Thursday, April 27, 2017

አሰፋ ጫቦ! ገናናው ብዕርተኛ!
ከጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
Assefa Chabo 4/26/2017 Posted at Ethiopian Semay

አቶ አሰፋ ጫቦ ወደ እዚያኛው ዓለም አልፈዋል።የተከበሩ አቶ አሰፋ ጫቦ ከዚህ ዓለም በድንገት መለየታቸው በዜና አውታሮች ተለጥፎ ባየሁ ጊዜ የተሰማኝ ድንጋጤ በህይወቴ እንደዚያ ያለ ስሜትና ሓዘን ተስምቶኝ አያውቅም። እጅግ አሳዛኝ መርዶ ነው። በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ እኔ ጌታቸው ረዳ ለቤተሰብ እና ወዳጆቻቸው መጽናናት እንዲሰጣቸው የሓዘን መልዕክት ለማስተላለፍ እወዳለሁ።

ይህ ካልኩኝ በኋላ አንድ ነገር ለማለት እፈልጋለሁ። በአንድ ድርጅት የሓዘን መግለጫ በኩል ስለ እሳቸው የተላለፈ “የሰብአዊ መብት ተሟጋች” ነበሩ’ የሚለው ከህይወት ታሪካቸው ተያይዞ የቀረበ መግለጫ አከራካሪ ስለሆነ፤ አስከሬናቸው በትውልድ አገራቸው ኢትዮጵያ አፈር ከለበሰ በኋላ ለድርጅቱ አዘጋጆች በጥያቄ የምመለስበት ስለሆነ በዚሁ ልለፈው።

ሆኖም ይህ ድንገተኛ ሞት ከማጋጠሙ በፊት በህይወት እያሉ እሳቸው በወያኔ ስርዓት ውስጥ “ኦሞቲክ” የሚበል የደቡብ የጎሳዎች ድርጅት በመምራት በወያኔ የሥልጣን ሽግግሩ ወቅት በተሳተፉበት ወቅት በርካታ አገር ወዳዶች እንደ እነ አሰፋ ማሩ፤ ፕሮፌሰር አስራት እና በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች፤ ህጻናት ሳይቀሩ በቢላዋ፤በገጀራ እየታረዱ፤ከነነብሳቸው ወደ ገደል እየተገፈተሩ ሲጣሉ፤ በርካታ ምሁራንና ዜጎች  በወያኔ ነብሰገዳዮች እየተገደሉ እና እየታደኑ ሲሰወሩ፤ ዝነኛው አገር ወዳድ ፕሮፌሰር ዶክተር አስራት ወልደየስ ስለ አመራው መጨፍጨፍ እና ስለ ኤርትራ መገንጠል በመቃወማቸው ስብእናቸው በቴ/ቪዠን ሲገፈፍ እሳቸው (አቶ አሰፋ ጫቦ) እና የሲዳማ ነፃ አውጪ ድረጀት መሪ የነበረው ሟቹ ወልዳማኑኤል ዱባለ ግምባር በመግጠም  ፕሮፌስ አስራት ያቀረቡትን አቋም በመተቸት፤  ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያው ኢሳያስ አፈወርቅ በተገኘበት አዳራሽ ለኤርትራ ወንበዴዎች ፤አገር ሿጮች፤ነብሰገዳዮች፤ከሃዲ ባንዳዎችን በመደገፍ፤ ምን አቋም አንደያዙ እና ካንደበታቸው ሲወጡ የነበሩ እጅግ አስገራሚ ቃላቶች እና ክርክሮች በማሕደር የተመዘገበ አንደበታቸው መከራከሪያ አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል (ሌሎች ያልገለጽኳቸው ጉዳዮችም ለሟቹ ክብር ስል እዚህ አልጠቅስም)። በዚህ አጋጣሚ ጽሁፎቼን ለማንበብ ከፈለጋችሁ አስፋ ጫቦንስ ከፍተን ብናያቸው? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮያጵያን ሰማይ አዘጋጅ)  ወልቃይት.ካም http://welkait.com/?p=7482  ወይንም  ኢትዮ-ጳትረዮትስ.ካም 
http://www.ethiopatriots.com/pdf/አስፋ-ጫቦንስ-ከፍተን-ብናያቸው.pdf

ወይንም Ethiopian Semay facebook ወይንም Ethiopiaan seamy blogspot.com

ብላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። የመጨረሻው ትችቴ ማርች 20/2017 ነው። ለዚህ ጽሑፍም ሆነ ለመጀመሪያው ትችቴ መልስ መስጠት አልፈለጉም ነበር። በድንገት ከመለየታቸው በፊት፤ ሌሎች ርዕሶችን በሚመለከት ሲጽፉ እንደነበር አይቻለሁ እና፤ መልስ መስጠትም የሚችሉበት የመከራከሪያና የማምለጪያ መስኮቶቹ ዝግ ስለነበሩ፤ መልስ አልነበራቸውም። በዚህም አከብራቸዋለሁ ። (ለኢሕአፓንም ሌላ ተመሳሳይ ጉዳይ ጠይቄው መልስ ስላለስጠኝ  ኢሕአፓም አፉን ስለዘጋ፤ አክብሮት እሰጠዋለሁ ማለት ግን አይደለም፡ ጉዳዩ ለየቅል ነውና) ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በድንገተኛ ሞት ከዚህ ዓለም ተለዩን። በጣም ነበር ከውስጥ አንጀቴ እጅግ ያዘንኩት። በወቅቴ የተሰማኝን ድንገተኛ ሓዘን ለመግለጽ ቃላት አላገኘሁም።

