የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በእኔ ዕይታ
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
Ethiopian
Semay
9/2/26
ቲክቶክን ጨምሮ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ ከመከታተልና አልፎ አልፎም በአስተያየት መስጫዎች ከመሣተፍ ባለፈ ለበርካታ ወራት ከመጣጥፍ አስተዋፅዖ ተቆጥቤ ቆይቻለሁ - የሚገርመው “ያ ሰው ወዴት ጠፋ?” ብሎ አንድስ እንኳ የጠየቀ የለም፡፡ ይህም በራሱ አለመታደል ነው፡፡ ምን አዚም እንደወደቀብን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ የሚያጨካክንና ከዚያም ባለፈ እርስ በርስ እንደበግ የሚያስተራርድ ድግምትማ ተደግሞብናል፡፡ ለነገሩ እንኳንስ በወረቀት ለጮኸ ለሀገርና ለሕዝብ ነፃነት ትግል ደረቱንና ግምባሩን የሰጠ ሰማዕትም በማይታወስባትና ቤተሰቡ በርሀብና በዕርዛት በሚማቅቅባት የአይሞቄ-አይበርዴዎች ምድር እኔ ያነሳሁትን ነጥብ ማንሳትና አጥጋቢ መልስም መጠበቅ ቅንጦት ነው፡፡ አብዛኛው ሰው የተቀፈደደው “ሀ ራስህን አድን” በሚለው የፈሪዎች መርኅ ነው፡፡ ስንቶች ጭዳ ሆነው ቤተሰባቸው ተበትኗል፤ በብዙ ነገር ተሰቃይቷል፡፡ በቃችሁ ካላለን መፃኢ ሁኔታችን ከአሁኑም በእጅጉ አሳሳቢ ነው፡፡
ሀገራችን
ከድጥ ወደማጥ እየተንከባለለች መጥታ ዛሬ ላይ ደርሳለች - ነሐሴ ወር መጨረሻ አካባቢ 2018 ኢ.አ ማለትም ዓ.ሂ … የዘመን አቆጣጠሩም
እንደጊዜው ተወነባበደብኝ - ለማንኛውም ዓመተ ምሕረት ማለቴ ነው፡፡ (ኦህዲዳችን የሰጠንን አዲሱን የቀን መቁጠሪያ በሾርኒ ማስተዋወቄ
እኮ ነው፡- ኢ.አ - እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር፤ ዓ.ሂ - ዓመተ ሂጅራ የሚሉ አማራጮችን በምክክር ኮሚሽን ተብዬው አጸድቀዋል አሉ፡፡)
ኢትዮጵያ አሁን የተናጋሪ እንስሳት ማጎሪያ ሆናለች፡፡ ግሩም ጭራቅ መሪ ተሰጥቶናል፡፡ አቢይ ባይኖር ምን ይውጠን ነበር? በሀገራችን
የተቸገረው አንድ ሰው ብቻ እስኪመስልና የመቶ ሚሊዮኖች ችግርና ብሶት በአንድ ሰው ሰላማዊ ሰልፍ እስኪወከል ድረስ ዝምታችን መጽናቱ
ግን እጅግ አስደንጋጭ ነው፡፡ የቁም ሞት ከዚህ በላይ የለም፡፡
