Wednesday, October 28, 2015

ግንቦት 20 በትግራይ ፋሺስቶችና በኢትዮጵያ አርበኞች መሃል የተደረገው የማይረሳው የሰንደቅ ዓላማው ግብግብ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ)


                                                                          
ግንቦት 20 በትግራይ ፋሺስቶችና በኢትዮጵያ አርበኞች መሃል የተደረገው የማይረሳው የሰንደቅ ዓላማው ግብግብ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ)
ጣታቸውን ቀስረው የሚታዩት ሻለቃ አድማሴ ናቸው። ቀጥለው ያሉት ስማቸው ያልተጠቀሰ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
                                                                         


ጸረ ኢትዮጵያው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሪ የነበረው ወደባችንን ለጠላት አስረክቦ፤ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ወደ ግብአተ መሬቱ የገባው ባንዳው መለስ ዜናዊ
“……ድሮም ነበሩ፤ ዛሬም ቢሆን መንግሥታት አሉ። መንግሥት ምንድነው? እንዲያው ልብ ብላችሁ አድምጡኝ። የሕዝቦችን መሞት ልነግራችሁ ነኝ። መንግሥት የክፉዎች ሁሉ ክፉ አውሬ ነው። ሲዋሽም እንዲያ ነው። “መንግሥት ማለት  ሕዝብ ማለት ነው።” የሚል ቅጥፈት ከአንደበቱ አይጠፋም። በሕዝቡ ላይ ያዘጋጁትን ወጥመድ ነው መንግሥት የሚሉት። ልዩ ልዩ ሕዝቦች ይህንን ቋንቋ ይኖራቸዋል። ሕዝቦች ይህን ቋንቋ መረዳት አይችሉም። መንግሥት ግን በሁሉም ቋንቋዎች የሚዋሽ አፍ ነው። የሚናገረው ሁሉ ውሸት ነው፤ ንብረቶቹ ሁሉ የተሰረቁ ናቸው። የሚናከሰውም በተሰረቁ ጥርሶቹ ነው። ሆዱ እንኳ ሀሰተኛ ነው።

በየአገሩ እልፍ ኣእላፍ ሰዎች ይወለዳሉ። መንግሥት የተፈጠረው ለኒህ እልፍ ኣእላፍ ሰዎች ነው። እንዴት እንደሚያባብላቸው ብቻ ተመልከቱልኝ። ሲያላምጣቸው፤መልሶ መላልሶ ሲያኝካቸው አያችሁልኝ? እልፍ ኣእላፍፎችን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። የብልሆችን ሀብትና ፈጠራ ቀምተው ይወስዳሉ። የዘረፉትንም ባህል ነው ይላሉ። ሰው ሁሉ ቀስ በቀስ ራሱን መግደል የያዘበት አገር ይሏል መንግሥት ነው። (1)

ከወራሪ ጣሊያን በከፋ መልኩ፤ በመንግሥትነት ስም ገብቶ፤ የአገራችን ኢትዮጵያን አንድነትና ታሪክ እንዲሁም ልዓላዊነታችንን በሚጻረር መልኩ፤ በመለስ ዜናዊ የተመራው “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” የተባለው ይህ የጎሳ ድርጅት፤ ግንቦት 20/ 1983 ዓ.ም ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር፤ ባለፈበት ገጠርና ከተማ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ አውርዶ፤ በምትኩ የወያኔን ሰንደቃላማ በመስቀሉ፤ ሕዝቡ በመቆጣቱ፤ በዚህ ፋሺስታዊ ድርጅት እና በኢትዮጵያ አገር ወዳድ አርበኞች መካከል ስለ ሰንደቃላማ ጉዳይ ተነስቶ በጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎችና በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጎራ ተለይቶ የታየው ግብግብ፤ ታሪክ “ሀ“ ብሎ የዘገበው የመጀመሪያው የትግል ምዕራፍ የሰንደቃላማችን ጉዳይ ነበር ። (2)  
የዛሬ ትችቴ በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ነው፡
                         
                               ከፍል -ሀ-
ባለፈው ሰሞኖች ወያኔ “የባንዴራ ቀን” እያለ ጣሊያን ባሰመረለት ዕቅድ ተጉዞ የአትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ህልውና እና ክብር ሲያረክስ ተመልክታችሁ ይሆናል። ይህ ለዓይን እና ለልቦና የሚሰቀጥጥ “ባንዳዊ/ቅጥረኛነት” ስራ ምንም የማያውቁ ታዳጊ ወጣቶችን እና ሴራው በቅጡ ያልተረዱ ጀሌዎቹን አሰልፎ 44 ወያኔ ሰራሽ ባንዴዎችን እያውለበለበ በኢትዮጵያ ሉአላዊ ክብር ሲያሾፍ በድረገጾቹ አማካይነት የለጠፋቸው ፎቶግራፎች አይታችሁ ይሆናል።

ይህ ቅጥረኛነት ሴራ የጀመረው ወያኔ ከትግራይ በረሃ ገስግሶ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የኢትዮጵያ ብሔራዊ/አገራዊ ሰንደቃላማን ሳይሆን እንደ ባዕድ ወራሪ፤ ጣሊያን ይመስል የተለየ መልክና ቅርጽ ያየዘ የራሱን ባንዴራ እያውለበለበ ነበር በግንቦት ወር ሴራው “ሃ” ብሎ የጀመረው። ሲኣይኤ መንግስቱ ሃይለማርያምን ወደ ዝምባብዌ በሰላም ካሸጋገረ፤ ከዚያች ወር ጀምሮ በስምምነቱ መሰረት ‘ወያኔዎች’ በሩ ክፍት ከተደረገላቸው በሗላ ኢትዮጵያን ‘በአፈሙዝ’ ተቆጣጥረው ትኩረታቸው በሰንደቃላማ፤በተዋህዶ ርቶዶክስ ክርስትያን እና በአማራ ማሕበረሰብ ላይ ዘለፋቸውን ማነጣጠር ጀመሩ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በየአመቱ ግንቦት ወር ሥልጣናቸውን ለማስቀጠል ሴራቸውን የሚፈትሹበት ወር አድርገው ያዩታል። በተቀናጀ ዝርፊያም በምርጫ አሸነፍን ብለው ሕሊናቸው ስተው በዕርዳታም ሆነ ከአገሩቱ የሚዝቁት የንግድ እና የተፈጥሮ ሃብት  ከሚገኘው ገቢ በሺ የሚቆጠር ዶላር፤ ለዊስኪ እና ለቁርጥ ስጋ በየሸራተን ሆቴል እና በዓለም ዙርያ ባሉ የወያኔ ዲፕሎማቲክ ጽ/ቤቶች ወጪ እየተደረገ በፈንጠዚያ ያበዱበት ጊዜም ነው። ሰሞኑ ደግሞ ስለ ባንዳዊ ባንዴራዎቻቸው ሲለፍፉ ሰንብተዋል።

በሌላ ጎራ ደግሞ በህዝባዊ ግምባር ኤርትራ/ሻዕቢያ/ እና በውስጠ ሴረኞች መንግስታት በገንዘብ የሚታገዘው፤ “የግንቦት 7 እና የሻዕቢያ ቱልቱላ” ብለው አገር ወዳዶች የሚጠሩት ራሱን “ኢሳት” ብሎ የሰየመ ራዲዮ እና ቴ/ቪዥን ጣቢያ፤ በሞሳድ፤በሲ አይ ኤና በሻዕቢያ አፍቃሬ ግለሰቦችና በጸረ ኢትዮጵያ የታጀበ “ኤርትራዊ/ሻዕቢያዊ” አጀንዳ በማዘጋጀት ሻዕቢያዊው፤ ኢሳያስ አፈወርቅንና ኤርትራን እንደ “አገር” ለማዳን ፕሮፓጋንዳ ሲሰራ መሰንበቱን የታዘባችሁ ይመስለኛል። ይህ ከብዙ አመት በፊት የጀመረው ካፈርኩ ላልመለስ ባዩ እንደዛው እንደ “ይሁዳዊው” ካሳ ከበደ፤ ስለ ሻዕቢያ በጎነትና አጀንዳ ሽንጡን ገትሮ በየመድረኩ የሚቀደደው በግንቦቱ ሰውየ “በንአምን ዘለቀ”፤በሻዕቢያ ካድሬዎች በእነ ሶፊያ ሃብተማርያም


ሲሰራበት የነበረና አሁንም እየቀጠለ ያለው ጸረ-ኢትዮጵያ አጀንዳ በአዳዲስና ነባር እንሰሳዎች የወጣቱን ሕሊና የማጠብ  ዘመቻ ቀጥሏል። አጀንዳው አፍቃሬ ሻዕቢያ ኢትዮጵያዊያንን


(ከላይ በመጀመሪያ የሚታየው ፎቶግራፍ ይሁዳው ካሳ ከበደ ነው።ካሳ ከበደ፤ የሻዕቢያ የኢሳያስ አፈወቀርቂ ታሪክና ተክለ ሰውነት አሳማሪ ሆኖ የኢሳያስ ለኢትዮጵያ በጎ አሳቢነት መቆሙን ሽንጤን ገትሬ እከራከርለታለሁ በማለት ሕዝባችን በወንጀል የሚከሰውን ባለ ብዙ ገበናው ለኢሳያስ አፈውርቂ ጥብቅና ለመቆም ሽንጡን የገተረ ሰው ነው።  ከዚያ ቀጥለው ያሉት በየጊዜው ንግግራቸውን በማምታታት አድማጮቻቻውን ግራ በማጋባት ከኦነግ ፤ ከኦብነግና ከሻዕቢያ ጋር ጭራቸውን በመቁላት የታወቁት አዲሶቹ  የጠላት “ሳብቨርሲቭ” ዘመቻ  አስፋፊዎች  ከቀኝ ወደ ግራ “ዶከተር ዜሮ/0/” በመባል የታወቀው “ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ አቅረቦ አያውቅም” ብሎ ወጣቱን ለማሳሳት የደሰኮረ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውና  አንገቱን አጎምብሶ እየከተበ ያለው የግንቦት 7 “ የሻዕቢያ አድናቂ’  “ታጋይ” ንአምን ዘለቀ ነው ።)

ያካተተ፤ በወያኔ እግር ለመተካት የተደረገ ሕቡዕ ሳይሆን ግልፅ የሆነ “የግንቦት 7’ ፤ የ ሲ አይ ኤ እና የሻዕቢያ ታላቁ ሴራ  እውን ለማድረግ በኢትዮጵያ ክብርና እና ሉዓላዊነት ለመቋመር “የዲሞራላይዘይሽን” ዘመቻቸው በሕዝባችን አስተሳሰብ ለውጥ እንዲኖር የውጭና የውስጥ ያነፈነፉ ተውሳኮችን ወደ ሕዝባዊ መድረክ በመጋበዝ ተበራክተው ብቅ ያሉበት አጀንዳ ነው።

