Monday, June 29, 2009


የትግራይ ምሁራን እና የወያነ ትግራይ ሰመመን ፍቅራቸዉ ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com ዛሬም ይህ ዓምድ ይዞላችሁ የቀረበዉ ካለፈዉ የቀጠለ ተከታታይ ዓምድ ሆኖ፣ በየጎሳ ፖሊሲ እየታመሰች ያለችዉን አገር ምን ብናደርግ መከራዉ ባጭሩ ሊቀጭ ይችላል? ከሚለዉ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እና አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ በነጻነት ራዲዮ አንስተዉት የነበረዉን ዉይይት የሚመለከት ነዉ፣፣ እንደምታስታዉሱት በዉይይታቸዉ ላይ ብዙ ቁም ነገሮችን ተወስተዋል፣፣ አካባቢን ቋንቋን ባማከለ የተዋቀረዉ የወያነ ትግራይ መንግሥታዊ አስተዳዳር ሃገሪቱ ወደ ከፋ ትርምስ እና ቀዉስ ይዟት ከመሄዷ በፊት የትግራይ ምሁራን/ኢሊቶቹ ስርዓቱን የመቃወም ሓላፊነት ቸል ብለዉታል ብቻ ሳይሆን ሆን ብለዉ የሥርዓቱ ጠበቆች እና ገምቢዎች እንደመሆናቸዉ መጠን ለብዙ ዓመታት የዘለቀዉ የወያነ ትግራይ ደጋፊነታቸዉም ሰብረዉ የመዉጣት አቅማቸዉ አሁኑኑ ማሳየት እንዳለባቸዉ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ አጥብቀዉ እንዳስገነዘቡ ተከታትለናል፣፣ በሌላ በኩል የመለስ ዜናዊን መንግሰሥት በሕግ አማካሪነት እያገለገሉ ቆይተዉ “ኢሕአዴግ” ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ ከላካቸዉ በሗላ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ እዚሁ አሜሪካ በመቅረት ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሕግ ሞያ ተሰማርተዉ የሚኖሩት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊም “ከሌላዉ ጎሳ በተለየ ለምን የትግራይን ምሁር እና የትግራይ ተወላጅ ብቻ በዚህ እየተወቀሰ ዓይን ዉስጥ ታስገቡታላችሁ? ወዘተ….የሚል ክርክር አንስተዉ መከራከራቸዉንም ጭምር እናስታዉሳልን፣፣ ሥርዓቱ በፈጠረዉ የጎሳ ፌደራሊዝም ምክንያት በመዋደድ እና በመከባባር በጋብቻ እና በፍቅር ተሳስሮ አምላኩን እያመሰገነ በግብርና ሞያ ተሰማርቶ በሰላም ሲኖር የነበረዉ ኢትዮጵያዊ አራሽ የገበሬዉ ሕብረተሰብ ለግጭት እንደዳረገዉ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ያብራሩትን የተከሰተዉ ሁኔታ ግልጽ እንዲሆንላችሁ ባለፈዉ ሰሞን ዓምዳችን ላይ፣- በወያነ ትግራይ ፖሊሲ ምክንያት በአማራዉ ሕዝብ ላይ የተነጣጠረ ጥቃትም በፎቶግራፍ የተደገፉ የግጭቱ ሰለባዎችና ሰለባዎቹ የደረሰባቸዉ ጥቃት ሞትና መፈናቀል ከአንደበታቸዉ የተገኘዉ ቃለ መጠይቅ በማስረጃ አስደግፌ እንዳቀረብኩም ይታወሳል፣፣ በስፋት የተቸሁበትን ያለፈዉ ሳምንት ዓምድ በማስታወስ ከዚያዉ በመነሳት ጥሪዉ “የትግራይ ምሁራን ለምን በብዙ ሰዎች ሕሊና እንዲተኮርባቸዉ ሆነ?” ለሚለዉ እሮሮ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም የወያኔ ፖሊሲን ከመደገፍ ይልቅ የትግራይ ምሁራን ወደ ኢትዮጵያዊነት ጎራ እንዲቀላቀሉ ከመቸዉም ጊዜ ዛሬ ጥሪዉ የበረታበት ምክንያት አገሪቱ ከቀዉስ ወደ ቀዉስ እየተረማመደች እንደመሆንዋ መጠን፣ ወያኔም በትግራይ ተወላጆች ድጋፍ ደም እና ላብ ተመስርቶ የተገገነባ ድርጅት በመሆኑ፣አገር ዉስጥ ያለዉን የትግራይ ሕዝብ ላሁኑ ወደ ጎን በመተዉ ለዛሬ የምናተኩረዉ ዉጭ አገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንደሚታወቀዉ ከወያኔ ቁጥር ዉጭ ቢሆኑም፣ አብዛኛዉ የወያኔ ደጋፊዎች እንደነበሩ ይታወቃል፣፣ ወያነ ለሁለት ከተሰነጠቀ በሗላ ግን ከአንድነት ሃይሎች ጋር የጋራ ዉይይት መስርተዉ አንዳንዴም ለኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች የገንዘብ ዕርዳታ እያደረጉ ግንኙነታቸዉ በማጠንከር ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል አሳይተዉ ነበር፣፣ከጊዜ በሗላ ግን ተመልሰዉ ወደ እዛዉ ወደ ወየኔ ቀስ በቀስ ወደ መለስ ጎራ ሲቀላቀሉ አብዛኛዉ ክፍል ግን ወደ ገብሩ አስራት “የዓረና ወያኔ”፣ ደጋፊ በመሆን የፋሺስቶቹ የአንቀጽ 39 ድጋፍ ሰጪዎች ሆነዉ አረፉት፣፣ በዚህም ድጋፋቸዉ አሳሳቢነት ምክንያት ነዉ ዛሬም በጎሳ እና በወንዝ ልጅ ዙርያ ያለዉ ጠባብ ጭንቅላት እና መሰባሰብ ሰብረዉ መዉጣት ካልቻሉ ከመቸዉም በበለጠ አሳሳቢና አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኖ መቀጠሉ አይቀርም የምንልበት ምክንያቶች አሉን ፣፣ በዚህ ዓምድ የምንመለከተዉ የትግራይ ተወላጆች/Community (መሰረታዊ ማሕበራት የሚሉዋቸዉ) እና የትግራይ ምሁራን ሊሂቁ/ኤሊቱ እንዴት የወያኔ መገልገያ ሆኖ እንደቆየ ማሕደሩን እንፈትሻለን፣፣ ለዚህም በርካታ የትግራይ ተወላጆች የሚሰጡት መከራከያ “ምሁሩ ዝም ስላለ ወያኔን ደግፏል ማለት አይደለም”፣ እያሉ “ከናንተ ከአንድነት ሃይሎች ስንት ኦሮሞ ስንት ጉራጌ ስንት ሶማሌ ስንት …ስንት,…. ስንት….. በቁጥር ጸረ ወያኔ ሆኖ በግልጽ የሚቃወም ኖሮ ነዉ የትግራይን ምሁር/መሰረታዊ ማሕበራትን ዓይን ዉስጥ ለማስገባት የምትሞክሩት? ትግል በጎሳ እየተቆጠረ ‘ከእገሌ ስንት መጣ ከእገሌ ስንት ጩኸቱን አሰማ… እየተባለ ሳይሆን በፍላጎት ነዉ ትግል የሚቀጥለዉ” የሚሉት “አዲስ አዚም” የመከራከሪያ ነጥብ ይዘዉ “Defensive” (የማምለጫ መአዘን/መጠምዘኛ)መሸሽያ በመፈለግ ሲከራከሩ የሚደመጡት ወንድሞቻችን ስሕተታቸዉን ለማሳት ካለፈዉ ማሕደራቸዉ እንጀምራለን፣፣ ከሁሉም እስገራሚዉ ጉዳይ ደግሞ የባሕር ወደብ እንድናጣ ተከራክሮ እና ለጠላት ወግኖ ተዋግቶ አገሪቱን አምቆ ያስጨነቃት አደገኛ ቡድን ወያኔ መሆኑን ቢያዉቁም “የተቃዋሚ ሃይሎች ደጋፊም፣ተቃዋሚም አይደለሁም፣ የመንግሥት ደጋፊም ተቃዋሚም አይደለሁም” የሚለዉ ሌላኛዉ የልደቱ አያሌዉ ዓይነት “አዲስ ፈሊጥ” እነኚህ የትግራይ ተወላጆችም ይህንኑ ጅላጅልነት በማስተጋባት አቅጣጫቸዉ ሁሉ ከመቸዉም አስቸጋሪ እየሆነ ስላገኘነዉ፣ የደረስንበት ግንዛቤ አብዛኛዎቹ የትግራይ ምሁራን ለጠባብ ጎሳ (ናሮዉ ናሺናሊዝም)ያላቸዉ ፍቅር ከዉስጥ የተከናነበ በሃይለኛ ያካባቢነት ሰሜት የሚሰቃዩ ናቸዉ ወይንም በግልጽ የወጣ ጎሰኛነት እያጠቃቸዉ ነዉ፣ ወደ ሚል ድምዳሜ ያደርሰናል፣፣ ለዚህም መስረጃዎቻችን ከማሕደሮቻቸዉ ፈትሸን የት ነበሩ አሁንስ የት ነዉ ያሉት? ለሚለዉ መልስ የምናገኘዉ የትግራይ ምሁራን ኢትዮጵያዊያን ወላጆቻቸዉ የእነ አሉላ አባ ነጋ የነ ዮሐንስ አጥንት እና ደም የፈሰሰበትን የምጽዋን ዶጋሊን መሬት እና ባሕር ከጠላት ጋር ወግኖ ኢትዮጵን ወግቶ የትግራይ ህጻናትን እንደ ሙሶሎኒ በቦምብ ለደበደበዉ ለሻዕቢያ ወደቦቻችንን ተከራክሮ ላስረከበ “ለህዝባዊ ወያነ ሓርንት ትግራይ” ያለ ምንም ሓፍረትና ድጋፍቹን በመለገስ እንኚህ ምሁራን ለዚህ ድርጀት ያላቸዉ ያልተሸራረፈ የሰመመን ፍቅር ያሳዩበትን “አሳፋሪ ማሕደራቸዉ” መፈተሽ የነበሩበትን እና አሁን የቆሙበት መድረክ ለመረዳት እንዲያስችለን ላንዴም ቢሆን ወደ ሗላ መለስ ብለን መፈተሽ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፣፣ ከዚህ በታች የሚቀርበዉ ዓምድ “የትግራይ ምሁራን አሳፋሪ ማሕደር” ከሚለዉ አምዳችን ቀንጭቤ አንዳንዱን ለናሙና ላቅርብ፣፣ ታሪክ ዘጋቢዎችም ለምትጽፏቸዉ ታሪካዊ ሰነዶች ይረዷችሁ ዘንድ እነሆ፣፣ በቅድሚያ ቀንጨብ አድርጌ ለናሙና የማቀርበዉ የትግራይ መሰረታዊ ማሕበራት ወያኔ እንዴት ይገልገልባቸዉ እንደነበር አዲስ አበባ ሲታተም በነበረዉ በዜጋ መጽሄት በቁጥር አንድ መስከረም ጥቅምት 1994 ዓ.ም (በፈረንጅ 09/05/2001) ብርበራ በተባለዉ ዓምድ “ጋዶ እዩ! ጋዶ! ጋዶ! (የሁሉም ደጋፊዎች አይደለንም?) በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ዉጭ አገር በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መሰረታዊ ማሕበራት ተጠሪዎች ወያኔዎች ለሁለት ሲሰነጠቁ ያስደመጡን አቋማቸዉ ምክንያት አድርጌ እላይ በተመለከተዉ ርዕስ በወቅቱ እኔ የተቸሁበት አምድ አንዷን ክፍል በጥቅስ ይቀርባል፣፣ ሌላዉ ሁለተኛዉ ደግሞ “ትግራይን ለማዉደም ለምን ፈለጋችሁ? ከትግራዊያን ፕሮፉሽናሎች” በሚል የቀረበ ጋዜጣዊ መግለጫቸዉ ከሰፊዉ ሀተታቸዉ ጥቂት ነገሮችን ብቻ በመጥቀስ አቀርበዋለሁ፣፣ ሦስተኛዉ በጣም ጠቃሚ የነበረዉ በዜጋ መጽሄት የታተመ “ሃሎ! ሃሎ! መቐለ ድዩ? ሃሎ! ሃሎ!መቀሌ ነዉ? በሚል ርዕስ የጻፍኩትን ያኔ ወያኔ ተሰነጠቀ ሲባል የትግራይ ተወላጆች ከዓለማቱ ተሰባስበዉ ያሰሙት በጣም አስገራሚ የሆነ የተሰማቸዉ ድንጋጤ የሚያንጸባርቁ ልዩ ልዩ መግለጫቸዉን ላቀርብላችሁ ብየ መጽሄቱ ብፈልገዉ ለጊዜዉ አላገኘሁትም፣፣ ሲገኝ ሌላ ጊዜ አስነብባችሗለሁ፣፣ አሁን ወደ ሁለቱም መረጃዎች እንለፍ፣፣መጀመሪያ ከኔዉ ሕትምት “ጋዶ እዩ! ጋዶ! ጋዶ!የሁለቱም ደጋፊዎች አይደለንም?” ከሚለዉ ቀንጭቤ ላስነብባችሁ፣ “……አብዛዠኛዎቹ ዉጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለድርጅቱ/ለወያኔ ፖሊሲ ዕድገትና ጥንካሬ የመንፈስ፣ የሰዉ ጉልበት እና የቁሳቁስ ድጋፍ በመለገስ ድርጅቱን የአትክልት “ዉሃ” ሆነዉ ይህ ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን አሁን ወደ አደገበት ደረጃ እንዲያድግ ያልተቆጠበ ድጋፍ ለረዢም ዓመታት ድጋፍ ሰጥተዋል፣፣ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ከወያኔ ጋር ያላቸዉ ግንኙነት “ከልማት ያላለፈ ግንኙነት” እንዳልነበራቸዉ ይገልጻሉ፣፣ እያንዳንዱ መሠረታዊ ማሕበራት ለትግራይ ልማት ዕድገት ሰበብ ሲሰባሰብ፣ በልማት ስም ጎሰኛነትን እንዲጠነክር መግቢያ በር እንደነበር ካንዳንዶቻችን የትግራይ ተወላጆች ዓይን እና ሕሊና የተሰወረ አይደለም፣፣ በትግራይ ኮሚኒቲ የልማት ስብሰባ በሚዘጋጁት መድረኮች ወያነ ትግራይ የዉሸት ሰበካ በማሰራጨት ለኢትዮጵያ ብሔረሰቦች የፍትህ፣የልማት ዕድገትና እኩልነት እንዳጎናጸፋቸዉ የሚሰብክበት መድረክ እንደነበረም መረጃ ማቅረብ ይቻላል፣፣ መሰረታዊ ማሕበራት የሚላቸዉ የሴቶች፣የወጣቶች ማህበራት ሁሉ በልማት ስም የስርዓቱ አቀንቃኞች መጠቀሚያ እና የዉሸት ቅስቀሳ ማስተጋቢያ መስመሮች/ቻነሎች ሆነዋል፣፣ ለምሳሌም አንድ ማስረጃ ለማቅረብ ከተፈለገ “አቶ ካሕሳይ በርሄ “The national Movement in Tigray Myth and Realities –February 1991)(ብሔራዊ እንቅስቃሴዉ በትግራይ አፈታሪክ እና እዉነታዎች-1983) በአቀረቡት ጽሁፋቸዉ ላይ እንዲህ ብለዉ ነበር፣፣ “ብዙሃኖቹ ድርጅቶች በዉጭ ከህወሓት ጋር የተቆራኙ የተለያዩ የትግራዊያን ማሕበራት በዚሁ ድርጅት ለሚመራዉ ብሔራዊ ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፣፣ ከየግል ገቢዎቻቸዉ የሚያዋጡት ወርሃዊ የገንዘብ መዋጮ የፕሮፖጋንዳ ሥራ (ዉጭ ሰዎችን በመቀስቀስ እና በማሰባሰብ) ከሕወሓት የማሰባሰቢያ ድርጅት ሥር ሆነዉ እንዲሰሩ ለማድረግ፣ ወዘተ…ከፍተኛ ሚና ተጫዉተዋል፣፣ በዉጭ የሚገኘዉ የትግራይ ማሕበረሰብ ከሁሉም በላይ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠዉ አስተዋጽኦ ያደረገዉ ለ1977-78 ዓ.ም. የሕዝብ ረሃብ በሰጠዉ ወደር የለሽ ምላሽ ነበር፣፣ ከግል ገቢያቸዉ ካዋጡት ጠቀም ያለ መዋጮ ሌላ የገንዘብ ማሰባሰብያ ዝግጅቶችን በያካባቢዉ በማድረግ ዝናብ እና የበረዶ ክምር በሚያስቸግሩባቸዉ ወቅቶች፣ በአዉሮጳ እና በአሜሪካ አዉራ ጎዳና ላይ ከአላፊዉ አግዳሚዉ ገንዘብ አሰባስበዉ በጣም ከፍተኛ ገቢ አስገኝተዋል፣፣ በትግራይ የተከሰተዉን የረሃብ መቅሰፍት ለማስወገድ በርካታ የትግራይ ልጆች ሥራቸዉና ትምህርታቸዉን መስዋእት አድርገዋል፣፣የትግራይ ምሁራንም የዕርዳታ ድርጅቶችን በማነሳሳት እና በማስተባበር የአስቸኳይ ጊዜዊ ዕርዳታ ሊገባ የሚችልበትን ስልት በመቀየስ ብዙ አስተዋጽኦ አድርገዋል፣፣ በብሔራዊ ትግሉ ፖለቲካ እና ድርጅታዊ ሕይወት ዉስጥ እኒህ ማሕበራትም ልክ በነፃዎቹ ክልሎች እንዳሉት ብዙሃን ድርጅቶች ሁሉ ተሳትፎአቸዉና ሚናቸዉ የተጠናከረ ሳይሆን በጣም ዉሱን የነበረ ነዉ፣፣ ህወሓት እንዚህን ማሕበራት የተሳሳቱ መረጃዎችን በመስጠት በአሻጥርና በተንኮል፣ በማስፈራራት እና ከሕብረተሰቡ በማግለል የገቢ ምንጭ እና የዝምታ አሜን ባዮችና ተመልካቾች ብቻ ሆነዉ እንዲቀሩ ለማድረግ ተችሎታል፣፣ “ኢትዮጵያዊያን ራሳቸዉን ለማደራጀት የሚያደርጉትን ማንኛዉንም ሙከራ ለማሰናከልና ለማምከን ህወሓት እንደ መሣሪያ ይጠቀምባቸዋል፣፣” (ቅንፍ እና ኢታሊክ የኔ) ባጠቃላይ በዉጭ የሚገኙ በርካታ የትግራይ ካሉ ዘመዶቻቸዉ ጋር ለመገናኘት ሚችሉት በህወሓት በኩል ሲሆን ብቻ ነዉ፣፣ ይህንን አጋጣሚ/ሁኔታ በመጠቀም ለብዙሓን ማሕበሮቹ በድርጅት አባልነት እንዲመዘገቡ ተጽእኖ ያደርግላቸዋል፣፣ ያስገድዳልም፣፣ ማንም ከዉጭ የመጣ እና በትግራይ ያሉትን ዘመዶቹን ለመጠየቅ የሚፈልግ ሰዉ (ሴት -ወንድ) ከመጣበት ሃገር ካለዉ የህወሓት ብዙሃን ማህበራት የመሸኛ ደብዳቤ ከያዘ እና ሱዳን ከሚገኘዉ የህወሓት ጽ/ቤት ማቅረብ እና ማረጋገጥ ከቻለ ብቻ ነዉ ወደ ትግራይ የመግባት ፈቃድ ለሰጠዉ የሚችለዉ፣፣ ይህን ማድረግ ካልቻለ ወደ ትግራይ ሊገባ አይችልም, ማለት ነዉ፣፣ በእነዚህ የብዙሃን ማህበራት አባላት ዘንድ የህወሓት ፖሊሲዎች እና ኢዲሞክራሲያዊ ልምዶች የተቸ ሁሉ የትግራይ እና የትግሉ ጠላት ተደርጎ ታይቷል” (ትርጉም ጎህ 1985)፣፣ የትግራይ ሕብረተሰብ ማሕበራት ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አስከዛሬ ድረስ (በተመሳሳይ ሞኝነት “ገዛ ተጋሩ ፓል-ቶክ” “አይጋ ፎረም” “ዩትና” ተብለዉ በሚታወቀዉት መድረኮች በስሜት የሚጋልብ አባል የሚጨፍርበት ጨምሮ ያንኑ የዉሸት ቅስቀሳቸዉ ሕብረተሰቡ በስሜት እያጋለ የዉሸት ሰላባቸዉ እየሆነ እንዳለዉ ጭምር) የወያኔ የገቢ ምንጭ በልማት ስም የወያኔ የዉሸት ፕሮፖጋንዳ ማስጋቢያም ጭምር እንደነበሩ ከላይ ተመልክተናል፣፣ ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ “ትግርራይን ለማዉደም ለምን ፈለጋችሁ?” (ከትግራዊያን ፕሮፌሽናሎች) በሚል ለምኒሊክ መጽሄት ተልኮ በሚያዚያ 1993 የትግራይ ኤሊቶች/ምሁራን አንጃዉን በመደግፍ ለሕትምት ካበቁት አንዱን ላቅርብ፣፣ “በድርጊታችሁ የተበሳጨን ትግራዊያን ነን፣፣ እኛን ጣል እርግፍ አድርጋችሁ የጣላችሁንና የተከዳን ትግራዊያን ጓዶቻችሁ ነን፣፣ሕዝባችንና ድርጅታችንን ከልባቸዉ ከሚመኙትና ከሚጠይቁት ዓላማ ዉጭ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ዓላማና አጀንዳ የሌለን ትግራዊያን ፕሮፈሽናሎች ነን፣፣ ቁጣችንን በምንም ዓይነት መልኩ ማቀዝቀዝም ሆነ በሱኳር ማጣፈጥ አንችልም፣፣ከልባችን ቀጥተኛ የሆነ ንግግር እንዲኖረን እንፈልጋለን፣፣ ቁጣና ንዴታችንም እዚህ ላይ ነዉ፣፣ አቶ መለስ ጥቂት ጥያቄዎች አሉን፣፣ምን ዓይነት የጨለመ ተግባር ነዉ እየፈጸማችሁ ያላችሁት?ሕሊናችሁ አጥታችሗል እንዴ? ልበቢስ እንዴት ልትሆኑ ቻላችሁ? አለመጨነቅ፣ በጣም ሚዛናዊ አለመሆን፣ ኢትዮጵያችንና ትግራይን ለማዉደም የብረት ሳህን ላይ ለማስቀመጥ መቻኮል ለምን ፈለጋችሁ? ምን ያህል ደንታ ቢስ እና ሓላፊነት የማይሰማችሁ ናችሁ? ከሕዝባችን ጥቅም ይልቅ ራሳችሁን ጥቅም ማስቀደም እራስ ወዳድት እና ምን ያህል የሥልጣን ጥም ቢኖርባችሁ ነዉ? ከድርጅቶቻችን (ህወሓት እና ኢሕአዴግ) ከትግራይ እና ኢትዮጵያ ጥቅም አስፈላጊነት ዉጭ የሆነ ስራ ለመስራት እንዴት ፈለጋችሁ? የ40,000 ሰማዕታትን ለአረሜናዊ ኢሰብአዊ እና በተስፋ ለሚኖር ሥርዓት መስዋዕትነት ወደ ጎን መተዋችሁ ምን ያህል የሓዘን ስሜት የማይሰማችሁ እና ምን ያህል ዓላማ የለሽ ብትሆኑ ነዉ? የሕዝባችን ክብር ለማዋረድ ስትመርጡ ስታበላሹና በዉጪዉ ዓለም ዘንድ አስጊ ደረጃ ላይ መሆናችንን በሰሙ ሁሉ አስፈሪ የምታስደርጉን ምን ያህል ሕሊና ቢስ ብትሆኑ ነዉ? ምን ያህልስ ምክንያት ቢስ ሰዎች ናችሁ? ለክፈለ ዘመን ሕዝባችን ታግሎ ያገኘነዉን ድል ፍሬ አልባ በማድረግ እመቃብር አፈፋ ላይ እንዲዳረግ ስታደርጉት ምን ያህል ሓላፊነት የጎደላችሁ ብትሆኑ ነዉ? ኢፍትሓዊ የሆኑ ለመዋጋት ብዙ መሠረተ ልማቶችን በዓለም ደረጃ የጣለዉን ሕዝባችንን የሞት አፋፍ ላይ እንዲደርስ ስታደርጉ ምንስ ያህል ስሜት የለሽ ብትሆኑ ነዉ? “ጀግኖቻችንስ “የማያስፈልጉ”፣ “አፈንጋጮች”፣ “ሴረኞች” እና “በጥላቻ የተሞሉ” በማለት ዝናቸዉን የምታጠፉትና የምታዋርዷቸዉ ለምንድነዉ? እንዴት እንዲህ ልትሉ ቻላችሁ?የሕዝባችን ስቃይና ሰቆቃ ለማስቀረት ሲሉ የተሰዉ መሆናቸዉንስ እንዴት ዘነጋችሁት? የሰማዕቶቻችን ኑዛዜ፣ምኞት የመሞትስ ምክንያት መሆኑን ምን ያህል ልበ ቢስ ብትሆኑ ነዉ? ምን ያህል ከተያቂነት ነፃ ብትሆኑና ንቀት ቢኖራችሁ ነዉ? በሰማዕቶች ሞት የተመሰረተዉ ህወሓትሕግ መሪዎቻችን በህወሃት ሕገ መንግሥት ላይ ልትዘምቱበት የቻላችሁበት ምን አህል ማን አለብኝነት ቢሰማችሁ ነዉ? አቶ መለስ አስፈላጊ አይደለም ያሏቸዉ ሰዎች ለማገድና ዋጋ የለሽ ማድረግን ወይም የማዉረድን ሥራ ሲሰሩ ምን ያህል ሓላፊነት ቢጎልዎት ነዉ ብለን ልንጠይቀዎ እንፈልጋለን፣፣ እንደዚህ ማዋረድ ማንቋሸሽ ስም ማጥፋትና እገዳ አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን ለይ የሚጠበቅ ይመስለዎታልን? በህወሓት -ኢሕአዴግ በሃገራችን ደረጃ በእሳት ተፈትነዉ የወጡትን ጠቃሚ ጀግኖች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እና እንዲሁም አባቶቻችንና እናቶቻችን ላይ የጥላቻ ነበልባልዎን በመርጨት በማዛመት የሚገልጹት ለምንድነዉ? ለምን የነዚህ ጥሩ ሰዎችና ጀግኖቻችን በዓላማ የታነጸዉን ጥሩ ስም ለማጥፋት ለምን ፈለጉ? የእነዚህን የወያኔዎች አለኝታዎች ስም በማጥፋት፣ ለሰዉ መጥፎ አሳቢ እንዲመስሉ የተሳሳቱ እና በጥባጮች እንደደሆኑ አድርገዉ ይገልጿቸዋል? ሥልጣን በራስዎት መንገድ እንደካሁን ቀደሙ ያደርጉት እንደነበረዉ ሁሉንም ነገር በነፃነት የመስራት ጥማት አለበዎት? ለሕዝባችን ፍላጎት፣ለሐገራችን ጥቅም ለአርባሺዎቹ ሰማዕታቶች ሞት እና ዝክር-አልቆሙምን?