊሶች ይህነን ይሰማሉ።-
ድርጉቱ ሲፈጸም አጋጣሚ ምሽት ስለነበር፤-የበላይ አለቆች በእዛ ሰዓት በየአረቄ ቤቱ ስለነበሩ ከወገንተንነቱ ነጻ የሆኑ ፖሊሶቹ ይህነን ሃላፊነት ለመወጣት ጥሩ አጋጣሚ አግኝተዉ የዘረፋዉ ዜና በየወረዳዉ በስልክ ስያስተላልፉልን፤ጥበቃ ማድረግ ጀመርን። በዘረፋዉ ወቅት ዘራፊዎቹ የተጠቀሙባት የታክሲ መኪናዋ ልዩ መለያ ምልክት ተነግሮን ስለነበር እመክሲኮ አደባባይ ስትደርስ ታክሲዋን አየናት። ተከታተልንባቸዉ። እነሱን ተከታትለን ወደ ልደታ አቀናን ቀጠሉና ሄዱ፡ ከልደታ ወደ…(የቴፑ ድምጹ ጥራት በደምብ አይሰማም) ሲሄዱ እዛዉ ደረስንባቸዉ። ከመኪና ሲወርዱ አስቆምናቸዉ። ስናያቸዉ የለበሱት ልብስ የመከላከያ ነዉ፡ሽጉጥ ይዘዋል፤ክላሽ አነግተዋል፡ ይገርማል! ይሄነን ለተመለከተ ሰዉ እነኚህ ሰዎች ዘራፊዎች ናቸዉ ብሎ ደፍሮ ለማለት የስቸግራል። መጨረሻ እጃችነን አንሰጥም አሉን። እኛም አግባብተን “አይ ሌሎች ሰዎች መስላችሁን እኮ ነዉ፣ ለካ እናንተም ታጋዮች ናችሁ’ ብለን አዘናጋናቸዉ እና በመጨረሻ የተጠቀምነዉ ስልት አለ፦አያነጋገርን ያዝናቸዉ።መሳሪያቸዉንም የዘረፉት ንብረትም ገንዘቡንም ሁሉ አነሱንም ይዘን ወደ ጣቢያ ሄድን።
ታክሲዋ/መኪናዋም ጭምር ወረዳዉ ፖሊስ ጣቢያ ታግታ ለብዙ ጊዜ ቆማ ነበር። ሾፌሩ “እኔ ተገድጄ አስገድደዉኝ ነዉ እንጂ በዚህ ስራ ወድጄ አልተሰማራሁም” ስላለ ዳኛዉም ዉሳኔ መስጠት አቅቶት ነገሩ ሲጎትተዉ መኪናዋ ለብዙ ጊዜ ቆማ ተገትራ እዘዉ ነበረች። በመጨረሻ ላይ ምርመራ ተደርጎላቸዉ ሲጠየቁ “ዛሬ ብታስሩን -ነገ እነፈታለን”እያሉ ያሾፉብን ነበር። የዉም የሚገርመዉ “መታሰራችን ሳይሆን የሚቆጨን የዘረፍነዉን ገንዘብ ሳንጠቀምበት መቅረቱ ነዉ”-አለን ‘የማነ’ የሚባለዉ ከዘረፉት ንብረት ጋር ፎቶግራፍ ሳስነሳዉ።”እኔን ዘረፍክ ትሉኛላችሁ-የተዘረፍኩት ግን እኔ ነኝ” አለን የዘረፉት ንብረት ባንድነት ተቀምጦ ሲያየዉ አሳሳዉ/አስጎመጀዉ። “ይሄ ሁሉ ይዤ ብሄድ ኖሮ ነበር “ዘረፍክ የምባለዉ፤ነገር ግን የተዘረፍኩት አኔ ነኝ እያለ ሲቀልድብን ነበር።
በመጨረሻ ተጣርቶ ለሚመለከተዉ ስናስረክብ በዋስ እንዲለቀቁ ተደረገ። መሳሪያን ተጠቅሞ በሰላም የሚዝናናን በሰላም በየጎዳናዉ እና በየ አደባባዩ ወደ ቤቱም ወደ ስራም የሚንቀሳቀስ ሰላማዊ ዜጋን መዘርፍ እና ሽብርን መልቀቅ በጣም ከባድ ወንጀል እና አስከ 15 ዓመት በእስር የሚያስቀጣ የወንጀል ድርት ነዉ።ዜጎች እንደልብ እንዳይንቀሳቀሱ በየመንገዱ እና በንግድ ተቃሟት እገባ የሚያስጨንቅ በፍርሃት ሚገድብ ሚያሸማቅቅ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚዎች በወቅቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት የነበሩት የትግራይ ሰዉ “አቶ ሐጎስ” የሚባሉ እንዲለቀቁ አደረጓቸዉ።
አብዛኛዉ እንደዚህ ያለ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ አለበት ከተማ ዘረፋ ሽብር ላያዉቀዉ ወይንም ሰምቶት የማያዉቅ ብዙ ሰዉ ሊኖር ይችላል።ለዚህም ነዉ እኔ በፖሊስ ሞያነቴ ተሰማርቼ እንደዚህ ዓይነቶቹ መንግስታዊ ወንጀሎች ሲፈጸሙ በማየቴ ያየሁትን መረመርኩትን ለህዝብ ምስጢሩ ተደብቆ እንዳይቀር የማጋለጥ ሃለፊነት ሙያየ ስለሚያስገድደኝ ህዝቡ እንዲያዉቀዉ ይገባል በሚል ነዉ።በመንግሥት የተቀነባበረ ግድያ (ለምሳሌ ሻምበሉን እንደገደሉት ዓይነት)፤በቡድን እና በግለሰብ በባለስልጣኖች የተቀነባበረ ዘረፋ፤ነጋዴ ሕብረተሰቡን ማስጨነቅ ማስፈራረት የመሳሰሉት ከመንግስት ባለስልጣኖች ጋር እተመሳጠሩ የወንጀል ድረጊቶች ተፈጽመዋል። ኢሕአዴግ ነጋዴ በመሆኑ ፤ነጋዴዎችን በማስፈራራት እንዲሸማቀቅ እና ከጨዋታዉ ዉጭ ሊያደረግዉ ይፈልጋል። ወደደም ጠላም ከፍራቻ ነፃ ለመሆን (እንዳይዘረፍ) ከኢሕአዴግ ባለስልጣን ቢያንስ አንድ ወዳጅ እንዲይዝ እንዲሞዳሞድ ሰላም በዉስጡ እንዲሰማዉ ጀርባዉን እንዲተማመን ያደርጉታል። ስለዚህ በሕዘብ ላይ የሚደረግ መንግሥታዊ ደባ ህዝቡ ማወቅ አለበት።
ይህ ተቀነባበረ የዘረፋ እና የፖለቲካ ወንጀል ፖሊስ ኮሚሽነረሩ አቶ ተስፋይ አብርሃ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወንጀል መከላከል ሃለፊ የአቶ ረዳኢ ገብረአነኒያ እጅ እንዳለበት ከላይ የገለጽኩት በወረዳችን በወረዳ 21 ሲካሄድ የነበረዉ የተቀነባበረዉ ዘረፋ ወደ ወረዳ 20 ሽፍት አድረጎ ወደ ወረዳ 20 አዞሩት። ወረዳ 20 ማለት በዞን ሁለት ቄራ አካባቢ የሚገኘዉ ወረዳ ማለት ነዉ። እና በሌሎች ወረዳዎች በወረዳ 19 17 20 23 24 ወረዳዎች እየተዘዋወረ የሚዘርፍ ቡድን ነበረ። ከነዚህ ቡድኖች ዉስጥ አሁንም ዜናዊ ነበረበት። ዜናዊ ማለት ቅድም ስጠቅስ ከነ ጀማል ጋር የነበረ ነዉ። እንደገና ከዚህ ቡድን ጋራ አስቀድሞ ሲዘርፍበት በነበሩት ወረዳዎች ትቶ በእነዚህ በተጠቀሱት አዳዲስ የዘረፋ ወረዳዎች መዝረፍ ጀመሩ። እነዚህ በተከታታይ በጦር መሳሪያ በመደገፍ በየመንደሩ በየቤቱ እየገቡ እያሰሩ ዘረፋቸዉን ያካሂዱ ነበር። ይህ ድርጊት በጊዜዉ ጉዳዩን ሲከታተሉት የነበሩት እነ መቶ አለቃ ክፍሉ እነ መቶአለቃ ስሞኦን እ… እራሱ የወያኔዉ ሹም የነበረዉ የዞን አዘዥ “አጋዓዚ” እ…… እነ ወታደር ማዕርጉ እ….. ምሕረታብ የሚባሉ ይህነን ነገር ያወቁታል። ምክንያቱም እነሱ ነበሩ እንዲመረምሩ ትዕዛዝ ተሰጣቸዉ።
ከላይ የጠቀስኳቸዉ የምርመራ ባልደረቦች በምርመራዉ ላይ ጥሩ አልሰራችሁም ተብለዉ ከስራ አገዷቸዉ።ሜርኲሪ የሚባል የማጭበርበሪያ ስልት አለ፡ የተጣራዉ ዝርዝር ምርመራ በእዛኛዉ በሜሪኩሪ ኮሚቴ አልፎ ወደ ደህንነት ከዛዉ ወደ ትላልቆቹ ባለስልጣኖች ቢሮ ሲሄድ የነበራቸዉ አማረጭ ምርመራዉን ማስቆም ነዉ። ምርመራዉን ለማስቆም ደግሞ ሲመረምሩ የነበሩትን ልጆች ምርመራ አሳጥታችሗል/አጋልጣችሗል፤ሰብአዊ መብት ረግጣችሗል በሚል እነ ወታደር ማዕረጉ እነ ምሕረታብ እነ መቶአለቃ ክፍሉ እራሱ “አጋዓዚ” ሳይቀር ይመሰክሩታል። አጋዓዚ ራሱ በዚህ ምክንያት ከስራዉ ታግዶ ነበር። መርማሪዎቹ ከስራ ሲባረሩም ሁኔታዉ በጣም ስለገረማቸዉ “ ሰራቂዉ ትግሬ፤ዓቃቤ ሕጉም ትግሬ፤ዳኛዉም ትግሬ፤ ታዲያ ይሄ ከሆነ የኛ በቦታችን ሆነን ጉዳዩን መመርመር ፋይዳዉ ምንድነዉ? ብለዉ በምሬት ስለተናገራቸዉ -ከስራ ተባረሩ። ምክንያቱም በተጨባጭ የተረጋገጠ እና የምናዉቀዉ ሲዘርፉ የነበሩት ትግሬዎች ናቸዉ፤