የመጀመሪያው የሕሊና አጣባው የጀመረው፤ “ኢሳያስን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ ተደርጎ እንዲታይ የተሰበከበት”፤ ሁሌም እንድትጠነቀቁበት የማስጠነቅቃችሁ “ሳብቨርሲቭ” ተብሎ የሚታወቀው “ያስተሳሰብ/የሃይማኖት/የባሕል/የአመጋገብ/የቋንቋና ሉአላዊ የድምበር አዋሳኝ እሴቶች በሚጎዳ መልኩ ለውጥ እንዲኖር፤ ሕዝባችን ከያዘው ትክክለኛ አቅጣጫ ለቅቆ ለጠላቶች ሸብረክ እንዲል” ፤ አዲስ የሚመስል ጠላቶች በሉአላዊነታችን የሚያነጣጥሩበት ነባር የማጥቃት ስልት ነው። ሰሞኑን “በሰላምና በዲሞክራሲ ስም” በኢሳት/ግንቦት7 መሪነት የተዘጋጀው ‘ኮንፈረንስ’ ይህንኑ የሚያሳይ ነው።

ይህንን ስትመለከቱ፤ የአገሪቱ መጻኢ ሕልውና የሚፈታተኑ ዛሬም ከውስጣችን የተጐለጎሉ ብዙ ያበዱ እንሰሳዎች መኖራቸውን መዘንጋት የለባችሁም። ትኩረታችን በወያኔም ሆነ በተቃዋሚ ውስጥ ያሉ የውጭና የውስጥ ተውሳኮች ላይ ጭምር መሆን አለበት ብየ ካሁን በፊት ደጋግሜ የጻፍኳቸውና የተናገርኳቸው ቁም ነገሮችን፤ እንዲህ ያሉ ተከታታይ የአጥቂዎች ዘመቻ እንደማይለዩን በማጤን ነው። በተቃዋሚው እና በተቃዋሚው፤ በወያኔ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሳይፈቱ የት የሌለ ርቀት እየሄዱ አንዴ ምስራቅ አፍሪቃን አንድ ለማድረግ፤ አንዴ ኤርትራና ኢትዮጵያ ኮንፈረነስ እያሉ “የአገራቸውንን ታሪክና ገመና” ለገበያ በማቅናት፤አገራችንን ለስውር በቀልተኞች በማጋለጥ ላይ ናቸው።

እንኳን ለኢትዮጵያ፤ለኤርትራ ሕዝብና  አብረው ለታገሉት ጓዶቹ ሳይቀር፤ ከነ ህፃናት ልጆቻቸው ያሰቃየ፤ ኢትዮጵያ ወታደራዊና ስቪላዊ ሙርኮኞች በባርነት ቀንበር ይዞ አፍኖ  የሚገኝ፤ “ተንኮል፤ ክፋት፤ ጭካኔና በቀልተኛነት” እንጂ “እውነትና በጎነት” ከጎኑ ቆማ የማትታወቅ ኢሳያስ አፈወርቅ  የተባለው “ጸረ ኢትዮጵያ ተውሳክ” አጀንዳውን የሚዘረጋው ፤ በበጎነት የሚያወድሱት በእነዚህ በአበዱ ጦጣዎች በኩል እንደሆነ ከንግግራቸው ማወቅ ትችላላችሁ።

አንድ ነገር ብየ ወደ ርዕሴ ልገባ ነው ። በየፓልቶኩ ስጎበኝ “አማርኛ የሚናገሩ ‘አሚቼዎች’ እና ኢትዮጵያዊያን የግንቦት 7 ደጋፊዎችና አባሎች” የሆኑ ንግግራቸው ሁሉ የኢሳያስንና የኤርትራን ክብር ከፍ እያደረጉ እያወደሱና እያጎሉ፤ የትግራይን ሕዝብ “አጋሜዎች” በማለት ዘለፋና የዘር ማጥፋት ዛቻ በማስተጋባት፤ አብዛኛውን “የፓልቶክ ክፍል” አንዳለ በብዛት ተቆጣጥረውታል። ይህ አገር በታኝ ዘመቻ የሆነ ዘረኛነት ቅስቀሳ በግልጽ እያሰራጩበት ይገኛሉ። ይህ አደገኛ የግንቦት 7፤ የሻዕቢያ፤ የኦብነግና የኦነጎች “ሴራ” ሕዝብ ከዚህ አጥፊ ስራ እራሱን አንዲያጸዳ እጠይቃለሁ።

ይዋል ይደር እንጂ ተጠያቂነት ስለሚኖር፤ “አውዴዎች እየተቀዱ፤ ማንነታቸውንም ጭምር እየተመዘገበ ስለሆነ” ካሁኑኑ ጥንቃቄ ብታደርጉ እመክራለሁ። ግራ ቀኙ ሳታስተውል በስሜት እየከነፍክ የምትገኝ ዜጋ ሁሉ፤ በሚደረደርልህ የሻዕቢያ “በገና” ሕሊናሕ ከመታፈን ነፃ አውጣ። ከታፈንክበት ግማታም አየር ለመላቀቅ፤ መስኮቱን ሰብረህ ወደ ክፍቱ አየር ብትወጣ፤ ላንተም ላገርህም ጤንነት ይበጃል።
        
ከፍል -ለ-
በዲያስፖራ ግንቦት 7 አባሎች የታየው ሻዕቢያን የማጎልበትና የኤርትራን ደህንነት የማጉላት ዘመቻ ከላይ ተመለክተናል። ሰሞኑን ደግሞ በወያኔ በኩል ባለፈው ሰሞን በተጓዳኝ ተመሳሳይ ጸረ አገራዊ ትዕይነቱና ጸረ ኢትዮጵያ ባንዴራዎቹን እያውለበለበ “ከጫካ ይዞት የመጣ ታላቁ የሳብቨርሲቭ” ዘመቻው ባለፈው ሰሞን የጨፈረበትን  ትዕይንቱን እንመለከታለን።

የወያነ ትግራይ መሪዎች፤ ገና ከጅምሩ ቀርጸው የተነሱበትን ጸረ ኢትዮጵያ አጀንዳቸውን ለማካሄድና ሥልጣን ለመያዝ እንዲያመቻቸው፤ ወያኔዎች ለ24 አመት ኢትዮጵያን ከመቆጣጠራቸው በፊት፤ በአጥንት፤በደም በስጋ ዘመድ አዝማድነትና በጋብቻ በቤተሰብነት እዛው በዛው መተሳሰራቸው ለሚቆጣጠሯት ኢትዮጵያ ቀላል እንደሚሆንላቸው በማሰብ የድሮ የትግራይ መሳፍንትና ነገሥታት ሲጠቀሙበት የነበረውን አስተዳደራዊ ስልት በመከተል ነበር ይዘው ወደ አዲስ አበባ የገቡት። ዘጠኝ “የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” የፖሊት ቢሮ አባሎች እና ወደ ሰላሳ የሚሆኑ የድርጅቱ ማዕከላዊ አባላት አብዛኛዎቹ በትዳር እና በዘመድ አዝማድ የተቆላለፉ ናቸው። ሌሎቹ በወያኔ ጥላ የተሰባሰቡ የብእዴን እና የመሳሰሉ አሽከሮቻቸውም ልክ እንደ ወያኔዎች እርስ በርስ በጋብቻ ተጋብተው የመጡ ናቸው። አስተዳደሩ የከፋ ካደረገው አንዱ የስርዐቱ መሪዎች እና አስፈጻሚ አሽከሮቻቸው፤ በዘመድና በጋብቻ ሐረግ ተጠናንገው ስለሰሩ፤ እነ መለስ ዜናዊ ይዘውት የመጡትን ጸረ ኢትዮጵያ ፖሊሲ ለማስፈጸም እጅግ ቀለለላቸው።

ወያኔዎች በዚህ በተጠናናገ ቤተሰባዊ እና የጋብቻ ትስስር ትከሻ ለትከሻ ተያይዘው ወደ አገሪቱ መሃል ለመግባት እንዲያመቻቸው፤ ግንቦት 20 በ ሲ አይ ኤ ተደግፈው ወደ አዲስ አበባ ገብተው ፓርላማውን ተቆጣጠሩት። በእነሱ ስር የተደራጁም የአለቆቻቸውን ንግግርና ሴራ እየተከተሉ ፓርላማውን በቁጥጥራቸው አድርገው ሌላውን መፈናፈኛ አሳጡት።  በዚህ ወቅት ወያኔዎች በመሰረቱት አዲሱ የሽግግር ፓርላማ፤ ሁለት ተቃራኒና የተፋጠጡ ክፍሎች በመድረኩ ላይ ለሕዝብና ለታሪክ እይታ ብቅ አሉ።

አንደኛው ክፍል ከሰሜን ክፍለ ሃገራችን ከትግራይና ከመረብ ምላሽ/ኤርትራ ገስግሰው የመጡ ባንዳዎች ሲሆኑ፤ በሌላው በኩል ደግሞ ከመላ ኢትዮጵያ የተወለዱ በፈታኝና በቁርጥ ቀን ብቅ ብለው ልሳናቸው በታሪክ ማሕደር ለማስመዝገብ በተገኙ ኢትዮጵያዊያን መሃል ግብግቡ ተጀመረ።

በወቅቱ በግምባር ቀደም ወያኔን ፊት ለፊት ተጋፍጠው እስከ ሕልፈተ ሞታቸው ለኢትዮጵያ የቆሙ እንደ እነ ፕሮፌሰር አስራትና እንደ እነ ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት የመሳሰሉ እንደነበሩ ባለፈው ጽሑፌ ላይ ያነበባችሁ ታስታውሳላችሁ። ዛሬ ከፕሮፌሰር አስራት ባልተለየ መልኩ ወያኔን ከተጋፈጡት መሃል ሻለቃ አድማሱ እና ስማቸው ያልተጠቀሱ ጥቂት አርበኞችም ነበሩ። አብዛኛው የዛሬ ወጣቶች የእነኚህ ሰዎች ግብግብ በብዛት አያስታውሰውም። እንኳን የእኚህ ግለሰቦች ገድል ይቅርና፤ በአማራ ሕብረተሰብ ላይ የተነጣጠረው በሚሊዮኖች የጠፉበትና ካገራቸው እንዲባረሩ የተደረገው ጥቃት እንኳ ምንም እውቀት የለውም።ይህ ደግሞ ሳንሆዜ ለስፖርት በዓል መጥተው ባነጋገርኳቸው ብዙዎቹ ወጣቶች የታዘብኩት ትዝብት ነበር። አማራ ምን ደረሰበት? ሞረሽ ማለት ምን ማለት ነው? አማራን ከጨርሶ ጥፋት እንታደግ ማለት ምን ማለት ነው? ብለው የሚጠይቁ በርካታ ወጣቶች ነበሩ (አሳፋሪ ምሁራን ነን ተብየዎችን፤ የምኒሊከን ጥቅሶችንና የአማራ ህፃናት መሬት ላይ ተኝተው ለረሃብና ለብርድ የተጋለጡትን ፎቶ ግራፎችን በጎሪጥ እያዩ፤ የሞረሽን ድንኳን ያለፉትን እኔ የማውቃቸው ታዋቂ ሰዎችና የማላውቃቸው ስሜታቸው በሕዝብ ሰቆቃ ሳይሆን በባዓሉ ዝግጅት ሜዳ ላይ በእስክስታ የተማረኩትን ሳላወሳ መለቴ ነው።

