Wednesday, November 30, 2011
ሰንደቃላማችን በስያትል ባንዳዎች ለድርድር ቀረበ!
Monday, November 21, 2011
ውሸታሞቹን ስንት ጊዜ ይማራችሁ እንበላቸው?
There is no point of me to expose TPLF when it insult the Amhara population, and not fair if I shut my mouth when journalists conspired with racist individuals to insult Tigrayan population to be insulted. We have all kind of enemies inside us, masquerading as political opposition and opposition media.
http://ethioforum.org/?p=9025#comments
To see the page/font with a wider range, please press the key Ctrl and + sign. To view the page/font with a narrow range, please press the key CTRL and _ sign.
ብርሃኑ ነጋ
አረጋዊ በርሔን/እና ሁለቱ የሻዕቢያ መንግሥት በVolunatry/በጐ ፈቃደኝነት ለሻዕቢያ ስራ አስፈጻሚነት ደጀ ጠኚዎች (ግንቦት7 እና ኦነግን) የጨመረ የስያትል ስብሰባ ከተካኼደ በኋላ “በኢትዮ-ሚዲያ” ድረገጽ ላይ ከስያትል ከአንድ “ግዕዝ ተናጋሪ” ኦነግ የተለፈፈው የውሸት ዕልልታ ጽሑፍ ጨምሮ ኢትዮ-ሚዲያ አዘጋጅ አብርሃ በላይ የለጠፈውና ያጋነነው ደማቅ ውሸት እንዲሀም እራሱ የኦነግ ጸሐፊ ነኝ የሚል “አሚን ጃንዳይ” ያስተላለፈውን ሃሰት ሁሉ እንመለክታለን።ወይ ትጉዱ! ይኼ ትግሬ ደግሞ ምን አመጣብን እንዳትሉ “የፊልድ መርሻሉ”ንግግርን ነው የማስደምጣችሁ። አትቸኩሉብኝ የፈጠራ አይደለም።
እሰኪ እዩት ይህ ቅዠት ምን ይባላል? ኦነግ በዓለም ውስጥ ያልታየ አገራዊ ምስረታ “ፌርማ” የሚለው ከየት አንዳመጣው አይገርማችሁም። አሜሪካ እንግሊዝ ጣሊያን ሩሲያ ቻይና….ሀሉም እየተፋጀ እየተጋባ እየተገበያየ ነው አገር የመሰረተው በፌርማ እንዳልሆነ እየታወቀ።ኦነግ በዚህ በተመራመረ ዘመን “አገርን” የሚያክል የፈጣሪ ትልቅ አገራዊ ምስጢር እረስቶት ልክ እንደ ባልና ሚስት “ በጋብቻ ፌርማ” አገር እንደማይቀና እና እንደማይመሳሰል እየታወቀ ኢትዮጵያ ስትመሰረት “የቤት ህንፃ” ይመስል ‘ፌርማ” ሚባል ነገር አልነበረም; ካለ ደግሞ አሳዩን ሲለን “ኦነግ” በግብዝ መሪዎች የተሞላ ብቻ ሳይሆን ድርጅቱ ጭራሽኑ የባሰበት በሽተኛ መሆነን ተረዱልኝ።
ትዝ ይላችኋል የድሮው የዶክተር በየነ ጴጥሮስ የሕዝብ ግንኙነት የዛሬው የግንቦቱ የሕዝብ ግንኙነት አቶ ኤፈሬም ማዴቦ የተባለው ሰው ስለ ኦሮሞ ነጻ አውጪ ትርጉም ሲነግረን? በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር እና የኦሮሞ ነፃነት ግምባር ልዩነት የማይገባቸው ደንቆሮዎች አሉ፡ብሎናል ኤፍሬም ማዴቦ የቃላት ስንጠቃ ውስጥ ሲገባ። እንደ እኔ የገረመው ወዳጄ አቶ ጊዜው ደረሰ “አዘለም አሉ አቀፈ ሁሉም ተሸከመ ነው” ብሎ የአማርኛውን አጠቃቀም ዘይቤ አስተማረው። ልክ አንዳርጋቸው ጽጌ የጻፈው ዘረኛው “የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት” ስለሚለው መጽሐፉ ተጠይቆ ዘረኛ መጽሐፍ መሆኑን ለመሸፋፈን ሲመክር “መጽሐፍም ነው ለማለት አይቻልም። ያው ትንሽ ገጽ ያላት መጽሐፍ ብጤ ነች….” ይላል። ሰዎቹ ጥፋታቸውን ላለማረም ይቅርታ ተሳስተናል ማለት ዳግቷቸው ላለማመን እንዴት እንዴት ዙርያ ጥምጥም ዳር ዳሩን እንደሚሸሹ ማየት ያሳዝናል።