የትግራይጀግኖችሲያገልሉ የሕዝባችንና የሰማዕቶቻችንም ከብር ማግለልዎ መሆኑንስ በቅጡ ተረድተዉታል? ተገንጣዮቹ ለእዉነት ለሕዝባችን ፍላጎት፣ለሃገራችን ጥቅም ለአርባሺዎቹ ሰማዕታቶች ሞትና ዝክር አልቆሙምን? ያቁሙ አቶ መለስ!! የእርስዎ የግል ፍላጎት ከሰማዕታቶች ከሕዝቡና ከሃገራችን ፍላጎትና ጥቀም ማስቀደምዎት ያቁሙ! “አቶ መለስ ያቁሙ!!..... አሁን አፈንጋጭ የሚሏቸዉ ሰዎች በአንድ ወቅት የሞሶሎኒን ርዕዮተ ዓለም ያራምዱ የነበሩትን ሰዎች ለመጣል የረጂም ጊዜ ትግልና መስዋዕት የከፈሉ መሆናቸዉን አያዉቁምን? ለምን ፋሺዝም በሕዝባችን ላይ እንዲነግሥ ፈለጉ? የክብራችን፣የማንነታችን ባህላችን መከታ በሆኑት ላይ የሚዘምቱበት ምክንያት ምንድ ነዉ?ለምንስ ነዉ ትግራይ የወለደቻቸዉ ብርቅየ ሰዎች ለማባረር የፈለጉት? ይመልሱ እንጂ አቶ መለስ፣የህወሓት ሊቀመንበር? ህወሓት ማለት ለትግራይ ሕዝብ ማንኛዉም ነገር ማለት እንደሆነ ልናስታዉስዎ ይፈልጋሉ እንዴ አቶመለስ?በመጀመሪያ በአቋማቸዉ ፀንተዉ እንዲቆዩ ያደረጋቸዉ ነገር ይህ ዕነቁ ነገር ነዉ፣፣ በዚህ ትልቅ እና “ዕንቁ ድርጅት” የፈለገዉ ዓይነት ሊከሰት ይችላል፣፣ ህወሓት ለህይወታችን ወሳን የሆኑና ዋና ዋና ዉድ ነገሮችን ሰጠን ብቻ ሳይሆን አንድ ህይወትን እራስዋን አድኖልናል ብንል ማጋነን አይሆንም.፣፣ ድርጅታዊ መርሕ አለን በራሳችን እንድንተማመን፣ጠንካሮች ጠንቃቆችና የሕግ ዜጎች እንድንሆን ትልቅ ትምህርት አስተምሮናል፣፣ የሕግ ሰዎች ብቻ እንድንሆን ብቻ ሳይሆን እኛን ለመከላከል የፍትሕ ምሰሶም አቁሞልናል፣፣ ተወዳጁ ድርጅታችን፣፣ ይህ ትልቅ የህወሃት የሕግ ምሰሶ፣ሕገ መንግሥት፣አካሄዶች፣ፕሮቶኮሎች (ሁሉ) የኛ ከለላ ነቸዉ፣፣ ይህንኑን ነዉ እርስዎ በመፈንቀልና እንዲጠላ በማድረግ የእኛን የወደፊት ሁኔታ ትልቅ ጉዳት እና አስጊ ደረጃ ላይ የጣሉት፣፣ በእነዚህ የተስፋ እና የፍትሕ ምሰሶዎች ላይ ነዉ እንደ መናኛ ነገር “ዕቃ -ዕቃ” እየተጫወቱባቸዉ እየሆኑ እንዳሉ ልናስታዉሰዎት ይፈልጋሉ? በጥንካሬያችን፣በተስፋችንና በፍላጎታችን ላይም… በሃገር ዉስጥ ላይ ባሉት ህዝቦች ብቻ ሳይሆን በመላዉ ዓለም ላይ ተበታትነን በምንኖሮዉም ላይ ዕቃ-ዕቃ እየተጫወቱብን ነዉ፣፣ በችግረኞች ትግራዉያን ሕዝቦች እና አርባ ሺሕ ሰማዕታት አርበኞች የተሰጡንን እንዚህ መሠረታዊ መብቶችን እንንከባከባቸዋለን፣፣በኛ በኩል ባሉት እነዚህ ምሰሶዎች፣ሚዛናዊ ጨዋታ ህልቆ-መሳፈርት የሌላቸዉን ምኞቶቻችን ተስፋዎች እናልማለን፣ ወደ ሃገራችን በመሄድም ለህዝባችን ዕድገት አስተዋጽኦ እናደርጋለን፣፣ እናም አቶ መለስ ያቁሙ! ይህን የሕዝባችን ሕልምና ራዕይ ወደ ገደል አይክተቱት፣፣ “… በእርስዎ መካከል እና እርስዎ “አንጃዎች”በሚሉዋቸዉ መሃል ምን እንደተፈጠረ እናዉቃለን፣፣ በምንም ዓይነት አንጃዎች አይደሉም፣፣በፍሰጹም! አቶ መለስ! በፍጹም “ተገንጣዮች አንጃዎች” አይደሉም! እዉነታዉ “ተገንጣዮቹ” ሕጉ በሰማእታት ደም እንደተጻፈዉ ሁሉ አክብረዉ ስለያዙት እና ከእርስዎ አፍራሽ ዓላማ ጋር ለመጓዝ ፈቃደኞች ባለመሆናቸዉና ከሰማዕቶቻችን ከሕዝባችን ለተረከብነዉ ሕግ ስለተገዙና አክብረዉ ስለያዙት ብቻ ነዉ፣፣ እኛ በተሻለ እናዉቃቸዋለን፣፣ እነዚህ ቀናኢ ወንድና ሴቶች ሰዎች፣ ሙሉ መስዋዕትነት የሚያደርጉ ጀግኖች እንደሆኑ እናዉቃለን፣፣ ለገንዘብና ለሥልጣን ብለዉ ሙስና የሚፈጽሙ እንዳልሆኑ ጠንቅቀን እናዉቃለን፣፣ለዚህም ነዉ እናንተ በፈረንሳይ ሱፍ ስትዘንጡና ፋሺን ስታማርጡ እነሱ ግምባር በነበሩበት ጊዜ የለበሱት ቲ- ሸርት አሁንም ድረስ ታንቀዉ ያሉት፣፣ከዚህ በላይ እንኚህ ትጉ ጀግኖቻችን ከመጀመሪያ አንስቶ ተወዳጁ ድርጅታችን የሆነዉ ህወሓት ከመመስረት ጀምሮ የሕዝቡን ንቃተ ሕሊና ከማነጽ እና በዛዉ ሳይወስን ድርጅቱን ወደ አስተማማኝ ደረጃ እንዲደረስ ከተረባረቡበት ወቅት ጊዜ ጀምሮ እናዉቃቸዋለን፣፣ አሁንም “ተገንጣዮቹ” “ተራሮችን ያንቀጠቀጠዉ ትዉልድ”The (Generation That Shook the Mountain)ናቸዉ”፣፣ ማለቂያ የሌለዉ የክርክር ባህል ምን ሆነ? የሃሳብ መረዳዳት እና አንድ ሃሳብ እና አመለካካት ላይ መድረስን ምን በላዉ? ቢያንስ ከተመሳሳይ መጽሓፍ የማንበብ ባሕል ማን ወሰደዉ? የድርጅታችን በራስ መተማምንና የሕዝባችን ምንጭ ምልዑነት ግን ሁሉም ነገር እንዲፈጠር አደረገ፣፣የድርጅታችን ፖሊሲ ለዚህ አብቅቷል፣፣መስፍን ኢንጂነሪንግ (ለሎች ኢኮኖሚ ተቋማትን) ብንመለከት ከማንም የኢኮኖሚም ሆነ የፖለቲካ ሃይል ወይም ከማንም ሀገር የተሰጠ አይደለም፣፣ የማይነቃነቀዉ መርሆአችን እና በራስ መተማመን እና ብሎም አንጸባራቂ ነፃነታችን የመንፈስ ፈጠራ ፣የጥሩ ዉጤት ምኞት የመስዋዐትንት ፍሬ (ያስገኘዉ) ነዉ፣፣ ለመሆኑ አቶ መለስ ለምንድነዉ ወንድም በወንድም እህት በህትዋ ላይ ፊት እንዲዟዟሩ ያደረጉበትን ሁኔታ ለምንድነዉ ሊፈጥሩት የፈለጉት? አቶ መለስ እንደሚያዉቁት፣ ህወሓት ካስተማረን በርካታ ነገሮች አንዱ “ሃቅን” መፈለግ ነዉ፣፣ ድርጅታችን ተጠያቂነትና ታማኝነት ያለዉ ሕሊና እንዲኖረን አስተምሮናል፣፣ እናም ህዝባቸን አንድን ነገር ከፊቱ አይቶ ሳይሆን መርምሮ እንዲገዛ አስችሎታል፣፣ በማለት የዛሬዎቹ ባለ አንቀጽ 39ኞቹ እነ ግበሩ አስራት በአንጃነት ከመለስ ዜናዊ ሲለያዩ የትግራይ ፕሮፌሽናል ነን የሙለት እነኚህ ከላይ ያስነበበቡን ደጋፊዎቻቸዉ ሰፊ እሮሮ ካስሰሙን በሗላ የመለስ ዜናዊ አስተዋጽኦ ናቸዉ በማለት ብዙ ነጥቦች ከዘረዘሯቸዉ ነጥቦች አንዱ እነኚህ ምሁራን ነን የሚሉት ሰዎች አሁን መለስን በሚከስሱበት ጉዳይ በወቅቱ እተደረገ በነበረበትም ሆነ ድርጊቱ ከተፈጸመ በሗላም ቢሆን ለበርካታ ዓመታት በመለስ መሪነት አምነዉ አክብረዉ ድጋፋቸዉ ሲለግሱ እንደነበር እናዉቃለን፣፣ አንደኛዉ ክስሳቸዉ እንዲህ ሲሉ መለስን ይከስሳሉ፣፣ “በእርስዎ ሰዓት (የስልጣን ጊዜ) ትልቁ ቁስል የሚሆነዉ የህወሓት ሙዚቀኞች ለኤርትራ ባንዴራ ክብርና ስም መዘመራቸዉ ነዉ፣፣ በትግራዊት እናት ክብር ሥም ሳይሆን ለኤርትራዊት እናት ዝና እና ክብር መዘመራቸዉ ነዉ፣፣ለኛዉ ታጋዮች ክብር ሳይሆን ለሻዕቢያ ታጋዮች ነበር የተዘፈነዉ፣፣ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል፣፣መቁጠሩ የሕመም ስሜት ያሳድራል፣፣ በእርስዎ ዘመን ምን ያልሆነ ነገር አለ? ….ስለዚህ በዝነኞቻችን (ተገንጣይ አንጃዎች) ሕይወት ላይ ቁማር እንዲጫወቱ አንፈልግም፣፣ይበቃወታል እና ይግቱት!ለማመን ያዳግታል ልክ እንደ ሕልም ነዉ! እነዚህ ሰዎች ባርማጌዶን ጊዜ በእሳት ተጠብሰዉ፣ተፈትነዉ ያለፉ ጀግኖቻችን “ንጉሶቻችን” ናቸዉ፣፣ ሕዝባችን ወደ ነፃነት መድረክ ያመጡ የተከበሩ እና ሓላፊነት የሚሰማቸዉ “እንፀባራቂ ከዋክብቶች” ናቸዉ፣፣” አቶ መለስ ህወሓት ትግራይን ይቅርታ ይጠይቁ! አንጃዎቹ ወደ ድሮ ቦታቸዉ ይመለሱ እርቁን ይጀምሩ አቶ መለስ!.....ወዘተ በማለት ወያኔ ተሰነጠቀ አገር ጠፋ! ትግራይ ለነፍጠኛ ተጋለጠ! ወዘተ እያሉ የተደመጡበትን “የትግራይ ሊሂቃን ቆሻሻ ማህደር” ጋዜጣዊ መግለጫቸዉ ይህን ይመስላል፣፣ በወያኔ ፖሊሲ እና ባንዳንድ የግንጠላ ፖለቲካ በሚያራምዱ መሪዎች ምክንያት የተካሄደዉ የጎሳ እልቂት እና የጠፋዉ ንብረት እና ሕይወት ተጠያቂዎች ሁሉ ወደ ዓለም ፍርድ ቤት የሚከሰሱበትን ዘመቻ ምሁራን እና የሕግ ሊቃዉንት ካሁኑኑ እንድትዘጋጁበት ዛሬም ደግሜ ደጋግሜ እወተዉታለሁ፣፣ ሕዝብ እንደ ጤዛ እያሳጨዱ፣በደም የተነከረዉ እጃቸዉ እያወራጩ ወደ ፖለቲካ መድረክ ገብተዉ አዳራሽ ተፈቅዶላቸዉ ያንኑ ፋሺስታዊ ፖለቲካቸዉ እንዲረጩ መፍቀድ መፍቀድ ጅልነት ነዉ፣፣ ጊዜዉ ይረዝም እንደሆን እንጂ ወንጀለኞች-ለሕግ-ይቀርባሉ!አመሰግናለሁ፣፣ ጌታቸዉ ራዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Sunday, June 21, 2009

የአማራዉ ሕዝብ ዕልቂት በአንድ ዘር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት

የአማራዉ ሕዝብ ዕልቂት በአንድ ዘር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት
Please visit http://www.ethiolion.com/ and http://www.ethiopatriots.com/ for PDF Format of the article.
ካለፈዉ እትም ክፍል ሦስት “የትግራዩን ኤሊት/ሊሂቅ” በወያነ ትግራይ ያለዉ አመለካከት ለማቅረብ ቃል ገብቼላችሁ ነበር፣፣ ያንን ለሚቀጥለዉ ሰሞን አስተላልፌዋለሁ፣፣ በሰሞኑን ከትግርኛ ሚዲያዎች አምዳችን የሚተላለፉትን ዜናዎችና የሚደረጉት ቃለ መጠይቆች በመተርጎም ለመተቸት እና ትግርኛ ለማትናገሩ ዜጎችም አብራችሁ ለመከታተል ያመች ዘንድ ያዘጋጀሁት አምድ ነበር እና አሱን ላስቀድም አልኩኝ፣፣ ለዚህም አንደኛዉ እንግዳ ስብሓት ነጋ ራድዮ መርሃዊት ከተባለዉ የትግርኛ ራዲዮ ጣቢያ ያደረገዉ አስገራሚዉ ቃለ መጠይቁ እና ሰሞኑን ከዶ/አሰፋ ነጋሽ በነፃነት ራዲዮ ላይ ሲከራከር ነበረዉ የዋሺንግተን ዲሲዉ የሕግ ጠበቃዉ የአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ቃለ መጠይቅ ከእዛዉ ከራዲዮ መርሃዊት ጋር ያደረገዉ ሌላኛዉ አስገራሚ ቃለ መጠይቅ (በሌላ አምድ ሙሉዉን ቃለ መጠይቅ አቀርብላችሗለሁ) ነበር እና ሁለቱንም በማዘጋጀት ላይ የትኛዉ ይቅደም ብየ ስወስን-የአቶ ሙሉጌታን መረጥኩ፣፣ ለምክንየቴም አቶ ሙሉጌታ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ዘር ስለሆንን “የዘር ፍጅት” ሊከሰት አይችልም በማለት ግንቦት 7 ለትግራይ ሕብረተሰብ የአስተላለፈዉ መግለጫ መሰረት በማድረግ ሰፊ እርስ በርስ የሚጋጭ ቃለ መጠይቅ ከመስጠቱ ባሻገር እና የቃላት ጨዋታ ከመግባቱም ባሻገር “የዘር ፍጅት/እልቂት” ከ “ኤትኒክ ክሊንሲነግ- የጎሳ ፍጅት/ እልቂት” በትርጉም ቢለያይም በተግባር ያዉ የሰዉ ልጆች ሕይወት መቅሰፍት ነዉና “የሰዉ ልጆች ዘር የእርስ በርስ ፍጅት የሚያካሂዱት አረሜናዊ እርምጃ መሆኑን እንስማማ እና ” ኤትኒክ ክሊንሲንግ (የጎሳ ፍጅት)“በቲ ፒ ኤል ኤፍ” ሊካሄድ አይችልም በማለት ተከራክሯል፣፣አምዱን የመረጥኩበት ምክንያትም ለዚህ ነዉ እና የአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ሙግት ቀንጨብ አድረጌ ላቅርብ እና እሳቸዉ ያልሰሙት ያላዩት የጎሳ እልቂት በዘመነ ህዝባዊ ሓርነት ትገራይ መንግሥት “ቲ-ፒ ኤል ኤፍ”/መንግሥት ባለስልጣኖችና ሹሞች እንደዚሁም ኦሮሞን እንወክላለን ነፃ አገር/ሕዝብ እናደርግሃለን በማለት የኦሮሞ ደግ ማሕበረሰብ ሰብአዊ ሕሊናዉን በማሳሳት የኦሮሞዉን ሕዝብ/ገበሬ በአማራዉ ሕብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲይዝ በማድረግ በአማራዉ ሕብረተሰብ የተፈጸመዉ እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ “የጎሳ ጽዳት” ከወያኔ የገበና ማሕደራችን ላስተላልፋችሁ ነኝ፣፣ ካሁን በፊት ይህንን ዘገባ ያላነበባችሁ ሰዎች ካላችሁ “አሳዛኝ ነዉና ‘ትንሽ ረጋ ብላችሁ ራሳችሁን በንዴት አትጉዱ” የተፈጸመዉን “አይፈጸምም” ወደ አሉት የዕልቂት ማህደር-ከመዉሰዳችሁ-በፊት-አቶ ሙሉጌታን ልጥቀስ፣- አቶ ሙሉጌታ ግራ የገባቸዉ (ለእሳቸዉ ብቻ ሳይሆን ለእኔም ጭምር ግራ የገባኝ የግንቦት 7 ደንቆሮ መግለጫ ቃል በቃል ለትግራይ ህዝብ ያስተላለፈዉ “የትግራይ ሕዝብ (ሊሂቁን ከማስታወቅ እና ሃለፊነቱን እንዲፈትሽ ከማድረግ ይልቅ)የዘር ፍጅት ሲፈጸም (መፈንቅለ መንግስት ጋር/ሽብር? ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ጥቂት የአማራ (?) ህዳጣን/ሕብረተሰብ አባሎች ማለቱ ነዉ መግለጫዉ “ከዘር- ፍጅት” ጋር ያያያዘበት ምክንያት) ዝምታ ከመረጠ ዝምታም ወንጀል ነዉና በተባባሪነት ወንጀል ትጠየቃላችሁ፣ ብሎ አጠቃላይ ምንም የማያዉቀዉን ገበሬዉንም ጭምር (ለትግራይ ሕዝብ ብሎ) ላስተላለፈዉ “ደንቆሮ መግለጫ” በመዉቀስ ለትግራይ ሕዝብ የተላለፈዉ ግንቦት 7 መግለጫ መግለጫዉ ጥቅሱን ካነበቡ በሗላ፣ - አቶ ሙሉጌታ “……………………………………” “ኤትኒክ ክሊንሲንግ ግንቦት 7 እንዳለዉ TPLF –Ethnic Cleansing ያካሂዳል ማለት ነዉ (በመግለጫዉ መሰረት)፣፣ መጀመሪያ ይህ (ዉንጀላ) ከየት እንደመጣ አላቅም፣፣ ምክንያቱም “በዴፌኒሺኑ/Definition” ስትመለከተዉ ቲ ፒ ኤል ኤፍ “ማጆሪቲ/Majority” ሊሆን አይችልም፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቲ ፒ ኤል ኤፍ TPLF (ትግሬዉ) በቁጥር፣ ማይኖሪቲmainority ናቸዉ፣፣ “ሶ/So” ቲ ፒ ኤል ኤፍTPLF በማን ላይ ነዉ ኤትኒክ ክሊንሲንግ/Ethnic Cleansing የሚያካሂደዉ? ቲ ፒ ኤል ኤፍ /ፎች ትግሬዎች ናቸዉ፣፣ ትገሬዎች ማንን ነዉ “ዲፖርት/Deport” ሚያደርጉት? ማንን ነዉ ገፍተዉ የሚያወጡት( “ጠርገዉ የሚያወጡት”) ከኢትዮጵያ ጠርገዉ ለማስወጣት የሚመክሩትን አማራዉን ነዉ? ኦሮሞዉን ነዉ? ቢሞክሩስ እንደዚያ ማድረግ ይቻላል ወይ? ምክንያቱም “ማጆሪቲ/Majority” “ማይኖሪቲዉን/Minority ማስለቀቅ አይችልም፣፣ እራሱ አባባሉ “ቲኦሮቲካል ዊክነስ/Theorotical Weakness” አለዉ፣፣ ነገሮችን ለማጋነን ነዉ (እንደዚህ ዓይነት ቅስቀሳ ማካሄድ) ምክንያቱም በዓለም ዉስጥ እንዲሰራጭ እና ጋዜጠኞችም ዜናዉን አግኝተዉ እንደፈለጉት ስለሚጠቀሙበት (ሆን ተብሎ የተሰራጨ ነዉ)፣፣ኤትኒክ ክሊንሲንግ Ethnic Cleansing ወይንም በአማርኛዉ “የዘር ማጥፋት” የሚባል (ቃል) ለመጀመሪያ ጀሮየ ከግንቦት 7 ነዉ የሰማሁት፣፣” በማለት ወንድሜ አቶ ሙሉጌታ አራጋዊ የጎሳ እልቂት “ማጆርቲ/majority” እንጂ “እንደ ቲ ፒ ኤል ኤፍ ማይኖሪቲTPLF/Minority ያለዉ የጎሳ እልቂት ማካሄድ አይችልም የሚለዉ ፈረንጆች የሚጭሩት ጽሁፍ/ትርጉም ብቻ በመመርኮዝ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በተደጋጋሚ ምን እንተደረገ ያወቁት አይመስለኝም፣ ካወቁትም በምን ዘዴ ይሄንን ከዚህ በታች ያለዉን በወያኔ ዘመነ መንግሥት የተፈጸመዉ የጎሳ ማጽዳት ስራ እንደሚመለከቱት ባላዉቅም፣ ለኔ ይህ ከዚህ በታች የተዘገበ ወንጀል የጎሳ እልቂት ሃላፊነቱ (የማንም ይሁን የማን ከሌሎች ተጠያቂዎች ጋር ጨምሮ) ወያኔም ለዚህ እልቂት በቀየሰዉ የጎሰ ፖለቲካ ግምባር ቀደም ተጠያቂ ነዉና ወያኔ ትግራይ በተዉኔት በዘፈን በፕሮግራም በቅስቀሳ አማራዉ በሌሎች ህዳጣን የኢትዮጵያ ሕብረተሰቦች እንዲጠላ እና እንዲጠቃ በአማራዉ ላይ ሲቀሰቅሰዉ የነበረዉ ጥላቻዉ በግብር እንዴት እንደዋለለት እንመልከት፣፣ በ እግረ መንገዳችሁም ‘ብሔር ብሔረሰብ ባንዴራዉን እያዉለበለበ በፍቅር እዮኖረ ነዉ ለሚሉዋችሁ “የወንጀለኞቹ አዳማቂዎች” ለምስኪኑ ገበሬ ያወረዱበትን ግፍ “ጉዳቸዉን እዩላቸዉና እና ፍረዱን ለናንተ ልተዉ”፣፣ እነሆ፣፤- ልዪ ጥንቅር- ጦቢያ ቅጽ 8 ቁጥር 8 1993 ምስራቅ ወለጋ የአማራዉ ሕዝብ ዕልቂት ባንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ዘጋቢ ኦርዮን የጎሳ ግጭት እና የሕዝብ ዕልቂት ዛሬ፣ዛሬ፣ጀሮአችን፣ እንዲያም ሲል ዓይናችን እየለመደዉ መጣና እንደሌላዉ ጊዜ ብዙም የሚሰቀጥጥና የሚዘገንን ወሬ አይደለም፣፣ ዛሬ ካለንብት ጊዜ ላይ የደረስነዉ ባለፉት ዓሥር ዓመታት የበደኖን፣ የአርባ ጉጉን፣የአርሲን፣ የአደባባይ ኢየሱስን፣ የገዴኦንና የጉጂን ወዘተ፣ ግጭት እና ዕልቂት ከስደትና ከፍርሃት ጋር መኖሩን በግዱ እየተለማመደዉ ነዉ ማለት ይቻላል፣፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሌለዉ ቀርቶ ለሰልፍ የወጣዉን ተማሪ፣ ለምርጫን የተነሳ ሕዝብ፣ በጥይት መደብደብና በቦምብ መጨፍጨፍ አዲስ ነግር እየሆነ አይደልም፣፣ ሞትን እና ዕልቂትን ሁሉም ከልጅ እስከ አዋቂ እየቀመሰዉ ነዉ፣፣ “ሞት ይለመዳል? ዕልቂት ይለመዳል?” ብሎ መጠየቅ ሌላ ነገር ነዉ፣፣ ሃቁ ግን ከሞትና ከዕልቂት ጋር እየኖርን ነዉ፣፣ ቡሬ ላይ በቆየሁባቸዉ ጥቂት ቀናት የተረዳሁት ይህንን ሃቅ ነዉ፣፣ ብዙዉ ሰዉ እንዲህ በተለምዶ ለአፉ ብቻ ካልሆነ በስተቀር ዛሬ “ግጭቱን ማን ፈጠረዉ? ግድያዉን ማን ፈጸመዉ?” ብሎ መጠየቁን ትቷል፣፣የትም ይሁን የት በጎሳዎች መካከል የሚቀጣጠለዉ ኹዉከት እና ግጭት በእነማን ፍላጎትና በእነማን ግፊት እንደሚካሄድ ልቡ ያዉቀዋል፣፣ በዚህ ምክንያት፣ የዛሬዉን የሃገራችንን ሁኔታ በዉል ለምታዉቁ አንባቢያን ሁሉ በዚህ ልዩ ጥንቅር ዉስጥ የምናቀርብላችሁ ታሪክ ምን ያህል አዲስ ሊሆንባችሁ እንደሚችል እናዉቅም፣ ፣ ብቻ በዚያም በሉት በዚህ አንድ ነገር ማረጋገጥ ይቻላል፣፣ በምስራቅ ወለጋ በአንድ ዘር ላይ ተነጣጥሮ የተካሄደዉን የጭፍጨፋና የዕልቂት ባለቤት፣ እጅ ከፍንጅ ሲያዝ ታዩታላችሁ፣፣ከዕልቂቱና ከሰቆቃዉ ተርፎ ጎጃም ዉስጥ፣ ቡሬ ከሚባል ከተማ ላይ የሰፈረዉ የጎጃምና የጎንደር የሸዋ የወሎ አማራ በእንባዉና በደሙ ይናገራል፣፣ ስሙት፣፣ ቡሬ ሰፈራ ጣቢያ መጋቢት 15 ቀን ሐሙስ፣ ከማርቆስ ተነስቼ 10 ሰዓት ገደማ ቡሬ ደረስኩ፣፣ጓዜን ከአንድ ቦታ አስቀምጨ ወዲያዉ ወደ ከተማዉ ወጣሁ፣፣ ብቻየን ነኝ፣፣ ቡሬ ብዙ አላዉቃትም፣፣የከተማዋ ዋናዉ መንገድ ቡሬን ለሁለት ገምሷት ያልፋል፣፣አብዛኛዉ የከተማዉ ክፍል ከመንገድ በላይ ዳገታማዉን ሥፍራ ይዟል፣ቀሪዉ ከተማ ከመንገዱ በታች ቁልቁል ከሚታይ ረባዳ ቦታ ይገኛል፣፣ “ሠፋሪዎቹ የት ነዉ ያሉት?” ብየ መጠየቅ አላስፈለገኝም፣፣ ከአዉራዉ ጎዳና ዳር ላይ ቆሜ ሳማትር ከወደ ረባዳዉ የከተማዉ ክፍል፣ በብዙ ሁኔታ ተመሳሳይ የሆኑ ሰዎች እንዲት መንገድ ይዘዉ ሲመላለሱ አየሁ፣፣ ወደ መሐል ከተማዉ ይመጣሉ፣፣ በዚያዉ መንገድ ወደ መጡበት ይመላለሳሉ፣፣ ሕጻናት ልጆች ያዘሉ እናቶች ሕፃናት ልጆችን የተሸከሙ ወይም እጆቻቸዉን ይዘዉ የሚጎትቱ አባቶች ዕድሜአቸዉ የገፋ ባልቴቶችና ሽማግሌዎች በዚያ መንገድ ይመላለሳሉ፣፣ “እነዚህ ሠፋሪዎች ናቸዉ” አልሁ፣፣ ጊዜዉ እየመሸ ነበርና አንዱን ቀረብ ብየ ለማነጋገር ወሰንሁ፣፣ አንድ ሕፃን ደረቱ ላይ-አቅፎ-የያዘ-ጎልማሳ-አየሁና ሄድሁ፣፣ 1 ጠጋ ብየ “ሰፋሪ መሰልኸኝ!” አልሁት፣፣ 2 “አዎን ሰፋሪ ነኝ” አለኝ፣፣ 1 “ምን ፍለጋ ቆመሃል?” 2 “ሥራ የሰራሁለት ሰዉ ነበረ፣፣ ገንዘብ እዚህ ድረስ አመጣልሃለሁ ብሎኝ እሱን እየጠበቅሁ ነዉ፣፣” 1 ”መሽቷል ከእንግዲህ ይመጣልሃል? 