Tuesday, October 30, 2012

መለስ ማን ገደለው?


ንባብዎን ከመጀመርዎ በፊት፡
አረሜኔዎቹ የወያኔ ትግራይ የፈሺስት ፌዴራል ፓርላማ አባላት መሪያቸው መለስ ዜናዊን ማን እንደገደለው ስለሚያውቁ አንድ የፓርላማ አባል “ኢትዮጵያ ገራችን እና ሕዝቧን እግዚአብሔር በበረከት ይጐብኛት” ብሎ ንገግሩን በመደምደሙ “በኢትዮጵያ አምላክ” ላይ ተቃውሞዋቸውን በማሰማት “በስላቅ በመሳቅ” በኢትዮጵያ አምላክ ላይ ሲያፌዙ የተቀዱት  ለማየት ዩቱብ ላይ ይህንን አድራሻ በመጫን Ethiopia - "God Bless Ethiopia" quote brought the biggest laugh at the Parliament http://youtu.be/v09ak8RKNKY   የአጋስሶቹ የሕሊና ብቃት ለመመዘን ለጽሑፌ ማገናዘቢያ እንዲረዳዎ ይመልከቱ።    
                
Muna is combing Tina’s hair; the two Ethiopians prostitutes will soon be heading to a club. “The best is to find an American soldier,” says Tina. “The French are the most generous clients; they pay for our apartments so that we do 
           
The Godless anti Christ and anti Ethiopia Meles Zenawi buried In the compound of God's house by the priests who worshipped him as their leader 
መለስ ማን ገደለው?
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)getachre@aol.comwww.ethiopiansemay.blogspot.com

ተቃዋሚ ጋዜጠኞችም ሆኑ ምሁራን መለስ ዜናዊን የገደለው በሽታ ምን እንደሆነ እና መቸ ወር እና ቀን እንደሞተ ባሉት ዙርያዎች ለማወቅ እያብሰለሰሉ ጥያቆችን ማንሸራሸር እንጂ “መለስን የገደለ ሃይል ማነው?” የሚል ጠለቅ ያለ ሰውዬው ከነበረው ከኢትዮጵያዊ ባህል፤አገራዊ እና ሃይማኖታዊ የራቀ ሸካራ ግንኙነት ከፖለቲካው ትንተና ባሻገር እነኚህ የተጠቀሱ ሦስቱ የአገሪቱ አድባራዊ (ስፒሪት) ምሶሶሰዎች ባለው ዙርያ ሊያስከትሉበት የቻሉት መለኰታዊ ቅጣቶች ብዙም ትኩረት አልሰጡትም።

ዘመናዊ ጋዜጠኞችም ሆኑ የተማሩት ክፍሎች ትኩረታቸው ምድር ላይ ከሚታያቸው ጉዳይ ማያያዝ እንጂ የዓለም ሕዝቦች የሕይወት ታሪክ መዛግብቶቻቸው ከሚኖሩበት ከኢትዮጵያ ሰማዬ ሰማያት ማለትም ከምድሪቱ በላይ ያለው ሃይል መመርመር ዘመኑ ያለፈበት የቂሎች እምነት እንዳያስብላቸው ስለሚሰጉ፤ለመለስ መሞት እንደ ሽፋን ሆኖ ተከስቶ ከገደለው በሽታ በላይ ያለው ቀጪ ሃይል ማየት ስላልቻሉ ስለ ገደለው በሽታ እና የሞተበት ቀን እንደትልቅ ጉዳይ አድረገው ሲተነትኑ ይታያሉ።

 ይህ እንደዋዛ የሚታይ እይታ ሳይሆን ፤ ለመለስ መሞት ምክንያቶች “ኢትዮጵያን እንደ አገር ተከብራ እንድትኖር፤ያቆዩዋትና የተከላከሉላት” *የባህል እና የሃይማኖት* ተቋማት በወያኔ ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ መሪዎች በተለይም ድርጅቱን በመራው በመለስ ዜናዊ የስልጣን መማገጥ ተሰነጣጥቀዋል። መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ያነጣጠረው ጥቃት የምድርቱ ሕግ ሊገቱት አልቻሉም እና ኢትዮጵያን የፈጠረ ሃይል ገድሎታል።

 ወያኔዎች ልብ ያላሉት ነገር፤ “ኢትዮጵያ” የምትባል አገር በውስጧ የሚኖሩት ፍጡራን ሳይሆኑ ባለቤቶቿ ፤በምድሪቱ ውስጥ ሰፍረው የሚገኙ እልፍ ኣእላፍ እንሰሳዎች እና ሕዝብ በጥበቡ ያሰፈራቸውና የፈጠራቸው ንብረቶቹ የእግዚአብሔር መሆናቸውን ልብ አላሉትም። ልብ ስላላሉትም መሬቱም ሕዝቡም እንሰሳዎቹም ወንዞቹም ተራሮቹን እያንቀጠቀጡ በቁጥጥራችን አስገብተናል በማለት በማን እህሎኝነት ብዙ ግፍ ፈጽመዋል። እነኚህ ግፎች በወያኔ ትግራይ የሃይማኖት መሪያቸው በአባ ጳውሎስ እና በፖለቲካ መሪያቸው በመለስ ዜናዊ እና በኪነት እና በባሕል መሪያቸው በእያሱ በርሔ  ላይ ባንድ ዓመት ውስጥ የወረደው የእግዚአብሔር ቅጣት በጣም አስገራሚ ተአምር መሆኑን ልብ እንድትሉት ደጋግሜ አደራ እላለሁ።

 ይህ ትኩረት የተናገርኩት ዘሬ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ባደረጉበት ሴራ እና አልጀሪስ ስምምነት ከተደረገ በሗላ የጻፍኩበት ቦታ የት እንደሆነ አሁን ትዝ ባይለኝም” ያስታወሳችሁ ብትኖሩ የጻፍኩትን ልብ እንድትሉት ደግሜ አሳስባለሁ። “ ልጆቿ ከድተዋት ብቻዋ ቀርታ ሰንደቋ እና ሕዝቧ እየተዘለፈ ለውርደት የተዳረገቺው ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪዋ ስታመለክት “ዓለም” ያላየቺው ቅጣት ይወርድባታል።” ብየ ነበር። በተለይ ሃያል ነን በሚሉ አገሮች አንደ አውሮጳ፤አሜሪካ እና አረቦች እንዲሁም ሶማሌ’፡ ቅጣት ይደርስባቸዋል ብዬ ነበር። አሜሪካን አገር የደረሰው እና እየደረሰ ያለው የመከራ ዘመን እያያችሁት ነው። እነ ሶርያ እነ ኢራቅ እነ ሊቢያ እነ ግብፅ እንዲሁም ምጢጧ ሶማሌ “ኢትዮጵያን” ለመበተን የኤርትራ ሽምቅ ተዋጊዎች እያስታጠቁ  ራዲዬ ጣቢያ ከየመዲኖቻቸው እያስተላለፉ እርስበርሳችን ያጋደሉንን ያህል፤ ዛሬ እነ ሶርያ እነ ኢራቅ ሊቢያ  ሶማሌ;…….ፍዳቸውን ከፈጣሪ እያገኙ መሆናቸው ስትመለከቱት ‘በእጁ ጠፍጥፎ የሰራትን ኢትዮጵያ’ የተጫወቱባትን ያህል ፈጣሪዋም በበኩሉ ጊዜውን ቆጥሮ ትእግስቱ ካሟጠጠ በሗላ አንድ ባንድ ሲቀጣቸው ምን ትታዘባላችሁ?።  ይህ ትንቢት ከመድረሱ በፊት  ጽፌዋለሁ። ምናልባትም ሃዋርያ ጋዜጣ ላይ ወይንም ኢንተርኔት ላይ። ያስታወሳችሁት ሰዎች ከላችሁ እርዱኝ።