“አንተ ነጋዴ እያላችሁ ለምን ትሳደባለችሁ ገበያ ከደመቀ ምን ደኅና አለ።” መጽሐፈ ጨዋታ ገጽ 20 (አሁንም ወዳጄ የላከልኝ ግሩም መጽሐፍ ካገኘሁት)::
“ ስለዚህ የኦሮሞ ጥያቄ አሳንሶ ወደ መገንጠል ጥያቄ ለመውሰድ የሚፈልጉ ቡድኖች ወይንም ሕዝቦች የኦሮሞን ሕዝብ ችግር መፍትሔ ላለመስጠት የተደረገ መከራ/ዱለታ ነው እንጂ የኦሮሞ ነፃ አውጪ የኦሮሞ ሕዝብ (ኦሮሚያ ሪፐብሊክ የሚባል አገር ለመመስረት እታገላለሁ ብሎ አያውቅም) ይገንጠል ብሎ አንድም ቀንም አልተናገረም የጻፉትም እስከነመረጃቸው መምጣት ይችላሉ።” ይላል አሚን ጀንዳይ (የኦሮሞ ነፃ አውጪ ዋና ጸሐፊ/ “የኦሮሞ ነፃነት ግምባር” ብየ በአቶ ኤፍሬም ማዴቦ አጠራር ልጠቀም 'እንዳይቆጣ') ልብ በሉ። የኦነግ ጥያቄ የመገንጠል ጥያቄ መሆኑን ባንዴራው እያውለበለበ 40 ዓመት የዋሸውን ውሸት ግጥም አድርጐ ክዷል።ይህ አባባል ፖለቲካውን ያልገባቸው እና የኦነግ ውሸታም እና ዳር ዳር ሩጫ ባሕሪ ያላወቁ ሰዎች “መገንጠል ጠይቆ አያውቅም” ሲላችሁ ኦሮሞዎች የሚኖሩት በተፈጠሩበት ስታብሊሽድ በሆነው “ኦሮሚያ ሪፑብሊክ” በምትባለዋ ኦሮሞ የሚባል ሰው ሁሉ የትም ይኑር የትም በሚኖርበት አገርና ቦታ ሲፈጠር የኖረበት ስለሆነ ከየት ነው የምንገነጠለው እያለው ያለውን አበክራችሁ መመለከት ያስፈልጋል። ስለዚህ የምንገነጠለው ከየት ነው? የሚለው አባባሉ ይግባችሁ። የሚገነጣጠሉት በኦሮሞ መሬት /ድምበር “ዙርያ የከበቡትን ጎሳዎች ባዲሲቷ ሪፑብሊክ ስፋት/ስታብሊሽመንት የሚጋረዱት ናቸው እንዳይገናኙ የሚጋረዱት/የሚገነጣጠሉት እንጂ ትልቁ ሰፊው አሮሚያ አይደለም የሚገነጠለው/ የሚጋረደው ማለቱ ነው (ከሁሉም ጋር መገናኘት ይችላል ማለቱ ነው)። ይኼ በጣም ወንጀል ነው።
ከወራት በፊት የአርሊነግተን ስብሰባ ውስጥ ብርሃኑ ነጋ እና አዲሱ “የኦነግ ጸናጽል” ደ/ር ጌታቸው በጋሻው ሆነው ስለ ኦነግ ማንነት ሲዋሹን፡ ዜግነቴ ኦሮሞ ነው የሚል አንድ ወጣት “ዕድሜ ለኦነግ “ኦሮሞ ነኝ” ብየ እዚህ አዳራሽ ውስጥ ቆሜ ደፍሬ እንድናገር ስላደረገኝ ኦነግ ምስጋና ይግባውና “ቅንጅት” አንድ ባሕል ፤አንድ ሃይማኖት፤ አንድ ቋንቋ፤አንድ አገር የሚለውን አጀንዳው አሁን ደግሞ ግንቦት 7 በፕሮግራሙ ሊደግመው ይሆን? ይህን በሚመለከት ምንድነው አቋማችሁ?” ብሎ ብርሃኑን የጠየቀው ትዝ አለኝ::
(የኦነግ አባሎች እንዴት በውሸት ቅስቀሳ እንደሚወናበዱ ለማሳየት ምሳሌ ልስጣችሁ ብየ ነው)።
ጠያቂው እንዲህ ብሎ ሲጠይቅ፡ ብርሃኑ ነጋ አንጀቴን ያኔ አራሰኝ (ከዚያ ሁለ የብርሃኑ ነጋ ሙጃና አራሙቻ የሞላው አቅማዳ ውሸቱ ማለቴ ነው)። ብርሃኑ ነጋ እንዲህ አለው፡ ‘አንተ በየትኛው የቅንጅት አጀንዳ ነው እንዲህ ዓይነት የተዛባ መረጃ ያገኘኸው? አንተ ነበርክ አዲስ አበባ? እኔ ነበርኩ አንተ አልነበርከም የኔ ወንድም! እንዲህ ብሎ ነገር አንድም ቅንጅት ፕሮግራመ ላይ አታገኘኘም። ቅንጅት በሌላው ነገር ማማት ትችል ይሆናል እንጂ “በስቱፒዲቲ” ልተከሰው አትችልም። አልተባለም። የት አንዳገኘኸው እና ማን እንደነገረህ ልትነግረኝ ትችላለህ? ብርሃኑ ነጋ ዝርዘር ፕሮግራሙ አጠር አድርጐ ሲጠቅስለት ...” “ኦነግየው” ቆማ ሳታስበው ጐርፍ የወሰዳት ጥጃ መስሎ “ሰመም” (ሲንሳፈፍ) ሲል አይቼው፡ - ያኔ ብርሃኑን እውነት “በመናገሩ አመሰገንኩት”።