2 “ከእንግዲህስ መሽቷል፣፣ከእንግዲህ እንኳን አይመጣም፣፣ የሰዉ ነገር! አለና ለመሄድ ፊቱን አዞረ፣፣ “ቶሎ ብየ ወደዚህ እንሂድና እህል እንቅመስ” አልሁት፣፣ አንገቱን ሰበር አድርጎ “እሺ” አለ፣፣ አጠገባችን ከምትገኝ ጠላ ቤት ገባን፣፣ ምግብም አለ፣፣ እንጀራ በወጥ፣ ከጠላ ጋር ቀረበልንና በላን፣፣ጠጣን፣፣እየመሸ ስለሆነ ሰዉየዉ ወደ ሠፈር ጣቢያዉ ለመመለስ ልቡ ቆሟል፣፣በዚህ ሁኔታ ዉስጥ 1 “ይሄ ሕፃን ልጅ ያንተ ልጅ ነዉ?” አልሁት 2 “እህስያ፣፣ የኔ ነዉ እንጂ፣፣” 1 “እናቱስ?” 2 “እናቱማ በጥይት ገደሉብኝ፣፣” 1 “ሴቷን ልጅ?” 2 “አዎን፣፣” “ምን ምርጫ አለ”፣፣”ሴቱን ሕጣኑን፣ ሽማግሌዉንና ባልቴቱን አይደል የፈጁት፣፣መቸ መረጡ፣፣ እና የኼዉ ጨቅላ ልጅ ታቅፌ ቀረሁ፣፣” እያለ ሕፃኑን እንደታቀፈ ለመነሳት ሽመሉን ከጎኑ ሳበ፣፣ 1 “ስንት ዓመቱ ነዉ?” 2 የልጁን ዓይን እያየ “ቀረብህ?” ሁለት ዓመቱ ነዉ፣፣ እናቱ ጥላዉ ስትሞት ጊዜ “ቀረብህ” አልሁት”፣፣ እያለኝ ከቤት ወጣን፣፣ ከመለያየታችን በፊት ስለ ሠፈራዉ ጠየቅሁት፣፣ 1 “የሠፈራዉ ቦታ ከዚህ ይርቃል?” 2 አቅጣጫዉን በአገጩ እያመለከተ “አረ እዚህ ነዉ! ቅርብ አይደል?” አለኝ፣፣ 1 “እናንተ እንደልብ እየወጣችሁና እየገባችሁ መሰለኝ፣፣ሌላስ ሰዉ መዉጣትና መግባት ይችላል?” 2 ምን ችግር አለዉ! ይሄዉ እንደሚያዩት እኛም ስንመላለስ እንዉላለን፣፣ ሌላዉም ሰዉ ከልካይ የለዉም፣፣ይመጣል፣ ይሄዳል!”አለኝ፣፣ ድህና እደር ተባብለን ተለያየን፣፣ በሁለት እጁ ቀረብህን ደርቱ ላይ ጥብቅ አድርጎ ይዞ በቁልቁለቱ ደፋ ደፋ እያለ ሄደ፣፣ ሠፈራዉ ቅርብ ነዉ፣፣”ሌላዉም ሰዉ ከልካይ የለዉም፣፣ ይመጣል፣፣ ይሄዳል፣፣ለነገ ዜናየ ጥሩ ዜና ነበር፣፣ የካቲት እና 17-ሁለት፣ ግን አጫጭር ቀናት ነበሩ፣፣ በእርግጥ አዲዩ “ሌላዉም ከልካይ የለዉም፣፣ይሄዳል.፣ይመጣል፣፣” ሲል የነገረኝ ከልቤ አልጠፋም፣፣ ቢሆንም ሠፈራ ጣቢያዉ በሩቁ መቃኘት ቀስ በቀስ መቅረብና ገብቶ መመለከት አስፈላጊ ነበር፣፣14,000 ሰፋሪዎች እንደያዙ የሚገመቱ አረንጓዴ ድንኳኖች በሩቁ ለሚመለከታቸዉ ረድፍ ጠብቆ የበቀለ ቁጥቋጥ ይመስላሉ፣፣ ከእነዚህ ድንኳኖች ዉስጥ ለመግባት ጭንቅላት ከጉልበት መታጠፍ፣ አለዚያም መንበርከክ ያስፈልጋል፣፣ ከዉጭ የቆመዉ ሕዝብ ሲታይ ድንኳኖች ዉስጥ ሰዉ የቀረ አይመስልም፣፣ ድንኳን ዉስጥ ሲገባ ደግሞ መረማመጃ ቀርቶ ጠጠር መጣያ ቦታ የለዉም፣፣ ዓይን ተወርዉሮ ማየት እስከሚችልበት ድረስ ሰዉ አንዱ ባንዱ ላይ ተነባብሮ ተኝቷል፣፣ ድንኳን ዉስጥ ያሉት ሁሉም ማለት ይቻላል ሕፃናትና ደካማ አረጋዊያን ናቸዉ፣፣ሁኔታዉ ይሄ ነዉ፣፣ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ጥቂት ፎቶግራፍ ማንሳት ይቻል ይሆናል፣፣ ሰዎችን መራርጦ ተስማሚ ቦታ ይዞ ለመነጋገር ግን ሁኔታዉ አይፈቅድም.፣፣ በዚህ ቦታ የሚገኙ ሁሉም ሠፋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ”ሠራተኞችም” ይኖራሉ፣፣ ስለዚህ ከሰፋሪዎቹ ቀስ ብሎ ሰዉ ማፍራት፣ በሰዉ ዕረዳታ ምሥራቅ ወለጋ ላይ የደረሰባቸዉ ችግረ መግለጥ የሚችሉ ሰዎችን ማግኘትና አመቺ ቦታ ይዞ ማነጋገር አስፈላጊ ነበር፣፣ይኼ፣ ይኼ ጊዜዉን በላዉ፣፣ዛሬ ሁኔታዎችን ተባብሰዉ ወይም ተሻሽለዉ ሊሆኑ ይችላል፣፣አላዉቅም፣፣በወቅቱ ግን ከሠፈራዉ ጣቢያ በየዕለቱ ሁለት እና ሶሦት ሬሣ ይወጣ ነበር፣፣የሚሞቱት ሕፃናት ናቸዉ፣፣ ቡሬ እንኳንስ እንግዳ ልታስተናግድበት ለራሷም የምትጠጣዉ ዉሃ የላትም፣፣ለሠፋሪዎቹ ዉሃ በቦቴ ሲከፋፈል አይቻለሁ፣፣ የሠፈራዉ ጣቢያ የመጸዳጃዉ ሁኔታ ለወረርሽኝ እና ለበሽታ መቀስቀስ በሚያመች ሁኔታ የትም ነዉ፣፣ያሳፍራል፣፣በዚህ ላይ የአማራን ትምክሕት ለመዋጋት የቆሙት የክልል ሦስት ባለሥልጣናት ለእነዚህ ከወለጋ ተቀጥተዉ ጎጃም ለገቡት መከረኞች የሚራራ ልብ ያላቸዉ አይመስልም፣፣ ዘግይተዉ እየመጡ ላሉት ለወለጋ ተፈናቃዮች ዕርዳታ እንደደረሱ አይሰጥም፣፣ “እናንተማ ከብቶቻችሁና እህላችሁ ስትሸጡ ቆይታችሁ የመጣችሁ ስለሆነ ለእናንተ ዕርዳታ እንሰጥም”-እያሉ እንደሚጨክኑባቸዉ ስደተኞቹ ያስረዳሉ፣፣ የተዋለባቸዉን ግፍ ይናገራሉ እነዚህ ምሥራቅ ወለጋ ላይ ከተፈፀመባቸዉ ዕልቂት ተርፈዉ ዛሬ ቡሬ ሠፈራ ጣቢያ የሚገኙት የአማራ ተወላጆች ወደ ወለጋ የሄዱ በተለያየ ጊዜ መሆኑን ይናገራሉ፣፣ ባጠቃላይ ግን “በደረግ ዘመን ከኢሐዴግ በሗላ” ብሎ በሁለት ጊዜያት መክፈል ይቻላል፣፣ በእነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ወለጋ የገቡት ገበሬዎች የእርሻ ቦታ ያገኙበት ሁኔታም ይለያያል፣፣ይሁን እንጂ በሁሉም የደረሰዉ ሰቆቃ አንድ እና ተመሳሳይ ነዉ፣፣ በመሆኑም በዛ በከራ ዉስጥ ያለፉት ሁሉ ስለደረሰባቸዉ ችግር የሚናገሩት ከመርሳትና ከማስታወስ ወይም ጥቃቅን የአጋጣሚ እና የአገላለጽ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር የሁሉም ታሪክ አንድ ዓይነት ነዉ፣፣ በዚህ ምክንያት አጠቃላይ ችግሩን በተመለከተ ከአነጋገርሗቸዉ ብዙ አርሶ አደሮች ዉስጥ ሁለቱ ብቻ. አንዱ በደርግ ዘመን ሌላዉ ከኢሕአዴግ በሗላ ወለጋ የገቡ አርሶ አደሮች የተናገሩት ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል፣፣ በርይሁን አያሌዉ- “አገሬ ወሎ ነዉ፣፣ ወደ ወለጋ የሄድሁት በ1976 ዓ.ም. ነዉ፣፣ በ176 መሬቱ ጫካ ነበር፣፣ መንግሥት ግቡ አለን፣፣ገባንበት፣፣ ስንገባ ምንም አልከፈልንም፣፣ ካርኒ ቆርጠን እንገብር ጀመር፣፣መሬቱ የመንግሥት ነዉ፣፣በ76 ችግር አልነበረም፣፣ ችግሩ የመጣ አሁን ነዉ፣፣ ኢሕአዴግ ከገባ በሗላ፣፣ በድንበር እንካሰሳለን፣፣ ስንካሰስ ቀበሌ የእኛን ማመልከቻ ከስር የነሱን በላይ ያደርገዋል፣፣ ቀበሌ ጨቆነን ብለን ወረዳ ስንሄድ ፖሊስ ጣቢያ እየወሰዱ ያስሩናል፣፣ቀበሌዉና ፖሊስ ጣቢያዉ አስከ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ “እናንተ ወሎዎች! እናንተ ቋሪቶች! እናንተ ጎጃሞች!በእኛ መሬት ማን ተከራካሪና ተሟጋች አደረጋችሁ?የዕለቱ ብቻ ብሉ፣፣ እኛ አገር ዉስጥ ባፈራችሁት ማዘዝ አትችሉም፣፣ የዕለቱን እየበላችሁ ተቀመጡ፣፣ ከእንግዲህ ወዲያ ማን አስቀምጣችሗል?”ይሉናል፣፣ እናም ልጅ ሆነን መጥተን እዚህ አደግን፣፣ እዚህ ተወልዶ ያገባ ሞልቷል፣፣ እየተዛመድን ነዉ፣፣ መንግሥት የሰጠንን መሬት ለቅቀን ወዴት እንሄዳለን? ደግሞስ በገዛ ሃብታችን እና አገራችነ እንዴት እንደዚህ ይሉናል?” እያልን ቆየን፣፣ ዕዉነት አልመሰለንም ቆየን፣፣ ወደ ሗላ ነገር አመጡ፣፣ ስንከራከር ያስሩናል፣፣ገንዘብ እየከፈልን እንወጣለን፣፣ አሁን ሌሊት ሌሊት ስርቆት ተጀመረ፣፣ የሌሊት ሌባ ድሮም የቆየ ነዉ ብለን ከብቶቻችን ስንጠብቅ ፖሊስና ምክር ቤት ከላይ መጥተዉ መሣሪያ ግዙ አሉን፣፣ መሣሪያ ገዝተን “አስመዝግቡ”-ሲሉን በሕጋዊ መንገድ አስመዘገብን፣፣ከዚያ “እናንተ በእኛ አገር መሣሪያ ልትይዙ አይገባችሁም” ብለዉ ሕግ አስመስለዉ ገፈፈዉ እዚያዉ ለእኛ ጓደኞች ለወረሞዎች አስታጠቋቸዉ፣፣ “ከብቶቻችን ሌሊት ሌሊት ይሰርቁ ጀመር፣፣ወደ ሗላ ቀን ቀን መዝረፍ ተጀመረ፣፣ “ከብቶቻችንን ለምን ትወስዳላችሁ?” ስንል እረኞቹን ገደሉብን፣፣ ምን እናድርግ እያለን ሳለን አንደገና “ተረጋጋ” -አሉን፣፣ መሣርያ ግዙ እና ሃብታችሁን ጠብቁ፣፣ከእንግዲህ ነገር የለም፣፣ የንብረታችሁ ጌታ ናችሁ” ሲሉን መለስን መሣርያ ገዛን፣፣ተነሱ አገር የነሱ መሣሪያ ነዉ የገዛነዉ፣፣ “አስመዝግቡ”-አሉን፣፣ አስመዘገብን፣፣ አሁንም ሁለተኛ ገፈፉን፣፣ “ከብቶቻችን ከተዉልን ደግ ነዉ”-ብለን ዝም ብለን ተቀምጠን “ሕጉንም ከላይ እንዳልሆነ አይተነዋል”፣፣ “”አቸንፈዉናል፣ተቸንፈናል” ብለን ተቀመጥን፣፣ እንዲያ ተቀምጠን እያለን ባለሥልጣኖች መጥተዉ “እናንተ እንግዲህ ያለባችሁ ወደ ክልል ሦስት መግባት ነዉ፣፣መግቢያችሁ ደረሰ፣፣ሃብትም ከዚህ ይዛችሁ አትሄዱም፣፣ አመላችሁን አሳምራችሁ ሹልክ በሉ፣፣ካልሸሎካችሁ ሕይወታችሁ ይጠፋል”አሉን፣፣መንግሥት እንዲህ ያደርግ አልመሰለንም፣፣አሁን ከብቶቻችንን ቀን ቀን ይዘርፉን ጀመር፣፣ ለመከላከልም አቅም አጣን፣፣መሣሪያችን ተገፍፈናል፣፣ ከዚያ በሗላ “ተነሱ” አሉን፣፣በቃ የሚገድሉትን “ገደሉ፣፣ ገደሉ፣፣ ገደሉ፣፣”’ ይህ የሆነዉ ሕዳር 21 ቀን ነዉ፣፣ ወረዳዉ በፊት መጥቶ ፈተሸ፣፣ ከዚያ ሠራዊት መጣ! ከየት እንደመጣ አናዉቅም፣፣ የታጠቁ ናቸዉ፣፣ “እቤትህ እንዳትቀር” እያሉ ገበሬዉን ጨምረዉ እነሱ ከፊት ከፊት ገበሬዉ ከሗላ ሆነዉ ሕዝብን ጨፈጨፉት፣፣ አጠፉት ከሞት የተረፈዉን ወደ እስር ቤት ወሰዱት፣፣ ከዛ እየሾለክን ሆሮ ከሚባል የመስመር ቦታ ላይ ተሰባሰብን፣፣ ያልተነሱት ቀበሌዎች እየደበደቡ ከኛ ዘንድ አመጧቸዉ፣፣ እዚያ ታክተን ቆየን፣፣ ሕጣናት በረሃብ እየተሰቃዩ ሞቱ፣፣ ደካሞች ሞቱ፣፣ ትንሽ አቅም ያለዉ እየሾለከ ከዚህ ደረስን፣፣ “ከ15 ያላነሱ የቀንድ ከብቶች፣ 12 ፍየሎች፣ አንድ አህያ ነበሩኝ፣፣እኩሌታዉ እዛ ቀረ፣፣ እኩሌታዉ ዓባይን እስክሻገር ድረስ ዝርፍያዉ አላቆመም ነበርና ወሰዷቸዉ፣፣ እህሉ ሁሉ እዛዉ ቀረ፣፣ መሣሪያ ነበረኝ፣፣ወሰዱት፣፣ስድስት ልጆች አሉኝ፣፣ሁሉንም ይዤ መጥቻለሁ፣፣” ዓለሙ መኮንን ከጎንደር በ1990-ነዉ ወደ ወለጋ የሄድሁ፣፣ መርጃ ጂረኛ ቀበሌ እኖር ነበር፣፣ መንግሥት “መሬት ባለቤት መሥርተህ ብላ” የሚል መስሎን ነበር፣፣ መጀመሪያ ስንደርስ ለመመዝገቢያ ሁለትም ሦስት መቶ የከፈልን አለን፣፣ያን ካስከፈሉን በሗላ ለባለ መሬት ያስተላልፍናል፣፣ባለመሬቱ መሬት ሰጥቼሃላሁ ይልና እንደመሬቱ መጠን ሁለትም ሰሦትም ሺሕ ብር ይቀበለናል፣፣ ከዚያ መሬት ይዘን እናርሳለን፣፣ ቀደም ብለዉ የሄዱት ተመርተናል ይላሉ፣፣ “መሬት ከሰጠን በሗላ ገንዘቡ ሲያልቅ ለመክሰስ ይነሳሉ፣፣ከገበሬ ማሕበር የክስ ደብዳቤ ይመጣል፣፣አክብረን መልስ ይዘን እንመጣለን፣፣ “አልተስተካከለም” ብለዉ ኪሳራ ይቆረጥብናል፤፤ የምናቀርበዉ መልስ አይታይም፣፣ እንታሰራለን “ዋስ ጥሩ” እንባላለን፣፣ አማራ መሬት ስለሌለዉ ዋስ አይሆንም ይሉናል፣፣ሌሎችን በ ሺ ብር እየገዛን ዋስ እንጠራለን፣፣ ከሳምንት በሗላ “ቅረቡ” ይሉናል፣፣እንቀርባለን፣፣ዋሳችን “ዋስትናየን አዉርጃለሁ” ይላል፣፣ ሺ ብር የከፈልነዉ ዋስ፣፣ታሰሩ እንባላለን፣፣ ሌላ ሺ ብር ከፍልን ዋስ እንጠራለን፣፣ በዚህ ስንማረር፣ በሗላ ስርቆት ተጀመረ፣፣ ስርቆት ይባላል እንጂ ዘረፋ ነዉ፣፣ ከግንቦት አስከ ሐምሌ 1992 ዘረፋዉ ቀጥሏል፣፣ሐምሌ 7 ቀን በሬ ተሰረቀ እረ!እሪ! ተባለ፣፣ተሰበሰብን፣፣ “ምን እናድርግ ምን ይሻላል?”ተባባልን፣፣ይህን ሁሉ የሚሰራን የገበሬ ማሕበሩ ሊቀመንበር ወይም ፀሃፊዉ ነዉ፣፣ታጣቂዎች ናቸዉ፣፣ በሬአችን እናስመልስ ብለን ከፀሐፊዉ ዘንድ ሄድን፣፣ ፀሃፊዉ “ደረጀ መለስ”ይባላል፣፣ እየሄድን እያለ የአየለ አዱኛ ቤት ተዘረፈ፣፣”ኡ!ኡ! ተባለ”፣፣የሄድነዉም ተመልሰን መጣን፣፣ከላይ እና ከታች ያለዉ ሰዉ ተሰባሰበ፣፣ እንዳጋጣሚ ቶክስ ተተኮሰና ሁለት ሰዉ ቆሰለ፣፣ ይህ የተፈፀመዉ ሓምሌ 8 ቀን ነበር፣፣ሓምሌ 10 ቀን “የበላይ አካል ነን” ብለዉ መጡ፣፣ ይህን ሁሉ የሚሠራን የበላይ አካል እየተሰኘ ነዉ፣፣ይህን የሰራን የመንግሥት አካል ነዉ፣፣ ገበሬዉ አይደለም፣፣ልንጮህለትም አቅቶናል፣፣ “እኛ እንግዲህ ይህን መንግሥት ብለን መቀመጥ እንችላለን? ዳኝነትስ እንዴት አለ ማለት ይቻላል?” ስንባባል፣ ሐምሌ 19 ቀን የበላይ አካል ተወካዮች መጡ ተባለ፣፣ ትክክለኛ ዳኞች ናቸዉ ሲባል ጊዜ ገበሬዉ ተሰበሰበ፣፣ ከክፍለሃገር፣ፖሊስ፣ከገበሬ ማሕበር የመጡ ናቸዉ፣፣ “የወረሞ ገበሬዎች ሣር አጨዱ፣ ደን ጨፈጨፉ ይሏችሗል” አሉን፣፣”መሬት ‘ሰጡን’ አረሱተ፣ እንጨቱን ቆረጡት ሣሩን አጨዱት አሉን፣፣አረስን ፣አጨድን፣ ቆረጥን፣፣ ይሄ ምን ጥፋት ሆኖ ይታያል፣፣?”አልን፣፣ “የእኛ ጥፋት ነዉ ብላችሁ እመኑ”ተባልን፣፣ “እረሱ ባልተባልን እንጂ ይሄ እንዴት አድርጎ ጥፋት ይሆንብናል?”ብለን ብዙ ተጨቃጨቅን፣፣ አሁን እናንተ ጥፋታችሁ በትክክል ካላመናችሁ፣ጥፋተኛ ንን ካላላችሁ “የወረሞ ክልል እናንተን ሊቀበላችሁ አይችልም” አሉን፣፣ እንዲህ ከሆነማ ምን እናደርጋለን? “በደለኛ በደለኛ ወታደር በደለኛ፣ ግን ቢሆንም ባላገር ይካስ”ከተባለ ይሄ በደል ከኛ ከሆነ ሣሩንም አጭደነዋል እንጨቱንም ቆርጠነዋል፣፣ ያዉ ለእንጀራ ብለን ነዉ፣፣ አልናቸዉ፣፣ ይሄ ጥፋት ነዉ ከተባለ ተቀብለነዋል አልን፣፣ወረሞዎችም ጥፋታችን ነዉ ብለዉ አመኑ፣፣ “ከእንግዲህ ተስማምታቸሁ ኑሩ ተብለን ሽማግሌዎች ከወረሞም ከአማራም ተመረጡ፣፣ የጠፋዉ ሁሉ በቅንጅት እንዲመለስ ተባለ፣፣ “አገሪቱ ኢትዮጵያ የሁሉም የጋራ ናት፣፣የወረሞም የአማራም ብቻ አይደለችም፣፣ አገሪቱ የጋራችን ናት፣፣ እኛ የሁላችሁ ዳኞች ነን” አሉን፣፣ ሽመግሌዎች ሲደክሙ ራቦር(ሪፖርት) ሲተላለፍ ቆየ፣፣ እኛ ቋንቋዉን አናቀዉም፣፣ ይሄ ሲሆን ብዙ ቆየ፣፣ እሱስ ሲመክሩ ቆይተዋል፣፣ ‘ሕዳር 21 ቀን የማርያም፣ ዲቡክ ማርያም በዓል ነበር፣፣ወረዳዉ ‘ተሰብሰቡ” አለና ጠራ፣፣ለበዓሉ የመጣ ሰዉ ሁሉ አለ፣፣ ወረዳዉ እኔም በአካል አዉቀዋለሁ፣፣አሰፋ ፋይሳ ይባላል፣፣ ሌሊት ከምሽቱ 5-ሰዓት ገብቶ ነዉ ያደረ፣፣ የአካባቢዉ ሰዉ ይሰበሰብ ጀመረ፣፣ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ይሆናል፣፣ መትረየስ ጠምዷል፣፣ ሰዉ ሲሰበሰብለት፣ “በመትረየስ አጨደዉ”፣፣ ዓመት በዓልም ስለነበረ ተሰበሰበዉ ሰዉ ብዙ ነበር፣፣ አብረዉት የነበሩ ሁሉ ቶክስ ከፈቱ፣፣ ቶክስ ሲከፈት ሰዉ በየአቅጣጫዉ ሮጠ፣፣ ላዉንቸር አለ፣፣የማላዉቀዉ የመሣሪያ ድምፅም ነበር፣፣ ሲተኩሱ ሲገድሉ ዉለዉ ሄዱ፣፣ ሕዳር 21 ቀን ጥይት ሁሉ የሚተኮስ ከነሱ ነበር፣፣ ግን ከዚያም ወገን ሰዉ ሞቷል አሉ፣፣ “ሕዳር 25 ቀን እንደገና ጦር ተጭኖ መጣ፣፣ሠራዊት ነዉ፣፣መትረየስ፣ከላሽ ላዉንቸር ታጥቀዋል፣፣ቁጥሩ አይታወቅም፣ በቅጠሉ ቁጥር ነዉ፣፣ ብዛቱ ይነገር ቢባል 500 እና 600 ይሆናል፣፣ሰዉን ይገድል፣ቤትን ያቃጥል ጀመረ፣፣ በያካባቢዉ ሰዉ እየያዘ ገደለ፣፣ እኔ እንኳ በማዉቀዉ ብዙ ሰዉ ሞተ፣፣ከሕዳር ማርያም ጀምሮ ያለቀዉን ሰዉ እግዚሔር ይቁጠረዉ፣፣ እኔ እንኳ የማልረሳቸዉ ቁጥር የላቸዉም፣፣ “ገበያ ሙሉነህ፣ፈጠነ ገብሬ አያል አዱኛ፣ ጋሻዉ እዉነቱ፣ ጋሻየ ጌቴ፣ ይበልጤ መንግሥቴ፣ ይበልጤ ድረስ፣ አዘዘ ይበልጤ፣ይግዛዉ ታምራት፣አሻግሬ ገበየሁ፣ አስረግደዉ ዉቡ፣ ተስፋዬ አለማየሁ፣ ሰጤ ወርቅዬ፣ መልካሙ ዉባለም፣ ዉብ ሞንሟኔ፣ምሕረት እዉነቱ፣ ቢራሪ ታደሰ፣ ደስታዉ አብተዉ አባ በላይ ቃለ፣ ….አረ ስንቱ! ያለቀዉ ቁጥር ለዉም፣፣ እኔ ድሮ የማዉቀዉ በሃይለስላሴ ዘመን ደርሻለሁ፣ በደርግም አልፌአለሁ፣ ቤቱን ከፍቶ የሚቆይ አማና ሰዉ አይደበደብም፣፣ አይገደልም፣፣ ሰላም ነዉ ብለዉ ከቤታቸዉ የተቀመጡትን ሰዎች “ከክልል ሦስት ነን የመጣን፣፣ከባሕር ዳር ነን የመጣን፣፣” እያሉ ቤቱን ከፍቶ ሲያገኙት ያዉ መግደል ነዉ፣፣ገደሉት፣፣ ቤቱን በእሳት፣ክምሩን በእሳት አነደዱት፣፣ሰዉን በጥይት ፈጁት፣፣የሞተዉ ቁጥር የለዉም በሺ ነዉ፣፣ እስከ ሕዳር 27 እና 28 ድረስ ዕልቂት ነበር፣፣ ይተኩሳሉ፣፣ይገድላሉ፣፣ የተቀመጠዉን በዱላ፣የሮጦዉንም በጥይት ይሉታል፣፣ልጅም፣ ህጣንም፣ሴትም ዱላ የበዛበት “ፈቀቅ ሲል”በጥይት ነዉ፣፣ወንጀሉ ይሄ ነዉ አይባልም፣፣ጥያቄም የለበትም፣፣”ከመስመር ያለዉን አማራ በጠቅላላ አጥፉ ነዉ የተባልነዉ” አሉ፣፣ ወደ ድሬ ወደ ሃሮ የሚያወጣ መንገድ አለ፣፣ ከዚያ ወዲህ ሰባት ገበሬ ማሕበሮች ነን፣፣ እነዚያ በሙሉ “እንዲጠፋ ታዝዘናል”ይሉ ነበር፣፣“ትዛዝ ነዉ አባቴንም ባገኝ አልምርም፣፣ሁላችሁን እናጠፋችሗለን”አሉ፣፣ አጠፉን፣፣የተቀበረም-የለም፣፣ያለቀሰም-የለ፣፣ንብረትም-እዛዉ ከሰለ፣፣ሕይወትም እዛዉ አለቀ፣፣” ከዕልቂቱ አስከፊ ገጽታ በከፊል፣- (1) “ጌጣ ጌጡን አይተዉ አንቀልባዉን ለመዉሰድ በሃይል ጎትተዉ ሲፈቱት የሁለት ዓመት ሕፃን ከእናቱ ጀርባ ከሚነደዉ ቤት ደጃፍ ላይ ወድቆ በእሳት ተቃጥሎ ሞተ፣፣” (2) “መልካሙ ዉባለም የተባለዉን ገድለዉ ምላሱን አዉጥተዉ ወሰዱት፣፣” (3) አስረግደዉ ዉቡ የተባለዉን በጥይት አንካሴ አንገቱ ላይ፣ ወገቡ ላይ እግሩ ላይ ቸክለዉበት ሄዱ፣፣ (4) አንድ ሴት ሦስት ልጆቿን አስከትላ ስትሸሽ ወንዝ ላይ ስትደርስ በጥይት ገደሏት፣፣ ሦስቱ ልጆቹ በርረዉ ወንዝ ዉስጥ ገቡና እዛዉ ሞተዉ ቀሩ፣፣” (5) አባ በላይ ዋለ የተባሉትን ዓይነ ሥዉር ገደሏቸዉ፣፣ አማራ! አማራ ነዉ! ብለዉ ብልታቸዉን ቆረጡት፣፣” (6) መልካሙ ዉባለም አርደዉ ገደሉትና ምላሱን አዉጥተዉ ወሰዱት” ማጠቃለያ፣- ፖሊሲዉ አማራን ማስወጣት ብቻ ሳይሆን አማራ እንዳይገባም ይከለክላል፣፣ ባለዉ የጎሳ ፖሊሲ መሠረት በአሁኑ ጊዜ የአማራዉን ተወላጅ እየጨፈጨፉና እያሳደዱ ከወለጋ ማስወጣት ብቻ ሳይሆን ወደ ወለጋም እንዳይገባም እገዳ እየተደረገ ነዉ፣፣ ከአንድ ወር በፊት ወለጋ ይኖሩ ከነበሩ አማራዎች ዉስጥ ዘመድ ጠይቀዉ ለመመለስ ጎጃም መጥተዉ ነበር፣፣ የካቲት 14 ቀን 1993ወደ ነበሩበት (ወለጋ)ለመመለስ በሦስት መለስተኛ አዉቶቡሶች ተሳፍረዉ ሄዱ፣፣ ኪራሞ ላይ ሲደርሱ 10የሚሆኑ የኦሮሞ ፖሊሶች አትሄዱም ብለዉ መለስዋቸዉ፣፣ ይሁን እንጂ ከሦስቱ አቡቶቡሶች አንዱ፣ የሰሌዳ ቁጥር 3-13316የሆነዉና የአቶ ተሻለ ዓለማየሁ በተባለዉ ሾፌር የሚነዳዉ በአጋጣሚ አልፎ ሄደ፣፣ ሁለቱ የሰሌዳ ቁጥር 3-39522-በአቶ ቴዎድሮስ ዘርዓይ የሚነዳዉና አቶ አምሳሉ ወርቅነህ የሚያሽከረክሩት የሰሌዳ ቁጥር 3-13282-አቶቡሶች ሰዎችን እንደጫኑ ተመልሰዋል፣፣ ቤተሰቦቻቸዉ ወለጋ፣ እነሱ ክልል ሦስት!!!/--/ በወያኔ ጎሰኛ ስርዓት የተካሄደዉ “የጎሳ -ጽዳት/ዕልቂት”የወያነ ትግራይ “ፖሊሲ/ሕገ መንግሥት” መንስኤዉ አይደለም የምትሉን ካላችሁ “ግፍ የተዋለባቸዉ አማራዎች በእንባቸዉ የመሰከሩት ማሕደር፣ዉሸት ከሆነ ይሄዉ ደግመን ለክርክሩ ጥሪ እናደርግላቸዋለን፣፣ሕሊናቸዉ በጎሰናነት የተበከለዉ የትግራይ ሊሂቆችምኤሊቶችም በዚህ አጋጣሚ ይህ ሰነድ ካነበቡ በሗላ “አንድ ዘር ነን እና አንጨፋጨፍም” “በወያኔ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሳ አልተጋደለም”የሚሉት ሰንካላ መከላከያቸዉ ከዚህ እንደሚማሩ እና መስመራቸዉም እንደሚያስተካክሉ ተስፋ አደርጋለሁ፣፣ “ጻድቃን፣ዓለምሰገድ፣አረጋሽ፣ተክለሃይማኖት፣ዓዉዐሎም፣ስየ፣ መለስ ፣ስብሓት፣ጸጋይ፣ ገብሩ ወ ዓረና”-ምንትስ ምንተስ የምትሏቸዉ ሁሉም በደም የታጠቡ የሲአይኤ ባለጌዎች ናቸዉና የወንጀሉ ነዳፊዎችና ተጠያቂዎች ስለሆኑ የትግራይ የሕግ ባለሞያዎች ከሌሎቹ ጋር ተባብራችሁ ይህ ወንጀል ሲፈጸም በሃለፊነት የሚጠየቁት ሁሉ ወደ ፍርድ የሚቀርቡበት መንገድ መሻት ሲገባችሁ “ያገራችን ሕዝብ ጨዋ ነዉ- አይጋደልም፣ አይበታተንም …” የሚለዉ ያረጀ ያፈጀ መሸፈኛ ትተን በነባራዊዉ ላይ እንረባረብ፣፣ የወያኔ ፖሊሲ ከመደግፍ ታቀቡ፣፣ ኢትዮጵያ ፍትሕ ትጠብቃለች ጌታቸዉ-ረዳ-ሳንሆዘ-ካሊፎረኒያ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

Wednesday, June 17, 2009

ሙሉጌታ አረጋዊ ተቃዋሚዉን “ሪሳይክል/ሎች” ናቸዉ አለን?