ግንቦት ወር የወያኔ ባንዴራ የተሰቀለበት ፤የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቃላማ የወረደበት ወር ነው። ትንቅንቅ ካደረጉት አንደኛው ሻለቃ አድማሴ ይባላሉ። የዛሬ ወጣቶች አያውቋቸውም። ዛሬ እንዲያውቋቸው በግንቦት ወር ወያኔዎች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ፤ የኢትዮጵያን ወደብ ከነመርከቦች እና ጀልባዎች ለጅቡቲ እና ለኤርትራ በስጦታ መልክ ለጠላት ያስረከቡበት፤ የኢትዮጵያን ሠራዊት በትነው በምትካቸው የትግሬ ወታደሮችን የተኩበትና፤ለማኝ እንዲሆን ያደረጉበት፤ ወያኔዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሰንደቃላማ ያዋረዱበትና ብሔራዊ ሰንደቃላማችንን ዝቅ አድርገው በመመልከት፤ ያለፉትን ስርዐቶች፤ባሕል፤ሃይማኖትና ታሪክና ገድል እያሳነሱ የወያኔ ገድል ከፍ አድርገው በሚያከብሩበት የባንዴራቸው ዓመታዊ በዓል ከመመልከታችን በፊት፤ ወያኔዎች ባዘጋጁት የሽግግር መንግሥት በጉባኤው ላይ ተገኝተው፤ ሻለቃ አድማሱ እና ሌሎች አገር ወዳዶች በቪዲዮና በጽሑፍ አስደግፌ ከወያኔዎች ጋር ያደረጉት ፍጥጫ ለታሪክ አስመስግበውልን የሁዱትን ትግላቸውን  ባንዳዎቹ “ዊስኪ ሲራጩ” እኛ ደግሞ የአርበኞች ኢትዮጵያዊያን ወላጆቻችንን “የኢትዮጵያዊነት ልሳን” እንደ ዊስኪ እየጠጣን ሕሊናችንን በጠነከረ ኢትዮጵያዊነት ትግላችን እንዲቀጥል የማቀርብላችሁን ስዕለ ድምፅ/አውድዮ-ቪዲዮ እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ።

ከዚያ በፊት ግን በመለስ ዜናዊ እና በሦስት ቆራጥ ኢትዮጵያዊያን የተደረገው ፍጥጫ ከንግግራቸው ያገኘሁት ለታሪክ ንባብ እንዲመች አቀርብላችሗለሁ፡

“ይህች ሰንደቃላማ አንድ ነጥብ ቢጨመርባት፤አንድ ነጥብ ቢቀነስባት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያዝናል። የሽግግሩ መንግሥት ሰንደቃላማውን በዘምባባ እና በወይራ ቅጠል ከሚያስተካክል ይልቅ፤ ባንድ አገር ሁለት አስተዳደር አይመስርት!”

“እኩልነት ሲጠበቅ ማለት ደግሞ፤ ባንድ መንግሥት ሁለት አስተዳዳር ሳይኖር፤  የመንግሥት መ/ቤት ሁሉ ባንድ ብሔረሰብ ከጠራጊ ጀምሮ እስከ ሚኒስትሬ ድረስ በአንድ ብሔረሰብ ሳይያዝ፤ላንዱ የተደረገለት ለሌላው ሲደረግለት፤ ይኼ፤ እውነተኛ ዲሞክራሲ ልንለውና አብሮ የመኖር ተስፋ ያጠናክራል ልንል እንችላለን!”

 “አንዱ ጎሳ በሌላው ላይ መቀስቀስ፤ ተዋልዶ ተጋብቶ በሰላም የኖረውን፤ ‘ከመቶ አመት በፊት ጡት ቆርጠሃል’ ሲባል፤ ለምን ከመቶ አመት በፊት የነበረውና የተቆረጠው ምላስ አብሮ አይነገርም? ለምን ጡት ብቻ? ምላስ ቢቆረጥ ምላስ ቢቆረጥ ልዩነቱ ምንድ ነው?” 
 “በሽግግሩ ወቅት ሻለቃ አድማሴ ከተናገሩት ንግግር ”

ስለ ሰንደቃላማ የተደረገው ውይይት፤

መለስ ዜናዊ፤

“ጨርቁ የፈለገው ሰው ሊያውለበልበው ይችላል። ጨርቁ ለኛ ኢሚንት ነው። እኛ ኢሕአዴግ የራሳችን መለያ አርማ አለን።” (መለስ ዜናዊ፤ በሽግግር መንግሥት ወቅት የተናገረው)

ጨርቅ እያለ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማና የአገር መለያ ምልክታችንን ነው “ጨርቅ” ሲል ያጣጣለው። ባንዳው መለስ በዚህ አላበቃም። ጋዜጠኛ የሚከተለው ይጠይቀዋል፡

የኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ ጥያቄ፦

ጥያቄ አለኝ!

“ኢሕአዴግ በደረሰባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሙሉ የኢትዮጵያን ባንዲራ ያወርዳል፡የሚባል ነገር አለ። እዚህ አዲስ አበባም እራሴ ባላይም፤ ከውጭ እንደሰማሁት፤ ሰላማዊ ሰልፍም ሲደረግ፤ የሰላማዊ ሰልፉ አንዱ መነሻ፤ የኢሕአዴግ ሠራዊት አባላት የኢትዮጵያን ባንዴራ አውርደው የኢሕአዴግን ባንዴራ ስለሰቀሉ ነው፡ የሚባል ነገር አለና፤የዚህ ድርጅት ግልፅ ያለ አቋም ስለ ኢትዮጵያ ባንዲራ በተመለከተ ምን ዓይነት አቋም እንደሆነ ቢገልፁልን?

የባንዳዎቹ መሪ መለስ ዜናዊ፤- መልስ፤---     ባንዴራው በተመለከተ፤ ከባንዴራው በስተጀርባ ያለው አመለካከት ያለው መሰለኝ ወሳኙ። ጨርቁ የሚያመለክተው ነገር ይመስለኛል ወሳኙ፤ ከቀለሙ በላይ። አንዳንዶቹ 3000 አመት ዕድሜ ያለው ባንዴራ ነው እያሉ ሁሉ፤ ያልሆነ ነገር ተረት፤ተረት ሲናገሩ፤ ምናልባት ሰምታችሁ ይሆናል፤ ምናልባትም ያንኑ ዜና አሰራጭታችሁም ሊሆን ይችላል። ይህ ባንዴራ መቸ እንደተፈጠረ፤ በታሪክ ጸሐፊነት ስም፤ በምናምን ስም፤ ከአዝማሪነት ያላነሰ ስራ፡…… ከጨርቁ በስተጀርባ ያለው ምንድ ነው?  “ነፃነት” ነው? እኩልነት ነው? ዲሞክራሲ ነው? የኢሕአዴግ ጠብ ከበስተጀርባው ያለው አመለካከት ነው ጠቡ። በሚቀጥለው መድረክ (በሚቀጥለው መንግሥት/ስርዓት) የኢትዮጵያ ሕዝብ “ጨርቁ” የሚፈልገው ከሆነ “የራሱ ጉዳይ ነው!!!!” የጨርቁ፤ የባንዴራው ጥያቄ ለኛ ትርጉም የለውም! ኢምንት ነው! “ጨርቁ” የፈለገው ሰው “ሊያውለበልበው” ይችላል። ጨርቁ ለኛ ኢምንት ነው። ኢሕአዴግ የራሳችን መለያ አርማ አለን።”  
  
“ምናልባት አንዳንድ የኢሕአዴግ አባላት በጨርቁ ላይ ቁጭታቸውን አውጥተው ሊሆኑ ይችላል። ጨርቁ ሊውለበለብ ይችላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቀየር ካለ ጊዜው ጠብቆ ሊቀይረው ይችላል።

ከዚህ በታች በቪዲዮ የማቀርበው መለስ ዜናዊን የተቃወሙት በሰነዱ ሚታየው በጉባኤው ላይ የነበሩ የመጀመሪያ ተናጋሪ ከነበሩት ሁለት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች መካከል ስማቸው ማወቅ ያልቻልኩ (ምናልባት የኢድዩ ተወካይ ሳይሆኑ አይቀሩም የሚል ግምት አለኝ። ስማቸው የምታውቋቸው ካላችሁ በኢመይል ጠቁሙኝ። ምክንያቱም በመጽሐፍ መልክም እያሰፈርኩት ስለሆነ።) እና  ከእሳቸውም ጋር አብረው የነበሩት ተናጋሪ ሻለቃ አድማሴ ፤ ሁለቱ ተነጋሪዎች የሚከተለው መልስ ለመለስ ዜናዊ ከቁጭትና ከማስረጃ ጋር እንዲህ ሲሉ ኢትዮጵያዊ ኩራት በተመላበት ከተቀመጡበት መንብር ተነስተው በድምፅ ማጉልያ መልስ ሰጥተውታል።

ስማቸው ያላወቅኩት ኢትዮጵያዊ አርበኛ ተነጋሪ፡-ከመቀመጫቸው ተነስተው ለመለስ ዜናዊ የሰጡት መልስ እንዲህ በማለት ንግግራቸው ይጀምራሉ፤-

“የመጀመሪያ ተናጋሪ ወንድሜ የተጠቀመው ቃላት “ጨርቅ” የሚለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው በጨርቅነቱ ሳይሆን በክብርነቱ ነው። በወርቅ ፤ በልዕልና (በዘውድ) በከፍተኛ መዓረግ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቃት! ዘውድ ስል፤ የዘውድ መንግሥት ማለት አይደለም።ልክ እንደ ዘውድ፤ በልዕልና እንጂ፤ እንደ እንቁ እንጂ፤ በጨርቅነት አይደለም! እኛ ታሪኩን፤ባሕሉን በየመድረኩ ሸፋፍነን ብንሄድ ታሪኩም የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ስለሆነ፤ባሕሉን የሚመሰክረው ነው። ሕዝቡ ያውቀዋል። ጥንቃቄ ብናደርግ ጥሩ ነው። ባሕር ወስጥ ነን ያለነው። ሕዝብ ባሕር ነው፤ እኛ ዓሳዎች ነን። መልሶ ቢተፋን በምን ምክንያት እንደተተፋን መልሶ ማወቅ ተገቢ ይመስለኛል። ከሕዝቡ ወጥተን መራቁን ይህን ያህል ርቀን መራቁን፤ይህን ያህል ርቀት መራመድ የሚያስኬድ አይመስለኝም። ስለዚህ የሕዝብ ፍላጎት ማወቅ አዋቂነት ይመስለናል።”
ሲሉ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።

ሻለቃ አድማሴ፡ ደግሞ እንዲህ ሲሉ ከፊታቸው ከተናገሩት አርበኛ ቀጥለው ንግግራቸውን እንዲህ ሲሉ ለመለስ ዜናዊ መልስ ሰጡ፦

ክቡራን ጌቶቼ!