አለሁ ለማለት ያህል እንግዲህ ከዚህም ከዚያም አንዳንድ ነጥቦችን ላንሳ፡፡ በርዕሴ ላይ ያለውን ላስቀድም፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን ኦነግ/ኦህዲድ የሚባል የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐውሬ የኢትዮጵያን መናገሻ አዲስ አበባንና መላውን የሀገሪቱን ሀብት ንብረት ተቆጣጥሮ የምዕተ ዓመታት ቅዠቱን እውን ሊያደርግ ጫፍ ላይ የደረሰበት ዘመን ነው፡፡ ስለዚህን ዓይነቱ አደጋ ብዙዎቻችን ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ ብንለፈልፍም ታይታኒካውያን ኢትዮጵያውያን ግን ከጭፈራቸውና ከዳንኪራቸው ቆም ብለው ሊሰሙ አልቻሉም፡፡ በኦሮሙማና ቅጥረኞቹ አማካይነት አማራ አንገቱ በሠይፍ እየተቀላ ሀብት ንብረቱ ደግሞ በዘረፋ እየተቀማና በእሳት እየጋዬ ባለበት በዚህ የሰቆቃ ዘመን ደስታን ቀነስ ጸሎትን ጨመር እንደማድረግ “ጎጃሞች ዘነጡ” በሚል ዘፈን በአረግራጊ መኪና አደባባይ ወጥቶ ጮቤ መርገጥ በርግጥም የኛን የኢትዮጵያውያንን ሥነ ተፈጥሮ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፤ አንጎላችን መፈተሸ አለበት፡፡ የተነገረውና የተባለው ሁሉ እውነት ሆኖ መርከቢቷ ልትሰምጥ ወይም በአንዳች ተዓምር ልትተርፍ የመጨረሻ ቅጽበት ላይ ትገኛለች፡፡ ያ ቅዠታም አክራሪ ኦሮሙማ ከ500 ዓመታት በኋላ ቤተ መንግሥቱን ማን ሰጠው ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀደም ሲል በመለስ ዜናዊና እርሱ ካለፈ በኋላ ደግሞ በሙት መንፈሱ የሚመራው ሕወሓት የተባለ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል መሆኑን እንረዳለን፡፡
አዎ፣ ለጥፋት የተፈጠረ ከጥፋት ውጪ አይጠበቅበትም፡፡ ለምሣሌ እሳት
የተፈጠረው ለማቃጠል … ምግብ ለማብሰል… ብርድን ለማጥፋት ነው፡፡ ከዚህ ተፈጥሮው እንዲያፈነግጥና የውኃ ጥማችንን እንዲቆርጥ ልናደርግ
ብንሞክር የእሳትን ተፈጥሮ ካለመረዳት የሚመነጭ ሞኝነት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ሕወሓት በማኒፌስቶው ጭምር በድፍረትና በማንአለብኝነት
ያሠፈረውን አማራንና ኦርቶዶክስን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዓላማና ግብ ሰርዞ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን መመኘት የቂልነቶች ሁሉ ቁንጮ መሆን
አለበት - እርግጥ ነው ለውጥ አለ፤ ለለውጥ የሚገዛ አካል ግን ያስታውቃል፤ ሕወሓት ለውጥን ራሷን ቢያገኛት አይለቃትም - በጥይት
ይደፋታል፡፡ እኔ የምለው ታዲያ አክራሪውን ሕወሓትን ነው፡፡ እኔ በዚህ መልክ አምርሬ የማነሳው የኢትዮጵያ መሠረት የሆነውን የትግራይን
ሕዝብ በፀረ-አማራነትና በፀረ-ኢትዮጵያነት የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ አእምሮውን በርዞ ከልሶ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራውን እንዲረግጥና