 በህይወት ያሉ ተመሳሳይ ሞኞቻቸውም የሚናገሩትን አንደበት ልብ ብንል ለፈጣሪ የሚፈሩ አይደሉም። ለምሳሌ “ስየ አብርሃ” ባንድ የክርክር መድረክ ከመለስ ካድሬዎች ጋር በፖለቲካ እንካ ስላንትያ ገጥሞ መልስ ሲሰጥ “አታስፈራሩን! ካስፈራራችሁን፤እስካሁን ድረስ ያልተናገርነውን (የደብቀን ያቆየነውን) ምስጢር እናወጣዋለን” ብሎ ነበር። እየሰማችሁኝ ነው? ሰዎች የሚፈሩት ምድር ላይ ያሉት “አስፈራሪዎች” እንጂ ጠረፍ ላይ በኢትዮጵያ ሰማይ በመስኮቱ ብቅ ብሎ ወደ ታች እየተመለከታቸው ያለውን የሰማዩ ንጉሥ የሚሰጣቸው ሕጎች እና ማስጠንቀቂያዎችን አያስፈራቸውም።ሰውን እንጂ ከነሱ በፊት የነበረ፤ከጊዜ በፊት የኖረ ለወደፊቱም የሚኖር እና ዓለምን እና እነሱን የፈጠረ አምላክ አይፈሩም። ለአምላክ ሕግ የማይፈራ ባለሥልጣን እራሱ ባጭር ቀጭቶ ምድሪቱንም ለአምላክ ቁጣ ይዳርጋል (ለዚህ ነው አልኩ ባልኩት ትንቢቴ ውስጥ እኛንም እንዳይጨምሩን እንጸልይ ያልኩት)። ሃይማኖት ለመስበክ አላማየ አይደለም። ልብ እንድትሉት ግን አሳስባለሁ።

 የመለስ ሞት ምክንያቶች ሁለት ናቸው።

(1)  ባህል እና ሃይማኖት በማንኳሰስ የተፈጥሮ ሕጎችን ተጻሯል

(2) የሕዝብ ሃይል/ሥልጣን በጉልበት ይዞ ብሔራዊ ወንጀሎችን ፈጽሟል።

እነዚህ የተጠቀሱ 2 መሰረታዊ ክሮች ከምድር ጋር ሳይሆኑ እትብታቸው የተለቆመው ከተፈጥሮ እና ከፈጣሪ ስለነበሩ አላግባብ በጥሷቸዋል።እነዚህን የበጠሰ ሕግ ወጥነት ነውና በምድር የመኖር መብቱ ባጭሩ ይቀጠፋል።

 መለስ ሲቀጠፍ ጎራው በሁለት ተከፍሏል።ደጋፊዎቹ “መለስ ለምን ሞተ፤ሞተ? ሲሉ ተቃዋሚዎቹ ደግሞ “መለስ እንኳን ሞተ!ሞተ!” በሚል መስመር ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል። አንዳንድ በጐልማሳነት ዕድሜ ያሉ የወያኔ ቄሶችም “መለስን ወደ ፈጣሪ በመለወጥ” “መለስ እውነት ነው” በማለት “እግዚአብሔር እውነት ነው” የሚለውን ሃይማኖታዊ መመሪያ በመለስ ዜናዊ በመተካት “ፍፁም” አምላክ ብለውታል (በወያኔዎቹ የዋሺንግተን ዲሲ አምባሲ አዳራሽ ለቀብሩ ሃዘን ሲደረግለት የተቀዳው ስእለ ድምፅ ‘ዮ- ቱብ’ ‘አውዲዩ-ቪዲዮ’ ይመልከቱ) ።
ፈጣሪን ልሳን መልእክተኞች የምንላቸው ቄሶች ‘ሰውን’ ወደ “ፍጹምነት/እውነት” በመለወጥ ሲያመልኳቸው ፈጣሪን እያስቆጡ ለሃገር ውድቀት እና ቅጣት እየዳረጉን ነው። ይህንን አምልኮ “አምባገነኖች” በሚገባ ስለሚያውቁት ከኛ ይልቅ “ፍፁማን” ተብለው ከሚመለኩት ሰዎች አንደበት የተነገረውን መፈተሽ ያስፈልጋል። ከላይ ለጠቀስኳቸው ተፈጥሮአዊ እና ዓለማዊ መብቶች መፈረካከስ ምክንያቱና መነሻው የመለስ ለኢትዮጵያ አምላክ የነበረበው ንቀት እና የስልጣን አልጠግብ ባይነት ነው። መለስ ስልጣን ከመውደዱ የተነሳ ገደብ ያጣ አገርን እና ባህልን ያናጋ ግለሰብ ነበር።  ይህንን ልብ በሉ “አምባገነንነት የፈጠሪን ቅንድብ የሚያስቆም ከባድ ወንጀል ነው”። ፈጣሪን የማይፈሩ መሪዎች ስለ ሕገ ወጥነት ጉዳይ ሲነሳ አምባገነኖች  የውንጀላ ጣታቸውን የሚቀስሩት፤ ወደ እራሳቸው ሳይሆን፣ወደ ሌላ አምባገነን ነው። መረጃ ልስጥ። ለአፍሪካ ውድቀት ምክንያት መለስ ዜናዊ ምክንያቶች የሚባሉ ነገሮች ተጠይቆ ሲመልስ እንደሚከተለው ነበር የመለሰው።