እርግጥ ግፍ ተሰርቷል።አሁን ዘርዝሬ መናገር የማልችለው። ግን፤ግን፤ግን…ይህች ሰንደቃላማ ደግሞ ብዙዎችን ነፃ አውጥታለች! ብዙዎችን የዲሞክራሲ መብት አጎናጽፋለች! አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢጠየቅ፤ተራ በተራ እያንዳንዱ ሰው ቢጠየቅ፤ ይህች ሰንደቃላማ፤ አባቶቻችን ለሷ ሲሉ ደም የተፋሰሱባት ነች። የወላይታ ንጉሥ የነበሩት፤ ምርጥ ጦር ልከው ዓድዋ ላይ የዘመተው የወላይታ ጦር ነው። የታሪክ መጽሀፍ አምጣ ከተባልኩ ማምጣት እችላለሁ፡ ታሪክ መዝግቦታል። ይህችን ሰንደቃላማ ይዘው ነው፤ አባቶቻችን ከጠላት ጋር የተፋጁባት!

ክቡራን ጌቶቼ!

ስለ ዲሞክራሲ ብዙ ተናግራችሗል።
ዴሞክራሲ የሚኖረው፤ከሰንደቃላማ ምልክት ጋር ሳይሆን፤ ከአገዛዝ ከአስተዳደር ጋር ነው። የብሔር ብሔረሰብ እኩልነት ሲጠበቅ ነው። ይህንን እደግመዋለሁ! የብሔር ብሔረሰብ እኩልነት ሲጠበቅ ነው። እኩልነት ሲጠበቅ ማለት ደግሞ ‘በአንድ መንግሥት ሁለት አስተዳዳር ሳይኖር፤የመንግሥትን መሥርያቤት ሁሉ በአንድ ብሔረሰብ ከጠራጊ ጀምሮ እስከ ሚኒስቴር ያለ ባንድ ብሔረሰብ ሳይያዝ፤ላንዱ የተደረገው ለሌላው ሲደረግ፤ይሄ እውነተኛ ዲሞክራሲ አለ፤ ተብሎ አብሮ አውነተኛ የመኖር ተስፋ አለ ማለት ነው።
በወረቀት ላይ ቃላት ማስፈር ፤ በተግባር የማይተገበር የዲሞክራሲ ታሪክ ማብዛት ምን ይጠቅማል?

አንዱ ጎሳ በሌላው ጎሳ እንዲነሳ መቀስቀስ፤ ተዋልዶ ፤ተጋብቶ፤በሰላም አብሮ የተቀመጠውን ሕዝብ፤ እገሌ እንዲህ አድርጎሃል፤ከመቶ አመት በፊት ጡት ቆርጧል፤ ለምን ከዚያ በፊት ምላስ የተቆረጠውን አብሮ አይነገርም? ለምን ጡት ብቻ? ምላስ ቢቆረጥ፤ምላስ ቢቆረጥ ልዩነቱ ምንድ ነው? ነውር ነው! አንዲህ ያለ መጥፎ ነገር አለ።

ጌቶቼ ሆይ!
ወደ ኤርትራም ስናተኩር ወደ ሰንደቃላማው ስንሄድ፤ ኤርትራው ተወካይ “አቶ አሊ አብዱ” እዚህ እኛ ጋር ቁጭ ብለው አሉ፡ ዋሽተሃል እንዳልባል፤ ሊጠየቁ ይችላሉ፤ (ነጋሶ ጊዳዳ አቋርጠዋቸው “ይቅርታ ወደ ኤርትራ አይሂዱ ስለ ባንዲራው ስለ ሰንደቃላማ ጉዳይ፤ ወደ ሌላ ጉዳይ አንዳይሄዱ፤…) እሺ! ኤርትራ የማነሳው ስለ ሰንደቃላማ ጉዳይ በሚመለከት ነው። እዛም ቢሆን ተከብራ አንደኖረች ልናገር ፈልጌ ነው። እዚህ በመላ ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በሌለችበት ጊዜ፤ አስመራ ውስጥ ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ኤርትራኖቹ ‘የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ይዘው እንደኖሩ ለማስረዳት ነው’።

“ይህች ሰንደቃላማ፤አንድ ነጥብ ቢጨመርባት፤ አንድ ነጥብ ቢቀነስባት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያዝናል! የሽግግሩ መንግሥት ሰንደቃላማውን በዘምባባና በወይራ ቅጠል ከማያስተካክል ይልቅ፤በአንድ አገር ሁለት አስተዳዳር አይመስርት! ለአንድነታችን ትክክል የሚሆነው ይህ ሲሆን ነው።”                                                                        On Record: When Meles vilified the Flag
ማጣቀሻዎች
(1)     Thus Spake Zarathustra ከሚል ልብ ወለድ ፍልስፍና መጽሐፍ የተገኘ። ደራሲ ከፍሬደሪክ ኒች/ ትርጉም ነስሩ ዑመር። ከጀርመንኛ ወደ እንግሊዝኛ ትርጉም የተመለሰው መጽሐፉ አማዞን ውስጥ ብትገቡ ከ $4.00 00 በታች በርካሽ ዋጋ ታገኙታላችሁ።)

                                  (2)-    (ጌታቸው ረዳ፤ ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ፤ የትግሬ  ልሂቃን በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን    የመነጨ ነው? ከሚል በመጽሐፍ መልክ በመሰራት ላይ ካለው የተወሰደ።)
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian semay) getachre@aol.com
Sunday, October 25, 2015

የኢሕአፓ ዘረኝነትና ዛቸው! ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay)የኢሕአፓ ዘረኝነትና ዛቸው!
ጌታቸው ረዳ
ነብሱ ይማረው በገጣሚ ሃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው) ግጥም ጽሑፌን ልጀምር።
  በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መካከል
ህይወት የምንለው እንደ ጥሬ እህል
                                                            በኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ ቢማሰል
  የበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል!!
(ገጣሚው ገሞራው)

አሁን ትልቅ አገራዊ ርዕስ በመጻፍ ላይ ስለሆንኩኝ፤ ጊዜ ላለመሻማት ስል ሌላ ቀን በሰፊው እስክመለስበት ጊዜ፤ ሰሞኑ ኢሕአፓዎች በድረገጻቸው በአሲምባ ላይ ስለ እኔ የለጠፉትን ‘ዘረኛና አግላይ ካርቱን” አማራና ኦሮሞን በማናከስ ዘርን ከዘር ለማጨራረስ በወንጀል የሚከሰሰው ኤርትራዊው ተስፋዬ ገበረአብ ጋር እኔን በማነጻጸር “እኝህ ሰው ምን ነካቸው ከአማራ በላይ አማራ! የከለላ ታሪክ ፤ጋጋታ ምን የሚሉት?” በማለት፤ “ትግሬው ለትግሬ” እንጂ ስለ አማራው አያገባውም፤ ሌላው ስለ አማራ የመጨነቅ፤ የመቆም መብት የለውም!’ ከማለታቸው ሌላ፤ እጅግ አስገራሚ ካርቱናቸው ደግሞ “የከለላ ታሪክ” በማለት እኔን ለአማራው ሕብረተስብ እንደ ባዕድ ወገን አድርገው በመሳል፤ ለሰሚው እጅግ አሳፋሪና ዝቃጭ የሆነ የመንደር ብስለታቸውን ለማንጸባረቅ ሞክረዋል።

በፓልቶክ ስሙ “ፋኖ” በመባል ወይንም “አደባባይ” በመባል የሚታወቀው እዚህ ሳንሆዜ ከኔ ጋር የሚኖር ምስኪን የኢሕአፓ ካልትም ሳይቀር፤ “አማራ፤ አማራ ፤የሚሉ ፡ስለ አማራ፤ ስለ ሞረሽ የወገኑ ሰዎች” አማራዎች ሳይሆኑ ከሌላ ጎሳ የተወለዱ የወታደር ልጆች ናቸው” ሲል ከኤርትራዊያን በባሰ መልኩ የዘቀጠ “ዘረኛነቱን” ሲያነበንብ የተደመጠውን በአውድዮ ቀድተው ወዳጆቼ  የኢሕአፓ ‘ጉድ አደምጥ”  ብለው የላኩልኝም አደምጬ ሰዎቹ ጭልጥ ብለው ወደ ዘር ቆጠራ መግበታቸው አጅግ አዘንኩላቸው።

ኢሕአፓዎች ስለ አርበኛቸው ስለ ማርክሲስቱ ዋለልኝ መኮንን እና ስለ ድርጅታቸው የተቸሁትን ተገቢውን መልስ ጽፈው መከራከር ሲገባቸው፡ የነቁ፤የበሰሉ መስለውኝ የነበሩት ሰዎች ወደ ዘረኛነትና ወደ አሉባልታ ሲገቡ ማየቴ በፕሮፓጋንዳው ዘርፍ እጅግ የወረዱ፤ ቢቆሉ፤ቢቆሉ የማይበስሉ መሆናቸውን ነው የታዘብኩት።

ስለ ኢሕአፓ በሰፊው ለወደፊቱ የምንነጋገርበት ሲሆን፤ ለአሁኑ ግን ለዚህ ዘረኛ እና ዝቃጭ ብስለታቸው አሁንም በድጋሚ ያስታወሰኝ ነገር ቢኖር “ገዴዎን ለቪን” የተባለው እስራላዊው የሰው ልጆች ተሟጋች እና ጋዜጠኛ “ሰለ ፍልስጢኤማዊያን ሰብአዊ መብት በመቆም እስራላዊያንን በመቃወሙ ምክንያት” ከእስራላዊያኑ የተሰጠው ስምና የካርቱን ጥላሸት “ከፍልስጥኤማዊያን በላይ ፍልስጢኤማዊ” ሲሉ ካርቱን ለጥፈውበት የነበረውን አስታውሰውኛል። ይህ በኢሕአፓዎች አልተጀመረም፤ ወያኔዎች ብለውኛል፤ ኦነጎች ብለውኛል፤ ዛሬ የአሲምባ ድረገጽና መሰል የኢሕአፓ ካልቶች የሚለፋደዱት ያንኑ ከአቻዎቸው የቀዱትን ዘረኛና ያልበሰለ ጥሬ መልሳቸው፤ በማስረጃ ለጻፍኩት መልስ፤ በመረጃ አስደግፈው መልስ መስጠት ሲያቅታቸው፤ መልስ ይሆናል ብለው ከወንጀለኛውና “አገሬ ኤርትራ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለም” ብሎ ኢትየጵያን ከከዳ ‘ከተስፋዬ ገብረአብ” ጋር ያነጻጸሩኝን ካርቱናቸውን ለማዬት ትዝብታችሁን ለማኖር ክቡራን አንባቢዎቼ ድረገጻቸውን እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ።