ጉዳዩ ተጠርቶ ለከፍተኛ ሲላክ ጉዳዩን በአጋጣሚ የተላለፈለት የተረከበዉ አቃቤ ሕግም ትገሬ ነዉ፤ አሱ ጋር ሲደርስ አሱም በዋስ ልቀቁዋቸዉ አለ። ዳኞች ጋር ቀርበዉ ሲያመለክቱ “አይ እኛ አናስርም” አሉ። አናስራቸዉም ብሎ ትዕዛዝ የሰጠዉ ዳኛ ደግሞ ትገሬ ነበር። በዚህ ተበሳጭተዉ ነበር “እንዴ! ዘራፊዉ ትግሬ ፤ዓቃቤ ሕጉም ትግሬ ዳኛዉም ትግሬ ስለዚህ በማሃል ገብተን መዳከራችን ምን ዉጤት አመጣ?” በማለታቸዉ “መንግሥትን ነቅፋችሗል የመንግስት ወገኖች ሳትሆኑ መንግስት ጠላቶች ናችሁ” ብለዉ እንዲባረሩ ተደረገ። አሁን ስራ የላቸዉም እነዚህ ሰዎች። አጋዓዚን የዞኑን አዛዥ የነበረ በዚህ ረገድ የኢሕአዴግን ጥቅም አላስጠበቅክም ተብሎ አሱንም ከ ሌሎቹ ቅን መርማሪዎች ጋር አግደዉት ለወራቶች ካንከራተቱት በሗላ ይመስለኛል መልሰዉ ከዞን አዘዥነት ስልጣኑን አዉርደዉ በወረዳ 28 አካባቢ በጣም ትንሽ ደካማ ጣቢያ በሆነች የወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ አድርገዉ መለሱት። የተቀሩት ስራ አጥ ሆነዉ ተንከራትተዉ ነበር። ዛሬ በምን ሁኔታ ላይ አንዳሉ አላወቅኩም። እና እነዚህ የመሳሰሉት ወንጀሎች፤ባለስልጣኖቹ የፖሊስ ሃይል ጽ/ቤቶችን የደህንነት ስለጣኖችን በመጠቀም ያስዘርፋሉከዘራፊዎችም ጋር ጥቅም ይካፈላሉ።
ሌላዉ በጣም ልብ ብሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊገነዘበዉ የምፈልገዉ ነገር ለየት ያለ የአገሪቱን ከኢኮኖሚ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የዘረፋ ድርጊት ልግለጽ። አንድ ባገሪቱ ዉስጥ በግምባር ቀደም የሚጠቀስ ድረጅት አለ፡ እና በጥሞና እንድታዳምጡኝ እጠይቃለሁ። የድርጅቱ ስም “የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን” የሚባል መረጃዉ እንደሰማሁት ምናልባትም ካገሪቱ በጀት ግማሹን ለዚህ ድርጅት ተመድቧል። በዚህ መ/ቤት ዉስጥ ሚደረግ ምዝበራ አስመልክቶ አንድ ማስረጃ ላቅርብ። የህ ድርጅት በወረዳ 021 ቀበሌ 24 ልዩ ቦታዉ መክሲኮ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ነዉ የሚገኘዉ።ትልቅ ህንጻ ነዉ። እ…. መስርያቤቱ በማዕከልነት ለመምራት የተቋቋመ መስርያቤት ነዉ። ሌሎች የክልሎች ባለስልጣኖች አሉ። ይሄ የጠቅላላ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ነዉ።ግዙፍ ነዉ። ስራዉ መንገድ መስራት ነዉ። ሁለት የመንገዶች የስራ ዘርፎች አሉት። አንዱ በመንግስት የሚከናወን ሌላዉ የግል ኮንትራክት ተጫራቾች የሚያከናዉኑት አሰራር ነዉ። ኮንትራክተሮቹ ከዚህ ድርጅት ጋር ተፈራርመዉ የሚሰሩ ተዋዋየች ናቸዉ።
እኔ አስከ ማዉቀዉ ድረስ በ1989 ዓ/ም አካቢ ጀምሮ በዚህ መስርያቤት ዉስጥ በተከታታይ ዘረፋዎች ሲካሄድ እኔ የማዉቀዉ በተጫባጭ የደረስኩበት ምርመራ ነዉ።ዘረፋዉ ሚካሄደዉ ምንድ ነዉ? የመስሪያቤቱ ንብረት ይሰረቃል፤ በወረዳ 21 እና ቤሎችም ንበረቶች የሚቀመጥበት ግምጃ ቤት አለ።ሌሎችም በወረዳ 18 እና ሌሎች ግምጃቤቶች አሉት። ግን እኔ መግለጽ የምፈልገዉ በእኔ ወረዳ በነበረዉ ጉዳይ ነዉ። ምረመራዎች በሂደት እየተደረጉም እያሉ፤ አሁንም በተደጋጋኒ ያለማቋረጥ ሌላ ስርቆት ይካሄዳል። ዕቃዎች ይጠፋሉ ይዘረፋሉ። ዘራፊዉ አይታወቅም። መቸ ተዘረፈ? በማን ተዘረፈ? የሚል አይታወቅም።የመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ለይስሙላ ብቻ መሰረቁን ደብዳቤዎች ይጽፉ ነበር። የሚጽፉት ለማን ነዉ_ለማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራ ማስተባበሪያ ለእነ “ታደሰ መሰረት”፤ ታደሰ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ነዉ። ለነሱ ይጻፋል። ቀጥሎ የሚጽፉት ለአዲዩስ አበባ ፖሊስ ነዉ። “ተስፋይ አብረሃ” ሳይቀር ያዉቀዋል።ኮሞሽነር በነበረበት ጊዜ በተከታታይ ደብዳቤ ተጽፎለታል።
ይሄ መስርያቤት በእኛ ወረዳ በወረዳ 21ፖሊስ ጸ/ቤት ክልል በመሆኑ ለተጠቀሱት መ’ቤቶች ሲጻፍ ለእኛ በግልባጭ ያመለክቱን ነበር። እኔ ጋር ይመጣል፡ ቢሮ ዉስጥ ተመዝግቦ ይቀመጣል። ሁኔታዉን አያለሁ።ከስድስት ወር በፊት የተጻፈዉ ደብዳቤ መለስ የለዉም፤ዘረፋዉ አሁንም ቀጥሏል፤ አሁንም አዲስ የዘረፋዉ አመላካች ደብዳቤ በተከታታይ ይጎርፋል። በክልሉ የምርመራ ሃለፊ የነበሩ መቶ አለቃ አስፋ አየለ የሚባሉ ይሄን ነገር ጠየቅካቸዉ።እንዴ! ይሄ መስሪያ ቤት ተከታታይ ደብዳቤዎች ለናንተ ይጽፋል፡ ለኛም በግልባጭ ያስታዉቀናል፤የተካሄደ ምርመራም የለም። ይሄ ብሔራዊ ወንጀል/ናሺናል ክራይም ነዉ እና እንዴት ነዉ መቶ አለቃ አሰፋ የምታዉቀዉ ነገር አስቲ አካፍለኝ፤ይሄ ጉዳይ አሳሳቢ ነዉ፤አገሪቱን ይጎዳል ብየ አወያየሁት። መቶ አለቃ አሰፋ አየለ ጥሩ አዋቂ የፖሊስ መኮንን ነዉ። አይ! “አበረ” ይሄን ነገር ባታነሳብኝ ጥሩ ነዉ አለኝ። የተወሰኑ ሦስት የመስሪያ ቤቱ ዘበኞች ምርመራዉን ለማጣራት አስሮ አንደነበር ነገረኝ። በሁለተኛዉ ቀን ልቀቁዋቸዉ ተብሎ ተለቀቁ። እንዴት? ለምን? ሲባል -በስረቆቱ ጉዳይ ብዙ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣኖች እጅ ስላለበት እነኚህ ዘበኞች ለትንሽ ጊዜ በእስር ቢቆዩ ምስጢሩን ስለሚያወጡ እና ባለስልጣኖቹ እና ንክኪያቸዉ አብረዉ ስለሚጋለጡ በዚህ ስለሰጉ እንዲለቀቁ ተደረገ። ይቀጥላል…….