ሙሉጌታ አረጋዊ ተቃዋሚዉን “ሪሳይክል/ሎች” ናቸዉ አለን? ጌታቸዉ ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
አቶ ሙሉጌታ ማናቸዉ ለምትሉ ሰዎች በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሙያ የስደተኞች ጠበቃ (Attorny)ናቸዉ፣፣ ባለፈዉ ሰሞን ሙሉጌታ አረጋዊ ከዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ጋር በነፃነት ራዲዮ ላይ ያደረገዉ የራዲዮ ዉይይት ሰፊዉን ዉይይታቸዉ በመጠኑ ቀንጭቤ ለእይታ አቅርቤላችሁ እንደነበር ይታወሳል፣፣ በዛ ዉይይት ደ/ር አሰፋ ነጋሽ ለጠየቀዉ የጎሳ ፌደራሊዝም ቀያሾች የሆኑትን እነ ገብሩ አስራት ከመለስ ዜናዊዉ ቡድን ሲለዩ የእነ ገብሩ አስራት ቡድን ደጋፊ በመሆን ለጎሰኞቹ ድጋፍ የመስጠቱን ጉዳይ አስመልክቶ ጥያቄ ሲመልስ ‘እኔ የነ ገብሩም ሆነ የማንም ቡድን ደጋፊ ሆኜ አላዉቅም” በማለት አጠንክሮ ለመለሰዉ “አሉታ”፣ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ የነ ገብሩ አስራት እንጃ ደጋፊ እና እምባ አፍሳሽ ሆኖ በዋሽንግተን አካባቢ (ምናልባትም በመላ ዓለም ላሉት የትግራዋዮች ማሕበረሰብ) ለሚኖሩ የትግራይ ማሕበረሰብ ቃል አቀባይ በመሆን ድጋፉን ያስተላለፈበት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ቅጅ እንዳስነበብኳችሁ ይታወሳል፣፣ ዛሬ ደግሞ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ በግንቦት 25/2002ዓ.ም. “ራዲዮ መርሃዊት” በመባል የሚታወቀዉ “የመንግሥት የተቃዋሚዉም ደጋፊም” አይደለሁም ዓይነቱ ‘ዉሉ የጠፋ”-የሙሉጌታ አረጋዊ ዓይነት “የፖለቲካ አቋም”-ያለዉ ድሮ የአንጃዎቹ ጠንካራ ደጋፊ በመሆን ከኢትዮጵያን ኮሜንታተር (ደጀን)ራዲዮ ጋር አብሮ ሲያዘጋጅ መለስ ዜናዊን በቃላት ሲወርፈዉ የነበረ “ሃብቶም ተኽለ”-የተባለ የራዲዮ መርሃዊ (ስድስት ወር እድሜ ያለዉ አዲስ ራዲዮ) አዘጋጅ ጋር ባደረገዉ የትግርኛ ቃለ መጠይቅ፣- ግንቦት7-የተባለዉ ድርጅት የትግሬዉ ማሕበረሰብ በትግሉ ያለመሳተፍ ቅሬታ እና ጥሪ ያስተላለፈዉ የድርጅቱ ጥሪ አስመልክቶ (እንደ ሙሉጌታ እና እና እንደ አዘጋጁ አባባል)ሙሉጌታን ለጠየቀዉ ጥያቄ ሙሉጌታ አራጋዊ ሲመልስ “ትግሬዎች በዉጭ አገር በሚካሄዱ ሰላማዊ ሠልፎች አይሳተፉም፣ ቢሳተፉም በጣት የሚቆጠሩ ናቸዉ፣ - አብዛኛዎቹ መንግሥትን የሚደግፉ ናቸዉ እያሉ ትግራዋይ ባንድ ወገን ትግርኛ ቋንቋ የማይናገረዉ ክፍል ደግሞ በሌላዉ በረት የሚለዩን እነማን ናቸዉ?” እነዚህ “ሪሳይክልድ” የሆኑ ሃይሎች ናቸዉ፣፣ በዉጭ አገር መንግሥትን እንቃወማለን የሚሉት ሰላማዊ ሠልፍ የሚያዘጋጁ ክፍሎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸዉ?(ብልህ ብትጠይቅ) ልንገርህ!?በዚህ በዋሽንግተንና በኖርዝ አሜሪካ የተደረጉ ሠላማዊ ሰልፎች የተከታተለ ሰዉ ሠላማዊ ሠልፍ የሚያደራጁት ሰዎች የተወሰኑ ሰዎች ናቸዉ የሚያደራጁት፣- በተደጋጋሚ!፣፣ “ሪሳይክልድ”- “ሪሳይክልድ!” ሲሆኑ ነዉ የምታየዉ፣፣ በተለያዩ ጊዜ አንድ ጊዜ “መላዉ አማራ” በሌላ ጊዜ “ኢደፓ” አንድ ጊዜ “ኢዲዩፒ” አንድ ጊዜ “ኤ ኤፍ ሲ” አንድ ጊዜ “ቅንጅት” አንድ ጊዜ “አንድነት” ሌላ ጊዜ “ግንቦት 7” እየሆኑ ታያቸዋለህ፣፣ ከመጀመሪያ ጊዜ ከጥንት ጀምሮ ለአስራ ስምንት ዓመት እነዚህ ድርጅቶች ናቸዉ የኢትዮጵያን መንግሥት ሲቃወሙ የምናያቸዉ፣፣ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ድርጅቶችን የሚመሩትም ቢሆን የሚታወቁት ያዉ አንድ/ሪሳይክልድ የሆኑ የምናቃቸዉ አዲስ ያልሆኑ ሰዎች ናቸዉ፣፣ ሌሎቻችንን በጎሰኛነት ሲከሱን “የአንድነት ሃይሎች ነን” “አንድ ነን” ይበሉ እንጂ እነሱም የምታያቸዉ “አንድ አይደሉም”፣፣ ዛሬ አንድ ይሆናሉ፣ ነገ ሲጣሉ ሲናከሱ ታያቸዋለሁ፣፣ ዋሽንግተን ዲሲ መጥተዉ መኣት ገንዘብ ያዋጣሉ ገንዘቡ የት እንደሚገባ አይነግሩህም፣፣ “የኢትዮጵያ ሕዝብ -ማይነስ - (ሲቀነሰዉ) ተጋሩ” ባንድ ወገን (ቀደም ብየ እንደነገርኩህ)…. (ነዉ ራሳቸዉን የሚያዩት)፣፣ እኛ የምንወክለዉ ትግሬዎች ያልሆኑ የኢትዮጵያ ሕብረተሰቦችን ነዉ ይላሉ፣፣ ስለዚህ እነዚህ ምንድ ናቸዉ “ሪሳይክሊንግ” የሚባል ነገር አለ አደለም?!አንድ ዕቃ ዛሬ ተጠቅመህበት ነገ ትጨፈልቀዉና ሌላ ዓይነት ዕቃ አድረግህ ታወጣዋለህ- ነገር ግን ዉስጡ ያዉ “ሪሳይክልድ” የሆነ ነዉ፣፣ ዉድ ወንድሜ አቶ ሙሉጌታ፤- “ተቃዋሚዉ የአንድነት ሃይል” ትግሬዉን አልወክልም ብሎም አያወቅም፣፣ የትግራይ ገበሬ ኗሪ ሕዝብ በሻዕቢያ ተከብቦ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ ሻዕቢያ ሲኦል ሲያሳየዉ፣ ወያኔ ትግራይ መሪዎች ሻዕቢያን ለብቻቸዉ መቋቋም አቅቷቸዉ በእርስዎ አነጋር “ኢትዮጵያ ማይነስ ትግራይ”የሚሉትን አነጋገርዎ ልጠቀም እና ያ ሃይል ነበር (80ሚሊዮን -5ሚሊዮን “75 ሚሊዮኑ ኢትዮጵያዊ) ዛሬ መለስ እየቦጨቀ ሚጥላት ሰንደቃላማችን ዓይነት ያላት ቀለም የያዘ ሕዝብ እያዉለለበለበ ነበር ወደ ትግራይ መጥቶ ህዝቡን ከመንገላታት ያዳነዉ፣(የምኒሊክ ዓድዋዉ ዓይነት ወገናዊ እርዳታ ተደግሟል)፣፣ ይህ የተቃዋሚዉ ክፍል ነበር ከፍተኛ ድጋፍ፣ አስተዋጽኦ አድረጎ በገንዘብም በፕሮፖጋንዳም በሞራልም በፕረስም የራሱ ቤተሰብና ዘመድ ወደ ባድሜ አስልኮ በደሙ የትግራይን ሕዘብ ከሻዕቢያ ወላፈንና ዉርደት ያዳነዉ፣፣ ታዲያ ይህ ተቃዋሚ እንዴት ሆን ነዉ “ትግራይን አንወክልም ይላሉ” ሚሉን አቶ ሙሉጌታ? መቸ ነዉ እንዲህ ያሉት? በየትኛዉ ፕረስ መግለጫቸዉ? አቶ ሙሉጌታ ንግግሩ ይቀጥል እና “ትገሬዎች ባንድ በኩል፣ የተቀረዉ ኢትዮጵያ ባንድ ጎራ ናቸዉ የሚሉን እንኚህ ሰዎች (ሪሳይክሎች)እነሱ እንደሚሉን “እኛ ትግሬዎች አንድ አይደለንም ይሉናል”፣፣ እንደዚህ የሚባል ነገር የለም፣፣ አንድ ቋንቋ የሚናገር፣ (አንድ ጎሳ)አንድ አይነት ጭንቅላት የለዉም፣፣ “የተገጠመብን” (ፕላንትድ ማለቱ ነዉ) አንድ ዓይነት ተመሳሳይ ራስ (ጭንቅላት/አስተሳሰብ ማለቱ ነዉ)የለም፣፣ ግለሰቦች የተለያዩ ራሶች አሏቸዉ፣፣ እና ትግሬዎች አንድ ናቸዉ ስትል “ጎሰኛነትን ማንፀባረቅ ነዉ”፣፣ ትግራዋይ እንደ አንድ ግለሰብ አድርገህ ማየት አትችልም፣፣ እነዚህ ግን እንዲመቻቸዉ (ጎሰኝነታቸዉን በሽፋን ለማንፀባረቅ ማለቱ ነዉ) “መንግሥትና ሕዝብ ኣንድ ነዉ ይሉሃል”፣፣ መንግሥትና ሕዝብ አንድ አይደለም፣፣ሌላ ቀርቶ የተለያየን ሰዎች ለቃለ መጠይቅ ስንቀርብ እንኳ አንድ ዓይነት አመለካካት አናቀርብም፣፣ ሌላ ቀርቶ የትግራይ ሕዝብ አንድ ነዉ ማለት ቋንቋችን እንኳ ከኣዉራጃ ወደ አዉራጃ ተለያየ ነዉ፣፣ አማራዎችም “The same thing” ናቸዉ፣፣ ዲሲ ያሉት ራዲዮ ጣብያዎች እንኳ ብትመለከት “አንድ ኢትዮጵያ የሚባል አለ፣ነጻነት ለኢትዮጵያ የሚባል አለ፣ ኢትዮጵያዊነት የሚባል አለ፣ ሕብረት የሚባል አለ፣ እነዚህ ሁሉ በአማርኛ ቋንቋ ሚተላለፉ ራዲዮ ጣቢያዎች ናቸዉ፣፣ የእነዚህ ራዲዮ ጣቢያዎች አዘጋጆች፣ በአንድ ሻይ ቤት እንኳ ቁጭ ብለዉ ተስማምተዉ ሊጠጡ የሚችሉ ሰዎች አይደሉም፣፣ Actually,እርስ በርሳቸዉ አንዱ በሌላዉ ዘመቻ ሲያካሂዱ ናቸዉ የሚዉሉት፣፣ እንኳን ለኢትዮጵያ ሕዘብ ሊወክል ቀርቶ አንድ ራዲዮ ጣቢያ ከአንድ ራዲዮ ጣቢያ አዘጋጅ በሰላም ቁጭ ብለዉ መወያት የማይችሉ ናቸዉ፣፣ ስለዚህ አማራዎች የሚባሉትም አንድ ዓይነት አንድነት ያለቸዉ ሰዎች አይደሉም፣፣ በጎንደር በሸዋ ወሎ ሸዋ ያለዉ አማራ አንድ አይነት አመለካከት አለዉ ማለት አትችልም፣፣ የሰዉ ልጅ አፈጣጠር አና አስተሳሰብ ያለመረዳት ድክመት የመጣ እምነት ነዉ፣፣ ስለዚህ እነዚህ የአንድነት ሃይሎች ነን(ስለ ኢትዮጵያ አንድነት እንቆረቆራለን እንወክላለን)የሚሉት የግል ፍላጎታቸዉን ለማራመድ “የ ኢትዮጵያ አንደነት አንድ ነዉ” ይላሉ፣፣ ልክ የአሜሪካ ሕዘብ ፍላጎት አንድ ነዉ እንደማለት ነዉ፣፣ የአሜሪካ ሕዝብ ፍላጎት አንድ ሊሆን አይችልም፣፣ እንኳን የኢትዮጵያ ህዘብ ፍላጎት አንድ ሊሆን ቀርቶ “የአንድ ቤተሰብ አባል እንኳ የተለያዩ ፍላጎት ስላላቸዉ-አንድ ፍላጎት አላቸዉ ማለት አይቻልም” (በሙሉጌታ አባባል አንድ የሚያደርጋቸዉ ማእከላዊ “የሃገር ህልዉና እና ያገር ፍቅር እና ሉኣላዊነት” ጉዳይም እንደ መናኛ ዕቃ የዕለት ተለት ፍላጎት ሁሉ ሕዝቦች የጋራ እሴት የሆነ የአገር ሕልዉና/ኢንተረስት የተለያየ ፍላጎትና አስተአየት እንዳለን አድርገዉ ወደ ታች ያወርዱናል።ተከብሮ የመኖር ፍላጎት፤ በዉጭ በጠላት እና በዉስጥ ጠላት ስንነደፍ/ስንጠቃ ባድሜ ላይ የታዉ “የጋራ ሕዝባዊ ፍላጎት”የረሱት ይመስላሉ)፣፣ ይቀጥሉ እና ባገር እና ባንደነት ጉዳይ የሚያክል ትልቅ ጉዳይ “ሂፕክሪት ፍልስፍና” ዉስጥ ሲገቢ እንዲህ ይላሉ “ የወንድም የሴትም ፍላጎት እንደዚሁ የተለያየ ፍላጎት አላቸዉ፣፣ እና ትግሬዎች ከኛ ጋር አላበሩም የሚሉት …. Look …(እነሱም አንድ አይደሉም) “ትግሬዎች ለምን ያስፈልጉሃል?ለምን ድ ነዉ ትግሬዎችን ለይተህ ከኛ ጋር አብረዉ ድምፃቸዉን አያስተጋቡም የሚሉት?ስንት አገዉ ይሳተፋል?ስንት ዓፋር ይሳተፋል ስንት ኦሮሞ ይሳተፋል ስንት ሶማልያ ይሳተፋል?ይታወቃል? ለምንድ ነዉ ትግሬዎች ዓይን ዉስጥ የገቡት?ምክንያቱም ትግሬዎች ስልጣን ዉስጥ ስላሉ ከሚል የተነሳ ነዉ፣፣” ይሉና በመቀጠል
ስለዚህ የነሱ ሰዎች (ትግሬዎች-ወያኔዎች ማለታቸዉ ነዉ) ስልጣን ላይ ስላሉ “ተጠቃሚ እስከሆን ድረስ ምን አገባን ይላሉ” ወደ ሚል ትርጉም እንዲመጣ ነዉ ጥረት እየተደረገ ያለዉ፣፣ የተቀረዉ ኢትዮጵያዊ ቅር ብሎት በተቻለ መጠን “ቆስቁሰህ” “እንዲበሳጭ አድርገህ በትግሬዉ ላይ እንዲነሳ ለማድረግ ነዉ”፣፣ስለዚህ ትግሬዎች ለምንድነዉ እኛ ጋር የማይተባበሩት የሚሉት ነገር ፣ መጀመሪያ ነገር “እኛ”የሚባል ነገር የለም ምክንያቱም ትግሬ ያልሆነ“Non-Tigrayan”የሆነ Populationአንድ-ነዉ-የሚባል (አነጋገር/እምነት) ልክ አይደለም፣፣ ምንም ማስረጃ የለዉም፣፣ እንደነገርኩህ “ቅንጅት እንኳን አንድ አይደለም”፣፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን ስትመለከት ራሱ “አንድ” አይደለም፣፣ እነ ልደቱ እና እነ ሃይሉ ሻዉል ቁጭ ብለዉ ሻይ ሊጠጡ አይችሉም፣፣ ሁለቱም ግን ከአንድ ድርጅት የወጡ ሰዎች ናቸዉ፣፣የግንቦት 7 መሪዎች “ትናንት” ምን ይሉን ነበር? Look! ደ/ር ብርሃኑ እስር ቤት ዉስጥ እያለ ጻፈዉ የተባለዉ መጽሓፍ ስትመለከት የሚሰብከዉ ስለ “ሰላም” ነዉ፣፣ አንድ ኣመት ሳይቆይ “ጦርነት” ሲል ያስተዛዝባል። “ምን ዓይነት ሕሊና ነዉ” ትላለህ፣፣ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ “ትናንት ከኢሕአዴግ” ጋር ኖሮ ‘ኢሕአዴግን’ እንዳላደራጀ እና የኢሕአዴግ ወታደር እንዳላደራጀ፣ ዛሬ ዞር ብለህ “የወታደሮችን ቁጥር ዘርዝረህ”-አብዛኛዎቹ “ትግሬዎች” ናቸዉ ብለህ You know የጎሳ መርዝ ለመበተን መሞከር፣ ከአንድ የኢትጵያ አንድነት ለመጠበቅ እታገላለሁ ከሚል ክፍል የሚጠበቅ አይደልም፣፣ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነዉ፣፣….” በማለት “ሂፒክሪት” የሆነ ለሙግት የማያመች “ብር አምባሩ” የተደበላለቀ “ዉሉ የጠፋ” ነገር በመግባት “የወያኔን የጎሳ አደረጃጀት እና ያድልዎ ስራ “ክደኑት” (የወታደሩ ክፍል አብዛኛዉ በትግራይ ታጋይ የተያዘ ቢሆንም -ዝም በሉ!ኢ-ፍትሃዊ ስራ አትዋጉ ነዉ የሚሉን)። አስኪ ከኔ በበለጠ የተረዳችሁት ብትኖሩ ከሰጠዉ መልስ የተረዳችሁት ከሆነ ቀስ ብላችሁ አንብቡትና ለማስመር የፈለገዉ/ብልቱን ያገኛችሁት ከሆነ ተቹበት “እባካችሁ!”፣፣ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ እኛን “ሪሳይክሎች” ብለዉናል፣ እና አስኪ አንዳንድ በስንት መከራ ደጋግሜ ለመረዳት ሞክሬ ሊገባኝ ያልቻለዉን ለናንተ ትቼ -ጥቂቶቹን በበኩሌ የተረዳሁዋቸዉ አንዳንዳንዶቹን በሚቀጥለዉ በሌላ አምድ ሊሂቁንና እና የትግራይ ህብረተሰብ ያለዉ አንድነትና ልዩነት ልዩ አስተያየት አቀርብላችሗለሁና ያንን በሚመለከት ጠብቁኝ፣፣ እስከ እዛዉ ድረስ ግን አቶ ሙሉጌታ አረጋዊን ለማስታወስ የምፈልገዉ “የተለያዩ ራዲዮኖች/ሚዲያዎች እና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የተለያየ ስም የያዙ ተቃዋሚ ድርጅቶች አለመስማማት ይኑራቸዉ እንጂ- (እርስዎ ሪሳይክሎች- የሚሏቸዉን ማለቴ ነዉ) አብዛኛዎቹ (አሰምርበታለሁ ---- “አብዛኛዎቹ”) ተቃዋሚ ድርጀቶች ልዩነታቸዉ የስትራተጂ ሳይሆን “የታክቲክ”ልዩነት መሆኑን ላስታዉሰዎ እፈልጋለሁ፣፣ ወያኔን እንዴት እናስወግድ በሚለዉ ላይ ልዩነት ያላቸዉ እንጂ “የወያኔ ተቃዋሚም-ደጋፊም”-አይደለንም በማለት አይደለም እየተጨቃጨቁ የሚያዩዋቸዉ፣፣ የትግራዩን ገበሬ ፖለቲካ ዉስጥ ሳናስገባ (ኤሊቱ ነዉና ወሳኙም ለዚህ ጉድ ያደረሰዉም) የትግራዩ ሊሂቅ/ኤሊት እንደ “አሰር ግመል” “ወደ ሌላ እንዳያይ -አይኑ በጨርቅ ተጨፍኖ” ባጭር የገመድ ሉጓም ከቀምበር እንጨት ጋር ታስሮ ባንድ ጠባብ“ክብ”አዉድማ ሙሉቀን ዙርያዋን እየዞረ ሰሊጥ እንደሚጨምቅ ገምል “ደግሞ ደጋግሞ”-በጎሰኞች ጠባብ አወድማ ዙርያ እየዞረ “የወያኔ መሪዎች ወደ አጠመዱለት የጎሰኛነት ወጥመድ” በጭፍን ስለ እነሱ ደህንነት እና ሙሉ ጤንንት “እንባ”-ባደባባይ የሚያፍስ እንደ እናነንተዉ የትግራዩ ኤሊቶች”እንዳልሆኑ ግን በእርግጠኝነት ልነግርዎ እወዳለሁ፣፣ “ሪሳይክለድ!” ሲሆኑ ነዉ የምናያቸዉ በማለት በተለያዩ ጊዜያት አንድ ጊዜ “መላዉ አማራ” በሌላ ጊዜ “ኢደፓ” አንድ ጊዜ “ኢዲዩፒ” አንድ ጊዜ “ኤ ኤፍ ሲ” አንድ ጊዜ “ቅንጅት” አንድ ጊዜ “አንድነት” ሌላ ጊዜ “ግንቦት 7” እየሆኑ ታያቸዋለህ፣፣ ከመጀመሪያ ጊዜ ከጥንት ጀምሮ ለአስራ ስምንት ዓመት እነዚህ ድርጅቶች ናቸዉ የኢትዮጵያን መንግሥት ሲቃወሙ የምናያቸዉ፣፣ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ድርጅቶች የሚመሩም ቢሆን የሚታወቁት ያዉ አንድ የሆኑ የምናቃቸዉ አዲስ ያልሆኑ “ሪሳይክልድ” ሰዎች ናቸዉ” ያሉዋቸዉን ተቃዋሚዎች አርስዎ እንባ ያነቡላቸዉ “ባለ አንቀጽ 39ኞቹ ዓረናዎች”ላይ እና እርስዎ “ለመቃወምም ለመደገፍም- “ፈራ ተባ” ለሚሉሏቸዉ መለስ ዜናዊንን “ጥይት ሳይተኩሱ” በፖለቲካዉ መስክ እርቃናቸዉን ያጋለጡ እነኚህ “ሪሳይክሊድ-ተቃዋሚዎች”፣-እንጂ የእርስዎ “ቡጥቡጥ-መስመርዎ”(የኔዉ ሃማቱማ እንዳለዉ-“ዝብርቅርቅ ፖለቲካ” )ዎ፣ እንዳልሆነ እንዲገነዘቡት አፈልጋለሁ፣፣ ለመሆኑ -አንዴ “ማገብት አንዴ “ተሓሕት”፣ አንዴ “ህወሓህት” አንዴ “ማሌሊት” አንዴ “ኢህአዴግ” አንዴ “ተሃድሶ” አንዴ “ዓረና” አንዴ “መጻኢት ትግራይ” ወዘተ….እያሉ ለ35ዓመት እስካሁን ድረስ እንደ ነገሥታት በሥልጣን ዙፋን ላይ የሚገኙ የትግራይን ገበሬ እና የትግራይ አዛዉንቶች በእሳት እየለበለቡ “ሲኦል’-ኑሮ እንዲገፋ ምክንያት የነበሩት “ሪሳይክልድ ወያኔዎች” ናቸዉ ለማለት ሳይደፍሩ (ያዉም እርስዎ የነሱ እምባ አዉራጅ ሆነዉ) ዘብ እና አገር በድለዋል እና ከስልጣን ይወገዱ ስላሉ “ሪሳይክልድ ናቸዉ” ማለትዎ ትንሽ ሕሊናዎ አይከብደዎትም? ለመሆኑ ጎሰኛ ስርዓትን የሚያራምዱ፣ የባሕር በራችን የዘጉብን ብሔራዊ ወንጀለኞች “ይወገዱ” ሲባል “እኔ እዛ ዉስጥ አልገባም” “ይወገድ የሚለዉ ቃል “ይከብደኛል” ሲሉ “ሪሳይክልድ ሊባሉ የሚገባቸዉ ”ብሔራዊ ወንጀለኞች እና የጎሳ ነገሥታትዎን“ “ከይወገዱ” በላይ ምን እንዲባል ፈለጉ? የአንድነት ሃይሎች ሊባሉ የቻሉት ወይንም አርስዎ “ኢትዮጵያን የወከሉ መሆናቸሁን ማስረጃ አቅርቡ ቢባሉ መልስ የላቸዉም” በማለት ዉሉ የጠፋ ነገር መከራከርዎ በእዉነት እርስዎ የሕግ ምሁር ነዎት “የሚጠይቁት መረጃ ከወያኔ ወይስ ከዓረና ቢያመጡለዎት ይመርጣሉ?” የአንድነት ሃይሎች መሆናቸዉ የሚጠራጠሩ ከሆነ በምርጫዉ ጊዜ የታየ መረጃ ካላጠገበዎ-ሌላ ምን እንዲቀርብ ይፈልጋሉ? ሌላ ቀርቶ አዲስ አበባ ዉስጥ የትግራይ ተወላጅ በብዛት ይኖርበታል በተባሉት አካባቢዎች ሳይቀር “ላንድነት ሃይሎች” እንጂ “ለጎሰኞች” እንዳልመረጠ ይነገራል (መረጃ ባይኖረኝም)፣፣ ስለዚህ ምን መረጃ ይምጣለዎ?ለመሆኑ እርስዎ “የትግራይ ራስ/ጭንቅላት የተለያየ እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ የትግራይ ድርጅቶች ልክ እንደሌሎቹ የተለያዩ መስመር/አስተሳሰብ የሚያራምዱ ድርጅቶች አሉዋቸዉ”በማለት ትግራይ ማሕበረስብ ድርጅቶች ዉስጥ ልዩነት እንዳለ ለማመለከት ሞክረዋል (አንድ እንዳልሆንን ለመከራከር ሞክረዋል፣፣ አርስዎ ያልገባዎት ነበር ትንሽ ጣል ላርግለዎት “በትግራይ ዉስጥ በትግራይ ሰዎች/ኤሊቶች የሚመሩ የትግርኛ ተናጋሪ ሰዎች የሚመሩዋቸዉ ድርጅቶች “መሪዎቻቸዉ እና አባሎቻቸዉ” ካንድ ጎሳ የወጡ ናቸዉ!ያንድነት ሃይሎች/ኢትዮጵያዊ ሃይል/ድርጅት ሚባሉት ደግሞ ከተለያዩ ጎሳዎች የተዉጣጡ መሪዎች እና አባሎች ያቀፉ ድርጅቶች ናቸዉ” ለዚህም ነዉ “የአንድነት ሃይል” ነን የምንለዉ፣፣ የኦሮሞ ከሆነ ኦሮሞ ብቻ ነዉ (ኦነግን ለምሳሌ)፣ ሶማሊ ከሆነ ያዉ መሪዉም ተመሪዉም ሶማሊ ነዉ፣ ጉራጌ .ዓፋር አገዉ ትግራይ ወዘተ ከሆነም መሪዉ ያዉ ካንድ ጎሳ የወጣ መሪ እና ካንደ ጎሳ የወጣ አባል ነዉ የሚሰባሰበዉ፣፣ ስለዚህ ልዩነቶቹ ከዚህ ቢነሱ የአንድነት ሃይሉ “ክስ” ቁልጭ ብሎ ሊገባዎ ይችላል፣፣ ኦሮሞዉ “ትግራይ ሶሊዳሪቱ” ዉስጥ አይገባም/ድርጅቱን መምራት አይችልም፣ትግራዩ የዓፋሩን ድርጅት የኦሮሞዉን የጋምቤላዉን ደርጅት የዓፋሩ የአማራዉን ድርጅት መምራት ወይንም አባል መሆን አይችልም፣፣ ምምራት እና አባል መሆን የሚችለዉ እርስዎ አብዛኛዉ ኢትዮጵያን ህብረተሰብ/ህዳጣን መወከሉን “ሰርትፊኬት/መረጃ”ያቅርብ እያሉ የሚጠይቁትን የ “በአንድነት ሃይሉ ዉስጥ ሲደራጅ ብቻ ነዉ!“ ስለዚህ የትግራይ ተወላጆች እንደተቀሩት (እንደተቀሩት የአንድነት ሃይሎች) የተለያዩ ድርጅቶች አሉን፣ ስለዚህም “ባንድ ጭንቅላት የምንጓዝ አይደለንም መወቀስ የለብንም” የሚሉትን “ፍሎሶፊካል -ሂፒክሪት” ክርክርዎ ለየት ባለ በፖለቲካዉ መልኩ ቢመለከቱት ጥሩ ነዉ የሚል ምዕዳን አለኝ፣፣ ከ ዓረና እና ከመለስ ወያኔ ሌላ ምን የፖለለቲካ ድርጅት አለ?ካሉም “ሲቪክ ማሕበራት ናቸዉ” እንሱ ደግሞ ፖለቲካ ዉስጥ አንገባም የማንም ፖለቲካ ደጋፊም ተቃዋሚም አይደለንም ባዮች ናቸዉ። ታዲያ ምን የሚሉት የተለያየ አስተያየት ነዉ የሚነግሩን? ስለዚህም ነዉ የአንድነት ሃይሉ “አንድ አይነት ሰዎች”ይምሩትም ይኑርትም “ከአንድ ጎሳ” የወጣ አባልና መሪ አይደለም ነዉ እያልን ያለነዉ፣፣ የድርጅት ስራ ለማጠናከር አባሎቹን እና መሪዎቹን በተለያዩ ዘርፎች አሰማርቶ ይለዋዉጣቸዋል እንጂ “እርስዎ ስም እንደለጠፉላቸዉ-“ሰዎች እንጂ” “ሪሳይክልድ እንደሚደረግ ዕቃ” ስላልሆኑ እንደ አለቀ ዕቃ አይጣሉም! የትም አይሄዱም! ሰዎች ናቸዉ! ዜጎች ናቸዉና ሕይወት አላቸዉ በድርጅቱ ዉስጥ መታቀፍ እስከፈለጉበት ጊዜ ታቅፈዉ የአንድነት ሃይሉን እያራመዱ አብረዉ ከድርጅቱ ጋር ያድጋሉ/ይቆያሉ፣ ይመራሉ (ላላ) ይመራሉ(ጠበቅ)፣፣ ድርጅቱን ለረዢም ጊዜ ሳይለወጡ ቦታዉን ይዘዉታል የሚል እሮሮ ካለ “የዲሞክራቲክ ምርጫን” የሚመለከት ጉዳይ እንጂ “ሰዎቹ አምናም ታች አምናም ሰላማዊ ሰልፍ የሚያዘጋጁት እና ተቃዉሞ የሚያሰሙት ኢትዮጵያዉያን ዜጎች የአንድ አይነት የሰዎች መልክ ብቻ ነዉ የምናየዉ እና ” የኢትዮጵያን የተለያዩ ህዳጣን ሊወክሉ አይችሉም” ማለት የተሳሳተ እምነት ነዉ፣፣ አዳዲስ አባሎች ሊታዩ የሚችሉት እንደ እርስዎ ያሉት ኤሊቶች “ሪሳይክልድ ሰዎች”ሆኑብን ከማለት “ተቃዋሚም-ደጋፊም አይደለንም”ከማለት ወደ አንድነት ሃይሎች ተቀላቅለዉ “የሪሳይክሉን ኡደት”ማዳንም ይጠበቅበዎታልና ወያነ ትግራይ የበለጠ ጉዳት ሳያደርስ ወደ አንድነቱ ጎራ ይቀላቀሉ፣፣ አንድ አይነት ሰዎች ተቃዉሞዉንም ፖለቲካዉንም ለዢም ጊዜ የሚያራምዱት እኮ ደሞዝ ይገኝበታል ተብሎ ሳይሆን ያገር ክብር ተደፍሮ አይተዉ ቁጭት እና አልክ ይዟቸዉ ነዉ “ነፃ እስካልሆንን ድረስ ከመድረኩ አንለይም”እያሉ ያሉት፣፣መድረኩ ላይ ቆመዉ የሚሰደቡ የሚንገላቱ ሚታሰሩ ሚሰደዱት እኮ “የኢሕአዴግን ተቃዋሚም ደጋፊም አይደለሁም”የሚሉት እንደ እርስዎ ዓይነት የትግራይ ሊሂቃን/ኤሊቶች ጥሪ ተደርጎ “አንደባለቅም” “እምቢ” ስላሉ እኮ ነዉ! አሳፋሪዉ የትግራይ አብዛኛዉ ሊሂቅ ጥግ ጥጉን ወደ ወያኔ አዳራሽ መሞቅ ስለመረጠ እኮ ነዉ! ፣፣ አንድ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሆነናል እና እደከምን ነዉ እና አግዙን እኮ ነዉ የጥሪዉ አንኳር? “እኛ” የሚሉት ሃይሎች( መላዉ ኢትዮጵያ “ማይነስ “ትግሬዉ” በራስዎ ቃላት አጠቃቀም) የሚሉት 75 ሚሊዮኖች ከሆኑ እኛ (ትግሬዎች) 5 ሚሊዮን ድጋፍ ለምን ይፈልጋሉ? “ብዙሃኑን የሚወክሉ ከሆነ?