“የአፍሪካ ውድቀት ሁሌም የግለሰቦች አምልኮ ነው።” ሲል አፍሪካን ለውድቀት የዳረጋት በመሪዎች ላይ  አምልኮ ማሳደር እንደሆነ አስምሮበት ነበር።እነኚህ የተመለኩ መሪዎችስ እነማን ናቸው? ሲባል መለስ እንዲህ ሲል ይመልሳል። “ስማቸውም ሁሌ በ “መ”  ፊደል ዘር የሚጀምር ይመስላል። በዚህ ረገድ ሞቡቱ እና መንግሥቱ ነበሩን።መለስን ግን ከዚህ ዝርዝር ውስጥ ማስገባት አልፈልግም” ሲል የመለሰውን መልስ “የአቶ መለስ ጥቅሶች” በሚል ርዕስ “መለስ ከልጅነት እስከ እውቀት” ተብሎ ‘በትኩእ ባሕታ’ የተጻፈ መጽሐፍ ተጠቅሷል። 
እሱ ከሄደ በሗላም  መለስን “ወደ ፍፁም/እውነት (አምላክነት) በመለወጥ” አምልኮ የአሳደሩበት ያደራጃቸው ቀሳውስቶቹ  ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ለሃይማኖት መበስበሰስ ምከንያት ናቸው።በ‘መ’ ፊደል ዘር የሚጀምር የአምባገነኖች ስም ሲጠቅስ ራሱን ለምን አልጠቀሰም? የሚል ጥያቄ ቢያስከትልም፡ የህጻናት፤የወጣቶች እና አረጋዊያን ደም ያለ ሕግ እንዲፈስ ያደረገ መሆኑን እያወቁ፤የራሱ ቀሳውስቶች መለስን በፈጣሪነት እና በፍፁም እውነትነት በማመን ለምን ሰበኩለት? ስንል ፍካሬ እየሱስ ላይ የተጻፈውን ማቴ፤7፡15 እንዲሁም 23፡5-7 ዘዳ 32 ብንመለከት የክህነት ልብስ በመልበስ መርዝ የሚረጩ ተኩላዎች በመካካላችን እንደሚቀላቀሉ እና እንደሚያሳስቱን ያስጠነቀቀው ትንቢት እውነታውን እያየን ነው ይላሉ መንፈሳዊ ምሁራን።
መለስ ዜናዊ የራሱን ሃሳዊ መሲሆችን በመመልመል ከቄስ እስከ ሃኪም  ከአረጋዊ እስከ ጎልማሳ እና ታዳጊ ብላቴናዎች ድረስ የተፈጥሮ እና የሰው ልጆች ሕግ የሚጻረሩ ርዕዮተአለሞችን እንዲቀበሉት በማድረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ “ፋሺስቶችና ጉልተኞች” የሚከተሉትን “የጎሳ እና የደም ጥራት” መለኪያ አድርጎ በቋንቋ ልሳን ተከልሎ እንዲተዳደር ቀይሶ ሕዝብን አናክሶ “በወንድማማቾች ማሃል ደም እንዲፈስ አድርጓል”።
(1)በባህል እና (2)በሃይማኖት እምነታችን የሕዝቡን እይታ እንዲበላሽ መለስ የሰራቸውን ስራዎቹ ለሞት ቅጣት ያደረሱት እንዴት እንደሆነ እንመለክት። ሕብረተሰብ እንደሚበሰብስ ባለፈው ገልጫለሁ። ሕብረተሰብ አይበሰብስም {“ሕዝቡ በስብሷል ከማለት ለዘብ ያለ ቃላት” ብትጠቀም ጥሩ ነበር} ብለው ስልክ የደወሉልኝ ወገኖቼ አሉ። መንፈሳቸው ይገባኛል። ክፋት የለውም።  ነግር ግን ‘ዘመነ ሎጥ’ የሰዶም እና የጎመራ ከተሞች ሕዝብ በስብሶ ለቅጣት እንደተዳረገው ሁሉ የኛ ሕዝብም ግስጋሴው ከዛው ያልተናነሰ  የባህል እና የሃይማኖት ወረራ ተፈጽሞበት በምድሪቱ ላይ እንዲስፋፋ መለስ ዜናዊ አስተዋጽኦ አድርጓል። የሕዝቡ መንቀዝ (መበስበስ) መረጃው ወደ ሗላ አመጣዋለሁ። 

(2) ‘በፍፁምነት’ በመልአክትነት ያመለኩት የራሱ ቀሳወስቶች ብቻ ሳይሆኑ የተማሩ አምላኪዎቹም “መለስ ዜናዊ” የተባለ “አዲስ ሃይሞኖት” መስርተናል በማለት ይፋ አድርገዋል።
ከዛሬ ጀምሮ ሃይማኖቴ “መለስ” ወደ እሚባል ሃይማኖት ለውጬአለሁ በማለት ምሁራን ዜጎችም መለስን ወደ ሃይማኖትነት ለውጠውታል። መረጃ ላቅርብ። በወያኔው “ዓይጋ ፎረም’ ድረገጽ  “ዓዳል ኢሳው” በተባሉት ጸሐፊ የቀረበውን ጽሑፍ ይመልከቱ። “I am again a born believer & my religioun is Meles Zenawi (Adal Isaw September 2, 2012)  “ፍሪኪሽ ቢሄቭዮር” (ለማመን የሚቸግር ባህሪ)የሚሉት እንዲህ ዓይነት የባህል እና የሃይማኖት መዛባት እንዲታይ መለስ ዜናዊ እና ድርጅቱ ያካሄዱት የአእምሮ ጠለፋ ምሁሩንም ኩፉኛ ጠልፈውታል።
 
በዚህ በሁለተኛው (በሃይማኖት መዛባት) እየታየ ያለው የሃይማኖትና የሕብረተሰብ መበስበስ ጎዳና ልጀምር።

ከላይ የተጠቀሱት ጸሃፊ I am again a born believer & my religioun is Meles Zenawi” ብለው ፡መለስ ዜናዊ” የተባለ አዲስ ሃይማኖት ለመመስረት የተነሱት “መለስ ዜናዊ” የተባለ “ሃይማኖት” ተከታይ የተነተኑልንን እንስኪ አንዳንዱን ልጥቀስ። 
“ I believe, Meles Zenawi was born for reasons other than the ordinary ones that you and I were born for” ይህ ሰው እየሱስ ነው፤ ከማንኛችንም በላይ የተለየ ተልእኮ እንዲፈጽም በምክንያት የተፈጠረ ከፈጣሪ የተላከልን ልዩ  ፍጡር/መልእክተኛ ነው። ነው እያሉን ያሉት። ይቀጥሉና የመለስ ዜናዊ ሃይማኖት ተከታይ እንዲህ ይላሉ “
“I have a reason to revert back to the religion that I have abandoned early in life. Things were trite and nothing was out of the ordinary then, and, I had to walk away from my religion as a result. But now, and after many years of abandoning my religious belief, I am a born-again believer and my religion is Meles Zenawi.” ……”I believe in Meles Zenawi and he is my religion from now on till the end of my time”….
“ Indeed; Meles Zenawi is my religion for he is a rarity—a gift from the Goddess of Ethiopia. And hence, he is the religion that I have now”. ((Adal Isaw September 2, 2012
 adalisaw@yahoo.com) 

እንግዲህ እንዳያችሁት ጸሃፊው መለስን የተመለከተው “አርበኛ፡ “አንበሳ”…የሚሉት ሙገሳዎች/መለኪያዎች ያንሱታል ነው የሚሉት። ለሱ የሚመጥነው “ለምክንያት የመጣ እኛን ተመስሎ ለማዳን ወደ እዚህ ምድር ከኢትዮጵያ አምላክ የተላከልን አዳኚያችን ነው” ብሏል በሰፊው ጸሐፊው ሲተንትኑ (ሊንኩን አንብቡት)። ይህ ጉድ እና በጣም አሳፋሪ የባህል፤የሃይማኖት መበስበስ እየታየ ያለው መነሻው የግዛቤ እጥረት እንደሆነ ምንም የሚያከራክር አይደለም። መለስ ዜናዊ የፈጸማቸው ወንጀሎች አምላክ እንዳትፈጽሙ ያላቸውን አብዛኛዎቹ በተለይም ትላልቆቹ (ትልቅ እና ትንሽ የሚባል የሕግ ጥሰት ካለ) አትግደል፤ አትዋሽ፤ በሕዝብ እና በአገር ክሕደት እንዳትፈጽም፤ ፈጣሪህን አክብር፤”ክረስትያን ወይንም እስላም” አማኝ ከሆንክ በምድሪቱ ውስጥ ግብረሰዶምነት አንዳይከናወኑ አጥብቀህ ኮንን/ተቆጣጠር፤ ከሌቦች፤ነብሰገዳዮች፤ከአመጸኞች ጋር አትመሳጠር፤ የአገሪቱን ዳር ድምበር ጠብቅ፤ አርበኞቿ እና ሰንደቅአላማዋን አክብር… የሚሉትን ትእዛዞች የጣሰ ክፉ ሰይጣን ነበር። መቸም በዚህ መረጃ ይታጣል የሚል ሰው ከተገኘ ሞኝ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ይህ “ፍፀም” ሆኖ ወደ አምላክነት እና ወደ ሃይማኖት የተለወጠ የወያኔ መለኰት “ፍፁም” ነው ብሎ ማለት አስቂኝ ብቻ ሳይሆን የወንጀሉ ተባባሪ እና በሕዝባችን፤በቤተሰባችን፤በጓደኞቻችን፤በአገራችን የፈሰሰው የሰው ልጆች ደም ደንታ ቢስነት መሆን ነው።