ከላይ የጠቀስኩት ፓልቶክ ውስጥ ሆኖ የጀገነ የኢሕአፓ ካልት ደግሞ “ድርጅቱ ድሮ ሲያደርገው እንደነበረው የግድያ ሱሱን በኔ ላይ ለመጀመር የቃጣው ይመስላል”፤ ወጣቱን በማደራጀት “የድሮ ዶሚናንስ ባሕሪያችን መመለስ አለብን” ይላል። በማርክሳዊያን ዓለም፤ ለዶሚናንት ባሕሪ መጓዝና መመኘት ምን እንደሚያስከትል እና ምን እንዳስከተለ፤ አሁንም ምን እያስከተለ እንዳለ የምናውቀው ይመስለኛል። የዚህ ጉረኛ ሰው የተለፋደደበትን ስድብና የማስጠንቀቂያው ዛቻ ወዳጆቼ እንዳደምጠው ቀድተው በአውድዬ ልከውልኝ፤አድምጬው፤ የካልት ድፍረት ምን ያህል ርቆ አንደሚሄድ አስገርሞኛል። ይህ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነው።

ኢሕአፓዎች ለማስፈራራት የተነሱበትን ሰው ማንነት አለማወቃቸው ይገርመኛል። ወያኔ ዝቶ፤ዝቶ፤ዝቶ፤ ስሜን አጥፍቶ፤ጎሳየን ሰርዞ፤ ያልሆነለት፤ አሁን ምስኪኑ የኢሕአፓ ካልት “ኢሰፓ” ብሎ ሲወነጅለኝ፤ እንኳን ኢሰፓ ልሆን ፤ ኢሰፓ ሲመሰረት አገሪቱ ባልነበርኩበት እና ትርጉሙ  ምን ማለት እንደሆነ እንኳን የማላውቀውን ሰውዬ፤ እኔን “ይሻለዋል” ብሎ ሲያስጠነቅቀኝ፤ ‘ተደራጁ እያለ የሚወተውታቸውን ወጣቶቹን “አስልኮ” ነጭ ሽብር ሊያራምድብኝ ካልሆነ በቀር ምን ሊያመጣ አንደሚችል ገርሞኛል።

እነኚህ አርበኞች ናቸው፤ ተውአቸው እያልኩ ስከላከልላቸው ከስንት ወዳጆቼ እየተቀያየምኩ፤ ስከላከልላቸው የነበርኩኝ ሰውዬ፤  ዛሬ ‘ቢቆሉ፤ ቢቆሉ፤ የማይበስሉ ሆኖው ሳገኛቸው፤ እውነትም ከዛው ከ70ዎቹ ምድጃቸው አሁንም እዛው አመዱ  ላይ ተዘፍቀው መውጣት እንዳቃታቸው ለማየት ችያለሁ።አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች” ብሎናል ወዳጄ ገብረመድህን አርአያ ‘ እውነትም እኔን ለመጎነታተል አምሮአቸዋልና እሰየው! ምርጫቸው ነውና፤ አከብርላቸዋለሁ፤ ለሁሉም ኳሱም ሜዳውም እንሆ! እንፈታተሽ።ጥርሱ ያለቀበት ውሻ መጮህ እንጂ መናከስ አያውቅም፤ ኢሕአፓ በዘረኛነት ቢጮህም “የእኔ ከአማራው ሕብረተሰብ መቆም” ሊያስቆሙኝ ከቶውኑ አይችሉም! “እንደ እናታቸው ጡት ያጡት እንደሆን እንጂ ፤ “እኔ አማራም፤ ትግሬም አገውም፤ኦሮሞም፤ወላይታም፤ ሐረሪም ሶማሌም…..ወዘተ ወዘተ…. ነኝ”  ኢሕአፓ “ባዕድ ነህ” ቢለኝም፤ ስለ አማራ የመቆም መብቴ ከተውኑ መንጠቅ አይቻለውም። እንዴት ደፋር ነው ይህ ኢሕአፓ እባካችሁ? ድፍረቱ ሌላ ሰው ጋር ቢያደርገው እንዴት ባማረበት ነበር። ወይ አለማወቅ!  

ኢሕአፓ ‘የዜጎችን ህይወት ሲያደርገው እንደነበረው” መሪና ተመሪ ሳይታወቅ ወደ አናርኪ ተለውጦ ህይወት በጥይት ሲቀስፍ እንደነበረው ሊቀስፍ ይችላል። ተጠያቂነትም አልነበረውም፤ እስካሁን ድረስ ተጠያቂነቱን አልወሰደም፤ “ገደሉኝ እንጂ ገደልኩ አይልም፡ አጥፍቻለሁ ተጠያቂ ነኝ አላለም። ይህ ደግሞ የተጠቂዎች ዝምታ ወደ ስንፍና ተተርጉሟል። እንግዲህ ማሾፍ ከቀጠሉ፤ አንድ የተቀናጀ ጥናት መደረግ አለበት እላለሁ።”  የሰው ልጆች ህይወት በማርክሳዊ፤አናረኮዊና ፋሺስታዊ እርምጃው ሰውን የመቅሰፍ መብት በገዛ እጁ ሊኖረው ይችላል። የኔን እና የዜጎችን ጎሳነትና የማንነት መብት’ የመንጠቅ ወይንም የመስጠት” መብት አልተሰጠውም። ሊኖሮውም አይችልም። 

ቢፈልግ ፓልቶክ ላይ እንደ እኩያዎቹ ዘረኛ ምላሱን ሊዘረጋ ሊሰበስብ ይችላል። ያንን ዘረኛ መብቱን አከብርለታለሁ፤ ስለ አማራ ማሕበረሰብ መብት መከራከር መብቴን ግን ሊነጥቀኝ አይቻለውም። ወያኔም፤ኦነግም፤ሻዕቢያም ሞክረውታል፤ ኢሕአፓም፤ ሊላላጥ ካልሆነ በቀር ከቶ አይቻለውም!

አላርፍ ካላሉ፤ “ኢሕአፓ በታጋዮቹ አንደበት” በሚል የማወጣው ሰነድ ይኖራል።ተከታተሉ፡ ይቀጥላል።
ጌታቸው ረዳ  (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) (Editor Ethiopian Semay)  getachre@aol.com
Monday, October 12, 2015

ማርክሳዊ ርዕዮት አልለቅ ያላቸው የአሲምባ ፈላስፋዎች! መልስ ለአሲምባ ድረገጽ አዘጋጆች ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)ማርክሳዊ ርዕዮት አልለቅ ያላቸው የአሲምባ ፈላስፋዎች!
መልስ ለአሲምባ ድረገጽ አዘጋጆች
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
ውይይቴ ከመጀመሬ በፊት በቅርቡ ሁለት ታዋቂ አንጋፋ ኢትዮጵያዊያን ማለትም ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ (የሗላ ሗላ በመጨረሻ ዘመናቸው እዚሁ ውጭ አገር ሆነው ሲያራምዱት የነበረው አቋማቸው ባልስማማም፤ ከዚያ በፊት ላገራቸው ያደረጉት አስተዋጽ ሚዛኑ ከባድ ስለሆነ ሃዘኔን ልገልጽላቸው ተገቢ ነው) የሙሉጌታ ሉሌን ሕልፈት ተከትሎ “የኤርትራ ጉዳይ” ደራሲና ጋዜጠኛ አምባሳደር  ዘውዴ ረታ ሁለቱም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ነብስ ይማር ለማለት እፈልጋለሁ።”
አሁን ወደ ኢሕአፓና የ ያኔ ትውልድ ጉዳያችን ይዤአችሁ ልግባ። ለብዙ ጊዜ ኢሕአፓን ስከላከል የነበረበትን ዞር ብዬ ስመለከት አሁን አሁን እራሴ እያስገረመኝ ነው። ማርክሳዊ ጥማታቸው ዛሬም እየተንከባከቡት መሆናቸው ስመለከት ባለማወቄ የሰጠሁዋቸውን ድጋፌ በዚህ ትችት ልሳበው።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት “የአዲስ አበባ ቀ.ሃ.ስ.ዩ” የተማሪዎች አንጋፋ መሪ እና “ኢሕአፓ ነበር” ተብሎ በመስራቾቹ የተነገረን ዋለልኝ መኮንን ላይ ባቀረብኩት ትቶልን በሄደው አመለካካቱ ላይ፤
 “በአሁኑ ወቅት የዚያን ትውልድ የትግል ታሪካ የማንቋሸሽና የመከለሱ ዘመቻ ለምን አስፈለገ?” በሚል ርዕስ ለኔ መልስ ተብሎ በአሲምባ አዘጋጆች በድረገጻቸው የተለጠፈው አንቤዋለሁ። “ያ ትውልድ” ብለው ለሰየሙት ያ ትውልዳቸው የተከተለው ማርክሳዊ/ፋሺስታዊ ርዕዮት፤ ዛሬም አልለቅ ብሎአቸው ስለ ማርክሳዊ ርዕዮታቸው ጥብቅና ቆመው፤ እንደ እነ ዋለልኝ የመሳሰሉት በዘመኑ የነበሩት ማርክሳዊያን ያስተማሩትን መስመር እስከዛሬ ድረስ አፍራሽ ሆኖ ኢትዮጵያን እያተራመሰ ያለው ማርክሳዊ/ሌኒናዊ/ማኦዊና ስታሊናዊ ርዕዮት አትንኩብን፤ከቶውንም ማርክሲዝምን አታንቋሽሹብን  ሲሉ መከራከራቸውን አስገርሞኛል።
ያ አልበቃ ብሎ፤ ኤርትራዊቷ ማርታ ለኤርትራ ትግል ስለመቆሟና ዋለልኝም ምናልባት ከእርሷ ጋር ከነበረው ቀረቤታ አንጻር ሲታይ በእርሷ ፍቅር ተነድፎ የኤርትራን ጥያቄ በኢትዮጵያ ተማሪዎች ሕሊና ተቀባይነት እንዲኖሮው የመጣሩንና ፤ከዚያም አልፎ ዓለም ድጋፉን እንዲሰጣቸው ለማድረግ ለአይሮፕላን ጠለፋው ያደረገችው ግፊት ከጥቂት አመታት በፊት እንደሚኖር ከአስመራ ከተማ የተላኩልኝ የታተሙ የኤርትራ ፋይሎችና፤ ኢትዮጵያዊያን ታሪክ ጻሐፊዎች ከፍርድ ቤት ያገኙት የማርታ የክስ ማሕደር በማገናዘብ ባቀናበርኩት መሰረት ተነስቼ የገመገምኩትን የግል አስተያየቴን በመቃወም የአሲምባ ድረገጽ አዘጋጆች “በርዕሰ አንቀጻቸው” እኔን “ሊቅ” እያሉ በመሸርደድ ተችተውኛል።
ሊቅ የሚለው ቃል ለኔ የማይገባ መስሏቸዋል። አንዳንድ በሊቃውንትነት ማዕረግ ያሉት ሊያልፉት ያልቻሉ አስቸጋሪ ረዢም የትግል ጉዞ፤ ሁሉም አገሩን ለመግባት ሲያሰፈስፍ፤ አልገባም ብዬ የወላጆቼ ቀብርና ሕመም በቅርብ ተገኝቼ ሳላስታምም እና ሳልቀብር ለአገሬ የቆምኩኝ ታጋይ መሆኔን ያሳለፍኩት ህይወት፤ ማንነነቴንና የአገሬን መከራ ለመጪው ትውልድ ለመግለጽ 5 መጽሐፍቶች (ትግርኛ አማርኛ) በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ የቀረበ ብቸኛ ጥናት፤ (ጥናቴም አንድ ፒ ኤች ዲ አንድ ማሰተርስ ዲግሪ ለምረቃ ስራቸው እንደሚረዳቸው አስፋፍተው እንዲያቀርቡት ፈቃድ ለጠየቁኝ ኢትዮጵያዊያን ያደረስኩ) ሁሉም ስለ ወያኔ ገበና የሚያጋልጡ መጽሕፍቶቼና በሺዎች ቁጥር የሚገመቱ የጋዜጣ፤የመጽሔትና የድረገጽ ጽሑፎቼ ሲነጻጻር ብቸኛ የትግራይ ሰው ስሆን፤ እኔ እራሴ “ሊቅ” ነኝ ባልልም፤ አሲምባዎች የኔን ጥልቅ አስተዋጽኦ ማንቋሸሻቸው ከኔ ይልቅ እኔን ዶ/ር ጌታቸው ረዳ / አንድ ለናቱ/  ኢትዮጵያዊው ገዴዎን (እስራኤላዊው ጋዜጠኛና ታጋይ ገዴዎን ለቪንን በማነጻጸር) rare bird ፤ አርበኛና አገር ወዳድ ወዘተ…ወዘተ… የሚሉ በርካታ ስሞች መጠራቴን አሲምባዎች አያውቁትም አልልም።