Wednesday, December 10, 2008

ቀይ ባሕርን በኑክሌር አተላ መበከል፤የኢሳያስ አፈወርቅ ትብብርና የአምባሳደሩ ግድያ
ቀይ ባሕርን በኑክሌር አተላ መበከል፤
የኢሳያስ አፈወርቅ ትብብርና የአምባሳደሩ ግድያ ጌታቸዉ ረዳ
አቶ ዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ በተባሉ ኤርተራዊ በተከታታይ በተለያዩ ርዕሶች በትግርኛ ጽሑፍ ለትግርኛ አንባቢዎችhttp://www.asena-online.com/
ይፋ እያደረጓቸዉ ያሉትን ምስጢራዊ ሰነዶችን እንድትከታተሉት በማለት በአማርኛ ተርጉሜ ለአንባቢዎች አንኳር ሰነዶችን እያዘጋጀሁ እንዳስነበብካችሁ ይታወሳል። ይህ የዛሬ ጽሁፍ ካለፈዉ የቀጠለ ተከታታይ ሰነድ ነዉ። የሰነዱ አቅራቢ/ምንጭ ሲዘግቡት ከላይ በአርዕስቱ እንደተመለከተዉ የቀረበ ርዕስ ሳይሆን በኔ በኩል ለታሪክ ዘጋቢዎች ዳሰሳ እንዲያመች በማለት ባንድ ተሰባስበዉ የተዘገቡና የተሰበጣጠሩ ሰነዶች ሰብሰብ በማድረግ ድርጊቶቹ የየራሳቸዉ ርዕስ ጠብቀዉ እንዲነበቡ አድረጌ አለሁ። ድርጊቶቹ የየራሳቸዉ አመድ ጠብቀዉ መዘገባቸዉ እንጂ ትርጉሙ ያዉ የቋንቋ መልስ እና ያጠቃቀም ስርዓት ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ከፍሬ ነገሩ የተለወጠ ነገር የለዉም። ሰነዱ ጠለቅ ያሉ ብዙ ነገሮችን በዉስጡ ይፋ አድረጓል። የዘመን ቆጠራዉ “በኤርትራዉያኖቹ -በፈረንጅ” አቆጣጠር ነዉ።ተከታተሉት። መልካም ንባብ።

“የኢጣሊያ መንግሥት ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ከኢንዱስትሪዎቿ የተገኙ ቆሻሻዎች እና የኑክሊየር አተላዎች መጣያ ስታፈላልግ ባጀታ፤ሕዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ በ02/17/1988 ደርግን የቀይ ባሕር ዉሃ የቆሻሻ መጣያ አድርጎታል፡ በማለት ሲቃወመዉ የነበረዉን የዉንጀላ አቋም በመዘንጋት በ14/03/2005 ኢሳያስ አፈወርቅ እና የኢታልያዉ መንግሥት ጠ/ሚኒስትር ቢሎስኮኒ መካከል በተደረገዉ ሰምምነት መሰረት፤ የ ኤርትራዉ ፕረዚዳንት ወደ ኢታሊ በመሄድ የጣሊያን የኢንዱስትሪዎች መርዛማ ቆሻሻ አተላዎችን በቀይ ባሕር እንዲጣሉ እና አንዲደፉ ዋና የጉብኝቱ አጀንዳ ያደረገ ስምምነትን ነበር።

በስምምነቱ መሰረትም በምፅዋ ደሴት(2) ‘ዕዳጋ’ በመባል በሚታወቀዉ የከተማዉ ቀጠና ዉስጥ (1) እና ሌላም ‘ጥዋለት’ በተባለዉ የምፅዋ አካባቢ ከሕዝብ ዕይታ በአጥር ከላላ ተጋርዶ በነበረዉ አካባቢ ላይ በድምሩ 136 ቶን መርዛማ አተላ አንዲጣል በመሰማማት 136 ቶን ክብደት ያለዉ መርዛማ አተላ በተጠቀሱት ቦታዎች ተደፍቷል።

ጉዳዩም በአንዳንድ የአካባቢዉ ሹሞች ዘንድ ቁጣ አስነስቶ ነበር። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢሳያስ ጋር ወደ ጣሊያን አገር ጉብኝቱን አጅቦ አብሮት የሄደዉ በጣሊያን አገር የኤርትራ አምባሳደር የነበረዉ አምባሳደር ዓንደሚካኤል ካሕሳይ ሚስጥራዊ የስምምነቱ ዉል በመቃወሙ ምክንያት በኢሳያስ አፈወርቅ ትዕዛዝ ለኮሎኔል ጋይም ተላልፎ በደህንነቱ ክፍል በካፕቴን እስቲፋኖስ እና በካፒቴን ነጋሲ ዓንደ አቀነባባሪነት “ጣባ” በተባለዉ አካባቢ ገድለዉት ሬሳዉ ተጥሎ ተገኝቷል።

ሰበቡ በዛ ብቻ አላቆመም።የቀይ ባሕር አዉራጃ አስተዳደር አስተዳዳደሪ የነበረዉ ‘አብራሂም ቶቲል’ በሰሜናዊ ቀይ ባሕር በምፅዋ ከተማ ሲካሄድ የነበረዉ ምስጢራዊ የመሬት ቁፈራ ባማያዉቀዉ እና አሱ ሳይፈቅድ በመደረጉ ቁፈራዉ ለምን እዳስፈለገ እና ማብራሪያ አስካልተሰጠዉ ድረስ ቁፈራዉ እንዲያቆም በማዘዙ፡ ‘ከሚገባህ በላይ ምስጢር ለማወቅ ሙከራ አድርገሃል”፡ በሚል ሰበብ ከስልጣኑ እንዲወገድ በማድረግ በጀነራል ሙሳ ራባዕ ተተካ። ጀነራል ሙሳም ብዙ ሳይቆይ ተመሳሳይ ዕጣ ደረሰበት።

የኤርትራ መንግሥትም ለዚህ ክንዉን 12 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሎታል። የኤርትራ የዜና መገናኛዎች እንደሚያወሩት፤ ኢሳያስ ወደ ጣሊያን አገር በሚመላለስበት ወቅት ‘የኤርትራ እና የኢጣሊያ መንግሥት ትልልቅ ፕሮጀክቶች ተፈራረሙ’ እያለ ዜና ቢያስተላልፉም፤ ትላልቅ ከተባሉት ፕሮጀክቶች አንድም የተሰራ የለም። በምትኩ የተከናወኑት ስምምነቶች- በቀይባሕር ምድር ቆሻሻ እንዲጣልና ለመጣያዉም የገንዘብ ክፍያ ስምምነቶች ብቻ ነበሩ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢራን ከሩቅ ሆና ስትከታተለዉ የነበረዉን ትራጄዲ ወደ ራሷ ኮመዲ ለመለወጥ ጊዜ አልፈጀባትም።በመሓመድ ቓስም አቀነባባሪነት ከ2007 ጀመሮ ኤርትራ የኢራን የኑክሌር አተላ ወደ ኤርትራ ቀይ ባሕር ዉሃዎች እንዲደፋ ስምምነት ፈርማለች። ቀይ ባህርን የምትቆጣጠረዉ ኢራን አስካሁን ድረስ በሁለት መርከቦች የተጫነ 680 ቶን መርዛማ የኒኩልየር ዌስት/አተላ ለመድፋት አስችሏታል።ለዚህም ትብብር ኤርትራ በመቶ ሚሊዮኖች ዶላር ተከፍሏት እንደ የዉጭ ምንዛሪ ገቢ ተጠቅማበታለች።