እነኘጂ የመሳሰሉ የዋህ ተከታዮቻቸውን እየዋሹ ነው ኦነጎች እስከ ዛሬ 40 ዓመት የበሰበሱት።
መሪዎቹ በጎረቤት አገር ኬኒያም ሆነ ኡጋንዳ አሜሪካም ሆነ አውሮጳ እየኖሩ ለምን ጫካ ይዛችሁን አትኼዱም ብለው ጠይቀዋቸው አያውቁም። ምክንያቱም ተከታዮቻቸውም ሙቀቱ ለምደውታልና ብርዱ ጥማቱ የኦሮሞ እረኛ የምስኪኑ ገበሬ ልጅ እንዲቀምስላቸው ስለሚፈልጉ እነሱም “ኦሮሚያ ኦሮሚያ ሪፑብሊክ” እያሉ ሃምበርገር እየገመጡ “ራፕ-ሚዩዚክ” እያደመጡ አብረው በውሸት ዓለም ተዘፍቀዋልና የሚገርም አይደለም። እውነቴን ነው የምነግራችሁ! ነፃ አውጪ አውሮጳ እና አሜሪካ አገር ውስጥ ምን ሥራ አለው?
እነኚህ የዋህ የኦነግ ከበሮ መቺዎች ብቻ ሳይሆኑ የአሚንን “ደማቃ ውሸት” በጭብጨባ ሲክቡ የነበሩት እነ አብርሃ በላይ (ኢትዮ ሚዲያ እና ስማቸው አሁን ለጊዜው ለመጥቀስ ያልፈለግኳቸው በይደር የያዝኳቸው የድሮ የወያኔ አባሎች) በድረገጹ ላይ የለጠፈው ደማቅ ውሸት እስኪ እንብቡትና ተወያዩበት እነሆ፦
አብርሃ በላይ የተቀበለው እና ያደመቀው ውሸት አሚን ያለውን በማድመቅ ብቻ ሳይሆን እሱም አምኖበት “ውንጀላው/accusation” አርቲኩለት” እንደሆነ ነው የገለጸው። ጃንዳይም እንዲህ ሲል ይወነጅለናል፡
“የኦሮሞ ጥያቄ ወደ መገንጠል ጥያቄ ለመወሰድ የሚፈልጉ በድኖች ወይንም ሕዝቦች የኦሮሞን ሕዝብ ችግር መፍትሔ ላለመስጠት የተደረገ መከራ/ዱለታ ነው እንጂ የኦሮሞ ነፃ አውጪ (ኦሮሚያው ሪፓብሊክ የሚባል አገር ለመመስረት እታገላለሀ ብሎ አያውቅም) ይገንጠል ብሎ አንድም ቀንም አልተናገረም የጻፉትም እስከነ መረጃቸው ማምጣት ይችላሉ።”
The Oromo Liberation Front (OLF) is a political organization established in 1973 by Oromo nationalists to lead the national liberation struggle of the Oromo people against the Abyssinian colonial rule.( OLF USA Office P.O.Box- 73247 Washington, DC 20056SA-USA-Phone #: (206) 462-5477 Ext. 202-Fax #: (202) 332-7011) አሁንም ተለጥፎ በፕሮገራሙ የሚነበበው ሕያው መመሪያው አንደሆነ ማረጋገጥ ከድረ ገጹ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
አልቀየረም።
-MAP OF OROMIYA REPUBLIC – shows- MORE THAN HALF OF ETHIOPIAN TERRITORY EXTENDING TO ABAI IN THE NORTH AND HARAR IN THE EAST. Capital sity of Ormia Republic – Finfine (እንደ ላይኛው)።