(2)መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያን ባህል እና አርበኞች ክብር አልነበረውም።

መለስ ዜናዊ ሰፊ አገር ያስገኙለት የድሮ የጦር አርበኞችና ነገሥታትን ሙገሳና ክብር መስጠቱ ይቅርና በአትሌቲክስ/ስፖርት አገራቸውን ያስጠሩ አርበኞች በተቻለው መጠን መንፈሳቸው እና ህይወታቸው እንዲሰበር ከማድረግ የቦዘነበት ጊዜ አልነበረም። መለስ ዜናዊ ስልጣን ሲቆጣጠር እሴቶቻችንን ነበር መልቀም የጀመረው። አርበኛው ማሞ ወልዴን ታስታውሳላችሁ? ዊክዴፒያ/ኢንሳይክሎፒዲያ የተባለው የታሪክ ማህደር እንዲህ ይላል፡ “In 1993, Wolde was arrested on the accusation that he participated in a Red Terror execution during the regime of the dictator Mengistu Haile Mariam. He argued that although he was present at the killing, he was not a direct participant. The IOC pressured the Ethiopian government to release him. In early 2002 he was convicted to six years of imprisonment, but released because he had spent nine years in detention already waiting for his trial.”

እየተከታተላችሁኝ ነው? አንደኛ በግድያው አልተሳተፍኩም፤ ሆኖም እዛው ቆሜ ነበር በማለት የተከራከረበት ክስ 6 አመት ሲያስፈርድበት፤ እሱ የታሰረው ግን 9 ዓመት ነበር። ይታያችሁ አንግዲህ፤ መለስ ዜናዊ የተባለ “ፍፁም አምላክ” እና “መለስ ዜናዊ የተባለ ሃይማኖት” በሚያስተዳድራት አገር 6 አመት የተፈረበት ሰው 9 አመት ፈጽሞ ወደ 10ኛው አመት እያመራ እንዳለ በ9ኝ አመቱ ፍርድ ስለተሰጠው፤ ከሚገባው በላይ ስለታሰረ አሰናብተውታል። ሲሰናበት የጉበት በሽታ ይዞ በመውጣቱ ወዲያውኑ ለሞት ተዳረገ።  ይህ “መለስ ዜናዊ የተባለ ከፈጣሪ የተላከ ልዩ መልአክ” 6 አመት የሚያስፈርድን ክስ 9 አመት እንዲበሰብስ የሚያደርግ መልአክ ከየትኛው ሰማይ እንደወረደ የዜናዊ ሃይማኖት  ተከታዮች እንዲያብራሩልን እንጠብቃለን።

የማሞ ወልዴ ባለቤት ወ/ሮ አበራሽ ከባድ የሕሊና እና የኑሮ ጫና ለማወቅ መሉ ንባኑን ለማግኘት ይህንን ይመልከቱ፤http://www.kennymoore.us/kcmarticles/woldehonolulu/woldestory.htm

“ፆታህንም መቀየር ትችላለህ”

መለስ ዜናዊ እና ፓርላማው ሹሟሙንቶቻቸውን ሲሾሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ወይንም ቁርአንን ወይንም የኢትዮጵያ ሰንደቃላማን  አስይዘው መሃላ አያስፈጽሟቸውም። ምክንያቱም መመሪያቸው ፋሺስታዊ እና ኮሚኒስታዊ ፈጣሪ አልባ መመሪያቸው በሞሆኑ። ለዚህም ግብረሰዶምን እንደነውር አይቆጥሩትም እና በአንደበታቸው ሲያበረታቱት ተደምጠዋል። “ፆታህን መቀየር ትችላልህ” በማለት ፃየፍ ይህ ብልግና የተሞላበት መልስ የሰጠ መሪ ማን ነው? መለስ ዜናዊ! ይህ ስብእናን እና አርበኛን የሚያቆሽሽ ኢትዮጵያዊ ባህል የሚጻረር የብልግና ስድብ ምላሽ የተናገረው ለማን ነበር? ታሪኩን እንመልከት።

መለስ ዜናዊ የስፖርት አርበኞችን ያከብራል፤ለሙዚቀኞችን፤ ለከያኒያንን አክብሮት ነበረው፤ እያሉ ከራሳቸው ከአፍቃሬ ወያኔ ባለሞያዎቹ አለቃቸው ሲሞት እያለቀሱ ሲያከብራቸው እንደነበረ አስደምጠውናል። እውነታው ግን ውርደትን እንደ ክብር እና ጀግንንት የተቀበሉት እነኚህ ካፍንጫቸው አካባቢ ውጭ አርቀው ማየት ያቃታቸው ሕሊናቸው በገንዘብ የተጭበረበረ የስፖርት ባለሞያዎች መለስ በህይወት እያለ ምን እያለ ክብራቸውን ይጋፋ እንደነበር ንግግሮቹ እና ቃለ ምልልሶቹ በመጽሐፍ መልክ ካድሬዎቹ ጠርዘው ባሳተሙለት መጽሐፍ ውስጥ ሲላቸው የነበረውን ነግረውናል። ይህንን እንመልከት፦

“አንድ ዝነኛ አርቲስት ክስ ተመስርቶበት ከታሰረ ትንሽ ቆየት ብሎ ነበር። በዚህን ወቅት አንድ ታዋቂ አትሌት በውጭ አገር አስደናቂ ድል ተቀዳጅቶ ወደ አገሩ ሲገባ ጠ/ሚኒስተር መለስ አድናቆታቸውን ለመግለፅ ኤየርፖርት ድረስ ሄደው ይቀበሉታል። አትሌቱም አንድ አንገብጋቢ ጥያቄ እንዳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይናገራል።

“ምን ችግር አለ ጠይቃ” አሉት ጠ/ሚኒሰትሩ።

“እከሌ የተባለ አርቲስት ካልተፈታ ዜግነቴን እቀይራለሁ”።” “አንኳን ዜግነትሀ ፆታህንም መቀየር ትችላለህ! አሉት ጠ/ቅላይሚኒስትሩ።

 (መለስ ከልጅነት እስከ እውቀት- ደራሲ ትኩእ ባህታ)

እንዲህ ያለ ነውር፤ ያውም የዓለም አምበሶች የተባሉ ሯጮች ያስናቀ የወንዶች ወንድ “ሱሩህን ፈትትህ ከወንድ ጋር ተዳራ” የሚል በነውር የተሞላ አርበኛን የሚንቅ በትዕቢት የተሞላ መሪ አንኳን በተቀደሰቺው ኢትዮጵያ ይቅር፤ ነውር በሚያከብሩ ነውራም አገሮችም ለአንድ አርበኛቸው እንዲህ ያለ ሰብአዊ ጥያቄን ለጠየቀ አገር ያስጠራ አትሌት ነውር የመለሰ መሪ በታሪክ የለም። ግበረሰዶም እፈጽማለሁ ካልከኝም መብትህን አከብራለሁ የሚለው የግብረሰዶማዉያን መብት አስጠባቂ የነበረው መለስ ዜናዊ በንግግር ብቻ ሳይወሰን በግብርም ግብረሰዶም በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ እሱ እና ተከታዮቹ የተቻላቸውን ጥረዋል። እስላም እና ክርስትያን በመጽሓፋቸው የኰነኑትን እኩይ ስነምግባር አገር እንዲበሰብስ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በዚህም አምላክ ተቆጥቶ መለስን ባጭር ቀስፎታል።መረጃው እነሆ፤