ለምን እኛን ፈለጋችሁ? የሚለዉ በጣም አስገራሚ ጥያቄዎ ለሌሎቹ መልስ ቢሰጡበት ትልቅ አነጋጋሪ መድረክ ነዉና ለሰፊዉ አንባቢ ትቼ፣ ባጭሩ ግን ለማለት ምፈልገዉ“75ሚሊዮን ሕዝብ ባድሜ ድረስ ድረስልኝ ብሎ 5ሚሊዮን የትገራይ ሕዝብ ጥሪ ካቀረበ ዛሬ 75ቱ የ5ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ ፈልጎ የትግራይ ሕዝብ ድረስልን ቢል የሚያስቆጣዉና የሚያስከፋዉ የቱ ላይ ነዉ? ወይ ጋዶ! ወይ ቱ ጉዱ! “እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋነታችን እንድንወጣ ጥሪ አታድርጉልን” የሚሉ ከሆነ የታሳሰተ ቅሬታ በጣም አስገራሚም ነዉ፣፣ ለምን ሌሎቹን ጥሪ ሳታደርጉ ነጥላችሁ ትግሬዉን ለወቃሽ ዓይን ሰጥታችሁ እኛን ታስጠሉናላችሁ የሚለዉ “ማምለጫ ቀዳዳ”-{ዲፍነሲቭ -ሉፕ ሆል)አይሰራም፣፣ ወያኔ በግምባር ቀደም የገነባዉ (ከጥፍር እሰከ ራሱ) እኛ ትግራይ ተወላጆች እንጂ የኦሮሞ/አማራ/የሶማሊያ …ወዘተ ታጋዮች/ሕብረተሰቦች/ህዳጣን አይደሉም የገነቡት፣፣ ከገንዘብ አስከ የሰዉ ሃይል ምንጩ ከእኛዉ እና እኛ ብቻ ነበርን፣፣ ኤርትራ ድረስ ሄደን ’20,000 ሺሕ በላይ የትግራይ ታጋይ ይዘን ደሙ እና አጥንቱ እዛዉ አስከስክሰን የኤርትራን ሕዝብ ነጻ ካወጣን፣ ለምን ዛሬ በገዛ አገራችን እና ሕዝባችን ‘እኛዉ በፈጠርነዉ እና በእኛ እና ጉልበት፣ጥረት፣አስተዋጽኦ፣ጥብቅና እና ተንከባካቢነት ያሳደግነዉ ድርጅት “የኢትዮጵያን ህዝብ-እንደ ባእድ ኩፍኛ ሲበድል፤ ሕዝቡ “የፈጠራችሁት ድርጀት እናንተዉ ናችሁ እና “አንድ በሉልን! እባካችሁ ኑ እና አብረን ይህ ግፍ/በደል እናስቁም”ብለዉ ጥሪ ማድረጋቸዉ የሚያስቆጣዉ እምኑ ላይ ነዉ? በስማችሁ እየነገደ ነዉና እናንተን የሚወክል ከሆነ እባካችሁ እናንተን ተባባሪ አድርገን ከመመልከታችን በፊት በጠላትንት እናዳንመለከታችሁ “እኛ የለንበትም” በሉን ‘የለንበትም” የምትሉ ከሆነም አብራችሁን ታገሉ አና ይሄ በትግራይ ስም የሚነግደዉ ድርጅት አብረን እናስወግደዉ “ኑ!” ምነዉ ድምፃችሁ ራቀብን? በማለት ለእርዳታ ጥሪ በማድረጋቸዉ ለምን ትወቅሱናላችሁ?ለምን ለብቻችን/ለትግሬዉ ህብረተሰብ/ኤሊት ጥሪ ታደርጋላችሁ? የሚለዉ “የማምለጫ ቀዳዳ” መዉጫ ይቅርታ የማይደረግበት አጉል “ካብ’ ነዉ፣፣ ለጥሪዉ ምክንያትም መነሻ አለዉ፣፣፣፣ የትግራዩ ኤሊት ለምን እሱ ብቻ “ዓይን ዉስጥ” ይገባል ለሚሉን “ሂፒክርት ክርክርዎ” በሚቀጥለዉ አምዴ ለምን የትግራዩ ኤሊት እና ማሕበረስብ ዓይን ዉስጥ ሊገባ እንደቻለ መልሱ ያገኙታል እና መልሱን ይጠብቁ፣፣ ኤሊቱ የወያኔ ፖለቲካ አራማጅ ሆኖ የትግራይ ሕዝብን “ሳያስበዉ’ የወያኔ ሰለባ’ እና “በኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይን እንዲገባ መጥፎ ሚና ተጫዉቷል” ‘ለጎሳዉ ልዩ እንክብካቡ እና አስተዳደራዊ እና ቁሳዊ አድልዎ አድርጓል ስለተባለ “የኢንተርሃሙዎ’ፖለቲካ ነዉ እያካሄዱብን ያሉት “የትግራይን ሕዝብ ልታስፈጁ ትቀሰቅሳላችሁ”እያሉ ከመለስ ዜናዊ በላይ ሆኑብን እሳ ምነዉ አቶ ሙሉጌታ?!የትግራይ ሕዝብ “ዘርፏል አልተባለ! ዘራፊዉም አድልዎ ፈጻሚዉም “ወያነ” ትገራይ” የተባለ በመንግሥትነት ዙፋን ላይ በሻጥር እና በጠመንጃ ሃይል የተቀመጠዉን ጎሰኛ ድርጅት/ቡድንን ነዉ እየተወቀሰዉ እና ሃላፊነት እየወሰደ ያለዉ! ይሄንን የማቃናት ጉዳይ “አትዝረፍ’-አታዳላ’-የማለት ሃላፊነት በስሙ እየተነገደበት ያለዉ ክፍል በተለይም “ሊሂቁ” ነዉ፣፣ ይህ ከማድረግ ፈንታ “ወደ ተቃዋሚዉ አድልዎ እየተፈጸመ እንዳለ በማስረጃ ስለተከራከረ “ኢንተርሃሙዌ/ ዘር ማጥፋት ዘመቻ በትግራይ ሕዝብ ላይ እያካሄዱ ነዉ ማለት ለጀሮ አይጥምም፣- ጋዶ!! የትገራይ ህዝብም ሆነ ሊሂቁ አንድ ጭንቅላት የለዉም እያለን ያለዉ ሙሉጌታ አረጋዊ ሊሂቁ ባንድ የወያኔ ጭንቅላት አስተሳሰብ ዉስጥ ተጠፍሮ እንደነበር ማስረጃ ለማቅረብ እንዲመቸኝ፣ ወያነ ትግራይ የትግራዋዩን ሊሂቅ እንዴት እንደተጠቀመበት እና ሊሂቁ አስከ ቅርብ ድረስ ወያኔ ትግራይ ለሁለት ሲሰነጠቅ ያለቀሰዉ አሳፋሪና አስተዛዛቢ ልቅሶ እና ያሳዉ የዘቀጠ ሃገራዊ የፖለቲካ ብስለት በሚቀጥለዉ እትም “ትግራይን ለማዉደም ለምን ፈለጋችሁ?“ከትግራዊያን ፕሮፌሽናሎች”የሚል ያስተላለፉት አስቂኝ መልክታቸዉ አንድ ዓይነት ጭንቅላት (በዛዉ በጎሳ አዉድማ ዙርያ) እንዴት ያስቡ እንደነበር እንድትመለከቱት አቀርባለሁ፣፣ለምን ሰብሰባ ላይ በተቃዉሞ አብረዉን አይቆሙም ለሚለዉ ጥያቄ ምን ያህል ልክ እንደሆንን እና ከምን ምክንያት እንደተነሳን ታዩታላችሁ፣፣ ተከታተሉ፣፣ ይቀጥላል….. ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Sunday, June 14, 2009

ለአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ

ለአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ የጎሳ ፖሊሲን የነደፉ የወያኔ ጭንቅላቶች ለሁለት ሲከፈሉ የማን ደጋፊ ነበሩ?
ለሁለት ተከታታይ ሳምንት በነፃነት ራዲዮ አወያይነት ተማክሎ በዶክተር አሰፋ ነጋሽ እና በአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ መካካል ሲካሄድ የነበረዉ ዉይይት እንደተከታተላችሁ ተስፋ አለኝ፣፣ የወይይቱ አርዕስት ወያነ ትግራይ ያመጣብን አደጋ እና መፍትሄዉ ነበር፣፣ ላምልጥ እንኳ ቢባል የዉይይቱን ብልት/አንኳር ለማሳየት “ጉዳቱና የጉዳቱ ደጋፊዎች” ከማንሳት (Identify-መለየት) ማምለጥ አይቻልምና ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ፣ወያነ ትግራይ ያመጣዉ የጎሳ ፖለቲካ በአገሪቱ ዉስጥ ያስከተለዉ ሰበብ እና ለዚህ የጎሳ ፖለቲካ ፈጣሪዎች እንክብካቤ እና ድጋፍ የሚሰጡ ክፍሎች እነማን መሆናቸዉ ለይተን ካላስቀመጥን እና መለየት ብቻ ሳይሆን ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሲያራምድ “ነፃ አወጣሃለሁ፣ እጠቅምሃለሁ፣’ በማለት በእርሱ/በጎሳዉ ማለትም በትግራይ ሕዝብ ስም እየተጠራ እንደመንግሥትነቱ የያዘዉን ሥልጣን ተጠቅሞ ለጎሳዉ ልዩ እንክብካቤ እና አትኩሮት ከሌሎቹ አካባቢዎች በበለጠ በመቆርቆር “የአስተዳደር አድልዎ” በማድረጉ፣ ይህ አድልዎ በሰፊዉ /በአብዛኛዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አሳድሯል፣፣ በዚህ ሳያበቃ ስርዓቱ የጎሳ ፖሊሲ ማራመድ ዓይነተና መመሪያዉ እና የታገለለት ፕሮግራም ስለሆነ በዛ ስርዓት አወቃቀር የሕዝቡን አንድነት እያጨለመ ‘አካባቢያዊ/ጎሳዊ”ሕሊና እንዲያድርበት በማድረጉ ምክንያት የአገሪቱ የሕሊና አመለካካት (Psychology) ከአንድነት ይልቅ አካባቢያዊና ክልላዊ- ማለትም “ትግራዋይነት፣ ጉራጌነት፣ ኦሮሞነት፣ አደሬነት፣ ሶማሌነት ወዘተ…”በመከናነብ “ኢትዮጵያዊነትን እና የጋራ ሰብአዊ ቤተሰብነትን”አኮስምኖታል፣፣ ለዚህም በተጨባጭ የታዩት የጎሳ ግጭቶች፣ እልቂቶች ፣መፈናቀሎችና እና ምሬቶች ህያዉ ማሕደር ይዘዋል፣ እና ለዚህ ችግር “ኤሊቱ” በተለይም በስሙ የሚነገድበት “የትግራይ ኤሊት” ተቃዉሞዉ ጎልቶ አልታየም፣ ስለዚህ “ኤሊቱ”በግምባር ቀደም ሕዝቡን አስተባብሮ የጎሰኛ ስርዓት የሚያስተምረዉን ትምህርት ከማመንመን ይልቅ ወይም “ዝምተኛ”ሆኗል አልያም “ስርዓቱ ደጋፊ”በመሆን ለተማረረዉ ሕብረተሰብ መከራዉ እንዲራዘም “በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ” አስተዋጽኦ እያደረገ ስለሆነ “ መፍትሄዉ ለመሻት (ጎሰኛዉን ስርዓት ለማስወገድ”)1-አስከ ዛሬ ድረስ ስርዓቱ በቀጣይነት ለራሱ ጎሳ (ከድህነት ነፃ አወጣሃለሁብሎ ለታገለለት የትግራይ ኗሪ)እያደረገለት ያለዉ እጅግ ቁሳዊም ሆኑ ሞራላዊ ድጋፎች በአድሎአዊ ፖሊሲዉ እየታጀበ ጎሰኛ መንግሥታዊ አስተዳደር ማራመዱን ሳንሸሽግ (ፈራ ተባ ሳንል) ያለዉን ሃቅ መነጋገር መቻል አለብን፣፣ (2) ለዚህ ጎሰኛ-ፖሊሲ እንዲቀጥል የትግራይ ኤሊቶች እዉነት ወያኔን እንቃወማለን/የጎሳ ፌደራሊዝመ እንቃወማለን የሚሉ ከሆነ እና “በነሱ ስም መነገዱ ካልወደዱት ቅዋሜአቸዉ ጎልቶ መዉጣትና ያለዉን አድልዎ “ደፍረዉ” መዘርዘር “ማመን” አለባቸዉ፣፣ ይህ ያደረጉ የትግራይ ተወላጆች ካሉ በጣት የሚቆጠሩ ናቸዉ፣፣ ስለሆነም በነሱም ላይ መወያየት “የችግሩ ግማሽ መፍትሄ” በመሆኑ “ሊሂቁ” ለምን “ሎሆሳሳ” ድምፁን ወደደዉ? ነበር የዶክተር አሰፋ ነጋሽ ክርክር (በራሴ ቃላቶች ሳጠቃልለዉ) የተደመጠዉ፣፣
የትግራይ ተወላጅ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ደግሞ ያሉት እጠቅሳለሁ፣- “አሁን ዶክተር አሰፋ ነጋሽ እያለ ያለዉ ምንድነዉ? “…ሃሳቡን እየገለጸ ያለዉ የት ቆሞ ነዉ ብለህ ስትጠይቅ”ዶክትር አሰፋ ራሱ የሆነ ጎሳ ግቢ ዉስጥ ገብቶ ነዉ”፣፣ …እያለ ያለዉ In this case ይሄ የአድልዎ የጎሳ ፖለቲካ ትግሬዉን እየጠቀመ ነዉ! እንግዲህ ትግሬዉ እየተጠቀመ ነዉ ካልክ “እሚጎዳ ሌላ ወገን አለ ማለት ነዉ”፣-እሱ ደግሞ “አማራ” ነዉ ማለት ትችላለህ፣፣ አሁን ዶከትር አሰፋ እምገምተዉ “አማራ” ማለቱ ይመስለኛል፣፣ እና እንደዚህ አሉ አሃዞች (ደ/ር አሰፋ የዘረዘራቸዉ በትግራይ ዉስጥ ከሌሎቹ አካባቢዎች እያነጻጸረ ያቀረባቸዉ የግንባታ መሰረቶች/ተቋሞችን ነዉ አሃዝ እያለ አለዉ) complete ሊሆን አይችልም፣፣ በአሃዙ መከራረከር ኢቻላል፣፣አንተ የተቀበልከዉ አሃዝ እኔ ላልቀበለዉ እችላለሁ፣፣ እ..well የሚቀበለዉም ሊኖር ይችላል፣፣ እዚህ ላይ ብዙ “ዘመን” አዉርተንበታል፣፣ለና ሊጠቅመን የሚችለዉ ጠቅለል ባሉ ነገሮች መስማማት ስንችል ነዉ፣፣ ምን ማለት ነዉ “Ethnic federalism” የጎሳ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ እሚበጅ አይመስለኝም እሚለዉ አስማማለሁ ተቀብየዋለሁ፣፣ ለምን የሚለዉም ካሁን በፊት ተነጋግረንበታል፣ -አሁን መደረግ ያለበት የሚመስለኝ እኔ ከ35 ኣመት በፊት ሌላ ያ የምናወግዘዉ አሁን ማለት ነዉ- እሚያደርገዉን አሁን በሌላ መንገድ አቅርበን (35በፊት የሚለዉ ወያኔዎች የትግራይን ሕዝብ ሲሰብኩት”አማራዉ ጎድቶሃል፣ የሸዋ ክፍል ሲበለጽግ አንተን/ትግራይን እንድትደኸይ አደርገዋል ሲሉ የነበሩትን ቅስቀሳ ማለቱ ነዉ)፣-አንድ ጎሳ በሌላ ጎሳ ሊያነሳሳ እሚችል (ቅስቀሳ በዚህ በ21ኛዉ ክፍል ዘመን ዛሬም እየደገምከዉ ነዉ)፣- ለምሳሌ ስማ ኢሳያስ (የራዲዮኑ አዘጋጅን ነዉ) ትግሬዉ እየተጠቀመ ነዉ ብለህ ስትናገር ምን እያልክ ነዉ?ሌላዉ ትገሬ ያልሆነ ምንድነዉ እሚሰማዉ? ይሄዉ ትግሬዉ እየተጠቀመ ስለሆነ አንተ ዝምብለህ ሞኝ ነህ!ምነድነዉ “በሞኝ ደጃፍ ምንድነዉ የሚባለዉ?{ዋትኤቨር?}(ሞፈር/ዛፍ ይቆረጣል፣ እንደሚባለዉ ማለት ነዉ፣፣ የኢትዮጵያ ንብረት ባይዘወይ አዲስ አይደሉም፣፣ ኢትዮያ እየተዘረፈች፣ ትግሬዎች ኢትዮጵያን እየዘረፉት ነዉ ብሎ የሚናገር ሰዉ ነዉ፣፣ እና እየዘረፉ ሊሆኑ ይችላሉ፣፣ እሱ አይደለም ችግሩ፣፣ግን ካንድነት “አንግል”እምታየዉ ከሆነ፣ የኢትዮጵያ አንድነት-እሚቆረቁርህ ከሆነ ተዳክሟል የምትለዉ አንድነት እንዲጠናከር እምትፈልግ ከሆነ፣ ግን ሁሌ መርሳት የሌለብህ፣ እምትሰራዉ ነገር እና የምትናፈገረዉ ነገር አንድነትን ያጠነክራል ወይስ እያላላ ነዉ?እሚለዉ ላይ ትኩረት መደረግ ያለበት ይመስለናል፣፣ አሁን ዶ/ር አሰፋ ምን እያለ ነዉ “ጎበዝ!ትግሬ ያልሆንከዉ እየተዘረፍክ ነዉ በትግሬዎች! አድልዎ እየተፈጸመብህ ነዉ!” እያለ ነዉ፣፣ እና ይሄ ምን፡መጣል መሰለህ “እሱ ያለዉ ግሩፕ ሳይኮሎጂ “Group psychology” ያለዉ ተገልብጦ “ትግሬ ባልሆነዉ ላይ ሊሰራ ይችላል” ምን ማለት ነዉ? By the way Group Psychology” ያለዉ እቀበለዋለሁ፣፣ ግለሰዎች በደርጀት ማሰብ ወይም በቡድን ማሰብ በግል ማሰብ ሲችሉ ለደርጅት surrender እንደሚችሉ ይገባኛል፣፣አሁን ደ/ር አሰፋ እያደረገዉ ያለዉ ግን ያኛዉ ሪቨርስ ለማድረግ እየታገለ ነዉ፣፣ ለምሳሌ ምን እያለ ነዉ “ስማ አማራ እየተዘረፍክ ነዉ! ስለዚህ አንተም “ኢሞሽናል ታደርገዉ እና “አማራዉ ምንድነዉ እሚለዉ “እነዚህ ትግሬዎች አድቫንተጅ እየመቱብኝ ነዉ- ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ አለብህ እማን ላይ? “ትግሬዩ ላይ”፣፣ ስለዚህ አንድንት የሚያጠናክር አይደለህም እየሰራኸዉ አለኸዉ ዶ/ር፣፣ አንድ ጎሳ በሌላ ኮሳ የሚያጨቃችቅ ፣ እሚጨምር ነገር እየተናገርክ ነዉ፣፣” ነፃነት ራዲዮ አዘጋጅ፣- አቶ ሙሉጌታ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል፣-አንዴ ላቋርጠዎት እና እኔ እነደገባኝ እና እርስዎ እንደሚሉት ባጭሩ አርስዎ “አሁን ያለዉ ስርዓት አድሎዋዊ የሆነ ነገረ (አስተዳደር)አይፈጽምም,…“ይፈጽማል ብለዉ ለመናገር ያልደፈሩበት ምክንያት (ዳርዳሩን እየሄዱበት ያሉት ምክንያት) ምንድነዉ? አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣- ይሄዉልህ፣-“አድሎአዊ የሆነ ነገር አይፈጽምም አላልኩም፣-ግበቶሃል? አድሎአዊ ነገር ይፈጽማል ስትል ግን፣ “በጎሳ ማየት አልፈልግም!” ነፃነት ራዲዮ፣- አሁን እርስዎ በሚያዩት አተያይዎ…. አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣- አቶ ኢሳያስ አድልዎ ያልኩህ ለምሳሌ ዶ/ር አሰፋ የሚለዉ አሁን ስልጣን ላይ ያለዉ መንገስት አድልዎ ሲፈጽም ትግሬዉን ለመጥቀም ነዉ,፣፣ የሚለዉ፣፣ እኔ እሱን Reject(አልቀበለዉም፣ ወያነ ትግራይ ቡድን “ትግሬዉን ለመጥቀም “አድልዎ” አያደርግም ማለቱ ነዉ፣፣ ሙሉጌታ -)አደርጋለሁ! ይሄ መንግሥት አድልዎ ሲፈጽም የራሱን ፖሊሲ ተቀብለዉ የሚያራምዱትን ነዉ የሚጠቅመዉ፣፣ ማአት አማራ ተጠቃሚ አለ!ማአት ኦሮሞ ተጠቃሚ አለ!ይኼ መንግሥት ፍልስፍናዉን ደግፈህ ከእርሱ ጋር እስከተሰለፍ ድረስ መጠቀም ትችላለህ፣፣ትገሬ ሆነህ ፍልስፍናዉን ካልተቀበልክና ከእርሱ ጋር ካልተጠጋህ-ትግሬም ብትሆን ትመታለህ፣፣ ስለዚህ ይኼ መንግሰት ትግሬዎችን ነዉ የሚጠቅመዉ ብሎ በደፈና ፣ይሄ መንግስት አማሮችን ነዉ የሚጎዳ የሚለዉ እኔ አልቀበልም፣፣ ነፃነት ራዲዮ፣- ዶ/ር አሰፋ በርስዎ ዙርያ ያጠነጠኑ አሳቦች ተሰንዝረዋልና ባጭሩ ያጠቃልሉልኝ እና ወደ አቶ ሙሉጌታ የሚጤቁ በርካታ ጥያቄዎች አሉ እመለስባቸዋለሁ? ደ/ር አሰፋ ነጋሽ፣ እሺ!አንደኛ ምንድነዉ፣-አንድነትን እኮ የሚያላላዉ እኔ እምለዉ ነገር ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተጨባጭ እየሆነ ያለዉ ነገር ነዉ፣፣እ…ይሄ ከ35 ዓመት (የወያኔ መሪዎች)በፊት ሸዋ ተጠቀመ ይሉ ነበር ምንትስ ይባል ነበር …የሚባለዉ (አሁንም አሰፋ ትግራይ ተጠቀመ አማራዉ ደኸየ ይላል) ለሚለዉ (ሙሉጌታ ለሚለዉ)-ነገር ፣ሸዋ የሁሉም መኖርያ ነዉ፣፣ ሸዋ የሚባለዉ አሁን በቲ ፒ ኤል ኤፍ አጠራር “ሸዋ ስትል “ሰሜን ሸዋ ማለትህ ነዉ?) ያ ከሆነ- በወቅቱ I can tell you- ሰሜን ሸዋ ዉስጥ ከ2(ሁለት) ሃይስኩል በላይ አልነበረም፣፣ በትግራይ ደግሞ 5እሰከ 6ሃይስኩል እንደነበሩ (በሃይለስላሴ ጊዜ) መናገር እችላለሁ፣፣ እዛ መግባቱ አሁን አላስፈላጊ ቢሆንም (አሁንም ሆነ በዛ በድሮ ጊዜ ካወዳደርነዉ ሸዋ ተጠቀሞ ነበር የሚባለዉ የወያኔዎች ክርክር ከእዉነታዉ ጋር አያስኬድም- ቅንፎቹ ሁሉ የኔ ናቸዉ -ለማብራረት የተደረጉ ናቸዉ)፣፣ አቶ ሙሉጌታ እንዴት ሊገባዉ እንዳልቻለ አላቅም እንጂ “ይሄ ስርዓት እኮ ሳያፍር በጎሳ Identity/አማክሎ እኮ ነዉ የተመሰረተዉ፣ ፣ ይሄ እኮ ጥቂት ከተለያዩ ጥቂት ሰዎች በካድሬነት “ኦፒዲኦ” ዉስጥ አሉት ወይንም “ በ አማራ” የተደራጁ ብቻ ነዉ (አገልጋዮቹ ብቻ ናቸዉ) የሚጠቀሙት/ ወይንም አገኙት የሚባለዉ ጥቅም እሱ “በጣም ቁጥር ዉስጥ የማይገባ ነዉ”እኛ የምንለዉ ያለዉ ከዛ በላይ ያለፈ ነገር ነዉ ፣፣በክልል ደረጃ ነዉ ማየት ያለብን፣፣ እንዴ! ትግራይ ዉስጥ ይሄ ሁሉ ትምህረት ቤቶች የተሰሩት እና በስፋት ተዘርግተዉ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት እኮ ለመለስ ዜናዊ ጥቂት ቤተሰብ ለመጥቀም እኮ አይደለም! እንዴ! ይሄ ሁሉ መንገድ የተዘረጋዉ እኮ የመለስ ዜናዊን ጥቂት ቤተስቦች ለማጓጓዝ እኮ አይደለም፣፣ ይሄ ቀደም ብየ በዝርዝር ለማሳየት እንደሞከርኩት በንጽጽር ሌሎች ታዎች አናየዉም፣፣ አንድ ነገር ስናገር እኔ “አንድን ጎሳ” ወክየ አይደለም የምናገረዉ (ሙሉጌታ አረጋዊ “አማራዉን ወክለህ እየተናገርክ ነዉ ብሎ በፈጠራ ደ/ር አሰፋን ስለወነጀለዉ ነዉ)፣፣ እኔ በኢትዮጵያ ሲሰተም ነዉ የምናገረዉ (ከሬከርዱ እንደምታዳምጡት ደ/ር አሰፋ የአማራ ጎሳ እወክላለሁ ብሎም አያዉቅም አሁንም በዛዉ አላነሳም- ትዝበቱ ለናንተ ልተወዉ)፣፣ “ኢትጵያ በዚህ ዓየነት መንገድ ልትጠቀም አትችልም! የትግራይ ብሄረተኝነት ባለፉት 18 ዓመታት በፈጸማቸዉ ነገሮች የኢትዮጵያ አንድነት ከሚገባዉ በላይ አላልቷል፣፣በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ቤተሰቦች/ቤቶች በፈጠረዉ የጎሳ ግጭት ካካባቢያቸዉ ተፈናቅለዋል!በአስር ሺሕዎቹ የሚቆጠሩ ተገድለዋል!በባድሜ ጦርነት ተወስዶ በብዙ ሺሕ ሰዉ ሊያልቅ ምክንያት የሆነዉ እኮ “ሁለት የጎሳ ፖለቲከኞች”በፈጠሩት ሃላፊነት የጎደለዉ አለስፈላጊ ግጭት እኮ ነዉ! ያለቀዉ ሰዉ እኮ ከማሃል-አገር በዚህ ጎሰኛ ስርዓት ሲቀጠቀጥ የነበረዉ ሰለባ (ቪክቲም)የነበረዉ እኮ ነዉ ሄዶ ነዉ እዛ ጦርነት ዉስጥ ሊማገድ የቻለዉ! ይሄን የፈጠረዉ እኮ ይሄ ስርዓት ነዉ! እኔ ዲፕሎማቲክ ፖለቲካ አደለሁም እየተናገርኩ ያለሁት፣፣ ዲፕሎማቲክ ለመሆንም አልፈልግም፣ አይጠቅመንም!ያለዉ ነባራዊ ተጨባጩን ሁኔታ በሕዝቡ ላይ በአገሪቱ ላይ እየደረሰዉ ያለዉ ግፍ፣ አድልዎ እና አገሪቱ እየጎተታት ወዳለዉ አሰከፊ እና አስፈሪ ሁኔታ መናገር መግለጽ ካልቻልን “ቀስ በቀስ መጥፎ ስሜት እየፈጠረ ነዉ”!፣፣ ችግሩን በድፍረት መግለፅ እንደ “ጠላት”መቆጠር የለበትም፣ ፣… ስለዚህ “We have to face this reality”. ኢትዮጵያ ዉስጥ እየከፋፈለዉ ያለዉ ይህ ጎሰኛ ስርዓት ነዉ! አቶ ሙሉጌታ “For all I know” አንተ አሁን አቶ ሙሉጌታ አንተ አሁን የEthnic ፈederalism” እቃወማለሁ ትላለህ፣Ethnic-Federalismተቃወምኩ የምትል ከሆነ ይሄ የኤትኒክ ፌደራሊዝም ያመጣቸዉ “ዉጤቶች” (ሰበቦች/ጉዳቶች) መከፋፈል፣ ቅሬታ፣ ይሄን ሁሉ “አድሚት ማድረግ/መቀበል ያስፈልጋል”!ግን ወደ “Solution”ወደ መፍትሄዉ እንሂድ ትላለህ፣ ግን አንድ “መፍትሄ” ለማግኘት ችግሩ“ይሄ”ነዉ ሳንል እንዴት ብለን ነዉ “ወደ መፍትሄዉ ዘለን የምንሄደዉ?እንዴ አነጋገሩ ራሱ እኮ አለ-“ችግሩን መረዳት የችግሩን መፍትሄ 50%ግማሽ መፍትሄዉን ማግኘት እኮ ነዉ” ይባል የለ?!