እንዲያቃጥል፣ ኢትዮያዊነትንም አምርሮ እንዲጠላ ያደረገውን የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጠባብ ቡድንን ነው፡፡
ኢትዮጵያን
ያህል ሰፊ ሀገር ተቆጣጥሮ እየገዛ ባለበት በዚያን የ27 ዓመታት የመንግሥትነት ዘመኑ እንኳን ከትግራይ ነጻ አውጪነት ስሙ ሊላቀቅ
ያልፈቀደ የልዩ አጋንንታዊ ተፈጥሮ ሰለባ ነው፡፡ ይህ ቡድን ጥቂት ግለሰቦችን ብቻ ይዞ ቢጠፋ ዕዳው ቀላል ነበር፡፡ ነገር ግን
ከሞላ ጎደል የመላውን ትግራይ ሕዝብ አበከተው፤ ለማያባራ መከራም ዳረገው፡፡ እልኸኛና ሰይጣን የሆነ ሰው ዓላማው ከሚኮላሽ ዓለም
ብትጠፋ ደስታው ነው፡፡ ሕወሓትን ጤናማ አስተሳሰብ እንዲኖረው መምከርም ሆነ መመኘት ፍሬቢስ ነው፡፡ ለብዙ አሠርት ዓመታት አየነው፤
በተስፋም ጠበቅነው፤ እውነቱ ግን ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡ አዲስ ትውልድ መጥቶ ነባሩን ካልተካና ዘረኝነት ከትግራይ ካልተወገደ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ባመጣው ጣጣ ሲባላ መኖሩ ሊካድ አይገባም፡፡
ይህ ቡድን እስካለ ድረስ ኢትዮጵያም አማራም ኦርቶዶክስም ከመጥፋት የሚያድናቸው አንድም ኃይል የለም፡፡ ለ500 ዓመታት ያህል ውስጥ ውስጡን ሲያደባ የነበረው ዐውሬው ኦሮሙማ ኢትዮጵያን የመዋጥና የሚቃዥበትን የታላቋ ኦሮምያ ኢምፓየር ምሥረታ የተቃረበውም በዚህ ሕወሓት በሚባል ቡድን አማካይነት ነው - እርግጥ ነው ኦሮምያን የመመሥረት ሤራ ገሃድ ወጥቶ ሥራ ላይ መዋል የጀመረው ከደርግ ዘመን መባቻ ወዲህ መሆኑ ብዙ መረጃዎችና ማስረጃዎች አሉ፡፡ ለኦሮሙማ መንሰራፋትም ሆነ ለኢትዮጵያ ውድቀት የአማራ ጅልነትና በዋል ፈሰስነትም ቀላል ሚና አልተጫወተም፡፡ አማራን ማታለል ከምንም ነገር በላይ ቀላል ነው፡፡ ገንዘብ፣ ሴት፣ መጠጥ፣ ጨዋታና ድልቂያ ካገኘ አብዛኛው አማራ የማይተውልህ ነገር አታገኝም፡፡ አማራ “ኢትዮያ ኢትዮጵያ” ካልክለት በቂው ነው፡፡ ኢትዮጵያን እስከጠራህለት ድረስ ዝንጀሮም አራት ኪሎ ቢገባ ጉዳዩ አይደለም፡፡ በብዛቱ አይኮራ፤ በሥልጣኔው አይመጻደቅ፤ በምልዓቱ አይጀነን፤ … ምሥኪን ግን ምሥኪንነቱ ክፉኛ የሚያስደፍረውና የሚያስጠቃው ሕዝብ ነው አማራ፡፡ ተባብሮ ቢነሣ እኮ እንኳን ለኢትዮጵያ ለአፍሪካም የሚበቃ ብዙ ነገርና እምቅ ኃይል አለው፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው - የት ይደርሳል ያሉት ጥጃ ማረፊያው ሉካንዳ ቤት ሆነና አማራን ያህል ታላቅ ሕዝብ እዚህ ግባ በማይባል የበሻሻ ጩልሌ ጉድ ተሠራ፡፡ የአማራ አፈጣጠር ግን በርግጥም ይገርማል … አምስት ቀጣፊ ሆነህ አንድ ሺውን አማራ እንደከብት ልትነዳው ትችላለህ፡፡ አንድ እረኛ አሥር ሺህ በጎችን እንደሚነዳው ማለት ነው፡፡ እቅጭ እቅጩን ነው የምናገረው፤ መንቆለጳጰስ አይጠቅምም፡፡ እንዲህ ባይሆን ኖሮ የአማራን ዘር ለማጥፋት የሚደፍር ግልጽና ድብቅ ኃይል ባልተፈጠረ፤ ኢትዮጵያም ኅልውናዋ ሊከስም ጀምበሯ ባላዘቀዘቀ፡፡
እንጂ ሕወሓት ባይኖርና ትክክለኛ የትግራይ ኢትዮጵያዊ ቢኖርማ ኖሮ በአሁኑ ወቅት አማራ ትግሬ፣ ሳሆ ብሌን፣ አድዋ ተምቤን፣ ኦቆርዳት ተሰነይ፣ አሥመራ መቀሌ፣ ጎንደር ባሕር ዳር፣ ጎጃም ወሎ፣ ሸዋ ወለጋ … ሳይል መላውን የሰሜን ሕዝብ አርዶ ጨርሶ የዋቄ ፈታ ገዳ ሥርዓት ሊመሠርት አንድ ሐሙስ የቀረው ዐውሬ ኦሮሙማ አማራና ትግሬ በተገኘበት አንገቱ እየተቀላ፣ ሀብት ንብረቱ እየተዘረፈና እየተቃጠለ ባለበት ወቅት ወልቃይትና ሰቲት ሁመራ ላይ ሕወጣት ቀን ከሌት እያላዘነ የጋራ ትግልን ባላጓተተ ነበር፡፡ እንደኔ ወልቃይትና ራያን ማንም ቀቅሎ ሊበላቸው ይችላል፡፡ እነዚህ ቁርጥራጭ የግጦሽም ይሁኑ የሰብል መሬቶች ከ70 እና 80 ሚሊዮኑ የአማራና ትግሬ ሕይወት አይበልጡም፡፡ እዬዬም ሲደላ ነው ይባላል፡፡ የሰው ልጅ ከውሾች እንኳን መማር ካልቻለ ከንቱነት ነው፡፡ ውሾች በአንድ አጥንት እየተጣሉ ጅብን የመሰለ የጋራ ጠላት ቢመጣባቸው አጥንቱን ጥለው ያን የጋራ አጥፊ ይፋለማሉ፡፡ ትልቅ ዕውቀት ነው፡፡ አጥንቱ የት ይሄድባቸዋል? ሕወሓትነት ምን ያህል መረገም መሆኑን የምረዳው ከዚህ ነጥብ አኳያ ነው፡፡ ዋሸሁ?
በነገራችን ላይ አማራ እያደረገ ያለው ትግል ፍትኃዊ መሆኑን ማንም ይረዳዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ሆዳሙና ባንዳው እንዲሁም ለንግሥና የሚሻማው ጅላጅል አማራ በዝቶ ትግሉ በሚፈለገው ፍጥነት አልሄደም እንጂ “አትግደሉኝ ሀገር አታሳጡኝ” ብሎ የነፃነት ትግል ማካሄድ በሰማይም ሆነ በምድር ኩነኔም ወንጀልም አይደለም፡፡ ችግሩ የአማራ ተፈጥሮ ለዬት አለና አደናቃፊው በዛ፡፡ ባልተጨበጠ የአራት ኪሎ ወንበር ገና ከአሁኑ የሚራኮተውንና በሸርና በሤራ እየተጠላለፈ ከኩራዝና ፋኖስ ወጥቶ ሻል ያለች ከተማ እንኳን ሳያይ የሚረግፈውን የሰው ብዛት ስንሰማ በሰው ልጅ ሞኝነትና ከንቱነት እየሣቅን ባላስፈላጊ የኃይል ብክነቱ ግን እናለቅሳለን፡፡ አማራ ውስጣዊና ውጫዊ መሰናክሎች ባይኖሩበት ኖሮ ይሄኔ ኢትዮጵያ ከቡርኪና ፋሶ ይበልጥ በነፃነትና በምቾት በተንደላቀቀች ነበር፡፡ አንድ ወጣት ብቅ ብሎ ነው በዚያች ሀገር የዘመናት ብሶትንና ኋላ ቀርነትን በሦስት ዓመት ውስጥ ብቻ ጠራርጎ ቤት