ምከንየታዩም እሳቸው፤ የኋላኋላ ጸረ ኢሳያስ / ከዚያም ጸረ ኦነግ፤ ጸረ ወያኔ፤ ብርቱ ብዕርተኛ ፤ሲጽፉ ለዛቸው የሚጥም፤ልዩ የብዕር ስልተኛ ነበሩ። ከዚያ ባለፈ ግን ጽ/ቤቱ ዋሺንግተን ያደረገው ከኣንድ ተቋም ክቡር አቶ አሰፋ ጫቦን “የሰብአዊ መብት ተሟጋች” ነበሩ ያለውን በኔ በኩል አልቀበለውም። አቶ አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት እንደ እነ ጸሀፊው ጸጋዬ ገ/መድህን (ሙሉጌታ ሉሌ) እና የመሳሰሉት ከግንቦት 7 ጋር (ባጭሩ ኤርትራ ከሚያሰለጥናቸው ጋንጎች ጋር) አልተሻሹም፤አልቆሸሹም። እንደ እነ ሙሉጌታ ሉሌ ለጸረ አማራው እና ለጸረ ምኒሊክ ለነ የግንቦት 7ቱ ኤፍሬም ማዴቦ “አምባ አላቀረሩም”፤ ኤፍሬም ማዴቦን ጀግናዬ አላሉትም። ስለሆነም በዚህ በዚህ  ለአቶ አሰፋ ልዩ ከበሬታ አለኝ።  በሓዘን ላይ ሆነ እንጂ በጣም የሚገርመኝ እዚህ ውጭ አገር ያሉ የፖለቲካ አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች ጋዜጠኞች ‘በወያኔ (እንዲሁም በደርግ) ለታሰረ ሁሉ “ጀግናዬ”/ጀግና/ እያሉ አንዳንዶቹን ሲያሞካሹ አይቻለሁ; ያስገርመኛል፤ የደርጉን አንተወው እና የወያኔን እስረኞች ብንመለ፤ከት ታምራት ላይኔም፤ ስየ አብርሃምም፤ ብስራት አማረም፤ አንዳርጋቸው ጽጌም፤ ጁነዲን ሰዶ ወዘተ ሰንቶቹ የስለላ እና የመረጃ አቀባይ የነበረ፤ በአንድነታቸወን ላይ ሲያሰር እና ሕግ ሲያጸድቅ የነበረ፤ ናዚያዊ ጸረ አማራ መጽሐፍ የጻፈ ሁሉ በወያኔ ታስረው ተሰቃይተዋል፡ ስለሆነም እነሱም በጥቅሉ ወደ ጀግና መንደር እየደባለቁ ሲሞካሽዋቸው አይተናል። ለዚህም ነበር ብርሃኑ ነጋ “ጎህ ሲቀድ” በሚለው ስለራሱ (ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት) በጻፈው መጽሐፍ ላይ፤ የወያኔን ካርታ ከመለጠፉ አልፎ መጽሐፉን ለስየ አብርሃ ነበር ማስታወሻነቱ እንዲሆንለት የገለጸው። (የተስፋየ ገብረ አብ መጽሐፍ መቅድም ጻሀፊው እና አሻሻጩ “ብርሃኑ ነጋም በሌለቹ “ጀግና” ተብሏል። የዘመኑ ጀግና እጀግ  ያስገርማል። አርበኛነት በ$500.00 ዶላርም መግዛት የተቻለበት ዘመን መጥተናል።

አንድ እጅግ የታዘብኩት ነገር አለ። እሱም አቶ አሰፋ የተሳሳቱት (ምክንያታቸው ባልታወቀ ምክንያት እና ምንም ተቀባይነት በሌለው ምክንያት “ምጽአተ አማራ የሚለው መጽሐፍ እና የሞረሽ ሲቪክ ድርጅት መሪው ክቡር አቶ ተክሌ የሻውንም የመዝለፋቸው እንቆቁልሽ) እንዳለ ሆኖ፤ ለሟቹ ለክቡር አቶ አሰፋ ጫቦ ልዩ አክብሮት የምሰጣቸው ምክንያት፤ ብዙ ታላላቅ ጸሐፊዎች ፤ጋዜጠኞች፤ምሁራን ለኢሳያስ ግብር ሲያድሩ፤ ከተሰቀሉበት አስከባሪ ማዕረግ እራሳቸው በቅሌታቸው ወደ አፈር አውርደው ሲጥሉት እና ሲያዋረዱ፤ ለኤርትራ ወንበዴዎች ልዩ ሙገሳ ሲያቀርቡ፤ ከጐሰኛ  ቡድኖች ጋር ሕብረት በመፍጠር ልዩ ፕሮፓጋንዳ ለተግንጣዮች እና አማራን ለጨፈጨፉ እና ላስጨፈጨፉ ወንጀለኛ የተግንጣይ መሪዎች ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩ፤አልፎም “በእነሱ ጫማ ስር ገብተን ጫማቸውን አንድንለካላቸው” ሲገፋፉን፤ እና በርካታ ‘አጋሰስ ምሁራን”  ለግንቦት 7 እና ለኦነግ ጎሰኛነት አክብሮታዊ  ትኩረት በመስጠት እንደ እነ ጌታቸው በጋሻው፤ ፕሮፌሰር መሳይ፤ ሻለቃ ዳዊት ወልደግዮርጊስ፤ አምባሳደር ካሳ ከበደ….ወዘተ…..ወጣቱን ሲያጃጅሉት፤  አቶ አሰፋ ጫቦ ግን በዚው ጭቃ አላደፉም። ለዚህም ነው አክብሮት የምሰጣቸው እና ሓዘን የተሰማኝ። እግዚአብሔር ነብሳቸውን ይማር! ለቅርብ ቤተሰብ እና ለወዳጅ ዘመድ የኢትዮጵያ አምላከ እግዚአብሔር መጽናናት ይስጣቸው!
ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com


Monday, April 17, 2017

ጥያቄ ለኢሕአፓ

      ከአዘጋጁ ማስታወሻ፤-  
ጥያቄ ለኢሕአፓ               
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) 4/17/2017
Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay)
Getachew Reda Editor Ethiopian Semay
ዛሬ የምንመለከተው ለኢሕአፓ አመራሮች፤ ለድረገጽ ተቋማቶቻቸው እና ለተከታዮች አጭር ጥያቄና አስተያየት ነው። ባለፈው ወር እኔን በእጅጉ በአግራሞት ያስደነገጠኝ እና እጅግ ያስገረመኝ ኢሕአፓ ስለ ኢትዮጵያ፤ ስለ አማራ፤ስለ አጼ ምኒልክ፤ስለ ሶማሌ፤ ስለ ኦጋዴን….ወዘተርፈ ያተተበት የቆየ የድርጅቱ ሰነድ ነው የተባለ  “እስኪ ዶሴው ይውጣ! የማን? የኢሕአፓ” በሚል በአቻምየለህ ታምሩ የቀረበ ለኢሕአፓ መሪዎችና ተከታዮች እንዲሁም ደጋፊዎች እጅግ ፈታኝ የሆነ ሰነድ በተከታታይ ቀርቧል። ይህ ሰነድ እስካሁን ድረስ ከኢሕአፓ መሪዎችም ሆነ ከተከታዮች መልስ ያላገኘ ነው። እኔ በበኩሌ እንዲህ ያለ ሰነድ ለሕዝብ ይፋ ሲሆን እውነት ነው፤ ይርታ፤ ወይንም ውሸት ነው፤ እንዲህ ነው…፤ ተብሎ መልስ መሰጠት ነበረበት። እስካሁን ድረስ መልስ አላገም።

ዋለልኝ መኮንን ተችተሃል ተብየ በኢሕአፓ ጀሌዎች ያልተሰደብኩት ስድብ አልነበረም። አሲምባ በሚባለው የኢሕአፓ ድረገጽም “አሲምባ” ጽሁፎቼ ለሕዝብ እንዳይስተናገዱ እስከማገድ ድረስ የደረሰ ብቻ ሳይሆን ስለ እኔ ካርቱን ለጥፎብኛል። በዚህም ጸብ እንደፈጠርን የሚታወቅ ነው። ዛሬ ከዋለልኝ በባሰ “ኢትዮጵያን ፤አማራን፤ ታሪኩን፤አንድነቷን፤ሚኒሊክን…. የሚዘልፍ ሰነድ የኢሕአፓ ነው ተብሎ ይፋ ሲወጣ፤ ኢሕአፓዎች “አፋቸው ሲዘጉ” ማስተዋል ለኔ በጣም ከማስገረሙ በላይ አስደንግጦኛል።

አቻምየለህ በ 6 ተከታታይ ምዕራፎች (ሁሉንም ማግኘት ባልችልም አንዳንዱን ተመልክቼቻቸዋለሁ) በወጣው ሰነድ ላይ አንድ ባንድ፤ነጥብ በነጥብ አንዲት መስምር ሳይዘሉ የተጠቀሱት ክሶች ኢሕአፓ መልስ ካልሰጠበት ኢሕአፓ እንደተቀበለው አድርገን እንወስደዋለን (ኢሕአፓ ስንል ሁሉም “ዲ”/አንጃ የሚባለውም ሆነ ዋናው ኢሕአፓም ሆነ የሚመለከታቸው ሁሉ መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል)። መልስ ካልሰጡበት “ዋለልኝ መኮንን አትንኩብን” እያሉ “ማሃይሞች” ሲሉን እና ሲዘልፉን የነበሩት የኢሕአፓ “ሊቃውንቶች” ካሁን ወዲያ “ከኔ ወዲያ ስለ ኢትዮጵያ ለአሳር፤ ዋለልኝን አትተቹ… ወዘተ” የሚለው መስመራቸው “የኢሕአፓ ሊቅነት” ከባድ ፈተና ውስጥ ገብቷል እና መልስ እንዲሰጡበት እንጠብቃለን። ለምን ጠየቅከን ተብየ በድጋሜ አንደማልዘፍ ተስፋ አደርጋለሁ።  አሎ! አሎ! ሃሎ! ሃሎ! ይሰማል?

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com



Tuesday, April 11, 2017

የኢሳት እንግዳው ዮሐንስ ዘለቀ ማነው?
Editor’s Note 
The fellow who is the subject of the following topic written in Amharic is one of the Israelite communities better known as Falasha/Bete Israel/ living in USA. He is been the guest of the so called Ethiopian Satellite (ESAT) the mouthpiece of Berhanu Negga, a TV station financially aided by foreign powers through Ginbot 7 postured as Amhara (based on the following commentary).

As I have been saying all along, there are many elements who acted as Ethiopians still fooling you big-time, but they do not believe they are Ethiopian natives, they are wolfs in sheep’s’clothing. For the life of me, I don’t understand the honest motive there is inviting to Ethiopians’ media as guests those who denounce their “Ethiopiawinet race” and called themselves native citizens of Israelite race; surprisingly still allowed to talk about Ethiopia current politics.

I say, if you are not Ethiopians?! Stay out of it! Leave that for us and leave us alone. Stay with your beautiful race called Israelite. Leave Ethiopia alone as you already denounce your race.

We knew, After the change of power took place in Ethiopia, the subverters took advantage of the 1991 “crisis” and the Imperialists power (Israei Mosad/US/CIA)moved in with a large cargo plane and took the Felasha to Isralel with permission and collaboration of the new mercenaries /native banda namely TPLF.

From 1977 on words new modern slave trade flourished in Africa. Many Africans including Ethiopians started to be recruited as a maid to Arabs and also Felashas traded for money and transferred to Israel as Israelite native citizens.
If you want to read more of it… read my old commentary 

Slave Trade in Tens of Thousands of Ethiopians Branded as “ Falasha” “Black Jews” Smuggled out of Ethiopia was the Direct Rape of  Our Dignity Recorded in History  Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay)

Now, let us go to read

የኢሳት እንግዳው ዮሐንስ ዘለቀ ማነው?

የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ | ለመሆኑ የኢሳት እንግዳው ዮሐንስ ዘለቀ ማነው? (ዴቭ ዳዊት)
April 11, 2017 | by ethioexploreradmin
እያንዳንዱ አማራ ይህን እንዲያነብ እና እነማን ናቸው ጠላቶችሁ እነማን ናቸው ታሪኩን ጥላሸት እሚቀቡት እሚለውን ሊገነዘብ ይገባል

Yohannes Zeleke is a man of many hats” ይላል ዴቪድ ካግሰዌል የተባለው ሰው ኦክቶበር 24-2014 ትራቭልፐልስ ዳት ካም በተባለ ድረ ገጽ ላይ በጻፈው ጽሁፉ። አብሮ አደጎቹ እና በቅርበት በዋሽንግተን የሚያውቁት ደግሞዮሐንስ ስጡይሉታል። በተለምዶ ያለገደብ የሚዋሽ ሰውስጥተብሎ ይጠራ የለ?!እኛ ደግሞ ዮሐንስ ብዙ የበግ ለምዶችን ደራርቦ የለበሰ ተኩላ ነው እንላለን፤ ብለንም አንቀርም በእውነት ካራ እያንዳንዱን ለምድ እየገፈፍን ተኩላነቱን እናሳያለን። ማርች 29-2017 .. ኢሳት የተባለው የቁጭ በሉዎች የወሬ ቋት ይህንን ግለሰብ ቃለ መጠይቅ አደረግሁ ብሎ በአማራነታችን ላይ አፉን እንዲያላቅቅ ካደረገው በኋላለመሆኑ ዮሐንስ ዘለቀ ማነው?” የሚለውን መልስ ለማግኘት እንዲህ እና እንዲያ ስንል ቆይተን አማራዊ የሆነው ወገናችን እውነቱን ያውቅ ዘንድ ከነማስረጃው እነሆ ብለናል!መልካም ንባብ።

15 አመቱ አርኪዮሎጂስት

ዮሐንስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጁላይ 4 ቀን 1963 .. በጎንደር ተወለደ። ታድያ ትራቭል ፐልስ ከተባለ ድረ-ገፅ ጋር ኦክቶበር 24-2010 .. ባደረገው ቃለ ምልልስ በህይወቱ ጉልህ ከነበረው ክስተት አንዱ ሀገሪቱን የናጣት አብዮት ሲሆን በዚህም ወንድሙን፣አባቱን እና አያቱን በአብዮቱ እንደተነጠቀ ይገልፅ እና በሱ የደረሰው ግን የተለየ እንዳልሆነ ይልቁን አብዛኛው ሰው ከቤተሰቡ አንድ እና ሁለት ሰው እንዳጣ ይገልፃል። ድረ-ገፁ 1981 .. አካባቢ ፕሬዝደንት ሬገን የአሜሪካንን በር ለኢትዮጵያኖች ክፍት እንዳደረጉ እና በተለይ ከጎንደር አካባቢ በጅምላ ወደ አሜሪካ እንደተሰደዱ አውስቶ ዮሐንስን ለምን ወደአሜሪካ አልመጣህም ሲለው እንዲህ በማለት ነበር የመለሰው -

“I didn’t want to leave my mother,” said Zeleke. “I had several chances to leave, but if you lose someone from family due to the revolution, you were called counter revolutionary, so you couldn’t leave. I had a chance to come to America for a scholarship. I was working as an archaeologist with the ministry of culture since 1978.” 