አሁን አንተ የለም ያንን ነገር እንለፈዉ የሚል አመለካከት አለህ፣፣ ሌላዉ አቶ ሙሉጌአተ እዚህ ላይ ግልጽ ላደርግ የምፈልገዉ-ለምሳሌ አንተ እንደ ግለሰብ “የወያኔ አመራር ለሁለት ሲሰነጠቅ (የዛሬ 8 ዓመት አካባቢ) የገብሩን ቡድን ደጋፊ ሆነህ ነዉ ወጣኸዉ፣፣ይሄ-ግሩፕ(የነ ገብሩ አንጃ) የሚያራምደዉና የሚከተለዉ ፖሊሲ “Ethni Federalism” ነዉ….. ሙሉጌታ አራገዊ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽን ንግግር በማቋረጥ “እባክህ ደ/ር እማታዉቀዉን…. እንዴ!.... ነፃነት ራዲዮ አዘጋጅ፣- ጉዳዩን ወደ ሌላ ሙሉጌታ አረጋዊ “ምን ማለትህ ነዉ? እንትን አደረግከዉ እኮ! (ለ ዶክተር አሰፋ ነጋሽን ነዉ ምን ማለትህ ነዉ/ ያለዉ) ነፃነት ራዲዮ አዘጋጅ-፣- ይቅርታ! አንዴ! ዶክተር አሰፋ አስቀድመህ ጥሩ አድረገህ አስቀምጠኸዋል- ችግሩን መረዳት የመፍትሄዉ አንዱ ክፍል ነዉ፣፣ አሁን አቶ ሙሉጌታ እንደምትለዉ ወደ ችግሩ ከመነጋገር ይልቅ ወደ መፍተሄዉ እናተኩር ነዉ የሚሉት፣- (ችግሩ “ለዘመናት” ተነጋግረንበታል ነዉ የሚለዉ ሙሉጌታ፣- ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ለመጥቀም ሲል ከሌላዉ ሕዝብ ለይቶ በልዩ ዓይን አያየዉም ነዉ የሚለዉ አቋሙ)- አስኪ አቶ ሙሉጌታ አርስዎ መፍትሄ የሚሉዋቸዉ አንድ ሁለት ብለዉ እንዲለዩልን አንድ ሁለት ብየ ልጠይቀዎ፣፣ የጎሳ ፌደራሊዝም ‘ችግር እንደፈጠረ ገልጸዉልናል፣ ያ ችግር አለ፣- ይሄንን በኢትዮጵያ የተመሰረተዉ የጎሳ ስርዓት ለማስወገድ “ማስገድ” ከሚለዉ ዉጪ ምን ‘መፍትሄ አለ? በዚህ መፍተሄ ይስማማሉ ወይ አርስዎ? ሙሉጌታ አረጋዊ.- ማስወገድ እሚለዉ ቃል እፈራዋለሁ፣፣ ነጻነት ለኢትዮጵያ፣- ለምን?ያብራሯት፣ ሙሉጌታ አረጋዊ፣-ማስወገድ ማለት፣ እንዴት አድርገህ ነዉ የምታስወግደዉ? ነፃነት ራዲዮ.- እሱ ላይ እንነጋገራለን ፣ በግቡ ብቻ እንስማማ፣፣ ሙሉጌታ አረጋዊ፣-- የጎሳ ፌደራሊዝም ችግር ይፈጥራል፣፣ ነፃነት ራዲዮ- ፣ ፈጥሯል ብለን እናምናለን መጀመሪያ? ሙሉጌታ አረጋዊ፣- አዎ ፈጥሯል፣፣ ለወደፊቱም የባሰ ችግር ሊገጥም ይችላል የሚል ስጋት አለኝ፣፣ ነፃነት ራዲዮ- እንደ ስርዓት መወገድ አለበት? ሙሉጌታ አረጋዊ፣- እንደስርዓት መቀየር አለበት፣፣ “ማስገድ” ስትል እኔ ፖሎሲዉን ነዉ እየተቸሁ ያለሁ፣፣ ማስገድ ስትል “እኔ ጦርነት እየጋበዝኩ አይደለሁም ያለሁት”፣፣ ፖሊሲዉ ትክክለኛ አይደለም፣፣ ይሄ ፖሊሲ መቀየር አለበት፣፣ ላገር በሚጠቅም መረጋጋት የሚያመጣ፣ አስተማማኝ የሆነ ፖሊሲ መነደፍ አለበት፣፣ አዲስ አፕሮች መኖር አለበት፣፣ ይሄ ፖለቲካ አያዋጣም ባይ ነኝ፣፣መወገድ አለበት ስትል፣ -ለምሳሌ አሁን ስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ነዉ አንግዲይ ይሄ “ኤትኒክ ፌደራሊዝም”-ስራ ላይ ያዋለዉ፣፣ ስለዚህ “ኤትኒክ ፌደራሊዝም” “መወገድ” አለበት ስትል “ይሄ መንግሥት መጥፋት አለበት”የምትል ከሆነ “እኔ እዛ ዉስጥ መግባት አልፈልግም”፣፣ የመጠፋፋት ሳይኮሎጂ እንዲኖረኝ አልፈልግም፣፣ አሱ አይደለም ዲቤት ለማድገር የመጣሁት፣፣
ነፃነት ራዲዮ (አቶ ዓለም)፣-……ከ አንዳን አድማጮቻችን አንዳንድ አስተያየቶች ሰንዝረዋል,፣ ለምሳሌ እርስዎ ያለፈዉ ምንም አያስፈልግም ስለወደፊቱ እንነጋገር እሚባለዉ ላይ ስሕተት ያለዉ በአቶ ሙሉጌታ በኩል “ያለፈዉ ቢቆም ኖሮ እኮ ነዉ” የሚካሄደዉ ፖሊሲ ቢቆም ኖሮ አዎ ስለወደፊቱ እንነጋገር ግን ይሄን ፖሊሲ የሚያካሂደዉ ቡድን “የትግራዩ” ቡድን፣ ይሄንኑ እያካሄደ ነዉ (ቀደም ተብሎ በስፋት በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ተዘረዘሩት አድለዎአዊ እና አገርን እና አንድነትን የሚያላላ አስተዳደር) እንዴት አደርገን ነዉ የምናቆመዉ? ሙሉጌታ አረጋዊ፣-Thank you!እንዴት አድረገን አንደምናቆመዉ ለመግለጽ እችላለሁ፣-ማለትም ‘እሞክራለሁ’፣፣መጀመሪያ ዶ/ር አሰፋ እንዲያዉቅልኝ የምፈልገዉ “እኔ የገብሩ አስራት ደጋፊ ሆኜ አላዉቅም!-የማንም ድረጅት አባል ሆኜ አላዉቅም!-የማንም ቡድን አባል-ሆኜ አላቅም!ደጋፊም ተቃዋሚም ሆኜ አላቅም!”ሁሌ እኔ የምቃወመዉ ፖሊሲዩን ነዉ፣፣በጅምላ ይሄኛዉ ትክክል ነዉ ፣ይሄኛዉ ስህትት ነዉ ብየ አላቅም፣፣ እኔ ከተቃዋሚዉ የምቀበለዉ አለ፣ ከመንግሥትም,-የምቀበለዉ አለ፣፣ እኔ እሚመስለኝን የኔ የግል ኦፒንየን ነዉ እያቀረብኩ አለሁት፣፣ የማንም ሆኜ አላቅም ከማንም ተጠግቼ አላቅም፣፣…..” ማጠቃለያ አሁን -ወደ ኢትዮጵያ ሰማይ ወደ እኔዉ የግል አስተያዬን በተነጋገሩበት ጣልቃ ገብቼ ልሰንዝር፣፣አቶ ሙሉጌታ የሰነዘራቸዉ አስተያየቶች ሰፊ ጽሁፍ የሚጋብዝ እና በሁኔታዉ ካሁን በፊት ብዙ ያልኩበት ስለሆነ አሱን ለናንተዉ ግምገማ ልተዉና አቶ ሙሉጌታ ያቀረበዉ የመጨረሻዉ፣ “የማንም ደጋፊ ወይንም የነ ገብሩ ደጋፊ ሆኜ አላቅም የሚለዉ መልሱን፣-ካሁን በፊት “አገሪቷን በጎሳ ሸንሽነዉ” አንድነቷን በማዳከም ጣሊያን በወረራ ጊዜ የታየዉ ጸረ አማራ ዘመቻ፣ ብዙ የጎሳ ግጭቶችም በፖሊሲዉ ምክንያት እንዲጎዱ ያደረጉት እቃወመዋለሁ እያለን ያለዉ የፖሊሲዉን ፈጣሪ ችንቅላቶች/ማለትም እነ ግብሩ ከወያኔዉ ከመለስ ቡድን ለሁለት ሲለዩ (አሁንም ተለይተዉ ያዉ ፖሊሲ ለማራመድ በዓረና/ወያነ ፕሮግራም ያስተዋወቁ) አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ የማንም ቡድን ይሁን የነ ገብሩ ቡድን ደጋፊ አልነበርኩም ሲለን -አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የወያኔ መሰነጣጠቅ እሰየዉ ሲል’-እነ ሙሉጌታ-አረጋዊ “ኤትኒክ ፌደራሊዝም ዕድሜዉ እንዲረዝም - “መሰነጣጠቃቸዉ ሕጋዊነት የለዉም ፣ወደ ቦታቸዉ ይመለሱ፣ ስለ ደህንነታቸዉ እጅግ እጅግ ሰግተናል.እነኚህ አገር ወዳዶች፣ ጀግኖች ናቸዉ….” ሲል በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ጊዜያዊ ሊቀመንበር በመሆን ‘-ከሰባት ዓመት በፊት” በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ትልቁ ዜና ሆኖ ሲተላለፍ የነበረዉ እስኪ እናዳምጥ እና ወንደሜ አቶ ሙሉጌታ እኔ የለሁበትም፣ አኔ አይደለሁም የሚል ከሆነ መልሱን እንጠብቅ፣፣ ሙሉጌታ አረጋዊ ማለት እኔ አይደለሁም ካለም ይቅርታ እነጠይቃለን፣፣ ልትቀስ ተከታተሉት እነሆ.-“
“ከሰባት ዓመት በፊት የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃየ የሚቀጠለዉ ዘገባ አቅርባ ነበር_“ከዚህ ከዋሽንግተን ከቨርጂኒያ ከሜሪላንድ ከኒዉዮርክ ከቦስቶን ከፍላደልፊያና ከአትላንታ የተወከሉ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ስለሁኔታዉ ከተወያዩ በሗላ አንድ “ኮሚቴ”መመስረታቸዉን፣የኮሚቴዉ አባል የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ገልጿል ። ኮሚቴዉ የተመሰረተዉም የሕዝቡን ድንጋጤና ስሜት ለኢትዮያ መንግሥትና ለሕዝባዊ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆዩ ድርጅቶች ለትግራዩና ላጠቃላዩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስተላለፍ ነዉ ሲሉ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ አስተላልፈዋል።አስራ አንዶቹ አንጋፋ የህወሓት አባላት የተወገዱት በሕገወጥ መንገድ ነዉ ይላሉ። ይህንን መሰረት በማድረግም የሚከተሉትን ዉሳኔዎች በማብራራት አቶ ሙሉጌታ እንዲህ ይላሉ፦“በመጀመርያ እነዚህ አስራሁለት የማአከላዊ ኮሚቴ አባላት በተለይም በቅርቡ ማለትም ከሻዕብያ ጋር የተደረገዉ ጦርነት…ጀግንነታቸዉ ያስመሰከሩ፣ አገር ወዳድነታቸዉ…በግልጽ ያሳዩ ከመሆናቸዉም በላይ፣ አሁን ታግደዉ ,ከስራ ተባርረዋል። ስለዚህ ሕይወታቸዉ አደጋ ላይ የወደቀ ይመስላል። ችግር ብያጋጥማቸዉ አንድ ነገር ይፈጠራል ብለንም እናምናለን። ችግር ቢገጥማቸዉ ያባረራቸዉ መንግሥት ተጠያቂ እንደሚሆንከዚያ ቀጥሎ ያስተላለፍነዉ ዉሳኔ ምንድነዉ፦
እነዚህ የተባረሩ አስራሁለቱ ሰዎች ያለ ቅድመ ሁኔታዎች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ፦ ሦስተኛ-በድርጅቱ ሕግና በሌሎችም ተጓዳኝ ሕጎች መሰረት የህወሓት ቁጥጥር ኮሚቴ ባሳለፈዉ መሰረት አስቸኳይ ጉባኤ ተጠርቶ ጉዳያቸዉ በጉባኤ እንዲታይ፡- አራተኛ፦ጉባኤ አስኪጠራ ድረስ ነጻ ሚድያ እንዲፈቀድላቸዉ፡ አምስተኛ፦አሁን በስልጣን ላይ-ያለዉ ክፍል በነዚህ ሰዎች ላይ የሚያካሂደዉ ፕሮፖጋንዳ ስም-በማጥፋት፣ በራሳቸወና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ቀጣይ የማባረር እርምጃ ..ባስቸኳይ እንዲያቆም፡ ስድስተኛዉ ዉሳኔ-ደግሞ፦ ከኤርትራ ጋር የሚደረገዉ ድርድር በታገዱት በሰላማዊ የቲ-ፒ-ኤል-ኤፍ አባላች ተሳታፊነት መካሄድ ሲገባ አሁን ግን አስራ-ስምነት ብቻ ስለቀሩ ባስራ ስምንቱ ብቻ 2/3ኛ ድምፅ ሳይኖራቸዉ ማለት ነዉ፡ በነሱ ብቻ የሚደረግ ድርድር ተቀባይነት ሊኖረዉ ስለማይችል ድርድሩ ባስቸኳይ እንዲያቆም ነዉ።””(አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ)ካሉ በሗላ ትላለች አዳነች ፈስሃየ “የትግራይ ክፍል ሀገር ተወላጆችን ወክለዉ የተናገሩተር አቶ ሙሉጌታ በመቀጠል “የህወሓት ካድሬዎችና በተለይም የመከላከያ ሠራዊቱ አገሪቱን ከዚህ ቀዉስ በሰላም እንድትወጣ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸዉ ሳያሳስቡ አላለፉም። ሌሎቹም የኢሕአዴግ አባሎች ያስታራቂነት ሚና እንዲጫወቱ የትግራይ ተወላጆች መጠየቃቸዉ ገልፀዋል።””
አሜሪካ የኢንዲያና ክፍለሃገር አቶ ሃይለማርያም አበበ ደግሞ ከ70 አባላት የሆኑ ኢትዮጵያዊያን አባላት ወክለዉ ተናግረዋል። አቶ ሃይለማርያም አበበ Ethiopian Commentator”የተባለ መጽሄት አዘጋጅ ሲሆኑ በሙያ “Micro Biologist” ናቸዉ። “በዚህ መጽሄት ዙርያ የተሰባሰቡት ሰዎች ባለሞያዎች ሲሆኑ ቡዱኑ የፖለቲካ ስብስብ አይደለም:ያለዉን ሁኔታ ኢንፎርመሺን ለሕዝቡ ለማሳወቅ ሲባል ብቻ የተደራጀ ነዉ”ሲሉ አቶ ሃይለማርያም አበበ አስምረዉበታል። በዚህ ዙርያ በህወሓት የተፈጠረዉ ችግር የቡዱኑ ስሜት አንጸባርቀዋል።
“ባሁኑ ጌዜ በኢትዮጵያ የተፈጠረዉ ችግር የኛ ሜምበሮች ተሰባስበን አቋም ወስደናል። ይህም ምንድነዉ የነዚህ አስራሁለቱ በተመለከተ በእዉነቱ የእነ አቶ መለስ ዜናዊ ቡድን የህወሓትን ሕግ ጥሰዉ እንዳገድዋቸዉ ሙሉ በሙሉ እናምናለን። እንዲሁም እዚህ ያሉት የትግራይ ተወላጆች በሙሉ (በእነ አቶ መለስ የተወሰደዉ እርምጃ)መቶ በመቶ ከሕግ ዉጭ መሆኑን ያምናል። እርምጃዉ ከሕግ ዉጭ መሆኑን ያምናል። እኛም እናምናለን፡በዘህ ትልቅ፣ትልቅ ቁጣና ንዴት ተሰምቷቸዋል።ስለዚህ የተባረሩት ሰዎች ወደ ስራቸዉ ባስቸኳይ እንዲመለሱ በብዙ ከተሞች የሚኖሩ ትግራይ ተወላጆች ለአቶ መለስ ዜናዊ የቅሬታ ደብዳቤ አስተላልፈዋል፡ ለዚህ አስካሁን ድረስ የተሰጠ ምላሽ የለም ። በጣም በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነዉ።””
አዳነች ፍስሃየ ትቀጥልና “አቶ ሃይለማርያም አበበ አያይዘዉም “በህወሓት ሕግ መሰረት የትግራይ ምክር ቤት መሰብሰብ የሚችለዉ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገብሩ አስራት ናቸዉ::አሁን ግን የትግራይ ምክርቤት ባቶ መለስ ተጽዕኖ ራሱ ስበሰባ ጠርቶ ፕረዚዳንቱን ማዉረዱ ራሱ ተገቢ አይደለም። ካሉ በሗላ “ዲሞክረሲን በመርገጥ ዲሞክራሲን ማምጣት አይቻልም”ብለዋል።..በመጨረሻም አቶ ሃይለማርያም “ዉጭ ያለን ኢትዮጵያዊያን አገራችን አደጋ ላይ ወድቃለች የሚል እምነት ስላለን ሕዝቡ ያልተበረዘና ተገቢ የሆነ ኢንፎርመሺን ለማግኘት የራዲዮ ስርጭት ለመክፈት እየተዘጋጀን ነዉ ብለዋል:”:ስትል የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃየ የህወሓትን-መሰንጠቅ አስመልክቶ ከመቀሌ እና ከዉጭ የሚኖሩ የትግራይ ክፍልሃገር ተወላጆች የተጠናቀረዉን ዘገባ እላይ የተዘገበዉ ዓይነት ለነገብሩ የድጋፍና የደህንነት መቆርቆር ስሜት ለዛሬዉ የዓረና የፍቅር እርሾ መነሻዉ ያኔ ያስተላለፏቸዉ-ዉሳኔዎች እንደነበሩ ልብ ልንለዉ ይገባል። ድብቅም ይሁን ደብቅ ያልሆኑ የጎሰኝነቶች እንዋጋ!
ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Thursday, June 11, 2009

ስብሓት ነጋ “የወያኔዉ ማሞ ቂሉ!

ስብሓት ነጋ “የወያኔዉ ማሞ ቂሉ! ጌታቸዉ ረዳ (www.ethiopiansemay.blogspot.com) ‘የራስን ዕድል በራስ መወሰን’ ምን ማለት ነዉ? ጎሳስ ማለትስ ምን ማለት ነዉ?