The aim of the Oromo struggle led by the OLF is only to gain back our country that was taken away from us by force. It is not, in any way, against the rights of any other people. (OLF USA Office P.O.Box- 73247 Washington, DC 20056SA-USA-Phone #: (206) 462-5477 Ext. 202-Fax #: (202) 332-7011)
ይህ የሚለው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅት ፕሮግራም እና በድረ ገጹ ተለጥፎ ዛሬም የሚታይ ነው። ብዙ በኦነግ የሚጠሩ ኦ ኤል ኤፎች አሉ። ታዲያ ማንኛቸውን ኦነግ እንመን? ሁሉም በኦነግ ነው የሚጠሩት። መልከአ ምድሩ “ሪፑብሊክ ኦፈ ኦሮሚያ” ይላል “ስፋቱ ሦስት አራተኛ ያገሪቱ የቆዳ ስፋት በካርታው አስቀምጦታል” ታዲያ መጠሪያቸው “ኦ ኤል ኤፍ” (ኦነግ) ፕሮግራማቸው አንድ ሰንደቃላማቸው አንድ ጽሑፋቸው “ላቲን” እና “ሁሉም “ዜግነታችን ኦሮሚያ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለም፤ለ ኢትዮጵያ ባዕድ ነን” ብለው ራሳቸው የሚገልጹ ከኣእላፍ ኦነጐች ማንን ለይተን “አይደለንም ሲሉን ኢትጵያዊያን ናቸሁ እንበል?” (ናችሁ ካልን ደግሞ “ሰስድብ አለ፤ ኦሮሞ አንጂ ኢትጵያ አየደለሁም” ብሎ እስኪ በቃህ ይሰድብሃል።
ታዲያ እንዴት መገንጠልን፤ የኢትዮጵያ አንደነትና አገር ማፈራረስን አያቀነቅንም ማለት ይቻላል? የ ኦነጉ ጸሓፊ “አማን ጃንዳይ” ኦ ኤል ኤፍ አገር ለመገንጠል አልተነሳም አላለም ፤አልጻፈም ይላል። ፕሮግራሙ ግን ከላይ ያነባችሁት ነው። ታዲያ ከዚህ የባሰ የደመቀ ውሸት አለ? ይሄ ነው ደማቅ ውሸት የምላችሁ። ደማቅ ውሸት ደግነቱ እንደ ባውዛ (ሓዊ ለይቲ (በትግርኛ) አማርኛ “አጭበርባሪ ብርሃን” ልበለው) ደምቆ ይቆይና በጨለማ ዓይንን ያስደሰተ አጭበርባሪ መብራት በደቂቃዎች ራሱን በልቶ ከድቶህ ይጠፋል። ዓይንህ ተጭበርብሮ ጭለማ ውስጥ ተውጠህ ቁጭ!
ፖለቲካ ለማሳመን አንዳንድ ቅመም መቀመም የታየ የተለመደ ብልሃት ነው። ነገር ግን ራስህ ፈስተህ ፈሳሽብኝ እሳ ምነው? ስትላት ለዚህ ውሸት ምን የሚባል ስም ይውጣለት? ለዚህ ነው ባለፈው ሰሞን ትችቴ ውስጥ ተቃዋሚ ነን የሚለት ድረገፃች አብዛኛዎቻቸው ወገንተኞች ብቻ ሳይሆኑ ውሸትን እያደመቁ ሕዝብን እያሳሳቱ ነው፡ ያልኩት ከላይ በኢትዮ ሚዲያ አብርሃ በላይ የተለጠፈው ውሸታሞችን “አርቲኩሌት” “አስተዋይ/ብልህ” እያለ ያለውን “የፖለቲካ ደላላነት” (ሎቢ) አስተውሉት ። የኦነጉ “አሚን” ኦነግ ልገንጠል ብሎ በአጀንዳው ጽፎም ተናግሮም አያውቅም ብሎ ዑውር ውሸት ሲዋሽ ሰው ምን ይለኛል ብሎ “ትንሽ ሃፍረት’ አልተሰማውም። ምክንያቱም የውሸት በሸተኞች ሲዋሹ እየዋሹ እንደሆነ አይታወቃቸውም እና ልዩ የሕሊና ሕክምና ያስፈልጋቸዋል። የሰከረ ሰው “ሰክራሃል” ስትለው አንተነን ተመልሶ “ውሸታም አልሰከርኩም” እንደሚለህ ሁሉ ማለት እኮ ነው።ከውሸታሙ ይልቅ ውሸቱን የሚያደምቁለት በሁለተኛ ደረጃ የታመሙ አዳማቂ በሽተኞችን ስንት ጊዜ “ይማራችህ” እንበላቸው? “ወትሩ ሕሙም ክንደይ ጊዜ ይብጻሕ? “ለረዢም ዓመታት የታመመን በሽተኛ በደረስከው ቁጥር ስንቴ “ እግዚሔር ይማርህ” ማለት ይቻላል?” ይላል የትግሬ ሰው። እውነትም ስንት ጊዜ ይማራችሁ እንበላቸው?