ቀደም ብለን እንደተመለከትነዉ በብርጋዴር ጀነራል ፍጹም ገ/ሕይወት ሲቀነባበር የነበረዉ የባሕር ላይ የጠለፋ ዉምብድናዉ ሁሉ፤ ይህ አደገኛ መርዛማ የኢንዱስትሪ ቆሻሻ መድፋት ምስጢራዊ ክንዉንም በማዕከልነት የሚመራዉ ጀኔራል ፍጹም ገ/ሕይወት ሆኖ አብሮት በጣምራ የሚሰራዉ የባሕር ሃይሉ አባል ኮሎኔል መሓሪ ደስታ ነወ። በዚህም መሰረት በ11/06/2007 ቆሻሻዉን የመድፋት ክንዋኔ ተፈፅሟል።
ኮሎ ኔ ል መሓሪ ደስታ በዚህ የምስጢር ተግባር በመሳተፉ ለስራዉ አገልግሎት ጉርሻ በብርጋዴር ጀኔራል ኢዮብ ፍስሃየ (ሓሊባይ) አስተዳደር ሥር ሚካሄደዉ የመንግሥት ቤቶችና የምሪት ቦታዎች ዕደላ ጽ/ቤት፤ ድሮ ጣሊያናዊዉ ሃብታም ‘ሲኞር-ባራቶሪ’ ገንብቷቸዉ በነበሩት ምርጥ የመኖርያ ቤቶች (ደቡባዊ ምዕራብ አስመራ አካባቢ) አካባቢ በየማነ ገብረመስቀል (ቻርሊ) በኩል በኢሳያስ አፈወረቅ ትዕዛዝ ምርጥ የመኖርያ ቪላ እንዲሰጠዉ ተደረገጓል። ከዚህ ሌላ ከብርጋዴር ጀነራል ፍጹም ገ/ሕይወት እጅ $25,000 ዶላር ጉርሻ ተሰጥቶታል።

ኢሳያስ አፈወርቅም በበኩሉ በ04/15/2002 ወደ ሊቢያ ሲጓዝ ለሶማሌ እስላሞች ፍርድቤት ግምባር ትብበር እና እርዳታ በማድረጉ ምክንያት ከኮለኔል ጋዳፊ እጅ የ$1,000,000,000.00 (አንድ ቢሊዮን ዶላር) ጉርሻ አግኝቷል።

የኢራን መርከብ የኒኩልየር ዝቃጭ ቆሻሻ ጭና ወደ ቀይ ባሕር ስትጓዝ የነበረችዉን መርከብ የአሜሪካን ባሕር ሃይሎች ለፍተሻ በማስቆም ፤መርከቢቷ የጫነችዉን ጭነት ማስፈተሽ እንዳለባት ወይንም አቅጣጫዋን በማዞር ወደ መጣችበት ማዞር እንደሚኖርባት ትዕዛዝ ሰጥተዉ ያስቆሟት ዕለት መርከቧ ዉስጥ ተሳፍሮ የነበረዉ ኤርትራዊዉ ሰዉ በዳይቪነግ ከፍተኛ ችሎታ ያለዉ የኤርትራ የባሕር ሃይል አባል የነበረዉ ሌተናል ኮሎኔል ተስፋሚካኤል ባሲሎስ ነበር።

በዚህ ወቅት በOctober 06/2008 የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታዉ ክፍል በሶማሊ ቀይ ባሕር አካባቢ እየታዩ ያሉት የተለያዩ ሕገ ወጥ ተግባሮችን ለመቆጣጠር በአካባቢዉ ሚንቀሳቀሱ ተዋጊ አይሮፕላኖች እና የመርከብ ባለቤቶች ሁሉ አስፈላጊዉን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ያስተላለፈዉ።እንደሚታወሰዉ ባለፈዉ ምዕራፍ እንደተገለጸዉ በዚህ ምክንያት ተነሳ ነበር ሁሉም የዓለም አባል ሃገሮች ማሕበር በዉሳኔዉ እና በጥሪዉ ሲስማሙ ኤርትራ ግን በወኪሏ በተባበሩት መንግታትሥታት የኤርትራ አምባሳደር በአቶ አርአያ ደስታ በኩል ተቃዉሞዋን አሰምታ እንደነበር ይታወሳል። ይቀጥላል… “

Tuesday, December 9, 2008ኤርትራ ፤ሕገ ወጥ መሳሪያ ፤ዓለቃይዳና ታሚል ታይገሮች ጌታቸዉ ረዳ ካለፈዉ የቀጠለ- ምንጭና የሰነዱ አቅራቢ ኤርትራዊዉ አቶ ሕሉፍ ፈዳይ ንጉሥhttp://asena-online.com/ በትግርኛ ለትግርኛ አንባቢዎች እያስነበቡት ያሉትን የቀይ ባሕር አካባቢ ሁኔታ ወደ አማርኛ በመመለስ ለአማርኛ አንባቢዎች እያስነበብኩኝ ነበር። ዛሬም ከላፈዉ የቀጠለ ኢሳያስ እና የባሕር ዉንብድና ተግባሮች ከሚለዉ የቀጠለ ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ ኤርትራ አልቃይዳ፤አሸባሪዉ የሶማሌዉ ቡድን የመሳሪያ ማሸጋገር ተግባር እና የታሚል ታይገሮች ግንኙነት ወዘተ ጉዳዮችን እንመለከታለን። “በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የሶማሌ እስላሞች ማሕበር ታጣቂዎች በኤርትራ መንግሥት ተባባሪነት እና እንክብካቤ ከሶማሌ ወደኤርትራ ከዛም ወደ ሶሪያ ሊቢያ በመጓዝ ወታደራዊ ስልጣና ካገኙበሗላ ወደ ሊባኖስ በመሄድ ከሑዝብላ ታጋዮች ጋር በመዋሃድ የ”ሻሃዳ” ተልዕኮ የሚጠይቀዉን ተግባር በመፈጸም ላይ እንዳሉ የሚያሳይ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣቸው ሰነዶች የክስ ጣንወደ ኤርትራ ያመለክታል። (ምናለባት ሻሃዳ ሚለዉ አረባዊ የሃማኖት ቃል ትርጉሙ ለማታወቁት “መጠመቅ፣ በአባልነት መመዝገብ፤-----እንግሊዝ “መምበር-ሺፕ” የሚለዉ አባባል ነዉ- ትርጉም ጌታቸዉ ረዳ)
የመሳሪያ ሽያጭ እና ሽግግርም በሚመለከት ለምሳሌ የ “ህግደፍ” በመካካለኛ ምስራቅ አገሮች ጉዳይ የኤርትራ ተጠሪ በሆነዉ መሐመድ ቓስም ሐመድ የተከናወነዉ የመሳሪያ ግዢ በ14/7/2007 ከኢራን ወደ ኤርትራ በምጽዋ የ አይሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ የተራገፈዉ 125 Shoulder –surface-to air missiles 80፡ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ከሌሊቱ በ2፡45 ሲራገፍ እራሱ በአካል ተገኝቶ ተረክቦታል። በእርግጥ ሰፊዉ የመሳሪያ ሽያጭ ሽግግር ተከናወኑት ቀደም ብሎ በ2006 ሲሆን ፕረዚዳንት አሳያስ አፈወርቅ የ አስመራ ጽ/ቤቱን ዘግቶ ለዚህ ለማሳሪያ ሽግግር ተግባር በቅርብ እንዲቆጣጠረዉ ሲባል ጽ/ቤቱ ከአስመራ ወደ ምጽዋ አዙሮ ነበር።ለዚህ ተግባር በቅርቡ ተከታትሎ እንዲአስፈጽም የመደበዉ የብርጋዴር ጀኔራልነት ማዕረግ ያለዉ ጠዓመ (መቐለ) የተባለዉ ከኢሳያስ አፈወርቅ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለዉ ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያምን ለመግደል ሁለት ራሱ ሆኖ ዝምባዉዌ ድረስ በመሄድ የከሸፈ የመግደል ሙከራ በማድርግ በ1995 በዝምባቡዌ መንግሥት ፍርድ ቤት ሁለት ዓመት ተፈርዶበት እስራቱን ፈጽሞ ወደ ኤርትራ የተመለሰዉ ነዉ። (Evgueny Zakharove, the owner of Aero lift, an airline with a fleet of ageing Antonov and LLyushin transport aircraft, based in Johannesburg registered in the British Virgin Islands), ባለንብረት ከሆነዉ ግለሰብ እና ብርጋዴር ጀኔራል ጣዓመ፣ ምፅዋ ላይ በ08/2006 ከ19 እስከ 21 ድረስ ያሉት ቀናቶች የቆየ የጋራ ስብሰባ አድርገዉ ነበር።ቅጽል ስሙ “መቐለ” (መቐለ የሚለዉ በአማርኛ ተነጋሪዎች “መቀሌ” በመባል የሚነበበዉ ቃል ነዉ) በመባል የሚታወቀው ብርጋዴር ጠዓመ ጎይተኦም ከኤርትራ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ዉጭ ሌላ ተራ ፓስፖርቶች ማለትም የኢትዮጵያ ፓስፖርት፤ የስዑዲ የኩዌት እና የመሳሰሉት ፓስፖርቶች በመያዝ በአፍሪካ ቀንድ ለሚንቀሳቀሱ ለሶማሌ የእስላማዊ ፍረድ-ቤት ህብረት ታጣቂዎች እና ለታሚል ታጋዮችን የመሳሪያ ሽያጭ እና ማስተላለፍ ስራ ለሚሰሩ ቡድኖች ለመምራት እና ለማስተባበር በኢሳያስ አፈወርቅ የተመደበ ሰዉ ነዉ።
ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ እና በኤቭጉኒይ ዛካሮቭ ፌርማ እና ፈቃድ ኣማካኝነት በብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ አስተባባሪነት 76 ጊዜ በረራ በማካሄድ ከሶቭየት ሕብረት ከዩክረይን ከኢራን ከ ሊቢያ የመሳሪያ የግዢ ጭነት ሲያመላልስ ለዛካሮቭ በተለይም በ12/07/2008 ከቁጥር የበረራ መዝገብ 76496 የ$1.5 ሚሊዮን ዶላር (770.000 ሺሕ ፓዉንድ) በተናጠል በኮንትሮባንድ ዋጋ ሲከፈለዉ፡ 76ቱ ጊዜ በዉጭ ምንዛሬ በማዕከላዊ 114 ሚሊዮን ዶላር (58 ሚሊዮን ፓዉንድ) ተከፍሎታል። ይህ የመሳሪአዎቹን ዋጋ አይጨምርም።ለበረራ ብቻ የተከፈለ ነዉ። በመሳሪያ ሽግግር እና ግዥ ስራ ቀንደኛ ተዋናይ ሌላዉ ክፍል “ቀይ ባሕር የንግድ ተቋም” ተብሎ የሚጠራ ስራስኪያጁ ዛሬ በእስር የሚገኝ “ተክኤ ኪዳኔ” ነበር። በጁላይ 13/2007 ጽ/ቤቱ አስመራ የሆነዉ ኤሪክ ኢንተርፕራይዝ (Moscow and Asmara, the capital of Eritrea, between Aerolift and Eriko Enterprise of Asmara) በመስኮ እና በአስመራ ከተሞች የመሳሪያ ግዥ ስምምነት ተፈራርሟል።ፌርማዉን ከፈረሙት ተፈራራሚዎች “ታደሰ ክታሙ” የተባለ በኤርትራ በኩል ከሞስኮ ደግሞ “ሺቶላይ አንደረንስኪ” ናቸዉ። ሺቶላይ አንደረንስኪ በደርግ ጊዜ ወደ ኢትየጵያ ሲጫን የነበረዉን ማሳሪያ እና ሎጂስቲክ ሲቆጣጠር እና በሃላፊነት ሲያስተዳድር የነበረ የኬጆቢ አባል ነዉ። ይህ የኮንትሮባንድ መሳሪያ ሽግግር ሲደረግ እንዳሁኑ ዝርዝር ኖሮት ግልጽ ባያደርገዉም ዘሳንደይ ታይምስ የተባለ ጋዜጣ በጁላይ ጠቅሶት እንደነበር ይታወሳል።
“…ዛካሮቭ የሚያበራዉ የጭነት አይሮፕላን ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸዉን የብሪታንያ የአሜሪካ እና የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸዉ አክራሪ እስላሞች ወደ ኤርትራ እንደልባቸዉ እንዲገቡ እና እንዲወጡ ረድቷል። ዛሬም ቀጥሏል። በረራዉ ከተለያዩ አገሮች ማለትም ማሳሪያ በመሸጥ የታወቁት አገሮች ከዩከረይን ከካዛኪስታን ከኢራን ሞስኮ ቻይና ወደ ሊቢያ እንዲጫን ከተደረገ በሗላ ለማየት እንዲያስችላቸዉ ዓይናቸዉ ብቻ ክፍት በማድረግ ፊታቸዉን በጥምጣም ጭምብል በመሸፈን ማንነታቸዉ የማይታወቅ ሰዎች ከሊቢያ አስከ ኤርትራ ድረስ ታጅቦ መሳሪያዉ እንዲራገፍ ተደርግዋል።
ምፅዋ አይሮፕላን ማረፊያ ከወረደ በሗላ በ ኢሳያስ አፈወርቂ እና በባሕር ሃይሉ አዛዥ ፍጹም ገ/ሕይወት በምስጢር ተጎብኝቶ ርክክቡ ከተከናዋነ በሗላ መንግስት አልባ ወደ ሆነችዉ ወደ ሶማልያ እና ወደ ታሚል ታይገርስ ወደ ስሪላንካ ተሸጋግሯል። ከስር ላይ ሆኖ የመሳሪያዉ ቅብብሎሽና የባሕር መርከቦችን የጠለፋ ዉንብድና የሚያጠናክረዉ፤ የሶማሊዉ “ዳሂር አወስ” ሲሆን የባህሩን ዉንብድና እንደ ዋነኛ የገቢ ምንጭ እና ለዉጭ አገር ምንዛሪ የሚጠቀምበትና ዉንብድናዉን የሚመራዉ ግን የኤርትራዉ ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ነዉ። ወደ ሶማሊ ሲጫን የነበረዉ ማሳሪያ የሶማሌ ግምባሮች እንደተከፋፈሉ. ጂቡቲ ወስጥ የሶማሊን ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያ በወቅቱ ከሶማሌዉ የእስላሞቹ ሕብረት ጊዜአዊ መንግስት ጋር ከነበረዉ ሸኽ ሸሪፍ ጋር ስትነጋገር መሳሪያ ከኤርትራ እደሚያገኙ በDecemebre 2007 ፍንጭ አግኝታ ነበር።የተባበሩት መንግስታት ተከታትሎ መረጃዉን ለማግኘት ዕቅድ እና ፍላጎት ያደረበት መሆኑን ያወቀዉ ኢሳያስ አፈወርቅ አንዳች ዘርዝር ሚስጢር ቢወጣ በሸኽ ሸሪፍ ላይ የግድያ እርምጃ እንደሚያስወስድበት በተዘዋዋሪ ለሸኽ ሸሪፍ እንዲደርሰዉ ስለተደረገ የሚያዉቀዉ ዝርዝር ምሰጢር ከማዝረክረክ አግዶታል። አከታትሎም፤ የአሜሪካ ቴክሳስ ክፈለሃገር የኤፍ ቢ አይ ምርመራ ክፍል ሃላፊ እንደዘገበዉም አንድ በቴክሳስ ከተማ ፈርድ ቤት በሽብር ተግባር በመሳተፍ በጥፋተኛነት ተከስሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ የተፈረደበት የአልቃይዳ አባል በጊዜ የሚፈነዱ ቦምቦችን አያያዝ እና አጠቃቀም የስልጠና ተግባር ሶማሌ ድረስ ሄዶ የሰለጠነ መሆኑን ሲያምን አብረዉት ከኤርትራ መንግስት የተላኩ የቦምብ ጠመዳ ምህንድስና ባለሞያ አሰልጣኞች ትምርቱን ለእሱ እና ለመሰል ሰልጣኞች ያሰለጥኑዋቸዉ እንደነበሩ አምኗል።
ይህንን የሚያረጋግጥ ለልዩ ልዩ ተልዕኮ ኤርትራ ወደ ሶማሌ የተላኩ ሰዎች ኬኒያ ከእስላማዊ ሃይል ሽብርተኞች ጋር በተግባር ተስማርተዉ ከሶማሌ የኢትዮጵያ ጦር ሸሽተዉ ወደ ኬኒያ ድንበር ሲገቡ የያዝኳቸዉ ናቸዉ ለኢትዮጵያ አስተላልፋ ከሰጠቻቸዉ መካከል የሃምሳ እልቅና ማዕረግ የነበረዉ የወታደራዊ መሃንዲስ ባለ ሙያ እና አብረዉትም የተያዙት ጋዜጠኞች መካከል ተስፋልደት ኪዳነ ፤ተስፋዝጊ እና ሳልሕ እድሪስ የማሳሰሉት መያዛቸዉን ኢሳያስ አፈወርቅ ከቲቪ ኤሬ ጋር ባደረገዉ ቃለ መጠይቅ በሽርደዳ መልክም ቢሆን በተዘዋዋሪ ሳይወድ መያዛቸዉን መልስ በመስጠት አምኗል።…ይቀጥላል