ስብሓት ነጋ ለማያዉቀዉ በእዉነቱ አዋቂ እና የዋህ ገራገር ሰዉ ይመስለዋል። በጣም “ጎጠኛ” ፤ “ቂመኛ” እና “ማሃይም” ቢኖር ስብሓት ነዉ (አስከ ዚህ ድረስ ባሕሪዉ ከጥንት ጀምሮ አዉቀዋለሁ)። ስለ ጭካኔዉ አብረዉት የነበሩት እነ መኮንን ዘለለዉ- ግርማይ ባህሊ እና ሌሎቹ በሚገባ ያዉቁታልና ለነሱ ልተወዉ። በማሌሊት የጎሳዎች አተናተን እና፡ “ራስን በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል” ለሚለዉ ዕዉቀቱ ግን ስብሃት ነጋ “አህያን ያህል ከባዱ እንስሳ እራሱ ላይ ተሸክሞ ገበያ ለገበያ ከሚዞሮዉ “ከማሞ ቂሉ” አይለይም። በዚህ ዓምድ ልተነትን ወደ አነሳሳኝ መነሻ-ልግባ።ስብሓት ሰሞኑ- በየፓልቶኩ. በየቪኦኤዉ ስለ “ጎሳ” “ስለ ብሔር/ብሔረሰቦች/ሕዝቦች….” ራስ ዕድል በራስ የመወስን እስከመገንጠል መብት”-በወያኔ ሕገ መንግሥት እንደተከበረ በጮርቃ ላሃጩ ሲለፋደድ አሽከሮቹ (ካድሬዎቹ)“አስደናቂዉ ዕዉቀቱን”አዳምጡልን ብለዉ በየሰሌዳዉ የለጠፉትን ዲስኩሩን ሳዳምጥ፤ በተለይም የወያኔ ፓል-ቶክ አሽከሮች ስለዚህ ጉዳይ ሲያስተምራቸዉ ሲያሞግሱት፤ አባባ ሲበትኑለት ሳዳምጥ “ፎከታሙ ሕሊናቸዉ”-እጅግ ይገርማል። ስብሓት እና ድርጅቱ ለኢትዮጵያ አመጣንላት ብሎ የሚለፋደደዉ ‘ራስን በራስ የመወሰን እስከመገንጠል” ፖለቲካ ምን ያህል “የቂሎች ፖለቲካ” እንደሆነ በጥልቅ የምሁራን አንደበት የተነገሩትና የተፃፉት ማንበብ ይኖርብናል። በዚህ ጉዳይ ብዙ የኢትዮጵያ ተመራማሪዎች ብዙ ያሉበት ቢሆንም - በቀላሉ ሊገባ በሚችል አቀራረብ ለመጪዉ ትዉልድ የተዉልንን ከሕሊናየ የማይረሳ የክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “የክህደት ቁልቁለት”መጽሃፋቸዉ -በዚህ “ራስን በራስ የመወሰን አስከ መገንጠል” የወያኔ ፋሺስቶች እና ኮሚኒስቶች ፖለቲካ ርዕየተ ዓለም ምንኛ “የቀልድ ፖለቲካ” እነደሆነ በዚህ ጉዳይ ምስጋና ይግባቸዉና በሚገባ አሳይተዉናል። ይህን “አስከ መገንጠል”የሚለዉ “የፋሽስቶች እና የኮሚኒሰቶች ፖለቲካ” ፕሮፌሰር መስፍን ካሁን በፊት በቃለ መጠይቅ እንደገለፁት እንዲህ ያለ ፖለቲካ “የልጆች- ጨዋታ” መሆኑን አብራርተዋል። ለማንኛዉም የስብሓት የወያኔ “ራስን በራስ የመወሰን አስከ መገንጠል መብት”ፖለቲካ ትንተና ፕሮፌሰር መስፍን እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ። ‘የራስን ዕድል በራስ መወሰን’ ምን ማለት ነዉ? “የወያኔ ሕገ መንግሰሥት አንቀጽ 39 (1) ‘ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሔር፤ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለዉ መብቱ በማንኛዉም መልኩ ያለገደብ የተጠበቀ ነዉ፣፣ ይላል። ለራሳቸዉ ግልጽ ያልሆነላቸዉን ሀሳብ በተገማመደ ጨቅላ አስተሳሰብ ለሌላዉ ሰዉ ለማስተላለፍ በመሞከር አዋቂ መስሎ ለመታየት የተደረገ ሙከራ ነዉ። ድንቁርናን ወደ አዋቂነት፣ዉሸትን ወደ እዉነት ለመለወጥ ባይቻልም ግራ ገብቶአቸዉ ግራ የሚያጋቡ ሰዎች የባሕርይ ጥረት ነዉ። በመጀመሪያ ደረጃ በሕገ መንግሥቱ ዉስጥ የተደረደሩት ቃላት-ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ በትከክል ምን ማለት እንደሆኑና በመሀከላቸዉስ ያለዉ ልዩነት ምን እንደሆነ ቢጠየቁ አያዉቁትም። ከነሱ የባሰዉን ሰዉ ለማደናበር የሚጠቀምባቸዉ ቃላት ናቸዉ.። ሌኒንም ሆነ ስታሊን የጻፉት በትክክል አልገባቸዉም። በቀላሉ ጎሳ ብለዉ እንዳያልፉት ቃሉ ለሁሉም ሰዉ ግልጽ ስለሚመስል ለማደናገር አያመችም። የሚደንቀዉ ነገር አዲስ ቋንቋ እፈጠሩ ሰዎችን ማደናገር የአዲስ ኮሚዩኒሰት ካድሬዎች (አሽከሮች) ጠባይ ነዉ። ሌኒንም ማኦም እንደዚህ ያሉ ካድሬዎች ተቸግረዉ ስለነበረ በሰፊዉ ጽፈዋል። (በወያኔዎች የጎሳ ትንታኔ-) በጎሳዎች-መሃከል አንድ ዓይነት ደረጃ ለማዉጣትም ፍላጎት ያለ ይመስላል። ብሔር ትልቅ ጎሳ. ብሔረሰብ አነስ ያለ ጎሳ፤ ሕዝብ ደግሞ ምኑም ያልታወቀና ዝቅተኛ ጎሳ ብለዉ እንዳያቀርቡት የሚደረገዉ ልዩነት ብዙዉን የሚያስቀይም ሊሆንባቸዉ ነዉ፤ስለዚህም ማንም ሳይለይ ቃላቱን ደርድረዉ የፈለገህን አድርግ ማለታቸዉ ነዉ። ሌላዉ ማደናገርያ ደግሞ “የኢትዮጵያ ህዝቦች”የሚባለዉ ነዉ። በዚህ አባባል ደረጃ የተሰጠዉ ‘ሕዝቦች” ቃል እንደ (ደቡብ ሕዝቦች) ወደ ከፍተኛ ደረጃ ይወጣና ሰፍቶና አድጎ ለአገር ደረጃ ይበቃል። ወይም ሁሉም ወደ ዝቅተኛ ደረጃ ይወርድና “የኢትዮጵያ ሕዝቦች’-ይባላል።ስለዚህም “የኢትዮጵያ-ሕዝቦች” ሲባል“መዉጣታችን ይሁን መዉረዳችን አይታወቅም። ገዢዎቻችን የሚነግሩትን ያዉቃሉ ወይ? የሚያሰኘዉ ለዚህ ነዉ። የማደናገሪያዉም ቃላቱን አልፈን ወደ ሀሳቡ ስንገባ፤ሀሳቡም የሞተና መነሻ የሌለዉ ሆኖ እናገኘዋለን። የራስን ዕድል በራስ የመወሰን”የሚባለዉ ብዙ ተብሏል። ይህ ሃሳብ ሁለት መነሻ መሰረቶች አሉት አንደኛዉ በ1ኛወ የዓለም ጦርነት የአሜሪካ ፕረዚዳንት የነበሩት “ዉድሮዉ ዊልሰን” ያነሱትና በሗላም የተባበሩት መንግስታት ተቀብሎ በቅኝ ግዛት ስር ላሉ ሕዝቦች ያዋለዉ ሀሳብ ነዉ። 2ኛዉ ደግሞ- የኮሚኒስቶች የትግል ስልት ነዉ። ሃሳቡ እኛ አገር የገባዉ ፊደል የቆጠረዉ ሁሉ፤ሳር ቅጠሉ ሳይቀር ኮሚኒስት በነበረበት ጊዜ ስለሆነ ሃሳቡ የኮሚኒስቱ እንደሆነ ኣያጠራጥርም። ነገር ግን የዚህ ሃሳብ አቀንቃኞች የኮሚኒሰት የራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚባለዉ ሀሳብ “ስልት”እንጂ “ቁምነገር” እንዳለሆነ አልገባቸዉም። በደርግ ዘመን የነበሩት በመከራ ተማሩ፤ ያልተማሩት መጡና ሕግ አደረጉት። (……ይሉና ሰፊ ሀተታ ካብራሩ በሗላ- እንዲህ ይላሉ-- የራስን በራስ የመወሰን ኢትዮያ ወይንም ነፃ አገር አይመለከትም (ማለት በተባቡሩት መንግስታት ዓላማ)። ለቅኝ ግዛቶች ተብሎ የወጣ መመሪያ ነዉ። ስለዚህ ያንን ሃሳብ ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት አንድ የኢትዮጵያ ክፍል ቅኝ ግዛት ነዉ እንዲባል በግድ አስፈላጊ ይሆናል። ሻዕቢያም ጀብሃም ያደረጉት ይህንን ነዉ። የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ)የሚለዉም ይህንኑ ነዉ። ለጊዜዉ እዚህ የታሪክ ክርክር ዉስጥ አንገባም። ሆኖም ጉዳዩ ከሁት በአንድ መንገድ መፈታት አለበት። ወይ በፖለቲካ (ማለትም በሕዝብ ዉሳኔ)አለዚያ በጦርነት። የኤርትራ ለጊዜዉ አልቆለታል፤ እንዲያዉም የማግደርደሪያዉን በር የዘጋዉ ይመስላል። የኦነግ ጥያቄ ገና በ እንጥልጥል ያለ ነዉ። ሁለተኛዉ መነሻ የኮሚኒስት ስልት መሆኑን ገልጫለሁ። ይህንን በሚገባ ለመረዳት የፈለገ ሰዉ ማርክስ ወይም ኤንግልስ ስለ ጀርመን የጻፉትን በ አንድ በኩል፤ ስለ እንግሊዝ አገር የጻፉትን በሌላ በኩል እያነፃፀራችሁ አንብቡት። ከዚያም በላይ እነዚህ ሰዎች “ስልት”እንጂ ቋሚ የሆነና ሁልጊዜም ለሁሉም አገር የሚሰራ አለመሆኑን በማያሻማ ቋንቋ ገልጸዉታል። 3ኛ--- የዚህን ሀሳብ መሰረት ፈጽሞ የሚንድ የሊቃዉንት ትንተና አለ። የራስን ዕድል በራስ መወሰን ሲባል መነሻዉና መድረሻዉ ምንድነዉ? ማነዉ “ራስ”? ብለዉ መጠየቅ ይጀምራልሉ። (1)ራስ ማለት አንድ ሰዉ ነዉ? ያለምንም ጥርጥር ስለ ራሱ መናገር የሕግም ሆነ የተፈጥሮ ችሎታ ያለዉ ግለሰቡ ነዉ።ነገር ግን ዕድሜዉ ትንሽ ሆኖ የሌላ ሰዉ ጥገኛ ካልሆነ ፤ በሕጋዊ ስርዓት በወንጀል ተከስሶ የተፈረደበትና በወህኒ ቤት ያለ -እነዚህ ሁሉ ወንድም ሆነ ሴት ራስ ለሚለዉ ብቁ አይደሉም፡ (2) ራስ የሚለዉ ለአንድ ቤተስብም ይሰራል? የቤተሰብ “ራስ” ነኝ ብሎ የሚቀርበዉ ማን ነዉ? ሚስት ወይስ ባል? ለልጆችስ የሚወስንላቸዉ ማነዉ? በባልና ሚሰት መሃከል የራስን ዕድል በረስ “መወሰን”ማለት “መፋታት” ማለት ነዉ። ለዚህም በመብት ደረጃ ባልም ሚስትም እያንዳንዳቸዉ “ራስ “ በመሆን የመፋታት ዉሳኔን መወሰን ይችላሉ፤ አብረዉ ካሉ ሃብታም ከነበሩ ሲፋቱ የዕኩልነት ስርዓት ካለ ዕኩል ስለሚካፈሉ (ሴቶች በበታችነት በሚኖሩበት ማሕበረሰብ ባዶ እጃቸዉን ይወጣሉ) ሁሉም ይደኸያሉ። ሁለቱም ደሃዎች ከሆኑ ሁለቱም የባሰ ደሃ ይሆናሉ። (3)- “ራስ” ለአንድ ቀበሌ ይሰራል ወይ? የአንድ ቀበሌ ነዋሪዎች ተሰብስበዉ፤ እያንዳንዱ ነዋሪ በነፃነት አስተያየቱንና ምርጫዉ ገልፆ ተስማምተዉ ለመገንጠል ቢፈልጉ ምንም የሚከለክላቸዉ ነገር አይኖርም። ከዚህ በላይ በጥቂቱ ለማሳየት እንደተሞከረዉ የራስ ዕድል በራስ መወሰን እንደቁም ነገር ከተወሰደ-ከ እያንዳንዱ ግለሰብ ጀምሮ እያንዳንዱ ቀበሌ-፤ወረዳ-፤_ሊጠይቅ ይችላል።ከዚህ ብቻ የራስን ዕደል በራስ የመወሰኑ ምክንያት በቋንቋ ብቻ ነዉ ከተባለ ይኼዉ ብቻ “ቁም ነገር”የተባለዉን ያፈርሰዋል። የራስን በራስ የመወሰን የምትችለዉ “በቋንቋ” ብቻ ነዉ እንጂ “በሃይማኖት ወይም በሌላ” መነሻ አድርገህ መገንጠል አትችልም ከተባለ ዕድል የተባለዉ መብት “በቅድሚያ”ተወስኗል። “ራስ”ለራሱ የሚወስነዉ “ጌቶች በፈቀዱለት” መንገድ ነዉ እንጂ ‘ራስ” እንደፈለገ አይደለም ማለት ነዉ። አንድ ወገን የሃይማኖት ልዩነትን መሰረት አድርጎ መገንጠል ቢሻ እና ቢገነጠል፤ በሗላ ደግሞ በቋንቋ ልዩነት መሰረት አንዱ ክፍል ለመለየት ቢፈልግ ቀጥሎ በዘር፤ ቀጥሎ ወደ ቤተሰብ፤ቀጥሎ ወደ ግለሰብ ደረጃ ለመዉረድ ምንም የሚያግደዉ ነገር የለም። የራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚለዉን ሃሳብ እንደ ቁም ነገር ከተቀበልነዉ ለመገንጠል ሚፈልገዉን ሁሉ ማስተናገድ አለብን። በሃይማኖትም ሆነ በቋንቋ ወይም በዘር ሆነ በጎሳ ወይም በቀየ- ሆነ በታሪክ፤ ወይም በፐለቲካ አመለካከት ልዩነት ያለዉ ሁሉ መገንጠልን ከመረጠ መገንጠል መቻል አለበት። ቁጥሩ አነሰ ብሎ መገንጠልን መከልከል አይቻልም። “ቁም ነገር”-ከሆነ ለግለሰብም ቢሆን መስራት አለበት። ይህ ካልሆነ እንደ ወያኔ የጎሳ ክልል በምንም ዓይነት ቁም ነገር ላይ ሳይሆይን በዘፈቀደ የሚሰራ ይሆናል። የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ ክልል ይለያያል ከሚል ቁም ነገር ከተነሳን እያንዳንዱ ጎሳ፤ ትልቅም ይሁን ትንሽ፤ የራሱ ክልል ሊኖሮዉ ይገባል። ጎሳ የሰዉ ማንነት መግለጫ ነዉ ከተባለ፤ ክልል የጎሳ መግለጫ ነዉ ከተባለ፤ ጎሳ ከጎሳ የሚለየዉ በቁጥር አይደለም። (አማራ?)፤ ኦሮሞ፤ሶማሌ፤ትግሬ፤ ጉራጌ፤ ሲዳሞ፤ ወላይታ ከምባታ፤ ሀድያ፤ ጊዴዎ፤አፋር፤አገዉ፤ጋሞ፤ ጎፋ፤ ሻኪሶ፤ኩሎ፤ ኮንታ ሌሎቹም ሁሉ የክልል ባለቤቶች መሆን አለባቸዉ። ይህ ካልሆነ “ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” እኩል ናቸዉ እየተባለ የሚለፈፈዉ ባዶ ማታለያ ይሆናል። ከሁሉም በላይ የሚያስደንቀዉ አንዱን ጎሳ የክልል ማለትም የከፍተኛ አስተዳደር ደረጃ ባለቤት አድርጎ ሌላዉን ጎሳ የዞን ማለትም የዝቅተኛ የአስተዳደር ደረጃ ባለቤት (በክልል ስር) ማድረግ ይባስ ብሎም ሌላዉን ጎሳ የወረዳ ወይም የመጨረሻዉ ዝቅተኛ የአስተዳደር ደረጃ ባለቤት ማድረጉ ነዉ። የሕዝቡ ቁጥርም እንኳን ሚዛን ዉስጥ እንዳልገባ ከሰንጠረዡ መረዳት ይቻላል።…… (የክህደት-ቁልቁለት-ገጽ115-116-117) www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Monday, June 8, 2009

ጣሊያን ሊጥላት የታገላትን ሰንደቅ ዛሬም በወያነ ትግራይ ተደገመ!

ጣሊያን ሊጥላት የታገላትን ሰንደቅ ዛሬም በወያነ ትግራይ ተደገመ! ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
ይህ ጽሁፍ ለማጸፍ ዓላማ አልነበረኝም፣፣ይህ አስቸኳይጽሁፍ ለመጻፍ የገፋፋኝ ምክንያት በwww.Ethiopianpatriots.com የህዋ ሰሌዳ ላይ AEUP and the Issue of the National Flag in Tigray በሚል ቪኦኤ ከትግራይ ያስተላለፈዉን ዘገባ ሳደምጥ በኢንጅኔር ሃይሉ ሻዉል ሊቀመንበርንት የሚመራ የመኢአድ ኢትዮጵአዊ ድርጅት በትግራይ ክፍልሃገር ዉስጥ በአላማጣ ከተማ ዉስጥ የከፈተዉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰቅሎት የነበረዉን አያሌ ኢትዮጵያዊያን ከዘመነ ንጉሥ አምደጽዮን እና ከዚያም በፊት የምትታወቀዉ ባለ ሦስት ሕብረ ቀለም ያላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅዓላማ (አረንጓዴ፣ቢጫ እና ቀይ)፣ ‘የትግራይ ሕዝብ ነፃ አዊጪ ግምባር’ብሎ ራሱን የሚጠራ “እጆቹን በደም የታጠበዉ ይህ ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅትና- ሕገ ወጥ መንግሥት” በሾመዉ የከተማዉ ከንቲባዉ በኩል “የወያኔ ትግራይ ‘ሁለተኛዉ ባንዴራ’ የሆነዉ ከማሃሉ ሰማያዊ ቀለም የለበሰ የአይሁዶች ምልክት ያለበት ባለ ጨረር ኮከብ ባንዴራ” ካልሰቀላችሁ ሰቅላችሁት ያላችሁትን “ሕጋዊ ሰንደቃላማ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አይደለም” {ህወሓት አያዉቀዉም!!} በማለት ጽ/ቤቱ ህንጻ ላይ ተሰቅሎ የነበረዉ ይህ ለዘመናት የተከበረና - ህወሓት ብሎ ራሱን የሚጠራ ይህ “የሻዕቢያ ቅሪት/ቁሻሻ”ገና በዚህ ዓለም ሳይፈጠር፣ “ብሔራዊ ሰንደቃላማ” ሆና በትግራይ ሕዝብና በብዙ ነገስታቶቿ የተከበረቺዉ “ሰንደቃላማቺን” በጠመንጃ አፈሙዝ ተጠቅሞ በጉልበት አስፈራርቶ እንዲወረድ ካስደረገ በሗላ የመኢአድ ጽ/ቤትም እንዲዘጋ አድርጛል የሚል የዜና ዘገባ ሳዳምጥ ንዴቱ አላስችል ብሎኝ እንቅልፍ ሳልተኛ ይህንን ቁጭቴን ጽፌ አንድ ሳዓት ሳልተኛ ወደ ስራ መሄድ ነበረበኝና-ኢትዮጵያ በአደገኛ መንገድ ላይ እንዳለች ሁለቻሁም እንድታዉቁት ደጋግመን እያሳሰብን ነዉ፣፣ እንደምታዉቁት ወያኔ ሲፈጠር የማያዉቁት የዋህ ተከታዮቻቸዉ በሞኝነታቸዉ ብንስቅባቸዉም፣ባለማወቅ እየተከተሏቸዉ-ያሉት የመሃል አገርና የደቡብ/የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ ተወላጆች ወያኔን በማመገስ አድርጉ የሚላቸዉ የጥፋት ተልዕኮአቸዉ እየፈጻሙ ስለምናዳምጣቸዉ አገሪቱን እነሱንም ጭምር ይዛ ወደ ገደል እየተጓዘች መሆኗን ሳልገልጽ አላልፍም፣፣ ወያኔ ከነ እሱ ይልቅ ተጀምሮ አስኪያልቅ እኟ የትግራይ ተወላጆች በደምብ ስለምናዉቃት እኛ የምንሰጣቸዉን መረጃ ሳይንቁ ይህ “የሻዕቢያ ጥራጊ ጭፍራ”ከመደገፍ እንዲያቆሙ ዛሬም በድጋሜ እናሳስባለን፣፣ ይህ የሻዕቢያና የጀብሃዎች “ኩሩሩ-ቡችላ”የትግራይን ህዝብ ወዶ ሳይወድ እየተገደደ በቁመናቸዉ ከነህይወታቸዉ ሳይሞቱ ብዙ የተከበሩ አዛዉንቶች በእሳት እያሰቃየ ዛሬ ወዳለበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት። ደርግ በቀይ ሽብር የከተማዉን ወጣት ሲጠርግ ፤ የሻዕቢያ ቅጥረኛ የሆነዉ ወየኔም፤ ትግራይ ዉስጥ በገጠሩ፤ ኢትዮጵያዊነቱን ያልካደና እምነታቸዉን ያላመነ ገበሬዉንና ወዛደሩን <ኮራኹር አምሐሩ፤ ሽዋዉያን ተጋሩ> (ያማራ ቡችሎች- የሸዋ ትግሬዎች) እያለች የ “ኢዲህ” ታጋይ ቤተሰብ ዘመድና አዝማድ የተባለ ሁሉ በጠቅላላ፤በሬና ላሙን፤በግ አና ፍየሉን፤ አህያዉን በቅሎዉን፤ ደሮዉንና ጎተራ እህሉን፤ ማርና ቅቤዉን፤እየወረሰች ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ፤ ለሐማሴኖች መደሰቻ ተብሎ፤ላሻዕቢያ ያልሰገደ’ምስኪን የትግራይ አራሽ ገበሬ፤ “ዘር ማንዘሩ”ከምድር እነዲጠፋ እየረሸነች፤ ለሌሎች መቀጣጫ ተብሎም በወጉ በቤተዘመድና በጎረቤት እንዳይቀበር፤ለንቃተ ህሊና ትምህርት ወደ በረሃ ተልኳል እየተባለ፤ ሳይመለስ የቀረዉ የቤትና ጎረቤት ሰዉ ታዝቢ ይቁጠረዉ። በማለት “አሞራዉ”ደራሲ ወንድሜ አቶ ግደይ ባሕሪሹም ያሰሰቡትን ዛሬም ለነዚህ የዋህ ተከታዮቻቸዉ ወያነ ትግራይ ማንነት ለማስታወስ እገደዳለሁ፣፣ ሻዕቢያ የተባለዉ የኤርትራዉ ድርጅት፤ በግማሽ ትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ዘመዶቹን፤ ወየኔ ትግራይ ድርጅት “ቁንጮ”ላይ አስቀምጦ፤በንጹህ የትግራይ ዘርና ትዉልድ ላይ ግፍ የፈጸመበት “በሃያኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጊዜ” እነደነበር፤ ለተተኪዉ የትግራይ ትዉልድ ታሪክ መጥቀስና ማዉረስ የተቆርቋሪ ወገን ግዴታ ነዉ። ትግርኛ በመናገራቸዉና ወላጆቻቸዉ ትግራይ ዉስጥ ተወልደዉ የትግራይን መሬት ፍሬና እህል በልተዉ በማደጋቸዉ፤ትግሬዎች ነን በማለት፤ትግራይን ህዝብ-"ለነጻነትህ ብርሃን ነዉ"-እያሉ፤ በዘር ወገናቸዉ ለሆነዉ ለሻዕቢያ በተንኮል ተወክለዉ፤የትግራይን ሕዝብ የወገኑ የመሃል አገር ያማራና የኦሮሞ ወዳጅ ለዘላለም እንዳይኖረዉ ፤በኤርትራዊያን ተጨቁኖ፤ በአማራዉም ተጠልቶና ተራርቆ እንዲኖር፤ በተንኮል ወደ ገሃነም ጨለማ መሩት። ዉጠቱም ይሄዉና “ጣሊአኖችና የኮሚኒስት ፋሺስቶች” “ብሄር ቤረስብ” እያሉ ኢትዮጵያን አንድነት በዘዴ ለመበታተን ባቀዱት የተንኮል ዘዴ ዛሬ በወያኔ አማካይኝነት በስራ ላይ ዉሎ ያልነበረ ታሪክና ሰንደቃላማዎች እንደ አሸን ፈልቶ እርስ በርሱ ወደ ጨለማ እና መበታተን ወደ ገደል እያዘገመ እንደሆነ በዓይን እያየን ነዉ፣፣ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አናዉቅም ሲል ወያኔበቀሪዉ ያገራችን ሕዝብ -"ባንዳ አስገንጣይ ተገንጣይ ታሪክ ሻጭ"እየተባልን እኛ የትግራይ ተወላጆች እንድንወቀስ፤ ታሪክ ዘላለም እንዲከሰስና በታሪክ እነዲኮነን አደረጉን። በሻዕቢያ መሠረተ ዓላማ የተጠመቁ “ግማሽ ትዉልዳቸዉ ከሃማሴኖች/ሰራየ እና ትግራይ የተወለዱ”፤ የትግራይ ሕዝብ በመሀል አገር ህዝብ እና በተቀረዉ ያገቱ አካባቢ ሕዝብ እንዲሞገስና እነዲመሰገን አይፈልጉም። ይልቁንም እንዳቀዱትና ዘፈናቸዉና ፕሮግራማቸዉ ደጋግሜ እንዳቀረብኩላችሁ በትግሬዉና በአማራዉ መካከል የከረረ ጠብ ተፈጥሮ በዚህ ባገሪቱ ሰንደቃላማ እና ታሪኳ እንዲሁም ያገሪቱን ብሔራዊ ቋንቋ እንዲጠፋ እን በጣለትነት እንዲታይ በመሞከር ምክንያት የትግራይ ሕዝብ ከአማራዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እየተጋጨና ተቀያይሞ እንዲኖር ጥረዋል፣፣ ብሔራዊ ያገሪቱ ቋንቋ በላቲን ቋንቋ ተተክቶ መጪዉ ትዉልድ አፍሪካነቱን እንዲጥል እርስ በርሱ እንዳይገበያይበት እና እንዳይነጋገርበት ከፍተኛ ዘመቻ ሲያደርግ ከቆየ በሗላ - በዚህ በቅርብ ወራት ደግሞ በ1988ዓ.ም እና በ1928 ዓ.ም ጣሊያን ሊጥላት ሞክሮ ታግሎ ያቃተዉን ያገራችን ብቸኛ እና ብሄራዊ ሰንደቃላማችንን “የአፓርታይዱንና የእስከ መገንጠሉን ፖሊሲዉ” የሚቃወሙትን በየተቃዋሚ ጽ/ቤቶቻቸዉ ድረስ ጠብመንጃ የያዙ ሎሌዎቹን አስከትሎ በመሄድ “ኢትዮጵያዊነት መለያቸዉ የሆነቺዉ ወላጆቻችን የሞቱላት የተሰዉላት፣ በዱር ሸንተረሩ የተንከራተቱላትና የተጋዙላትን ባለ ሦስት ቀለም ሰንደቃላማችንን” ወደ መሬት በመጣል ሕልዉናዋን ለማጥፋት ለመጨረሻ ጊዜ እየታገላት መሆኑን መረጃዉ ቁልጭ ብሎ ይታያል፣፣ በኔዉ አገላለጽ- ወያነ ትግራይ ብሎ ራሱን የሰየመ ይህ ወራዳ “የሻዕቢያ ቅሪት- (EPLF Artifact”) በወያኔዉ በአስገደ ገብረስላሴ አገላለጽ “የሻዕያ ጊላ” (የሻዕቢያ - (ባርያ) የለየለት የአፓርታይድ ስርዓት እያካሄደ መሆኑን ለሚጠራጠር ሰዉ ካለ አሁኑኑ ቢያዉቀዉ የተሻለ ነዉ እላለሁ፣፣ ይህንን አስመልከቶ አንድ እውቅ የአገራችን ጸሃፊ ብዕር ያሰመሩበትን እንደገና ዛሬም ላስታዉሳችሁ እፈልጋለሁ፣፣ ወያኔ ከቋንቋ እስከ በዘር ማስተዳደር የጀመረዉ -ዛሬ ደግሞ የህወሓትእንጂ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማን አላዉቃትም ሲለን -ወያነ ትግራይ የጣሊያን ዲቃላ (ግልባጭ) የሆነ ፕሮፖጋንዳዉ ስራ ላይ እያዋለዉ መሆኑን በግልጽ ሲነገረን፣ እዉነት እላችሗለሁ-ከየዓለማቱ በጥራጊ መልክ ወደ ኢትዮጵያ የመጣዉ አፓርታይድና ፋሽዝም ይፋ ሆኖ ለጎብኚዎች የሚነበብ ነጋሪት (ማስታወቂያ) ገና አልወጣም አንጂ፤አሁን ከሚሰራዉ የጣሊያኖች ግልባጭ ስራ ከስራዉ ጋር አብሮ ማስታወቂያዉ ቢወጣ ኖሮ የጦቢያዉ ጸሃፊ አቶ ጸጋየ ገ/መድህን አርአያ ያስቀመጡትን ዓይነት ማስታወቂያ በምድሪቱ ለይ መለጠፍ ነበረበት የሚል እምነት አለኝ። ልጥቀስና በዛዉ ልሰናበት፦ "የሰላምሐዋርያት ወደ ሚኮነኑባት ዓለም አንኳን ደህና መጡ! ነቢያት ዛሬም ወደ ሚወገሩበት መዲና ጥሩ እግር ጥለዎታል። ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የወጣዉ አፓርታይድና ፋሺዝም ሥር እየሰደዱ በሚገኙበት አሮጌ አገር አዳዲስ ጋንግስተሮችን ያገኛሉ። ማስታወሻ ደብተርዎን ይቆጥቡ።ብዙ የሚያስጽፍ ድርጊት አለና!ለማንኛዉም እንኳን ወደማፊያዎች አገር መጡ!ስለሕግና ስለሕጋዊነት ብዙ ይሰማሉ! እንኳን ደህና መጡ ብቻ!"….. "ስለንግድና እንቅስቃሴ የሚያስተምረዉን ሥነ ኣእምሮ አወቃለሁ ባልልም ቱሪስት ድርጅት (እሱም ስሙን ቀይሮ ካልሆነ)የተነሳሁበትን ዓይነት ማስታወቂያ ገና ከቦሌ እላይ እና ቀጥሎም የአራዳነት ማእከል በሆነዉ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ቢለጠፍ-ከ24-ዓለም ድንቅ ነገሮች አንደኛዉ አንደሚሆን እገምታለሁ።" (ጸጋየ ገ/መድህን አርአያ ጦቢያ ቁጥር 10/1993) የአገሪቱ ታሪክ፣ አንደነት፣ ቅርስ ማንነት ብሄራዊ ቋንቋ ዛረ ደግሞ በጥበብ ለማጥፋት የተሞከረዉ የቆየዉ ያገሪቱ ብሄራዊ ሰንደቃላማ የማጥፋት ዘመቻ “ግልጽ- አካላዊ የጥቃት” ዘመቻ የተከፍተባት መሆኑን እና ያገሪቱን ሰንደቅ መለኳ እና ክብሯን ለመጠበቅ ያመች ዘንድ ማንኛችንም ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ አንዲዘጋጅ ባገሪቱና በዉጭ ላሉት ለፖለቲካ እና ሲቪክ ማሕበራት መሪዎች መልእክቴን አስተላልፋለሁ፣፣
ጌታቸዉ-ረዳ-(ሳንሆዘ-ካሊፎርኒያ-አሜሪካ) www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Friday, June 5, 2009

ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊ ወይስ ትግሬ (ኢትጵያዊ)?

ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊ ወይስ ትግሬ (ኢትጵያዊ)? ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
ከላይ የሚታየዉ የኢሳያስ የልጅነት ፎቶግራፎች ምንጭ ከEthiopiansemay.blogspot.com ዝግጅት ክፈል ነዉ፣፣ “ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊ ወይስ ትግሬ (ኢትዮጵያዊ)?” በሚል ርዕስ በምኒሊክ መጽሄት ላይ ሰኔ 1993 ዓ.ም በዶ/ር ፍስሃ ጽዮን መንግሥቱና ጓደኞቹ ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ ትዉልድ እና ዜግነት ሰፋ ባለ መልኩ ቀርቦ ነበር። በዛ ጽሁፍ ዉስጥ የኢሳያስ አፈወርቅ ወላጆች የትዉልድ ስፍራ እና የቤተሰብ ስም ዝርዝር በስፋት ከመቅረቡ ሌላ “ትልቁ የኤርትራዊያኑ ስህተት የማንነቱን መሠረት የማያዉቁ መሆናቸዉን ነዉ”-በማለት አብዛኛዎቹ ኤርትራዉያን በትግራይ ሕዝብ ላይ ያላቸዉ የተሳሳተ አመለካከት እና ንቀት ለምን ማንጸባረቅ እንደሚፈልጉ በጥልቅ አትቷል።በዚህ ጽሁፍ የማቀርብላችሁ“ኤርትራዉያኖቹ-ለምን በትግራይ/ኢትዮጵያዉያን ላይ ንቀት እንደሚያሳድሩ ሳይሆን፣ ትኩረቱ በኢሳያስ አፈወርቂ ብቻ ይሆናል፣፣ ከዚህ መረጃ በመነሳት የማቀርብላችሁ.እንደሚታወቀዉ ሰሞኑ በሻዕቢያ ቴሌቢዥን የተላለፈዉ በአቶ ኤልያስ ክፍሌ እና የኢትዮጵያ አርበኞች ግምባር ብሎ ራሱን የሚጠራ የዉጭ ዩዳይ ተጠሪ አቶ ስለሺ አማካይኝነት አስመራ ድረስ በመሄድ ከሻዕቢያዉ መሪ ከኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ለሕዝብ ይፋ መደረጉን ታስታዉሳላችሁ። ቃለ-መጠይቁን የተከታተላችሁ ሁሉ እንደምትገነዘቡት ጋዜጠኞቹ በአማርኛ ሲጠይቁት ኢሳያስ ሲመልስ የተጠቀመበት ቋንቋ የገዛ ቋንቋዉ በአማርኛ ሳይሆን በባእድ-በእንግሊዞች ቋንቋ-ነበር።ይህ-“ስልጡን”ኤርትራዊ “አጋሜዎች” የሚጠቀሙበት አማርኛ ቢጠቀም ስልጡንነቱ እንዳይራከስበት በማለት ይሆን? የሚል ጥያቄ ባብዛኛዎቻችሁ ሕሊና እንደሚኖር እርግጠና ነኝ። በዚህ መሰረት አድርገን ሰዉየዉ አማርኛ ለምን እንደተጠየፈ የኢትዮጵያን ረቪዉ አዘጋጅ አቶ ኤልያስ ክፍሌ ተጠይቆ ሲመልስ “አማርኛ የመናገር ችሎታዉ ደካማ ስለሆነበት ነዉ …” የሚል መልስ እንደሰጠ አንድ ቦታ ላይ ያነበብኩ መሰለኝ፣፣ ነገሩ ከብዙ ዜ ጀምሮ የተከታተለዉ ሰዉ ከተሰጠዉ መልስ የተለየ ነዉ፣፣ መረጃዎቹ የሚያሳዩት ለአማርኛ ያለዉ ጥላቻ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ምግብ ለሆነ ለእንጀራችንም ጥላቻ እና ንቀት ያለዉ መሆኑን ከፈረንሳይ መጽሄቶች ጋር ያደረጋቸዉ ቃለ ምልልሶች ያረጋግጣሉ፣፣ መረጃዎቻችን በመጠኑም ቢሆን ለማሳየት እንሞክራለን፣፣
ግልጽ ላልሆነላቸዉ ሰዎች ኤርትራዊ ነኝ የሚለን የኢሳያስ ማንነት እና ትዉልድ ካሁን በፊት ላላወቃችሁ አዳዲስ ወጣቶች ማህደሩን እንደገና ወደ ፊት በመሳብ ላለንተ አቀርባለሁ። አማርኛዉን ወደ ጎን በመተዉ -በዓረብኛ ቋንቋ፤ እና በ እንግሊዝኛዉ የመጠቀሙ አባዜ ከምንም የመነጨ ሳይሆን የኢሳያስ ኢትዮጵያዊነት/ትገሬነት እንዳይታወቅበት የሚያደርገዉ ከንቱ የደካሞች- የበታችነት የሕሊና ስሜት እና ራስን የማጣት የዕብደት ምልክት መሆኑን አንባቢዎች እንድታዉቁት “ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊ ወይስ ትገሬ/ኢትዮጵያዊ?” ከሚለዉ ትንታኔ በመጀመር ኢሳያስ የትግራይ ተወላጅ ሆኖ የኢትዮያ ምግብ የሆነዉ እንጀራ የማጥላላት እና እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የሆነዉን አማርኛ ከእንግሊዞች እና ከዓረቦች ቋንቋ እያሳነሰ ማየት ለምን እንደመረጠ ለመሸፋፈን የሞከረዉ የትዉልድ ታሪኩንና የተያያዙ አጫጭር ትንታኔዎች እንመለከታለን፣፣
ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊ ወይስ ትግሬ/ (ኢትዮጵያዊ)?
“ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊነት ተረት ነዉ ወይስ እዉነት ነዉ? የኢሳያስ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቅ አብርሃ ይባላሉ፣፣ እናቱ ወይዘሮ አዳነች በርሄ ይባላሉ፣፣ ልጆቻቸዉም (1) አቶ አማረ አፈወርቅ (አፈወርቂ) (ይህ ስያሜ ኤርትራዊነትን ለማስመሰል ነዉ፣፣) (2) አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ (3) አቶ አማኑኤል አፈወርቅ (4) አቶ ኤርሚያስ አፈወርቅ (5) አቶ ዮናስ አፈወርቅ (6) ወ/ሮ ጽጌረዳ አፈወርቅ (7) ወ/ሮ አርዮን አፈወርቅ
ከኤርትራ ፕረዚዳንት ቤተሰብ በስተጀርባ ያለዉ ታሪክ፣- የኢሳያስ አባት አቶ አፈወርቅ የመጡት ከትግራይ ተምቤን ሲሆን ዘራቸዉ የኢትዮጵያ አካል ከሆነዉ ከአጋሜ አዉራጃ የተዉጣጣ ነዉ፣፣ የአቶ ኢሳያስ አባት ይሰሩ የነበሩት በትግራይ አስተዳደር ክፍለ ሃገር በመቀሌ መዲና ነበር፣፣ ጡሮታ እስከወጡ ም ድረስ በመሬት ንብረት ይዞታ ማሻሻያ ሚኒስቴር ዉስጥ ነበር የሚሰሩት፣፣ ጥቁር ሙሉ ልብስና ጥቁር ክራባት ለባሽ ተብለዉ ይጠሩ እንደነበር ይነገራል፣፣ (“ካንትሪ ጀንትል ማን”ተብሎ አንዳንዴ ከሚታወቀዉ ከጥቁር ሱፍ የተሰራ ክብ ቆብ ከራሳቸዉ አይለዩም ነበር፣፣ ጋዜጣም ከእጃቸዉ በፍጹም አይለዩም ነበር፣፣ (በቅንፍ የተጨመረዉ- ጌታቸዉ ረዳ)፣፣ በናታቸዉ በኩል የኢሳያስ አጎቶች፣- (1) ደጃዝማች ሰለሞን አብርሃ (2) ካፒቴን መኮንን አብርሃ (3) አቶ ሓጎስ አብርሃ ናቸዉ፣፣
የአቶ ኢሳያስ አጎት ደጃዝማች ሰለሞን አብራሃ (በጊዜዉ ሲጠርዋቸዉ በነበሩ ጋዜጦች አጠራር “ሰለሞን አብሃም” በቅንፍ የተጨመረ- ጌታቸዉ ረዳ) በሃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት ማለት (በ1946 ዓ.ም) የወሎ እንደራሴ ሆነዉ ያገለገሉ ናቸዉ፣፣ በዚያ ጊዜ መቀሌ ከተማ ዉስጥ ተደራጅቶ የነበረዉ የባህል ቡድን አስመራን ከጎበኘ በሗላ ወደ ደሴ መጣ፣፣ እንደራሴዉ ደጃዝማች ሰለሞን ለክብር እንግዶቹ በተዘጋጀዉ የእራት ግብዣ ላይ ምስጋናቸዉን ለቡዱኑ ከገለጹ በሗላ እሳቸዉም ትግሬ መሆናቸዉን አንስተዉ የባህል ቡድኑ የትግራይ ባህላዊ ሙዚቃ እና ባህላዊ ዉዝዋዜ ለማስፋፋት ላደረገዉ አስተዋጽኦ አድናቆታቸዉ ገለጹ፣፣ በተጨማሪም የደጃዝማች ሰለሞን እናትም አጋሜ አዉራጃ ዉስጥ ተወላጅ ትግሬ መሆናቸዉን እና አባታቸዉም በትግራይ ክ/ሃገር ዉስጥ የተምቤን ተወላጅ መሆናቸዉን አንስተዉ ለባህል ቡድኑ ገልጸዉላቸዋል፣፣ የባሕር ሃይል ካፒቴን የሆኑት ካፒቴን መኮንን አብርሃ የኢቴጌ መኮንን ትምሕርት ቤት ተማሪ የነበረቺዉ የደጃዝማች ገብራይ ልጅን አግብተዉ ሦስት ልጆች እንደወለዱ ይታወቃል፣፣ አቶ ሐጎስ አብርሃም ቢሆን በአዲስ አባባ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የጥንት ተማሪ ሲሆን ለዚያዉ ተማሪ ቤት የእግር ኳስ ቡድን በረኛ ነበር፣ ሆኖም በበሽታ ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ ለጥቂት ጊዜ በብሔራዊ ባንክ ስራ ተቀጥሮ እየሰራ እንዳለ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ይታወቃል፣፣
የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አያቶችና ሌሎች ዘመዶቻቸዉም - በሚመለከት፣-
በእናቱ በኩል የኢሳያስ አፈወርቂ አያት (የእናት እናት)ወይዘሮ መድህን “በራድ” ይባላሉ፣፣ በራድ (ተብለዉ በቅጥያ ስም የተጠሩበት ምክንያት ወ/ሮ መደህን በጠጅ ስራ ንግድ ተሰማርተዉ ይኖሩ ስለነበር “ጠጅ”ባካባቢዉ የሚቀዳዉ “በራድ” ተብሎ በሚታወቀዉ “ማንቆርቆርያ” ስለነበር ነዉ፣፣ መድህን የኢሳያስ እናት የወይዘሮ አዳናች በርሄ እናት ናቸዉ፣፣ ኢሳያስ የልጅነት ትምርቱ የተከታተለዉ በሴት አያቱ በወይዘሮ መድህን ተንከባካቢነት ነዉ፣፣ በቅንፍ የተጻፈዉ- ጌታቸዉ ረዳ)፣፣ ወ/ሮ መድህንም በትዉልዳቸዉ ዓድዋ ሲሆኑ፣ የፊታዉራሪ ኪዳነ መስቀል አጎት ናቸዉ፣፣ ፊታዉራሪ ኪዳነ የአቶ የማነ ኪዳነ (የየማነ ጃማይካ)-አባት ናቸዉ ይባላል ፣፣ ይህ እዉነት ከሆነ የአቶ የማነ ኪዳነ (ጃማይካ)-እና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ “በኢትዮጵያ አጠራር” ወንድማማቾች ናቸዉ ናቸዉ፣፣ በአዉሮጳዉያኖች አጠራር ግን “የአጎት ልጆች ናቸዉ”፣፣ባጭሩ አሥመራ የሚገኙ አክራሪ ጠላቶች ናቸዉ የሚባሉት አብዛኛዎቹ የትግራይ ዝርያ የሆኑና በተለይ ከትግራይ በጠቅላላም ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ የስጋ ፣ የአጥንት እና የደም ቁርኝት ያላቸዉ ናቸዉ፣፣
የኢሳያስ አክስት (የኢሳያስ እናት እህት) ወ/ሮ ሃና ይባላሉ፣፣ የአቶ በላይ ባለቤት ናቸዉ፣፣ አቶ በላይ የዓድዋ ሰዉ ናቸዉ፣፣ እንደሚባለዉም ልጆቻቸዉ ስዊድን ሃገር ዉስጥ ይኖራሉ፣፣ በእናታቸዉ በኩል የአቶ ኢሳያስ አጎት የሆኑት ከዓድዋ ተወላጅ ከሆኑት በአሁኑ ጊዜ ጀርመን ዉስጥ የሚኖሩ ወ/ሮ ዘዉዴ የሚባሉትን ወልደዋል፣፣ ከላይ በተገኘዉ መረጃ መሰረት የአቶ ኢሳያስ ኤርትራዊነት ኤርትራ መሬት መወለዳቸዉ ብቻ ነዉ፣፣የአቶ ኢሳያስ ባለቤትም ወ/ሮ ሳባ ሃይለ ይባላሉ፣፣ ኤርትራዊት ናቸዉ፣፣
ይህ የሚያስገርም ነገር ነዉ፣፣ለእዉነተኛ ኤርትራዉያኖችና በጭፍን ኢሳያስን በጭፍን ለሚደግፉ ይህ ግልጽ የሚሆነዉ ከብዙ ዘመናት በሗላ ነዉ፣፣አእምሮአችን ዉስጥ ስለ ኤርትራዊዉ ፕረዚደንት ማንነት ታሪክ አዳዲስ ነገሮች እየታወቀ ሲመጣ ስሜታቸዉ እንደሚለወጥ አያጠራጥርም፣፣ ኤርትራዎቹ አስመልክቶ ልጆቻቸዉንና ሌላም ዓይነት መስዋእትነት ለሰላሳ ዓመታት የከፈሉ ፣የኢሳያስ ዉሸትና ተግባር በጣም አስነዋሪ፣ የክፍለዘመኑ የእዉነት ታሪክ ያለመሆኑ ቀስ በቀስ እየተረዱት እንደሚሄዱ እርግጠኞች ነን፣፣
እነኚህ ሰዎች ለሰላሳ ዓመታ ቤተሶቦቻቸዉ ይህንን አመጸኛ ሰዉየ ሥልጣን ላይ ለማቆት መስዋእትንት የከፈሉና የዉሸት የ ኤርትራዊነቱ ዜግነትበጭፍን ይደግፉ ነበር፣፣ ከዚህ በፊት አቶ ኢሳያስ ትግሬ ነዉ ያላልንበት ምክንያት ስለሟች ወላጆቹ ማንነታቸዉ በቂ መረጃ ስላልነበረንና ሕዝባችንን ባልተረጋገጠ ነገር ለማጣደፍ ወይም ስሕተት ነገር ላለመስጠት ስለፈለግን ነዉ፣፣ በጥብቅ ለማስገንዘብ የምንፈልገዉ ይህንን መረጃ የሰጡን ግለሰቦች ሰለ ኢሳያስ በቂ ዕዉቀት እንዳላቸዉ ስለቤተስቡና ዘመዶቹ በቂና ምስጢራዊ ዕዉቀት እንዳላቸዉ እናዉቃለን፣፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ ላላቸዉ ሰዎች በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም ኤርትራዊያኖች የራሳቸዉ ጥናት አካሂደዉ ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ እንማጸናለን፣
ለኢሳያስ ተከታዮች አስቸጋሪ አማራጮች፣-
አንዳንድ የኢሳያስ ታማኝ ተከታዮች ኢትዮጵያዊያንን እንደ ጠላቶቻቸዉ ያዩዋቸዋል፣፣ በሚያሳፍር አባባል “ከአጋሜ ወይም ከድሆች ካልሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ጋር ምንም ግንኙነት ለማድረግ እንደማይፈልጉ ይናገራሉ”፣፣ እንደዚህ ያሉ አስመራ ዉስጥ ወይም በስደት ሌላ ሀገር ዉስጥ የሚኖሩ “ስልጡን” ኤርትራዊያን ምንም እንኳ ጥቂት ቢሆኑም ራሳቸዉን እንደሃብታሞችና ስልጡኖች ይቆጥራሉ፣፣ ከትግራይ የሚመጡ “አጋሜዎችም”ይንቃሉ፣፣ እነኚህ አንዳንዶቹ ኤርትራዊ ያልሆኑ ያለ ፅዳት ስራ ወይንም እንደ ቤት ስራተኛነት እና ግምበኛነት ያለ የስራ መስክ የሆኑት በጠቅላላዉ ኤርትራዊ ሊሰራዉ የማይፈቅደዉን ስራ መስራት እንዳለባቸዉ ያምናሉ፣፣ አንድ ትግሬ ወይም ኢትዮጵያዊ የኤርትራ ፕረዚዳንት ይሆናል ብሎ ማስብ ዘበት ነዉ፣፣ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንዳያስተዳድረን ብለን አይደለም ወይ ሰላሳ ዓመት የተዋጋነዉ!? ይላሉ፣፣
ኤርትራዉያኖቹ ከኢትዮጵያዊያኖቹ ልዩ ፍጡር ናቸዉ ብሎ ለማለት፣ እንደቻይና ወይም እንደበርሊን ግንብ እንዲገነባ የሚፈልጉ ወይም አጋሜዎችንና ያልሰለጠኑ ድሃ ኢዮጵያዊያኖችን የሚንቁ ታማኝ የኢሳያስ ተከታዮች፣ አሁን ይህ አረመኔ አምባገነን በእርግጥ ኤርትራዊ አለመሆኑና ትዉልዱ ትግሬ/ኢትዮጵያዊ መሆኑን ሲረዱ ደንግጠዉ ተሸማቅቀዉ መሪነት እንደማይገባዉ ይረዳሉ፣፣
ኤርትራዊያኖች አዲስ ጅምር ለማድረግ ስለ ኤርትራዉ ፕረዚደንት መመለስ ያለበቻዉ ጥያቄዎች፣-
ከላይ ከተባለዉ አንፃር ቢያንስ ሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ አለባቸዉ፣፣ (1)የኤርትራ ፕረዚዳንት ለምን የትግራይ/ኢትዮጵያ ትዉልድ እንዳለበት እያወቀ በጠቅላላ የ ኢትዮጵያ በተለይም የትግራይ ጠላት ሆነ?ለምን በእናቱ እና በአባቱ በወላጆቹ አገር ጦርነት አካሄደ? (2)ለምን ዋሽቶ የትግሬይ/ኢትዮጵያ ታሪክ መስረቱን ደልዞ ንፁሕ የኤርትራ ደም ካላቸዉ ዜጎች የበለጠ የኤርትራዊነት ብሔረተኝነት አሳየ? (3) ለምን ትግሬ/ ኢትዮያዊ የሆነዉ ኢሳያስ የሰላም ድልድይ ከመሆን ይልቅ ለራሳቸዉ ጥቅም ቅኝ ገዢዎች የከፋፈሏቸዉ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች በማጋጨት አፋጃቸዉ? (4)የሃገራቸዉን ነፃነት ለማስከበር አኩሪ ታሪክ ያስመዘገቡ የራሱ የሆኑ ወገኖቹ የትግራይ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለምን ያፍርባቸዋል? (5) ለምን የራሱን መሰረት እንደሌለዉ ይቆጥራል? (6) ኤርትራዊያኖች የሰላሳ ዓመትመስዋእት ለምን ለአንድ ሰዉ ጥቅም ተብሎ የተከፈለ ከሆነ ለምን ተከፈለ? (7) ኤርትራ እና ኢትዮጵያኖች በመከባበር ወንደማማችነታቸዉ ከማጠንከር ይልቅ ለምን በኢሳያስ ሰበብ ደም ተፋሰሱ?ለምንስ ጦርነት ተመረጠላቸዉ? (8) የኢሳያስ ቤተሰቦች ለምን ስለ ትዉልዳቸዉ እዉነቱን ከመናገር ዝምታን መረጡ?ለምን ቤተሰቦቹ አኩሪዉ የትግራይ/ኢትጵያዊ ህዝበ አካል መሆናቸዉ ለመናገር ይፈራሉ? (9) የኢሳያስ ቤተሰብ ለምን የጥንቱን የአክሱምን ስልጣኔ ኢትዮጵያዊ ባህልና ታሪክ ይክዳሉ? (10)ብዙዎቹ ኤርትራዊያኖች ወደፊት የሃገራቸዉ ልማት መሰረት ኢትዮጵያ መሆኗን እያወቁ ኢትዮያን ለሰላሳ ኣመታት ተዋግተዉ ይባስ ብሎ ደግሞ ይልቁንም በ1991 እንደገና ለምን ዉግያ ዉስጥ በመካፈል ብዙ መስዋዕት ከፈሉ? (11) ኤርትራዊያን ጊዜያቸዉና ዕድሜአቸዉ ተጠቅመዉ ለሰላምና ለእድገት ከማዋል ይልቅ ከወንድመማቾች ጦርነት ምን ፋይዳ ይገኝበታል ብለዉ ለምን ራሳቸዉን አይጠይቁም?”””
በማለት ዶ/ር ፍስሃጽየን መንግሥቱ እና ጓደኞቹ ከላይ የተመለከታችሁት በጣም አስደናቂ ትንተና እና ብዙ መልስ የሚሹ ጥያቄዎች አቅርበዋል፣፣ እንግዲህ የሰሞኑን የኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ ስለ ኢትዮጵያ መቆርቆር እና “ኤርትራ” የምትባል “ልዩ አገር” መሆኗን እና ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ታሪካዊ/ባሕላዊ/ፖለቲካዊ/ማሕበራዊ ጉዳይ እና በኢትዮጵያዊያን በኩል ሊነሳ የሚችል ማንኛዉም ሕጋዊ ጥያቄ እንደማይኖርና “የተዘጋ ምዕራፍ” በማለት የሰጠዉ የቃለ መጠይቅ መልሱ ይታወሳል፣፣ ኢሳያስ ስለራሱ ማንነት ለሰላሳ ኣመት ሲዋሽ ሲያደናግር ቆይቷል፣፣ ትግሬነቱ/ኢትዮጵአዊነቱ እንዳይታወቅበትም ከኤርትራኖቹ በላይ ኤርትራዊ ሆኖ በመቅረብ “ሕዘብ ከሕዝብ የሚያጋጩ ዉሳኔዎችና ትንኮሳዎች በመመርያ ደረጃ እና ጸረ ኢትዮጵያ/ትግራይ የሆኑ እርምጃዎችን ሲወስድ እንደቆየ የታወቀ ነዉ፣፣ በተለይም ጸሃዎቹ እንደሚሉት “ግማሽ ትግሬ -ግማሽ ኤርትራዊ”ከሆኑት ጋሻ ጃግሬዎቹ ጋር ተባብሮ የኤርትራን ሕዝብ አሳስቶ ለስልጣን ሲል በኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ላይ ከፍተኛ ደባ ከመፈጸሙ በላይ (ልክ የአክሱማዊዉ “ከሃዲ” የወልደ አብ ወልደማርያም ፈለግ በመከተል) ሁለቱ ሕዝቦች የተለዩ ሕብረተሰቦች አድርጎ በመስበክ ከፍተኛ የደም መፋሰስ እንዲካሄድ ምክንያት ሆኗል፣፣
ኢሳያስ ኢትዮጵያዊነቱን ሊጠላ ወይም ሊደብቅ የቻለዉ ለራሱ ብቻ የሚታወቅ ምክንያት ቢኖረዉም፣ ጸሃፊዎቹ እንደገለጹት አልፎ አልፎ ኢሳያስ በሕሪያቶቹ እንዳእስስት ሲለዋዉጥ ይታያል፣፣ ደስ ሲያሰኘዉ -እኛ ከሌሎቹ በተለይም ከትግራይ ሕዝቦች በብዙ መልኩ የተሳሰርን ነን ሲል፣ ሌላ ጊዜ ከጣሊያን ሃገር የተላኩ ሃገር እና ንብረት የሚዘርፉ የፋሽስቶች ዱርየዎች “ያሰመሩበትን የዉሸት ድምበር”እና “ከፋፋይ ፖለቲካ”በመቀበል የምድሪ ባሕሪ ሕዝቦች “ኤርትራዊያኖች” እንጂ “ኢትዮጵያዊያኖች” እንዳልሆኑ ይሰብካል፣፣ ይህ ደግሞ በብዙ ንግግሮቹ የተገለጹ ናቸዉ፣፣ በበለጠ ግን ጸሃፊዎቹ በሚከተለዉ ግልጽና አጭር አገላለጽ እንዲህ ሲሉ ይናገራሉ “ኢሳያስ በዙርያዉ ያሉትን አንዳንድ ግለሰቦችን የምናወግዝበት ምክንያት እዉነተኛ ማንነታቸዉን ስለሚደብቁና ይህንን ማንነት ለመደበቅ ሲሉ “ጨካኝ ሆነዉ” ዉጤቱ ሞትና ዉድመት በሆነ የማያባራ ጦርነት ዉስጥ ሕዝቡን አስገብተዉ ለስቃይና ለዉርደት መዳረጋቸዉ ነዉ፣፣ ዘግናኙ የኢሳያስ የጦርነት ሱስ፣ የችግር የዉድመት፣ እንዲሁም የራሱን እውነተኛ ማንንት የታሪክና የባህል ከሃዲነት ተምሳሌት ነዉ፣፣ የማያጠራጥር ነገር ቢኖር ኢሳያስ ሁልጊዜ የሸፍጥ ልምድ ያለዉና በግድያ የሚኖር ግለሰብ ነዉ፣፣”ሲሉ ስለ ኢሳያስ ማንነት ገልጸዉታል፣፣ እንግዲህ ኢሳያስ በኤርትራኖች ዓይን ማንነቱን በእንዲህ ሲገልጹት አንዳንድ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች ወደ ኤርትራ ምድር በመዝለቅ የ የእርሱን እርዳታ በመሻት ወይንም የኢሳያስ ሰብአዊነት በበጎ ሲሰብኩ መስማት አብዛኛዎቻችሁ ምንኛ እንደሚያሳዝናችሁ መገመት አያዳግትም፣፣ እንኚህ ሰዎች፣ ለማንኛዉም ከኢሳያስ የሎጅስቲክ እርዳታ በማግኘት፣ኢትዮጵያ ዉስጥ ካለዉ ሌላኛዉ የታሪክ አተላ ከሆነዉ የአሜሪካና የዓረቦች ቅጥረኛ የደደቢቱ መንጋ “ከወያነ ትግራይ”ነጻ ለማዉጣት የሚታገሉ ዜጎቻችን ናቸዉ በማለት እቅዳቸዉን በበጎ የተነሳሱበት ነዉ እንኳ ብንል፣ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጉዳይ አሁን ባለበት ሁናቴ፣ ኢትዮጵያም የባሕር በሮቿን ተነጥቃና አስነጥቃ ይቀጥል ከተባለ ፣ ያዉም ኢሳያስ የዚህ መርህ ቀንደኛዉ አራማጅ መሆኑንና ጉዳዩም “የተዳፈነ የወደፊት እሳት”እንደሆነና ፣ ኢሳያስ የሚያክል አረመኔ የብዙ ሺህ ሰዉ ኢትዮጵያዊ ህይወት ለሕልፈት የዳረገ ጸረ-ኢትዮጵያ መሆኑን እያወቁ አስመራ ድረስ ሄደዉ “ወያነ ትግራይ”ብሎ ራሱን የሚጠራ ሌላኛዉ “የትግራይ ሻዕቢያ”ለመጣል ወታደራዊ ትጥቅና ስልጠና እንዲረዳቸዉ ለመማጸን እየተሰባሰቡ ናቸዉ እየተባለላቸዉ ያለዉ የግንቦት 7 (ዜናዉ እዉነት ከሆነ) እና ሌሎቹ ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችን ከዚህ አረመኔ በምን መልኩ እና አስከ የትኛዉ ርቀት ሊያታግላቸዉ እንደሚችል አስካሁን ድረስ ለኔ ግራ የገባ እንቆቅልሽ ነዉ፣፣ ለማንኛዉም ጊዜ ደጉ ነዉና ሁሉም አስኪ በትዕግስት እርምጃቸዉን እንመለከት እያልኩ፣ ኢሳያስ አፈወርቅ ኢትዮጵያዊነት ዜጋነቱ ብቻ ሳይሆን የካደዉ የኢትዮጵያ በሕል ምግብና አኗኗርም ሲያጣጥል ተዘግቧል ብየ ቀደም ሲል የጠቀስኩላችሁን ጉዳይ ለማስታወሻችሁ (for your file) ይሆን ዘንድ- ለምሳሌ እንጀራ እና አስፓጌቲን በማወዳደር እንጀራ የ ያልሰለጠኑ ህዝቦች ምግብ ሲል አስፓጌቲ ደግሞ የሰለጠኑ ህዝቦች ምግብ በማለት የኢትዮጵያን ባህልና ሕዝብ ለማሳነስ በመሞከር እራሱን ከኢትያዊነቱ ለማስራቅና ለመሸፈን ያላደረገዉ ደካማ ጥረት እንደሌለ ካሁን በፊት ከአንዱ ከፈረንሳይ ጋዜጣ ጋር ያደረገዉ ቆይታ ጠቅሼ ልሰናበታቸወሁ፣፣ ከዚህ በታች የተገኘዉ ጽሑፍ በትሁትነታቸዉ የሚመሰገኑ ለኢትዮጵያዉያን ቀና መንፈስ ያላቸዉ የሆኑት ኤርትራዊዉ ምሁር ፕሮፌሰር ተስፋጽየን መድሃንየ “Towards Confederation in the Horn of Africa” በተባለዉ አዲሱ መጽሓፋቸዉ በገጽ 137ላይ ከፈረንሳይ ቋንቋ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ “በሪፖርተር እና በኢትዮጵያ ፈረስት ድረገጾች” ላይ ታትሞ የነበረዉን ኢሳያስ ከፈረንሳይ ጋዜጦች ጋር ያደረገዉ ቃለ መጠይቅ እንዲህ ሲሉ አቅርበዉታል፣፣
“… Similar to such an incorrect view of history is disdain for Ethiopian cultures and traditions, which are also shared by Eritrea. The propaganda of the cadres of the regime occasionally denigrates the traditional ways of Ethiopian life of Ethiopian life, which is unwittingly disparaging towards Eritrean tradition as well. President Isayas himself is known to have made some vulgar and primitive comments in this regard. In an interview with a French journalist, he bellitted the cultural ways of life- e.g-, traditional homes and staple food-, which he associated with backwardness. He also sneered at Ethiopia’s “evolutionary and traditional” process of development. In the same breath, he expressed admiration for things European such as villas and spaghetti, which he regarded as evidence of modernity-seemingly concedering Italian colonial rule of Eritrea as a “revolutionary” process. (30. Fabiene Le Heuerou, “The Birth of Eritrea” (Interview with Isayas Afewerki-English translation). The Reporter (Addis Abeba- December 8, 1999), in (Ethiopiafirts.com-Dec, 1999) In effect, the president was contending that Eritrea was more advanced and more modern than Ethiopia. After all, in the words of the president, “the Italians have put the foundations on which the Eritrean identity was built by way of transforming the society economically, politically, culturally and socially.”31 (Ibid) To the Ethiopians, this remark was both foolish and nauseating. By it President Isayas distinguished himself as “the first man to praise colonialism, especially facist Italy’s style”.(32)(Getahun gebre-Amlak “In Issayas Landl, Wonders never End, (Ethiopiafirst.com) Dec.30,-1999.) Actually his hypothesis on cultural and modernity was ridiculed by Ethiopian commentators, some of whom stressed in satirical language (at which they are very good) that no matter how Europeanised (a’ la Isayas) Eritrea may be, it is no match for backward Ethiopia. (33) With reference to President Isayas’ remark an Ethiopian commentator wrote- “When Isayas finishes eating his spaghetti to complete his metamorphoses into the likes of his Western masters and joins the club of high tech warriors (being facetious here) Ethiopia shall still whip Eritrea with only spear and arrows.”(M.Azene- May 2000). It was a good example of the ‘we are special people’ syndrom” expressed by a leader who “lives in total delusions” (34) (Getahun Gebere-Amlak- 1999). Such contemptuous views of Ethiopia history and culture, pose obstacles to co-operation and association. Remarks of the kind made by president Isayas lead some Ethiopians to oppose confederation arguing that Eritreans are racist, hate Ethiopia and still love Italy. Undoubtedly, a few Eritreans need to be advised to exercise due care lest they express arrogance towards Ethiopians.} Tesfatsion Medhanie- (Towards Confederation in the Horn of Africa- (P.137, 138, 139) ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com