ሲተረጎም 
ይህን ይመስላልእናቴን ትቼ መሄድ አልፈለኩም። ለመሄድ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩኝ፤ግን ከቤተሰብህ አንዱን በአብዮቱ ካጣህ ፀረ አብዮተኛ ተብለህ ትፈረጃለህ ስለዚህ መሄድ አትችልም። በስኮላርሺፕ ወደ አሜሪካ የመምጣት ዕድል ነበረኝ። 1978 ጀምሮ በባህል ሚንስቴር ውስጥ በአርኪዮሎጂስትነት እሰራ ነበር።

ከዚህች መልስ ብሎ ከተናገራት ውስጥ ሁለት ትልልቅ ውሸቶችን እናውጣ።
15 ዓመቱ በምን ተዓምር ነው አርኪዮሎጂስት ሆኖ ተመርቆ ፕሮፌሽናል ስራ በባህል ሚኒስቴር ውስጥ ሊሰራ የሚችለው?

ከቤተሰብህ መካከል በአብዮቱ ሰው ከተገደለብህ መሰደድ አትችልምያለው ለመሆኑ ሁሉ አሜሪካ የገባው የጎንደር አማራዊ ቤተሰቡ ያልተገደለበት ነበር ማለት ነው? ይሄ ትልቅ ውሸት ነው። እንዲያውም አብዛኛው የተሰደደው ቤተሰቡ የተገደለበት እና እሱም ሊገደል እየተፈለገ የነበረው ነው።
(
ማስረጃ ይሆን ዘንድ ቃለ ምልልስ ያደረገበትን የድረ-ገፅ ማስፈንጠሪያ/Link/ ይመልከቱ፡-

http://www.travelpulse.com/…/meet-the-tour-operator-yohanne…)

የትምህርት ደረጃ
ከላይ የጠቀስነው ትራቭል ዳት ካም የተባለው ድረ-ገጽ ዘገባውን በመቀጠል እንዲህ ይላልምንም እንኳን ወደ አሜሪካ መሄድ ባይችልም ወደ ሶቭየት ህብረት ግን ለትምህርት ሄደ።መቼ ተመረቀ?ምንስ አጠና? የሚለውን ደግሞ Strategy XXI የተባለው የአምባገነን ሀገራትን ገፅታ በአለም ፊት በመገንባት የህዝብ ግንኙነት እና የሎቢ ስራ በመስራት የሚተዳደረው ድርጅት ዮሐንስን በአማካሪነት ያቀፈ ሲሆን በድረ-ገፁ የዮሐንስን የትምህርት ደረጃ፣ መቼ እና የት እንዲሁም ምን ተማረ የሚለውን እንዲህ ይገልፀዋል፡- “Dr. Zeleke has a B.A. in History (1992) and an M.A. in Archeology (1993) from the St. Petersburg State University in Russia and a Ph.D. in Archeology (1997) from the Russian Academy of Sciences” 
ሲተረጎም 
/ ዮሐንስ የባችለር ኦፍ አርት ዲግሪውን በታሪክ ትምህርት 1992 .. በአርኪዮሎጀ የማስተር ዲግሪውን 1993 .. ከራሻው ሴንት ፒተርስበርግ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪውን በአርኪዮሎጂ 1997 .. ከራሽያ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ተመረቀይለናል። እንግዲህ ዮሐንስ እንደ ኤዲ አሚን ዳዳ ለራሱ ረጃጅም ማዕረጎችን እየሰጠ በየድረ-ገፁ ቢለጥፍም እውነታው ደርግ በመውደቂያው ዋዜማ በኮታ ተዋፅኦ እና በኢሠፓ አባልነቱ ወደ ሶቭየት ህብረት ከላከው በኋላ 29 ዓመቱ የመጀመሪያ ዲግሪውን በታሪክ ትምህርት 1992 .. ያገኘ ሲሆን ሶቭየት ፈራርሳ በለውጡ ክፉኛ ከደቀቀችው ራሽያ ነው እንግዲህ እነዚያን ብራና በአምስት አመታት ሰብስቦ በአንድ ጊዜ ዶክተር የሚለውን ስያሜ ያገኘው።ከዚህ ባሻገር የአሜሪካኖቹ ጆርጅ ታውን እና በርክሌ ዩኒቨርሲቲዎች 1998-2003 .. የመስክ ጥናት እና ምርምር ሲያደርጉ ዮሐንስ 13 ዓመቱ ጀምሮ በግሉ የቱሪስት አስጎብኚ [Tour Guide] ሆኖ ይሰራ ስለነበር /13 አመቱ ጀምሮ ከቤተሰቡ ወጥቶ በቱሪስት አስጎብኚነት ትናንሽ ልጆች ለፈረንጆች ስለ አካባቢው እያስተረጎሙ እና መንገድ እያሳዩ ገንዘብ እንደሚያገኙት ሁሉ እሱም ያንን እየሰራ ይተዳደር እንደነበር

https://blog.privatefly.com/…/interview-with-a-global-tour-…
መመልከት ልብ ይሏል/እና አካባቢውን ስለሚያውቅ በቡድኑ ውስጥ እንዲካተት ተደረገ። ይህንንም እንደአንድ ትልቅ ስኬት በመቁጠር በነዚህ ተቋማት ውስጥ የጥናት ቡድን አባል እና መምህር እንደነበር አድርጎም የራሱን ገፅታ ሲገነባ ይስተዋላል።
ፀረ-አማራው ዮሐንስ
ከላይ በጠቀስነው ትራቭል ዳት ካም በተባለው ድረ-ገጽ ላይ ዮሐንስ ጎንደር እንደተወለደ ቢናገርም ኤፕሪል 6-2017 በተላለፈው የኢሳት ቃለ ምልልስ ክፍል ሁለት ላይ /