ጥቅስ እንዲህ ይላል፤
1-   ሰሞኑን የዋለልኝ መኮንንን ታሪክ የማጥቂር ዘመቻው ተጧጡፏል። የአማራ ሕዝብ ጠላትም እየተደረገ እየቀረበ ነው። የማርታ መብራቱም የትግል ታሪክ በኤርትራዊነቷ የነሻቢያ መሣሪያ በመሆን እነዋለልኝን እንዳነሆለለች ተደርጎ የኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴም የዘረኞች መጠቀሚያ ሆኖ እንደነበር የሚሰብኩን ሊቃውንት በየመድረኩ ብቅ ብለዋል። ዕውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ነውና የዚያን ትውልድ ትግል ለመሆኑ የዛሬውን የዘረኝነት መነጽር ተላብሶ ለመመልከት መሞከር ስህተት አይሆንም ወይ? “    

እስኪ አንዴ ባጭሩ ልድገመው!?
“የማርታ መብራቱም የትግል ታሪክ በኤርትራዊነቷ የነሻቢያ መሣሪያ በመሆን እነ ዋለልኝን እንዳነሆለለች ተደርጎ የኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴም የዘረኞች መጠቀሚያ ሆኖ እንደነበር የሚሰብኩን ሊቃውንት በየመድረኩ ብቅ ብለዋል።”
አዎ ያ ትውልድ የዘረኞች ፍልስፍና፤የጸረ ኢትዮጵያ ክፍሎች መፍለቅያ፤ የኤርትርያኖች ትግል መጠቀሚያ ነበር።  እንዲያውም ካለችሁ እማ፤ ያ ትውልድ የሚባሉ እነማን ነበሩበት? ኤርትራኖች፤ ወያኔዎች/ኦነጎች/ኢሕአፓዎች!!!! እነኚህ እራሳቸው ዘረኞች ሆነው የተመለመሉ ጸረ አማራዎች መሆናቸው ከጻፉት የጽሑፍ ስርጭት ማረጋገጥ ይቻላል። አማራውን በነፍጠኛነት ሰይመው በጨቋኝ ብሔር ወንጅለውታል (ኢሕአፓም ሳይቀር!!!!)። ያውም እንነጋገር ካላችሁ እማ፤ አማራን በደመኛ ጠላት የፈረጁት ዘረኞቹ ኤርትራዊያን ‘ማርታ መብራቱን’ መላክ አላስፈለጋቸውም። ምክንያቱም ወይንም በማርታ አማካይኝነት ወይንም በ እነሱ ስብከት ወይንም ….ባንዳች ነገር የተነሳ፤ የኤርትራ ተገንጣይ ቡድኖች መሳሪያ የመሆኑ ጉዳይ ዋለልኝ የማርታን ጉትጎታ ያስፈለገውም አይመሰልም። እንዲህ ይላል በግልጽ፦
To applaud the ELF is a sin. If anything favorable is written out, it is automatically refuted by both USUAA and NUEUS. But the Gojjam affair was different. Support for it was practically a show of identity to the so-called revolutionaries.

On The Question of Nationalities In Ethiopia By Walleligne Mekonnen – Arts IV, HSIU  Nov. 17, 1969

ዋለልኝ በግልጽ የኤርትራ የግንጠላ አቀንቃኝ እና መሳሪያ መሆኑን ነው በግልጽ ከላይ እየነገረን ያለው። ጀብሃን ማሞገስ ማለት በሁለቱም የተማሪዎች ማሕበር ማለትም USUAA እና NUEUS እንደ ሓጢያት ሆኖ ይፈረጃል። ይላል በግልጽ።  ሃሎ! ሃሎ! ሃሎ!  አሲምባዎች!

እንዲህ ይላል፤-
“…I do not oppose these movements just because they are secessionists. There is nothing wrong with secessionism as such. For that matter secession is much better than nationally oppressive government.

As long as secession is led by the peasants and workers and believes in its internationalist obligation, it is not only to be supported but also militarily assisted.”

ዋለልኝ ምንድ ነው እያለን ያለው? ከብሔራዊ ጨቋኝ መንግስት ስር ከመኖር አገርን ማፈራረስ ይሻላል። ይላል።  የጀብሃን ግንጠላ እንቅስቃሴ ተቃወዋሚ የምሆን ከሆንኩኝ፤ ተገንጣዮች ተገንጣዮች ስለሆኑ ብየ ሳይሆን፤ ግንጣለው የሚመራው ክፍል ሰራተኛውና ገበሬው የእንቅስቃሴው አካል እስካልሆነ ድረስ ነው። በሁለቱም መደቦች ተሳታፊነት የሚመራ ግንጣላ ከሆነ እና ግንጠላው አለማቀፋዊ ላብአደራዊነት ሕግጋት እስከተከተለ ጊዜ ግን ግንጠለው መደግፍ ብቻ ሳይሆን በወታደራዊ እገዛም መታገዝ አለባቸው። ነው እያለን ያለው።

ማርታ ከጎኑ ሆና ካላበረታታችው፤ ለዚህም አነሳሽነት ከራሱ ከሆነ ደግሞ እራሱ የገንጣዮች አቀንቃኝ  መሳሪያ የመሆኑ ደግሞ የባሰውኑ “በአገር ግንጠላ አበራታችነት፤ በ የተጠያቂነት ቀለበት መነጽር ክብ ውስጥ ያስገባዋል”። እንዴት ነው ነገሩ!
ስለ ያ ትውልድ/ ስለ ዋለልኝ አስተምሕሮ ባሁኑ ጊዜ መነጋጋር እጅግ ወቅታዊ መሆኑን የአሲምባ ፈላስፋዎች አልገባቸውም። ብሔር  ብሔረሰብ፤ሕዝቦች እየተባለ በማርክሳዊ ርዕዮት የታጠረ ትምሕርት የተከተለው ዋለልኝ እንዲሁም ኢሕአፓና ወያኔ ያስተማሩት ትምሕርት (አሁም ስራ ላይ ውሎ አሁንም ያስከተለው መዘዝ ገና አልበረደም፤ በቂ ብሔራዊ ውይይትም አልተደረገበትም። አገሪቷም በዚህ እየተናጠች ናት፤ ማርክሳዊ ርዕዮት ካልተገታ ገደብ ካልተደረገለት፤ ገና ትናጣለች። ስለዚህም ትችቱ አስፈላጊና ወቅታዊ ነው።)  የአሲምባ ማርክሰዊ ርዕዮት ጠበቃዎች “ዋለልኝ” አትንኩብን የሚሉትም ፡ለማርክሳዊ ርዕዮት ያላቸው ፍቅር፤ ገና እንዳልበረደላቸው  ከላይ የጠቀሱትን ፤ ርዕስ ማስረጃ ነው።

ዋለልኝ አማራን አስመልክቶ ስለተቸው፤ መልስ ሰጥቻለሁ። ባለፈው ትችቴ ዋለልኝ መኮንን “ኦርቶዶክስ ሃይማኖትና አማራ” ሁለቱም ላደረሱት የፖለቲካ፤የባሕል፤ የአስተዳዳር ተጠያቂነት ከሚገባው በላይ እያጎላ ወንጅሎአቸዋል። ለዚህም መልስ ሰጥቻለሁ። መላው ኢትዮጵያ ስራ ፈላጊ ሕዝብ የአማራ ስም ካልያዘ ሥራ አንደማይሰጠው ዋሽቷል (ግለሰቦችን እንደምሳሌ እያጣቀሱ ማቅረብ ለሰፊ ውንጀላ በቂ መረጃ ሊሆን አይችልም። የአማራ ስም የያዘ አማራ እራሱ ስራ አልነበረውም። ለዚህም በመረጃ አሳይቻለሁ። ዋለልኝ ስያሰኘው በሁለት ብዕር (በሁሉም ጽሑፎቹ እንሚያደርገው ) እያምታታ የሚጽፈውን ስንመለከት ‘አማራው የተበደለ መሆኑንም’ አልካደም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ስሜት የሕዝቡ ስሜት ሳይሆን “የነፍጠኞች” (የአማራዎች) ብሔራዊ አገራዊ ስሜት ብቻ እንደሆነ ዋሽቷል። ትግሬዎች የአማራ ስም የያዙት ታሪክ ሃ ብሎ ሲቆጠር “ምኒሊክ፤ሃይሌ፤………ወዘተ ባልተወለዱበት ዘመን ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ ተያይዞ የመጣ መሆኑን ረስቶ፤ በግድ የአማራ ስም እንሰተሰጣቸው አድርጎ አማራዎችን ይወነጅላል)፤ አማራው የኢትዮጵያን ታሪክና መንግስት ለብቻው እንደመራው ዋሽቷል። ሰለ ባሕል ረጋጭነት፤ ምግብ፤ ሻማ/አለባበስ፤ሙዚቃ፤ ስለ ነፍጠኛነት ሕዝብን በግድ ረግጦ እንዲከተለው ማድረግ፤ አማራውን በማይገባ ወንጀሏል። አማራና የአማራ ስም የያዘ አማርኛ የሚናገረው የጎጃምም ሆነ፤ አማራ የበዛበት የወሎ ሕዝብ በመጥፎ አስተዳዳርና በርሃብ መጠቃቱ የዋለልኝን ማርክሳዊ ውሸት ቁልጭ አድርጎ የሚያረጋግጥ  እንደሆነ ገልጫለሁ።