የገረመኝ ነገር ደግሞ አማን ደረቱን ነፍቶ ኦነግ ሰው አልገደልም፤ ምንንም ህዝብ አልበደለም ይላል። በግድያ መሳተፉን መረጃውን ይመልከቱ
"[ (http://en.wikipedia.org/wiki/Oromo_Liberation_Front#OLF_policies) ደግሞ ኦነግ ሽብርተኛ አይደለም ይላልThe Institute for Security Studies stated that, "Changes in target selection has led to the assessment that OLF transformed from a revolutionary movement into a terroristmovement."[56] . ."[ (http://en.wikipedia.org/wiki/Oromo_Liberation_Front#OLF_policies)
አሁን ወደ ብርሃኑ ነጋ እናምራ።
ብርሃኑ ራሱን በውሸት ሲያሞካሽና ሲክብ “ቢሰድቡንም አንሳደብም” ሲል ይቈይና በሰከንድ የተናገረውን ስልጡን ንግግሩን ጥሎ ወደ ፋራ ፖለቲካው ወደ “ሰድብ” ይገባል። እራሱ ፈርጥጦ እንዳልፈረጠጠ ሁሉ ሌላውን ፈሪ እና ፈርጣጭ ሲል ጭብጨባ ተለግሶለታል። መረጃው እንሆ።
“ራሳቸውን በቃላት “የአንድነት ሃይሎች” እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩ ሃይሎች ድርጊታቸው የአንድነት ጠላትን ሚያጠናክር እንደሆነ ልንነግራቸው ይገባል። ግንቦት 7 ከማንኛቸውም ድርጅቶች ግምባር ቀደም “የተግባር ድርጅት” ነው ብየ በድፍረትና በሙሉ ልብ ለመናገር እችላለሁ (ሞቅ ያለ የተለመደው የበሽተኞቹ የጭብጨባ ሱስ ይደመጣል) ። ግንቦት 7 በአንድነት ጥያቄ ያለው ተግባር እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ በ ግቡ ለመጠየቅ የሚሞክሩ ሃይሎች እዚህ አሜሪካን አገር “የፕረዚዳንት ኦባማን ዜግነት ከሚጠይቁ አክራሪ የፖለቲካ ሰዎች “የደበርዘር ሙቭመንት” ከሚሉት ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር አለ።….
ለመሆኑ ግንቦት 7 መልስ ላለመስጠት በሰለጠነ ፖለቲካ ለመጓዝ ከወሰንን ቆይተናል የተቀራችሀትም ሆነ እነሱ በዚህ ስልታችን እንዲጓዙ ጥሪ እናቀርባለን ሲል ይቆይና ደቂቃ ሳይሞላው እኛን ከኦባማ ጽንፈኛ /አልትራ ወግ አጥባቂ እና ያበዱ ውሾች ከሚባሉት ነብሰ ገዳዮች ከጆን በርች ሶሳይቲ” ጋር በማያያዝ የሰደብንን ስድብ እሱ ከሚለው “ምንም ዓይነት ያመለካከት ልዩነት ይኑረን” ከነዚህ ሃይሎች ጋር “አላስፈላጊ እንካ ስላንትያ” ላለመግባት ድርጅታችን ከተቋቋመ ጀምሮ በተግባር እየፈጸመ ያለውን ውሳኔ አሁንም እያከበረ እንደ ሚቀጥል ይህም ለወደፊቱ አስፈላጊ አወንታዊ የስነ ልቦናዊ ድባብ ስለሚፈጥር ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች የምር እንዲወስዱትና ከልብ እንዲተገብሩት በአጽንኦት እጠይቃለሁ።” ከሚለው ንግግሩ በምኑ ሊጣጣም ይችላል? ፈረንጅ ሲጨንቀው “ካን ሳም ዋን ሐልፕ!” ይላል። ወገኖቼ እንዲህ ዓይነት ዘለፋ እራሱን ከሚያመጻድቅ ግለሰብ ሲደመጥ ነውር የሚለው ሰው ታጣ? አሁን እሱን ብንሰድበው እኛ እንዴት ልንወቀስ እንችላለን? ልታስረዱኝ ትችላላችሁ? “ዛኣኽለን ጥሒነን በዓለ ማርያም ይብላ” (የሚበቃትን ፈጭታ በዓለ ማርያም ነው ይብቃኝ” ትላለች ይባላል። የሚበቃውን ሰድብ ተሳድቦ ‘ላለመሳደብ ቃል ገብተናል” ይላል። ወይ ትጉዱ!