\ ይመልከቱ/ 6ኛው ደቂቃ 4ኛው ሰከንድ ጀምሮ በክፍል አንድ ላይ ራሱ ፈጥሮጎጃም ውስጥ ከኦሮሞ ያልተዋለደ ቡዳ ነው ይባላልየምትለውን አባባሉን እንዲያብራራ የቁጭ በሉዎች አውራ የሆነው ጋዜጠኛ ሲጠይቀው 6ኛው ደቂቃ 37ኛው ሰከንድ ላይ ዮሐንስ ራሱ አባቱ የጎጃም ቡሬ አካባቢ ሰው እንደሆነ እና እሱም የጎጃም አማራ እንደሆነ ይናገራል። እኛ ግን ይህቺን የለበሳትን የአማራዊነት ለምድ በማስረጃ ገፈን ይህ ግለሰብ አማራዊ እንዳይደለ ይልቁን በርካታ የወንጀል እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎችን በአማራ ህዝብ ላይ ያሰራጨ መሆኑን እንዲህ እናሳያለን።

ኩላኑ” /Kulanu/ በመባል የሚጠራው የአይሁድ ድርጅት ተቀማጭነቱን በኑዮርክ ከተማ ያደረገ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በዋናነት በመላው ዓለም የተበታተኑ አይሁዳውያንን መርዳት፣ ስለ ጁዳይዝም እምነት ማስተማር እና በሂደትም ከሰፊው የአይሁድ ማህበረሰብ ማለትም እስራኤል ካሉት ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ ነው። ይህ ድርጅት በተለያዩ ቀጣናዎች ተከፋፍሎ የሚሰራ ሲሆን ዮሐንስ ዘለቀም የኢትዮጵያ እና አካባቢው አስተባባሪ ከሆኑት ሁለት ግለሰቦች አንዱ ነው። ይህ ድርጅት ምንም ማስረጃ ባልቀረበበት እና ዮሐንስ የሚያቀርበውን አፈ ታሪክ እንዳለ በመቀበል ሄርየት ቦጋርድ 2009 በፃፈው ፅሁፉ፡-

.
ቀደምት አማራዊ አባቶቻችን የመሰረቷትን የአዳዲ ማርያም ቤተክርስቲያንን ፈላሻዎች ለሲናጎግ /የአይሁድ የእምነት ቤት/ እንደሰሯት በኋላም ክርስቲያኖች እንደወረሷቸው በማስመሰል በአማራዊው ላይ የታሪክ ዝርፊያ እንዲፈፀም ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

.
በመካከለኛው ዘመን የተገነቡ የጎንደር አቢያተ መንግስታትንበአይሁዶች/ፈላሻዎች/ ነፃ ጉልበት የተገነቡበሚል 2700 ዓመታት ቤተ እስራኤላውያኑ እምነት፣ባህል እና ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ ያደረገውን እና በእንግዳ ተቀባይነት ጨዋ ስነ-ምግባሩ የሚታወቀውን አማራዊውን ታሪኩን በዚህ መልኩ እንዲቆሽሽ ዮሐንስ ብቸኛውና ዋነኛው ሰው ነው። ለግንዛቤ እንዲረዳ አይሁዳውያን ሀገር አልባ በሆኑበት ሁለት ሺህ አመታት ውስጥ በተለያዩ ሀገራት ተበታትነው የነበረ ሲሆን በየዘመኑ በእንግድነት ያስጠጓቸው ሀገራት ከሀገራቸው እንዲለቁ አባረዋቸዋል። ከግሪክ፣ከራሽያ፣ከኢንግላንድ፣በሰባተኛው ክፍለ-ዘመን-ከሳኡድ-አረቢያ፣ ከግብጽ፣ ከስፔን፣ ከፖርቱጋል፣ ከቱርክ፣ከጀርመን፣ከሞሮኮ፣ከአልጄሪያ ብቻ በየዘመኑ አይደለም ወግ ልማዳቸውን መጠበቅ ኑሯቸው እንኳ ነገ ምን ይመጣ ይሆን በሚል የዛፍ ላይ እንቅልፍ እንዲሆን ተደርጎ ነበር።ታድያ አማራዊው ብቻ ነውእንግዲህ በቃን እንሄዳለንእስካሉበት ዘመን ድረስ ባዕድነት ሳይሰማቸው እንዲኖሩ ያደረገው።
. ዮሐንስ ዘለቀ እና ቢጤዎቹ ተረቶቻቸውን ሲቀጥሉም የአማራውያንን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን በነዮሐንስ ዘለቀ /ስጥ/ አያቶች በሆኑት በአይሁዶች እንደተሰራ እና ሀገሪቱንም 200 ዓመታት እንዳስተዳደሯት ይናገራል። ለመሆኑ ከመቼ ወዲህ ነው አይሁድ በሰራው ነገር ላይ የመስቀል ቅርፅ የሚያደርገው? ሲጀመር ላሊበላ ራሱ የመስቀል ቅርፅ ነው ያለው።ሲቀጥል በየግርግዳ እና መስኮቱ ላይ ለቁጥር የሚያታክት መስቀል ነው ያለበት።ታድያ አይሁድ ከሰራው እንዴት የሚጠላውን እና የማያምንበትን መስቀል በየቦታው መቅረፅ ፈለገ?
ዮሐንስ በሚፈጥራቸው ተረቶች እና አንድም ማስረጃ ማቅረብ በማይችልበት እንዲሁ የጥላቻ ዘሩን አሰራጭቷል የአማራዊውን ታሪክ በመዝረፍም ያለበትን የትንሽነት በሽታ /Inferiority complex/ ለማስታገስ እየሞከረ ይገኛል። ዮሐንስ የካሉኑ የኢትዮጵያና አካባቢው አስተባባሪ እንደሆነ እና ሄርየት ቦጋርድ የፃፈውን ከዚህ መመልከት ይቻላል
እና

ዮሐንስ ፀረ-አማራ ብቻ ሳይሆን ፀረ-ኦርቶዶክስም ነው!!!

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2003 የተቋቋመው እና በአህፅሮተ ቃል ቢና /BINA/ ወይም የሰሜን አሜሪካ የቤተ እስራኤል የባህል ማዕከል /The Beta Israel of North America (BINA) Cultural Foundation, Inc./ ዋና ተልዕኮው የቤተ እስራኤል ወይም ፈላሻዎችን ታሪክ እና ባህል ማስተዋወቅ፣ በኢትዮጵያ በእስራኤል እና በአሜሪካ የሚገኙ ፈላሻዎችን ማጠናከር፣ ወደ አሜሪካ የሚመጡ ፈላሻዎችን መርዳት እና የመሳሰሉት ሲሆን ይህ ተቋም 2013 አስረኛ አመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር ዮሐንስ ዘለቀ “The Story of Ethiopian Jews,” የተሰኘ ባለ አምስት ገፅ ግን ብዙ መርዞችን የያዘ ፅሁፍ አቅርቦ ነበር። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ፡-