Monday, December 8, 2008

ጀንራል ጠዓመ ጎይተኦም ማነዉ?

ጀንራል ጠዓመ ጎይተኦም ማነዉ? ጌታቸዉ ረዳ አስመሮም ከተባሉ አንድ ኤሪትራዊ በhttp://asena-online.com በተባለዉ የህዋ ሰሌዳ በለጠፈዉ ሰነድ መሰረት የትግርኛዉ ቋንቋ ወደ አማርኛ በመመለስ ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ “መቐለ” በሚል ቅጽል ስም የሚጠራ የሻዕቢያ ሹም ማን መሆኑን እና በምን ተግባራት ተሰማርቶ ምን እንደፈጸመ እና እየፈጸመ እንዳለ የሚያሳይ ሰነድ ይቀርባል። ተጠቃሹ ካሁን በፊት በኢሳያስ የባሕር ዉምብድና እና የመሳሰሉት ሕገ ወጥ የመሳሪያ ሽግግር ተግባሮች ንክኪ ተሰማርቶ እንደነበር ቀደም ብሎ ከወጡት የምስጢር ሰነዶች እንዳስነበብኳችሁ ይታወሳል። በዛ መሰረት ሰዉየዉን በቅርብ የሚያዉቁት የሰዉየዉን ማንነት በመጠኑ የዘረዘሩትን ታሪክ እንሆ። ለአቅራቢዉ ለአቶ አስመሮም በአንባቢዎች ስም እና በ“ኢትዮጵያን ሰማይ” ስም በቅድሚያ እያመሰገንኩ አሁን በቀጥታ ወደ ትርጉሙ እንሆ፦
“ጠዓመ ጎይተኦም (መቐለ) (ቅጽል ስሙ መቐለ ወደ ህዝባዊ ግምባር በ1977 ተቀላቅሎ በ80ዎቹ ከተራ ተዋጊነት ወደ “ክፍል 72” ወደ ሚባለዉ ማለትም ወደ ስለያ እና ጸጥታ ክፍል ተመድቦ አስከ ነጻነት ድረስ በዚሁ ክፍል ሲሰራ ቆይቷል። ከነጻነት በሗላ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄድ ተመደቦ ማዕከሉን አዲስ አበባ በማድረግ የኤርትራ የሻዕቢያ ተቃዋሚ ሃይሎችን እያፈነ እና እየገደለ የቆየ ነዉ።የመግደል እና የማፈን ተልዕኮዉ የሚተላለፈዉ ትዛዝ በቀጥታ ከኢሳያስ አፈወርቅ ነዉ። የሚታፈኑ እና የሚገደሉ ግለሰዎች ስም ዝርዝር ተሰጥቶት ከነጻነት በሗላ አዲስ አበባ ሄዶ የወንጀሉን ተግባር ፈጽሞ የግድያዉ እና የአፈናዉ ሰላባዎቹ ከሆኑት መሃል ጥቂቱን ብንጠቅስ፦
· ታዋቂዉ አቶ ተስፋሚካል ጆርጅዮ
· በደረግ ጊዜ የደርግ ደጋፊዎች እና በኤርትራ የራስ ገዝ አስተዳደር አካባቢዎችና የመሳሰሉት ለደርግ በመቆም ፓሊሲዉን ተግባራዊ ለማድረግ ሲሳተፉ የነበሩ ግለሰዎች፦
· ትግሉን ጥሎ የወጣ ይሕደጎ ወልደጊዮርጊስ የተባለ የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት የዓንደብርሃን ወልደጊዮርጊስ ወንድም
· ከተለያዩ የኤርትራ ነፃነት ግምባር ከድተዉ ወደ ደርግ የገቡ እና በርከታ ሌሎች ሰዎች ሰለባ ሆነዋል።
አያሌ ሰዎች በኢሳያስ ትዕዛዝ በጠዓመ ጎይተኦም ፈጻሚነት ከተገደሉ በሗላ በ90ዎቹ አካባቢ በኢሳያስ አፈወርቅ ምስጢራዊ ሌላ ከፍተኛ የግድያ ስራ ለመፈጸም ወደ ዚምባቡዌ ሐራሪ ከተማ በመሄድ በኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ላይ የጥይት ተኩስ ከፍቶ የከሸፈ የግድያ ሙከራ ሲያደርግ እጅ ከፍንጅ በመያዙ በሃራሪ ፖሊስ ተይዘዉ ፍረድ ቤት ቀርቦ አሱ እና ሌላ ተባባሪዉ ግለሰብ ሁለት ዓመት ታስረዉ ተለቅቀዉ ወደ አስመራ ሄደዉ በቀጥታ ኢሳያስ ጋር በመቅረብ ልዩ ሙገሳ ተደርጎለት ከጥቂት ጊዜ ራሱን ካደላደለ በሓላ ተመሳሳይ ለሌላ ዝግጅቶች ከኢሳያስ አፈወረቅ ትዕዛዝ እየተቀበለ ተመሳሳይ ድረጊቶችን ለመፈጸም የተመደበ ሰዉ ነዉ።
ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ ከኢሳአስ አፈወረቅ ሌላ ማንም አያዘዉም።ከሌሎች ባለ ስልጠኖችም ጋር የ አዛዥ ታዛዥ ግንኙነት የለዉም። ከዝምባቡዌ መልስ በሗላ -ምድብ ስራዉ አሲያስ እንዲፈጸሙ የሚፈልጋቸዉን ነገሮችን በቅጽበት ተግባራዊ ማድረግ ብቻ ነዉ።ኢሳያስ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ ወይንም እንዲፈጸሙ የሚፈልጋቸዉ ድርጊቶች ካሉ ተልዕኮዉ የሚሰጠዉ ለጠዓመ ብቻ ነዉ።
በአዉሮፓ፤በ አሜሪካ እና በመካከለኛዉ ምስራቅ አገሮች ያሉት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች እየሄደ የሚያደራጃቸዉ እና የሚገናኛቸዉ ጠዓመ ጎይተኦም ነዉ።ኦሮሞ ነፃነትን (OLF) አደራጅቶ ወደ ኢትዮጵያ በቀጥታ ሰርገዉ በመግባት ወታደራዊ ጥቃቶችን እንዲፈጽሙ የሚያቀናብረዉ እሱ ነዉ። ለተልዕኮዉ ማስፈጸሚያም ሆነ ሌላ አስፈላጊ በጀት የሚመድበላቸዉ እና የሚፈቅድላቸዉ የበላይ ባለ ስልጣን እሱ ነዉ።
አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ በአንዳንድ ቦታዎች በድብቅ ተጠምደዉ የሚፈነዱት ቦምቦች ( ወያኔ ለ ፕሮፖጋነዳ ጠቀሜታ ከሚለፍፈዉ ዉጭ ወደ ጎን ትተን) ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ ጎይተኦም በሚሰጠዉ መመሪያ የሚፈጸሙ ናቸዉ። ከዚህ ሌላ ሶማሌዎችን ከዘመነ ዓይዲድ ጀምሮ አስካሁን ድረስ ያሉትን የተለያዩ የሶማሌ ቡድኖችን እንቅስቃሴ እየተከታተለ የሚያስተባብራቸዉ እና ከኢሳያስ የተሰጠዉ መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርገዉ ጠዓመ ነዉ።
የኢትዮጵያ ጦር ሶማሌ ድረስ ገብቶ የእስላማዊዉን ሃይል ሲመታ ከሶማሌ ሸሽተዉ ወደ ኬኒያ ሲገቡ የተያዙ ኤርተረዉያኖች ለማስፈታት ኬኒያ ድረስ ተጉዞ ጉቦ ከፍሎ በማስፈታት ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ ያደረገም አሱ ነዉ።
ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ በዓይኑ ያላየ አያምንም። የሚያንቀሳቅሰዉ የዉጭ ምንዛሪ ገንዘብ መጠኑ በጣም ብዙ ነዉ፡ የፈለገዉ የገንዘብ መጠን ቢያንቀሳቅስም ኢሳያስ ሙሉ መብት ስለሰጠዉ የተመደበ የበጀት መጠን የለዉም።የፈለገዉ የገንዘብ መጠን ወደ ፈለገዉ ነገር ቢያዉለዉ ጠያቂ የለዉም።ነገ ጎህ ሲቀድ ፈትህ ሲሰፍን ገሃዱ ሲወጣ በንቅዘት ከተበላሹት የኤርትራ መንግስት በላስልጣነት ጠዓምን የሚያክል ብልሹ ባለስልጣን እንደማይኖር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