ታዋቂው ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አርአያ በኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ ድረገጽ ላይ “በኢትዮጵያ አስደንጋጩ የባሕል ወረርሽኝ” በሚል ርዕስ ለሕዝብ ያስነበበውን የግብረ ሰዶም መከሰት በኢትዮጵያ መለስ ዜናዊ እና ስርዓቱ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንዳደረገ በሰፊው እንዳስነበበን ታስታውሳላችሁ። ከ10 እና 12 ዕደሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሃያ (20) ታዳጊ ሕፃናት በውጭ አገር ሰዎች እንደተደፈሩና ደፋሪውም ወደ አገሩ እስኪመለስ ደረስ ሆን ተብሎ መንግስት ቸል እንዳለው ዘገባዎች አመልክተዋል። ችግሩ ጠለቅ ብልን እንድንረዳው ጋዜጠኛ እየሩሳሌም ግበረሰዶማዉያን በደብቅ ሳይሆን በቡድን ወደ መደራጀት ደረጃ እንደደረሱ ሁኔታውን እንዲህ ይገልጸዋል፤-

“ግብረሰዶማዊያን ማሕበር (ቡድን) እስከ መደራጀት ደርሰዋል። ከላይ እንደጠቀስኩት የመለስ አስተዳደር ምን አቋም እንዳለዉና እንደሚከተል ጠንቅቀዉ የተረዱ ግብረሰዶማዊያን 2000.. ሚሊኒየም በማስታከክሕጋዊ ዕውቅና ይሰጠንእስከማለትና የመለስ ዜናዊን በቀጥታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል።ስለዚሁ ጉዳይ ወይም ጥያቄሪፖርተርጋዜጣ የዜና ሽፋን በወቅቱ ሰጥቶታል።” ይላል ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም (እየሩሳሌም አርአያ)።

ቀጥሎም፤

“በአገር ዉስጥ ከሚታተሙ የኪነጥበብና ማሕበራዊ ነክ የግል መጽሔቶች ሳይቀር ሕብረተሰቡን የሚንቁ ጽሑፎችን ማዉጣት ይዘወል። አንድቢኒያምነኝ ያለ ግበረሰዶማዊ ባወጣዉ መጣጥፍ- በአዲስ አበባ ብቻ 7 ሺሕ (ልብ በሉ ሰባት ሺሕ ነዉ!) ግብረሰዶማዉያን በአንድነት እንደተሰባሰቡና ማሕበር እንደመሰረቱ፤ለሚመለከተዉ የመንግሥት አካል ሕጋዊ ዕዉቅና እንዲሰጣቸዉ ጥረት እያደረጉ መሆኑን (ግብረሰዶማዉያንን (Gay) ገይ በሚገልጽ ሁኔታ በአዲስ አበባ ዕምብርት (በስማቸዉ መሆኑ ነዉ) ትልቅ ናይት ክለብ ለመክፈት አስፈላጊዉ ዝግጅት መጠናቀቁና ለዚህም የሚያስፈልገዉ ገንዘብ በበቂ ሁኔታ መመደቡን፤ አባላቱ ያቋቋሙት ማሕበር የፋይናንስ ችግር የሌለበት መሆኑን፤የበለጠ ለመደራጀት ሲሉ የአባላት ቁጥር በየፊናዉ እየመለመሉና እያበራከቱ መሆኑን እዉቅና ካገኙ በሗላ በስማቸዉ ጋብቻ የሚፈፅሙበት የሃይማኖት ተቋማት (ቸርች) እንደሚመሰርቱ፤ 2000 .. ጀርመን ከሚገኝ ወንድ ጓደኛዉ ጋር የጋብቻ ስነስርኣት አከናዉኖ መምጣቱንበሰፊዉ ከዘረዘረ በሗላ አያይዞምሕብረተሰቡን እያግለን፤ግብረሰዶማዉያንን ማግለል ይቁምእያለ በጽሑፍ ዘላብዷል። ይኸዉ ግለሰብ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ መግብረሰዶማዊያን ማሕበር (ቡድን) እስከ መደራጀት ደርሰዋል። ከላይ እንደጠቀስኩት የመለስ አስተዳደር ምን አቋም እንዳለዉና እንደሚከተል ጠንቅቀዉ የተረዱ ግብረሰዶማዊያን 2000.. ሚሊኒየም በማስታከክሕጋዊ ዕዉቅና ይሰጠንእስከማለትና የመለስ ዜናዊን በቀጥታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል።ስለዚሁ ጉዳይ ወይም ጥያቄሪፖርተርጋዜጣ የዜና ሽፋን በወቅቱ ሰጥቶታል።መጣጥፍ በመጽሔት ያቀረበ ሲሆን በዛው ጽሑፍ ያካተተዉ ተጨማሪ ጉዳይ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የመዝናኛ ክለቦች ተከፍተው በስራ ላይ እንዳሉና ግብረሰዶማውያን በአንድነት ተሰባስበው እንዲዝናኑ ሲባል ታስቦበት የተከፈቱ መሆናቸውን አክሎ ገልጿል።”