. በገጽ 2 አንቀጽ1 ላይ አማራዊውን ቅማንት መጤ አይሁድ ነው ይለናል።የዚህ ሰው ነውረኝነት እና ድንቁርና የሚጀምረው ደግሞምናልባትብሎ በመጀመር ታሪክን ሊፅፍ በመሞከሩና መከራከሪያ ብሎ ያቀረበው ፌዝ ነው። ለማንኛውም እንዲህ ነበር ያለው

“Perhaps the earliest Hebraic people came to the land of Ethiopia during the time of the prolonged drought and famine in Canaan at the time of Abraham. These are ancestors of the Qemant, who worship the Lord in the same manner as Abraham did.”
ሲተረጎምም
ምናልባት ቀደምት የዕብራውያን/አይሁድ/ ህዝቦች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በአብረሃም ዘመን በከነዓን ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የድርቅ እና የረሃብ ወቅት ነው።እነዚህ ሰዎች የቀደሙ የቅማንት አባቶች ሲሆኑ አምልኳቸውም አብረሃም አምላኩን እንደሚያመልክበት ያለ ሥርዓት ነው።

እስኪ በዚህ ሎጂክ እኛም እናስብ እና እንዲህ እንበል ከዚያ ያስኬዳል ወይስ አያስኬድም የሚለውን እንይ።
ምሳሌ ነው

 “ምናልባት ቀደምት የቁሬሽ /መካ ይኖሩ የነበሩ እና እስልምናን በመጀመሪያው የተቀበሉ የነብዩ መሃመድ ጎሳዎች ናቸው/ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በነብዩ መሀመድ ጊዜ በተከሰተው የሙስሊሞች መሳደድ ወቅት ነው።እነዚህ ሰዎች የቀደሙ የወሎ ሙስሊሞች አባቶች ሲሆኑ አምልኳቸው ነብዩ መሃመድ አምላካቸውን እንደሚያመልኩ ያለ ሥርዓት ነውብንል ይሄ እውነት ነው?አይደለም!!!

ምክንያቱም የአምልኮ መመሳሰል የዘር አንድነትን አያሳይም።ጣና ሀይቅ ላይ ካሉት ገዳማት መካከል ናርጋ ስላሴ በሚባለው ገዳም በኦሪት እንደተጠቀሰው የቀደሙ አማራውያን የኦሪቱን መስዋዕት የሚያቀርቡበት አለት እና ንዋየ ቅድሳት ዛሬም ድረስ አለ። ታዲያ አማራ አይሁዳዊ ነው አምልኮ እኮ የምትቀበለው እንጂ በደም የሚተላለፍ አይደለም። ደግሞስምናልባትብሎ ጀምሮ እርግጠኛ ሆኖ ድምዳሜ ላይ ይደረሳል እንዴ? ደግሞም ያልተገነዘበው ነገር ቅማንት አይሁድ ከሆነ መጤ እንግዳ ነው ማለት ነው።እንግዳን ደግሞ አንተ ካልፈለግከው በማንኛውም ሰዓት ልታባርረው ትችላለህ ማለት ነው።
.
ሌላው በዚሁ በገፅ ሁለት የመጨረሻው አንቀፅ ላይ እንዲህ በማለት ይፅፋል “The history of Ethiopian Jews has never been told in a way that is based on archaeological and historical facts. Most writers have recognized the fact that Ethiopian Jews were the founders of the early Ethiopian state and the Church of Ethiopia. But they have been denied credit for their contributions to the history and civilization of Ethiopia and world Jewry.” 

ሲተረጎምም

የኢትዮጵያ አይሁዶች ታሪክ በአርኪዮሎጂያዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች ላይ ተመስርቶ ተነግሮ አያውቅም። በርካታ ፀሐፍት የኢትዮጵያ አይሁዶች የኢትዮጵያ የመንግስት ስርዓትንና ቤተክርስቲያንን መስራቾች ናቸው የሚለውን እውቅና ይሰጡታል። ነገር ግን ለኢትዮጵያ ታሪክ እና ስልጣኔ እንዲሁም ለአጠቃላዩ የአይሁድ ማህበረሰብ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ተክዷል።ለዚህ ታሪካዊ ዝርፊያ ጉንጭ አልፋ ክርክር ማድረግ ባያስፈልግም አንድ ነገር ብቻ ብለን ማለፍ እንፈልጋለን። ሲጀመር የኢትዮጵያ አይሁዶች እንደማንኛውም አይሁድ ክርስቲያን አይደሉም።ታድያ በምን ስሌት ነው የቤተ ክርስቲያኗ መስራች የሚሆኑት? ሲቀጥል መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው 34 .. ማለትም ክርስቶስ ወደ ሰማይ ባረገ በመጀመሪያው ዓመት በፊልጶስ እጅ የተጠመቀው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እንጂ ሌላ አልነበረም።ያ ሰው ደግሞ አማራዊ እንደነበር እኛም ጠላቶቻችንም እኩል የምናውቀው ነው። በእርግጥ ዮዲት ጉዲት ብዙ ቤተክርስቲያናትን አቃጥላለች። ይህም እንደ አስተዋፅኦ ይቆጠር ካለ ማለት ነው።

. በመቀጠል በገፅ 2 የመጨረሻው አንቀጽ እና በገፅ 3 የመጨረሻው አንቀጽ ላይ እንዲህ ይላል፡-
 “In the past, the history of Ethiopian Jews was told by different groups of people including: (a)……(b) the Ethiopian Orthodox Church, which sought to annihilate and demonize the Ethiopian Jewish population as the Antichrist”

ሲተረጎምም

 “ባለፉት ጊዜያት የኢትዮጵያ አይሁዶች ታሪክ በተለያዩ አካላት ይነገር ነበር ከነዚህም መካከል :-(a)……(b)የኢትዮጵያ አይሁዶችን ፀረ-ክርስቶስ ናቸው በማለት የምታሰየጥናቸው እና እንዲደመሰሱ የምትፈልገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንዷ ናት።

አማራዊ ወገናችን ሆይ! እንግዲህ በቅዳሴ ፀሎቷ በየዕለቱበስደት እና በምርኮ ያሉትን አንተ /ፈጣሪ/ አስባቸውእያለች የምትፀልየውን፣ ምዕመኖቿ ማንም ቢሰደድ በእንግድነት እንዲሁ እንዲቀበል ፈሪሃ እግዚአብሔርን ያስተማረችውን፣ዮዲት ፈላሻዋ 40 ዓመታት ስታሳድዳት እና ስታቃጥላት ድርሳናትና ንዋየ ቅድሳቶቿን ስታወድም ቀን ጠብቃ ልበቀል ያላለችውን ለሁሉም በእኩል የምትፀልየውን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ነው እንግዲህ ዮሐንስ በተረቱ የሚያብጠለጥላት።

. በገፅ 4 የመጨረሻው አንቀጽ ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል

 “Due to the nature of church doctrine and its policy of forced conversion, the silent Islamic population was forced to rebel against Emperor Lebne Dengel.”