2-  ዕውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ነውና የዚያን ትውልድ ትግል ለመሆኑ የዛሬውን የዘረኝነት መነጽር ተላብሶ ለመመልከት መሞከር ስህተት አይሆንም ወይ?     ብላችሁ ጠይቃችሗል።
እውነት እነዚህ ወንድሞች የሚናገሩትን ያውቃሉ? የዚያ ትውልድ ትግል ምንድን ነበር? የተከተለው ርዕዮት ምን ነበር? እኔው ልመለስስላችሁ!
“ማርክሳዊ ሌሊናዊ” አይዲኦሎጂ/አስተዳዳር ነበር ለኢትዮጵያ ያስተማረውና የተከተለው። በማርክሲዝም ጠባዩ ተነሳስቶ በቡድን ተቧድኖ፤ በጥይት የተደባደበበትም ርዕዮት ይህንን ርዕዮት ለማስፈን ነበር። የዚያ ትውልድ ርዕዮት ማርክሲዝም ማለት “ፋሺዝም” ማለት ነው። ሁለቱም ማርክሲዝም እና ፋሺዝም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። አይደለም የምትሉ የአሲምባ ሊቀውንት በግልጽ እንከራከር። 

አዎ እውነት እና ንጋት እያደረ ሲጠራ ነው ብላችሗል። ብዙ ሰዎች ይህንን እውነታ ሊገነዘቡ ሲችሉ፤ ምሳሌውን ብቻ ተገልጾላችሗል። አሳዛኙ ግን እውነታው እንደ ንጋት በርቶ እያለም፤ አሁንም ይህንን ትምህርትና ሃቅ ማገናዘብ አቅቷችሁ “ማርክሲዝም፤ያስተማሩ አስተማሪዎቻችሁና ያስከተሉብን መዘዝ ፤መነጋጋር ፤መተቸት፤መወቀስ፤የለበትም፤ትላላችሁ።” ብዙ ሰዎች የእነ ዋለልኝ ቅስቀሳ “አፍራሽ፤ አናካሽ” መሆኑን ማየት ሲችሉ፤ ለናንተ ብቻ ሊበራላችሁ አልቻለም። ንጋቱ ወለል ብሎ በርቶም ዓይናችሁ አሁንም ማርከሳዊውን ርዕዮት ብቻ አቶኩሮ ተቸክሎ ስላለ “አውነታው ጠጥሮ” ሊታያችሁ አልቻለም። ለዚህ ነው የ ያን ትውልድ ሃዋርያት ያስተማሩት “ትምሕርተ ክርሰቶስ” ነው እና ታቦቱን አትንኩብን የምትሉት።
ያኔ የት ነበራችሁ ዛሬ ወቃሾች የምትሆኑ የሚሉ ሊቃውንቶቻችሁ፤ ለኔ ያስቁኛል። ያኔ ይህንን የ “ኒሂሊሰቶች” አፍራሽ የሆነ ባዕዳዊ ርዕዮት ባሕላችን፤ታሪካችን፤አንድነታችን፤ሰላማችን ኩፍኛ ሊያደፈርስብን ነው ብለው ለተከራከሩ ሁሉ፤ ዋለልኝ ምን ብሎ ነው የመለሰላቸው “ፊውዳሎች!” ፤ “ሪአክሺነሪ!”። ያኔ የተቃወሙት እንዲህ ያለ ስም ነበር የተሰጣቸው። ያኔ አንዲያ የተቃወሙትን፤ እንዲያ ያለ ስም ሲለጥፍባቸው ፤ ዛሬ ደግሞ የትምሕርቱን መርዛማነት ስለተቸን እኔን “ሊቃውንት/ሊቅ” እያለችሁ “ማሾፋችሁ” አሁንም ከዋለልኝ አስተምሕሮ ዝንፍ አላላችሁም።
“የያኔ ትውልድ ትግል ለመሆኑ የዘረኝነት መነጽር ተላብሶ ለመመልከት መሞከር ስህተት አይሆንም ወይ?’ ብላችሗል።

ማነው ዘረኝነትን አፍራሽነትን አንባገነንነትን፤ መደባዊ መገዳደልን፤ መደባዊ አምባገነናዊነትንና ግንጠላን፤ ማአከላዊ አምባገነናዊነትን ያስተማረ? ያ ትውልድ!!!!!!!! እንዴት ብላችሁ ጠይቁኝ። መልሱ ፤ያ ትውልድ ያስተማረውና የተከተለው ርዕዮት ፡ማርክሲዝም ነው። ማርክሲዝም ምንን ያስተምራል? በቡድን መቧደንን፤ወገንተኛነትን፤መደብን፤ገበሬን ፤ወዛደርን/ላብ አደርን ተለያይቶ አንዱ ቡድን አንዱን እንዲያዘው፤ የግል ንብረትና መሬት በላብ አደር ጨቛኝነት በሚመራ በመንግስት ተይዞ/ተወርሶ፤ንብረት አልባ በመሆን፤ማንነቱ ተነጥቆ ግለሰብ/ሲቲዝን የመንግስት ጥገኛ/ጢሰኛ፤ተከራይ/ዲፐንዳንት እንዲሆንና “ኗሪ/ቡድን/ግለሰብ አሜን ብሎ ለላብ አደር ዓለም ዓቀፋዊነት መርሆ እንዲገዛ” ፤  ‘አንዱ ቡድን መሪ አንዱ ቡድን ተመሪ ሆነው፤ በስሩ፤ በማአከላዊት ትዕዛዝ እየተመሩ “ሌላወን ክፍል” እንዲጨቁኑት ነበር ያስተማረውና የታገለው። የታገለው ለማን ነበር? ለሥልጣን!? የማን ሥልጣን? “የላብ አደሩ” የበላይነት ሥልጣን! አይደለም እንዴ!? 

ለያይቶ አንዴ በጋራ ተቧድኖ አንዱን ክፍል መጨቆን፤ አንዴ ደግሞ ‘ላብ አደሩ አምባገነን ሆኖ ሁሉም በስሩ ለይ ሰጥ ብሎ አንዲገዛ መጨቆን፤ አንዴ ደግሞ ገበሬውና ላብ አደሩ ተቧድኖ በሃብታሙና በከተሜው አንዲዘምት ፤ የላብ አደሩ ፓርቲ የበላይነት አንዲኖረው፤ መሪ አንዲሆን ፤ዜጎች “ተጨቋኞች ሆነው” አንዲገዙ የሚሰብክና የታገለ መርሆ ነበር። ይህ የማርክሲዝም ትምህርት ነው። አሲምባዎች ትንሽ ሳያፍሩ “የአይጥ ምስክሩ ድምቢጡ” እንዲሉ ሆነና ገብሩ አስራትን ለእማኝነት ምስክራቸው ሲያመጡ እንዲህ ይላሉ፡

ከገብሩ በፊት ግን አሲምባዎች አንዲህ ይሉናል፤
“ከሁሉም በላይ ግን በኢትዮጵያዊነት ላይ ከማንም ሰይጣን ጋር አልተደራደረም።” አሲምባዎች ቀልደኞች ናችሁ ጃል!!!!!!
 አልተደራደረም? ድርጅታችሁስ ስለ በኢትዮጵያዊነቱ ስለ መደራደሩ ይቅርታ አልጠየቀም? ወይስ ስለምንድነው ይቅርታ ጠየቀ አስተካከለ የሚባለው?  ከኤርትራዊያን ጋር ወግኖ ዛላምበሳ ላይ በሃይል ተገድዶ የዘመተን ምስኪን ምሊሺያ ገበሬ ላይ ተኩሳችሁ አልፈጃችሁም? መሪያችሁ ክፍሉ ታደሰ እኮ ነው የነገረን! ወያኔ ምጽዋ ላይ ያደረገው የቅጥረኛነት ተሳትፎ-ታሪክ ኢሕአፓ ዛላምበሳ ላይ አልፈጸመም? የኤርትራን ነፃነት ከመደገፍ አልፋችሁ አልታገላችሁም? 

ፕሮግራማችሁ እንዲህ ይላል “ከማወቅ ባሻገር የኤርትራ ሕዝብ ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል መደገፍ ነው” ይላል። ከነሱ ጋር ወግናችሁ ነበር ወደ ኢትዮጵያ ሚሊሺያ ምስኪን ገበሬ ያነጣጠራችሁት። ለምን እኔን መጎነታተል መረጣችሁ? ለመወያት ከሆነ፤ ሃቁ ይሄው ነው።

ደግሞ ትንሽ አታፍሩም “የአይጥ ምስክሩ ድምቢጡ” እንዲሉ እንዲህ ትላላችሁ 
 “ከሁሉም በላይ ግን በኢትዮጵያዊነት ላይ ከማንም ሰይጣን ጋር አልተደራደረም። ለምሳሌ የወያኔ አንዱ መሪ የነበረው ገብሩ አሥራት በቅርቡ በጻፈው መጽሐፍ ገጽ 54 ላይ እንዲህ ይላልለ-“   ትላላችሁ፦
ኢሕአፓ በፕሮግራሙ ውስጥ የኢርትራ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት ከመግለጹም በላይ በዴሞክራሲያ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ከሰላማዊ ድርድር ውጭ ሌላ መፍትሔ ማፈላለግ ዕልቂት እንጂ ሌላ ውጤት እንደማይኖረውም በተደጋጋሚ ይገልጽ ነበር። ይህ የኢሕአፓ አቋም የኤርትራን ድርጅቶች የሚያረካ አልነበረም። የኤርትራ ድርጅቶች ኢሕአፓ በሁለት ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም እንዲኖረው ይፈልጉ ነበር። አንደኛው አቋም የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት መሆኑና ቅኝ ገዥዋም ኢትዮጵያ እንደሆነች መቀበል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጥያቄው በኤርትራ ነጻነት መፈታት እንዳለበት መቀበል ነበር። እነዚህን ሁለት አቋሞች ከኢሕአፖ ሊያገኙ ባለመቻላቸውም የኤርትራ ድርጅቶች በኢሕአፓ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬና ጥላቻ ነበራቸው….” ወረድ ብሎ በዚሁ መጽሐፍ ገጽ 135 ላይ ለምሳሌ ከኢሕአሠ ተገንጥሎ ወደ ወያኔ የተቀላቀለው ጦር (እነ ታምራት ለይኔ፣ ሕላዊ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሣ፣ ያሬድ ጥበቡ (ጀቤሳ) ኃይሌ ጥላሁን፣ በረክት ስምዖንና አዲሱ ለገሠ ኢሕዴን ብለው በሰየሙት ድርጅት አማካይነት የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ነው ብለው ተቀብለዋል ብሎ ያቀርባል። የአሲምባ ድሕረ-ገጽ ዝግጅት ክፍል” ይላል ለምስክርነት የመረጣችሁት ገብሩ አስራት፦

እኛ ትግሬዎች “ሁለት ጉድጓድ የማሰች አይጥ መውጪያዋን አታጣም” እንላልን። ገበሩም እናንተም ሁለት ጉድጓድ በመማስ ለማመምለጫ እንዲመቻችሁ ሁለታችሁ ታሾፋላችሁ። ለምን ነበር የማሻሻ ለውጥ አድርገናል ያላችሁት? ገብሩ ይህን ማሻሻያ ነው እየዋዠቀ ያለው ወይስ ፕሮግራማችሁ እውን አላነበበም ነበር? 