ጋዜጠኛ አርአያ በግብረሰዶማውያኑ ዳንስ ቤት ድረስ በመሄድ ያተዘበው ዘገባ ሲያጠቃልል እንዲህ ይላል።

“ነበር።እንደተገለጸዉ አስኳሉ ሸራተን የሆነዉ ወረርሺኝ በይፋ ከከፈታቸዉ የምሽት መዝናኛ መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ። በአካል ጭምር ተገኝቼ ያረጋገጥኳቸዉ ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የሚገኘዉሸገርሕንፃ ሦስተኛ ፎቅ በሰፊ አዳራሽ (ሁለት ቦታ ተከፍሎ) ተከፈተዉሻምፒዮንወይም በሌላኛዉ መጠሪያዉዲቫይንየተባለዉ የግብረ ሰዶማዉያን መዝናኛ በዋናነት ይገኛል። የባሩ ባለቤት በአሜሪካ ለረጂም ዓመት የኖረና 1999.. እንግሊዝ-ለንደን ከተማ ከወንድ ጓደኛዉ ጋርጋብቻመስርቶ እንደተመለሰ ተረጋግጧል፡፤ ለጋዜጠኛነት ስራየ እንዲሁም ባሕላዊ ወረርሽኝ ለመከላከል ባለብኝ ግዴታ በመነሳት ወደተጠቀሰዉ ባር በእኩለ ሌሊት አመራሁ። የገጠመኝ ሁኔታ ከሰማሁት የበለጠ ነበር! በምሽት ደብዛዛ የብርሃን ጨረር የተሞላዉ ይህ ባር እንደነገሩ ሁለት ቦታ ተከፍሏል። እንደ ዊስኪና ሌሎች የአልኮሆል መጠጦች በዉድ ዋጋ የሚቸበቸቡበትና በዲጄ በሚለቀቁ የዉጭ ዘፈኖች ታጅበዉ የሚደነስበት ሲሆን፤ በሌላኛዉ ክፍል ደግሞ እጅግ ከደበዘዙና ብዙም የብርሃን ጨረር ከማይፈነጥቁ አምፑሎች በመታገዝ ግብረሰዶማዉያን የሚፈጽሙት የሚያቅለሸልሽ አፀያፊ ተግባር የሚፈፅሙበት ነዉ። ከሰኞ በቀር በሁሉም የሳምንት ቀናቶች ይህ ወራዳ ተግባር ይፈጸማል።በጣም የሚገርመዉ ፈረንጆች ወንድ ለወንድ ፤ሴት ለሴት ሆነዉ (ካፕል- ካፕል መሆኑ ነዉ) እየተላላሱ በሚያጠይፍ አኳሗን መመልከቴ ነበር።ይሕች ያልታደለች፤ተቆርቋሪ መንግሥት ያጣች አገርድሕነት አሳሯን የሚያሳያት አልበቃ ብሎ፤ የነርሱ ቆሻሻ ባሕል ማራገፊያ መሆኗ ስታይ ያቃጥላልአልኩ በወቅቱ ለራሴ የእኔን ሃሳብና ቁጭት የሚጋራ ድፍን ሙሉ አገር እንደሆነ አልጠራጠርም። በሌላ ቀን ጥቆማ ወደ ደረሰኝ መዝናኛ ስፍራ አመራሁ። ቦታዉ ከቦሌ ትምህርት ቤት ሽቅብ እንደተጓዘቦሌ ኬክ ቤት ያገኛሉ፡ ከኬክ ቤቱ በግምት 200 ሜትር ርቀት ላይ ከመንገዱ ግራና ቀኝ በመደዳ ከሚገኙ በርካታ ባር ቤቶች ከቀን በኩል ቅድሚያ የሚያገኙትላጌቶየተባለዉን የግብረሰዶማዉያን መናኻርያ ባር ነዉ። በሚታይ ጉልሕ ጽሑፍ የመዝናኛዉ ታፔላ ተሰቅሏል። በግራዉንዱ አልፈዉ ባሩ ወደ ሚገኝበት አንደኛ ፎቅ ይደርሳሉ። ከእነሱ በቀር ሌላ ተጨማሪ ሌላ ሕንጻ የለም። የባሩ ባለቤት አስመራ የቆየናላጌቶየሚል ተመሳሳይ መጠሪያ የሰጠዉ መዝናኛ ከፍቶ እስከ ዘጠናዎቹ አመታት አጋማሽ ሲሰራ እንደቆየ ከራሱና ከኤርትራዉያን ጭምር ማረጋገጥ ተችሏል። አስመራ ያለዉ መንግስት በግብረሰዶም ዙርያ ጠንካራ አቋም ያለዉ ሲሆን በዚህ ርካሽ ተግባር ተሰማርቶ የተገኘ ማንኛዉም ግለሰብ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በሞት እንዲቀጣ ይደረጋል። ይህ ግለሰብ ሻዕቢያ ሲደርስበት አምልጦ በየመን በኩል አዲስ አበባ ይገባል። አስመራም አዲስ አበባም የሚታወቅበት መጠሪያ ስሙላጌቶበባሩ ስያሜ ነዉ። ይህ ማለት ( Gay-ጌይ) የሚለዉን ለማመላከት ነዉ የሚሉ አሉ።በየዕለቱ በዚህ ባር አካባቢ ፖሊሶች አይጠፉም። ግለሰቡ ኤርትራዊነቱን ሸሽጎሻዕቢያ ሊገድለኝ ሲል ያመለጥኩ የትግራይ ተወላጅ ነኝእያለ ከማደናገሩ በተጨማሪ ሴትጥንዶችወይምሌዝቢያንበብዛት አይጠፉም። ለመግለጽ የሚቀፉ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የሚታየዉ ኤርትራዊዉ እና ግብረሰዶማዉያኑ አባላቶቹ በሚለቀቀዉ ዘፈን (ዘፈኖቹም የነጭ እና የሻዕቢያ ናቸዉ)ጣልቃም አየአቅጣጫዉአሞሬ”…አሞሬየሚሉት ቃላት ይወረዉራሉ። ትርጉሙን ስጠይቅፍቅረኛየማለት እንደሆነና “Gay”ዮቹ ቋንቋ እንደሆነ ተረዳሁ። ሽንት ቤት ሳመራ ባየሁት ነገር አስታወኩ! ወዴት ያመራን ይሆን?” በማለት ደምድሞታል።

በዚህ የባህል ወረራ መበስበስ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር ቁጣ ወርዶ መለስ ዜናዊን  እንደ “ሎጥ” ዘመን ሕብረተሰብ ዋና አበስባሽ መሪው መለስ ዜናዊን በሞት ቀጥቶታል።




በአገራችን ውስጥ በጀርመን ፊልም ሰሪዎች ቅንብር አንድ የሃይማኖት ሴራ ለመፈጸም ሙከራ ተደርጎ ነበር።


ማርያም መግደላዊት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የተለየ ፍቅርና ፆታዊ ግኢነኙነት እንደነበራት የሚገልፀው እየሱስ አልዓዛርን ከሞት በተአምር ማስነሳቱ ተጥሶ በአፉ -ለአፍ ሳይንሳዊ መፍትሔ ተጠቅሞ እንደሆነ ያሳያል። ይባስ ብሎ ሓዋርያት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ሲሰሩ ይገልጻል።

በፊልሙ ስክሪፕት ላይ ሳይጻፍ (በተንኮል ሰናሱሩን ለማሳለፍ) በልምምዱ (ተዋናዮቹ እንዲለማመዱት የተደረገው) ወቅት የተከሰተው አስደንጋጩ ክፍል ደግሞ እየሱስን አሳልፎ የሸጠው ይሁዳ ጋር ከንፈር ለከንፈር እንዲሳሳሙ የተደረገበት አስደንጋጭ ክስተት ለፊልሙ ተመርጠው በነበሩት በኢትዮጵያ ገዳማት እና በተክርስትያናት ቅጥር ግቢ ውስጥ ድርጊቱ እንዲቀረጽ ተደርጎ በጀርመንኛ እና  

በአማርኛ ቋንቛ አንዲሆን በተንኮለኞዩ በጀርመኖች እና ተባባሪ ኢትዮጵያዊያን ፊልሙ አንዲቀረጽ ተዶልቶልን እንደነበር መዲና የተባለው ጋዜጣ ታህሳስ 2004 ዓ.ም ዜናው አውጥቶት እንደነበረ ይታወሳል። ሆኖም በጠንካራ አገር ወዳድ እና ሃይማኖታቸውን በሚያከብሩ ወገኖች ሴራው ከሽፏል። ክርስቶስ ግብረሰዶም ፈጻሚ እንደነበረ እና ኢትዮጵያዊ ንም አጸያፊው ተግባር እንዲከተሉ የሚገፋፋ የሰይጣኖች ሴራ ነበር። የወያኔ ስርዓት የላመጣብን ጉድ የለም

በጣም የሚገርመው ደግሞ በዚህ አስጸያፊ ግብረሰዶም ስነ ምግባር የሚያበረታቱ ድረገጾች እና በግብረሰዶማዉያኖቹ የታተሙ መጽሐፍቶች ቢኖሩ ስፈልግ ፤ ይህንን አግኝቻለሁ።EthiopiaLGBT.com (GBT የሚለው ገይ፤ባይሴክሹዋል፤ እና ትራንስ ጀንደር ማለት ነው)እና Ethiopiangay.com  እና ከዚህ ሌላ  “የሰዶም ነብሳት” የሚል የግብረሰዶም አበረታታች መጽሃፍ ታትሟል። መለስ ዜናዊ ሲሞት ከልብ ካለቀሱለት አልቃሾቹ እነኚህ ክፍሎች አንደኞቹ ክፍሎች ነበሩ። የዚህ ጉደኛ መጽሑፍ ደራሲ ቃለ መጠይቅ ለማንበብ አድራሻ ገብታችሁ አንብቡት። በጽሑፏ ላይ ወደ 500 የሚሆኑ የወንድ ሸርሞጦች አዲስ አባባ እንዳጣበቧት ይጠቁማል። “መሃረነ ክርስቶስ!!http://www.ezega.com/news/NewsDetails.aspx?Page=news&NewsID=2805