Wednesday, December 3, 2008

ከእሳት ዘሪዎች እሸት አይጠበቅም

ከእሳት ዘሪዎች እሸት አይጠበቅም ጌታቸዉ ረዳ ስለ ጋህዲ ደራሲ ትንሽ ልበል።የጋህዲ ደራሲ አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ “ጋህዲ” የሚል መጽሐፍ በመጻፋቸዉ ሊመሰገኑ ይገባል። እኔ መጽሐፉን አላነበብኩትም።የምኖርበት ከተማ እና ከባቢዉ ያሉት የኢትዮጵያዉያን ሱቆች እንጀራ እና የሻዕብያ ሙዚቃ የሲዲ መሸጫ እንጂ አገራችንን የሚመለከት መጻሕፍት ወይንም ጋዜጦች ለአመሉም ቢሆን አንዴም እንኳ አስመጥተዉ ሊያስነብቡን አልታደልንም።በዚህ አልታልደንም እና መጽሐፉን ለማንበብ ዕድል አላገኘሁም። መጽሐፉ አንበብኩ ኣላነበብኩ ለኔ አዲስ መሰረታዊ መረጃ የሚሰጠኝ ኣይመስለኝም። ምክንያቱም ወያኔ የሻዕቢያ ሎሌ መኖሩ እና ዛሬም በግልጽ እነ ስብሐት የሚፎክሩበት እና የሚኮሩበት ስለሆነ ፤አዲስ ኣይሆንም። ቢሆንም፤ መጽሐፉን የት ማግኘት እንደሚቻል ወኪሎቹ ለሕዝብ ብያስታዉቁ ለማንበብ ዕዱልን ባገኘን።ጻሓፊዉን ማናናቅ ተደርጎ ባይወሰድብኝ አስገደ ስለ ወያኔ ሻዕብያ ሎሌነት መግለጹ ቢያስመሰግነዉም፤ በወያኔ መሰረታዊ ወታደራዊ እና በስላላ እንዲሁም በወያኔ የጉድጓድ እስርቤቶች(06) በመሳሰሉት ሰብኣዊ ጥሰት ማለትም ድርጅቱ የወሰዳቸዉ የአፈና፤ የማሰቃያ እና የርሸና ወንጀሎች የመሳሰሉት አገር አቀፍ እና አህጉራዊ የክህደት ዉል ምስጢራዊ ሰነዶችን ይፋ የሚያደርግ የህወሓት “ታጋይ-ነበር” “በጥልቀት እና በስፋት” አስካሁን ስጠብቅ ይፋ ያደረገ ሰዉ ስለሌለ በዚህ በጣም ቅር ተሰኝቻለሁ። የምጓጓዉ በዛ ረገድ ነበር ለማለት ነዉ።ቢሆንም አቶ አስገደን የማመሰግነዉ እና ከበሬታ የምሰጠዉ በድፍረት ጅቦቹ በሚኖሩበት ከተማ እየኖረ ጉዳቸዉን ማጋለጡ እጅግ አከብረዋለሁ።ትግል ዉስጥ ነበርን ከሚሉን ምንም ካለስተማሩን አብዛኛዎቹ የህወሓት ታጋዮች የሚያዉቁትን ለማስተማር የጣሩት እኔ የማመስግናቸዉ ሌላዉ ደራሲ “ታጋይ ገሠሠ እንግዳ” የተባሉ “ታሪክ አጉዳፊዉ የ አልባኒያዉ ደብተራ” የሚል መጽሐፍ በመድረስ ወያኔን ያጋለጡ እና ሌላዉ አድናቆቴ ሁሌም የምቸራቸዉ “የታላቁ ሴራ” ደራሲያን እነ አቶ ገብረመድህን አርአያ ፤ካሕሳይ በርሄ፤ ተስፋይ አጽብሃ እና ምንም እንኳ የሗላ ሗላ መጥፎ አወዳደቅ በመዉደቅ ታሪካቸዉን ራሳቸዉ ያጎደፉትም ቢሆን አቶ አብርሃ ያየህንም በዛዉ በክፉ ቀን የወያኔ ጉድ ማጋለጣቸዉን ሳላመሰግናቸዉ አላልፍም። ሌላዉ “ከዚህ ድረስ ያደረሰ መንገድ” የተባለዉ ሰነድ የጻፉትን አቶ ብስራት አማረንም ሳለመሰግን አላልፍም። በተቀረ ከወያኔ ነበር አባላት የተማርነዉ ብዙም ሰነድ የለም። ለምን? ብየ ይህ የዘወትር ጥያቄየን አቅርቤ ልለፍ። የዛሬ አመጣጤ አቶ አስገደ ገ/ስላሴ እና ቃለ መጠይቁ ያዘጋጁት አቶ አበበ በለዉንም ጭምር ለመተቸት ነዉ። ለመተቸት ስነሳ፤ ብዙ የትግራይ ወንድሞቼ እንደልማዳቸዉ በእኔ ላይ ያላቸዉ ዉዥምብራም አመለካከት ሲበራታባቸዉም ዘረኝነታቸዉን በእኔዉ ላይ ከማዝነብ ጋር ትችቴን እንደሚያነብቡት የምጠብቀዉ ነዉ። የወያኔ መሪዎች እና የትግራይ ተወላጆች አትኩሮታቸዉ በአካባቢያቸዉ ብቻ በማድረግ ትግራይን የትምርት፤የጤና፤የመገናኛ፤የእርሻ፤የኩባንያዎች እና ኢንዱስትሪዎች መዋዕለ ንዋይ ከሌላዉ አካባቢ በበለጠ እንዲፈስበት የተቻላቸዉን ሁሉ በማድረግ ለአካባቢአቸዉ ብቻ በመቆርቆር ወገንተንኝነታቸዉ እንዳሳዩ አሌ አይባልም። ለዚህም የትግራይ ሕዝብ ከአስመራ እና ከባሕር ዳር ከደብረብርሃን ...ለወራት እና ዓመታት እየጠበቀ ሲገበያቸዉ የነበሩትን የዕቃዎችና ልዩ ልዩ ምርቶች፤- ካለ ምንም የዓመት አና የወራት፤የሳምንታት እና የቀናት ጉዞ ሳያደርጉ ወይንም ጠብቅ ሳይባል ከደጃፉ በራቸዉ ካለዉ ሱቅ እና ኩባኒያ ላይ ወይንም ከቅርብ መንገዶች ርቀት እና የሰዓታት ጉዞ በማድረግ በቀላሉ በመሸመት ዕደሉ ስላገኘ፤ ከሌሎቹ ይልቅ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል። ይሄ አቶ አስገደ ገ/ብረስላሴም አቶ ገብሩም ባጠቃላይ ሁሉም ልበል እና የትግራይ ሕዝብ ምንም የተደረገለት ነገር የለም። ብለዋል። ቢህ ብዙ ጊዜ ስለሄድንበት ብዙም የምለዉ ስለሌለ፡ ወደ ዋናዉ ትችቴ ልግባ። አስገደን ስተች “ኢሕአፓዉ ጌታቸዉ ረዳ” ኢሕአፓ ስለሆነ አስገደን መተች ጀመረ ፡ በማለት እንደ ዕንቁራሪት አንዴ በሻዕቢያነት አንዴ በኢሕአፓነት ወዘተ.. ሁሌም ከሚከሱኝ ዕንቁራሪቶች የምጠብቀዉ ስለሆነ። ሁሉንም ወገን በፈትሕ ዓይን ስለምመለከት የበደለ በድሏ የካደ ከድቷል መልካም ስራ የሰራዉ መልካም ስራ ሰርቷል በማለት ለዓመታት ግራ ቀኙን ስሰደብ አስካ ሁን መቆቴ ለአገሬ ያለኝን ፍቅር ለምቾት ኑሮ ሳልደለል ታግያለሁ። ተችት አቅርቤ አለሁ። በዚህ ልዩ ኩራት ይሰማኛል። ታሪክ አንድ ቀን ሁላችንን ይመዝነናል። ስለተሰደብኩ ወይንም ዛቻ ስለተወረወረብኝ ከመተቸት አልገታኝም። አሁንም ስለ ፍትሕ ትችቴ ይቀጥላል።
እነሆ፦ ሰሞኑን አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ አዲስ ድምጽ ከተባለዉ ራዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። አስገደ ወደ ህወሓት ሲቀላቀል ከመስራቾቹ አንዱ ነበር። ለትግሉ መነሻ ምክንያት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት እንደነበር ገልጿል። አሁን ግን ነገሩ ተበላሽቶ የአንድ ፓረቲ/ድርጅት የበላይነት መንገሱ “ከመነሻዉ” “ፈር” ለቋል ሲል ህወሐት አምባገነን ፓረቲ መሆኑን ገና ህወሓት የመንግስት ስልጣን ሲይዝ የወያኔ ምንነት የተገለጸለት እና ሜዳ ላይ 17 አመታት የሕዝቡን ልሳን፤ የታጋዮቹን ሕይወትና መብት በብረት ቡጢ በተ-ተበተበ ፋሽታዊ እና ማርክሳዊ የስለላ አወቃቀር ይዞ የተራመደበትን ጎዳና ኢዲሞክረሳያዊ ብቻ ሳይሆን “ፋሺስታዊ” በሕሪ እንደነበረዉ እያወቀ መስመሩ መሳት የጀመረዉ ስልጣን ላይ ሲመጣ ስልጣኑን ለሕዝብ እናስረክብ ስንለዉ “አሻፈረኝ” ስላለ ከድርጅቱ ተሰናብቼ አለሁ ብሏል። የህወሓት አነሳሱ እና አስከ ዚህ ድረስ የተጓዘበት በሕሪዉ ከልቡ እያወቀዉ፡ የወያኔን አምባገነንነት ማወቅ የጀመረዉ በ1983 እንደሆነ አስመስሎ መናገሩ ግራ ገብቶኛል? ሁሌም ግራ የሚገባኝ ነገር፤ አብዛኛዎቼ ወያኔ ዉስጥ የነበሩ ታጋዮች ሊነግሩን የሚንደረደሩት “የወያኔ” አምባገነንነት ወይንም “ካዳተኛ” ባሕሪዉ የጀመረዉ ገና በ1983 መሆኑ እና የትችታቸዉ መነሻ በአብዛኛዉ ከዚህ ከ1983 እንደሆነ ነዉ የምናነባቸዉ። ወይንም ከባድሜ ጦርነት ወዲህ። ለምን? አስገደ በቃለ መጠይቁ እንደሚለን “ወደ የቻይና ዓይነት ፈላጭ ቆራጭነት ባሕሪ እየተጓዘ ነዉ” ሲለን በእዉነቱ አስገደ የወያኔ ድርጅት አሰራር እና ባሕሪ ወደ ማኦዊ ወይንም አልባንያዊ ኮሚኒስታዊ ባሕሪ የተሸጋገረዉ /የጀመረዉ ገና ወደ መንግሥትነት ሲዞር ነዉ? አቶ አስገደ “ራሱ ከጽንሱ ጀምሮ የነበረ ያሳደገዉ የገነባዉ የታገለለት የደማለት ድርጅት ትውዉቁ በ1983 ነዉ? አስገደ ከመሰረተዉ ድርጅት የተለየበት ምክንያት ሲገልጽ “ደርግ በወታደራዊ ጉልበት ደምስሰነዋል፡ ስለዚህ ስልጣኑን ለሕዝቡ እናስረክብ ብለን ሓሳብ ስላቀረብን በዚህ ብዙ ሰዉ እንግልት ስለደረሰበት እኔም ከድርጅቱ ወጥቻለሁ ብሎናል። መልካም አቋም!ነገር ግን “ጉና ካብ ዕርዲ መንጥል! ናብ ዕርዲ መትከል” በሚል ሐምሌ 1989 “ወይን” የትግርኛ የወያኔ ልሳን ጋዜጣ ባወጣዉ የትግል ዓምዱ ላይ “ሳሞራ የኑስ” አንዳስቀቀመጠዉ “ታጋዩ ብቻ ሳይሆን ቁጥሩ አነስተኛ የማይባል በርካታ የትግራይ ሕዝብ ትግላችን ፈጽመናል፤ ይበቃናል ከዚህ ወዲያ አንሄድም፤የተቀረዉ ህዝብ የየራሱን አምባ ነጻ ያዉጣ በማለት የተከራከሩ እና ብረታቸዉን እየጣሉ ወደ ከተማ የተመለሱ እና ወደ 20ሺሕ የሚጠጋ ታጋይ “እምቢኝ” አንሄድም “ትግራይ ነጻ ወጥታለች፤የቤት ስራችን ሰርተናል ከዚህ ወዲያ የተቀረ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ ታግሎ ራሱን ነጻ ያዉጣ በማለት ለወራት የቆየ ክርክር እንደተደረገ እና ያዉም ለአንድ ወር ሙሉ ጉና ላይ በደርግ እየተደበደበ ወደ ፊት መገስገስና መላወስ ካቃተዉ ዋናዉ ምክንያት ታጋዩ ምሽጉን እየጣለ ከዚህ ወዲሕ የትግራይ ቦታ አይደለም በማለት ጥለዉት ወደ’የ ቄያቸዉ በመፍለሳቸዉ እንደ ነበር ሰነዱ እና የሳሞራ የኑስ ቃለ-መጠይቅ ያስረዳል።አቶ አስገደ ይሄንኑ ያቃል። ታዲያ የወያኔ እና የታጋዮቹ ዲሞክረሲ ፍለጋ እና አገር ዋዳድ ኢትዮጵያዊነት ፍለጋዉ ሲመረመር በጥያቄ እናስቀመጠዋለን። የእምቢታዉ ክርክር ሁኔታ ለ6 ወር ያህል እንደተካሄደም አንዳነድ ሰነዶች አንብበናል። የክልልተኝነቱ በሽታ በመሪዎቹ ብቻ ሳይሆን የተንጸባረቀዉ ከታጋዩ እና ቁጥሩ አነስተኛ ከማይባል የትግራይ ሕዝብ ጭምር “ከዚህ ወዲያ አንሄድም” እንዳለ ሳሞራ ያስረዳበትና ብዙ የትግራይ ሕዘብም ሆነ ታጋዩም የተሳሳተ ኢትዮጵያዊ አመለካከት እንደነበረዉ እያወቀ ታጋዩ ጠባብ አልነበረም፤ዲሞክራሲ ፍለጋ የታገለ ነበር፤ በማለት ለሕዝቡ እና ለታጋዮቹ የተሰጠዉ ጎሰኛ እና በትግራይ ጂኦግራፊያዊ ክልል/ማፕ ብቻ እንዲመለከት የተሰጠዉ ጠባብ የትምርት “ጠባሳ” ከፍተኛ ጉዳት አንደነበረዉ እየታወቀ ከአስገደ ገ/ስላሴ ቃለ መጠይቅ አንደበት እተደመጠዉ ግን ታጋዩ ክልልተኛ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ስሜት ኖሮት ስልጣን ለሕዝብ ይተላለፍ ብሎ የደመቀ አቋም አንደነበረዉ ነዉ።