አጥነትንና ርሀብን ታሪክ ያደረገው፡፡ ከ24 ሚሊዮን ሕዝብ አንድ ትራኦሬ ሲገኝ ከ139 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል ደግሞ ሰይጣን የሚቀናበት አንድ አቢይ የሚባል አጭበርባሪ ሉጢ ተገኘና አሣራችንን ያበላናል፤ በጎሣና በነገድም ተከፋፍለን በማን አባት ገደል ገባ የሕጻናት ጨዋታ ተጠምደን አንዳችን ሌላኛችንን በሰላ ጎራዴና ሜንጫ ያስተራርደናል፡፡ ፊደል የቆጠረው ሁሉ ከእሱ ጋር ወይም ከእሱ በተቃራኒ በመሰለፍ ያልበላንን እያከከ በቃላት ጦርነት በመተጋተግ መቀመቅ ይከተናል፡፡ ምን ያልሆንነው አለ …
ጥሩ ጥሩ ትግሬዎች ካሉ ካለፈ መጥፎ ታሪክ ተምረው ከአማራ ጋር ቢተባበሩና ይህን ትግሬንና አማራን ካልጨረሰና ካላጨራረሰ ዕረፍት የሌለው ኦሮሙማ ቢገጥሙት ድላቸው የቀናት ግፋ ቢል የጥቂት ሣምንታት ጉዳይ ነው፡፡ የጋራ ገዳያቸው ከተወገደ በኋላ ደግሞ በሠለጠነ መንገድ ተነጋግረውና ተወያይተው አለን የሚሉትን ችግር ማስወገድ ይችላሉ፡፡ የካንሰርና የጉንፋን ህመሞች ያሉበት ሰው ቅድሚያ የሚሰጠው ለጉንፋኑ ሳይሆን ለካንሰሩ ነው፡፡ አሁን ባለው አስጠሊታ የፖለቲካ ሁኔታ ከአቢይ በቀር አሸናፊ የለም፡፡ የአቢይ እጅ ረጂም ነው፡፡
ከማሕጸን ጀምሮ ሲማር የነበረው ስለተንኮልና ሤራ ነው፡፡ ተፈጥሮው
ነው፤ ተልእኮውም - ማን እንደላከውና የማንን አጀንዳ ኢትዮጵያ ላይ እያስፈጸመ እንደሆነ እዚህ መናገሩ ጊዜ ማባከን ነው፤ በዋናነት
ግን ኢትዮጵያ ደህና መሪ እንዳታገኝ የውጪ ጣልቃ ገብነት ከዱሮ ጀምሮ መኖሩ መረሳት የለበትም፡፡ ከፍ ሲል ገልጫለሁ፡፡
አንድ ነገር ከተፈጠረበት ውጪ እንዲሆን መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ በፊት በፊት አቢይን እንቀው ነበር - በጣም፡፡ አሁን ግን በዓለማችን
ያለፈም ይሁን የወደፊት ታሪክ ማንም ሊስተካከለው በማይችለው ሰይጣናዊ ተፈጥሮው አደንቀዋለሁ፡፡
ዓላማውን ለማሣካትና ወንበሩን ላለማጣት የማይፈጽመው የሤራና የሸፍጥ ዓይነት የለም፡፡ እሱ አንድ ሰው በቻ አይደለም፡፡ አንዱ አቢይ ከሚሊዮንም ይበልጣል - ምንም የማይፎርሽ ልዩ አጋንንታዊ ተሰጥዖ አለው፡፡ አንድ ሰው ንቀህ ደግሞ የምታመጣው መፍትሔ የለም - ከነተረቱ “የናቁት ያደርጋል ራቁት” ነው - እየሆነ ያለውም ይሄው ነው፡፡