ሲተረጎምምበቤተክርስቲያኗ የዶግማ ባህርይ እና አስገድዶ ሃይማኖትን የማስለወጥ ፖሊሲ ምክንያት በዝምታ ይገዛ የነበረው የሙስሊም ማህበረሰብ በአፄ ልብነ ድንግል ላይ እንዲያምጽ ተገደደ።

ሲጀመር የቤተክርስቲያን ዶግማ በጊዜ መርዘም እና ማጠር አልያም በሁኔታዎች መቀያየር የሚለወጥ አይደለም።ታድያ የቤተክርስቲያን የትኛው ዶግማ እና ምን ላይ የተፃፈው ነው ሃይማኖትን በግድ እንዲቀየር የሚያዘው እና ነው እንደዚህ ብሎ የሚፅፈው?ለምሳሌ የትግሬው ንጉስ ዮሐንስ ሃይማኖትን እንደሽፋን በመጠቀም የወሎ አማራውያንን በግፍ ጨፍጭፏል ግን የቤተክርስቲያን አስተምህሮም ዶግማም አልነበረም።ታድያ ጭፍን ጥላቻ ካልሆነ እንዴት ዮሐንስ ዘለቀ ደፍሮ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ በሌለ ነገር ይኮንናል?

የዮሐንስ ዘለቀ ስር የሰደደ የኦርቶዶክስ ጥላቻ እና በቴዎድሮስ ታሪክ መቆመር እንደሚታወቀው በኢሳት አይዞህ ባይነት ዮሐንስ ዘለቀ ለከት የለሽ ንግግሩን የጀመረው በክፍል አንድ ማርች 29-2017 ነው። እናም በዚህ ፕሮግራም 52ኛው ደቂቃ 40ኛው ሰከንድ ጀምሮ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ሲያወራ

በዘመነ መሳፍንት ማብቂያ ልጅ ካሳ ተነስቶ ቴዎድሮስ ነኝ ብሎ ነገሰ እናም ሀገሪቱን በደም አዋዥቃት፤ አሁን የኔን አያት ብትጣይቀው እብድ ነው የሚልህ ……….ድራስቲክ የሆነ የመንግስት ለውጥ እንደዚህ አይነት ክራይስስ ያስከትላል።

በዚህ ንግግር መሰረት ቴዎድሮስ ፈጣን የመንግስት ለውጥ አመጣለሁ በሚል እብደት ሀገሪቱን በደም አዋዥቋት ሲል 2013 ቢና አስረኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ባቀረበው

The Story of Ethiopian Jews,” በተሰኘው ጽሁፉ ገፅ 5 አንቀጽ 1 ላይ እንዲህ ይላል

“Once again, in 1847, a Jewish emperor, Tewodros II, appeared and begun to reunite and modernize Ethiopia. The Ethiopian Orthodox Church, especially the Egyptian Patriarch, would not recognize Tewodros as the legitimate Emperor of Ethiopia. First of all, Tewodros was born to a Jewish family in Quara. Secondly, he sought to separate church and state. Third, Tewodros wanted to introduce technological change in Ethiopia. The church was very backward in its thinking and could not reconcile technological changes with religious faith. It saw Tewodros’s attempt at introducing technology as an act of blasphemy. Fourth, Tewodros wanted to educate the masses. The church resisted this because it saw education of the masses as a threat against church doctrines and its control of the populace. There were many church-instigated uprisings and bloodshed in several parts of the kingdom”

ሲተረጎም
1847 ቴዎድሮስ የሚባል አይሁዳዊ ንጉስ ኢትዮጵያን ሊያዘምን እና አንድ ሊያደርግ ተነሳ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተለይ የግብጹ ጳጳስ የቴዎድሮስን ንግስና እውቅና መስጠት አልፈለጉም። ምክንያቱም በመጀመሪያ ቴዎድሮስ የተገኘው ቋራ ከሚኖሩ የአይሁድ ቤተሰብ ነው፤ሁለተኛ ቤተክርስቲያንን ከመንግስት መለየት ይፈልግ ነበር፤ ሶስተኛ ቴዎድሮስ ቴክኖሎጂን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ይፈልግ ነበር ግን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአስተሳሰቧ በጣም ኋላ ቀር እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከእምነቱ ጋር ማጣጣም የማትችል በመሆኑ ቴዎድሮስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማስተዋወቅ ያደረገውን ጥረት ቤተክርስቲያኗ እንደ ክሂዶተ-እግዚአብሔር መመልከቷ፤ አራተኛ ቴዎድሮስ ብዙሃኑን ለማስተማር ፍላጎት ማሳየቱ እና ቤተክርስቲያኗ ይህንን ለዶግማዋ እንደ አንድ አደጋ በመውሰዷ እና በህዝቡ ላይ የነበራትን ስልጣን አደጋ ውስጥ ይከታል ከሚል ስጋት ነበር። በዚህም ቤተክርስቲያኗ የቀሰቀሰችው አመጽ እና ደም መፋሰስ በተለያዩ ግዛቶች ተፈጽሟል።

ከላይ ኢሳት ለሚባለው በእርጥባን ለሚተዳደረው የቁጭ በሉዎች የወሬ ቋት ቴዎድሮስ ለውጥን በፍጥነት አመጣለሁ ብለው ሀገሪቱን በደም አጠቧት ይል እና ለአይሁዶቹ ደግሞ አማራዊውን ንጉስ የአይሁድነት ካባ ደርቦለት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቴዎድሮስ አይሁዳዊ ስለሆነ ገና ከመጀመሪያው ልትቀበለው አልወደደችም ይላል።

በሌላ በኩል ቋንቋን ከነ ሰዋሰው፣ዜማን ከነአገባቡ፣ቅኔን ከነአቋቋሙ፣ስነ ፈለክን ከቀን አቆጣጠር፣መጽሐፈ ሄኖክን ከመጽሐፈ ጥበብ፣ ኦሪትን ከብሉይ አስማምታ አይሁዱንም ሙስሊሙንም ቤቴ ቤታችሁ ብላ የኖረችውን ያቺን ስንዱ እመቤት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነው እንግዲህ ማንም አያየኝም በሚል ወገኖቼ ለሚላቸው አይሁዶች በዚህ መልኩ የሚያማት። ለማንኛውም ዮሐንስ በቢና (BINA) ድረ ገጽ ላይ የጻፈውን ሙሉ ጽሁፍ ለማስረጃነት ታዩት ዘንድ በሚከተለው አድራሻ ታገኙታላችሁ;

http://www.binacf.org…/The%20Story%20of%20the%20Ethiopian%…

ለማንኛውም ለአማራዊ ወገናችን እንዲህ ልንልህ እንወዳለን። ማንም ተነስቶእኔም አማራ ነኝ ግን…..” ብሎ አማራን እና አማራዊ የሆነውን ባህልህን እና እሴትህን የሚሰድብ እና የሚያንቋሽሽ ከሆነ እሱ አማራ አይደለም።ተጠራጠር!!!ተጠራጥረህም ዝም አትበል እውነቱን ፈልግ ያን ጊዜ ያጠለቃት ለምድ ስትወልቅ ተኩላነቱን ትደርስበታለህ።

የመጨረሻው ለምድ ሲገፈፍ- ዮሐንስ የወያኔ አማካሪ ነው!!!