ነገሩ ግን አስካሁን ታጋዮቹ በስፋት ሊገልጹልን ያልፈለጉት “መጻጉእ” ግን ተሸፋፍኖ እየታለፈ ነዉ። ለምን? በመሪዎቹ ብቻ ሳይሆን በታጋዩ እና በህዝቡ ላይ የነበረ የተሳሳተ ሀገራዊ አመለካከት በሚመለከት ቢገልጽልን በጣም አመሰግነዉ ነበር። ሕዝቡ እና ታጋዩ በተለይም በ አማራዉ ላይ የነበረዉ አመለካከት እና የተሰጠዉ ቅስቀሳን በሚመለከት የሚናቅ አጀንዳ አልነበረም። ሆኖም ጠያቂዉ ለእንደዚህ ዓይነት ጥያቄ የተዘጋጀ አልነበረም እና አልጠየቀዉም። አስኪ አቶ አበበ በለዉ ከተናገረዉ የቃለ መጠይቁ መግቢያ ልጀምር እና ከዚያ አቶ አስገደ ስለ ኢህአፓ ያለዉን እንመለከታለን። “ሕወሐት ቀደም ብሎ ለ ኢትዮጵያ የነበረዉ አስተሳሰብ አሁን እንዴት እንደተቀየረ ብዙዎች የህወሓት ኣባላት እንዴት ጥለዉት እንደወጡ ተንትኖ የሚያሳይ ታሪካዊ መጽሐፍ በዚህ ዙሪያ ላይ ረዘም ላለ ሰዓት ይዧቸዉ እቆያለሁ…እንድትከታተሉ እጋብዛሉ።” (አበበ በለዉ- አዲስ ድምጽ)። “ህወሓት ቀደም ብሎ ለኢትዮጵያ ከነበረዉ (ቀ ና) አስተሳሰብ (ወጥቶ) አሁን እንዴት እንደተቀየረ” ለመጠየቅ ይህ የአቶ አበበ በለዉ አረፍተነገር እዉን የጋህዲ መጽሐፍ ደራሲ አቶ አስገደ ከመጽሐፉ ዉስጥ በመጽሐፉ የዘገበ አባበል ከሆነ ሊያከራክረን ነዉ። ላብራራ። ወያነ ትግራይ ስለ ኢትዮጰያ በጎ ነገር አስተሳሰቡ ድሮም ሆነ አሁን የለወጠዉ ነገር ደግ ነገር አልነበረዉም። በ አስተሳሰብ የምንለያየዉ ነጥብ እዚህ ላይ ነዉ። በትገራይ ሜዳዎች፤ተራሮች እና አምባዎች ብቸኛ የሚያገሳ አምበሳ ሆኖ ስለ ኢትዮጵያ “ቀና “ አስተሳሰብ የነበራቸዉን የኢትዮጵያ ስም የያዙ እነ ኢሕአፓ እና ኢድሕ የመሳሰሉት ኢትዮጵያዊ ድረጅቶች “ዓባይ ኢትዮጵያ” በማለት ቅጽል ስም በመስጠት ከትግራይ መሬት ጠራርጎ እንዲወጡ የጀመረዉን ኢትዮጵያዊነት የጥላቻዉ አስተሳሰብ ከዚህ የጀመረ መሆኑን አንድ በሉ። አነሱን በማባረር እና ቅጽል ስም በመስጠት ኢትዮ ያዊነቱን መፋቅ የጀመረዉን ያስተሳሰብ በሽታዉ፦ “ትግራይ የ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች” ስለዚህም “ከሽዋዉያን አምሓሩ” ነጻ በማዉጣት “የትግራይ ሪፑብሊክን” አንመሰርታለን፡ በማለት ማኒፌስቶ አስጽፎ፤ ጭራሽኑ አስተሳሰቡ ጸረ -ዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን ጸረ-ኢትዮጵያዊነቱ አስተሳሰቡ ይፋ አደረገበት ምዕራፍ “ሁለት በሉልኝ!”። ማኒፌስቶዉን ጽፈዉታል የተባሉት ከ5 ቱ 3ቱ በስልጣን ላይ ሆነዉ ኢትዮጵያን እየገዙ ናቸዉ። “ስልጣኑን የሚቀማን ሃይል ከመጣ- “ወደ እየ መንደራችን እንበታተናለን”” በማለት ስብሓት ነጋ ያስጠነቀቀንን ልብ በሉ። ይህ አስተሳሰብ አዲስ አበባ የተፈጠረ አስተሳሰብ (የተለወጠ አስተሳስብ) ሳይሆን አስተሳሰቡ ደደቢት ሜዳ ትግራይ ዉስጥ እንደነበረ ሁላችንም ማመን ይኖርብናል። “ወያኔ ለኢትዮጵያ የነበረዉ አስተሳሰብ” የተለወጠ ነገር ወይም አዲስ ነገር እንደሌለዉ አጠር አድርጌ አቶ አስገደን እና ሌሎቹን ላስታዉሳቸዉ እፈልጋለሁ። የትግራይ ሕዝብ እና ነገስታት መኳንንት እና ቀሳዉስት አርበኞች እና የትግራይ ገበሬዎች የሞቱላትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓለማ የባሕሉ የመንፈሳዊ ቅርሱ፤ መመክያዉ ተስፋዉ እና የማንነቱ መታወቂያዉ የነበረችዉን ብሔራዊ ባንዴራችን በማዉረድ ሻዕቢያ ሰፍቶ የሰጠዉን ባለ ሁለት ቀለም ቀይ ቢጫ የኮሚኒስት ሞዳ ጨርቅ ባንዴራ አስሰፍቶ በእየ ስብሰባዉ እና በጠመንጃዉ አፈሙዝ ሸምበቆዉ፤ በሙዚቃ መሳሪያዎች እና በከበሮ ሽፋን በየሰርጉ በቀብር ስነ ስርዓት እና በህዝባዊ ባዓላት የራሱን ድርጅቱን ባንዴራ ወደ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓለማነት በማሳደግ፤ “ሰገናት” በማለት የሚጠራቹ ታዳጊ ወጣቶች ህጻናትን አንገታቸዉ ላይ መሃረሙን አስረዉ “የክብር መዝሙር በመዘመር” በማዉረድ እና በመስቀል እንዲተዋወቁዋት አደርጎ “ያገሪቱን ሰነደቅ ዓላማ ጭራሽኑ እንዳያዉቋት በማድረግ ሰንደቅ ዓላማችን ባካባቢዉ ለ17 ዓመት ተሰዉራ እንደነበር ይታወቃል። ካላመናችሁኝ (የትግል ሜዳ ሰነዶች እና ስበሰባዎች ጭፈራዎች የሚየሳዩ ፊልሞችን ተመልክቱ)። ሌለ ቀርቶ “ክብሪት” ተብለዉ በከተማዎች ዙርያ በሚገኙ ገጠሮች እና በዋና አዉራ ጎዳናዎች አካባቢ የተመደቡ የተሓሕት “ፈዳይን” ተብለዉ የሚጠሩ ለነብሰ ግዳያ እና ተፈላጊዎች/ተቃዋሚዎች ከከተማ እያፈኑ የሚያወጡ ቡድኖችን “እከተማ ዉስጥ ድረስ በመግባት በአውረጃ እና በወረዳ መዘጋጃ ቤት መንግሥት ጸ/ቤቶች፤ በትምርት ቤቶች ሰርገዉ ተሸሽገዉ በመግባት እና በማስፈራራት በክብር የተሰቀሉትን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓለማዎች የፋሸስት እና የጠላት የቅን ገዢ ባንዴራ አድረገዉ በመቁጠር ሰንደቅ ዓላማይቱን በማዉረድ “የህወሓት” ባንዴራን ሰቅለዉ ይሄዱ እንደ ነበር ይታወቃል።በህዝቡ እና በሰንደቅ ዓላማዉ ላይ የነበራቸዉ ንቀት እና ኢትዮጵያዊ “አስተሳሰብ” ሃቁ ይሄ ነበር። በቃለ መጠይቁ ያዳመጥነዉ “ህወሓት ቀደም ብሎ ለኢትዮጵያ የነበረዉ በጎ አስተሳሰብ ስለተቀየረ” አቶ አስገደም ሆነ ሌሎቹ ድርጅቱን እየጣሉት እንደሄዱ፡ ሲገልጽ ‘ህወሓት መቸ ነበር ለኢትዮጵያ በጎ አስተሳሰብ የነበረዉ? ከማለት አልፈን ‘የነበረዉ አስተሳሰብ እየተለወጠ ሄደ” የሚሉንን አስተሳሰብ “መጥፎዉን ለመተዉ እየቃጣዉ ስለሄደ ያንኑ መጥፎዉን እንዲቀጥልበት ነበር ፍላጎታችን ማለታቸዉ አንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ለመቀበልም ስለሚያዳግት። ወያነ ጥሩ አስተሳሰብ ኖሮት የተለወጠበት መንገድ እና ጊዜ አባካችሁ በማስረጃ እየተደገፈ ይቅረብልን። አሁን ወደ ኢሕአፓ እንግባ። አቶ አስገደ በቃለ መጠይቁ ዉስጥ በጣም ከገረሙኝ አበባሎቹ አነሆ።-“ኢሕአፓ የብሄረሰብ መብት አያስፈልግም ብሏል”_ ሲል- ኢሕአፓን ካለ ስሙ ስም ሰጥቶት ሲቀባዉ አድምጣችሁት ይሆናል። ኢህአፓ ስለ ብሔር ብሔረሰብ መብት በፕሮገራሙም የሚነበበዉ አስገደ ገ/ስላሴ ከሚለዉ እጅግ ተጻራሪ ነዉ። ያዉም እኮ አስከ መገንጠል ድረስ አክብሯል ተብሎ የሚወቀስ ድርጅት! ይህ በዉሸት እና በጥላቻ የተመሰረተ ዉንጀላ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ሰዎቹ ከወያኔ ድርጅት በ አካል ቢወጡም በህሊናዊ አስተሳሰብ ድሮ ህወሓት ያስተማራቻቸዉን ጸረ ኢሕአፓ ትምርት ዛሬም በያንዳንዱ ወያነ “ነበር” አባሎች አለ። መከራከሪያቸዉ “ዉሃ የማይቋጥር” ነዉ። አስገደ ኢሕፓን በዛ ብቻ ሳይሆን የከሰሰዉ “በትምክህተኝነትም” ጭምር ነዉ። አስገደ ወያኔን ሲተች “በጠባብነት” ሲከስስ አድምጬዋለሁ። የራሱን ቡድን መዉቀሱ ትክክለኛ ሲሆን ኢህአፓን “በትምክህት” መክሰሱ ግን መለስ ዜናዊ ስብሓት ወይንም የመሳሰሉት የህወሓት የፓለቲካ “ሀሁ” ጽፈዉ ስለ ኢሕአፓ ጥላቻ ሲያስተምሩዋቸዉ የተጠናወታቸዉ ዉዥምብራም ትምሕርት ዛሬም እየደገመዉ መስማቴ ይገርማል። ኢሕአፓን የመሰረቱት እና በግምባር የመሩት ያዉ የ እኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። እንዴት ሲኮን? በምን ታምር ኢሕአፓ ትምክሕተኛ ሊሆን ይችላል? እንዴትስ የትግራይ ሕዝብ መብት አይከበር ብሏል (የብሔር ብሔረሰብ መብት አያስፈልግም ብሏል) ተብለዉ በእነ አስገደ ባልሆነ ዉንጀላ አገር ቤት በሚደመጥ ራዲዮን ይከሰሳል? ኢሕአፓ የትግራይ ገበሬዎች በ “ክልተ አዉላዕሎ” የሚገኙ ገበሬዎች እና አካባቢዉ አደራጅተዉ ስለ እርሻ አሰራር እና ጥናት ማህበራዊ ኑሮ እና አደረጃጀት ለማስተማር ሲጥሩ የወያኔዎቹ እነ ብረሃነ ገ/ክርስቶስ ሄደዉ ከትግራይ ዉጭ እንጂ የትግራይን ሕዝብ ለህወሓት መተዉ እንዳለበት ነግረዉ በጠመንጃ ሃይል እንዲፈረስ አላደረጉም ወይ? ታድያ ትምክህተኝነት የተሸከመዉ ማን ነዉ? ተስፋይ ደበሳይም ሆኑ ሌሎቹ ብዙ የትግራይ ተወላጆች መሪዎች እና አባሎቹ እንዴት ጸረ ትግራይ እና የትምክሕት ሃይል ሊሆኑ ይችላሉ? የራዲዮኑ አዘጋጅ መልሶ አስገደን መልሶ አምጥቶ በዚህ ጉዳይ እንዲአብራራ መጠየቅ አለበት። ተስፋይ ደበሳይ እና ሌሎቹ የሚመሩት ድርጀት (ያዉም ህይወታቸዉ ከፎቅ ወርዉረዉ ለሞት የሰጡ ሰዎች) እንዴት የአካቢያቸዉ ንጉሶች ለመሆን ፈልገዉ ነበር ብሎ አስገደ በማይሆን ዉዥምብር ዉስጥ ራሱን ከትቶ ይከሳቸዋል? ነዉር አይደለም ወይ!? ወያኔዎች እና ወያኔ ነበር “አጓጉሎች” በዚህ አስገደን በመተቸቴ “ጌታቸዉ ኢሕአፓ ነዉ ለዚህ ነዉ የሚተቸዉ” በማለት እኔን በመዉቀስ ‘ራሳቸዉን እንደሚያታልሉ አርግጠኛ ነን.. ሓቁ ግን አንድ ተቺ የማይሆን ነገር ሲሰማ የመተቸት መብቱ ስለ ፈትሕ እና እዉነትነቱ መተቸት ተገቢ ነዉ። በዚህ ተቀበሉኝ። አይሆንም ኢሕአፓ ነህ ካለችሁኝ “እሰየዉ ፤ከእዛ በፊት ግን ኢህአፓ የብሔር መብት መከበር አያስፈልግም ብሏል የምትሉትን ማስረጃችሁ አምጡ እና አሳምኑን። በመጨረሻ የአበበ በለዉን አስገራሚ እሮሮ አድምጣችሁታል? ለምን የትግራይ ሰዎች ወይም የኦሮሞ… ሰዎች በስብሰባ በሰላማዊ ሰልፍ አይወጡም ፤አይታዩም? የሚሉ ሰዎች ተገቢ አይደለም እና ስሞታቸዉን ማቆም አለባቸዉ። አርስዎ ምን ይመስለዎታል? ሲል አስገደን ይጠይቃል። ብርቱኳን ስትለዉ የነበረዉን አበበ በጠበቃነት ደግፏት ሲከራከርላት ነበረዉን “ለምን የትግራይ ሰዎች በስብሰባየ አላየሁም?” ያለችዉን እና ስንት ንትርክ ያስከተለዉን አባባሉንና አባባሏን ረስቶት መከረኛ “ተቃዋሚን” ትግራይ፤ የኦሮሞ…ለምን ወደ ስበሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ ለ17 ዓመት ሙሉ አልመጡም? ለምን ከኛዉ ጋር አይመክሩም ወይንም አልተሰበሰቡም? እያላችሁ ሰዉን አትለያዩ ይለናል። “የፈረደብን!” አቶ አበበ ረሳዉ እንጂ፤ ስሞታዉ እና ጥያቄዉ ሕጋዊ ተገቢ እና በምክንያት ተደገፈ አንጂ የተወሰኑ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖችን ለማስቀየም ወይንም አታካራ አምሮን ለመለያየት ተብሎ የተባለ አልነበረም። ስሞታችን ሕጋዊ እና ምክንያታዊ ነዉ። ለምን እንዲህ ትላላችሁ ብሎ እኛን አቶ አበበ በለዉ ተመልሶ እኛኑን ለመክሰስ ከቃጣዉ ዉጭ አገር ከመጣ በቅርብ ጊዜ ከሆነዉ ታሪክ ማጥናቱ የሱ አንጂ የኛ ፈንታ አይሆንም። ምስኪኖቹ ከ ወዳጅም ከጠላትም እየተወነጀልን እየተነተርን ነዉና እባካችሁ ዛሬስ አረፍ እንበልበት። ከእሳት ዘሪዎች እሸት አንጠብቅምና ይብቃን። //-//www.ethiopiansemay.blogspot.com