መደምደሚያ፡

  አሁን በቅርቡ “ጎልጉል” በተባለ የህዋ ሰሌዳ ጋዜጣ “ቀጭኑ ዘቄራ” በተባለ የብዕር ስም የተዘገበ የዛሬቱ ኢትዮጵያ ወጣቶች እና የወያኔ ባለሥልጣናት እና ካድሬዎቻቸው የተላበሱት የበሰበሰ የመንፈስ እና የባህል ወረርሺኝ በየዝግ ቤቶች እየዞረ የታዘበው አስገራሚ ዘገባ እንድትመለከቱት ላስነብባችሁ እና ልደምድም።

በሬ ለምኔየፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙበሬ ለምኔቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም።
 





………እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው።……አንዱንሮዚናዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው ከተንበሪውን የሚያስከፍቱ ደንበኞች ብቻ ናቸው።ደንበኞችስል እንግባባለን ብዬ አስባለሁ።

ሮዚና ወገቧ ሸንቃጣ፣ አንጀት የሚባል ነገር ያልሰራባት፣ ዳሌዋ ሰፊና ክብ፣ ሽክ ያለች፣ አንገቷ ውድ ነገሮች የሚቀመጡበት፣ ሽታዋ የሚያውድ፣ ዓይነ ርግቧ በቀለም እንደ ስዕል የሚዋብ፣ ሳሳ ያለ ልብስ የምትለብስ፣ እንግዳዎቿን በምትዘጋባቸው ቤት እየተዘዋወረች የምትቀበል አራዳ ነች። አስተናጋጆቿ በጣም ትንንሽ ልጆች ሲሆኑ ጸሃይ አይነካቸውም። ስራቸው ለሮዚና እንግዶች መስተንግዶ ሳይስተጓጎል መስጠት ነውየሚጠጣ ያቀርባሉ፤ ፍም እሳት አዘጋጅተው ቡና ያፈላሉ፤ ለማሟሟቂያ የቡናው ስነ ስርዓት በየክፍሎቹ ከተከናወነ በኋላ የጫቱ ሙቀት እየጨመረ ሲሄድ ሺሻ ይለኮሳል። ህጻናቱ ሺሻ እያሞቁ ደንበኞቹን ለማስተናገድ ከቡና ማፍያው በርጩማ ተነስተው ፍራሹ ላይ ሲወርዱ ከአባታቸው ጋር በሰንበት የሚጫወቱ እንጂ የስራ ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም። ጫት እየቀነጠሱ፣ ሺሻ እያሞቁ ደንበኛቸውን ባፍ ባፉ መከደም ዋና ስራቸው ስለሆነ ተክነውበታል።……..ተጋብዤ የተመለከትኩት ክፍል የነበረችው ልጅ ሪታ ትባላለች። ንግግሯ የቀምጣላ ልጆች አይነት ነው። ስትስቅ አማርኛ አይመስልም። ጠይም ቀለሟ የጸዳ፣ ለጋ ነች። እንደ ጋባዤ አገላለጽጥፍሯ ይበላል ዕድሜዋ ከአስራ አምስት አይበልጥም። ቡና እንደጨረሰች ስስ ነገር ለብሳ ደንበኛዬ ጎን ቁብ አለች። መቃም ትችልበታለች። ጫት ላኪዎች በትዕዛዝ የሚልኩትን ጫት ትጠጣዋለች። ያለ ምንም ማጋነን የቅጠል አበላሏን ፍየል ብታየው በቅናት ምላሷን ትቆርጠዋለች። ምን አደከማችሁ ቅማ ታቃቅማለች። አልፎ አልፎ ሮዚና ለጉብኝት ብቅ ብላ ስትመለስ ቤቱን ታውደዋለች።ምርቃናው ሲጨምር ወዳጄ ቀስ በቀስ ከልጅቷ ጋር ተጣበቀ። እጆቹም ሁለመናውም እሷ ላይ ሆነ። በቃ ደረቱ ላይ ጣላት። ደረቱ ላይ አንጋሏት ሺሻውን ይምጋል። ብቸኝነቱ ሊውጠኝ ሲደርስ መሄድ አለብኝ ብዬ ተነሳሁ። ፒኮክ እንደምጠብቀው ነገርኩትና ተለየሁት። ህጻኗን ልጅ ደረቱ ላይ አንጋሏት ስመለከት ልጄን አቅፌ ሳስገሳው ትዝ አለኝ። የሚያስገሳት እንጂ የሚዳራት አይመስልም። እንዲህ ያሉትን ትውልድ አምካኝ ቤቶች ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪና ህግ አወጪዎቹ በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶች በሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንና ሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደማሉ። ዝግ ቤቶች

ያራዳ ልጅበማለት ሳንቲም የሚለምኑ፣ ሎተሪ የሚያዞሩ የጎጃም ጉብሎች፣ የመንገድ ላይ ነዋሪዎች፣ ቀበሌና አድራሻ የሌላቸው ወንድምና እህቶች፣ ኑሮ ያዞራቸው የኑሮ ሰለባዎች ይታያሉ። አዲስ አበባ ሁሉን ተሸክማ እየመሸላት ይነጋል።
 

አፕሬቲቬን እየቀነደብኩ ስለ ሮዚ ቤት እያሰብኩ ቆዘምኩ። ቤቱ ውስጥ ያሉት ህጻናት የተመረጡ ናቸው። መልምሎ የሚያመጣቸውና ስልጠና የሚሰጣቸው አለ። በህጻንነታቸው ተከትበው ሺሻ ስር ሲርመጠመጡ በዛው ሱስ ይዟቸው ገደል የከተታቸው፣ ኖረውም ተስፋ ያጡ፣ ታመው የፈረደባት እናት እጅ የወደቁ አሉ። አገሩ እንዲህ ሆኗል። የኢትዮጵያ ህዳሴና የኢኮኖሚ እድገት ያተረፈው እንዲህ ያሉትን ዜጎች ነው። በርግጥ አገሪቱ ኢኮኖሚዋ አድጓል። ያደገው ግን ለዝግ ቤት ተጠቃሚዎች እንጂ ለሌሎች አይመስልም። እድገቱ የሚታያቸው በዝግ ቤትና ቤታቸውን ለሌሎች ዘግተው አገሪቱን እያለቡ ላሉት ይመስላል።

በሃሳብ እየቀባጠርኩ፣ አፕሬቲቬን እየሳብኩ ቆየሁ። ወዳጄ ተመችቶታል መሰል አልመለስ አለኝ። ፒኮክ ስለሰለቸኝ ደወልኩለትና እንስራ እንገናኝ አለኝ። ወደ እንስራ አመራሁ። እንስራ ደግሞ ሌላ ትዕይንት አለ።