ግንጠላን በማስተማር!፤- ኢሕአፓ/ዋለልኝ “ግንጠላን” የችግር መፍቺያና የመውጪያ ጉድጓድ ምንጭ አድርገው አስተምረዋል። ማርክስዝም የተከተለው ርዕዮት ግንጠላ ለጭቆና እንደ መፍትሔ አድርጎ አስተምሯል። ወያኔ የማርክሲዝን ትምህርት ተከትሎ በ1968 የፋሺዝም/ማርክሲዝን መግለጫ ሲያወጣ፤ ኢሕአፓ ደግሞ በ1976 ከ8 አመት ቆይታ በሗላ ማለት ነው፤ የኢትዮጵያ ሉአላዊነትን በሚጻረር መልኩ ፤ መገንጠልን በፖለቲካ ፕሮግራሙ አካትተ ብቅ አለ። ወያኔ “ጨቋኛ ብሔር” እያለ (1968) ሲያስተምር ኢሕአፓ ደግሞ “ጨቋኙ ብሔር” ሲል ያንን የወያኔ/ትሓህት ፕሮግራም በመደገፍ በ1976 ኣ/ም በፕሮግራሙ ነድፎ አሰራጭቷል። “እንዴ? !!!!!!! በሉ መሪጌታ ሃይሉ” ይላሉ ትግሬዎች። “እንዴ? !!!!!!! አሉ መሪጌታ ሃይሉ”


  
የአሲምባ ፈላስፋዎች ፕሮግራማችሁ ሳልቀንስ ፤ሳልጨምር እንዳለ እንድታነብቡት ልጥቀስ፤
“የጭቁን ብሔሮችን የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብት/እስከ  መገንጠልና የራሳቸው የሆነ ነፃ መንግስት እስከ ማቋቋም ድረስ  መከበር እንዳለበት ማስተማርና መታገል አንዳለብን ሁሉ ጭቁን ብሔሮች በፈቃደኛነትና በእኩልነት “ከጫቋኝ ብሔር” ሰፊው ሕዝብ ጋር መዋሃድ እንዳለባቸውም ማስተማርና  መታገል አለብን።” ሲል የወያኔን የ1968 ንቱን የፖለቲካ ፕሮግራም ኢሕአፓ በ1976 ከ8 አመት ቆይታ በሗላ ፎቶ ኮፒ ትክክለኛ ግልባጭ በፕሮግራሙ አስፍሮታል።  ገጽ 23 እና 24 ….ይመልከቱ።
ታዲያ ጌታቸው ረዳ ፤አንድነታችን እንዲጠነክር ተቻችለን ለመኖር ስንል ባሞግሳችሁ እራሴ ላይ ወጥታችሁ ዋለልኝ ለምን ተነካ ብከላችሁ እኔን በማሾፍ ‘ሊቅ” እያላችሁ መጎነታታል ምን አመጣው? እንዴ! ትንሽ አታፍሩም? ይህንን ግንጣላ እንዳስተማራችሁ እያወቃችሁ “ያ ትውልድ” ለምን ተነካ፤ ትላለችሁ እንዴ?
አዎ! ያ ትውልድ “ጨቋኝ ብሔር” ሲል አማራ ማለቱ ነው፡ ሌላ ሊሆን አይችልም። እንዳለ ከዋለልኝ በበሳ መልኩ በፕሮግራሙ ቁልጭ አድርጎ መግለጹ ብቻ ሳይሆን ፤

ኢሕአፓ ኤርትራንም በፕሮግራሙ መርሆ ተደግፎ እንደዚህ ይገልጻታል፡
“የኤርትራ ሕዝብ የራሱን መብት በራሱ የመወስን እስከ መገንጠል ከማወቅ ባሻገር የኤርትራ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከ መገንጠል ድረስ  ያለውን መብት ከማወቅ ባሻገር የኤርትራ ሕዝብ ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል መደገፍ ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ የድርጅቱ አቋም ሆኗል። ……የኤርትራ ሕዝብ ነፃነቱን አረጋግጦ የራሱን መንግስት  ለመመስረት  የነበረው  ፍላጎትና  ለነፃነት ትግሉ ይሰጥ የነበረው  ድጋፍ ከፍተኛ ነበር።…” ይላል።
 ሆኖም የሗላ ሗላ፤ አውነትና ንጋት እያደረ ሲጠራለት  ኤርትራን ችግር በመገንጠል ሳይሆን “በፌደራል ሩፓብሊክ” መፈታት አለበት ይላል። ፌደራል ሪፓብሊክ ምን ማለት እንደሆነ ባያብራራውም። ይህ ይበል እንጂ የሐገሪቱ ሉዓላዊ የወደብና የመሬት፤ እንዲሁም የሕዝብ ቁርኝት በሚመለከት እርማት አድርጌአለሁ ባለው እርማት ላይ የተጠቀሱት ሉዓላዊ ጉዳዮችን በሚመለከት የመጠየቅ መብታችን በግልጽ  አላብራራም።  
ታዲያ ያ ትውልድ ጫቋኝ ብሔር በሌለበት “ጨቋኝ ብሔር” ነበር እያለ የወያኔ ትክከለኛ ቅጂ ቀድቶ “የተቀሩት ብሔር ብሔረሰቦች” ብሎ ኢሕአፓ የሚጠራቸው “በጫቋኙ ብሔር”  ላይ “ትግል አንዲያካሂዱ” ካልሆነላቸው ደግሞ “እንዲገነጠሉ” የሰበከን ያ ትውልድ በተመለከተው መነጽር መመልከቱ እንዴት ስሕተት ሊሆን ይችላል? ይህ ፍልስፍና ያመጣው ሰበብ አሁንም አገሪቷን እያመሳት ስለሆነ፤ እኔ ይህንን አንስቼ መነጋገሪያ ማድረጊዬ በምንም መልኩ አሲምባዎች ሽርደዳ ውስጥ መግባት አልነበራችሁም።     
አዎ ያ ትውልድ ትምህርት ዘረኛነትን ሳይሆን ጭቆናን ፤አምባገነንነትን አስተምሯል። ዘረኝነት በሌላ መለክያው የወያኔን አይነት እስከ መገንጠልን ሰብኳል። አንድ ሎችን ክፍሎች የጨቆነ “ጨቋኝ ብሔር” አለ ብለህ ስታስተምር “ ጨቋኝ በተባለው ብሔር ተወላጅ ላይ ጥላቻ አንዲነሳ መቀስቀስ ነው። ይህ ነው ኢሕአፓ ወያኔ ኦነግ የቀሰቀሱት ትምህርት “ነፍጠኛ/አማራ” (በዋለለልኝ አመርኛ) የሚባል “አንድ ጨቋኝ ብሔር” አለ ብላችሗል።  ስለሆነም ጨቋኝ ብሔር ብላችሁ ባስተማራችሁት ቅስቀሳ ውጤቱ “የአማራን በነፍጠኘነት” ስም መለያ መስጠትና ዛሬ እንዲባረር፤አንዲጨፈጨፍ ሰበብ ሆኗል።  አንድ ዜጋ፤ወይንም ግለሰብ በቡድን አንዲረገጥ ያ ትውልድ  እስተምሯል። ለዚህ ነው አሁንም ቡድኖች እነሱን በማይመስል (ላብ አደር፤አርሶ አደር፤ ብሔር፤ብሔረሰብ፤ሕዝብ……) ልዩ ክፍል ካለ ለጥቃት፤ለመረገጥ ምክንያት ሆነ እየተባረረ፤እየተገደለ ንብረቱ፤ንግዱ እየተቀማ ያለው።
የአሲምባ ፈላስፎች በጽሑፌ ከተስማሙ “ጥሩ” አበቃሁ በዚህ እደመድመዋለሁ ማለት ነው።  ካልሆነ ግን በሚቀጥለው ጽሑፌ ማርክሲዝም ማለት ፋሺዝም መሆኑንና ስለ ዋለልኝ በጻፍኩት ላይ ሁለት የኢሕአፓ ምሁራን ከጥቂት አመታት በፊት የጻፉትን ለኔ በዋለልኝ የሰጠሁትን  መልስ ተብሎ  ባለፈው ወቅት አሲምባ ድረገጽ ላይ የተለጠፈው በዝርዝር አብራራለሁ። ለሁለም ኳሷ ለነሱ ሰጥቻለሁ። እንቀጥል አንቀጥል፤ የናንተ ጉዳይ ነው። እውነት የመጻፍ ነጻነት ትርጉሙ ቢገባችሁ ኖሮ፤ የናንተ እና የመሪዎቻችሁ ጽሑፍ ስትለጥፉ አብሮ የኔንም መልስ እና ትችት በድረገጻችሁ መለጠፍ ነበረባችሁ፤ አለመታደል ሆኖ፤ ያንን ለማድረግ አልፈቀዳችሁም። ወደዳችሁ ጠላችሁ የኔን መልስ ከድረገጻችሁ ለመሸሸግ ብትጥሩም፤ ከቁጥጥራችሁ ውጭ በሆኑ ድረገጾች ከኢትዮጵያዊያን አንባቢዎች (ከወዳጅም ከጠላትም) ዓይን ልተጋርዱት ከቶ አይቻላችሁም። ደግነቱ እንኳን መንግሥት አልሆናችሁ። መንግስት ብትሆኑ የኔን ጽሁፍ እንዲህ ከሕዝብ እይታ የሸሸጋችሁት ፤ በላብ አደር ፓርቲ እየተመራችሁ እመንግስት ሥልጣን ላይ ወጥታችሁ ብትኖሩ ኖሮ፤ በአካል ምን ታደርጉኝ ኖሯል? ትግሬዎች እንዲህ ይላሉ “ንዘረባ አስተውዒልካ፤ ንእኽሊ ኣኾምሲዕካ” ይባላል (ስትናገር አስተውለህ ስትበላም አኝከህ” ይላሉ።  አበቃሁ!
አመሰግናለሁ፤
ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay) October 12, 2015