አስገራሚው ደግሞ የሚከተለውን ተመልከቱልኝ። ብርሃኑ ነጋ እንዲህ ይላል፦
“ለመሆኑ የኢትዮጵያ ፍቅር በምን ይለካል? ስለ ኢትዮጵያ አንድነት መፈክር ከሚያወርዱት ውስጥ ስንቶቹ ናቸው የመጨረሻዋን ጥይት ተጐንጭተው ቃላቸው በተግባር ፈጽመው አለፉት? መንግሥቱን ጨምሮ! “ ብርሃኑ ነጋ ከሲያትል ንግግሩ የተገኘ።
እግዚሔር ውለታውን ይክፈለው እና ቴክሳስ የሚኖር ጥሩ ወዳጄ ትናንት የማይገኙ መጽሐፍቶች በፖስታ ልኰልኝ “መጽሐፈ ጨዋታ፤መንፈሳዊ” የሚለው መጽሐፍ ስመለከት በገጽ 12 እንዲህ ይላል “ሥጋም ፍራቱን እጅግ አበዛው ከታረደ በኋላ ምን ያንቀጠቅጠዋል፤ምንስ ያንበደብደዋል?”ይላል። በግ/ፍየል ከታረደ በኋላ ስጋው ሲርገበገብ ሲንቀጠቀጥ አይታችኋል አይደል? ትርጉሙ ይግባችሁ።
ብርሃኑ ታዲያ እንኳን ታርዶ ገና ለገና “ኦመታለሁ፤ይይዙኛል” ብሎ ምንም ሳይነኩት ከእስር ሲለቁት እግሬ አውጪኝ ብሎ ሕዝቡን አጣብቂኝ አስገብቶ፤ያለ መሪ አስቀርቶ፤ ሜዳ ላይ ጥሎት፤ ፈርጥጦ ለትምህርት ወደ ውጭ አገር መጥቶ “ተራራ ላይ ውጥተህ ተፈላሰፍ በለውኛል” ብሎ መራራዋን ሞት እና ጥይት አንዳትቀድመው አገር ጥሎ ቀድሟት መውጣቱን ዘነግቶት “መንግሥቱን” ፈርጣጭ ብሎ ዓለም ሙሉ እያደመጠው በሌላ ሰው ሲሳለቅ ምን ዓይነት ደፋር ሰው እንደሆነ ይገርመኛል። እንኳን ብርሃኑ ነጋ ባለ ጦር ባለ ታንክ፤ባለ ኮማንዶ ነብስ ጠባቂ ያለው መለስ ዜናዊ ሳይቀር “ፍርሐት” ወርሮት እንደ ነበር ጥቅምት 2003/ኦክቶበር 2010 ቮልዩም 11 ቁጥር/ናምበር 21 “ፍርሓት” የሚለው ዘ ሐበሻ ጋዜጣ ላይ በእውቁ ኢንቬስቲጌቲቭ ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አርአያ የተጻፈውን ስታነብቡ ለካ “ፍርሃት” ክፉ ነው፡ የማይጐበኘው ሰው የለም ትላለህ። ፍርሐት የማይበግረው ሰው ግን የግንቦቱ ጠቅላይ ጦር አዛዥ እና አዋጊው ጀኔራል ብርሃኑ ነጋ ብቻ ናቸው።
ለመሆኑ ኰለኔሉ ሲፈረጥጡ እኮ እንደ ብርሃኑ “ተራራ ላይ ወጥተው የፍልስፍና ትምህርት ለመማር” እንኳ ባይሆን እሳቸውም የራሳቸው የሰጡት ምክንያት አለ። ለመፈርጠጣቸው ምክንያት፤ ፈረጠጥኩ አላሉም: “ካገሬ ለመሰሰድ ምክንያት ለጉብኘት ለአስቸኳይ የስራ ስብሰባ ኬኒያ መኼድ ስለነበረብኝ፤ እንደኼድኩኝ ተቀናቃኞቼ መፈንቅለ መንግሥት አደረጉብኝ። ኬኒያውያኖችም ከዱኝ፡ ስለዚህ ለጊዜው ዚምባበዌ አመራሁ።” ነው ያሉት። ሁልም ፈርጣጭ የየራሱ የራስ መጠምጠሚያ መሸፈኛ “ሻሽ/መንዲል” አለው። ከብዲ ይጹሮ! ብኽድኑ! ትላለች አንዲት ትግርኛ የምትሞከር ኢትዮጵያዊት አገር ወደዳድ ሲገርማት (ሆድ ይቻለው/ይሸከመው! ተከድኖ ይብሰል!) ማለቷ ነው።
ስለዚህ ኰለኔሉም ሞት ሳትቀድማቸው ቀድመዋት ሲፈረጥጡ “ፈረጠጥኩ” አላሉም። የሰጡት ምክንያት የራሳቸው ምክንያት ሲሰጡን ፤ የግንቦት 7ቱ የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ እና ዶከተር ፕሮፌሰር ፈልድ ማርሻል ጀኔራል ብርሃኑ ነጋ ደግሞ የወያኔ “ዊፕ/ጅራፍ” ቀምሶ ስላማያውቅ ‘እስር ቤት ውስጥ ሌሎች ሲገረፉ” (ስዬ አበርሃን “የምን እሪታ የምን ጅራፍ ነው የሚጮኸው ብሎ ደንግጦ መጠየቁን አስታውሱት መጽሐፉ ላይ) ሰምቶ ሞት ላለመጐንጨት ተደናግጦ ያላደረገውን ወንጀል “አዎ ፈጽሜአለሁ” ብሎ “ፈርሞ” ሲወጣ “ወያኔዎች ሰውን ሲገረፉ የሰማው የብርሃኑ “ቂጥ” በፍርሃት ተምበድብዶ ሲንቀጠቀጥ የወያኔዎቹ ጅራፍ “ጀኔራሉ” ቂጥ ላይ ከማረፏ በፊት ሲፈረጥጥም ለመፈርጠጡ የሰጠን ሽፋን “ባይ ኤኒ ሚንስ -ከትግሉ ቀደም ብሎ መቀጠል ያለብኝ ኤክስቴንሽን ትምሕርት የመቀጠል እቅድ ስለነበረ መውጣት ነበረብኝ” አለን እንጂ “ፈረጠጥኩ እኮ አላለም። ማን ፈረጠጥኩ እንዳለ ብርሃኑ ነጋ ብቻውን መፈርጠጡን ይመን? ሞኝህን ፈልግ አለ ያማራ ሰው!