እንደምን ከረማችሁ አሁን እንስራ ነኝ። እንስራ ለማታውቁ ላስተዋውቃችሁ። እንስራ ቦሌ ቴሌ አካባቢ የሚገኝ የምሽት ንዳድ ቤት ነው። በመለስ ሞት ምክንያት ተፋዞ ከርሞ ነበር። እንስራ ሲገቡ በጡንቸኞች ይዳብሳሉ። ፍተሻ መሆኑ ነው። እንስራ በር ላይ ተዳብሰው ሲዘልቁ ቀለሙ አይን ይወጋል። የደም ጢስ የሚጨስበት ይመስላል። እንስራ ውስጡ በዲጄ ይናጋል፤ ይነዳል። በምድር ቤት ውስጥ የሚደለቀው ሙዚቃ ከተለያዩ አቅጣጫ ከሚፈሰው የተደበላለቀ ቀለም ጋር አንድ ላይ ተዳምሮ የሲኦል ቤተ ሙከራ ይመስላል። መድረኩ ላይ እየተገመዱ የሚላቀቁት ተዋንያኖች እንግዳ ያስደነግጣሉ። ቁመታቸው ረጃጅም የሆኑ እንስቶች የተጠና ዳንስ ይተውናሉ።

እርቃናቸውን ያለ ልብስ የሚናጡት እንስቶች ሃፍረታቸው ላይ የቻይና ማራገቢያ የምትመስል አነፍናፊት ከመለጠፋቸው ውጪ ሁሉም ነገር እንደ አዳምና ሄዋን እንደ ድሮው፣ እንደ ጥንቱ ነው። እርቃን!! ዳንሱብልግና ተኮርይባላል። ወገብና መቀመጫን በማላመጥ ሲወዘውዙት ማየት ይመስጣል።ኮረኮንችየሚባለው ምንነቱ የማይታወቀውን አልኮል በሉት ዊስኪ እየተጋቱ አብረው የሚያውካኩትን ለተመለከተ አገራችን ውስጥ ችግር በቃል ደረጃም የሚታወቅ አይመስልም።
ከየአቅጣጫው የሚወርደው ባለቀለም ጨረር የሰውነታቸውን ቀለም እንደ እስስት ይቀያይረዋል። እየነደደ ወርዶ የሚቀንሰው ብርሃን ውስጥ ኮሮኮንች ያሳበዳቸው ይዘላሉ። አንዳንዶች መድረኩ ላይ ሳያስቡት ደርሰውበት ዓይናቸውን ከእምብርት በታች ቸክለው ይቅበዘበዛሉ። አንዳንዶች ጥንድ ሆነው መጥተው ብቻቸውን ያሉ ይመስል በሜዳ ላይ ወሲብ መሰል ዳንስ ተማርከው ዓይናቸው ሲቅበዘበዝ አለመስማማት የሚፈጠርበት አጋጣሚ አለ።

ስድስት የሚሆኑት ዳንሰኞች አጎንብሰው መቀመጫቸውን ሲወዘውዙት፣ ተሸብርከውእንካ፣ አምጣሲሉ፣ ሙዚቃው ሲያቃጥርየኮረኮንቹኮታ ሳይታወቅ ይበረታል። ከቦሌ አካባቢና ከዩኒቨርሲቲ መንደር የሚዝናኑ መስለው የሚነግዱ በተመሳሳይ ራቁታቸውን ከጊዜያዊ ጓደኞቻቸው ጋር ያስነኩታል። የዩኒቨርሲቲ ዳይ ካነሳሁ አንዴ ወደ አንጋፋው የዝሙት ገበያ ናዝሬት ፔንሲዮን ላምራችሁ።

ናዝሬት ፔኒስዮን እንደ ዛሬው ሳይሆንሻሞየሚባልበት ለሞት መጣደፊያ አልኮል መቸርቸሪያ ባር ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን አካባቢው የጫት መቃሚያና የድለላ ስራ እምብርት በመሆኑ ሰው ስፍሩ ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን በብዛት የንግድ ስራ ኮሌጅ ተማሪዎች እንደሚታደሙበት አንድ ወቅት መረጃዎች በይፋ ተሰራጭተው ነበር።

በተለይ ከክፍለሃገር የሚመጡ ተማሪዎች ከመንግስት የሚሰጣቸው ወርሃዊ ድጎማ ለቀለብና ለማደሪያ ስለማይበቃቸው ናዝሬት ፔንሲዮን ለስራ መሰማራታቸው ያደባባይ ወሬ ነበር።ይሞታል ወይ?” ያለች ተማሪም ነበረች። ውዱ መሪያችን፣ ነብሳቸውን ይማረውና፣ ስጋቸውን እየሸጡ የሚማሩ ተማሪዎችን አስተዋውቀውናል። እኚህ መሪያችን ናቸውልማታዊ ሴቶችን አፈሩ፣ ለሴቶች ልዩ ትኩረት አዘነቡየሚባሉት፣ እየተባሉ ያሉት። የኮሜርስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ወደ ሀዋሳና አርባ ምንጭ ችግሩ ያስከተለው ቀውስ ቤተሰብን አንገት ማስደፋት የደረሰበት ደረጃ ደርሷል።

ቤተሰብ ልጄ ተምራ ተመረቀች ብለው ሲጠብቁ አጅሬው የቀሰፋቸው ጥቂት አይደሉም። ሃዋሳ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የቡና ቤት ኮማሪቶች ገበያዬንወሰድሽብኝ ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ሲገቡ ማየት የተለመደ እንደሆነ ሀዋሳ በነበርኩበት ወቅት ያስተዋልኩትና ያረጋገጥኩት ጉዳይ ነው። አንዴ እኔው ራሴ አብራኝ እንድትጠጣ ለጋበዝኳት ልጅ ይህንን ጥያቄ አቅርቤላትገበያችንን ዘጉትበማለት የስድብ ናዳ እያወረደች ነበር ሁሉንም ያጫወተችኝተማሪዎቹን ማለቷ ነበር። የሴቶች ተሳታፊነት አደገ ይሏል እንዲህ ነው። ነብስ ይማር።

ወደ እንስራ ልመልሳችሁ። እንስራ ጥቂት እንደቆየሁ ወዳጄ ያችኑ ልጅ አንጠልጥሎ መጣ። መጨለጥ ቀጠለ። አስቀድሞም ሲጠጣ ስለቆየ ለመስማት ጊዜ አልወሰደም። እንደውም እንደ አዲስ ጀበና መንተክተክ ጀመረ። ህጻኗን ከፊትለፊቱ ወትፏት በቁሙ እንደውሻ ይቀነዝራል። መብራቱ ስለሚመች ስጋት የለም። በቁሟ በዳንስ እያስመሰለ ፈትጎ ሊገላት ምንም አልቀረም። ይህ ሰው ያለውን ኃላፊነት እዚህ ከሚያደርገው ተግባሩ ጋር በማገናዘብ ሳስበው አመመኝ። እንዲህ ያሉ ብዙትልልቅ ሰዎችይመሩናል። በችጋር ይጠብሱናል። ሲሞቱ በደቦ ያስለቀሱናል። በጀት ከልክለው በረሃብ ያቃጥሉናል። ሲሞቱ ደግሞ በጀት መድበው ደረት ያስመቱናል።ያገራችሁን ህዳሴ ከእኛ ጠብቁእያሉ ያለ ሃፍረት ይሰብኩናል። አጽማቸውን እናመልክ ዘንድ ይመኛሉ። ከወዳጄ ጋር የትና እንዴት እንደተገናኘን አስታውቃለሁና ተረጋጉ። አሁን በፈጣሪ እጅ ላይ ሆኖ እየኖረ እንደሆነ፣ ከቤቱም እንደማይወጣ ሰምቻለሁ። ሮዚ አራዳዋ አለች እንዳማረባት። ህጻናቱ ግን ሰላም እንሰንብትና ሳምንት እንገናኝ!!”
መለስን ከቀጣ የፈጣሪ ቁጣ ያድነን። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com
www.ethiopiansemay.blogspot.com