·
·
ጉድ ስማ ሙሽሮቹ ከነ አጃቢና ሚዜወቻቸው ታስረዋል
Posted on Sofanit Love Asamnew facebook (source Zemedkun Bekele)
Ethio Semay
Ethio Semay
የፋሺስቱ የአፓርታይድ አብይ አሕመድ የኦሮሞ መንግሥት ዱርየ (ጌስታፖ )ወታደሮች ዜጎች በሠርጋቸው ዕለት ሓዘን እንዲለብሱ አድርጎአቸዋል። ናዚው አብይ በጊዜው ካለስቆምነው ሌላ ጉድ ያሳየናል! ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ
|
ሌሎች ዘግናኝ የግድያ ታሪኮች ሳሰናድ ስላመሸሁ የነገ ሰው ይበለን። በግድ ስላሰለሟቸው ክርስቲያኖች፣
ሀገር ለቀው ስላስወጧቸው ዐማሮች፣ በገጀራ ስለከተፉት ህጻን፣ የገደሏቸውን ዜጎች ዕጣ ተጣጥለው ስለወሰዷቸው ቤቶች እሱን ሳወራ
ነው ያመሸሁት። በመሃል ይሄ መጣ። በሉ እያነበባችሁ ስለ ራሳችሁ አስቡ። ጮሆ መሳቅ ሊያሳስር ይችላል። አዳሜ ይሄን እወቅ ።
ፎቶው ሙሽራውና ሙሽሪት ዘብጥያ ገብተው የተነሳ ፎቶ ነው።
•••
ሰርጋቸው ከትናንት ወዲያ እሁድ ዕለት ነበር። ዛሬ ማክሰኞ ደግሞ ያው እንደተለመደው በሀገሩ ወግና
በባህሉ መሰረት የሙሽሪት ቤተ ሰቦች መልስ የሚጠሩበት ዕለት ነው። ይህ ቀን በሙሽሪት ቤተሰቦች ዘንድ ታላቅ የደስታ ቀን መሆኑ
ይታወቃል።
•••
ቦታው አዲስ አበባ ጀሞ ቁጥር 3 ነው። ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መጥተዋል። ወዳጅ ዘመድ ቦታ
ቦታውን ይዟል። መጠጡም፣ ምግቡም በየዓይነቱ በመልክ በመልኩ መዘጋጀቱም ተነግሯል።
•••
የሚጠበቁት ሙሽሮች መጡ። አቧራው ጨሰ ተዘፈነ። እልልታ፣ ጭፈራም ሆነ። ከበሮው ተመታ፣ እልልታው
ጭፈራው ደራ። በመሃል የሙሽሪትና የሙሽራውን ደስታ ልዩና የሚታወስ ለማድረግ ሲባል የመልስ ጥሪው ላይ ርችት ተተኮሰ።
ድብልቅልቅ ያለ ደስታም ሆነ። አበቃ።
•••
ቆይቶ ፎሊስ ነፍሴ ከተፍ አለ። ዓይናቸው ደም ለብሶ አራስ ነብር መስለው ነው የመጡት አሉ። ይቆጣሉ።
ማነው ሙሽራው? ማነው ሙሽሪት? ጠየቁ። ተነገራቸው። አንዴ ይፈለጋሉ ያናግሩን አሉ። ሰው ግራ ተጋባ። ለምን ብለው ቢጠይቋቸውም
አሻፈረን አሉ። ሙሽሪትና ሙሽራው ጉዳዩ ተነግሯቸው ከአዳራሹ ወጥተው ፖሊሶቹን አናገሯቸው።
•••
ወደ ፎሊስ ጣቢያ ቀጥሉ አሏቸው ፎሊስ ነፍሴ። ደነገጡ ሙሽሮች። ለምን? ጠየቁ ሙሽሮች። ቀጥሉ ቀጥሉ።
ተቆጡ ፖሊሶቹ። ሁሉም ደነገጡ። ቢባል ቢሠሩ ትእዛዝ ትእዛዝ ነው ቀጥሉ ተባሉ። ግራ የገባው ነገር። ሚዜዎቹም ጠየቁ ለምን
ይሄዳሉ? ፎሊስ ነፍሴ እናንተም ቀጥሉ።
•••
እልህ ቁጣቸው ሲታይ ነገሩ ወደ ሌላ የከፋ ነገር ሊሄድ ስለሆነ ሽማግሌዎች መሃል ገብተው፣ ስለ ሙሽራ
ክብር፣ ቢያስረዱም ኧረ እነሱ እቴ ቀጥሉ ብቻ ነው። ሙሽሮቹ ከነ ሚዜዎቹ ወደ ጣቢያ ሄዱ። ሰርጉ በአንዴ ሀዘን ቤት ሆነ።
•••
የክሳቸው ምክንያት ወንጀላቸው ተነገራቸው። ወንጀሉም ርችት ተኩሳቹሃል አሏቸው። ታዲያ እኛ ምን
አገባን። እኛ እንግዶች ነን፣ መልስ ተጠርተን ነው የመጣነው ቢሉ ማን ሰምቷቸው። በዚህ ተልካሻ ሰበብ ምክንያት በህይወታቸው
አንድ ጊዜ ብቻ የሚገጥማቸውን የደስታ ምሽት ተረኞቹ ነጠቋቸው።
•••
ሙሽሮቹ ከምሽቱ 2 : 00 ጀምሮ ታስረዋል። 2 እህታማቾች ሙሽራውና 2 ሴት ሚዜዎች ከአጃቢዎች ጋር
ታስረዋል። ደጋሹ አቶ ፍጹምም ታስረዋል። ለሽምግልና ጣቢያ የሄዱትንም በሙሉ አስረዋቸዋል። የጣቢያው ኃላፊ ከበላይ በመጣ ትእዛዝ
ስለሆነ እዚሁ ነው የምታድሩት መባላቸውን የታሳሪዎቹ ቤተ ሰቦች ይናገራሉ። ነገርየው ደስ አይልም ነው የሚሉኝ የሰርጉ ተጋባዥ
የመረጃ ምንጮቼ።
••• ይንጋና ደግሞ ጠዋት የሚሆነውን አብሮ ማየት ነው።
••• አፓርታይድ ኢዝ ካሚንግ አለ ማንዴላ ነፍሱን ይማረውና !!
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥቅምት 19/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
No comments:
Post a Comment