አይጋ ፎረም የተባለው የወያኔ ድረ ገፅ በዲሴምበር 2014 ባወጣው ዘገባ መሰረት የኔሽናል ቱር አሶሴሽን አባል የሆኑ ጋዜጠኞች፣አስጎብኚዎች እና በዚህ ሙያ የተሰማሩ ሰዎች ከአሜሪካ ተነስተው ለአስር ቀናት የሚቆይ ጉብኝት እንዳደረጉ እና የኢየሩሳሌም የጉዞ እና የትራንስፖርት ድርጅት ባለቤት የሆነው ዮሐንስ ዘለቀ አብሮ እንደነበር ያትታል።

http://aigaforum.com/…/Ethiopia-Tourism-NTA-Magazine-Dec201…

ነገር ግን አይጋ ሊነግረን ያልወደደውን አንድ ሀቅ ራሱ ዮሐንስ በቅርብ ባቋቋመው እና አፍሪካን ሌጀንድ ቱርስ /african legend tours/በሚል የድርጅቱ ድረ ገፅ ላይ

https://www.africanlegendtours.com/other-services
እንዳስቀመጠው በጄንዋሪ 24-2012 .. ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ የወያኔ ትግሬ አምባሳደር የነበረው ግርማ ብሩ በኤምባሲው የኢትዮጵያ የቱሪዝም የአማካሪዎችን ቦርድ የሰበሰበ ሲሆን ከነዚህ የአማካሪ ቦርድ አባላት መካከል ዮሐንስ ዘለቀ አንዱ ሲሆን ፌብሯሪ 14 2012 . ይፋ የተደረገውን የስራ ዕቅድንም /Action Plan / በዋናነት ያዘጋጀውም እሱው ነበር።

በስራ ዕቅዱ ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው በአሜሪካን ሀገር የሀገሪቱን ገፅታ መገንባት፣ አሜሪካን ከሚገኙ ልክ የሱ ድርጅት አይነት አስጎብኚ ድርጅቶች እና ዛሬ ላይ በትግሬዎች በበላይነት በተያዙ ኢትዮጵያ ባሉ አስጎብኚ ድርጅቶች መካከል የቢዝነስ ትስስሮችን መፍጠር እና መሰል ተግባራት ላይ ያጠነጥናል።

በዚህም መሰረት በኤፕሪል 9-2013 . ኤምባሲው ባዘጋጀው የቢዝነስ ትውውቅ ላይ ከኢትዮጵያ የተጋበዙ 14 የትግሬ ድርጅቶች ተሳታፊ ሲሆኑ ትግራይ ኦንላይ የተባለው የትግሬ ድረ-ገፅ


ሁኔታውን በዚህ መልኩ ነበር የገለፀው

“A “Business to Business Meeting” designed at bolstering Ethiopian Tourism Market in the US and engage American Tour Operators with their Ethiopian counter-parts was held at the premises of the Ethiopian Embassy here today, a press release obtained from the Embassy stated. The event is seen as an ideal venue for creating the necessary enabling conducive environment for networking of enterprises deployed in the hospitality industries of the two countries, according to the press release.

በሌላ በኩል አፍሪካን ቱር አሶሴሽን ስለዚሁ ስብሰባ በድረ-ገጹ [http://www.africa-ata.org/texas2.htm] ግርማ ብሩ፣ የባህል ሚንስቴር ምንስትሯ ታደለች ዳነቾ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ /2012 ጀምሮ ደግሞ የቱሪዝም አማካሪዎች ቦርድ አባል የሆነው/ ዮሐንስ ዘለቀ ንግግር አቅራቢዎች እንደነበሩ ያትታል።

በሌላም በኩል በሴፕቴምበር 2016 በአሜሪካ የወያኔ ኤምባሲ በድረ ገጹ

http://www.ethiopianembassy.org…/NewsletterSeptember2016.p…

 ባወጣው ዘገባ መሰረት በኦገስት 30-2016 የወያኔ ትግሬ ኤምባሲ ገጽታውን ለመገንባት በማሰብ የሀርቫርድ እና የማሳቹሴትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ክለብ አባላትን በመሰብሰብ ስለሀገሪቱ ሲደሰኩሩ ከነበሩት እና ሀገሪቱተለውጣለች፤መጥታችሁ ጎብኙንእያለ ሲያላዝን የነበረው ዮሐንስ ዘለቀ አንዱ ነው። አዎ ዮሐንስ ስጥ የወያኔ ትግሬው አማካሪ፣ ሁለት ልጆች የወለደችለት ሴት በዚህ ውሸታም ባህርይው ምክንያት በአይኔ ላይህ አልፈልግም ብላ ወደ ሚንሶታ ጥላው የሄደችው፣ ትናንት በዌል ፌር ይኖርበት በነበረበት ቤት ዛሬም በዚያ የሚኖረው ዮሐንስ ዘለቀ። እነሆ ታዩት ዘንድ የኢሳት ታላቅ ወንድም የሆነው የወያኔው ኢቢሲ ወይም የድሮው ኢቲቪ የኦገስት 30-2016ቱን የነዮሐንስን ንግግር ከታች በምታዩት ቪድዮ ላይ በምታዩት መልኩ ነበር ያቀረበው።

በመጨረሻም ለአማራዊው አንድ ነገር ልንል ወደድን። ደግመን ደጋግመን በዘመናት እንዳየነው ከእኛ ውጪ ለእኛ ማንም ሊሆነን አልያም ሊታደገን እንደማይችል የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ብቻ በቂ ምስክር ነው። ስለሆነም ለአማራ ህዝብ ትግል እና የመጨረሻ ግባችን ለሆነው ግዮናዊውን አባት ሀገር ለመመስረት የሚዲያ ሚና የማይተካ እና ለነገ የማይባል ነው።

ይህንን በልቦናህ ካኖርክ ዘንድ የራሳችንን የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ በንቃት እንድትሳተፍ፣ በማንነትህ እና በዘርህ ላይ ጥላቻን በሚዘሩ ላይ ጀርባህን በመስጠት ባንተው ኪስ በሁለት እግራቸው እንዳቆምካቸው ሁሉ ኪስህን በማጥበቅ እና የሸፍጥ ሴራቸውን በማጋለጥ እንድታንበረክካቸው ልናሳስብህ እንወዳለን።