ታዲያ ብርሃኑ ነጋ ““ለመሆኑ የኢትዮጵያ ፍቅር በምን ይለካል? ብሎ ይጠይቅና “ስለ ኢትዮጵያ አንድነት መፈክር ከሚያወርዱት ውስጥ ስንቶቹ ናቸው የመጨረሻዋን ጥይት ተጐንጭተው ቃላቸው በተግባር ፈጽመው ያለፉት? መንግሥቱን ጨምሮ!” (በርሃኑ ነጋ)
እያለ እራሱ ከፈርጣጮቹ አንዱ ትልቁ ጉሬዛ ሆኖ እያለ ሌሎቹን “ፈርጣጮች” እያሉ ሲመጻደቅ እና ጥያቄ ሲያቀርብ “ምሕረት የውርድ” (ምሕረቱን ያውርድ) ከማለት ምን እንበል?
መንግሥቱ አስመራ መሄድ አይችሉም፤ ሽምቅ ተዋጊ ማሰማራትና መምራት አይፈቀድላቸውም። ብርሃኑ ግን አስመራ መሄድ ይችላል፤ ጫካ መሄድ ይችላል።ጫካ መሄዷን ግን አልወደዳትም። ምክንያቱም መራራዋን ጽዋ መጐንጨት ያልለመደች ፈርጣጭ ነብስ “ወያኔ ጐማ እግሩ” ጫካ ውስጥ “ጦሽ” ብሎ ድንገት ቢመጣበት “አድነኝ ብሎ የሚማጸነው ጓደኛው በረከት ስሞን” እንደ ማያገኘው ያውቃል እና ነው! ወይ እኚህ መንግሥቱ ፈርጣጭ ሁሉ የእንጨት ፈለጣ ተማሪ መለማመጃ አደረጋቸው። ወይ አለመታደል! ያረጀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል፡ የሚባለው ለካ እንደዚህ ነው።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com (Ethiopian Semay) getachre@aol.com
Monday, November 14, 2011
ሕሊና ቢስ ተቃዋሚዎች ሚዲያዎቻቸውና የሻዕቢያ ገበን
ይህ ውጭ አገር በተቃዋሚነት እየቀጠለ ያለው ቡዱን የተጠናከረው በንግድ ጨዋታ የተካኑ ተንኰለኞች የተበተቡት ድር በመሆኑ ትግል ዓለም ልምድ ለሌላቸው ወጣት ዜጎች በቀላሉ ያርበኝነት የምስክር ወረቀት በገንዘብ እየገዙ እንዲጭበረበሩ አድርጓል። ሌላም ሌላም።
አንድ አስገራሚ ነገር ላንሳላችሁና ላጠቃልል። “ገለልተኛ” ብሎ ራሱን የሚጠራ ኢሳት የተባለው የዜና ማሰራጫ ስትመለከቱት ባለፈው ሳምንታት ደ/ር ግሬጐሪ ከተባሉት አሜሪካዊ የሰው ልጆች መብት ተከራካሪ አበበ ገላው በተባለው ወጣት ጋዜጠኛ የተካሄደው ቃለ መጠይቅ የታዘብኩት ነገር ቢኖር አዘጋጁ የጋምቤላዎች እና የኦጋዴኖችን እና 200 የሚያክሉ በ1997 ምርጫ በወያኔ ፖሊሶች የተገደሉ ሰላመዊ ተቃዋሚዎች ብቻ ወያኔ የፈጸማቸው የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን በእንግዳው በኩል እንዲረጋገጥ ደጋግሞ ሲጠይቅ ፤ ለ30 ዓመት (20 ዓመት ብቻ አይደለም) ሙሉ በወያኔዎች እና በሻዕቢያዎች እንዲሁም በኦነጐች እና በኦጋዴን ነፃ አውጪዎች የተለያዩ የሃይማኖት ሽብርተኞች ያደረሱት በአማራው ሕብረተሰብ የደረሰውን የዘር ማጥፋት ጥቃት አንድም ቃል አንድም አረፍተ ነገር ከጥያቄው ውስጥ አላስገባም።