Saturday, November 29, 2008

የኢሳያስ አፈወረቅ የባሕር ላይ ዉንብድና ተግባር

               የኢሳያስ አፈወረቅ የባሕር ላይ ዉንብድና ተግባር ያጋለጠዉ ሰነድ

ጌታቸዉ ረዳ

ከላይ የሚታየዉ ፎቶግራፍ እና የዚህ ጽሑፍ ርዕስ የቀረበዉ ከእኔው ከተርጓሚዉ www.Ethiopiansemay.blogspot.com ነዉ።ይህ ጽሑፍ ካነበቡ በሗላ ከወደቀኝ በኩል የተለጠፈዉ የባሕር ጠለፋ ዉምብድና የሚያሳይ ቪዲዮ መመልከቱን አይርሱ። በዚህ ወር በተከታታይ እየተረጎምኩ ለናንተ እያዘጋጀሁት ያለሁን በቅርቡ ይፋ ሆኖ በተከታታይ ለትግርኛ አንባቢዎች በትግርኛ የተጻፈ ልዩ ልዩ ሚስጢራዊ ሰነዶችን በኤርትራዊዉ በአቶ ዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ ጸሓፊነት ይፋ እየሆኑ ያለዉትን ሚስጢራዊ ሰኖዶችን አንዳንዶቹ ባለፉት ዕትሞች በብሔራዊ ቋንቋችን ለአማርኛ እንባቢዎች እንዲነበብ አድርጌአለሁ። ጸሓፊዉ Saturday, 22 November 2008 http://asena-online.com/ በተባለዉ የኤርትራ የህዋ ሰሌዳ በዛሬዉ ክፍል 5 ይፋ ያደረጉት ሚስጢራዊ ሰነድ “ዕቅዳችን መጪዉን አስፈሪዉ ዳማና መበተን ነዉ!!!” በሚለዉ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን አገሮች “ኔቶ” ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ፋን ቤንጃንጉዝ ከተናገሩት ርዕስ በመነሳት የቀይ ባሕር አካባቢ ኤርትራ እና ሶማሊያ እንዲሁም አጎራባች አገሮችን አስመልክቶ የሚታዩት ዉጥረቶችና መጪ ሁኔታዎችን አስመልክቶ አሜሪካ ዓይኖቿን በአካባቢዉ የባሕር ቀጠና እያሳረፈችበት ያለችዉን አትኩሮት ይተነትናል። የሰነዱ ትንተና ብዙ ነገሮችን ያካተተ በመሆኑ እኔዉ ራሴ ለአንባቢዎቼ እንደሚመች በሦስት ክፍል በመመደብ (1-) የኢሳያስ አፈወርቅ የባሕር ላይ የዉምብድና ተግባሮች (2-) ሕገ ወጥ መሳሪያዎችን የመሸጥ እና የማስተላለፍ (3-) የኑክሌር አተላ በኤርትራ ዉሃዎች እንዲጣል የመፍቀዱ ሁኔታ የሚመለከቱትን ከፍየ የየራሳቸዉ ርዕስ ጠብቀዉ እንዲነበቡ በተለያዩ ገጾች የተበታተኑት ጉዳዮች እየለቀምኩ በ አንድነት እንዲነበቡ አጠናቅሬዋለሁ። በርዕስ ብከፍለዉም የትርጉሙ ይዘት አልተቀየረም። ከሦስቱ ርዕሶች ቅደም ተከተል ከቀረቡ በሗላ ዝምበባዌ ድረስ በመጓዝ በኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም የነብስ ግድያ የተሳተፈዉ “መቐለ” በመባል የሚታወቀዉ ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ ጎይተኦም ማን መሆኑን እና በነዚህ በሚጠቀሱት የዉምብድና ስራዎች ምን ሚና እንደነበረዉ በሰፊዉ ይብራራል።
መልካም ንባብ፦
-1-የባሕር ዉንብድናዉ የመርከቦች ጠለፋ
“… ዛካሮቭ የተባለዉ ሩስያዊ ባለንብረት የሆነችዉ 140 ቶን ክብደት ያላት መሳርያዎች የጫነች የጭነት አይሮፕላን በJuly 26/2007 በኤርትራዊዉ ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ ጎይተኦም (መቐለ) አጃቢነት ሶማሌ ዉስጥ የማራገፉን ሁኔታ እና በማስከተልም የአካባቢዉ ዉጥረት የመጨመሩ አሳሳቢነት በሚመለከት የአሜሪካ ፕረዚዳንት ጆርጅ ቡሽ እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ የሽብር ቡድኖችን ክትትል በሚመለከት የጋራ ስምምነት ለመፈራረም ያበቃቸዉ ሁኔታ የታወሳል። በተከታታይ በዳሂር አወይስ ሲመራ የነበረዉ የሶማሌዉ የእስላሞች ሕብርት የሽግግር መንግሥት በተቀናቃኞቹ ከተፈነቀለ በሗላ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከኤርትራ መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመመስረት መጠለያ ተሰጠዉ። የሶማሊያዉ ዳሂር አወይስ ከኤርትራ ጋር የጠበቀ ግንኙነት የጀመረዉ ግንኙነቱ የቆየ ሲሆን፡ መጠለያ ተስጥቶት የኤርትራ እንግዳ በመሆን ወዳጅነት የመሰረተዉ በቅረብ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሶማሌ ገና በ1994 በጎሳ ነገሥታት ስትታመስ ጀምሮ ወደ አሥመራ በመመላለስ ብርጋዴር ጀኔራል አብርሃ ካሳ በወቅቱ ሐማሴን ሆቴል እና አምባሴራ ሆቴልን ስያስተዳድር ለነበረዉ ለኮሎኔል ሰሎሞን አብርሃ በአደራነት ተሰጥቶት የክብር እንግዳ እንክብካቤ እንዲደረግለት መመሪያ ተላልፎ በክብር ይስተናገድ እነደነበረ እና ዛሬም አስፈላጊዉ የክብር እንክብካቤ እየተደረገለት በኤርትራ እንደተጠለለ ይታወቃል። ግንኙነቱ እየጠነከረ የአካባቢዉ ሁኔታ እየተለወጠ ሲሄድ በSeptember 2008 የአዉሮጳ ሕብርት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ስብሰባም በአፍሪቃ ቀንድ እየታየ ያለዉ አሳሳቢ ክስተት ካገናዘበ በሗላ ወታደራዊ ክንዋኔዎችን ለማካሄድ የሚያስችለዉን ዕቅድ አጸደቀ። ቀጥሎም በተመሳሳይ መንገድ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አድሚራል ፊሊፕ ግሪን ከየመን ጋር የባሕር ላይ ዉንብድና ለመግታት አሕጉራዊ የመተላለፊያ የቀ ይ ባሕር ቀጠናዎች ጸጥታን ለመቆጣጠር እንዲያመች ወታደራዊ የጋራ ትብብርን በሚመለከት ዉይይት ተደረገ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ አሜሪካ አንዲት መርከብ የተጠለፈች መሆኗን ካሳወቀች በሗላ፤ ወደ ኤርትራ የዉሃ መስመር በመቅዘፍ ተሰወረችዉ ነብረትነትዋ የኢራን የሆነች መርከብ ለመከታተል ወደ ኤርትራ የዉሃ መስመር የመግቢያ ፈቃድ ለማግኘት መርከቧን ለጠለፏት ሽፍቶች $7 ሚኒሊዮን ዶላር እንደከፈለ የተለያዩ ጋዜጦች አስተጋቡ ። አሜሪካ $7ሚሊዮን ዶላር ትክፈል እንጂ በተዘዋዋሪ መንገድ ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ጀምሮ የአካባቢዉ ጸጥታ በብቸኝነትና በበላይነት ለመቆጣጠር የነበራትን ጥም በደረግ ጊዜ አጥታዉ የነበረዉን ዕድል ከሰሜን አትላንቲክ ኔቶ ጋር ሃይሏን በማዋሃድ ወደ ቀይ ባሕር ቀጠና በማዝገም፡”የጥቁር ዳማና ጠረጋ ዘመቻ” ለማድረግ የተጠናከረ እንቅስቃሴ ለማድረግ ዕድሉን አገኘች። ሩሲያም በበኩሏ ከሴፕተምበር 2008 መጨረሻ ገደማ ጀምሮ በሶማሊያ የባሕር ደንደሶች ተዋጊ መርከቦቿን ለማንቀሳቀስ ዝግጁ እንደሆነች’ና ሲያስፈልግም ተዋጊ መረከቦቿም ስራ ላይ እንደሚዉሉ በተጓዳኝ አስታወቀች። ይበልጥ መስህቡ እየጎላ ሲሄድ M.V.Faina የተባለች መረከብ ከጠለፈች በሗላ የት እንደምታርፍ በቅጡ ያልታወቀ ታንክ እና ወታደራዊ ዕቃዎችን ጭና ስትጓዝ የነበረችዉ ንብረትነትዋ ይኩረይን የሆነች በሗላ ላይ በSeptember 28/2007 በኤርትራ ማርሳዎች(ወደቦች) በብርጋዴር ጄኔራል ፍጹም ገብርሕይወት ተረካቢነት የጫነቺዉ መሳሪያ ማራገፏን ከተደረሰበት በሗላ የአትላንቲክ ኔቶ ጦር ወደ ቀይ ባሕር ቀጠና የዉግያ መርከቦችን በመላክ አሰመርቶ ነበር። በወቅቱ የባሕር ሃይሉ አዛዥ የነበረዉ ብርጋዴር ጀኔራል ፍጹም ገ/ሕይወት ነዉ። ከጊዜ በሗላ የኤርትራ የባሕር ሐይል አዛዣነት ስልጣኑን ለመጄር ጄኔራል ሑመድ ካሪካሪ በሕዳር November 18/2007 እንዲለቅ ተደርጓል ። ለስልጣኑ ቅሚያ ምክንያትም ኢሳያስ አፈወረቂ የኒኩሌር አተላ ወደ የኤርትራ የቀይ ባሕር ዉሃዎች እንዲጣል የመፍቀዱን ጉዳይ በመቃወሙ ነዉ። ዛሬ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የባሕር ጠለፋ ዉምበድና እየበረታ መሄዱና ቢያንስ አስከ 61ጊዜ የመርከብ ጠለፋ ሲካሄድ መርከቦቹን ለማስለቀቅ የተከፈለዉ ገንዘብ ወደ 300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚጠጋ ይነገራል። የፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ አስተዳደርም በመርከቦች ጠላፋ እና ከኑክሊየር አተላ መጣያ በሚገኝ ገንዘብ ተግባር ላይ ተጠምዷል። Sirius Star ሳይረስ ስታር ተባለችዉ መርከብ 2ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ጭና ካሳዉዲ ዓረብያ ስትጓዝ ከመጠለፏ በፊት November 14/2008 ወደ 15 አጥቢያ ክዉ ብሎ ጸጥ ባለዉ ሌሊት በ5ፈጣን ጀልባዎች ተሳፍረዉ በጀኔራል ፍጹም ገ/ሕይወት ሸኚነት-ኮሎኔል መሓሪ ደስታ፤ ካፒቴን ያሲን ፈረጅ ካፒቴን ሓሰን ፍካክ የሚመሩት 46 ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቁ የኤርትራ የባሕር ሃይል አባላች አቅጣጫቸዉን ወደ ሕንድ ዉቅያኖስ አዙሮዉ በመቀዝፈ ተጓዙ ። ዕሁድ November 16/2008 በዛዉ ዕለት ንብረትነቷ የአሜሪካ የሆነች US bounder tanker ወደ ደቡባዊ ምስራቅ ሞምባሳ አካባቢ በምትጓዝበት ወቅትም ብርጋዴር ጄነራል ጠዓመ (መቐለ) ከሶማሊያዉ የእስላሞች ሕብረት ግምባር የሽምቅ አባል ኮማንደር አይዘን ሑሴን ከማል ከተባለ ቀደም ብሎ በኢራን የባሕር ሃይል አባል የነበረ በዜግነቱ ኩርድ የሆነ አብሮዉ ከአስመራ ወደ ኬኒያ የጥድፉያ በረራ አድርገዉ ነብር። Syrus Star የተባለች ካሁን በፊት ከተጠለፉት መርከቦች እጀግ ግዙፍ የሆነች መርከብ በሶማሌ ጫፍ በፑትላንድ አካባቢ የመጠለፉ ዜና ሲሰማ፤ነገሩ በፍጥነት እየተባባሰ መሆኑና የነገሩም ዉስብስብነት ይበልጥ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ጠላፊዎቹን እና የዉስብሰቡን ሁኔታ አድኖ የማግኙትን ጉጉት ይበልጥኑ ከፍ ሲያደርገዉ፤”ከበስተጀርባዉ ያለዉ ጥቁር መጋረጃ” እንዲገለጥ በር የሚከፍት መሆኑን የአሜሪካ የማዕከላዊ የስለያ ድርጅት ያምንበታል። በዚህ ትኩረት ላይ የፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ አስተዳደርም በመረከብ ጠለፋ እና ዝርፊያ እንዲሁም ቀይ ባሕርም የመርዘኛ ቆሻሻዎች መጣያ እንዲሆን በማድረግ በዛ የሥራ ትኩረት ተጠምዶ ይታያል። የመርከብ ጠለፋዉ ዉምብድና በጣም በመጧጧፉ በቅርቡ የኮሮሽያ ፤የፊሊፕኖ እና የፓልንድ መርከቦች የባሕር ጠለፋ ሰለለባ ሆነዋል። የጃፓን የቻይና ዘመናዊ አሳ አጥማጅ መርከብ እንደዚሁም ኬሚካል የጫነች የቱርክ መርከብ ስትጠለፍ የኤርትራ ባሕር ሃይል ወዲያ ወዲህ ሲወራጭ ነበር። በወቅቱ ተከታታይ የጠለፋ ክስተት ከታየ በሗላ የአሜሪካ መንግሥት በህዳር (November 2008) ዜጎቿ ብቻ ሳይሆን የአዉሮፓ ዜጎችም ጭምር ወደ ኤርትራ እና ወደ ሶማሌ እንዳይጓዙ ጥብቅ ማሳጠንቀቂያ የሰጠዉ። ተያይዞም በዛዉ ወር በህዳርNovember 19/2008 ደግሞ የአዉሮጳ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች የአሜሪካን መግለጫ በመከተል የሶማሊ እና የኤርትራን ሁኔታ በመገምገም አምባሲዎቻቸዉ በተጠንቀቅ እንዲቆዩ እና ዜጎቻቸዉም ወደ እነዚህ አገሮች እንዳይጓዙ አገደች። ይህንን በመቃወም የኤርትራ መንግሥት የፈረመበትን የተባበሩት መንግሥታት ተስማምተዉ ያጸደቁትን አንቀጽ 36ትን ዉል በማፍረስ በዲፕሎማቶች ላይ ጥበቅ ፍተሻ በማካሄድ ይገኛል። ይህ ክስተት የኔቶ ወታደራዊ ቺፍ አድሚራል ዳኒኤል ቤንጃንኩዝ በOctober 2008 የተናገረዉ “ዕቅዳችን ከወዲሁ እየተጠራቀመ ያለዉን አስፈሪዉ ጥቁር ዳመና መበተን ነዉ!!!” በማለት ያስተጋባዉን ማስገንዘቢያ የ አሜሪካ የባሕር ሃይል ወደ ቀይ ባሕር ዉሃዎች ማዝገሙ አና የአሜሪካ መንግሥት (ኖቨምበር) 11/2008 ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየተናኮሰችዉ ያለዉን አሳት እና በሌላ በኩል በጁቡቲ ላይም የምትጭረዉ የጠላትነት እሳት በመገንዘብ የፈረንሳይ የባሕር ሃይል ጦሮች ወደ ራስ ዳሜራ መገስገሳቸዉ እና ጁቡቲ አካባቢ ያሉት የጀርመን ጦርም በተጠንቀቅ መሆናቸዉን ስንመለከት “ሁኔታዉ ወዴት እያመራ ነዉ?” የሚለዉን የዉጥረቱ ሁኔታ አሳሳቢነት አሁንም እንዳለ ነዉ። የአሜሪካና የአወሮጳ ሕብረት በጣምራ እያካሄዱት ያለዉን ጸረ ሽብር እና የባሕር ላይ ዉንብድና የመከታተል ዘመቻ በመቃወም የኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኖቨምበር 20/2008 የሰጠዉ የቁዋሜ መግለጫዉ ላይ የቀይ ባሕር ዉሃ የኒኩልየር አተላ መጣያ እየሆነ ነዉ በማለት ያወጣዉ መግለጫዉንም ጭምር ድርጊቱ የሚፈጽሙት ወገኖች እነማን እንደሆኑ በስም ሳይገልጽ በደፈናዉ ተሽቀዳድሞ መክሰሱ -አንድ ዓይኗ ሌላዉን ሸዉራራ ዓይን ብላ አስቀድማ የመሳደቧን ጉዳይ “ሳትቀድመኝ ልቅደማት” ዓይነቱ መግለጫ አዉጥቷል። ያካባቢዉ ተነካኪ ሁኔታ ቢነኩት በቀላሉ ሊቀጣጠል የሚችል ዉጥረት በበዛበት ቀጠና ላይ ሆኖ፤ በዉጥረቱ ላይ ገብቶ ባለበት ሁኔታ የድሮዉ የአሜሪካ ፕረዚዳነት ቢል ክሊንተን መንግሥትነቴን ሊገለብጥ ሲያሾር ነበር በማለት የኤርትራ ፕረዚዳንተ ኢሳያስ አፈወረቅ ደጋግሞ የከሰሰዉን ፓርቲ እና የቢል ክሊንተን ባለቤት የሆኑት ዛሬ በኦባማ አዲሱ አተዳደር የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሆኑን ዜና ጋር ተያይዞ የ አካባቢዉ ዉጥረት ወደየት ሊያመራ ይችላል የሚለዉን ጥያቄ ያስነሳል? ከአካባቢዉ ዉጥረት በተጨማሪ የኢራን የባሕር ሃይል ወታደራዊ ባለሞያዎች ወደ ዳህላክ የመግባታቸዉን ጨምሮ የኤርትራ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እንደዚሁም በሕባዊዉ ሠራዊቱና በአዛዦቹ፤የሕግደፍ ዉስጣዊ ዉጥረትና የካቢኔ ሚኒስትሮቹ በሌላ ገጽ ያለዉን ሁኔታ ምን ይመስላል? ይቀጥላል…. ።