በስምንት ዓመታት ውስጥ የዋሸውን፣ ያስመሰለውን፣ የጨፈጨፈውንና ያስጨፈጨፈውን የሰው ብዛት፣ ያታለለውን፣ የቀላመደውን፣ በመሳም ወይም በመጨበጥና በማቀፍ ያበከተውን የምሁርና የታዋቂ ሰው ግትልትል … ስንመለከት የዚህ ሰው ተፈጥሮ ልዩ መሆኑን እንረዳለን (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም በሕይወት አለ ግን?)፡፡ በትምህርት ዜሮ፣ በወታደራዊ ሥልጠናና ግንዛቤ ዜሮ፣ በአይኪውና በመሳሰለው የዕውቀትና የችሎታ መለኪያ ዜሮ ሊሆን ቢችል እንኳን በተንኮልና በሸፍጥ፣ በክህደትና በጥላቻ፣ በአንዳች ነገር የጠረጠረውን ሁሉ በመግደልና በማዋረድ አንድም የሚስተካከለለው የለም፡፡ ታሪክ የሚያውቃቸው እነሂትለተርንና ሙሶሊኒን፣ እነጆሴፍ ስታሊንንና ፒኖሼን የመሰሉ ጨካኞች በጭካኔያቸው የአቢይን አንድ አሥረኛ አይሆኑም፡፡
እነዚያ ቢያንስ የማይገድሉት የማኅበረሰብ አባል ወይም ክፍል ነበራቸው፡፡ ይሉኝታና ርህራሄም ነበራቸው፡፡ አቢይ ግን የግል ጠንቋዩ ከጠቆመው ለምን ልጁን አይሆንም ይደፋታል፡፡ ሚስትና ውሽሞቹንም አይራራላቸውም ያርዳቸዋል፡፡ (የቴሌዋ ፍርዬ ግን ደህና ናት? አልደገመች(ለት)ም ይሆን?) አቢቹ በወንበሩ ቀልድ አያውቅም፤ እንቅልፍ አጥቶ ሲባዝን የሚያድረው ለማን ሆነና! ለዚህም ነው ባገኘሁት አዲስ የድረ ገፅ መረጃ መሠረት 139 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአቢይ ወንበር በጭዳነት ተዘጋጅቶ በየቀኑ ለመታረድ ዝግጁ የሆነው፡፡
ብዙ ሰሞነኛ ወሬዎች ነበሩ፡፡ የምክክር ኮሚሽኑ ማለቂያ፣ የነሐሴን ወር ጠብቆ የአቢይ መጥፋት፣ የእስክንድር ነጋ የቢቢሲ ንግግር፣ የአዲስ አበባ ወደኦህዲድ ግዛት መግባት፣ ኦህዲድ ጋር ተሰልፈው አማራን ስለሚያጠፉ ሆዳም አማሮች ወዘተ. ብዙ መናገር በተቻለ፡፡ ሳልጠቁም ማለፍ የማፈልገው ግን አዲስ አበባ ወደዚህ ወደዚያ ተካለለች የሚሉት የቂሎች ፈሊጥ ነው፡፡ ስለዚህ ነገር ሲንጨረጨሩ ሳይ ይገርመኛል፡፡ ሽንት ቤት ተቀምጦ ፈስ ገማኝ ይባላል? አይባልም፡፡ እያንዳንዱ የአገዛዝ ዘመን ሲመጣ የመሰለውን ሁሉ ያውጃል፡፡ ሲገለበጥ ደግሞ መጪው አገዛዝ የነበረውን እንዳልበር ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ኦህዲድ አዲስ አበባን ወደ ኦሮሙማ በህግ ሰበብ ወሰዳት ብሎ መንጨርጨርን ምን አመጣው? አሁንስ የማን ሆነችና ነው? አዲስ አበባ ውስጥ አሁን አማራና ትግሬ የሚረባ ሥልጣን አላቸው? የላቸውም፡፡ የመንግሥት ቢሮ ሁሉ የተሞላው በማን ሆነና ነው? ስለዚህ ስለነገ ራሱ ይጨነቃልና አትድከሙ፡፡ ቀድሞ የመቀመጫየን ብላለች ዝንጀሮ፡፡ ዛሬን በደህና ባደርን - ነገን ተውትና፡፡ ለአሥር ሺህ ብር ገቢህ ከገቢዎች የተላከ ደቻሣ ፈይሣ 100 ሺህ ብር እንድትከፍል እያስገደደህ አንተ አዲስ አበባን ወሰዱ ትላለህ፡፡ ቢወስዳት ቢወስዳት ባሌን አሳልፎ ኬንያና ማዳጋስካር አይወስዳት፡፡ ዋናው ትኩረት መሆን ያለበት ነቀርሣን ማስወገድ ነው፡፡ ከዚያ ጤናማነት ይመለሳል፡፡