ሰሞኑንም የገረመኝ ደግሞ ኢያሱ በርሐ የተባለው ዘረኛ እና ትዕቢተኛ/ትምክሕተኛ በወያኔ ህንፍሽፍሽ ጊዜ የሚገደሉት ሰዎች “በደላላነት” የ“አ ሽ ዓ”መሪዎች ፎርማቶሪ ሆኖ በእንደርታ ተወላጅ ተዋጊ ሃይሎች የፈጸመው አሰቃቂ ገበና ተረስቶ ዛሬ “ኢሳት” የተዋጣለት አርቲስት እያለ ድሮ ሜዳ ጫካ ሆኖ ሲዘላብዳቸው የነበሩትን ጸረ ኢትዮጵያ ዘፈኖችን “በኢሳት” ጣቢያ በመልቀቅ “ኢያሱ ተገደለ ወይስ ሞተ? ” እያሉ ሲያዘፍኑልን ያደመጠ ሕሊና ያለው ሰው ሳይገርመው አልቀረም። በጣም የገረመኝ ግን ሕንድ አገር ውስጥ የዜጋ ያለህ እያለ ኢየሩሳሌም አርአያ ከእናት አልባ በሽተኛ ህጻን ልጁን ታቅፎ የድረሱልኝ ጩኸት ሲጮህ ደንታ ያልሰጣቸው የኢሳት ዋና ዋና ሰዎች ለቅንብር እንዲመችላቸው ማቀናበሪያ ፕሮግራማቸው በማድረግ አርአያ ተስፋማርያም አገር ውስጥ እያለ የዘገባትን ጽሑፍ አስደምጠውናል። መቸም የነዚህ ግለሰዎች ወገንተኛነት፤ትዕቢት የማያውቅ አድማጭ እውነት ይመስለው ይሆናል። አሳት ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን (ሁሉም አንኳ ባይሆኑ) እንደሚዘላብዱት ሳይሆን ለቡድናቸው ብቻ የሚጮሁ የሚደርሱ “ወገንተኞች” መሆናቸው ባለኝ ሰነድ በተጨባጭ መከራከር እችላለሁ ። አጫዋች እና ዘፋኝ ታማኝ በየነ ጌታቸው ረዳ ስለ አርአያ (እየሩሳሌም) አርዳታ ጉዳይ ምን ብሎ ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርቦልህ ነበር ብላችሁ ጠይቁት። ምን እንደሚመልስላችሁ ከነገራችሁኝ በሗላ መረጃው እነግራችኋለሁ። በትግርኛ አንዲህ ያለ ነገር ሲገጥም እንዲህ ይባላል “አድጊ አብ ምእራጋ መስከብ ትወልድ ዒሉ ሓዲጋ” “ አህያ ልታረጅ ስትል ውርንጭላን መውለድ ትታ የእንግዴ ልጅ ትወልዳለች” ። እንግዲህ እንዲህ አይነት ኩራት የሚያሳዩት ለምን ይመስላችል? ሊሂቅና አርቦሽ አርቦሽነት ስብስብ ሲጎለብት ጉልበት ያለው/ኦምኒፖተንስ ስለሚመስለው ኩራታቸው መከራ ነው። አንድ ትግርኛ ምሳሌ ልጨምር “ አድጊስ ሳልሳይ ርእሳ እንተ ኾነት ዝብኢ ዝኽእላ ኣይመስላን” (አህያ ሦስት እራሷ ጋር ስትሆን ጅብ የሚችላት አይመስላትም”)
ታሪኩ የተገኘው በቅርቡ “ጥልመት’ ከተባለ በወያኔው በዶክተር ሰለሞን ዕንቋይ የተጻፈ የተገኘ ጥናት እና ታሪክ ነው።
ሌላ ሦስት ሬሳ ደግሞ ጉል (ጉልዒ) ዛፍ ስር ወድቆ ተመለከትኩኝ። ከነዚህ ሬሳዎች አንደኛው ይኼ የምታዩት ከወደ እዚህ በኩል ያለው ሬሳ ‘አደንዝዝ” እየተባለ በፈረስ ስም ስንጠራው የነበረው አጋሜው እኮ ነው እየተባባሉ ሰማኋቸው።…”
በጣም ዘግናኝ የሆኑ የሻዕቢያ እና ጀሌዎቹ ዘግናኝ ገበና በክፍል ሁለት በሚቀጥለው ሰሞን ይቀጥላል። እነ ታማኝ በየነ ኢሳት የግንቦት 7 “ቢሆንስ!” እያሉ በድርቅና የሚደነፉት ዕብጠት ባንዳው የግንቦት 7 ድርጅት ከጌቶቹ ከሻዕቢያዎቹ ጋር ሲሞዳመድ ወገኖቻችንን የወደቀበት እሬሳ እየረገጠ አዛዣቸው ኢሳያስ አፈወርቂን ለመማጸን በደም መሬት ላይ እየተረማመደ መሆኑን መታወቅ አለበት። ይቀጥላል…።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ Ethiopiansemay.blogspot.com ( just Goole it Ethiopian Semay) getachre@aol.com