መጻፍ ሳልጀምር ቦታ አለቀብኝና መጻፌን ላቆም ነው፡፡ ለማንቻውም የተመረጡ ይመጣሉ፤ በጸሎትና በቻልነው ሁሉ እናግዛቸው፡፡ እነሱ በደም ሲዋጁን እኛ በስንቅና በትጥቅ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል፡፡ በዚህ ሥርዓት በተለይ በዘር ሐረጋችሁ ምክንያት የምትንገላቱና ሀብት ንብረታችሁን የምትቀሙ ወገኖች ማስረጃችሁን በጥንቃቄ ያዙ፡፡ ትክክለኛ የፍትኅ ሚዛን አደባባይ የምትወጣበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርምና ተስፋ ቆርጦ ማስረጃውን የትም የሚጥል ሰው እንዳይኖር ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ የሚመጣው መንግሥት ጆሮና ዐይን እንደሚኖረው ተስፋ እናደርጋለንና ፍትኅን እንደሚያሰፍን በበኩሌ አምናለሁ፤ የተበደለን የሚክስ - የተጣላን የሚያስታርቅ - የወደቀን የሚያነሣ ትክክለኛ መንግሥት ይመጣል ብዬ እጠብቃለሁ፡፡ ሁሉ ነገር እንዳለ አይቀጥልም፡፡ በቦሌም ይሁን በባሌ የሚመጣ መልካም ነገር እንደሚኖር ይሰማኛል፤ ሁሉም ነገር በወያኔና በልጁ ኦህዲድ እንደተጨመላለቀና እንደበከተ አይቀጥልም፡፡ ፖለቲካውም ሃይማኖቱም ባህልና ወግ ሥራቱም በቅርቡ በአንድዬ ይጎበኛል የሚል ጽኑ ተስፋ አለኝ፡፡
መልካም ትግሬዎች ታሪክ ሥሩ፡፡ ሆዳም አማሮች ተመለሱ፡፡ ለእናንተ ሳይሆን ለትውልዳችሁም አስቡ፡፡ ተጸጽቶ ከጥፋት
መመለስ አያሳፍርም፤ ትልቅነት ነው፡፡ መጥፎው ነገር በካፈርኩ አይመልሰኝ መምጣቱ የማይቀርን ነገር ለማገድ መንደፋደፍ ነው፡፡ ከሁሉም
ከሁሉም ማንንም ላሳስብ የምወደው ለአንደበታችን ልጓም እናብጅለት፡፡ ከጥይት ይልቅ አንደበት ይበልጥ ያደማል፤ ያቆስላል፡፡ አማራ
ላይ ስድ አፋችሁን የምትከፍቱ ወገኖች ወደራሳችሁ ተመለሱ፡፡ ትግሬዎች አማራን እንድትጠሉ ያደረገውን የቆዬውን የወያኔ የጥላቻ ስብከት
እርሱት፡፡ አማራ ወንድማችሁ እንጂ ጠላታችሁ አይደለም፡፡ ካልተባበራችሁ በኔ ግምት በሁለትና በሦስት ዓመታት ውስጥ ሁለታችሁም ትጠፋላችሁ
- ምላሤ ጥቁር ነው፡፡ ግን ግን ሌላ ትንቢትም አለ፡፡ ብናገር ያሳንፋችኋልና ይቅርብኝ፡፡ በሌላም በኩል ያንን ትንቢት ብናገር
ኦሮሞ ወዳጆቼን ማስከፋት ይሆንብኛል፡፡ የተዘራው ሁሉ ሲታጨድ ኦሮሞ ያሳዝነኛል፡፡ ኢትዮጵያ ነገረኛና ሸረኛ ሀገር ናት - ወዳጆቿን
አትክስም፤ አትጠቅምምም፡፡ ጠላቶቿን ግን አወፍራና አስብታ ስታበቃ በመጨረሻ ባላሰቡበት ሰዓት እገቡበት ገብታ እንደ እንቧይ አንስታ
ታፈርጣቸዋለች፡፡ ይህን ከራሴ በላይ አውቃለሁ፡፡ ቀኑን ጠብቅ፡፡ “ዕድሜ ስጠኝ” ብለህ ጸልይ እንድታየው ከፈለግህ - አዲስ ነገር
አልነገርኩህም፤ የዐዋጁን በጆሮ ዓይነት ነው፡፡ ሰላም፡፡